query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
7
297
category
stringclasses
6 values
passage
stringlengths
137
5.93k
link
stringlengths
28
740
84890908414bfdd95d7d6fc9b1e96f47
29bb3ebfc54c214f56a34622c0f6eab9
“ጠላቶች ኢትዮጵያን በብሔርና በሃይማኖት ለመከፋፈል ያላቸው ፍላጎት ዛሬም አልጠፋም’’ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ጠላቶች ኢትዮጵያን በብሔርና በሃይማኖት ለመከፋፈል ያላቸው ፍላጎት ዛሬም አልጠፋም ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ትናንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከመተከል ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት፤ ጠላቶች ኢትዮጵያን በብሔርና በሃይማኖት ለመከፋፈል ያላቸው ፍላጎት ዛሬም አለመጥፋቱን የገለጹ ሲሆን፤ ምንም እንኳን ጠላቶች በዚህ መልኩ ቢሰሩም አስተዋይ ሕዝብ ይዘን ችግሮች እንዳይደገሙ አድርገን እንፈታዋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡“ከመተከል ነዋሪዎች ጋር ባደረግኩት ውይይት ሕዝባችን ለአንድነት፣ ለሰላም፣ ለልማት እና ለብልጽግና ያለው ፍላጎት የትኛውንም የመከፋፈል አጀንዳ እንደሚያከሽፍ ተመልክቻለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ በመሆኑ ምክንያትም ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን በጎሳ እና በሃይማኖት የመከፋፈል ፍላጎታቸው አሁንም ድረስ ቢኖርም ይህ ፍላጎታቸው እንዳልተሳካላቸው ገልጸዋል። ይሄንን ጽኑና አስተዋይ ሕዝብ ይዞ ደግሞ ችግሮችን እንዳይደገሙ አድርጎ መፍታት እንደሚቻልም ተናግረዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ በመድረኩ ላይ በአካባቢው የተከሰተውን የፀጥታ ችግር መፍታት በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት የተካሄደበት መሆኑንም ነው ኢዜአ የዘገበው። በተያያዘ፣ ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት እንደዘገበው፤ ውይይቱ መድረኩ በመተከል ዞን በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን ለማስቆም ዘለቄታዊ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ሲሆን፤ በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሀገሪቱ አንድነትና ሠላም ብቸኛው አማራጭ ኢትዮጵያውያን ከጥላቻ፣ ከስሜት እና ከመገፋፋት ወጥተው አንድነታቸውን እና አብሮነትን ማጠናከር ነው ብለዋል። በቀጣናው የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለማስቆም ጥረት የተደረገ ቢሆንም በርካታ ተዋናዮች በመኖራቸው ችግሩን በአፋጣኝ እንዳይቆም አድርጎት መቆየቱንም ገልጸዋል። በመሆኑም አካባቢውን ወደ ሠላም የመመለሱ ሥራ በትኩረት እንደሚሠራ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ባለፈ ግን በዞኑ እየተካሄደ ያለው የህግ ማስከበር ተግባር ገለልተኛ እና ከአድሏዊነት በፀዳ መልኩ እንዲተገበር አሳስበዋል። በስሜት እና በብሶት የጁንታውን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብሎ ወደ ጫካ የሸሸው ኃይል በሠላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ለማድረግ አመራሩና በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።ከዚህ ባለፈ የክልሉን የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀምሥራ አጥ ወጣቶችን በማደራጀት የክልሉ መንግሥት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንዲሰራም መልዕክት አስተላልፈዋል። መንግሥት እየወሰደው ካለው እርምጃ ባሻገር በቀጣናው ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች ጋር በዞኑ የተፈጠረውን የሠላም እጦት ለመፍታት ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርጉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ያቀረቡት።የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ ኃላፊነት የጎደለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ባለፋት 27 አመታት የህወሓት ጁንታ የፈፀመው የፖለቲካ አሻጥር በቀጣናው ዘላቂ ሠላም እንዳይረጋገጥ አድርጎ መቆየቱን ተናግረዋል። በመተከል ዞን በተደጋጋሚ የሚፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለማስቆም ጥረት ቢደረግም፤ አባባሽምክንያቶችን ለይቶ መፍትሄ መስጠት ባለመቻሉ የፀጥታ ችግሩ እስካሁን መቀጠሉን አንስተዋል።ዞኑ የተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለዘመናት በአብሮነት የሚኖሩበት አካባቢ እንደመሆኑ መጠን፤ የህዝቦችን አንድነትና አብሮነትን ለማጠናከር መንግሥት በትኩረት ሊሠራ ይገባልም ሲሉ ነው ተሳታፊዎቹ ያስገነዘቡት።አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37919
5abe410f60a6f17e83454c55ccf460b6
eec78e643fb6f1c77aeb6a271955baf0
የፀረ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መድኃኒት ከቅዱሳን መጻህፍት አስተምህሮ አኳያ
ሀገር አቀፍ ዜና
አስመረት ብስራትበሃይማኖት አባቶች ፀሎት የተከፈተው ጉባኤ እጅግ መከባበር የሞላበት ነበር። በፀረ ኤች አይቪ መድሀኒት ላይ አተኩሮ የኤች፣አይ.ቪ ታካሚዎች ህክምናቸውን በመውሰድ እንዳያቋርጡ ለማድረግ የተከናወነው የቅስቀሳ መድረክ የተለያዩ ታላላቅ መንፈሳዊ አባቶች፤ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፤ የሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸው ሰዎችና ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተውበት ነበር።የጉባኤውን መጀመር በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የጀመሩት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሀፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ በሀገራችን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚቻለው ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች የህክምና ክትትላቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዲችሉ ሲደረግ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አዲስ እያንሰራራ ያለው የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ስርጭትን ለማቆም በሃይማኖት ሰበብ መድሀኒታቸውን የሚያቋርጡ ህሙማን ከዚህ ተግባር መቆጠብ እንደሚኖርባቸው አስረድተዋል።ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉት አቶ መኮንን አለሙ በበኩላቸው፤ ከፀበል፣ ከዱአና ከፀሎት ጎን ለጎን መድሀኒቱን መውሰድ ያለምክንያት የሚጠፋውን የቫይረሱ ተጠቂዎችን ህይወት ሊታደግ እንደሚችል አስረድተዋል። ከሃይማኖት አባቶች ጋር የሚደረግ ግንኙነት የመንፈስ ጥንካሬን እንደሚያጎናፅፍ በመጥቀስም፤ መንፈሳዊውንም ሆነ ዘመናዊውን ህክምና ጎን ለጎን ማስኬድ አዲስ ከቫይረሱ ጋር የሚወለዱ ልጆች እንዳይኖሩ ማድረግ እንደሚያስችል ገልፀዋል። ቀደም ሲል የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የሃይማኖት አባቶች አስተዋፅኦ የላቀ መሆኑን ያስታወሱት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው፤ አሁንም ቢሆን በመቀዛቀዝ ላይ ያለው ኤች.አይ.ቪ ቫይረስን የተመለከተ ንቅናቄ አሁንም በሃይማኖት አባቶች አስተምሮት ሊደገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል። በሀገራችን ከ667ሺ በላይ ሰዎች በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ መኖሩን በመጠቆም፤ በሁሉም ህብረተሰብ የጋራ ርብርብ መጥቶ የነበረው የአመለካከት ለውጥ ወደኋላ እንዳይመለስ የሃይማኖት አባቶች አስተምሮአቸውን አጠናክረው መቀጠል የሚገባቸው መሆኑን ጠቁመዋል።ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እንዳሉት ደግሞ፤ ለመድሀኒት ሰሪዎች ጥበብን የሰጠው ፈጣሪ በመሆኑ መድሀኒትን መውሰድ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ አይከለክልም። የሰው ልጅም በምድር ኖሮ ለማለፍ እስከተፈጠረ ድረስ በህይወቱ መቀለድ የለበትም። በመሆኑም ፀበሉንም እምነቱንም ፀሎቱንም ሳያቆሙ መድሀኒት በመውሰድ እራሳቸውን ከከፋ ህመም መጠበቅ የሚገባቸው መሆኑን ያሳሰቡት ብፁዕ አቡነ ማትያስ፤ በእምነት እያሳበቡ መድሀኒት ማቆም ራስን ከመግደል የማይተናነስ መሆኑን አስረድተዋል። ፈጣሪ ከፈጠራቸው ተክሎች የተፈጠሩ መድሀኒቶችን አልውጥም ማለትም በፍፁም ከመንፈሳዊ አስተምህሮት ውጪ ነው ብለዋል።የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እንድሪስ በበኩላቸው፤ የሰው ልጅ በቅድሚያ በበሽታ እንዳይጠቃ መጠንቀቅ እንዳለበት በመግለጽ፤ በበሽታ ከተያዘ በኋላ መድሀኒት አልወስድም ማለት ግን የእስልምና ሃይማኖት አስተምህሮ የማይደግፈው ተግባር መሆኑን አስረድተዋል። ህመም የመጣው ከፈጣሪ ማርከሻ መድሀኒቱም የሚገኘው በፈጣሪ ፍቃድ በመሆኑ የሃይማኖታዊ ስርአቶችን ከማከናወን ጎን ለጎን መድሀኒቶቻቸውን በአግባቡ መውሰድ የሚገባቸው መሆኑን አሳስበዋል።̋ካለ እርጅና ሞት በስተቀር፤ አላህ መድሀኒት የሌለው በሽታ አልፈጠረም፤” ያሉት ሀጂ ኡመር፤ ጥበቡን ሰጥቷቸው በቅንነት ሊረዱን የመጡ የህክምና ባለሙያዎችን ትዕዛዝ አለመተግበር ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል። ብፁእ ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል ሊቀጳጳስ ዘካቶሊካውያን የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፤ በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልእክት፤ የሳይንስ ግኝት የፈጣሪ ፀጋ በመሆኑ መድሀኒቶች በምንም ሁኔታ ከሃይማኖታዊ ስርአት ጋር የማይጋጭ መሆኑን ተናግረዋል። በተለያዩ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎች የተለያዩ መድሀኒቶችን መጠቀም መፈቀዱን አስታውሰው፤ ከሃይማኖት አባቶች ጋር የሚከናወኑ መንፈሳዊ ተግባራት ለስነልቦና እጅግ በጣም ጠቃሚ በመሆኑ ከመድሀኒቱ ጎን ለጎን እምነታዊ ተግባራትን መፈፀም ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል።በጉባኤው ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉ ሰባት የተለያዩ ሃይማኖቶች አባቶችም፤ መድሀኒት ማቋረጥ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ አለመሆኑን አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37933
4f0ec72203684303c6cb02bb116a8949
f975224814eb85aad08a27c995817262
አልጄሪያና የ2020 የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ዝግጅት
ስፖርት
 በቀጣዩ ሰኔ ወር የአፍሪካ ምርጥ አትሌቶች በሰሜን አፍሪካዊቷ አገር አልጄሪያ ለመፋለም ቀጠሮ ይዘዋል።መዲናዋ አልጄርስም በሃያ ሁለተኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና የአህጉሪቱ ኮከብ አትሌቶችን ለመቀበል ከወዲሁ ዝግጅቷን እያገባደደች እንደምትገኝ አሳውቃለች።የአፍሪካውያን አትሌቶች ከቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አስቀድሞ በቻምፒዮናው ለኦሊምፒክ የሚያበቃቸውን ሰዓት ለማሟላት ብርቱ ፉክክር የሚያደርጉበት ትልቅ አጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል። የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽንም ይህ ቻምፒዮና የተሳካ እንዲሆን ከአልጄሪያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡‹‹ ለቻምፒዮናው በሚደረገው ዝግጅት ረክተናል፣ ነገር ግን ይህ ለኛ አዲስ አይደለም›› በማለት ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን የተናገሩት የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ዳይሬክተር ላሚን ፋቲ የአልጄሪያን ዝግጅት ለመገምገም ወደ ስፍራው ያቀናው ቡድን ነገሮች በጥሩ መልኩ እየሄዱ እንደሚገኙ ማረጋገጡን አስረድተዋል።ለዚህም አልጄሪያ የሰውሃብትና አስፈላጊው ቁሳቁስ በበቂ ሁኔታ ያላት አገር መሆኗ ዝግጅቱን ቀላል እንዳደረገው ተናግረዋል። እ.ኤ.አ ከሰኔ 24 እስከ 28 በሚካሄደው ቻምፒዮና ውድድሮችን የሚያስተናግደው ‹ጁላይ 5› ስቴድየም እድሳትና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲካተቱበት ተደርጎ ሰማንያ ሺ ተመልካች እንዲይዝ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።እኤአ በ1972 በቀድሞው የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት ሁአሪ ቡሜዴን ተመርቆ ስራ የጀመረው ስቴድየም በርካታ ታላቅ ውድድሮችን የማስተናገድ ልምድ አለው።እኤአ በ1975 በሜድትራኒያን ጨዋታዎች ይህ ስቴድየም የአትሌቲክስ ውድድሮችን በዋናነት ማስተናገድ ችሏል።እኤአ 1978ና 2007 የመላ አፍሪካ ጨዋታዎችን ከማስተናገዱ በተጨማሪ 2000 ላይ የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻፒዮናን ማስተናገድ እንደቻለ ይታወሳል። የኮንፌዴሬሽኑ ዳይሬክተር ፋቲ ባለፈው ወር ለአልጄሪያ መገናኛ ብዙሃን ‹‹የስቴድየሙ እድሳት ገና ሳይጠናቀቅ ገምጋሚ ቡድኑ እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች ረክቷል፣ በቀጣይ በሚከናወኑ ስራዎች ደግሞ የተሻለ ነገር እንደምናይ ተስፋ አለን›› ማለታቸው ይታወቃል።የአልጅሪያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ጋር በጋራ በመሆን አትሌቶች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም በቻምፒዮናው ለመታደም ወደ ስፍራው ለሚያቀኑ አካላት የቪዛና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ በርካታ ስራዎችን ከወዲሁ እያከናወኑ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።ውድድሩ በበርካታ የአፍሪካ አገራት የቀጥታ የቴሌዥን ስርጭት ሽፋን እንዲያገኝም የተለያዩ ስራዎች ተሰርተዋል። በቻምፒዮናው የአትሌቶች አበረታች ንጥረ ነገሮች ተጠቃሚነት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲኖር ከወዲሁ ዝግጅት መደረጉም ታውቋል።አልጄሪያ ይህን ቻምፒዮና ስታስተናግድ የዘንድሮው ሦስተኛዋ ይሆናል።ከዚህ ቀደም እኤአ በ1988 በአናባ ከተማ ቻምፒናውን ያስተናገደች ሲሆን ከሃያ ዓመት በፊት 2000 ላይ በአልጄርስ ቻምፒዮናውን ማስተናገድ ችላለች። በ1988 ቻምፒዮና አልጄሪያ በአስራ አንድ የወርቅ ሜዳሊያ ቀዳሚ ሆና ካጠናቀቀችው ናይጄሪያ በአንድ የወርቅ ሜዳሊያ ዝቅ ብላ በሁለተኛነት ማጠናቀቋ ይታወቃል።ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ 2000 ላይ ባስተናገደችው ቻምፒዮና ግን አስራ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎች በመሰብሰብ ቀዳሚ ሆና አጠናቃለች።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 22/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=25009
7e04ba08911309739e6193c571693f7b
d6202e31853222632ea578e0bf2aed5a
የቶኪዮ ኦሊምፒክ የጎዳና ላይ ውድድሮች ስፍራ ተቀየረ
ስፖርት
በ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮች የሚካሄድባቸው ስፍራዎች መቀየር ላይ ሲነሳ የቆየው አወዛጋቢ ሃሳብ መቋጫ አግኝቷል፡፡ የኳታር ዓለም ቻምፒዮና የማራቶን ውድድር ላይ የታየውን ክስተት ተከትሎ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከዓለም አትሌቲክስ ጋር በመሆን ውድድሩ የሚካሄድበት ስፍራ እንዲቀየር ጥያቄ ማንሳታቸው የሚታወስ ነው፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴው በበኩሉ የውድድር ስፍራውን ከቶኪዮ ወደ ሌላ ስፍራ የማዘዋወር ዓላማ እንደሌለውና በሃሳቡም እንደማይስማማ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ትናንት በወጣው ዜና መሰረትም በውድድሮቹ ላይ የመርሃ ግብር ቅየራ መደረጉ ታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት የማራቶን እና የእርምጃ ውድድሮቹ ከቶኪዮ በ800ኪሎ ሜትር ርቀት በሆካኢዶ ተራራማ አካባቢዎች በሚገኘውና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ባለው ሳፖሮ የተባለ ከተማ የሚካሄዱ ይሆናል፡፡ የውድድር ስፍራውን መቀየር ተከትሎ መርሃ ግብሮቹም ላይ ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ የሴቶች ማራቶን እና በሁለቱም ጾታ የእርምጃ ውድድሮች ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳሉ፤ የወንዶች ማራቶን ደግሞ እንደተለመደው የኦሊምፒኩ የመዝጊያ ውድድር ይሆናል፡፡ ሁለቱ ዓለም አቀፍ ተቋማት አትሌቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ ሃሳቡን በቅድሚያ ያነሱት ሲሆን የውድድሩ አዘጋጆች ተቃውሟቸውን ሽረው ይሁንታቸውን ለመስጠት ምክንያት የሆነው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም የአትሌቶች ማህበር መሆኑን ስካይ ስፖርት አስነብቧል፡፡ ከውሳኔው ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን የሰጡት በዓለም ዓቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የአትሌቶች ኮሚሽነር ክርስቲ ኮቬንተሪ፤ የአትሌቶች ጤና ከሁሉ አስቀድሞ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም ‹‹የማራቶን እና እርምጃ ውድድሮችን ከቶኪዮ ወደ ሳፖሮ መውሰዳችንም በአትሌቶች ጉዳይ ምን ዓይነት አቋም እንዳለን የሚያሳይ ነው›› ብለዋል፡፡ ወራት ብቻ የቀሩት ኦሊምፒኩ በሚካሄድበት ወቅት በጃፓኖች ዘንድ በጋ ነው፤ በጊዜው የቶኪዮ የሙቀት መጠን ደግሞ እስከ 30ዲግሪ ሴሊሽየስ በማሻቀብ ከፍተኛ ወበቅ የሚያስከትል ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ረጃጅም ርቀት ለሚሸፍኑት የውድድር ዓይነቶች የማይስማማ በመሆኑ በኳታር ያጋጠመው እንዳይደገም ያሰጋል፡፡ የውድድሩ አዘጋጆችም ሙቀቱን ለመቋቋም፤ መጠለያዎችን በማበራከት፤ የውሃ ማቀዝቀዣና ከፍተኛ የውሃ አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ እንዲሁም አትሌቶች ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ሙያዊ እገዛ ለማድረግ ማሰባቸውን ነበር ያሳወቁት፡፡ሆኖም በዓለም አቀፎቹ ተቋማት በተደረገው ግፊት የውድድር ስፍራው እንዲለወጥ ተደርጓል፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ስራ አስኪያጅ ቶሺሮ ሙቶ ‹‹በሳፖሮ የሚገኘው የኦዶሪ ፓርክ ለእነዚህ ውድድሮች የተመቸ ስፍራ ነው፡፡ በመሆኑም ውሳኔውን ተከትለን በፍጥነት ቦታውን በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን፡፡ ኦሊምፒኩ ስምንት ወራት ብቻ ቢቀሩትም በትብብር ዝግጁ የምናደርገው ይሆናል›› ሲሉም ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡አዲስ ዘመን አርብ ህዳር 26/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=23653
7906ba8d719a16388bb66f7bcb1e7ace
54a31e997b69cf8e8eb5159a05b79e7a
አፍሪካን ያገለለው የዓለም አትሌቲክስ ሌጋሲ
ስፖርት
 የኦሊምፒክ የ1500 ሜትር ቻምፒዮኑ እንግሊዛዊ አትሌት ሴባስቲያን ሎርድ ኮ የዓለም አቀፉን አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ከአራት ዓመት በፊት የተመረጡት አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው የማህበሩ ጉባዔ ላይ ነበር። ኮ ከአራት ዓመት በኋላም ባለፈው መስከረም በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ዋዜማ ላይ ማህበሩን ለቀጣይ አራት ዓመታት ለመምራት ይሁንታ አግኝተዋል። ዓለም አቀፍ ማህበሩ ስሙን ‹‹የዓለም አትሌቲክስ›› በሚል በቅርቡ ከመቀየሩ አስቀድሞ በቀድሞው የመካከለኛ ርቀት ኮከብ አትሌት ኮ ቆራጥ አመራር ሰጪነት በርካታ ነገሮችን እንደቀየረ ይታመናል። በተለይም የቀድሞ የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሴኔጋላዊው ላሚን ዲያክ የአስራ አንድ ዓመት የስልጣን ዘመን በአትሌቲክሱ ዓለም የተበላሹ የአመራር ክፍተቶችን በመድፈን ረገድ ኮ የተሳካላቸው መሆኑን ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል። እኤአ ከ1999 እስከ 2015 ማህበሩን የመሩት ዲያክ መንበረ ስልጣናቸውን ባስረከቡ ማግስት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ላይ በሰማንያ ስድስት ዓመታቸው ፓሪስ ውስጥ በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። የሃምሳ አራት ዓመቱ ልጃቸው ፓፓ ማሳታም ዓለም አቀፍ ማህበሩን ተገን አድርጎ ህገ ወጥ ገንዘብ ህጋዊ በማድረግና ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም አብረው ወህኒ ወርደዋል። የክስ ሂደታቸውም በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማግስት መታየት ይጀምራል። በብዙ ዝቅጠት ውስጥ የነበረውን ማህበር ለመረከብ ኮ ከምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት አንስተው ያልገቡት ቃል የለም። አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ ማሸነፍ የቻሉት ኮ በአመራር ዘመናቸው ትኩረታቸውን በአትሌቶች፣ በውድድሮች፣ በልማት፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለበት የአመራር ጉዳዮች ላይ ማድረጋቸው የብዙዎችን ድምፅ እንዲገዙ አስችሏቸዋል። ባለፉት አራት ዓመታትም የዓለምን አትሌቲክስ ቀዳዳዎች እየፈለጉ በመድፈንና በስፖርቱ ስር ነቀል ለውጦችን በመተግበር ተመስግነዋል። የዓለም የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ሽልማት ባለፈው ሳምንት በሞናኮ ሲካሄድም የዓለም አትሌቲክስ የፅህፈት ቤት ሃላፊውና የኮ ቀኝ እጅ የሆኑት ብሪቶን ጆን ሪድገን ለመገናኛ ብዙሃን‹‹ ቀጣዩ ስራችን እድገት ነው›› ሲሉ ተደምጠዋል። ሪድገን በንግግራቸው ጥራት ያላቸው ውድድሮችን በየትኛውም ደረጃ መፍጠር ዋና አጀንዳቸው መሆኑንም አብራርተዋል። ለተመልካቾች፣ ለስፖንሰሮችና ለንግድ አጋሮች ከዓለም ቻምፒዮና ባሻገር በሌሎች ውድድሮች ምቾትን መፍጠርም የዓለም አትሌቲክስ በቀጣይ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። ኮ እንዲሁም ካቢኔያቸው የዓለምን አትሌቲክስ በገቢ ከማሳደግና የውድድር ጥራትን ከመፍጠር አኳያ የጀመሩት መንገድ የሚጠላ ባይሆንም አካሄዱ ላይ ጥያቄ ያላቸው ወገኖች አልጠፉም። በተለይም አፍሪካውያን። ከ2020 ጀምሮ በዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ላይ የተደረገው ለውጥ የጥያቄው መሰረት ሲሆን ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን ከዚህ ለውጥ በተቃራኒ የቆሙ የአትሌቲክስ አገራት ናቸው። አምስትና ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ከዳይመንድ ሊጉ መቀነሳቸውን ተከትሎ የርቀቱ ፈርጥ የሆኑት ሁለቱ ጎረቤታሞች ቀደም ሲልም ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ሪድገን ለምስራቅ አፍሪካውያኑ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ግን የተቀነሱት ርቀቶች ጥናት ተደርጎባቸው ከቴሌቪዥን ስርጭት ጋር እንዲስማሙና ለዓለም አትሌቲክስ የገቢ ምንጭ እንዲሆኑ ታስቦበት ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ አብራርተዋል። ‹‹ዳይመንድ ሊግ ስፖንሰር የለውም፣ ውድድሩን የሚመለከቱ የስፖርቱ አፍቃሪዎች ቁጥርም እያሽቆለቆለ ነው፣ ዳይመንድ ሊግ ጥሩ ውድድር ነው፣ ስፖንሰሮችና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የተሻለ እንዲሆን ይሻሉ›› በማለት ሪድገን ቃል በቃል ተናግረዋል። እንደ ሪድገን ገለፃ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ይበልጥ ሳቢና ለቴሌቪዥን ስርጭት አመቺ እንዲሆኑ ቀደም ሲል በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት 120 ደቂቃዎች ያስፈልጉት ነበር። አሁን ግን በዘጠና ደቂቃዎች ውስጥ በሚተላለፍ ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲከናወኑ ለማድረግ ነው በተለያዩ አምስት አገራት ጥናት ተደርጎ ረጅም ርቀቶችን መቀነስ ያስፈለገው። በዚህ ጥናት ውስጥ ግን የዳይመንድ ሊጉ ድምቀቶች፣ የአትሌቲክሱ ዓለም ውበት የሆኑት ምስራቅ አፍሪካውያን አልተካተቱም። በውሳኔው ላይም ድምፃቸው አልተሰማም። ሪድገን ለዚህ ምላሽ ሲሰጡ‹‹ በቀጣዩ ዓመት ሙሉ መልሶ ምልከታ እናደርጋለን›› ከማለት ውጭ የተነፈሱት ነገር የለም። የዓለም አትሌቲክስ በዳይመንድ ሊግ ላይ ሃያ አምስት በመቶ ድርሻ አለው። በቅርቡም ከቻይና ግዙፍ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር የዳይመንድ ሊግ ውድድሮችን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለማስተላለፍ ለአስር ዓመት የሚዘልቅ ስምምነት ማድረጉ ይታወቃል። ስለዚህ የዓለም አትሌቲክስ ዳይመንድ ሊጉ ላይ ለውጥ ለማድረግ በቻይና ተፅዕኖ ውስጥ ወድቋል ብለው የሚያምኑ የስፖርት ቤተሰቦች ጥቂት አይደሉም። ለዚህ ሌላ ማሳያው በዳይመንድ ሊጉ ለውጥ ለማድረግ ጥናት ሲካሄድ በአትሌቲክሱ ዓለም ትልቅ ድርሻ ያላቸው ምስራቅ አፍሪካውያን አገራት እያሉ ቻይና ተመራጭ መሆኗ ነው። ለዚህ ውሳኔ ይረዳቸው ዘንድ ኮ የዓለም አትሌቲክስ ትልቅ የስራ ሃላፊነቶች በራሳቸው አገር እንግሊዝ ዜጎች ቀደም ብለው እንዲያዙ ማድረጋቸው ማሳያ ተደርጎ ይቀርባል። ከኮ በተጨማሪ የዓለም አትሌቲክስ የፅሕፈት ቤት ሃላፊው እንዲሁም የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዋናው ሰው ጃኪ ብሮክ ዶይል እንግሊዛዊ መሆናቸውን እዚህ ላይ ልብ ይለዋል። በእርግጥ በዓለም አትሌቲክስ ውስጥ ይህ ነገር ብርቅ አይደለም። ከዚህ ቀደም ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩት የነበሩት ላሚን ዲያክ ከልጃቸው ጀምሮ ሌጋሲያቸውን የሚያስቀጥሉላቸው እንደ ፕሪሞ ኔቢሎ አይነት ጣልያናውያንን በማህበሩ ቁልፍ ቦታዎች አስቀምጠው ነበር። የዓለም አትሌቲክስ በቅርቡ ይፋ ያደረገው ‹‹ኮንቲኔንታል ቱር›› የተባለው ሁለተኛ ትልቅ ውድድር በተለያዩ አስር የዓለማችን ከተሞች እንዲካሄድ ውሳኔ ላይ ሲደረስ አብዛኞቹ የውድድሩ መዳረሻ ከተሞች በአውሮፓ የሚገኙ መሆናቸው ሌላ ጥያቄ የሚጭር ጉዳይ ነው። ከነዚህ ውድድሮች መካከል ዘጠኙ በየትኛው ከተማ እንደሚካሄዱ ተወስኗል። ቶኪዮ፣ ናንጂንግ፣ ኦስትራቫ፣ ሄንግሎ፣ ቱርኩ፣ ኪንግስተን፣ ዤክስፈርቫር፣ ሲሌሲያና ዛግሬብ ውድድሩ የሚካሄድባቸው ከተሞች ናቸው። የኬንያ የስፖርት ካቢኔ ፀሐፊ አሚና ሞሐመድ እንዲሁም የኬንያ አትሌቲክስ ዋና ፀሐፊው ኪሪሚ ካቤሪያ ይህ ውሳኔ በሞናኮ ሲተላለፍ ናይሮቢ አስረኛው ውድድር እንዲሰጣት ጥያቄ ለማቅረብ በስፍራው ነበሩ። ጥያቄያቸው ግን አዎንታዊ ምላሽ እንደማያገኝ የዓለም አትሌቲክስ ተንታኞች ከወዲሁ ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። ምክኒያታቸውም ዓለም አቀፍ ማህበሩ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት ያለው ዝግጁ በሆነ መሰረተ ልማት ላይ እንጂ እንደ አዲስ በሚገነባ ላይ እንዳልሆነ ነው። አስረኛው ውድድር ምናልባትም ለአፍሪካ መሰጠት ካለበት የደቡብ አፍሪካዋ ፕሪቶሪያ ከተማ ከናይሮቢ በበለጠ ተመራጭ ልትሆን ትችላለች።የዓለም አትሌቲክስ ግን ከሁለቱም የአፍሪካ ከተሞች በተሻለ በአሜሪካዋ ዩጂን ከተማ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ። ምክኒያቱም ዩጂን የ2021 የዓለም ቻምፒዮናን ለማስተናገድ በኦሪገን ግዛት በሐይዋርድ ፊልድ ዩኒቨርሺሲቲ አዲስ ስቴዲየም እያስገነባች ትገኛለች። የዓለም አትሌቲክስ በዓለም ዙሪያ የልማት ስራዎችን ለማከናወን መቶ ሚሊየን ዶላር እየመደበ ይንቀሳቀሳል። አሜሪካ ከዚህ ገንዘብ እስካሁን ተቋዳሽ እንዳልሆነች የሚናገሩ ወገኖች አሁን ላይ ተራው የዩጂን እንደሚሆን ጠንካራ እምነት አላቸው። ሪድገን ‹‹አሜሪካውያን አትሌቶች ከአሜሪካ ጎዳናዎች በተሻለ በአውሮፓ ጎዳናዎች ይታወቃሉ፣ ይህ ሆን ተብሎ የተፈጠረ ባይሆንም አሁን መቀየር አለበት›› ማለታቸው አስረኛው ውድድር ለዩጂን ስለመሰጠቱ ፍንጭ ይሆናል።አዲስ ዘመን ኅዳር 22/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=23446
91be22f70cde65b2bccfc64d43ce501a
c2238b1ce8e1b5913331d36b61cd1d5e
ኢትዮጵያውያን በድልና በክብረወሰን የደመቁበት የቫሌንሲያ ማራቶን
ስፖርት
‹‹ስፖርታዊ ጨዋነት ለሰላማዊ ውድድር›› በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የውይይት መድረክ በሀዋሳ ተካሄደ፡፡ በውይይቱ የደቡብ ክልል መስተዳድር ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው፣ የኢፌዴሪ ባህል ፣ ቱረዝምና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ የሺዋስ ዓለሙና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ አመልክቷል፡፡ በውይይቱ ከፕሪሚየር ሊግ፣ ከብሔራዊ ሊግና ከፍተኛ ሊግ የመጡ አሰልጣኞች፣ ሥራ አስኪያጆች፣ ቡድን መሪዎች፣ ቴክኒካል ዳይሬክተሮችና የክልሉ ዞኖች ስፖርት ዘርፍ ሃላፊዎች፣ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በ2012 ዓ.ም በክልሉም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሰላምና የመቻቻል እንዲሆኑ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አቶ ርዕስቱ ይርዳው ተናግረዋል። ስፖርታዊ ውድድሮችን የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ የሚፈልጉ አካላትን መታገልና መስመር ማስያዝ ጊዜ የሚሰጥ ጉዳይ አለመሆኑን የተናገሩት አቶ ርዕስቱ ችግር በሚፈጥሩት አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አብራርተዋል፡፡ የአካል ጉዳተኛ ስፖርት ባለሙያዎች ስልጠና ለአካል ጉዳተኛ ስፖርት ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በአዳማ እየተሰጠ ነው። አካል ጉዳተኞች በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳታፊና እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ ሊፈጠርላቸው እንደሚገባ በስፖርት ፖሊሲው የትኩረት አቅጣጫ ላይ በግልፅ ሰፍሯል። ይህን ተግባራዊ ለማድረግ በተለይም የአካል ጉዳተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን በስፖርት ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በተለያየ ጊዜ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች፣ ስልጠናዎች እንዲሁም የውድድር መድረኮች ሲፈጠሩ ቆይተዋል። ትናንት የተጀመረው ስልጠናም በፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ከኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ፌዴሬሽንና ከኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ለፖራሊምፒክና መስማት ለተሳናቸው ስፖርት ባለሙያዎች በስርዓተ ፆታና በአመራርነት ዙሪያ የተዘጋጀ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መሆኑን የስፖርት ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል፡፡ ስልጠናው ለተከታታይ 3 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ60 በላይ ሙያተኞች ተሳትፈዋል። ስልጠናውን ከሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርሲቲ በመጡ ባለሙያዎችና ከኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ፌዴሬሽን ባለሙያዎች አማካኝነት እየተሰጠም ይገኛል። በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። የዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ደረጃ በሰጠውና በስፔኗ ቫሌንሲያ በተካሄደው ውድድር ላይ በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል። በተለይ በሴቶች ምድብ በተካሄደው ውድድር በጎረቤት አገር ኬንያ አትሌቶች ጋር እስከ 10ኛው ኪሎ ሜትር ድረስ የአንገት ለአንገት ትንቅነቅ በተካሄደበት ውድድር ኢትዮጵውያን ባልሸነፍ ባይነት እስከ መጨረሻ ታግለው ድሉን የግላቸው ማድረግ ችለዋል። በውድድሩ እስከ 15 ኪሎ ሜትር ድረስ ሁለት አትሌቶች ወደ ፊት መውጣት ቢችሉም በማሬ ዲባባና ቪቪያች ቼሮይት መካከል የነበረው አስገራሚ ፉክክር ሩጫውን ከመነሻውም አጓጊ አድርጎታል። ከዚያ በኋላ ባሉት ኪሎ ሜትሮችም ኢትዮጵያ ውያኑ ሮዛ ደረጀ ፣ አዝመራ አብረሃና ብርሃኔ ዲባባ እየተፈራረቁ በመምራት ለኬንያውያኑ ፈታኝ መሆን ችለዋል። በነበረው ጠንካራ ፉክክር አትሌቶቹ የርቀቱን ግማሽ የሸፈኑበት ሰዓትም ፈጣን እንደነበር ለመታዘብ ተችሏል።፡ ከ40ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ ሮዛ ደረጃ የበላይነቱን ብትይዝም በኬንያዊቷ አትሌት ብርቱ ፉክክር ገጥሟት ነበር። ሆኖም አዝመራ አብረሃ ተጭና በመሮጧ ምክንያት ሮዛ ወደ ፊት ለመውጣት ስታደርግ የነበረውን ጥረት እንዲሳካ አድርጋለች። በቅርቡ በተካሄደው የለንደን ማራቶን ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው ሮዛም ባገኘችው ዕድል በመጠቀም ርቀቱን በቀዳሚነትና የቦታውን ክብረ ወሰን በማስመዝገብ ጭምር ለማጠናቀቅ ችላለች። የገባችበት ሰዓትም 2:18:30 ሆኖ ሲመዘገብ ቀድሞ ከነበራት ፈጣን ሰዓት በ47 ሰከንዶች የፈጠነ ሆኗል። ሮዛ ያስመዘገበችው ሰዓት በርቀቱ ቀዳሚ ከሆኑ አስር ባለ ፈጣን ሰዓት አትሌቶች መካከል እንድትካተት አስችሏታል። በርቀቱ ለድሉ መገኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራት የ21 ዓመቷ ወጣት አትሌት አዝመራ አብረሃ ደግሞ ጠባብ በሆነ ልዩነት 2:18:33 የሆነ ሰዓት በማስመዝብ ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን ፈጽማለች። የድሉ ባለቤት የሆነችው ሮዛ በስፔን አገር ላይ ሮጣ ስታሸንፍ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። በዚሁ ዓመት ከወራት በፊት አትሌቷ በባርሴሎና በተካሄደ ግማሽ ማራቶን 1:06:01 የሆነ ሰዓት በማስመዝገብ ቀዳሚ ሆና ማጠናቀቋ ይታወሳል። ሁለተኛ ድሏን ከትናንት በስቲያ ካስመዘገበች በኋላም ‹‹ቫሌንሲያ ከተማውንና ውድድሩን በጣም እወዳቸዋለሁ። ሁለተኛ ድሌን በስፔን በማስመዝገቤ እንዲሁም ሰዓቴን በማሻሻሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ›› በማለት አስተያየቷን ሰጥታለች። ውድድሩን ሦስተኛ ሆና የፈፀመችው የ2015 የዓለም ቻምፒዮኗ ብርሃኔ ዲባባ ስትሆን የግል ሰዓቷን ያሻሻለችበትን 2:18:46 አስመዝግባለች። በውድድሩ ጫና ለመፍጠር የሞከረችው ኬንያዊት ቪቪያን ቼሩይት ደግሞ ከብርሃኔ በስድስት ሰከንዶች ዘግይታ አራተኛ ሆና ውድድሩን ፈፅማለች። ሌላኛዎቹ ኢትዮጵያዊያን ዘይነባ ይመር፣ ወርቅነሽ እዴሳ፣ አበባ ገብረመስቀልና ታደለች በቀለ ደግሞ አንዲት ኬንያዊትን ብቻ በጣልቃ ገብታባቸው ከአምስት እስከ ዘጠኝ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል። በወንዶች በኩልም ተካፋይ ከነበሩት አትሌቶች መካከል አራት የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በማራቶን ከ2 ሰዓት ከ05 በታች መሮጥ የቻሉ መሆናቸው ከውድድሩ ቀደም ብሎ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚካሄድበት ሲጠበቅ ነበር። ንፋሳማ በነበረው የአየር ሁኔታ አትሌቶቹ ከመነሻውም ተበታትነው ይሩጡ እንጂ ኢትዮጵያውያኑና ኬንያውያኑ አራት አትሌቶች ርዕስ በርዕስ ተከታጥለው ጠንካራ ፉክክር ሲያደርጉ ታይተዋል። የውድድሩን ግማሽ ወይም ሃያ አንድ ኪሎ ሜትሩን ለማገባደድ የፈጀባቸው ጊዜ 1:01:58 በመሆኑም የቦታው አዲስ ክብረወሰን እንደሚሰበር ፍንጭ የሰጠ ነበር። በመጨረሻም ክንዴ አጥናው መሪነቱን በማጠናከር አሸናፊ ሊሆን ችሏል። ርቀቱን በቀዳሚነት አጠናቆ ክሩን ለመበጠስ የፈጀበትም 2:03:51 የሆነ ሰዓት ነው። ከሩጫው በኋላም ‹‹አሁን ማራቶንን የማሸነፍ ጊዜው የእኔ መሆኑን አውቅ ነበር። በዝግጅት ወቅት አሸናፊ ለመሆን እሰራ ነበር፤ ይህም እውን ሆኗል›› ሲል ክንዴ አስተያየቱን ሰጥቷል። ቱርካዊው ካን ኪግን በ2:04:16 ሁለተኛ ሆኖ ሲገባ፤ ጉዬ አዶላና አበበ ደገፋ ደግሞ በሰከንዶች ልዩነት ሦስተኛና አራተኛ በመሆን ውድድሩን ፈጽመዋል። አሸናፊ ሞገስ፣ ፀጋዬ ጌታቸውና ልዑል ገብረሥላሴም እስከ አስር ባለው ደረጃ ተከታትለው መግብት የቻሉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው። ከማራቶን ውድድሩ ቀደም ብሎ እዚያው ቫሌንሲያ በተካሄደው የአስር ኪሎ ሜትር ውድድር ዩጋዳዊው አትሌት ጆሹአ ቺፕቴጌ የዓለም ክብረወሰን በማሻሻል ማሸነፉ ያልተጠበቀ ነበር። ከሁለት ወራት በፊት በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በአስር ሺ ሜትር ፉክክር ሳይጠበቅ ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻን አስከትሎ በመግባት ማሸነፍ የቻለው ቺፕቴጊ 26፡38 በሆነ ሰዓት የክብረወሰን ባለቤት ሆኗል። ይህ አትሌት በውድድር ዓመቱ በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና ላይ አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል። ከሳምንት በፊት የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌቶች ሽልማት በሞናኮ ሲካሄድ ቺፕቴጌ ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች መካከል አንዱ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ያሻሻለው ክብረወሰን ምናልባትም ከሳምንት በፊት ቢሆን የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማትን የማሸነፍ ከፍተኛ ዕድል ይኖረው ነበር። ቺፕቴጌ ያሻሻለው የዓለም የጎዳና ላይ አስር ኪሎ ሜትር ክብረወሰን እ.ኤ.አ 2010 ላይ በኬንያዊው ሊዮናርድ ፓትሪክ ኮመን የተያዘ ሲሆን ሰዓቱም 26፡44 ነበር። ሮዛ ደረጄ በቫሌንሲያ ማራቶን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸናፊ ሆናለች፣ አዲስ ዘመን ኅዳር 23/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=23492
9c83e168717bc72026c3341fae950960
48933cfd926f37a6b1251aab5639163c
የኢቨስትመንት ህጉ መሻሻል ለቴክኖሎጂ ሽግግርና የሥራ እድል ፈጠራ እንደሚያግዝ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
በኃይሉ አበራአዲስ አበባ:- የኢንቨስትመንት ህጉ መሻሻል የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በማረጋገጥ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በማሻሻል፣ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት እና ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር በኩል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሰሞኑ ከእስራኤል፣ ከእንግሊዝ እና ከአውስትራሊያ ከመጡ ባለሀብቶች ጋር በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አበባ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሂዷል።በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ኃይሉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ መንግሥት የኢንቨስትመንት ህጉን በማሻሻል፣ የግሉን ዘርፍ ሚና በማጎልበት እንዲሁም ኢትዮጵያ ከመቼውም በላይ ለቢዝነስ የተሻለችና ምቹ እንድትሆን ከማድረግ አንጻር በትኩረት እየተሰራ ነው። ይህም የውጭ ባለሀብቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ኢንቨስትመንቱን እያሳደገው ይገኛል።በሀገራችን በተካሄደው የፖለቲካ ሪፎርም በሌላኛው ጎኑ የኢኮኖሚ መሻሻሎች ማምጣቱን የገለጹት አቶ መኮንን፤ ኢትዮጵያ ያሻሻለችው የኢንቨስትመንት ሕግ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ደረጃ በኢትዮጵያ ያለው መደላደል ምቹ መሆኑን ግንዛቤ መወሰዱን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ እንድትሆን ከማድረግ አንጻር ባለፉት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አስተባባሪነት እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ተሳትፎ ተቋማቶችን ባካተተ መልኩ የንግድና ኢንዱስትሪ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የባንክና ሌሎች መሰል ነገሮች ጋር በተያያዘ ኢንቨስትመንቱን የማቅለል ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ መኮንንን እንደሚሉት፤ አንክታድ በሚባል ዓለም አቀፍ ሪፖርት በቅርቡ ባወጣው መረጃ ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም ላይ ትገኛለች፤ በአፍሪካ ደረጃ ደግሞ ከግብጽ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ኮንጎና ሞሮኮ በመቀጠል በአምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በመሆኑም በሀገራችን የውጭ እና የሀገር ውስጥ ተሳትፎ የሚያሳድግ እና የግል ዘርፉን ሰፋ ባለ መልኩ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያስችል የኢንቨስትመንት ሕግ ተሻሽሎ መቅረቡ ሀገራችን የበለጠ የወጭ ባለሀብቶች ትኩረት እንዲኖራት ያስችላታል። ይህ ደግሞ ለዜጎቻችን ሰፊ የሥራ እድል ከመፍጠር አንጻር የጎላ እና የላቀ ሚና ይኖረዋል። እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ግኝት እና የቴክኖሎጂ ሽግግሩንም የተሻለ ያደርገዋል፤ ነው ያሉት።የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በበዙ ቁጥር ኅብ ረተሰቡ በሚያገኘው አቅርቦት ከትምህርት ቤት፣ ከሆስፒታሎችና መሰል የመሠረተ ልማት እና የማህበራዊ ተቋማት አገልግሎት እያደጉ የሚመጡ በመሆኑ ለዜጎች የሥራ እድል ፈጠራ ባሻገር የማህበራዊ ተቋማት አገልግሎትን በማሳደግም በቀጥታ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉም ነው አቶ መኮንን የገለጹት።በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ተሳታፊ የነበሩት አቶ አሰፋ፣ መንገሻ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በፀሐይ ኃይል ውሃ የሚያሞቁ መሳሪያዎችን የሚያመርት ፋብሪካ በሰንዳፋ የኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ ያቋቋሙ ባለሃብት ናቸው። በእስራኤል ሀገር ከ30 ዓመት በላይ መኖራቸውን የገለጹት አቶ አሰፋ እንደሚሉት፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን ኢንቨስትመንት ከማሻሻል አንጻር ጥሩ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ነገር ግን ከዋና ኮሚሽኑ ከወጣ በኋላ ያለው የቢሮክራሲ ሁኔታ በጣም መሻሻል ይኖርበታል።አሁን ያለው የኢንቨስትመንት ህግ መሻሻልን ተከትሎ የኢንቨስትመንት የአቀባበል ሁኔታውን ማፋጠን ከተቻለ፣ እስራኤል አነስተኛ አገር ብትሆንም የቴክኖሎጂ ባህር እንደመሆኗ በእርሻ፣ በሶላር እና ሌሎችም በርካታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ እንደሚችሉ ነው አቶ አሰፋ የተናገሩት። በፀሀይ ኃይል ውሃ የሚያሞቁ መሳሪያ ማምረቻው ወደ ሀገራችን ቢገባ ያለውን ጠቀሜታና አዋጭነት በማሰብ እና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት በሚል ቴክኖሎጂውን ማቋቋማቸውን የገለጹት አቶ አሰፋ፤ ፋብሪካውን ካቋቋሙ ስድስት ዓመት እንደሆነውና ምርት ማምረት ከጀመረ አራት ዓመት እንደሆነው ተናግረዋል። ከብዙ ድካምና ውጣውረድ በኋላም በግል መኖሪያ ቤቶች በፔንሲዮኖች፣ በአፓርትመንቶች፣ በሆቴሎች እና ጤናጣቢያ ላይ ሁሉ መግጠም መጀመራቸውን ገልጸዋል። አቶ አሰፋ፣ በእስራኤል ሀገር ሲኖሩ በነበረበት ቅቡጽ በሚባል ኩሚዩናል በሚኖርበት አካባቢ የእርሻ ሂደቱን ታዝበዋል። በሦስት ወር እና በአራት ወር ውስጥ የተለያየየምርት አይነት ይመረትበታል ብለዋል። በሦስት ወር እና በአራት ወር ውስጥ መሬቱ በተለያየ የምርት አይነት ይሸፈናል። ብዙ ሄክታር መሬት በበቆሎ ተሸፍኖ ይታያል፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደግሞ ያንን የዚያ ምርት ተሰብስቦ መሬቱን አለስልሰው በዚያ በቆላ መሬት ላይ የተንጣለለ የስንዴ ማሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲያሰሩ ይታያል፤ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ደግሞ አትክልቶች ሲሰራበት መመልከታቸውን ገልጸዋል። ይሄንን ቴክኖሎጂ በሀገራችን ተግባራዊ በማድረግ ኢትዮጵያን በይበልጥ የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ማድረግ ይቻላል፤ የስንዴ ቋት መሆን እንችላለን። ቴክኖሎጂውን ደግሞ ለመቀበል እና ወደ ፊት ለማራመድ በሀገራችን በእርሻ ኢንጂነሪንግ የተማሩ ሰዎች በኩል ቴክኖሎጂውን በማስፋፋት ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን በማገናዘብ ከራሳችን አልፈን ለሌላው ሀገር ማቅረብ የሚቻልበትን ሰፊ እድል አለ ብለዋል። በሀገራችን ባሌና አርሲ የስንዴ ሜዳ መሆናቸው እንደሚታወቀው ሁሉ በወሎ እና አፋር ድንበር ላይ ከፍተኛ የስንዴ ምርት ማምረት ይቻላል። በሱማሌ ክልል ገናሌና ሸበሌ ወንዞች አሉ ሜዳው የሰጠ ነው ሰላም እና ደህንነት እስካለ ድረስ ከራሳችን አልፈን ምርቱን ሽጠን ለሌላም ሀገር መቀለብ የሚያስችል አቅም አለ። ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ አይደለችም የሚለውን የውጪ ኢንቨስተሮች እይታ ለመቀየር ኢትዮጵያውያን የሀገራችንን ጥቅም በሚጠብቅ ሁኔታ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በግልጽ በመወያየት እና ግብረመልስ መስጠት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል። የምርት አይነት ይመረትበታል ብለዋል። በሦስት ወር እና በአራት ወር ውስጥ መሬቱ በተለያየ የምርት አይነት ይሸፈናል። ብዙ ሄክታር መሬት በበቆሎ ተሸፍኖ ይታያል፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደግሞ ያንን የዚያ ምርት ተሰብስቦ መሬቱን አለስልሰው በዚያ በቆላ መሬት ላይ የተንጣለለ የስንዴ ማሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲያሰሩ ይታያል፤ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ደግሞ አትክልቶች ሲሰራበት መመልከታቸውን ገልጸዋል። ይሄንን ቴክኖሎጂ በሀገራችን ተግባራዊ በማድረግ ኢትዮጵያን በይበልጥ የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ማድረግ ይቻላል፤ የስንዴ ቋት መሆን እንችላለን። ቴክኖሎጂውን ደግሞ ለመቀበል እና ወደ ፊት ለማራመድ በሀገራችን በእርሻ ኢንጂነሪንግ የተማሩ ሰዎች በኩል ቴክኖሎጂውን በማስፋፋት ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን በማገናዘብ ከራሳችን አልፈን ለሌላው ሀገር ማቅረብ የሚቻልበትን ሰፊ እድል አለ ብለዋል። በሀገራችን ባሌና አርሲ የስንዴ ሜዳ መሆናቸው እንደሚታወቀው ሁሉ በወሎ እና አፋር ድንበር ላይ ከፍተኛ የስንዴ ምርት ማምረት ይቻላል። በሱማሌ ክልል ገናሌና ሸበሌ ወንዞች አሉ ሜዳው የሰጠ ነው ሰላም እና ደህንነት እስካለ ድረስ ከራሳችን አልፈን ምርቱን ሽጠን ለሌላም ሀገር መቀለብ የሚያስችል አቅም አለ። ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ አይደለችም የሚለውን የውጪ ኢንቨስተሮች እይታ ለመቀየር ኢትዮጵያውያን የሀገራችንን ጥቅም በሚጠብቅ ሁኔታ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በግልጽ በመወያየት እና ግብረመልስ መስጠት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37781
14c7587e7d2a79a010c98ea21ca5ef6a
0a2f85fd7eddba79b0bdfed188ee1622
ጁንታው ለዘረፋ ያሰማራቸውን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታ ከማረሚያ ቤት በመልቀቅ ለዘረፋ ያሰማራቸውን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ። በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ ዛሬ በመቀሌ ከተማ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።ኢዜአ እንደዘገበው፤ ምክትል ኮሚሽነር መካሉ እንደገለጹት፤ ጁንታው ከተሞችን ለቆ ከመሸሹ በፊት በማረሚያ ቤት የነበሩ ወንጀለኞችን መሳሪያ አስታጥቆ በመልቀቅ በከተሞች አካባቢ ዝርፊያ እንዲፈጽሙ አድርጓል። እነዚህ ወንጀሎችም የመንግሥት ተቋማትን ንብረት ጭምር ዘርፈዋል። የፌዴራል ፖሊስ ከኅብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉን ሥራ አጠናክሮ መቀጠሉንም የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ ወንጀለኞቹ የታጠቁትን የጦር መሳሪያዎች የማስፈታቱ ተግባር እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። በተጨማሪም ህገ-ወጡ የህወሓት ጁንታ በመንግሥት ተቋማት ያሉ ሰነዶችንና ሰነድ የያዙ ኮምፒውተሮችን አቃጥሎ መሸሸኑም ገልጸዋል።ይህም ቡድኑ ከራሱ ስልጣን ውጭ ለህዝብ ምንም አይነት ደንታ የሌለው መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ በመጠቆምም፤ የአካባቢው ማኅበረሰብ የፌዴራል ፖሊስ እያከናወነ ያለውን ተግባር በመደገፍ ረገድ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑንም ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37783
ee513b92306a9ccfeeec02f0313c16cd
72ce3520235e92db5c4defc40866fd86
ኦነግ ሸኔን በመደምሰሱ ሂደት የህዝቡ ድጋፍ ትልቅ ድርሻ እንደነበረው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዋቅሹም ፍቃዱ አዲስ አበባ፡- በሰላም ለመታገል ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ወደ ትጥቅ ትግል የተመለሰው ኦነግ ሸኔን በመደምሰስ ሂደት ህዝቡ ከጸጥታ አካሉ ጎን ሆኖ በአሰሳ እያገዘ፤ በሰላማዊ ሰልፍም ቡድኑን እያወገዘ መሆኑ ተገለጸ።ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተወሰደው እርምጃ 846 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሲደመሰሱ፤ ከ3ሺህ 700 በላይ ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ሆነው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ተናግረዋል። ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የኦነግ ሸኔ ቡድን ኃይሉን ለማጠናከር በክልሉ ጠረፋማ አካባቢዎች ተደብቆ የጥፋት ኃይሎችን በመመልመል ሲያሰለጥን፤ እንዲሁም በህወሓት ጁንታ ኃይል የሎጀስቲክ ድጋፍ ተደርጎላቸው በትግራይ ክልል ጭምር በመሄድ ስልጠና ሲወስድ ነበር። አሁን ላይ ግን ጁንታው በመደምሰሱ የቡድኑ ኃይል እየተዳከመ ከመሆኑ በተጨማሪ፤ ባለፉት ሦስት ወራት የክልሉ መንግሥት ህዝቡን በጎኑ በማሰለፍ በወሰደው እርምጃ 413 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እጅ ባለመስጠታቸው ሲገደሉ፤ እጅ የሰጡና የተያዙ ደግሞ 433 ናቸው። በዚህም በጥቅሉ 846 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደምስሰዋል።የኦነግ ሸኔ ቡድን እጅግ ጨካኝ ከመሆኑ የተነሳ ስልቱን በመቀያየር አንዳንድ አካባቢዎች እንደ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ በብሔር ላይ ያነጣጠሩ ጥቃት ይፈጽማል፤ በምስራቅ ኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ሀይማኖታዊ መልክ ያለው ጥቃት በመፈጸም አገርን ለማተራመስ ይጥራል። በዚህ መልኩ እስካሁን መንግሥት ሹመኞችና በንጹኃን ዜጎች ላይ በወሰዳቸው እርምጃዎችም ከ500 በላይ ንጹኃን ህይወታቸውን አጥተዋል።አሁን ግን አንዳንድ እንደ ቄለም ወለጋ ያሉ አካባቢዎች ህዝቡ ወጥቶ አሰሳ እያደረገ፣ በሠላማዊ ሰልፍም እያወገዘ በመሆኑ እንደ ከዚህ በፊቱ ጉልበቱን አጠናክሮ የጥፋት ስራውን መፈጸም አይችልም። እንደከዚህ በፊቱም መንገድ ዝጉ እንዲ አድርጉ የሚሉ ትዕዛዞችን ህዝቡ እየተቀበለ አይደለም። የክልሉ ጸጥታ አካላትም ቡድኑ የሚንቀሳቀስበት አካባቢን ተቆጣጥረው እንዳሉ፤ እና ህዝቡም የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ነው ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ የተናገሩት።እንደ ኦነግ ሸኔ ቀጥታ ጠመንጃ አንግበው ህዝቡን የሚጨርሱና ተኩሰው ባይገሉም ኦነግ ሸኔን በቁሳቁስ፣ በገንዘብና በሞራል የሚደግፉ እንዲሁም ኦነግ ሸኔ የሚፈጽመውን ጥቃትና ጥፋት ወደ መንግሥት በማዞር በተሳሳተ መረጃ ህዝቡን የሚያደናግሩና መንግሥትን በተለይ የጸጥታ ኃይሉን ለማጠልሸት በኦነግ ሸኔ የተደራጁ በርካታ የሶሻል ሚዲያ ሠራዊት ጭምር መኖራቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ፤ በዚህ መሰል ጥፋት የተሰለፉ ከ3ሺህ 700 በላይ ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ሆነው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ከመንግሥት መስሪያ ቤት ሳይቀር ሰፊ የማጥራት ስራ ለመስራት በቅርቡ እንደሚጀመር ተናግረዋል። ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዘው አገሪቱን የብጥብጥ ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት 1ሺህ 700 በላይ በተለያዩ የስልጣን እርከን ላይ በነበሩት አመራሮች ላይ የተወሰደው እርምጃ አሁን በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ ላለው እርምጃ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የገለጹት ኮሚሽነር አራርሳ፤ በወቅቱ የተተኩ አዳዲስ አመራሮች በቁርጠኝነት የሰሩት ሥራ ኦነግ ሸኔን ለማድከም ትልቅ አስተዋፅዖ እንደነበረው ገልጸዋል። ህዝቡም ቡድኑን አሳልፎ በመስጠትና ለጸጥታ አካላት መረጃ በማቀበል ጉልህ ሚና መጫወቱንም አብራርተዋል።እንደ ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ ገለጻ፤ በዓለም ተሞክሮ ሽምቅ ተዋጊ ኃይል በአንድ ቦታ ሆኖ በግንባር የሚዋጋ ኃይል ባለመሆኑ በአንድ ጀምበር ማጥፋት ሊያዳግት ይችላል። ሆኖም ሁለት መሠረታዊ ስልቶችን በመጠቀም በድኑን ከነ ዓላማው መቅበር ይቻላል። አንደኛው፣ በህዝቡ ላይ በመስራት የጥፋት ቡድኑን ብቻውን በማስቀረት ተስፋ ቆርጦ እንዲጠፋ ማድረግ ወሳኝ ስልትና ትልቁ የመንግሥት የቤት ስራ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ሁሉንም የድጋፍ በሮችን በመዝጋት የሎጅስቲክ ረሃብተኛ፣ ከዓለም የተነጠለ፣ ከህዝብ የተገለለ በማድረግ ይህን የሽምቅ ተዋጊ ቡድንን ከስራ ውጭ ማድረግ ይቻላል። በዚህ መልኩም እየተሰራ ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12 ቀን 2013  ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37765
12e8966685d5d855f752e32098dc605a
d1f2d1c8625e3d101bc6d32219aa38bb
ባንኩ እአአ 2020 መጨረሻ ከግብር በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ጸጋዬአዲስ አበባ፡- እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ከግብር በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን፤ ይሄም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በበጀት ዓመቱ የትርፍ መጠኑ የ6ነጥብ9 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አስታወቀ። ባንኩ ለተለያዩ ሀገራዊ ልማቶች 19 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገ ማድረጉንም ተገልጿል።የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ዶክተር ሰውአለ አባተ፣ ትናንት በአዲስ አበባ ባካሄደው የባንኩ ባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የበጀት ዓመቱን ሪፖርት ለባለ አክሲዮኖች አቅርበዋል። በወቅቱም እንደተናገሩት፤ የበጀት ዓመቱ ለባንኩ ዘርፍ በርካታ እንቅፋቶች የነበሩበት ቢሆንም፤ እነዚህን ችግሮች በመቋቋም እአአ በ2020 ከታክስ በፊት የ582 ነጥብ 04 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት ተችሏል።እንደ ዶክተር ሰውአለ ገለጻ፤ ባንኩ የውጭ ንግዱ 111 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኘ ሲሆን፤ ከውጭ ሀገር በሀዋላ እና በስዊፍት የተላከ ደግሞ የ28ነጥብ4 ሚሊዮን ዶላር አስገኝቷል። የባንኩ ሀብትም በበጀት ዓመቱ የ4ነጥብ37 ቢሊዮን ብር እድገት በማሳየት ጠቅላላ ሃብቱን ወደ 18ነጥብ87 ቢሊዮን ብር አሳድጓል።ዶክተር ሰውአለ እንደሚሉት፤ በተጠቀሰው በጀት ዓመት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን በ3ነጥብ29 ቢሊዮን ብር በማሳደግ የባንኩን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 13ነጥብ88 ቢሊዮን ደርሷል። ከአጠቃላይ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ውስጥ የተንቀሳቃሽ ሂሳብ የ19 በመቶ ድርሻን ሲይዝ፤ በአንፃሩ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ደግሞ የ5 በመቶ ድርሻ ነበረው። ይህም የባንኩን አብዛኛው ተቀማጭ አስተማማኝ እንዲሆን አድርጎታል። ባንኩ በዓመቱ ውስጥ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች 3ነጥብ29 ቢሊዮን ብር ብድር የሠጠ ሲሆን፤ ይህም ባንኩ አጠቃላይ የሰጠውን ብድር በ40 በመቶ አሳድጎታል።ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ባንኩ ትርፍ የብር 42ነጥብ99 ሚሊዮን ወይንም የ6ነጥብ9 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን የገለጹት ሊቀመንበሩ፤ ለዚህ ደግሞ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴውን ማቀዛቀዙ ግንባር ቀደምትነት ሚና እንዳለው ገልጸዋል። በአገሪቱ በአንዳንድ ክልሎች ተከስቶ የነበረው ማህበራዊና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ኢኮኖሚውን በጤናማ መንገድ እንዳይጓዝ በማድረግ በወጭና በገቢ ንግዱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ ባንኩ በበጀት ዓመቱ ለማሳካት ያሰበውን የትርፍ መጠን ባሰበው ልክ እንዳይሆን ማድረጉንም ጠቁመዋል።ባንኩ በ2030 በሀገራችን ሦስት ግንባር ቀደምና ተመራጭ ባንኮች መካከል አንዱ መሆንን አላማ አድርጎ ተነስቷል ያሉት ሊቀመንበሩ፤ የቡና ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት እንደ ‹‹ገበታ ለሀገር›› የመሳሰሉ ሀገራዊ የልማት እና ኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከል የሚሆን ድጋፍ በማድረግ በድምሩ 19 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል። ይህ ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት ቀጣይነት እንደሚኖረው በመጥቀስም፤ 37 አዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት ቁጥሩን ወደ 242 አሳድጎ በመስራት በበጀት ዓመቱ ብቻ የተቀማጭ ሂሳብ የደንበኞችን ቁጥር በ268 ሺህ70 በማሳደግ የደንበኞችን ቁጥር 809 ሺህ 493 ማድረስ መቻሉ ዓመልክተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37782
dcd9a549464e4b810e8b34df1aa85f1f
e80eca1580a68f3b29b9aa3cc7463c5a
በመቀሌ ለነዋሪዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- መቀሌ ከተማ የደረሰው የእለት ደራሽ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለዜጎች በመድረስ ላይ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ገለጸ። እንደ ኢዚአ ዘገባ፣ በመቀሌ ከተማ ለ80 ሺህ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን የጊዜያዊ አስተዳደሩ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ወይዘሮ ሳባ ገብረማርያም ገልጸዋል። የፌዴራል መንግሥት በክልሉ የምግብ፣ መድኃኒትና ሌሎች ቁሳቁሶችን በማቅረብ ላይ መሆኑን እና ጊዜያዊ አስተዳደሩም ለህዝቡ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝም ነው ያስረዱት።እንደ ወይዘሮ ሳባ ገለጻ፤ አሁን ላይ ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ እህል በመጋዘን ይገኛል። ይሄም እርዳታና ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች በመከፋፈል ላይ ነው። በዚህም በመቀሌ ከተማ ብቻ ለ80 ሺህ ዜጎች ድጋፉን ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ ነው። ሰብዓዊ ድጋፉ በመቀሌ ብቻ ሳይሆን በክልሉ የተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች በመዳረስ ላይም ይገኛል።በርካታ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎችም በችግር ላይ ያሉ ወገኖችን በመደገፍ ላሳዩት ተነሳሽነት ምስጋና ያቀረቡት ወይዘሮ ሳባ፤ ከፌዴራሉ መንግሥት የተላከውን ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት መድሃኒትም ማሰራጨት መቻሉን ገልጸዋል። ከፌዴራል መንግሥቱ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ እና አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተናግ ረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37784
b7a5c03bfd755b7197ad33ef944fbd83
51d70f649626a800c41661b9749822b9
የአንበጣ መንጋ ወደ ሰብል አብቃይ አካባቢዎች እንዳይዛመት እየተሠራ መሆኑን ተነገረ
ሀገር አቀፍ ዜና
ወርቅነሽ ደምሰውአዲስ አበባ፡- እንደ አገር በስፋት ተከስቶ የነበረውና አሁን ላይ በሱማሌ ክልል ብቻ ቀርቶ የነበረ የአንበጣ መንጋ ወደ ኦሮሚያና ደቡብ ክልል ሰብል አብቃይ አካባቢዎች እንዳይዛመት የመከላከል ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። በግብርና ሚኒስቴር የእጽዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ንጉሴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በሱማሌ ክልል ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረው የአንበጣ መንጋ አሁን ላይ ወደ ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች በመስፋት ላይ ሲሆን፤ መንጋው ወደነዚሁ አካባቢዎች ሄዶ በደረሱ ሰብሎች ጉዳት እንዳያስከትል የኬሚካል ርጭት ተጠናክሮ እየተካሄደ ነው።እስካሁን በሱማሌ ክልል የነበረው የአንበጣ መንጋ በኩኩባነት ደረጃ ያለው ቢሆንም አሁን ላይ አድማሱን እያሰፋ በመብረር ላይ ስለሆነ በቀላሉ መዛመት የሚችል መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ ከታህሳስ ወር ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ ከሱማሊያ አካባቢ ያደገው የአንበጣ መንጋ በስፋት ወደ ሀገራችን እየገባ በመሆኑ፤ የመከላከል ሥራም በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል። በሱማሌ ክልል የመከላከል ሥራ እየተሰራ ቢሆንም በመኪና ሆነ በሰው ኃይል በመግባት አንበጣውን መከላከል በማይቻልባቸው አካባቢዎች መንጋው በቀላሉ የመራባት ዕድል በማግኘቱ እና በሱማሌ ላንድና በፑትላንድ የሚደረገው የመከላከል ስራም እምብዛም በመሆኑ በቀጣይ በቂ መከላከል ካልተደረገ ሰብል አብቃይ ወደ ሆኑ አካባቢዎች በቀላሉ የመዛመት ዕድሉ አለ። እስካሁን 13 አውሮፕላኖች በመጠቀም የአሰሳ፣ የኬሚካል ርጭት ስራዎች እንዲሰሩ የተደረገ መሆኑን የሚናገሩት ዳይሬክተሩ፤ ባለፈው ከተከሰተው የአንበጣ መንጋ ዝግጅት አንጻር የአሁን ዝግጅት በኬሚካል አቅርቦትም ሆነ በርጭት ረገድ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል። የዓለም ምግብ ድርጅት(ፋኦ) ኬሚካልንና አውሮፕላኖችን በማቅረብ ከፍተኛ እገዛ በማድረጉ ርጭቱ በሰፊው እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።አሁን ላይ በሱማሌ ክልል አምስት ዞኖች ላይ በጀረር፣ በዶሎ ፣ በሸበሌ፣ በቆራሄ ና በአፍዴር ያደገው አንበጣ በብዛት ጎልቶ የሚታይባቸው ቦታዎች በመሆናቸው ከፍተኛ ሁኔታ ርጭት እየተካሄደ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ከባሌ ሮቤ ላይ ተነስቶ ግኒርና ራይቱን ወደመሰሉ ቦታዎች፤ እንዲሁም በደቡብ በኦሮሚያና በሐመር አካባቢ ከአርባ ምንጭ በመነሳት ርጭት እየተካሄደ ይገኛል። አሁን ባለው ሁኔታ ቁጥጥሩ በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ ስለሆነ እስካሁን ከአቅም በላይ የሆነ የአንበጣ መንጋ የለም ብለዋል ።ከፌዴራል ጀምሮ ከክልሎች አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጋር የተዘረጋው ቅንጅታዊ አሰራር ውጤት እያመጣ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በተለይ አርሶ አደሩ አንበጣ ያለበትን መረጃዎች በመስጠትና በህብረት በመስራት የሚያደርገው ጥረት መንጋውንለመከላከል እንዳስቻለ አመልክተዋል።እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ በሱማሌ ላንድ ላይ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረት አመርቂ ባለመሆኑ መንጋው በከፍተኛ ደረጃ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል የሚል ስጋት ያለ ሲሆን፤ በዚህ በኩል የሚገባ ከሆነ ደግሞ ከዚህ በተሻለ ተጠናክሮ ካልተሰራ የንፋሱን አቅጣጫ ተከትሎ ወደ ደቡብ ሄዶ የመስፋፋት ሁኔታ ይኖራል። ምንም እንኳን ከሱማሌ ላንድ በኩል የሚመጣው የመንጋ መጠን ከፍተኛ እንደሚሆን ቢገመትም ኢትዮጵያ የመከላከል አቅሟን በማሳደጓና በቂ ቅድመ ዘግጅት በማድረጓ መንጋው ወደ ሀገር ውስጥ ቢገባም ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል የሚል ግምት እንዳሌለ ያብራራሉ።የአንበጣ መንጋው ርጭቱ እየተካሄደ ያለው በቆላማ በሱማሌ ክልል አካባቢ ሲሆን፤ በሳር ላይና በግጦሽ ላይ ጉዳት እያደረሰ ቢሆንም እስካሁን ባለው ሁኔታ አካባቢ ላይ ሰብል ባለመኖሩ ጉዳትአልደረስም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ወደፊት የመስኖ ሰብሎች እየተመረቱ ያሉ ሲሆን፤ በተለይ ወደ ጎዴና ኦሮሚያ ውስጥ ራይቱ አካባቢ አሁን ላይ ሰብሎች በመዝራታቸው በተለይ ከቆላ ስንዴ ጋር ተያይዞ እየለሙ ያለበት ሁኔታ በመኖሩ በተቻለ አቅም ትኩረት በማድረግ እዚያ አካባቢ ሊያርፍ የሚችለውን የአንበጣ መንጋን ለመከላከል ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አቶ በላይነህ ጠቁመዋል።በቀጣይም በፌዴራል፣ በክልሎችና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በኩል የተቀናጀ አሠራር በመዘርጋት መንጋው ጉዳት እንዳያስከትል የተናበበ ሥራ እንደሚሰራ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ መንጋው በመስኖ የሚለሙ ቦታዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በድንበር በኩል ገብቶ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትልም ከሶማሊያና ከኬኒያ መንግሥታት ጋር የተናበበ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37794
86dd0cf6e79470e4f77e7c308457a912
3edfb11170db1ab0425775c58b94743f
በህግ ማስከበር ዘመቻው ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት እውቅና እንደሚሰጥ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
– የክልሎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል ሃይማኖት ከበደአዲስ አበባ:- በትግራይ ክልል በተደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት በየደረጃው እውቅና እንደሚሰጥ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። የክልል ልዩ ሃይሎች በየቦታው የነበራቸው አስተዋጽ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል። ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ትናንት ከኦቢኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ እንዳስታወቁት፤ በዚህ የህግ ማስከበር ላይ የተሳተፉ የሰራዊቱ አባላት እንደየደረጃቸው የተለያዩ ሽልማቶችን የሚሸለሙ ይሆናል። ሜዳሊያ እና ማዕረግ የሚሸለሙ እንዲሁም ሌሎች የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ስርአቶችም የሚሰጡ ይሆናል።“ጀግኖች ይሸለማሉ ታሪካቸውም ተፅፎ ለትውልድ ይቀመጣል” ያሉት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፤ እነዚህ ጀግኖች የሀገር ቅርስ ስለሆኑ እነሱን ማስተዋወቅ፣ መጠበቅና ማበረታታት ተገቢ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።እንደ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ማብራሪያ፤ በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፤ የአማራ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የአፋር፣ የሶማሌ እና ሌሎችም ክልሎች በተለያዩ መንገዶች ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር አብራርተዋል።የቆሰሉ የሰራዊቱ አባላት በአብዛኛው በአማራ ክልል ሆስፒታሎች ሲታከሙ መቆየታቸውን የገለጹት ጄኔራል ብርሃኑ፤ በክልሉ ያሉ ሆስፒታሎችና የህክምና መስጫ ተቋማት ለሰራዊቱ ክፍት እንዲሆኑ በማድረግ አምቡላንስና የህክምና ባለሙያ መድበው ቁስለኞችን በሰፊው ማከማቸውንና ሪፈር የተባሉት ብቻ ወደማዕከል መምጣታቸውን አስታውቀዋል። “ጁንታው በውጊያ ሲወጠር ባዶ እጃቸውን አግኝቷቸው ሳይማርክ ማርኬያለሁ ብሎ የፎከረባቸውና የታገቱ አባሎቻችንን ጥሏቸው ሲጠፋ ወደአማራ ክልል ነው የመጡት፤ አማራ ክልል ከድንበሩ ጀምሮ እስከመጨረሻው የመሰባሰቢያ ወረዳ ድረስ አጓጉዞ፣ አብልቶ፣ ሞራል ሰጥቶ ወገናዊነቱን አሳይቶ ነው የሸኛቸው፤ ይህ በጣም ከባድ ስራ ነው” ሲሉም ነው የክልሉ ህዝብን አስተዋጽኦ የገለጹት።“እኛ ያደረግነው እነሱ ያሰባሰቡትን፣ ያደራጁትንና በዩኒቨርሲቲ ያቆዩትንና የመገቡትን ተቀብለን ኦረንቴሽን ሰጥተን ነው ወደክፍላቸው የመለስናቸው” ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፤ “እኛ የጁንታውን ዋና ሃይል እየመታን ስንሄድ በእያንዳንዱ ውጊያ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ብዙ ቀዳዳ ሸፍኗል፤ ውጊያ ያለበት እየተዋጋ ውጊያ የሌለበት ደግሞ ቀጣናውን በመሸፈን ሰራዊቱ ቀጣና እሸፍናለሁ ብሎ ሃይል እየቀነሰ እንዳይሄድ አድርጓል፤” ሲሉም ነው የተናገሩት።እንደ ጄኔራል ብርሃኑ ገለጻ፤ በኦሮሚያም በኩል የነበረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። ከክልሉ ፕሬዚዳንት እና ከተወሰኑ አመራሮች በስተቀር ሁሉም አመራር ወደወረዳ አስገብቶ ልዩ ሃይሉን አስገብቶ በሸኔ በኩል ታቅዶ የነበረው እድል እንዳያገኝ የማድረግ ስራ ተሰርቷል። ሶማሌ ክልልም ራሱን ችሎ ጸጥታውን በመቆጣጠር ምንም ኮሽታ ሳይሰማ የህግ ማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁን የገለጹት ጄነራል ብርሃኑ፤ በክልሉ በምስራቅ ዕዝ የሚጠበቁ ብዙ ተቋማት እንደነበሩና አልሸባብም በዚያ አካባቢ የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ሁሉንም ስራ የክልሉ መንግስት ልዩ ሃይል በራሱ እንዳከናወነ አብራርተዋል። በተመሳሳይም የአፋር ክልል ልዩ ሃይል ያደረገው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ብርሃኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ህዝብም በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ገንዘብ አዋጥቶ ለሰራዊቱ ማበርከቱን በመጥቀስ መላው የአገሪቷ ህዝብ በተለያየ አስተዋጽኦ የተሳተፈበት ዘመቻ በድል መቋጨቱን አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37843
f521481ce72634358c44d9c83f5cbbba
9350d032ec1b27bf040345f12d9210c0
“መገንባት የምንፈልገው ዴሞክራሲ ጥቂቶች ብቻ የሚጫወቱበት ሜዳ ሳይሆን ብዙሃንን የሚያሳትፍ ሜዳ እንዲሆን ይፈለጋል”ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የሰላም ሚኒስቴር
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- መገንባት የምንፈልገው ዴሞክራሲ ጥቂቶች ብቻ የሚጫወቱበት ሜዳ ሳይሆን ብዙሃንን የሚያሳትፍ ሜዳ እንዲሆን ስለሚፈለግ ለሁሉም የሆነች አገርን በመገንባት ሂደት ላይ ሁሉንም ለማሳተፍ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ፡፡ትናንት በይፋ የተጀመረውን የብሔራዊ የማህረበሰብ ተኮር የምክክር መድረክን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን መሰረታዊ ተልዕኮ ለመወጣት ከባለድርሻዎች ጋር በትኩረት እየሰራ ይገኛል።እንደ አገር መገንባት የምንፈልገው ዴሞክራሲ ጥቂቶች ብቻ የሚጫወቱበት ሜዳ ሳይሆን ብዙሃንን የሚያሳትፍ ሜዳ እንዲሆን ስለሚፈለግም፤ ብዝሃነት ባለበት አገር ሁሉም ድምጾች እንዲደመጡ እድል መስጠት የሚያስችል ስራዎችን አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡የሰላም ሚኒስቴር ከተሰጡት መሰረታዊ ተልዕኮዎች መካከል አንዱ በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ የህግ የበላይነት እና የዳበረ ዴሞክራሲ እንዲገነባ፣ እናም ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መስራት መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ ይሄን መሰረት በማድረግም በሁለት እርከን የተከፈለ ብሔራዊ የምክክር መድረክ ለማዘጋጀት ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ሰፋፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ይሄም የመጀመሪያው መድረክ ሕብረተሰብ ተኮር የሆነ በየእርከኑ በተለይም ህብረተሰቡ የሚገኝበትን የመጨረሻውን እርከን ቀበሌን ማዕከል ያደረገ ምክክር የሚካሄድበት መርሃ ግብር ሲሆን፤ ሁለተኛው በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ልሂቃን የሚሳተፉበት የምክክር መድረክ ነው።በዚህም ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች ህብረተሰብ ተኮር ብሄራዊ የምክክር መድረኩ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፤ ለቀጣይ ሶስት ተከታታይ ወራት ያህል በቋሚነት የሚቀጥል ይሆናል፡፡ምክክር ልብ ለልብ መገናኘትን፣ መደማመጥን፣ መቻቻልን፣ እውን ለማድረግ፤ ችግሮችና አለመግባባቶች እንኳን ቢኖሩ ስልጡን በሆነ መንገድ በውይይት የመፍታት ባህልን የሚያለማምድ፤ ደረጃ በደረጃም ይሄንን መፍጠር የሚያስችል ልምምድ ነው።በኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ ምዕተ ዓመታት ጥሩ ጥሩ እሴቶች ያሉንን ያህል ችግሮቻችንን በሰለጠነ መንገድ ተቀራርቦ ከመፍታት አኳያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ የመጣ፤ በወጉም በተስተካከለ መሰረት ላይ ያልተገነባ እሴትና ባህል እንደመሆኑ መጠን፤ ችግርን በሃይማነ ጉልበት መፍታት አማራጭ ተደርጎ ሲወሰድ ቆይቷል።ይሄ ደግሞ የዴሞክራሲ ስርዓትን ለመገንባት ለሚተጋ አገር እጅግ አዳጋች የሆነ ጉዳይ ነው፡፡በመሆኑም በእነዚህ የውይይትና የምክክር መድረኮች ከአካባቢ ጉዳዮች ጀምሮ እስከ ብሔራዊናአገራዊ የሆኑ የጋራ የሆኑ ሀሳቦችና ጉዳዮችን የሚመለከት ስለሆነ የምክክር ሂደቱ መጨረሻ ላይ የሚያግባቡ አገራዊ ጉዳዮች ላይም የጋራ ድምዳሜ ይደረስበታል ተብሎ ይታመናል።ስለሆነም ትልቅ ዴሞክራሲን ለመገንባት ለምናደርገው ጥረት፤ ዘላቂ ሰላም ለመገንባት ለምናደርገው ጥረት መሰረታዊ የሆነ የእሳቤና የባህሪ ለውጥ ለማምጣት ያግዛል ተብሎ የተቀረጸ መርሃ ግብር ነው፡፡በዘሌ መንገድ ደግሞ ልሂቃን የሚያደርጉት ውይይት ተመሳሳይ ዓላማ ያለው ነው።ምክንያቱም ልሂቃን ሀሳብ የሚቀርጹ ናቸው።እናም የልሂቃን ሀሳብ በተስተካከለ መሰረት ላይ ማረፍ ከቻለ ለአገር ግንባታ ሂደት ትልቅ አበርክቶ ይኖረዋል።ስለዚህ ልሂቃንም በየፈርጃቸው አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጓቸው ውይይቶች እና የሚደርሱባቸው መግባባቶች ተመልሶ በህብረተሰብ ደረጃ ለሚካሄደው ውይይት፤ በህብረተሰብ ደረጃ የሚካሄደው ውይይትም የሚያወጣቸው ሀሳቦችና የጋራ የሆኑ ጉዳዮች መልሶ የልሂቃኑን ሀሳብ መልክና ቅርጽ ለማስያዝ የራሱ አበርክቶ ይኖረዋል፡፡ይሄ የሁለቱ ምግግቦሽ በአንድ በኩል ከላይ ወደታች ህብረተሰቡ ላይ አጀንዳ የሚጫንበት ሳይሆን በራሱ ይመለከተኛል፣ ያሳስበኛል፣ የሚለውን ጉዳይ አንጥሮ የሚያወጣበት ይሆናል።በዚህም መንግስት ከእነዚህ መድረኮች የሚገኙ ግብዓቶችን ወስዶ ህብረተሰቡን ለማድመጥና ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።መጨረሻ ላይም የሁለቱ መድረከች በጋራ መጥተው ብሔራዊ የሆነ ምክክር፤ ስልጡን የሆነ ውይይት የሚደረግበት፤ የጋራ አቋም የሚወሰድበት ምዕራፍ ይኖረዋል፡፡እነዚህ ሁሉ ሂደቶች ለአገር ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል፤ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ደግሞ ለአገር ግንባታ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ያሉት ሚኒስትሯ፤ መድረኩ የልሂቃን ብቻ እንዲሆን ያልፈለግነውና መሰረተ ሰፊ እንዲሆን የፈለግነው መገንባት የምንፈልገው ዴሞክራሲ ጥቂቶች ብቻ የሚጫወቱበት ሜዳ ሳይሆን ብዙሃንን የሚያሳትፍ ሜዳ እንዲሆን ስለሚፈለግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ከዚህ አኳያ መሰረተ ሰፊ የሆነ ህብረተሰብ ተኮር ምክክር የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ሌሎች ልሂቃን የሚሳተፉባቸው የምክክር መድረኮች ሲኖሩ፤ በጤናማ እና መሰረተ ሰፊ በሆነ ይዞታ ላይ የሚያርፍና የሚገነባ እንደሚሆን ተናግረዋል።ይህ ዘላቂ ለሆነ ሰላም ግንባታ የሚሆን የአገር ግንባታ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም አስረድተዋል።የአገራት ልምድ የሚያሳየውም አገራት የአገር ግንባታ ሂደቶቻቸውን በየራሳቸው ነባራዊ ተጨባጭ ሁኔታ እንደየአመቺነቱ አስኪደውታል፤ በእኛ ተጨባጭ ሁኔታም ብዝሃነት ባለበት አገር ሁሉም ድምጾች እንዲደመጡ እድል መስጠት፤ ከዚህ ተነስቶም ለሁሉም የሚሆን አገር መስራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡መድረኩም ይሄን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን፤ በቀጣይ ወራትም ተጠናክሮ የሚቀጥልና በቋሚነት የሚሰራ መሆኑን፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ሁሉንም ባለድርሻ ለማሳተፍ የሚያስችል ስራ ማከናወኑን በመግለጽ፤ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ከሚካሄዱ መድረኮች የሚገኝ ልምድም በዘላቂነት ለሚካሄደው መድረክ ተቀምሮ የሚሰራበት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37844
af019b8137733d4223220dc58ff5c360
aab9363fc20cec83af702f8728038a5c
“በኃይል ወንበር እይዛለሁ ብሎ የሚመጣ ይጎዳል እንጂ አይጠቀምም ” ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ጥሩ አላማ እና ህዝብ ይጠቅማል የሚል ሃሳብ ይዞ ከመቅረብ ያለፈ በሃይል ወንበር እይዛለሁ ብሎ የሚመጣ ማንኛውም ኃይል ከመጎዳት ያለፈ ምንም እንደማይጠቀም የህወሓት ጁንታ አፍኗቸው ከነበሩት መካከል አንዱ የሆኑት የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ተናገሩ።መከላከያ ሰራዊቱም በሰላማዊ መንገድና በዴሞክራሲያዊ አካሄድ የሚመጣውን ብቻ ተቀብሎ ለመሄድ የሚሰራ እንደሆነም አስገንዝበዋል።ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ እንደተናገሩት፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ለዓመታት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ላይ ተጠምዶ ከማሳለፉ ባሻገር በሃይል ወንበር ለመያዝ እንዲያመቸው በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ላይ የፈጸመው ጥቃት ውድቀቱን አፋጥኖለታል።መከላከያ ሰራዊቱም ለዚህ የሚመች ሃይል አለመሆኑን አሳይቷል።በመሆኑም የተሻለ ዓላማ ለህዝብ በሚጠቅም ሃሳብ ይዞ ከመስራት ባለፈ በሃይል ወንበር ለመያዝ የሚደረግ ሙከራ የማይጠቅም፤ ይልቁኑም ያንን ኃይል የሚጎዳ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡እንደ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ ገለጻ፤ የጁንታው ቡድን በህዝቡ ውስጥ ብቻ ሳይሆን መከላከያ ሰራዊትን የማጠልሸት እና የመከፋፈል ስራዎች ቀድሞ ሲያከናውን ነበር። ሰራዊቱ በአንድ መምሪያ እና ተቋም ስር ሆኖ ሳለ የሰሜን እዝ መጥፎ ነው ምዕራብ አሊያም ምስራቅ ዕዝ ጥሩ ነው የሚል መከፋፈል ሲታይ ቆይቷል። በማህበራዊ ድረገጾች እና በአካል ጭምር ሰራዊቱን የማጠልሸት ስራዎችን አከናውነዋል፤ በቻሉት መጠን የሰራዊቱን የውስጥ አንድነት ያናጋል ብለው የሚያስቡትን ለማድረግ ያልወረወሩት ጠጠር የለም። ሆኖም ችግሮቹ ከዛሬ ዛሬ ይስተካከላሉ በሚል ሀገር ተመልሳ ወደጦርነት እንዳትገባ ነበር ሰራዊቱ ነገሮችን በትዕግስት ለማለፍ የመረጠው። በዚህ መሃል ግን ሰራዊቱ ህይወቱን ብቻ ሳይሆን ከኪሱ አዋጥቶ ለህዝብ እያገዘ ባለበት ሥፍራ የጁንታው ቡድን የአፈና ተግባር የማፍያ ቡድንነቱን ያሳየበት ስራ ነው። ይሄን ተከትሎም በመንግስት በኩል የተሰጠው አቅጣጫ እና በመከላከያ ሰራዊቱ የተወሰደው የማጥቃት እርምጃ ደግሞ አገርን ከጥፋት የታደገ፤ በሃይል ስልጣንና ወንበር ለመያዝ ማሰብ ትርፉ ለራስ መጥፋት ምክንያት መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ክስተት ሆኖም አልፏል፡፡በዚህ ረገድ ህግን በማስከበር እርምጃው በመንግስትም ሆነ በመከላከያ ሰራዊቱ በጥበብና ጥንቃቄ በተመላበት መልኩ የተወሰደው ለመንግስትምለሰራዊቱም አድናቆትና ምስጋና የሚያስቸረው ነው።በቀጣይም የጁንታው አመራር አባላት ከያሉበት ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ ያደረግ ሲሆን፤ እኛም የጁንታው ቀሪ ቡድን ተይዞ ለህግ እንዲቀርብ የሚደረገው ጥረት ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ነን፣ ሲሉ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ ተናግረዋል።መከላከያ ሰራዊት ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ እንዲሰራ የተጀመረው ስራ እንዲጠናከር እንሰራለን ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም በምርጫ ከተሸነፉ ስልጣን ለመልቀቅ ፍቃደኛ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ከማሳወቃቸው ጋር ተያይዞም መከላከያ ሰራዊቱ በሰላማዊ መንገድና በዴሞክራሲያዊ አካሄድ የሚመጣውን ተቀብሎ ለመሄድ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡በመሆኑም ጥሩ አላማ እና ህዝብ ይጠቅማል የሚል ሃሳብ ይዞ ከመቅረብ ያለፈ፣ በጉልበትና በሃይል ወንበር እይዛለሁ ብሎ የሚመጣ ኃይል ቢኖር የሚጎዳ እንጂ የሚጠቀም አለመሆኑን መገንዘብ እንዳለበት አሳስበዋል።ችግር ቢኖር እንኳን በሃይል ሳይሆን በቀጣይ ችግሮችን አርሞ እና አሻሽሎ መምጣት አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆምም፤ ለተወሰነ የስልጣን ፈላጊ ቡድን ሲባል ብሔር ብሔረሰቦች በማንነታቸው፣ ባህላቸውና በወጋቸው ላይ ድርድር ስለማይኖር ሁሉም አካል ህዝብን መሰረት አድርጎ መስራት እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡እንደ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ ገለጻ፤ የአንዱ መብት መከበር የሌላኛው መከበር፣ የአንዱ መብትና ጥቅም አለመከበርም የሌላኛው አለመከበር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።ከዚህ ባለፈ ደግሞ የጋራ እሴቶች ላይ መሰራት ይኖርበታል። ጁንታው ግን በጋራ አንድነት ላይ የማዳከም እና ሁሉ ነገር ላይ መሰማት አለብኝ ሲል እና ሌሎች የተናገሩት ውሸት እኔ የተናገርኩት ግን እውነት ነው ብሎ ሲያምታታ የኖረ እንደመሆኑ በፍላጎቱ ተመርቶ ሞቱን አፋጥኗል።በመሆኑም ከዚህ ትምህርት ወስዶ ሁሉም አካል የጋራ ተጠቃሚነት የሚያበለጽጉ አካሄዶችን በማዳበር ድህነትን ለማስወገድ መስራት፤ ወንበርም ከጦርነት ይልቅ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመያዝ ልምድን ማዳበር ይኖርባቸዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37845
348e20b2a75919c8d8ad35e513ddf392
fa3b2da7adfb2e87723b00e9316e3be8
ማራቶንን በተፈጥሯዊ መንገድ ከ2 ሰዓት በታች የመሮጥ ውጥንነው፡፡
ስፖርት
ነገር ግን የድል ዜናው ቦታውን ቀይሮ በተገናኙባቸው ውድድሮች ኬንያዊው አትሌት የርቀቱ ፈጣን ተሰኘ፡፡ በጉዳት ምክንያት ከውድድር ርቆ የቆየው የሃገር አቋራጭ ንጉሱ ቀነኒሳም በርቀቱ ያለውን ተስፋ ከማሳየት በቀር ለሁለት ዓመታት ውጤት አላስመዘገበም ነበር፡፡ እአአ 2016 ግን የፓሪስ ማራቶንን በማሸነፍ በጠባብ የደቂቃዎች ልዩነት ሁለተኛው የርቀቱ ፈጣን አትሌት ለመሆን ችሏል፡፡ በቀጣዩ ዓመት በለንደን ማራቶን ያስመዘገበው ሰዓት ከፈጣኑ የዘገየ መሆኑ በርቀቱ ያለውን ተስፋ አጠራጣሪ አድርጎት ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በ5 እና 10ሺ ሜትር የሶስት ጊዜ የኦሊምፒክ ቻምፒዮኑ ቀነኒሳ የባት ፣ የቁርጭምጭሚት፣ ተረከዝ፣ ሽንጥ እና ቋንጃ ጉዳቶች ጋር ትግል ሲያደርግ በመቆየቱ ነው፡፡ የአትሌቱ የረጅም ጊዜ ማኔጀር ጆስ ሄርሜንስም ስለ ቀነኒሳ ከሰሞኑ በዓለም አትሌቲክስ ድረ ገጽ አጠቃላይ መረጃ ሰጥቷል፡፡ አሰልጣኙ አትሌቱ የነበረበትን ሁኔታ ሲገልጽም ‹‹በአዲስ አበባ ያለው ህይወቱ ውጥረት የበዛበት በመሆኑ ለልምምድ እንዲሁም ለማገገም የተመቸ ጊዜ የለውም፡፡ ከሩጫው ባሻገር በቢዝነስ ስራዎችም ላይ ተሳታፊ እና የልጆች አባት እንደመሆኑም አብዛኛውን ጊዜውን በዚህ ያሳልፋል፡፡ በዚህ ሂደትም ጊዜውን ያለእረፍት እያሳለፈ ነበር›› ሲልም ይገልጻል፡፡ ‹‹የማራቶን ሁለተኛውን ሰዓት ካስመዘገበበት የበርሊን ማራቶን ሁለት ወራት አስቀድሞም ለጥቂት ጊዜ ከውጥረት መላቀቅ እንዳለበትና ጥሩ የማገገሚያ ጊዜ እንደሚኖረው አስረዳነው›› ይላል ማኔጀሩ፡፡ ይህን ማሳመን ቀላል ባይሆንም በመጨረሻ ግን ከቤተሰቦቹ ተለይቶ ለሁለት ወራት በሆላንድ በምትገኝ አንዲት ከተማ ለማሳለፍ የግድ ሆነ፡፡ አትሌቱም የሩጫ ህይወቱን ከማቋረጡ አስቀድሞ በማራቶን አንድ ታሪክ ማስመዝገብ የሚፈልግ በመሆኑ ከጉዳቱ በቶሎ አገግሞ ወደ ልምምድ እንዲገባ የቻሉትን ሁሉ ማድረጋቸውን ማኔጀሩ ያስታውሳል፡፡ ክብደቱ በመጨመሩም በሆላንዳዊው የስነ ምግብ ፕሮፌሰር አርማንድ ቤቶንቬል እገዛ የአመጋገብ ሁኔታውን ማስተካከል ተችሏል፡፡ በአዲስ አበባ ቆይታው የአመጋገብ ሁኔታው የተጠና አልነበረም፤ አብዛኛውን ጊዜ የሆቴል ምግብ የሚያዘወትር ከመሆኑ ጋር በተያያዘ እንደ አትሌት በሚጠበቅበት ሁኔታ ላይ አልነበረም፡፡ በባለሙያዎቹ አማካኝነትም ፕሮቲን፣ ሩዝ እና ድንች በተሻለ ሁኔታ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡ ስልጠናውንም በአግባቡ ነበር የሚከታተለው፡፡ ወደ ዋናው ስልጠና ከገባም በኃላ በሳምንት እስከ 50 ኪሎ ሜትር በመሸፈን ጥሩ የሚባል ጊዜ አሳልፏል፡፡ የመልካም አስተሳሰብ ባለቤት በመሆኑም ከታሰበው በተሻለ ፍጥነት መሻሻል ሊያሳይ ችሏል፡፡ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኃላም በአሰልጣኝ ሃጂ አዲሎ ስር በመሆን ስልጠናውን ሳያዘባ ሲሰራ ስለ ነበር በጥቂት ጊዜ ወደ ቀደመ አቋሙ ሊመለስ ችሏል፡፡ ዝግጅቱ በርቀቱ ከፈጣኖች ተርታ ከሚሰለፈውና ከዓለም ቻምፒዮኑ አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ ጋር መሆኑም የተሻለ ነገር አስገኝቶለታል የሚል እምነት እንዳላቸው ኸርሜንስ ይናገራሉ፡፡ በእርግጥ ስልጠናውን በሚያደርግበት ወቅት አዲስ አበባ ዝናባማ የአየር ሁኔታ ነበራት፤ ይህም አስቸጋሪ ስለነበር ስልጠናውን በበፊቱ ልክ ማከናወን አንዳልተቻለም አልዘነጉም፡፡ ‹‹ውድድሩ ሲቃረብም በአትሌቱ ብቃት ሁላችንም ከመተማመን ላይ ደርሰን ነበር፡፡ እኛ በስልጠናው ወቅት ሲያሳይ በቆየው ብቃት ከፍተኛ ተስፋ ስንሰንቅ እርሱ ደግሞ በጥሩ ውጤት ማጠናቀቅን አላማው አድጎ ነበር፡፡ ከሚታመነው በላይ ጠንካራ አትሌት ነው፤ በውድድሩ ላይ ኬንያዊው አትሌት ከያዘው ክብረወሰን በሁለት ሰከንዶች ብቻ ዘግይቶ ገብቷል›› በማት አ ድ ና ቆ ታ ቸ ው ን ይገልፃሉ፡፡ እውቅና ያልተሰጠውና ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ቢሆንም የሰው ልጁ 42ኪሎ ሜትሮችን ከ2ሰዓት በታች መግባት ይችላል የሚለው ሙከራ በኬንያዊው ኪፕቾጌ እውን ከተደረገ በኃላም የስፖርት ቤተሰቡ ጥያቄ ተመሳሳይ ሆኗል፡፡ ‹‹ቀጣዩ ምንድነው?›› የሚለው ፤ ምላሹም ቀነኒሳን ከማየት የተሻለ አለመኖሩን የሚያሳይ ነው፡፡ ቀነኒሳ ማራቶንን በተለመደው መንገድ ሮጦ በቴክኖሎጂ ሳይታገዝ ከ2፡00 በታች መሮጥ እንደሚችል በቅርቡ አብሮ እየሰራ የሚገኘው አሰልጣኙ ሃጂ አዲሎም በቅዳሜው እለት እትማችን ባደረጉት ቃለ ምልልስ መግለፃቸው ይታወቃል፡፡ አሰልጣኙ ሃጂም ‹‹ ቀነኒሳ ሩጫ ከማቆሙ አስቀድሞ ማራቶንን ከ2፡00 በታች ይሮጣል፣ በየትኛው ውድድር እንደሚሆን ግን መናገር አይቻልም›› ይላሉ፡፡ ቀነኒሳ ምናልባትም ይህን ለማሳካት የቀጣዩን ዓመት የበርሊን ማራቶን መታገስ ላይጠበቅበት ይችላል፡፡ በቀጣዩ ሚያዝያ በለንደን ማራቶን ለመሳተፍ በሆላንድ አገር የሚያደርገው ዝግጅት በታሰበው ልክ ከሄደ ህልሙን በቅርቡ እውን ሊያደርግ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡አዲስ ዘመን ኅዳር 15/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=23109
381ab3999dd19cddfc26f2d9e264d750
32816ef5eb105c385ccff5fa9eb80d0d
ሉሲዎቹ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የመመለስ ሰፊ እድል አላቸው
ስፖርት
 የ2020 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያና ማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በቅድመ ማጣሪያና ማጣሪያ ጨዋታዎች የሚገጥሙትን ቡድን አውቀዋል። ሉሲዎቹ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር የፊታችን ሚያዚያ አራት ቀን የሚያደርጉ ሲሆን ጅቡቲን በደርሶ መልስ ጨዋታ ድምር ውጤት የሚያሸንፉ ከሆነ በመጨረሻው የማጣሪያ ጨዋታ ከሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚጫወቱ ይሆናል። በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው የኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድን ለ2020 የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከወዲሁ ለውድድሩ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን አሰልጣኙ ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ ካልቻሉ ራሳቸውን ከአሰልጣኝነት ስራ እንደሚያገሉ መግለፃቸው ይታወሳል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሰላሳ ሁለት አገራትን የሚያሳትፈው የ2020 የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 2018 ተካሂዶ ከነበረው ውድድር አስራ ሁለት አገራትን ጨምሮ ሲካሄድ ዘንድሮ የመጀመሪያው ይሆናል። ይሁን እንጂ ይህን ውድድር የሚያዘጋጀው አገር እስካሁን አልታወቀም።ካፍ የ2020 የሴቶችን የአፍሪካ ዋንጫ ሞሮኮ እንድታዘጋጅ ፍላጎት እንዳለው የተለያየ መረጃ እየወጣ ይገኛል።ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ የ2020 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫን እንደማታዘጋጅ ከተገለጸ ወዲህ የአፍሪካ እግር ኳስን በበላይነት የሚመራው ካፍ ደቡብ አፍሪካ ውድድሩን እንድታዘጋጅ ጥሪ ቢያቀርብላትም ለ2023 የሴቶች ዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ፉክክር ውስጥ በመግባቷና የዓለም ዋንጫውን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ስራ ውስጥ በመገኘቷ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጓ ይታወቃል። ካፍ የ2020 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫን አዘጋጅነት ጥያቄ በቅርቡ የመላው የአፍሪካ ጨዋታዎችን በድምቀት ወደ አዘጋጀችው ሞሮኮ ፊቱን በማዞር ጥያቄ ሊያቀርብ እንደተዘጋጀ ታውቋል። ሞሮኮ የ2020 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫን የምታዘጋጅ ከሆነ ሉሲዎቹ ከጅቡቲ አቻቸው ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ ትኬታቸውን በቀላሉ የሚቆርጡበት እድል ሰፊ ይሆናል። የጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ከአራት ሳምንት በፊት ተካሂዶ በነበረው የመካከለኛና ምስራቅ አፍሪካ(ሴካፋ) ዋንጫ ላይ ከዩጋንዳ፣ኬንያና ኢትዮጵያ ጋር ተደልድሎ በኬንያ 13ለ0፣ በዩጋንዳ 12ለ0 እንዲሁም በኢትዮጵያ 8 ለ 0 ተሸንፎ በውድድሩ በአጠቃላይ ሰላሳ አንድ ግቦች በማስተናገድ አንድም ግብ ሳያስቆጥር መቅረቱ ይታወሳል። ይህም ሉሲዎቹ በቅድመ ማጣሪያው ጨዋታ በቀላሉ አሸንፈው ወደ ቀጣዩ ማጣሪያ እንደሚያልፉ ከፍተኛ ግምት እንዲሰጣቸው አድርጓል። እኤአ 1991 ላይ በተጀመረው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 2002 ተሳታፊ መሆን ብትችልም በውድድሩ ከምድብ ጨዋታዎች ማለፍ እንዳልቻለች ይታወሳል። 2004 ላይ ዳግም ተሳታፊ በመሆን አራተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችበት ውጤት በታሪክ ትልቁ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በመድረኩ የተሳተፈችው 2012 ላይ ነው። ዘንድሮ ግን ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ መድረኩ የመመለስ ትልቅ ተስፋ ሰንቃለች።አዲስ ዘመን አርብ ህዳር 26/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=23656
a4881e48d8a7a85a6c01e0fbaafc1bc9
a9f22c79ecb8fe111d29a6cf10acf6ce
ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ወጣት ሴት ተማሪዎችን ከስኬታማ ሴቶች ጋር በማጣመር የድጋፍና የምክር አገልግሎት ማስጀመር ውጤታማ ሴቶችን ለማፍራት እንደሚያግዝ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- የመሰናዶ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ወጣት ሴት ተማሪዎች በስራ አለምና በህይወት ተሞክሮ ስኬታማ ከሆኑ ሴቶች ጋር በማጣመር የድጋፍና የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣ ወጣት ሴት ተማሪዎችን ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ አስታወቁ፡፡የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ሴት ተማሪዎች ውጤታማ ሆነው እንዲወጡ ከስኬታማ ሴቶች ጋር የምክክርና ድጋፍ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እንደተናገሩት፤ 12ኛ ክፍልን በጥሩ ሁኔታ አጠናቀው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ሴቶችን የደጋፊና መካሪ አገልግሎት እንዲያገኙ በህይወታቸው ስኬታማ ሴቶች ጋር ጥምረት እንዲፈጠር መደረጉ መንግስት ሴቶችን ወደ አመራር ለማምጣት ለሚያደርገው ጥረት አጋዥ ነው፡፡ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚውና በማህበራዊው ዘርፍ ስኬታማ የሆኑ ሴቶች፣ ለወጣት ሴት ተማሪዎች የድጋፍና የምክር አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ እንደ ፕሬዚዳንቷ ገለፃ፤ ወጣት ሴት ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሲቀላቀሉ የሚሄዱት አዲስ አካባቢና አዲስ ሁኔታ ውስጥ እንደመሆኑ ብዙ ውጣውረዶች ይገጥሟቸዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሚደግፋቸውና የሚመክራቸው መኖሩ በራስ የመተማመን አቅማቸውን አሳድገው አንገታቸውን ቀና ሊያደርግ፤ የአስተሳሰብ አድማሳቸውን በማስፋት የሚጎሏቸው ነገር ላይ በመምከር የበለጠ ሊያዘጋጇቸው የሚችል ነው፡፡ የደጋፊና መካሪ ስራ ደግሞ በቃላት ብቻ ሊገለፅ የማይችል ጥቅም ስላለው ለተማሪዎች በትምህርታቸው ላይም ሆነ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደስራ ዓለም ለመቀላቀል በሚዘጋጁበት ጊዜም ትልቅ አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡ በተለይም እንደተምሳሌት የሚያዩአቸው ሴቶች መኖራቸው ወደፊትም ለሚኖራቸው ራዕይ አርቀው እንዲያስቡ ያግዛቸዋል፡፡ ምክንያቱም የወጣት ሴት ተማሪዎች የደጋፊና የመካሪ መርሃ ግብር መጀመሩ በተለይም የወደፊት ራዕያቸውን በመመልከት በሚገጥማቸው ፈተና ሳይደናገጡ አላማቸውን ለማሳካት ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ከዚህ በፊት ያለፍንበት ሁኔታ እንድንፎካከር እንጂ እንድንደጋገፍ የሚረዳ አልነበረም ያሉት ፕሬዚዳንቷ፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ምንም አይነት ችግር ሳይበግራቸው ለስኬት የበቁ ሴቶችን አብነት በመውሰድ ወጣት ሴት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ለትልቅ ኃላፊነት ራሳቸውን ሊያዘጋጁ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ በዚህ ረገድ የደጋፊና የመካሪ አገልግሎት መርሃ ግብር መጀመሩ መልካም እድል መሆኑን በመጥቀስ፤ አንድ ስኬታማ ሴት የደገፈቻትና ያማከረቻት ተማሪ ለኃላፊነት በቅታ ማየቷ የራሷ ስኬት አድርጋ ልትቆጥረው እንደሚገባ፤ ይህ ሲሆን የምክርና ድጋፍ አገልግሎት መስጠት በሁለቱም ወገን ጥቅም ከፍተኛ እርካታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡አገልግሎቱ ከ45 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 50 ለሚሆኑ ተማሪዎች ሲሆን፤ ከአንድ ወር በኋላ ከአንድ ሺ 500 በላይ የሁለተኛና ከዚያ በላይ ያሉ ተማሪዎች የምክርና ድጋፍ አገልግሎት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37853
76acdd720cf636a1cd3bf484b22bc72b
fc20029fb20961311b63db235f127f99
ዋልያዎቹ በሴካፋ ዋንጫ ከዩጋንዳ ጋር ተደልድለዋል
ስፖርት
የ2019 የመካከለኛውና ምስራቅ አፍሪካ ዋንጫ(ሴካፋ) በዩጋንዳ አዘጋጅነት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 9 ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ በሦስት ምድብ ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ በምድብ አንድ ከኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተደልድለዋል፡፡ በዚሁ ምድብ አዘጋጇ ዩጋንዳና ቡሩንዲም ተደልድለዋል፡፡ በምድብ ሁለት በተጋባዥነት የምትሳተፈው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ጋር የተደለደለች ሲሆን በመጨረሻው ምድብ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ጅቡቲና ዛንዚባር መደልደላቸው ታውቋል፡፡ ርዋንዳ በዚህ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ትሆናለች ተብሎ ቢጠበቅም በበጀት እጥረት እንደማትካፈል ተረጋግጧል፡፡ ርዋንዳ በዚሁ የውድድር ዓመት በዩጋንዳ አዘጋጅነት ተካሂዶ በነበረው ከአስራ ሰባት ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ ምክኒያት ካለመሳተፏ ባሻገር ከቀናት በፊት በታንዛኒያ አዘጋጅነት ተካሂዶ በተጠናቀቀው የሴቶች ሴካፋ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ ምክኒያት መሳተፍ አለመቻሏ ይታወሳል ዋልያዎቹ ከሳምንት በፊት ለ2021 የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድባቸውን ሁለተኛ ጨዋታ ባህርዳር ላይ በማድረግ ትልቅ የእግር ኳስ ደረጃ ያላትን ኮትዲቯርን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡ ይህም በቡድኑ ላይ ትልቅ መነቃቃት የፈጠረ ቢሆንም ቀጣዩን የማጣሪያ ጨዋታ ከበርካታ ወራት በኋላ ለሚያደርጉት ዋልያዎቹ ስጋት እንዳለው ሲነገር ቆይቷል፡፡ ዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያውን ነሐሴ ወር ላይ ማካሄዳቸው አሁን የተፈጠረውን መነቃቃት እንዳያደበዝዘው እንደ ሴካፋ አይነት ውድድሮች አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ ዋልያዎቹ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የወዳጅነት ጨዋታዎችን በብዛት ማድረግ አለመቻላቸው ካተቀረፈ፣ የቡድኑ ስብስብም ለረጅም ጊዜ ተለያይቶ ሲገናኝ አሁን ያለው የአሸናፊነት መንፈስና መነቃቃት በነበረበት ላይገኝ ይችላል የሚሉ ስጋቶች አሉ፡፡ ዋልያዎቹ ቀጣዩን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እስኪያደርጉ ቻንን በመሳሰሉ ዋንጫዎች አለመሳተፋቸው ተጨማሪ ጉዳት ቢሆንም እንደ ሴካፋ አይነት ውድድሮች ላይ መሳተፍ መቻላቸው አሰልጣኝ አብረሃም መብራቱ ቡድኑን ለመገንባት በሚያደርጉት ሂደት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡አዲስ ዘመን ኅዳር 17/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=23237
1c82a9513a6040325d887cac1122f0e1
d94b6faf5448369e27cea8d63ea2e5df
ኢትዮጵያውያን የደመቁባቸው ዓለም አቀፍ ክብሮች
ስፖርት
 የዓመቱ የምርጥ አትሌቶች ሽልማት እጩዎች ከሦስት ሳምንት በፊት ይፋ ሲደረግ አንድም ኢትዮጵያዊ አትሌት ከምርጥ አስር እጩዎች ውስጥ መካተት አልቻለም ነበር። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይህን ክብር ደጋግመው ማግኘት ቢችሉም ባለፉት ሁለት ዓመታት በሁለቱም ፆታ ከእጩዎቹ መካከል እንኳን ሳይካተቱ መቅረታቸው አስገራሚ ነበር። ያም ሆኖ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዋናው ሽልማት በእጩነት ያልተካተቱበት አጋጣሚ በወጣቶች ወይም ከሃያ ዓመት በታች በእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ አትሌቶች በሚሳተፉበት ሽልማት ሁለት ወንዶችና አንድ ሴት አትሌት መካተት ችላለች። ከእጩነት ባሻገርም ወጣቱ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ሽልማቱን ማሸነፍ ችሏል። ባለፈው ቅዳሜ በሞናኮ በተካሄደው የሽልማት ስነስርዓት ላይ ኢትዮጵያውያን በኮማንደር ደራርቱ ቱሉ አማካኝነት ተጨማሪ ዓለም አቀፍ ሽልማት ማግኘት ችለዋል። እኤአ 1992ና 2000 ላይ በተካሄዱት የባርሴሎናና የሲድኒ ኦሊምፒኮች በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያጠለቀችው ጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ በዓለም አትሌቲክስ ‹‹ዘንድ የዓመቱ ምርጥ ሴት›› በሚል ሽልማት አግኝታለች። ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንትነት እየመራች ላሳየችው የላቀ አስተዋፅኦ ይህ እውቅና ተችሯታል። ደራርቱ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን የምክር ቤት አባል ስትሆን የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆንም እያገለገለች መገኘቷ ለሽልማቱ አብቅቷታል። የአስራ ዘጠኝ ዓመቱ ኢትዮጵያዊ አትሌት ሰለሞን ባረጋ የዘንድሮውን ዓመት የወጣትና ተስፈኛ አትሌቶች ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል። ሰለሞን በዶሃ በተካሄደው የዓለም ቻምፒዮና በአምስት ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ከማጥለቁ በተጨማሪ በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና አምስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በውድድር ዓመቱ የዓለም ከሃያ ዓመት በታች የአምስትና አስር ሺ ሜትር ርቀቶችን 12፡53፡04ና 26፡49፡46 በሆነ ጊዜ መሪ ሰዓቶች ማስመዝገቡ ለሽልማቱ አብቅቶታል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በመካከለኛና ረጅም ርቀቶች ድንቅ ብቃት እያሳየ የሚገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ባለፈው ዓመትም ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ስም ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ይታወሳል።የደቡብ ፖሊሱ ክለብ አትሌት የሆነው ሰለሞን ባረጋ ከእድሜው ከፍ ብሎ ከታላላቆቹ ጋር በመወዳደር እያስመዘገበ ላለው ስኬት ባለፈው ዓመት ክለቡ የኢንስፔክተርነት ማዕረግ የሰጠው ሲሆን ባለፉት ሦስት ዓመታት እያሳየ ያለው አስደናቂ ብቃት ወደ ፊት ተስፋ እንዲጣልበት አድርጓል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ታላላቅ የውድድር መድረኮች መጥቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ የስፖርት ቤተሰቡ አይን ማረፊያ የሆነው ወጣት አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውጤቱና አስደናቂ ብቃቱ ኢትዮጵያ በቅርቡ በታላላቅ መድረኮች አረንጓዴውን ጎርፍ ዳግም የማየት ብሩህ ተስፋ እንዳላት ማሳያ መሆኑን በርካቶች ይመሰክሩለታል። ድንቅ የሩጫ ተሰጥኦው በመካከለኛና ረጅም ርቀቶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ዙፋን ላይ እንደሚወጣ የስፖርቱ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ መስክረውለታል። በ2018 የውድድር ዓመት የአምስት ሺ ሜትር አጠቃላይ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊ መሆን የቻለው ሰለሞን ባረጋ በርቀቱ ከሃያ ዓመት በታች የዓለም ክብረወሰንን 12፡ 43፡02 በሆነ ሰዓት ከመጨበጡ ባሻገር እኤአ 2005 ላይ ቀነኒሳ በቀለ በርቀቱ ካስመዘገበው ሰዓት ወዲህ ፈጣን ሰዓት ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል። በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስት ሺ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ እንድታገኝ ያስቻለው አትሌት ለሜቻ ግርማ ከአምስቱ ተስፈኛ እጩዎች መካከል አንዱ በመሆን ከሰለሞን ጋር ሽልማቱን ለማሸነፍ ተፎካክሯል። ለሜቻ በውድድር ዓመቱ በርቀቱ ከሃያ ዓመት በታች መሪ የሆነውን ሰዓት በ8፡01፡36 ያስመዘገበ ሲሆን የኢትዮጵያን ክብረወሰንም የግሉ ማድረግ ችሏል። በዓለም ቻምፒዮናውም የወርቅ ሜዳሊያ ያመለጠው በ0ነጥብ01 ማይክሮ ሰከንድ ተቀድሞ እንደነበረ አይዘነጋም። ከሁለቱ ኢትዮጵያን እጩዎች ጎን ለጎን ብራዚላዊው የአራት መቶ ሜትር መሰናክል ተወዳዳሪ አሊሰን ዶስ ሳንቶስ፣ ኖርዌያዊው አትሌት ጃኮብ ኢንግብሪትሰን፣ ዩክሬናዊው መዶሻ ወርዋሪ ማይክሃይሎ ኮክሃን በሽልማቱ ተፎካካሪ ነበሩ። በወጣት ሴቶች ዘርፍ ከሰለሞን ባረጋ ጋር ተመሳሳይ ሽልማት ማሸነፍ የቻለችው ዩክሬናዊታ ያሮስላቫ ማሁቺክ ናት። ይህች አትሌት በከፍታ ዝላይ የተሻለ አቅም ያላት አትሌት ስትሆን 2 ሜትር ከ04 ሳንቲ ሜትር በመዝለል የክብረ ወሰን ባለቤት ናት። በዶሃው የዓለም ቻምፒዮናም የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። ከዚህም ባሻገር አውሮፓ ቻምፒን መሆን የቻለች ጠንካራ አትሌትም ናት። ይህን ሽልማት ለማሸነፍ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለምለም ኃይሉ ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ውስጥ ተካታ ተፎካካሪ መሆን ችላለች። ጃማይካዊቷ ብሪታኒ አንደርሰን፣ የኢኳዶሯ እርምጃ ተወዳዳሪ ግሌንዳ ሞርጆን፣ አሜሪካዊቷ 100 ሜትር የወጣቶች ባለክብረወሰን ሻካሪ ሪቻርድሰን የመጨረሻዎቹ ተፎካካሪዎች ነበሩ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከእጩዎች መካከል ያልተካተቱበት የዓመቱ የምርጥ አትሌቶች ሽልማት በወንዶች ዘርፍ ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል። የማራቶን ፈርጡ ኢሉድ ኪፕቾጌ በውድድር ዓመቱ ሁለት ፉክክሮች ላይ ብቻ ቢታይም ያስመዘገበው ታሪክ ሽልማቱን ለማሸነፍ አብቅቶታል። ኪፕቾጌ በውድድር ዓመቱ የለንደን ማራቶንን ክብረወሰን በማሻሻል በ2፡02፡37 ሰዓት ማሸነፉ ይታወሳል። ከዚህ በላይ ግን ከወር በፊት በቬና ማራቶን የሰው ልጅ የብቃት ጥግ ወሰን እንደሌለው ያሳየበት ውድድር አይዘነጋም። ኪፕቾጌ ከትጥቅ አምራች ኩባንያው ናይኪ ጋር በመሆን በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ታግዞም ቢሆን ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች ማጠናቀቅ እንደሚቻል አስመስክሯል። 1፡59፡40 በሆነ ሰዓት ማራቶንን በማጠናቀቅ በታሪክ የመጀመሪያው አትሌት ለመሆን ቢበቃም የተመዘገበው ሰዓት በዓለም ክብረወሰንነት እንዳልተያዘ ይታወሳል።ያም ሆኖ ዓለም ዓቀፍ ሽልማቱን ከማሸነፍ አላገደውም። ባለፈው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና የአስር ሺ ሜትር ቻምፒዮን የሆነው ዩጋንዳዊው ጆሹአ ቺፕቴጌ የመጨረሻዎቹን አምስት እጩዎች መቀላቀል የቻለ ሲሆን፣ አሜሪካዊው ምርኩዝ ዘላይ ሳም ኬንድሪክስ በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው አስራ ሰባት ከቤት ውጪ ውድድሮች አስራ ሁለቱን በድል በማጠናቀቅ የሽልማቱ ተፎካካሪ ነበር።አሜሪካዊው የአጭር ርቀት አትሌት ኖህ ላይልስና ኖርዌያዊው የአጭር ርቀት ኮከብ አትሌት ካርልስተን ዋርሆልም የሽልማቱ ተፎካካሪ ነበሩ። በሴቶች መካከል የተደረገውን ሽልማት አሜሪካዊቷ ደሊላ ሙሃመድ አሸንፋዋለች። በዓመቱ በ400 ሜትር ያሳየችው አቋም ለሽልማቱ ያበቃት ሲሆን አትሌቷ በሃገር አቀፍ ቻምፒዮና 52ሰከንድ ከ20ማይክሮ ሰከንድ መበመግባት ቀዳሚ ናት። በ400 ሜትር መሰናክል በራሷ የተያዘውን ክብረወሰን 52ሰከንድ ከ16ማይክሮ ሰከንድ በማሻሻል ብቃቷን አስመስክራለች። በ4በ 400 ሜትርም በተመሳሳይ የዓለም ቻምፒዮን ናት። በርዝመት ዝላይ ቬንዙዌላዊቷ ዩሊማር ሮጃስ ለመጨረሻው ዙር በመድረስ የተፎካከረች ሲሆን የአጭር ርቀት ተወዳዳሪዋ ጃማይካዊት አትሌት ሼሊ- አን ፍራዘር-ፕረይሲ፣የማራቶን ክብረወሰንን ሰበረችው ኬንያዊት አትሌት ብርጊድ ኮስጊ፣በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና በ1ሺ500 እና10ሺ ሜትር አሸናፊ የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትልት ሲፋን ሃሰን ለመጨረሻ እጩነት ቀርበው ተፎካካሪ ሆነዋል።አዲስ ዘመን  ህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ምቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=23174
838989e7421e5760de7c02511e99ce26
b9c3e896b5df99260852ab7f5f8717a3
”በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከተሳሳተ ግምት የመነጨ ነው” – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዋቅሹም ፍቃዱአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተስተዋለው የፀጥታ ችግር በተወሰኑ የሱዳን ሚሊሻዎች እና ጥቂት ወታደሮች የተሳሳተ ግምት በመነጨ በድንበር አካባቢ ተኩስ በመክፈታቸው ምክንያት የተፈጠረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ። አምባሳደር ዲና በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የህወሓት ጁንታ በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ መንግሥት በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ህግ የማስከበር ሥራ ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጰያ በድንበር አካባቢ ትኩረት አይሰጥም በሚል የተሳሳተ ግምት የተወሰኑ የሱዳን ሚሊሻዎች እና ጥቂት ወታደሮች የተሳሳተ ግምት በመነጨ በድንበር አካባቢ ተኩስ ከፍተዋል። ይሁን እንጂ መንግሥት ሙሉ ትኩረቱን በሰሜን የህግ ማስከበር ላይ ቢያደርግም በድንበር አካባቢም የጸጥታ ችግር እንዳይከሰት በትኩረት እየሠራ መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ዲና፤ በድንበር አካባቢ ያሉ የሱዳን ሀይሎች ግን “የኢትዮጵያ መንግሥት በድንበር አካባቢ ትኩረት አይስጥም” በማለት በተሳሳተ ግምት የድንበር አካባቢ ህዝባችን ለማጥቃት ተኩስ የከፈቱ ቢሆንም በመከላከያ ሠራዊትና በአካባቢው ሚሊሻ እንደ ተመከቱ ተናግረዋል። የደረሰ ጉዳት ካለም የጉዳቱ መጠን ለወደፊት ተጣርቶ የሚገለጽ ይሆናል ብለዋል። እንደ አምባሳደር ዲና ገለጻ፤ ግጭቱ የሁለቱም አገራትም መሪዎችም ፍላጎት አይደለም። የኢትዮጵያ መንግሥትም ጉዳዩን አስመልክቶ ከሱዳን ጋር ተነጋግሯል። በቀጣይም በአካባቢው አልፎ አልፎ ለሚከሰተው ችግር መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘላቂ እልባት እንዲያገኝ ይሰራል። የተጀመረው የህግ ማስከበር ስራም በአጭር ጊዜ ውስጥ ስለተጠናቀቀ ወንጀለኞችንም አድኖ ለመያዝ ከሱዳን መንግሥት ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል። በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖርና አርሶ አደሩ ምርቱን በአግባቡ እንዳይሰበስብ ፍላጎታቸውን በትርምስ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች በርካታ መሆናቸውን የገለጹት አምባሳደር ዲና፤ ኢትዮጵያ ግን የሁለቱም አገራት ዘላቂ ጥቅሞች በሚያስከብር መልኩ ከሰዳን ጋር እንደምትሰራ፣ እየሰራችም እንደ ሆነ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ሰሞኑን ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት “የተፈጠረውን ችግር ለማባባስ የሚጥሩ ኃይሎች፣ የኢትዮጵያና የሱዳን ታሪካዊ ትስስር ካለማወቅና ችግሮቻቸውን በድርድር ሲፈቱ መቆየታቸው ካለመገንዘባቸው የተነሳ ነው” ማለታቸው አይዘነጋም።አዲስ ዘመን ታህሳስ 11/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37691
ba3cebe9fde3900ca76e26c8f14b8e78
6516d6619bfd30ac4c1db2c467fffdda
ቢሮው 73 ከመቶ ያህል ሰብል መሰብሰቡን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
-127 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለመሰብሰብ እቅድ ተይዟል አስናቀ ፀጋዬአዲስ አበባ፡- በዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ73 ከመቶ በላይ የሚሆን ሰብል መሰብሰቡን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ። 127 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብም መታቀዱ ተገልጿል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግስቴ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ የዘንድሮው የግብርና ምርት አሰባሰብ በጎርፍና መሬት መንሸራተት፣ አምበጣ፣ ኮቪድና ጦርነት የተፈተነ ቢሆንም 73 ከመቶ በላይ የሚሆነውን ምርት መሰብሰብ ተችሏል። እንደ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገለፃ፤ በክልሉ የተከሰተው የአምበጣ መንጋ 900 ሄክታር የሚጠጋ መሬት ላይ የነበረ ሰብል ቢያወድምም፤ አምበጣው የተከሰተበት አካባቢ እምብዛም ምርታማ ባለመሆኑ ተፅእኖው ያን ያህል የከፋ አልሆነም። በክልሉ ባጠቃላይ 4 ሚሊዮን 282 ሺ 517 ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን የተናገሩት ምክትል ቢሮው ኃላፊው፤ እስካሁን ድረስ 3 ሚሊዮን 112 ሺ 165 ሄክታር ሰብል መሰብሰቡን አስታውቀዋል። በዚህም ከ73 ከመቶ በላይ ሰብል መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመዋል። በዚሁ የሰብል አሰባሰብ ወቅት 115 የሚሆኑ ኮምባይነሮችን በመጠቀም 847 ሺ 515 ኩንታል ስንዴ ለመውቃት መቻሉንም ገልፀዋል። ይህም 23 ሺ 30 ሄክታር የሚጠጋ መሬት እንደሆነና ከባለፈው ዓመት ጋር ሲወዳደር የተሻለ አፈፃፀም እንደሆነም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ጠቁመዋል። በግዳጅ ላይ ያሉ የአማራ ክልል ሚሊሻ አባላትን በማሳተፍ ሰብል እንዲሰበሰብ መደረጉንም ያነሱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፤ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊመጣ ስለሚችል በከፍተኛ ርብርብ ሰብል የማሰባሰብ ተግባሩ እየተከናወነ እንደሚገኝም አመልክተዋል። በዚህ ዓመት ባጠቃላይ ወደ 127 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እንደታቀደና በዓመቱ የታየው መልካም የዝናብ መጠንና ስርጭት የዘንድሮውን የምርት አሰባሰብ የተሻለ እንደሚያደርገውም ጠቅሰዋል። ያጋጠሙ ችግሮች እንዳሉ ሆነው የሰብል አሰባሰቡ አምና ከነበረው ጋር ሲነፃፀር መልካም የሚባል መሆኑንም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ጠቁመዋል። የሰብል አሰባሰብ አጠቃላይ አፈፃፀም የምርት ግምገማ ከተካሄደ በኋላ የሚታወቅ መሆኑንም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ጠቁመው፤ ቀሪ 27 ከመቶ የሚሆነውና በደጋማው የክልሉ ክፍሎች የሚገኘው ያልተሰበሰበ ሰብል እንደደረሰ በቀጣይ እንደሚሰበሰብም ጠቅሰዋል። በምርት አሰባሰብ ወቅት ብክነት እንዳያጋጥም እንደተለመደው ኮምባይነሮችንና ሌሎችንም የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርት እየተሰበሰበ መሆኑንም ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘው ገልፀዋል። በጥቅሉ የክልሉ የዘንድሮው የሰብል አሰባሰብ ያለበት ደረጃ መልካም የሚባል መሆኑንም አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 11/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37698
8277b84eb86f6dd23d0c1806e912d27d
203338a01e78370146af50b0a92b5a2f
ሆፕ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአምስት የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን 424 ተማሪዎች አስመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዳንኤል ዘነበ አዲስ አበባ ፦ሆፕ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአምስት የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪና እና በድህረ ምረቃ መርሐ ግብር ያስለጠናቸውን 424 ተማሪዎችን ትናንት አስመረቀ። በዕለቱ የተመረቁት ተማሪዎች በ2012 ዓ.ም መመረቅ የነበረባቸው እና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት በመቋረጡ ምክንያት የተላለፈ መሆኑም ታውቋል፡፡የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ፕሬዚዳንት ዶክተር ተረፈ ፈየራ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት፤ የመማር ማስተማር ሂደቱ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ቢቋረጥም፤ ተማሪዎቹ የማካካሻ ትምህርት ወስደው ለምርቃት በቅተዋል። በዚህም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በአምስት የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ እና በድህረ ምረቃ መርሐ ግብር ሲያስተምራቸው የነበሩ 424 ተማሪዎችን አስመርቋል ብለዋል።ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ካስመረቃቸው አጠቃላይ ተማሪዎቹ 368 በመጀመሪያ ዲግሪ፤ 44ቱ ደግሞ በድህረ ምረቃ መርሐ ግብር በቀንና በማታው የትምህርት መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። በመጀመሪያ ዲግሪ ለሰባት ተከታታይ ጊዜያት በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ማስመረቁን ተናግረዋል።«ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የትምህርት ፍላጎትና አቅም እያላቸው ከፍለው መማር የማይችሉ ችግረኛ ወጣቶችንም የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ይሰጣል» የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ወጣቶቹ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን መርዳት እንዲችሉ ብሎም በሀገር ግንባታ ላይ አዎንታዊ ሚና እንዲኖራቸው የራሱን ድርሻ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።ተቋሙ በየዓመቱ ከ200 ተማሪዎች በላይ የነፃ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በመጠቆምም፤ በዚሁ መሰረት በዲግሪ መርሐ ግብር ተመራቂ ከሆኑት 368 ተማሪዎች 58 በነፃ እድል ተጠቃሚ የነበሩ መሆኑን አብራርተዋል። ሆፕ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ባለፉት ሰባት ዓመታት በመጀመሪያ ዲግሪ 1ሺህ488 ተማሪዎች፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ደግሞ 44 ተማሪዎችን በድህረ ምረቃ፤ በአጠቃላይ 1ሺህ532 ተማሪዎችን ያስመረቀ መሆኑ ታውቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 11/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37703
d7d9775aa01fb9910228fde827446019
75c7c4e7bf9cf5db1cb3240497f4ccf6
ተመራቂዎች ቴክኖሎጂን በማህበረሰቡ ውስጥ ለማስረጽ መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ፋንታነሽ ክንዴአዲስ አበባ፡- የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚወጡ ተመራቂዎች ሳይንስ በማህበረሰቡ ውስጥ ባህል ሆኖ እንዲሰርጽ መስራት እንዳለባቸው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ገለፁ፡፡ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት ፕሮፌሰር አፈወርቅ፣ ለተመራቂ ተማሪዎችና ለወላጆቻቸው እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ፤ “ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያካበቱትን እውቀትና ክህሎት ከፍ ላለ ውጤት ለማዋል መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል” ሲሉ አሳስበዋል፡፡ እንደ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገለጻ፤ ሳንይንስና ቴክኖሎጂ የአንድ አገር ሁለንተናዊ እድገት መሰረት ነው፡፡ ሳይንስ የኅብረተሰባችንን ሁለንተናዊ እድገት እንዲደግፍና የዕለት ከዕለት ህይወታቸው አካልና ባህል እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ የሳይንስ ባህል ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ተመራቂዎችም ሳይንስ ባህል ሆኖ ወደ ማህበረሰባችን በመስራት እንዲሰርጽ ሊደግፉንና ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡በእውቀትና በክህሎት ያደገ ማህበረሰብ ቴክኖሎጂ የመፍጠርና የመጠቀም አቅሙ ያድጋል፤ ህግና ስርዓት የሚያከብርና የአካባቢውን ችግር የሚፈታ ሀሳብ ያመነጫል፤ ያሉት ፕሮፌሰር አፈወርቅ፤ ከዚህ አኳያ አገራችን አሁን ካለችበት ዘርፈ ብዙ ችግር እንድትወጣና ከፊት ለፊቷ ያሉትን በርካታ ተስፋዎች እንድትጠቀም ለማስቻል ተመራቂዎች መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር በማድረግ ረገድ ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ኃላፊነት እየተወጣ ሲሆን፤ ለዚህ የሚሆን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ አቅም ያለው የሰው ኃይል እያፈራ ይገኛል፡፡ በዩኒቨርሲቲው መምህራን የምርምር ሥራዎችም እያደጉ በመምጣታቸው በአገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ጭምር በኢንዱስትሪ-ዩኒቨርሲቲ ትስስሩ ትልቅ ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡በምርምርና ልህቀት ማዕከላቱ አማካኝነትም በህዋ ሳይንስ ላይ የበኩሉን ለመወጣት እየሰራ ሲሆን፤ ከዚህ በተጓዳኝ ለህብረተሰቡም ሙያዊ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል፡፡ በቀጣይም በርካታ ግዙፍ የምርምር ፕሮጀክቶችን እየሰራ ሲሆን፤ ኮሮናን በመዋጋት ጭምር ሲወጣ የነበረው ጠንካራ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ዶክተር ለሚ ያረጋገጡት፡፡ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ላሳዩት መልካምና ዓርአያነት ላለው ስነምግባር በማመስገን ለተመራቂዎችና ለቤተሰቦቻቸው እንኳን ደስያላችሁ ያሉት ዶክተር ለሚ፤ ለተመራቂ ተማሪዎች “አገሪቱን ወደፊት የሚያራምዱ ተግባራትን ማከናወን እንዲሁም የህዝቡን ኑሮ የማሻሻልና ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ከእናንተ ይጠበቃል እና የመማራችሁን ትርጉም በመገንዘብ ይሄንኑ በታላቅ ትጋትና ሥነምግባር እንድትፈጽሙ አደራ እላለሁ” ሲሉ አሳስበዋል፡፡ መጪው ዘመን በተሰማራችሁበት የስራ መስክ መልካም ውጤት የምታመጡበት እና ህዝባችሁን በቀናነት የምታገለግሉበት፣ አገራችሁንም ወደ ብልጽግና የምታሸጋግሩበት ዘመን ይሁንላችሁ፤ ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡ዩኒቨርሲቲው ትናትን 1ሺህ240 ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ በተለያየ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን፤ ከተመራቂዎች ውስጥ 1ሺህ 228 በመጀመሪያ ዲግሪ፤ 2 ደግሞ በዶክትሬት ዲግሪ የተመረቁ ናቸው፡፡ በዕለቱ ከተመረቁት ውስጥም 274 ሴት ተመራቂዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 11/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37704
5971ad77a1e692760ec9962f40ba90ee
c7d2e7b06fd49ca0109706283a3ab606
ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ህዝቡ መጪው ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው የአገሪቱ ህዝብ ወደ እውነተኛ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመሸጋገር የተወሰዱ የአገራዊ ለውጥ እርምጃዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም መጪው ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነጻና በሂደቱም ሆነ በውጤቱ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ የብልጽግና ፓርቲ ጥሪ አቀረበ። የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን መደበኛ ስብሰባ አጠናቅቋል። በጉባኤው ማጠናቀቂያ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ብልጽግና ፓርቲ =በመጪው ምርጫ ጠንካራ ተወዳዳሪ ሆኖ በውጤታማነት እንዲያጠናቅቅ በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ መክሮ አቅጣጫ አስቀምጧል። በአገሪቱ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለምርጫው ውጤታማነት እና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ኖሮት እንዲጠናቀቅ በማድረግ በኩል የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማበርከት ይኖርባቸዋል። ፓርቲው ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የፓርቲው ማዕከላዊ በሰላም፣ በልማት፣ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና መጪውን አገራዊ ምርጫ በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። በዋናነት ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በኢትዮጵያ የታየው ለውጥ በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፈተናዎችን ተጋፍጦ የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ ሰፊ እድል የፈጠረና አገራችንን ከብተና አደጋ ያዳነ መሆኑ በውይይቱ ከስምምነት ተደርሷል። በተለይም ብልጽግና ውሁድ ህብረ ብሄራዊ አገራዊ ፓርቲ ሆኖ መደራጀቱ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ከፍተኛ እድል ከመፍጠሩም በላይ ከአገሪቱ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ተገለው የዳር ተመልካች የነበሩ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለማቀፍና ለማሳተፍ የቻለ የመጪው ትውልድ ፓርቲ መሆኑ ተረጋግጧል። በአገራዊ ለውጡ የተገኙ ድሎችን ጠብቆ በማስቀጠል ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም የፓርቲውን መርሆዎች፣ እሴቶችና አሰራሮችን በጥብቅ ዲሲፕሊን ተግባራዊ ማድረግና ጠንካራ ተቋማዊ ባህል መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ከስምምነት ተደርሷል። ከዚህ በተጓዳኝ፣ ኮሚቴው በሁለቱ ቀናት መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጧል። ከእነዚህ መካከል አንዱ የቀጣዩን ምርጫ የሚመለከት ሲሆን፤ ብልጽግና ፓርቲ በመጪዉ ምርጫ ጠንካራ ተወዳዳሪ ሆኖ በውጤታማነት እንዲያጠናቅቅ በፓርቲው ማኒፌስቶ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ አጽድቆታል። መላው የፓርቲው አመራሮችና አባላት የጸደቀውን ማኒፌስቶ መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል። በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ እውነተኛ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመሸጋገር የተወሰዱ የአገራዊ ለውጥ እርምጃዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም መጪው ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነጻና በሂደቱም ሆነ በውጤቱ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። መላው የአገሪቱ ህዝቦች ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት በኢትዮጵያ የታዩ ለውጦችና የተገኙ ድሎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ መጪው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነጻና ተቀባይነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅና የዜጎች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልጽግና የተረጋገጠባት ጠንካራ አገር ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽዖ ሁሉ እንዲያደርጉም ነው ፓርቲው ጥሪውን ያስተላለፈው።
https://www.press.et/Ama/?p=37697
a32c82d913b3aed4dfcd668fce1da06d
cefcbd11c14200d02727eeb3f417b151
«በአገራችን ሰፊውን ህዝብ በአግባቡ ሊያንቀሳቅሱ የሚችሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አልተፈጠሩም»ዶክተር ዲማ ነገዎ የፖለቲካ ምሁር
ሀገር አቀፍ ዜና
አስቴር ኤልያስ አዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ ሰፊውን ህዝብ በአግባቡ ሊያንቀሳቅሱ እና ሊያነሳሱ የሚችሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገና አልተፈጠሩም ሲሉ የፖለቲካ ምሁሩ ዶክተር ዲማ ነገዎ ተናገሩ። ዶክተር ዲማ፣ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ አንዱ እና ትልቁ ችግር የፖለቲካ አደረጃጀት ጉዳይ ነው። በዚህም እስካሁን ሰፊውን ህዝብ ሊያንቀሳቅሱ የሚችሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መፈጠር አልቻሉም።“በአገራችን እስካሁን ድረስ የፖለቲካ ቡድኖች እንጂ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም” የሚሉት ዶክተር ዲማ፤ ከዚህም የተነሳ “ሰፊውን ህዝብ በአግባቡ ሊያንቀሳቅሱ እና ሊያነሳሱ የሚችሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገና አልተፈጠሩም” ብለዋል።በቀጣይ በአገራችን የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲፈጠር የፖለቲካ ፓርቲዎች መፈጠር መቻል አለባቸው የሚል እምነት አለኝ ያሉት የፖለቲካ ምሁሩ ዶክተር ዲማ፤ ለዚህ ምክንያታቸው ደግሞ በአገሪቱ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች በትክክል የህዝብን ፍላጎት ያገናዘበ እንቅስቃሴ ሲያድርጉ ባለመታየታቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸውለማለት የማያስችል በመሆኑ እንደሆነ አመልክተዋል።እንደ ዶክተር ዲማ ገለጻ፤ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ መሆን የሚጠበቅበት የሕዝቡን ልዩ ልዩ ጥቅም የሚያንጸባርቅ እንጂ የተወሰነውን ቡድን ስሜት ብቻ የሚከተል መሆን የለበትም። ስለዚህ ሰፋ ያለውን የህዝቡን ፍላጎት የሚያንጸባርቁ የፖለቲካ ድርጅቶች መፈጠር አለባቸው። እስካሁን ያሉት በቡድን ደረጃ ነው። ስለሆነም ትልቁ የሚቀረው ነገር ቢኖር በትክክል የተዋቀሩና ህዝብን መሰረት ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መፈጠር እንደሚኖርባቸው ማወቅ ነው። ለተቋማት መገንባት ደግሞ ሰፋ ያለ ፍላጎት ላይ የተመሠረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያስፈልጋሉ።በኢትዮጵያ ውስጥ የተረጋጋ እና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት ቢያንስ ገለልተኛ የሆነ የአገሪቱን እና ህዝቡን የሚያገለግል የመንግሥት ስርዓት መኖር አለበት የሚለውም ጉዳይ ሊተኮርበት እንደሚገባ የሚናገሩት ዶክተር ዲማ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በስርዓት መገንባት እና መደራጀት እንዳለባቸው ገለጸዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37768
612b053c9ebd6066e900ca753c02c5bf
28bfce8ecda1f44c6ec0c854ffb2f66e
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ38ኛው አስቸኳይ የኢጋድ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት፤ በ38ኛው አስቸኳይ የኢጋድ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ መግባታቸውን ተከትሎ፤ ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሓምዶክ፣ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ ፋርማጆ፣ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ሬቤካ ንያዴግ ዲ ማቢዮር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። መሪዎቹ ጁቡቲ እየተካሄደ በሚገኘው 38ኛው አስቸኳይ የኢጋድ የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድም ከመሪዎቹ ጋር የተናጠል ውይይት አካሂደዋል። በዚህም የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት  መሀመድ ፋርማጆ በተናጥል ካነጋገሯቸው በኋላ፤ ሁለቱን መሪዎች በአንድ ላይ በማምጣት አነጋግረዋል። ይሄንንም ‘’ከመሪዎቹ ጋር በአካባቢያችን አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየታችን ደስ ብሎኛል’’ ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የገለጹት። በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የሚመራው የጉባዔው ተሳታፊ ልዑክ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ሲሆን፤ ጉባዔውም በአፍሪካ ቀንድ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ እንዲሁም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ የሚመክር ይሆናል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12 ቀን 2013  ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37764
703378c7cc1476fc27f936bb100bde37
e93f4d4335bdcf01af96a4fc8f261570
አድሏዊ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ የህዝብን ጥላቻን በማባባስ የአገር አደጋ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ጽጌረዳ ጫንያለው አዲስ አበባ፡- የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች በከፍተኛ ሁኔታ አድሏዊነት እየታየባቸው በመምጣታቸው ጥላቻን በማባባስ የአገር አደጋ እየሆነ መምጣቱን አስተያየታቸውን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰጡ የዘርፉ ምሑራን ተናገሩ። በውጪ ሚዲያዎች የሚታየው የአድሎ ዘገባ ምንጩ ችግሩን ከምንጩ አለመረዳት እና ችግሩ ያደረሰውን እንጂ ያመጣውን ማየት አለመፈለጋቸው መሆኑንም ገልጸዋል።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህር ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ መገናኛ ብዙኃን የህዝብ ልሳን በመሆናቸው የሁሉንም ሀሳብ በእኩል ደረጃ ማስተናገድ ቢኖርባቸውም ይሄን እያደረጉት እንዳልሆነ በተለያየ መንገድ ይታያል። በዚህም ግለሰቦችን ለማጉላት ሲሞክሩ፤ የአንድ ወገን ሀሳብ ብቻ ሲያስተናግዱ፤ ከጋዜጠኛው ጀርባ ያሉ አካላት ፍላጎትን ሲያሳኩም ይስተዋላል። ይህ ደግሞ በህዝብ መካከል ጥላቻን በማባባስ አገርን አደጋ ውስጥ እንድትገባ እያደረጋት ይገኛል። በመገናኛ ብዙኃኑ ዘገባዎች የጋዜጠኛው ፍላጎት፣ የአገራት ፍላጎት፣ የፖለቲካና የሚፈለገው የርዕዮተዓለም ፍላጎት እንዲሁም የብሔር ፍላጎት ሰፊውን ድርሻ ወስዶ በመዘገቡ የህዝብን ሀሳብ እየታፈነ እንደሆነ ይታያል የሚሉት ዶክተር ሙላቱ፤ መገናኛ ብዙኃኑ የህዝብ አገልጋይነታቸውን መልቀቃቸውን እና ሀሳቦች እንዳይንሸራሸሩም ወገንተኝነታቸው መብዛቱን ይገልጻሉ። በተለይም የክልል ሚዲያዎች በዚህ ዙሪያ ከፍተኛውን ድርሻ እየወሰዱ መሆኑን፤ ይህ ደግሞ በህዝብ መካከል ጥላቻና ቂም እንዲፈጠር እድል መስጠቱን፤ ሂደቱም አማራጭ የመፍትሄ ሀሳቦች እንዳይኖሩም እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። የዜጎች ድምጽ መታፈንን ከሚያመላክቱ መንገዶች አንዱ አድሏዊ ዘገባ እንደሆነ የሚጠቁሙት ዶክተር ሙላቱ፤ ሀሳብ ሳይወጣ ሲቀር ፍርሀትና ስጋት ይፈጥራል። ይህ ደግሞ ቂም አርግዞ ለቀጣይ ጊዜ ከፍተኛ ችግር በህዝቦች መካከል እንዲከሰት ያደርጋል። የተረጋጋ ህይወት ለመኖርም አያስችልም። ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን ልዩነት በትክክል እንዳያዩ ያደርጋቸዋል። ስለዚህም አሁን በጥናት ባይረጋገጥም አገሪቱ ላይ እየሆነ ያለው ይሄው መሆኑን ተናግረዋል። ወቅቱ ብዙ ችግሮችን አርግዞ የቆየበት በመሆኑ የአገር ውስጥ ሚዲያዎች በተለይም የክልል መገናኛ ብዙኃን ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የሚናገሩት ዶክተር ሙላቱ፤ ተጎጂውም ሆነ ጎጂው የአንድ አገር ዜጋ በመሆኑ መገናኛ ብዙኃን ሁለቱንም ማዕከል ያደረገና ግራ ቀኙን ያየ ዘገባ ማዘጋጀት እንዳለባቸው አስረድተዋል። የሰላም ግንባታ ላይ መስራት ሚዲያው ለቆመለት አላማ ከመታመንም በላይ ህዝብንና አገርን ከችግር መታደግ ነው። ስለሆነም መገናኛ ብዙኃኑ ዘገባቸውን እንደ መከላከያ ለህዝብና ለሰላም ወገንተኝነትን መሰረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል። ለዚህ ደግሞ አድሏዊነትን ትተው ሚዛናዊነትን ማስቀደም እንደሚገባቸውም ገልጸዋል። እንደ ዶክተር ሙላቱ ገላጻ፤ በውጪ ሚዲያዎች የሚታየው የአድሎ ዘገባ ምንጩ የተለያየ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ችግሩን ከምንጩ አለመረዳት ነው። ሌላው ችግሩ ያደረሰውን እንጂ ያመጣውን ማየት አለመፈለጋቸው ነው። ነገሮችን ተከታትሎ አለመዘገብ፣ የራሳቸውን ፍላጎት ማስቀደምም፣ ሌላው የአድሎአዊነት መሰረታቸው ነው። ስለሆነም በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚገኙ አድሎአዊ ዘገባዎችን ለማስቀረት ከራስ የጀመረ ሥራ ያስፈልጋል። እንደ ሚዲያ ያለውን ህግ መሰረት አድርጎ ግራ ቀኝ አይቶ መዘገብ ደግሞ የመጀመሪያ መፍትሄ ነው። መረጃ የሚሰጡ አካላት ትክክለኛውን መረጃ ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ሊሰጡ እንደሚገባ የጠቆሙት ዶክተር ሙላቱ፤ በተለይም ለውጪ ሚዲያዎች በየቀኑ መግለጫ መስጠትና እውነታውን ማሳየት እንደሚገባ አስረድተዋል። በተመሳሳይ በኢንባሲዎች አካባቢ ሥራዎች መሰራት ያስፈልጋል። እንደመንግሥት ጋዜጠኞችን ወቅታዊ ጉዳይ ባለበት ስፍራ ይዞ በመጓዝም እውነታውን ማሳየት ተቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት ብለዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን መምህር እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪው መምህር ፍሬዘር እጅጉ በበኩላቸው እንደሚናገሩት፤ ከለውጡ በኋላ በተሰጠው የሚዲያ ነጻነት ጥናት ተደርጎ እንደተገኘው በአገሪቱ ያሉ የሚዲያ ተቋማት ዘገባ ከፍተኛ አድሏዊነት የሚታይበት ነው። የአንድ ወገንን ሥራ የሚያጎላም ነው። ይህ ደግሞ ቀጣይነት ያለው ችግር እንደሚፈጥር የታየበት ሲሆን፤ አሁን የተፈጠረውም ከዚሁ ግምት ጋር ይያያዛል።ከውጪ ሚዲያ አንጻር ሲታይ ደግሞ አፍሪካ በዓለም መገናኛ ብዙኃን የምትወከለው የጦርነት ምድርና የችግር ምሳሌ በመሆን ስለሆነ በፊት ገጻቸው ከዚህ የተለየ ማስፈርን እንዳይችሉ አድርጓቸዋል። ምክንያቱም የውጪ ሚዲያዎች በአፍሪካ ያለውን ሰላም፣ ስኬትና ልማት የሚያዩበት መነጽር የተሳሳተ ስለሚሆን ለተነባቢነታቸው ስለሚጨነቁ መዘገብ አይፈልጉም።እንደነዚህ አይነት ችግሮችን ለመፍታት ሁለት መንገዶችን መጠቀም እንደሚበጅ የሚናገሩት መምህር ፍሬዘር፤ በውጪዎች እይታ የሚደማ ነገር ካለና መጥፎ ዜና ከሆነ ጥሩ ዜና ተብሎ ፊት ገጽ እንዲሆን ይፈቀዳልና ይህንን ባህሪያቸውን አቅርቦ በጥሩ መቀየር እንደሚገባ ይገልጻሉ። ለዚህ ደግሞ አሁን በወቅታዊ ጉዳዮች እንደተቋቋመው የመረጃ ፍሰት ማዕከል አቋቁሞ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ስትራቴጂን መፍጠር ትልቅ ውጤት እንደሚያስገኝ ተናግረዋል። የአገር ውስጥ ሚዲያው መፍትሄ ደግሞ፣ ህዝብን ለውዥንብርና ብዥታ የሚዳርጉ ሚዲያዎችን ብሮድካስት እርምጃ እየወሰደ ማስተካከል እንደሚገባ በመጠቆም፤ ሚዲያው በራሱ የተለያየ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች በመጋበዝ ሚዲያው የሀሳብ ማንሸራሸሪያ መድረክ እንዲሆን መስራት ይኖርባቸዋልም ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37769
27500d30d06a5bf8188201126cb3116d
8d1d8fe88244a3b22e9bf9c11c783efe
በአማራ ክልል በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር 14 የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በመጭዎቹ ሦስት ዓመታት በአማራ ክልል ዝናብ አጠር እና ደረቃማ አካባቢዎች በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር 14 የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች እንደሚገነቡ ተገለጸ። ፕሮጀክቶቹ፣ በአማራ ክልል መካከለኛ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች ያለውን የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሳደግ ያስችላል የተባለለት ይህ ፕሮጀክት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በሰሜን ወሎ፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች እንደሚገነባም ነው የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የዘገበው። በዘገባው እንደተመላከተው፤ የፕሮጀክቱ አካል የሆኑት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከተማ እና በሰሜን ወሎ ዞን ሰኞ ገበያ የሚገነቡት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ የፊርማ ሥነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፤ የግንባታ ውሉ የፊርማ ሥነ ሥርዓትም በፕሮጀክቱ አስፈፃሚ የአማራ ክልል ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ እና በሚገነባው የጢስ እሳት ኮንስትራክሽን ድርጅት መካከል ተካሂዷል። በወቅቱም፣ የአማራ ክልል ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው እንደገለጹት፤ 14ቱ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች በአየር ንብረት አይበገሬነት የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ፕሮግራም የሚከናወኑ ሲሆኑ፤ ግንባታቸው በመጨዎቹ ሦስት ዓመታት ይጠናቀቃል ብለዋል። የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶቹን ገንብቶ ለማጠናቀቅ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ተመድቧል።በፕሮጀክቱ ግንባታ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውኃ መስኖና ኢነርጂ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ፈትያ የሱፍ፣ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ እና የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ የተገኙ ሲሆን፤ ለፕሮጀክቶቹ ተፈፃሚነት የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የውኃ ልማት ኮሚሽን እና የአማራ ክልል ውኃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ በጋራ እንደሚሰሩም ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ መናገራቸውን ነው አብመድ የዘገበው። አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37772
78197fea1447a37c06bef0376940b5c1
e3ed015bf8776e8da4df84d39dc225d2
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት እገዳ ተጣለባት
ስፖርት
ኢትዮጵያዊቷ የማራቶን ሯጭ እታፈራሁ ተመስገን አበረታች መድሃኒት ተጠቅማ በመገኘቷ ጊዜያዊ እገዳ ተጣለባት። አትሌት እታፈራሁ በዓለም አትሌቲክስ ገለልተኛ ሆኖ በተቋቋመው የአበረታች ንጥረ ነገሮች ምርመራ ቡድን በተደረገላት ምርመራ ብቃቷን ከፍ የሚያደርግ መድሃኒት ተጠቅማ በመገኘቷ እገዳው እንደተጣለባት ኢንሳይድ ዘጌምስ ዘግቧል። የሰላሳ ዓመቷ አትሌት እታፈራሁ ባለፈው ሰኔ በኦታዋ ማራቶን ተሳትፋ 2፡28፡44 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ሲሆን ከወር በፊት በቶሮንቶ ማራቶን 2፡27፡ 21 በሆነ ሰዓት ስምንተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወቃል። እ ኤ አ በ2018 በሜክሲኮ ማራቶን አትሌቷ 2፡40፡10 በሆነ ሰዓት ማሸነፍ ችላለች። አትሌት እታፈራሁ የተደረገላትን ምርመራ ማለፍ ባለመቻሏ በየትኛውም ስፖርት ላልተወሰነ ጊዜ ተሳታፊ እንዳትሆን ጊዜያዊ እገዳ የተጣለባት ሲሆን የዓለም አትሌቲክስና ገለልተኛው የምርመራ ቡድን ከአበረታች መድሃኒት ተጠቃሚነት ጋር የተያያዙ ዓለም አቀፍ ህግጋቶችን መሰረት አድርገው ወደ ፊት በቋሚነት ቅጣት እንደሚያስተላልፉ ዘገባው አመልክቷል። ከወር በፊት በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የአስር ሺ ሜትር አሸናፊ የሆነው ኢትዮጵያዊው አትሌት ብርሃኑ ፀጉ የተደረገለትን የአበረታች መድሃኒት ምርመራ ማለፍ ባለመቻሉ ተመሳሳይ እገዳ እንደተጣለበት ይታወሳል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአትሌቲክሱ አበረታች መድሃኒት ወይም ንጥረ ነገሮች ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ ሩሲያን የመሳሰሉ ታላላቅ አገራት ከታላላቅ ውድድሮች እስከመ ታገድ ደርሰዋል። እነዚህ አገራት አትሌ ቶቻቸው በብዛት አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆነው ከመገኘታቸው ጋር ተያይዞ በመንግሥት ጭምር ይደገፋሉ በሚል ከውድድሮች መታገ ዳቸው ይታወቃል። የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ እነ ሩሲያን በቀጣበት ወቅት ኢትዮጵያና ኬንያ አደጋው በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሰጋቸው በማሳወቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክረ ሃሳብ ሰጥቷቸው ነበር። ሁለቱ አገራት በተለይም ኢትዮጵያ ለጉ ዳዩ ትኩረት ሰጥታ በመስራት አበረታች ውጤት ማስመዝገቧም በኤጀንሲው ጭምር ተመስክሮላታል። ያም ሆኖ ስጋቱ ሙሉ ለሙሉ ተቀርፏል ለማለት አይቻልም። ባለፈው ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ኢትዮጵያና ኬንያን በአበረታች መድሃኒት (ዶፒንግ) ምክንያት ስጋት ካለባቸው አገራት ቀዳሚውን ደረጃ እንደሚይዙ ማሳወቁ ይታወሳል። ዘንድሮም ሁለቱ አገራት በአበረታች መድሃኒት ስጋት ቁንጮውን ደረጃ መያዛቸው እንደማይቀር እየወጡ ያሉ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ለዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ አምስት የአፍሪካ አገራት አትሌቶች አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆነው መገኘታቸው ማሳያ ተደርጓል። ቤላሩስና ዩክሬን ሁለቱን የአፍሪካ አገራት ተከትሎ ስማቸው ከቁንጮዎቹ ተርታ ተፅፏል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለይም በግል ውድድሮች ብቻ የሚታወቁት አልፎ አልፎ በአበረታች መድሃኒት ሲቀጡ ይታያል። ይሁን እንጂ አገርን ወክለው በሚወዳደሩ አትሌቶች ይህ ቅሌት አይታይም ማለት ይቻላል። ባለፈው ክረምት በሞሮኮ ራባት በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን ወክሎ በአስር ሺ ሜትር ወርቅ ማጥለቅ የቻለው ብርሃኑ ፀጉ ኢፒኦ የተባለ ንጥረ ነገር ተገኝቶበት ላልተወሰነ ጊዜ ከስፖርቱ ታግዷል። ይህ የሃያ ዓመት አትሌት ባለፈው ወር በኮፐንሃገን ግማሽ ማራቶን ላይ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ብርሃኑ ሔንግሎ በተካሄደው የዓለም ቻምፒዮና የኢትዮጵያውያን ማጣሪያ ውድድር ላይ 10ሺ ሜትሩን 27፡00፡73 በሆነ ሰዓት ማጠናቀቅ ችሏል። ብርሃኑ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ኤርትራዊው አሮን ክፍሌና ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ጀማል ይመር ተከትለውት መግባታቸው ይታወሳል። ብርሃኑ የወርቅ ሜዳሊያውን ተነጥቆ ለኤርትራዊው አትሌት፣ የብር ሜዳሊያው ደግሞ ለጀማል ይመር የሚሰጥ ሲሆን አራተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ኬንያዊው ኤድዊን ሦይ የነሐስ ሜዳሊያ ሊያገኝ እንደሚችል መረጃዎች እየወጡ ነው። በአዲስ አበባ አበረታች መድሃኒቶች በስታድየም አካባቢ ካለ ሐኪም ማዘዣ ጭምር እንደሚሸጡ የእንግሊዝ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ተከትሎ የዓለም አትሌቲክስ ኢትዮጵያን ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ፅሕፈት ቤትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቶች የተለያዩ ትምህርቶችን እየሰጡ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ኅዳር 18/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=23270
3e0e3de62e427a0415be59f5259e0d2e
14de21769223b2b3081f492260b42bb7
”ለመከላከያ ምንም ድጋፍ ቢደረግ ለሀገርና ለህዝብ የዋለውን ውለታ መመለስ አይቻልም” – አቶ የሺዋስ አሰፋ የኢዜማ ሊቀመንበር
ሀገር አቀፍ ዜና
ሶሎሞን በየነአዲስ አበባ:- ለአገር መከላከያ ሠራዊቱ የሚደረገው ማንኛውም ድጋፍ ሞራል ለመስጠትና አጋርነትን ለማሳየት ያህል ካልሆነ በስተቀር ሠራዊቱ አጥንቱን ከስክሶ አገር እንዳዳነው፣ ደሙን አፍሶ የኢትዮጵያን ሃጢያት እንዳጠበው እንደማይሆን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ገለጹ።አቶ የሺዋስ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንደገለጹት፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የአገር መከላከያ ሠራዊት ህግን ለማስከበርና የአገርን ህልውና ለማዳን መስዋዕትነት ከፍሏል፤ እየከፈለም ይገኛል። ይሄን ተከትሎም ኅብረተሰቡ ለመከላከያ ሠራዊቱ ሰፊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ሆኖም በዚህ መልኩ የሚደረገው ማንኛውም ድጋፍ ለሠራዊቱ ሞራል ለመስጠትና አጋርነትን ለማሳየት ያህል ካልሆነ በስተቀር ማንም ምንም አይነት ድጋፍ ቢያደርግ መከላከያ ሠራዊቱ አጥንቱን ከስክሶ አገር እንዳዳነው፣ ደሙን አፍሶ የኢትዮጵያን ሃጢያት እንዳጠበው አይሆንም።በአገር መከላከያ ላይ የተፈጸመው ክህደት እኛ ካልመራን አገር ትጠፋለች ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ የሺዋስ፤ ይህ አጥፊ ቡድን እራሱ የቆሰቆሰውን የኤርትራ ጦርነት ምክንያት አድርጎ የአገሪቱ ትልቁ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዲፖ፣ ብረት ለበስ ወታደራዊ ኃይል፣ የአገሪቷ መካናይዝድ ጦር፣ ስምንት ትልልቅ ክፍለጦር ያሁሉ የጦር መሳሪያ በአንድ ቦታ በማከማቸት የየራሱን ጉልበት ሲያጠናክር መቆይቱን ተናግረዋል። የጁንታው ቡድን በህዝብ ቁጣ አንድ ቀን ስልጣኔን አጣለሁ ብሎ ስለሚሰጋ ሰልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ለጦርነት ሲዘጋጅ እንደቆየና ጉድጓድ ሲቆፍር፣ ነዳጅና የጦር መሳሪያ ሲያከማች ጊዜውን እንዳጠፋ በመግለጽም፤ ከዚህ ባሻገር በአገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ከለውጥ መንግሥቱ ጋር ተባብሮ ከመስራት ይልቅ በሰበብ አስባቡ ጠብ እየፈለገ ሁከት ለመፍጠር ሲሞክር መቆየቱን አብራርተዋል። በመጨረሻም ቡድኑ ለ21 ዓመታት ያህል ድንበር ሲጠብቅ የቆየውን ሠራዊት ከትግራይ አይወጣም በማለት በሠራዊቱና በመንግሥት ላይ ጫና ለማሳረፍ ከመሞከሩም ባሻገር፤ ለትግራይ ህዝብ አለኝታና መከታ በነበረው ሠራዊት ላይ ጥቃት በመፈጸም ጁንታው ወራዳነቱን አሳይቷል። ይህ ድርጊቱም የትግራይን ህዝብ ባህልና ማንነት የማይገለጽና በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አውሬያዊ ስብስብ ባህሪ ነው ያሉት አቶ የሺዋስ፤ ድርጊቱ በክርስትናም ሆነ በእስልምናም ነውርና የተወገዘ መሆኑንም አስረድተዋል። ከህዝብ ጋር ሆኖ አንበጣ ሲከላከል፣ የህዳሴ ግድብን ሲጠብቅ፤ ሰብል ሲሰበስብ፤ ከሌለው ላይ አዋጥቶ ትምህርት ቤት ሲያሰራ በነበረን የህዝብ ሠራዊት ከኋላው መውጋት ከከሃዲነትም በላይ መሆኑን ገልጸዋል። ቡድኑ የፈጸመው አስጸያፊ ድርጊት ኢትዮጵያንም ሆነ ፖለቲካውን ከአለማወቅ፣ ሃሳባቸውም ያረጀና ያፈጀ መሆኑን ካለመገንዘብ ነው ያሉት አቶ የሺዋስ፤ በመከላከያ ላይ የተሰራው ግፍ ሁሉም ኅብረተሰብ ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ስሜቱ ዘልቆ የተሰማው መሆኑንም ገልጸዋል። በዚህም በኮቪድ እና ህዳሴ ግድቡ ወቅት ካሳየው የአንድነት ስሜት በላቀ መልኩ የህወሓት ጁንታ ቡድን ህግ መጣሱን ተከትሎ መከላከያ በወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ እንደአንድ ሰው ስሜቱ መተሳሰሩን ተናግረዋል። የህብረተሰቡ አንድነት ደግሞ ለኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ እንደመሆኑ በዚህ ረገድ ፓርቲዎችን፣ ሽማግሌዎችን፣ የኃይማኖት አባቶችን በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ ሊመሰገን ይገባዋል፤ ብለዋል። እንደ አቶ የሺዋስ ገለጻ፤ ህግን ለማስከበርና ሀገርን ለማዳን መከላከያ የወሰደው እርምጃ ሌላም ተመሳሳይ ዕኩይ ባህሪ ላላቸው አካላት አስተማሪ ነው። ሀገር ከማዳኑም ባሻገር ኢትዮጵያ የምትኮራበት ተቋም መገንባት መቻሉንም ያመላከተ ነው። መከላከያ ሠራዊቱ በአጠቃላይ መከላከያ ተቋሙ ምን ያክል ጠንካራ እንደሆነ ያስገነዘበ፤ ከአየር ኃይሉ እስከ እግረኛው ድረስ ከአገር ውስጥ ላለው ቦርቧሪ ከውጭ ለሚያስበውም ወራሪ በጣም ጥሩ ትምህርት የሰጠ እና ጀግኖችን ያፈራ ሂደትም ሆኗል። አምባገነን ሁል ጊዜ ጠብ የሚጭረው ከወጣቱ ባሻገር እናቶችን፣ አረጋዊያንና በሽተኞችን ጭምር ለማስፈጀት ነው ያሉት አቶ የሺዋስ፤ እንደፓርቲ ደም በመለገስ ገንዘብ በመስጠት በምንችለው ሁሉ ከመከላከያ ጎን ቁመናል። ኅብረተሰቡም የሚችለውን ሁሉ ለመከላከያ ድጋፍ እያደረገ ነው። ይህ ድጋፍ እስከመጨረሻ ድረስ እንዲዘልቅ በማድረግ ሁሉም አጋርነቱን ሊያሳይ ይገባል ሲሉ አመልክተዋል። ‹‹ከመከላከያ ጎን ቆማችኋል ተብለው በገመድ ታንቀው የተገደሉ የትግራይ ልጆች አሉ። ይህ ሲታሰብ ያለአግባብ የተከፈለው መስዋትነት በጣም ብዙና ያሚያም ነው” ያሉት አቶ የሺዋስ፤ ፖለቲካ ማወቅ ዓለማወቅ፣ ህዝብ ይቅርታ መቀበል አለመቀበል ሌላ ነገር ሆኖ በተለይ በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸሙት አረመኔያዊ ተግባር ፈጽሞ ከሰውነት የወጡ ከትግራይ ህዝብ ጋር የማይተዋወቁ ከሌላ ዓለም የመጡ ፍጡራን ናቸው እንድንል አድርጎናል ሲሉም ተናግረዋል። ይህ እኩይ ቡድን ለፍርድ እስኪቀርብ ድረስም ሁሉም ኢትጵያ ህዝብ ከመከላከያና ከጸጥታ አካላት ጎን እንዲቆምም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 11/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37692
ec6cd04a810eeb8f5e102836d9b15fa0
ede1323482ee788e2a68c8b3000627ca
የቮሊ ቦል ፕሪሚየር ሊግ ከ2ሳምንት በኋላ ይጀመራል
ስፖርት
 የሀበሻ ሲሚንቶ የቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመቱን ከሁለት ሳምንት በኋላ የሚጀምር ይሆናል፡፡ በ2011 ዓ.ም የሊጉ አፈጻጸምም ግምገማ መሰረትም የተሻለ የውድድር ዓመት እንደነበረም ተመልክቷል፡፡ በዘጠኝ ክለቦች መካከል የሚካሄደው የ2012 ዓ.ም የሀበሻ ሲሚንቶ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር መርሃ ግብሩን በሁለት ሳምንታት ውስጥ የሚጀምር መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በድረ-ገጹ አስነብቧል፡፡ ፌዴሬሽኑ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ያከናወነ ሲሆን፤ ያለፈውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ደረጃ መነሻ በማድረግም የመጀመሪያ ዙር የውድድር መርሀ ግብር ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት ወላይታ ድቻ ከውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ መደወላባ ዩኒቨርስቲ ከፌደራል ማረሚያ ቤት፣ ሙገር ሲሚንቶ ከጣና ባህርዳር እንዲሁም አዲስ አበባ ፖሊስ ከመከላከያ እንደሚገናኙ ታውቋል ፡፡ ፌዴሬሽኑ የ2011 ዓ.ም የሀበሻ ሲሚንቶ የወንዶች የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ግምገማ ያካሄደ ሲሆን፤ በግምገማውም የክለብ አመራሮች፣ የዳኞች ኮሚቴ፣ የቴክኒክ ኮሚቴ እና የውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴዎች ተሳትፈዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ በ 2 ዙር በአራት ከተሞች ባካሄዳቸው ውድድሮች ላይ የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችንና ክፍተቶችን በመለየት የመከረ ሲሆን፤ የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ወቅቱን ጠብቆ መጠናቀቅ፣ ጠንካራ የፕሪሚየር ሊግ ፉክክር መታየት፣ የኮኮቦች ምርጫ ያለምንም ቅሬታ መካሄድ እና አንፃራዊ የስፖርታዊ ጨዋነት መስፈን በጥንካሬ ከተነሱ ነጥቦች መካከል ተጠቃሾቹ ናቸው ፡፡ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የ2011 የሀበሻ ሲሚንቶ ፕሪሚየር ሊግ የተሻለ ውድድር የተካሄደበትም ነው፡፡ ነገር ግን በዳኞች የሚታዩ የዳኝነት ክፍተቶች፣ ከሜዳ ውጪ የሚታዩ የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለቶች፣ አሰልጣኞች በውድድር ሜዳ የሚያሳዩት ያልተገባ ስነ-ምግባር፣ የውድድር ኮሚሽነሮች የተሟላ ሪፖርት ያለ ማቅረብ፣ በአንዳንድ ተጨዋቾች የሚታዩ የስነ-ምግባር ጉድለቶች፣ ውጤትን በፀጋ ያለመቀበል እና ክለቦች ለውድድር ቅድመ ዝግጅት ባለማድረግ ችግሮች እንደነበሩበት በተሳታፊዎች ተነስቷል፡፡ በአዲሱ የፕሪሚየር ሊግ ዓመት እንዳይደገሙም የመፍተሄ አቅጣጫ ተቀምጧል ፡፡ ፌዴሬሽኑ ከግምገማ እና እጣ ማውጣት ስነ- ስርዓት በኋላ በውድድሩ ለሚሳተፉ ክለቦች የቁሳቁስ ድጋፍ ማበርከቱንም በዘገባው ተጠቁሟል፡፡አዲስ ዘመን ኅዳር 17/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=23241
26aeefc34a61ca72be39763d1b900eb1
b8f747ad91eee20d11655405f6d3ca4d
ከሽንፈት ማግስት የሚደረጉት ወሳኝ የብሔራዊ ቡድን ፍልሚያዎች
ስፖርት
ባለፈው ቅዳሜና ዕሁድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች በሁለቱም ፆታ ያደረጓቸውን ጨዋታዎች በሽንፈት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ቅዳሜ ዕለት ለ2021 የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድባቸውን የመጀመሪያ ጨዋታ ከሜዳቸው ውጪ አድርገው በማዳጋስካር አንድ ለምንም መሸነፋቸው ይታወሳል። የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሉሲዎቹ ደግሞ በመካከለኛውና ምሥራቅ አፍሪካ(ሴካፋ) ዋንጫ ዕሁድ ዕለት የምድባቸውን የመጀመሪያ ጨዋታ አድርገው በኬንያ ሁለት ለዜሮ ተረተዋል። ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ዛሬ ከሽንፈታቸው ማግስት ወሳኝ ፍልሚያ የሚጠብቃቸው ይሆናል። በኬኒያ አቻቸው በሁለት ደቂቃ ውስጥ ሁለት ግብ አስተናግደው የተሸነፉት ሉሲዎቹ ከምድባቸው ለማለፍ ዛሬ ከዩጋንዳ ጋር የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ይጠብቃቸዋል። አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው በዛሬው ጨዋታ መጠነኛ የተጫዋች ለውጥ እንደሚኖር ጠቅሰው፤ የሚችሉትን ሁሉ ሜዳላይ ለማድረግ ተጫዋቾቹ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ‹‹ተጫዋቾቹ ምንም የሚፈረድባቸው ነገር የለም፣ በርካታ ወራት አርፈው ነው የመጡት፣ ክለቦቻችን ዕረፍት ላይ ስለነበሩ የዝግጅት ጊዜ አልነበራቸውም፣ የኔ እና የተጫዋቾቼ ህልማችን በ2020 ብሔራዊ ቡድኑን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ ነው፣ ይህ ውድድር ደግሞ እንደ ዝግጅት ይጠቅመናል፣ ብናሸንፍም ጮቤ አንረግጥም ምክንያቱም አልሠራንም፣ ነገር ግን ያለንን ጊዜ በመጠቀም ህልማችንን እናሳካለን፣ ይህን ማድረግ ካልቻልን መጠየቅ ያለብኝ እኔ እንጂ ተጫዋቾቼ አይደሉም፣ ዝግጅት ሳይሠሩ ውጤት መጠበቅ እንጀራ ሳያዘጋጁ ወጥ አቅርቦ ምሳ እንብላ እንደማለት ነው፣ ስለዚህ ከዚህ ውድድር ብዙ እንማራለን ለአፍሪካ ዋንጫው ሠርተን ለማለፍ እንጥራለን›› በማለት ለሽንፈቱ ኃላፊነቱን እንደወሰዱ በስፍራው ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። በታንዛኒያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የሴቶች ሴካፋ ዋንጫ ኢትዮጵያ ከኬንያ፣ ዩጋንዳና ጅቡቲ ጋር መደልደሏ ይታወቃል። ሉሲዎቹ የመጀመሪያውን ጨዋታ መሸነፋቸውን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ያላቸውን ተስፋ የሚያለመልሙት ዛሬ ከዩጋንዳ ጋር በሚኖራቸው ወሳኝ ፍልሚያ ይሆናል። ይህን ጨዋታ በሽንፈት ደምድመው በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ጅቡቲን ቢያሸንፉ እንኳን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋ አይኖራቸውም። የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ የግድ ቢሆንም በአቻ ውጤት መለያየት ከቻሉ የሌሎቹን ውጤት ጠብቀው ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ ተስፋቸውን ሊያለመልሙ ይገደዳሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በ2021 በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን የመጀመሪያ ጨዋታ ከማዳጋስካር ጋር ከሜዳው ውጪ አድርጎ በ 1 ለ 0 ውጤት መሸነፉ ይታወቃል።ዋልያዎቹ በጨዋታው የታዩባቸውን በተለይም ኳስን ከመረብ የሚያገናኝ ጨራሽ አጥቂ ክፍተቶች ለመሸፈን አልጣኝ አብርሃም መብራቱ በውጭ ያሉ ተውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾችን በቀጣይ ጨዋታዎች ለማካተት እንዳሰቡ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። አሰልጣኙ ‹‹በዛሬው ጨዋታ ቡድናችን ከሜዳ ውጪ ከዕረፍት በፊት በመከላከል ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ አድርጓል፣ ኳስን በመቆጣጠር ከዕረፍት መልስ በማጥቃት ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴም አድርጓል›› ብለዋል።የማዳጋስካር ቡድን ከወራት በፊት በአፍሪካ ዋንጫ እነ ናይጄራያንና ኮንጎን አሸንፎ ግማሽ ፍፃሜ የደረሰ መሆኑን ያስታወሱት አሰልጣኙ ቡድናቸው 1ለ0 መሸነፉ መጥፎ የሚባል ውጤት እንዳልሆነ አብራርተዋል። በዋልያዎቹ ስብስብ አብዛኞቹ ተጫዋቾች አዲስ መሆናቸውን የጠቆሙት አሰልጣኝ አብረሃም በቀጣዩ ጨዋታ ክፍተቶችን እንደሚያርሙ ተናግረዋል። ‹‹የቡድኑን የአጥቂ ችግር ለመቅረፍ ከአገር ውስጥም ወይም ከውጭ ያሉትን በቀጣይ ጨዋታ እናካትታለን›› ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ዋልያዎቹ ከማዳጋስካሩ ጨዋታ ሽንፈት በኋላ ጊዜ ሳያጠፉ ወደ ባህርዳር ያቀኑ ሲሆን ዛሬ ጠንካራዋን ኮትዲቯር የሚገጥሙ ይሆናል። ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫው ማጣሪያ ከኮትዲቯር፣ማዳጋስካርና ኒጀር ጋር መደልደሏ ይታወቃል። ኮትዲቯር ቅዳሜ ዕለት ከሜዳዋ ውጪ ኒጀርን ገጥማ አንድ ለዜሮ በሆነ ውጤት ማሸነፏ ይታወሳል። አዲስ ዘመን ህዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ምቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=22770
84a739e96d82e1c15aad0069d9a30dcf
9a8011dfb402f8a8d44870896ce6e824
ለተሰንበት ግደይ የዓለም ክብረወሰን አሻሻለች
ስፖርት
ኢትዮጵያዊቷ ወጣት አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አስራ አምስት ኪሎ ሜትር ክብረወሰንን መጨበጥ ችላለች፡፡ ለተሰንበት ከትናንት በስቲያ በኔዘርላንድስ ‹ሰቨን ሂልስ ረን› በተባለ የጎዳና ላይ ውድድር ክብረወሰኑን ያሻሻለች ሲሆን ውድድሩን ያጠናቀቀችበት ሰዓት 44፡20 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ከወር በፊት በዶሃው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በአስር ሺ ሜትር አስደናቂ ብቃት በማሳየት የብር ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለችው ለተሰንበት በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በወጣቶች ምድብ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ቻምፒዮን እንደነበረች ይታወሳል፡፡ ለተሰንበት የዓለም የአስራ አምስት ኪሎ ሜትር ክብረወሰንን ከአንድ ደቂቃ በላይ ያሻሻለች ሲሆን ይህ ክብረወሰን ከሁለት ዓመት በፊት በኬንያዊቷ ጆይስሊን ጂፕኮስጌ 45፡37 በሆነ ሰዓት በፓራጓይ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ የተመዘገበ መሆኑን የዓለም አትሌቲክስ ድረ ገፅ ዘገባ አመልክቷል፡፡ የሃያ አንድ ዓመቷ አትሌት ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላ ‹‹ገና ለውድድሩ ዝግጅት ሳደርግ በጥሩ አቋም ላይ እንዳለሁ አውቅ ነበር፣ በውድድሩም ላይ ምቾት ተሰምቶኛል፣ እውነቱን ለመናገር የቀድሞውን ክብረወሰን በምን ያህል ሰዓት እንዳሻሻልኩኝ ለማየት ጓጉቼ ነበር›› በማለት የዓለም ክብረወሰን ስለመጨበጧ እርግጠኛ እንደነበረች ተናግራለች፡፡ ለተሰንበት ውድድሩን ከማሸነፏና የዓለም ክብረወሰን ከማሻሻሏ ባሻገር የመጨረሻዎቹን አስር ኪሎ ሜትሮች የሮጠችበት ፍጥነት የአትሌቲክሱን ቤተሰብ ያስደነቀና ወደ ፊት ትልቅ ተስፋ እንዲጣልባት ያደረገ ነበር፡፡ ለተሰንበት የመጨረሻዎቹን አስር ኪሎ ሜትሮች 29፡12 በሆነ ሰዓት ያገባደደች ሲሆን ይህም አልማዝ አያና በ2016 ሪዮ ኦሊምፒክ የአስር ሺ ሜርት የዓለም ክብረወሰንን ስታሻሽል ካስመዘገበችው 29፡17፡45 ሰዓት የፈጠነ ነው፡፡ የአስራ አምስት ኪሎ ሜትር የዓለም ክብረወሰን ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ 2009 ላይ በተመሳሳይ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ተሻሽሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ጥሩነሽ በወቅቱ የርቀቱን ክብረወሰን 46፡28 በሆነ ሰዓት ስታሻሽል ከእሷ በፊት ክብረወሰኑ 46፡55 በሆነ ሰዓት በጃፓናዊቷ ካዮኮ ፉኩሺ የተያዘ ነበር፡፡ ጥሩነሽ ይህን ክብረወሰን ባስመዘገበችበት ውድድር በወንዶች ባለቤቷ አትሌት ስለሺ ስህን ከዩጋንዳዊው ኒኮላስ ኪፕሮኖ ጋር እስከ መጨረሻ አንገት ለአንገት ተናንቆ በተመሳሳይ ሰዓት በመግባት አሸናፊ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ለተሰንበት በነገሠችበት የዘንድሮው ዓመት ውድድር በስቶች ኬንያዊቷ ኢቫሊን ቺርቺር 46፡32 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ ሌላኛዋ ኬንያዊት ኢቫ ቺሮኖ 48፡14 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ፈፅማለች፡፡ በወንዶች መካከል የተካሄደውን ውድድር የሃያ ሦስት ዓመቱ ዩጋንዳዊ ስቲፈን ኪሳ 41፡49 በሆነ ሰዓት ማሸነፍ ችሏል፡፡ እሱን ተከትለው ኬንያውያኑ ኤድዊን ኪፕቶ በሁለት ሰከንድ ዘግይቶ ሁለተኛ፣ ሞሰስ ኮይች በ42፡05 ሰዓት ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡አትሌት ለተሰንበት ግደይ ክብረወሰን ከማሻሻል ባለፈ ያሳየችው አስደናቂ አቋም ተስፋ እንዲጣልባት አድርጓል፣አዲስ ዘመን ህዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ምቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=22774
ba3e4abec2bd93ec8706990178b64f4b
911397b32dad73a22118d324d3254c9e
ዋልያዎች ከዝሆኖች ገዝፈው የታዩበት ምሽት
ስፖርት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን(ዋልያዎቹ) ከኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን(ዝሆኖቹ) ጋር ለ2021 የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድባቸውን ሁለተኛ ጨዋታ ትናንት 10 ሰዓት ላይ ከማድረጋቸው በፊት እንደ ቅፅል ስማቸው ፍፁም የተለያየ የእግር ኳስ አቅምና ደረጃ እንዳላቸው የዓለም ሕዝብ ያውቃል፡፡ ዋልያዎቹ በዓለም ካላቸው የእግር ኳስ ደረጃና ዝና አኳያ ዝሆኖቹ እንደ ስማቸው የገዘፈ ታሪክ ይዘው በዋልያዎቹ መንደር ሲከትሙ ጨዋታውን በቀላሉ እንደሚያሸንፉ እርግጠኞች ነበሩ:: ለዚህም ዝሆኖቹ ዋልያዎቹን ባህርዳር ላይ ለመግጠም በቀጥታ ከአገራቸው እንደመጡ ምንም አይነት ልምምድ ሳይሠሩ ወደ ሜዳ በመግባት ያሳዩት ንቀት ማሳያ ነበር፡፡ እርግጥ ነው ዋልያዎቹ የዓለም ዋንጫና የቻን ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ከዝሆኖቹ ያነሱ ቡድኖችን እንኳን ማሸነፍ እየተሳናቸው ተደጋጋሚ ሽንፈት እያስተናገዱ መምጣታቸው እንዲናቁ አድርጓቸዋል፡ ፡ ባለፈው ቅዳሜም በዚሁ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድቡን የመጀመሪያ ጨዋታ ከሜዳቸው ውጪ አድርገው በማዳጋስካር 1ለ0 በመሸነፋቸው ደጋፊያቸው ሳይቀር ከዝሆኖቹ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ተስፋ ሊጥልባቸው አይችልም፡፡ እግር ኳስ ግን እንዲህ አይደለም:: ያልተጠበቀ ውጤት ማስተናገድ፣ ያሰቡት ቀርቶ ያላሰቡት ነገር መከሰት እግር ኳስን በዓለም ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ ካደረጉት ምክኒያቶች ዋነኛው ነው፡፡ በትናንቱ የዋልያዎቹና የዝሆኖቹ ጨዋታም የታየው ነገር ተቃራኒ ነው፡፡ እንደ ስማቸው ግዙፍ የእግር ኳስ ታሪክ ተሸክመው ወደ ሜዳ የገቡት ዝሆኖቹ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴም ይሁን በውጤት ረገድ ከዋልያዎቹ አንስው ተገኝተዋል፡፡ በታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ በርካታ ከዋክብት ተጫዋቾችን ይዘው የመጡት ዝሆኖቹ ገና በሦስተኛው ደቂቃ ከቆመ ኳስ ግብ አስቆጥረው መምራት ሲጀምሩ በሙሉው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ዋልያዎቹ በምን ያህል የግብ ልዩነት እንደሚሸነፉ ያሰሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖችም ሆኑ ክለቦች ሽንፈት አስተናግደው የማያውቁበት ገዳሙ የባህርዳር ስቴድየም ትናንትም ዋልያዎቹን አላሳፈራቸውም፡፡ ሱራፌል ዳኛቸው 15ኛው ደቂቃ ላይ በዝሆኖቹ የግብ ክልል አካባቢ ያገኛት ቅጣት ምት ተጨርፋ ከመረቡ ጋር በመዋሃድ ዋልያዎቹን አቻ አድርጋለች፡፡ አሰልጣኝ አብረሃም መብራቱ ዋልያዎቹን መምራት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የተሻለ የቡድን እንቅስቃሴና ውህደት ማሳየት የቻሉት ዋልያዎቹ ዝሆኖቹን ለማንበርከክ መጠበቅ የነበረባቸው እስከ 24ኛው ደቂቃ ድረስ ብቻ ነበር፡፡ ጨዋታ አቀጣጣዩ ሽመልስ በቀለ በግሩም እንቅስቃሴ ኳስና መረብን አገናኝቶ ዋልያዎቹ ገና የጨዋታው አንድ አራተኛ ክፍለ ጊዜ ሳይጋመስ ከመመራት ወደ መሪነት አሸጋግሯቸዋል፡፡ በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜም ዋልያዎቹ ዝሆኖቹን ቁልቁል እየተመለከቱ በድንቅ እንቅስቃሴና መስዋዕትነት ውጤቱን አስጠብቀው መውጣት ችለዋል፡፡ አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ በዋሊያዎቹ አስራ ስምንት ወራት የኃላፊነት ቆይታቸው አስራ አራት ጨዋታዎችን አድርገዋል፡፡ እንደትናንቱ አይነት ጣፋጭ ድል አጣጥመው ግን አያውቁም፡፡ አሰልጣኙ ከእነዚህ አስራ አራት ጨዋታዎች መካከል የትናንቱን ጨምሮ አራቱን በአሸናፊነት ሲወጡ፣ አምስቱን በአቻ ውጤት ደምድመዋል፡፡ ቀሪዎቹን አምስት ጨዋታዎች ደግሞ ሽንፈት አስተናግደውባቸዋል፡፡ ከዚህም በላይ ዋልያዎቹ ዝሆኖቹን ማንበርከካቸው እየተዳፈነ በመጣው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ አዲስ ተስፋን የሚያጭር ክስተት ሆኗል፡፡ ምክኒያቱም ያንበረከኩት ኮትዲቯርን ነው፡፡ የዚህ ድል ትጉሙ ከኳስም በላይ የሚሻገር ስለመሆኑ መዘርዘር አያስፈልግም፡፡ ዋልያዎቹ ያስመዘገቡትን ያልተጠበቀ ድል ተከትሎ ወደ 2021 የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ተስፋቸው በእጅጉ ለምልሟል፡፡ ዝሆኖቹ ባለፈው ቅዳሜ በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኒጄርን በሜዳዋ አንድ ለምንም ማሸነፋቸውን ተከትሎ በሦስት ነጥብ እየመሩ ነበር፡፡ ዋልያዎቹም በምድቡ ተፎካካሪ የሚያደርጋቸውን ሦስት ነጥብ በእጃቸው አስገብተዋል:: በዚህ ምድብ የሚገኙት ማዳካስካርና ኒጄር ትናንት ምሽት ሁለተኛ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ ውጤታቸው ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ሰዓት ድረስ አልደረሰንም:: ይሁን እንጂ ማዳጋስካር በቅዳሜው ጨዋታ በሜዳዋ ከዋልያዎቹ ያገኘችው ሦስት ነጥብ በምሽቱ ጨዋታ ሽንፈት ቢገጥማት እንኳን በምድቡ እኩል ተፎካካሪ የመሆን እድል እንዳላት ግልፅ ነው፡፡ አዲስ ዘመን ኅዳር 10/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=22835
170de297b9a4e991684dc9fdfb0e33ba
81c3f5160a1771269bd7d585568b34cc
‹‹ ወንጀል ፈጽመው ወደጎረቤት ሀገራት የሸሹ የጁንታው አባላት የሰላም ጠንቅ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ሥራ መሠራት አለበት››-ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛ የትግራይ ክልል ተወካይ
ሀገር አቀፍ ዜና
ማህሌት አብዱል አዲስ አበባ፡- በግጭቱ ወቅት ወንጀል የፈፀሙና ሸሽተው ወደጎረቤት ሃገራት የሄዱ ወንጀለኞችና የጁንታው አባላት ተጠናክረው በመምጣት የአገር ሰላም ጠንቅ እንዳይሆኑ ከወዲሁ መሥራት እንደሚያስፈልግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛ የትግራይ ክልል ተወካይ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ አስታወቁ። ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በማይካድራም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ላይ በንፁሐን ላይ ጭፍጨፋ ፈፅመው ያመለጡ አንዳንድ የሳምሪ ቡድኖችም ሆኑ ሌሎች የጁንታው አባላት ተጠናክረው ተጨማሪ የሰላም ጠንቅ ከመሆናቸው በፊት መንግሥትና ህዝቡ በመተባበር የጥፋት ኃይሉን በማደን ሊይዙና በህግ ተጠያቂ ሊያደርጉ ይገባል። ‹‹እነዚህ ወንጀለኞች ሸሽተው ሄደው ተጠናክረው በመመለስ የሰላም ጠንቅ እንዳይሆኑ ከጎረቤት አገራት ጋር ባለን ጥሩ ዲፕሎማሲ ግንኙነት በመፍጠር በትብብር መሥራትና ጉዳዩንም መልክ ማስያዝ ይገባል›› ያሉት ወይዘሮ ያየሽ፤ በተለይም የአገሪቱን ሰላም ከማይሹ የውጭ ኃይሎችጋር ተቀናጅተው ችግር ከማስከተላቸው በፊት በከፍተኛ ጥንቃቄ መሠራት እንደሚገባ አሳስበዋል። በሌላም በኩል ጦርነቱን ሸሽተው የተሰደዱ ንፁሐንን ለይቶ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባዉ የተናገሩት ወይዘሮ ያየሽሽ ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ ትልቅ ስጋት ነው ያለኝ። መደበላለቅ የለበትም፤ የእውነት ንፁሐን የሆኑትን መለየትና ወደ አገራቸው እንዲገቡ ማድረግ ያስፈልጋል›› ብለዋል። ‹‹ጦርነት ሁልጊዜም ቢሆን አስፈሪ በመሆኑ ጦርነትን ሸሽተው የሄዱ ዜጎቻችንን በተቻለ መጠን አሳምነን መመለስ አለብን›› ያሉት ወይዘሮ ያየሽ፤ ይህም ጠላት ያልሆነውን ወደ ጠላትንት እንዳይቀር የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል። የጁንታው አመራሮች ህዝቡን “እከሌ መጣብህ፣ ተከበብክ” እያሉ ሲያሳምኑት እንደኖሩት ሁሉ በተሰደዱበት አገርም ተመሳሳይ ሊሠሩ ስለሚችሉ ይህ መልሶ የአገር ሰላም ጠንቅ እንዳይሆን ለይቶ ግንዛቤ መስጠትና መመለስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 10/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37619
314735bbbf3d25aa319ebdccf89aceb8
ab446527b425e60670a5afe4046312f1
“አሁን ያለችው ትግራይ 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት ናት ” -አቶ ሊላይ ኃይለማርያም፣ የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ከፍተኛ አስተዳደር
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲሱ ገረመው አዲስ አበባ፡- አሁን ላይ ያለችው ትግራይ የአምባገነኑ ጁንታ እንቅስቃሴ እምብዛም የማይታይበት 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት መሆኗን የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ተናገሩ። የህወሓት ጁንታ ከአሁን በኋላ እንደማይመለስና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ገሀነም መውረዱን በመገንዘብም ደጋፊዎችና አባሎቻቸው ወደ ህዝባቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲመሰርቱና በጋራ አገር ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ሊላይ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ አሁን ትግራይ በአጠቃላይ 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት ሆናለች። የአምባገነኑ ጁንታ እንቅስቃሴ የሚታይበት ሁኔታ ብዙም የለም። አውሮፕላንን ጨምሮ ትራንስፖርት ከጫፍ እስከ ጫፍ ይንቀሳቀሳል። መብራት እስከ አዲግራት እየሠራ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ዓደዋና አክሱም ይገባል። አብዛኛው ከተሞችም መብራት ያገኛሉ። የውሃና የኔትዎርክ አገልግሎትም እየተዳረሱ ነው። በሚቀጥለው ሳምንትም የባንክ አገልግሎት በሰፊው ይጀመራል። መቀሌም በጥሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው ያለችው። ወደ ቀደመ መልኳ ተቀይራለች።የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንጻር መቶ በመቶ እንዲከፈቱ ተደርገዋል። በሰለማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ሁሉም ሰው ወደ ሥራ ገበታው ገብቷል። ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሥራ ያልገቡ ሠራተኞች ላይ በአገሪቷ ህግ መሠረት ዕርምጃ ይወሰዳል። ይሄ ደግሞ የተሾሙት ካቢኔዎች ኃላፊነት ነው። ትጥቅን የማስፈታት እንቅስቃሴውም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል። ታጥቆ የነበረው ትጥቅ በየቦታው እየተፈታ ነው።ትጥቅን በማስፈታት ረገድ “ከሞላ ጎደል ህዝቡ ሳንጠይቀው ነው እየመጣ ትጥቅ እያስረከበ ያለው” ያሉት አቶ ሊላይ፤ የህወሓት ጁንታ ከጩቤ ጀምሮ እስከ ከባድ ብረቶች ከ200 ሺ በላይ ትጥቅ ያስታጠቀ ቢሆንም እነዚህ እየተመለሱ መሆኑን አስረድተዋል። አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ታጣቂ ያለበት ክልል እንደመሆኑ ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱ ቀላል እንቅስቃሴ እንዳልሆነና በአንድ ቀን የሚመለስ ሳይሆን ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን በመጠቆምም፤ ህዝቡ ግን በፈቃደኝነት እየመለሰ መሆኑንም ተናግረዋል። ይህ ተግባር ቀጣይነት ያለው መሆኑን እና በዚህ ረገድ መከላከያው እየረዳን ስለሆነ መከላከያ ባለበት ቦታ እየሄዱ ቀበሌ በተመሠረተበት በየወረዳው፣ በየዞኑ በየከተማው አጥጋቢ በሆነ መልኩ እየመለሱ መሆኑንም አብራርተዋል። እንደ አቶ ሊላይ ማብራሪያ፤ ከሰብዓዊ ድጋፍና የመድኃኒት አቅርቦት ጋር ተያይዞ በተለይ በጤና አገልግሎት ባለው ሂደት የፌዴራል መንግሥት በአቅሙ እየረዳ ነው። በቀጣይም ብዙ የሚፈለግ ነገር አለ። ምክንያቱም ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በጁንታው ተዘርፈዋል። ጁንታው ሲሸሽ ዘርፎ ነው የሄደው። በዚህ ረገድ ብዙ መሥራት ያለብን ነገሮች አሉ። ከዚህ ባለፈ ግን የሰብዓዊ ድጋፉም እየተከፋፈለ ሲሆን፤ በቀጣይ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት በተቀላጠፈና በተጠና መንገድ እየተሠራ ነው። ይሄን ተግባር እንዲፈጽም ኃላፊነት የተሰጠው ጊዜያዊ አስተዳደርም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዘመናዊ አመለካከት ባላቸው ሰዎች ጋር በመሆን የተዋቀረ ሲሆን፤ የአረና፣ የትዴፓና የብልጽግና ፓርቲዎች በዚህ ውስጥ ከተካተቱት መካከል ናቸው። የፓርቲ አባል ያልሆኑ ግለሰቦችም አሉ። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዕድሜም ስድስት ወር እንደመሆኑ፤ በዚህ ስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ህግና ስርዓትን በማስከበር ትግራይን ማረጋጋት ዋና ተግባሩ ይሆናል። ስድስት ወሩ ካለቀ በኋላ ምርጫ ማካሄድ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረው ምርጫ እንዲያደርጉም ይደረጋል። በዚህም ከቀበሌና ወረዳ ጀምሮ ባለው ሂደት ነፃ ምርጫ ይደረጋል። ሰው የፈለገውን እንዲመርጥ ይደረጋል። እንደ ከዚህ ቀደም በካድሬ የሚመራ ሳይሆን በአገር ሽማግሌ እንዲመራ ነው የሚፈለገው። ነፃ በሆነ መንገድ ሰው በወንዙ ልጅ ይመረጣል፤ ይዳኛልም። የጊዜያዊ አስተዳደሩም አቋም ይሄው ነው። ማንም የፖለቲካ ፓርቲ የፈለገውን አመለካከት ይዞ በነፃ በትግራይ በሠላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ ይችላል። ህልማችን ክልሉ የዴሞክራሲ ምልክት የሠላም ምልክት የልማት ምልክት እንዲሆን ስለምንፈልግ ምርጫው ፍጹም ሠላማዊ፣ ህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ይካሄዳል፤ በማለት አቶ ሊላይ ገልጸዋል።በመጨረሻም “የኢትዮጵያ ህዝብ ለትግራይ ህዝብ የሚያደርገውን ትብብር ማጠናከር አለበት። በዚህም አጋጣሚ የህወሓት ጁንታ ከአሁን በኋላ እንደማይመለስና ፍጹም ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ገሀነም እሳት መውረዱን ለደጋፊዎችና ለአባሎቻቸው እየገለጽኩኝ፤ ወደ ህዝባቸው ተመልሰውና ተቀላቅለው ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲመሠርቱ እና እነርሱ ላለፉት 46 ዓመታት ያወደሙትን አገር እንደገና በጋራ እንድንገነባ ጥሪ አቀርባለሁ” በማለት አቶ ሊላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 10/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37618
f440859b65252ea34d1a208f1088a179
605e6f5ae9e0f1d520641928b1d0bbec
በሦስት አገራት 800 ሺ ሕፃናትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የትምህርት ፕሮጀክት ሊተገበር ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
አስመረት ብስራት አዲስ አበባ፡- በሦስት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ተግባራዊ የሚደረግ ከሦሰት እስከ አስራ ሁለት ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 800 ሺህ ሕፃናትን በጨወታ መልክ ለማስተማር የሚያስችል ለአምስት ዓመታተ ተፈፃሚ የሚሆን ፕሮጀከት ስምምነት ተፈረመ።የፕሮጀክቱ መክፈቻ የፊርማ ስነ ስርዓት ትናንት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በተከናወነበት ወቅት የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ማረቲን ኦምኩባ እንዳስታወቁት፤ ፕለይ ማተር በሚል ስያሜ በኢትዮጵያ፥ በታንዛኒያና በዩጋንዳ የሚገኙ በስደተኛ ካምፖች ውስጥ የሚኖሩ ሕፃናት ፤ ብሎም በስደተኛ ካምፖች አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ልጆችን ያጠቃለለ እየተጫወቱ የሚማሩበት ዓይነት የትምህርት ስርዓት ለማዳረስ የሚያስችል ፕሮጀክት ነው።ይህ ፕሮጀክት ከሊጎ ፋውንዴሽን በተገኘ መቶ ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተፈፃሚ የሚደረግ መሆኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ በሀገራችን በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምቤላ በሶማሌና በትግራይ ክልሎች ተፈፃሚ እንደሚሆንም ተናገረዋል።ሕፃናት በባህሪያቸው ከቦታ ቦታ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ፤ የተለያዩ የጦረነትና በችግር ሁኔታ ውስጥ ሲቆዩ የተለያዩ የስነልቦና ጫናዎች ሊገጥሟቸው እንደሚችሉ የተናገሩ ሲሆን፤ በቅድመ መደበኛና በመደበኛ ደረጃ የሚገኙ ሕፃናት በስነልቦና፤ በጠቅላላ እውቀት በአዕምሯዊና በአካላዊ ዕድገት ሊደግፋቸው የሚችል የትምህረት ስርዓት መሆኑ ተጠቁማል።እንደ ዳይሬክተር ማረቲን ገለፃ፤ ሕፃናትን በተለያዩ የጨዋታ መልኮች በማስተማር አወንታዊ ተፅእኖዎቹ በጣም ከፍተኛ መሆኑን አስረድተው፤ በመማር ማስተማር ስርዓቱ ውስጥ ቤተሰቦቻቸው፤ የተለያዩ በቅርበት የሚገኙ አካላትና በስደተኛ ካምፑ ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ አገልገሎት ሰጪዎች ተሰታፊ የሚሆኑበት ነው።የፕሮጀክቱ መጨረሻ ላይ እንደ ግብ የተቀመጠው በመማር ማስተማሩ ልጆቹ የተሻለ የትምህርት አቅም መገንባታቸው ታይቶ እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ በመቀያየር ውጤት ላይ መድረስ መሆኑን ጠቁመዋል። በፕሮጀክቱ መክፈቻ እና የፊርማ ሥነስርዓት ላይ የስደተኛ ጉዳዮች ተወካይ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር የተወከሉ ግለሰብና፣ በፕሮጀክቱ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 10/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37629
1e90d47f2fe241729cdf2e7449f1f701
f7a1137ec576488975808084b5e38675
በዘንድሮ የመስኖ ልማት ከቆላማ አካባቢዎች በተጨማሪ በሌሎች ክልሎች ለማስፋት መታቀዱ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
እፀገነት አክሊሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት በቆላማ አካባቢዎች ላይ ስንዴን በመስኖ በማልማት የተገኘውን ውጤት በመቀመር ዘንድሮ ደግሞ ወደሌሎች ክልሎች በማስፋት ውጤታማ ሥራዎችን ለመሥራት መታቀዱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። በግብርና ሚኒስቴር የአነስተኛ መስኖ ልማት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ አወል በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት ባለፉት ዓመታት በተለይም በቆላማ አካባቢዎች ላይ ስንዴን በመስኖ ለማልማት የተጀመረው ሥራ እንደ ጠቅላላ መልካምና ጥሩ ውጤት የታየበት ነበር፤ በዚህም በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ላይ የተሠሩት ሥራዎች ብዙ ጥረት የጠየቁ ቢሆንም በውጤት ደረጃ ግን ሲመዘኑ አበረታች ናቸው።እንደ አቶ ኤልያስ ገለጻ ዘንድሮ ደግሞ ያለፉትን ጊዜያት ተሞክሮ በመቀመርና ከቆላማ አካባቢዎች በተጨማሪ በአማራ። ኦሮሚያና ደቡብ ላይ መስኖን በመጠቀም የተለያዩ ሰብሎችን ለማምረት ታቅዷል። በዚህም መሰረት ክልሎች የየራሳቸውን እቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አብራርትዋል። በየዓመቱ የመኸሩ የግብርና ሥራ እንደተጠናቀቀ የሚገባው ወደመስኖ ሥራ ነው ያሉት አቶ ኤልያስ ፤ በያዝነው ዓመትም ይህንኑ አቅጣጫ በመከተል ለአመራሩ የግንዛቤ ማስፋት እስከ ወረዳ ድረስ ላሉ ባለሙያዎች ደግሞ ስልጠናዎችን በመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አምና የመስኖ ሥራውን ለማስፋፋት በአብዛኞቹ ክልሎች ላይ ከከርሰ ምድር ውሃን ለመሳብ የሚያገለግሉ የውሃ መሳቢያዎች (ፓምፖች) በየክልሎቹ የማከፋፈል ሥራ ተከናውኗል ያሉት አቶ ኤልያስ፤ አሁን ላይ በብልሽት የቆሙም ካሉ ተጠግነው ሙሉ በሙሉ ወደሥራ እንዲገቡና የግብርና ሥራውን እንዲያቀላጥፉ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል። በሌላ በኩልም በግብርና ሚኒስቴር የሚተዳደሩ የመስኖ አውታሮች በተለያዩ ፕሮጀክቶችና በመንግሥት በጀት የሚሠሩ እንዳሉ የገለጹት አቶ ኤልያስ እነዚህም አምና የተጀመሩ በመሆኑ አሁን በተጠናከረ መልኩ ተጠናቀው ወደ ሥራ መግባት ስላለባቸው ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል። በተመሳሳይም አርሶ አደሩ በራሱና በቤተሰቦቹ ጉልበት እንዲሁም በአቅራቢያው የሚገኙ ቁሳቁሶችን ተጠቅሞ ከከርሰ ምድር ውሃ እያወጣ እንዲሁም በጓሮው የውሃ ማቆር ሥራን እያከናወነ የልማት ሥራውን እንዲያከናውን ሰፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑንም ተናግረዋል። በተለይም በቤተሰብ ደረጃ የተዘጋጁትን ከጥር ወር ጀምሮ ወደሥራ ለማስገባትና ውጤታማ ሥራን ለማከናወን እንደ ግብርና ሚኒስቴር ዝግጅቱ መጠናቀቁንም አብራርተዋል።የዘንድሮው የመስኖ ሥራ ከወትሮው በተለየ መልክ አምበጣም ኮሮና ቫይረስም በምርት ላይ ያሳደሩትን መጠነኛ ተጽዕኖ ለማለፍ በሚያስችል መልኩ ለመሥራትና ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል ዝግጅት ስለመኖሩም ጠቁመዋል። በዚህ መሰረት በዘንድሮው የመስኖ ልማት ሥራ በሽፋንም በአጠቃላይ በምርትም በኩል ጥሩና አበረታች ለውጦች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ኤልያስ ተናግረዋል። በተለይም በስምጥ ሸለቆ አካባቢ ባሉ ቦታዎች ላይ እንደ ሽንኩርት߹ ቲማቲምና ቃሪያ የመሳሰሉ አትክልቶችን በማምረትና ወደገበያ በማምጣት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ የመስኖ ውሃ መሳቢያ ማሽኖች (ፓምፖች) መሰራጨታቸውንና ይህ ሥራ ደግሞ በግለሰብ ደረጃም እንዲሁም የአካባቢው አርሶ አደሮች ተደራጅተው የሚሠሩት መሆኑን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 10/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37620
f5393d3ace043dcdbd271143d40c3339
2927a11a70c050d67c4269e9273f9a26
የጋራ ሀብት ለጋራ ጥቅም
ሀገር አቀፍ ዜና
ጽጌረዳ ጫንያለው የህወሓት ጁንታ የአገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በጥቂት ተቋማቱ አማካኝነት የግሉ አድርጎት ቆይቷል። ነገር ግን ሲጠቀምበት የቆየው የአገር ሀብት በመሆኑ እነዚህ የታገዱ ተቋማት በመንግሥት ተወርሰው አገርን ተጠቃሚ በሚያደርጉበት መልኩ ሊሠራባቸው እንደሚገባ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚ መምህር ዶክተር አሰፋ አድማሴ እንደተናገሩት፤ ነፃ ገበያ ማለት ዋና መርሁ ሁሉም በእኩል ደረጃ መገበያየት የሚለውን ይይዛል። የማወዳደሪያ ሜዳውም እኩል የሆነ ነው። ነገር ግን የህወሓት ጁንታ የሃገሪቱን ሀብት በመዝረፍ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ በመቆየቱ፤ ገበያውን እኩል መቀላቀል አይፈቀድም ነበር። በዚህም ያለፉት በርካታ ዓመታት እንደ አገር የነበረው ኢኮኖሚ በጥቂቶች የተያዘና ጥቂቶች የሚዘውሩት ነበር። በተለይም ከመንግሥት ጋር የተጣበቁ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች የበላይነትን ያገኙበት ነበር። የመወዳደሪያ መንገዱንም ለሥርዓቱና ለራሱ ተከታዮች ብቻ በማድረግ ሜዳውን አጥብቦት ቆይቷል። ይህ ደግሞ ሀቀኛ የነበሩ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ኩባንያዎችን ከጨዋታ ውጪ አድርጓቸዋል። እንደ ዶክተር አሰፋ ማብራሪያ፤ አሁን ታገዱ የተባሉት የጁንታው ኩባንያዎች በተለይ የአገሪቱን ማክሮ ኢኮኖሚ ሲዘውሩት ነበር። በነፃ ገበያ ስም ከሥርዓቱ ጋር እጅና ጓንት የነበሩ የተጠቀሙበት ነው። በዚህም ህግ የሚያስፈጽሙ ህጋዊ ተቋማት ሳይቀሩ የዚህ ድርጊት ተሳታፊ ነበሩ። ስርዓቱን ለማስፈጽም የተለያዩ ቢሮክራሲ ተጠቅመው የአገር ሀብትን እንዲበዘበዝ አድርገዋል። ህጋዊ የሆኑ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶችና ግለሰቦችም ከጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ በማድረግ የአገር ሀብት ወደ አንድ ቋት እንዲገባም ሲሠሩ ነበር። የኢኮኖሚ ጉዳይ የህወሓት ጁንታ መወገድ ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ የሚያነሱት ዶክተር አሰፋ፤ ስርዓቱ ሙሉ ለሙሉ ካልተወገደና አሠራሩ በሚባለው የኢኮኖሚ ህግ መመራት ካልቻለ አሁንም ቢሆን ችግሩ አይቀሬ ነው፤ የህወሓት ጁንታ የፈጠረው አስተሳሰብ አሁንም በኢኮኖሚው ሴክተር ላይ ይታያል ብለዋል። እነዚህ የጁንታው የንግድ ተቋማትም አሁን መታገዳቸው እንዳለ ሆኖ ወደ ተግባር ሲገቡም ጥንቃቄ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል። የኢኮኖሚና ፖለቲካ ምሁሩ አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን በበኩላቸው እንደሚናገሩት፤ እንዲህ ዓይነት ችግሮች የሚፈጠሩት የአገሪቱ ልሂቃን የአገሪቱን አንጡራ ሀብት ለታችኛው የህብረተሰብ ክፍል የሚደርስበትን ሁኔታ የሚወስኑበት ተቋማዊ አሠራር ሲጠቀሙ ነው። ይህም ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ይባላል። ስለሆነም የህወሓት ጁንታም የተጠቀመው ይህንን አሠራር ነው። በዚህም እርሱ ለፈቀዳቸውና አጋሬ ናቸው ለሚላቸው ገበያውን አመቻችቷል። ተጠቃሚም አድርጎበታል። ይህ ደግሞ ጥቂቶች በአገሪቱ ሀብት እንዲያዙ ዕድል ሰጥቷቸዋል። የፖለቲካ ስልጣን የያዘ አካል ሀብቱን የመያዝ ዕድሉ የተመቻቸ በመሆኑ ኢኮኖሚውን መዘወሩ እንደማይቀር የሚገልጹት አቶ ሸዋፈራሁ፤ የህወሓት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ስርዓትን ተከታይ እንደመሆኑ ይህ አስተሳሰብ ጠላትና ወዳጅን የመያዝን መርህ የተከተለ እንደሆነ አስረድተዋል። በመሆኑም ልማታዊ ባለሀብት፣ አርሶአደር፣ ወዘተ፣ እያለ ከእርሱ ወገን ያሰለፈውን ሲጠቅም የቀድሞ ናፋቂ ያላቸውን ደግሞ ሲጎዳና ከውድድር ውጪ ሲያደርግ መቆየቱን ተልጸዋል። በዚህ አስተሳሰቡም የአገሪቱን ሀብት የጥቂቶች መፈንጫ ማድረጉን እና ዛሬ ታገዱ የተባሉት ተቋማትም የተፈጠሩት በዚህ አማካኝነት እንደሆነ ይናገራሉ። የህወሓት ጁንታ ደግሞ ለሞራልም ለህግም የማይገዛ በመሆኑ ነው የአገሪቱን ሀብት በጥቂቶች እጅ እንዲገባ ያደረገው የሚሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው፤ በራሱ ብቻ የሚንቀሳቀስ ባለመሆኑ በአጋሮቹ አማካኝነት ጭምር ተቋማትን መስርቶ ታክስ የማይከፍሉ፣ ብድር ወስደው የማይመልሱ አድርጓል። ከዚያም አልፎ የአገሪቱ ሀብት ወደ አገር እንዳይመለስ እንዲባክንና ወደውጪ እንዲወጣ በታትኖታል። ሀገሪቷንም እዳ አሸክሟታል። ከዚያ ያለፈውን ደግሞ በብሔር እየከፋፈለም ሀብቱ በታገዱት ተቋማት አማካኝነት እንዲቀመጥ እንዳደረገም ይገልጻሉ። መፍትሔው የህወሓትን ጁንታ ሲደግፉና በሞኖፖል የአገሪቱን ገበያ ሲይዙ የነበሩ ተቋማት መታገዳቸው አንዱ መሆኑን የሚጠቁሙት ዶክተር አሰፋ፤ የተቋማቱ መታገድ የገበያ ተወዳዳሪነታቸውን ያሳልጣል፤ የእውነተኛ ተቋማትን ተወዳዳሪነትን አብዝቶ ነጋዴውም ሆነ ሸማቹ በእኩል ደረጃ እንዲጠቀም ያስችላል። አገር ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበት ተጽዕኖም ይቀንሳል። ዋጋ የሚተመነው ሜዳ ላይ በሚደረገው ፉክክርና ባለው አገልግሎት ልክ ይሆናል። በተለይ እስከአሁን ቅሬታ የነበረው የመወዳደርና ገበያውን የመቀላቀል ጉዳይን መፍትሔ ይሰጣል፤ ሲሉ አብራርተዋል። እነዚህ ተቋማት በመታገዳቸው ጊዜያዊ የሆኑ ችግሮች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ የሚያነሱት ዶክተር አሰፋ፤ እስከአሁን በነበረው ሥርዓት ገበያውን ጠቅልለው የያዙት ጥቂቶች በመሆናቸው ሌሎች ተወዳዳሪ ግለሰብና ድርጅቶች እንዳይኖሩ ሆናል። ስለዚህም የተወዳዳሪ ድርጅቶች እጥረት ያጋጥማል። ነገር ግን ፍላጎትን በማስፋትና ውድድሮችን ክፍት በማድረግ በአሠራር ይህንን መመለስ እንደሚቻል አስረድተዋል። አቶ ሸዋፈራሁ በበኩላቸው፤ መፍትሔ ነው የሚሉትን ያነሳሉ። የመጀመሪያው የታገዱ ተቋማት በመንግሥት መወረስ አለባቸው። ወደ ግል ተዛውረው ቁጥጥሩ በመንግሥት ሆኖ አገራዊ ዓላማን አንግበው አገልግሎት መስጠት ይኖርባቸዋልም ባይ ናቸው። ምክንያታቸውም ተቋማቱ ከአመሰራረታቸው ጀምሮ የአገር ሀብት የፈሰሰባቸው ናቸው። የባለቤትነት ጉዳይም ሌላው ችግር ይሆናል። ተቋማቱ የተቋቋሙት በኢትዮጵያ ሀብት በመሆኑ የኢትዮጵያውያን እንጂ የአንድ ብሔር አይደሉም። ስለሆነም የባለቤትነት ጥያቄን እንዳያስነሱ ተደርጎ ሊሠራባቸው ይገባል። እነዚህ ተቋማት በኢኮኖሚው ህግ መሪ ሴክተር ሞዴል ሊሆኑም የሚችሉ ናቸውና አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን እንዲመሩና ተጠቃሚነቱ የአገር እንዲሆን ማድረግ ከተቻለ እስከ ዛሬ የነበሩትን ስህተቶች በማረም ጭምር ዕድል እየሰጡ ያስጉዙናል ይላሉ። በተደረጉ አንዳንድ ውሳኔዎች ብቻ ለውጡ ከመጣ በኋላ ከፋይናንስ ተቋማት ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሱት ባንኮችና ኢንሹራንሶች ከፍተኛ ለውጥ አምጥተዋል። ለአብነት አሥራ ስድስቱ የግል ባንኮች ያስመዘገቡት ትርፍ ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል። ከ120 ሚሊዮን ብር ጀምሮ እስከ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር አትርፈዋል። የባንኮቹ ተቀማጭ ገንዘብም ቢሆን እንዲሁ ከ720 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኗል። አጠቃላይ ሀብታቸውም ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ እንደደረሰ የ2010 ሪፖርት ያስረዳል። የኢንሹራንስ ኩባንያዎችም እንዲሁ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ያተረፉበትና በጠቅላላው የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ የሰበሰቡበት ዓመት እንደነበር የኢንዱስትሪው ዓመታዊ የሒሳብ ሪፖርት ያመለክታል። በቀጣይ ሁለቱም ባለሙያዎች እነዚህ ተግባራት ቢፈጸሙ የሃገር ሀብት የግለሰቦች መጠቀሚያ አይሆንም ይላሉ። የመጀመሪያው የዴሞክራሲ ስርዓቱን በይበልጥ በህብረተሰቡ ውስጥ ማስረጽ፤ ያለፈው ስርዓት ብዙ ያስተማረው ነገር አለና ያንን ላለመድገም መሞከር፤ ሁሉም የኢኮኖሚ አጋር በእኩል ዓይን እንዲታይ ማድረግ፤ የገበያ ሁኔታን ክፍት ማድረግ ናቸው። አንዱ ተሸናፊ ሌላው አሸናፊ የሚለውን አስተሳሰብም ማስወገድ፤ አሸናፊ ሆኜ እወጣለሁ የሚለውን አስተሳሰብ መስበር፤ ፍትሐዊ የሆነ የምርት ስርዓት፣ የሀብት አጠቃቀምና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማውጣትና ተግባራዊ ማድረግ ሌላው አማራጭ ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 10/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37634
768bc1e928c421258b9560d4546e56bc
fbbfabafb2c778d2fbe510b89f50771d
ምክር ቤቱ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬታማነት የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዳማ፡- በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ውጤታማ እንዲሆን ድጋፍ እንደሚደረግ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አስታወቁ። በንግድ ስርዓት ማሻሻያ፣ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት አተገባበርና ኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለማድረግ እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ዙሪያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተዘጋጀ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ትላንት በአዳማ ከተማ ተጀምሯል።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በወቅቱ እንደገለጹት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ውጤታማ እንዲሆን በትብብር መሥራት ይገባል። ምክር ቤቱ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ማፅደቁን የገለጹት አፈ ጉባኤው ለስምምነቱ ውጤታማነት ምክር ቤቱ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። በንግድ ዘርፉም ሆነ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ማሻሻያው የታሰበለትን ውጤት እንዲያመጣ ምክር ቤቱ የህግ ማዕቀፎችን ከማሻሻል ጀምሮ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አመላክተዋል። “በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውስጥ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያስተሳስር መሰረተ ልማት ቁልፍ ሚና አለው” ያሉት አፈ ጉባዔው ከኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲና ሌሎች ሀገራት ጋር እየተከናወነ ያለው የመሰረተ ልማት ትስስር ለዚህ አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል። በቀጣይም ህጎችና አሠራሮችን በመፈተሽ ማሻሻያ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አፈጉባኤው ጠቁመዋል። በሀገሪቱ ለተጀመረው የንግድ ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ ከህግ አውጪው ጀምሮ ሁሉም በቅንጅት መሥራት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በመድረኩ የተሳተፉ የምክር ቤቱ አባላት በጉዳዩ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ በማድረግ በቀጣይ ለሚሠሩ ሥራዎች ውጤታማነት ተገቢው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ አፈ ጉባኤው አስታውቀዋል። የሀገሪቱን የንግድ ስርዓት ለማዘመን እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተወካይ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ናቸው።የውጪ ንግድን ማሳደግ፣ የገበያ መዳረሻዎችን ማስፋት፣ ምርትና ምርታማነትን መጨመር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማሳደግና ማስፋፋት ላይ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም አምባሳደር ምስጋኑ ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሳካ፣ ከመጪው ጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ ከሚሆነው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ተጠቃሚ እንድትሆንና የዓለም የንግድ ድርጅት አባል የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል። “ውህደቱ በሚፈጥረው ምቹ ሁኔታ ሀገሪቱ የተሻለ አገልግሎት እንድታገኝና ተወዳዳሪ እንድትሆን ጭምር እየሠሩ መሆናቸውንም አምባሳደር ምስጋኑ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 10/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37635
426f5fe44d52ba8f01e816efa2859f49
864df38eb4c878d290b2b0631b20e1cb
ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2013 ሰላማዊ የመማር ማስተማር እንዲኖር እየሠሩ መሆኑን ገለጹ
ሀገር አቀፍ ዜና
 • የኮቪድ-19 መከላከልን ታሳቢ አድርገው ተመራቂ ተማሪዎችን መቀበላቸውንም ጠቁመዋል ፋንታነሽ ክንዴ አዲስ አበባ፡- ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰትን የፀጥታ ችግር ከግንዛቤ በማስገባት በ2013 የትምህርት ዘመን ሰላማዊ የመማር ማስተማር እንዲኖር የሚያስችሉ ሥራዎችን እየሠሩ መሆኑን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ገለጹ። ዩኒቨርሲቲዎቹ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኮቪድ 19ን ለመከላከል የተቀመጡ ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ተመራቂ ተማሪዎችን መቀበላቸውንም አስታውቀዋል።የየዩኒቨርሲቲዎቹ አመራሮች ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች የሚስተዋል የፀጥታ ችግር በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ እክል ሲፈጥር ቆይቷል። በዚህ ዓመት ግን ያን ዓይነት ችግር እንዳያጋጥምና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲፈጠር እየሠሩ ይገኛል። የወቅቱ ስጋት የሆነው የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ለመከላከልም እየሠሩ ሲሆን፤ ተመራቂ ተማሪዎችን የተቀበሉትም በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠውን መስፈርት በማሟላት ነው።የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ካሣዬ ጉተማ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል በተማሪዎች ምክንያት በዩኒቨርሲቲው የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም፤ በ2013 ዓ.ም ያን ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲፈጠር ለማድረግ ሥራዎችን ሲሠሩ ቆይተዋል። በዩኒቨርሲቲው ከሚሠሩ ሥራዎች በተጓዳኝም በግቢው ውስጥ የፌዴራል ፖሊስ ጥበቃ እያደረገ ይገኛል።እንደ ዶክተር ካሣዬ ገለጻ፤ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የዩኒቨርሲቲውን ጥበቃ እና የፌዴራል ፖሊስን በማቀናጀት ለተማሪዎች የግንዛቤ መፍጠር ሥራ ተሠርቷል። ተማሪዎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች የሚገጥማቸው ትንኮሳ ካለ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል። ቀጣይ ሌሎች ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው በሚመጡበት ወቅትም በየባቻቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ይሠራል።ከፀጥታ ሥራው ባሻገር የኮቪድ-19 ወረርሺኝን መከላከል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ካሣዬ፤ በዚህም በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሟሉ የተቀመጡ መመዘኛዎችን በማሟላትና ይሄንኑ በማስገምገም ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብለው ማስተማር እንደሚችሉ ማረጋገጫ ከተሰጣቸው በኋላ ተማሪዎችን መቀበላቸውን ተናግረዋል። እንደ ዶክተር ካሣዬ ማብራሪያ፤ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገቡ የኮቪድ 19 ምር አድርገው እንዲገቡ፤ ኮቪድን ለመከላከል የሚያግዝ ሳኒታይዘር በዩኒቨርሲቲው ተመርቶ ለተማሪዎች እንዲቀርብ ተደርጓል። ከዚህም ባለፈ በኮቪድ ፕሮቶኮል መሰረት በዩኒቨርሲቲው ያሉ የተማሪዎች ማደሪያ፣ መታጠቢያና የመመገቢያ ቦታዎች ተጎብኝተው ብቁ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ በተለይ ከተማሪዎች ማደሪያ ጋር በተያያዘ በአንድ ዶርም ውስጥ አንድ አንድ ተማሪ ብቻ እንዲመደብ ተደርጓል። በመማሪያ ክፍሎችም ከ20 ያልበለጡ ተማሪዎችንመራ ብቻ በመመደብ የተመራቂ ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሥራውን ሲያከናውን የቆየና ተማሪዎቹም እንደሚመረቁ የጠቆሙት ዶክተር ካሳዬ፤ ቀሪ ተማሪዎችን ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቀበሉ አስታውቀዋል።የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተፈራ አስናቀ በበኩላቸው፤ በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራው በፀጥታ ችግር እንዳይስተጓጎል በማሰብ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም ይሄን ታሳቢ ያደረገ የትምህርትና ስልጠና አማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሚያ መመሪያ የላከ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ 30 አባላት ያሉት አማካሪ ምክር ቤት ተቋቁሟል። አማካሪ ምክር ቤቱ የዞኑ አስተዳዳሪ የሚመሩትና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፀሐፊ የሆኑበት ሲሆን፤ ከከተማው የአገር ሽማግዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ወጣቶች የተካተቱበት ነው።እንደ አቶ ተፈራ ገለጻ፤ አማካሪ ምክር ቤቱ በየጊዜው እየተገናኘ በግቢው ውስጥ ለግጭት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች መኖራቸውን እየገመገመ የመማር ማስተማር ሥራው በትክክል እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው። ምክር ቤቱ በዩኒቨርሲቲው በመገኘት ዝግጅቱ ምን ይመስላል የሚለውን የገመገመ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲውን ከሚጠብቁ ፌዴራል ፖሊሶችና የግቢው ጥበቃዎች ጋር በመሆን የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በምግብ አቅርቦት፣ በቤተመጽሐፍ በተለይም ደግሞ ከመብራትና ውሃ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮች ሲኖሩ ያንን መነሻ አድርገው ለግጭትና ለሁከት የሚዳርግ ነገር ሲፈጠር እንደነበር ያስታወሱት አቶ ተፈራ፤ ይህንን ለመፍታት ዩኒቨርሲቲው የራሱ የሆነ የውሃ መስመር እንዲኖረው መደረጉን እና የመብራት መቆራረጥ በሚኖርበት ጊዜም ጀነሬተር ማዘጋጀቱን ተናግረዋል። ከዚህ ባሻገር በዩኒቨርሲተው ዙሪያ የንግድ ቤቶች መኖራቸውንና በእነዚህ ቤቶች ደግሞ መጠጥ እና ሌሎች አደንዛዥ እጾች ሽያጭ እየተበራከተ እንደመሆኑ፤ እንዲህ ዓይነት ግጭቶች እንዲባባሱ በማድረግ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ችግር ለማስወገድም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።በጸጥታ ሥራው በተጓዳኝ የኮቪድ 19 መከላከል ሥራ ላይ ትኩረት አድርገው እየሠሩ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተፈራ፤ የመማር ማስተማር ሥራው ኮቪድ 19ኝን በመከላከል እንዲቀጥል በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑን ተናግረዋል። ኮቪድን ለመከላከል በተዘጋጀው ፕሮቶኮል መሰረት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለጹት አቶ ተፈራ፤ ሳኒታይዘር በግቢው ውስጥ በማምረት ለተማሪዎችና ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ እንዲቀርብ ተደርጓል። በዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች የተዘጋጀ ማስክም ተሰራጭቷል። ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ መታጠቢያ በየቦታው መቀመጡንም ተናግረዋል። እንደ አቶ ተፈራ ገለጻ፤ ከዚህ በፊት በአንድ ዶርም ውስጥ ስድስት ተማሪዎች ይመደቡ ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ሁለት ተማሪዎች ብቻ እንዲመደቡ ተደርጓል። በመማሪያ ክፍሎችም ሃያ አምስት እስከ ሠላሳ ተማሪዎች ብቻ እንዲማሩ በዩኒቨርሲቲው ሰኔት ተወስኗል። በቤተ መጽሐፍት እና በመመገቢያ አዳራሾችም አስፈላጊውን እርቀት ጠብቀው እንዲስተናገዱ ለማድረግ እየተሠራ ነው። ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ የኮቪድ 19 ምርመራ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ጠቅሰው፤ በሂደት ችግር ቢፈጠር እንኳን በግቢው ውስጥ ምርመራ እንደሚካሄድ ገልጸዋል። ይህንን ታሳቢ በማድረግም የለይቶ ማቆያ ቦታዎች ተዘጋጅተዋል። በኮቪድ መከላከል ፕሮቶኮል ዙሪያ ከተማሪዎች ጋር ውይይት መደረጉን እና ከተማሪዎች ጋር ቅርብ ግንኙነት ላላቸው ሠራተኞች የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ መሠራቱንም አስረድተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 10/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37627
c776db9ef0f7066ece305a5805e313ea
c16d7c0fc24e820e65b83e26cdb260b0
ከሀገራዊ የልማት እቅዱ ጎን ለጎን የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር እውነተኛ ዕድገት ማምጣት እንደሚቻል ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
ፍሬህይወት አወቀ አዲስ አበባ፡- ከ10 ዓመቱ ሀገራዊ የልማት እቅድ ጎን ለጎን የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ እውነተኛ ዕድገት ማምጣት እንደሚቻል ተጠቆመ።በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ዶክተር ሞላ ዓለማየሁ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር በአስር ዓመቱ አገራዊ ልማት እውነተኛ ዕድገት ማምጣት የሚቻል ሲሆን፤ የሀገሪቱን የ10 ዓመት የልማት እቅድ ማሳካት የሚቻለውም እቅዱን ለማሳካት ከሚሠሩ ሠራዎች ጎን ለጎን የዋጋ ግሽበቱን መቆጣጠር ከተቻለ ብቻ መሆኑን አመልክተዋል። እንደ ዶክትር ሞላ ገለጻ፤ የ10 ዓመት የልማት እቅዱ ታሳቢ ካደረጋቸው ጉዳዮች አንዱ የሀገሪቱን ዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ከፍ ማድረግ ላይ ነው። ነገር ግን ከነፍስ ወከፍ ገቢ ጎን ለጎን የዋጋ ግሽበቱን መቆጣጠር ካልተቻለና ግሽበቱ ከፍ ካለ የህብረተሰቡ የኑሮ ደረጃ እያሽቆለቆለ ይሄዳል እንጂ የታሰበው ዕድገት አይመጣም። ስለዚህ ከ10 ዓመት የልማት እቅዱ ጎን ለጎን የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር ተገቢ ነው። በዚህ ረገድ የ10 ዓመት መሪ እቅድ የሀገሪቱን አጠቃላይ የዕድገት አቅጣጫ የሚጠቁም በመሆኑ፤ ግሽበቱን መቆጣጠር ከተቻለ እውነተኛ የሆነ የሀገር ዕድገትን ማምጣት ይቻላል። ይህ ሲሆን ደግሞ አብዛኛውን የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ ማድረግ የሚችል በመሆኑ ፍትሐዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል እንደሚኖርም ነው የገለጹት። ይህ የሀገሪቱን አጠቃላይ የዕድገት አቅጣጫ የሚጠቁም የ10 ዓመት ኢኮኖሚያዊ እቅድ የኦፕሬሽን ዕቅድ አለመሆኑን የጠቆሙት ዶክትር ሞላ እቅዱ ግን ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እጅጉን ጠቃሚ መሆኑንም አስረድተዋል። ከዚህ በፊት የነበረውን ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መጠናቀቁን ተከትሎ ያንን ማስቀጠል የሚችል የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መዘጋጀቱም ተገቢነት ያለው ከመሆኑም በላይ ዕቅዱ ጠቋሚ ዕቅድ እንደመሆኑ የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያሳያልም ብለዋል።ዕቅድ ሲታቀድ ያለፈውን መነሻ በማድረግ እንደሆነ የጠቆሙት ዶክትር ሞላ፤ ይህም ባለፈው ጊዜ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መለየት የሚያስችል እንደሆነ አስረድተዋል። በመሆኑም መንግሥት ካለፈው ስህተቱ በመማር በሀገሪቱ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ ላይ ባለሙያዎችን ተሳታፊ ማድረጉ የሚበረታታና መለመድ ያለበት ተግባር እንደሆነም ተናግረዋል።በሀገሪቱ አጠቃላይ ዕቅድ ላይ ቢቻል ማህበረሰቡን ማሳተፍ ተገቢ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ሞላ፤ ከዚህ በፊት በነበረው አሠራር በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሳይሆኑ የመንግሥት ፍላጎት ብቻ እጅግ በተጋነነ ሁኔታ ይስተናገድ እንደነበር አስታውሰዋል። በመሆኑም ይህ የመንግሥትን ፍላጎት ብቻ መሰረት ያደረገ እቅድ ህብረተሰቡን ያላማከለ በመሆኑ ክንውኑ ዜሮ እንደሚሆን ተናግረዋል። በዚህኛው እቅድ ላይም ከባለሙያዎች ባለፈ፣ ምቹ ሁኔታ ካለ በሀገሪቱ ዕቅድ ላይ ህብረተሰቡን ተሳታፊ በማድረግ የእኔ ብሎ እንዲረዳውና የበኩሉን እንዲወጣ ማስቻል፤ ህብረተሰቡን አሳታፊ በሚያደርግ መልኩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 10/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37642
b41ab3df7ddfdba00d7afd0b82e36d68
4cf7869a2b4b5931b73896dd61351cca
የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ህዝብና አገርን ያማከለ ሳይሆን በፖለቲከኞች ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ እንደነበር ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዋቅሹም ፍቃዱ አዲስ አበባ፡- ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ህዝብና አገርን ያማከለ ሳይሆን አገሪቱን ሲመሩ የቆዩት ግለሰቦችና በሚያራምዱት ፖለተካ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ እንደነበር ዶክተር ዲማ ነገዎ ተናገሩ። ዶክተር ዲማ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፤ ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የአገርና ህዝብን ፍላጎት ያማከለ ባለመሆኑ አገሪቱ በውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ስኬታማ አልነበረችም። ምክንያቱም በጊዜዉ የነበሩት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የአገርና ህዝብን ሳይሆን የገዥዉ ቡድን ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲያስጠብቁ የነበሩ ከመሆናቸውም በላይ፤ ግለሰቦች ከስልጣን ሲወርዱ አብረዉ የሚጠፉ እንጂ አልፈዉ ህዝብና አገርን የሚጠቅሙ አልነበሩም። እንደ ዶክተር ዲማ ገለጻ፤ ኢትዮጵያ ቅኝ ያልተገዛችና የጥቁር ህዝቦች ተምሳሌት ብትሆንም፤ በተለያዩ ምክንያቶች ኢትዮጵያን ሊገፉ የሚፈልጉ እና ኩርፊያ ውስጥ ያሉ አንዳንድ አገሮችም አሉ። ከዚህ አንጻር ከቅርብም ከሩቅም በተለያዩ ምክንያቶች በብዙ ጠላቶች ከበባ ዉስጥ መሆኗን መረዳት ይቻላል። እነዚህ አገራት ደግሞ የፖለቲካ አኩራፊዎችን በማስታጠቅ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ሲሠሩ ታይተዋል። ኢትዮጵያ ከድሮም ጀምራ ከፍተኛ የዉጭ ተጽዕኖ ሲደረግባት የነበረች መሆኗን የሚናገሩት ዶክተር ዲማ፤ በዚህ ረገድ በተለይ ከሱዳንና ግብፅ ጋር በጋራ ተጠቃሚነት፣ በዘላቂ ልማትና ሰላም ዙሪያ የተሠራዉ ሥራ ዝቅተኛ መሆኑን ያሚያሳዩ ክስተቶች መኖራቸውን ገልጸዋል። ለዚህ ጉልህ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ የህዳሴው ግድብ መሆኑን በመጠቆምም፤ በዚህ ረገድ ግብፅ የዓባይ ጉዳይ በፊትአውራሪነት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ እዉን እንዳይሆን ከአህጉር እስከ ዓለም አቀፍ መድረክ ያደረገችዉ ግፊት ቀላል እንዳልነበረ ይገልጻሉ። በሱዳን በኩልም ቢሆን የሚዋዠቅ አቋም እንደነበር እና ሀያላን አገራት ሳይቀር በግድቡ ዙሪያ የሚያሳዩት አቋም ለአንድ ወገን ያደላ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ዲማ፤ በኢትዮጵያ በኩል ባለፉት ሁለት ዓመታት በዚህ በኩል የተሠራው ሥራ መልካም ቢሆንም አጥጋቢ እንዳልነበር ግን አልሸሸጉም። እንደ ዶክተር ዲማ አባባል፤ አሁን ላይ በትኩረት መሥራት ከተቻለ ኢትዮጵያ ጠንካራ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ኖሯት ተጽዕኖ ፈጣሪ እንድትሆን የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች አሏት። ለዚህ ደግሞ ገለልተኛ ተቋማትን የመገንባት ሥራ ማጠናከር፤ እንዲሁም ነፃ እና ፍትሐዊ የምርጫ ስርዓት እንዲኖር መሠራት አለበት። የህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅም ከኢኮኖሚ ፋይዳ ባሻገር በፖለቲካውም ሆነ በውጭ ግንኙነቱ ረገድ የሚያሳድረው አዎንታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ በትብብር ዳር ማድረስ ያስፈልጋል። በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ያላትን መልካም ገጽታ በማጉላት የሚታወቀው የመከላከያ ኃይሉን ተጠቅሞም ኢትዮጵያን በየትኛዉም የዓለም ክፍል የፀጥታ ማስከበር ላይ ማሳተፍ የሚያስችላት የወታደራዊ አቅም ለማጎልበት በበለጠ መሥራት ያስፈልጋል። ምክንያቱም መከላከያ ሠራዊቱ በዚህ መልኩ ሲሠራ ከሰላም ማስከበሩ ጎን ለጎን ለአገሩ አምባሳደር ሆኖ ይሠራል። በዚህ መልኩ ኢትዮጵያን ከውጭ አገራት ጋር ያላትን ግንኙት ዘላቂ ጥቅሟን በሚያስከብር መልኩ ጠንካራ ሥራ መሠራት እንዳለበት የጠቆሙት ዶክተር ዲማ፤ ከዚህ ጎን ለጎን የዉጭ ግንኙነቱ በአመዛኙ በዉጭ ቋንቋ የሚከወን በመሆኑ ለዉጭ ቋንቋዎች ትኩረት በመስጠት የቋንቋ አቅሙ ከፍ ያለ የሰው ኃይል በብዛትና በጥራት ማፍራት ላይ በትጋት ሊሠራ እንደሚገባም ምክረ ሃሳብ ለግሰዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 10/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37628
db801446f4e478a1029c23512b469e3b
73f3b79a04f40b29cb24b1527d8e65e5
ከትልቅ ድል የተገኘ ትልቅ ተስፋ
ስፖርት
 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በ2021 የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የምድባቸውን ሁለተኛ ፈተና እንደ ተራራ የገዘፈ የእግር ኳስ ስም ካላት ኮትዲቯር ጋር ባህርዳር ላይ ተፋልመው የሚፈልጉትን ውጤት አግኝተዋል። የተጋጣሚያቸው ክብደት ከተመዘገበው ድልና የጨዋታ የበላይነት አኳያ ዳግም የኢትዮጵያን የእግር ኳስ ትንሳዔ ከማነቃቃት ባለፈ በፖለቲካ ትኩሳት እየተሸረሸረ የመጣውን ብሔራዊ ስሜት የመጠገን ሃይል እንዳለው መታዘብ ይቻላል። ይህ ድል ኢትዮጵያ እንዳለፉት ዓመታት ወደ መሰረተችው የአፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ ዳግም ሦስት አስርት ዓመታት እንደማትጠብቅ ጠቋሚም ነው። ያምሆኖ ይህ የተነቃቃ መንፈስ እንዳይከስም ሥጋት የለበትም ማለት አይደለም። የዋልያዎቹ አለቃ ኢንስትራክተር አብረሃም መብራቱ ‹‹ጨዋታውን እንደተመለከታችሁት በብዙ ብልጫ ኮትዲቯርን የበለጥነበትና በተሻለ የኳስ ቁጥጥር እንዲሁም የግብ ሙከራ ያሸነፍንበት ነው:: አምላክ ደግሞ ልፋታችንን ቆጥሮ ለድል አብቅቶናል:: ከሁሉም በላይ ቡድኑ ላይ እየታየ ያለው መሻሻል ጥሩ ነው:: በማሸነፍ ውስጥ የተፈጠሩትን ስህተቶችና የሚጎሉ ነገሮችን እያሟላን ጠንካራ ቡድን መገንባቱን እንቀጥላለን:: እግር ኳስ ሂደት ነው: ይሄን ጨዋታ ስላሸነፍን ሂደቱ አለቀ ማለት አይደለም:: ይሄ ድል ትልቅ የሞራል ስንቅ ይሆነናል›› በማለት ከጨዋታው በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን አስተያየት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጠንካራ ለማድረግ የውጭ ሀብት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አሰልጣኙ ‹‹ውጭ ያሉ ተጨዋቾቻችን ሀብቶቻችን ናቸውና በነሱ አጠቃቀም ላይ ጠንካራ ሥራ መሥራት ይኖርብናል። ምክንያቱም እነሱ የሚያገኙት ስልጠና: የሚገኙትን ኢንተርናሽናል ተጽዕኖና ፕሮፌሽናሊዝም አስተሳሰብ ለብሔራዊ ቡድናችን ይጠቅመናል:: ከዚህም ሌላው አገርን ወደው ለመምጣት መፈለጋቸው የበለጠ ብሔራዊ ቡድኑን ይገነዘባዋል የሚል ጠንካራ አሳብ አለኝ›› ብለዋል። አሰልጣኙ እንደገለፁት በውጭ አገራት ሊጎች የሚጫወቱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ለቡድኑ ቀጣይ ጥንካሬ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱ አይቀርም። ከዚያ ባሻገር ግን ይህን የተለኮሰ መነቃቃት እንዳይቀዘቅዝ በተለይም ፌዴሬሽኑ በርካታ ሥራዎች እንደሚጠብቁት እውን ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች በተራራቀ ጊዜ መካሄዳቸው የተፈጠረውን መነቃቃት ሊያቀዘቅዙ ከሚችሉ ነጥቦች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ዋልያዎቹ ዝሆኖቹን ባሸነፉ ማግስት ሌሎች ጨዋታዎችን ቢያከናውኑ የተፈጠረው መነቃቃት ሳይቀዘቅዝ ሌላ ድል ለማስመዝገብ ላይቸገሩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ቀጣዩን የማጣሪያ ጨዋታ ከበርካታ ወራት በኋላ በዓመቱ መጨረሻና መጀመሪያ አካባቢ ማድረጋቸው አሁን የተፈጠረው መነቃቃት ላይ ውሃ ሊቸልስበት ይችላል። የቡድኑ ስብስብም ለረጅም ጊዜ ተለያይቶ ሲገናኝ አሁን ያለው የአሸናፊነት መንፈስና መነቃቃት በነበረበት ላይገኝ ይችላል። ይህን ሥጋት ግን ፌዴሬሽኑ ከወዲሁ ትኩረት ሰጥቶ ከተዘጋጀበት መቅረፍ እንደሚችል ይታመናል። በዋናነት ይህን ችግር ለመቅረፍ የወዳጅነት ጨዋታዎችን በፊፋና በካፍ መርሐ ግብር መሠረት ማከናወን ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች በየትኛውም ደረጃ የወዳጅነት ጨዋታዎች ማድረግ የዘወትር ችግራቸው መሆኑ ይታወቃል። ይህን ክፍተት ፌዴሬሽኑ እየደፈነ መሄድ ከቻለና ቡድኑ ተደጋጋሚ የአቋም መለኪያና የወዳጅነት ጨዋታ ማግኘት ከቻለ አሁን ያለውን መነቃቃት ማስቀጠል ብቻም ሳይሆን የቡድኑ ውህደት ላይ ትልቅ ለውጥ መፍጠር እንደሚቻል ይታመናል። በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያው አሁን ላይ ማዳጋስካር በ2 ጨዋታ፣ በ6 ነጥብና በ5 ንፁ ግብ ዋልያዎቹ የሚገኙበትን ምድብ ትመራለች። ኢትዮጵያ በ2 ጨዋታ፣ በ3 ነጥብና በ0 ግብ ሁለተኛ ስትሆን ኮትዲቯር ከዋልያዎቹ ጋር በተመሳሳይ ነጥብና የግብ ልዩነት ትቀመጣለች። ኒጀር በ2 ጨዋታ በ0 ነጥብና በ5 የግብ ዕዳ መጨረሻ ላይ ትገኛለች። ይህ ዋልያዎቹን ከስምንት ዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ለመመልከት በእጅ ያሚገኝ ትልቅ ዕድል ነው። የምድቡን ቀሪ ጨዋታዎችና ተጋጣሚዎች ከግምት በማስገባት ዋልያዎቹ አፍሪካ ዋንጫው ላይ ለመድረስ ያላቸውን ተስፋ ካሰላነው ወደ ተወዳጁ መድረክ ለመመለስ ከዚህ የተሻለ ዕድል እንደሌለ መገንዘብ ይቻላል። ቀጣይ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከበርካታ ወራት በኋላ መካሄዳቸው አሁን የተፈጠረውን መነቃቃት እንዳያቀዘቅዙት ሥጋት እንደመፍጠሩ ሁሉ ዋልያዎቹ ያላቸው ቀሪ መርሐ ግብር ተስፋ የሚሰጥ ነው። ይህም በሜዳቸው የገነደሱት የምድቡ ሃያል ቡድን ኮትዲቯር ጋር የሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ የማጣሪያው መጨረሻ መሆኑ ነው። ዋልያዎቹ ዝሆኖቹን ከመግጠማቸው አስቀድመው ከኒጄር ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ያደርጋሉ። ከዚያም ማዳካስካርን በሜዳቸው ይገጥማሉ። በዚህ መርሐ ግብር መሰረት አሰልጣኝ አብረሃም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየገነቡት የሚሄዱት ቡድን እንዳሁኑ አዳዲስ ለውጦችን መፍጠር ከቻለ በሜዳዋ ሁለት ሽንፈቶችን ከቀመሰችውና የምድቡ ደካማ ቡድን ከያዘችው ኒጄር ጋር በሚኖሩት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ቢያንስ አራት ነጥብ ማግኘት ከባድ አይሆንም። ዋልያዎቹ ኒጄርን በሜዳዋ ገጥመው አንድ ነጥብ ይዘው ከተመለሱ በሜዳቸው ሦስት ነጥብ መሰብሰብ ይሳናቸዋል ተብሎ አይጠበቅም። ቀጣይ ተጋጣሚ ማዳካስካር እንደመሆኗ ከዚህ ጨዋታም ቀላል ባይሆንም ሦስት ነጥብ መሰብሰብ የማይቻል ነገር አይደለም። ምክኒያቱም ማዳጋስካርን የሚገጥሙት እዚሁ በሜዳቸው ነው። ባለፈው ቅዳሜ ማዳጋስካር በሜዳዋ ዋልያዎቹን 1ለ0 ስታሸንፍ ያን ያህል ከባድ ቡድን እንዳልሆነች ታይቷል። ይህን ስሌት ዋልያዎቹ ማሳካት ከቻሉ የመጨረሻውን ማጣሪያ ከሜዳቸው ውጭ በኮትዲቯር ቢሸነፉ እንኳን ወደ ካሜሩን የሚወስዳቸውን ትኬት በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ ማለት ነው። በዚህ ስሌት መሰረት ነገሮች ሊጓዙ የማይችሉበት አጋጣሚ እንዳለ ሁሉ እንዳለፈው ጨዋታ ያልተጠበቁ ድሎች ሊመዘገቡ እንደሚችሉም እውን ነው። ይህም ለዋልያዎቹ ቀጣይ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ ትልቅ የሥነ ልቦና ስንቅ ሆኖ ያገለግላቸዋል። ይህን ተስፋ እንዳይከስም ግን የወዳጅነት ጨዋታዎችን ጉዳይ ከወዲሁ አጥብቆ መያዝ ለነገ የሚባል የቤት ሥራ አይሆንም። አዲስ ዘመን ኅዳር 11/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=22892
4ba3d527262773d086c4d7006808dd58
970212ebffe10d472dadf92cf4845dd0
አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የእገዳ ውሳኔውን አነሳ
ስፖርት
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌቶች ተወካዩ ሚስተር ሁሴን_ማኪ ላይ አሳልፎት የነበረውን የእገዳ ውሳኔ አነሳ። በዶሃው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ተሳትፈው የነበሩ አትሌቶች ከማገገሚያ ሦስት ወራት በፊት ውድድር እንዳያደርጉ ውሳኔ አሳልፎ የነበረ ቢሆንም በሚስተር ሁሴን ማኪ ወይንም ‹‹Elite Sport Management›› ስር ያሉ የተወሰኑ አትሌቶችን በኒውዮርክ ማራቶን ውድድር ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ከተወካዩ ሁሴን ማኪ ጋር የነበረውን ውል እንዳቋረጠ ይታወቃል:: ፌዴሬሽኑ ከትናንት በስቲያ ከሰዓት በኋላ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ግን ይህን የውል ማቋረጥ እገዳ እንዳነሳ አሳውቋል፡፡ በመሆኑም ውሳኔውን የሰሙት ማናጀሩ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ለፌዴሬሽኑ ከማስገባታቸውም በተጨማሪ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግንዛቤ በማስገባታቸው ከሚኖሩበት አሜሪካ ተነስተው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ ስህተታቸውን አምነው ይቅርታ እንዲደረግላቸው በመጠየቃቸው ፌዴሬሽኑ ጥያቄያቸውን በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በኩል ከመረመረ በኋላ ይቅርታቸውን ተቀብሎ እርምጃው ለሌሎችም አስተማሪ ይሆን ዘንድ ወደ ገንዘብ ቀይሮላቸዋል። የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በመግለጫው ወቅት ለጋዜጠኞች እንዳስረዱት ሚስተር ሁሴን ማኪ ከ120 በላይ ስመጥር አትሌቶችን ይዘው ለ13 ዓመታት ከፌዴሬሽኑ ጋር እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ በአራቱም የአገሪቱ ዋና ዋና ቦታዎች የታዳጊዎች አትሌቲክስ ፕሮጀክት ከፍተው እየሠሩ ከመሆናቸው ባሻገር፣ በአዲስ አበባ ቢሮ ከፍተው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናና በኦሊምፒክ በርካታ ውጤታማ አትሌቶችን ለአገራችን ማፍራታቸውን ከግምት በማስገባት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ይቅርታቸውን ተቀብሎ ቅጣታቸውን ወደ ገንዘብ ሊቀይር ችሏል፡፡ እገዳው በሃያ አምስት ሺ የአሜሪካን ዶላር እንደተቀየረላቸው የተገለጸ ሲሆን ቅጣቱ በቂ ነው ባይባልም ሌሎች እንዲማሩበት ውሳኔው መተላለፉን ኮማንደር ደራርቱ አብራርታለች፡፡ አዲስ ዘመን ኅዳር10/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=22840
2c5785c1d453295bafd398ebcd771172
4718f2a62c6baf81adfd79767ed4c4a3
‹‹ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ካልቻልን ራሴን አገላለሁ››
ስፖርት
የኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛውና የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ብርቱካን ገብረክርስቶስ ከትናንት በስቲያ ከሰዓት በኋላ በኢትዮጵያ ሆቴል አጠቃላይ ስለ ብሔራዊ ቡድኑ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የሉሲዎቹ አዲስ አሰልጣኝ ብርሃኑ ‹‹እቅዴ ለ2020 የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ነው፣ ይህን ማሳካት የማልችል ከሆነ በራሴ ፍቃድ ከኃላፊነት እራሴን አገላለሁ››በማለት በጋዜጣዊ መግለጫው ተናግሯል፡፡ አሰልጣኙ ቀደሞ የነበሩ አሰልጣኞች በቡድኑ የሰሩትን መልካም ስራ በማጠናከርና የጎደለው በመሙላት ስህተቱን አርሞ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ የሚችል ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን የመገንባት ፍላጎት እንዳለው አብራርቷል፡፡ አሰልጣኝ ብርሃኑ ሉሲዎቹን ለመምራት ከፌዴሬሽኑ የተሰጠው የስራ ውል ለሦስት ወራት ብቻ የሚዘልቅ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ በ2020 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች፣ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ(ሴካፋ) ውድድር በሚያስመዘግበው ውጤት መሰረት ውሉ የሚታደስ ይሆናል፡፡ ያም ሆኖ በአፍሪካ ዋንጫው ቡድኑን ማሳለፍ ካልቻለ ‹‹በእጄ ፈርሜ እንደገባሁ ፈርሜ ለመውጣት ዝግጁ ነኝ›› ብሏል። ከምስራቅና መካከለኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ጋር ተያይዞ አሰልጣኙ ቡድኑን ለማዘጋጀት ያለው ጊዜ አጭር መሆኑን በመግለፅ ተጫዋቾቹ ከእረፍት እንደመምጣታቸው ከፍተኛ የአካል ብቃት ችግር እንደተስተዋለባቸው ተናግሯል፡፡ በአሁን ወቅት አሰልጣኙና ረዳቶቹ መስራት የሚችሉት ነገር ተጫዋቾቹ በሜዳ ላይ የተሻለ ቅንጅት እንዲፈጥሩና ያላቸውን አቅም አውጥተው መጠቀም የሚችሉበትን ነገር መፍጠር መሆኑን አብራርቷል፡፡ ‹‹በሴካፋው ይህን ውጤት አመጣለሁ ብዬ መናገር የምንችልበት ነገር የለም፣ ውጤት ብናመጣም ባናመጣም ብዙም የሚያስከፋም የሚያስጨፍርም ነገር የለም፣ እኛ እቅዳችን የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ነው፣ የሴካፋን ውድድር የብሔራዊ ቡድናችንን እንቅስቃሴ የምናይበትና ችግራችንን እያረምን የምንሄድበት ነው›› ሲልም አክሏል፡፡ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ከፌዴሬሽኑ የሚደረግለት ድጋፍ ጥሩ መሆኑን በመግለፅ ቡድኑ የጎደለበት ነገር እንደሌለና ይህም ከፍተኛ ለውጥ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን አሰልጣኙ ከፌዴሬሽኑ ጋር እንደማይስማማ ሲነሳ ስለነበረው ሃሳብ አሰልጣኙ ምላሽ ሲሰጥ ‹‹ፌዴሬሽኑ የኔን ሃሳብ በበጎ እንጂ በመጥፎ አልተመለከተውም፣ ለ18 ዓመት በሴቶች እግር ኳስ በውድድር ውስጥ አሳልፌያለሁ ብዙ ውጣ ውረዶችን ፣ አስቸጋሪ ጊዚያቶችን አሳልፌያለሁ የሴቶች እግር ኳስ ለኔ ደሜ ነው ለፍቼበታለሁ የማነሳው ሃሳብ ለውጥ እንዲመጣ እንጂ ለመጥፎ አይደለም›› ሲል ገልጿል። የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ብርቱካን ገብረክርስቶስ በበኩሏ ቡድኑ የአንድ ሳምንት ዝግጅት ማድረጉን ገልፃ፣ በሜዳ ላይም ከሜዳ ውጪም ትምህርት መውሰዳቸውን አብራርታለች፡፡ ‹‹ በአሰልጣኞቻችን ጥሩ ስልጠና እየተሰጠን ነው፣ ጥሩ መነሳሳት ላይ እንገኛለን፣ እኔ ከበርካታ አሰልጣኞች ጋር ጥሩም መጥፎም ጊዜ አሳልፌያለሁ፣ አሁን ካለፈው ተምረን በመከባበርና ድክመታችን ላይ በመስራት ተደጋግፈን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመግባት ነው እቅዳችን›› ብላለች። ሉሲዎቹ ትናንት ጠዋት ከ15 ዓመት በታች ወንድ ቡድኖች ጋር የመጨረሻ የወዳጅነት ጨዋታውን ያደረጉ ሲሆን ዛሬ ወደ ታንዛኒያ ያቀናሉ። በታንዛኒያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የሴቶች ሴካፋ ዋንጫ ሕዳር ስድስት የሚጀምር ሲሆን ኢትዮጵያ በውድድሩ ከኬኒያ፣ ዩጋንዳና ጅቡቲ ጋር መደልደሏ ይታወቃል፡፡ የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በምድብ ‹‹ሀ›› ታንዛኒያ፣ ብሩንዲ፣ ዛንዚባርና ደቡብ ሱዳን ተደልድለዋል፡፡ በምድብ ‹‹ለ›› ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ኢትዮጵያና ጅቡቲ ይገናኛሉ፡፡ በቻማዚ ስታዲየም በሚደረገው ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ጨዋታ ከኬንያ ጋር ታደርጋለች፡፡ አዲስ ዘመን ጥቅም3/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=22445
364ed43b49c59d59ba329703d145c101
3fbd58382c3ed2d1fbcfea3a6c1bf46b
”በወረቀት የሰው በደም የእኛ ናቸው»
ስፖርት
በረሃማነት በእጅጉ ከሰፈነባቸው የአረብ ሃገራት ነዳጅ እንጂ አትሌት ይፈልቃል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ በሪዮ ኦሊምፒክ የታየው ግን ተቃራኒ ነበር፡፡ በአማዞን ጥላ ስር በተካሄደው የቁንጮ አትሌቶች ፍልሚያ ባህሬን የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ስታስመዘግብ የተለየ ትኩረት የሰጣት አልነበረም፡፡ ሁለተኛውን ስትደግም ግን ዓለም አይኑን ሊጥልባት ተገደደ። ባህሬን ሰንደቅአላማዋን በዓለም ሕዝብ ፊት ከፍ አድርገው ያውለበለቡላት አትሌቶች የኋላ ታሪክ ሲጠናም አምጣ ወልዳ አየሯን ተንፍሰው ያደጉ ሳይሆኑ ከሚስኪኗ አህጉር አፍሪካ ማህፀን የወጡ ኬንያዊያን መሆናቸው ተገለጠ፡፡ ይህ አይነቱ አጋጣሚ ለባህሬን ብቻም ሳይሆን ለአሜሪካ እና ለቱርክ በጥቅሉ ከ30 በላይ የሚሆኑ ኬንያዊያን በወረቀት ላገኙት ዜግነት እንደሚሮጡ መታወቁ አነጋጋሪ ነበር፡፡ ይህ በአትሌቲክስ ብቻ ሲሆን በሌሎች የኦሊምፒክ ስፖርቶችም የደም ሳይሆን የወረቀት ዜግነት ላገኙባቸው በርካታ አገራት የተለያዩ አትሌቶች አንፀባርቀዋል፡፡ኑሮን ለማሸነፍ በየተኛውም ዘርፍ ጠንክሮ መሮጥ የግድ በሆነባት ዓለም በቀጥተኛው መንገድ መጓዝ አሊያም አቋራጮችን መጠቀም የግድ እየሆነ ይመስላል፡፡ ከእነዚህ አቋራጮች መካከል አንዱ ደግሞ የተሻለና ምቹ ሁኔታ ወዳላቸው ባለፀጋ ሃገራት መጠጋት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በዚህ ወቅት የተለመደ ሲሆን፤ በርካታ አትሌቶች በዚህ መልክ የፈለጉትን አሳክተዋል፡፡ በአትሌቲክስ የተሻለ ብቃት ያላቸው የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ደግሞ አትሌቶቻቸውን ለሌሎችም በማጋራት ቀዳሚዎቹ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ የኬንያ፣ የናይጅሪያ፣ ሞሮኮ፣ የኢትዮጵያ አትሌቶችም ከትውልድ ሃገራቸው ቀጥሎ አሜሪካ፣ የአውሮፓ እና አረብ ሃገራት ዋነኛ መዳረሻቸው ነው፡፡ ሃገራቱም ያላቸውን የኢኮኖሚ ጡንቻ በመጠቀም አትሌቶችን ከማስኮብለል ወደኋላ አይሉም፡፡ ለአብነት ያህል በሪዮ ኦሊምፒክ ኳታር ካሰለፈቻቸው 39 አትሌቶቻ 23 የሚሆኑት ትውልዳቸዉ በሌሎች ሃገራት ነው፡፡ ሃገሪቷ እአአ በ2000 በአንድ ውድድር ላይ ለማሳተፍ ስምንት ቡልጋሪያዊያንን በአንድ ሚሊዮን ዶላር ማስማማቷን ፋይናንሻል ታይምስ ያስታውሳል፡፡ እንግሊዝም ብትሆን እአአ 2012 ባስተናገደችው ኦሊምፒክ ካሳተፈቻቸው 542 ስፖርተኞች መካከል 60 የሚሆኑት እትብታቸው በሃገሪቷ ያልተቀበረና በወረቀት ዜግነት ያገኙ ነበሩ፡፡ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር እአአ ከ2000-2017 በየሃገራቱ ባደረገው ጥናት መሰረት የኀያሏ ሃገር አሜሪካ ፍላጎት በማሻቀቡ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡ ባህሬን፣ ኳታር እና እንግሊዝ ደግሞ ተከታዮቹ ሃገራት ናቸው፡፡ በዶሃው ቻምፒዮና በ1500ና 10ሺ ሜትር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ወርቅ ያጠለቀችው የኑዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰንን ጨምሮ የዓለም ቻምፒዮኗ አበባ አረጋዊ፣ ኤልቫን አቢይ ለገሰና ሌሎችም በርካታ ስመ ጥር አትሌቶች ‹‹በወረቀት የሰው በደም የዕኛው ናቸው››፡፡ ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ አትሌቶቿም በወረቀት ላገኙት ዜግነት ከአገራቸው ወጥተው እየሮጡ ይገኛሉ፡፡ ባህሬን፣ ቱርክ፣ ኳታር፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ሆላንድ፣ እንግሊዝ፣ ፖላንድ፣ ቤልጂየም፣ ስፔን፣ ስዊድን፣ ጀርመን እና አሜሪካ ደግሞ ዜግነት የሰጧቸው ሃገራት ናቸው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነም በዚህ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ አትሌቶች የተለያዩ ሃገራትን መለያ ለብሰው ይሮጣሉ፡፡ አንዳንዶች ለዚህ በምክንያትነት ድህነትንና በፌዴሬሽን በኩል ያለ ብልሹ አሰራርን ምክኒያት አድርገው ያነሳሉ፡፡ ቱርክን በተለያዩ ኦሊምፒኮች የወከለው ትውልደ ኬንያዊው አትሌት አክዳክ አሌክስ ኪፕኪሩይ፤ ‹‹ወላጆችን ጨምሮ የማስተዳድራቸው አራት እህት እና ወንድሞች ነበሩኝ፤ ኑሮን ለማሸነፍ ስሮጥም አንድ አሰልጣኝ ፈቃደኛ መሆኔን ጠየቀኝ›› ሲል ሁኔታውን ፌር ፕላኔት ለተባለ ድረ ገጽ አስታውሷል፡፡ አሁን ቤተሰቦቹ በሚፈልጉት ሁሉ እየረዳቸው ሲሆን፤ የታናናሾቹን የትምህርት ወጪም መሸፈን ችሏል፡፡ በርካቶች በእንዲህ አይነቱ ጉዳይ እንደይስማሙ ይታወቃል፤ ምክንያታቸው ደግሞ ገንዘብ ከሃገር አይበልጥም የሚል ነው፤ ኪፕኪሩይ ግን ከድህነት አላቆታልና በዚህ አይስማማም በድርጊቱም እንደምይጸጸት ነው የሚገልጸው፡፡ ኬንያ ሳለች ማሪያም ጅፕቶ ትባል የነበረችው ሌላኛዋ ባህሬን ዜጋዋ ያደረገቻት አትሌትም የኪፕኪሩይን አስተሳሰብ ትጋራለች፡፡ ስሟን አሊያ ባስማ በሚል የቀየረችው አትሌቷ ኬንያ ውስጥ በርካታ ወጣት አትሌቶች ቢኖሩም ለዓለም አቀፍ ውድድሮች የመታጨት እድላቸው አነስተኛ መሆኑን ትጠቁማለች፡፡ ለልሎች ሃገራች የመሮጥ እድል ቢመቻችላቸው ግን በኦሊምፒክ እና ዓለም ቻምፒዮናዎች ላይ ለመሳተፍ እንደማይቸገሩ ልምዷን ታካፍላለች፡፡ በርካታ አፍሪካዊያን አትሌቶች የመነሻ ምክንያት ኑሮን ማሸነፍ ይሁን እንጂ የተቀሩት ደግሞ በልጅነታቸው በማደጎ ወደ ሌላ ሃገራት በመሄድ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሰደድ ነው ሁለተኛ ሃገርን የሚወክሉት፡፡ በተለይ የሰሜን አፍሪካ ሃገራት ወደ አውሮፓ በሚያደርጉት ስደት ምክንያት እግር ኳስ እና አትሌቲክስን ጨምሮ በሌሎች ስፖርቶች ተሳታፊ የሆኑ አትሌቶች ከትውልድ ሃገራቸው ይልቅ ላደጉበት ሃገር ለመወዳደር ይገደዳሉ፡፡ የተቀሩት ደግሞ በሃገራቸው ምቹ ሁኔታ ባለማግኘትና በመገፋታቸው በቀላሉ ዜግነት ወደ ሚሰጧቸው ሃገራት ያማትራሉ። በስፖርት አመራሮችና አሰልጣኞች ያለው የቀናነት ጉድለት፣ ለብሄራዊ ቡድን በሚደረገው ምርጫ የሚቀመጠው የማያስማማ መስፈርት፣ ለስፖሩቱ እና ለአትሌቶቹ የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆን፣ አትሌቶቹ የሚከፈላቸው ደመወዝ አነስተኛ መሆን፣ በልምምድ እና በማገገሚያ ወቅት በቂ ቁሳቁስ እንዳስፈላጊነቱ ባለማግኘት እና ሌሎች ምክንያቶችም አትሌቶች ከትውልድ ቀያቸው ይልቅ የሌሎች ሃገራትን ክብር እንዲገነቡ ሆነዋል፡፡ ወደ ባለጸጎቹ የመካከለኛው ምስራቅ አረብ ሃገራት መጓዝ ለአትሌቶቹ የተሻለ ነገር እንደሚያስገኝ ይታሰብ እንጂ፤ በተቃራኒው የስፖርት ባርነትን እንደሚያተርፍም ዘ ጋርዲያን የተሰኘው ድረገጽ በአንድ ዘገባው አስነብቧል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ሊሊ አብዱላይቫ ያሰቡት ካልተሳካላቸው አትሌቶች መካከል ትተቀሳለች። አትሌቷ ለቱርክ ለመሮጥ የተስማማችው በ300ዶላር ወርሃዊ ክፍያ እንዲሁም ስታሸንፍ ተጨማሪ 1ሺ ዶላር ሊከፈላት እንዲሁም ቤትና መኪና ሊሰጣት ነበር። ይሁን እንጂ ቃል የተገባላት አልተፈጸመላትም፣ የሽልማት ገንዘቧንም ማግኘት አልቻለችም፡፡ ሌላኛው ኬንያዊ ልዮናርድ ሙቹሩም የዚህ ታሪክ ገፈት ቀማሽ ነው፡፡ አትሌቱ ጉዳት ባጋጠመው ወቅትም የባህሬን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ደመወዙን ሊሰጠው ፈቃደኛ እንዳልነበረም ገልጣል፡፡በርካቶች ጉዳዩን ከህገወጥ ሰዎች ዝውውር ለይተውም አያዩትም፤ ዓለም አቀፍ ውድድሮችንም አደጋ ላይ ይጥላል በሚል ይገልጹጻል፡፡ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበርም በተመሳሳይ በዚህ ጉዳይ አይስማማም፤ ማህበሩ ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮ በአትሌቲክስ እና እግር ኳስ ስፖርቶች ዜግነት እንዳይቀይሩ የሚከለክል ጠንካራ ህግ ባለመኖሩ ይህ ዓይነቱ ዝውውር እያደገ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን በአንድ ወቅት ተናግረዋል፡፡ አብዛኛዎቹ አትሌቶችም ኦሊምፒክን መሰል ትልልቅ ውድድሮች ሲቃረቡ ወደ ዜግነት መለወጥ እንቅስቃሴ ይገባሉ፡፡ በመሆኑም በቅርቡ አዲስ ደንብ የሚወጣ መሆኑን ጠቁመው ነበር እስካሁን ምንም የተባለ ነገር ባይኖርም፡፡ በእርግጥ ከሁለት ወይም ከሦስት ዓመታት በፊት የወጣ አንድ ህግ አለ፡፡ ይህ ህግ አንድ አትሌት ዜግነቱን ቀይሮ ከመሮጡ በፊት ለትውልድ አገሩ ለሁለት ዓመታት መሮጥ እንዳለበት የሚደነግግ ነው፡፡ ይህ ግን አትሌቶችን ከስደት የሚታደግ አልሆነም፡፡ አዲስ ዘመን ጥቅም30/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=22258
ec606fbd0d3ed3b5566eb18916cbddb4
7a2be52d0f1ba4d19993aa253c06ffd2
የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ሽልማት የመጨረሻ እጩዎች
ስፖርት
የዓለም አትሌቲክስ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ሽልማት በሞናኮ ሊካሄድ ዛሬ አስራ አንድ ቀን ብቻ ይቀረዋል። ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በሁለቱም ፆታ አንድም ኢትዮጵያዊ አትሌት ከመጀመሪያዎቹ አስር እጩዎች ውስጥ እንኳን መካተት እንዳልቻለ ይታወሳል። በተመሳሳይ ወጣትና ተስፈኛ የሆኑ ከሃያ ዓመት በታች ያሉ አትሌቶች በሚወዳደሩበት ሽልማት ዘርፍ ሁለት ወንዶችና አንድ ሴት ኢትዮጵያዊት አትሌት ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ውስጥ መካተታቸው ይታወቃል። የዓለም አትሌቲክስ ትናንት ከሰዓት በኋላ በዘንድሮው ዓመት በወንዶች የመጨረሻዎቹን አምስት እጩዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የመጨረሻዎቹ ሴት እጩዎችም ዛሬ የሚለዩ ይሆናል። ጆሹአ ቺፕቴጌ ባለፈው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና የአስር ሺ ሜትር ቻምፒዮን የሆነው ዩጋንዳዊው ጆሹአ ቺፕቴጌ የመጨረሻዎቹን አምስት እጩዎች መቀላቀል የቻለ ሲሆን አትሌቱ በ2019 የውድድር ዓመት ያሳየው አስደናቂ ብቃት ሽልማቱን የማሸነፍ እድል እንዳለውም አመላካች ነው። ጆሹአ አርሁስ በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ በውድድር ዓመቱ ትኩረት የተሰጠው አትሌት ሆኗል። ባልተጠበቀ መልኩም ጠንካራዎቹን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዳይመንድ ሊግ በማሸነፍ በአምስት ሺ ሜትር አጠቃላይ አሸናፊ ለመሆን በቅቷል። በዶሃው የዓለም ቻምፒዮናም 26፡48፡36 የሆነ መሪ ሰዓት አስመዝግቦ በውድድር ዓመቱ ለታላቅ ስኬት እጩ መሆን ችሏል። ሳም ኬንድሪክስ አሜሪካዊው ምርኩዝ ዘላይ ሳም ኬንድሪክስ በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው አስራ ሰባት ከቤት ውጪ ውድድሮች አስራ ሁለቱን በድል አጠናቋል። የውድድር ዓመቱ የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ከመሆኑ ባሻገር የዓለም ምርኩዝ ዝላይ ቻምፒዮን ነው። በአሜሪካ የምርኩዝ ዝላይ ቻምፒዮና 6 ነጥብ 06 ሜትር በመዝለል ያስመዘገበው ስኬት ለዓለም ምርጥ አትሌቶች ሽልማት የመጨረሻ እጩነት አብቅቶታል። ኢሉድ ኪፕቾጌ ያለፈው ዓመት የሽልማቱ አሸናፊ የሆነው ኬንያዊው የማራቶን ፈርጥ ኢሉድ ኪፕቾጌ በውድድር ዓመቱ ሁለት ፉክክሮች ላይ ብቻ ቢታይም ያስመዘገበው ታሪክ ለመጨረሻ እጩነት አብቅቶታል። ኪፕቾጌ በውድድር ዓመቱ የለንደን ማራቶንን ክብረወሰን በማሻሻል በ2፡02፡37 ሰዓት ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ከዚህ በላይ ግን ከወር በፊት በቬና ማራቶን የሰው ልጅ የብቃት ጥግ ወሰን እንደሌለው ያሳየበት ውድድር አይዘነጋም። ኪፕቾጌ ከትጥቅ አምራች ኩባንያው ናይኪ ጋር በመሆን በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ታግዞም ቢሆን ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች ማጠናቀቅ እንደሚቻል አስመስክሯል። 1፡59፡40 በሆነ ሰዓት ማራቶንን በማጠናቀቅ በታሪክ የመጀመሪያው አትሌት ለመሆን ቢበቃም የተመዘገበው ሰዓት በዓለም ክብረወሰንነት እንዳልተያዘ ይታወሳል። ኖህ ላይልስ አሜሪካዊው የአጭር ርቀት አትሌት ኖህ ላይልስ የሁለት መቶና አራት በአራት መቶ ሜትር ዱላ ቅብብል ቻምፒዮን ነው። በሉዛን ዳይመንድ ሊግ ሁለት መቶ ሜትርን 19፡50 በሆነ ሰከንድ በማጠናቀቅ በታሪክ አራተኛው ፈጣን ሰዓት ባለቤት መሆኑም አይዘነጋም። የዳይመንድ ሊግ የመቶና ሁለት መቶ ሜትር አጠቃላይ አሸናፊ መሆኑም በመጨረሻዎቹ እጩዎች ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። ካርልስተን ዋርሆልም ኖርዌያዊው የአጭር ርቀት ኮከብ አትሌት ካርልስተን ዋርሆልም በአራት መቶ ሜትር መሰናክል የዓለም ቻምፒዮን ነው። ይህ አትሌት በውድድር ዓመቱ በተለያዩ ርቀቶች በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጪ ውድድሮች ሽንፈት አልገጠመውም። ዳይመንድ ሊግን ጨምሮ የአውሮፓ ቻምፒዮን ሲሆን ያስመዘገበው 46፡92 በታሪክ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኗል። ይህም ስኬቱ ምናልባትም ከዩጋንዳዊው አትሌት ጋር ሽልማቱን ለማሸነፍ ጠንካራ ተፎካካሪ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል። አዲስ ዘመን ኅዳር 2 /2012   ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=22339
73135cb98dda5480d6eef5474e12840c
36de16f6420f08fdee4e34e6b9e963f8
“በትግራይ ተጨማሪ የጅምላ መቃብር መገኘቱ አይቀርም” ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አስታወቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተሮች አዲስ አበባ፡- ባለፉት አስርት ዓመታት የህወሓት ጁንታ የተለያ የፖለቲካ አመለካከትና አቋም ያላቸውን የትግራይ ተወላጆች በጭካኔ ሲገድል ከመቆየቱ ጋር በተያያዘ በክልሉ ተጨማሪ በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸው አይቀርም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ነጋሲ በየነ ተናገሩ።የኢትዮ-አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል እና የኢትዮጵያዊያን ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ባዘጋጁት የዌብናር ውይይት ላይ የተሳተፉት አቶ ነጋሲ በየነ እንደተናገሩት፤ ጁንታው ስርዓቱን ያዋቀረው ከአልባኒያ ኮሚኒዚም በመኮረጅ ወዳጅና ጠላት በሚል ሲሆን፤ ከእርሱ ውጪ ያለን አስተሳሰብና አቋም የሚያራምዱ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ባለመቀበል ሲያስርና ሲገድል ኖሯል። በመሆኑም በትግራይ ክልል በቅርቡ ተጨማሪ የጅምላ መቃብር መገኘቱ አይቀርም። የህወሓት ጁንታ በ17 ዓመቱ የሽምቅ ውጊያ ወቅት በድርድር ሰበብ የጠራቸውን የትግራይ ነፃነት ግንባር (TLF) አመራሮችን ራት ጋብዞ ሌሊት በተኙበት እንደገደላቸው ያስታወሱት አቶ ነጋሲ፤ በተመሳሳይ አሁንም በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ የፈጸማቸው ክህደትና ግፍ የቡድኑ ተፈጥሯዊ ባህሪ ስለሆነ ዓለም ሊረዳውና ሊያወግዘው ይገባል ነው ያሉት። በኢትዮጵያ ከተደረገው የፖለቲካ ለውጥ በኋላ ኩርፊያ ውስጥ የገባው ጁንታው ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ዞር ብሎ አይቶት የማያውቀው የትግራይ ህዝብ ጉያ ውስጥ ገብቶ ተደብቆ ቆይቷል ያሉት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ፤ ለፖለቲካ ስልጣን ጥሙ ሲል የትግራይ ህዝብ በጠላቶች እንደተከበበ እንዲሰማው ለማድረግ ሲደክም ቆይቷል፤ በሰዎች መካከልም ፍርሐትን ለመጫን ሞክሯል፤ ራሱንም ብቸኛ የትግራይ ህዝብ ተከላካይ አድርጎ አሳይቷል ነው ያሉት። ከለውጡ በኋላም ወደ ትግራይ የተመለሰው የህወሓት ጁንታ ለትግራይ ወጣቶች ምንም ዓይነት የተሻለ የሥራ ዕድል አልፈጠረም፤ ይልቁንም ወጣቱን በልዩ ኃይል ስም እያሰባሰበ ሲያሰለጥን ምሽግ ሲያስገነባ መቆየቱን ነው ያብራሩት። በዚሁ ዌብናር ላይ የተሳተፉትና የውይይቱ አስተባባሪ አንድነት እምሩ እንደተናገሩት፤ ጁንታው ከውድቀት ለመዳን በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች ላይ ከፍተኛ የሐሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማወናበድና ኢትዮጵያን ለመበተን ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን ማረጋገጥ እንደቻሉ አስረድተዋል፡፡ጁንታው በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በሁሉም የሰሜን እዝ ላይ እና ሁሉም ወታደራዊ ካምፖች ላይ የተቀናጀ ጥቃት መፈጸሙን ያነሱት አቶ አንድነት፤ ጁንታው ጥቃቱን የፈጸመበትን እቅድ ባለማሳካቱ፤ ሐሰተኛና የፈጠራ መረጃዎች በመንዛት በሌላ የጥፋት መንገድ ተጠምዶ እንደነበር ማረጋገጥ እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ እቅዱም ከውድቀት ሊታደገው አልቻለም ሲሉ ነው ያስረዱት።ጁንታው በሕግ ማስከበሩ ሂደት በተወሰደበት ዕርምጃ ላይነሳ ተንኮታኩቷል፤ በመሆኑም እየሸሸ ሲሄድ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ዜጎችን ሕይወት ከማጥፋቱም ባለፈ በሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ ለማገት ሞክሮ በሁሉም ረገድ ለሽንፈት መዳረጉን አቶ አንድነት ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል። የአሜሪካ ሴኔት አባላት፣ የምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነት ሠራተኞች፣ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪዎች፣ የሃሳብ አመንጪዎች (ቲንክ ታንክ) እና ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን በተደረገው ገለጻ መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 8 2013/ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37523
4cfca7c18057291d1913d8df5bd3b728
d5741accc7522818cda29642327ddec8
“የትግራይ ወጣት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስማማት ወደ ኃላፊነት ሊመጣ፣ ሃገሩንና ህዝቡንም ሊያገለግል ይገባል” – አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል የትግራይ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ
ሀገር አቀፍ ዜና
እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ የትግራይ ወጣት የጁንታው ቡድን ማንንም የማይወክል መሆኑን በመረዳት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስማማት ወደኃላፊነት በመምጣት ሃገሩንና ህዝቡን እንዲያገለግል የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጥሪ አቀረበ። የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ውድቀት የትግራይ ህዝብም ሆነ ወጣት ውድቀት ሳይሆን የራሱ የጁንታው ብቻ ነው። በመሆኑም ወጣቱ በተፈጠረው ነገር መቆዘም ሳይሆን በተፈጠረው ትልቅ ዕድል በመጠቀም ወደ ኃላፊነት መምጣት፣ አገሩንና ህዝቡንም ለማገልገል መዘጋጀት ይጠበቅበታል። እንደ አቶ ነብዩ ገለጻ፤ አንዳንድ ወጣቶች የህወሓት ጁንታ ቡድን ውድቀት እነርሱንም አብሮ የሚጥላቸው ስለሚመስላቸው በቁዘማ ውስጥ ገብተው ይታያሉ። ሊያውቁት የሚገባው እውነት ግን የህወሓት ጁንታ ከወጣቱ፣ ከህዝቡ፣ ከመንግሥትና ከተለያዩ አካላት ብዙ ምክርና ዕድል ተሰጥቶት አልጠቀምም ብሎ በራሱ እብደትና ቅሌት ለዚህ ማብቃቱ ሲሆን፤ የጁንታው ውድቀትም ከትግራይ ወጣቶችም ሆነ ከማንኛውም ትግራዋይ ጋር የማይገናኝ መሆኑ ነው። ይልቁንም የሆነ ቡድን በራሱ መንገድ ብቻ እያየ ሲሄድ የጠፋ አድርጎ መውሰዱ ይገባል። ለጁንታው ቡድን ምክርና ሃሳብ ካዋጡ አካላት አንዱ  የትግራይ ወጣት መሆኑን የገለጹት አቶ ነብዩ፤ “ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው” እንደሚባለው ሁሉ አሁን ላይ ጁንታው በራሱ መንገድ ተጉዞ የጠፋ እንደመሆኑ ወጣቱ ለዚህ ቡድን ምንም ማድረግ አይችልም። ስለዚህ ወጣቱ የጁንታው ቡድን ማንንም የማይወክል መሆኑን በመረዳት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር አስማምቶ መቀጠል እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል። በሌላ በኩልም ወጣቱ ለውጡ የራሱ እንደሆነ በመረዳት ይህንን ደማቅ ምዕራፍ እውን አድርጎ ለራሱም ተጠቃሚ የሚሆንበት፣ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ አገሩንም ህዝቡንም የሚያገለግልበትን ዕድል በአግባቡ ሊጠቀም፤ ከአንዳንድ አላስፈላጊ ቁዘማዎችና መፋዘዞችም ሊላቀቅ እንደሚገባው አቶ ነብዩ አሳስበዋል። የጁንታው መወገድ ለትግራይ ህዝብ የነፃነት ቀኑ ተብሎ ሊጠቀስ የሚገባው ነው ያሉት አቶ ነብዩ፤ የታገለላቸው የዴሞክራሲ፣ የልማት እና የእኩል ተጠቃሚነት ዓላማዎች ተሳክተው የሚያይበት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑንም አብራርተዋል። በተለይም አዲሱ ትውልድ “እኛ ብቻ እናውቅልሃለን” ከሚለው አካል የተላቀቀበት እንደመሆኑ፤ አሁን ባገኘው ዕድል ተጠቅሞ የራሱን አስተዋጽዖ እንዲያበረክትና ወደ ኃላፊነት መጥቶ ህዝቡን እንዲያገለግል የሚያስችለው ጊዜ በመሆኑ አጋጣሚውን እንደ ወርቃማ ጊዜ ሊመለከተው እንደሚገባም መክረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ9/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37582
eedef5358a4a95f4467e365fe7087958
fcc0f34bea0812aa0b58a0cac4420d6a
ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ አራት ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ለመሳብ አቅዶ እየሠራ መሆኑን ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ጸጋዬአዲስ አበባ፡- በበጀት ዓመቱ አራት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢንቨስተሮች ለመሳብ አቅዶ እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። ኪሚሽኑ፣ ከአሜሪካና ከካናዳ ባለሀብቶች እንዲሁም ከሚሽነሪዎች ጋር በሃያት ሪጅንሲ ሆቴል ትናንት ተወያይቷል። ውይይቱ ላይ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳንኤል ተሬሳ እንደገለጹት፤ በተያዘው በጀት ዓመት በርካታ ባለሀብቶችን በመሳብ ከአራት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲለማ እየተሠራ ነው። እንደ አቶ ዳንኤል ገለጻ፤ የኢንቨስትመንት ህግ መሻሻሉ በኢኮኖሚው ላይ ብዙ ለውጦች እያመጣ ነው። በርካታ የአሜሪካና የካናዳ ባለሀበቶች በአዲስ መልክ በአዳዲስ ዘርፎች ላይ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ጥናት እያደረጉ ነው። ከዚህ በፊት በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ሲያለሙ የነበሩ ባለሀብቶችም ተጨማሪ ዘርፎች ላይ ለመሰማራት አማራጮችን እየተመለከቱ ነው። በተለይ በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግ በርካታ ዘርፎቸን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት አድርጓል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን በኢንቨስተሮች ተመራጭ ያደርጋታል። ዝግ የነበሩ የኢንቨርስትመንት ዘርፎችን ክፍት መደረጉ ለማልማት ፍላጎት እያላቸው ያልቻሉ ባለሀብቶችን ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ያደርጋል ያሉት አቶ ዳንኤል፤ ፍላጎት ያላቸው የአሜሪካና የካናዳ ባለሀብቶች ለመሰማራት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። የኢንቨስትመንት ህጉ መሻሻሉ በምሥራቅ አፍሪካ ያለንን የኢንቭስትመንት ተመራጭነት ለማስቀጠል ይጠቅማል ያሉት አቶ ዳንኤል፤ ምቹ ሁኔታዎችን በማሳወቅ ባለሀብቶች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲያለሙ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።እንደ አቶ ዳንኤል ገለጻ፤ የኮቪድን ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥት ካምፓኒዎች እንዳይጎዱ በማለት የተለያዩ ድጎማዎችን ሲያደርግ ነበር። እንዲሁም ወደ ውጭ ሲልኩ ለነበሩ ድርጅቶች በሀገር ውስጥ እንዲሸጡና የገንዘብ ዕርዳታ እንዲያገኙ በማድግ ሊዘጉ የሚችሉ ድርጅቶች ሳይዘጉና ሠራተኞቻቸውን ሳይበትኑ መቆየት ችለዋል። በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሥራት እቅዶችን ለማሳካትና አልሚዎችን በምቹ ሁኔታ እንዲሠሩ ለማድረግ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎች እተሠሩ ነው። የበርዳን አማካሪ ድርጅት ማናጀር የሆኑት ትዕግስት ገረመው በበኩላቸው እንዳሉት፤ የተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግ ለባለሀብቶች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ሆኖም በኢንቨስትሮች ላይ ሁሌም ይነሳ የነበረውን የግብር ችግር ለመፍታት ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አከላት ጋር ቢሠራ በጣም ጥሩ ነው። እንዲሁም ከመሬት ይዞታና ከባንኮች ጋር መሠራት ቢቻል ኢትዮጵያን በቀላሉ ተመራጭ ማደረግ ይቻላል። አልሚዎች በምን ዘርፍ መሳተፍ እንዳለባቸው የሚያሳዩ ማስታወቂያዎች ቢኖሩ በርካታ ኢንቨስተሮችን መሳብ ይቻላል ያሉት ማናጀሯ፤ ከምንም በላይ ደግሞ አዳዲስ ዘርፎች ለውጭ ባለሀብቶች መፈቀዳቸው ጥሩና አበረታች ነው። ኢንቨስተሮች በመጡ ቁጥር ለሀገር ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው መንግሥት ከአማካሪ ድርጅቶች ጋር በጋራ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 9/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37590
cc01f85c5b5966ebba1abb351c8f391d
090ae3ed5bacd8bac7552b67e74c4e06
የአንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ የአርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ከትናንት በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር አርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ ቀብር ሥነስርዓት ዛሬ ተፈጽሟል።ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ የህይወት ታሪክ እንደሚያስረዳው፤ በቀድሞው ሐረርጌ ክፍለ ሀገር ጎሮጉቱ በሚባል አካባቢ ከአባቱ ከአቶ ገሰሰ ቆለጭ እና ከእናቱ ወይዘሮ በለጥሻቸው ያየህይራድ መስከረም 17 ቀን 1929 ዓ.ም ነው የተወለደው። በስምንት ዓመት ዕድሜው በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የገባ ሲሆን፤ በትምህርት ቤቱ ስካውት ተሳትፎ ነበረው።በልጅነቱም ደራሲ ከበደ ሚካኤል በደረሱት “የትንቢት ቀጠሮ” ቴአትር ላይ የሚያለቅስ ሕፃን ልጅ ገጸ ባህሪይ ተላብሶ ተጫውቷል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር (በወቅቱ መጠሪያው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቴአትር ቤት) ከመጽሐፍ ቅዱስ የኢዮብን ታሪክ በመውሰድ በተዘጋጀ ተውኔት በመሪ ተዋናይነት የተጫወተ ሲሆን፤ በተውኔቱ ዳይሬክተር ጋባዥነት ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ አርቲስት ተስፋዬ ሲተውን ተመልክተዋል። አርቲስቱ በመሪ ተዋናይነት የተጫወተበት ይህ ተውኔት ወደ ቴአትር ሙያ እንዲገባ በር የከፈተለት እንደሆነም ይነገራል።አርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ በልጅ እንዳልካቸው መኮንን ወደ ፈረንሳይ ተልከው የሕግ ትምህርት ይማሩ ተብለው ከተመለመሉ ሰዎች እንዱ የነበረ ሲሆን የእሱም ፍላጎት የሕግ ትምህርት መማር ነበር። ይሁንና ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ኢትዮጵያ በቴአትርና ስነ ጥበብ ብዙ ባለሙያዎች ስለሌሏት ውጭ አገር በዚሁ ዘርፍ ብትማር ይሻላል ብለው በወቅቱ ለአርቲስቱ ያቀረቡለትን ጥያቄ ተቀብሏል። በ1951 ዓ.ም በጄነራል ሂውማነቲስ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን፤ በ1953 ዓ.ም በኖርዝዌስተርን ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ትምህርት ቤትም ተመርቋል። አርቲስቱ በ1954 ዓ.ም ወደ አገሩ በመመለስ በቴአትር ሙያው መሥራቱን ቀጥሏል። ወደ አገሩ ከተመለሰ በኋላ በሙያው ቴአትር መሥራትና ማዘጋጀት የጀመረ ሲሆን፤ “የሺ፣ እቃው፣ ፀረ ኮሎኒያሊስት፣ ተሃድሶ፣ “Cherchez Les Femmes” እና “ፍርዱ ለእናንተ” የተሰኙ ቴአትሮችን አዘጋጅቷል። በተለይም በ1968 ዓ.ም የደርግ ስርዓትን በሚተቸው “እቃው” ቴአትር ምክንያት በዋና ዳይሬክተርነት ተሹሞ ይሠራበት ከነበረው የአገር ፍቅር ቴአትር ቤት ታግዶ ለእስር ተዳርጓል። በፀረ-ኮሎኒያሊስትና ተሃድሶ ቴአትሮቹ በፖለቲካ ጉዳይ ያነሳቸው ሃሳቦች አወዛጋቢ እንደነበሩም ይገለጻል። አርቲስቱ የብሔራዊ ቴአትር ቤት ዳይሬክተር ሆኖም አገልግሏል።አርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ በ2010 ዓ.ም “የመጨረሽታ መጀመርታ” የተሰኘ ታሪክና ሕይወት ቀመስ ሽሙጥ ልቦለድ መጽሐፍ ለንባብ አብቅቷል። በዘመኑ የኡመር ካያምን ሩቢያቶች የግጥም መድበልን ጨምሮ በርካታ ድርሰቶች፣ ትርጉሞችና የተውኔት ጽሑፎችንም ለንባብ አብቅቷል። የቴአትር ምሁር፣ ተዋናይ፣ ደራሲ፣ መምህር፣ ተመራማሪና ተርጓሚ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በሙያው ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ቴአትር መሰረት የጣለና ባለሙያዎችንም ያፈራ እንደሆነ ይነገርለታል።አገር ወዳድ፣ ቅን፣ ታታሪና በሰዎች ስኬት የሚደሰት እንደሆነም የቅርብ ወዳጆቹና የሙያ አጋሮቹ ይመሰክራሉ። ተባባሪ ፕሮፌሰር አርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ የሦስት ወንዶችና የሁለት ሴቶች ልጆች አባት የነበረ ሲሆን 10 የልጅ ልጆችንም አይቷል። የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ወዳጅ ዘመዶቹ የሙያ አድናቂዎቹና የሥራ ባልደረቦቹ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፤ ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 9/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37592
ff3bf79769db4909a3e5201697ac27e1
5b1f1ae27bf93604bf31d4cb3ecd3e3b
ተመራቂዎች የኢትዮጵያን ሰላምና ልማት በማረጋገጥ የህዝብ አገልጋይ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ተመራቂ ተማሪዎች የኢትዮጵያን ሰላምና ልማት በማረጋገጥ የህዝብ አገልጋይ መሆን እንደሚገባቸው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር  ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ገለጹ። የመቐለ የኒቨርሲቲ ለ28ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎቹን ትናንት ማስመረቁን ኢዜአ ዘግቧል። በምርቃ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፤ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት ቀጥለውና የተለያዩ ችግሮችን አልፈው ለምረቃ በመብቃታችሁ ‘እንኳን ደስ ያላችሁ’ መልዕክት ለተመራቂዎች ያሲተላለፉ ሲሆን፤ ተመራቂዎች ለአገራቸው ሰላምና ልማት በመሥራት ህዝባቸውን ማገልገል እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ተመራቂዎቹ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያካበቱትን እውቀት ሕዝባቸውን ለማገልገል እንዲጠቀሙበት ያስገነዘቡት ዶክተር ሙሉ፤ በክልሉ በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተማሪዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ላደረጉት አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጎን በመሆን የከተማዋን ልማት እንዲያረጋግጡም ጠይቀዋል።ተመራቂ ተማሪዎች በበኩላቸው፤ በውጣ ውረዶች ውስጥ አልፈው ለዚህ በመብቃታቸው መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላም ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው በቅንነትና በተታሪነት አገራቸውን ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በዕለቱ ከተመረቁ ተማሪዎች አንድ የሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆን፤ የተቀሩት የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች ናቸው። ከተመራቂዎቹ መካከልም 38 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው። ዩኒቨርሲቲውም በሁሉም የትምህርት መርሐ ግብሮች ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ እንደሚገኝም ታውቋል።በምርቃ መርሓ ግብሩ ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት መታደማቸውን ነው ኢዜአ የዘገበው።አዲስ ዘመን ታህሳስ9/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37587
6dce761a06168208250bbe2283e04a3b
72203bd15176967a2ac738e6dbf89085
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሙስናን ለመዋጋት እየሠራ መሆኑን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ፋንታነሽ ክንዴአዲስ አበባ፡- ሙስናን ለመዋጋት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታወቀ። 17ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንንም ትናንት አክብሯል። የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ፍርድ ቤት ከፈጣሪ በታች ህግን ለማስከበር ትልቅ ስልጣን ያለው፤ ህገመንግሥቱን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት የተጣለበት አካል ነው። ሙስናን ለመዋጋትና ለመከላከል ጉልህ ሚና የሚጫወት እንደመሆኑም ሙስናን ለመዋጋት የሚያስችሉ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። እንደ ወ/ሮ አሸነፈች ገለጻ፤ ሌሎች ህግን እንዲያከብሩ ለማድረግ በመጀመሪያ በተቋሙ ውስጥ ያሉ ሠራተኞች ህግን እንዲያከብሩ ማድረግ ይጠበቃል። ዳኞች የሚሰጧቸው ትክክለኛ ውሳኔዎች ሌሎች ሙስናንና ህገወጥነትን እንዲከላከሉና ህግን እንዲያከብሩ ያግዛሉ። ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች የሚሰጡት የተቀላጠፈ አገልግሎትም ህገ ወጥነትን ለመከላከልና ሙስናን ለመዋጋት የማይተካ ሚና አለው። የዳኝነት አካሉ በሰው ሕይወት፣ ሀብትና ንብረት እንዲሁም ነፃነት ላይ ውሳኔ የሚሰጥና ትልቅ ኃላፊነት ያለበት አካል መሆኑን የጠቀሱት ወ/ሮ አሸነፈች፤ ሙስናን እና በአጠቃላይም ህገ ወጥነትን ከመከላከል አንጻር ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት ተናግረዋል። ይህንን ለማረጋገጥ ዳኞች ስነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ ለተገልጋዮች በእኩልነትና በገለልተኝነት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ተከታታይ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸዋል።የዳኞች መተዳደሪያ የስነ ምግባር ደንብ በመሻሻል ለመጽደቅ በሂደት ላይ መሆኑን ያስታወቁት ወ/ሮ አሸነፈች፤ የፌዴራል መጀመሪያ ፍ/ቤት የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና የሠራተኞች የስነ-ምግባር መተዳደሪያ ደንብም መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ከእነዚህ ተግባራት በተጓዳኝ የመንግሥት የሥራ ሰዓትን ካለማክበር አስከ ትልልቅ ጉቦ መቀበል ድረስ ችግር የተስተዋለባቸው ሠራተኞች ላይ ከሥራ እስከማሰናበት የሚደርስ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው መደረጉንም አብራርተዋል። እንደ ወ/ሮ አሸነፈች ማብራሪያ፤ ዕርምጃ ከተወሰደባቸው ባሻገር ከየምድብ ችሎቱ ሬጅስትራሮችና አስተባባሪዎች ጋር በመተባበር የስነ-ምግባር ችግር ያለባቸው 60 ሠራተኞች መለየታቸውንና ምን ዕርምጃ ይወሰድባቸው በሚለው ላይ በማኔጅመንት ደረጃ ውይይት እየተደረገበት ነው። የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዓለም ለ17ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የፀረ-ሙስና ቀን ‹‹የትውልድ የሥነ-ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፕሊን በመምራት ሌብነትና ብልሹ አሠራርን በመታገል የህዝብ አመኔታን ያተረፈ የዳኝነት ስርዓት እንገነባለን›› በሚል መሪ ቃል አክብሯል። በበዓሉ ላይ የመነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና የሠራተኞች የስነ-ምግባር መተዳደሪያ ደንብ መጽሐፍ ምርቃትም ተከናውኗል። አዲስ ዘመን ታህሳስ 9/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37589
2cb6149017366dc1b6ad8123c1101878
56b170014ca5f8e2f5eeaf91f0816422
በኮቪድ 19 ምክንያት በከፊል አቋርጦ የነበረው የህዝብ ቤተ መጽሐፍት ወደሥራ ሊመለስ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- በኮቪድ-19 ምክንያት ለሥምንት ወራት አገልግሎቱን በከፊል አቋርጦ የነበረው የህዝብ ቤተ መፅሐፍት አገልግሎት ክፍት ሊደረግ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፅሐፍት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡በኤጀንሲው የህዝብ ቤተ መፅሐፍት ዳይሬከተር አቶ ያሬድ ተፈራ እንደገለጹት፤ የህዝብ ቤተ መፅሐፍቱ ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ከተከሰተበት መጋቢት ወር ጀምሮ ለሥምንት ወራት በስፋት አገልግሎት መስጠት ሳይችል ቆይቷል፡፡ አሁን ላይ ግን የኮሮና ቫይረስን በመከላከል የህዝብ ቤተ መፅሐፍቱ አገልግሎት መስጠት የሚችልበት መመሪያ በመዘጋጀቱ አገልግሎቱ ክፍት ይደረጋል፡፡እንደ አቶ ያሬድ ገለጻ፤ የህዝብ ቤተ መፅሐፍቱ ከዚህ በፊት ተመራማሪዎችና ቤተ መዛግብትን ለመጠቀም ለሚመጡ ተገልጋዮች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ለብዙሃኑ ህዝብ ዝግ ሆኖ መቆየቱ ለተጠቃሚዎች ጫና ፈጥሮ ቆይቷል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ አሁን ላይ ከሕፃናት ውጪ ለሌሎች ተጠቃሚዎች ከፍት የሚሆንበት ሁኔታ እየተመቻቸ ሲሆን፤ መመሪያውም ተገልጋዮችም ሆኑ ሠራተኞች ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ሳይንስ ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚወጡ መመሪያዎችን በሚገባ ለመተግበር የሚያስችል ነው፡፡በኤጀንሲው የስልጠና እና የምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መኮነን ከፍያለው በበኩላቸው፤ የህዝብ ቤተ መፃሕፍቱ ለህዝብ ክፍት በሚሆንበት ወቅት መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት በቤተ መፃሕፍቱ ውስጥ ያሉትን ወንበሮች በመቀነስ በአንድ ጠረንጴዛ ውስን ሰዎች እንዲገለገሉ የሚያስችል አሠራር ተዘርግቷል ብለዋል፡፡ በዚህም ከዚህ በፊት ከ1ሺ 200 በላይ ሰዎችን ያስተናግድ የነበረው ቤተ መፃሕፍት አሁን ላይ ኮሮናን ለመከላከል በሚያስችል መንገድ 326 ወንበሮች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ይህ የሆነውም የቤተ መፃሕፍቱ ወንበሮች ደንበኞች ከተገለገሉባቸው በኋል ከሦስት እስከ ሰባት ቀን ኳራንቲን በማድረግ አስፈላጊውን የኬሚካል ርጭት ተደርጎላቸው አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃሕፍት ኤጀንሲ ከዚህ በፊት ከ2፡30 እስከ 9 ሰዓት ይሰጥ የነበረው አገልግሎት በአሁኑ ሰዓት የ24 ሰዓት አገልግሎት ለመስጠጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁም ተገልጿል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 9/2013 ዓ፣ም
https://www.press.et/Ama/?p=37597
525622b024630e4b6f3639a1a8fa434f
af937c8d69cad649811e8ac5199a6610
ቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተጨማሪ ባለሀብቶችን ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዳግማዊት ግርማአዲስ አበባ፡- የቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተጨማሪ ባለሀብቶችን ለመቀበል ዝግጅቱን መጨረሱን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የአዲስ አበባ ማስተባበርያ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የማስተባበርያ ፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የነበሩበትን ችግሮች ቀርፎ ለባለሀብቱ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ፤ በፓርኩ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶችም የተሻሉ ማበረታቻዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ለኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚውሉ ግብአቶች በአካባቢው የሚገኙ መሆናቸው ለባለሀብቶች ትልቅ ዕድል መሆኑን የተናገሩት አቶ ያየህ፤ በስፍራው ያለው ሰላማዊ እንቅስቃሴም ለባለሀብቶች ምቹ እንቅስቃሴን የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ኢንዱስትሪ ፓርኩ የመሰረተ – ልማት ችግር እንደነበረበት ያወሱት ኃላፊው፤ በአሁኑ ጊዜ ግን የአስፓልት መንገድ መሠራቱን፣ የመብራት አገልግሎት መኖሩን፣ ለሥራ የሚሆን መሬትም ተዘጋጅቶ ማለቁን እንዲሁም ለትምህርት ቤቶች እና ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ ስፍራዎች ተሠርተው መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡ፓርኩ 600 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ከዚህም 200 ሄክታር ያህሉ መልማት መቻሉን፤ ከለማው መሬት ውስጥም 100 ሄክታሩ ለባለሀብት መሰጠቱን፤ እንዲሁም መሬት ከያዙት ባለሀብቶችም ሥራ የጀመሩ እንዳሉና በአግሮ ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘው አንድ የዘይት ፋብሪካም በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ነው አቶ ያየህ የገለጹት፡ የቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚፈልጋቸው ባለሀብቶች በምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ላይ መሥራት የሚፈልጉና ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን በመግለጽ፤ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮም የበለጠ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየሠራ እንደሆነ እና በክልሉ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ባለሀብቶች ከወዲሁ ዝግጅት እዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡አግሮ ኢንዱስትሪዉ ከፍተኛ የሆነ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን እንዲሁም በክልሉ የሚገኘውን የእርሻ ምርት ውጤት በተሻለ ጥራት እሴት ጨምሮ ለመላክ የሚያስችል ሲሆን፤ ኢንዱስትሪዉ ሙሉ ሥራውን ሲጀምር ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም አቶ ያየህ አዲስ ተናግረዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 9/2013 ዓ፣ም
https://www.press.et/Ama/?p=37598
203d7a76d64706ed382a9c45db9c3add
bec2fd989735fdce95318aeb93807dbc
“ከጁንታው ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚሠሩ የውጭ ኃይሎችን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መታገል ይገባል” – ኦባንግ ሜቶ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች
ሀገር አቀፍ ዜና
 ጽጌረዳ ጫንያለውአዲስ አበባ፡- ከህወሓት ጁንታ ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚጥሩ የምዕራባውያን ጁንታዎችን ሴራ ለማጋለጥ በኢትዮጵያዊነት ስሜት በመቆም መታገል እንደሚገባ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለጹ። አቶ ኦባንግ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የእኔ ብሔር ብቻ ማለት ባለፉት 27 ዓመታት የወረስነውና ያሳደግነው አስተሳሰብ ነው። ይህ ደግሞ ለነጭ ጁንታዎች ተጠቃሚነት ሰፊ ዕድል የሰጠና ኢትዮጵያን የችግር ቋት ውስጥ የከተተ ነው። በመሆኑም ከብሔር አስተሳሰብ ወጥቶ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ቆሞ የነጭ ጁንታዎችን እጅ ማሳጠር ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የውጭ ኃይሎች ከሚያስተላልፉት መልዕክት ጀምሮ ኢትዮጵያን ለማቆርቆዝ ያለመ ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ ያሉት አቶ ኦባንግ፤ የነዚህን ኃይሎች ድርጊት ለማስቆም በቅንጅት መሥራት ካልተቻለ አደጋው የከፋ ይሆናል ብለዋል። የህወሓት ጁንታ በ27 ዓመታት የአገዛዝ ዘመኑ ከነጭ ጁንታዎች ጋር በመሆን አገሪቱን ለብዙ ችግር ዳርጓታል የሚሉት አቶ ኦባንግ፤ አሁንም ይህንን አሠራር ነጭ ጁንታዎች ይፈልጉታልና የተለያዩ ሪፖርቶችን ለህዝብ በማቅረብ ከህወሓት ጁንታ ጎን መሆናቸውን እያሳዩ መሁኑን ተናግረዋል። አቶ ኦባንግ እንደገለጹት፤ እነዚህ ነጭ ጁንታዎች በአገሪቱ የተፈጠረውን ግጭት መነሻ አድርገው የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ይገኛሉ። በተለይም የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ መስለው የሌለና የሀሰት መረጃ ከመስጠት አንጻር ከባድ ችግር እየፈጠሩ ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ እውነታውን ስለሚያውቀው ይህንኑ እውነታ ለዓለም ማህበረሰብ ማሳወቅ አለበት። ለዚህ ደግሞ በተናጠል ሳይሆን በአንድ ሃሳብ በአንድነት መቆም ይገባል። በኢትዮጵያ ያለው ጉዳይ የኢትዮጵያ እንጂ የነጭ ጁንታዎች ጉዳይ እንዳልሆነ ግልጽ ነው ያሉት አቶ ኦባንግ፤ እነዚህ ነጭ ጁንታዎች ግን እኛ እናውቅላችኋለን በሚል እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል። እንደ አቶ ኦባንግ ገለጻ፤ አሁን አገር እያተራመሰ ያለው ጁንታ ቀደም ሲል ከእነዚህ ነጭ ጁንታዎች ጋር ወዳጅ ነበር። በዚህ የተነሳ ጁንታው ሀገር በሚመራበት ወቅት ይፈጽም የነበረውን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለማሳየት አይፈልጉም። አሁን ግን የህግ ማስከበር ሥራ ሲሠራ ጩኸታቸው ሁሉ ሰብዓዊ መብት ሆኗል። አሁን አሁን ደግሞ የግጭቱ ፈጣሪ መንግሥት እንደሆነ ለማሳየት ይሞክራሉ። ‹‹የሰብዓዊ መብት ጉዳይ የመንግሥታት ድጋፍ ጉዳይ ሳይሆን ሰው የመሆን ጉዳይ ነው›› የሚሉት አቶ ኦባንግ፤ ነጭ ጁንታዎች ግን ይህንን ትተው 27 ዓመት ሙሉ የነበረውን አሰቃቂ ሰብዓዊ ጥሰት ሳያነሱ ዛሬ እየሆነ ያለውን ይኮንናሉ ብለዋል። ይሄን የሚሉ ኃይሎች ደግሞ ማመዛዘን እንኳን የተሳናቸው ለመሆናቸው ብዙ ምክንያት መጥቀስ ይቻላል የሚሉት አቶ ኦባንግ፤ የግጭቱ ጀማሪ የህወሓት ጁንታ ስለመሆኑ ጁንታው እራሱ ምስክርነቱን ሰጥቶ እያለ እነርሱ ግን መንግሥት ዋሽቷል ብለው ሲያቀነቅኑ መታየታቸውን ገልጸዋል። ከዚህ አንጻር የእነርሱ ድጋፍ ለጁንታው እንጂ ለሰብዓዊነት አለመሆኑን ነው አቶ ኦባንግ የገለጹት። እንደ አቶ ኦባንግ ገለጻ፤ የአውሮፓ ህብረት በተለያየ መንገድ ጫና እያሳረፈ እንደሆነ እሙን ነው። ስለሆነም ይህንን መመከት የሚቻለው ጉዳዩ የአገር መሆኑን አምኖ በተቀናጀ መልኩ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ላይ በመሥራት ነው። ለዚህ ደግሞ መንግሥትን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥልቅ ጥናት አድርገው ሁኔታውን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስረዳት አለባቸው። የማይወክለንንም ሃሳብ አይወክለንም ማለት ያስፈልጋል። የህወሓት ጁንታ ከሠራው ሥራ አንዱ የመደራጀትና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ተግባራዊ እንዳይሆን ማድረግ ነው ያሉት አቶ ኦባንግ፤ አሁን ግን ይህ ኃይል በመደምሰሱ ትክክለኛ ፍትህና የሰብዓዊ መብት መከበርን ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ ሁሉም በሚያውቀው ቋንቋ እውነታውን ማስረዳትና የኢትዮጵያን ገጽታ መገንባት ላይ መረባረብ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ያስፈልጋል፤ የነጭ ጁንታዎችን የረዘመ እጅ መቁረጥም ይገባል ብለዋል። በቅርቡ ወደ አሜሪካ አቅንተው የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ሲያስረዱ እንደቆዩና አሁንም በዚህ ሥራ ላይ እንደሆኑ የሚያነሱት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ፤ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ከኮንግረንስ እስከ ቲንክ ታንክ ግሩፕ ድረስ ወርደው መሥራታቸውን ተናግረዋል። አሁንም ቢሆን ነጭ ጁንታዎች ጠንካራ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲኖር ስለማይፈልጉ እነርሱ እጃቸው እንዲያጥር በመሥራት ላይ እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል። ሆኖም በግለሰቦች ደረጃ የሚደረገው እንቅስቃሴ በቂ ስላልሆነ ሁሉም በቻለው ሁሉ መሥራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 9/2013 ዓ፣ም
https://www.press.et/Ama/?p=37602
31f0acdeab873015cb7181123359c0ac
652b4dd6b1e8c6139964a6410e79018c
የዳይመንድ ሊግ ለውጥ ተቃውሞ እያስተናገደ ነው
ስፖርት
የዓለም አትሌቲክስ በየጊዜው የሚያስተላልፋቸው አዳዲስ ውሳኔዎች የስፖርቱን ቤተሰብ በማስከፋት የቀጠለ ይመስላል።የዓለም አትሌቲክስ በራሱ በሚያጸድቃቸው ሃሳቦች በበርካቶች ዘንድ ተቃውሞም ይቀርብበታል፤ ይሁን እንጂ ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ አላለም።ከእነዚህ መካከል አንዱ በዳይመንድ ሊግ ይካሄዱ የነበሩ ውድድሮች መቀነሳቸው ነው።ሃሳቡ በተነሳበት ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካዊያን የስፖርት ማህበራት ተቃውሟቸውን ቢያሰሙም ተቀባይነት ሊያገኙ ሳይችሉ ወደ ውሳኔ ተቀይሯል።ከአዲሱ የፈረንጆች አመት ጀምሮም ከዳይመንድ ሊግ እንዲቀነሱ የተደረጉ ውድድሮችን ተከትሎ በርካቶች ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።በተለይ የአሜሪካ አትሌቶች ለጥያቄ ያመቻቸው ዘንድ ማህበር በመመስረት ላይ የሚገኙ መሆኑን ሜይል ኦንላይን አስነብቧል።በርዝመት ዝላይ የኦሊምፒክ ቻምፒዮኑ ክርስቲያን ቴይለር በጉዳዩ ላይ አትሌቶች መታገል እንዳለባቸው በማህበራዊ ገጾች በመጠቀም አትሌቶችን እያነሳሳ ይገኛል።አትሌቱ በመግለጫው ላይ ስፖርቱን እያጠፉት መሆኑን የጠቀሰ ሲሆን፤ ለአትሌቶች መብት መታገል እንደሚገባም ገልጧል።ስፖርቱ እንዲያድግም መሰል ድርጊቶች መቆም እንዳለባቸውም ነው ያመላከተው። የውድድሩ አዘጋጆች ውድድሮቹ በቴሌቪዥን ሲተላለፉ ሳቢ እና ማራኪ እንዲሆኑ በማሰብ የቀነሷቸው የውድድር አይነቶች ላይ የዓለም አትሌቲክስ አሸማጋይ የሆነ ሃሳብ ከማንሳት ይልቅ ድጋፉን መስጠቱ ያበሳጫቸው አትሌቶችም ደብዳቤ ለዓለም አቀፉ የበላይ አካል ጽፈዋል።‹‹ውድድሩ በዓለም ህዝብ ዘንድ ሳቢ እንዲሆን ለውጦች መዳረጋቸውንና ማስፈለጋቸውን ብናምንም የዓለም አትሌቲክስ ግን አትሌቶችን ከግንዛቤ ያስገባ አይመስልም።በውሳኔው ላይ አትሌቶች አስተያየት እንዲሰጡ አለመደረጉም  ትክክል አይደለም›› ሲሉም አክለዋል።ማህበሩን በርካታ አትሌቶች እየተቀላቀሉት ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል እንግሊዛዊያኑ የዓለም ቻምፒዮን ዲያና አሸር ስሚዝ እንዲሁም የቀድሞው ርዝመት ዝላይ አትሌት ጆናተን ኤድዋርድስ ይጠቀሳሉ።አንጋፋው አትሌት የዓለም አትሌቲክስ በርካታ ስህተቶችን በመስራት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።ሆኖም ስፖርቱን በበላይነት የሚመራው አካል አስካሁንም የሰጠው ምላሽ ወይም አስተያየት የለም።አዲስ ዘመን ጥቅም4/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=22483
b51beeebc9e5b35635408d9be1060650
0831fa608e665eddf7a18af32f2a4656
የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት ማቋቋሚያ ጉባኤ ተካሄደ
ስፖርት
 የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤትን በአዲስ መልክ ለማቋቋም የሚረዳ መስራች ጉባኤ ተካሄደ። ምክር ቤቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 446/2011 ድንጋጌ መሰረትም የሃገሪቷን ስፖርት በበላይነት የሚመራ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ አደረጃጀት ወደ ተግባር ለመግባት እንደሚያስችልም ተጠቁሟል። የኢትዮጵያን ስፖርት ለመምራት ለኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር እንዲሁም ስፖርት ኮሚሽን ከተሰጠው ኃላፊነትና ተግባር ባሻገር በሚኒስትሮች ምክር ቤት የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት በማቋቋም ስፖርቱ ስለሚዳብርበት፣ ስለሚስፋፋበትና ስለሚመራበት ሁኔታ የተደነገገ መሆኑ ታውቋል።የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጉባኤውን በማስጀመር የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት መንግስት የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም ለዘርፉ ድጋፉን ሲያደርግ ቆይቷል፤ ለወደፊትም ይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። ዘርፉ በተለያዩ ጫና ዝግመታዊ ለውጥ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ችግሮች ቢስተዋሉም በውስን ስፖርቶች ግን አሁንም ሃገርን በማስጠራት ላይ ይገኛል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የስፖርት ዘርፍን ተወዳዳሪነት ለማላቅ፣ የህዝብ ኃላፊነትን ለማጎልበት፣ ዘርፉ እውቀት ባላቸው እንዲመራ የማድረግና ሁሉም ነገር በተወዳዳሪነት፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት እንዲሁም በውጤታማነት ብቻ መመራት እንደሚኖርበትም ጠቁመዋል። እንደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ በስፖርቱ ዘርፍ ፋይዳቸው ሚዛን በሚደፋ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በህጻናትና ታዳጊዎች በማተኮር ሃብትና ጉልበት በሚጠይቀው ሁሉ ዘርፉን ማዘመን የግድ ነው። ምክር ቤቱም ከዚህ አኳያ ኃላፊነቱን ለመወጣት ተጠናክሮ ወደ ተግባራዊነት ሊገባ ይገባል። የምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢዋ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው እንደገለፁት ምክር ቤቱ ምስረታ ስፖርቱ ደረጃውን በጠበቀና ወቅቱ በሚጠይቀው መልኩ እንዲመራ ያደርጋል። መንግሥት እስከ ታችኛው አደረጃጀት በመውረድና ከዘርፉ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት የሚያግዝ በመሆኑ በስፖርቱ የሚስተዋለውን ማነቆ ለመፍታት ያስችላል። ከዚህም ባለፈ ስፖርቱ ከእስካሁኑ በጠነከረ ሁኔታ እንዲጓዝ፣ አስተማማኝና ሰላማዊ ሆኖ እንዲካሄድ እንዲሁም ለኢኮኖሚው ጠንካራ መሰረት እንዲጥል የምክር ቤቱ መመስረት የሚረዳ መሆኑንም አብራርተዋል።ስፖርቱ በ1990 በተቀረጸው ፖሊሲ መሰረት ከመጓዝ ይልቅ በርካታ ስር ነቀል መፍትሄ የሚፈልጉ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ እንዲሁም እንደሚጠበቀው በጥሩ ቁመና ላይ አለመገኘቱ አዲስ ፍኖተ ካርታ መቀረጹንም በማቋቋሚያ ጉባኤው ላይ ተገልጿል። በፍኖተ ካርታው ላይ እንደተገለጠው ከሆነም የስፖርት ፖሊሲው በአፈጻጸም በኩል ችግሮች እንዳሉበት ተጠቁሟል። ስፖርት አደረጃጀቱ ብቃትና ጠንካራ አለመሆን፣ የማህበረሰብ ስፖርት ተሳትፎ አናሳ መሆን፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ትጥቅና ቁሳቁስ እጥረት፣ የስፖርት ባለሙያዎች ልማት ጥራትና አቅርቦት ችግር፣ የላቁ ስፖርተኞች ልየታና ልማት ችግሮች፣ ከስፖርት ውድድሮች፣፣ ከትምህርትና ምርምር ጋር ተያይዞ የሚታይ ችግር እንዲሁም እስካሁን ያልተሰራበት የስፖርት ለማህበራዊ ልማትና ለሃገር ብልጽግና አለማዋል ዋናዋናዎቹ ችግሮች መሆናቸው በሰነዱ ላይ ተዘርዝሯል።በመፍትሄ ሃሳብ ደረጃም በስፖርት ፖሊሲው ላይ ክለሳ ማድረግ፣ የአደረጃጀት ማሻሻያ፣ ዓለም አቀፍ ህግጋትን ህዝብ ወደሚረዳው ቋንቋ በመተርጎም ተደራሽ ማድረግ፣ የገንዘብ አቅርቦትና የሃብት ክምችትን ማሳደግ፣ የላቁ ስፖርተኞች ልየታ ልማት፣ የሃገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሳታፊነትን ማሳደግ፣ ዘመናዊ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና መስጠት እንዲሁም ስፖርትን ለማህበራዊ ልማትና ለሃገር ብልጽግና ለማዋል የሚያስችሉ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ የሚሉት ተጠቅሰዋል። ከዚህ ጎን ለጎንም ብሔራዊ የስፖርት ሙዚየም መገንባት አስፈላጊ መሆኑም ተመልክቷል።የቀረበውን ፍኖተ ካርታ ተከትሎ በምክር በተሳታፊዎች ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል። በምክር ቤቱ ማቋቋሚያ የስፖርት ባለሙያዎችን ባካተተ መልኩ አለመሆኑ ቅሬታ የፈጠረ ሲሆን፤ የተጠሪና የፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የሥራ ድርሻ ተለይቶ በፍኖተ ካርታው ላይ መቅረብ እንዳለበት ተጠቁሟል። ይህ ችግርም ከዓለምና ሃገር አቀፍ ስፖርት ማህበራቱ ጋር ለመስራት ችግር እንደሆነበት እና ለአሰራር ምቹ እንዲሆን ራሱን መቻል እንደሚገባ ተገልጿል። መንግሥት ለሌላው ዘርፍ የሚሰጠውን አይነት ትኩረት መስጠት እንደሚገባውና ስፖርቱ ራሱን እስኪችል ማገዝ እንደሚገባም በውይይቱ ተሳታፊዎች ተነስቷል። የባለሃብቶች ተሳትፎ አናሳ መሆንን ተከትሎ በዘርፉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማበረታቻ ቢደረግ፣ ለትልልቅ ስታዲየሞች መተዳደሪያ የሚሆን ደንብ አለመኖር፣ ስፖርታዊ ውድድሮች የችግር ምክንያት በመሆናቸው በፍኖተ ካርታው ላይ አቅጣጫ ሊቀመጥለት እንደሚገባም ተጠይቋል። በፖሊሲው ላይ የህዝባዊ አደረጃጀቱ በአማተሮች እንዲመራ የሚጠቁም ቢሆንም ለስፖርቱ ውጤታማነት አመራሩ ከፊል ፕሮፌሽናል መሆን እንደሚገባውም ተገልጿል። በአካል ጉዳተኞች ዙሪያም ፍኖተ ካርታው የተሻለ ትኩረት እንዲሰጥ፣ ስፖርተኞች ማበረታቻ አለመኖር ከብሄራዊ ቡድን እያራቃቸው በመሆኑ ቢታሰብበት፣ በየክልሉ ያሉ ስታዲየሞች ደረጃ ከመስፈርት በታች በመሆኑ ትኩረት ቢሰጠው እንዲሁም ስፖርቱን ከሰላምና ጠና መድረክነቱ ባለፈ በቱሪዝምና ገቢ ማግኛ መንገድ ማሳደግ ቢቻል የሚሉ ሃሳቦች ተንጸባርቀዋል። በመድረኩ ማጠቃለያ ላይም የተነሱ አስተያየቶችን በማካተት ሪፎርሙ እንደሚሻሻልም ተጠቁሟል።በማቋቋሚያ ጉባኤው ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ በሚኒስቴሩ የስፖርት ዘርፍ ዲኤታ አቶ ሃብታሙ ሲሳይ፣ የስፖርት ኮሚሽነሩ ኤልያስ ሽኩር፣ ምክትል ኮሚሽነሩ ጌታቸው ባልቻ፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ሃገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት ፕሬዚዳንቶችና የጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ለስፖርቱ እድገት ጉልህ ሚና ያላቸው የክብር እንግዶችና ባለድርሻዎች ተገኝተዋል። አዲስ ዘመን ጥቅም5/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=22532
dd2c9c7b55c39e085c52be6d492ca6ec
85f47c0c1d60fc34dafa3b55711aa596
የዓለም ምርጥ ሴት አትሌቶች የመጨረሻ እጩዎች ታወቁ
ስፖርት
ከተያዘው ሳምንት ጀምሮ ስሙን የዓለም አትሌቲክስ በሚል የቀየረው የስፖርቱ የበላይ አካል ዓመታዊው የምርጥ አትሌቶች ምርጫውን ሊያካሂድ ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ስፖርት ወዳዱ ህብረተሰብ እንዲሁም የአትሌቶቹ የቅርብ ሰዎች በኢሜይል እንዲሁም በማህበራዊ ድረገጾች በተዘጋጁት ድምጽ መስጫዎች ይገባዋል ለሚሉት አትሌት ይሁንታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በእስካሁኑ 25 ከመቶ ድርሻ ባለው የህዝብ ድምጽ እና ባለሙያዎች ባደረጉት ምርጫ መሰረትም የመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ታውቀዋል፡፡በዚህም መሰረት ባለፈው የውድድር ዓመት ብቃታቸው እንዲሁም በቅርቡ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ባገኙት ውጤት መሰረት ከአምስት ሃገራት አምስት የተለያዩ ሴት አትሌቶች ለመጨረሻው ዙር በቅተዋል፡፡ በመካከለኛ ርቀት ኔዘርላንዳዊቷ ሲፈን ሃሰን ከዓመቱ ምርጥ አትሌቶች መካከል ተገኝታለች፡፡ አትሌቷ በአበረታች ቅመሞች ምክንያት በምርመራ ላይ ከሚገኙት አሰልጣኟ አልቤርቶ ሳላዛር ጋር በተያያዘ በጥርጣሬ ትታይ እንጂ በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና በ1ሺ500 እና10ሺ ሜትር አሸናፊ መሆኗ በእጩነት ሊያስመርጣት ችሏል። ይህም ብቻ ሳይሆን የ 1ሺ500 እና 5ሺ ሜትር  የዳይመንድ ሊግ የድርብ ድል ባለቤቷ ሲፈን በማይል ውድድርም 4:12.33 የሆነ የዓለም ክብረወሰንን በሞናኮ አስመዝግባለች። ይህ በአመቱ ያስመዘገበችው ስኬትም አትሌቷን ከዘጠኝ ቀናት በኋላ በሞናኮ በሚኖረው ስነስርዓት የዓለም ምርጥ ሴት አትሌት በመባል የክብሩ ባለቤት እንድትሆን ይረዳታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የአጭር ርቀት ተወዳዳሪዋ ጃማይካዊት አትሌት ሼሊ-አን ፍራዘር-ፕረይሲም በዓመቱ በተካፈለችባቸው ውድድሮች ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች ለሽልማቱ አሳጭቷታል። አትሌቷ በዶሃው ቻምፒዮና በተካፈለችባቸው የ100 ሜትር እና 4በ400 ሜትር ውድድሮች 10 ሰከንድ ከ71 ማይክሮ ሰከንድ እና 41 ሰከንድ ከ44 ማይክሮ ሰከንድ የሆነ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ነበረች። የ32 ዓመቷ ፕረይሲ በአሜሪካ አህጉር በሚዘጋጀው ውድድር የ200 ሜትር አሸናፊም ነበረች፡፡ የዓለም ፈጣኗ ሴት አትሌት በአመቱ ከተሳተፈችባቸው አስር ውድድሮች በሰባቱ ቀድማ በመግባት ብርቱ አትሌትነቷን አስመስክራለች፡፡ የሰው ልጅ ማራቶንን ከአንድ ሰዓት በታች መግባት እንደሚችል የሃገራ ልጅ በሙከራ ውድድር ባስመሰከረበት ማግስት የዓለም ሴቶች የማራቶን ክብረወሰንን የሰበረችው ኬንያዊት አትሌት ብርጊድ ኮስጊም ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች መካከል ተገኝታለች፡፡ በቺካጎ ማራቶን ለ16 ዓመታት የቆየውን ክብረወሰን 2:14:04 በሆነ ሰዓት በመግባት የሰባበረችው አትሌቷ የለንደን ማራቶን አሸናፊም ነበረች፡፡ ወጣቷ አትሌት በዓመቱ በተሳተፈችበት የግማሽ ማራቶን ውድድርም 1:04:28 የሆነ ፈጣን ሰዓት አላት። ሌላኛዋ እጩ አሜሪካዊቷ ደሊላ ሙሃመድ በዓመቱ በ400 ሜትር ያሳየችው አቋም ሊያስመርጣት ችሏል፡፡ አትሌቷ በሃገር አቀፍ ቻምፒዮና 52 ሰከንድ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ቀዳሚዋ ስትሆን፤ በ400 ሜትር መሰናክል በራሷ የተያዘውን ክብረወሰን 52 ሰከንድ ከ16 ማይክሮ ሰከንድ በማሻሻል ብቃቷን አስመስክራለች፡፡ በ4 በ400 ሜትርም በተመሳሳይ የዓለም ቻምፒዮን ናት፡፡ በርዝመት ዝላይ ቬንዙዌላዊቷ ዩሊማር ሮጃስ ለመጨረሻው ዙር መብቃት ችላለች፡፡ አትሌቷ 15.37 ሜትር በመዝለል የዓለም ቻምፒዮን ስትሆን፤ ከዚህ ቀደም የዘለለችው 15.41 ሜትር ደግሞ ከዓለም የምንጊዜም ቀዳሚዎቹ መካከል ሊሰፍርላት ችሏል፡፡ ሮጃስ አህጉር አቀፍ ውድድርን ጨምሮ ከተካፈለችባቸው 12 ውድድሮች ዘጠኝ በሚሆኑት ላይ አሸናፊ መሆኗ ከዓለም ምርጦች ተርታ ያሰልፋታል የሚል ግምት አግኝታለች፡፡አዲስ ዘመን ጥቅም4/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=22486
0b957c344747e02c7e37aa257da3ec5c
6d2cfade0e42aee16171d154944096b8
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በታላቅ የስኬት ጎዳና
ስፖርት
ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዓለም በተለይም በረጅም ርቀት ውድድሮች ገናና ስም በማትረፍ ትታወቃለች።በረጅም ርቀት ውድድሮች ቁጥር ስፍር የሌላቸው ብርቅዬ አትሌቶቿ ከሰሩት ዘመን የማይሽረው ታሪክ ጎን ለጎን በአትሌቲክሱ ዓለም አንድ የሚጠቀስ ታላቅ ስኬትም እያስመዘገበች ትገኛለች።ይህ ስኬትም በጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ መስራችነት የተጀመረው ‹‹ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ›› የተሰኘው ታላቅ የጎዳና ላይ ውድድር ነው።ኢትዮጵያ ስፖርትን እንደቱሪዝም በመጠቀም ረገድ ብዙ ባልተጓዘችበት ዘመን ከሁለት አሥርት ዓመታት በፊት የተጠነሰሰው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ከስፖርታዊ ኩነቱ አይሎ የስፖርት ቱሪዝም ጥያቄን እስከ መመለስ ደርሷል።ከዓለም ምርጥ አሥር ተወዳጅና ሳቢ የጎዳና ላይ ሩጫዎች መካከል አንዱ የሆነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተወዳጅነት እንደዘለቀ ከሚያገኘው ገቢ ለሰብዓዊ እርዳታ እያዋለ ኢትዮጵያን በበጎ እያስጠራ ይገኛል።ይህም የዓለም አትሌቲክስ አፍቃሪዎችን ከየአቅጣጫው እየሳበ የተሳታፊዎቹን ቁጥር ከዓመት ዓመት እንዲመነደግ አስችሎታል።ከወር በፊትም “በሌትስ ዱ ዚስ” የሚታገዘውና በእውቁ የሩጫ መጽሔት “ረነርስ ወርልድ” የሚቀርበው “ዘ ቻሌንጅስ አዋርድ” የተሰኘ ውድድር በጎዳና ላይ ውድድር ዝግጅት ዘርፍ ትልቁን ዓለም አቀፍ ሽልማት ማሸነፍ ችሏል።ይህም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ከዓለማችን ስኬታማ የውድድር አዘጋጆች ጎራ ሲያሰልፈው የሀገራችንን ስም በበጎ የሚያስነሳ ሌላ ትልቅ ብሔራዊ ሀብት አድርጎታል።ደማቁና ተናፋቂው ዓመታዊ የአስር ኪሎ ሜትር ውድድርም ነገ ለ19 ጊዜ 45ሺ ተሳታፊዎችን ሊያወዳድር ዝግጅቱን አጠናቆ እየተጠባበቀ ይገኛል።ይህንን በማስመልከትም አዲስ ዘመን ቅዳሜ በውድድሩ ዋዜማ ላይ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ አየለ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ይመስላል፡፡አዲስ ዘመን፡- ነገ በጉጉት ስለሚጠበቀው ውድድር ምን ማለት ይቻላል?አቶ ኤርሚያስ፡- ይህንን ውድድር በ1993 ዓም የጀመርነው በ10ሺ ሰው ብቻ ነበር፤ በየዓመቱ ሳይቋረጥ ሲካሄድ ቆይቶም ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ ሲካሄድ 45ሺ ሰዎችን በማሳተፍ ነው።በእርግጥ ፍላጎቱ ከዚያም የበለጠ ነው፤ ነገር ግን ለውድድሩ ጥራት በማሰብ እንዲሁም ከመወዳደሪያ ቦታ ጥበት ጋር በተያያዘ ቁጥሩን ገድበነዋል።ሩጫው እንደሚታወቀው ሁሉንም የሚያሳትፍ በመሆኑ ተሳታፊዎችን የሚያዝናና የሚያስደስት ይሆናል፡፡አዲስ ዘመን፡- ዘንድሮ ካለፉት 19 ዓመታት የተለየ ምን አዲስ ነገር እንጠብቅ? አቶ ኤርሚያስ፡- ቁጥሩ ላይ ጭማሪ አድርገናል፣ አብዛኛው ተሳታፊ ርቀቱን የሚጨርሰው በእርምጃ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም ከአንድ ሰዓት በታች የሚገቡ ሯጮችን ቀድመው እንዲነሱ የሚያደርግ የተለየ ቀለም ያለው ከነቴራ (አረንጓዴ ማዕበል) እንዲለብሱ በማድረግ ላለፉት ዓመታት ተሞክሯል፤ ነገር ግን እንደሚፈለገው አልሆነልንም ነበር።በመሆኑም በሰዓት በመከፋፈልና ተሳታፊዎች እንደ ከነቴራቸው ቀለም በየመካከሉ አካላዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ በመቆየት ከጥቁር አንበሳ አካባቢ የሚጀምሩትን የአትሌቶችን እና ሌሎቹን በመለያየት የምናካሂድ ይሆናል።እንደተለመደው ውድድሩ ስድስት ሳምንት ሲቀረው ጀምሮ ተሳታፊው ለሩጫው ዝግጅት እንዲያደርግ ቅስቀሳ ስናደርግ ነበር።የመጀመሪያው ሳምንት ዱብ ዱብ ሲሆን፤ ተሳታፊዎች እንቅስቃሴ ከጀመሩ በኋላ ጤናቸውን እንዲመለከቱ ለማድረግ ሁለተኛውን ሳምንት ጤና ብለንዋል።እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን አረንጓዴ ጎርፍ በሚል ስያሜ ነው የሚጠራው፤ ነገር ግን ጎርፍ ከመሆኑ አስቀድሞ ምንጭ ነውና እኛም የአዳዲስ ስፖርተኞች መታያ እንደመሆናችን ምንጭ ስንል ሰይመነዋል።በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም ለመሳተፍ የሚፈልጉ አትሌቶች ሁሉ ጥያቄ ያቀርቡ ነበር አሁን ግን ይህ እንዳይፈጠር አስቀድመን የማጣሪያ ውድድር አዘጋጅተን ነበር።ቀጣዩን ሳምንት የበጎ ፈቃደኞች ሳምንት ያልነው ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ልምድ የማካፈል ስራ አከናውነናል።አምስተኛው ሳምንት ደግሞ የጽዳት በማድረግ ውድድሩ የሚካሄድበትን ስፍራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ከመነሻ እስከ መድረሻ ያለውን አጽድተናል። የመጨረሻውን ሳምንትም የስፖርት ኤክስፖ ሆኖ ነው ያለፈው።አዲስ ዘመን፡- ሌሎች ከሩጫው ጋር የተያያዙ መርሐ ግብሮችስ ይኖራሉ?አቶ ኤርሚያስ፡- በተለየ የምንሰራው የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የመሮጫ ከነቴራዎቹን ለበጎ አድራጎት ለማዋል በ900ብር እንዲሸጥ የማድረግ አንዱ መርሐ ግብር ነው።በዚህም ዘንድሮ በዋግህምራ ዞን አንድ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የሚውል ይሆናል። ዛሬ የሚካሄደው የህጻናት ሩጫ እና ምሽት ላይ ደግሞ ከውጪ ሀገራት የሚመጡ ተሳታፊዎቻችንን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አቀባበል የምናደርግበትም መርሐ ግብር አለን፡፡አዲስ ዘመን፡- ታላቁ ሩጫ ከሩጫነቱ በዘለለ የሃገር ገጽታ መገንቢያም ሆኗልና በዚህ የረጅም ጊዜ ቆይታው እንደሃገርም ሆነ እንደ ተቋም ያሳካችሁት ምንድነው?አቶ ኤርሚያስ፡- ያሳካነው በርካታ ቢሆንም በዋናነት ግን አራት ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል፤ የመጀመሪያው ከዓመት ዓመት የሃገራችንን በጎ ገጽታ ማሳየት መቻላችን ነው።ወቅታዊ ሁኔታዎች ባይፈትኑን ደግሞ እጅግ በርካታ የውጪ ሃገራት ዜጎች በሩጫው ለመካፈል ወደ እዚህ ይመጣሉ።ያልተቋረጠ የውጪ ሃገራት መገናኛ ብዙሃን ሽፋን ማግኘትም ለሃገሪቷ መልካም ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ሚና አለው።ሁለተኛው ስኬት በሃገር ውስጥ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ እንዲለመድ አድርገናል።ሌላኛው ለአትሌቶች ምቹ የመታያ መድረክ መሆናችን ነው።ማናጀሮች አትሌቶችን ለመመልከት የሚታደሙ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአብዛኛው ከአንድ እስከ አስር የሚወጡት አትሌቶች ማናጀር የማግኘት እድላቸው የሰፋ ነው።ይህም ለአትሌቶች ምቹ መድረክ ይፈጥራል።ሌላኛው ጉዳይ ደግሞ የበጎ አድራጎት ስራ ሲሆን፤ ባለፉት ስድስትና አምስት ዓመታት ብቻ ያሰባሰብነው ገንዘብ ወደ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው፤ በዚህም በርካታ ድርጅቶችን መርዳት ችለናል፡፡አዲስ ዘመን፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እንደ ሌሎች ሃገራት ውድድሮች በዓለም አትሌቲክ ደረጃ ተሰጥቶት ለምን አይካሄድም የሚለውም የብዙዎች ጥያቄ ነውና ውድድሩ ደረጃ እንዲያገኝ ያሰባችሁት ነገር አለ?አቶ ኤርሚያስ፡- እኛ የኤይምስ አባል ነን ይህም የዓለም አትሌቲክስ ከሚሰጠው ደረጃ በእኩል መቀመጥ የሚችል ነው።እንደ እኛ ሁሉ ከ400 በላይ የሚሆኑ ሩጫዎችም የዚህ አባል ሲሆኑ የእኛ የጎዳና ላይ ሩጫም ከእነዚህ መካከል አንዱና ታዋቂ ከሆኑት ሩጫዎች መካከል ነው።በመሆኑም ብዙም አስፈላጊ መስሎ አልታየንም።አዲስ ዘመን፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እዚህ ደረጃ ሲደርስ ብዙ ፈተናዎችን አልፎ ነው፣ አሁንም ፈተናዎች አሉበትና ብትጠቅሳቸው፡፡አቶ ኤርሚያስ፡- ባለፉት ጊዜያት ውድድሩን በየክልሉ ለማስፋት እቅድ ነበረን፤ ይሁንና ሃገሪቷ ውስጥ የነበረው ሁኔታ ብዙ ህዝብ ለመሰብሰብም ሆነ እንዲህ አይነት ዝግጅት ለማድረግ ምቹ አልነበረም።ይህም ብዙ ፍላጎቶቻችንን ነው የገታብን።ሌላው ሁሌም ውድድሩ ሲደርስ አሳሳቢ የሚሆንብን የውድድር ስፍራ ጉዳይ ነው።ቦታውን ቀድሞ አለማወቅ በስራችን ላይ ትልቅ ተጽእኖ እያደረሰብን ሲሆን፤ የመወዳደሪያ ቦታውን ሩጫው ሲደርስ ነው የምናውቀው።በመሆኑም ሩጫው የሃገሪቱ ጭምር በመሆኑ በከተማ አስተዳደሩና በሚመለከታቸው ሁሉ ትኩረት ቢሰጥበትና ቋሚ ቦታ ቢሰጠን መልካም ነው። በመጨረሻም ለተሳታፊዎች ይህ ሩጫ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ በመሆኑ በተለመደ ጨዋነቱ ሩጫው ላይ እንዲሳተፍና በኃላፊነት ስሜት የከተማዋን ንጽህና እንዲጠብቅም መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።አዲስ ዘመን፡- አቶ ኤርሚያስ አየለ ለሰጠኸኝ ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡አቶ ኤርሚያስ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡አዲስ ዘመን ጥቅም6/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=22603
4b966f7dda5055dc84699757de471b1a
417097662726bcc1924106189587c501
ፕሪሚየር ሊጉ እንዲጀመር ክልሎች የጸጥታ ማረጋገጫ አልሰጡም
ስፖርት
ክልሎች ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ማረጋገጫ አለመስጠታቸው የፕሪምየር ሊጉን መካሄድ አሳሳቢ እንዳደረገው አብይ ኮሚቴው ለብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ገለጸ።ምክር ቤቱም የስፖርቱ ተዋናዮች ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ጠቁሟል። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከዚህ ዓመት ጀምሮ አዲስ በተቋቋመው አቢይ ኮሚቴ የበላይነት እንደሚካሄድ መወሰኑ ይታወቃል።የውድድር ዓመቱን ህዳር 13 እና 14 ለማስጀመር ዕቅድ የያዘ ሲሆን፤ ትናንት በተቀመጠው መርሐ ግብር መሰረት በአዳማ ከተማ እጣ የማውጣት ስነስርዓት አካሂዷል።ይሁን እንጂ የክልል ጸጥታ አካላት በደህንነት ዙሪያ አስተማማኝ ማረጋገጫ እንዲሰጡ በደብዳቤ ቢጠየቁም ምላሽ አለመስጠታቸውን የኮሚቴው ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ከትናንት በስቲያ በተካሄደው የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ማቋቋሚያ ጉባኤ ላይ ገልጸዋል፡፡ኮሚቴው ምላሽ አለመስጠቱን ተከትሎ በድጋሚ ደብዳቤ ወደ ክልል ጸጥታ አካላት ቢልክም ማረጋገጫውን አስካሁን ማግኘት አልተቻለም።አንዳንድ ክልሎች በበኩላቸው በከተማ ደረጃ ብቻ ምላሽ መስጠታቸው ግራ አጋቢና የውድድር ዓመቱን ለማስጀመር አስተማማኝ እንዳልሆነም በሰብሳቢው ተጠቁ ሟል። በመሆኑም ምክር ቤቱ ሁኔታውን አመዛዝኖ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ሁሉም የስፖርቱ ተዋናዮች ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።ኮሚቴው በደብዳቤ ከመጠየቅም ባለፈ ምናልባትም ኃላፊዎቹ ስራ ሊበዛባቸው ስለሚችል ትኩረት ካልሰጡት በአካል ክልሎች ድረስ በመሄድ መወያየት እንዳለባቸውም ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።ከዚህም ባሻገር ምቹ ሁኔታዎችን ተመልክቶ ሊግ ማስጀመሪያውን ጊዜ ማመቻቸት እንደሚገባ በማንሳት መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚነጋገሩና ጊዜ ወስደው እንደሚሰሩም ጠቁመዋል። አዲስ ዘመን ጥቅም6/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=22608
092a5b4caa92ecb755a8133ede3bc518
956e9f4278467e5039f6ce84334848ed
በኒውዮርክ ማራቶን ኢትዮጵያውያን ለድል ይጠበቃሉ
ስፖርት
ከዓለማችን ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች አንዱ የሆነው የኒውዮርክ ማራቶን ዛሬ ይካሄዳል፡፡ ከሦስት ሳምንት በፊት በዶሃ የዓለም ቻምፒዮና በማራቶን የተሳተፉ በርካታ አትሌቶች በዚህ ውድድር እንደሚሳተፉ ቢጠበቅም ከዓለም ቻምፒዮናው ወዲህ እነዚህ አትሌቶች ለሦስት ወራት ማራቶን እንዳይሮጡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማስጠንቀቁን ተከትሎ ጠንካራ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አይሮጡም፡፡ በዓለም ቻምፒዮናው የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀው ሌሊሳ ዴሲሳ ያለፈው ዓመት የኒውዮርክ ማራቶን አሸናፊ ሲሆን ይህን ድል ለመድገም ከፍተኛ ግምት የተሰጠው በውድድሩ የማይካፈል አትሌት ነው፡፡ ሌሎች ጠንካራ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ግን ከኬንያውያን ጋር ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ በሴቶች መካከል በሚካሄደው ውድድር የ2018 ቻምፒዮኗ ኬንያዊት ማሪ ኪታኒ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት አግኝታለች፡፡ 2፡22፡48 በሆነ ሰዓት ሁለተኛውን የውድድር ክብረወሰን ማስመዝገብ የቻለችው ኪታኒ በኒውዮርክ ማራቶን ለአምስተኛ ጊዜ ለማሸነፍ ተዘጋጅታለች፡፡ ኪታኒ ካለፉት አምስት ውድድሮች አራቱን ማሸነፍ ብትችልም ከአስራ ስድስት ዓመት በፊት በማርጋሬት ኦካዮ ተይዞ የቆየውን 2፡22፡31 የሆነ የቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል አልቻለችም፡፡ ዘንድሮ ግን ይህን ክብረወሰን ለማሻሻል እንደምትሮጥ አሳውቃለች፡፡ ባለፉት አራት ውድድሮች ሁለተኛ ሆና ማጠናቀቅ የቻለችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሩቲ አጋ ኪታኒን የማሸነፍ ግምት ቢሰጣትም በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና በመሳተፏ ኒውዮርክ ላይ ተፎካካሪ ላትሆን ትችላለች፡፡ ያም ሆኖ ባለፈው ሁስተን ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው በላይነሽ ፍቃዱ ጠንካራ ፉክክር ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በላይነሽ በማራቶን 2፡26፡41 የሆነ የግሏ ፈጣን ሰዓት አላት፡፡ 2፡28፡06 ሰዓት ያላት ቡዜ ድሪባ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል አንዷ ነች፡፡ በወንዶች መካከል በሚካሄደው ውድድር የዓለም ቻምፒዮኑ ሌሊሳ ዴሲሳ ተሳታፊ ባይሆንም ባለፈው ዓመት በኒውዮርክ ማራቶን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ሹራ ቂጣታ ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቶታል፡፡ እስካሁን አስራ አንድ የማራቶን ውድድሮችን ያደረገው ሹራ ብዙ የአሸናፊነት ታሪክ ባይኖረውም ገና ሃያ ሦስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኝ መሆኑ ወደ አሸናፊነት ሊመጣ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ታምራት ቶላ የዚህ ውድድር አሸናፊ የመሆን አቅም እንዳለው እየተነገረ ነው፡፡ የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ታምራት 2017 ላይ በዱባይ ማራቶን ካሸነፈ ወዲህ በጥሩ አቋም ላይ ባይገኝም በማራቶን ጥሩ አቅም ያለው አትሌት ነው፡፡ ባለፈው ሚያዝያ በለንደን ማራቶን ስድስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ታምራት ባለፈው ቦጎታ ማራቶን አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል፡፡ኬንያዊው አትሌት ጂኦፍሪ ኮምዎረር በዛሬው ውድድር ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ በርካታ የግማሽ ማራቶን ድሎችን በማጣጣም የሚታወቀው ኮምዎረር በማራቶን ትልቅ ስም ባይኖረውም ዛሬ ለኢትዮጵያውያኑ ፈተና እንደሚሆን እምነት ተጥሎበታል፡፡አዲስ ዘመን ጥቅምት23/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=21918
bc9cfed9e1edc3d24d87d74c2d9c5712
b8381aa3bb617ed9451aee1bd182f430
ጁንታው የህግ ታራሚዎችን በመቀሌ ከተማ ውስጥ በመልቀቅ ዝርፊያ እንዲፈጸም ማድረጉን የከተማዋ ከንቲባ አስተወቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
መሀመድ ሁሴን አዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታ በትግራይ ክልል ባሉ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የህግ ታራሚዎችን ሰብስቦ በመቀሌ ከተማ ውስጥ በመልቀቅ ዝርፊያ እንዲፈጸም ማድረጉን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ።የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በመንግሥት የተወሰደውን የህግ ማስከበር ዕርምጃ ተከትሎ የጁንታው አባላት በክልሉ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ በተለያዩ ወንጀሎች ተይዘው የእስር ጊዜያቸውን እየፈጸሙ የነበሩ ታራሚዎችን መቀሌ ከተማ ለቀዋቸዋል። በዚህም በከተማዋ ውስጥ የዝርፊያ ወንጀል እንዲፈጽሙና ህዝቡ በስጋት ውስጥ እንዲወድቅ አድርገዋል።“በበርካታ ወንጀሎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች መቀሌ ላይ ተሰብስበው እንዲለቀቁ ስለተደረገ የግለሰቦች ሱቅ ጭምር እንዲዘረፉ ተደርጓል” ያሉት ከንቲባው፤ ይሄን ያደረጉትም አንድም ተቋማትን በመዝረፍ ሰነዶችን ለማጥፋት፣ ሁለተኛም ሕዝቡ ወደ ስጋት እንዲገባና እንዲጠራጠር በማድረግ በመከላከያ ሠራዊቱ እና በአዲሱ አስተዳደር ላይ እምነት እንዲያጣ ለማድረግ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህ ረገድ መከላከያ ሠራዊት ወደ መቀሌ ከተማ ሲገባ ህዝቡ በደስታ የተቀበለው መሆኑን የሚናገሩት አቶ አታክልቲ፤ ጁንታው በከተማዋ በለቀቃቸው ሰዎች አማካኝነት የሚፈጠሩ የዝርፊያና ስርቆት ተግባራት መበራከት ግን ህዝቡ የደህንነት ስጋት እንዲያድርበት የሚያደርጉ ችግሮችን ፈጥረው እንደነበር ያስታውሳሉ። እነዚህ ችግሮች ደግሞ ሆን ተብለው በጁንታው የተቀነባበሩ መሆናቸውንም ነው ከንቲባው የተናገሩት። “ዝርፊያዎቹን በባህሪያቸው በሁለት ተለይተው መታየት የሚችሉ፤ ብዙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ሆን ብሎ እንዲዘረፉ የተደረገበትም ነው” ያሉት ከንቲባው፤ ይህ የተደረገውም በተቋማቱ ውስጥ የሚገኙ ሰነዶችን ለማጥፋት አሊያም ለመውሰድ ታስቦ የተቀነባበረም ሆነ ዝርፊያ የተፈጸመበት እንደሆነም አብራርተዋል።በከተማዋ የታየው ዝርፊያ በጁንታው ትዕዛዝ የተፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽም፤ በተለይ በዋና ዋና መስሪያ ቤቶች ላይ ራሳቸው እዚያ ይሠሩ የነበሩ ሰዎች አንዳንድ ሰነዶችን ያጠፉበት መሆኑንም ገልጸዋል። በዚህ ረገድ የከተማ አስተዳደሩ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ሙሉ ለሙሉ መዘረፉን ተናግረዋል። በተጨማሪም የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎች የሆኑት የፍትህ ተቋማት፣ ማዘጋጃ ቤት፣ ፍርድ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሰነዶች ተዘርፈዋል ያሉት አቶ አታክልቲ፤ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ሆን ተብሎ የተቀናጀ ዝርፊያ ከተፈጸመ በኋላ ተሰርቆ ነው ለማለት ተቋማቱን ክፍት አድርገው መተዋቸውንም አስረድተዋል። ይህንን አጋጣሚ የተጠቀሙ ሌሎች ዘራፊዎችም የተለያዩ ቁሳቁሶችን መዝረፋቸውንም ጠቁመዋል።አሁን ከተማው ወደ ነበረበት የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎች እየተመለሰ መሆኑን የሚያሳዩ ጥሩ እንቅስቃሴዎች አሉ ያሉት አቶ አታክልቲ፤ ህብረተሰቡን ያማከለ ሥራ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን እየተሠራ ስለሆነ በአጭር ቀናት ውስጥ መቀሌ ወደነበረችበት መደበኛ እንቅስቃሴ እንደምትመለስ አረጋግጠዋል።ለዚህም “በከተማ ደረጃ በምናቋቁመው ምክር ቤት ሕዝቡ በቀጥታ የሚመርጣቸው የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲዎች አባል የሆኑና ለውጡን ደግፈው ሕዝቡን ወደ ተሻለ ደረጃ ሊያሸጋግሩ የሚችሉ አካላት ወደኃለፊነት ይመጣሉ” ያሉት ከንቲባው፤ አሁን የተፈጠረውን ጊዜያዊ ምስቅልቅል በመቆጣጠርና በመምራት ኃለፊነት ወስደው የሚሠሩ፣ ሕዝቡም የተቀበላቸው እና ጥሩ ስነምግባር ኖሯቸው በሕብረተሰቡ አካባቢ ያለውንና የሚነሱትን የፍትህ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በፍቃደኝነት መሥራት የሚችሉ ሰዎች በሙሉ የሚካተቱበት ዕድል እነዳለ አስታውቀዋል፡ አዲስ ዘመን ታህሳስ8/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37507
4fd75355e29a2876aa4ff66041cfc19a
7eb7b13444dfc85cd80d9b906176bc4c
በኮሮና ዙሪያ የሚስተዋለውን መዘናጋት ለመቅረፍ የማንቂያ መርሃ ግብር ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
በኃይሉ አበራአዲስ አበባ፡- በሀገራችን በኮቪድ-19 ዙሪያ በህብረ ተሰቡ መካከል ሰፊ መዘናጋቶች እየታየ በመሆኑ በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ እና ለሞት እየተዳረጉ በመሆኑ መዘናጋቱን ለመቅርፍ የሚያስችል ለአንድ ወር የሚቆይ የማንቂያ መርሃግብር መጀመሩን የአራዳ ክፍለ ከተማ የወጣቶች አደረጃጀት አባላት ገለጹ። የአራዳ ክፍለ ከተማ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አምባሳደር ረሂማ ዋበላ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጠችው አስተያየት በክፍለ ከተማው 20 የሚሆኑ የተለያዩ የወጣት አደረጃጀት በጎ ፈቃደኛ አምባሳደሮች ኮቪድ-19 መከላከልን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች፣ በአረጋውያን ቤት እድሳት እና በመሳሰሉት የበጎ ፍቃድ ስራዎች እየሰሩ ይገኛሉ። በተለይ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ መዘናጋት እየተስተዋለ በመሆኑ ህብረተሰቡ ካለበት ሰፊ መዘናጋት እንዲነቃ እና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲወስድ ለማንቃት ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብላለች።የንቅናቄው ዓላማ ህብረተሰቡ ግንዛቤ ቢኖረውም እንኳ ባለው መዘናጋት የተነሳ ለኮቪድ-19 እየተጋለጠ በመሆኑ እያንዳንዱ ሰው በሁሉም አካባቢ ርቀቱን እንዲጠብቅ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስኮችን በአግባቡ እንዲጠቀም፣ እጅን በውሃና በሳሙና ደጋግሞ እንዲታጠብ እና አልኮል ወይም ሳኒታይዘር እንዲጠቀም የማስታወስ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ወጣት ረሂማ ተናግራለች። የአራዳ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ አቶ ተካ ደመቀ በበኩሉ እንደገለጸው በኮቪድ-19 ዙሪያ አስፈላጊ ጥንቃቄ ማድረግን እየዘነጋ የመጣውን ማህበረሰባችንን ለማንቃት በሚል በትናንትናው እለት በተጀመረው የማንቂያ መርሃ ግብር ለቀጣይ አንድ ወር የሚቆይ ሰፊ ንቅናቄ ይሰራል።በአንድ ወር ቆይታውም በጎ ፈቃደኛ ወጣት አምባሳደሮችንና ሌሎች ወጣት አደረጃጀቶችን በየቦታው በማስተባበር፣ ህብረተሰቡ ርቀቱን እንዲጠብቅ፣ ማስክ በአግባቡ እንዲያደርግ ከመዘናጋቱ እንዲነቃ እና ሌሎችንም እንዲያስተምር ተደጋጋሚ ንቅናቄ ይደረጋል ብሏል።ከዚህ በፊት በአራዳ ክፍለ ከተማ ደረጃ ሰፊ የማንቂያ ንቅናቄ ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሰው አቶ ተካ በዚህ ሁለተኛ ዙር የማንቂያ መርሃ ግብር ህብረተሰቡ መዘናጋቱን በመስበር እና ከራሱ ጀምሮ ኃላፊነቱን በመወጣት ኮሮናን በመከላከሉ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስቧል። በማንቂያ መርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው የበጎ ፍቃደኛ አምባሳደሮችን ጨምሮ የተለያዩ ወጣት አደረጃጀቶች ከአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመነሳት በአራት ኪሎና በስድስት ኪሎ በኩል በመጓዝ ሰዎች በሚበዙበት አካባቢዎች የማንቃት ስራዎችን ሰርተዋል።በዓለም ዙሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ከ73 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውንና ከአንድ ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ በዚሁ የተነሳ ለሞት መዳረጋቸውን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃዎች ያሳያሉ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37472
9339865edb1be7e89a258ebcbc6c0f1a
34ba122f71fefb037606c9fcafc7d422
አፍሪካውያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሚፈለገው ደረጃ ኢንቨስት እንዳላደረጉ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ፋንታነሽ ክንዴአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉ አፍሪካውያን ባለሀብቶች ቁጥር በሚፈለገው ደረጃ አለማደጉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ከአፍሪካ አገሮች ለመጡ ባለሀብቶችና ሚሽን አባላት በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ፣ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የመጀመሪያው ኢንቨስትመንት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ከአፍሪካ በተለይም ከሱዳን ነበር። በአሁኑ ወቅትም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አፍሪካውያን ባለሀብቶች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም። ሆኖም ተሳትፏቸው የሚፈለገው ደረጃ ላይ አልደረሰም።እንደ ኮሚሽነር ለሊሴ ገለጻ፤ አፍሪካውያን በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስት እንዲያደርጉና ጠንካራ የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲፈጠር ይፈልጋል። ከዚህ አንጻር የተመዘገቡ የኢንቨስትመንት ቁጥሮች ግን ዝቅ ብለው እንደሚገኙ ነው። ይሄን ችግር ከማቃለል አኳያም የኢንቨስትመንት ህጉ መሻሻሉን ተከትሎ ኮሚሽኑ ከኤምባሲዎች፣ ከኢንቨስትመንት ጋር ግንኙነት ካላቸው የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ ከልማት አጋሮች እና ከተለያዩ አገሮች ከመጡ ኢንቨስተሮች ጋር ተከታታይ ውይይቶች አካሂዷል። አዲሱን የኢንቨስትመንት ህግ ለማስረዳትም ጥረት ተደርጓል። በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች ባለሀብቶች ያሉባቸውን ችግሮች በተሻለ ደረጃ ለመገንዘብ ዕድል መፍጠሩን ያስታወቁት ኮሚሽነሯ፤ ይህም በቀጣይ ኮሚሽኑ ምን ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት ለመረዳት ማስቻሉን ገልጸዋል። ተሳታፊዎችም በውይይቱ ደስተኞች እንደሆኑና በ2021 ላይ የተሻለ ውጤት እንደሚጠብቁ ገልጸውላቸዋል።ኮሚሽኑ ከትናንት በስቲያ ከአፍሪካ አገሮች ለመጡ ባለሀብቶችና ሚሽን አባላት በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን፤ ከማብራሪያው በኋላ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ለመጡ ባለሀብቶችና ሚሽን አባላት ጋር የተደረገው ምክክር ህጉ ከተሻሻለ በኋላ የተካሄደ ስድስተኛ መድረክ መሆኑ ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37459
6291b068151e380611c3bf855dc13b0a
77e6b9a3e2eb3d0b60f6a05d6f400d79
የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ብቻ ሳይሆን ለመጨረስ ታስቦ ወደሥራ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲሱ ገረመውአዲስ አበባ፡- የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች እንደ ሸገር ፕሮጀክቶች ሁሉ መጀመርን ሳይሆን መጨረስን ታሳቢ በማድረግ ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። ክልሎችም ሆኑ በፕሮጀክቱ ላይ የሚመደቡ አመራሮችና ባለሙያዎች ይህንኑ ታሳቢ አድርገው እንዲሠሩም አሳስበዋል። የሦስቱም የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች (ወንጪ፣ ጎርጎራና ኮይሻ) አስተባባሪዎች የፕሮጀክቶቹን አጠቃላይ ገጽታ አስመልክተው ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በተገኙበት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሊጀመሩ በታቀዱ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ላይ ሰፊ የልማት ፍላጎት መታዩትን ገልጸው፤ ነገር ግን ፍላጎትን ከአቅም ጋር ማጣጣም እንደሚገባ እና ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ እንደተከናወነው ከተማን የማስዋብ ሥራ ሁሉ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችም መጀመርን ሳይሆን መጨረስን ታሳቢ አድርገው ሊሠሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፤ ሁል ጊዜ ሥራን ከትንሽ በመጀመር በፍጥነት በማሳደግ የሚፈለገውን ትልቁን ነገር ማግኘት እንጂ የመሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ ያልተፈጸመበትን ምክንያት ማቅረብ አይደለም። በዚህም መሠረት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በሦስቱ ክልሎች (በኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ) እንደሚከናወኑ ተወስኗል። ፕሮጀክቶቹ ለሌሎች ልማቶች ሳቢ በሆነ መንገድ የሚሠሩ ይሆናሉ።በሦስቱም አካባቢዎች የፕሮጀክቶቹን ዓላማ በትክክል ያለመገንዘብና የማስፋት ፍላጎት ይታያል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይሄ ፕሮጀክት በክልልም ይሁን በፌዴራል መንግሥት በጀት ሳይሆን ህዝብን በማስተባበር እንደሚሠራ አመልክተዋል። የፕሮጀክቱ ዋነኛ ዓላማም በአዲስ አበባ የተከናወነውን ከተማን የማስዋብ ሥራ በየክልሉ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ማዳረስ ሲሆን፤ አስተባበሪዎች ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና ሃሳባቸውን ሰውተው በመሥራት የግሉ ሴክተር እንዲስፋፋ የበኩላቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ፕሮጀክቶቹ ተጀምረው እስከሚያልቁ የፌዴራል መንግሥት ፕሮጀክቶች እንጂ የክልሎች ፕሮጀክቶች አይደሉም። ሥራውን በማስኬድ  ሂደት የክልል ጣልቃ ገብነትም አይፈልግም። ነገር ግን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የፌዴራል መንግሥት ሥራውን ሲጨርስም ያስረክባቸዋል። ይህን ከወዲሁ ለሙያተኞች ማስገንዘብም ከአመራሮች ይጠበቃል። በገንዘብ አሰባሰብ ሂደቱ ከፌዴራል መንግሥት የመጠበቅ ዝንባሌዎች እንዳሉና ነገር ግን በፌዴራል መንግሥት የተለየ የገንዘብ ምንጭ ስለሌለ በዚህ ፕሮጀክት እሳቤ መሠረት ህዝብን የማስተባበር ሥራ እንደሚሠራ ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚያስፈልግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። በተጨማሪም ገንዘብ ሲሰበሰብ አንዳንድ ቦታ የተሳካ፣ አንዳንድ ቦታ ላይ ደግሞ ያነሰ ሊሆን ስለሚችል ገንዘቡ ሌላውንም ፕሮጅክት የልማት አካል አድርጎ ማሰብ ያስፈልጋል ብለዋል። በዚህም አጠቃላይ ገቢው ወደ ማዕከል ከገባ በኋላ የሚከፋፈል እንጂ አንዱ ክልል ያዋጣው ለክልሉ ብቻ እንደማይሆንም ጠቅሰዋል። የፕሮጀክቱ ሥራ መጀመርን ሳይሆን መጨረስን ታሳቢ ያደረገ እንዲሆንም በዚህ ሥራ ውስጥ በፌዴራል በተመደቡ የፕሮጀክት ኃላፊዎች ውጪ ክልሎች መመደብ እንደማይችሉ አሳስበዋል። የገበታ ለሀገር ሦስቱ ፕሮጀክቶች የዲዛይንና የደረሱበት ሂደት በአስተባ ባሪዎች ገለጻ ተደርጎ ውይይት ተካሂዶበታል። በውይይቱ ላይ የገበታ ለሀገር ሦስቱ ፕሮጀክቶች የሚከናወኑባቸው ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እና የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 8/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37508
5b2ed9efed9fa89cad1402051503e297
7f6ad3383ff2134d163bb9a69afdd62d
በኢትዮጵያ የተስተካከለ የግብርና ልማት ፖሊሲ ባለመቀረፁ ዘርፉ ስኬታማ ሳይሆን መቆየቱ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
አብርሃም ተወልደ አዲስ አበባ፡- የተስተካከለ የግብርና ልማት ፖሊሲ ባለመነደፉ እና ዕድገትን ከማፋጠን ይልቅ የማደናቀፍ ሚና የሚጫወቱ ፖሊሲዎች ሥራ ላይ በመዋላቸው በኢትዮጵያ ግብርናው ውጤታማ እንዳይሆን መደረጉ ተገለጸ።በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ምርምር ዳይሬክተር ዶክተር ተመስገን ደሳለኝ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት፤ የግብርና ምርትና ምርታማነት ባለማደጉ የተነሳ በምግብ ራሳችንን መቻል አቅቶን በየዓመቱ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን የምግብ ዕርዳታ ለመጠየቅ ተገድደናል።ለዚህ ደግሞ በዘርፉ የነበረው የእድገት ውስንነት አንዱ ምክንያት ሲሆን፤ በዚህም እንደማነቆ ከነበሩ ጉዳዮች ውስጥ የበጀት ማነስ፣ የሰው ኃይልንና መሬትን አቀናጅቶ አለመጠቀም እና አርሶ አደሩ የሚጠቀምባውን የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና ግብዓቶች በቀላሉ አለመገኘት ዋና ዋናዎቹ መሆናውንም ዶክተር ተመስገን ጠቁመዋል።የባለሙያው እውቀት ማነስ አንዱ ተግዳሮት መሆኑን የሚገልጹት ዳይሬክተሩ፤ አሁን ላይ ከዩኒቨርሲቲ ከሚወጣው ባለሞያ ይልቅ የአርሶ አደሩ እውቀት ልቆ ሄዷል ብለዋል። ይህም ለግብርናው የተሰጠውን ትኩረት ያክል ለዘርፉ ትምህርት እንዳልተሰጠ ማሳያ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።እንደ ዶክተር ተመስገን ማብራሪያ፤ ተማሪውም የግብርናን ትምህርት የሚመርጠው መጨረሻ ላይ ነው። ሥራም ስለማያገኝ ግብርናን የሚመርጠው ተማሪ በአቅሙ አነስ ያለ ነው። በዚህም ምክንያት አርሶ አደሩን የመደገፍ አቅሙ እያነሰ መጥቷል። ስለዚህ መንግሥት እዚህ ላይ ትኩረት መደረግ አለበት። ከዚህ በተጓዳኝ ሊታረስ ከሚችለው መሬት አርባ በመቶ ወይም ሦስት ሚሊዮን ሄክታር መሬት አሲዳማ አፈር መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ተመስገን፤ ከዚህ ውስጥ 10 በመቶውን እንኳ ማከም አልተቻለም ብለዋል። ነገር ግን ከዚህ ውስጥ ስንዴ የሚበቅልባቸውን ቦታዎች ብቻ እንኳን በኖራ ብናክም ከውጭ የምናስገባውን ስንዴ በ50 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ዶክተር ተመስገን ጠቁመዋል።ዶክተር ተመስገን ጨምረው እንደገለጹት፤ በአሁኑ ጊዜ በመንግሥታዊ የምርጥ ዘር ድርጅቶች ብቻ በዓመት ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ምርጥ ዘሮች ለአርሶ አደሩ እየቀረቡ ይገኛል። ማህበራትና አርሶ አደሩ እርስ በእርስ የሚለዋወጡት ሲጨመር መጠኑ ከሁለት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ይሆናል። ይህም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው እና መንግሥት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ከሚወስዳቸው ዕርምጃዎች አንዱ ማሳያ ቢሆንም፤ ግብዓት በሚፈለግበት ሰዓት የማይደርሰበት ሁኔታ አለ።ዶክተር ተመስገን እንደሚሉት፤ በርካታ ጥናቶች በመስኖ፣ በእንስሳት እርባታ እና መኖ በመሳሰሉት ተሠርተዋል። አብዛኞቹ ደግሞ ችግር ፈቺዎች ቢሆኑም ተግባር ላይ አልዋሉም። ስለዚህ ባለሀብቱም ይሁን መንግሥት መዋለ ነዋይ በማፍሰስ እነዚህን ጥቅም ላይ ማዋል ቢቻል ብዙ ችግሮችን ማቃለል ይቻላል።በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ለመስኖ ልማት የሰጠችው ትኩረት አናሳ በመሆኑ በዚህ ዘርፍ ግብርናውን ለማሳደግ እንዳልተቻል ዶክተር ተመስገን ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ የከርሰ ምድር ውሃን ሳይጨምር ወደ 123 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር የሚጠጋ የውሃ ሀብትና ከ36 ሚሊየን ሄክታር በላይ ሊለማ የሚችል መሬት አለ የሚሉት ዶክተር ተመስገን፤ በሰብል የለማው የአገሪቱ መሬት ደግሞ 16 ሚሊየን ሄክታር ብቻ እንደሆነና ከዚህ ውስጥም በመስኖ ልማት የለማው መሬት 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታሩ ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37512
78dbbd4b7ea979b7e41babe04c11bc88
5c5800593933c639b538fac47ffd79a8
የትግራይ ህዝብ አሁን ላይ የሚያስፈልገው ሰላሙን የሚያረጋግጥለትና ልማት የሚሠራለት መንግሥት ነው ሲሉ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ተናገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
• የህወሓት ጁንታ እና የትግራይ ህዝብም አንድ እንዳልነበሩ ገልጸዋል ዋለልኝ አየለአዲስ አበባ፡- ከአሁን በኋላ የትግራይ ህዝብ የሚያስፈልገው ሰላሙን የሚያረጋግጥለት እና ልማት የሚሠራለት መንግሥት ነው ሲሉ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ተናገሩ። የህወሓት ጁንታ ቡድን የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ጋር አንድ መስሎ እንዲታይ የሚያደርግ የሀሰት ትርክቱን ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ላለፉት 40 ዓመታት ሲሠራ ቢቆይም፤ በተግባር ግን የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ እንዳልነበሩም ገልጸዋል።የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ትናንት በጌት ፋም ሆቴል የተወያየ ሲሆን፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሕፃናት ጀምሮ በሁሉም ደረጃ በሠራው የሀሰት ትርክት በሌላው ህዝብ ዘንድ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው የሚል አረዳድ እንዲፈጠር ማድረጉን አስተያየታቸውን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰጡ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ እንዳልነበሩ፤ አሁንም የትግራይ ህዝብ የሚያስፈልገው ሰላሙን የሚያረጋግጥለትና ልማት የሚሠራለት መንግሥት መሆኑን ተናግረዋል። ወጣት ዳንኤል ኪዳነ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጸው፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ጋር አንድ መስሎ እንዲታይ የሚያደርግ የሀሰት ትርክቱን ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ላለፉት 40 ዓመታት በመሥራቱ ምክንያት ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው የሚለው አስተሳሰብ እንዲንጸባረቅ አድርጓል። ይሁን እንጂ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ሊሆን አይገባውም። ምክንያቱም ህወሓት ፓርቲ ነው፤ ፓርቲ ደግሞ ይመጣል፣ ይሄዳል። የትግራይ ህዝብ ደግሞ የሚፈልገው የተሻለ ነገር የሚያስገኝለትንና ሰላሙን የሚያስጠብቅለትን ነው። ህወሓት ሲያስተዳድር በቆየባቸው ዓመታት ደግሞ የትግራይ ህዝብ ከማንም የተለየ አልተጠቀመም።ይልቁንም ሥራ ወዳድና ሰላም ፈላጊ የሆነው የትግራይ ህዝብ ግን የራሱን ጥቅም ብቻ በሚያስጠብቀው የህወሓት ጁንታ ምክንያት ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል። እናም አሁን ላይ የትግራይ ህዝብ የሚያስፈልገው ሰላሙን የሚያረጋግጥለትና ልማት የሚሠራለት መንግሥት ነው። ‹‹በትግራይ ክልል ውስጥ እየተመረጡ ያሉት አዳዲስ አመራሮች የትግራይን ህዝብ ስነ ልቦና መቀየር አለባቸው›› የሚለው ሌላው አስተያየት ሰጪ ወጣት ኃይለሚካኤል ፍስሐ በበኩሉ፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ሲያስተዳድር በቆየባቸው ዓመታት የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ እንዳልነበር ይናገራል። በሀሰት ትርክት ግን የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ እንደሆኑና ህዝቡን ተጠቃሚ አድርጌያለሁ እያለ የህዝቡን ስነ ልቦና ሠርቶበታል።በመሆኑም አዲስ የተመረጡ አመራሮች በህወሓት ዘመን ሳይሠራባቸው የቆዩ የመሰረተ ልማቶችን በመሥራት የህዝቡን ስነ ልቦና መቀየር አለባቸው። ምክንያቱም፣ በትግራይ ክልል ውስጥ ህወሓት ሲያስተዳድር በቆየባቸው ዓመታት ሁሉ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ነበር። አዲስ አስተዳደር ለማስተዳደር እየተዘጋጀ ያለው፣ እንደ ጤና ጣቢያ ያሉ ወሳኝ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እንኳን መጠቀም ሳይችል የቆየ ህዝብ ያለበት ክልልን ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለሁ ከሌላ አካባቢ የሚመጡ ጓደኞቹ ሁሉ ‹‹እናንተማ የቤታችሁ በር ድረስ አስፋልት አላችሁ ይሉኛል፤ ይሄ አስተሳሰብ ደግሞ በጁንታው ተደጋጋሚ የሀሰት ትርክት ብዛት የተቀረጸ ነው›› የሚለው ኃይለሚካኤል፤ እውነታው ግን ለተሽከርካሪ መግቢያ እንኳን የሚሆን መንገድ ጠፍቶ ረጅም ርቀት በእግሩ ይሄድ የነበረ መሆኑን ይናገራል። ህዝቡም ቢሆን የጓድጓድ ውሃ ነው እየጠጣ የቆየው ሲልም ያስረዳል። ‹‹ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ የነበረው የበረሃ ትግል ውስጥ እያሉ ነው›› የሚለው ወጣት ኃይለሚካኤል፤ ህወሓት ትግል ላይ በነበረበት ወቅት ሙሉ ህዝባዊ ድጋፍ እንደነበረው ይናገራል። ይሁን እንጂ ከ1983 ዓ.ም በኋላ የተጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ህዝቡ የታገለለትን ዓላማ መነጠቁን እና ፓርቲውና ህዝቡ መለያየታቸውን ይገልጻል። በዚህም የትግራይ ህዝብ ‹‹ፍትሕ ጫካ ቀረ›› እስከማለት ምሬቱን ሲገልጽ መቆየቱን በመጠቆም፤ ህዝቡ በጁንታው የተነጠቀውን የትግል ፍሬ ለማጣጣም እንዲችል አሁን ከተመረጡት አመራሮች ጋር ወጣቱ በትብብር መሥራት እንዳለበት አሳስቧል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት ኤሊያስ መድህን እንደሚለው፤ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ የህወሓት ጁንታ በህዝቡ ላይ ጦርነት አያውጅም ነበር። ያን ሁሉ ንብረትና የመሰረተ ልማት አውታሮች አያወድምም ነበር። ይህ ደግሞ ጁንታውና ጁንታው የሚመራው ፓርቲው ከህዝቡ ጋር አንድ እንዳልሆነ ጉልህ ማሳያ ሲሆን፤ አሁን የተመረጡት አመራሮችም ነገሩን እልባት በመስጠት ህዝቡ ወደሚወደው ሰላምና ልማት እንዲመለስ ተግተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 8/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37506
4d496f5ab904d78e1c5f1bc4fc22c926
9cbe3fd1dfad805adceb9e10d1806cf9
በ782 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- በኦሮሚያ ክልል ከሕወሓት ቡድን ጋር በመቀናጀት ግጭቶች ሲያስነሱ፣ ግድያ እና ዝርፊያ ሲፈጽሙ የነበሩ 782 የኦነግ ሸኔ የጥፋት ኃይሎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ትላንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት መንግሥት የክልሉን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እየሠራ ይገኛል፡፡ሰሞኑን በሆሮ ጉዱሩ ወለጋና በሌሎች ዞኖች ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች እንዲቀሰቀሱ በማድረግ ግድያ በፈጸሙ የህወሓት ጁንታ ተላላኪዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱንም ገልጸዋል፡፡ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ ህግን ማስከበር ባቃታቸውና ከኦነግ ሸኔ ቡድን ጋር በመሆን በንጹሐን ዜጎች ላይ የጥፋት ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ የመንግሥት አመራሮች ላይም ዕርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል፡፡ይህም የክልሉ መንግሥት ሰላምና መረጋጋትን ማረጋገጥ አልቻለም በሚል በተለያዩ ወገኖች ለሚቀርበው ወቀሳ መልስ ሊሆን ይችላልም ነው ያሉት፡፡ህግ ለማስከበር በተሠራው ሥራ ከከባድ እስከ ቀላል የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውንም ነው ያስታወቁት፡፡ ከዚህ በኋላም ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን ለመቀስቀስ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን የክልሉ መንግሥት እንደማይታገስም አስረድተዋል ሲል የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=37515
981166cf5a0abc3bf22ba7f2fb94c482
cd169a8119d5071dcc10f893ddb937c8
የአትሌቲክሱ ዓለም የተወዛገበበት የመሮጫ ጫማ
ስፖርት
ያለፈው የፈረንጆች መስከረም ወር የአትሌቲክሱ ዓለም በርካታ አነጋጋሪና ታሪካዊ ክስተቶችን ያስተናገደ ነበር። በተለይም በማራቶን ውድድር ኬንያዊው አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ በቬና ማራቶን ከሦስት ሳምንት በፊት ለማመን የሚከብደውን አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከ2፡00 በታች ሮጦ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ያሳየበት ውድድር አሁንም ድረስ መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል፡፡ በሃያ አራት ሰዓት ልዩነት ውስጥ ሌላኛዋ ኬንያዊት ብሪጊድ ኮስጌ ቺካጎ ማራቶን ላይ ለአስራ ሰባት ዓመታት ሳይሰበር የቆየውን የዓለም ክብረወሰን ማሻሻሏ ታሪካዊና አነጋጋሪ ከመሆን አልፎ የውዝግቦች መነሻ ሆኗል፡፡ የውዝግቡ መነሻ ሁለቱ አትሌቶች የሰሩት ታሪክ ሳይሆን ታሪክ የሰሩበት የመሮጫ ጫማ ነው፡፡ ግዙፉ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ናይኪ ማራቶንን ከ2፡00 በታች መሮጥ ይቻል ዘንድ ባለፉት ዓመታት ትልቅ ፕሮጀክት ቀርፆ ከኬንያዊው አትሌት ኪፕቾጌ ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይህም እንዲሳካ ፍጥነትን የሚጨምር ልዩ የመሮጫ ጫማ ከማዘጋጀት ጀምሮ ያልቆፈረው ጉድጓድ አልነበረም፡፡ ይህ ፕሮጀክቱ ተሳክቶም ኪፕቾጌ በአርባ አንድ አሯሯጮችና በዘመናዊው ጫማ ታግዞ አርባ ሁለት ኪሎ ሜትሩን 1፡59፡40 በሆነ ሰዓት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ሌላኛዋ ኬንያዊት ኮስጌም በቺካጎ ማራቶን በቅርብ ዓመታት ይሰበራል ተብሎ ያልተጠበቀውን የፓውላ ራድክሊፍ 2፡15፡25 የሆነ የዓለም ክብረወሰን በዘመናዊው የናይኪ ጫማ ሮጣ በሰማንያ አንድ ሰከንድ አንክታዋለች፡፡ ኪፕቾጌ ይህን ታሪክ ለመስራት ከሦስት ዓመት በፊት ሲነሳም ከተለያዩ የስፖርት ቤተሰቦች ተቃውሞ ማስተናገዱ አልቀረም። ማራቶንን የሰው ልጅ በተፈጥሯዊ መንገድ ከ2፡00 በታች ማጠናቀቅ እየቻለ በቴክኖሎጂ መታገዙ በበርካቶች ዘንድ አልተዋጠም ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ጀግኖች አትሌቶች ኃይሌ ገብረስላሴና ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ ማራቶንን በቴክኖሎጂ ታግዞ ከ2፡00 በታች መሮጥ እንደማይዋጥላቸው ይልቁንም በተፈጥሯዊ መንገድ ጠንካራ ዝግጅት ተደርጎ ሃሳቡን ማሳካት እንደሚቻል ገና ከውጥኑ ሲናገሩ ነበር፡፡ ኪፕቾጌ ያሳካው ፕሮጀክት በስፖርቱ ትልቅ መነቃቃትን ከመፍጠር ባሻገር የሰው ልጅ የብቃት ጥግ ወሰን እንደሌለው ግንዛቤ ፈጥሯል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ስኬት በርካቶች ከስፖርታዊ ኩነቱ ነጥለው በመመልከት አትሌቱ ተጫምቶት የሮጠበትን የናይኪ ጫማ የማስተዋወቅ የንግድ ስራ አድርገው ተመልክተውታል፡፡ በንግዱ ዓለም ፍልስፍና ብዙ የሚዋጥ ባይሆንም ናይኪ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ በመላው ዓለም ትልቅ ስም እያለው በዚህ መንገድ ስፖርቱን ተጠቅሞ ምርቱን ለማስተዋወቅ መሞከሩ ሌሎች ተፎካካሪዎቹን ለመዋጥ ያደረገው ስግብግብነት እንደሆነ ያስቀመጡ ወገኖችም ጥቂት አይደሉም፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሯዊ መንገድ ሮጦ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ማጠናቀቅ እየቻለ ኪፕቾጌ በምቹ የውድድር ቦታ ላይ በረቀቀ ቴክኖሎጂ ታግዞ ማሳካቱ ከስፖርት መርህ ጋር ተቃራኒ እንደሆነ የሚያነሱም አሉ፡፡ በአርቴፊሽያል ነገሮች በአትሌቲክሱ መግባት ከጀመሩ ወደ ፊት ስፖርቱ አሁን ያለውን የፉክክር ለዛ ይዞ አይቀጥልም የሚል ስጋት ያላቸው የስፖርት ቤተሰቦች ከዚህም ከዚያም አትሌቲክሱ ላይ ጠንከራ ጥያቄና ትችት ሲሰነዝሩ ሰንብተዋል፡፡ ዛሬም ድረስ በበርካታ የቀድሞ የዓለማችን አትሌቶች ተቃውሞ እየገጠመውም ይገኛል፡፡ ዘ ታይምስ እንደ ዘገበው በርካታ አትሌቶች ናይኪ ባሰናዳው ዘመናዊ የመሮጫ ጫማ ላይ የተቃውሞ ድምፅ እያሰሙ ይገኛሉ። የቀድሞው ጣሊያናዊ የማራቶን ቻምፒዮን ጂያኒ ዲማዶናን ጨምሮ ሃያ አትሌቶች ተሰባስበው ለዓለም አትሌቲክስ የናይኪን ዘመናዊ ጫማ ተቃውመው ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ የዓለም አትሌቲክስ ህግ ‹‹የመሮጫ ጫማዎች አትሌቶች እግራቸው ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸውና በምቾት እንዲሮጡ እንጂ ተገቢ ያልሆነ ጥቅምና ድጋፍ እንዲያገኙ አይደለም›› ይላል፡፡ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2፡00 በታች ሲያጠናቅቅ የተጫማው ጫማ ግን ናይኪ በቴክኖሎጂ የተጠበበትና ገና ለገበያ ያልዋለ እንደመሆኑ ልዩ ትቅም ወይም ድጋፍ አላገኘበትም ማለት አይቻልም፡፡ ኮስጌ በእንግሊዛዊቷ አትሌት ፓውላ ራድክሊፍ ለአስራ ስድስት ዓመታት ተይዞ የቆየውን 2፡15፡25 ክብረወሰን በሰማንያ አንድ ሰከንድ ስታሻሽልም ይሄንኑ ጫማ አጥልቃ ነው የሮጠችው፡፡ ይህም መሮጫ ጫማ ፓውላ ራድክሊፍ ክብረወሰን ስትሰብር ከተጫመችው ከ60 እስከ 90 ሰከንድ አትሌቷን የማፍጠን ጥቅም ስላለው ያሻሻለችውን 81 ሰከንድ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ እንደነበረው የተለያዩ ትንታኔዎች ወጥተዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ዓለም አትሌቲክስ ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎች በተለይም ከመሮጫ ጫማው ጋር ተያይዞ ለአትሌቶች እገዛ ማድረግ አለባቸው የለባቸውም የሚለው ሃሳብ አከራካሪ መሆኑን ገልፃል፡፡ ስለዚህም ጫማው በአትሌቶች ፍጥነት ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ለመመርመር አንድ የጥናት ቡድን ለማቋቋም ተገዷል፡፡ አትሌቶች በተለያዩ ጊዜዎች በሚመረቱ ጫማዎች ሮጠው የተለያዩ ክብረወሰኖችን ሲሰብሩ ቆይተዋል፡፡ ይህ የናይኪ አዲስ ጫማ ከገበያ አኳያ ብዙ ስለተወራለት እንጂ ከዚህ ቀደም የሌለ ነገር እንዳልሆነ የሚሞግቱ የአትሌቲክስ ቤተሰቦች ቁጥርም ቀላል አይደለም፡፡ እንደ ዘ ታይምስ ትንታኔ ከሆነ ናይኪ አዲስ ያመረተው ጫማ ለአንድ አንድ አትሌቶች ይፋ የተደረገው ከ2016 በፊት ነው፡፡ 2014 ላይ ዴኒስ ኪሜቶ በበርሊን ማራቶን 2፡2፡57 የሆነ የዓለም ክብረወሰን ሲያስመዘግብ ይህን ጫማ ተጫምቷል፡፡ ከዚያ በኋም አምስት ጊዜ ይህን ጫማ ያጠለቁ አትሌቶች ክብረወሰን አሻሽለዋል። ይህን ልብ ያሉት የፕሮፌሽናል አትሌቶች የብቃት አሰልጣኝ ስቲቭ ማግኔስ ‹‹ጥናቶችን ካስተዋልን ጫማው በአትሌቶች ፍጥነት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አለው›› በማለት ለዋሺንግተን ፖስት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አዲስ ዘመን ጥቅምት24/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=21977
b8f378f014560d4d52b032a74e24f530
6709aa6b2e2a3482247205b289263ec9
ኮሚሽኑ ለ500 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል
ሀገር አቀፍ ዜና
ግርማ መንግሥቴአዲስ አበባ፡- በኦሮሚያ ክልል የቱሪዝም ዘርፍ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ለ500 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱን የክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ የቱሪዝም ኮሚሽነር ወ/ሮ ሌሊሴ ዱጋ ትናንት በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት መንግሥት ለቱሪዝም ሴክተሩ የሰጠውን ልዩ ትኩረት ተከትሎ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የክልሉን ቱሪዝም ዘርፍ ማሳደግ ያስችላል በሚል ያቋቋመው የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ሥራውን በይፋ ጀምሯል።ኮሚሽኑ ከዘርፉ የሚገኙትን ጥቅሞች ይበልጥ ለማሳደግ፣ አገርና ክልሉን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ፣ ዜጎችን በተለይም ወጣቱን በማሳተፍ ዘርፉን ለማበልጸግና የባለሀብቱን ቀልብ ለመሳብ ይቻል ዘንድ ታስቦ የተቋቋመ መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ሌሊሴ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥም ውጤታማ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል። “ክልሉን ለጎብኚዎች ቀዳሚና ተመራጭ መዳረሻ ሆኖ ማየትን” ራእዩ ያደረገው ኮሚሽኑ ለሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለማድረግ፤ በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ልማት ለማፋጠን፣ ለማገዝና ሌሎች ተግባራትንም ለማከናወን በሚያስችል ደረጃ የተቋቋመው “የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን” ክልሉ የሚታወቅበትንና ያለውን ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡና ለዜጎች በሚጠቅም መልኩ ለማከናወን እንደሚያስችልም ኮሚሽነሯ ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ መግለጫ በተለይ የቱሪዝም ኢንቨስትመንትን ከመሳብ፣ ከማስፋፋትና በዘርፉ መሳተፍ የሚፈልጉ ባለሀብቶች እንዲሰማሩ ከማድረግ አኳያ ሰፊ ሥራ የሚሠራ ሲሆን፤ ይህም ሴክተሩ ለሀገር ልማት የሚጠበቅበትን ጉልህ ሚና እንዲወጣና የራሱን ሚና እንዲጫወት ማድረግ የኮሚሽኑ ዋንኛ ትኩረት ሆኖ ተቀምጧል። የክልሉ ቱሪዝም ልማት ሙሉ ለሙሉ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማዕከል ባደረገና ወጣት መር በሆነ መልኩ እንደሚሠራ የተናገሩት ወ/ሮ ሌሊሴ ይህ መርህ አገራችን ከዘርፉ ማግኘት እየተገባት እስከ ዛሬ ያጣችውን ጥቅም እንድታገኝ ከማስቻሉም በላይ ዘርፉ ከራሳችንም አልፎ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አገራችንን ከአፍሪካም ቀዳሚ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል። በክልሉ ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን ለማረጋገጥ የቱሪዝም ፈንድ በማቋቋም ሴክተሩንም በስፋት ለማጠናከር በእቅድ ተይዞ እንደሚሠራ የተናገሩት ኮሚሽነሯ ለዚህም ፍላጎቱና ሀብቱ ካላቸው ከማናቸውም ወገኖች ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ የሥራ ዕድል ፈላጊ ወጣቶች መኖራቸውን የሚናገሩት ኮሚሽነር ሌሊሴ ይህን ችግር በመሰረታዊነት ለመቅረፍና የተለያዩ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከ500,000 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል ሲሉም ተናግረዋል። አዲስ ዘመን ታህሳስ 8/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37524
cec70fd3885a922fa5c345f9819049a7
7ab4c704fe9482d0e95141a0dfc3be88
“ከለውጡ በፊት ጀምሮ በነበረኝ የሃሳብ ልዩነት በጁንታው አባላትና ደጋፊዎች ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርስብኝ ነበር”-የተከበሩ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ
ሀገር አቀፍ ዜና
ማህሌት አብዱልአዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታ በአገሪቱ ህዝብ ላይ ያደርስ የነበረውን ጭቆና እና ግፍ በመቃወማቸውና የሃሳብ ልዩነት በማንጸባረቃቸው በጁንታው አባላትና ደጋፊዎች ከፍተኛ ማስፈራሪያና ዛቻ ሲደርስባቸው እንደነበር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ ገለጹ። ተወካዩዋ የተከበሩ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ድርጅቱን ከተቀላቀሉበት ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ጁንታው የህወሓት ቡድን በአገሪቱም ሆነ በመላዉ የትግራይ ህዝብ ላይ ያደርስ የነበረው ጭቆና እና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሲቃወሙና ሲታገሉ ቆይተዋል። በተለይም በምክር ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ሚዛኑን ያልጠበቀና እውነትን መሰረት ያላደረጉ ውሳኔዎች ላይ የሚያምኑበትን ሃሳብ በግልጽ በመናገራቸው ምክንያት በድርጅቱ አመራሮች የተመደቡ ግለሰቦች በስልክና በማሕበራዊ ሚዲያ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱባቸው እንደነበር ወይዘሮ ያየሽ ተናግረዋል። ‹‹በፌስቡክና በተለያዩ ማሕበራዊ ሚዲያዎች አርፈሽ ካልተቀመጥሽ እንዲህና እንዲያ እናደርግሻለን ከማለትም በተጨማሪ ገንዘብ ተሰጥቶሽ ነው፤ የሚሉ ማስፈራሪያዎች፣ ስድብና ዛቻ ይደርስብኝ ነበር›› ያሉት ወይዘሮ ያየሽ፤ አንዳንዳቹም ለእሳቸው በማሰብና በመስጋት ፊትለፊት መጋፈጥ እንደሌለባቸው ይመክሯቸው እንደነበር ጠቁመዋል። በተለይም መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም የትግራይ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳይገቡ በጁንታው የተላለፈውን ጥሪ ባለመቀበላቸው ምክንያት የቅርብ በሚሏቸው አባላት መገለል ያጋጠማቸው መሆኑንና  ይህም ቡድኑ የሃሳብ ልዩነትን የማይቀበልና ፅንፈኛ ድርጅት መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል። ከዚህም ባሻገር ይህ ድርጊታቸው አባላቱ በስነልቦናዊ ጫና ውስጥ ተሸብበው እንዲኖሩ ያደረገ አሸባሪ ቡድን መሆኑንም በግልጽ እንደሚያስረዳ ወይዘሮ ያየሽ ተናግረዋል። እንደርሳቸው ማብራሪያ አገር ሲመራ የነበረው ይህ ህገወጥ ቡድን ህገመንግሥቱንና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን በመተላለፍ ምርጫ ማካሄዱ አልበቃ ብሎ ከመስከረም 25 ጀምሮ መንግሥት የለም በሚል አገር ለማፍረስና ህገመንግሥቱን ለመናድ ያደረገው ሙከራ ምንም እንኳን ባይሳካለትም በታሪክም ሆነ በህግ ተጠያቂ ከመሆን አያግደውም ብለዋል። በተለይም የኮሮና ቫይረስ በዓለም ደረጃ በተስፋፋበት ጊዜ ምርጫ ማካሄዱ ድርጅቱ ከራሱ ጥቅም ውጪ ለህዝቡ የማያስብ መሆኑን አመላካች መሆኑን ወይዘሮ ያየሽ ጠቁመው፤ ‹‹ምርጫው መራዘም እንዳለበት በባለሙዎች ዓይናችን እያየ፣ አሳማኝ ጭብጥ በዝርዝር እየቀረበ መክረንበት የተወሰነ መሆኑ እየታወቀ›› በጁንታው የተላለፈው ምክር ቤት አትግቡ የሚል ትዕዛዝ ፈፅሞ አሳማኝ እንዳልነበረ ያሳያል ብለዋል። በወቅቱም እሳቸው ውሳኔውን በግልጽ ከመቃወም አልፈው ሌሎች አባላትም ውሳኔያቸውን እንዲያስተካክሉ እና ለወከላቸው ህዝብ ታማኝ እንዲሆኑ መምከራቸዉንም አመልክተዋል። “ጁንታው ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ነው ይላል በመሰረቱ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ከሆነ ምርጫ ለምን ያስፈልጋል? ለምን ሀብትና ጊዜስ ይባክናል?” ሲሉም የተካሄደው ምርጫ ከአሳማኝነቱ ይልቅ ከመስመር የወጣ ተግባርና ለማንም የማያስተምር እንደነበር አንስተዋል። ብዙሃኑ የትግራይ ህዝብ አሁንም በከፍተኛ ድህነት ውስጥ ነው እየኖረ ያለው የሚሉት ወይዘሮ ያየሽ፤ ከጁንታው ጋር ጥገኛ የሆኑ ጥቂት ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር የክልሉ ህዝብ አሁንም በርካታ ችግሮችን እየተጋፈጠ እንደሆነ ጠቁመዋል። ለአብነትም በክልሉ አሁንም ከፍተኛ የውሃ እጥረት አለ፤ ተማሪዎች አሁንም በዳስ ነው እየተማሩ ያሉት፤ በክፍተኛ መጠን እየጨመረ የመጣውን አዲስ ትውልድ በአግባቡ ሊቀርፅ የሚችል ተቋም አልተገነባም ሲሉም አስረድተዋል።‹‹ለምርጫ የሚያባክኑት ገንዘብ ለእነዚህ ሥራዎች ቢውል ኖሮ፤ ጠቃሚ እንደነበር የጠቆሙት ወይዘሮ ያየሽ፤ ቡድኑ የራሱን ጥቅምና ፍላጎት ብቻ የሚያስቀድም እንደነበረና የጁንታው አባላትም በገዢነት መደብ ቁጭ ብለው አድራጊና ፈጣሪ ሆነው የሚቀጥሉበትን ዕድል ሲያመቻቹ መቆየታቸውን ጠቁመዋል። አዲስ ዘመን ታህሳስ 8 /2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37517
a7c373522e3ac0d02dd3a63460f6043f
fac7c437e3f4ccceb88ba7da6e7f3004
አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ አረፉ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ደራሲ እና ተዋናይ አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ፣ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ የተለያዩ መፅሐፍትን የደረሱ ሲሆን፤ በተለያዩ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይም በተዋናይነት ተሳትፈዋል። በርካታ ተውኔቶች ላይም የትወና ችሎታቸውን ያስመሰከሩ ሲሆን፤ በአጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞቻቸው በሩሲያኛ ተተርጉመው ሩሲያ ውስጥ ታትመዋል። ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ መተከዣ (ግጥምና ቅኔ)፣ ጥላሁን ግዛው፣ ዕቃው፣ የሺ፣ አባትና ልጆች፣ ላቀችና ደስታ፣ ተሐድሶ የተሰኙ ተውኔቶችንም ደርሰዋል። እንዲሁም የዑመር ኻያምን ልቦለዳዊ የሕይወት ታሪኩና ሩብ አያቶቹ የትርጉም መፅሐፍ ለአንባቢያን አድርሰዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴዓትር እና ጥበባት ኮሌጅም ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል። በቀድሞው ሐረርጌ ክፍለ ሀገር ጎሮጉቱ በሚባል አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ገሰሰ ቆለጭ እና ከእናታቸው ወይዘሮ በለጥሻቸው ያየህይራድ መስከረም 17 ቀን 1929 ዓ.ም የተወለዱት ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ፤ በትናንትናው ዕለት በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አንጋፋው የጥበብ ሰው ብሄራዊ ቴዓትር ቤት የሽኝት ፕሮግራም እንደሚያዘጋጅ የተገለጸ ሲሆን፤ ቀብራቸው በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ተጠቁሟል።የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትም በአንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ዜና ዕረፍት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መጽናናትን ይመኛል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 8/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37532
7d9a550169b97974f26a7361d4ef0866
721145480b76984363e8a73c5bcf2259
ሩጫ በባዶ እግ
ስፖርት
 ብስራቱን ለመንገር የመጀመሪያውን ማራቶን ከአቴንስ እስከ ስፓርታ የሮጠው ወታደሩ ፊዲፒደስ ከ30 ሰዓታት በላይ ፈጅቶበታል። ከዘመናት በኋላ ደግሞ 42 ኪሎ ሜትሩ በሁለት ሰዓት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሆኗል፡፡ ነገር ግን በቅርቡ ከዚህም በታች በሆነ ሰዓት መግባት እንደሚቻል ኬንያዊው አትሌት አረጋግጧል። ይህንን ሃሳብ በመያዝ ሲንቀሳቀስ የቆየው ናይኪ የተባለው የስፖርት ትጥቅ አምራችም በጫማዎቹ አማካኝነት ርቀቱ እስካሁን በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅበት ሁኔታ ከሁለት ሰዓት በታች መግባት እንደሚቻል አሳይቷል። ነገር ግን የማራቶን ሰዓት እዚህ ከመድረሱ ናይኪም በዘመን አመጣሽ ጫማዎቹ ሳይራቀቅ በፊት ፊዲፒደስ ርቀቱን በምን ሸፈነው በማለት የታሪክ ማህደርን ማገላበጥ አስፈላጊ ይሆናል። ሩጫ መለያዋ የሆነው ኢትዮጵያም የተከበረውን የኦሊምፒክ መንደር አሃዱ ያለችው በምን መልኩ ነው ለሚለውም ታሪክን መለስ ብሎ ማስታወስ በቂ ነው። ባለሙያዎች «ተፈጥሮአዊ ሩጫ» ሲሉ የሚጠሩትና በተለምዶ በባዶ እግር መሮጥ ለማራቶን ስፖርት መሰረት ነው ለማለት ይቻላል። በዘመነው ዓለም የማይታሰበው የባዶ እግር ሩጫ በአፍሪካ እና በደቡባዊው አሜሪካ ግን እስካሁንም በስፋት ይስተዋላል። በኢትዮጵያም ይህ አሯሯጥ የተለመደ ቢሆንም ምርጫ በማጣት (ከድህነት ጋር በተያያዘ ምክንያት) አሊያም በአስገዳጅ ሁኔታ የሚከወን ስለመሆኑ ዋቢ መጥቀስ አያሻም። በአንጻሩ ከሃብት ማማ ላይ በሚገኙት ምዕራባዊያን ዘንድ ይህ ዓይነቱ ሩጫ ጥቅሙን በመረዳት ይዘወተራል። ከጊዜ ወደ ጊዜም እየታወቀና እየተስፋፋ የመጣ የአሯሯጥ ዓይነት ሆኗል። በተለይ በሃይቅና ውቅያኖስ ዳርቻዎች እንዲሁም በሳር በተሸፈኑ መስኮች ላይ ባዶ እግርን መሮጥ እያደገ ያለ ተግባር ነው። በዚህ የሩጫ ዓይነት ስሙ ጎልቶ የሚነሳው ኢትዮጵያዊው ታላቅ አትሌት አበበ ቢቂላ ቢሆንም ከእርሱ አስቀድመውም ሆነ በዚያው ዘመን በርካቶች ባዶ እግራቸውን በውድድሮች ላይ ይካፈሉ ነበር። ከታዋቂዎቹ መካከልም ደቡብ አፍሪካዊቷ የሁለት ጊዜ የሃገር አቋራጭ ሻምፒዮና ዞላ ቡድ፣ አውስትራሊያዊው የ1ሺ500 ሜትር እና 800 ሜትር አትሌት ኸርብ ኤሎት እንዲሁም እንግሊዛዊው የ3 ማይል ሻምፒዮን ብሩች ቱሎህ ጥቂቶቹ ናቸው። ጀግናውን አትሌት ከሌሎቹ ልዩ የሚያደርገውም በባዶ እግር ቀርቶ በጫማም የማይደፈረውንና እህል ውሃ የማያሰኘውን ማራቶንን በመሮጡ ነው። እርግጥ ነው ከረጅም ዓመታት በኋላም ሌላ ኢትዮጵያዊ አትሌት በዚህ መልክ 42 ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ ዓለምን አጀብ ማሰኘት ችሏል። ከሰው ልጅ ስልጣኔ እና የአኗኗር ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሰው ልጅ ሩጫን በባዶ እግሩ አሊያም ከድብ እና ከሌሎች እንስሳት ቆዳ በሚሰራ ጫማ ሲከውነው እንደነበረ ጥንታዊያን ታሪኮች ያስረዳሉ። ግሪካዊያንም በጥንታዊው ኦሊምፒክ ጭምር በሩጫ ብቻም ሳይሆን በተለያዩ ስፖርቶች የሚካፈሉ ተወዳዳሪዎች ባዶ እግራቸውን ነበር የሚቀርቡት። እንደሌላው ዘርፍ ሁሉ የስፖርት ቁሳቁሶችም ከዘመን ጋር እየዘመኑና በረቀቁ ቴክኖሎጂዎች ታግዘው እየተካሄዱ ይገኛሉ። ለዚህም በቅርቡ ኬንያዊው አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ በ1ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ40ሰከንድ በሆነ ሰዓት ማራቶንን የሮጠበትን ጫማ ማንሳት ይቻላል። ናይኪ ቫፖርፍላይ የተባለው ይህ የመሮጫ ጫማ ከተፈጥሮአዊው አቅም ባሻገር አትሌቶችን ወደፊት በማፈናጠር ተጨማሪ ፍጥነት የሚሰጥ ነው። በርካቶች ግን 250 ዶላር ዋጋ የተተመነለት ናይኪ ቫፖርፍላይን በህግ ከሚያስቀጣው የአበረታች ቅመሞች ተጠቃሚነት ለይተው አያዩትም። ይህ ከዘመናዊው ዓለም ጋር ከመራመድ እና ከተፈጥሯዊው ልማድ ጋር የመቀጠል እሳቤም የአትሌቲክስ ቤተሰቡን ከሁለት የከፈለ አድርጎታል። በተፈጥሯዊ መንገድ በባዶ እግር መሮጥ ግን ላለንበት ወቅት የማይመጥን ተግባር ተደርጎ ይወሰድ እንጂ የጤና ባለሙያዎች እንዲተገበር የሚመክሩት የአሯሯጥ ዓይነት ነው። ሳይንስም በባዶ እግር መሮጥን ከጉዳት ማገገምን ጨምሮ በርካታ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ ያረጋግጣል። ነገር ግን ተግብሮት ለማያውቅ ሰው በመጀመሪያ ፈታኝ እንደሚሆን እና የሚሮጡበትን ስፍራ ደህንነትም አስቀድሞ ማረጋገጥ እንደሚገባም ያሳስባል። የመጫሚያዎች ምቾት ከሳምባ፣ ከአእምሮ፣ ከደም ዝውውር እንዲሁም ከነርቭ ጋር ይያያዛል። በመሆኑም ከባድ፣ ጠባብ፣ ከተረከዛቸው ከፍ ያሉ፣… ጫማዎች ያደረገውን ሰው ምቾት ከመንሳት ባሻገር ጤናም ላይ ተያያዥ እክሎችን ማድረሱ አይቀርም። በመሆኑም አልፎ አልፎም ቢሆን ባዶ እግርን መጓዝ እና መሮጥን መለማመድ ጠቃሚ ይሆናል። የደም ዝውውርን ለማስተካከል ተመራጭ መንገድ ሲሆን፤ በተለይ ለልብ ህመም እንዲሁም በደም ውስጥ የሚኖሩ መርዘኛ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ እንደሚረዳ ተመራማሪዎች በሳይንስ ጆርናሎች ያሳተሟቸው ጽሁፎች ያስነብባሉ። በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ዳንኤል ሊበርማን እንደሚገልጹት ከሆነ፤ (cushioned shoes) በመባል የሚታወቁትን የስፖርት ጫማዎች የሚያዘወትሩ አትሌቶች ተረከዛቸው በመዶሻ የመቀጥቀጥን ያህል ጉዳት ይደርስባቸዋል። በመሆኑም አሰልጣኞች አንዳንዴም አትሌቶቻቸውን ባዶ እግራቸውን በሳር ላይ እንዲሮጡ ቢያደርጉ፤ የእግራቸውን ጤንነት ከመንከባከብም በላይ ከደረሰባቸውም ጉዳት እንዲያገግሙ እንደሚረዳቸው ያስረዳሉ። በጫማ መሮጥ በባዶ እግር ከመሮጥ ይልቅ የኦክስጅን ፍጆታን በሁለት እጅ ይጨምራል፤ ይህም አትሌቱ (ሯጩ ግለሰብ) ከሚያወጣው ጉልበት የሚያያዝ በመሆኑ በሚሸፍነው ርቀት ላይ የራሱን ተጽእኖ ማሳረፉ አይቀርም። በእግር ጤንነት፣ ሚዛን፣ ነርቮችን በማነቃቃት፣ የእግር ቅርጽ እና እድገት ላይም በጫማ እና ያለጫማ እንቅስቃሴ ማድረግ ሚናው ይለያያል። በተለይ ደግሞ በሽንጥ፣ ባት፣ ተረከዝ፣ ቁርጭምጭሚት፣ ጅማት፣ አጥንት እና ጡንቻዎች ጤና ላይ የራሱን አሻራ ያሳርፋል። ከዚህ ባሻገር ሰው ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ቁርኝትም በማስፋትና ተፈጥሮን በመንከባከብ ረገድ የራሱን ስነ-ልቦናዊ በረከት ያስገኛል።አዲስ ዘመን ጥቅምት24/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=21980
ae558075093775b89e9d4a453c24a393
3c652ca655f93861775394e54257c746
የኦሊምፒክ ኮሚቴና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አለመግባባት ቀጥሏል
ስፖርት
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አሁንም አለመግባባት ውስጥ ይገኛሉ። በተለይም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ መካከል አለመግባባት መፈጠር ከጀመረ የሰነበተ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አለመግባባቱ ከግለሰቦቹ አልፎ ተቋማዊ እየሆነ መጥቷል፡፡ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ፣ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የሚጓዝበት መስመር እና ውሳኔዎች የሚተላለፉባቸው መንገዶች ግልጽ የሆነ አሠራርን የማይከተሉ ከመሆናቸው ባሻገር መመሪያ እና አሠራርን ሳይሆን የግለሰቦች ፍላጎትን ብቻ መሠረት አድርገው የሚካሄዱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ «ስፖርቱ እውነተኛ ተቆርቋሪ አጥቷል» ሲሉ ቅሬታቸውን ለኦሊምፒክ ኮሚቴው ከትናንት በስቲያ በፃፉት ደብዳቤ አብራርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው «ምንም የተፈፀመ ስህተት የለም» በማለት ትናንት ረፋድ ላይ ለሸገር ስፖርት ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አክለውም ትናንት በአምባሳደር ሆቴል አዲሱ የኦሊምፒክ ኮሚቴ መተዳደሪያ ደንብ ውይይት ሲደረግበት ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በተያያዘ የሚነሳውን ቅሬታ እንደሚመክሩበት አብራርተዋል፡፡ በአምባሳደር ሆቴል እንደሚካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ወይም ስብሰባ ላይ ተሰብሳቢዎቹ የተጠሩበት ሂደት እና የጉባኤው አጀንዳዎች በግልጽ ምን ምን እንደሆኑ ቀደም ብለው አለመታወቃቸው፡ ከኮሚቴው መተዳደሪያ ደንብ እና አሠራር ጋር አብሮ የሚሄድ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ለልዩ ስፖርት ገልጸዋል፡፡ ደራርቱ ቱሉ ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ራሷን ለማግለል ውሳኔ ላይ ደርሳ የነበረች ቢሆንም ሃሳቧን መቀየሯ ይታወሳል፡፡ ደራርቱ በኦሊምፒክ ኮሚቴ የውሳኔ አሰጣጥ ረገድ የምትመለከታቸውን ሕጸጾች ከዚህ በኋላ የማይታረሙ ከሆነ ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ራሷን እንደምታገል ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡ ደራርቱ ባለፈው ነሐሴ በደብረ ብርሃን ከተማ በተደረገው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከሥራ አስፈፃሚነት ለመልቀቅ መወሰኗን የተናገረች ቢሆንም በጠቅላላ ጉባኤው በርካታ ሰዎች ውሳኔዋን እንድታጥፍ ግፊት በማሳደራቸው ሃሳቧን ልትቀይር ችላለች፡፡አዲስ ዘመን ጥቅምት27/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=22111
b242d1aba1024f0833eab75a8f5dd7a0
fc4397620b01080488b5aa030598c229
በመላ አፍሪካ የተሳተፉ ፌዴሬሽኖች ገንዘብ አላወራረዱም
ስፖርት
ከሁለት ወር በፊት በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው አስራ ሁለተኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ የተሳተፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስፖርት ፌዴሬሽኖች ለውድድሩ የወሰዱትን ገንዘብ እስካሁን በሕጋዊ ደረሰኝ እንዳላወራረዱ ተገለጸ።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ትናንት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሪፖርትን ባቀረበበት ወቅት እንደተገለፀው በውድድሩ አስራ ሦስት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ተሳትፈዋል።ለመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በአጠቃላይ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ብር ገደማ ወጪ መደረጉ በሪፖርቱ የተገለፀ ሲሆን መንግሥት ለውድድሩ ስልሳ ሚሊዮን ብር መመደቡ ተጠቁሟል።መንግሥት በቂ በጀት የመደበ ቢሆንም የበጀት ክፍፍሉና አጠቃቀሙ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ታምኖበት እንዳልተሰጠው ተጠቅሷል።ይህም በጀቱ የዕዝ ሰንሰለቱን በጠበቀ መልኩ እንዳይፈፀም ማድረጉ ተብራርቷል።መንግሥት ለውድድሩ የበጀተው ገንዘብ በቀጥታ ውድድሩን ለሚመራው ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሳይሆን በፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን በኩል ለፌዴሬሽኖች እንዲከፋፈል መደረጉ ቀደም ሲልም ሲነገር ቆይቷል።ወደ ውድድሩ ስፍራ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ሰባ ሰው የተጓዘ ሲሆን አላግባብ የተጓዘ ልዑካን ቡድን እንደሌለ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።ወደ ውድድሩ አቅንቶ ሳይሳተፍ የተመለሰው የክብደት ማንሳት ልዑካን ቡድን ጉዳይ አነጋጋሪ እንደነበር የሚታወስ ነው።ኢትዮጵያን ወክለው በክብደት ማንሳት ስፖርት ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ስፖርተኞች ሳይሳተፉ የተመለሱት በፀረ አበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ከውድድሩ በፊት ምዝገባ ባለማድረጋቸው መሆኑ ታውቋል።ያም ሆኖ ስፖርተኞች ወደ ስፍራው ከመሄዳቸው አስቀድሞ ማሟላት ያለባቸውን አስፈላጊ ነገር ሳያሟሉ በመቅረታቸው ለተፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን የትኛው አካል መውሰድ አለበት የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል።ለዚህ ችግር መፈጠር የውድድሩ አዘጋጆች የመረጃ ክፍተት አንዱ ምክንያት ከመሆኑ ባሻገር «የእኛም ክፍተት አለበት» በማለት በሪፖርቱ ቀርቧል።በውድድሩ ወቅት ችግር ተብለው ከተነሱ ጉዳዮች አንዱ የዳኝነት ችግር በጉልህ ተጠቅሷል።በአንዳንድ ውድድሮች ዓለምአቀፍ የውድድር ልምድ ማነስ ሌላኛው ችግር እንደነበር ተነስቷል።በተለይም በጅምናስቲክ ስፖርት በአገራችን ዘመናዊ መሣሪያዎች አለመኖር ተወዳዳሪዎች እዚያ ሲሄዱ ያጋጠማቸው አዳዲስ መሣሪያ ግራ እንዳጋባቸውና ሳይወዳደሩ እንደቀሩ ጭምር ተገልጿል።ትልቅ ብቃት ያላቸውና ታዋቂ የሆኑ አትሌቶች በውድድሩ አለመሳተፋቸው የተሻለ ውጤት እንዳይመዘገብ ማድረጉ ተብራርቷል።በዝግጅት ወቅት የተለያዩ ስፖርቶች የተዘጋጁበት ወቅት መለያየትም አንድ ችግር ሆኖ ተነስቷል።በዚህ ረገድ ቦክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶና አትሌቲክስን በመሳሰሉ ስፖርቶች ዘጠና ያህል ቀናት የተዘጋጁ ሲሆን ሌሎች ስፖርቶች ከአርባ አምስት እስከ ስልሳ ቀናት ብቻ ነው ዝግጅት ያደረጉት።በውድድሩ የገጠሙትን የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የተሞከረ ሲሆን አሰልጣኞች ከዘመኑ ጋር አብረው መጓዝ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸውና ከዚህ በኋላ በልምድ ብቻ መጓዝ እንደማይቻል የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።ስፖርተኞች የዓለም አቀፍ ውድድሮች ልምድ ቀደም ብለው ማግኘት እንዳለባቸውም ተብራርቷል።በመላ አፍሪካ ጨዋታ አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ ስፖርተኞች እስካሁን ድረስ እውቅናም ይሁን ሽልማት አለማግኘታቸው አነጋጋሪ መሆኑ አልቀረም።ኦሊምፒክ ኮሚቴም ከውድድሮች በኋላ በወቅቱ የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሞች በማዘጋጀት ማበረታታት እንደሚገባ በሪፖርቱ ተመልክቷል።ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአስራ ሦስት የስፖርት ዓይነቶች መላ አፍሪካ ጨዋታ ላይ በመሳተፍ በቦክስ፣ አትሌቲክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶና ብስክሌት ስፖርቶች ባስመዘገበቻቸው ሜዳሊያዎች ዘጠነኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።ከተመዘገቡት ሜዳሊያዎች መካከል ስድስት የወርቅ፣ አምስት የብርና አስራ ሁለት የነሐስ መሆናቸው ይታወሳል።በውድድሩ በአትሌቲክስ አምስት የወርቅ፣ አምስት የብርና ስምንት የነሐስ ሜዳሊያ የተመዘገበ ሲሆን በወርልድ ቴኳንዶ አንድ የወርቅና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ተመዝግበዋል።በቦክስ ስፖርት አንድ የነሐስ ሜዳሊያ ሲመዘገብም ቀሪው በብስክሌት ስፖርት የተመዘገበ ሆኗል።ይህም በበርካታ ስፖርት ተሳታፊ በመሆን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል የታየበት ነው ተብሏል።የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሪፖርት እስካሁን ያልቀረበው ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በወቅቱ ሪፖርታቸውን ባለማቅረባቸውና እንደ አትሌቲክስ ያሉ ፌዴሬሽኖች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ተጠምደው በመክረማቸው መሆኑ ታውቋል።አዲስ ዘመን ጥቅምት25/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=22004
777e2f6d8cfe64212dbcad7d5b117fa6
2f89919a68929c341288c33e30e069b1
ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለታላቅ ሽልማት ታጭተዋል
ስፖርት
የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በየዓመቱ በሚያዘጋጀው የምርጥ አትሌቶች ሽልማት ከዚህ ቀደም በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ቢሆኑም አምናና ዘንድሮ በሁለቱም ፆታ ከምርጥ አስር እጩዎች ውስጥ እንኳን ሳይካተቱ መቅረታቸው ይታወቃል። ይሁን እንጂ ዓለም አቀፍ ማህበሩ በሚያዘጋጀው ተመሳሳይ የሽልማት ዘርፍ ወጣትና ወደፊት ትልቅ ተስፋ ባላቸው አትሌቶች ሽልማት ዘርፍ ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከመጨረሻዎቹ ምርጥ አምስት እጩዎች ውስጥ መካተት ችለዋል። ከሃያ ዓመት በታች የሆኑ አትሌቶች በሚሸለሙበት ዘርፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመካከለኛና ረጅም ርቀቶች ድንቅ ብቃት እያሳየ የሚገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ስም ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ታውቋል።ሰለሞን ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ሽልማት እጩ መሆን እንደቻለ ይታወሳል። የደቡብ ፖሊሱ ክለብ አትሌት የሆነው ሰለሞን ባረጋ ከእድሜው ከፍ ብሎ ከታላላቆቹ ጋር በመወዳደር እያስመዘገበ ላለው ስኬት ባለፈው ዓመት ክለቡ የኢንስፔክተርነት ማዕረግ የሰጠው ሲሆን ባለፉት ሦስት ዓመታት እያሳየ ያለው አስደናቂ ብቃት ወደ ፊት ተስፋ እንዲጣልበት አድርጓል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ታላላቅ የውድድር መድረኮች መጥቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ የስፖርት ቤተሰቡ አይን ማረፊያ የሆነው ወጣት አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውጤቱና አስደናቂ ብቃቱ ኢትዮጵያ በቅርቡ በታላላቅ መድረኮች አረንጓዴውን ጎርፍ ዳግም የማየት ብሩህ ተስፋ እንዳላት ማሳያ መሆኑን በርካቶች ይመሰክሩለታል። ድንቅ የሩጫ ተሰጥኦው በመካከለኛና ረጅም ርቀቶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ዙፋን ላይ እንደሚወጣ የስፖርቱ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ መስክረውለታል። ከ18 እና ከ2o ዓመት በታች የዓለም ወጣቶች ቻምፒዮና አሸናፊ መሆን የቻለው ሰለሞን የለንደን የዓለም ቻምፒዮና በቀጥታ ወደ ትልቅ ደረጃ ተሸጋግሮ የኢትዮጵያውያንን የአምስት ሺ ሜትር ስብስብ ምን ያህል አስፈሪ እንዳደረው ይታወሳል። ዘንድሮም ይህን አቋም በመድገም በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ወደ ማስመዝገብ ተሸጋግሯል። በ2018 የውድድር ዓመት የአምስት ሺ ሜትር አጠቃላይ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊ መሆን የቻለው ሰለሞን ባረጋ በርቀቱ ከሃያ ዓመት በታች የዓለም ክብረወሰንን 12፡ 43፡02 በሆነ ሰዓት ከመጨበጡ ባሻገር እኤአ 2005 ላይ ቀነኒሳ በቀለ በርቀቱ ካስመዘገበው ሰዓት ወዲህ ፈጣን ሰዓት ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል። ሰለሞን በዓለም ከሃያ ዓመት በታች ቻምፒዮናና በአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮናም በርቀቱ አራተኛ ደረጃን ይዞ በመፈፀም በውድድር ዓመቱ በርካታ ስኬቶችን አግኝቷል። ዘንድሮም በዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ከማጥለቁ ባሻገር በአምስት ሺ ሜትር 12፡53፡04 በመሮጥ ከሃያ ዓመት በታች አትሌቶች ሁሉ ፈጣን መሆን ችሏል። በአስር ሺ ሜትርም ከሃያ ዓመት በታች የዓመቱን መሪ ሰዓት 26፡ 49፡46 በሆነ ሰዓት ማስመዝገቡ ይታወሳል። አርሁስ ላይ ተካሂዶ በነበረው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በአዋቂዎች ምድብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁም ለሽልማቱ እጩ አድርጎታል። በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስት ሺ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ እንድታገኝ ያስቻለው አትሌት ለሜቻ ግርማ ከአምስቱ ተስፈኛ እጩዎች መካከል አንዱ መሆን ችሏል። ለሜቻ በውድድር ዓመቱ በርቀቱ ከሃያ ዓመት በታች መሪ የሆነውን ሰዓት በ8፡01፡36 ያስመዘገበ ሲሆን የኢትዮጵያን ክብረወሰንም የግሉ ማድረግ ችሏል። በዓለም ቻምፒዮናውም የወርቅ ሜዳሊያ ያመለጠው በ0ነጥብ01 ማይክሮ ሰከንድ ተቀድሞ እንደነበረ አይዘነጋም። ከሁለቱ ኢትዮጵያን እጩዎች ጎን ለጎን ብራዚላዊው የአራት መቶ ሜትር መሰናክል ተወዳዳሪ አሊሰን ዶስ ሳንቶስ እጩ መሆን የቻለ ሲሆን በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና ሰባተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ይህ አትሌት የፓን አሜሪካን ቻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል። ኖርዌያዊው አትሌት ጃኮብ ኢንግብሪትሰን ሌላኛው እጩ ሲሆን የአውሮፓ የሦስት ሺ ሜትር ቻምፒዮን ነው። ይህ አትሌት የዓለም ከሃያ ዓመት በታች የ1500 ሜትር መሪ ሰዓት ያለው ሲሆን የአውሮፓ ከሃያ ዓመት በታች ክብረወሰን ማሻሻሉ በውድድር ዓመቱ የሚጠቀስለት ስኬት ነው። ዩክሬናዊው መዶሻ ወርዋሪ ማይክሃይሎ ኮክሃን ከሃያ ዓመት በታች የመዶሻ ውርወራን 77ነጥብ 39 በመወርወር በውድድር ዓመቱ መሪ ሲሆን በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና አምስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በሴቶች በኩል አፍሪካን የወከለችው ብቸኛዋ አትሌት ኢትዮጵያዊቷ ለምለም ኃይሉ ሆናለች። በዓለም ከ20 ዓመት በታች ቻምፒዮና በ 1ሺ500 ሜትር 4:02.97 የገባችው ለምለም የርቀቱ ቀጣይ ተስፋ እንደምትሆን እምነት ተጥሎባታል። በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ በዚሁ ርቀት ነሃስ ሜዳሊያ ባለቤት እንዲሁም በዶሃው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ላይ አገሯን ለመወከል በቅታለች። ለምለም በቻምዮናው ላይ ውጤት ባታስመዘግብም እስከ ግማሽ ፍጻሜ በመጓዝ ያሳየችው አስደናቂ ብቃት እጩ አድርጓታል። በወጣቶች ዓለም ቻምፒዮናው ላይ በ100 ሜትር መሰናክል 12.71 በሆነ ሰዓት በመግባት ዓለም ክብረ ወሰንን የሰበረችው ጃማይካዊቷ ብሪታኒ አንደርሰንም ከእጩዎቹ መካከል ትገኛለች። ዩክሬናዊታ ያሮስላቫ ማሁቺክ ሌላኛዋ እጩ ስትሆን በከፍታ ዝላይ ስፖርት የተሻለ አቅም ያላት አትሌት ናት። አትሌቷ በቻምፒዮናው 2 ሜትር ከ04 ሳንቲ ሜትር በመዝለል የክብረ ወሰን ባለቤት ናት። በዶሃው የዓለም ቻምፒዮናም የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። ከዚህም ባሻገር አውሮፓ ቻምፒን መሆን የቻለች ጠንካራ አትሌትም ናት። የኢኳዶሯ እርምጃ ተወዳዳሪ ግሌንዳ ሞርጆን በወጣቶች ቻምፒዮና ያስመዘገበችው ውጤት እጩ አድርጓታል። ያስመዘገበችው 1:25:29 የሆነ ሰዓት ደግሞ ከዓለም ምርጦች ተርታ ሲሰለፍ በደቡብ አምሪካ ደግሞ ቀዳሚው ሆኖላታል። አትሌቷ በአህጉር አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ላይ የገባችበት 43:04 ሆነ ሰዓትም ክብረወሰን ነው። አምሪካዊቷ 100 ሜትር የወጣቶች ባለክብረወሰን ሻካሪ ሪቻርድሰንም ከአምስቱ እጩ አትሌቶች መካከል አንዷ ናት። በወጣቶች ዓለም ቻምፒና 100 ሜትሩን በ 10.75 ስታጠናቅቅ 200 ሜትሩን ደግሞ በ 22.17 ገብታለች። ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ሽልማት ኢትዮጵያዊቷ ወጣት አትሌት መሰረት በለጠ ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች አንዷ በመሆን መመረጧ ይታወሳል። መሰረት ባለፈው የውድድር ዓመት ግማሽ ማራቶን ውድድር ከዓለም ከሃያ ዓመት በታች ምርጥ የተባለውን 1፡07፡ 51 ሰዓት ማስመዝገቧ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ በስፔን ቫሌንሲያ ተካሂዶ በነበረው የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና ላይ ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ቢሆንም በቡድን የወርቅ ተሸላሚ ነበረች። በጉተንበርግ ግማሽ ማራቶንም አሸናፊ ሆና ማጠናቀቋ አይዘነጋም። ሌላኛዋ ወጣት ኢትዮጵያዊት አትሌት መስከረም ማሞም አምና ከእጩዎቹ መካከል የተካተተች ሲሆን በውድድር ዓመቱ በዓለም ከሃያ ዓመት በታች የሦስት ሺ ሜትር ውድድር በ8፡33፡63 ሰዓት ፈጣን ተብላ ነበር። የ2018 ምርጥ ታዳጊ አትሌት ሽልማት አሸናፊ በፈረንጆቹ ህዳር 23 ቀን በፈረንሳይ ሞናኮ በሚደረገው የዓለም የዓመቱ ምርጥ የአትሌቶች ሽልማት ይፋ እንደሚሆን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አሳውቋል።አዲስ ዘመን ጥቅምት26/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=22051
651c0ad15871db56943d07451f1fa2f5
6341bc919ff668d2332502bab8dda291
አካዳሚው ባለፉት አምስት ዓመታት
ስፖርት
አካዳሚዎች የሁሉም ስፖርቶች መሠረት ለመሆናቸው ዓለም አቀፍ ልምዶችን መመልከት በቂ ነው። በስፖርቱ መሠረት ያላቸውን ታዳጊዎች ሰብሳቢ የሆኑት አካዳሚዎች ድንቅ የእግር ኳስ፣ አትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ቦክስ ወዘተ…ጥበበኞች በማፍራት ረገድ ስኬታማ መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። በአካዳሚዎች ገና ከሕፃንነታቸው እንዲሰለጥኑ መንገድ በመክፈት፤ ወደ ታዳጊነት በማሸጋገር ራዕያቸውን እንዲያሳኩ በማንደርደርና ወደ ታላቅነት ስፍራ በማድረስ ይሄንኑ አስመስክረዋል። በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች ስኬታማ መሆን የቻሉ ስፖርተኞች መነሻቸው ሲፈተሽ በዚህ መንገድ የተጓዙ ሆነው እናገኛለን። የአካዳሚውን መሠረታዊ ጥቅም የተረዱ እንደነ እንግሊዝ፣ ስፔን ወዘተ… በተለይ በእግር ኳሱ ላይ ትኩረት አድርገው ሰርተዋል። ውጤታማ ለመሆንም መብቃታቸው በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ምስክር ሆነው ይቀርባሉ። ከዚህ አኳያ አካዳሚዎችን ወደ አገራችን ማምጣቱ ለስፖርቱ ትንሳኤ ዋነኛው መድህን እንደሚሆን በስፖርት አዋቂዎች በኩል ሲንጸባረቅ ቆይቷል። ምክረ ሃሳብ ተደጋግሞ በስፋት ተነግሯል። በተለይ ደግሞ፤ ኢትዮጵያ በዓለም ታላላቅ መድረኮች የታወቀችበትን አትሌቲክስ ስፖርት በመጥቀስ፤ ከዓለም በ5 ሺ ፣10 ሺ ሜትር እንዲሁም በማራቶን ስሟ በቀዳሚነት ትጠራለች።ከዚህ ጥሪ ፊት ለፊት ሞገስ ሆነው የሚቀርቡት ደግሞ ጀግኖች አትሌቶቻችን ናቸው። የአትሌቶቹ ስኬታማነት በግላቸው የሚያደርጉት ጥረትና ከአሰልጣኞቻቸው የሚቸራቸውን ሙያዊ እገዛ ምርኩዝ በማድረግ ነበር። የተፈጥሮ ችሎታቸውን መሠረት ባደረገ ሁኔታ በሳይንሳዊ ሥልጠና ባልታገዙበት በዚያን ዘመን፤ በፍላጎትና በአገር ፍቅር ለድል በቅተዋል። የትናንት ጀግኖች አትሌቶቻችን ከተፈጥሯዊ ችሮታቸው ጋር ሳይንሳዊ ሥልጠናው ቢደመር ምናልባትም ከሰሩት ታሪክ የበለጠ እንደሚሰሩ ጥርጥር የለውም። በአካዳሚዎች መሠረት ባለው ሁኔታ በአትሌቲክሱ ያለውን የተፈጥሮ ችሮታ ደግፎና አሳድጎ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ በስፖርት አዋቂዎች በኩል ተደጋግሞ ሃሳብ ሲቀርብ ቆይቷል። መንግሥት ምክረ ሃሳቡን «ጆሮ ዳባ ልበስ» በሚል አንጥሮ በመመለስ ዓመታትን ተጉዟል። አትሌቲክስን ጨምሮ በተለያዩ የስፖርቱ ዓይነቶች እየተስተዋለ ያለው የውጤት መዋዠቅ ብሎም፤ አንጋፋዎቹን የሚተኩ ታዳጊዎች አለመኖር አካዳሚዎችን ማቋቋሙ መሠረታዊ መፍትሄ እንደሆነ አቋም እንዲያዝ አድርጓል።ስፖርቱን በሚመራው ኮሚሽን ዘንድ ሃሳቡን በመግዛት ወደ ትግበራ ለመቀየር በቅቷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ በማድረግ በወጣቶች ተስፋ ሰንቆ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ተቋቋመ። መንግሥት የአካዳሚው መቋቋም ፋይዳው ዘግይቶ ቢገባውም፤ ወደ ትግበራው መግባቱ እንደመልካም የተቆጠረለት ነበር። ይሄንን መስመር በማለፍ አካዳሚው በ2005 ተመርቆ በ2006 ዓ.ም ስፖርተኞችን መልምሎ ሥራውን ጀምሯል። በአትሌቲክስ፣ በፓራሊምፒክ፣ በቮሊቦል፣ በእግር ኳስ፣ በውኃ ዋና፣ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በቦክስና በብስክሌት የስፖርት ዓይነቶች ሥልጠና በመስጠት ጉዞውን ሊጀምር በቅቷል። አካዳሚው የሥልጠና አቅሙን ከፍ ለማድረግ በ2002 ዓ᎐ም ሥራ ከጀመረው የጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከልን በመጠቅለል ትግበራውን አጠነከረ። የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ በአዲስ አበባ ካምፓስ በሀገሪቱ ስፖርት የሚስተዋለውን የተተኪ ችግርን ሳይንሳዊ በሆነ ሥልጠና ታግዞ ለመቅረፍ ወደ ትግበራ ከገባ አምስት ዓመታትን አስቆጥሯል። አካዳሚው በአምስት ዓመት ቆይታው ያስመዘገበውን ውጤት፣ የነበሩበትን ተግዳሮቶችንና ቀጣይ ለመጓዝ ያሰበውን አቅጣጫ በተመለከተ በጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በአካዳሚው መሰብሰቢያ አዳራሽ ለጋዜጠኞች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል። የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ አንበሳው እንየው እንደገለፁት፤ የአካዳሚው አላማ የታዳጊዎችና ወጣቶች ሥልጠና አደረጃጀት እና አሠራር ከልማዳዊ አሠራር በማላቀቅ ሳይንሳዊ ዘዴ ላይ እንዲመሰረት ማድረግ ነው። ስፖርቱን ወደ ተሻለ አድማስ ለማድረስ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ ታዳጊዎችን በ10 የስፖርት ዓይነቶች በመመልመል አሰልጥኖ ማስመርቁን ይገልጻሉ። አካዳሚው ምርጥ ስፖርተኞች የማፍራት ተልዕኮውን በመያዝ ከአምስት ዓመት በፊት መቋቋሙን አስታውሰውም፣ ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም በሦስት ዙር ያሰለጠናቸው 181 ስፖርተኞች 140 የተለያዩ ክለቦችን እንደተቀላቀሉ አብራርተዋል። በዚህም አካዳሚው ተልዕኮው ከማሳካት አኳያ እየተሳካለት እንደሚገኝ ይናገራሉ።እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ፤አካዳሚው ባለፉት አምስት ዓመታት በነበረው ጉዞ በጥንካሬ በርካታ ነጥቦችን አንስቷል። የመጀመሪያው ሰልጣኞች በአካዳሚው በሥልጠና ላይ እያሉ በክለቦች መመረጣቸው ነው። በተናጠልም በቡድን አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ውጤቶች ማስመዝገባቸው ሌላኛው ጥንካሬ ነው። ሰልጣኞች በስፖርት ሥልጠና የተለያዩ ክህሎቶች እንዲሁም በአካዳሚክ እና ተጨማሪ የቋንቋ እና የመሠረታዊ ኮምፒዩተር ክህሎት እንዲይዙ መደረጉ እና በተለያዩ ምክንያት በውድድር ስፖርት መቀጠል ያልቻሉ በተጓዳኝ ሙያዎች (በአሰልጣኝነት አልያም በዳኝነት መቀጠራቸው) እንደ ጥንካሬ ተነስቷል።ሰልጣኞቹ ከተመረቁ በኋላ እያደረጉ የሚገኘውን እንቅስቃሴና ያመጡትን ውጤት ምን እንደሚመስል ዳሰሳ ማድረግ እንደተቻለ የተገለፀ ሲሆን እንደ ጥንካሬም ተወስዷል። የአካዳሚው ቆይታቸውን የጨረሱ ሰልጣኞች የሙያ ብቃት ምዘና ሲኦሲ እንዲወስዱ የሚደረግ መሆኑ ሰልጣኞቹ በአቅም፣ ችሎታና እውቀት ምልኡ በመሆን እንዲወጡ ማድረጉም ተቀምጧል። በሦስት ዙር ተመርቀው ከወጡ ስፖርተኞች የሙያ ብቃት ምዘናውን ከወሰዱት 99 በመቶ ያህሉ ያለፉ ናቸው። ይህም በአካዳሚው የሚሰጠው ሥልጠና ፍሬያማ መሆኑን ያስገነዘበ ጭምር መሆኑን በጥንካሬ ታይቷል። በተጨማሪም ሰልጣኞች የመደበኛ ትምህርት ፍላጎት እያደገ መምጣቱ በመልካም ጎኑ የተገለጸ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከአካዳሚው የሚወጡ ስፖርተኞቸ በስፖርተኞቹ ብቻም ሳይሆን በመደበኛውም ትምህርት የተሻሉ እንዲሆኑ የሚያግዝ ተሞክሮ መሆኑን ነው ያብራሩት። የአካዳሚው ትምህርትና ሥልጠና ውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዮት ተስፋዬ፤ የአካዳሚው ፍሬዎች በ2011 ዓ.ም በነበሩ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች በመሳተፍ የነበራቸውን ውጤታማነት ለአካዳሚው ስኬት እንደማሳያ አንስተዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ ውጤታማ ያልነበረችበት ርቀት ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ቢሆንም አሁን ታሪክ ተቀይሯል። በራባት ሞሮኮ በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታና የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ የሆነው የኢትዮጵያ የርቀቱ ባለ ክብረ ወሰን ጌትነት ዋለ አካዳሚው ካፈራቸው ስኬታማ አትሌቶች ዋነኛው መሆኑን ነው ያመላከቱት። ቦነስ አይረስ ላይ በተካሄደው የዓለም የታዳጊዎች ኦሊምፒክ የወርቅ ባለቤት የሆነው አብርሃም ስሜ፣ በማራካሽ ሞሮኮ በተካሄደው 4ኛው ኢንተርናሽናል ፓራሊምፒክ አትሌቲክስ ውድድር በ1 ሺ500 ሜትር ወርቅ፣ በ800 ሜትር ነሐስ ሜዳሊያ ማስመዝገብ የቻለው ገመቹ አመኑ እንዲሁም በተመሳሳይ መድረክ በ200 ሜትር እና በ400 ሜትር ወርቅ ያስመዘገበችው ዝናሽ አሰፋ የአካዳሚው ስኬታማነት ማሳያ መሆናቸው ይገልጻሉ። በዓለም አቀፍና በአህጉር አቀፍ መድረኮች የአካዳሚው ፍሬ የሆኑ ስፖርተኞች እያስመዘገቡ የሚገኙት ውጤት አካዳሚው ከተቋቋመበት አላማና ራዕይ እኩል እየተጓዘ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አስቀምጠዋል:: አካዳሚው የቆመለትን ዓላማ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የሁለተኛ ዘመን ስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ትግበራ በሕዝብ እና አጋሮች ተሳትፎ እንዲከናወን የሚያስችል ሥራ የሚሰራ መሆኑንም ነው ያብራሩት። አዲስ ዘመን ጥቅምት 16/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=21516
4d51de5e5a15ba0a30b7cb9e0769e19b
932abc02cc3373e3e666d7ca3599ea22
ዓብይ ኮሚቴው የእስካሁን ክንውኖቹን አስታውቋል
ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘንድሮ ውድድር ዓመት በቅርቡ በተዋቀረው ዓብይ ኮሚቴ እንዲመራ መደረጉ ይታወቃል። ይህ ኮሚቴም እስካሁን ድረስ የተለያዩ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፤ ከትናንት በስቲያም ኮሚቴው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተገኝቶ በክንውኖቹ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።የዚህ ዓመት ውድድር የሚጀመረው ኅዳር 13 እና 14/2012 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል። የሊጉ ዕጣ አወጣጥ ሥነሥርዓትም ኅዳር አምስት የሚደረግ መሆኑን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ጠቁሟል። በዕለቱ በውድድር ደንቡ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን፤ ደንቡ ቀደም ብሎ ለሁሉም የሊጉ ተሳታፊዎች እንዲደርስ በማድረግ አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ይጸድቃል። ዓብይ ኮሚቴው ለዚህ የሚሆነውን የውድድር ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ አባላትን የመረጠ መሆኑም አስታውቋል። ሰባቱ አባላትም፤ አቶ ሃብታሙ ኃይለሚካኤል፣ ዶክተር ወገኔ ዋልተንጉስ፣ አቶ ወንድአወቅ አበዜ፣ አቶ አብርሃም ተክለሃይማኖት፣ ኮማንደር ጌታቸው ኤጀርሶ፣ አቶ ዮናስ ገብረሚካኤል እና አቶ ሞገስ በሪሁን ናቸው። የኮሚቴ አባላቱ ምርጫም በመስፈርትነት የትምህርት ማስረጃ በትንሹ ዲግሪ ያለው ዕድሜው ከ60 ያልበለጠ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በውድድር ታዛቢነት እና በኮሚሽነርነት ያልሰራ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። ይህ የተደረገበት ምክንያትም ሁለቱ ዓመታት በተለይ በእግር ኳሱ ጥሩ የሚባል ጊዜ እንዳልነበረ ታሳቢ በማድረግ ነው። በዚህም ትክክለኛ ባልሆነ ፍርድ ተሳታፊ የነበሩ አካላት በኮሚቴው አልተካተቱም። የኮሚቴው አባላትም በቅርቡ ተሰባስበው የሥራ ክፍፍል የሚያደርጉ ሲሆን፤ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ሥራቸውን እንደሚያከናውኑም ነው የተጠቆመው። ከዚህ ቀደም የነበረው የውድድር ሥርዓት ኮሚቴ አሠራርን ፌዴሬሽኑ ማሻሻያ ሊያደርግበት አስቦ ነበር። ይህንን ተከትሎም ዓብይ ኮሚቴው መመሪያዎችን በማዘጋጀት ለሥነሥርዓት ኮሚቴው የሚሰጥ ይሆናል። ኮሚቴው የተለያዩ ሜዳዎችን ተዘዋወሮ የተመለከተ ሲሆን፤ ለውድድሩ የማይመጥኑትን በመለየትም ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ከዚህ ቀደም ማሳሰቡ ይታወቃል። በዚህም የድሬዳዋ፣ ሰበታ እና ወልቂጤ ሜዳዎች ለውድድር ብቁ ባለመሆናቸው ሌላ ሜዳ መፈለግ እንደሚገባ ተገልጾላቸዋል። የሆሳዕና፣ ወላይታ ሶዶ እና ጅማ ስታዲየሞች ደግሞ ማስተካከያ ማድረግ የሚገባቸው ናቸው። በዓብይ ኮሚቴው ምልከታ መሠረት አጥር የሌላቸውና የተመልካችን ደህንነት ለማረጋገጥ ከዓለም አቀፉ መስፈርት ቢያንስ ትንሹን ማሟላት እንደሚገባቸውም አመልክቷል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 16/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=21519
7f46fc2c2db649d76554b04e9c278401
161a89eee2e1cacf130a7d476a58887a
ጁንታው በጠለምት ሕዝብ ላይ ያደረሰው በደል ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- ጁንታው እስካሁን ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ካደረሳቸው በደሎች በጠለምት ህዝብ ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የጠለምት ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ወረታ ተናገሩ፡፡ አቶ መርሻ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ የትህነግ ጁንታ ቡድን በጠለምትና አካባቢው ማህበረሰብ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚ እንዳይሆን ዘርፈ ብዙ ጭቆና አድርሶበት ቆይቷል፡፡ የጥፋት ቡድኑ ገና ከጥንስሱ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ካደረሳቸው በደሎች በጠለምት ህዝብ ላይ ያደረሰውና ያሳደረው ጭቆና ዘርፈ ብዙ ነው፡፡አቶ መርሻ፣ ጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ ፀጋዎች የታደለ ቢሆንም ተፈጥሮ ከቸረው የበዛ ፀጋ ውስጥ ግን ህዝቡ ተጠቃሚ እንዳይሆን ተደርጓል፤ የጁንታው ቡድን ተጽዕኖም የበይ ተመልካች አድርጎታል፤ በህዝቡ ላይ ተጭኖት የነበረው የአምባገነን ቀንበር ልኩም በቃላት መግለጽ ከሚቻለው በላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡እንደ አቶ መርሻ ገለፃ፤ ጁንታው ወረዳውን ከመሰረተ ልማት ውጭ አድርጎት ቆይቷል፡፡ ለራሱ የጥፋት ዓላማ የሚመቹትን ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን እየቀየሰ የአስፓልት መንገድና ኮንክሬት ምሽግ እየሠራ ሲደራጅና መደበቂያ ዋሻ ሲያዘጋጅ ነው የኖረው። ማህበረሰቡን ግን በተጎሳቆለ ሁኔታ በድህነት እንዲማቅቅ አድርጎት ቆይቷል፡፡ጁንታው በሀገር ላይ ካደረሰው ጥፋት በጠለምት ወረዳ ላይ ያደረሰው ጉዳት የተለየ መሆኑን የሚናገሩት አቶ መርሻ፤ ጁንታው የህዝቡን ሁለንተናዊ ማንነት ብቻ ሳይሆን ገና ሮጠው ያልጠገቡ ታዳጊ ወጣቶችን የበላ ቡድን መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ይህ ደግሞ የጠለምትን ህዝብ ህይወት በመቅጠፍ ያልተገደበ፣ ይልቁንም የህብረተሰቡን ሥነ ልቦና እና የመኖር ዋስትናውን ነጥቆት የቆ በመሆኑ የጁንታውን ጥፋት ልዩ እንደሚያደርገው አብራርተዋል፡፡ እንደ አቶ መርሻ ገለፃ፤ የጥፋት ቡድኑ ለበርካታ ዓመታት በሀገር ያስከተለው ኪሳራ ሳያንሰው ጥቅምት 24 በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የራሱን ግብአተ መሬት አፋጥኖታል፡፡ በተለይም የጠለምት ወረዳ ከትግራይ ክልል ጋር በሚዋሰኑባቸው 12 በሚደርሱ ቀበሌዎች ዙሪያ ዳግም ሥልጣንን እቆናጠጥባቸዋለሁ ብሎ የተመካባቸው የሠራቸው ምሽጎች በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በአማራ ልዩ ኃይል ድባቅ ተመቶ ከለቀቀ በኋላ ህብረተሰቡ ደስታውን የገለፀበት መንገድ ልክ ለሌለው የግፍ ሥራው አንዱ ማሳያ ነው፡፡ እንደሀገር አሁን ላይ የሕግ ማስከበር ሂደቱ የተጠናቀቀ ቢሆንም የተወሰኑ ኃይሎች የመሸጉበት በጠለምት ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ ስለሚገኝ አስፈላጊውን እርምጃ በመስጠት የማጽዳት ሥራ ይሠራል፡፡ በጁንታው ኃይል ታፍነው የቆዩ 1ሺ845 በላይ የሚሆኑ የሀገር መከላከያ የሠራዊት አባላትን በሁለት ዙር ተቀብለው ተንከባክበው እንዳሳለፏቸው የሚናገሩት አቶ መርሻ፤ በዚህ ልክ የፌዴራል መንግሥትም በከፍተኛ ሁኔታ ሕግ የማስከበር እርምጃውን አጠናክሮ የሚቀጥልበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ከፍተኛ ሥራ ተሠርቷል፡፡ አሁን ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ ማህበረሰቡ ከዚህ አረመኔ ጁንታ ሙሉ ለሙሉ ተላቆ ያለምንም ሥጋት እንደማንኛውም ማህበረሰብ የልማት ተቋዳሽ ሆኖ ለመኖር በጉጉት እየጠበቀ እንደሆነ ነው ምክትል ዋና አስተዳዳሪው የገለፁት፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37386
96dd2eb0b4ac8fd5975e792e137a3f15
30ed5efed7f80a6c3ffde802ffea0e2a
በዘንድሮው የመኸር እርሻ እስካሁን በ10 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ያለው ሰብል መሰብሰቡ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
እፀገነት አክሊሉ አዲስ አበባ፦ ከክልሎች በተሰበሰበው መረጃ መሰረት የዘንድሮው የመኸር ወቅት በዘር ከተሸፈነው 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር ውስጥ እስካሁን 10 ሚሊዮን የሚጠጋ መሬት ላይ ያለው ሰብል መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የእርሻ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት የዘንድሮው የመኸር እርሻ በምርትና ምርታማነት በኩል እጅግ ጥሩና ተስፋ ሰጪ ነው፡፡እንደ ዶክተር ማንደፍሮ ገለፃ በዘር የተሸፈነው መሬት 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ ሁሉም መረጃ ተጠናቅቆ ባይገባም 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሄክታር መሬት ላይ ያለው ሰብል ተሰብስቧል፡፡ ከዚህ ጋር ታያይዞም አሁን ያለው የሰብል ይዞታ የምርታማነት መጠን በጣም ጥሩ በሚባል ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ያሳያል፡፡ ለዚህ የመኸር ወቅት ውጤታማ መሆን የነበረው የዝናብ መጠን ለሰብል ምርታነማነት የሚመች መሆኑ ተጠቃሽ ነው ያሉት ዶክተር ማንደፍሮ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩልም ለግብርና ሥራው አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ግብዓቶችን በማቅረብ ረገድ ሰፊ ሥራ መሠራቱን አብራርተዋል፡፡በመኸር የሥራ ወቅት በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች የጎርፍ አደጋዎች መብዛትና የአምበጣ መከሰት በአገሪቱ በተለይም በግብርና ሥራው ላይ ከፍተኛ የሆነ መደናገጥን ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ተጽዕኗቸው ግን የተፈሩትን ያህል አልነበሩም ብለዋል ዶክተር ማንደፍሮ፡፡እንደ ዶክተር ማንደፍሮ ገለፃ ማሳቸው በጎርፍ የተወሰደባቸው። በአምበጣ የተወረረባቸው አርሶ አደሮች ነበሩ በግለሰብ ደረጃም ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አድርሷል፡፡ ነገር ግን እንደ አገር በመኸሩ እርሻ ይገኛል ተብሎ ከታሰበው ውጤት አንፃር ሲገመገም ግን ያን ያህል ከባድ ተጽዕኖ አድርሷል ለማለት እንደማይቻል አብራርተዋል፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ የወቅቱ የግብርና ሥራ በተቀናጀና ጥሩ በሆነ ሁኔታ ዝግጅት ተደርጎበት አስፈላጊው ግብዓት ተሟልቶለት ወደ ሥራ በመገባቱ ነው ያሉት ዶክተር ማንደፍሮ፤ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ በክረምቱ ወቅት የጣለው ዝናብ እጅግ ለሰብል የሚመችና የተመጣጠነ በመሆኑ ብዙ ምርት ተመርቷል ብለዋል፡፡ በዚህም ምርትና ምርታማነት ከምን ጊዜውም በላይ የጨመረበት ወቅት በመሆኑ ይህንን በጎርፍ እንዲሁም በአምበጣ የተጎዳውን ሰብል ለማካካስ ከባድ እንደማይሆንም አብራርተዋል፡፡ የዘንድሮው የግብርና ሥራ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ለእርሻ ሥራው የዋለው መሬት ስፋት የተጠቀምነው የዘር። የማዳበሪያ መጠንና የነበረው የዝናብ ሥርጭት ከፍተኛ ነው፤ በዚህም ካለፈው ዓመት በተሻለ ሁኔታ ምርትና ምርታማነት የጨመረበት የተከሰቱት የተፈጥሮ አደጋዎች እንኳን ያልበገሩት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ ዶክተር ማንደፍሮ እንደገለፁት፤ የግብርና ሥራ ዓመቱን በሙሉ የሚሠራ ሥራ ነው ያሉት ዶክተር ማንደፍሮ ከዚህ የተነሳም ለቀጣይ የሥራ ጊዜ በተለይም ለመስኖ ምርት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ነው፤ በመስኖ ለማረስ መሬት ዝግጅት ያስፈልጋል፤ ዘር ውሃ እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች ያስፈልጋሉ፤ ይህንን አቀናጅቶ አቀናብሮ ከማዕከል እስከ ቀበሌ ድረስ ማጓጓዝም ሌላው ሥራ ነው ፤ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በተለይም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከል እንዲሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37393
7aa22f6204874f17f0e6abcce82ba7ad
1a820d8d816a3850ce1e908fd731448c
የጁንታው ቡድን ለወንጀሉ ተገቢውን ቅጣት እስኪያገኝ እርምጃው ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ፀጋዬ አዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታ ቡድን በሠራዊቱ ላይ የፈፀመው ጥቃት እና ንፁሃንን የገደለበት መንገድ በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው እንደመሆኑ ለሠራው ወንጀል ተገቢውን ቅጣት እስከሚያገኝ ድረስ የሕግ ማስከበር ተግባሩ ሊቀጥል እንደሚገባው በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም ተስፋዬ አስታወቁ፡፡ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም፣ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ከባድ ወንጀል በመፈፀሙ መደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ላያየው ይችላል፡፡ ተግባሩም በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ወንጀለኛ ቡድን ለሕግ እስከሚቀርብ ድረስ የሕግ ማስከበር እርምጃው ሊቀጥል የሚገባው ነው፡፡ እንደ ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም ገለፃ፤ የጁንታውን እኩይ ሥራዎቹን በሦስት ከፋፍሎ ማየት ተገቢ ነው፡፡ ይሄውም አንደኛ፣ አገር ሲመራ በነበረበት ጊዜ፣ ሁለተኛ፣ ከለውጡ በኋላ እና ሦስተኛ ማይካድራ ላይ የፈፀሙት ወንጀል ነው።፡ በዚህ ረገድ ለምሳሌ፣ በማይካድራ የፈፀሙት ወንጀል የሚዳኘው በጦር ወንጀል ሲሆን፤ ቀደም ብሎ የፈፀማቸው በመደበኛ ወንጀል የሚያስከስሳቸው ነው፡፡ የወንጀል ሕግ ደግሞ በባህሪው ያጠፋውን ወገን ወደ ፍትህ በማቅረብ ዜጎች ሰላማዊና የተረጋጋ ህይወትን እንዲመሩ ማስቻል ነው፡፡ “አሸንፋለሁ ብለህ ጦርነት አውጀህ በዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ማካሄድና የሰላማዊ ዜጎችን ህይወትን ማጥፋት በጦር ወንጀል ያስጠይቃል፤” ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም፤ በተመሳሳይ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት መፈፀም እና ያገቱትንም የመከላከያ ሃይል በጅምላ ረሽኖ መቅበር ሌላው በጦር ወንጀልን የሚያስጠይቃቸው እኩይ ሥራቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም እንደሚሉት፤ ከላይ የተጠቀሱት ድርጊቶቻቸው ብቻ በጦር ወንጀል ለመጠየቅ በቂ ነው፡፡ ምክንያቱም በንፁሃን ዜጎች የወሰዱት እርምጃ በየትኛውም መንገድ ሲገመገም አግባብነት የለውም፡፡ ብሔር ተኮር የሆነ ጥቃት አድርሶና በጅምላ ጨፍጭፎ አስከሬን በየጥሻውና በየገደሉ መጣልም ሌላው ተጨማሪ እኩይ ተግባራቸው ነው፡፡ እንደ አጠቃላይ ሲወሰድም ይህ ሁሉ ወንጀላቸው ተደምሮ የጁንታውን አባላት በጦር ወንጀል ለመከሰስ በቂ ማስረጃ ነው፡፡መንግሥት ሀገርን የመጠበቅ ሃላፊነትና ግዴታ ስላለበት የሕግ ማስከበር ዘመቻው አግባብ መሆኑን የሚናገሩት ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም፤ መንግሥት ሕግ ማስከበርና የዜጎችን ዋስትና የመጠበቅ ግዴታ ስላለበት የተጀመረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባውም ገልፀዋል፡፡ የሕግ የበላይነት ልዕልና ተከበረ የሚባለውም መጨረሻ ላይ ፍትህ ሲሰፍን ብቻ እንደመሆኑም ለተፈፀሙ ጥፋቶች ተገቢው ቅጣት እስኪወሰን ድረስ በጥሩ መልኩ የቀጠለው የድል ጉዞ መቀጠል እንዳለበት መክረዋል፡፡እንደ ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም ገለፃ፣ ፍትህ ሰፈነ የሚባለው አጥፍተው በየቦታው ያሉ ግለሰቦች ተለቅመው ለሕግ ሲቀርቡና ውሳኔ ሲሰጥ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ሕግን ከማስከበር ባለፈ ፍትህን ከማስፈን አንፃር በቀጣይ የሚሠሩ በርካታ ሥራዎች አሉ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ህዝቡን ማረጋጋት፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ መደበኛ ኑሯቸው መመለስና ክልሉን የመልሶ ግንባታ ሥራን እንዲሁም የክልሉን የመንግሥት መዋቅር መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡በዚህ ዘገድ የመንግሥት ሥራ ብዙ ነው፡፡ የሕግ ማስከበር ዘመቻውም በዚህ መልኩ መጠናቀቅ አለበት።፡ ሰላም የማምጣት ሂደት ተቋማትን የመገንባት ጉዳይ ስለሆነ ተቋማትን በአዲስ መልኩ ማደራጀት ከሁሉም በላይ በፍጥነት ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37397
0a8b9d1dfa32bb8faa7871ea7eb7408f
af7f932e36472dad3c1e4ac569c36d3c
ሽሬ ያፈራችው ዳግማዊው ሓየሎም
ሀገር አቀፍ ዜና
ጌትነት ተስፋማርያምየአገርንና ህዝብን ጡት ከነከሱና ካስለቀሱ ጁንታዎች በተቃራኒ የትግራይ ምድር ለአገርና ለህዝብ የታመኑና ህይወታቸውን ሳይሳሱ የሚሰጡ ጀግኖችን ማፍራት ታውቅበታለች። ለኢትዮጵያና ለክብሯ ሲሉ ውድ ህይወታቸውን የሰዉና የእነአሉላ አባነጋን ፈለግ የተከተሉ ብዙ ጀግኖችም ከትግራይ ማህጸን ፈልቀዋል፤ አሁንም በመፍለቅ ላይ ናቸው።ይህን ጉዳይ ስናነሳ በቅድሚያ ወደ አዕምሯችን ከሚመጡት አንዱና ቀዳሚው በጁንታው ሴራ ህይወቱን የተነጠቀው ሜጀር ጀኔራል ሓየሎም አርአያ ነው። ለዴሞክራሲና ለህዝቦች አኩልነት በተደረገ ትግል አኩሪ ገድል የፈጸመውና በብዙዎች ልብ ውስጥ በጀግነንት ታሪኩ የተጻፈው የሽሬው ሜጄር ጀኔራል ሓየሎም አርአያ፤ የሃሳብ ልዩነት ስላንጸባረቀ ብቻ ግፍና ሴራ ኑሯቸው ባደረጉት የጁንታው አባላት በግፍ ህይወቱን እንደተነጠቀ ብዙዎች የሚናገሩት ሀቅ ነው።ይህን በቅርበት ከሚያውቁት እና ጉዳዩን አስመልክቶ ሃሳባቸውን ለአዲስ ዘመን ከተናገሩት መካከል አቶ ሊላይ ኃይለማርያም አንዱ ናቸው። አቶ ሊላይ በአንድ ወቅት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ስለ ግድያው ሲያስረዱ፣ “ሓየሎምን ጁንታው እንደገደለው እርግጠኛ ነኝ። ሓየሎም በሰራዊቱ በጣም ተወዳጅ ከመሆኑም በላይ በአንዳንድ ጉዳዮች ከእነሱ ጋር አይስማማም ነበር። በትጥቅ ትግሉ ወቅት በረሃ ላይ እንዳይገድሉት ከአጠገቡ ሰው ስለማይጠፋ አልተመቻቸውም። በተገደለበት ወቅት ከእሱ በታች ያሉ ጄኔራሎች እንኳን በጥበቃ ነበር የሚሄዱት። እሱ ግን ጥበቃ አልነበረውም። እናም እነዚህን ሁሉ ስታይ እና ማን ገደለው ብለህ ስትጠይቅ እነሱ እንደሆኑ ትረዳለህ” ብለው ነበር።አገራችን ኢትዮጵያ ጀግኖችን ለመውለድ ማህጸነ ለምለም ናትና ዛሬም የሓየሎምን የጽናት ታሪክ የደገመ አንድ ጀግና ከሽሬ አፍርታለች። ይህ ጀግና ሃምሳ አለቃ ሓየሎም ነጋ ይባላል። ሽሬ ዞን አዲዳዕሮ በተባለ የትግራይ አካባቢ የተወለደው ሃምሳ አለቃ ሓየሎም፣ የመከላከያ ሰራዊት የ23ኛ ክፍለጦር አባል ነው። ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ሓየሎምና ጓደኞቹ በሱዳን ጠረፍ ሁመራ አካባቢ የሀገር ድንበር በመጠበቅ ላይ እንደነበሩያስታውሳል። ሀገር አማን ብለው አረፍ ባሉበት ምሽት ግን ጁንታውና ተላላኪዎቹ ጥቃት በመፈጸም እርሱንና ሌሎች የሰራዊቱ አባላትን አፍነው ወሰዱ። ከሁመራ ሉግዲ ወደ ሽሬ እና አክሱም ከተሞች ታፍነው በሚወሰዱበት ወቅት ሓየሎምና ሌሎች የሰራዊቱ አባላት መከራቸውን ሲያዩ እንደነበር አይዘነጋውም። ምግብና መኝታ እንኳን ሳይመቻች በአድዋ እና በጉዊሃ አካባቢዎች በአንድ ክፍል ታጉረው ቆይተዋል። ከዚህ ባለፈ ከቦታ ወደቦታ በተሽከርካሪ ሲያንቀሳቅሷቸው ሰው በሰው ላይ አነባብረው ያጓጉዙ እንደነበር ሓየሎም በኀዘን ያስታውሰዋል። ለ21 ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ታፍነው ሲቆዩ በየቀኑ አንድ አንድ የማታጠግብ ዳቦ እና አልፎ አልፎ ገንፎ እየበሉ ህይወታቸውን ለማትረፍ መታገላቸውንም ነግሮናል። የጁንታው ቡድን አባላት የትግራይ ተወላጆችን አስገድደው በመውሰድ ለራሳቸውም እኩይ ዓላማ እንደሚያሰልፉ ሓየሎም አጫውቶናል።እርሱ ግን አገሩን መክዳት ስለማይፈልግና በኢትዮጵዊነት ላይ ጽኑ አቋም ስለነበረው ከጁንታው ታጣቂዎች ጋር ላለመሰለፍ የትውልድ ቦታውን ቀይሮ የደቡብ ተወላጅ ነኝ በማለት ለአፋኙ ቡድን ታጣቂዎች ተናገረ። ይህን ዘዴ የተጠቀመውም ከመከላከያ ሰራዊት ጓዶቹ ጋር አብሮ ለመቆየት መሆኑን ይናገራል። ሓየሎም የትግራይ ተወላጅ መሆኑን በማሳወቅ ብቻ ከታፈኑት መካከል መውጣት እንደሚችል ቢያውቅም፤ አብረውኝ ከበሉ እና ከጠጡ ጓደኞቼ የሰራዊት አባላት አልለይም ብሎና አብሯችው እንደሚሆኑ እሆናለው የሚል ውሳኔ ላይ መድረሱን ይናገራል። በሌላ ጎኑም ታላቅ ክቡር ነውና ሀገር መክዳትን ፈጽሞ አልመረጠም።በአፈናው ወቅት ጓዶቹን አይዟችሁ ከሞትንም አብረን ነው የምንሞተው እያለ ያበረታታ እንደነበር አይዘነጋውም። በወቅቱ የጁንታው ታጣቂዎች አብረህ ከእኛ ጋር ሂድ ቢሉኝ እንኳን ዓላማ ስለነበረኝ ግደሉኝ እንጂ አይሆንም እንደምላቸው እርግጠኛ ነበርኩም ይላል። እንደሌሎች አይደለሁም ክደው የሄዱ ቢኖሩም እኔ ሰራዊቱን ክጄ አልሄድም፤ ሁለት መለዮ አልለብስም ብዬ ነው ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር የቆየሁት ማለቱን ሓየሎም ነገሮናል። ጓደኞቼንና አገሬን አልዋጋም የሚል የጸና አቋም እንዳለው የነገረን ሃምሳ አለቃ ሐየሎም፤ እኔ ሀገሬ ኢትዮጵያ ነችና ለሀገሬ ክብር ብዬ ነው የተነሳሁት፤ ለብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቆምኩ እንጂ፤ ለአንድ የጁንታ ቡድን ፍላጎት ብቻ አይደለም የሚል የጸና ሃሳብ በአዕምሮው መያዙንም ነግሮናል። በመጨረሻም የመከላከያ ሰራዊት ደርሶ የጁንታው ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ሲወስድ አፋኞቹ ሓየሎምን እና ሌሎች የሰራዊት አባላትን ከተከዜ ወንዝ ድንበር አካባቢ ወስደው ለቀቋቸው። ሓየሎምም ከጓደኞቹ ጋር ወደአማራ ክልል በእግሩ ተሻገረ። በአማራ ክልል የነበረው አቀባበል ጥሩ ነበር፤ ምግብ፣ አልባሳት እና የሞራል ድጋፉም አስደሳች እንደነበር ሓየሎም በኩራት ይነገራል። በአስቸጋው ቆይታ ወቅት የሰራዊቱ አባላት ሓየሎም ንጹህና ከእኛ ጋር አብሮ ሲታገል የቆየ ታማኝ ወታደር ነው በማለት በሙሉ ልብ አብረውት እንደተሰለፉ ያስታውሳል። በጁንታው ቡድን አማካኝነት ታፍነው የቆዩ የሰራዊቱ አባላት ጎንደር ላይ ተመልሰው ከተደራጁ በኋላ፤ ዳግም ወደግዳጅ ሲሰማሩ ሓየሎምም በትልቅ የሀገራዊ ስሜት አብሮ ወደትግራይ ክልል ተመለሰ። ጓደኞቹ አድናቆታቸውን በመግለጽ ያንተ ታማኝነት እና ተወዳጅነት ከፍተኛ ነውና፤ የያዝከውን መስመር ቀጥልበት ብለው በምላሹ ማበረታቻ ሰጥተውታል። “እኔ ህዝብን ወክዬ ቃለመሃላ የገባሁለት ጉዳይ አለኝ፤ ብሔር ብሔረሰቦችን በአጠቃላይም ኢትዮጵያን መጠበቅ አለብኝ ብዬ ነው ቃለመሃላ የገባሁት። በማንም ይሁን በማን ላይ በሀገሬ ኢትዮጵያ ጉዳይ ህግን የማስከበር ተግባር ሲያጋጥመኝ ወደኋላ አልልም። አሁንም ቢሆን ከጓደኞቼ ጋር ግዳጄን ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ሀገራችንን የበለጠ ሰላም እንደምናደርግም ተስፋ አለኝ” በማለት ለሀገሩ ያለውን ታማኝነት በገሃድ አሳይቷል። ከምንም ነገር ቅድሚያ ለአገር የሚለው የሽሬ ዞን ተወላጁ ሓየሎም ነጋ፤ ከአጥፊው ቡድን የሴራ ፖለቲካ ይልቅ ለህዝብ መወገኑ ብቻ ሳይሆን ለህይወቱ ሳይሳሳ ሀገሩን ያስቀደመ የሰራዊቱ አባል መሆኑንንም ጭምር በዳግማዊ ሓየሎምነቱ ሥራው ሲያስታውሰው ይኖራል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37451
73bc44290eae2ca799c92d992087be0c
5313d7fc3ae1401c55495a4cc8e83b16
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመዲናዋ ነዋሪዎች እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በመዲናዋ ለሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ ሥራዎች ለሚያደርጉት ድጋፍ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ምስጋና አቀረቡ፡፡ ነዋሪዎቹ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠይቀዋል። ጃን ሜዳን ለሃይማኖታዊ በዓል በሚመጥን መልኩ የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ እንደሆነም ገልፀዋል። ኢዜኣ እንደዘገበው፤ ምክትል ከንቲባዋ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩን የተለያዩ ሥራዎች ሲያግዙ ቆይተዋል። በተለይም መከላከያ ሠራዊት ለህዝብ ሰላም፣ ደህንነት አብሮነት ለከፈለው መስዋዕትነት የደረሰበት ጥቃት የከተማዋን ነዋሪዎች ያስቆጣና በጋራ ያቆመ መሆኑን ገልጸዋል። ምክትል ከንቲባዋ፣ መከላከያ ሠራዊት “ራሱ እየሞተ እኛን ያኖረ ሠራዊት ነው” ያሉት ምክትል ከንቲባዋ የተፈጸመበት ጥቃት “እጅግ በጣም አሳፋሪና አስነዋሪ ተግባር ነው” ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ የመዲናዋ ነዋሪዎች ካደረጉት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በላይ ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አክብሮት አሳይተዋል ነው ያሉት። ለአብነትም በአንድ ሳምንት ውስጥ ለመከላከያ ሠራዊት ከ 1ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ መቻሉ የከተማ አስተዳደሩ በአድናቆት የሚመለከተው መሆኑን አንስተዋል። ከዚህ ጎን ለጎንም ኅብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ አጋር እንደነበር ገልጸው በየቀኑ ከሚደርሱት ጥቆማዎችም 98 በመቶዎቹ ትክክለኛ ጥቆማዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል። የአዲስ አበባ ነዋሪ ኮቪድ 19ን መከላከል፣ ለተማሪዎች ምገባ፣ ለታላቁ ህዳሴ ግድብና ለሌሎችም በጎ ተግባራት በጥቂት ወራት ውስጥ በድምሩ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመዋል። “የአዲስ አበባ ነዋሪ በጣም ተባባሪና አስተዋይ ነው” ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ድጋፉን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ጃን ሜዳ የጥምቀት በዓል ብቻ የሚከበርበት ሳይሆን ሌሎችም በርካታ ማኅበራዊ ኩነቶች የሚካሄዱበት በመሆኑ በዚህ ደረጃ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። አሁንም የጥምቀት በዓል እየተቃረበ በመሆኑ ሥፍራውን ለሃይማኖታዊ በዓሉ በሚመጥን መልኩ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ገልጸዋል።በስፍራው በጊዜያዊነት ተዘዋውረው የቆዩ ነጋዴዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሃይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚሰሩበት የገበያ ማዕከል ተገንብቶ እየተጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመዋል። ስፍራው ሁሉንም የገበያ ተዋናይ፤ የግብዓት አቅራቢንም ጭምር ማዕከል ያደረገና ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል መሆኑን አስረድተዋል። የአትክልት ተራ ነጋዴዎችም ማፍረስና ማጽዳት ይጀመራል ከተባለበት ቀናት በፊት ሥራዎችን ከወዲሁ እያጠናቀቁ መሆኑን አንስተው፤ ለነጋዴዎቹ ምስጋና አቅርበዋል።በሌላ በኩል ከ 1 ሺህ 400 በላይ ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ፣ ሱቆችና ሌሎች አገልግሎቶችን መስጠት የሚችለው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ነው ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37398
b6b96c67a0ed6d091eb2b32e2f5c650c
e3005ee1aa72de148186ce4d66b5ecad
ባለፉት አራት ወራት ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በህዳሴ ግድብ አካውንት ገቢ መደረጉ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ጸጋዬአዲስ አበባ፡- በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎች ያልተገ ታው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ድጋፍ ከምን ጊዜውም በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉ እና ባለፉት አራት ወራት ብቻ ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በልማት ባንክ የተረጋገጠ በህዳሴው ግድብ አካውንት ገቢ መደረጉ ተገለጸ።በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቀላል የማይባል የህዝብ ለህዝብ የዲፕሎማሲ ሥራ እየሠሩ መሆኑንም ነው የታላቁ የህዳሴ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ያስታወቀው።የጽህፈት ቤቱ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝብ ተሳትፎ ከወቅታዊ የህግ ማስከበር ሂደት ጋር በተያያዘ የሚዲያው ትኩረት ቢቀንስም አሁንም ድጋፉ ሳይቋረጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም ከመላ ሀገሪቱ ባለፉት አራት ወራት ብቻ በልማት ባንክ የተረጋገጠ ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በህዳሴ ግድብ አካውንት ገብቷልእንደ አቶ ኃይሉ ገለጻ፤ ላለፉት አራት ወራት የነበረው የህዝብ ተሳትፎ እጅጉን ከፍ ያለ ሆኖ ተስተውሏል። ለአብነትም የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት ከተጠናቀቀ በኋላ በሀምሌ ወር 119 ነጥብ 9 ሚሊዮን፣ በነሐሴ ወር 152 ሚሊዮን፣ በመስከረም ወር 197 ሚሊዮን እና በጥቅምት ወር 155 ሚሊዮን ብር የተጣራ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ በዋናነት ቦንድ በመሆኑ ህብረተሰቡ የቦንድ ግዥን አጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሠራ ነው ያሉት አቶ ኃይሉ፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያየ መልኩ እያገዙ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም ዲያስፖራው በግድቡ የሚነሱ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ የሚሞክሩ ሥራዎችን በመቃወም ከፍ ያለ ኃላፊነት እየተወጡ መሆኑንም ገልጸዋል።‹‹ድምፃችን ለግድባችን›› በማለት በዓለም የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ከኢትዮጵያውያን ፕሮጀክት ጎን በመሆን ድጋፋቸውን አሳይተዋል። ለዚህም በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት 72 ያህል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክር ቤቶች ያሉ ሲሆን፤ ምክር ቤቶቹም በያሉበት የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች በመሰባሰብ ዕርዳታ የሚያሰባስቡባቸው ናቸው። በዚህ ረገድ ዘንድሮ አስረኛ ዓመቱን አስመልክቶ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ፣ በዲያስፖራ ኤጅንሲና በምክር ቤቶች አማካኝነት በየሀገራቱ እንደሚከበር እና የቦንድ ግዥም እንደሚካሄድ ነው አቶ ኃይሉ የገለጹት።እንደ አቶ ኃይሉ ገለጻ፤ በውጭ ሀገር ያሉ ኢትዮጵያውን ቦንድ ለመግዛት ቢፈልጉም የብር ማስኮብለል ተደርጎ ስለሚቆጠር ምቹ አልነበረም። ነገር ግን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ድጋፋቸውን አጠናክረው እየሄዱ ነው። በዚህ ዓመት ለመምህር ግርማ ወንድሙ ወደ 450 ሺህ ብር በስጦታ መልክ በመላክ የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል። ከገንዘብ ድጋፍ በላይ ለሀገራቸው ጠበቃ በመሆን ለማስረዳትም በተለያዩ ጆርናሎች ላይ በመሳተፍ ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጠቀሜታ በማሳወቅ ላይ ናቸው። በማህበራዊ ሚዲያ ላይም ቀላል የማይባል ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ።ሁሉም ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ጉዳይ ሳያዘናጋቸው ዓይናቸውን ከግድቡ ማንሳት እንደሌለባቸው የሚናገሩት አቶ ኃይሉ፤ በዘንድሮው ዓመት የሙከራ የኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር፣ ለዚህም አጠቃላይ የቴክኒካል ሥራዎች እያለቁ ስለሆነ በቀጣይ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እና አሁን ባለው ሁኔታ የግድቡ አፈጻጸም ወደ 77 በመቶ መድረሱን በመጠቆም፤ እስከ ግድቡ ፍጻሜ ሁሉም በሚችለው ሁሉ ድጋፎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37447
7746893d2feed08746533b7d5c82077c
b0d6e386b61de598910aa5fa085c56f2
“የጁንታውን አባላት በሕግ ተጠያቂ ማድረግ እና ሕዝብንም ከጁንታው መርዘኛ አስተሳሰብ ለማላቀቅ መሥራት ያስፈልጋል”አቶ ውብሸት ሙላት የሕግ ባለሙያ
ሀገር አቀፍ ዜና
ወርቁ ማሩ አዲስ አበባ፡- መንግሥት የወንጀለኛውን ጁንታ አባላት ነጥሎ በማውጣት ተጠያቂ ማድረግ፤ ህዝቡንም ከጁንታው የተሳሳተና መርዘኛ አስተሳሰብ እንዲላቀቅ መሥራት እንዳለበት የሕግ ምሁር አሳሰቡ። እንዲህ አይነት ሥራዎች ህዝብንም ከእንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ለመነጠልና ፓርቲው የሚፈጽማቸውን መጥፎ ነገሮች በሙሉ ለማሳወቅ እንደሚረዳም ጠቁመዋል። የሕግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ ወንጀለኛው ጁንታ በኢትዮጵያ ከፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ምዝበራና ዘረፋ ባሻገር አስተሳሰብን ለማዛነፍ የሄደባቸው መንገዶች በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል። እንዲህ አይነት አስተሳሰቦች ደግሞ ቶሎ ካልታረሙ ትውልዱን በማበላሸት ዘመን ተሻጋሪ ጉዳት እንደሚሚ ያስከትሉ የተናገሩት አቶ ውብሸት፤ ይህ በመሆኑም ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ችግሮች ሲከሰቱ መንግሥታት የፈቱባቸው ተሞክሮዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል። ለአብነትም በጀርመን የናዚ አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች ለማንፃት “ዲ-ናዚፊኬሽን” የሚባል ሕግ በማውጣት ትውልዱን የማንፃት ሥራ መሰራቱንና በኢራቅም ከሳዳም ሁሴን ህልፈት በኋላ ሀገሪቱን ከባዝ ፓርቲ አስተሳሰብ የማንፃት ሥራ መሰራቱን ጠቁመዋል። አቶ ውብሸት እንደገለጹት፤ ወንጀለኛው ጁንታ ለ27 ዓመታት መንግሥትን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ተቋማት ተቆጣጥሮ እና በትግል ወቅት የነበረውን ልምድ ጨምሮ ሀገሪቱን ለማተራመስ ወይም የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ በሰፊው የሰራበት ወቅት ነበር። በዚህ የተነሳ በህዝብ እና በሀገር ላይ በርካታ ጉዳቶች ደርሰዋል። ያንንም መንግሥት ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ተቸግሮ ነበር። ይህ ቡድን ከአራት ኪሎ ከወጣ በኋላ ያደርሳቸው የነበሩ በርካታ ጥፋቶች ነበሩ ያሉት አቶ ውብሸት፤ እነዚያ ጥፋቶች ደግሞ ከጊዜ ወደጊዜ እየጠነከሩ እና እየጨመሩ በመሄዳቸው በመጨረሻ ለውድቀቱ መፋጠን መንስኤ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ከነዚህም ውስጥ በመከላከያ ላይ የሰነዘረው ጥቃት እንደተጠበቀ ሆኖ ምርጫ ማካሄዱ የውድቀቱ ማፋጠኛ እንደነበር አንስተዋል። አቶ ውብሸት እንዳሉት፤ ሕገ መንግሥቱ ሲፀነስ ጀምሮ ዋና አጋፋሪው የነበረው ይህ ቡድን ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም ሕገ መንግሥቱ እስከሚፀድቅበት ጊዜ ድረስ ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ ነው ሲሰራ የነበረው። ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀ በኋላም በትልቁ ያላከበረውና የጣሰው ራሱ ይኸው ጁንታ ነው። መጨረሻ ላይ በዚህ ሕገ መንግሥት አልገዛም ያለውም ይኸው ቡድን ነው። አቶ ውብሸት ስለጁንታው የጥላቻ ጉዞ ሲያስረዱ፣ “ይህ ቡድን ኢትዮጵያን ጠልቶ ትግል ጀመረ፤ ኢትዮጵያን ጠልቶ ሲታገል ኖረ። ሥልጣን ይዞም ኢትዮጵያን እንደጠላ ኖረ። ከአራት ኪሎን ከለቀቀም በኋላ ያንኑ ጥላቻውን የበለጠ አጠናክሮ ቀጠለ። የመጨረሻ የጥላቻ ቦምቡንም መከላከያ ሠራዊት ላይ ወረወረ፤” በማለት ነው። ጁንታው በመጨረሻው ይሄን ሲያደርግ የርስ በርስ ጦርነት እንዲከፈት ጭምር ለማድረግ አስቦ የተሰራው ደባ እንደነበርም ተናግረዋል። ትንሽ የሚይዝ የሞራል፣ የሕግና የሥነ ምግባር መሰረት ከሌለ የሰው ልጅ አውሬ ነው የሚሆነው የሚሉት አቶ ውብሸት፤ ለዚህም በማይካድራ ላይ የፈፀመው ዘግናኝ ተግባር ማሳያ ነው ብለዋል። እነዚህ ሰዎች ደግሞ ከትግል ወቅት ጀምረው ሕግ አለማክበራቸው፣ መሰረታዊ የሆኑ እና ሰው የሚተዳደርባቸው፣ መርሆዎችን አለማክበራቸው እንደዚህ አይነት ወንጀሎችና የጭካኔ ተግባሮችን የስግብግብነት ባህርይዎችን እየተላበሱና እያሳደጉ መሄዳቸው ዋነኛ ባህርያቸውና መገለጫቸው እንዲሆን እንዳደረጋቸውም ጠቅሰዋል። ወልቃይት አካባቢ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ የተገደለው የህዝብ ቁጥር ብቻውን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ብዙ ጊዜ በጅምላ ጭፍጨፋ የሚያስከስስ ነው የሚሉት አቶ ውብሸት፤ የጠፋው እና የተሰወረው ህዝብ ቁጥር በንግግር ብቻ ስንገልፀው ስሜት አይሰጥም እንጂ እጅግ በጣም የጭካኔ ሥራ ነው ብለዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አንዳንድ የውጭ ሃይሎች ይህንን ሕግ የማስከበር ሥራ በተዛባ መንገድ ለዓለም ማበረሰብ ለማሳየት ይሞክራሉ የሚሉት አቶ ውብሸት፣ ይህ ደግሞ ብዙዎቹ ከዚህ ቀደምም የተካኑበት የሴራ ተግባራቸው አካል እንደነበር አንስተዋል። አቶ ውብሸት እንደሚሉት፤ ከግጭት እንጀራቸውን የሚጋግሩ ሃይሎች አሉ። ብዙዎቹ ተቋማት ኮሮጆአቸውን ይዘው የሚዞሩት ግጭት በመፍጠር እንጀራቸውን ለመጋገር ነው። ለምሳሌ፣ ሽምግልና ብሎ ለማስታረቅ፣ መልሶ ለማቋቋም፣ አንዳንዶቹም በሞቱት ሰዎች ስም በርካታ ገንዘብ ለመሰብሰብ ግጭትን ይጠቀማሉ። በዚህ ረገድም የውጭው ጩኸት የሚታወቅ ነው። የጁንታው አባላት የስግብግብነት ምንጭ ደግሞ አንዳንዶቹ የከፋ የድህነት የስልቦና ጫና የነበረባቸው በመሆናቸው ናቸው። በልጅነታቸው በአብዛኛው በረሃ በማሳለፋቸው እና የልጅነት ጊዜያቸውን በዚህ ልክ ማሳለፍ ባለመቻላቸው አሁን ላይ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ገንዘብ ሲገኝ ያዩትን ሁሉየመመኘት አባዜ ውስጥ ገቡ። ያዩት ነገር ሁሉ አጓጓቸው። በዚህም ያዩትን ሁሉ የማድረግ እና ያዩትን ሁሉ የመውሰድ አባዜ ተጠናወታቸው። እነዚህ ሰዎች ለህልውናቸው ሲሉ ህፃናትን ለጦርነት ይማግዳሉ። ለዚህ ደግሞ አደንዛዥ እጽ ሊጠቀሙ ይችላሉ። ከአንድም ሁለት ጊዜ የተያዘው በርከት ያለ የአደንዛዥ እጽ ይህንን እንድንጠራጠር የሚያደርግ ነው። ይህ ደግሞ እነዚህ ሰዎች ይሄን ነገር በአንድ በኩል እንደ ንግድ ውስጥ ተሰማርተውበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ለተልዕኮአቸው ማስፈፀሚያነት እየተጠቀሙበት ሊሆን ይችላል። ብዙ የአሸባሪ ድርጅቶች ህፃናትን በሽብር ተግባራት ሲያሰማሩ በዋናነት የሚጠቀሙት በአደንዛዥ እጽ ነው ያሉት አቶ ውብሸት፣ የጁንታው አባላትም ይህን ተጠቅመው እነዚ ህን ህፃናት ወደጦርነት ውስጥ አስገብተው ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። አቶ ውብሸት እንደገለፁት፤ ይህ ቡድን ከነአልቃይዳ፣ ከነአይኤስ ኤስ እና ከአልሸባብ የበለጠ እንጂ የሚያንስ አይደለም። ስለዚህ ይህ ቡድን ሲሰራ የነበራቸው ነገሮች በሙሉ የሽብር ተግባራት ናቸው። የራሱን አስተሳሰብ በሃይል በሌሎች ላይ ለመጫን እና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በሰዎች ላይ፣ በመሰረተ ልማቶች ላይ፣ በመንግሥት ተቋማት ላይ ትልቅ ጉዳት ሲያደርስ ነበር።ይህንን የሚጠቀመው ደግሞ ፕሮፓጋዳዎችን በመንዛት ነው። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ሚዲያዎች ያስፈልጋሉ። ስለዚህ ይህንን ድርጅት አሸባሪ ለማለት ምንም ያልተሟላ መስፈርት የለም። በመሆኑም ቡድኑን በአሸባሪነት እንዲፈረጅ በማድረግ ህብረተሰቡንም ከዚህ አስተሳሰብ ማንፃት እንደሚገባ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37446
4ac721622392518ff82698dd093297c0
02b3db0ba6df04dfd0184ae9e7a9b07b
ወንጀለኞች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፖሊስን እየተገዳደሩ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ክፍለዮሐንስ አንበርብርአዲስ አበባ፡- ወንጀለኞች የተወሳሰበ እና ዘመናዊ ቴክሎጂዎችን በመጠቀም ፖሊስን እየተገዳደሩ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ፖሊስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ቀድሞ መታጠቅና ወንጀልን ቀድሞ መከላከል ላይ ማተኮር አለበት በሚል ታቅዶ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿልየፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት አቶ መስፍን አበበ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ በዓለምም ሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂን ተገን አድርገው በርካታ ወንጀሎች እየተፈፀሙ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ይህም የፖሊስን ሥራ ፈታኝ እና በእጅጉ ጥንቃቄ በታከለበት ሁኔታ እንደሚሠራ እያስገደደ መሆኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመታጠቅ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም አሁንም ያለው በጣም ኋላቋር ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን፤ ‹‹ወንጀለኞች ቴክኖሎጂ በመታጠቅ በንፅፅር ይቀድማሉ። በሳይበር እና በሶሻል ሚዲያ የሚፈፀም ወንጀልም እየረቀቀ ነው። ለአብነት በቴሌ ላይ እየተሰሩ ያሉ ወንጀሎችን በሚሊዮኖች እና በቢሊዮኖች ኪሳራ አደረሱ ሲባል ይሰማል። ይህን ከወንጀለኞች ሰምተን እንጂ ቀድመን አውቀን የማስቀረት አቅም የለንም›› ብለዋል። በመሆኑም እንደ ፖሊስ ቴክኖሎጂን ቀድሞ መታጠቅና ወንጀልን ቀድሞ መከላከል አለብን በሚል ታቅዶ እየተሠራ ነው ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራል መስፍን፤ ወንጀል ቢፈፀም እንኳን በፍጥነት ማወቅ አለብን ብለዋል። በቀጣይም በቴክኖሎጂ የትምህርት ክፍል የቴክኖሎጂ ፖሊሲንግ የመከፈት ውጥን ያለ ሲሆን በዚህም ምርምር ማድረግ፣ ባለሙያ የማፍራት እና ቴክኖሎጂን የመታጠቅ አስፈላጊነት ታምኖበት እየተሠራ ነው ብለዋል። እንደ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን ገለፃ፤ ‹‹መጪው ጊዜ የቴክኖሎጂ ዘመን ነው። እንደባለፈው ዘመን በጥንት የፖሊስ አሠራር መቀጠል አያዋጣም። አሁን የምንከተለው ዕድገት አገርን ወደ ኢንዱስትሪ የማሸጋገር ወቅት በመሆኑ ዘመናዊ ቴክሎጂን የመታጠቅ ሁኔታ ግድ እየሆነ ነው። በመሆኑም የፖሊስ አሠራር ይህን መከተል አለበት። አገር አዘምኖ ፖሊስን ኋላቀር አድርጎ መጓዝ አይቻልም›› ብለዋል። ዘመናዊ ከተሞች በተሠሩ ቁጥር ዘመናዊ የፖሊስ ሥራ መታከል አለበት ያሉት ኮሚሽነሩ፤ እጅግ የረቀቁ የዘመኑን የፖሊስ ቴክኖሎጂ በሁሉም ቦታ ማግኘት ተገቢ መሆኑ ታምኖበታል። ይህን የመታጠቅ፣ የመጠቀም ብሎም በቴክኖሎጂ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ቀድሞ አውቆ ማስቀረትን ታሳቢ በማድረግ መሥራት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።ከተቋሙ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፤ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአገሪቱ ዘመናዊ ፖሊስ ማደራጀት ከተጀመረ አራት ዓመት በኋላ ከ1939 ዓ.ም የተቋቋመ አንጋፋ ተቋም ሲሆን በእውቀት እና በክህሎት የበቃ ሠራዊትና ተልዕኮውን በአግባቡ የሚወጣ የፖሊስ አመራር ማሟላት ዋንኛ ዓላማው ነው። ይህ ተቋም ለ34 ዓመታት በ42 ዙር ለአገር ትልቅ ውለታ ያበረከቱና በማበርከት ላይ ያሉ የአገር ባለውለታና አይረሴ የፖሊስ ዕጩ መኮንኖችን ማሰልጠኑም ይታወቃል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37448
4801fc349ef10630f9b5f16963b2b5f5
7c84ac503336f93af8e8b10eea9d4592
አፍሪካውያን በዶፒንግ ስጋት ከዓለም ቀዳሚ ናቸው
ስፖርት
ጎረቤታሞቹ የምስራቅ አፍሪካ የረጅም ርቀት ፈርጦች ኬንያና ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ያላቸውን መልካም ስም ያህል በስፖርቱ ትልቅ አደጋ እያንዣበበባቸው ይገኛል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአትሌቲክሱ አበረታች መድሃኒት ወይም ንጥረ ነገሮች ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ ሩሲያንን የመሳሰሉ ታላላቅ አገራት ከታላላቅ ውድድሮች እስከመታገድ ደርሰዋል። እነዚህ አገራት አትሌቶቻቸው በብዛት አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆነው ከመገኘታቸው ጋር ተያይዞ በመንግስት ጭምር ይደገፋሉ በሚል ከውድድሮች መታገዳቸው ይታወቃል። የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ እነ ሩሲያን በቀጣበት ወቅት ኢትዮጵያና ኬንያ አደጋው በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሰጋቸው በማሳወቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክረሃሳብ ሰጥቷቸው ነበር። ሁለቱ አገራት በተለይም ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥታ በመስራት አበረታች ውጤት ማስመዝገቧም በኤጀንሲው ጭምር ተመስክሮላታል። ያም ሆኖ ስጋቱ ሙሉ ለሙሉ ተቀርፏል ለማለት አይቻልም። ባለፈው ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ኢትዮጵያና ኬንያን በአበረታች መድሃኒት(ዶፒንግ) ምክንያት ስጋት ካለባቸው አገራት ቀዳሚውን ደረጃ እንደሚይዙ ማሳወቁ ይታወሳል። ዘንድሮም ሁለቱ አገራት በአበረታች መድሃኒት ስጋት ቁንጮውን ደረጃ መያዛቸው እንደማይቀር እየወጡ ያሉ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ለዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ አምስት የአፍሪካ አገራት አትሌቶች አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆነው መገኘታቸው ማሳያ ተደርጓል። ቤላሩስና ዩክሬን ሁለቱን የአፍሪካ አገራት ተከትሎ ስማቸው ከቁንጮዎቹ ተርታ ተፅፏል። የአስራ ስምንት ዓመቷ ኬንያዊት አትሌት አንጌላ ሙንጉቲ ከቀናት በፊት አበረታች መድሃኒት ተጠቅማ በመገኘቷ እገዳ ተጥሎባታል። በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የስምንት መቶ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነችው ይህች አትሌት በዚህ ወንጀል የተያዘች አርባ አራተኛዋ ኬንያዊት አትሌት ሆናለች። አትሌቷ ባለፈው ዓመት አርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የወጣቶች ኦሊምፒክም በስምንት መቶ ሜትር አገሯን ወክላ መወዳደር ችላለች። የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒት አዋጅ የትኛውም አትሌት በውስጡ ለተገኘ አበረቻች ንጥረ ነገር ሃላፊነቱን ይወሳዳል። ይህችም አትሌት ኖራንድሮስቴሮን የተባለ አበረታች ንጥረነገር ተጠቅማ መገኘቷ ተረጋግጣል። ሙንጉቲ በስምንት መቶ ሜትር 2፡06፡21 የሆነ የራሷ ፈጣን ሰዓት ያላት ሲሆን ባለፈው ዓመት በኬንያ ከሃያ ዓመት ቻምፒዮና ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች። ፊሊፕ ሳንጋ ኪሙታይ የተባለው የሰላሳ ስድስት ዓመት ኬንያዊ አትሌት ቴስቴስትሮን የተባለ አበረታች ንጥረነገር ተጠቅሞ የተገኘ አርባ ሦስተኛው ኬንያዊ አትሌት ነው። የዚህ አትሌት ምርመራ በሂደት ላይ ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ከስፖርቱ ለአራት ዓመታት ሊታገድ እንደሚችል ታውቋል። ኪሙታይ በማራቶን 2፡06፡07 ሰዓት ያለው ሲሆን እኤአ 2011 ላይ በፍራንክፈርት ማራቶን ያስመዘገበው ይህ ሰዓት በውድድር ዓመቱ አስራ ሦስተኛው ፈጣን አትሌት አድርጎት ነበር። ይህ አትሌት ባለፈው ዓመት በጎልድ ኮስት ማራቶን አምስተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ 2፡11፡44 ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል። በሆንግኮንግ ማራቶንም አስረኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡15፡31 ሰዓት ተመዝግቦለታል። በዚህ ወር በአበረታች መድሃኒት ተጠቃሚነት ቅጣት የተላለፈበት ወይንም የተገኘበት አርባ ሁለተኛው ኬንያዊ አትሌት ቪንሰንት ኪፕሴጊች ነው። ይህ የሰላሳ ዓመት አትሌት ቀደም ሲል የተጠቀሰው ኬንያዊ አትሌት ኪሙታይ በጎልድ ኮስት ማራቶን አምስተኛ ሲያጠናቅቅ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል። 2፡09፡59 የሆነ የራሱ ፈጣን ሰዓትም አለው። ሚያዝያ ወር ላይም በቬና ማራቶን ሰባተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡10፡02 አስመዝግቧል። በተመሳሳይ ከዓመት በፊት በሆኖሉሉ ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ጨርሷል። ኢትዮጵውያን አትሌቶች በተለይም በግል ውድድሮች ብቻ የሚታወቁት አልፎ አልፎ በአበረታች መድሃኒት ሲቀጡ ይታያል። ይሁን እንጂ አገርን ወክለው በሚወዳደሩ አትሌቶች ይህ ቅሌት አይታይም ማለት ይቻላል። ባለፈው ክረምት በሞሮኮ ራባት በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን ወክሎ በአስር ሺ ሜትር ወርቅ ማጥለቅ የቻለው ብርሃኑ ፀጉ ኢፒኦ የተባለ ንጥረ ነገር ተገኝቶበት ላልተወሰነ ጊዜ ከስፖርቱ ታግዷል። ይህ የሃያ ዓመት አትሌት ባለፈው ወር በኮፐንሃገን ግማሽ ማራቶን ላይ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ብርሃኑ ሔንግሎ በተካሄደው የዓለም ቻምፒዮና የኢትዮጵያውያን ማጣሪያ ውድድር ላይ 10ሺ ሜትሩን 27፡00፡73 በሆነ ሰዓት ማጠናቀቅ ችሏል። ብርሃኑ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ኤርትራዊው አሮን ክፍሌና ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ጀማል ይመር ተከትለውት መግባታቸው ይታወሳል። ብርሃኑ የወርቅ ሜዳሊያውን ተነጥቆ ለኤርትራዊው አትሌት፣ የብር ሜዳሊያው ደግሞ ለጀማል ይመር የሚሰጥ ሲሆን አራተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ኬንያዊው ኤድዊን ሦይ የነሐስ ሜዳሊያ ሊያገኝ እንደሚችል መረጃዎች እየወጡ ነው። በአዲስ አበባ አበረታች መድሃኒቶች በስቴድየም አካባቢ ካለ ሃኪም ማዘዣ ጭምር እንደሚሸጡ የእንግሊዝ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ተከትሎ የዓለም አትሌቲክስ ኢትዮጵያን ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ፅሕፈት ቤትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቶች የተለያዩ ትምህርቶችን እየሰጡ ይገኛሉ። በቅርብ ወራት አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆኖ በመገኘት ስማቸው ከተዘረዘሩ አፍሪካውያን መካከል ሞሮኳዊው ሙስጠፋ ኤል አዚዝ አንዱ ነው። ይህ አትሌት ለአራት ዓመታት ከስፖርቱ እንዲርቅ ቅጣት የተጣለበት ሲሆን 2014 የአፍሪካ ቻምፒዮና ላይ በአስር ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ በማጥለቁ ይታወቃል። ይህ የሰላሳ ሦስት ዓመት አትሌት ባለፈው ሰኔ ክሮሽያ ውስጥ በተካሄደ የጎዳና ላይ ውድድር አበረታች ንጥረነገር ተጠቅሞ በመገኘቱ እገዳው እንደተላለፈበት ተነግሯል። ሞሮኮ በአበረታች መድሃኒት አደጋ ውስጥ ከሚገኙ አገራት መካከል ትጠቀሳለች። ይሁን እንጂ በዚህ አደጋ እጅግ ችግር ውስጥ ካሉ አገራት ተርታ በ2017 የወጣች ቢሆንም አሁን ተመልሳ ገብታበታለች።አዲስ ዘመን ጥቅምት 17/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=21537
93fccab33835ddd6e4c317ef64051b89
e58e7e93b89ddd0aeab323858e7de141
የወታደሩ ህይወት – ከመጋረጃው ጀርባ
ሀገር አቀፍ ዜና
ጌትነት ተስፋማርያምየሰራዊቱ አኗኗር ከግንባር መልስ በተለይም በእረፍት ሰዓት ላይ አዝናኝ ገጽታ አለው። አንዳንዶች ቢጫ ጀሪካኖችን በመጉረድ የቡና ማቅረቢያ ረከቦት ሲያዘጋጁ ሌሎች ደግሞ የውሃ ማሸጊያ ፕላስቲኮችን በመቁረጥ ቡና እና ሻይ መጠጫዎችን ያዘጋጃሉ።በየአካባቢው የተገኘው ቡና ተቆልቶ በተከፈተ ጣሳ ላይ ሊወቀጥም ይችላል። ምክንያቱም ጁንታው ቡድን የሰራዊቱን ንብረት ዘርፎ ሲሄድ ያልሰባበረው እና ያላወደመው አይነት እቃ የለም ማለት በሚያስደፍር ሁናቴ በየማዘዣ ጣቢያዎቹ ከኤሌክትሪክ እቃ አንስቶ እስከ ቢሮ መሳሪያዎች ድረስ የነበሩ ንብረቶች ተበላሽተዋል፤ አሊያም ጠፍተዋል።በሚያሳዝን ሁናቴ የሰራዊት አባላት በገንዘባቸው የገዟቸው አነስተኛ ቡና እና ሻይ ማፍያዎች እንኳን በአካባቢው እንደሌሉ ከጁንታው ጥቃት በኋላ አካባቢውን የተቆጣጠሩ የሰራዊት አባላት ሲናገሩ ይደመጣል።የሰባተኛ ወጋገን ሜካናይዝድ ክፍለጦር አባል የሆነችው ወታደር እታገኝ ሞላ፣ ሰራዊቱ በእረፍት ሰዓቱ የሚያሳልፍባቸው የካምፕ ውስጥ ካፌዎችና ሬስቶራንቶች በመውደማቸው ጓደኞቿ ድብርት (ድበታ) እንዳይገባቸው የበኩሏን ጥረት እንደምታደርግ ነገረችን።ለቀረጻ ሙያው ልዩ ፍቅር ያላት እና በካሜራ ቀረጻ ሙያ ለአንድ ዓመት በሰራዊቱ ያገለገለችው እንስት፤ በህግ ማስከበር ዘመቻ ደግሞ በተለያዩ ግንባሮች ተሰልፋ ተተኳሾችን እና መሳሪያዎችን በማቀበል በኦርዲናንስ ሙያ አገልግላለች።ከህግ ማስከበሩ ዘመቻ መልስ በሚኖራት የእረፍት ጊዜ ደግሞ፣ ሰራዊቱ አረፍ በሚልባቸው አካባቢዎች ሻይ እና ቡና በማፍላት ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ታደርጋለች። በአካባቢዋ የምታገኛቸውን ምግብ ማዘጋጃ ቁሶች በማሰባሰብ አምባሻ በመጋገርም ተወዳጅ ባለሙያ መሆኗን አስመስክራለች።በተለይ ኮቾሮ ብስኩት በሚበላባቸው አብዛኛው የግንባር ቦታዎች ላይ፣ ስቃጥላ የተሰኘውን የታሸገ የሰራዊቱ ምግብ በልዩ ሁኔታ በማብሰል በፍቃደኝነት ለሰራዊት አባላት ታቀርባለች። “ይህን ማድረጌ ሰራዊቱ በእረፍት ጊዜው ድብርት ውስጥ እንዳይገባ እና ዘመቻውን ዓላማ እንዳይዘነጋ በማሰቤ ነው” የምትለው ወታደር እታገኝ፤ በማንኛውም ሙያ ላይ በመተጋገዝ ለመስራት መምረጧን ነግራናለች።ከግዳጅ መልስ በሚኖረው ቆይታ የእታገኝ ቡና እየተፈላ ስለውሏቸው እና ስለጓዶቻቸው ጀግንነት እየተወራ ሳቅ እና ጨዋታው ይደራል። ከተለያዩ ቦታዎች የመጡትና የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩት የሰራዊት አባላትም አንድነታቸውን በሚያሳይ ሁኔታ የተጋገረውን አምባሻም ሆነ የተፈላውን ቡና አንተ ትብስ አንቺ ትብስ ተባብለው በጋራ በመቋደስ ቀናቸውን በደስታ ያሳልፋሉ።ሃምሳ አለቃ ሄኖክ ከተማ፣ እንደ ወታደር እታገኝ ሁሉ ሰራዊቱ አረፍ በሚልባቸው ቦታዎች አምባሻ መጋገሩን እና ቡና ማፍላቱ የሚያዘወትር የአውራምባ ማህበረሰብ የስራ ባህልን የተላበሰ ወታደር መሆኑን በርካቶች ይመሰክራሉ። እሱም ቢሆን፣ በልጅነቱ ቤት ውስጥ እንጀራም ሆነ ሌሎች ስራዎችን በመከወን ወላጆቹን ያግዝ እንደነበር ነው የነገረን። ያ የልጅነት ልምዱ ደግሞ ሰራዊቱ ውስጥም እንዳገዘውና በእረፍት ጊዜው የተለያዩ ደረቅ ምግቦችን እያዘጋጀ ለጓደኞቹ ለማቅረብ እንዳላስቸገረው ገልጾልናል።ሽሬ ከተማ ላይ የማረጋጋት ስራ ከማከናወን እና ከእጀባ ስራው በተጨማሪነት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቡና እና ሻይ በማፍላት መረጃ እየተለዋወጠ አረፍ ለማለት ይሞክራል። ዱቄት በተገኘ ወቅትም እርሱ ለማቡካት ሲነሳ ጓደኞቹ የልብስ እጀታቸውን ሰብስበው በጉልበታቸው ተንበርክከው ያግዙታል። እርሱ ደግሞ እንጨት እንድዶ በምጣድ አምባሻውን ይጋግራል። ከህዝብ የተገኘው የሰንጋ አቅርቦትም ካለ በጋራ ታርዶ ለሰራዊቱ ይከፋፈላል። በዚህ ሂደት ታዲያ ሁሉም የሚችለውን ለማድረግ ግን ወደኋላ አይልም።እንደ ሃምሳ አለቃ ሄኖክ ከሆነ፤ በምግብ ዝግጅቱ ላይም ሆነ በማንኛውም ስራ ላይ ያለው የሰራዊቱ ህብረት ይበል የሚያሰኝ ነው። አንድም ቀን ጊዜውን በሰላም እና በፍቅር እያሳለፈ በየቦታው ሆኖ ሰራዊቱ ያበሰለውን ምግብ በጋራ ይመገባል፤ በጋራ እየተጫወተ የእረፍት ጊዜውን ያሳልፋል እንጂ፤ ጸብና ክርክርን አያውቁም። እናም ይህ ህብረት ብዙዎችን የሚስብ በመሆኑ ሊጠናከር የሚገባው እሴት ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37458
919aacefcdae6a821103e0c79bbd2117
dddd8d7435829f393f144bd4f2a4d7db
በመጪዎቹ 10 ዓመታት የነፍስ ወከፍ ገቢን ከ2 ሺህ ዶላር በላይ ለማድረስ ታቅዷል
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በመጪዎቹ አስር ዓመታት የነፍስ ወከፍ ገቢን ከሁለት ሺህ ዶላር በላይ ለማድረስ መታቀዱን የፕላን ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ መሪ እቅዱን በተመለከተ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ጋር ምክክር አድርጓል።የፕላንና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ነመራ ገበየሁ የ10 ዓመቱ እቅድ የጋራ እቅድ እንደመሆኑ መጠን የሚዲያ ባለሙያዎች መሳተፋቸው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።በልማት እቅዱ ላይ ከ12 በላይ የመነሻ ጥናቶች፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት፣ የሙያ ማኅበራት፣ ገለልተኛ ባለሙያዎች እና የመንግሥት ተቋማት ተሳትፎ እንደነበራቸው የተጠቆመ ሲሆን፣ የሌሎች ሀገራት ልምድ ተወስዶ ኮሚሽኑ ምን እና እንዴት እንደሚሠራ የመነሻ ሃሳብ ቀርቦ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መቅረቡንም ዶክተር ነመራ አስታውሰዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም እያንዳንዱ አስፈጻሚ ተቋም የራሱን እቅድ እንዲያዘጋጅ እንደጠቆሙ ገልጸዋል።በልማት እቅዱ መሠረት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከ2013 እስከ 2022 ባለው ጊዜ በአማካይ 10 በመቶ እንደሚያድግ አመልክተዋል።በዚሁ የልማት እቅድ በ10 ዓመት የነፍስ ወከፍ ገቢ በአማካይ በ8 በመቶ እንደሚያድግ፣ በ2022 የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 2 ሺህ 201 የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ የታቀደ ሲሆን እንዲሁም የድህነት ምጣኔውንም ከግማሽ በላይ ለመቀነስ እቅድ አለ ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ።በተጨማሪም ሀገራዊ የከተማ ሥራ አጥነት ምጣኔ በ2012 ከነበረበት 18 ነጥብ 7 በመቶ በ2022 ወደ 9 በመቶ ለመቀነስ እቅድ ተይዟልም ነው ያሉት።በልማት እቅዱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የመጠጥ ውሃ፣ የጤና አገልግሎት እና ትምህርትም ዋና ዋና አቅጣጫዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።በጤና እቅዱ መሠረት አማካይ የመኖር እድሜ ጣሪያን በ2012 ከደረሰበት 65 ነጥብ 5 በመቶ ዓመት በ2022 ወደ 68 በመቶ ከፍ የማድረግ ግብ መጣሉም ተመላክቷል ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37460
f07fe57e10eab8ac3b6924d965efe63c
c4fc27a94a3fe24850ed23b3927e7d03
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በድል የደመቁበት ሳምንት
ስፖርት
 በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት በተካሄዱ በርካታ ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች እንደተለመደው የድል ባለቤቶች ሆነዋል። በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የወርቅ ደረጃ በተሰጠው የፍራንክፈርት ማራቶን ፍቅሬ ተፈራ አሸናፊ ሆኗል። አትሌቱ የበላይነቱን የያዘው 2:07:08 በሆነ ሰዓት ሲሆን፤ በሁለት ሰከንዶች የዘገየው ዳዊት ወልዴ ደግሞ ሁለተኛ ሆኗል። ለባህሬን የሚሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አወቀ ይመር በሦስተኛነት ማጠናቀቅ ችሏል። በሴቶች በኩልም የቦታው ክብረወሰን በኬንያዊቷ አትሌት ተሻሽሏል፤ ቫለሪ አያቢ ያጠናቀቀችበት ይህ 2:19:10 የሆነ ሰዓት በዓለም የምንጊዜም 12ኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ መገርቱ ከበደ እና መስከረም አሰፋ ደግሞ በጠባብ ደቂቃዎች ልዩነት ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል። ቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን የወርቅ ደረጃ ባለው በዚህ ውድድርም ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸናፊዎች ሆነዋል። በዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና በ3ሺ ሜትር የክብረወሰን ባለቤቱ የሆነው ዮሚፍ ቀጄልቻ 59:05 በሆነ ሰዓት የመጨረሻዋን መስመር አቋርጧል። ዮሚፍ በቅርቡ በተጠናቀቀው የዶሃው የዓለም ቻምፒዮና በ10ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በሁለት ሰከንድ የዘገየው ኬንያዊው በናርድ ኔጌኖ ሁለተኛ ሲሆን፤ ጀማል ይመር ሶስተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡ በሴቶች በኩል አሸናፊዋ አትሌት ሰምበሬ ተፈሪ 1:05:32 የሆነ ሰዓት ስታስመዘግብ ሰዓቷ የኢትዮጵያ ክብረወሰን ሆኗል፡፡ በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና የ10ሺና 1500 ሜትር ቻምፒዮን የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፋን ሃሰን በ21 ሰኮንዶች ዘግይታ  በመግባት ሁለተኛ ሁናለች።ኬንያዊቷ ጆዋን ቼሊሞ ደግሞ እነርሱን በመከተል በሶስተኝነት ያጠናቀቀች አትሌት ናት። ስሎቫንያ ማራቶን በዚህ ማራቶን ከልክሌ ገዛኸኝ ኬንያዊያኑን አትሌቶች በማስከተል አሸናፊ ሆኗል። አትሌቱ የገባበት ሰዓት 2:07:29 ሲሆን፤ አንቶኒ ኪፕላጋት ማርቲም እና ቪንሰንት ሮኖ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል። በሴቶች መካከል በተከናወነው ውድድርም ኬንያዊቷ ቦርነስ ቺፕኪሩይ ኪቱር 2:21:26 በሆነ ሰዓት የቦታውን ክብረወሰን አሻሽላለች። በዚህ ውድድር አምስት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአራተኛ እስከ አስረኛ ባሉት ደረጃዎች ውድድራቸውን ጨርሰዋል። ሃዋይ ማራቶን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የነሃስ ደረጃ በተሰጠው በዚህ ውድድር ሌንጮ አንበሳ፣ ሄነሪ ኪፕሮፕ እና አንድሬው ኪሚታይ እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡ በሴቶች በኩልም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዋቄ መቃ ሁለት ኬንያዊያን አትሌቶች ተከትላ በመግባት በሶስተኛነት ውድድሩን ፈፅማለች፡፡ ቻንግሻ ኢንተርናሽናል ማራቶን የነሃስ ደረጃ ባለውና በብርዳማ የአየር ሁኔታ በተካሄደው በዚህ ውድድር አብዲ ከበደ፤ በቦታው የተያዘውን ክብረወሰን በ50 ሰከንድ በማሻሻል 2:10:23 በሆነ ሰዓት ገብቷል። ኬንያዊው ዴቪድ ኪፕሮኖ እና ኢትዮጵያዊው ወርቅነህ ተስፋም ከቀደመው ክብረወሰን በፈጠነ ሰዓት ውድድራቸውን አጠናቀዋል። ማርሴል 20 ኪሎ ሜትር በፈረንሳይ ማርሴል ሃያ ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያዊው ኦሊካ አዱኛ አሸናፊ ሆኗል፡ ፡ ከአስር ዓመታት ወዲህም በውድድሩ በተከታታይ ሁለት ዓመታት ማሸነፍ የቻለ አትሌት ሆኗል፡፡ ኦሊካ ውድድሩን በ1:01:10, 41 ሲፈፅም ኬንያዊው ኪፕሮኖ ሜንጆ 1:01:50 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ፣ ኮሪር ኪፕየጎን በ1:02:13 ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡ ሰንበሬ ተፈሪ የኢትዮጵያን የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በ1:05:32 ሰዓት አስመዝግባለች፣አዲስ ዘመን ጥቅምት 18/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=21580
0de89358dd39c5f4ca43743a218dae7b
9d564045b3a7badbc72d112f83fd0480
‘‘ለአፍሪካ ዋንጫ ጠንካራ ቡድን መፍጠር እንችላለን’’ – ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ
ስፖርት
ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት መስራት ከጀመሩ ከ 1 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሲሾማቸው የአራት ዓመት ኮንትራት በመስጠት ነበር። አሰልጣኙ ብሄራዊ ቡድኑን ለ2020 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ለማሳለፍ፤ እኤአ ለ2019 የግብጽ የአፍሪካ ዋንጫ ብሄራዊ ቡድኑን ለማሳለፍ ቃል በመግባት ነበር ኃላፊነታቸውን የተረከቡት። አሰልጣኙ ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ጉዟቸው በርካታ ጨዋታዎችን አድርገዋል። ፌዴሬሽኑ የብሄራዊ ቡድኑን ውጤት ግምገማ እስካሁን ይፋ ባያደርግም የአሰልጣኙ ጉዞ አመርቂ እንዳልሆነ ይነሳል። አሰልጣኙ ከፌዴሬሽኑ ጋር ውል ሲያስሩ ከገቡት ቃል መካከል አንዱ የሆነው ‹‹ኢትዮጵያን በቻን ተሳታፊ ማድረግ›› የሚለው ነው። ይህ የቻን ዋንጫ ተስፋ ከሳምንት በፊት በሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን ተደናቅፏል። በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚዘጋጀው 2020 ቻን ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን በአጠቃላይ ውጤት 2 ለ1 ተሸንፎ ከተሳትፎ ወጥቷል። አሰልጣኙ ብሄራዊ ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ የማብቃት ቃልም አልተፈፀመም። አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ስለ ብሄራዊ ቡድኑ አቋም ፣የቻን ማጣሪያ ጨዋታን፣ የብሄራዊ ቡድኑን ቀጣይ አቅጣጫና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከትናንት በስቲያ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የዋልያዎቹና አሰልጣኙ ጉዞ አሰልጣኝ አብረሃም ከዋልያዎቹ ጋር በአሰልጣኝነት በቆዩባቸው ጊዜያት ቡድኑ ከውጤት አንጻር ሲመዘን ደስተኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ነገር ግን ውጤቶች በተናጥል የቡድን መሻሻል አይጠቁሙም ብለዋል ።‹‹በግሌ ደስተኛ የምሆንባቸው ጉዳዮች አሉ። በተለይ ብሄራዊ ቡድኑ በወጣቶች እየተገነባ መሆኑና ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ማሳየቱ ስሜት ይሰጠኛል። በዚሁ የምንቀጥል ከሆነ በመጪው የአፍሪካ ዋንጫ ጥሩና ጠንካራ ብሄራዊ ቡድን መፍጠር እንችላለን›› የሚል ተስፋ በቡድኑ ማደሩ እንደሚያስደስታቸው አስረድተዋል። የቡድኑ ጥንካሬን ሲመዘን ጠንካራና የተረጋጋ ሊግ በሌለበት ጠንካራ ብሄራዊ ቡድን መገንባት ከባድ መሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኙ ይህን ችግር ለመቅረፍ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ለተጫዋቾች ክፍተቶችን ለመድፈን ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ ከሀገር ውጪ ባደረጉት ጨዋታዎች የተሻለ የስነልቦና ዝግጅቶች ማሳየታቸውን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ከጉዳት ጋር በተያያዘ ያጣቸው ተጫዋቾች እንዳሉ አንስተዋል። ነገር ግን አንድ ቡድን ተቀየረ የሚባለው ከግማሽ በላይ ተጫዋቾች ሲለወጡ ነው ይላሉ። አሁን ላይ ያለው ቡድን 90 በመቶ ያህሉ ነባር ተጫዋቾች ናቸው። ስለዚህ አሁንም በሂደት የተወሰኑ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን በመጨመር ጠንካራ ቡድን ለመገንባት እንደሚጥሩ አብራርተዋል። የቡድኑ ጨዋታ እንቅስቃሴ ብሄራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ፣ በቻን ውድድር ማጣሪያ፣ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ፣ በወዳጅነት ጨዋታ የነበሩትን እንቅስቃሴዎች ትንተና እንዳልተሰራ ተናግረዋል። አሰልጣኙ ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነት ወስደው መስራት ከጀመሩበት የቻን የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ ጀምሮ ያደረጉትን የጅቡቲውን የደርሶ መልስ ጨዋታ ለመገምገም እንደሞከሩ አብራርተዋል። የሩዋንዳውንም ጨዋታ በቅርቡ ከቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በመሆን በጋራ እንደሚገመግሙ ጠቁመዋል። ከዘንድሮ ጀምሮ የአሰልጣኞች ቡድን አባላትና ሌሎች እምነት ከሚጣልባቸው ባለሙያዎች ጋር በመሆን የጨዋታ ምስል ትንተና መስራት መጀመራቸውን አንስተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፐርፎርማንስ ትራከር በመጠቀም የእያንዳንዱ የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች የአካል ብቃት መረጃ ከክለቦች ጋር መረጃ በመለዋወጥ ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩም ተገልጿል። በብሄራዊ ቡድንና በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መካከል ያለው ስልጠና መናበብ ካልቻለ ብሄራዊ ቡድኑም ሆነ ሊጉ መረጋጋት እንደማይችል አሰልጣኙ ተናግረዋል። ከሌሴቶ ጋር በነበረው ጨዋታ በሜዳው የተገኘውን ተመልካች ለማስደሰት ከመነጨ ጉጉት ከተፈለገው አጨዋወት ውጪ የመወጣት ሁኔታ እንደነበር የገለፁት አሰልጣኙ፣ በባህር ዳር የነበረውን ጨዋታ እንደማሳያ በማንሳት በ41 አጋጣሚዎች ረጃጅም ኳሶች ወደ ተቃራኒ የሜዳ ክልል በመውሰድ 39 ኳሶች ስኬታማ እንዳልነበሩ አስታውሰዋል። ይህንንም እንዲህ ገልፀውታል ‹‹በሜዳችን ስንጫወት ተጫዋቾች በደጋፊዎቻቸው ስሜት ውስጥ ገብተው ከጨዋታ እቅድ የመወጣት ነገር ይስተዋላል። በተቃራኒው ከሀገር ውጭ በምንወጣበት ወቅት ከተመልካቾች ከጫና ውጭ ሆነን በመጫወት በእቅዳችን መሠረተ ለመጫወት መሞከራችን የተሻለ ብልጫ መውሰድ አስችሎናል››። በቻን ውድድር ማጣሪያ መርሃ ግብሩ በድንገት የወጣ እንደነበር ያስታወሱት አሰልጣኙ ዝግጅታቸው አጭር እንደነበር አብራርተዋል። በመጀመሪያው የጅቡቲ ጨዋታ ከሜዳ ውጪ ቢሆንም የተሻለ ስነልቦና በመያዝ አሸንፈው ወጥተዋል። በመልሱ ጨዋታ ግን በውጤት ቢያሸንፉም በቡድኑ እንቅስቃሴ ደስተኛ እንዳልነበሩ ተናግረዋል። ከዚያ ጨዋታ በመነሳት የነበሩ ችግሮችን ለማረም በተለይም በአካል ብቃት የነበሩብን ክፍተቶች አርመው ለሩዋንዳ ጨዋታ መዘጋጀታቸውን ያስረዳሉ። ከሩዋንዳ ጋር በመቐለ በተደረገው ጨዋታ ከመጀመሪያው የማጣሪያ ጨዋታ በብዙ መልኩ የተሻለ ቡድን እንደነበረና ሙሉ ለሙሉ ጨዋታውን ተቆጣጥሮ መጫወት እንደተቻለ ይናገራሉ። ያም ሆኖ የተጫዋቾች ልምድ ማነስ፤ በመጠነኛ የተከላካዮች ትኩረት ማነስ ማጣሪያውን እንዳያልፉ ማድረጉን አስቀምጠዋል። በቻን ማጣሪያ ወቅት በያዙት የቡድን ስብስብ ላይ የተወሰኑ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች አካተው ለቀጣይ ጨዋታዎች ልምምድ እንደሚጀምሩም ጠቁመዋል። ‹‹በዕቅዳችን መሠረት ዓርብ ለመጀመር ነበር። ነገር ግን በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕና በአሸናፊዎች አሸናፊዎች ዋንጫ የተነሳ ቀኑ ወደ መጪው ሰኞ ሊዘዋወር ችሏል። ዝግጅታችን ሰኞ በመቐለ ከተማ የምንጀመር ይሆናል›› ያሉት አሰልጣኝ አብረሃም ቡድኑ ከፊት ለፊቱ ያሉበት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ጥንቃቄ እንደሚፈልጉ አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 19/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=21680
39b5c63bbb60ed86a19c08ca37f0cb10
67d9cbf431318b0cf377214e82d18597
የቮሊቦል ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተራዘመ
ስፖርት
የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ እንዲራዘም ፌዴሬሽኑ በ20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ውሳኔ አስተላለፈ። የኢትዮጵያ የቮሊቦል ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ባለፈው ቅዳሜ አዲስ አበባ ላይ ሲያካሂድ፤የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽንን ለ4 ዓመት ሲያገለግል የነበረው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የስራ ዘመኑ የካቲት ወር 2012 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ቢሆንም የጀመረውን ስራ ማጠናቀቅ አለበት በሚል እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 መቆየት እንዳለበት ወስኗል። በብሔራዊ የስፖርት ፌዴሬሽኖች የመተዳደሪያ ደንብ መሰረት የፌዴሬሽኖች የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስልጣን ጊዜ እንዳለቀ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መመረጥ እንዳለባቸው ያስቀምጣል። በዚህ መሰረት አሁን ያለው የቮሊቦል ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከአራት ወራት በኋላ የስራ ዘመኑ የሚጠናቀቅ በመሆኑ የስራ አስፈጻሚውን ቆይታ በተመለከተ የጉባኤው ተሳታፊ ሃሳብ እንዲሰጥበት አጀንዳ ቀርቧል። የጠቅላላ ጉባኤው አባላት በጉዳዩ ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ አዲሱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ ለአራት ወራት እንዲራዘም ወስነዋል። የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ከውሳኔው በኋላ በሰጡት አስተያየት፤ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የጀመረውን ስራ መጨረስ እንዲያስችለው በማሰብ ውሳኔ ላይ እንደደረሱ ተናግረዋል። በዚህ መሰረትም በቀጣዩ በጀት ዓመት ምርጫው በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም እንዲካሄድ ያላቸውን ፍላጎት አንጸባርቀዋል። የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ መስፍን አበራ፣ በጠቅላላ ጉባኤው በኩል ውይይት ተደርጎ በአሁኑ ወቅት ሥራ ላይ የሚገኘው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቆይታ ጊዜ ለአራት ወራት እንዲራዘም ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚያከብሩት ገልጸዋል። ያም ሆኖ የጠቅላላ ጉባኤውን ውሳኔ የመቀበልና ያለመቀበል ስልጣን የፌዴሬሽኑ ሳይሆን የስፖርት ኮሚሽን መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ውሳኔ ለስፖርት ኮሚሽን እንደሚቀርብ አመልክተዋል። በጉባኤው ላይ የነበሩት የስፖርት ኮሚሽን ተወካይ በሰጡት አስተያየት፤ የፌዴራል የስፖርት ኮሚሽን የጉባኤውን ውሳኔ የሚያከብር ቢሆንም ደንቡ በሚለው መሰረት ምርጫ መሄድ ያለበት በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም እንደሆነ ገልፀዋል። ያም ቢሆን የስፖርት ኮሚሽኑ አመራር በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ አመልክተዋል ።አዲስ ዘመን ጥቅምት 11/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=21210
266c1d7a7080cfe1c9dcb7223c0c0922
eaf99a3999d4b05513c99c95b8ab7e5e
54 ቋንቋዎች ለማስተማሪያነት ቢውሉም፣ ለመጥፋት የተቃረቡ መኖራቸውም ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ክፍለዮሐንስ አንበርብርአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ 54 ቋንቋዎች ለሥርዓተ ትምህርት ማስተማሪያ የዋሉ ቢሆንም በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እና ለመጥፋት የተቃረቡ ቋንቋዎች መኖራቸውን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ::በሚኒስቴሩ የትርጉም ሥራ ልማት ቡድን መሪ አቶ ዓለማየሁ ጌታቸው በተለይም ለአዲስ ዘመን ዝግጅት ክፍል እንደገለፁት፤ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ለሁሉም ቋንቋዎች እውቅና የሰጠ ቢሆንም የቋንቋ ልማት የሚመራበት የራሱ የሆነ እውቅና አለመኖር፣ ቅደም ተከተል በሥርዓቱ አለመበጀቱና በብቁ ባለሙያዎች ባለመመራቱ ቋንቋዎች በሚገባው ደረጃ ለምተው ለህብረተሰቡ በሚጠበቀው ደረጃ እየደረሱ አይደለም:: በዚህም የተነሳ የተወሰኑ ቋንቋ ተናጋሪዎች ቁጥር እየቀነሰ ሲሆን ለመጥፋት የተቃረቡ እና የጠፉም መኖራቸውን አስረድተዋል::እንደ አቶ ጌታቸው ገለፃ ቀደም ሲል ጋፋትኛ ቋንቋ የጠፋ ሲሆን፣ አሁን ለመጥፋት የተቃረቡ እና አደገኛ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ቋንቋዎች ይገኛሉ:: በአሁኑ ወቅት ሱዳን የሚነገረው የሙርሌ ቋንቋ በኢትዮጵያ ጠፍቷል ብለዋል:: ደቡብ ኦሞ አካባቢ ይግባቡበት የነበረው ኦንጎታ የሚባለው ቋንቋም ከአስር ዓመት በፊት ከስድስት የማይበልጡ ተናጋሪዎች እንደነበሩ አስታውሰው፤ የመጥፋት አደጋ እንደተደቀነበት አሊያም ሳይጠፋም እንዳልቀረ ገልፀዋል:: የወይጦ ቋንቋ የሚባለውም በዚሁ ደረጃ የጠፋ መሆኑን ገልፀዋል:: በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ 80 በላይ ቋንቋዎች እንደሚነገሩ ግንዛቤ መኖሩን የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፤ በሥርዓተ ትምህርት የተካተቱት ግን 54 ብቻ መሆናቸውን ገልፀዋል::እነዚህ ቋንቋዎች በአገሪቱ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካተው ግልጋሎት እየሰጡ ቢሆንም፣ በተፈለገው ደረጃ የትምህርት ጥራት ላይ ለውጥ አለመምጣቱንም አብራርተዋል:: ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቱ ከሚነገሩ ቋንቋዎች አኳያ በበቂ ደረጃ አለመልማቱን ማሳያ መሆኑን አስገንዝበዋል::የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪም በበኩላቸው፤ ልሳነ-ብዙነትን በማበረታታት ሕብረ-ብሔራዊነትን በማጎልበት ቋንቋ ትልቅ ሚና እንዳለውና ለመግባቢያ የሚሆኑ ቋንቋዎች ማዳበር እንደሚገባ ተናግረዋል:: ኢትዮጵያ ከሌላ አገር የተለየ የምልክት ቋንቋ ያላት ሲሆን፤ ይህም በባለሙያዎችና ሳይንቲስቶች በመታገዝ ማደግ አለበት:: አሁን ባለው ሁኔታ በኢትዮጵያ ምን ያክል ቋንቋ በአግባቡ ሥራ ላይ እየዋለ ነው፣ ችግር የተጋረጠባቸው የትኞቹ ናቸው የሚለውን በሚገባ መለየት ይገባል:: የዓደባባይ ቋንቋ አጠቃቀም ጭምር ሕግ እንደሚያስፈልግና ለዚህም መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል::ጀርመን፣ ካናዳ እና አሜሪካ የግዕዝ ኢንስቲትዩትን እንዳላቸው የተናገሩት ፕሮፌሰር ሂሩት፤ የቋንቋው ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ አለመሥራቷን ጠቁመዋል:: የጥንታዊ ቋንቋ ላይ ጥናትና ምርምር ማድረጉም ጠቀሜታው የበዛ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህን ለማስፈፀም ፖሊሲ ብቻውን ጠቃሚ አለመሆኑንና ቴክኒካዊ ሥራዎችን መሰረት በማድረግና ከቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል::ልሳነ-ብዝሃነትን ለማበረታታት ሕብረ-ብሔራዊነትን ለማጎልበት በማሰብ የካቲት 2012 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማልኛ፣ አፋርኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎች በፌዴራል ደረጃ የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ መወሰኑ ይታወሳል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37316
1132e8822fb17604951ba9fb69f6b33e
83df25928c37463b790de0f1eeec3567
የጋዜጠኞች የሌላውን ሆድ ከሚያሻክር ዘገባ መቆጠብ የሚፈለገውን አገራዊ ስዕል ለማምጣት እንደሚያስችል ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- እያንዳንዱ ጋዜጠኛ የሌላውን ሆድ ሊያሻክር የሚችል ዘገባ ላለመሥራት ለራሱ ቃል ከገባ ድምሩ እንደ አገር የሚፈለገውን ትልቁን ስዕል ለማምጣት የሚያስችል መሆኑ ተገለፀ:: ኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከአዲስ አበባና ከክልል ለተውጣጡ የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች የግጭት አዘጋገብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል::በስልጠናው ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የተገኙ ሲሆን፤ ስልጠናው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች ሚዲያ ተቋማት በተውጣጡ ባለሙያዎች ተሰጥቷል ::በስልጠናው ወቅት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ እንደገለፁት፤ የመገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ሁኔታ አውጥቶ ወደ ሰላም በመመለስ ያላቸው ሚና እና ኃይል ከፍተኛ በመሆኑ አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የግጭት አዘጋገብ ዘይቤዎችን ተገንዝቦ መሥራት ያስፈልጋል:: ስልጠናው በዚህ ላይ እንዲያተኩር መደረጉም ጋዜጠኞች በዚሁ አግባብ እንዲሰሩ የሚያስችላቸውን ግንዛቤ ለመፍጠር ነው::የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኒስቴር ደኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ከመገናኛ ብዙሃን የሚሰሙ አስደንጋጭና በሰላም ማስፈን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ዘገባዎች እየተበራከቱ መጥተዋል:: ስለሆነም ህዝብን እኩል ማገልገልና ተገቢ ያልሆኑ አዘጋገቦችን አርሞ ለሀገር ሰላምና ገጽታ ግንባታ የሚውል በጎ መርህ ላይ የተመሰረተ መረጃ አሰጣጥ ሊኖር ይገባል::በስልጠናው ወቅት በቅድመ ግጭት፤ ግጭትና ድህረ ግጭት ላይ መገናኛ ብዙሃን ያላቸው ሚና፣ በዲጂታልና ማህበራዊ ድረ ገጽ የግጭት አዘጋገብ እንዲሁም ሥርዓተ ፆታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ ላይ ያተኮሩ ጥናቶች ቀርበዋል:: የጥናት አቅራቢዎቹ እንደገለፁት ደግሞ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ሕግን የማክበርና የማስፈን ሂደቱ ላይ የጎላ አስተዋፅኦ ነበራቸው:: በጊዜ ሂደት ግን እያደጉ ሄደው መጥፎ አሻራ ሊጥሉ የሚችሉ አንዳንድ መርህ አልባ አዘጋገቦች ተስተውለዋል::በዚህም ከቃላት አጠቃቀም ጀምሮ ህዝብን የማበላለጥ አንድምታ ያላቸው የአዘጋገብ ቅኝቶችን መከተል እና በማህበራዊ ሚዲያ መረጃ ተጽዕኖ ሥር መውደቅ ይታይባቸዋል::የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አዷለም በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ስልጠናው ግቡን የሚመታው ተሳታፊ ጋዜጠኞች ቢያንስ የሌላውን ወገን ሆድ ሊያሻክር የሚችል ነገር በዘገባ ውስጥ ላለመሥራት በተቻለ መጠን እጠነቀቃለሁ ብለው ለራሳቸው ቃል መግባት ሲችሉ ነው::“እያንዳንዱ ጋዜጠኛ የሌላውን ሆድ ሊያሻክር የሚችል ዘገባ ላለመሥራት ለራሱ ቃል ከገባ፤ ድምሩ የምንፈልገውን ትልቁን ስዕል ይሰጠናል” ያሉት አቶ ወንደሰን፤ አሁን የሚታየው ችግርም የብሔር ሚዲያ በመብዛቱ ወይም መኖሩ ሳይሆን “የአንድን ማህበረሰብ ቋንቋ ባህልና ትውፊትን ለማሳደግ ሚዲያ አቋቁመን ስናበቃ ለሌላው ወገን የሚኖር የአመለካከት ብልሹነት በመኖሩ ነው” ብለዋል::የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ በተለይ የቃላት አጠቃቀም ላይ ያሉ ችግሮች ቶሎ ካላስተካከሉ የቅርብ መዘዛቸውና በቀጣይ ትውልድ ላይ የሚፈጥሩት የመራራቅ መንፈስ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ሲሉ ሃሳባቸውን ገልጠዋል:: ዘገባውን ያደረሰን የባለሥልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=37317
981b808fcc8a59659523a8421058c550
f9995c1020992adfac68cd87c5791535
ኢትዮጵያዊያን በድል ያንፀባረቁበት ሳምንት
ስፖርት
ጥቅምት ወር በአትሌቲክሱ ዓለም በተለይም የጎዳና ላይ ሩጫዎች በስፋት የሚካሄዱበት ነው። ባለፈው ሳምንት መጨረሻም በመላው ዓለም ዙሪያ በርካታ የማራቶን ውድድሮች ተካሄደዋል። በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር እውቅና ኖሯቸው ከተካሄዱት ውድድሮች መካከልም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች እንደተለመደው የሳምንቱን መጨረሻ ቀናት በድል አንፀባርቀዋል፡፡ አምስተርዳም ማራቶን በዓለም አቀፉ ማህበር የወርቅ ደረጃ በተሰጠው በዚህ ውድድር በተለይ በሴቶቹ ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው የቦታውን ክብረወሰንም ያስመዘገበችበት ነበር። አትሌቷ 2:19:26 የሆነ ሰዓት ያስመዘገበች ሲሆን ንፋስ አልባው አየር ለውድድሩ ምቹ እንደነበረም ተጠቁሟል። በሰከንዶች የዘገየችው ትዕግስት ግርማ ሁለተኛ ስትሆን 2:19:52 ደግሞ የገባችበት ሰዓት ነው። አዝመራ ገብሩ እና በሱ ሳዶ ደግሞ ሦስተኛ እና አራተኛ በመሆን ውድድራቸውን ፈጽመዋል። በወንዶች መካከል በተካሄደው ውድድር ኬንያዊው ቪንሰንት ኪፕቹምባ ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ፤ ሰለሞን ዲክሲሳ እና በተስፋ ጌታሁን ደግሞ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን የብርና ነሐስ ሜዳሊያ ባለቤቶች ሆነዋል። ዴልሂ ግማሽ ማራቶን በዚህ ውድድርም 1:06:00 በሆነ ሰዓት የገባችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ፀሐይ ገመቹ ናት፡፡ ያለምዘርፍ የኃላው ፀሐይን ተከትላ ሁለተኛ ስትሆን፤ ዘይነባ ይመርም የአገሯን ልጆች ተከትላ በሦስተኝነት አጠናቃለች። በወንዶች በኩል አንዱአምላክ በልሁ አሸናፊ ሲሆን፤ የገባበት 59:10 የሆነ ሰዓት ደግሞ የግሉ ምርጥ ሰዓት ሆኗል። ሰለሞን በሪሁ በሁለተኛነት ሲገባ ኬንያዊው ኪቢዎት ካንዴ በሰከንዶች ልዩነት ሦስተኛ በመሆን ውድድሩን ደምድሟል። ቶሮንቶ ማራቶን እስከ 30ኛው ኪሎ ሜትር በርካታ አትሌቶች አንገት ለአንገት ተናንቀው በሮጡበት በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆነችው ኬንያዊቷ ማግዴልይኔ ማሳይ ናት። በጤና መታውክ ምክንያት ውድድሩን ልታቋርጥ ትችላልች የሚል ስጋት ያሳደረችው ኢትዮጵያዊቷ ብሩክታይት እሸቱ ደግሞ ሌላኛዋን ኬንያዊት ቤትሲ ሴናን በማስከተል ሁለተኛ ሆናለች። በወንዶች ምድብ ኬንያዊው ፊሊሞን ሮኖ ለሦስተኛ ጊዜ አሸናፊ መሆን ችሏል። ኢትዮጵያዊው ለሚ ብርሃኑ እና ኡጋንዳዊው ፍሊክስ ቼሞንገስ ደግሞ እርሱን ተከትለው እጅግ በተቀራረበ ሰዓት የገቡ አትሌቶች ሆነዋል። ሊዝበን ማራቶን በጥሩ የአየር ሁኔታ ታጅቦ በተካሄደው በዚህ ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያዊያን አሸንፈዋል። በሴቶቹ በኩል ሲጫሌ ደላሳ ስታሸንፍ፤ ኬንያዊቷ ሄለን ጄፕኩራጋት እና ኢትዮጵያዊቷ ሱሌ ኡቱራ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነዋል። በወንዶች፤ አንዱዓለም ሽፈራው ኬንያዊያኑን ሳሙኤል ዋንጂኩ እና ስቴፈን ቼምላኒን አስከትሎ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 11/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=21214
805cdf04a2c56a19b5438d206b9e8c69
7b8cab770bbc78efd22446e5e11ca082
በአዲስ አበባ የአማራ ባለሀብቶች የክልሉን ልማት ለማስቀጠልና የፀጥታ መዋቅሩን ለመደገፍ ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በአዲስ አበባ የአማራ ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ልማት ለማስቀጠልና የፀጥታ መዋቅሩን ለመደገፍ ከክልሉ ህዝብና መንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ:: በሀገሪቱ እና በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከአማራ ባለሀብቶች ጋር ምክክር ተደርጓል።የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደዘገበው፤ የጁንታው አጥፊ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ በፈፀመው ክህደት በመንግሥት በኩል በተወሰደው ሕግ የማስከበር ሥራ ይህ የጥፋት ኃይል በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚኒሻና ሌሎችም የፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ተጋድሎ ላይመለስ ተቀብሯል። ይህን ታላቅ ገድልም ትውልድ ሲዘክረው ይኖራል:: ይሄን ተከትሎም በአዲስ አበባ የአማራ ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ልማት ለማስቀጠልና የፀጥታ መዋቅሩን ለመደገፍ ከክልሉ ህዝብና መንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል::መረጃው እንዳመለከተው፤ መድረኩን የመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በሕግ ማስከበር ሂደቱ የነበሩ እውነታዎችን ለባለሀብቶች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል::ሀገር ችግር ውስጥ በሆነችበት ጊዜ መደጋገፍ እና አብሮ መቆም ከአባቶቻችን የወረስነው ነው ብለዋል:: በዚህ ሕግ የማስከበር ሥራ ክልሉ ያለውን ሁሉ አድርጓል፤ በቀጣይ የጀመረውን ሰላምና ልማት ለማስቀል ባለሀብቶች እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በአማራ ህዝብ ላይ ሲደርስ የቆየው አማራን አጥፊና በዳይ አድርጎ በጠላትነት የመፈረጅ የሴራ እሳቤ እና ጥላቻ እውነታው መጋለጡን ጠቅሰዋል:: ወራሪው፣ ተስፋፊውና አሸባሪው የትህነግ አጥፊ ቡድን በመከላከያ፣ በጀግናው የአማራ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ እንዲሁም በአማራ ህዝብ ሽንፈት መከናነቡን ገልፀዋል፤ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ “ቀጣዩ ምዕራፍ በጋራ ቆመን የኛን የቤት ሥራ የምንሰራበት ጊዜ ነው” ብለዋል::የክልሉ መንግሥት ሕግ በማስከበር ሂደቱ የተለያዩ ወጪዎችን ማውጣቱን የጠቀሱት ዶክተር ፋንታ፤ ባለሀብቶች የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብም አለኝታነታቸውን በተግባር አሳይተዋል ብለዋል::በውይይቱ የተሳተፉ ባለሀብቶች በበኩላቸው፣ “ይህን ማድረግ ለኛ ክብር ነው፤ እኛ የምንከበረው የሚከበር ሀገር እና የዘመነ የፀጥታ ኃይል ሲኖር ነው፤ እናም የክልሉ መንግሥት እየሠራቸው ያሉ ሥራወችን ወደፊትም ለማገዝ ዝግጁ ነን” ብለዋል:: በዕለቱም ከ3 መቶ 76 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ቃል የተገባ ሲሆን፤ በእውቀትና በቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግም ሌላው በመድረኩ ቃል ከተገባው ውስጥ ነው::በመጨረሻም፣ “ከ40 ዓመታት በላይ በዘራፊውና የጥፋት ኃይሉ ትህነግ የአማራ ህዝብ መዋቅራዊ በሆነ መልኩ አጥፊና በዳይ በሚል ትርክት ጥቃቶች ሲፈፀሙበት ኖሯል፤ ዛሬ ልጆቹ በከፈሉት ዋጋ ነፃ ወጥቷል፤ ቀጣዩ ዘመን ድሉ ለአማራ ህዝብ ትንሳኤ መሆኑን በመገንዘብም በአብሮነት ቆመን ልንሠራ ይገባል፤” ሲሉ የአዲስ አበባ አማራ ባላሀብቶች ጥሪ አቅርበዋል::“ነፃነታችን አውጀን መሥራት እና ሀገርን መደገፍ በምንችልበት ልክ እኛም ከህዝብና ከመንግሥት ጎን እንቆማለን፤” ሲሉም አረጋግጠዋል:: “ጎጠኝነት የህዝባችን ሥነ ልቦና የማይፈቅደው፣ አባቶቻችን ያላወረሱን እኩይ ተግባር ነው” ያሉት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ ከዚህ በኋላ አብረን በመቆም የሚመጣውን መታገል እንጅ በጎጥ እና በሰፈር በመከፋፈል እንቅፋት መሆን ሊቆም እንደሚገባም አሳስበዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37326
6b28b1db6863d627f5913ce1bbe69b74
139f7c312697c537c794f69dab344020
በመተከል አካባቢ ከአንድ ሺህ በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በመተከል አካባቢ እና ቀጠናውን ለማረጋጋት በተደረገው ሕግን የማስከበር ሥራ 1 ሺህ 1 የሚሆኑ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ጉዳያቸው በሕግ እየታየ መሆኑን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት እንደዘገበው፤ በዞኑ በተፈጠረው የሰዎች ሞት እና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ 284 ፀረ ሰላም ሃይሎች መደምሰሳቸውን ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል። መንግሥት የሰጣቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለፀረ ሰላም ሃይሉ መረጃ በመስጠት የተጠረጠሩ ከክልል እስከ ወረዳ በሚገኙ 66 አመራሮች ላይም እርምጃ መወሰዱን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል::በተጨማሪም፣ ኮማንድ ፖስቱ እያከናወነ ባለው ኦፕሬሽን 50 ሰዎች የተማረኩ ሲሆን፤ 43 የሚሆኑት ደግሞ በመግባባት እጅ ሰጥተዋል። በተደጋጋሚ ግጭቱ እንዳይቆም ህዝባዊ ሃላፊነት ባልተወጡ 32 የፖሊስ አባላትና 35 የፀረ ሽምቅ አባላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ጉዳዩም በሕግ እየታየ ይገኛል ነው የተባለው። ቀጠናውን ለማረጋጋት በሚደረገው ሕግን የማስከበር ሥራ 119 ዘመናዊ የጦር መሣሪያ፣ 108 ኋላ ቀር መሣሪያ በአጠቃላይ 227 የጦር መሣሪያ እና የተለያዩ የወታደር ልብሶችም ተይዘዋል።በዘገባው እንደተመላከተው፤ በቀጠናው በተፈጠረው አለመረጋጋት እስካሁን 22 ሺህ 768 የህብረተሰብ ክፍሎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ለእነዚህ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ እና ወደ ነበሩበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነም ተገልጿል። በመተከል ዞን የተከሰተውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ለመፍታት 2 ሺህ 679 አዲስ የሚኒሻ አባላት በማሰልጠን ከህብረተሰቡ ጋር ቀጠናውን እንዲጠብቁ ተደርጓል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37325