query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
7
297
category
stringclasses
6 values
passage
stringlengths
137
5.93k
link
stringlengths
28
740
29e4a62e56bc0a30b52455f25f77cb6d
7c47f9a75ff3e98196a243494a6afca1
የቢሮ ሕንፃው ያሰጋቸው ሄልሜት አጥልቀው የሚኖሩ ህንዶች
መዝናኛ
መንግሥት ከህዝብ ከሚሰበስበው ግብር የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላቱ ግድ ነው፡፡ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው የመንግሥት የዕለት ተዕለት ሥራ እየሠሩ ደግሞ በአለቆቻቸው ችላ ከተባሉ የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ወይም አመራሩ ምንዝሩን (የበታቹን ሠራተኛ) በማማረር አልያም አለቃው በመደናበር ግዴታውን ያለመወጣቱ ማሳያ ነው፡፡ ሕንፃቸው እያሰጋቸው መሆኑን ለመንግሥትና ለመገናኛ ብዙኃን ተደጋጋሚ አቤቱታ ሲያቀርቡ የነበሩ ህንዳውያን ተሰላችተው ‹‹ለቢሮ ሥራቸው ሄልሜት አጥልቀው መሥራት ጀመሩ፡፡›› ይለናል የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ፡፡ በግሌ የአለቆችን ቸልተኝነት ብንቅም የህንዳውያን ምንዝሮች ሥራን ግን አደንቃለሁ፡፡ እኛ ብንሆን ኖሮ ሕንፃ ለመደርመስና ሕይወት ለማፍሰስ እንሮጥ ነበር፡፡ ህንዳውያኑ ሀገራቸውን ስለሚወዱ መንግሥት ቢሮክራሲ በማብዛት ችላ ቢላቸውም ለሀገራቸው ለመሥራት ግን አልቦዘኑም፤ ሀገራቸውንም ችላ አላሉም፡፡ በህንድ ኡተር ፓራዳሽ ግዛት ባንዳ ከተማ የሚገኙ እነዚህ የመንግሥት ሠራተኞች የሞተር ሳይክል ሄልሜት (የራስ ቅልን ከአደጋ መከላከያ) አጥልቀው የቢሮ ሥራ እየሠሩ በቅርቡ በማኅበራዊ ድረ ገፅ የብዙዎችን ትኩረት ስበው ነበር፡፡ ምናልባት የሕንፃው ጣራ በላያቸው ላይ ሊራገፍ ቢችል ተብሎ መሆኑን የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ አስረድቷል፡፡ በከተማው የኤሌክትሪክ ክፍል ቅጥር ሠራተኞች ትልልቅ የሞተር ሳይክል ሄልሜት ለጭንቅላታቸው አጥልቀው ቢሯቸው ሲሠሩ የሚያሳዩ ፎቶዎችን ማኅበራዊ ትስስር ገፆችና የህንድ ዜና አገልግሎት ተጋርተውታል፡፡ አብዛኛዎቹ ምንጮች የመንግሥት ተቀጣሪዎቹ የሞተር ሳይክሎች ደጋፊ ወይም አቃፊ አይደሉም። ቀስ በቀስ እየተፈረካከሰ ያለው ጣራ ግን እንዳይጎዳቸው ጭንቅላታቸውን ለመከላከል ሊሆን ይችላል፡፡ ከዓመታት በፊት ለሪፖርተሮች የጽህፈት ቤቱ ሕንፃ እንደሚያሰጋቸው ቢናገሩም ማንም መፍትሔ የሚሰጥ አልተገኘም፡፡ እናም የራስ ቅላቸውን ከአደጋ ሊከላከል የሚችለውን ሄልሜት አጥልቀው ወደ ቢሮ እየገቡ ለመሥራት ወስነው ተገበሩት፡፡ ‹‹ይህን መሰል ሁኔታ ያጋጠመን እኔ ከተቀላቀልኩ ከሁለት ዓመት በፊት ነው፡፡ ለባለሥልጣኖች ጽፈን ነበር ግን ጆሮ ዳባ ልበስ አሉን፡፡›› ሲሉ ከተቀጣሪዎች መካከል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ለህንድ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል፡፡ የዛሬይቱ ህንድ የተባለ ጋዜጣ እንደዘገበው፤ የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች አንዲት ስንስዝር ያጋነኑት ነገር የለም፡፡ በቤቱ መካከል ጣራው እንዳይፈረካከስ የሚረዳ ምሰሶ ወይም አምድ ቢኖረውም ጣራዎቹ በቀዳዳዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ የሚገርመው በህንድ ቢሮዎች የሞተር ሳይክል ሄልሜት አጥልቀው የሚገቡ ሠራተኞች በዜና ሲዘገብ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ እኤአ ከ2017 ወዲህ በተሰነጣጠቀ የመንግሥት ሕንፃ ውስጥ ስለሚሠሩ ሠራተኞች ቢሀር በሚባል አካባቢ በተመሳሳይ መልኩ የቢሮ ሥራቸውን ለመሥራት በስጋት ሄልሜት ለማጥለቅ እንደተገደዱ ተዘግቦ እንደነበር የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ ያመለክታል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 05 ቀን 2012 ዓ.ም ኃይለማርያም ወንድሙ
https://www.press.et/Ama/?p=22780
1fe4eb5e2f5e758740b904093af971a8
bf4bab508ff73e38ba6dad5d61b0e48d
ዲግሪን በዘጠኝ ዓመት
መዝናኛ
 በሀገራችን ባለው አሠራር ሕፃናት ቅድመ መደበኛ ትምህርት መከታተል የሚጀምሩት በአራት ዓመታቸው እንደሆነ ይታወቃል፤መደበኛ ትምህርት እንዲጀመሩ የሚጠበቀው ደግሞ በሰባት ዓመታቸው ነው፡፡ ይህ በከተሞች እየተሠራበት ሲሆን፣ በገጠር እና በአንዳንድ ከተሞች ግን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ጉዳይ በቄስ ትምህርት ቤት እና ቁርአን ትምሀርት ቤቶች የሚሸፈን እንደ መሆኑ የአጸደ ሕፃናት ትምህርት አለ የሚባል አይደለም፡፡ አንዳንድ ሕፃናት ግን ከሰባት ዓመታቸው በፊት ትምህርት እንዲጀምሩ ሲደረግ ይስተዋላል፡፡ ትምሀርት የጀመሩት በአምስት ዓመታቸው መሆኑን የሚገልጹ ያጋጥማሉ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች 12ኛ ክፍልን መቼ ጨርሰው መቼ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እንደሚይዙ መገመት አይከብድም፡፡ በአምስት ዓመታቸው አንደኛ ክፍል ቢገቡና ብርቱ ሆነው አስራ ሁለተኛ ክፍልን በሰዓቱ ቢያጠናቅቁ ከ21 ዓመታቸው በፊት የመጀመሪያ ዲግሪ ለመያዝ አይችሉም፡፡ በ7 ዓመታቸው የሚገቡት ደግሞ መቼ ሊጨርሱ እንደሚችሉ እናስብ፡፡ በእኛ ሀገር አንዳንዶች ትምህርት ቤት ሊገቡ በሚችሉበት ዕድሜ የመጀመሪያ ዲግሪ የያዙ ታዳጊዎች ያጋጥማሉ፡፡ ኤንዲቲ የተሰኘው ድረ ገጽ በቅርቡ ይዞት የወጣ ዘገባ እንዳመለከተው የአምስተርዳም ነዋሪው የዘጠኝ ዓመት ሕፃን የመጀመሪያ ዲግሪውን በቅርቡ እንደሚይዝ ይጠበቃል። በዚህም በዓለም የመጀመሪያ ዲግሪ ያየዘ በሕፃንነቱ መያዝ የቻለ ብቸኛው ሕፃንም ለመባል በቅቷል።፡ በኤይንሆቭን ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ለውረንት ሲሞንስ የተባለው ይህ ሕፃን የመጀመሪያ ዲግሪውን የሚይዘው በኤሌክትሪካል ምህንድስና ነው፡፡ ሕፃኑ የመጀመሪያ ዲግሪውን በሚቀጥለው ወር እንዳጠናቀቀም ፣ከሦስት ወራት በኋላ ሦስተኛ ዲግሪውን ለመያዝ ትምህርት እንደሚጀምርም ተናግሯል፡፡ እናቱ ሊዲያ የልጁ አያቶችና መምህራን ልዩ ተሰጥኦ እንዳለው ሁሌም ይናገሩ እንደነበር ስትገልጽ፣ አባቱ አሌክስንደር ሲሞንስ በበኩሉ ልጁ በእርግጥም መረጃ በመያዝ በኩል ማንም አይደርስበትም ሲል ገልጿል፡፡ ሎውረንት ገና ምኑ ተይዞ ይላል፡፡ ለዘ ቴሌግራፍ በሰጠው አስተያየትም ወደ ካሊፎርኒያ በመሄድ ትምህርቱን ለመቀጠል ይፈልጋል፤አባቱ ግን እንግሊዝ ሄዶ ቢማርለት እንደሚመርጥ አስታውቋል፡፡ የ37 ዓመቱ የጥርስ ሀኪም የሆነው አባቱ ‹‹ኦክስፎርድና ካምብሪጅ በአንግሊዝ ዋና ዋናዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ከእነዚህ ዩኑቨርሲቲዎች በአንዱ ገብቶ ቢማር ምርጫው መሆኑን አስታውቋል፡፡ ላውረንት ሲሞንስ ለሲኤንኤን በሰጠው አስተያየት በቀጣይም ማጥናት የሚፈልገው ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ መሆኑን ጠቅሶ፣ በተወሰነ ደረጃ የህክምና ትምህርት መማርም ይፈልጋል፡፡ ቤተሰቦቹ በሕፃንነቱና በእውቀቱ መካከል የሆነ ሚዛናዊ ነገር እንደሚፈልጉ ሎረንት ገልጾ፣ እሱ ደግሞ ለትምህርቱ ከሚሰጠው ትኩረት በተጓዳኝ የተለየዩ ጨዋታዎችን መጫወት፣ ከጓደኞቹ ጋር መሆን እንደሚወድ ይናገራል፡፡ በኢንስታግራም በኩል ከ11 ሺህ በላይ ተከታዮች አንዳሉት ተናግሮ፣ በዚህም አማካይነት የህይወትን የተለያዩ ጎኖች እንደሚመለከት ያብራራል፡፡ እስከ አሁን ባለው መረጃ መሰረት በዓለም በልጅነቱ የመጀመሪያ ዲግሪ በመያዝ የሚታወቀው ሚካኤል ኬርኒይ የተባለ ታዳጊ ሲሆን ፣ዲግሪውን የያዘውም በአስር ዓመቱ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 9/ 2012 ዓ.ም ዘካርያስ
https://www.press.et/Ama/?p=22776
87ecf514311349c41b6afcf02971c1fa
5ae2e2375b53d779e4a234768d414b18
ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በጁባላንድ ኮሪደር በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት ድንበር በጁባላንድ ኮሪደር በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ፡፡ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ እንደ ሚያ መለክተው ፣ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት ድንበር በጁባላንድ ኮሪደር በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡በውይይቱ በቀጣናው ስላለው ወቅታዊ የጠላት እንቅስቃሴ የመከሩ ሲሆን በቀጣናው በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡በውይይቱ ላይ የሴክተር ሁለት አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ጄማ፣ የሴክተር ስድስት ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ማኩርጋ ፓናርድ፣ የ5ኛ ሞተራይዝድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን፣ የጁባላንድ ክልል ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የፌደራል ኤስ ኤን ኤ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የጁባላንድ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡የጁባ ላንድ ምክትል ፕሬዚዳንት ማህሙድ ሰይድ ሶማሊያ ፣ ኢትዮጵያና ኬንያ ወንድማማች ህዝቦች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡የአዋሳኝ ድንበር ቦታዎች ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር የጋራ ጠላት የሆነውን አልሸባብን በጋራ መዋጋት ይገባልም ብለዋል፡፡በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) የሴክተር ስድስት ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ማኩርጋ ፓናርድ፥ የኢትዮጵያና ኬንያ ሰላም አስከባሪ ሃይል በጋራ በአካባቢው ሰላም ለማስፈን እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡የክልሉ የፀጥታ ሃይል፣ ከፍተኛ የስራ አመራሮችና ህብረተሰቡም ከጎናቸው እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡የ5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን በበኩላቸው፤ የቀጣናውን የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ለማጠናከር አልሸባብን በመዋጋት እንዲሁም የኬላ ፍተሻዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡አዲስ መን ታህሳስ 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38959
b3c36df09f2093c7ea034e2dd1f58513
5185dadf64d68adb195255824800fbd0
የማህበረሰባችን ሞራል የት ደረሰ?
መዝናኛ
በልጅነቴ ያስተዋልኩትን ሐቅ ልንገራችሁ። ነገሩ እንዲህ ነው። ሰዎች ተሰባስበው፣ እንዲቀናቸው ተመርቀው አደን ይሸኛሉ፡፡ኑሯቸውን በዱርና በገደል ያደርጋሉ፡፡በዚህ ሁኔታ ለወራት በመቆየት በለስ የቀናው አንበሳ በመግደል ጀግና ይሰኛል፡፡በለስ ያልቀናው በርሃብ ሲናውዝ ከርሞ ይመለሳል። ገዳዩም ጀግንነቱን በገበያ ያስመርቃል፤ ያውጃል፡፡የገደለውን የአንበሳ ቆዳ በትከሻው ላይ ይደርባል፤ ፀጉሩንም ቅቤ ይቀባል፡፡ከዚያም ሌሎች ጥቂት የሥጋ ዘመዶቹን አስከትሎ በገበያው መሐል እየተንጎማለለ ስለመፈጠሩ እንኳን በውል የማያውቁት በርካታ ሰዎችን በመንጋ ያስጨፍራል፤ ሲዘፍኑለት ይውላሉ፡፡እርሱም እንደሙሽራ ሲሳምና ሲሸለም የሞራል ግለቱ ጣራ ይነካል፡፡እግር የጣለው ሁሉ እያጨበጨበ አብሮ ይተማል፡፡የእንስሳት መብት ተሟጋች በማያውቃት አገራችን በቀደሙት ጊዜያት የአንበሳ ነፍስ ማጥፋት በመንጋ ያስከብርና በመንጋ ያዘፍን ነበር፡፡አሁን ላይ ይባስ ብሎ የሰው ልጅ ሕይወትን በመንጋ ማጥፋት እና በመንጋ አስክሬን መጎተት በመንጋ ያስከብር ይዟል፡፡በመንጋም ሲያስጨፍር አስተውለናል፡፡ እርግጥ ነው በዚህ የመንጋ እንቅስቃሴ ውስጥ የሀብት ጥሪት የመቋጠር ዕድል ያጋጠማቸው እንዳሉም ሹክሹክታ ይሰማል፡፡በመንጋው በአባልነት ተቀላቅለው የዘመቱ በቀን እስከ 500 ብር ሲቋደሱ፤ በመንጋው ዘመቻ በርካታ ሰው በመውረር ‹‹አራስ ነብር›› ሆነው ለዋሉ ደግሞ እንደዘመቻ አውዱ በበቃኝ ሳንቲም እንዲዘግኑ ይደረጋል መባሉን ከመከራ ቀማሿ ድሬ ሹክ ብለውናል፡፡አጃኢብ ያሰኛል፤ ጆሮ አይሰማው የለ፡፡ይሄ ገንዘብ የሚበቅልበትን ዛፍ አምላክ ይወቀው፡፡ተሠርቶ ያልተገኘ በጂኒ የሚመጣ ገንዘብ ሕዝቡን በመንጋ የጂኒ አመል እንዲኖረው አደረገ፡፡ለመልካም ተግባር ሲሆን የመሰባሰቡና የመደመሩ ጉዳይ ዳገት ይሆንብናል፡፡የእኛ ትውልድ እንዲህ ነው፡፡ቅን መሪዎችን ሳይሆን ቅንቅኖችን የሚሻ፡፡ከአብዮች ሳይሆን ከአባዮች የሚወዳጅ፣ ከሚወዱት ሳይሆን ከሚንቁት ጉልበት ሥር የሚወሸቅ፤ ተራማጅ አስተሳሰብን ያልፀነሰ ጮርቃ ሆኗል፡፡ ቢቆነጠጥና አደብ ቢይዝ አይሻልም ትላላችሁ? ‹‹አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል›› ነበር ብሂሉ፡፡ታዲያ አገሬ ተባይ ማፍራቷ አርጅታ ይሆን እንዴ? እንጃ አይመስለኝም፡፡ትውልዳችንን ልንፈትሽና ልንመረምር ይገባል፡፡ወቅቱን ጠንቅቆ የሚረዳ ብልጥ ትውልድ ያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ዋሽቶ ማስታረቅ እንጂ ዋሽቶ ማጋደል በክብር ሲያስጠራ ከታሪካችን አልሰማንም፤ አልተማርንም፤ ለማንም አይበጅም፡፡ዘመኑን የተነጠቀና ቀልቡ የተገፈፈ ባካኝ በአንዳንዶች አጠራር ‹‹የተረገመ›› ትውልድ እንዲበቅል ቆላ ከደጋ እየባከኑ ደም ሲያራጩ መዋልን ሥራዬ ብለው የተያያዙት በርክተዋል፡፡አዎ አገሪቱ እንዲህ አይነት አዳዲስ የሥራ መስኮች የሚፈጥሩ ሰዎች እንዳሻቸው የሚኖሩባት አገር ሆናለች፡፡የተራ ዜጋውም ጉዳይ ‹‹በሬ ካራጁ ….›› አይነት ሆኗል ወዳጄ፡፡‹‹ከደሙ ንፁህ ነን›› ባይ አፈቀላጤዎችም ወንድም ወንድሙን መግደልና ሲያሸብሩ መዋል እንደ ሥራ ስለመቆጠሩ እየነገሩን ነው፡፡እንደው ማን ይሙት በእኔ ልጅ ደም የእሱን ልጅ እንጀራ የሚያበስል የዋህ ኢትዮጵያዊ ስለመፈጠሩ እንደመስማት የሚያንገሸግሽ ሕመም ምን አለ?፡፡ በእምነት ቅንብብ አጥር ውስጥ በቅሎ እዚህ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ‹‹ያልዘራውን የሚያጭድ›› አለመኖሩን መረዳት አያዳግተውም፡፡ የሰው ልጅ በሥራው ልክ ተመዝኖ የሚከፈለው በአንድ ወቅት በዓለም ላይ የበቀለ አረም ተደርጎ ሊታይ ይገባል፡፡ራሱን ዘላለማዊ በማስመሰል የአልማዝ፣ የወርቅና የብር ደረጃዎች እየሰጡ እያንዳንዱን ነገር ‹‹ለእኔ›› እያሉ መስገብገብ የኢትዮጵያውያን ስብዕናም አይደለም፡፡የሰው ልጅ ሕይወት መጥፋት የሚያስጨፍረው አካል መታየት ሲጀምር መላ ሊበጅለት ይገባል፤ ሕመም መለከፉን መረዳት ያስፈልጋል። ነገ ራሱ ተራ ጠባቂ ሟችነቱን ረስቶታል ማለት ነው፡፡‹‹ሆሆይ›› ለካ ነገረ ሥራው ከተቀየረ ዋል አደር ብሏል። የምኑ እንዳትሉኝ፤ ከመኖሪያ ቀያችሁ እስከ ፌስቡክ ሰፈራችሁ የምታዩትንና የምትሰሙትን ወሬና ድርጊት አብጠርጥራችሁ ፈትሹ፡፡‹‹ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር…›› ነው ነገሩ፡፡ከእነ እንትና ሰፈር ዕሳት እየጫሩ በእነ እንትና ሰፈር በ‹‹ቪ ኤይት›› ቄንጠኛ መኪና መንፈላሰስ ዋ! ካላስባለ፣ ነገ ጨዋ ልጅ ከሰፈርህ ቀርቶ ከአብራክህ ሊወጣ አይችልም፡፡የሰውነት ሚዛናችን እያነሰ የእንስሳነት አመላችን እየጎለመሰ ይሄድ ይዟል፡፡ እኔ ለአቅመ ማስተዋል ከደረስኩበት ጊዜ አንስቶ ያስተዋልኩት የሰው ልጅ ሞራል የማጣት ልክ እንደዚህ ጊዜ ሲዘቅጥ አስተውዬ አላውቅም፡፡ምን አልባት የእኔ የማስተዋል ልክ ከሆነ አላውቅም፡፡ኧረ እንደውም ባደግንበት ወግና ባህልማ የሰው ልጅ በሕይወት ሲኖር ከሚያገኘው ክብር የላቀ አስክሬኑ ይከበር ነበር፡፡አብሮን ባደገው የመበቃቀል ክፉ ልማዳችንም ውስጥ ቢሆን እንጥፍጣፊ መከባበር ነበረበት፡፡እንኳንስ ሰውን ያህል ነገር ቀርቶ የእንስሳትም ቢሆን አስክሬን የተመለከተ ሰው ያዝናል፤ ባስ ሲልም በዓይኑ በብረቱ የሰው አስክሬን ወድቆ በድንገት የተመለከተ ሰው ራሱን ለከፍተኛ ፀፀት ይዳርጋል፡፡ምን የሠራሁት ሐጢያት (ክፉ ሥራ ) ቢኖር ይሆን ፈጣሪ ይሄን ያሳየኝ፤ በሚል ነፍሱን እሱ ያጠፋ ያህል ፈጣሪውን በፀፀት ይለምናል፡፡ነፍሱ በፈጣሪው ፊት ትጠየቅ እስከሚመስለው ድረስ ይፀፀታል፡፡‹‹ማረኝ›› ይላል፡፡አሁን አሁን የሚስተዋለው ድርጊት ግን ለየቅል ሆኗል፡፡እመኑኝ ታሪክ ዋሽቷል ወይም ትውልዱ ላሽቋል የሚያሰኝ ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡በመንጋ ተነስቶ በመዝመት የሰው ልጅ ሕይወትን ማጥፋት በየትኛውም እምነት የተወገዘ ብቻ ሳይሆን አውሬነት ተደርጎ የሚቆጠር ተግባር ነው፡፡እንዲህ አይነት የአውሬነት ተግባር የመፈፀም ድፍረት እንዲሁ በአጭር ጊዜ የሚለመድ ባህሪ አይምሰላችሁ፡፡ይህ ትውልድ ጤንነቱ ሊፈተሽ የሚገባ ይመስለኛል፡፡በማንኛውም መመዘኛ ሊያሳምን የሚችል አመክንዮ የሚቀርብበት ጉዳይ አይደለም፡፡አዲስ ዘመን ኅዳር 11/2012 ሙሐመድ ሁሴን
https://www.press.et/Ama/?p=22886
2003e5ce6624d9898ab41b0f32c9ada7
9147b8e23c7a66fc6999222e020bd253
መገናኛ ብዙሃን የአገር ሰላምንና አብሮነትን በማጎልበት ረገድ የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ እንዳልሆነ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
 አዲስ አበባ (ኢዜአ)፦ መገናኛ ብዙሃን የአገር ሰላምና የህዝቦችን አብሮነትን በማጎልበት ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና እየተወጡ እንዳልሆነ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ትናንት በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሃፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንዳስታወቁት፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መገናኛ ብዙሃን እውነተኛ መረጃን ከማሰራጨት ይልቅ የህዝቦችን አብሮነት የሚሸረሽሩ ዘገባዎችን እያቀረቡ ነው። መገናኛ ብዙሃን የሚያሰራጯቸው መረጃዎች በዜጎች ደህንነት ላይ የሚፈጥሩትን አደጋ ሊገነዘቡ እንደሚገባም ያመለከቱት ቀሲስ ታጋይ፤ ‘እኛና እነሱ’ በሚል አስተሳሰብ የሚሰራጩ የተሳሳቱ ዘገባዎች በርካታ ንጹሃን ላይ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን አስታውቀዋል።የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ በበኩላቸው፤ በተለይ የፖለቲካ ሰዎችና አክቲቪስቶች በሚዲያ ቀርበው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጥላቻ ንግግሮችን ሲያስተላልፉ እንደሚስተዋል ተናግረዋል።“አብዛኞቹ የጥላቻ ንግግሮችም በዜና መልክ ለህዝቡ የሚቀርቡ ናቸው” ብለዋል።በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ለሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና በአግባቡ ከመወጣት ይልቅ ግጭቶች ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆኑንም አስታውቀዋል።በቅርቡ 15 ያህል መገናኛ ብዙሃን ላይ በተደረገ ጥናት 28 በመቶ የሚሆኑት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።18 በመቶው የሚሆነው ሽፋናቸው ደግሞ በግጭቶችና ከዚያ ጋር ተያይዞ በሚከሰቱ ሰብዓዊ ቀውሶች ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።ጥናቱ መገናኛ ብዙሃን ለሰላም መስፈን ያበረከቱት አስተዋጽኦ ዝቅተኛ መሆኑን ያመላከተ እንደሆነም አስታውቀዋል።“የመገናኛ ብዙሃን አሰራር በሚፈለገው ልክ አለመዘመን ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ አድርጓል” ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዷለም ናቸው።የሚዲያ ስነ-ምግባር ከየትኛውም ሃይማኖት አስተምህሮ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ በተለይ የህብረተሰቡን መልካም እሴቶች አጉልቶ በማውጣት ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።የመገናኛ ብዙሃኑም ህግና ስርዓትን አክብረው ለአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት የድርሻቸውን እንዲወጡ የአቅም ግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል።የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶችም መገናኛ ብዙሃን ለአገሪቷ ሰላምና ለህዝቦች አንድነት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ መን ታህሳስ 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38960
a0029c313cf0f4f90ba350bd387de7a8
ff0227b399f04d5e01002f2f502a6739
ኮሚሽኑ ለመተከል ተፈናቃዮች ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
አሶሳ፡- በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የመተከል ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የሚደገውን ጥረት በዘላቂነት እንደ ሚደግፍ አስታወቀ፡፡ በኮሚሽኑ የአሶሳ ንዑስ ቢሮ ኃላፊ ሚስ ጆላንዳ ቫን ለኢዜአ እንዳስታወቁት ፣ ኮሚሽኑ የመተከል ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ከክልሉ መንግስት ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው፡፡በክልሉ የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ረጂ ድርጅቶች እንዳሉ የጠቀሱት ኃላፊዋ፤ ድጋፉን ለማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራር ፈጥረን እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል፡፡ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ ለዞኑ ተፈናቃዮች ምግብ ነክ ያልሆኑ የቁሳቁስ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየታቸውን አመልክተዋል፡፡የመተከል ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም መንግስት የሚያደርገውን ጥረት ኮሚሽኑ በቀጣይም በዘላቂነት እንደሚደግፍ አስታው ቀዋል፡፡ ከኮሚሽኑ ጋር በመቀናጀት ለመተከል ተፈና ቃዮች ድጋፍ እያደረጉ ከሚገኙ ተቋማት መካከል አክሽን ፎረ ዘ ኒዲ የተባለ ረጂ ድርጅት የአሶሳ ቅርንጫፍ አንዱ ነው፡፡ የቅርንጫፉ ኃላፊ አቶ መላኩ ገዛኸኝ እንዳሉት፤ ድርጅቱ ሰሞኑን ለመተከል ተፈናቃዮች ባደረገው የመጀመሪያ ዙር እገዛ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አቅርቧል፡፡ከቁሳቁሶች መካከል የምግብ ማብሰያ እና መመገቢያ ቁሳቁሶች፣ አልባሳት፣ ፍራሽ፣ የአልጋ አጎበር እና ሌሎችም ለክልሉ አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን ማስረከቡን ጠቅሰው፤ ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው አስታውቀዋል፡፡የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ተሲሳ በበኩላቸው ፣በክልሉ የመተከል ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋም መንግስት ብቻውን የሚወጣው ባለመሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የማሳተፍ ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ድርጅቶቹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ተግባራዊ ምላሽ እየሰጡ ነው ብለዋል፡፡ድጋፉን እያደረጉ ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መካከል የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና አብረው የሚሰሩት ድርጅቶች ዋነኞቹ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ድጋፉን በክላስተር በመለየት ለማሰባሰብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ድጋፉን ወደ መተከል በቀጥታ ማድረስ የማይችሉ ድርጅቶች በአሶሳ እና አካባቢው እንዲያስረክቡ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ እስካሁን በርካታ ምግብ እና ቁሳቁሶች በድጋፍ መሰብሰባቸውን ጠቁመዋል፡፡በቅርቡ የተሰባሰበው ድጋፍ ወደ መተከል ቡለን እና ድባጤ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቀደም ሲልም ለመተከል ተፈናቃዮች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉ በወቅቱ ተገልጿል።አዲስ መን ታህሳስ 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38973
a068bd97ab6741a96eabc91cc3b6aa37
548896a85a6f3a40c83b6d19a8d83b8f
ከባድ ፈተናን ተሻግሮ የሚወለድ ስኬት
ስፖርት
ማንኛውም ሰው በሕይወት ዘመኑ ፈተና ይገጥመዋል፡፡ ፈተናው ከባድም ቀላልም ሊሆን ይችላል፡፡ ቁምነገሩ ፈተናውን አልፎ ወደሚታሰብ ስኬት መድረስና ለዚህም ተስፋ ሳይቆርጡ የሚቻለውን ብቻ ሳይሆን የማይቻለውን ነገር ለመሞከር ጥረት ማድረግ ነው፡፡ የስፖርቱ ዓለም ሰዎች ወደ ታላቅ ስኬት ከመሸጋገራቸው በፊት የተለያዩ ከባድ ፈተናዎችን የመጋፈጥ አጋጣሚዎች በሕይወት ዘመናቸው ሲከሰቱ ማየት የተለመደ ነው፡፡ የስፖርቱ ዓለም በርካታ ከዋክብቶች ከሞላ ጎደል በዚህ ዓይነት የሕይወት ውጣ ውረድ ማለፋቸውን የስኬታቸው ጫፍ ላይ ሆነው ሌሎችን ለማስተማርና ለማነሳሳት ብሎም በሕይወት ዘመናቸው የቱንም ያህል ከባድ ፈተና ቢገጥማቸው ውስጣቸውን በተስፋ ለመሙላት ሲናገሩት ይደመጣል፡፡ ዓለማችን በጤና ቀውስ ውስጥ ባለችበት በዚህም ወቅት የተለያዩ የስፖርቱ ዓለም ወጣትና ተስፈኛ ትውልዶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ችግሮች ሊደቀኑባቸው እንደሚችሉ እርግጥ ነው፡፡ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገራት ውስጥ ነገን በትልቅ ተስፋ የሚጠባበቁ ወጣት ስፖርተኞች የአገራችንም ይሁን የዓለም ስፖርት መድረኮች ሽባ በሆኑበት በዚህ ወቅት በምጣኔ ሀብትና በሌሎች ፈተናዎች ሊወጠሩ እንደሚችሉ ግልፅ ነው፡፡ ይህን ፈተና በፅናት ለማለፍ የሥነልቦና ጥንካሬና ተስፋ አለመቁረጥ በባለሙያዎችም ይመከራል፡፡ ከዚህም በዘለለ አሁን ላይ በስኬት ማማ ላይ የተቀመጡ ከዋክብቶች ካለፉባቸው የሕይወት ውጣ ውረዶች በመማር ራሳቸውን በተስፋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለዚህም የሼን ደፊ ፈተናና የኋላ ስኬት ታሪክ አንዱ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡ እ.አ.አ በ2010 ሰኔ ወር ሼን ደፊ መልዕክት ደረሰው። ለአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ መጠራቱን የሚያበስር መልዕክት ነበር። ገና በአስራ ስምንት ዓመቱ ለብሔራዊ ቡድን መጠራቱ ታላቅ ተስፈኛነቱን ያረጋገጠለት ስለነበር ደስታው ወደር አልነበረውም። ደፊ ዘለግ ያለ፣ ደንደን ያለ የፈርጣማ ሰውነት ባለቤት ነው። ሃያ ዓመት ሳይሞላው ዘጠና ኪሎ ግራም ይመዝናል። ቁመቱ ደግሞ 1ነጥብ 93 ሜትር ይረዝማል። እ.አ.አ በ2010 በኤቨርተን ጥቂት ጨዋታዎች ላይ እንደተሰለፈ ጆቫኒ ትራፓቶኒ ለአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን የጠሩት ለመሐል ተከላካይነት ስፍራ ያስፈልጋል የሚሉት ተክለ ሰውነት ስላለውም ጭምር ነበር።አየርላንድ ከፓራጓይ ላለባት ግጥሚያ ቡድኑ ዝግጅት ጀመረ። በልምምድ ማዕከሉ የልምምድ ጨዋታ ሲያደርግ ደፊ በተከላካይነት ሚናው ተጫወተ። በጨዋታው እንቅስቃሴ መሐል ከክንፍ በኩል ኳስ ተሻማ። ደፊና የተከላካይ መስመር አጋሮቹ የሚያጠቃው ቡድን ተሻጋሪዋን ኳስ እንዳያገኛት ለማገድ ተረባርበው ታገሉ። ደፊም ተሻማ። ግን ግጭት ደርሶበት ወደቀ። አጋጣሚው ወትሮ ከሚያጋጥም የ«ጎል ላስቆጥር፣ አታስቆጥርም» ፍልሚያ የተለየ አልነበረም። ጉዳቱም ከተለመደ ጉዳት ይለያል ብሎ መገመት አይቻልም። ግን ግዙፉ ጎረምሳ ከወደቀበት መነሳት አቃተው። የተቧጨረ፣ የደማ፣ የተሰበረ የውጪያዊ ሰውነት ክፍል አይታይበትም። ሆኖም ደፊ ጣር ያዘው። ተሰቃየ። የሲቃ ድምፁን አሰማ። የአየርላንድ ቡድን የሕክምና ቡድን አባላት ህመም የሚሰማው የትኛው የሰውነቱ ክፍሉ ላይ እንደሆነ ሲጠይቁት በጎድን አጥንቱ ስር ያሳያቸዋል። ስቃዩን አይተው የገጠመው ጉዳት ቀላል እንዳልሆነ በመረዳታቸው በአስቸኳይ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ወሰዱት።በደብሊን በሚገኘው ማተር ሆስፒታል ሲደርስ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና ታዘዘለት። ግብ ክልል ውስጥ የነበረው ፍትጊያና ግጭት ውጪያዊ ሳይሆን ውስጣዊ አካሉ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሶበታል። በቢላዋ የሸረከቱት ይመስል ጉበቱ ተቀደደ። 3ነጥብ6 ሊትር ደም በመፍሰሱ ሆዱ ተነፋ። ከሰውነቱ የደም መጠን ሁለት ሦስተኛ የሚሆነው ሆድ ዕቃውን ሞላው። እሱንም ለማስቀረት የቀዶ ጥገና ርብርቡ ቀጠለ። በዚያች ክፉ ማክሰኞ አደጋው ደርሶበት ሆስፒታል ከገባ በኋላ እስከ ሐሙስ ድረስ ራሱን ስቶ ቆየ። ከዚያም እስከ እሁድ ድረስ በከፍተኛ የሕክምና ክትትል መስጫ ክፍል ውስጥ ከረመ። በሆስፒታል ኮሪደር ላይ በጭንቅ ወዲያ ወዲህ የሚሉት ወላጆቹ ከከፍተኛ የሕክምና ባለሙያዎቹ ቁርጡ ተነገራቸው። «ልጃችሁ የመትረፍ ዕድሉ ጠባብ ነው» ተባሉ። የልጃቸውን የሞት ዜና መጠባበቅ ጀመሩ።የደፊ ጉበት ደም ስሮች በመተርተራቸው ደሙ ውስጡ ተንዠቅዥቋል። ብዙ ደም ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሆኗል። የተጫዋቹን ሕይወት ለመታደግ ብዙ ደም ወደ ሰውነቱ መጨመር አስፈለገ። ልቡና አእምሮው ደም ማጣት የለባቸውምና። በእግር ኳስ ሜዳ ላይ እንዲህ ዓይነት ጉዳት የተለመደ አይደለም። ጉዳቱ በከባድ የመኪና አደጋ ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል እንደሆነ ዶክተሮቹ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ሕክምናው ስኬታማ ነበር። አቅሉን ከሳተበት ሲመለስ ምን ዓይነት አደጋ እንደደረሰበት ተነገረው። እርሱም «በቃ አበቃልኝ» በማለት ተስፋ ቆረጠ። ሐኪሞቹ ግን ጥረታቸውን ቀጠሉ። ደፊ ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ ለማገገም ስድስት ሳምንታት አስፈለጉት። ለማገገም ብዙ ለፍቶ ከስድስት ወራት በኋላ ልምምድ ጀመረ። ዘጠና ኪሎ ግራም ይመዝን የነበረው ተከላካይ አስራ ስምንት ኪሎ ግራም ቀንሶ ወደ ሰባ ሁለት ኪሎ ግራም ወረደ። አቅሙን ሁሉ ለመመለስ ሁለት ዓመት ገደማ ፈጀበት። ደፊ ከዚህ ሁሉ ፈታኝ ውጣ ውረድ በኋላ ወደ ጨዋታ ሲመለስ ግን ኤቨርተን ቀድሞ የሚያውቀውን ብቃቱን ማግኘት አልቻለም። ስለዚህ እ.አ.አ ከ2011 እስከ 2016 ድረስ በበርንሊ፣ ስካንትሮፕ ዩናይትድና ዩኦቪል ታውን በውሰት ተዘዋውሮ ለመጫወት ተገደደ። ከ2014 – 2016 ደግሞ በብላክበርን ሮቨርስ ቆየ። ከአሰቃቂው ጉዳት ስድስት ዓመታት በኋላ በሁለተኛው ዲቪዚዮን የሚወዳደረው ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን አስፈረመው። ያኔ የመከራውና የጭለማው ዘመን አልፎ የንጋቱ ወጋገን ደምቆ ታየው። «ሳቢሳዎቹ» ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሲያድጉ ደፊ ከቁልፍ ተጫዋቾቻቸው አንዱ ለመሆን በቃ። እ.አ.አ በሰኔ 2017 የአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ይህን ከሞት የተረፈ ተጫዋች በድጋሚ ጥሪ አደረገለት፡፡ እንደ አጋጣሚም ሆኖ ይሁን የዕጣ ፈንታ ጉዳይ ደፊ ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ሲደረግለት ዳግም ጣጣ አላጣውም፡፡ ከሊድሱ ተጫዋች ዩናይ ኦካኒ ጋር ከትውልድ ከተማው ዴሪ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ካምፕ በመጓዝ ላይ ሳሉ የመኪና አደጋ ደረሰባቸው። ሆኖም አደጋው ጉዳት ሳያደርስባቸው አለፈ። የመኪና አደጋ ሳይሆን እግር ኳስ ጨዋታ የመኪና አደጋ ያህል የጎዳው ሼን ደፊ ዛሬ ላይ ዕድሜው ሃያ ስምንት ደርሷል። የመከራው ጊዜ አልፎለት በየሳምንቱ መጨረሻ ለፕሪሚየር ሊጉ ብራይተን ተሰልፎ ለመጫወትም በቅቷል፡፡ ፅናቱም በተሻለው ደረጃ ላይ አስቀምጦታል። ከዚያ ሁሉ መከራና የጭንቅ ጊዜ አልፎም ከአጥቂዎች ጋር በግብ ክልል ውስጥ ሲታገል ታይቷል፣ ሲከላከልም ሆነ ሲያጠቃ የ2010ሩ አሰቃቂ የሕይወት አጋጣሚው አይታወሰውም። ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=33455
d526c6154a1d67de1f5d856fe78ced57
d1e1d8fb996069b2ab657ee61c2de97b
የውድድሮች መመለስ ስጋትና ጥቅሙ ሚዛን ላይ ሲቀመጥ
ስፖርት
በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ስጋት ምክንያት ተቋርጠው የቆዩ እንቅስቃሴዎች አሁን ወደ ነበሩበት እየተመለሱ ነው። የአውሮፓ ሊጎችም የውድድር ዓመቱን ካቆመበት በመቀጠል ሂደት ላይ ናቸው። የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ከሁሉም ቀድሞ ወደ ውድድር የተመለሰ ሲሆን፤ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ እና የጣሊያን ሴሪ ኤም ከተያዘው የፈረንጆቹ ወር ጥቂት ቀናት በኋላ ካቆሙበት ለመቀጠል ክለቦች ልምምድ ጀምረዋል። የዓለም አትሌቲክስም የዳይመንድ ሊግ ውድድሮችን ለማስጀመር ቀን መቁረጡ ታውቋል። በዚህ ወቅት ሃገራት ከቫይረሱ ቀውስ መጠነኛ ማገገም እንጂ ጥናትና ምርምሩ ያልተጠናቀቀውን ወረርሽኝ ጨርሰው ተቆጣጥረውታል ለማለት አዳጋች እንደሆነባቸው ግልጽ ነው። ዓለም በዚህ ጭንቀት ውስጥ ባለችበት ወቅት ስፖርት ወደነበረበት መመለሱ በጤና ነው? የሚሉ አስተያየቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲነሱ አድርጓል። እርግጥ ነው ክለቦች እንደ ቀድሞው የተጫዋ ቾቻቸውን ሙሉ ደመወዝ መክፈል በማይችሉበት ደረጃ ተቸግረዋል። አትሌቶችም በውድድሮች መሰረዝና መራዘም ምክንያት ገቢ ማግኘት አልቻሉም። በአጠቃላይ በስፖርቱ ዘርፍ የሚሰሩ አካላት በቢሊዮን ለሚቆጠር የገንዘብ ኪሳራ ተዳርገዋል። አሁን ካሉበት በጥቂቱም ቢሆን ለማገገም ደግሞ ውድድሮችን ማካሄድ ይኖርባቸው ይሆናል። ለተመልካች ዝግ የሆኑ ስታዲየሞችና የስፖርት ሜዳዎችም አማራጭ በመሆናቸው ላይ ሁሉም የሊግ አመራሮች ተስማምተዋል። እንዲያም ሆኖ ግን የጤና ባለሙያዎች ዓለም ራስ ምታት ከሆነባት ወረርሽኝ ሳታገግም ወደ ውድድሮች በመመለሳቸው ስጋታቸው ማየሉን አልሸሸጉም። በመድሃኒቶች ላይ የማማከር ስራ የሚሰሩት ዶክተር ማሶድ ኤጋ ‹‹ይህ ወቅት አሁንም መገለል የሚያስፈልግበት እንጂ ውድድሮች የሚጀመሩበት ነው ለማለት ያስቸግራል›› ሲሉ ቲአቲ ወርልድ ለተባለ ድረ ገፅ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አሁን በጨዋታ ላይ የሚገኘው ቡንደስ ሊጋ ከመንግስት ፈቃድ ያገኘው እያንዳንዱ ክለብ ንጽህናውን በሚገባ እንዲጠብቅ በማሳሰብ ጭምር ነው። ከዚህ ቀደም በእግር ኳስ ማህበሩ ሁለት ዲቪዚዮን ውስጥ የሚጫወቱ 1ሺ724 ተጫዋቾች ላይ በተደረገው ምርመራ 10 የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸውን ዘገባው አስታውሷል። በመሆኑም ንጽህናን ከመጠበቅ ባሻገር እያንዳንዱ ተጫዋች በየዕለቱ መመርመር እንዳለበት ዶክተር ማሶስ ያሳስባሉ። ይህ ካልሆነ ግን ቫይረሱ ድምጹን አጥፍቶ ከአንዱ ተጫዋች ወደሌላው ከዚያም ወደ ክለቦች በመዛመት ለመቆጣጠር አደገኛ ሊሆን እንደሚችልም ይጠቁማሉ። አሁንም ከተመልካች ውጪ ጨዋታን ማካሄድ አቻ የሌለው አማራጭ መሆኑ በስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ ታምኗል። የጤና ባለሙያዎች በአንጻሩ ተመልካቾች ባይኖሩም በስታዲየም አካባቢ ከ100 የሚልቁ ሰዎች መገኘታቸው ከስጋት እንደማያድን ነው የሚያስገነዝቡት። ሊጎች እንዲሁም ክለቦች በበኩላቸው ከገቡበት የኢኮኖሚ ጫና ለመውጣት ባላቸው ብርቱ ፍላጎት ምክንያት የባለሙያዎችን ምክር ችላ እንዳሉ ቀጥለዋል። ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቀሪዎቹን 92 ጨዋታዎች በማካሄድ የውድድር ዓመቱን ካላጠናቀቀ የ1ነጥብ25 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ የሚያጋጥመው ይሆናል። በመሆኑም በተመረጡ ስታዲየሞች ከደጋፊ ውጪ ጨዋታዎቹን ለማካሄድ ቀናት ብቻ ቀርተዋል፤ ክለቦችም የልምምድ ሜዳዎቻቸውን ከፍተዋል። የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው ጨዋታዎቹን የግድ መቀጠል ቢገባ እንኳን ክለቦች ተጫዋቾቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ላይ ሞት ሊከተል እንደሚችል፣ የሚገጥማቸውን ኪሳራ እንዲሁም ካሳን ታሳቢ ማድረግ እንዳለባቸው ያሳስባሉ። ሌላው የባለሙያዎች ስጋት የወረርሽኙ ፈጣን ስርጭት ሲሆን፤ በላብ እንዲሁም በግብ ጠባቂዎች ጓንት አማካኝነት የመዛመት እድሉ ሰፊ መሆኑንም ነው ያመላከቱት። ለዚህ ስጋት ምክንያት የሆነው ደግሞ ባለሙያዎቹ ለሚሰጡት ምክር የየክለቡ የጤና ባለሙያዎች ትኩረት እየሰጡ አለመሆናቸውን ነው። ከዚህ ባሻገር ተጫዋቾች በሚገባ በየዕለቱ ምርመራ እያደረጉ እንኳን፤ ደጋፊዎቻቸው ደግሞ ጨዋታን በቴሌቪዥን ለመከታተል አካላዊ ርቀታቸውን ሳይጠብቁ ይሰባሰቡ ይሆናል የሚል መሆኑን ዶክተር ማሶድ ያሰምሩበታል። የቡድን ስፖርቶች በባህሪያቸው ለአካላዊ ርቀት የማይመቹ በመሆናቸው እንደየስፖርት ዓይነቱ ውድድሮች ቢቀጥሉ የሚል ምክረ ሃሳብ የሚያቀርቡት ደግሞ በአሜሪካ የኮቪድ 19 ግብረ ኃይል አማካሪ እንዲሁም የብሄራዊ የኢንፌክሽን በሽታዎች ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፉሲ ናቸው። መታሰብ ያለበት ወረርሽኙ እንዴት በቀላሉ ከአፍንጫ ወደ እጅ ከዚያም ወደ ልብስ በመጨረሻም ወደ ሌላ ሰው እንደሚተላለፍ ነው። በመሆኑም ቀጣዩ የስጋት አቅጣጫ ጨዋታዎችና ግጥሚያዎች እንዳይሆኑ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው። የዓለምን እግር ኳስ የሚመራው ፊፋ የሕክምና ኮሚቴ ሊቀመንበርና የፊፋ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ሚካኤል ባሮን ሆግ በበኩላቸው ‹‹ዓለም ለእግር ኳስ ውድድሮች ዝግጁ አይደለችም›› ይላሉ። ቤልጂየማዊው ዶክተር ዘ ሰን ከተባለው ድረ ገጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ዓለም ለጤና እና ለመድሃኒት ቅድሚያ መስጠት ያለበት ወቅት ላይ መሆኗን ይገልጻሉ። አደጋውን ሲያመለክቱም ‹‹በዚህ ድራማዊ በሆነ ክስተት ውስጥ ኃላፊነት መውሰድ ከባድ ነው። ተጫዋቾች በትክክል ሁለት ሜትሮችን ተራርቀው አይጫወቱም፤ የፊት ጭምብል ማድረግም አይችሉም። በሜዳ እና በመልበሻ ቤትም አብረው ናቸው። በዝግ ስታዲየም ይጫወቱ ቢባልም በሆነ አጋጣሚ ቡድናቸውን ለመደገፍ የገቡ ደጋፊዎች ይገኛሉ። ምርመራውን በየወቅቱ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም፤ አንድ ሰው በቫይረሱ ተያዘ ማለት ግን ቡድኑን በሙሉ ወደ ለይቶ ማቆያ ማስገባት የግድ ይሆናል። ስለዚህ እግር ኳሱ መታገስ እና የጤና ባለሙያዎችን ምክር መስማት አለበት›› በማለት ያስረዳሉ። አዲስ ዘመን ግንቦት 24/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=33507
c9877fb05e3b1eacb4b3fa18da1f9983
2a7cf8fc16f8ee5a8efc81cc955ff885
ለአፍሪካ እግር ኳስ ፈተና ድጎማ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣ ይሆን?
ስፖርት
በመላው ዓለም ከ210 ሀገራት በላይ የተዛመተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የዓለምን የስፖርት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ከቶታል። በወረርሽኙ ሳቢያ ትልልቅ የስፖርት ውድድሮች በመራዘማቸው፣ በመሰረዛቸው እና በመስተጓጐላቸው ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ገቢ እንደሚያሳጣው የተለያዩ ትንበያዎች አመልክተዋል። የስፖርት ኢንዱስትሪውን በስፖንሰርሺፕ የሚደግፉ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የበጀት ቀውስ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትኬት ሽያጭ ከማርኬቲንግና ከተለያዩ ንግዶች የሚገኙ ገቢዎች መቆማቸው ሁሉንም ስፖርት ጎድቷቸዋል፡፡ በተለይ የእግር ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። በዚህ ዓመት የእግር ኳሱ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ሲጠበቅ ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል። የአብዛኛዎቹ የእግር ኳስ ክለቦች ዋነኛ ገቢያቸውን የሚያገኙት ከሶስት ምንጮች ሲሆን፤ ይኸውም ከመገናኛ ብዙሃን የስርጭት መብት፣ ከስፖንሰርና ማስታወቂያዎች እንዲሁም በጨዋታ ወቅት ከስታዲየም የትኬት ሽያጭ እንደሆነ የወርልድ ኢኮኖሚ ፎረም መረጃዎች ያመላክታሉ።10 በሚደርሱ ሊጎች ያለው ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነም ክለቦቹ ከሚዲያ መብት ብቻ ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገኛሉ። ይህም ከአጠቃላይ ገቢያቸው 60 ከመቶ ይሸፍናል። በወረርሽኙ ምክንያት የውድድሮች መቋረጥን ተከትሎ ክለቦች ከእነዚህ ምንጮች የሚያስገቡት ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ያመላክታል። ዴይሊሜይል በዚሁ ዙሪያ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን እንደማሳያ በመጥቀስ ያወጣው ይሄንኑ ያጠናክራል። የዓለማችን እጅግ ተወዳጅ ከሆኑ ሊጎች በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሰው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በወረርሽኙ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን በዘገባው ጠቅሷል። ፕሪምየር ሊጉ ባለፈው ዓመት አዲስ በገባው (ለሶስት ዓመታት) ኮንትራት 12 ቢሊዮን ዶላር ከሚዲያ መብት ብቻ ለመሰብሰብ አቅዶ ነበር። እግር ኳሱ አሁን ካለው ቁመና አኳያ እቅዱን ማሳካት የሚቻል አይሆንም ሲል ዘገባው አትቷል። ውድድሩ ሁለት ወራትን እንኳን ሳያስቆጥር ክለቦቹ ከ60 እስከ 150 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ማስተናገዳቸውን እያስታወቁ ይገኛሉ። በመሆኑም ከቴሌቪዥን መብት ከሚገኝ ገቢ ብቻ እያንዳንዱ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለብ 750 ሚሊዮን ፓውንድ ያጣል። ስለዚህ ፕሪሚየር ሊጉ በዚህ ምስቅል ቅል ውስጥ ሆኖ ለማግኘት ያቀደውን ገቢ ማሳካት እንደማይችል በመግለጽ ፤ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የእግር ኳሱን ኢንዱስትሪ ለከፍተኛ የፋይናንስ ቀውስ የዳረገው መሆኑን በዘገባው አትቷል። የእግር ኳስ ጨዋታዎችና መሰል እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ መደረጉን ተከትሎ እንደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁሉ በሁሉም ሀገራት የሊግ ውድድሮች ላይ መጠኑ ይለያይ እንጂ በፋይናንስ ቀውሱ የተጎበኙ መሆናቸው መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ። በተለይ በአህጉር አፍሪካ የሚገኙት ክለቦችና ብሄራዊ ፌዴሬሽኖችን በከፍተኛ ደረጃ እንዳቃወሳቸው ተነግሯል። የአፍሪካ ሀገራት ወረርሽኙን ለመከላከል የእንቅስቃሴ እግዳ መጣላቸውን ተከትሎ ኢኮኖሚያዊ መቃወስ ውስጥ አስገብቷቸዋል። የኢኮኖሚው መቃወስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የክለቦች ቀጣይ ህልውና አስጊ ደረጃ የሚያደርስ ይሆናል። በዓለም አቀፍ ደረጃ አንቱ የተባሉ የእግር ኳስ ተንታኞች «የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የዓለም እግር ኳስን በተለይ የአፍሪካ እግር ኳስን ከባድ ፈተና ይገጥመዋል» የሚሉ መላምቶችን እያስቀመጡ ይገኛሉ። የአህጉሪቱ እግር ኳስ በተለያዩ ችግሮች ተተብትቦ «የእድገት ውስንነት በሽታ» ሰለባ መሆኑን ያነሳሉ። የዓለም ፈተና የሆነው ኮቪድ-19 የወለዳቸው ችግሮች ተደምረውበታል። ይህም «በእንቅርት ላይ ጆሮ… » ያደርግበታል ። መጪው ጊዜ በተለይ ለአህጉር አፍሪካ እግር ኳስ ህልውና እጅጉን ፈታኝ እንደሚሆን መላምቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። ለዓለም እግር ኳስ እድገትና ድምቀት እርሾ የሆነችውን አፍሪካ የእግር ኳኳ ህልውና ከገባበት አጣብቂኝ እንዲወጣ ድጎማ ማድረግ እንደሚገባ ምክረ ሃሳቦች ቀርበዋል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የቀረቡትን ምክረ ሃሳቦች መሰረት ያደረገ ተግባር ሊፈጽም መሆኑ በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ አድርጓል። ካፍ ዓለምን በአንድ የጭንቀት ቀረጢት ውስጥ የከተተው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ በእግር ኳሱ ላይ ያሳደረውን ጫና ከፍትኛ መሆኑን በመረዳት የበኩሉን ድጋፍ ለማድረግ ውጥን መያዙን አስታውቋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገሮች ዓመታዊ የእግር ኳስ መርሐ ግብሮቻቸውን በዓለም አቀፉ ኮቪድ 19 ወረርሽን ምክንያት በሰረዙበት በዚህ ወቅት፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለአባል አገሮቹ የገንዘብ ድጎማ ሊያደርግ መሆኑ ታወቀ፡፡ ኮንፌዴሬሽኑ ለእያንዳንዱ አገር 200 ሺሕ ዶላር ሊሰጥ ማቀዱ ነው ያስታወቀው ፡፡የ54 አገሮች ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችን የሚያስተዳድረው ካፍ፣ በየዓመቱ በመደበኛነት ከሚያከናውናቸው ውድድሮች መካከል የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግና የአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁንና ሁሉም በወረርሽኙ ምክንያት ውድድሮቹ እንዲሰረዙ አድርጓል፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን በሚመለከት አሁን ላይ ምንም ያለው ነገር የለም፡፡ የዘንድሮን የውድድር ዕጣ ፈንታ በሚመለከት ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ስለመደረጉ ወይም ስለመሰረዙ ውሳኔ ላይ ባይደርሱም፣ 16 አገሮች መደበኛ ውድድሮቻቸውን መሰረዛቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዓመቱን ውድድር ከመሰረዟም በላይ በሚቀጥለው ዓመት በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግና የክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውክልና እንደማይኖራት ለጊዜውም ቢሆን ይፋ አድርጋለች፡፡ የተቀሩት 15 አገሮች ደግሞ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሩ እስከተቋረጠበት ድረስ በደረጃ ሰንጠረዡ በተቀመጠላቸው ውጤት መሠረት የሚያሳትፏቸውን ክለቦች በማሳወቅ ውድድሮቻቸውን መሰረዛቸው ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ እነዚህም ቡርኪና ፋሶ፣ ጋምቢያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሞሪሸስ፣ አንጎላ፣ ኬቨርዴ፣ ጊኒ፣ ቶጎ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ካሜሮን፣ ሩዋንዳ፣ ኒጀር፣ ኮንጎ ብራዛቪልና ላይቤሪያ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ አህጉራዊው ተቋም እንደ አውሮፓና መሰል አህጉሮች በእሱ ሥር የሚያስተዳድረውን እግር ኳስ ወደ ገንዘብ በመለወጡ ረገድ ክፍተኛ ክፍተት ያለበት መሆኑ ተጠቅሷል ፡፡ ይሁንና ካፍ በየዓመቱ ለአባል አገሮቹ የሚሰጠውን የገንዘብ ድጎማ ሳያቋርጥ ለመስጠት ማረጋገጫ መስጠቱን የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የካፍን ድረ ገጽ ዋቢ በማድረግ ዘግበዋል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለአባል ሀገራቱ የ200 ሺህ ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርገው ሁሉ፤ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የ150 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደርጋለው ማለቱን ይታወሳል። ከዓለም እግር ኳስ ራስ የሆነው ተቋም ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑ፤ ከሰሞኑ ደግሞ የአህጉሪቱ እግር ኳስ የበላይ ጠባቂ ካፍ ለአባል ሀገራቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል። የአፍሪካ እግር ኳስ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት መጪው ጊዜ ፈታኝ እንደመሆኑ፤ ፈተናውን በድጎማ ይታለፍ ይሆን? አዲስ ዘመን ግንቦት 25/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=33579
c78f34b4103116c4dadb1411c51ff206
7e5e36b2bb400322dbc8ac93c3165d71
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሄራዊ ፌዴሬሽኖች ቃል የገባውን ገንዘብ ዛሬ ያስረክባል
ስፖርት
የዓለም ህዝብን በአንድ የጭንቀት ቋጥ ውስጥ ባስገባው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት በስፖርቱ ዘርፍ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ማሳደሩ ይነገራል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሀገሪቱ የኮሮና ወረርሽኝ በስፖርቱ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና የሚዳስስ ውይይት ከሀገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች ጋር አድርጎ ነበር። የሁሉም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ውቅር የሆነው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከሀገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች ጋር ካደረገው ውይይት መነሻነት እንዲሁም ፌዴሬሽኖቹም በሰጡት ጥናት መሰረት አንድ ውሳኔ አስተላልፏል። «ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችን የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸው ። ከዚህ በተጓዳኝ የገንዘብ አቅም የሌላቸው ስፖርቶችና ስፖርተኞች ወቅታዊ ብቃታቸው እንዳይወርድ ዕገዛ ይደረግላቸው» ሲል ነበር። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ትናንት በመደበኛ የፌስቡክ ገጹ ፤« የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገባውን የገንዘብ ድጎማ ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚያስረክብ አስታወቋል። በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶችን ለማሳደግና ለማስፋፋት የተቋቋሙ ከ26 በላይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ከማናቸውም ዓይነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተቆጥበዋል፡፡ በኅብረተሰቡ ዘንድ በስፋት የሚዘወተሩት ስፖርቶች ከሚመሩ ፌዴሬሽኖች በቀር ብዙዎቹ በወረርሽኙ ምክንያት ከቢሮ ይልቅ ቤት ውስጥ መዋል ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ ኦሎምፒክ ኮሚቴው የብሄራዊ ፌዴሬሽኖችን ምክረ ሐሳብን መነሻ በማድረግ ቃል የተገባውን ገንዘብ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሩ እና ምክትል ኮሚሽነሩ በተገኙበት ርክክቡ የሚደረግ ይሆናል ብሏል። ኦሎምፒክ ኮሚቴው ሥነ ሥርዓቱን መገናኛ ብዙሃን በስፍራው ተገኝተው መረጃውን በመከታተል ለህዝብ ተደራሽ ያደርጉለት ዘንድ ጥሪውን በመደበኛ ማህበራዊ ፌስቡክ ገጹ አስፍሯል። ሕጋዊ ሰውነት አግኝተው በአገሪቱ በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙ ብሔራዊ ፈዴሬሽኖች የኢትዮጵያ አትሌቲክስና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ካልሆኑ ሌሎቹ በአጠቃላይ ከመንግሥት ቋት በሚለቀቅላቸው አነስተኛ በጀት የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ መንግሥት ከሚመደብላቸው በጀት ይልቅ ከስፖርት ኮሚሽንና ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተሻለ የገንዘብ ድጎማ እንደሚደረግላቸው የሚናገሩት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖቹ፣ ስፖርት በቂ ፋይናንስ ታክሎበት ካልሆነ በስተቀር ብሔራዊ በሚለው ስያሜ ብቻ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴና ውጤት ማስመዝገብ እንደማይችል ጭምር ያምናሉ፡፡ የፌዴሬሽኖቹ አመራሮችም የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለወትሮ በዓመት አንድ ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ ይሰጥ የነበረው የሙያ ማሻሻያ ኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ በወረርሽኙ ምክንያት ስለመቋረጡ ጭምር ይናገራሉ፡፡ አዲስ ዘመን ግንቦት 25/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=33574
7e2a71c9429381ff7be3117ead173eb4
550c564b74472fc797ee8b1b9d39b489
የዘረኝነት ተቃውሞ በስፖርቱ ዓለም ከዋክብት
ስፖርት
ዘመናዊው ኦሊምፒክ በተመሰረተበት ወቅት ከጸደቁ ድንጋጌዎች መካከል በግምባር ቀደምትነት የሰፈረው ሃሳብ ‹‹ስፖርት ለሰው ልጆች ሰላምና ሁለንተናዊ ስብዕና መዳበር እንዲውል ማድረግ›› ይላል፡፡ ይህንንም ከምስረታው (እ.አ.አ 1896) ጀምሮ በውድድር ሜዳዎች ሳይወሰን መልካም ያልሆኑ አሠራሮችን በመቃወምና የህብረተሰቡ ትግል አጋር በመሆን ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባሳተመው መጽሔት ላይ ሰፍሯል፡፡ ለአብነት ያህልም እ.አ.አ 1964 ኮሚቴው አፓርታይድን በመቃወሙ ደቡብ አፍሪካን ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎ ማገዱን ማስታወስ ይቻላል:: ከዚህም ባለፈ የራሱን ቡድን በማቋቋምም ደቡብ አፍሪካዊያኑ በአፓርታይድ ምክንያት ከሚደርስባቸው ጭቆና እስኪላቀቁ ድረስ መታገሉም ተጠቃሽ ነው፡፡ የስፖርት ውድድሮች ሁሉ ራስ የሆነው ኦሊምፒክ ተሳትፎ ዓላማና ግብ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም በተለያዩ ጊዜያት በዓለም ላይ የታዩ ኢ ሰብዓዊ የሆኑ ክስተቶችን በመቃወም፤ የስፖርት መነሻና መድረሻው ሰብዓዊነት መሆኑን አስመስክሯል፡፡ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ሁነቶች ጎን በመቆም ዘመናት የተሻገረው ስፖርት አሁንም የአጋርነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን የሰሞኑ ክስተት አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ዓለም በስልጣኔ እንደመራቀቋ የሰው ልጅም በአስተሳሰቡ እንደመምጠቁ የቆዳ ቀለምን መሰረት ያደረገ የዘረኝነት ጥቃት ሊገፋ ያልቻለ ቋጥኝ ሆኗል፡፡ የቆዳ ቀለምን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችና አስነዋሪ ድርጊት ለዓመታት በስፖርት ሜዳዎችም ጭምር ተንሰራፍተው ታይተዋል፡፡ ሰሞኑን መነሻውን በአንድ ጥቁር ግለሰብ ግድያ ላይ ያደረገውና አሜሪካንን እየናጠ ባለው ተቃውሞም ስፖርት እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ፀያፉን ተግባር በመቃወም ግንባር ቀደም ሆኗል፡፡ ከስፖርቱ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው የቀድሞ ቦክሰኛ ፍሎይድ ሜይዌዘር በሚኒያፖሊስ በጭካኔ የተገደለውን የ46 ዓመቱን አፍሪካ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድን የቀብር ስነ-ስርዓት ወጪ እንደሚሸፍን አስታውቋል፡፡ የከባድ ሚዛን ዓለም ቻምፒዮናው ሜይዌዘር በቲውተር ገጹ ላይ ይህንኑ እንዳሰፈረም ነው ዘ ኢንዲፔንደንት በዘገባው ያመላከተው፡፡ የጎልፍ ተጫዋቹ ታይገር ውድስም በተመሳሳይ በሁኔታው ማዘኑን እንዲሁም የሟች ፍሎይድ ቤተሰቦች እንዲበረቱ በትዊተር ገጹ መልዕክት አስፍሯል፡፡ የፖሊሱንም ተግባር ‹‹ያለ ቦታው ኃይልን የተጠቀመና ዕርምጃውም መስመር ያለፈ›› ብሎታል፡፡ አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ሚካኤል ጆርዳን በበኩሉ በአሜሪካ ያለው ዘረኝነት ስር የሰደደ መሆኑን አስምሮበታል፡፡ ሌሎች የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾችና ስፖርተኞችም በገንዘብና በሃሳብ ከተጎጂው ቤተሰቦች ጋር መሆናቸውን ከመግለጽ ባለፈ አስነዋሪውን ተግባር በመቃወም አጋርነታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ የአሜሪካንን ድንበር ያቋረጠውና ወንዝ የተሻገረው ተቃውሞና ለጥቁሮች ወንድማዊ ስሜትን የማሳየቱ ሂደትም በመላው ዓለም እንደቀጠለ ነው፡፡ በአውሮፓ የሚገኙ በርካታ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጨዋታ እንዲሁም በልምምድ ሜዳዎች ላይ በግልና በቡድን በድርጊቱ የተቃውሞ እንዲሁም ከጥቁሮች ጋር የአብሮነት ስሜታቸውን አንጸባርቀዋል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን የእግር ኳስ ውድድር ከሌሎች ቀድሞ በጀመረው የጀርመን ቡንደስሊጋም ይኸው እንቅስቃሴ ተስተውሏል፡፡ የቦሩሲያ ዶርትመንዱ ተጫዋች ጃደን ሳንቾ ‹‹ፍትህ ለጆርጅ ፍሎይድ›› የሚል ካኒቴራ ከማሊያው ስር በመልበስ ያሳየ ሲሆን፤ ሌሎችም በጉልበታቸው በመንበርከክ ኀዘናቸውን መግለጻቸውን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡ የተቋረጠውን ሊግ ለመቀጠል በልምምድ ላይ የሚገኙት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾችም በተመሳሳይ ሁኔታ አብሮነታቸውን አሳይተዋል፡፡ 29 የሚሆኑ የሊቨርፑል ተጫዋቾች በሜዳቸው አንፊልድ ከጉልበታቸው በመንበርከክ መልዕክት አስተላልፈዋል፡ ፡ የማንቺስተር ዩናይትድ ተጫዋቾቹ ፓውል ፖግባ እና ማርከስ ራሽፎርድም ድምፃቸውን ካሰሙ ተጫዋቾች መካከል ይገኙበታል፡፡ ፖግባ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ‹‹ለፍሎይድና ለመላው ጥቁር ማህበረሰብ የንዴት፣ የኀዘን እና የመከፋት ስሜት ተሰምቶኛል፡፡ ጥቁሮች በእግር ኳስ፣ በትምህርት ቤት፣ በሥራና ሁሉም ስፍራ ይህንን ስሜት በየዕለቱ ያስተናግዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቆም አለበት፤ ዛሬውኑ›› ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ እንግሊዛዊቷ የአጭር ርቀት አትሌት ዲና አሸር ስሚዝ፣ የሜዳ ቴኒስ ኮከቧ ሴሪና ዊሊያምስ፣ የፎርሙላ ዋን ሞተር ስፖርት ተወዳዳሪዎች እንዲሁም ሌሎች የስፖርቱ ሰዎችም በሁኔታው መከፋታቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን የገለጹም የስፖርቱ ዓለም ከዋክብት ናቸው፡፡ አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=33634
4475f876324333f5fe7798bf207f8fcd
a436d05e77ebec652e2df7e593088beb
ኮሚቴው ለፌዴሬሽኖችና የቀድሞ አትሌቶች ድጋፍ አደረገ
ስፖርት
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና ለቀድሞ አትሌቶች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ‹‹የኮቪድ 19 መሰራጨት የዓለምን ስፖርት ቢያጠቃም፣ እንደ ስፖርት እኛም ክፉኛ ብንጎዳም በሥራችን ያሉ ፌዴሬሽኖችን ማገዝ አለብን በሚል ፅኑ አቋም ድጋፉን አድርገናል›› በማለት ትናት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት ለየፌዴሬሽኖቹ በነፍስ ወከፍ ሃምሳ ሃምሳ ሺ ብር የተሰጠ ሲሆን፤ ለቀድሞ አትሌቶች 200 ሺ ብር እንዲሰጥ መወሰኑን ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በስሩ ሃያ አራት ፌዴሬሽኖችና አራት የስፖርት ማህበራት ያሉት ለድጋፉ ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ ታውቋል፡፡ በኦሊምፒክ ኮሚቴው ጽሕፈት ቤት በተካሄደው መግለጫ ላይ የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩርና ምክትል ኮሚሽነሩ አቶ ዱቤ ጅሎ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ባለፈው መጋቢት ወር የሦስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2012
https://www.press.et/Ama/?p=33641
34478a826f311fbf640d8d4970bff80a
b870ed8398d3514062288bfaf0e31a71
አበረታች ቅመም የተጠቀመው አትሌት ቅጣት ተጣለበት
ስፖርት
የኢፌዴሪ ብሄራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ በተረጋገጠበት አትሌት ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ የሌሎች ሁለት አትሌቶች ጉዳይም እየተጣራ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡ የስፖርት አበረታች ንጥረ ነገር በመጠቀም በውድድር ላይ መሳተፉ በተደረገበት ማጣራት የታወቀው አትሌት የአራት ዓመታት እገዳ ተጥሎበታል፡፡ የቅጣት ውሳኔው የተላለፈበት አትሌት ወንደሰን ከተማ የሚባል ሲሆን፤ እአአ ታህሳስ 01/2019 በቻይና በተካሄደውና ዓለም አቀፍ ደረጃ ባለው ሻንዛቢ ማራቶን በግሉ ተሳትፎ ነበር፡፡ በውድድሩ ወቅት በተወሰደው የደምና የሽንት ናሙና በመጠርጠሩ ምክንያት ላለፉት አምስት ወራት የአበረታች ቅመም መጠቀም አለመጠቀሙን ለማወቅ ማጣራት ሲደረግበት መቆየቱን ጽህፈት ቤቱ የላከው መግለጫ ያሳያል፡፡ አትሌቱ በተደረገበት ተጨማሪ የማጣራት ተግባተርም (Cahinone) የተባለና በስፖርት የተከለከለውን አበረታች ቅመም መጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ በዚህም የኢፌዴሪ ብሄራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት በአትሌቱ ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ ወስዷል፡፡ በቅጣቱም የአትሌቱ ጥፋት የመጀመሪያ ደረጃ መሆኑን ከግምት በማስገባት እአአ ከየካቲት 01/2020-የካቲት 01/2024 ድረስ በየትኛውም ሃገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ እንዳይሆን የሚያደርገውን እገዳ ጥሎበታል፡፡ ከእገዳው ባሻገር በቻይናው ውድድር ያስመዘገበው ውጤት እንዲሁም ሽልማቱ እንዲሰረዝም ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑ ታውቋል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ሌሎች ሁለት አትሌቶች ላይም ማጣራት እየተደረገ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ አትሌቶቹ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በግላቸው ተሳትፎ ያላቸው ሲሆን፤ የተከለከሉ የስፖርት አበረታች ንጥረ ነገር መውሰዳቸው ከጥርጣሬ ገብቷል፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ ተጣርቶ ተጠቃሚነታቸው ከተደረሰበት የስም ዝርዝራቸውንና የቅጣት ውሳኔያቸው ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አትሌቶች ራሳቸውን ከኮሮና ወረርሽኝ እንዲሁም ከአበረታች ንጥረ ነገር እንዲጠብቁም ጽህፈት ቤቱ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡ ወቅቱ የዓለም ህዝብ ከወረርሽኙ ጋር ግብ ግብ የገጠመበት እንደመሆኑ ውድድሮች መቋረጣቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በሃገሪቷ በየደረጃው የሚደረገው የስፖርት አበረታች ቅመሞች ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ አበረታች ቅመሞቹን መጠቀሙ የተረጋገጠበትም ይሁን በተለየ መልኩ የህግ ጥሰት በሚፈጽሙ አትሌቶችና ከጀርባ በመሆን በሂደቱ በሚሳተፉ ግለሰቦች ላይ ጽህፈት ቤቱ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁሟል፡፡ አዲስ ዘመን ግንቦት 30/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=33864
a73b20050af93ea17c6eeff0ce0521b6
24c212eb0cbc2bfc4fa9a396312bd847
ኮቪድ-19 በስፖርት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቋመ
ስፖርት
የዓለምን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ወደተለየ አቅጣጫ ያዞረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በስፖርቱ ዓለም ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ተዘርዝሮ የሚልቅ አይደለም። አንዳች ውድድር በዓለም ላይ እንዳይኖር ከማስገደድ ባለፈ የስፖርቱን ዓለም ሽባ አድርጎታል። ብዙ ታቅዶባቸው፣ብዙም ተለፍቶባቸው ለዓመታት በዝግጅት ላይ የነበሩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በትልቅ ኪሳራ የሚካሄዱበት ጊዜ እንዲራዘም ግድ ብላል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በዓለም ዙሪያ ከተንሰራፋ ወዲህ በግለሰብ ደረጃ ካልሆነ በስተቀር የትኛውም የስፖርት እንቅስቃሴ ተገድቦ እንደቆየ ይታወቃል። የቫይረሱ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ መሄዱን ተከትሎም ታላላቅ ስፖርታዊ ውድድሮች በቅርቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለም። ይሁን እንጂ የዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ሊጎች በዝግ ስታድየምም ቢሆን የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሐግብሮች ለማጠናቀቅ በቅርቡ ወደ ውድድር እንደሚመለሱ ተስፋ መስጠታቸው አልቀረም። የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ባለሙያዎች ግን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በትልቅ ደረጃ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እንዳይመለሱ ምክራቸውን ለግሰዋል። በዓለማችን ብሎም በአገራችን በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት የስፖርት ቤተሰቡ መደበኛ እንቅስቃሴውን ገቶ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ ከጀመረ ሰነባብቷ። የስፖርት ቤተሰቡ ወረርሽኙን ለመከላከል ግንዛቤ ከመፍጠር እስከ ደም ልገሳ፤ ከቁሳቁስ እስከ ገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል ፤ በማሳየት ላይም ይገኛል። ወረርሽኙ በዓለም ላይ ከተከሰተና ከተስፋፋ ወዲህ የስፖርቱን ዘርፍ ክፉኛ የጎዳው ሲሆን የአገራችንን ጨምሮ በዓለም ላይ በርካታ ታላላቅ ውድድሮች እንዲቆሙ አስገድዷቸዋል። በተለይም ወረርሽኙን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተወሰዱ እርምጃዎች ስልጠናዎች፣ ውድድሮች ቁመዋል ፤ ስፖርተኛው እና የስፖርት ቤተሰቡ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አጋጥሟቸዋል ። በርካታ የስፖርት ክለቦች የመፍረስ አዳጋ ተደቅኖባ ቸዋል፤ አንዳንዶቹም ለስፖርተኞች ወርሃዊ ደመወዝ እስከ መከልከል ደርሰዋል። በመሆኑም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በወረርሽኙ ወቅት እና ከወረርሽኙ በኋላ ስፖርቱ እንዴት ወደ ነበረበት መመለስ ያስችላል የሚለውን የሚያጠና እና ለመንግሥት የሚያቀርብ ጠንካራ ኮሚቴ መቋቋሙን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ መናገራቸውን የተቋሙ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ ላይ ተዘግቧል። የተቋቋመው ኮሚቴ አብይ እና ቴክኒካል ኮሚቴ ያለው ሲሆን አብይ ኮሚቴው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ጣሰው የሚመራ ይሆና። ቴክኒካል ኮሚቴው ደግሞ በአቶ ዱቤ ጅሎ እንደሚመራ ታውቋል። ኮሚቴው አጠቃላይ የኮሮና ወረርሽኝ በአገራችን ስፖርት ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና እና መፍትሔዎችን በማጥናት ሰነዱን ለመንግሥት የሚያቀርብ ይሆናል። በጥናቱም የሌሎች አገራት ተሞክሮ ምን እንደሚመስል ተካቶ እንደሚቀርብ አቶ ዱቤ አብራርተዋል። ጥናቱን መሠረት በማድረግ መንግሥት ስፖርቱ ለአገራችን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል ።አዲስ ዘመን ግንቦት 27/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=33697
086c95a1ae339991f19b5b45619f6526
30eb40de4b6cb9700e8f81d08acfc01f
በአንድነት ፓርክ፤ ትናንትንም ዛሬንምይመልከቱ
መዝናኛ
 ሳልፍና ሳገድም፤ አሻግሬ ከማየት ባለፈ ዥንጉርጉሩን የደንብ ልብስ ለብሰው፣ መለዮአቸውን አድርገው፣ መሳሪያቸውን አንግበው በበሩ ላይ ሆነው ሌት ተቀን ከሚጠብቁት ጠባቂዎች አልፌ ከቅጥር ግቢው እገባለሁ ብዬ ላስብ ቀርቶ ተመኝቸው እንኳን አላውቅም፤ ብሔራዊ ቤተ መንግስት። እነሆ ዛሬ በወጣት አስተናጋጆች በአክብሮት በግቢው ዘልቄ ከግር እስከራሱ ለመጎበኘት በቃሁ። ጊዜ ለኩሉ ይል የለ። ፍተሻውን አልፈው ወደ ግቢው ከገቡ በኋላ በቅደም ተከተል የሚጎበኟቸውን እና የማረፊያ ቦታዎችን ሙሉ መረጃ የያዘ መግለጫ (ማፕ) ይሰጥዎታል። አንድሺ ብር ከፍለው ከገቡ በአስጎብኚ (በአስረጅ) ይታገዛሉ። የከፈሉት ሁለት መቶ ብር ከሆነ ግን የተሰጥዎትን አቅጣጫ ጠቋሚ በመጠቀም ይመራሉ። በመግቢያ ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ በትላልቅ ፊደላት ‹ኢትዮጵያ› ተብሎ ተጽፏል። ፅሁፉ እንደ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ ተሰቅሎ በራሱ ‹‹እባክዎን ወደ ውስጥ ዝለቁ›› የሚል ያህል ይጋብዛል። ጽሁፉን ሲያነቡትም ልብ ይሞላል። እድሜ ጠገብ ከሆኑት ሀገር በቀል ዛፎች የሚነፍሰው ንጹህ አየርም ጎብኚዎችን ለመቀበል ተባባሪ የሆነ ይመስላል። ምድረ ግቢው፣ በውስጡ የተገነቡት የቤቶች የስነ ህንፃ ውበትና ጥበብ፣ ኢትዮጵያ ታላላቅ ተብለው ከሚጠሩ ሀገራት ጋር ስለነበራት ግንኙነት፣ በታሪክ ተሰንዶ የሚታየው ሁሉ ከአዕምሮ በላይ ነው። በቃላት ብቻም የሚታለፍ አይደለም። ታሪክ ይናገራል። የት እንዳለሁ ትገምታላችሁ በሚል። ብዙ አወራሁ፤ ‹አንድነት ፓርክ› ውስጥ ነኝ! በሉ ተከተሉኝ። የፓርኩን የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ለንግድ ለማረፊያና ለተለያየ አገልግሎቶች የሚውሉ ግንባታዎች፣ የአትክልትና የአበባ ሥፍራዎችን በማዘጋጀት፣ ብቻ በፓርኩ ውስጥ ያስፈልጋሉ የተባሉ ነገሮችን ለማሟላት የሚከናወኑ ተግባራትንም እግረ መንገድ እየተመለከትኩ፣ በሥራው በመሳተፍ ላይ ያሉት የዛሬ ወጣቶች የነገ የዕድሜ ባለጸጋ የታሪክ ተቋዳሽ መሆናቸው ደግሞ ሌላው ድንቅ ታሪክ ነው። የአንድነት ፓርክ በውስጡ ስድስት የቱሪዝም ዋና ዋና መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን፣ እያንዳንዱም ሰፊ ታሪክ ያለው በመሆኑ አለፍ አለፍ እያልኩ የተደመምኩበትንና የታዘብኩትን ብቻ ነው በምናብ በመውሰድ እየሳልኩ የማስተዋውቃችሁ። ወደ ሰው ሰራሽ የጥቁር አንበሳ ዋሻ አመራሁ። ዋሻው ከአለት ድንጋይ ተፈልፍሎ የወጣ እንጂ የእጅ ጥበብ አይመስልም። የዱር እንስሳት መኖሪያ በስፍራው ስለሚገኝ ብቻዬን በዋሻው ውስጥ ለማለፍ አልደፈርኩም። በአጋጣሚ በኤሌክትሪክ ሙያ የተሰማሩ ወጣቶች ለሥራ በውስጡ ሲያልፉ ተከተልኳቸው። በዋሻው መግቢያ ላይ አራት አናብስት አየሁ። ደነገጥኩ። እንደማይደርሱብኝ ስላረጋገጥኩ ፍርሃቴ አልቆየም። እንኳን በአካል በድምጹ ከሚያስፈራው አንበሳ ጋር ከመስተዋት ማዶና ወዲህ በቅርበት ተያየን። ‹‹ማን ይባሉ ይሆን?›› በፓርኩ የሚሰሩት ወጣቶች ወንዱን ቀነኒሳ፣ ሴቶቹን ደግሞ በጥሩነሽና በገንዘቤ ሰየሙልኝ፤ በስያሜው ተሳስቀን ተለያየን፡፡ ዋሻውን አልፌ ወደ ሌላው የታሪክ ሥፍራ ሳመራ በባህላዊ የመድኃኒት ተክል የተሞላ አካባቢ ደረስኩ። ለምች መድኃኒት የሚወሰደው ዳማከሴ፣ ጤና አዳም፣ ጠጅ ሳር፣ ሮዝመሪኖ ሌሎችም እይታን በሚስብ ቦታ ተተክለዋል። ተክሎቹን እንዳለፍኩ ካየኋቸው የነገሥታትና የመሪዎች ፎቶግራፎች መካከል የንግሥት ዘውዲቱን ፎቶግራፍ ማየቴ ለጾታዬ እንዳደላ አድርጎኛል። የስምንተኛው መሪ የዶክተር ዐብይ አህመድ ፎቶ ግራፍ ግን አልተካተተም። የትናንቱን ብቻ እንድናስታውስ ታስቦ ይሆን? አለፍኩት። በጉብኝቴ ውስጥ ‹ላንቺያ› የተባለችው የአፄ ኃይለ ሥላሴ መኪናም ትኩረትን በሚስብ እይታ ቦታ ነበረች። ገና ከፋብሪካ የወጣች እንጂ እድሜ ጠገብ አትመስልም። ባለ8 ማዕዘኑ እና የእንቁላል ቅርጽ ጉልላት ባለው የዳግማዊ ሚኒልክ ቤተመንግሥት ውስጥ ትኩረቴን የሳበው በግድግዳው ውስጥ የተቀበረው ከብረት የተሰራው የድምጽ ማስተላለፊያ ቱቦ ነበር። ምድርና ፎቅ ሆነው በድምጽ መልዕክት የሚለዋወጡበት መሳሪያ መሆኑ ባስጎብኝዋ ሄለን በቀለ ገለፃ ባይደረግልን ኑሮ የውሃ መውረጃ የሚመስለን ጥቂት አንሆንም ነበር። አፄ ሚኒልክና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ የተለያየ መኝታ ክፍል እንዳላቸው በአስጎብኝዋ ገለጻ ሲደረግልን ቀልደኛ ጎብኚ ደንገጥ ብሎ ‹ለየብቻ ነው የሚተኙት› በማለት ጠየቀ። መልስ ባይገኝም ሳቅ ፈጥሯል። የመጀመሪያው የስልክ ቤትም በዚሁ የሚኒልክ ቤተመንግሥት ውስጥ ይገኛል። ስምንት ሺ ኪሎ ሜትር ይረዝማል ተብሎ በሚገመተው ጠፍር ጣሪያው የተሰራው፣ ሰባት መስኮቶችና 12 በሮች ያሉት፣ እስከ ሶስት ሺ እንግዶች የሚያስተናግደው የግብር አዳራሽ ልዩ ድባብ አለው። ሥራውን ለኪነ ህንጻ ጠቢባን ትቸዋለሁ። በዚህ ክፍል ውስጥ ከዛሬ አምስት አስርት ዓመት በፊት በቀድሞ ተግባረዕድ በአሁኑ እንጦጦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ተብሎ በሚጠራው ትምህርት ቤት ሲማሩ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት በማምጣታቸው ተጋብዘው ከአፄ ኃይለሥላሴ ዲፕሎማና ሽልማት የወሰዱት አቶ ነጋሽ ገብሬ የታሪክ አጋጣሚው ያኔ ለሽልማት አሁን ደግሞ ‹አንድነት ፓርክ› ተብሎ ተሰይሞ ለጉብኝት አብረን ታድመናል። ለአቶ ነጋሽ መታደማቸው ልዩ ስሜት ነበር ያሳደረባቸው። በጉብኝታቸው የተደመሙበትንና በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የቀረጿቸውን ወደ ሚኖሩበት አሜሪካን ሜሪላንድ ሲመለሱ ለወዳጆቻቸው ለማሳየት ቸኩለዋል። የማስተዋወቅ ኃላፊነትም እንዳለባቸው አጫውተውኛል። የሌሎች ጎብኚዎችን ስሜትም እየተጋራሁ ስለነበር ‹‹ለካ እንዲህ ነው እንዴ ያረጁ ቤቶችን ነበር የጠበኩት›፣ ‹ጉብኝቱ በግማሽ ሰዓት የሚያልቅ ነበር የመሰለኝ›፣ ‹እድሜ ሰጥቶን ይሄን ማየታችን ዶክተር ዐብይ እግዚአብሄር ይስጠው› የሚሉ በደስታ የሚገለጹ ስሜቶችን ነበር የሰማሁት፤ ከገጽታቸው ያነበብኩት ይህንኑ ነው። በምስል፣ በድምጽና በጽሁፍ ተቀነባብሮ አፈታሪክ በተባለው ክፍል ውስጥ የሚጎበኘው ደግሞ በጽሁፍ ከምገልጽላችሁ በላይ ነው። በአንድነት ፓርክ ውስጥ ከበጎ እስከ ክፋት የተፈጸሙ ነገሮች ቢቀርብልዎትም ታሪክ ነውና ያለፈውን በትዝታ የወደፊቱን ደግሞ በአንድነት ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያስተሳስሩ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ባህልና ወግ የሚያንጸባርቁ እሴቶችም ይገኛሉ፤ አበቃሁ።አዲስ ዘመን ጥቅምት27/2012 ለምለም መንግሥቱ
https://www.press.et/Ama/?p=22108
785fdbd629b6989a9b3604b85f73603b
b0f3f15da6770a931ef4b9947ecf883a
ነፃ ጠረጴዛ ፈልጉ!
መዝናኛ
በጠዋት ነው ቢሮ የገባሁት፤ በወሩ የመጨረሻ ቀናት ላይ ነኝና የሚደርሰኝን ገቢዬን ከወጪዬ ጋር እያሰላሁ ነው:: የቤት ኪራይ፤ የምግብ፤ የትራንስፖርትና ሌሎች ለመኖር አስፈላጊ የሚባሉ ወጪዎችን አሰላለሁ። ደመወዜንም አሰብኩት:: ኦ! አምላኬ ለካስ ደመወዜ ስንት እንደሆነ አላውቅም:: ማሰቡ ስለከበደኝ ተውኩት:: ወጪና ገቢዬን ሳመዛዝን ስላስጨነቀኝ ማሰቡን ለመርሳት ሞከርኩ:: የምር ግን ደመወዛችሁ ስንት እንደሆነ ታውቃላችሁ ወዳጆቼ? እኔ ግን ደመወዜ ስንት እደሆነ አላውቅም:: ”እንዴት?” ካላችሁኝ ምክንያት አለኝ:: ቆዩማ፤ እንዴት ላውቀው እችላለው እኔ ዘንድ ደርሶ አያውቅማ፤ ያልቀረበን ነገር ማወቅ ይከብድ የለ? ከእጄ ሳይደርስ እኮ ነው ተከፋፍሎ የሚያልቀው፤ ሳሳዝን! ሰርቼ፤ ጥሬ ግሬ የማስረክባቸው ብዙ ጠባቂዎች አሉኝ::እኔ ምለው!? እኔ ወጪና ገቢዬን እያሰብኩ ከምጨነቅና ግራ ከምጋባ ሰዎችን ላስቸግር መሰለኝ:: እስኪ አስታውሱኝ ስንት ነበር? የቤት አከራዬ፤ የመስሪያ ቤቴ ሻይ ክበብ፤ የምመላለስባችሁ ታክሲዎች፤ እኔ ሰፈር ያለኸው ባለ ሱቅ፤ የምትቀፍሉኝ ጓደኞቼ፤ እስኪ አንዴ ሰብሰብ በሉና ወርሐዊ ወጪዬን ንገሩኝ:: እኔ ምንም ገቢ የለኝማ:: የተቀበልኩትን መስጠት፤ የተሰጠኝን ለእናንተ ማድረስ ስለሆነ ገቢዬን አላውቅም:: እናንተ ከእኔ የምታገኙት ገቢ ምን ያህል እንደሆነ ደመር.. ደመር አድርጉና ንገሩኝ:: ከወጪ ይልቅ ገቢ መደመር ደስ ይል የለ? አዎን!በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ሰኞ ላይ የሥራ “ሙዴ” ቶሎ አይቆሰቆስም:: ልምድ ይሁን እንጃ ብቻ ሰኞ ዕለት ብሰራም የሰራሁት ለእኔም አያጠግበኝም:: በጠዋት ቢሮዬ ገብቼ ኮምፒዩተሬን መነካካት፤ መረጃዎችን ማየት ቀጠልኩ። በሳምንቱ ውስጥ በምሰራቸው ተግባራት ምንነት ላይ በወጉ እያሰብኩ ቆዬቼ፤ ሥራ ከመጀመሬ በፊት ቡና ጠጥቼ ነቃ ለማለት ወደ ሻይ ክበብ ሄድኩ:: ዛሬ ቀኔን ብሩህ ላደርገው አስቤያለሁ:: ደስ የሚል ቀን ማሳለፍ ፈልጌያለሁ:: ሰላም መናፈሻ ውስጥ የተመለከትኳቸውን ባልደረቦቼን ተቀላቀልኳቸው:: ሙግት ይዘዋል። አንዱ የሌላውን ሐሳብ ይነቅፋል፤ የራሱን ደግሞ ያስከትላል:: የሚከራከሩበት ርዕሰ ጉዳዩ አንድ፤ አተያያቸው ግን ለየቅል ሆኖ ላለመግባባት በሚመስል ሁኔታ በቃላት ይፋለጣሉ:: ጉዳዩ የሰለቸኝ የፖለቲካ ጉዳይ ነው:: መከራከሪያው ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳይ ነው:: ይሄ ክርክር ተደጋገመና በየሄድኩበት የሚወራው እሱ ሆነና ሰለቸኝ:: ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚያነሳና የሚጥለው ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ ሆነና አሰለቸኝ:: ወሬው ሁሉ ፖለቲካ የተቀላቀለበት ሆነና እረፍት ፈለኩ:: ቦታዬን የቀየርኩት በምክንያት ነው። ክርክሩን ለመራቅ፤ ተሳካልኝና በቀየርኩት ጠረጴዛ ላይ ሌላ ርዕሰ ጉዳይ ተይዟል:: “ኡፉፉ…ግልግል”፤ እዚህ በሚወራው ሌላ ርዕሰ ጉዳይ ደስ ተሰኘሁ:: ሰሞኑን በወጣ መጽሐፍ ላይ ነው ውይይቱ፤ አጋጣሚ እኔም መጽሐፉን አንብቤው ስለነበር አፍታም ሳልቆይ ሐሳቡ ሲገባኝ መሳተፍ ጀመርኩ:: ትንሽ ሐሳብ እንደተለዋወጥን በመጽሐፉ ላይ ያለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ “የሆነ ወገን የሚነካ ነው” መባሉ ከዚያው ከተወያዮች መካከል ተነሳ:: ይሄኔ ጠረጴዛው ላይ ያለው ውይይት መልኩ ሊቀይር እንደሆነ ገባኝና ተከፋሁ:: በተቻለኝ መጠን ርዕሰ ጉዳዩን ልቀይረው ፈለግሁ። አልተሳካልኝም:: ጭራሽ ጉዳዩ ከርሮ የተናገረውን ልጅ ትርጓሜ ተቃራኒ የሆነ ሐሳብ ያለው ነበረና “እነሱ ድሮም…” ማለት ሲጀምር ያዘዝኩትን ቡና ሳልጨርስ ከመቀመጫዬ ተነስቼ መዝናኛ ክበቡን ለቅቄ ወደ ቢሮዬ አመራሁ:: ቢሮዬ ገብቼ ሥራ ከመጀመሬ በፊት የዓለምን አዳር ለማየት ማህበራዊ ገፆችን ከፈትኩ:: ማየት ከሰለቸኝ ርዕሰ ጉዳይ ውጭ የተጻፈ ጽሑፍ፣ ማየት ከመረረኝ ዜና ውጭ ብዙም አዲስ ነገር አጣሁ:: ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ምንም ባይኖርም ነፃ የሆነ ሐሳብ ግን ሞልቷል:: የት ሄዶብን ይሆን ነፃ የሆነው ሃሳባችን እንዲህ የሌሎች ሃሳብና አተያይ ጥገኛ ሆነን የቀረነው ጎበዝ!? እንዴት ነፃ መውጣትና በራሳችን መልካም እሳቤ መጓዝ፤ እኛው በምናምንበት በጎ አመለካከት መዝለቅ አቃተን? በጣም ናፈቀኝ፤ የናፈኩት ግን ከአይኔ የራቀ፤ የጠፋብኝ ዘመዴ ወይም ወዳጄ አይደለም:: በጣም አሰኘኝ፤ ያሰኘኝ የምበላው ምግብ ወይም የምጎነጨው ጣፋጭ መጠጥ ግን አይደለም:: የናፈቀኝ ነፃ ጠረጴዛ ነው። መደማመጥ ያለበት፤ ፍሬ ያለው ሐሳብ የሚለዋወጡበት፤ ከፖለቲካዊ ክርክር ነፃ የሆነ ጠረጴዛ፤ ሰዎች ሁሉ የራሳቸውን ሥራ እርግፍ አድርገው መደበኛ “ሥራዬ ፖለቲከኛነት ነው፤ ወሬዬም ከዚያ የማይሻገር” ብለው ከያዙት አሰልቺ ንትርክ ነፃ የሆነ ጠረጴዛ ናፈቀኝ፤አሁን ላይ እኮ ብሶብናል ወገን፤ እንዴት ሁላችንም ፖለቲከኛ ሆነን እንችለዋለን? ግዴለም የምግብና የመጠጥ ማጀቢያችን፤ የጉዞና የአብሮነት ቆይታችን ማጣፈጫ ሌላ መሆኑን ትተን ይሄው ጉዳይ ይሁን፤ ግን እንዴት መሰማማት ተሳነን? ምንም አይነት መደማመጥ በሌለበት የቃላት ልውውጡ ድንበር አልፎ ለጠብ የሚዳርግ እየሆነ ነው:: ታዲያ ይሄ አይሰለችም ወገን? ሃሳብ በመሞገት ማሸነፍ ሳይሆን፤ የራስን ስሜት ብቻ የሚከተሉበትን፤ መግባባት የራቀውን ክርክር ጠላሁ::ነፃ የሆነ ሰው ታውቃላችሁ? ነፃነትን ተጎናጽፎ ንፅት፤ ፅድት ብሎ ህይወቱን የሚመራ ሰው የምታውቁ ከሆነ አገናኙኝ:: አመላክቱኝና ይሄ ሰው ነፃ መሆንን እንዲያጋባብኝ ልወዳጀው፤ እንዴት ይሆን የሚኖረው? ምን አይነት ሐሴት ተጎናፅፎ፤ ምንኛ ከፍ ያለ የመንፈስ እርካታ በውስጡ ናኝቶ? የቱስ አይነት ሐሴት በውስጡ ሰርፆ፤ ሰላም አስገኝቶ ይሆን? ሲያስቀና! እንዲህ ያለ ሰው የማግኘት ህልም አለኝ:: ወዳጆቼ ምሩኝና ላግኘው እባካችሁ! ነገሮችን ሚዛናዊ ሆኖ የሚያይ፤ በስሜት ከመፍረድና ከመወሰን ይልቅ አስልቶ የሚጓዝ ሰው ፈልጉልኝማ፤ ነፃነቱን ተጎናፅፎ ሐሳቡን የሚያራምድ ሰው ተወደደ አይደል? ታዲያ ወዳጆቼ እንዲህ ያለ ሰው መናፈቅ ይነሰኝ? ነፃ የሆነ ባጣ፤ ሁሉም በራሱ ነፃነቱን አጥቶ፤ አርነቱን አስነጥቆ በተገኘበት ዘመን ነፃ የሆነ ሰው መፈለጌ ትክክል አይደለሁ?ነፃ መሆን ውስጣዊ ሰላም ይሰጣል:: ነፃነት ውድ ቢሆንም ሊጎናፀፉት ግድ የሚል የሐሴት መድረክ ነው:: ነፃነት የደስታ ጥግ ላይ የሚያደርስ ብቸኛ መንገድ ነው:: ግን ደግሞ አብዛኞቻችን ነፃነታችንን የምናጣው በኛው በግል ተግባራችን ነው:: ውዶቼ የምናስበውን ነፃነት ነፃ ሆነን ካላሰብነው ነፃነቱ በራሱ ባርነት ነው:: አርነት ውስጥ የማይጎናፀፉት ድል የለም:: አቦ! ከአድልኦ፤ ከበደል፤ ከምቀኝነት ነፃ ያውጣን! አበቃሁ:: ቸር ያሰማን! አዲስ ዘመን ጥቅምት28/2012 ተገኝ ብሩ
https://www.press.et/Ama/?p=22165
b6595143a5bfc7b773e347d18ab4eddd
0891d2ddb29e46baecd847562998e2ca
‘‘ነፃነት… ነፃነት…. ነፃነቴን ስጡኝ”
መዝናኛ
 አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በአዕምሮዬ ሁለት ሐሳቦች ይመላለሳሉ፤ ነፃነት እና ባርነት። ይህንኑ አወርዳለሁ አወጣለው ፤ ታዲያ በመሐል አንድ ሐሳብ ብልጭ አለልኝ። ከማን ነው ነፃነት የሚመጣው? ባሪያ ያደረገኝ ማን ነው ? ሌላ የሐሳብ መንገድ… ሌላ መልስ ፍለጋ… ለነገሩ አዕምሮ አታስብ አይባል። በዚህ መሐል ነው በአንድ ወቅት ከቡክ ወርልድ ድረ ገጽ ያነበብኩት ታሪክ ትዝ ያለኝ።በድሮ ጊዜ አንድ ታላቅ የነፃነት ታጋይ በተራራማው የሀገሪቱ ክፍል እየተጓዘ በአንድ ማደርያ ቦታ ለተወሰነ ጊዜ ለማሳለፍና ለማረፍ ወሰኖ ጎራ አለ። በዚያ ቤት ውስጥ አንድ የሚያምር ተናጋሪ ወፍ (ፓሮት) በወርቅማ የወፍ ቤት ውስጥ ተቀምጦ “ነፃነት፣ ነፃነት፣ ነፃነት” እያለ ይጮሐል። ድምፁንም ጋራ ሸንተረሩ እያስተጋባው ተመልሶ “ነፃነት … ነፃነት …” በሚል ድምፅ አካባቢው ይሞላል።የነፃነት አርበኛው እንዲህ ሲል አሰበ” በህይወቴ በዚህ ዓለም ስዞር ብዙ የፓሮት ወፎችን በፍርግርግ ብረት ውስጥ ተቆልፎባቸው ሲኖሩ አይቻለሁ። እንደዚህ ወፍ ግን የነፃነት ናፍቆት ያለው በየደቂቃው ነፃነቴን እያለ የሚጮህ አይቼ አላውቅም !” ቀኑን በዚህ ወፍ እየተገረመ ውሎ መምሸት አልቀረም መሸ። የቤቱ ባለቤት በጊዜ እንቅልፍ ወስዶት ቤቱ ጭር እንዳለ ቀኑን በወፉ ሲገረም የዋለው በተፈጥሮው ለነፃነት ታላቅ ክብር የሚሰጠው ሰው አንድ ሐሳብ ብልጭ አለለትና ተነስቶ ወደ ወፉ ቤት በመሄድ የብረት ቤቱን በር ከፈተለት። ወፉ ግን ወደተከፈተለት በር በመቅረብ ፋንታ ወደኋላ እየሸሸ “ነፃነት፣ ነፃነት፣ ነፃነት… “ ሲል ጮኸ፤ አርበኛውም “አሁን በሩ ተከፍቶልሐል፣ ና ውጣ በሰማዩ እንደፈለክ ብረር የነፃነትን አየር ተንፍስ ሁሉም ተኝተዋልና የሚይዝህ የለም፤ አምልጥ አለው” ተናገሪዋ ወፍ ግን ይበልጥ ከመውጫ በሩ እየሸሸ በፍርግርግ ብረቶቹ መታከኩን ቀጠለ ግራ የተጋባው ሰው እጁን ወደወፉ ቤት ሰዶ ሊይዘውና እንዲወጣ ሊረዳው ሞከረ ወፉም ባለ በሌለ ሃይሉ እጁን ቧጨረው ነከሰው እንደዛም ሆኖ ጎትቶ አውጥቶ እንዲበር ለቀቀው እና ክፉኛ የተነከሰው እጁ ህመሙ ቢሰማውም በሠራው መልካም ተግባር ግን ልቡ ረክቶ ተኛ በጠዋት ሲነሳ የተቀበለው የፓሮት ወፉ ድምፅ ነበር “ነፃነት ነፃነት ነፃነት” ይላል አርበኛውም አንድ አለት ላይ ወይም ዛፍ ላይ ተቀምጦ እንደልማዱ እየጮኸ ነው ብሎ እያሰበ ከመኝታው ተነስቶ ወደ ወፉ ቤት ሲመለከት ባየው ነገር ደነገጠ ወፉ በሩ በተከፈተው እስር ቤቱ (ጎጆው) ውስጥ ሆኖ “ነፃነት ነፃነት ነፃነቴን ስጡኝ” ብሎ እየጮኸ ነው።አሁን ባለችው ኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ይኸው ነው፤ በተከፈተ በር በሚረዳ እና በሚያግዝ መሪ የመጣውን ሰላም ማጣጣም አቅቶን የምንባክነው። ልክ ከላይ እንዳለችው ፓሮት ከነበርነበት ፍርግርግ ወይ ከእርዳታ አልወጣን፣ አሊያም በራሳችን ጉልበት እንዲያው ፍርግርግ ውስጥ ሆነን በመጋጨት አካላችን ጎዳን እንዲሁም ለነፃነታችን ዋጋ የከፈሉ ሊረዱን የተዘረጉ እጆችን አደማን፤ ጎዳን። እስቲ ወደ ልቦናችን እንመለስ የምንፍልገው ምንድነው? ጭራስ የሌለን ነው? ወይስ የጎደለን? ለሁሉም እንደ ፓሮቷ ከመጮሐችን በፊት እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችን እያነሳን እንጠይቅ፤ ታላቁ መጽሐፍ “የጻድቅ አይኖች ወደራሱ ናቸው” ይላል። ይህም ማለት ራስን በመግዛት ራስን ማየት ብዙውን ጥያቄና የምንፈልገውን ሰላም ይመልስልናል።ስለዚህም ለምንጠይቀው ጥያቄ መልሱ ያለው እኛው ጋር መሆኑን መረዳት ይኖርብናል፤ ወዳጆቼ እንደሚታወቀው ነፃነት አንፃራዊና ከእንቅስቃሴ ጋር የተዛመደ ነው። የሰው ልጅ ሲፈጠርም ሆነ ሲኖር ነፃ አይደለም። እድገቱና አኗኗሩ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አጥሮች የተከበበ ነው። ያሻውን፣ የፈለገውን ማድረግ አይችልም። ውስንነት አለበት። አንድም በባህልና በሃይማኖት ሌላው ደግሞ በሰው ሰራሽ ሕግጋት ተጽዕኖ ሥር ነው።በሌሎች ላይ በደል ያደረሰ ሰው ፈፅሞ በነፃነት መኖር አይቻልም። የመኖር መለኪያ ደግሞ ነፃነት ነው። የመሥራት፣ የማደግ ዋልታ ደግሞ ስምምነት ነው። ምድር የሁሉም ቤት ናት። ሰውም ምድርን በጊዜያዊነት ይገለገልበታል። አርሶ፣ ዘርቶ፣ አጭዶ፣ ወቅቶ ይጠቀምበታል። አምርቶ፣ ፈብርኮ፣ ለብሶ፣ አጊጦ ይታይባታል። ተወልዶ፣ አድጎ፣ አግብቶ፣ ወልዶ ተዛምዶ ይኖርባታል። ግን በነፃነት አይኖርም። ምክንያቱም ነፃነት በተፈጥሮ ሳይሆን በፍለጋ የሚገኝ በመሆኑ ነው። ነፃነት ያለ ተጠቃሚነት ባርነት ነው። በድህነት ሥር የሚዳዳ ሰው ነፃ ይሁን አይሁን ትርጉም አይሰጠውም። ለምን የቅድሚያ ቅድሚያ ተጠቃሚ አይደለምና። የነፃነት መለኪያ በስምምነት ላይ የተተከለ ተጨባጭነቱ የተረጋገጠ የተጠቃሚነት ውህደት ድምር ውጤት ነው። ሰው በተፈጥሮና በሰው አዕምራዊ ውጤት የሚገኝ ጥቅም ተጠቃሚ ካልሆነ ነፃነት አልባ ከመሆኑም በላይ የዲሞክራሲ ሥርዓት የለውም። ተጠቃሚነት ባልስፈነበት ዲሞክራሲ ይጎረብጣል። ዲሞክራሲ ከፍላጎት ጋር ካልተጣጣመ ጉዳት ነው። ምክንያቱም ዲሞክራሲ የነፃነት ጥቅም ማስከበሪያ መሣሪያ በመሆኑ ከማህበረሰብ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል። ፍትሐዊ ጥቅምና ለውጥ ያለፍትሐዊ ነፃነት ዋጋ ቢስ ከመሆነም በላይ የጋርዮሽ ስምምነት መርሆች ያፈርሳል። በጋራ ለመኖርና ለመበልፀግ የጋራ መርሆ ያስፈልጋል። የመርሆች ተፈፃሚነት ማሳያ አንዱ ሰብአዊ ብልፅግና ነው።ሁሉም የተሰጠውን በአግባቡ ቢጠቀም፤ የጎደለ ካለ ከራሱ ለራሱ እየሞላ ምክንያቱም አገር ማለት ጠያቂው (ግለሰብ፣ ማህበረሰብ)፣ ተጠያቂው (መንግሥት)፣ መሬቱ፣ ጋራው፣ ሸንተረሩ… ስለሆነ…. የኮንትራት ህይወቱ እስክታልቅ በነፃነት በሰላም ለሰላም እየኖሩ ማለፍ….. ትውልድ ይመጣል …ትውልድ ያልፋል። መልካም ዕለተ ሰንበት !!አዲስ ዘመን ጥቅም30/2012 አብርሃም ተወልደ
https://www.press.et/Ama/?p=22254
ff490b97df1704d73733a1e8f8b2cb40
7e87f7ef3b202a0728b5a33d4f995337
ከፅዳት ሠራተኝነት እስከ አብራሪነት
መዝናኛ
ህይወት በብዙ ውጣ ውረዶች የተፈተነች ናት። ገሚሶቹ ዛሬን ተቸግረው ነገን በተስፋ ሲያልሙ የተቀሩት ደግሞ በአቋራጭ ለመክበር ድንጋዮችን ሲፈነቅሉ ይስተዋላል። ተስፋን የሰነቁ ሁሉ በመንገዳቸው የሚገጥማቸውን እንቅፋት ገሸሽ በማድረግ የነገ መንገዳቸውን ያመቻቻሉ። ችግር ከጉዟቸው እንዳያደናቅፋቸው ከወዲሁ የሰነቁትን የሞራል ስንቅ በመከላከያነት ይጠቀማሉ። ውጣ ውረዶችን እንዲሁም ከፍታና ዝቅታን የህይወት አንድ አካል አድርጎ በመቁጠር በተስፋ ወደፊት መገስገስን የሚለማመዱት እነዚህ የነገ አላሚዎች መነፅራቸው ስኬትን እንጂ ውድቀትን አይመለከትም።ሁሌም የሚያስቡትና የሚያልሙት ትናንትናቸው አስተማሪ፣ ዛሬያቸው ተስፋ እና ነጋቸው ብሩህ መሆኑን ብቻ ነው። ከፍታ የሚጀመረው ዝቅ ብሎ ከተቀመጠው መወጣጫ መሆኑን ጠንቅቀው የሚያውቁት እነዚህ ግለሰቦች ከግባቸው ለመድረስ ለአፍታም ሲያመነቱ አይስተዋልም። እሾሁን ለቅመው፣ ጠጠሩን ጠርገው፣ አቧራውን አራግፈውና የችግር አጥርን ጥሰው ከፍ ብለው መታየት ቀጣዩ የህይወት ጉዞ መሆኑን በመረዳት ለዚህ ጉዞ ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው ይታጠቃሉ። በሀገራችንም ሆነ በአለማችን በተለያዩ ጊዜያት እጅግ ዝቅ ካለ የኑሮ ደረጃ ተነስተው አለምን የሚቀይር ሃሳብ፣ እውቀትና ገንዘብ ያካበቱ በርካታ ግለሰቦችን ታሪክ አይተንም ሰምተንም እናውቃለን።ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የጠቀሙና አንቱታን ያተረፉ ግለሰቦች የስኬት መንገዳቸው ሲመረመር የአንዳንዶቹ ለማመን ሲከብድ ይስተዋ ላል። የስኬታማ ግለሰቦች የራስ ጥረትና ትጋት ተጨምሮበት በሩጫቸው ውሃ ያቀበሏቸው አጋሮ ችም የስኬት መሰላልን የሚያስጨብጡ ተምሳሌቶች ናቸው።ዛሬ ከወደ ናይጄሪያ የተሰማ የአንድ ስኬ ታማ ግለሰብን ታሪክ ልናስነብባችሁ ወደናል። ኢንተለጀንስ ዶት ኮም እንዳስነበበው ግለሰቡ አብራሪ የመሆን ህልሙን የጀመረው ከአውሮፕላን የፅዳት ሰራተኝነት ተነስቶ ሲሆን አሁን ላይ የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ለመሆን በቅቷል። የዚህ ስኬታማ ሰው አጭር የስኬት ታሪክ እንደሚከተለው ነው።ናይጀሪያዊው መሀመድ አቡበከር ከዛሬ 24 አመታት በፊት የአውሮፕላን ፅዳት ሰራተኛ ሆኖ ነበር ካቡ ኤር በተባለ ኩባንያ የተቀጠረው። በካዱና ፖሊ ቴክኒክ ለመማር አመልክቶ የትምህርት ማስረጃዎቹን በጊዜው ባለማስገባቱ ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው መሀመድ ምንም እንኳን የስራ ምርጫው ባይሆንም ለረጅም ጊዜ ያለስራ መቀመጥን ባለመምረጥ ነበር በካቡ ኤር ውስጥ ለመቀጠር የወሰነውና በአውሮፕላን የፅዳት ሰራተኝነት ስራ የጀመረው።የመሀመድ ደመወዝ እጅግ ዝቅተኛ ማለትም በቀን 200 የናይጀሪያ ናይራ ወይም 0.5 የአሜሪካን ዶላር በመሆኑ ማንም ሰው በስራው ላይ ይቆያል ብሎ አልገመተም ነበር፤ ነገር ግን ይህ ባለሩቅ ተስፋ ሀልመኛ ወጣት በስራው በመግፋት ብቻም ሳይሆን ውጤታማ ሰራተኛ በመሆን ከጊዜ ቆይታ በኋላ በሜዱግሪ ኤር በግራውንድ ስታፍነት ተቀጠረ።ራሱን በዲሲፕሊን የታነፀና ውጤታማ ሰራተኛ ያደረገው መሀመድ በአቪየሽን ዘርፍ በርካታ እውቀቶችን እንዲያካብት አስቻለው። በቀጣይም መሀመድ በካቦ ኤር የበረራ አባልነት ላይ የማመልከት እድል አግኝቶ ስራውን መስራት ጀመረ። በዚህ ስራም ስምንት አመታትን በወር 17 ሺህ ናይራ ወይም 47 የአሜሪካን ዶላር እየተከፈለው ሰራ። ከዚህ በኋላም በበረራ ተቆጣጣሪነት ወደ ኤሮ ኮንትራክተርስ ተዛወረ።የስራ ታታሪነቱና ፈጣን አዕምሮው በድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ትኩረትን መሳብ የቻለው መሀመድ ወርሀዊ ደመወዙ በወር ወደ 170 ሺህ ናይራ ወይም 469 የአሜሪካን ዶላር ከፍ አለ። ይህንን ማመን ያቃተው መሀመድ የመጀመሪያ የደመወዝ ክፍያ ቼኩን ሲቀበል ገንዘቡን ለመመለስ ሞክሮ እንደነበር ተገልጿል።የሚያገኘውን ደመወዝ በዋዛ ፈዛዛ ማጥፋት ያልፈለገው መሀመድ ቁጠባ በመጀመር አብራሪ የመሆን ህልሙን እውን ለማድረግ ጉዳዩን ለዋና ዳይሬክተሩ አስረዳ፤ ዳይሬክተሩም የመሀመድን ሃሳብ በመደገፍ ድጋፍ ተደርጎለት በካናዳ የግል አብራሪነት ፈቃድ ለማግኘት ትምህርቱን ጀምሮ በስኬት አጠናቀቀ።መሀመድ ወደ ናይጀሪያ ከተመለሰ በኋላ የንግድ አብራሪነት ፈቃድ መያዝ ቢፈልግም በቂ ገንዘብ ስላልነበረው ይህንን ማሳካት አልቻለም፤ ይሁን እንጂ ችግሩ ይህንን ህልሙን እና ጠንካራ መንፈሱን ሳይጎትተው ወደ ፊት በመገስገስ የድርጅቱን ም/ዋና ዳይሬክተር ድጋፍ በመጠየቅ ታማኝነቱና ስራ ወዳድነቱ በኩባንያው ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግለት ረዳው።ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ካናዳ በመሄድ የንግድ አውሮፕላን አብራሪነት ስልጠናውን አጠናቆ ወደ ትውልድ ሀገሩ ናይጀሪያ ተመለሰ። ከ24 አመታት ጠንካራና ውጤታማ የስራ ጊዜያት በኋላ መሀመድ በአዝማን ኤር ውስጥ የአውሮፕላን አብራሪ ሆኖ በመቀጠር ህልሙን እውን አደረገ። አሁን መሀመድ በዚህ አየር መንገድ ውስጥ በአብራሪነት ስራውን እየሰራ ይገኛል፡አዲስ ዘመን ኅዳር 1 / 2012 በድልነሳ ምንውየለት
https://www.press.et/Ama/?p=22304
ca6f5cf77fedc16587c7bd2f453f5bcd
8f2dcea4c8ff5fb0ab9188b332f8db37
ሙስና በሀገር ህልውና ከደቀነው አደጋ አንጻር መገናኛ ብዙሀን ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት እንደሚገባ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዳማ፦ መገናኛ ብዙሀን ሙስና በሀገር ህልውና ላይ ፈጥሮት ከነበረው አደጋ አንጻር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት እንደሚገባ የፌደራል የስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ጸጋ አራጌ “ ስነ ምግባርን በመገንባትና ሙስናን በመከላከል ረገድ የሚዲያ ተቋማት ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ በአዳማ ከተማ ትናንት በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንዳስታወቁት፤ በሀገሪቱ የተንሰራፋው የሙስና ችግር የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት ሆኗል። በቅርቡ ሀገሪቱ የገጠማትና ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈላት ችግር ከሙስና ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጸጋ፤ ችግሩ በሙስና የተዘፈቀ ስርአትን ለማስቀጠል፣ በሙስና የተሰበሰበን ሀብት ያለ ችግር ለመጠቀም ካለ ከፍ ያለ መፈለግ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። ይህ ችግር ለአንድ ተቋም ወይም ለተወሰኑ የመገናኛ ብዙሀን የሚተውት ሳይሆን የሁሉንም የመገናኛ ብዙሀን ንቁ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመው፤ ሁሉም ችግሩ ሊያስከትል ከሚችለውና አስከትሎት ከነበረው አደጋ አንጻር ሊመለከቱት ይገባል ብለዋል።ከጋዜጠኝነት ሙያ አንጻር የሙስና ጉዳይ ወቅታዊ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ጸጋ፤ ጉዳዩን አጀንዳ በማድረግ መገናኛ ብዙሀን በስፋትና በጥልቀት ሊሄዱበት እንደሚገባ አስታውቀዋል። ወቅታዊነቱም የችግሩ ስፋት እስኪቀንስ ሊቀጥል የሚችል እንደሆነ አመልክተዋል። ኮሚሽኑ ከ2008 ዓ.ም በፊት የማስተማር ፣የመከላከል ፣የመመርመርና የመክሰስ ተቋማዊ ኃላፊነትና ህጋዊ ስልጣን እንደነበረው አመልክተው፤ በአሁኑ ወቅት ተልእኮው በማስተማርና በመከላከል ላይ እንዲያተኩር መደረጉን አስታውቀዋል። የመመርመርና የመክሰስ ስልጣንና ኃላፊነት ለፖሊስና ለአቃቤ ህግ መሰጠቱንም ጠቁመዋል። በሀገሪቱ በተቋሞች መካከል ካለው በአግባቡ ያለመናበብ ባህል አንጻር ለጸረ-ሙስና ትግሉ ስኬት ኮሚሽኑ ስራዎችን በራሱ ተቋማዊ አቅም “ከመነሻ እስከ መጨረሻ” የሚሄድበት ስልጣንና ኃላፊነት ቢሰጠው የተሻለ እንደሚሆን አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት ኮሚሽኑ ከተሰጠው ተልእኮ አንጻር በአብዛኛው ከምርመራና ከክስ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ስሙ እንደሚነሳ አመልክተው፤ ከምርመራና ከክስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከፖሊስና ከአቃቤ ህግ ጋር የተያያዙ ስለመሆናቸው አመልክተዋል። ኮሚሽኑ ቀደም ባሉት ጊዜያት በአብዛኛው ስኬታማ አለመሆኑ የሚነገረው እንደ ተቋም የተሰጠውን ተልእኮ የመወጣት ችግር ስለነበረበት ሳይሆን ከነበረው ሰፊ ጣልቃ ገብነት የተነሳ እንደነበር ገልጸው፤ በተቋሙ ላይ የነበረው ጣልቃ ገብነት ግላዊ ፍላጎትን እስከማስፈጸምና መበቃቀያ እስከመሆን የደረሰ እንደነበር አስታውቀዋል።የመገናኛ ብዙሀን የምርመራ ዘገባዎችን በስፋት በመስራት በጸረ ሙስና ትግሉ ውስጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችሉ ያስታወቁት ኮሚሽኑ፤ መገናኛ ብዙሀን ይህን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ለዚህም ኮሚሽኑ የሙያ ክህሎት ስልጠናዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆኑ ለመስጠት ፈቃደኝ መሆኑን አስታውቀዋል። የምርመራ ጋዜጠኝነት ሙስናን ለመከላከል የሚደረገውን ትግል በማቅለል ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክተው፤ የምርመራ ጋዜጠኝነት የኮሚሽኑን ፣ የፖሊስና የአቃቤ ህግን ስራዎች በማቅለል የሚኖረው አዎንታዊ ጠቀሜታ የጎላ ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ ከመገናኛ ብዙሀን ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ያስታወቁት ኮሚሽነሩ፤ መገናኛ ብዙሀን የሙስና ጉዳይ ችግሩ ለተወሰነ አካል የሚተው አለመሆኑን በአግባቡ ተገንዝበው አብረውት እንዲሰሩ ጠይቀዋል። በውይይት መድረኩ ላይ” ሙስናን ለመዋጋት የመገናኛ ብዙሀን ሚና “በሚል ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቄ በበኩላቸው፤ መገናኛ ብዙሀን ሙስናን በመከላከል ሂደት ውስጥ ከፍ ያለ ሙያዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። በቀደሙት ጊዜያት መገናኛ ብዙሀን በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ማለፋቸውን ያመለከቱት ዋና ዳሬክተሩ፤ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀር በአደባባይ የምርመራ ጋዜጠኝነት ለሀገሪቱ እንደማያስፈልግ ለመናገር የተደፈረበት እውነታ እንደነበር አስታውሰዋል። ይህም ጋዜጠኞች ላይ የነበረው ጫና የቱን ያህል ከባድ እንደነበር ማሳያ ነው ብለዋል።የምርመራ ጋዜጠኝነት ከፍ ካለ ኃላፊነት የሚመነጭ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ፣ በሙያው ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ጌታቸው፤ በስራው የሚሰማራው ጋዜጠኛም ከሚያነሳቸው ጉዳዮች ክብደት አንጻር ለአደጋ የሚያጋልጡ እንደሆኑ አመልክተዋል።ይህም ሆኖ ግን ልንገነባው ካለነው የዴሞክራሲ ስርአት አንጻር የምርመራ ጋዜጠኝነት ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልግ በመሆኑ መገናኛ ብዙሀን ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት እንደሚገባ አመልክተዋል።መገናኛ ብዙሀን እስካሁን በመጡበት ሂደት ከምርመራ ጋዜጠኝነት አንጻር የጀመሯቸው ስራዎች መኖራቸውን አመልክተው፤ ስራዎች በህዝብ በሰፊው ተቀባይነት እንደነበራቸው አስታውቀዋል። እነዚህን ጅማሮች አጠናክሮ በመቀጠል ያለባቸውን ሙያዊ ኃላፊነት መወጣት የሚያስችል የተሻለ ዝግጁነት መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ባለሙያዎች እና አመራሮች ተሳትፈዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 27/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38879
096056600d57553cead695a25fc307d6
42a89dae8ef854cce06d8e6ee0b25d01
የበቆሎ ምርት በሄክታር ከ42 ኩንታል በላይ መድረሱ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሰላማዊት ውቤአዳማ፦ በአሁኑ ወቅት ከሦስት ዋና ዋና የግብርናው ዘርፍ መርሐ ግብሮች አንዱ በሆነው የድህነት ቅነሳ የበቆሎ ምርትን በሄክታር 42 ኩንታል ማድረስ መቻሉ ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ጥሩ ሂደት ላይ መሆናችንን እንደሚያሳይ ተገለጸ። የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ከትናንት በስቲያ በአዳማ ከተማ ለግማሽ ቀን በተካሄደና አጠቃላይ ግብርናው ያለበትን ሁኔታ የዳሰሰ ፓናል ውይይት ላይ እንዳስታወቁት፤ ባለፉት 20 ዓመታት የበቆሎ ምርት ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል።ዕድገቱ በአንደኛውና በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ጭምር የተገኘ ነው ያሉት ዶክተር ማንደፍሮ፤ እስከ አምና ድረስ በሄክታር የተገኘው 42 ነጥብ 4 ኩንታል መሆኑንም ጠቅሰው፤ በዚህ ዓመት ሲጨመር ደግሞ በሄክታር የሚገኘው የበቆሎ ምርት ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችልም ጠቁመዋል።የምርት ዕድገቱ ምን ያህል ለድህነት ቅነሳ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ የሚያመለክት መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በዓለም ላይ በሄክታር በአማካኝ ያለው የበቆሎ ምርት ዕደገት 58 ኩንታል መሆኑንም ተናግረዋል።እንደ ሀገር በሄክታር የደረስንበት 42 ነጥብ 4 ኩንታል ከዓለም ጋር የሚቀራረብና ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ በዚህ ሰብል ጥሩ ሂደት ላይ ነን ማለት የሚያስችል መሆኑን ዶክተር ማደፍሮ ጠቁመው፤ የስንዴ ምርትም ባለፉት አስር አመታት በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉንና አሁን ላይ ከራሳችን አልፈን ወደ ውጪ ለመላክ በዘመቻ መርሐ ግብር መልክ እየሰራን ነው ብለዋል። ‹‹የአሁን ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ መርሐ ግብር የድህነት ቅነሳን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም አመጣጥኖ የሚሄድ ነው›› ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ግብርና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ የተጀመረውን ድህነት ቅነሳ ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ጠቁመዋል።የድህነት ቅነሳ መተግበር ሲጀምር የነበረው አጠቃላይ አገራዊ የምርት መጠን 69 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ ሲሆን በሁለተኛው 181 ሚሊዮን ኩንታል፣ በሦስተኛው ደግሞ 270 ሚሊዮን ኩንታል መድረሱን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ዘንድሮ ደግሞ 414 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚታሰብና ይህም የምርት አሰባሰብ ሂደቱ በየጊዜው በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መሄዱን ማሳያ ነው ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 27/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38881
7a099b232ac855f71d04d73815cdaa61
e44f6ab286a0ed4c2f746d9750dd442c
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ20 ሚሊዮን ብር የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዛየፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ20 ሚሊዮን ብር የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዛ
ሀገር አቀፍ ዜና
– ለግድቡ በአምስት ወራት ከ888  ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧልበጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማገዝ የ20 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዥ ፈፀመ። የቦንድ ግዢው የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲያድግ መንግሥት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ የተደረገ መሆኑን ትናንት በተደረገው የርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል። የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን በመወከል ቼኩን ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ያስረከቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ረሻድ ከማል ናቸው። የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለተለያዩ ሀገራዊ ልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውሰው፤ ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ በልዩ ሁኔታ በመመልከት ሰፊ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት የሆነው የህዳሴው ግድብ እስኪጠናቀቅ ድረስ ኮርፖሬሽኑ ታሪካዊ አሻራውን ማኖሩን አበክሮ ይቀጥላል።ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው የገንዘብ አስተዋጽኦዎች ለገበታ-ለሀገር ፕሮጀክት 20ሚሊዮን ብር፣ ለመቄዶኒያ የአረጋዊያን መኖሪያ ግንባታ 5 ሚሊዮን ብር፣ የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል እየተደረገ ላለው ሀገራዊ ርብርብ 10 ሚሊዮን ብር፣ ባለፉት 6 ወራት የኮርፖሬሽኑ ተከራይ ደንበኞች 50% የቤት ኪራይ ክፍያ እንዲቀነስላቸው በማድረግ 400 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፤ ለገበታ-ለሃገር የተሰጠውን 20 ሚሊዮን ብር ጨምሮ በድምሩ 455 ሚለዮን ብር ገደማ ወጪ በማድረግ ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሚገኝም አቶ ረሻድ ጠቁመዋል።የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሔ በበኩላቸው፤ የሕዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ ወሳኝ ነው ብለዋል። ኮርፖሬሽኑ ያደረገው ድጋፍ ለሌሎች ተቋማት አርአያ የሚሆን ተግባር እንደሆነ የጠቆሙት ዶክተር አረጋዊ፤ ሁሉም ተቋማትና ዜጎች ተሳትፎአቸውን በማሳደግ ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚደረገውን ርብርብ እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል።ባለፉት አምስት ወራት ብቻ መላ ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥና በውጪ ከ790 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ ድጋፍ ማደረጋቸውንና በ8100 የገቢ ማስገኛ ፕሮግራምም ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍቅርተ ታምር ገልጸው፤ ይህም በግድቡ ግንባታ ታሪክ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መሆኑን አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 27/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38880
36313869fe3e18eb5a11f9a84b2c852b
808c5762711e84121e49097498e5f2df
የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ ተራዘመ
ስፖርት
በመጪው ጥቅምት ወር በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ ሊካሄድ የነበረው የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ በኮሮና ቫይረስ ስጋት መራዘሙ ታውቋል። የሁሉም አገራት ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች የሚሳተፉበት ወሳኝ ጠቅላላ ጉባዔ በመጪው ጥቅምት አጋማሽ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር። የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎቹ እንዲሁም ጠቅላላ ጉባዔውን የምታዘጋጀው ደቡብ ኮሪያ የስፖርትና ኦሊምፒክ ኮሚቴ በጋራ በሰጡት መግለጫ ጠቅላላ ጉባዔው የተራዘመው በሁሉም ባለድርሻ አካላት ፍላጎት መሆኑ ታውቋል። እኤአ የ1988 ኦሊምፒክ የሆነችው ሴኡል ከተማ ይህን ታላቅ ጠቅላላ ጉባዔ በመጪው 2021 የፈረንጆች ዓመት እንደምታስተናግድ ይገለፅ እንጂ መቼ እንደሆነ ቁርጥ ያለው ቀን አልተነገረም። ጠቅላላ ጉባዔው የሚካሄድበት እርግጠኛው ቀን ወደ ፊት እንደሚገለፅም ተጠቁሟል። ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎቹ ወሳኝ በሆነው ጠቅላላ ጉባዔ ሃሳባቸውን እንዲያቀርቡ በማህበሩ በኩል ሪፖርቶችና አጀንዳዎች ቀደም ብሎ ተሰጥቷቸው ነበር።‹‹ጠቅላላ ጉባዔው በተያዘለት ጊዜ ባለመካሄዱ ቅር ተሰኝተናል፣ ይሁን እንጂ ዓለም አሁን ካለችበት ወቅታዊ ችግር አኳያ ጠቅላላ ጉባዔውን ማራዘማችን ትክክለኛ ውሳኔ ነው›› በማለት የማህበሩ ፕሬዚዳንት ተወካይ ሮቢን ሚሼል ለዓለም መገናኛ ብዙሃን በተሰራጨው መግለጫ ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል። የፕሬዚዳንቱ ተወካይ አክለውም፣ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ የነበሩት የደቡብ ኮሪያ ስፖርትና ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባውን በታቀደለት ጊዜ ለማስተናገድ ያደረጉትን ጥረትና ስብሰባው ይራዘም ሲባል ሃሳቡን ለመቀበል ላሳዩት ቅንነት ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም ጠቅላላ ጉባዔው እዚያው ሴኡል ከተማ እንዲካሄድ ከአገሪቱ የስፖርት ኃላፊዎች ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል። በኮሮና ቫይረስ ፈጣን ስርጭት የተነሳ በርካቶቹ የዓለማችን አገራት የዜጎቻቸውን እንቅስቃሴ ከመግታት ጀምሮ ዓለም አቀፍ ጉዞዎች ላይ እገዳ እንደጣሉ ይታወቃል። የደቡብ ኮሪያ ስፖርትና ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ሊ ኪ ሁንግ በጠቅላላ ጉባዔው የሚሳተፉ የተለያዩ አገራት የስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት የጤናና ደህንነት ሁኔታን ከግምት በማስገባት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተስማሙት መሰረት ስብሰባው እንዲራዘም መደረጉን ገልፀዋል። ጠቅላላ ጉባዔውን በተራዘመው መርሐግብር መሰረት ለማስተናገድም አገራቸው ፍቃደኛ መሆኗን ተናግረዋል። ‹‹ዓለም አሁን የገጠማት ችግር የኦሊምፒክ እንቅስቃሴን ያስቆማል የሚል እምነት የለንም›› ያሉት ፕሬዚዳንቱ በቀጣይ የዓለማችን ስፖርት እጣፋንታ ላይ የሚወስኑ የሁለት መቶ ስድስት አገራት ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎችን ልዑካ ቡድን አባላት ለመቀበልና የተሳካ ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ እንደሚዘጋጁም ቃል ገብተዋል። ከዚህ ቀደም የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ የሚካሄደው በማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መካከል እንዲሁም በማህበሩ የሥራ ባልደረቦች መካከል ነበር። በዚህ ጠቅላላ ጉባዔ እኤአ ከ2014 ወዲህ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔውን በሚያካሂድበት ከተማም ትልቅ ዓመታዊ የሽልማት ሥነሥርዓት እንደሚያደርግ ይታወቃል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንቶች በዚህ ጠቅላላ ጉባዔ ተገኝተው ንግግር የሚያደርጉም ሲሆን በዓለማችን ስፖርቶች እንዲሁም ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ዙሪያ ምክክር ይደረግበታል። ማህበሩ ባለፈው ዓመት ኳታር ዶሃ ላይ ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሼክ አሕመድ አል ሳባህ የፍርድ ሂደት መቋጫ እስኪያገኝ ድረስ ሮቢን ሚሼል የማህበሩ ፕሬዚዳንት ተወካይ ሆነው እንዲያገለግሉ መወሰኑ ይታወቃል። ባለፈው ወር ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች የባህር ዳርቻ የስፖርት ውድድሮች በኮሮና ቫይረስ ስጋት እኤአ እስከ 2023 እንዲራዘም መወሰኑ አይዘነጋም። የዓለምን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ወደተለየ አቅጣጫ ያዞረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በስፖርቱ ዓለም ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። አንዳች ውድድር በዓለም ላይ እንዳይኖር ከማስገደድ ባለፈ የስፖርቱን ዓለም ሽባ አድርጎታል። ብዙ ታቅዶባቸው፣ብዙም ተለፍቶባቸው ለዓመታት በዝግጅት ላይ የነበሩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በትልቅ ኪሳራ የሚካሄዱበት ጊዜ እንዲራዘም ግድ ብሏል። ጃፓን ካለፉት ሰባት ዓመታት በላይ ከፍተኛ ዝግጅት ስታደርግበት የቆየችው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በትልቅ ኪሳራ ለአስራ ስድስት ወራት የተራዘመና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ታላቅ የስፖርት መድረክ ነው። ይህን ታላቅ የስፖርት መድረክ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እየተናነቀውም ቢሆን ለ2021 ለማራዘም ተገዷል። ኦሊምፒኩን ጨምሮ በርካቶቹ ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮችና ጉባዔዎች ወደ ቀጣይ ዓመት የተሸጋገሩት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በቁጥጥር ስር ይውላል በሚል ተስፋ ነው። ይሁን እንጂ በዓለም ላይ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከተስፋ በስተቀር የቫይረሱ ስርጭት በጊዜ የሚገታ ወይም ፈውስና ክትባት በዚህ ጊዜ እውን ይሆናል የሚያስብል እንዳልሆነ መታዘብ ይቻላል። ይህንን ከግምት ያስገቡት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ ኦሊምፒኩ የቫይረሱን ስጋት ለማምለጥ በአሥራ ስድስት ወራት ቢራዘምም ከቫይረሱ ተፅዕኖ ሊያመልጥ እንደማይችል ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማመልከታቸው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ግንቦት 12/2012
https://www.press.et/Ama/?p=32747
b47b1d7702e6c139ef56e701f645ec19
4a980366ef66ea523c47939ecb1a465e
ከአካላዊ ውድድር የተነጠለው ስፖርት በቴክኖሎጂ ተጠናክሯል
ስፖርት
ስፖርት የማይካተትበት ዘርፍ የለም፤ ቴክኖሎጂም እንዲሁ።ሁለቱም ዘርፎች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በመቆራኘት ህይወትን በማቅለል ለዘመናዊው ዓለም የጎላ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።ከዚህ ባለፈ አንዱ ለሌላኛው ቁልፍ ጉዳይ መከወኑም አልቀረም።በልምድ ይካሄድ የነበረው ስፖርት በሳይንስና ቴክኖሎጂ በመደገፉ፤ ዘመናዊውን ስፖርት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ለይቶ ማሰብ በዚህ ወቅት አዳጋች ሆኗል።በቴክኖሎጂ የታገዙ ፈጠራዎች መበራከትም የስፖርተኞችን ብቃት በማሳደግ እንዲሁም የስልጠና ሂደቱን በማቃለልም ዘርፉን ትርፋማ ማድረግ ችሏል።የዘመኑ ስትንፋስ የሆነው ቴክኖሎጂ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ስፖርትን ተቀላቅሎ በቁጥር የማይተመኑ ለውጦችን አስገኝቷል።በስፖርት ትጥቅና የስልጠና ቁሳቁስ፣ ውድድሮችን በቀጥታ ለደጋፊዎች በማስመልከት፣ በውድድር ሜዳዎች ተገኝቶ ለመመልከት ትኬት የመቁረጫ አማራጭ፣ የስፖርት ሜዳዎች ሁለገብና ዘመናዊ እንዲሆኑ፣ ከውድድር አጨራረስ እንዲሁም ዳኝነት፣ የስፖርተኞችን መረጃና ውጤትን በመመዝገብ፣ ከዚህ ቀደም የነበረን ውድድርና ብቃት ለመገምገም፣ ስለ ስፖርቱ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎችን ለመከታተል፣ ስፖርተኞችን ከደጋፊዎቻቸው በማገናኘት፣ ንጹህ ስፖርትን ለማካሄድና በስፖርት የሚፈጸሙ የረቀቁ ወንጀሎችን ለማጣራት (ከአበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ)፣ ከጉዳት ለማገገም (ስፖርት ህክምና)፣ በትልልቅ ጨዋታዎችና ውድድሮች ከአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ ችግር እንዳይገጥም እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ግኝቶችንም አበርክቷል። በዋናነት እነዚህ ተጠቀሱ እንጂ ቴክኖሎጂ በእያንዳንዱ ስፖርት ለእያንዳንዱ ሂደት እየተወጣ ያለው አስተዋጽኦ ይዘርዘር ቢባል አዳጋች ነው የሚሆነው።ለአብነት ያህል ግን ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በጉልህ ከታዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል በሁለት ተወዳጅ ስፖርቶች የታዩትና የስፖርት ቤተሰቡን ቀልብ የሳቡትን ማንሳት ይቻላል።በአትሌቲክስ ስፖርት በመሮጫ ጫማ ላይ የነበረው የቴክኖሎጂ እገዛ የሰው ልጅ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ አዲስ ታሪክ እንዲያስመዘግብ አድርጓል።በቪዲዮ የታገዘ ዳኝነት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መተግበሩም እስካሁን በእግር ኳሱ ነጥረው ያልወጡ ጉዳዮች እንዲስተዋሉ ያደረጉ ሆነዋል። የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ዓለምን በእጅጉ እያስጨነቀ ባለበት በዚህ ወቅት ደግሞ ቴክኖሎጂ ለስፖርቱ እጅጉን አስፈላጊ መሆኑ በተግባር እየታየ ይገኛል።በተለይ ከስፖርታዊ ውድድሮች መሰረዝና ‹‹ከቤት አትውጡ›› ትዕዛዝ ጋር በተያያዘ ስፖርተኞች እንዲሁም ስፖርት ወዳዶች ቴክኖሎጂን እንደ አማራጭ ይዘውታል።የስፖርት መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ድረ ገጾችም የውድድሮች አለመኖርን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ውድድሮችን በድጋሚ በማስታወስ ላይ ይገኛሉ።ስፖርተኞች በበኩላቸው በግላቸው የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች በተለያዩ ድረ-ገጾች ለሌላው ህዝብ በማጋራት ላይ ናቸው።አሰልጣኞችም ስፖርተኞች በቤታቸው ሲቆዩ እንዳይዘናጉ በተለያዩ ቴክኖሎጂ አፈራሽ መንገዶች ስልጠናቸውን ቀጥለዋል።የውድድር አዘጋጅ አካላት ደግሞ በአካል ስፖርተኞችን ማፎካከር ባይችሉም በስልኮች ላይ በሚጫን መተግበሪያ ውድድሮችን እያካሄዱ ይገኛሉ።የ ‹‹በቤት ቆዩ›› ቻሌንጆችም በዓለም ላይ እየተበራከቱ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ነው። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያም እየተለመደ ያለ ሲሆን፤ ስፖርተኞች፣ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ማህበራት እንዲሁም ስፖርቱን የሚመሩ አካላት የብዙሃን መገናኛዎችንና ድረገጾችን በመጠቀም ህዝቡን ተደራሽ እያደረጉ ናቸው።አሰልጣኞችም በማህበራዊ ድረ-ገጾች ከሰልጣኞቻቸው ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ። የስፖርትና የስልጠና ባለሙያዎችም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚከወን ህብረተሰቡን ግንዛቤ እያስጨበጡና እያነቁም ይገኛሉ።የኢትዮጵያን ስም ከገነኑ አትሌቶች እኩል የሚያስነሳው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ አማካኝነት የሩጫ ውድድር እያካሄደ ይገኛል።‹‹ቨርቹዋል ሬይስ›› የሚሰኘው ይህ የውድድር ዓይነት እየተለመደ ያለና በርካቶች ተሳታፊ እየሆኑበትም ይገኛሉ፡፡በወቅታዊው ሁኔታ ስፖርት ለጊዜውም ቢሆን ከአካላዊ እንቅስቃሴ ጋር መለያየቱን ተከትሎም ከስፖርት ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ድርጅቶች ገበያቸው እየደራ መሆኑም ተስተውሏል።ፎርብስ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰራው ዘገባ፤ ስፖርተኞች በቤት ውስጥ ከመቆየታቸው ጋር በተያያዘ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መከወኛ መሳሪያዎች ፍላጎትና ግዢ ጭማሪ አሳይቷል።በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ የስፖርት ቁሳቁስ አምራች ከድረ-ገጹ ጋር በነበረው ቆይታ፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ባልታየ መልኩ የፈረንጆቹ 2020 ከገባ በኋላ ጥያቄው መበርታቱን ጠቁሟል።በተለይ የኦሊምፒክ ተሳታፊ አትሌቶች፣ ቡድኖች እና ታዋቂ አትሌቶች ደግሞ ቀዳሚ ፈላጊዎች መሆናቸው ታውቋል። ዘ ኢኮኖሚክስ ደግሞ የዓለም ስፖርት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በወራት ውስጥ ከአካላዊ እንቅስቃሴ ወደ ዲጂታል (በቴክኖሎጂ የታገዘ) መቀየሩን አመላክቷል።ይህ ‹‹ኢ-ስፖርት›› የተሰኘው ውድድር በኮምፒዩተር የሚካሄድ ሲሆን፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የሚያሸልም ነው።በዚህም ምክንያት የተሳታፊዎቹ ቁጥር በእጥፍ እያደገ መሆኑ ተረጋግጧል።ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነም፤ እአአ በ2019 የተሳታፊዎች ቁጥር 443 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከ2018 ጋር ሲነጻጸር በ12 ከመቶ ጭማሪ ያሳየ ነው።በዚህ ዓመት ደግሞ በዚህ ጨዋታ ተሳታፊ ከሆኑ ሰዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱም ታውቋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 17/2012 ብርሃን ፈይሳ አጫጭር ዜናአትሌቷ እርዳታ አድርጋለች ኢትዮጵያን በኦሊምፒክ፣ በዓለም ቻምፒዮና፣ በዳይመንድ ሊግ እንዲሁም በሌሎች ውድድሮች በ5 እና 10 ሺ ሜትሮች የሜዳሊያ ባለቤት ያደረገችው አትሌት አልማዝ አያና እርዳታ አድርጋለች።አትሌቷ ከባለቤትዋ ጋር በመሆን ከአሁን በፊት የጀመረችውንና ከ30 በላይ የሚሆኑ አቅመ ደካማ አዛውንቶችን ለሁለተኛ ጊዜ የለገሰች ሲሆን፤ ከ50 ለማያንሱ ገቢያቸው አነስተኛ ለሆነና ወደፊት ሀገራቸውን ሊያስጠሩ ለሚጥሩ አትሌቶችም እርዳታውን ማበርከቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በድረ ገጹ አስነብቧል።ተረጂዎች እያንዳንዳቸው እንዳንድ ካርቶን ፓስታ፣ 5 ሊትር ዘይት እና 50 ኪሎ ዱቄት አግኝተዋል።ከዚህ ባሻገር የኮሮና ወረርሽኝን (ኮቪድ 19) ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት የሚውል 150 ሺህ ብር ለድጋፍ አስተባባሪው አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ አስረክበዋል።አትሌቷ በጥቅሉ 267ሺ ብር እርዳታ ነው ያደረገችው።ሁለተኛ ዙር የምገባ መርሃ ግብር ተጀመረ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስና እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች እንዲሁም ቢጂአይ ጋር በመሆን ለአንድ ወር የሚቆይ የምገባ መርሃ ግብር ማካሄዳቸው የሚታወስ ነው።አሁን ደግሞ ለአንድ ወር የሚቆይና በአዲስ አበባ ስቴድዮም ዙሪያ የሚገኙ ችግረኞችን የሚያቅፍ ሁለተኛ ዙር የምገባ መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሯል።ምገባውን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስና እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች፣ ከኢትዮጵያ ጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት፣ ከወጋገን ባንክ፣ ከቢጂአይ ኢትዮጵያ እና ከአቶ አብነት ገብረመስቀል ጋር በመተባበጀር የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በቀጣዩ ወር ይመለሳል በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጡ የሊግ ውድድሮች እየተመለሱ መሆኑ ይታወቃል።ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግም በቀጣዩ ወር የሚቀጥል መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ ልምምድ የጀመሩት ክለቦቹ ከ17 ቀናት በኋላ ውድድር የሚጀምሩ መሆኑን የፕሪምየር ሊጉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሪቻርድ ማስተር አረጋግጠዋል።በሊጉ ከሚሳተፉ 20 ክለቦች ውስጥ ባሉ ተጫዋቾች በተደረገው የኮቪድ 19 ምርመራ በሶስት ክለቦች ውስጥ የሚገኙ ስድስት ተጫዋቾች ላይ መገኘቱም የሚታወስ ነው።አዲስ ዘመን ግንቦት 17/2012
https://www.press.et/Ama/?p=33056
a060178ceb7c8e5b0a79d72d83373cb1
4bd04bb6d2cdcbd8afed2fbdd019ec6b
ስፖርት የአብሮነትና አጋርነት መገለጫ ነው !!
ስፖርት
ስፖርት ከአካላዊ እንቅስቃሴና ከመዝናኛነት ባለፈ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል፡፡ በተለይም ዓለም በኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ምክኒያት ጭንቅ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት ስፖርትና የስፖርቱ ማህበረሰብ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት ረገድ ትልቅ ስራ እየሰራ ይገኛል።ስፖርት የአብሮነትና አጋርነት መገለጫ የመሆኑን “ሃቂቃ” ባለፉት አምስት ወራት በዘርፉ የተከናወኑ ሰብዓዊ ድጋፎች በቂ ማስረጃ ተደርገውም ይነሳሉ። በሀገራችንም በተመሳሳይ በስፖርቱ ዘርፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ ሰፊ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ መናገር ይቻላል። በዘመነ ኮሮና በስፖርቱ ዘርፍ በኩል ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ሲደረግ የነበረውን ርብርብ ዘወር ብሎ መመልከቱ ለዚህ እማኝ ይሆናል።በሀገራችን ኮሮናን ለመከላከል ሲደረግና እየተደረገ ባለው ርብርብ የስፖርት ዘርፍም በዚህ እንቅስቃሴ ቀዳሚ ተሰላፊ ነበር። የስፖርት አመራሮች፣ የስፖርት ማህበራት፣ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው፤ መልእክት በማስተላለፍ፣ በየቤታቸው ላሉ ዜጎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማሰራት፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ የምግብና ሌሎች መገልገያዎችን በመለገስ እንዲሁም በሌሎች ተግባራት ላይ እየተንቀሳቀሱ ነው። ዘርፉን የሚመራው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ይህን እንቅስቃሴ በማስተባበር እንዲሁም እንደ አንድ ባለድርሻ አካል በሚጠበቅበት ሁሉ የራሱን ድርሻ በመወጣት ረገድ የነበረው ሚና ደግሞ ግዙፍ ነበር። ኮሚሽኑ ወገናዊነቱን ለመወጣት እየሄደ ያለባቸው ርቀቶች ደግሞ የበለጠ እንዲመሰገንና እንዲደነቅ ያደረገ መሆኑ የተለያዩ አካላት እያነሱ ይገኛሉ። በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድን በመጋቢት መጨረሻ “ማዕድ ማጋራት” ሲሉ በሰየሙት የድጋፍ መርሃ ግብር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመረው ተግባር በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል። በስፖርት ኮሚሽኑ አስተባባሪነት ሚያዝያ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም በይፋ የተጀመረው “ማዕድ ማጋራት” መርሃ ግብሩ ስፖርት የአብሮነትና የአጋርነት መገለጫ መሆኑን በተጨባጭ ያሳየ ተግባር እንደሆነ ብዙዎች መስክረውለታል።የስፖርቱን ዘርፍ ወገናዊነት የሚንፀባረቅበት ማህበራዊ ኡደት እንደሆነ በመርሃ ግብሩ 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር ያህል በመመገብ ባከናወነው ተግባር አስመስክሯል።ስፖርት ኮሚሽኑ የተለያዩ የስፖርት ተቋማቱና አጋር ድርጅቶችን አስተባብሮ ለአንድ ወር ያህል ሲያከናውነው የነበረው የምገባ መርሃ ግብር ባሳለፍነው እሁድ ተጠናቋል።የስፖርቱ ማኅበረሰብ በዘመነ ኮሮና ህዝባዊነቱን በተጠናከረ መልኩ ያሳየ መሆኑን የመጀመሪያው ዙር የተጠናቀቀው የምገባ መርሃ ግብር አስረጂ ይሆናል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ግን «ስፖርት የአብሮነትና የአጋርነት መገለጫ እንደመሆኑ ማህበራዊ ኃላፊነት የመወጣቱ ተልዕኮ የሚቋጭ ሳይሆን በአዲስ ምዕራፍ የሚጀመር ነው »ሲል ሁለተኛውን ዙር የምገባ መርሃ ግብር መጀመሩን አስታውቋል። በስፖርት ኮሚሽን ፊት አውራሪነት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቢጂ አይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር 300 ጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር ያህል በምገባ መርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውሷል።የስፖርት ቤተሰቡ ወገናዊነት በተግባር የሚያሳየውን መርሃ ግብር በመሆኑ ኮሚሽኑ ሁለተኛ ወር ለማስቀጠል ሌሎች አጋዥ አካላትን በማስተባበር እንዲሁም ድጋፎችን ማሰባሰብ በመቻሉ መርሃ ግብሩ ለቀጣይ አንድ ወርም ተጠናክሮ ሊቀጥል መቻሉ ተነግሯል። በስፖርት ኮሚሽኑ ፊት አውራሪነት ተግባራዊ የተደረገው የምገባ መርሃ ግብር በሁለተኛ ዙር ላይ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት፣ ወጋገን ባንክ እንዱሁም አቶ አብነት ገብረ መስቀል አጋርነታቸውን ያሳዩበት ሆኗል። ግንቦት 15 ቀን 2012 ዓ.ም አቶ ኤሊያስ ሽኩር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋው አረጋ እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተጀምሯል። ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር መርሃ ግብሩን ሲያስጀምሩ፤«የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተወሰዱ እርምጃዎች ስፖርተኛው እና የስፖርት ቤተሰቡ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አጋጥሟቸዋል ።ችግሮች ቢያጋጥሙም ስፖርተኛው እና የስፖርቱ ቤተሰብ በአንድ በኩል ከአለው ላይ በመቀነስ ለሌሎች በመደገፍ፤ በሌላ በኩል ሌሎች አካላትን በማስተባበር ወረርሽኙ ሊያስከትለው የሚችለውን ማህበራዊ እና ሰብዓዊ ቀውስ ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ »ሲሉ ዓለም በኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ምክኒያት ጭንቅ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት ስፖርትና የስፖርቱ ማህበረሰብ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት በኩል እያበረከተ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። አቶ ኤልያስ በሌላ በኩል «በመዲናችን ኗሪ ለሆኑ 300 ጎዳና ተዳዳሪዎች ለአንድ ወር ያህል በምገባ መርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ሲደረግ የነበረበት ሁኔታ መቋረጥ እንደሌለበት በማመን ሁለተኛውን ዙር እንዲጀመር ተደርጓል። በመሆኑም ሁለተኛው ዙር የምገባ ፕሮግራም መንግስት የጎዳና ተዳዳሪዎች በዘላቂነት ህይወታቸውን እንዲመሩ እሲኪያመቻች ድረስ በእኛ ደረጃ ለአንድ ወር የምገባ ፕሮግራሙን ለማራዘም ነው »ያሉት። አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በበኩላቸው፤ ወረረሽኙን ለመከላከል ከጅምሩ ጀምሮ ቀጣይነት ባለው የስፖርት ቤተሰቦች እያደረጋችሁት ላለው ድጋፍ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል። በስፖርቱ መስክ የሚገኙ አካላት ለህዝብ ያላቸውን ወገንተኝነት እና ታማኝነት አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን አመልክተዋል። «ህዝብ ሲኖር ስለሆነ ስፖርት የሚኖረው። ስለዚህ ሁላችንም በአንድ ላይ መቆም የምንችልበት የበለጠ የምንተባበርበት ወቅት በመሆኑ የተጀመሩ ድጋፎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል» ሲሉ ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮናን ለመከላከል ሲደረግና እየተደረገ ባለው ርብርብ የስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ረገድ በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል።የስፖርት አመራሮች፣ የስፖርት ማህበራት፣ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው፤ መልእክት በማስተላለፍ፣ በየቤታቸው ላሉ ዜጎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማሰራት፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ የምግብና ሌሎች መገልገያዎችን በመለገስ እንዲሁም በሌሎች ተግባራት ላይ ሲደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች ይሄንኑ ይመሰክራሉ።ዘርፉን የሚመራው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ይህን እንቅስቃሴ በማስተባበር እንዲሁም እንደ አንድ ባለድርሻ አካል በሚጠበቅበት ሁሉ የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል።ኮሚሽኑ በእርሱ አውራሪነት ተግባራዊ ያደረገው የምገባ መርሃ ግብር ደግሞ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያደረገ ያለውን አስደማሚ ጥረት መስካሪ ተግባር ነው። በመርሃ ግብሩ 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር በመመገብ የፈፀመውን ሰብዓዊ ተግባር ቀጣይነት ይኖረው ዘንድ፤ ግንቦት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ሁለተኛው ዙር መርሃ ግብር እንዲጀመር በማድረግ «ስፖርት የአብሮነትና አጋርነት መገለጫ ነው !!»የሚለውን አባባል በተጨባጭ፣ በተግባር……እንዲታይ አድርጓልና ሌሎችም ከዚህ ሊማሩ ይገባል ባይነን።አዲስ ዘመን ግንቦት 18/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=33113
a2475ddb5ea958fc94bf827bca5aefe6
b51f763bf921b4a573c378567725493d
ሌጣዎችን ብቻ የሚያስተናግደው ቡና ቤት
መዝናኛ
 ሰዎች መዝናናት ሲፈልጉ ሰብሰብ ማለትን ይመርጣሉ።ሰብሰብ ማለት የተለያዩ ጨዋታዎችን ማምጣት የሚያስችል ሳይሆን ወጪንም ሊቆጥብ ይችላል።ለእዚህም ነው ጉዞ እና የመሳሰሉትን በቡድን የሚደረጉት፤ ድንኳን እየተጣለም ዳንኪራ የሚረገጠው።ጓደኞሞች ተጠራርተው ተቀጣጥረው ተያይዘው መጠጥ ቤት፣ ካፌ ቤት ወዘተ የሚገናኙት በጋራ የሚያደርጉት ጨዋታ ሁሌም የማይገኝ በመሆኑም ጭምር ነው። ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ደረ- ገጽ ሰሞኑን ያስነበበን ግን ከዚህ የተለየ ነው።በጃፓን ቶኪዮ የሚገኝ አንድ አነስተኛ ቡና ቤት ሌጣውን የሚመጣን ሰው ብቻ ማስተናገድን ምርጫው አድርጓል።ሂይቶሪ የተሰኘው ይህ ቡና ቤት በሌሎች ቡና ቤቶች የማይመረጥ የራሱን ደንበኞች የሚያስተናግድበት መንገድ አለው፡፡ መረጃው እንዳመለከተው፤ ብቻውን እስከ ሆነ ድረስ የትኛውም ግለሰብ ቡና ቤቱን መገልገል ይችላል።ወደ ቡና ቤቱ በቡድን ሆኖ መግባት ክልክል ነው።ፈቃዱም ሆነ ክልከላው በቡና ቤቱ መግቢያ በር እና በሌሎች ስፍራዎች ላይ በግልጽ ተልጥፏል፡፡ ‹‹ሰብስብ ብላችሁ ዘና ማለት የምትፈልጉ ከሆነ ይህ ቡና ቤት ለእናንተ ዝግጁ አይደለም፡፡›› ያለው መረጃው፣ ይህ ማለት ግን ቡና ቤቷ የብቸኞች ወይም የሌጣዎች ወይም ማህበረሰቡ ያገለላቸው ሰዎች መሰብሰቢያ ነው ማለት አይደለም ይላል፡፡ ቡና ቤቱ ለተገልጋዮቹ ያልተለመደ የተባለ ፖሊሲ ማውጣቱን የሰማችው አንድ የሶራ ኒውስ 24 መገናኛ ብዙሃን ሪፖርተር ማሪኮ በቅርቡ ቡና ቤቱን ጎብኝታለች።ጋዜጠኛዋ ቡና ቤቱ ከምትጠበቀው በላይ አካታች ሆኖ እንዳገኘችውም ተናግራለች።ወደ ቡና ቤቱ እንደገባችም ከስድስት የማያንሱ ተገልጋዮችን ማየቷን ጠቅሳ፣ ሰዎቹ ብቻቸውን እንደገቡ ሰዎች ሆነው እንዳለገኘቻቸው ተናግራለች።ለየብቻቸው ከመሆን ይልቅ ተሰብሰብው ሲጨዋወቱም ተመልክታለች።በአስተናጋጁ አማካይነት ቀረበቻቸውናም አጠገባቸው ተቀመ ጠች። ተገልጋዮቹ ለየብቻቸው ቢመጡም ብዙ ጊዜ አብረው እንደኖሩ ጓደኛሞች እርስ በእርስ ሲያወሩ ትመለከታለች።ማሪኮ መጠጥ አዘዘች፤ ይሁንና ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለበት አላወቀችም።አስተናገጁ ምን እንደተሰማት ተረድቷል፤ ወደ ቡና ቤቱ የመጣሽው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሲልም ጠየቃት፡፡ ጋዜጠኛዋ ለቀረባላት ጥያቄ ምላሽ ስትሰጥ ሌሎቹ ደንበኞች ጭምር መሳተፍ ጀመሩ፤ ወደ ቡና ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት ሊመጡ እንደቻሉ ሀሳብ ተለዋወጡ።ማሪኮም በውይይቱ ውስጥ መሳተፍ ቀጠለች።ወደ ቡና ቤቱ የሚመጡ ሁሉ በዚህ አይነት መልኩ እየተቀላቀሉ ተደስተው እንደሚመለሱም ተነገራት።የቡና ቤቱ ባለቤትም ይህን አስቦ ቡና ቤቱን መክፈቱን መረጃው ይጠቁማል። ‹‹ ሰዎች ቡና ቤት መሆን አለበት ብለው በሚያስቡት አይነት ቡና ቤት እኔ እምነቱ የለኝም›› ሲል ለሪፖርተሯ የተናገረው የቡና ቤቱ ባለቤት፣ ቡና ቤቴን እንዴት ባደርገው ከቡና ቤቶች ሁሉ የተለየ ሊሆን ይችላል እያለ ሲያስብ መቆየቱንም ይገልጻል።ቡና ቤቱ አዳዲስ ሰዎች እየመጡ የሚገናኛኙበትና የሚደሰቱባት እንዲሆን ይፈልግ እንደነበርም ይናገራል። ‹‹ቡና ቤቱ እንደገባህ ራስህን ብቸኛ ያረገህ ይመስልሃል፤ በሌሎች የተገለልክም ይመስልሃል፤ በእርግጥም ይመስላል፤ ከዚያም በቡና ቤቱ ከሚገኙት በርካታ ሰዎች ጋር ማውራት ውስጥ ተገባለህ›› ሲል አንዱ ተገልጋይ ይናገራል።ሌላው ተገልጋይ በበኩሉ ‹‹በሌሎች ቡና ቤቶች የማላውቃትን ሴት ለማውራት ብሞክር ሌሎች ድብደባ የሚፈጸምብኝ እየመሰላቸው ይበሳጩብኛል፤ እዚህ ግን ሁላችንም የመሰለንን እንጨዋወታለን፤ ነገሮች ቀለል ያሉ በመሆናቸውም እንደሰታለን›› ሲል የቡና ቤቷን ምቹነት ገልጿል። የሂቶሪ ቡና ቤት የመስተንግዶ ፖሊሲ ማህበራዊነትን የሚጻረር ቢመስልም አዳዲስ ሰዎች ማግኘት የሚቻልበትን ከባቢ ለመፍጠር የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል።በዚህም ምንም አይነት ግፊት በሌለበት ሁኔታ ሰዎች በራሳቸው ፍላጎት መግባባት የሚችሉበትን መድረክ ለመፍጠር ምቹ ስፍራ ነው ሲል መረጃው ያመለክታል።ይህ ሁኔታ ሲታይ ቡና ቤቱ ከተቀሩት ቡና ቤቶች አንጻር ሲታይ የበለጠ አካታች ነው ሲል መረጃው ያመለክታል፡፡አዲስ ዘመን ጥቅምት 18/2012 ዘካርያስ
https://www.press.et/Ama/?p=21578
235b2aba826e824a5d636f65c8304686
66e0e14f27a08cecb713d5ae9e964fe9
የፌዴሬሽኑ አማራጭ እቅዶችን የመጠቀም እንቅስቃሴ
ስፖርት
ይህ ዓመት እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ቢሆን፤ በስፖርቱ ዓለም በተለይ በዚህ ወቅት በርካታ ውድድሮች፣ ጉባኤዎችና ሥልጠናዎች ሊካሄዱ ይችሉ ነበር። ነገር ግን ሳይታሰብ ተከስቶ ዓለምን ባዳረሰው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሮች ብቻም ሳይሆኑ በርካታ ጉዳዮች በታቀደላቸው ሁኔታ እንዳይካሄዱ ማድረጉ ግልጽ ነው። ታዲያ የስፖርት ማህበራትና ሌሎች ተቋማት እቅዶቻቸው በዚህ መልኩ አቅጣጫቸውን ሲስቱ ምን ዓይነት አማራጮችን ተጠቀሙ? ከዓመት እስከ ዓመት በሩጫ ላይ ከሆኑና በሥራ ከሚወጠሩ ፌዴሬሽኖች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው። የፌዴሬሽኑ የሥልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተሩ አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ የሚናገሩት አላቸው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቻምፒዮናን ጨምሮ የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን፣ የወጣቶች ቻምፒዮና እንዲሁም ሌሎች ውድድሮች ፌዴሬሽኑ በዚህ ዓመት ያላካሄዳቸው የውድድር ዘርፍ እቅዶች ናቸው። በሥልጠና ጥናትና ምርምር ዘርፍ ደግሞ የዚህ ዓመት ዋነኛ እቅድ የነበረው ባለሙያዎችን ማብቃትና መመዘን መሆኑን ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። ዳኞችና አሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ሥልጠናዎችን አግኝተው ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ባለበት ወቅት ግን የዓለም ትኩሳት የሆነው ጉዳይ በመከሰቱ እንደታሰበው ማስኬድ አልተቻለም ይላሉ። በተለይ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የሥራ ክፍሉ በዚህ ለማሳለፍ ያስቀመጠው እቅድ ወደ መሬት ሳይወርድ ቀርቷል። በዓመቱ ኦሊምፒክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፍና ብሔራዊ ቡድንን የማዘጋጀት እቅድም ተመሳሳይ ዕጣፈንታ ገጥሞታል። ለብሔራዊ ቡድን የተጠሩ አትሌቶችም ተበትነው ወደየ ቤታቸው ሄደዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ግን ሥራውን ከማቋረጥ ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መጠቀምን መርጧል። ዋናው የአትሌቶች ጤንነትና በብቃት መቆየት በመሆኑም የተሻለ ያለውን ተግባር ሲከውን እንደቆየ ዳይሬክተሩ ያስረዳሉ። ፌዴሬሽኑ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ስፖርታዊ ክዋኔዎችን ማካሄድ አዳጋች መሆኑን በመገንዘቡ ቀደም ብሎ ወደ ዝግጅት መግባቱን ይጠቁማሉ። አትሌቶች ሥልጠና ማቋረጣቸውን ተከትሎ ከስፖርቱ እንዳይርቁ እንዲሁም አሰልጣኞችም ከአትሌቶቻቸው በጋራ ያላቸው ግንኙነት እንዳይቋረጥ ምን ማድረግ ይገባል? የሚለውን በማሰብም ነው በቴሌቪዥን ስርጭት በትምህርትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ፕሮግራሞች እንዲተላለፉ የተደረገው። በዚህም የስፖርቱ ባለሙያዎችን በማካተት በሦስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለስድስት ሳምንታት ለአትሌቶች ጠቃሚ የሆኑ መርሃ ግብሮች ሲተላለፉ ቆይቷል። የመርሃ ግብሩ ይዘትም ሥነ-ልቦና፣ ሥነ-ምግብ፣ ሕክምና፣ ማህበራዊ ግንኙነት፣ የተምሳሌት አትሌቶች መልዕክት፣ የአሰልጣኞች ምክረ ሃሳብ እንዲሁም አትሌቶች በአጠቃላይ ምን ማድረግ ይገባቸዋል የሚለውን ያጠቃለለ ነበር። ከቴሌቪዥን ስርጭቱ ባሻገር በፌዴሬሽኑ ይፋዊ ማህበራዊ ገጽ (ፌስ ቡክ) እንዲሁም በድረገጹ አማካኝነትም አትሌቶችን ተደራሽ ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህ ሂደትም ፌዴሬሽኑ ማድረግ የሚገባውን መልካም ተግባር ማከናወኑን ለመታዘብ ተችሏል። አትሌቶችና ሌሎች ባለሙያዎችም ለዚህ የሚሰጡት ግብረ መልስ ጥሩ ሥራ መሰራቱን የሚያሳይ ነው። አትሌቶች ቤታቸው በሚሆኑበት ወቅት ምን መስራት እንዳለባቸው ግራ ተጋብተው ነበር የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ አሰልጣኞች በሚሰጧቸው አቅጣጫ ተጠቃሚ ሆነዋል። በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙና እነዚህን አማራጮች የማያገኙ አትሌቶችን ደግሞ አሰልጣኞች በስልክና በሌሎች መንገዶች በተመሳሳይ እየረዷቸው ይገኛሉ። አሁን ካለው ሁኔታ አንጻር ጥናት መስራትና አትሌቶችን ማግኘት ባይቻልም በተለያዩ መንገዶች ምስጋናቸውን ያደርሳሉ። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክር የሚጠይቁ አትሌቶች ቁጥር መበራከትም ይህንኑ የሚያመላክት ነው። አሰልጣኞች በበኩላቸው ወትሮ ከነበረው ሁኔታ በተሻለ መልኩ ከፌዴሬሽኑ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጠናከሩ ሲሆን፤ ግብረመልስ በመስጠትም አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው። ከዚህ በኋላም ፌዴሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ጎን ለጎን መርሃ ግብሩን በአዲስ መልክ የሚያስቀጥልም ይሆናል። የሀገርን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስጠራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ቅድሚያ ተሰላፊ መሆኑን በተግባር በማሳየት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም በግሉ፣ ከሌሎች ተቋማት ጋር እንዲሁም በአትሌቶቹ አማካኝነት በገንዘብ እንዲሁም በቁሳቁስ የድርሻውን በማድረግ ላይ ይገኛል። አመራሩና ሌሎች ታዋቂ አትሌቶችም ለሕዝቡ መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ናቸው። አሁንም ከዚህ በላቀ መልኩ ለመስራት የሚያስችል ተነሳሽነት አለ። እንደሚታወቀው በዚህ ወቅት ውድድሮችና ሌሎች የሥልጠና መርሃ ግብሮች ተቋርጠዋል። በዚህ ምክንያት ፌዴሬሽኑ ቀድሞ የያዛቸውን እቅዶች በመቀየር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች ላይ ለማተኮር ማቀዱን ዳይሬክተሩ ይጠቁማሉ። በዚህም ከፌዴሬሽኑ ስፖንሰር ማልታ ጊነስ ጋር በመሆን በቴሌቪዥን የሚተላለፉ መርሃ ግብሮችን በመስራት ላይ ነው። በአንድ ወር ውስጥ ለ16 ቀናት ያህል የሚተላለፈው መርሃ ግብሩ እንደ ቀድሞ በምክረ ሃሳብ ላይ ሳይሆን በተግባር ላይ የተመሰረተ እንደሚሆንም ታውቋል። በአትሌቶች ዘንድ ተምሳሌት የሆኑና ዝነኛ አትሌቶች እንዲሁም ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፤ ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች በምን መልኩ እንደሚሰሩ የሚያሳይም ይሆናል። እንቅስቃሴው ከአትሌቶች ጋር ብቻ ሳይሆን ሌላውን ኅብረተሰብም የሚጠቅምም ነው የሚሆነው። ለዚህ የሚሆነው ዝግጅት በመጠናቀቁ በቅርቡ አየር ላይ የሚውልም ይሆናል። በዚህ ወቅት አብዛኛው ኅብረተሰብ ትኩረቱ የመገናኛ ብዙኃን ላይ በመሆኑ፤ ትብብራቸውን እንዳያቋርጡ ይጠይቃሉ። ከቴሌቪዥን ባሻገር በርካቶችን ተደራሽ የሚያደርጉ የመገናኛ ብዙኃን አብሮነታቸውን እንዲያሳ ዩም ጠይቀዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 19/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=33175
b91e809768c12e8c3fecd81698d6e003
d3fe25035bb9c528b189a342e6f49656
ኢትዮጵያ 50 ዓመታት የተጠቀመችበትን የንግድ ህግልትቀይር ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
 ክፍለዮሐንስ አንበርብርአዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ስትጠቀምበት የነበረውን የንግድ ህግ ከዘመነ ቴክኖሎጂ ጋር የተናበበና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ አዲስ ህግ ልትቀይረው መሆኑን ተገለጸ። አገሪቷ ከምትጠቀምባቸው መድሃኒቶች ውስጥ 80 ከመቶ የሚሆነው በውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ ወደ አገር ውስጥ የሚገባ መሆኑም ተገለጸ።የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ምስጋኑ አረጋ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፤ ኢትዮጵያ ግማሽ ክፍለ ዘመን ስትጠቀምበት የነበረው የንግድ ህግ ከዘመነ ቴክኖሎጂ ጋር የተናበበና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በአዲስ ህግ ልትተካ ነው።አገሪቷ እያካሄደች ያለው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ መርህ በዋናነት በማክሮ ኢኮኖሚ፣ መዋቅራዊ እና የዘርፍ ማሻሻያ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመው ፣ በዚህም በአሁኑ ወቅት ሁለንተናዊ ለውጦችን ለማምጣት ከመቼውም በላይ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አብራርተዋል። እንደ ሚኒስትር ድኤታው ገለፃ፤ እየተደረጉ ካሉ ማሻሻያዎች መካከል 50 ዓመታትን በሥራ ላይ የነበረው የንግድ ህግ ዘመኑ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ የማሻሻል እና ህግ ሆኖ የማውጣት ሂደቱ ከጫፍ መድረሱን አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅትም የተረቀቀው ህግም ለተወካዮች ምክር ቤት መላኩን ጠቁመው ። ውይይት ከተደረገበትና የተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታን ካገኘ በኋላ ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ይህም አገሪቱ የጀመረችውን ዕድገት ለማፋጠን እና አቅም በፈቀደ መጠን የንግዱን ማህበረሰብ ጥያቄ ለመመለስ አጋዥ እንደሚሆን አመልክተዋል። የዓለም ማህበረሰብ በአሁኑ ወቅት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከፍተኛ ግብይት እያካሄደ ይገኛል ያሉት ሚኒስትር ድኤታው፤ የመጠቁ አገራት የንግድ ፈቃዳቸውን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችንና መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በኦንላይን እያስተናገዱ ይገኛል ብለዋል። ይሁንና ኢትዮጵያ ከዚህ አኳያ እጅጉን ወደ ኋላ የቀረች በመሆኑ እነዚህንና መሰል ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረጉ ማሻሻያዎች እየተደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።የኢትዮጵያ የንግድ አካሄድ ሚዛን ያልጠበቀ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ምስጋኑ ፣ በቀጣይ እነዚህን ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል ብለዋል። ለአብነትም አገሪቱ ከምትጠቀምባቸው መድሀኒቶች ውስጥ 80 ከመቶ የሚሆነው በውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገቡ አመልክተዋል። በዘርፉ ሀገር ውስጥ ያሉ አምራቾችን አቅም በማጎልበትና በቁጥር እንዲበዙ በማድረግ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ በተጨማሪ ለውጭ ገበያ እንዲያቀርቡ ለማድረግ መንግሥት ከአምራቾች ጋር በቅርበት የሚሠራ መሆኑን ሚኒስትር ድኤታው አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 25/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38749
3162b048c7054488da32a450654857de
25fb5df0538f947475c8b3e3b8b97f05
ኮሚሽኑ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ለመዋጋት ጠንካራ ሥራዎችን መስራቱን ገለጸ
ስፖርት
የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ለመዋጋት የስፖርት ቤተሰቡንና ባለድርሻ አካላት በማሳተፍና በማስተባበር ጠንካራ ሥራዎችን መስራቱ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ዕቅዶችና ከተከሰተው የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ አንፃር የተከናወኑ አበይት ተግባራት ትናንት ለማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ሱፐር ቪዥን ቀርበው ግምገማ ተደርጎባቸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይ በዕለቱ እንደተናገሩት፤ በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ቁልፍና አበይት ዕቅዶችን አውጥቶ በታዳጊ ወጣቶች ስልጠና መርሀ ግብር፣ በማስ ስፖርት (በማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ) በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማት፣ በውድድርና ተሳትፎ፣ እና በተቋማዊ ለውጥ ሥራ በሽታው ከመከሰቱ በፊት በርካታ ሥራዎች ማከናወን ተችሏል። አቶ ዮናስ አክለው «ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ከመደበኛ ሥራው ትይዩ ቫይረሱ ከተከሰተ ጀምሮ በከተማ አቀፍ ደረጃ ወረርሽኙን ለመዋጋት እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ነበር። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ለመዋጋት የስፖርት ቤተሰቡንና ባለድርሻ አካላት በማሳተፍና በማስተባበር ጠንካራ ሥራዎቹን አከናውኗል ሲሉ ገልጸዋል። ኮሚሽኑ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ለመዋጋት በከተማ ደረጃ በአብይ ኮሚቴ ውስጥ በመሳተፍ እነዚህን ሥራዎች ሲያከናውን እንደነበር ገልፀው፤ የስፖርት ቤተሰቡንና ባለድርሻ አካላት በማሳተፍና በማስተባበር በገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከባቸው፣ ለታማሚ የሚሆን የቅድመ ቦታ መለየትና ማዘጋጀት፣ ለወገን ወገን በመሆኑ የደም ልገሳ መመደረጉ፣ የኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰፊ ሥራዎች መሠራታቸው እና በተለይ በቤታቸው ቫይረሱን ለመከላከል የሚኖሩ የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ቤታቸው አካላዊ ርቀትን ጠብቆ የተሰሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ዋና አስተባባሪ አቶ ሀይለሰማዕት መርሀጥበብ በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸው ተግባራት እጅግ የሚያስደስቱና የሚበረታቱ እንደሆኑ አመልክተዋል።ኮሚሽኑ በቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ያሉበትን ክፍተቶች በመሙላት የበለጠ ለውጤት መብቃት እንደሚገባው አስገንዝበዋል። አዲስ ዘመን ግንቦት 4/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=32176
cc1994dc2b7d4d40ded99ef3b9793a8b
8a386a521ff85dd418130bbb6c14ce92
የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል
ሀገር አቀፍ ዜና
 ዳንኤል ዘነበ አዳማ፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል። በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክተር አቶ ዩሴፍ አበራ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የአጠቃላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ለመስጠት መርሐግብር ተይዟል። በዚህ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ መደረጉን ገልጸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል። ምዝገባው ከትግራይ ክልል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በስተቀር በሁሉ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን የገለጹት ኃላፊው፣ በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ካጋጠመው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እንዳልተቻለ አመልክተዋል። በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ቀደም ሲል ምዝገባ የተጀምረ ቢሆንም ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ መቋረጡን አስታውሰው፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል። በትግራይ ክልል 80 ያህል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በመተከል ደግሞ እስከ 14 ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሎ ይገመታል፣ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ምዝገባ ከተደረገ ቁጥሩ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል። ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በበኩላቸው፤ መንግሥት በወሰደው ቁርጠኛ አቋም ትምህርት ሚኒስቴር እና ኤጀንሲው በመቀናጀት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ለመፈተን መደረግ የሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች እያጠናቀቁ መሆኑን ገልጸዋል። በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። በክልሎች ደረጃ የሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ከወዲሁ ለሂደቱ አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን አሟልተው እንዲገኙ ከፌዴራል በወረደላቸው አቅጣጫ መሰረት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አመልክተዋል። በዘንድሮ አዲስ ቴክኖሎጂ ይዘን ወደ ተማሪዎቻችን የምንቀርብ ከመሆኑ አንጻር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከኤጀንሲው ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል። ባለድርሻ አካላትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሑሪያ አሊ በበኩላቸው፤ የብሔራዊ ፈተናዎች አሰጣጥ ባህላዊነት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ወጪ፣ ውስብስብ አሠራር፣ ስርቆትና ኩረጃ፣ አድካሚ የሥራ ሂደትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች አሉበት ብለዋል። ኮምፒውተርን መሰረት ያደረገ የፈተና ሠርዓት መዘርጋት ችግሩን ለመቅረፍ፣ አሊያም ለመቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነም አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 25/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38751
5011952b0cf03095ad227da4d4337bf6
e8663d90ba4e1e548c8b57b587d39a11
መገናኛ ብዙሃን በቅርበት አብረውት እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጥሪ አቅረበ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በኃይሉ አበራአዲስ አበባ፦ መገናኛ ብዙሃን በቅርበት አብረውት እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጥሪ አቀረበ። ተቋማቱ የሚያሰራጯቸው መረጃዎች ተአማኒነት በአግባቡ ሊፈተሸ እንደሚገባ አሳሰበ።የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ እየደረሰ ያለውን ውድመት አስመልክቶ ትናንት በፅሕፈትቤቱ በሰጠው መግለጫ፣ የአካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፅጌ ገብረማርያም እንዳስታወቁት፣ ሀገራችን ለዓለም የሚተርፍ ሀብት ባለቤት ብትሆንም በታሪካችን ሂደት ባስተናገድናቸው የእርስበርስ ጦርነቶችና ግጭቶች የተነሳ ሳንጠቀምበት ቀርተናል ብለዋል።አካዳሚው በተለያዩ ሙያዎች ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ፤ ያካበቱትን እውቀትና ተሞክሮ መሰረት በማድረግ ለሀገርና ለህዝብ የሚጠቅሙ ምክረ ሃሳቦች ሊሰጡ የሚችሉ ምሁራን የሚገኙበት መሆኑን ጠቁመው፣ መገናኛ ብዙሃን ይህንን ሀገራዊ አቅም ለመጠቀም ከተቋሙ ጋር በቅርበት እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።ማንም ዜጋ የመኖር መብት ያለው ቢሆንም፣ በሀገራችን የመኖር መብት ጥያቄ ውስጥ እየገባ መሆኑን አመልክተዋል። ይህ መብት በማንም መወሰድ እንደሌለበትም አሳስበዋል።አካዳሚው በተለይም ከሁለት ዓመታት በፊት በሀገሪቱ ተከስተው የነበሩ አለመረጋጋቶችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የፖሊሲ ግብአቶች እና በመርህ ላይ የተመሰረቱ የተለያዩ ሃሳቦች ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሰዋል። አካዳሚው በመርህ ደረጃ ጥናትን መሰረት ያደረጉ መረጃዎችን ለሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት እየሰጠ እንደሚገኝ አመልክተዋል። የአካዳሚው የቦርድ አባል ዶክተር ፀደቀ አባተ በበኩላቸው፣ ከጥላቻ፣ ከግል ጥቅም እና የመሳሰሉ አፍራሽ ሁኔታዎችን ከማስወገድ አንጻር የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሚና ሊጫወቱ ይገባል ብለዋል።በእለቱ በጽሑፍ በተነበበው የአካዳሚው የአቋም መግለጫ ፣ መንግሥት በሀገራችን የህግ የበላይነት ለማስፈን የሚወስደውን እርምጃ አካዳሚው እንደሚደግፍ ገልጸው ፣ እርምጃውም በሁሉም አካባቢ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፤ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎችም ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።በሶሪያ እና በሊቢያ እና በየመን እንደታየው ሁሉ በሀገራችንም መሰል ቀውስ እንዳይፈጠር ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በውይይት ብቻ እንዲፈቱም መልእክት አስተላፈዋል።አካዳሚው ከ177 በላይ አባላት ያሉት መሆኑም በወቅቱ ተገልጿል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 25/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38753
4a19b9cbe59ffea7ccb961d07fb66e46
04391ed189555d5cdfcd4a8774625eeb
የጅት ኩንዶው ማዕከል ምስጉን የረድዔት ተግባር
ስፖርት
ስፖርት ከአካላዊ እንቅስቃሴና ከመዝናኛነት ባለፈ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል። በተለይም ዓለም በኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ምክኒያት ጭንቅ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት ስፖርትና የስፖርቱ ማህበረሰብ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት በኩል እያበረከተ የሚገኘው አስተዋፅኦ እዚሁ አገራችንም ትልቅ ቦታ እንዳለው መታዘብ ይቻላል። ኤርሚያስ ገሰሰ ጂምና ማርሻል አርት ማዕከል ወጣቶችን በጅት ኩን ዶ እንቅስቃሴ ከማብቃት ጎንለጎን የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ይታወቃል። የበጎ አድራጎት ስራ ከማርሻል አርት ስፖርት ጋር አብሮ እንደሚሄድ የሚናገረው ማስተር ኤርሚያስ ወጣቶች ማርሻል አርትን ሲማሩ የስነምግባር ትምህርትም አብሮ እንደሚሰጣቸው ያብራራል። ይህ የስነ ምግባር ትምህርት መገለጫው ደግሞ በጎ ተግባር ነው። 1995 ዓ.ም አካባቢ የተማሪ ቤተሰቦች፣በጎ ፍቃደኞችና ሌሎችም በጋራ ሆነው የስፖርቱን እንቅስቃሴ ሲጀምሩ ገንዘብ በማዋጣት ጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን በምግብ፣ በአልባሳት ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በዘላቂነት በማቋቋም መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እያደረገም ይገኛል። የበጎ አድራጎት ስራውን ከስፖርቱ ባሻገር ለማስፋት በቅርቡ ‹‹ዿጉሜ 5 የበጎ አድራጎት ድርጅት›› በሚል ስያሜ በማሳደግ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰም ነው። በየዓመቱም የትንሳዔን በዓል ምክኒያት በማድረግ በጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን የመመገብ፣አልባሳትንና ገንዘብ የመስጠት መርሃግብሮችን ያካሂዳል። መማር የሚችሉ እንዲማሩ፣መስራት የሚችሉ እንዲሰሩ ማድረግም አንዱ ተግባሩ ነው። በዚህም የበርካታ ወጣቶችን ሕይወት መለወጥ ተችሏል። ይህ ምስጉን የረድዔት ተግባር በየጊዜው እያደገ ሄዶም ኤርሚያስ ገሰሰ ጂምና ማርሻል አርት ማዕከል ከ‹‹ዿጉሜ 5 የበጎ አድራጎት ድርጅት›› ጋር በመተባበር ባለፈው እሁድ ሃያ ሁለት የጎዳና ልጆችን በማንሳት ማዕድ ከማጋራት ባሻገር መስራት የሚችሉ ወደ ስራ እንዲገቡ፣ ወደ ቤተሰብ የመመለስ ፍላጎት ያላቸው አስፈላጊው ነገር ተሟልቶላቸው እንዲመለሱና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ እስከ ማድረግ የደረሰ የረድዔት ተግባር አከናውኗል። በስፖርቱ የሚሳተፉ ወደ በጎ አድራጎት ድርጅቱ አባልነት እንዲካተቱ በማድረግ ችግርተኛ ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየተሰራ መሆኑን የሚናገረው ማስተር ኤርሚያስ አምስት መቶ ያህል አባላት ያሉት የበጎ አድራጎት ድርጅት ከዚህም በላይ የረድኤት ስራዎችን የማከናወን ፍላጎት ቢኖረውም ከጎዳና ላይ የሚያነሳቸውን ልጆች ማሳደሪያ ወይም ማረፊያ ቦታ ትልቁ ችግር እንደሆነ ያስረዳል። ተረጂዎቹ ወጣቶች ቢታመሙም የሕክምና ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነባቸው ገልጿል። በዚህ ረገድ ማንኛውም አካል ቢደግፋቸው ሌሎቹን አስፈላጊ ግብዓቶች ለማሟላት እንደማይከብድም ይናገራል። በተለይም እነዚህ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ አቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ አሁን ያለንበት አስቸጋሪ ጊዜ እስኪያልፍ ማንኛውም አካል ትብብር እንዲያደርግ ጥሪውን አቅርቧል። ይህም ልጆቹን ከቫይረሱ ተጋላጭነት ከመጠበቅ ባለፈ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ያለውን እምነት ተናግሯል። በቀጣይም ሌሎች ወጣቶችን ከጎዳና ለማንሳት ጥረት እንደሚደረግ ቃል ገብቷል። ባለፈው እሁድ ማዕድ የማጋራት መርሃግብሩ ሲከናወን በስፍራው የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስራ አራት ዋና አስፈፃሚ ወይዘሮ ወይንሸት አስናቀ፣ የስፖርት ማዕከሉና የእርዳታ ድርጅቱ ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመሆን መሰል ስራዎችን ከዚህ ቀደምም ሲያከናውን መቆቱን ተናግረዋል። በተለይም በኮሮና ቫይረስ ስጋት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ማዕድ የማጋራት መርሃግብርን ይፋ ካደረጉ ወዲህ የስፖርት ማዕከሉና የእርዳታ ድርጅቱ በጋራ በመሆን ጎዳና ላይ ያሉ ወጣቶችን ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ መስክረዋል። ‹‹በወረዳችን በርካታ ጎዳና ላይ ያሉ ወጣቶች አሉ›› ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ እነዚህን ወጣቶች ማዕድ ከማጋራት ባለፈ ወደ ስራ እንዲሰማሩና እንዲቆጥቡ በማድረግ፣ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ወደ ቤተሰባቸው መመለስ የሚፈልጉትን በመመለስ በርካታ ተግባራት መፈፀማቸውን አስታውሰዋል። ሌሎችም ከዚህ ምስጉን ተግባር በመማር ተመሳሳይ የረድዔት ስራዎችን እንዲሰሩ በማድረግ የስፖርትን ማህበራዊ ኃላፊነት በተግባር ማሳየት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ወረዳው የስፖርት ማዕከሉና የረድዔት ተቋሙ የሚያደርጉትን በጎ ተግባር ለመደገፍም ማደሪን የመሳሰሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል። አዲስ ዘመን ግንቦት 6/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=32321
0488a2fb62ce04e9736c05051373b177
d9a6c910e351136919c0b9932f8b36b6
የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከኦሊምፒክ ቀድሞ ይካሄዳል
ስፖርት
የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከኦሊምፒክ ቀድሞ ይካሄዳል የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት መሰራጨቱን ተከትሎ የሁሉም ዓለም አቀፍ የስፖርት መርሃግብሮች ዝብርቅርቅ መውጣቱ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በርካታ ታላላቅ የስፖርት መርሃግብሮችን ዳግም መከለስ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት ክለሳ የተደረገባቸው የተለያዩ መርሃግብሮች ውዝግብ ሲያስነሱ ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ከተያዘለት መርሃግብር እንዲራዘም የተደረገው የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ2021 እንዲካሄድ ከተራዘመው የቶኪዮ ኦሊምፒክ አስቀድሞ እንዲካሄድ የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ውሳኔ ላይ መድረሱን ከሁለት ቀናት በፊት አሳውቋል፡፡ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሐማድ ካልካባ በአልጄሪያ የሚካሄደው የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ የዓለም አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ካልካባ የውድድሩ አዘጋጅ አገርም አዲሱን መርሃግብር የመቀበል ግዴታ እንዳለባት ገልፀዋል፡፡ ካልካባ ቻምፒዮናው ከተራዘመው ኦሊምፒክ በፊት መካሄዱ ለአትሌቶች ጥቅም እንደሚኖረው የገለፁ ሲሆን ውድድሩ በተከለሰው የኦሊምፒክ ማጣሪያ መርሃግብር ውስጥ እንደሚካተት ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ውድድሩ የኦሊምፒክ ማጣሪያ(ሚኒማ) ለሚፈልጉ አትሌቶች ጠቃሚ ይሆናል›› ያሉት ካልካባ የዓለም አትሌቲክስ የኦሊምፒክ ማጣሪያ መርሃግብር እስከ ቀጣዩ ዓመት ሰኔ ወር እንዲራዘም ግፊት ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ስጋት የተነሳ የአትሌቲክስ ስፖርት የኦሊምፒክ ማጣሪያ ውድድሮች እስከ መጪው ታህሳስ ወር ድረስ እንዳይካሄዱ የዓለም አትሌቲክስ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ እስከ ተጠቀሰው ጊዜ የሚካሄዱ ማንኛቸውም ውድድሮችና ውጤቶች የኦሊምፒክ ማጣሪያም ይሁን እውቅና እንደማያገኙ ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡ ይህ የዓለም አትሌቲክስ ውሳኔ በበርካታ ታላላቅ የዓለማችን አትሌቶች የሰላ ትችት ሲሰነዘርበት እንደሰነበተ ይታወቃል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የስፖርቱ ዓለም ካለፉት ሁለት ወራት በላይ እንቅስቃሴው ተገድቦ ቢቆይም ከቅርብ ቀናት ወዲህ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው ለመመለስ ሲፍጨረጨሩ እየተስተዋለ ነው፡፡ ታላላቆቹን አውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች ጨምሮ አንዳንድ አገራትም ስፖርታዊ ውድድሮቻቸውን ለማስጀመር ከቫይረሱ ስጋት ነፃ ሳይሆኑ ጥረት እያደረጉ ሲሆን አብዛኞቹ ውድድሮችን በዝግ ስቴድየሞች በማድረግ የውድድር ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት መርሃግብሮቻቸውን ስለመፈፀም እየተጨነቁ ይገኛሉ፡፡ በርካቶቹ የዓለም አቀፍ ውድድሮች ግን ቀደም ሲል ቫይረሱ በቀጣዩ ዓመት ይጠፋል ወይም በቁጥጥር ስር ይውላል በሚል ተስፋ ወደ ቀጣይ ዓመት እንዲዞሩ መወሰናቸው ይታወሳል፡፡ ከነዚህ መካከል በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዘግይቶም ቢሆን በቫይረሱ ስርጭት ስጋት የተነሳ ታላቁን የስፖርት መድረክ ለአስራ ስድስት ወራት እንዲራዘም ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይህም እንደሌሎቹ ውድድሮች ሁሉ ቫይረሱ በቀጣዩ ዓመት በቁጥጥር ስር ይውላል ከሚል ተስፋ እንጂ በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ አልነበረም፡፡ በርካቶቹ ይህን ተስፋ የሙጥኝ ብለው እያንዳንዱ ቀን እንደ ዓመት እየረዘመባቸውም ቢሆን ቀጣዩን ዓመት በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ የቫይረሱ ስርጭት ግን በተቃራኒው እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ በአስደንጋጭ ፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ ይህንን ያስተዋሉ የጤና ባለሙያዎችም ለአስራ ስድስት ወራት የተራዘመው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በቀጣዩ ዓመት ላይካሄድ እንደሚችል ከወዲሁ እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ የኦሊምፒኩ አዘጋጅ የሆነችው ጃፓን የተላላፊ በሽታዎች ፕሮፌሰር የሆኑት ኬንታሮ ዋታ የቫይረሱ ስርጭት ኦሊምፒኩ በተራዘመበት ወቅት በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ አጠራጣሪ በመሆኑ ውድድሩ ላይካሄድ እንደሚችል ስጋታቸውን ለመገናኛ ብዙሃን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ በዓለም ላይ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከተስፋ በስተቀር የቫይረሱ ስርጭት በጊዜ የሚገታ ወይም ፈውስና ክትባት በዚህ ጊዜ እውን ይሆናል የሚያስብል እንዳልሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡ ይህንን ከግምት ያስገቡት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ ኦሊምፒኩ የቫይረሱን ስጋት ለማምለጥ በአስራ ስድስት ወራት ቢራዘምም ከቫይረሱ ተፅዕኖ ሊያመልጥ እንደማይችል ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማመልከታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ማስነበቡ ይታወሳል፡፡ የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮናም ከዚህ የተለየ እድል እንደማይገጥመው ማንም እርግጠኛ አይደለም፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 8/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=32480
961296da632878431b7e9a26e599d3f5
2b496ca70b2dec0cc2b42aeb261c5e95
ግንቦት አምስት- የጥቁር ተጫዋቾች የነፃነት ቀን
ስፖርት
ግንቦት አምስት ቀን ባለፈው ረቡዕ ነበር። ጥቁር ተጫዋቾች በዓለም ነፃ እንዲወጡ በኢትዮጵያ ውስጥ ታሪክ የተጠነሰሰበትና ታሪካዊው የእግር ኳስ ግጥሚያው የተደረገበት ቀን ነው። ሀሳቡን ያመነጩት፤ ተግባራዊ ያደረጉት ፤ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ አቋርጦ በዓለም አደባባይ እንዲደርስ ጥረት ያደረጉት የጥንቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ማህበረሰቦች ናቸው። ይሄ ነገር ለረጅም ጊዜ ክለቡ አካባቢም አይነሳም ነበር። የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ነጋሪና ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ(ሊብሮ) በአንድ ወቅት ‹‹ከመሳለሚያ እስከ ፍራንክፈርት- የ32 ዓመት ፈታኝ ጉዞ›› በሚል ካሰፈረው የጥቁር ተጫዋቾች የነፃነት መሰረት ድንጋይ የተጣለበትን የታሪክ አጋጣሚ የሚዳስስ የታሪክ ማስታወሻ የተወሰደውን ፅሁፍ በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችን ቀንጭበን ለንባብ ለማብቃት ወደድን። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ጨዋታ ከነጮች ጋር ያደረገው(ከውጭ ሀገር ሰዎች ጋር እንደመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ጨዋታ ከተቆጠረ) አራራት ከተባለ የአርመኖች ቡድን ጋር ነው። ጊዜውም በየካቲት 28 ቀን 1928 ዓ.ም ነበር።(በተመሰረተ በሁለት ወሩ)ለሁለተኛ ጊዜ ከነጮች ጋር የተደረገው ግጥሚያ ደግሞ በግንቦት 5 ቀን 1934 ዓ.ም ነው። ይሄ ጨዋታ ከግጥሚያዎች ሁሉ ትልቅ ትርጉም ያለውና በዓለም ያሉ ጥቁር ተጨዋቾችን ነፃ ለማውጣት መሰረት የተጣለበት ቀን ነው። ዛሬ ላይ በርካታ ጥቁር ተጫዋቾች በበርካታ ታላላቅ ክለቦች ተቆጥሮ የማያልቅ ገንዘብ እየተከፈላቸው ለመጫወታቸው መሰረት የሆነችው ይህች ቀን ነች። ጊዮርጊሶች ታሪካዊውን ጨዋታ የተጫወቱት ከጣሊያኑ ፎርቲቲዲዮ ጋር ነበር። ጨዋታውን ለማድረግ ድርድሩ አንድ ዓመት ያህል ፈጅቷል። ጦርነቱ ካለቀ ገና ጥቂት ወር ውስጥ ነው ድርድር የተጀመረው። በአንድ በኩል የሀገሬው ሰው ‹‹እንዴት ሲገድሉን ከነበሩት ጣሊያኖች ጋር እርቅ አድረጋችሁ ኳስ ትጫወታላችሁ?››በሚል ቅሬታና ተቃውሞ ሲደርስ ፤በጣሊያኖች በኩል በኳስ አሳበው አደጋ ቢያደርሱብንስ በሚል ላለመጫወት ብዙ መጓተት ታይቷል። የያኔው ኳስ ጨዋታ ለእርግጫ በጣም የቀረበ መሆኑ ለዚህ ጥርጣሬ መነሻ ነበር። ሁለቱ ቡድኖች ፋሽስቱ ያወጣውን ህግ አፍርሰው ‹‹ጥቁርና ነጭ አንድ ነው›› በሚል ተስማምተው ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ተፈራርመው ተጫወቱ። ይሄ ፊርማ መጨረሻ ላይ ፊፋ ውስጥ ኢትዮጵያ አቅርባው ሁሉም ተስማምቶ የፈረመበት የመጀመሪያው መሰረት ነው። ይሄ ፊርማ በእግር ኳስ ሜዳ ልዩነትን የሚያጠፋ ወንድማማችነትን የሚያሰፍን ነው። የዓለም እግር ኳስ ዛሬ ላይ ለደረሰበት ሁለንተናዊ እድገትም ትልቅ ድርሻ አለው። የዚህ ሀሳብ መነሻ ደግሞ የጊዮርጊስ መስራች የሆኑት አየለ አትናሽና ጆርጅ ዱካስ ናቸው። ሁለቱ በቆዳ ነጭና ጥቁር ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ ጣሊያን ህጉን ሲያወጣ መጀመሪያ እንዲለያዩ ማስጠንቀቂያ የሰጠው ለእነርሱ ነበር።ሁለቱ ጀምረው ሌሎች የጊዮርጊስ ሰዎች አቀጣጥለውና ህግ አውጥተው ህጉ በአፍሪካ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደንብ ሆኖ ሲወጣ በመጀመሪያ የተደሰቱትም ሁለቱ መስራቾች ነበሩ። ይህ ዓለም አቀፍ ደንብ ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከተው በቀላሉ እውን የሆነ ሊመስል ይችላል። ይሁን እንጂ ረጅም ጊዜ የፈጀ፣ ብዙ ውጣውረድና ትግል የተደረገበት ነው። በወቅቱ ፊፋ ውስጥ ያሉ እንግሊዞችና ደቡብ አፍሪካ ያሉ አመራሮች ይሄ ጉዳይ በካፍና በፊፋ ላይ እንዳይነሳ አቅምና ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው በገንዘብም ጭምር ለመደለል ቢጥሩም ኢትዮጵያ በቀላሉ ጉዳዩን ችላ የምትል አልሆነችም። ጉዳዩን ሲያጣሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ነገሩን አጥብቀው የያዙት የጊዮርጊስ ማህበረሰብ እንደሆኑ ታወቀ። በዚህ የተነሳም ‹‹የጊዮርጊስ ሰዎች ናቸው ያስቸገሩት›› በሚል ጥርስ ተነክሶባቸው ነበር። በርግጥም በየስብሰባው ታላቁ ይድነቃቸው ተሰማ ጉዳዩን በጥብቅ ስለሚያነሱት ግምታቸው ትክክል ነበር። የደቡብ አፍሪካ ነጮች ኬንያ ባለው ‹‹ሚስር አሌክሳንደር›› በተባለ የናይሮቢ ከንቲባ በኩል ክለቡን ለማፍረስ ብዙ መጣራቸውም እዚህ ጋር ሳይነሳ አይታለፍም። ያም ሆኖ ኢትዮጵያኑ በመጨረሻም አሸንፈው ህጉ ጸድቋል። የዚህ ሀሳብ መነሻው ጊዮርጊስ ክለብ ይሁን እንጂ ነገሩ የሀገርን ስም ከፍ የሚያደርግ በዓለም ከክለቦች አንስቶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሳተፈበት ታሪካዊ ድል ነው። (ፊፋ ላይ ያቀረበው ፌዴሬሽኑ በመሆኑ)። ጊዮርጊሶች በሀገራቸው ተገልለው የተጫወቱት መሳለሚያ በሚገኘው ኳስ ሜዳ ነው። ለዓለም ጥቁሮች ነጻ መውጣት እና የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ከስፖርት እንዲገለል ህጉ የጸደቀው ፍራንክፈርት ላይ በተደረገው የፊፋ ስብሰባ ነው። ያቀረበችው ኢትዮጵያ ስትሆን ተከራካሪው ይድነቃቸው ተሰማ ነበሩ። ይድነቃቸው ከመሳለሚያ እስከ ፈራንክፈርት ባለው ጉዞ ተሳታፊ ናቸው። ለ32 ፈታኝ ዓመታት ትግል ከተደረገ በኋላ ህጉ ጸድቆ ጥቁር ተጫዋቾች ያለምንም ገደብ በየትኛውም የዓለም ክልል እንዲጫወቱ ሆኗል። አዲስ ዘመን ግንቦት 9/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=32528
18a483db5cd486c031946f7ebd686e31
ecca94964ee2573c01afae2acf372265
«ተምዘግዛጊው ሚሳኤል» አረፈ!
ስፖርት
ከአዲስ አበባ በ110 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ወንጂ ከተማ በእግር ኳሱ በርካታ ተጫዋቾችን ማፍራቷ ይነገርላታል። ይህም ከተማዋ ከምትታወቅበት ጣፋጭ የሸንኮራ አገዳ አምራችነቷ፣ የስኳር ፋብሪካ ማዕከልነቷ ትይዩ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መፍለቂያ አሰኝቷታል። የወንጂን ከተማ በእግር ኳሱ ካስተዋወቁት ተጫዋቾች መካከል ደግሞ አንጋፋው ተጫዋች ተስፋዬ ኡርጌቾ ይጠቀሳል። በወንጂ ከተማ ተወልዶ ያደረገው ተስፋዬ፤ በእግር ኳሱ ትልቅ ቦታ መድረስን የልጅነት ህልሙ አድርጎ የተነሳ መሆኑን የቅርብ ወዳጆቹ ይናገሩለታል። ከልጅነቱ ጀምሮ ለእግር ኳስ ልዩ ፍቅር በመያዝ መነሻው ከሰፈር ሜዳ ነበር። በኳሱ የመጓዝ ህልሙ ሩቅ የሆነው የትናንቱ ታዳጊ ተስፋዬ፤ በስፖርቱ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በማጎልበቱ ወደ ክለብ እንዲያድግ አጋጣሚን አገኘ። ከከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መሠረት አንዱ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ያቋቋመውን «የወንጂ ስኳር እግር ኳስ ክለብ» ነበር የተቀላቀለው። ተስፋዬ የወንጂ ስኳርን መቀላቀሉ በኳሱ ለሚያልመው ህልሙ፣ ለሰነቀው ተስፋ እውን መሆን መንደርደሪያውን የትውልድ ከተማው ሆነለት። ከክለቡ ጋር የተወሰኑ ጊዜያትን ቆይታ ካደረገ በኋላ የሕይወቱ አቅጣጫ ወደ ሌላ ምዕራፍ ተሸጋገረ። በወንጂ ስኳር እግር ኳስ ክለብ በፈጣንና ጥበብ የተሞላበት እንቅስቃሴ ባለቤትነቱ በአየር ኃይል እግር ኳስ ቡድን እይታ ውስጥ አስገባው። በወቅቱ የአየር ኃይል አሰልጣኝ የነበረው አንጋፋው አሰልጣኝ ሀጎስ ደስታ ልብ በማሸነፍ አሰልጣኙ አየር ኃይልን እንዲቀላቀል አስቻለው። በእግር ኳሱ ትልቅ ደረጃ የመድረስ ተስፋ በልቡ ሰንቆ ወደሜዳ ለሚመጣው ታዳጊ ትልቅ ዕድል ነበር። በአየር ኃይል ቤት ተስፋዬ ምኞቱን መኖር ለመጀመሩ መንደርደሪያው ነበር። በቡድኑ ውስጥ ያሳየው እንቅስቃሴ ክለቡ እንዲደሰትበት ከማድረግ አልፎ፤ ለብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት ሀገራዊ ጥሪ እንዲቀርብለት አድርጎታል። በ1983 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን በመመረጥ በግብጽ አዘጋጅነት በተካሄደው 7ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ችሏል። የወንጂው ፍሬው ተስፋዬ የስኬት ጀንበርን በአጭር ጊዜ ውስጥ መመልከት የቻለ ሲሆን፤ በሜዳ ላይ የሚያሳየው ብቃትና የተላበሰው መልካም ስብዕናው ተደምረው ጉዞው ያማረ እንዲሆን አደረጉት። የወጣት ብሔራዊ ቡድኑ በሻምፒዮናው ላይ ከተሳትፎ መልስ የተስፋዬ የክለብ መዳረሻ ከአየር ኃይል ተወርውሮ ወደ አንጋፋው ቅዱስጊዮርጊስ ላይ አረፈ። በ1983 ዓ.ም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ አንፀባራቂ ታሪክ ባላቸው በኢንስትራክተር መንግሥቱ ወርቁ አማካኝነት ክለቡን ተቀላቀለ። የእግር ኳሱ ጥበበኛ ተስፋዬ ፈረሰኞቹን መቀላቀሉ በኳሱ የስኬትን ቁንጮ ለመቆናጠጥ ትልቅ ዕድል ፈጥሮለታል። በአማካይና የተመላላሽ ቦታዎች ላይ በመጫወት ክለቡን ለስኬት ማብቃት በመቻሉ የክለቡ ደጋፊዎች ዛሬም ድረስ ትልቅ ቦታ እንዲኖራቸው አድርጓል። ከ1983 ዓ.ም እስከ 1992 ዓ.ም ፈረሰኞቹን ማገልገል የቻለው አመለሸጋው ተስፋዬ፤ በቆይታው ከፍተኛ ዝናና ተወዳጅነት አትርፏል። በፈረሰኞቹ ቤት በቆየባቸው የሰባት ዓመታት ቆይታ ውስጥ በ1986 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሻምፒዮን ኮከብ ተጫዋችነትን ክብር አግኝቷል። ክለቡ ቅዱስጊዮርጊስ ከ1986 እስከ 88 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሻምፒዮናነትን ክብር ሲቀዳጅ ግብ አስቆጣሪ ከሆኑት ተጫዋቾች ጀርባ የእርሱ ሚና ግዙፍ እንደነበር በወቅቱ የነበሩ ተጫዋቾች መስክረውለታል። ከክለቡ ስኬት ተሻግሮም ለሚወዳት ሀገሩ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተመርጦ በርካታ ጨዋታዎችን ተጫውቶ አሳልፏል። በ1985 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ናይጄሪያን 1ለ 0 ስታሸንፍ ብቸኛዋን ግብ በማስቆጠር ሀገሩን ለድል ያበቃበት አጋጣሚ በአብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ ዘንድ ይታወሳል። በብሔራዊ ቡድን ብሎም በክለብ ደረጃ የነበረው እንቅስቃሴ ከክለቡ ተሻግሮ በስፖርት አፍቃሪው ዘንድ ከፍተኛ ተደናቂነት ማትረፍ የቻለ ተጫዋች ነበር። በሀገር ውስጥ የክለብ ፍልሚያዎች በፈረሰኞቹ ቤት በ4 ቁጥር ማሊያ መንገስ ችሏል። በሜዳ ላይ ፈጣንና ድንቅ እንቅስቃሴ የሚያሳይ መሆኑን ተከትሎ «ተምዘግዛጊው ሚሳኤል» የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ተስፋዬ፤ ከሀገር አልፎ ወደ አውሮፓም አምርቶ በፊንላንድ ሊግ መጫወት ችሏል። በኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ዛሬም ድረስ እንደ ብርቅ በሚታየው የአውሮፓ ሊግ የኳስ ጥበበኛው ተስፋዬ ባህር ተሻግሮ። እግር ኳስን በተጫወተባቸው ዓመታቶች በመሀል ሜዳ የጨዋታ ብቃቱ የብዙዎቹን የእግር ኳስ አፍቃሪዎች እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን ቀልብ ይስብ የነበረው፤ ተስፋዬ የተጫዋችነት ዘመኑን ቢያበቃም ከኳሱ አልተለየም ነበር። ከተጫዋችነት ወደ አሰልጣኝነት የሕይወቱ አቅጣጫ ተሸጋገረ። በአሰልጣኝነትም ሕይወት በመሰማራት የጌታ ዘሩን የታዳጊ ፕሮጀክት እና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲንም ክለብን በመያዝ አሰልጥኗል። የሕይወቱን ፍጻሜ ከኳስና ከእናት ሀገሩ ለመነጠል ፍላጎት ያልነበረው ተስፋዬ፤ መኖር ግድ ነበርና በአሜሪካ በስደት በርካታ ዓመታትን አሳልፏል። «ተምዘግዛጊው ሚሳኤል» በገጠመው ህመም ከሚኖርበት አሜሪካ የመጣ ሲሆን፤ በሚወዳት ሀገሩ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 05 ቀን 2012 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕይወቱ አርፏል። በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የራሱን አሻራ ማሳረፍ የቻለው ተስፋዬ የቀብር ሥርዓቱ በትውልድ ከተማው ወንጂ ሸዋ ኪዳነ ምህረት ከትናንት በስቲያ ተፈጽሟል። የተስፋዬ ሞት ብዙዎቹን ያሳዘነም ሲሆን የዝግጅት ክፍላችን በተስፋዬ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ ለወንድሙ ተከተል ኦርጌቾና ለመላው ስፖርት አፍቃሪ እና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች መፅናናትን ይመኛል። አዲስ ዘመን ግንቦት 7/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=32391
cd1d26eb06bf39e7476e73b82224ece4
07df64fca5d4e5b970b1eb0f54cd4e58
የኢትዮጵያ ቨርቸዋል ሩጫ ተካሄደ
ስፖርት
ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያሳደረውን ተፅዕኖ መቀነስና መቀየር ይቻል ዘንድ በኢንተርኔት የታገዘ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት የቨርቿል ሩጫ ተካሄደ። በኢንተርኔት የታገዘ የቀጥታ ቪዲዮ «ቨርቿል ሩጫ» መርሐ ግብር በተሳካ ሁኔታ ከትናንት በስቲያ መካሄዱን የሩጫ አዘጋጁ የታላቁ ሩጫ በዋሽንግተን ዲሲ አስታውቋል። በቨርቹዋል ሩጫ መርሐ ግብሩ ላይ አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ ስለሺ ስህን፣ ፋጡማ ሮባ፣ ሚሊዮን ወልዴ እና እጅጋየሁ ዲባባ መሳተፋቸው ታውቋል። በውድድሩ አንድ ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ከመላው ዓለም ሆነው ዙም በተሰኘ መተግበሪያ ላይ በኢንተርኔት በቀጥታ እየተያዩ በቤታቸው እና ግቢያቸው ውስጥ ሆነው በመሮጥ እና ሶምሶማ በማድረግ ተሳትፈውበታል ተብሏል። የኢትዮጵያ ቨርቹዋል ሩጫ ዋና አዘጋጅ ዶክተር ጋሻው አብዛ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ፤ የኮቪድ-19 በሽታ በዓለም ዙሪያ ከፈጠረዉ የጤና ፈተና ጎን ለጎን፣ በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ኢኮኖሚያዊና ስነ ልቦናዊ ጫና አስከትሏል። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይህ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ረዘም ላለ ጊዜ ቤት ውስጥ ለመቀመጥ ተገደዋል። በመሆኑም የወገኖቻችንን ችግር በተወሰነ መልኩ ማቃለል ይቻል ዘንድ በኢንተርኔት የታገዘ ቨርቿል ሩጫ ማዘጋጀት አስፈልጓል ብለዋል፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ወረርሽኙ በበረታባቸው አሜሪካና አውሮፓ የሚገኙ ኢትዮያዊያን ከተለመደው የአኗኗር ዘይቤ በወጣ ሁኔታ ረዘም ላለ ጊዜ ቤት ውስጥ ለመቀመጥ በመገደዳቸው ሥራን እንደ ወትሮው ወጥቶና ነፃ ሆኖ መሥራት አልተቻለም። ስለዚህ በበርካቶች ላይ ስጋትና የአዕምሮ ጭንቀት በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ዶክተር ጋሻው፤ ጫናውን በተወሰነ ደረጃ ለመቀነስ የሚያግዝ በኢንተርኔት በቤትና ግቢ ውስጥ ሆነው የሚሮጡት የቨርቹዋል ሩጫ ተዘጋጅቶ በስኬት መከናወኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ቨርቹዋል ሩጫ ላይ አንጋፋና ብርቅዬ አትሌቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መሳተፍ የቻሉ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ጋሻው ፤ከዝግጅቱ የተገኘው ገቢ በኮቪድ-19 ዙሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚሠሩ ሁለት መንግሥታዊ ያልሆኑና በኢትዮጵያዊያን ለሚመሩ አነስተኛ ድርጅቶች የሚበረከት መሆኑንም ተናግረዋል። በሩጫው ላይ አትሌቶች በያሉበት ቦታ ሆነው በቪዲዮ ተራ በተራ እየሮጡ ለውድድሩ በተዘጋጀ መተግበሪያ ላይ በቀጥታ በማህበራዊ ሚዲያ ከተሳታፊዎች ጋር ሩጫውን አካሄደዋል። ተሳታፊዎችም በቤትና ግቢ ውስጥ እንዲሁም የመሮጫ ማሽን ላይ በመሆን እየሮጡ በስልካቸው፣ በኮምፒዩተርና በሌሎች የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በመታገዝ አትሌቶችን እየተከተሉ ሮጠዋል። በፌስቡክ እና ዩቲዩብ ላይቭ ላይ ከተለያዩ የዓለም ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ ሰዓት በአንድ ላይ ሆነው በኢንተኔት በታገዘው ሩጫ ላይ ካሉበት ሆነው መሳተፋቸው ታውቋል። ቨርቹዋል ሩጫ (Virtual Race) የሚባለው ከየትኛውም ቦታ እና አካባቢ በመሆን የሚከናወን ሩጫ ወይንም ፈጠን ያለ የዕርምጃ ውድድር እንደማለት ነው።አዲስ ዘመን ግንቦት 11/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=32673
95ad2208ea229ea528eb497af03d874b
c906c640a35645044bc92f96bce009a4
በመተከል ዞን እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ዕርምጃ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን እየሰጡ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ(ኢዜአ):- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ዕርምጃ በርካታ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን ለጸጥታ ኃይሉ እየሰጡ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል አስታወቀ።የህግ ማስከበርና የፀጥታውን ዘርፍ በበላይነት የሚመሩት ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ፤ የጥፋት ቡድኑ በመተከል ዞን በተለይም ቡለንና በቆጂ ወረዳዎች ዜጎችን በመግደል፣ ንብረት የመዝረፍና የማቃጠል አረመኔያዊ ተግባር መፈፀሙን አስታውሰዋል።የተጠናከረ ዘመቻ በማካሄድ በአካባቢው ህግ በማስከበር ሰላምን ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት በርካታ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን ጠቅሰዋል።ታጣቂ ቡድኑ ቀደም ሲል የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ስጋት አድሮባቸው መኖሪያቸውን ለቀው የነበሩ ዜጎችም ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን ሌተናል ጀኔራል አስራት ገልጸዋል።ግብረ ኃይሉ አካባቢውን ከተረከበ በኋላ በተለይ ስጋት ተፈጥሮባቸው የነበሩ አካባቢዎችን በማረጋጋት ወደ ተሻለ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል።በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪና የኮማንድ ፖስቱ የፖለቲካና ህዝባዊ ውይይቶች መሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በዜጎች ላይ ጥቃት የፈፀመውን ታጣቂ ቡድን የማደን ሥራ መቀጠሉን ገልጸዋል።የተፈፀመውን ጥቃት በመምራትና በማስተ ባበር የተጠረጠሩና ጥቃቱን መከላከል ሲገባቸው ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ አመራሮች ላይ ህጋዊና ፖለቲካዊ ዕርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።የጥፋት ቡድኑን ዓላማ ያልተቀበሉ የጉሙዝ ማህበረሰቦችን ጨምሮ በተለያዩ የማህበረሰብ አካላት ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወት ማጥፋት፣ አካል ማጉደልና ንብረት ማውደም መፈፀሙን አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል።ችግሩ እኩይ ዓላማ ያላቸው ኃይሎችን ብቻ የሚመለከት መሆኑን ጠቅሰው፤ “በዘላቂነትመፍትሔ ለማበጀት ግብረ ኃይሉ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው” ብለዋል።ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ የማድረስና ወደ ቀዬአቸው መልሶ የማቋቋም ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል።በሂደቱ የሰላምና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ህዝባዊ ውይይቶች እንደሚካሂዱም አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 24/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38672
349e2fc3a305e3323bae14796ed2f9e6
2e5a56a38898fa53cc0db39853f93dbd
የበርሊን ማራቶን ላይካሄድ ይችላል
ስፖርት
በርካታ የማራቶን የዓለም ክብረወሰኖች የሚሻሻሉበት የበርሊን ማራቶን በዚህ ዓመት የመሰረዝ ወይም የመራዘም እድል ያልገጠመው ብቸኛው ውድድር ነው ማለት ይቻላል። ይህ ታላቅ የማራቶን ውድድር የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ ከመከሰቱና ከመስፋፋቱ አስቀድሞ መስከረም ወር ላይ በመካሄዱ የሌሎቹ ታላቅ ውድድሮች እጣ ፋንታ ሳይገጥመው ቀርቷል። ያም ሆኖ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እስካሁን የሚያቆመው ባለመኖሩና ወደ ፊትም መፍትሄ ማግኘቱ አጠራጣሪ እየሆነ በመምጣቱ በቀጣዩ መስከረም የበርሊን ማታሪን የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል። የውድድሩ አዘጋጆች ሰሞኑን እንደጠቆሙትም ውድድሩን በተለመደው ወቅት ለማካሄድ እስካሁን ውሳኔ ላይ መድረስ አልቻሉም። ውድድሩን ለማካሄድ ወይም ለማራዘም ውይይት እየተደረገ ሲሆን ውሳኔ ላይ ለመድረስ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቀዋል። የጀርመን መንግስት በኮሮና ቫይረስ ስጋት እስከ መጪው ጥቅምት ወር መጨረሻ ከአምስት ሺ ሰው በላይ የሚሰበሰብባቸው ማንኛቸውም መርሃግብሮች ማገዱን ተከትሎ የውድድሩ አዘጋጆች ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ ጠቁመዋል። እንደ በርሊን ማራቶን ሁሉ ዋነኞቹ የዓለማችን የማራቶን ውድድሮች የሆኑት የቦስተንና የለንደን ማራቶን ውድድሮችም በተመሳሳይ ምክንያት መካሄድ ከነበረባቸው ወቅት የመራዘም እድል እንደገጠማቸው ይታወሳል። የበርሊን ማራቶን አዘጋጆች ውድድሩ ካለው ስፋትና ከሚያሳትፈው የሰው ብዛት አኳያ የሚካሄድበት እድል መኖር አለመኖሩን በማጥናት ላይ የሚገኙ ሲሆን ውሳኔ ላይ ለመድረስም የተወሰነ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቀዋል። ለዚህም የውድድሩ አዘጋጆች አሁን ላይ በቫይረሱ ስጋት የተነሳ በሙሉ ሃይላቸው ተገናኝተው መስራት አለመቻላቸው አንዱ እንቅፋት መሆኑን ገልፀዋል። በርካታ የዓለም ክብረወሰኖች የሚመዘገቡበት የበርሊን ማራቶን 2018 ላይ ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ 2፡1፡39 የሆነ አዲስ የዓለም ክብረወሰን በርቀቱ እንዳስመዘገበበት ይታወሳል። ባለፈው መስከረም ደግሞ ቀነኒሳ በቀለ ይህን ክብረወሰን ለማሻሻል በሁለት ሰከንድ የዘገየ ሰዓት ማስመዝገቡ አይዘነጋም። ከቀናት በፊት የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በጀርመን ከ172 ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከ7600 በላይ የሚሆኑ ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል። ይህም የ2020 በርሊን ማራቶን ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ከማሳደሩ ባለፈ እንዲሰረዝ ወይም እንዲራዘም ሊያደርገው እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። አዲስ ዘመን ግንቦት 9/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=32529
788adee6ee5dac6a3824620ea0f82e11
01f73fe2dd71eb57e86861f0d6e6addf
የአበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ከጥንቃቄ ጋር ይቀጥላል
ስፖርት
የወቅቱ የዓለም ራስ ምታት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች አንቀላፍተው ቢቆዩም ከሰሞኑ የአውሮፓ ሊጎች ወደ ልምምድ መመለስን ተከትሎ የስፖርቱ ኢንዱስትሪ መነቃቃት ጀምሯል። አሁንም የኮሮና ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) ስጋት እንዳለ ቢሆንም ጥንቃቄን በተላበሰ መልኩ ወደ ቀድሞው መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ ጥረቶች እየታዩ ነው። በዚሁ ምክንያት ተቀዛቅዞ የቆየው አበረታች ቅመሞችን መከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ነው። ይህ ስፖርትን በተፈጥሯዊው መንገድ ብቻ እንዲካሄድ የማድረግ ጥረት ሊቀዛቀዝ የቻለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ውድድሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ ነው። ይሁን እንጂ ከዓላማው አንጻር ረጅም ጊዜ መውሰዱና መዘናጋቱ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል። በመሆኑም ዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በስሩ ለሚገኙት ብሔራዊ ጽሕፈት ቤቶች መመሪያ ማዘጋጀቱን ከሰሞኑ በድረገጹ አስነብቧል። ይህም በየሀገራቱ የሚገኙ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤቶች ወደ ቀደመ ሥራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ርምጃ ነው። ኤጀንሲው በወረርሽኙ ምክንያት በዓለም ዙሪያ ሲሰሩ የቆዩት ናሙና የመውሰድና ምርመራ የማድረግ ሂደቶችን የቀነሰና አንዳንድ ሥራዎችንም በጊዜያዊነት ማቋረጡን በዘገባው ተጠቁሟል። ነገር ግን አሁን ወደ ሥራ ለመመለስ እንቅስቃሴ መደረግ እንዳለበት የኤጀንሲው ፕሬዚዳንት ዊቶልድ ባንካ ይገልጻሉ። በኤጀንሲው ስር ካሉ ተቋማት ጋር ከወቅታዊው ጉዳይ ጋር በተያያዘ በቅርበት ሲሰሩና ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁን ግን ሥራው እንደቀድሞው መቀጠል ያለበት በመሆኑ፤ በቴክኖሎጂ በታገዘና የናሙና አወሳሰዱን በአዲስ መንገድ ማካሄድ ተገቢ መሆኑን ያመላክታሉ። ለዚህ ደግሞ በጸረ አበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ላይ የሚሰሩ አካላት አዲስ ነገር ለመፍጠር ርብርብ ላይ ይገኛሉ። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኦሊቨር ኒግሊ በበኩላቸው፣ በዚህ ወቅት ናሙናዎችን ከአትሌቶች ለመውሰድ አዳጋች መሆኑን ነው የሚጠቁሙት። ምርመራው መቀጠል የሚገባው አስፈላጊው የጤናና ንጽህና ሁኔታ የተስተካከለ ሲሆን ብቻ ነው። የአትሌቶችና በዙሪያቸው ያሉ አካላት ጤናም ኤጀንሲው ትኩረት የሚሰጠው ቀዳሚ ጉዳይ ነው። ተቋሙ የአትሌቶችን ናሙና በመውሰድ አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚነታቸውን በምርመራ መለየት ብቻም ሳይሆን የጤና ግለ ታሪካቸውንም መመዝገብ ሌላው ተግባሩ ነው። ንጹህ ስፖርት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ግንዛቤ ማስጨበጥም እንዲሁ። በመሆኑም በቀጣይ ሳምንታት ከብሔራዊ ተቋማቱ ጋር በመሆን ሥራው በምን መልኩ መቀጠል ይገባዋል በሚለው ላይ መፍትሄ በማፈላለግ ወደ ሥራ የሚመለስ እንደሆነ አብራርተዋል። የሯጮቹ ሀገር ኢትዮጵያም የኤጀንሲው አባል ሀገር በመሆን ንጹህ ስፖርት እንዲካሄድ ሚናቸውን ከሚወጡት መካከል ትጠቀሳለች። ተሞክሮውን ለሌላው ዓለምም ማጋራት የቻለና በሥራው ምስጉን የሆነ ጽሕፈት ቤትም በአጭር ጊዜ ለማቋቋም መቻሉ ይታወቃል። በመላው ዓለም ባጠላው በዚህ የወረርሽኝ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤት እንቅስቃሴውን በምን መልኩ እያከናወነ ይገኛል? የሚለውን የጽሕፈት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ያስረዳሉ። የተቋሙን ውስጣዊና ውጫዊ እንቅስቃሴ በሁለት የሚከፍሉት ዳይሬክተሩ፤ የኮሮናን ቫይረስ በመከላከል ረገድ ሠራተኞችን የመቀነስና የንጽህና ቁሳቁስን የማዘጋጀት ሥራዎች መከናወናቸውን ይጠቁማሉ። ሁለተኛውና ከተቋሙ ውጪ ከአትሌቶች ጋር በመገናኘት የሚከናወነው ደግሞ ከአበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ጋር የተያያዘው ሥራ ነው። ይሁን እንጂ ከአትሌቶች ናሙና መውሰድ በእጅጉ ለንክኪ የሚያጋልጥ በመሆኑ አትሌቶችንም ሆነ በምርመራው ተሳታፊ የሆኑ ባለሙያዎችን ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ ለጊዜው ገታ ተደርጓል። ነገር ግን ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ማቆም የማይቻል በመሆኑ ለቫይረሱ አጋላጭ ይሆናሉ የሚል ስጋት ያሳደሩ ሥራዎችን ፎርማት ለመቀየር መሞከሩን ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። በዚህም መሠረት አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቃሚ የሆኑ አትሌቶችን የማጋለጥ፣ አትሌቶች ባዮሎጂካል ፓስፖርት ፕሮግራም ሥራን የማጠናከር እንዲሁም ሌሎች ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህ ጊዜ ውድድሮች የተቋረጡ ቢሆንም ስፖርተኞች ግን በየግላቸው በቤታቸው ውስጥ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አላቆሙም። ይህንን ተከትሎም ከውድድር ውጪ የሚወሰዱ አበረታች ንጥረ ነገሮችን ከመውሰድ እንዲቆጠቡም ያሳስባሉ። በጥቅሉ በጊዜያዊነት ንክኪ ካለባቸው ሥራዎች በቀር ሌሎች ሥራዎች እንደቀጠሉ ሲሆን፤ የአድራሻ ምዝገባቸውን በመደበኛ መልኩ የሚያደርጉ በመሆኑ በዚህ ላይም መዘናጋት አይገባም። ዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች መድኃኒቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በመግለጫው ባመላከተው መሠረት፤ ጽሕፈት ቤቱም እንደቀደመው የአትሌቶችን ናሙና ወደመውሰድና መመርመር ሥራው ለመመለስ የሚያስችለውን ሁኔታ እያጠና ይገኛል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ከሆነም ስፖርተኞች ከባለሙያዎች ጋር የሚኖራቸውን ንክኪ በሚቀንስና ለበሽታው አጋላጭ በማይሆን መልኩ መፍትሄ እንደተገኘ በቀጥታ ምርመራው የሚጀመር ይሆናል። በብሔራዊ ቡድን፣ በክለብ እና በማሰልጠኛ ተቋማት የተያዙ አትሌቶች እንዲሁም በቡድን ሆነው የሚሰሩ ሰልጣኞች በዚህ ወቅት ልምምድ አቋርጠው በቤታቸው ይገኛሉ። ምንም ዓይነት የቡድን እንቅስቃሴ የማይፈቀድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አትሌቶች በያሉበት አነስተኛ ልምምድ ብቻ የሚያደርጉ ይሁን እንጂ አሁንም እንደ ተቋም አስጊ ሁኔታዎች መኖራቸው አልቀረም። ይህም ወቅታዊውን ሁኔታ ሽፋን በማድረግ የተከለከሉ ንጥረነገሮችን የመጠቀም አዝማሚያ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት ነው። እስካሁን በተጨባጭ የተገኘ መረጃ ባይኖርም በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ እንደ ተቋም ስጋቱ አለ። ከአትሌቶች ባሻገር ከጀርባ በመሆን አጋላጭ የሆኑ አካላት አበረታች ቅመሞችን እንዲጠቀሙ በመገፋፋትና በማሳመን የሕግ ጥሰት የመፈጸም አዝማሚያ ሊኖር ይችላል የሚል ግምት አለ። በመሆኑም ስጋቱን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ ነው የሚገኙት። በስፖርተኞች በኩል ስለ ጉዳዩ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋትም በመገናኛ ብዙኃን በመታገዝ መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ። በተመረጡ መገናኛ ብዙኃን ላይም የማስታወቂያ እንዲሁም የማንቂያ ሥራዎች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙት ዳይሬክተሩ በጽሕፈት ቤቱ ድረገጽም መረጃዎችን እያስተላለፉ ይገኛል። ይህም አትሌቱ በሚመቸው መንገድ መረጃ እንዲያገኝ ያስችለዋል። በቀጣይም በመደበኛነት ማስታወቂያዎቹ የሚተላለፉባቸውን የመገናኛ ብዙኃን ቁጥር ለመጨመር ታቅዷል። ሌላው ጽሕፈት ቤቱ በትኩረት እየሄደበት ያለው የሕግ ማዕቀፍ የማሻሻል ሥራ ነው። ኤጀንሲው የጸረ አበረታች ቅመሞች ሕግን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን አሻሽሏል፤ በመሆኑም በጽሕፈት ቤቱ በኩል እአአ በ2021 ተግባራዊ የሚሆኑ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን ለመከለስ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። በመጨረሻም ዳይሬክተሩ ስፖርተኞችም ሆኑ ሌሎች የሀገሪቷ ዜጎች የሕክምና ባለሙያዎችን ምክር በመተግበር በዓለም ላይ ከተከሰተው ወረርሽኝ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ስፖርተኞች፣ የስፖርት ባለሙያዎች፣ የስፖርት አመራሮች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው በአበረታች ንጥረ ነገር መከላከልና መቆጣጠር ሥራው ለአፍታ የቆመ ባለመሆኑ መዘናጋት እንዳይኖር ዳይሬክተሩ ያሳስባሉ። ዓለም አቀፉ ኤጀንሲም ሆነ የዓለም አትሌቲክስ ይህ ጊዜ ሲያልፍ ስፖርቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በጥንቃቄ እየተመለከቱት ነው። በዚህ መሠረት የሚመለከታቸው አካላት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ተጠቃሚነታቸው ከተረጋገጠም ጽሕፈት ቤቱ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እንዲሁም የወንጀል እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ የማይል በመሆኑ ስፖርተኛው በመደበኛ ጥንቃቄው መቀጠል እንዳለበት ዳይሬክተሩ አስቀምጠዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 10/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=32614
63aaefa72e4685a78c07f61f96348365
1e5b708ea52a6dc2098961124a2a4f47
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ አነሳች
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያ ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠት (Extradition) የሚደነግገው የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ አነሳች። የፌዴራል ሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ለዝግጅት ክፍሉ በላከው መግለጫ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ ያላትን ተዓቅቦ አንስታለች ብሏል።ኢትዮጵያ የኮንቬንሽኑን አንቀጽ 44 አስመልክቶ ተዓቅቦ (reservation) እንዳላት የኮንቬንሽኑ ምዕራፍ ሦስት ውስጥ የተመለከተውን የሙስና ወንጀልን ወንጀል አድርጎ መደንገግና ምዕራፍ አራት ዓለም አቀፍ ትብብርን አስመልክቶ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2010 አስከ 2015 ባለው ጊዜ የነበራትን አፈጻጸም ለገምጋሚ አገራት አቅርባ ማስገምገሟን ገልጿል። የአፈጻጸም ግምገማን ተከትሎ ኢትዮጵያ እንድታስተካክል ተሰጥተዋት ከነበሩ ምክረ ሃሳቦች አንዱ ከላይ በተጠቀሰው የኮንቬንሽኑ አንቀጽ ላይ ያላት ተዓቅቦ እንደነበር በመግለጫው ተመልክቷል።በዚህ ግምገማ መሠረት ኢትዮጵያ አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ ያነሳች ሲሆን፤ የፕሮቶኮሉን ድንጋጌዎች በሙሉ በማክበር ግዴታዎቿን እንደምትወጣ አረጋግጣለች። አንቀጽ 44 ላይ ያላት ተዓቅቦ መነሳቱን መቀመጫውን ኦስትሪያ ቬና ላደረገው የተባበሩት መንግሥታት የአደገኛ ዕፅ እና ወንጀል መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት (UNODC) እንዳስታወቀችም የኮሚሽኑ መግለጫ አመልክቷል። ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አባል አገር በመሆን በኮንቬንሽኑ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ለመተግበር በመስማማት በፊርማዋ አጽድቃ በሕግ አውጪ ፓርላማዋ በአዋጅ ቁጥር 544/1999 ኮንቬንሽኑን በማጽደቅና የሀገሪቱ የሕግ አካል በማድረግ ኮንቬንሽኑን ከሚተገብሩ አገራት መካከል ትጠቀሳለች፡፡ አዲስ ዘመን ታህሳስ 24/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38673
084adbe590142d2b7afe8ffd2182b24b
35430572a053b74df06f2fa400489660
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል
ስፖርት
ዓለምን በአንድነት እያስጨነቀ የሚገኘው ወቅታዊ ጉዳይ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ መሆኑ ይታወቃል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያስቻለ ፈውስ በዓለም ሳይንቲስቶች፣ የህክምና ጠቢባንም ይሁን በሃያላን አገራት አቅም ማምጣት አልተቻለም። ይህም የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ከመለወጥ አንስቶ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በርካታ አሉታዊ ተፅዕኖው እንዲያርፍ አድርጓል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ተጽዕኖ እያስተናገደ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን መረጃዎች ያመላክታሉ። በወረርሽኙ ሳቢያ ትልልቅ የስፖርት ውድድሮች በመራዘማቸው፣ በመሰረዛቸው እና በመስተጓጐላቸው ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ገቢ እንደሚያሳጣው የተለያዩ ትንበያዎች አመልክተዋል። የስፖርት ኢንዱስትሪውን በስፖንሰ ርሺፕ የሚደግፉ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የበጀት ቀውስ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትኬት ሽያጭ ከማርኬቲንግና ከተለያዩ ንግዶች የሚገኙ ገቢዎች መቆማቸው ሁሉንም ስፖርት ጎድቷቸዋል፡፡ በተለይ የእግር ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። በዚህ ዓመት የእግር ኳሱ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ሲጠበቅ ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል። የስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ ሌሎች መደበኛ እንቅስቃሴዎችን በቅርብ ጊዜ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች እየታዩ አለመሆኑ፤ በኢንደስትሪው ላይ የሚደርሰው ቀውስ እንዲያሻቅብ እንደሚያደርገው ተነግሯል። የቫይረሱ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ በመሆኑ ታላላቅ ስፖርታዊ ውድድሮች በቅርቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ጠባብ መሆኑ እየተነገረ ባለበት ወቅት ቢቢሲ ከቀናት በፊት ይዞት የወጣው መረጃ ተስፋ ሰጪ ሆኗል። ቢቢሲ ፤ የዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ሊጎች በዝግ ስታድየምም ቢሆን የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሃግብሮች ለማጠናቀቅ በቅርቡ ወደ ውድድር ሊመለሱ መሆኑን ጽፏል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግንባር ቀደም ሊሆን እንደሚችል አስነብቧል። የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሃግብሮች ለማጠናቀቅ ማሳባቸውን ጠቅሶ፤ በተለይ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል ሲል አስነብቧል። የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ባለሙያዎች ግን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በትልቅ ደረጃ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እንዳይመለሱ ምክራቸውን መለገሳቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ የዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ሊጎች በዝግ ስታድየምም ቢሆን የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሃግብሮች ለማጠናቀቅ የተለያዩ ሀገራት ሊጎች እንደ አማራጭ እየቀረበ ይገኛል። በዝግ ስታዲየም ውድድሮችን አማራጭን ወደ ተግባር ለመቀየር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቆርጠው መነሳታቸውን አስነብቧል። የ2020 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር የተቋረጠው። ሊጉ የውድድር ዘመኑ ሊጠናቀቅ 92 ጨዋታዎች ይቀሩታል። የቫይረሱ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ መሄዱን ተከትሎም የውድድር ዘመኑን በመደበኛው መልኩ ለማካሄድ ለመመለስ የሚያስችል ተስፋ የለም። የ2020 ውድድር ዘመን 92 ጨዋታዎችን እንዴት እናጠናቅ በሚለው ዙሪያ የሊጉ ክለቦች የቪድዮ ስብሰባ አድርገዋል። በስብሰባው ላይ እንደ ሕክምና ባለሙያዎች ያሉ ያገባቸዋል የተባሉ ሰዎችም ተገኝተው ነበር። ክለቦች ሊጉ በቀላሉ ወደ ውድድር እንደማይመለስ መግባባት ላይ ደርሰዋል። የውድድር ዓመቱን ለማጠናቀቅ የተቀሩትን ውድድሮች በዝግ ስታዲየም ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውን ቢቢሲ አስነብቧል። በቪዲዮ ስብሰባ ወቅት «የሊጉ ክለቦች ይህን ለማድረግ ደግሞ ቢያንስ 10 ገለልተኛ ሜዳዎች ያስፈልጋሉ ። ገለልተኛ ሜዳዎችን መጠቀም ያስፈለገው ደጋፊዎች ከሜዳ ውጪም ቢሆን እንዳይሰበሰቡ በማሰብ ነው። አልፎም የሚመረጡት ሜዳዎች ከፖሊስና የስፖርት ሜዳዎችን ደህንነት ከሚመረምር አካል ይሁንታ ያገኙ መሆን አለባቸው» መባሉን በዘገባው አስፍሯል። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሳምንት ሁለት ጊዜ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይደርግላቸዋል። በየቀኑ ደግሞ የበሽታው ምልክት ታየባቸው አልታየባቸው የሚለው ይለካል። አልፎም ሜዳዎች በየጊዜው ንፅህናቸው ይጣራል ተብሏል። ተጫዋቾች ከጨዋታ ውጪ ባሉት ጊዜያት ሁሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ አለባቸው። በውድድር ስፍራዎች ውስጥም ምግብ መብላትም ሆነ ገላን መታጠብ እንዳይችሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክቷል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሊጉን ለማ ጠናቀቅ በገለልተኛ ሜዳ ውድድሮችን ለማድረግ ከስምምነት መድረስ ቢችሉም ከሀገሪቱ መንግስት በኩል የሚኖረውን ተቀባይነት ምን ሊሆን ይችላል ? የሚለው ምላሽ የሚያሻ መሆኑን ዘገባው አንስቷል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው። የፕሪሚየር ሊጉ አስተዳዳሪ አካል መንግሥት ይሁንታ ሲሰጥ ብቻ ወደ ሜዳ የሚመለስ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። የውድድር አመቱ የቀሩትን 92 ጨዋታዎች ለመጫወት ከስምምነት ቢደርሱም የሀገሪቱ መንግስት ውሳኔ ምን ሊሆን እንደሚችል የተባለ ነገር አለመኖሩን ዘገባው ጠቅሷል። የዚህ ዓመት ወድድር ይቋረጥ የሚል ሐሳብ ከየትኛውም ክለብ አልመጣም ነበር። በመሆኑም በሁሉም የሊጉ ክለቦች በኩል የተወሰነው ውሳኔ ከመንግስት ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መቋጫው በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስፍሯል። የእንግሊዝ መንግሥት እንቅስቃሴዎች ቀስ በቀስ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ካደረገ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዝግ ሜዳ ወደ ውድድር እንደሚመለስ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=31713
aa80469b1aeaeecbf46038af5e5d2477
982986101bc0dcb4fb98ac2c435347af
ኦሊምፒክ ኮሚቴ አትሌቶችን እደግፋለሁ አለ
ስፖርት
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከውድድር ውጪ ለሆኑ ብሔራዊ አትሌቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ምንም እንኳ ለሁሉም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ቢሆንም፣ ብሔራዊ አትሌቶችን በሒደት ከገንዘብ ድጎማ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ እየሠራ መሆኑ ፕሬዚዳንቱ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ አስታውቀዋል፡፡ ከድጋፉ ባሻገር የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት ለአገሮች በሰጠው ነፃ የትምህርት ዕድል ኮታ መሠረት ኤሊት አትሌቶች ዕድሉን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ ብሔራዊ ተቋማት ችግሩ በአትሌቶች ላይ ሥነ ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዳያሳድር የሚችሉትን እያደረጉ ይገኛሉ። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት አትሌቶችንና መሰል ሙያተኞችን መደጎሙ አይዘነጋም፡፡ አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012
https://www.press.et/Ama/?p=31712
d0749959d4d5edf763bf108a42a73620
b64df88ee77d7e21f8a290922665ac3a
ካፍ ለአፍሪካ እግር ኳስ አባል አገሮች የሰጠው ቀነ ገደብ ዛሬ ይጠናቀቃል
ስፖርት
አፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ አባል ሀገራት የተቀመጠላቸው ቀነ ቀደብ ዛሬ ይጠናቀቃል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የየአገሮቹ የውስጥ ሊግ ለማስቀጠልም ሆነ ለማቋረጥ መደረግ ስለሚገባው የጋራ አቋም አገሮች ከየራሳቸው የሊግ አደረጃጀትና ሁኔታ በመነሳት የሚኖራቸውን ሐሳብ በሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም መጠየቁ ይታወሳል። ለአፍሪካ እግር ኳስ አባል አገሮች በጻፈው ደብዳቤ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የየአገሮቹ የውስጥ ሊግ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት መቀጠልም ሆነ መቋረጥ ካለበት አገሮቹ የየራሳቸውን ሐሳብና ዕቅዳችሁን አሳውቁኝ ነበር ያለው፡፡በዕቅዱ መካተት ይኖርባቸዋል ብሎ የጠቀሳቸው ነጥቦች፣ ሊጉ የተጀመረበትና የሚጠናቀቅበት ጊዜ እንዲሁም ሊጉ የሚቀረው የጨዋታ መርሐ ግብርና የቡድኖች የደረጃ ሰንጠረዥ፣ ሊጉ የተቋረጠበት ወር፣ የሚቀረው የጨዋታ ብዛት፣ ቀሪውን ውድድር እናጠናቅቃለን ለሚሉ ሊከተሉት ስላሰቡት የጨዋታ ሥርዓትና ሁኔታ፣ ማስቀጠል አንችልም የሚሉ ካሉም እንዲሁ በዝርዝር ተብራርቶላቸዋል፡፡ ጥቅሙን በሚመለከት ተቋሙ ወደፊት ውድድሮችን ከመምራት ጀምሮ የሚያከናውናቸው ዕቅዶች ከአባል አገሮች ዕቅዶች ጋር እንዳይጋጩ የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይችል ዘንድ መረጃ ለማሰባሰብ እንደሆነ አስገንዝቧል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ደብዳቤውን ከመላክ ባሻገር አባል ሀገራቱ ውሳኔያቸውን እስከ ሚያዚያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እንዲያሳውቁት ነበር ያሳሰበው። ካፍ ሀገራቱ በውስጥ ውድድራቸውን በተመለከተ ውሳኔ የሚያስተላልፍበት ቀን በዛሬው እለት የሚጠናቀቅ ይሆናል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012
https://www.press.et/Ama/?p=31720
f5776257b0f643ba235b83f1fb8902af
3a6997daa61fb58690997bfb9f80ec3a
የተራዘመው ኦሊምፒክና የዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች የገንዘብ ጥያቄ
ስፖርት
የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለአስራ ስድስት ወራት ከመራዘሙ አስቀድሞ የተፈራው ሊደርስ የሚችለው የፋይናንስ ቀውስና ትልቅ የገንዘብ ኪሳራ መሆኑ ይታወቃል።ኦሊምፒኩ እንደተራዘመ ይፋ ከተደረገም በኋላ የአዘጋጇ አገር ጃፓን መንግስትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሚደርሰው ኪሳራና ተጨማሪ ወጪ ዙሪያ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው አልቀረም።ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ገና ከጅምሩ ኪሳራውን ለማካካስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጋሩት ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም አሁን አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ትልቅ ባለድርሻ አካል የሆነው የዓለም አትሌቲክስ ከተራዘመው ኦሊምፒክ ገቢ ጋር በተያያዘ ድርድር መጀመሩን አሳውቋል።የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንቱ ሴባስቲያን ኮ በዚህ ጉዳይ ላይ ከዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር ንግግር መጀመራቸውን ከትናንት በስቲያ ይፋ አድርገዋል። የኢንሳይድ ዘ ጌምስ ሃተታ እንደሚያመለክተውም በርካታ ዓለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ከተራዘመው ኦሊምፒክ ሊያገኙት የነበረውን ገንዘብ መጠየቅ እንደሚጀምሩ ተረጋግጧል።የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩ በመራዘሙ ምክንያት ብቻ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ ገብቶ በሚዳክርበት በዚህ ወቅት ባለድርሻው የሆኑት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ድርሻቸውን ለመጠየቅ ወደ ኋላ አለማለታቸው አስደንጋጭ ዜና ሆኗል። አሁን ድርሻውን የጠየቀው የዓለም አትሌቲክስ ትልቁ ባለድርሻ ሲሆን የዓለም ውሃ ዋና እና የዓለም ጅምናስቲክ ፌዴሬሽኖች በተከታይነት ትልቅ ድርሻ አላቸው።እነዚህ ፌዴሬሽኖች ብቻ ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ቢያንስ እያንዳንዳቸው አርባ ሚሊዮን ዶላር ድርሻ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው እንደማይቀር ታውቋል።ይህም ኦሊምፒክ በመራዘሙ ብቻ በርካታ ውስብስብ ፈተናዎች ውስጥ ለገባው የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል። ‹‹እንደ አብዛኞቹ የኦሊምፒክ ስፖርቶች የዓለም አትሌቲክስም ከኦሊምፒክ የቴሌቪዥን ስርጭት በሚያገኘው ገቢ ላይ ጥገኛ ነው›› ያሉት ሴባስቲያን ኮ ባለፉት አራት ዓመታት ይህን ገቢ ለማግኘት ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው ይህን ገንዘብ ማግኘት የግድ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የዓለም አቀፉ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከኦሊምፒኩ የሚያገኘው ገቢ ለጊዜው ቢራዘምም እስከ 2020 አጋማሽ ገቢ ሊደረግ እንደሚገባ ከወር በፊት ማሳወቁ ይታወሳል።የዓለም አቀፉ እጅ ኳስ ፌዴሬሽንም ተመሳሳይ ሃሳብ ያንፀባረቀ ሲሆን ሌሎችም በቀላሉ ሃሳብ እንደማይቀይሩ ይጠበቃል።በተለይም የዓለም አትሌቲክስ ኦሊምፒኩ በመራዘሙ በ2021 በአሜሪካ ዩጂን የሚያካሂደው የዓለም ቻምፒዮና ላይ ተፅዕኖ በመፍጠሩና ጥያቄውን በቀላሉ ወደ ኋላ እንደማይመልሰው ተገምቷል።የ2021 ዩጂን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከተራዘመው ኦሊምፒክ ጋር የሚካሄድበት ወቅት የሚጋጭ በመሆኑ ወደ 2022 እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል። ላለፉት ሰባት ዓመታት የበለጠ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው የኦሊምፒክ ውድድር መራዘሙ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ማስከተሉ የአዘጋጆቹ ራስ ምታት እንደሚሆን ቀድሞም የታወቀ ነው።ይህ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ የጃፓን መንግስትንም ይሁን ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴን በእጅጉ ሊፈትን እንደሚችል በባለሙያዎች አስተያየት ሲሰጥበት የቆየ ሲሆን ሁለቱ አካላት ኪሳራውን ለማካካስ እንደሚደጋገፉና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ለዚህ እንዲዘጋጁ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲገጥሙት ትልቅ ተቋም እንደመሆኑ የመድህን ዋስትና እንዳለው ይታወቃል።አሁን የገጠመው ግን ካለው የመድህን ዋስትና አቅም በላይ በመሆኑ ነው እዚህ ችግር ውስጥ የተዘፈቀው።ስለዚህ የመድህን ዋስትናው በህጉ መሰረት የሚሸፍነው ኪሳራ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ ኪሳራውን የሚያካክስበት አንድ ነገር መፈጠሩ የግድ ይሆናል።ይህንን ተጨማሪ ኪሳራ የጃፓን መንግስት እንደሚሸፍን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ቀደም ሲል በተለያዩ አጋጣሚዎች መስማማታቸው ቢገለፅም አሁን የሃሳብ ለውጥ እንዳደረጉ የሚጠቁሙ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ውዝግቦች መነሳታቸው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=31846
7c3a33a43c8527884df820313c620e7e
c57ef452850e760a86c3743811e5a17b
ቡንደስሊጋው በባዶ ስታዲያም ከ10 ቀናት በኋላ ይጀመራል
ስፖርት
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የዓለምን ሕዝብ በአንድ ልብ የጭንቀት ቋት ውስጥ በመክተት የተጽእኖ በትሩን ማሳረፍ ከጀመረ አራት ወራት አለፉት። በወቅቱ በሀገረ ቻይና ውሃን ከተማ የወረርሽኙ መከሰት ሲሰማ ጉዳዩ እንደዋዛ፣ እንደዘበት ነበር የዓለም ሕዝብ ያደመጠው። ኮቪድ 19 መነሻውን በአንድ ሀገር ያድርግ እንጂ የስርጭቱን አድማስ በፍጥነት በመጨመር ዓለምን አዳርሷል። የቫይረሱ መከሰት ዜና ይፋ ሲደረግ ጉዳዬ ያላለውን የዓለም ሕዝብ በአንድ ልብ ትኩረቱና ስጋቱ ኮሮና ከሆነ አራት ወራት አልፈውታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሩብ ሚሊዮን ሰዎችን እንደቅጠል ያረገፈው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ጥረቶች ቢደረጉም ዛሬም መፍትሄ ማግኘት አልተገኘም። በዓለም ሳይንቲስቶች፣ የህክምና ጠቢባንም ይሁን በኃያላን አገራት አቅም ማምጣት አለመቻሉ ደግሞ የተጽእኖውን በትር እንዲበረታ አድርጎታል። ኮቪድ-19 ከሰው ልጆች ሕይወት ባሻገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጉዳት ያልዳሰሰው ምድራዊ ኃይል የለም። ወረርሽኝ በእጅጉ ከጎዳቸው ዘርፎች መካከል ስፖርቱ በዋናነት ይጠቀሳል። የስፖርት ኢንዱስትሪውን በስፖንሰር ሺፕ የሚደግፉ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የበጀት ቀውስ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትኬት ሽያጭ ከማርኬቲንግና ከተለያዩ ንግዶች የሚገኙ ገቢዎች መቆማቸው ሁሉንም ስፖርት ጎድቷቸዋል። በተለይ የእግር ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። በዚህ ዓመት የእግር ኳሱ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ሲጠበቅ ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል። የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር የሚቻል እንዳልሆነ እየወጡ የሚገኙት መረጃዎች የስፖርት እንቅስቃሴን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ማድረግ ይጀመራል የሚል ተስፋ እንዳይጣል አድርጓል። ወረርሽኙ በታላላቆቹ የአውሮፓ ክለቦችን ጨምሮ ሁሉም የስፖርት ዘርፍ ላይ እያሳደረ ያለውን የፋይናነስ ቀውስን እንዲያሻቅብ ያደርገዋል ተብሏል። ከሰሞኑ እየወጡ የሚገኙት መረጃዎች ግን ይሄንን የሚሽሩ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል። በአንዳንድ ሀገራት ላይ ወረርሽኙን መቆጣጠር እየተቻለ መሆኑን ተከትሎ፤ ስፖርታዊ ውድድሮች ሊያደረጉ መሆኑ አስነብቧል። መራሂተ መንግሥት አንጌላ መርኪል በሀገሪቱ የኮሮና ወረርሽኝ እያሳደረ ያለው ተጽእኖ በተመለከተ ከፌዴራል መንግሥቱ ሹማምንቶች ጋር ትናነት በቪዲዮ ኮንፍረንስ ውይይት አድርገዋል። የጀርመን ቦንደንስሊጋው ከአስር ቀን አልያም ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ ለማስጀመር የሚያስችለው የስምምነት ሰነድ በውይይቱ ላይ መቅረቡን አመልክቷል። በሀገሪቱ 16ቱም ግዛቶች ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር በመጣመር የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አመርቂ ውጤት ማምጣታቸው ተከትሎ መንግሥት ጥሏቸው የነበሩ ገደቦችን እንዲነሱ ውሳኔ ሊያስተላልፍ መቻላቸውን ዘገባው አትቷል። መራሄተ መንግሥት አንጌላ መርክል እንደተናገሩት «ጀርመን የቫይረሱን የስርጭት ፍጥነት ለመቀነስ የወጠነችው ግብ በመሳካቱ የንግድ ቦታዎች እንዲከፈቱና ደንበኞቻቸውን ማስተናገድ ይችላሉ። ከዚህም በተጨማሪ ቡንደስሊጋውም እንዲጀመር ተወስኗል» ማለታቸውን ጠቅሶ፤ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ከተቋረጡ የሊግ ውድድሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የጀርመን ቡንደስሊጋ በቅርቡ ወደ ውድድር የሚመለስ ይሆናልም ብሏል። ጀርመን እንዲህ ዓይነቱ መረጃ ከተሰሙባቸው ጥቂት ሀገራት ግንባር ቀደም መሆን ያስችላታል የሚለው ዘገባው፤ የጀርመን እግር ኳስ ሊግ ቡንደስሊጋው የፊታችን ግንቦት 1 ወደ ውድድር በመመለስ ያለ ተመልካች ውድድሮቹን አድርጎ ለማጠናቀቅ ዝግጁ እንደሆነ ሲገልጽ መቆየቱን አስታውሷል። ቡንደስሊጋውን እና የሁለተኛ ዲቪዥን ጨዋታዎችን የሚያስተዳደረው የጀርመን እግር ኳስ ሊግ ከ36 ፕሮፌሽናል ክለቦች ጋር ከሳምንት በፊት በነበረው ውይይት የዘንድሮውን የውድድር ዓመት ያለተመልካች የመጨረስ ፍላጎት እንዳለው ከስምምነት ተደርሶ ነበር። የጀርመን እግር ኳስ ሊግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክርስቲያን ሲፈርት ቦንደንስሊጋው ከአስራ ቀናት በኋላ እንዲጀመር በተላለፈውን ውሳኔ በእጅጉ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። በውድድሩ ተሳታፊ ክለቦች መካከል ውድድሩን መስመር በያዘ መልኩ ለማካሄድ ቀደም ሲል የስምምነት ሰነድ መዘጋጀቱን ሥራ አስፈጻሚው ገልጸው፤ «ግጥሚያዎቹ ከመጀመራቸው በፊት ለሁለት ሳምንታት በለይቶ ማቆያ፤ ምናልባትም በስልጠና ካምፖች ውስጥ እንዲሆኑ ይጠይቃል። በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዲቪዚዮን 36 ቡድኖች ውድድራቸውን እንዲጀምሩ የሚደረግ መሆኑ በሰነዱ ተካቷል። ክለቦች የሚደርስባቸውን የምጣኔ ሀብቱን ጉዳት መቀነስ እንዲቻል ከግንዛቤ በማስገባት ነው» ሲሉ አስተያየታቸውን መስጠታቸውን ዘገባው አስፍሯል። ቢቢሲ በዚሁ ዘገባው ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ከተቋረጡ የሊግ ውድድሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የጀርመን ቡንደስሊጋ ወደ ውድድር እንዲመለስ መደረጉን ትልቅ ተስፋ ይሰጣል መባሉን የገለጸው ዘገባው፤ የጀርመን ቦንደንስሊጋ በቅርቡ መጀመሩ ስጋትና ቅሬታ ያስነሳ መሆኑንም አያይዞ አመልክቷል። በጀርመን ከሚገኙ ክለቦች አንዱ በሆነው ኮሎኝ ክለብ ተጫዋች የሆኑ ሦስት ተጫዋቾች በኮሮና ተሐዋሲ ተጠቅተዋል። በገለልተኛ ቤተ-ሙከራ ውስጥ ጠቅላላ የቡድኑ አባላት በተደረገላቸው ምርመራ ከሦስቱ በስተቀር ነጻ ተብለዋል። የጀርመን ቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ውድድር ለመጀመር ፍቃድ ማግኘቱ አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ቅሬታ መነሳቱን ዘግቧል። የጀርመን ቡንደንስሊጋ በቅርቡ በመመለሱ ቅሬታን ከፈጠረባቸው አካላት መካከል የተለያዩ ክለብ ተጫዋቾች መሆናቸው አያይዞ አንስቷል። ተጫዋቾቹ «ውድድሩ የሚጀምርበት ጊዜ ተፋጠነ» ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል። ዓለም አቀፍ ስጋት ለሆነው የኮሮና ወረርሽኝ ክትባት አልያም መድሃኒት አልተገኘም። የኮሎኝ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በቫይረሱ መጠቃታቸው በታወቀበት ሁኔታ ወደ ውድድር በቅርቡ መመለስ አደጋው ከፍተኛ ይሆናል። ከዚሁ ትይዩ ደግሞ በሀገሪቱ የሰዎች እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ባልተፈቀደበት በዚህ ወቅት የጀርመን እግር ኳስ ሊግ አስተዳዳሪዎች ፍቃድ ማግኘታቸው ግርምትን መፍጠሩን አትቷል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 30/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=31911
113a0537c5784a5e5d933806ab29d347
d72f0cca261bbd4f4d28a62fa25e7ecb
የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የፈታኙ ወቅት ተሞክሮ
ስፖርት
የዓለማችን ኮከብ አትሌቶች በዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) በተስፋፋበት ወቅት በምን ሁኔታ ቀናቸውን እያሳለፉ እንደሚገኙ የስፖርቱን ዓለም ሰዎችና ሌላውን ማህበረሰብ ከማስተማር አኳያ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን እያገኘ መሆኑ ይስተዋላል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የአትሌቲክስ የጀርባ አጥንት የሆኑትና አትሌቶችን ላሉበት ደረጃ ትልቅ ሚና የሚጫወቱት አሰልጣኞች ሥራቸውን በምን መልኩ እያከናወኑ እንደሚገኙ ከሥራቸውና ከቫይረሱ ባህሪ አኳያ ብዙዎች ጥያቄ ሲያነሱ ይስተዋላል፡፡ የዓለም አትሌቲክስም በድረ ገጹ በተለያዩ ዓለማት ቻምፒዮኖችን ያፈሩ አሰልጣኞች በዚህ ወቅት ሥራቸውን በምን መልኩ እየከወኑ እንደሚገኙ የተለያዩ ቅኝቶችን በማቅረብ ሌሎች እንዲማሩበት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ በዓለም አትሌቲክስ ተሞክሯቸውን እንዲያጋሩ ከተመረጡት አሰልጣኞች መካከል አንዱ ደግሞ የዓለም ሁለተኛው የማራቶን ፈጣን ሰዓት ባለቤቱ ቀነኒሳ በቀለ አሰልጣኝ መርሻ አስራት ናቸው፡፡ አትሌቱ በሦስት ኦሊምፒኮች ተሳትፎው ወርቃማ ታሪክ እንዲጽፍ ከጀርባ በመሆን ከፍተኛውን ድርሻ የተጫወቱት አሰልጣኝ፣ በዚህ የውድድር ዓመት ኮከቡ አትሌት በለንደን ማራቶን የርቀቱን ክብረወሰን እንዲሁም በጃፓኗ ቶኪዮ ለማካሄድ በታሰበው ኦሊምፒክ በማራቶን አራተኛውን ድል ለማስመዝገብ ትልቅ ዝግጅት አድርገው ነበር፡፡ የኦሊምፒኩንና የተጠባቂውን ለንደን ማራቶን መራዘም ተከትሎም ቀነኒሳ ከምንጊዜም ተቀናቃኙና የወቅቱ የማራቶን የዓለም ባለ ክብረወሰን ከሆነው ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ ጋር በተንቀሳሳሽ ምስል የታገዘ ውይይት ማድረጋቸውን ኤንኤን ትሬኒንግ የተባለው ድረገጽ አስመልክቷል፡፡ በዚህም አትሌቶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቤታቸው በመሆን የግል እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አሰልጣኞች ዓለም ውጥረት ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት ሥራቸውን በምን መልኩ ይከውናሉ፣ ቀናቸውንስ እንዴት ያሳልፉታል፣ አትሌቶች ከልምምድ እንዳይርቁና ብቃታቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ የአሰልጣኞቹ ሚና በምን መልኩ አትሌቶች ጋር እየደረሰ ይገኛል? ለሚለው የአምስትና አስር ሺ ሜትርን ክብረወሰን ለረጅም ዓመት ሳያስደፍር ይዞ የቆየው አትሌት ቀነኒሳ አሰልጣኝ ተሞክሯቸውን ያጋራሉ፡፡ አሰልጣኝ መርሻ የመጀመሪያው ቁም ነገር ዓለም የገጠማትን ይህንን ወጀብ በምን መልኩ ማለፍ ይቻላል? የሚለውን ማሰብ ቀዳሚ እንደሆነ እምነታቸው ነው፡፡ ወረርሽኙ በውድድሮች ላይ እንዲሁም በቡድን በሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ የራሱን አሉታዊ አስተዋፅዖ እንዳሳደረ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ጊዜውን በጥንካሬ ማሳለፍ የግድ ነው ይላሉ፡፡ ሰልጣኞቻቸውም በዚህ መልክ መቆየት እንዳለባቸው ይጠቁማሉ፡፡ በንግግራቸውም ‹‹ሁሉም አትሌቶቼ ጠንካራና በባህሪያቸውም ለሌሎች ምሳሌ መሆን ይገባቸዋል፤ እንደ አሰልጣኝ የምነግራቸውም ይህ ጊዜ ያልፋል ብዬ ነው›› ብለዋል፡፡ ምንም እንኳን በዚህ ወቅት ሁሉም ውድድሮች ከተያዘላቸው መርሐ ግብር ሽግሽግ እንዲደረግባቸውና ሌሎቹም የተሰረዙ ቢሆንም አትሌቶች ልምምዳቸውን ማቆም እንደማይገባቸው አሰልጣኝ መርሻ ይመክራሉ፡፡ አትሌቶች የሚሠሩት እንቅስቃሴም ለጥንካሬ እና አቅምን ለማዳበር የሚረዱ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ሲያብራሩ ‹‹ለተወሰኑ ጊዜያት ውድድሮች ስለሌሉ ጠንክሮ መሥራት ተገቢ የሆነበት ወቅት ነው፡፡ በመሆኑም በእኔ ስር ለሚሰለጥኑ ሁሉም አትሌቶቼ መሥራት የሚገባቸውን እየጠቆምኳቸው ነው፡፡ ወቅቱ ጥንካሬን የሚያዳብሩበት ነው፤ በደንብ እንዲሠሩም ዕድል ይሰጣቸዋል›› ብለዋል፡፡ ከዓለም አትሌቲክስ ጋር ቆይታ ያደረጉት ሌሎች አሰልጣኞችም በተመሳሳይ ለአትሌቶቻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የማራቶንና ግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤቶቹ ኬንያዊን ኢሉድ ኪፕቾጌ እና ጆፈሪ ካምዎረር አሰልጣኝ ፓትሪክ ሳንግም ተሞክሯቸውን አጋርተዋል፡፡ በርካታ አትሌቶች በቡድን የሚያሰለጥኑት አትሌቱ ቡድናቸውን የበተኑት ከወር በፊትም ነበር፡፡ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ታግዘው አትሌቶቻቸውን ቢያገኙም ለውጣቸውን የመመልከት ዕድል አለማግኘታቸው ፈተና እንደሆነባቸው ጠቁመዋል፡፡ ብራዚላዊው አሰልጣኝ ሞራ ኮት አትሌቶች ቀድሞ በነበራቸው መነቃቃት ማቆየት አዳጋች መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ አሰልጣኞችና አትሌቶች መልካም መግባባት ያላቸው ከሆነም በሚያወጧቸው እቅድ መሰረት ባሉበት ሆነው በእንቅስቃሴ ላይ መቆየት ይችላሉ፡፡ ቢሆንም ይህ ጊዜ ሲያልፍ ምን ሊከሰት እንደሚችል ለመገመት አዳጋች መሆኑን አልሸሸጉም፡፡ ‹‹አዲስ ልምድ እንደምናገኝና ይህ ሁኔታ ለበጎ እንደሚሆንም ተስፋ አለኝ›› ይላሉ፡፡ የኒውዝላንድን አትሌቶች ሲያዘጋጁ የቆዩት አሰልጣኝ ዳሌ ስቴቨንሰን በበኩላቸው አትሌቶቻቸውን በስነልቦና እያገዙ እንደሚገኙና በቅርቡ ወደነበሩበት እንደሚመለሱ እየነገሯቸው መሆንኑን ገልጸዋል፡፡ ወቅቱ ወደኋላ የሚመለሱበት ሳይሆን በጥሩ ሞራል እንደ ሙሉ ጊዜ አትሌት ጊዜያቸውን መጠቀም እንዳለባቸውም ምክረሃሳብ ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኞችም አትሌቶቻቸው በምን መልኩ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳየት ተገቢ ነው የሚሉት አሰልጣኙ፤ በአንዳንድ አትሌቶቻቸው መደነቃቸውንም ይናገራሉ፡፡ አትሌቶች በአካባቢያቸው በሚያገኟቸው ቁሳቁስ ስልጠናቸውን እያደረጉ እንደሚገኙና በዚህም እንዲቀጥሉ አሳስበዋል:: ሌላኛው አሰልጣኝ ብራም ሶም አትሌቶች ከሁኔታዎች ጋር ራሳቸውን በማስማማት በዝግጅት ላይ መቆየት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡ ከአትሌቶች ጋር ፊት ለፊት በመተያየት ብቃታቸውን መገምገም ባይቻልም አዲስ ተሞክሮ እንዳስገኘላቸውም አክለዋል፡፡ አዲስ ዘመን ሚያዝያ 28/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=31772
cd43a49aa8dbc57dda79680d3356be1e
4a42253801a00ffc42c86e838d256005
የሊግ ካምፓኒው የሳተው መስመር
ስፖርት
የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ወረርሽኝ እንደሌሎቹ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኩነቶች ሁሉ የዓለምን ስፖርት ውጥንቅጡን አውጥቶታል። ታላላቅ የዓለማችን ሊጎች የሚያዙትን የሚጨብጡትን አጥተዋል። በተለይም ወትሮውንም ችግር የማያጣት አፍሪካ የዚህ ገፈት ቀማሽ መሆኗ ነገሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚያደርግባት ቀድሞም የተገመተ ነው። በእንደዚህ አይነት አስቸጋሪ ወቅት በሁሉም ረገድ ነገሮችን በብልሃት የሚያልፍ የበሰለ አመራር ሰጪነት ወሳኝ ነው። ለዚህም ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ አፍሪካ ውስጥ የቡርኪናፋሶ እግር ኳስ ተሞክሮን መመልከት አንዱ ማሳያ ነው። ቡርኪናፋሶ እንደሌሎቹ የዓለማችንም ይሁን የአፍሪካ አገራት ሰሞንኛ ማህበራዊ ሁኔታዋ ጤነኛ አልነበረም ። አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የኮሮና ቫይረስ ያጠቃቸው ፖለቲከኞች ተመዝግበውባታል። የቡርኪናፋሶ መንግስት ይህ ቫይረስ ተስፋፍቶባቸዋል ብሎ ካወጀባቸው ቦታዎች መካከል የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ይገኙበታል። ጅምናዚየም ፣ የኳስ መጫወቻ ሜዳዎች ለዚህ ተጠቃሽ ከሚባሉት ቦታዎች ውስጥ ይገኛሉ። ስለዚህ ይህንን አደጋ ለመቀነስ እና ለማህበረሰቡ ዋስትና ለመስጠት ሊጉን ሰርዞ የተለያዩ ውሳኔዎችን በዚህ ሳምንት አሳልፏል። የዘንድሮው የውድድር ዓመት እንደማይጠናቀቅ እና በዚሁ ውጤት እንደሚያልቅ፣ ሁሉም ክለቦች በውል ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾቻቸውን ውል እንዲያከብሩላቸው እና እስከውል ማለቂያው ድረስ ደመወዝ እንዲከፍሉ፣ ማንኛውም ክለብ ያለምንም በቂ ምክንያት ምንም አይነት የክለብ አባላት ቅነሳ እንዳያደርግ፣ የትኛውም ተጫዋች ተበደልኩ ቢል ለፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት እንዲያመለክት፣ ከሁሉም በላይ በዘንድሮ 2019 የውድድር ዘመን በኢንተርናሽናል መድረክ አገሪቱን የወከሉት ቡድኖች ማለትም (ራሂሞ ኤፍ ሲ) እና (ሳሊታስ) የተባለው ክለብ በክለቦች ኮንፌዴሬሽን ጨዋታ በሚመጣው ዓመት አገሪቱን እንዲወክሉ አድርጓል። ይህንን ያደረገውም የዘንድሮ ልፋታቸው ሽልማት እንኳን ቢሆን ብሎ በማሰብ ነው ። አሱማ ሲሪማ የቡርኪናፋሶ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ናቸው። ይህንን ውሳኔ ሲወስኑ ሁሉንም እንደሚያስማማ በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል። ቡርኪናፋሶን የወከሏት ቡድኖች የተገኙት አምና ባስመዘገቡት ውጤት ነው ። ይህ አንዳንዴ የተቀመጠን ህግ እና አሰራር ወቅቱ በሚፈቅደው ነገር እንደሚጠመዘዝ ማሳያ ነው ። የኢትዮጵያ ሊግ ካምፓኒ ምንም አይነት ቡድን ኢትዮጵያን በኢንተርናሽናል ውድድር አይወክልም የሚል ውሳኔ ከቀናት በፊት አስተላልፏል። ይህ እንደ አገር በድጋሚ ሊጤን የሚገባው ውሳኔ እንደሆነ በርካቶች አስተያየት ሰጥተውበታል። በኢንተርናሽናል ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉት ቡድኖች ከየትም ወገን ይምጡ የሚወክሉት ሊጉን ነው ። ሊጉ ደግሞ በድግግሞሽ በየዓመቱ ኢትዮጵያን በጥራት የሚወክሉ ቡድኖችን ይፈልጋል። ይህንን ጥራት ለማምጣት ደግሞ የቡድኖችን የኢንተርናሽናል ተሳትፎ መንገድ መቁረጥ ሌላ ፈተና ይዞ እንደሚመጣ ሳይታለም የተፈታ ነው። ይህን መቁረጥ በአንድ ዓመት የኢንተርናሽናል ልምድ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኝ ተጫዋች ራሱን የማሳየት ተስፋ ማጨለሙ አይቀርም። የክለቦችን የአስተዳደራዊ ዝግጅት ደረጃ ከፍ የማድረግ ልምድ ማ ሳነስም ሌላኛው ኪሳራ ነው። ለምሳሌ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ዘንድሮ ጥሩ የውድድር ዘመን አሳልፏል። ይህ ማለት ቡድኑ ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ራሱን በሚገባ እያዘጋጀ እንደነበር ማሳያ ነው ። ተከታዮቹ መቐለ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስም ወደ ውድድሩ የገቡት በተጠና እና የዝግጅታቸውን አቅም ፣ ጥልቀት በሚያሳይ ጥራት ነበር። ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ ወደ ኢንተርናሽናል ውድድር ለመቅረብ ቡድኖች ቢመረጡ እና እንዲወከሉ ቢደረግ ለቡድኖቹ ረዥም የሜዳ ተግባር እና የገንዘብ አቅም ቅድመ ዝግጅት ያገኙ ነበር ። የሊግ ኮሚቴው ውሳኔውን ክለቦች ተስማምተውበት እንዳሳለፈ ቢያሳውቅም ራሱን በሚገባ ሳያዘጋጅ የቀረበ እና የሊግ ካምፓኒው ሊጉ በአጠቃላይ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዳያገኝ አድርጎታል። ጉዳዮ ቻምፒዮን የመሆን እና ያለመሆን ጥያቄ አይደለም። በኢንተርናሽናል መድረክ ሊጋችንን የመወከል እና ያለመወከል ጥያቄ ነው። በድግግሞሽ ውስጥ መማር የሚገባው ሊግ ሊማርበት የሚገባውን አንዱን ነጥብ እንደሳተ ብዙዎች ይስማማሉ። እግር ኳሱ ላይ አብዛኛውን ጊዜ የሚወሰኑ ውሳኔዎች የሚሰጡት ጥቅም በአገራዊ መነፀር መታየት ይኖርባቸዋል ተብሎ ይታመናል። ለዚህ ደግሞ ክለቦች ጊዜ ወስደው እንዳያስቡና ፣ ጥናት ያለማድረግ ፣ ማንን ላስደስት የሚለውን አመለካከት አውልቆ አለመጣል ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ይታመናል። የቡርኪናፋሶ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አምና በኢንተርናሽናል መድረክ የተወከሉትን ቡድኖች ዘንድሮም ‹‹እነሱ ናቸው የሚወክሉኝ›› ብሎ ሲወስን ክለቦችን ጊዜ ሰጥቶ በሚገባ አናግሯል። ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትንም በቴሌ ኮንፈረንስ ገንቢ ሐሳብ እንዲሰጡበት አድርጓል። ኘሬዚደንቱ ‹‹እኛ የሚያስጨንቀን የሚመጣው ዓመት የሚሰጠንን ኮታ እንዳናጣው ነው ፣ ምክንያቱም ክለቦቻችን ልምድ እና ተሞክሮ ያስፈልጋቸዋል›› ነበር ያሉት ። ሁለቱ ቡድኖች ዘንድሮ አገሪቱን በኢንተርናሽናል መድረክ ሲወክሉ ፣ ራሂሞ የተባለው ቡድን በቅድመ ማጣሪያ 5ለ1 ተረቶ ነበር ። ከዚህ ሽንፈት በኋላም ሌላ ልምድ እናግኝ ብለው እንደገና ተነጋግረው ፣ ተግባብተው ወካያቸው አድርገውታል። የሊግ ካምፓኒው ውሳኔውን ካሳለፈ በኋላም ቢሆን ስህተቱን አምኗል። ማመን ብቻ ግን በቂ አይደለም። ካለመሳተፍ መሳተፍ ልዩ ዋጋ እንዳለው ተገንዝቦ የተሳሳተውን ውሳኔ የሚያርምበት ቀዳዳ መፈለግ ይኖርበታል።አዲስ ዘመን ግንቦት 1/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=31988
39e58906243ca455f75f386a2ba93c32
992f639de4543547b025498f4591203c
ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለአትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አባላቱ ቃል የገባውን ገንዘብ ማስረከብ ጀመረ
ስፖርት
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለብሔራዊ ቡድን አባላት ቃል የገባውን የአራት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማስረከብ መጀመሩን አስታወቀ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመሰረዛቸው ምክንያት ጥቅማ ጥቅም ለሚያጡ ብሔራዊ አትሌቶች አራት ሚሊዮን ብር ለመደጎም ከሳምንታት በፊት ውሳኔ መተላለፉን አስታውሷል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወቅቱ በገባው ቃል መሠረት ከሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ ለብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን አባላት ማስረከብ መጀመሩን አስታውቋል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርዱ ለ267 ብሔራዊ አትሌቶችና አሠልጣኞች በተናጠል የሚደረጉትን ልምምድና ዝግጅት አጠናክረው መቀጠል ይችሉ ዘንድ፣ ለእያንዳንዳቸው 15 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ከስምምነት ተደርሶ ነበር። በብሔራዊ ቡድን የሚገኙ አትሌቶቹና አሰልጣኞቹ እያንዳንዳቸው ቃል በተገባላቸው መሠረት 15 ሺህ ብር እንዲሁም ሙሉ የስፖርት ትጥቅ ከነመለማመጃው በተዘጋጀው መርሃ ግብር መሠረት እየተረከቡ ይገኛሉ ብሏል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የገንዘብ ድጋፉን ለማድረግ ውሳኔ ባስተላለፈበት ወቅት እንደተናገረው ከውሳኔ፤ በዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ ደረጃ የአትሌቲክስ ውድድሮችና በቡድን የሚካሄዱ ልምምዶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቋረጡ ተደርጓል፡፡ በተለይም በብሔራዊ ቡድን ደረጃ በተለያዩ የውድድር ዓይነቶች ማለትም የሜዳ ተግባራትን ጨምሮ ከአጭር ርቀት እስከ ማራቶን 211 አትሌቶችንና 56 ብሔራዊ አሠልጣኞች በድምሩ 267 የአትሌቲክስ ቤተሰቦች ሥነ ልቦናቸው ተጠብቆ ልምምዳቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ፌዴሬሽኑ አምኖበታል፡፡ ሌላው የውጭ የአትሌቲክስ ውድድሮች በመቋረጣቸው በተለይ የአጭር ርቀትና የሜዳ ተግባራት አትሌቶችና አሠልጣኞቻቸው ያገኟቸው የነበሩ ጥቅማ ጥቅሞች በማነሳቸውና በመቀነሳቸው ተቋሙ ከጎናቸው መሆኑን እንዲያረጋግጡ የሞራል ስንቅ ከመሆኑ ባሻገር፣ ለቀጣዩ ኦሊምፒክ ከወዲሁ ተገቢውን ዝግጅትና ተያያዥ ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ያለመ ስለመሆኑ ጭምር ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለቅድመ ማጣሪያው ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉት ርቀቶች ለተመረጡ 91 ብሔራዊ አትሌቶች እንዲሁም ለኦሊምፒክ ዝግጅት አትሌቶችን ላስመረጡ 27 አሠልጣኞች፣ ለ63 የአጭር ርቀትና የሜዳ ተግባራት አትሌቶችና ለ16 አሠልጣኞች፣ ለ57 ተተኪና ወጣት አትሌቶች እንዲሁም ለ13 ተተኪ ወጣት አትሌቶች አሠልጣኞች በገንዘብ ድጋፉ የተካተቱ ሲሆን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ባወጣው መርሃ ግብር መሠረት ድጋፍ ለማድረግ ቃል የተገባውን ገንዘብና ትጥቅ የሚረከቡ ይሆናል ተብሏል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዓለም አቀፍ ውድድሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ ለአትሌቶች እያደረገው እንዳለው ድጋፍ ሁሉ ፤ የዓለም አትሌቲክስና ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፋውንዴንሽን በወረርሽኝ ለተጎዱ አትሌቶች የ5 መቶ ሺህ ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን ከሳምንት በፊት ማሳወቁ ይታወሳል። የዓለም አትሌቲከስ ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮ እንደተናገሩት ድጋፉን የሚያገኙት በወረርሽኙ ምክንያት ባለፉት ወራት ውድድሮች ባለማድረጋቸው ገቢ ያጡ ፕሮፌሽናል አትሌቶች ነው። ድርጅቱ ድጋፉን የሚያደርገው እኤአ በ2020 እና በ2021 በጀቱ በመቀነስ መሆኑ ነበር ያሳወቀው። አዲስ ዘመን ግንቦት 4/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=32181
c5a742e5fba1f489ca2d6cf330a21896
59cbb6cea81e6e20224432ebd962e39c
ዶፒንግ ቅሌት በምን ይዳኝ?
ስፖርት
ጀግናው አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ እኤአ በ2016 መባቻ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኖ መመረጡን ተከትሎ አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ አትሌቶች በስፖርት ህግ ሳይሆን በወንጀል መቅጫ ህግ እንዲጠየቁና ለእስር እንዲዳረጉ መበረታታት እንዳለበት ሲሞግት ነበር። የኢትዮጵያ መንግስትም በዚህ ወንጀል የተሳተፉ አትሌቶች በወንጀል መቅጫ ህግ እንዲጠየቁና ለእስር እስከሚዳርግ ቅጣት እንዲጣልባቸው ማድረጉን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ብዙ ክርክሮች ተነስተው እንደነበር አይዘነጋም። ይህ አከራካሪ ጉዳይ አሁንም መቋጫ አላገኘም። በተለይም ሃይሌ ከቀናት በፊት ከዓለም አቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ወጣት ሪፖርተሮች ጋር በነበረው የልምድ ልውውጥ በዚህ አቋሙ እንደፀና መግለፁን ተከትሎ በጉዳዩ ላይ የሚነሱ ክርክሮች በርትተው ታይተዋል። በተለያዩ መገናኛ ብዙሃንም ሰፊ ሽፋን እየተሰጠው ይገኛል። በእርግጥ የስፖርቱን ቤተሰብ ለሁለት የከፈለው ‹አበረታች መድሃኒት የተጠቀሙ አትሌቶች በስፖርት ወይንም በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ይዳኙ?› የሚለው ሃሳብ አከራካሪ መሆኑ የግድ ነው። የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ(ዋዳ) አበረታች ንጥረ ነገሮችን በሚጠቀሙ አትሌቶች ላይ ምንም አይነት ምህረት እንደሌለውና እንደማይታገስ ቢታወቅም አትሌቶች በወንጀል መቅጫ ህግ እንዲጠየቁና ለእስር እንዲዳረጉ አይደግፍም። ይሁን እንጂ ኤጀንሲው በራሱ ህግ መሰረት አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ አትሌቶችን በቅድሚያ ለአራት ዓመት ከየትኛውም ውድድር በማገድ ያገኙትን ክብር ሁሉ ይነጥቃል። ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ አትሌትም ለስምንት ዓመታት ተመሳሳይ ቅጣት ይጣልበታል። ከዚህ ካለፈም ለእድሜ ልክ ከስፖርቱ ይታገዳል። ይህም በቂ ቅጣት ነው ብሎ ያምናል። ሃይሌ ግን ይህ ቅጣት ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ያምናል። አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ አትሌቶች በስፖርቱ ህግ ብቻ ሳይሆን በወንጀል መቅጫ ሕግ እስከ እስር የሚደርስ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚገባ ይሞግታል። ለዚህም የተለያዩ ሞጋች ምክንያቶችን ይደረድራል። ‹‹አበረታች መድሃኒት መጠቀም ውድድሮችን ለማሸነፍ ብቻ በማሰብ የተፈፀሙ ተደርጎ መታሰብ የለበትም፣ ሰዎች ቀለል አድርገው ይመለከቱታል›› የሚለው ሃይሌ ወንጀሉ ከስፖርታዊ ኩነትም የበለጠ ትርጉም እንዳለው ያምናል። እንደ ሃይሌ እምነት አንድ አትሌት በአንድ ውድድር ሲያሸንፍ ሁለት ወይም ሦስት መቶ ሺ ዶላር ሽልማት ያገኛል። ይህን ሽልማት በማሰብ አበረታች መድሃኒትም ይጠቀማል፣ ከዚያም ተይዞ ለአራት ዓመት ከውድድር ይታገዳል። አትሌቱ ሽልማቱን እስካገኘ ድረስ ከውድድር መታገዱ ምንም ላይመስለው ይችላል፣ እገዳውን ሲጨርስ ዳግም ተመሳሳይ ጥፋት ይፈፅማል። በሌላው ህብረተሰብ ዘንድም ወንጀል እንደሰራ ላይታሰብ ይችላል። ይሁን እንጂ ይህን ድርጊት የፈፀም አትሌት በወንጀል ቢጠየቅና ለእስር ቢዳረግ በሌላው ማህበረሰብ ዘንድም እንደ‹ሌባ› ሊቆጠርና ሊወገዝ ይችላል። ዳግምም በዚህ ድርጊት ተሳታፊ እንዳይሆን በእርስ ቅጣቱ ሊማር ይችላል። የሃይሌን ሃሳብ ከሚቃወሙት የስፖርቱ ቤተሰቦች መካከል የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ(ዋዳ) የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሰር ክሬግ ሬዲ አንዱ ናቸው። አበረታች መድሃኒት እንደ አጋጣሚ ተጠቅመው ለሚገኙ አትሌቶች ስፖርታዊ ቅጣቶቹ በቂ መሆናቸውን ያምናሉ። በእርግጥ ሰር ክሬግ አገራት በአትሌቶች ላይ ሳይሆን አበረታች መድሃኒቶችን በማምረት፣ በማሰራጨትና አትሌቶች እንዲጠቀሙ በማድረግ ተሳታፊ የሆኑ ማንኛቸውም ግለሰቦችና ተቋማት በወንጀል ህግ እንዲጠየቁ ዋዳ እንደሚያበረታታም አልዘነጉም። ሃይሌ የአበረታች መድሃኒት ተጠቃሚነት ጉዳይ የኢትዮጵያን አትሌቲክስና የአገሪቱን ባህል ከመጣስ አኳያ ትልቅ ክብደት የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ ይናገራል። ኢትዮጵያ የምትወስደውን እርምጃ ሌሎች አገራት የግድ ይተግብሩት የሚል አቋም ግን የለውም። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ቅጣትም መጥፎ ነው ብሎ አያምንም። እያንዳንዱ አገርም በራሱ መንገድ ነገሮችን እንደሚመለከት ይናገራል። ሰር ክሬግ በበኩላቸው እያንዳንዱ አገር የየራሱ የወንጀል መቅጫ ህግ ያለው እንደመሆኑ መጠን ተመሳሳይ ጥፋት ያጠፉ አትሌቶች በየአገራቱ የወንጀል መቅጫ ህግ ይዳኙ ከተባለ ሚዛናዊነት ገደል ይገባል። ይህ ማለት እንደየ አገራቱ የወንጀል መቅጫ ህግ ልዩነት ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀሉን የፈፀመ አትሌት ሌሎች አገራት ላይ ተመሳሳይ ወንጀል ከፈፀመ አትሌቱ እኩል ቅጣት ሊገጥመውም ላይገጥመውም ይችላል።አዲስ ዘመን ግንቦት 3/2012
https://www.press.et/Ama/?p=32125
a43cb76bc94bb7f2eb95b822d433a115
e597523192cc3eb90518f5f9552dc021
የእግር ኳሱ ዓለም ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር››
ስፖርት
የፍቅር ጉዳይ ሲነሳ በዓለማችን የተለያዩ ጥንዶች በተለያዩ ዘመናት የነበራቸው የሚያስቀና ፍቅር በብዙ ታሪኮች ሲጠቀስ ይታያል፡፡ በአገራችንም ተሰምተው የማይጠገቡ፣ ለበርካቶች ትምህርት የሆኑ ዘመን ተሻጋሪ የፍቅር ታሪኮች አሉ፡፡ ብዙ ጊዜ የልብ ወለድ እንጂ በገሃዱ ዓለም ያሉ ወይም ተከስተው የነበሩ የማይመስሉ የተለያዩ የፍቅር ታሪኮችን ቢያንስ አንድ የሚያውቅ አለ ተብሎ አይታሰብም፡፡ ዘመን አይሽሬው የአገራችን ልብ ወለድ ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር›› የሁለት ጥንዶችን የፍቅር ጥግ በማሳየት በብዙዎች ዘንድ የሚረሳ አይደለም፡፡ ከዚያም የተነሳ በውጣ ውረድ የተሞላ፣ ፈተናዎች የበዙበት የፍቅር ሕይወትና ፅናት ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር›› የሚል ስያሜ ሲቸረው ማየት የተለመደ ነው፡፡ በስፖርቱ ዓለምም በተለይም በእግር ኳሱ አንድ የፍቅር ታሪክ በርካቶችን ሲያነጋግር ኖሯል፣ እያነጋገረም ይኖራል፡፡ የዚህ ፅኑ ፍቅር ታሪክም በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችን እንዲህ ይነበባል፡፡ የዚህ ፍቅር ታሪክ መሪ ተዋናይ ቤርናዴት አዳምስ ትባላለች፡፡ ቤርናዴት ዘወትር ማልዳ ትነሳለች። አንድ ሰዓት እንኳን ሳይሞላ ቀኗ ይጀመራል። ቁርሷን ትበላለች፣ ባለቤቷን ለመንከባከብ ራሷን ታዘጋጃለች። ልብስ ትቀይርለታለች። ምግብ ታበስልለታለች። ወደ መፀዳጃ ቤት ትወስደዋለች። ቆሻሻውን ሁሉ ታፀዳለታለች። ጡንቻውን ታፍታታለታለች። ይህ የአንድ ቀን ብቻ ልማዷ አይደለም። ላለፉት ሰላሳ ስምንት ዓመታት አድርጋዋለች። በየዕለቱ ደጋግማዋለች። እስከ መጨረሻው ላታቋርጥም ለራሷ ቃል ገብታለች… ዘመኑ በ1960ዎቹ ፈረንሳይ በጄኔራል ሻርል ደጎል አመራር ሥር ሳለች፣ የመንግሥት ወግ አጥባቂ አስተዳደር እያደር የህዝብ ቅሬታ ሲያስነሳ ነበር። ጥቁሮች ከነጭ ፈረንሳዊያን ጋር በጋብቻ ከተጣመሩ ጉድ የሚባልበት ያ የዘረኝነት ዘመን…። ጥቁሩ ዣን ፒዬር አዳምስ ግን ከነጯ ቤርናዴት ጋር በፍቅር ወደቀ። ወደደችው፣ ወደዳት። አገር ጉድ ይበል ብለው ፍቅራቸውን እስከ ጋብቻ አደረሱት። ገና አማተር ተጫዋች ሳለ ነበር የተዋወቁት። በ1969 አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከጋብቻ በኋላ፣ ከፍተኛ ዲቪዚዮን የነበረው ኒም ፕሮፌሽናል ኮንትራት አቀረበለት። ተቀበለው። ዣን-ፒየር እና ቤርናዴት ኑሯቸውን ወደ ኒም ከተማ አዛወሩ። በፍቅር ሲኖሩም ወንድ ልጅ ወለዱ። 1970ዎቹ ለጥንዶቹ አስደሳች ዘመናት ነበሩ። አዳምስ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጥቁር ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ዝና፣ ገንዘብ፣ መሽቀርቀር፣ መደሰት የአዳምስ የዕለት ተዕለት ልማድ ነበር። ቀልድ ያውቃል። ፈገግታ ከፊቱ አይጠፋም። ዝና ሲጨመርበት ደግሞ… አለ አይደል… አብሮ የሚስቅም አይጠፋም። ገና የ10 ዓመት ብላቴና ሳለ አያቱ በመንፈሳዊ ጉዞ ሰበብ ይዘውት ከመጡ በኋላ የሴኔጋሉ ልጅ ፈረንሳይን ቤቴ ብሏል። ፓሪ ሰን ዠርመ እና ኒስን ጨምሮ እስከ 1981 ድረስ በዲቪዚዮኑ ለእውቅ ክለቦች ተጫወተ። 34 ዓመቱ ላይ ጫማውን ሰቅሎ፣ ለቀሪው ህይወቱ ህፃናትን ለማሰልጠን ለትምህርትና ልምምድ ወደ ዲዦ ከተማ አቀና። እዚያም በልምምድ ላይ ሳለ በጉልበቱ ላይ ጉዳት ደረሰበት። የሊጋሜንቱን ህመም ለመገላገል በሊዮን ከተማ በሚገኘው ኤድዋርድ ሄሪዮ ሆስፒታል ምርመራ አደረገ። ጉዳቱ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልገው በማረጋገጡ ለቀዶ ጥገናው ቀን ተቀጠረ። የቀን ጎዶሎ፣ እ.ኤ.አ መጋቢት 17 ቀን 1982። አዳምስ ቀጠሮውን ጠብቆ ቢመጣም በአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል። ህሙማን ብዙ ቢሆኑም ሐኪሞች ጥቂት ነበሩ። የአዳምስ ቀዶ ጥገና አስቸኳይ ባለመሆኑ እንደገና ሊቀጠር ይችል ነበር። ሆኖም ባሉት ባለሙያዎች ጉልበቱ ሊከፈትና ሊጠገን ተወሰነ። አንድ የማደንዘዣ ባለሙያ ብቻ ሥራ ላይ ነበረች። ተለማማጅ ተማሪዎችም አሉ። ህሙማን እንደ ቦኖ ውሃ በየተራ ማደንዘዣ ተሰጣቸው። አዳምስ ተራው ደርሶ አሸለበ። ግን እንደተጠበቀው አልሆነም። ጉልበት ላድን ያለው ህክምና እጅና እግሩን ጨምሮ መላው አካላቱን ከጥቅም ውጭ አደረጋቸው። ከዓይኖቹ ሽፋሽፍት በስተቀር ቢጠሩት እንኳን ፊቱን ዞር ማድረግ ተሳነው። አንደበቱ ተዘጋ፣ በድጋሚ መናገር አልቻለም። የማደንዘዣው ሂደት የህክምና ስህተት ነበረው። ተለማማጆቹ ወደ ሰውነቱ ያስገቧቸው ትቦዎች እንኳን በቅጡ አልተሰኩም። ወደ ሳንባው የተላከው ትቦ የአሰካክ ስህተት ስለነበረው ሳምባዎቹ በቂ ኦክስጅን ባለማግኘታቸው የልቡ ሥራ ተስተጓጎለ። አንጎሉ በቂ ኦክስጂን ባለማግኘቱ ለአደጋ ተጋለጠ። ያ ፈርጣማ ተከላካይ ሰውነቱ ከዳው። መላወስ አቃተው። በዚያች እርጉም ቀን ያለ ድጋፍ ወደ ሆስፒታል ቢገባም፣ በራሱ አቅም ወደ ቤቱ መመለስ አልቻለም። ቤርናዴት ለአምስት ቀን በሆስፒታል እየዋለች፣ እያደረች ጠበቀችው። ፍቅሯ፣ የልጇ አባት፣ የህይወቷ ጓድ ከተኛበት ሳይነሳ ቀረ። ከእንግዲህ በሰው ድጋፍ እንጂ በራሱ አቅም መንቀሳቀስ እንደማይችል ቁርጡን ነገሯት። የህክምና ኃላፊዎች ለአረጋዊያን መንከባከቢያ ማዕከል እንድትሰጠው መከሯት። ለቤርናዴት ይህ የሰነፎች ምክር ነበር። አልተቀ በ ቻቸውም። <<ወደ ቤታችን እወስደ ዋለሁ፣ እዚያም እስከመጨረሻው እንከባከበዋለሁ>> ብላ ወሰነች። በደግ ዘመን ፍቅርን ወዳዩበት ቤታቸው አመጣችው። 2018…፣ ዣን ፒየር አሁንም በህይወት አለ። ዕድሜው ሰባዎቹን አልፏል፡፡ ቤርናዴትም አልሰለቸችም። ዕድሜ ተጭኗት ቆዳዋ ተሽብሽቧል። የዚያ ዘመን ውበቷ ረግፏል። እርጅና ቤት እየሰራባት ነው። ግን እጅ አልሰጠችም። ባሏን መንከባከብ የዕለት ተዕለት ሥራዋ ከሆነ 38ኛ ዓመቷን ልትደፍን ተቃርባለች። ዘመናት ቢያልፉም ታማኟ ሴት ግን ሰው ሥራሽ ስህተት አልጋ ላይ የጣለውን ሸበላ አይኗ እያየ ልትጥለው አልፈቀደችም። የመጀመሪያ ፕሮፌሽናል ክለቡ ከሚገኝበት ኒም ከተማ አቅራቢያ ዣን ፒየር አዳምስ አሁንም ተኝቷል። ዛሬም ቤርናዴት ከጎኑ አለች። ከአደጋው በኋላ በእያንዳንዷ ቀን እንዳደረገችው ሁሉ ዛሬም ማልዳ ትነሳለች። ታጥበዋለች፣ ታለብሰዋለች፣ ትመግበዋለች፣ ከመተኛት ብዛት ጎኑ እንዳይላላጥ ታገላብጠዋለች። አልታከተችም፣ አልሰለቸችም። መልስ ባይሰጣትም ታወራዋለች፣ እ.ኤ.አ በ1969ና 1976 የወለዷቸው ልጆች ላውረንትና ፍሬድሪክ እንደወለዱና ሃያት እንደሆነም አብስራዋለች፡፡ አንድ ቀንም ይነቃል የሚል ተስፋዋ አብሯት አለ፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 2/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=32041
f7f048a51b303f6e8317d26538aebf11
8ddc44e3491fe2866267c4b7798aa23c
የታክስ ውስጥ ጥቅሶች
መዝናኛ
በተለምዶ ጥቅስ ሲባል፤ በመደበኛ አጠቃቀም ከመጻሕፍት (ቅዱሳን መጻሕፍት፣ የምርምር እና የሣይንስ መጻሕፍት፣ የታሪክ ድርሳናት እና የልብ ወለድ ድርሰቶች) የሚታወቁ እና ለምንናገርበት ወይም ለምንጽፈው ጉዳይ ማጠናከሪያ ሆነው የሚጠቀሱ እና ባለቤት ያላቸውን ነው፡፡ ነገር ግን ጥቅስ ተናጋሪው ወይም ጸሐፊው ሳይታወቅ ሀሳብን በተቃውሞ ወይም በድጋፍ የማኅበረሰቡን ሥሜት ሲገልፁ ይስተዋላል፡፡ለዚህ ተግባር ከሚጠቀሱት ደግሞ የመፀዳጃ ቤቶች /በተለይ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት/ እና የታክሲ ውስጥ ጥቅሶች በዋናነት ይነሳሉ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የጥናት እና ምርምር ርዕሰ ጉዳይ በመሆን በርካታ ጥናቶች ተካሂዶባቸዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግም በማኅበራዊ ሚዲያዎች የመወያያ ሀሳብ እየሆኑ መቅረብ ጀምረዋል፡፡ እኛም በዚህኛው አውድ የተወሰኑትን ጀባ ብለናል፡፡ ከታክሲ ሥራ ጋር የተያያዙ ጥቅሶች ዘመን መፂሄት መስከረም 2012 አባይ ፈለቀ
https://www.press.et/Ama/?p=19999
0012a8763d6f5bb58290c93249b38779
b13c6fb00ac903f9d14d20ac0e6a3e3f
ኮሚሽኑ ኮቪድ 19ን ለመከላከል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል
ስፖርት
የዓለም ህዝብ ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) የሚያስከትለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመቋቋምና ለመከላከል መተጋገዝ አስፈላጊ መሆኑ ተደጋግሞ ይነገራል። በዚህም ምክንያት የተለያዩ አካላት በዓይነት፣ በገንዘብ እንዲሁም ባለሙያዎችም በጉልበታቸው ጭምር ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የስፖርት ዘርፍም በዚህ እንቅስቃሴ ቀዳሚ ተሰላፊ መሆኑ ታይቷል። የስፖርት አመራሮች፣ የስፖርት ማህበራት፣ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው፤ መልእክት በማስተላለፍ፣ በየቤታቸው ላሉ ዜጎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማሰራት፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ የምግብና ሌሎች መገልገያዎችን በመለገስ እንዲሁም በሌሎች ተግባራት ላይ እየተንቀሳቀሱ ነው። ዘርፉን የሚመራው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ይህን እንቅስቃሴ በማስተባበር እንዲሁም እንደ አንድ ባለድርሻ አካል በሚጠበቅበት ሁሉ የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል። ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ የመንግስትን አቅጣጫ በመከተል የተለያዩ እርምጃዎችንም ወስዷል። በቅድሚያም ህዝቡን በብዛት በማሳተፍ ቫይረሱን በማሰራጨት ረገድ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችል ስጋት የሚያሳድሩ የእግር ኳስና ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮችን ማቋረጥ ነው። በቀጣይም በየክለቦቹ እንዲሁም በማሰልጠኛ ተቋማት ያሉ ሰልጣኞች ወደ የአካባቢያቸው በመሄድ ራሳቸውን በየቤታቸው እንዲያቅቡ ማድረግ ነው። በቀጣይም የቶኪዮ ኦሊምፒክ ብሄራዊ ቡድኑን አባላት መበተንን ጨምሮ የተለያዩ የቡድን እንቅስቃሴዎች በስፖርቱ ዘንድ እንዳይካሄዱ ማገድ ነው። ከዚህ በኋላም ስፖርተኞችና ማህበራት በግላቸውና በቡድን ከሚያደርጉት እገዛ ባሻገር በስሩ ያሉትን አካላት በማስተባበርና በማቀድ እየሰራ ይገኛል። ኮሚሽኑ በዋናነትም አራት ተግባራትን በመለየት ኃላፊነቱን እየተወጣ እንዳለም ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገልጸዋል። ይኸውም የገንዘብ ድጎማ፣ በስፖርት ቤተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በመገናኛ ብዙሀን ማስተላለፍ እንዲሁም የማሰልጠኛ ተቋማት ቫይረሱን ለመዋጋት በሚደረገው እንቅስቃሴ አንድ አካል እንዲሆን የማድረግ ትብብር ነው። የገንዘብ ድጎማውን ተከትሎም የስፖርት ማህበራት በግላቸው ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በኮሚሽኑ አስተባባሪነት ከአገር አቀፍ ስፖርት ማህበራትና የአትሌቶች ማህበር ጋር በመሆን የተደረገውን የሶስት ሚሊየን ብር ድጋፍ ጨምሮ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስና እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን፣ የወጣቶች ስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ በጥቅሉ ወደ 15 ሚሊዮን የሚሆን ብር ለብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረክቧል። አቅም ለሌላቸው ዜጎች የሚውሉ የምግብና የንጽህና ቁሳቁሶችንም በተመሳሳይ ገቢ ማድረግ ተችሏል። ለህብረተሰቡ እንዲሁም ለስፖርት ቤተሰቡ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድም የተለያዩ ስራዎች ተከናውነዋል። ታዋቂና ተጽእኖ ፈጣሪ የስፖርት ሰዎችን በመጠቀም ተደራሽነታቸው ሰፊ በሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ትምህርታዊ ማስታወቂያዎች እየተላለፉም ይገኛል። ሌሎች ስፖርተኞችም በተመሳሳይ በግላቸውና በቡድን በመሆን ግንዛቤ በማስጨበጥ ላይ ይገኛሉ። ከዚህ በተጓዳኝ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቫይረሱን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ኮሚሽኑ በመገናኛ ብዙሃን ለማስተላለፍ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቶች የሚሰጠው ምክርና አቅጣጫም ለዚህ ተጠቃሽ ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚንና የጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከልን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የስልጠና ማዕከላትን ከቫይረሱ ጋር በሚደረገው ጦርነት በተፈለጉ ጊዜ እንዲያገለግሉ ዝግጁም ተደርጓል። ሌላው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ይፋ የተደረገው የምገባ መርሃ ግብር ነው። በዚህም 300 ለሚሆኑ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያና ሌሎች አካባቢዎች ለሚገኙ ጎዳና ተዳዳሪዎች ለአንድ ወር የሚቆይ የምገባ መርሃግብር ነው። በቀጣይም ኮሚሽኑ በምን መልኩ መደገፍ እንዳለበት ከስፖርት ማህበራትና ተጠሪ ከሆኑት ተቋማት ጋር ውይይት በማድረግ ጉድለት ያለባቸው ቦታዎችን በመለየት ድጋፉን የሚቀጥል መሆኑን ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 22/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=31441
7c34f74c12242599e16f33349d00b40f
c6132eb1ae8632b1cb425d11c6f98a83
የጃፓን መንግሥትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውዝግብ
ስፖርት
የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለአስራ ስድስት ወራት በመራዘሙ ምክንያት የአዘጋጅ አገሯ ጃፓን መንግሥትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ገና ከጅምሩ በርካታ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ መዘፈቃቸው ሲነገር ቆይቷል። የኦሊምፒክ ውድድሩ በዓለም ላይ ከፍተኛ ስጋት በፈጠረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዞ ወደ ቀጣዩ ዓመት መራዘሙ ግድ መሆኑ ከታመነበት ወቅት አንስቶ አዘጋጆቹ በርካታ ፈተናዎችን መጋፈጣቸው የማይቀር ሆኗል። በተለይም ላለፉት ሰባት ዓመታት የበለጠ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው የኦሊምፒክ ውድድር መራዘሙ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ማስከተሉ የአዘጋጆቹ ራስ ምታት እንደሚሆን ቀድሞም የታወቀ ነው። ይህ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ የጃፓን መንግሥትንም ይሁን ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴን በእጅጉ ሊፈትን እንደሚችል በባለሙያዎች አስተያየት ሲሰጥበት የቆየ ሲሆን ሁለቱ አካላት ኪሳራውን ለማካካስ እንደሚደጋገፉና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ለዚህ እንዲዘጋጁ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲህ ዓይነት ችግሮች ሲገጥሙት ትልቅ ተቋም እንደመሆኑ የመድህን ዋስትና እንዳለው ይታወቃል። አሁን የገጠመው ግን ካለው የመድህን ዋስትና አቅም በላይ በመሆኑ ነው እዚህ ችግር ውስጥ የተዘፈቀው። ስለዚህ የመድህን ዋስትናው በሕጉ መሠረት የሚሸፍነው ኪሳራ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ ኪሳራውን የሚያካክስበት አንድ ነገር መፈጠሩ የግድ ይሆናል። ይህንን ተጨማሪ ኪሳራ የጃፓን መንግሥት እንደሚሸፍን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ቀደም ሲል በተለያዩ አጋጣሚዎች መስማማታቸው ቢገለፅም አሁን የሃሳብ ለውጥ እንዳደረጉ የሚጠቁሙ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ውዝግቦች ተነስተዋል። የዓለም አቀፍ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ሰሞኑን ከአንድ የጀርመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ እንደጠቆሙት፣ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከጃፓን መንግሥት ጋር በተስማማው መሠረት ለሚደርሰው በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚገመተውን ኪሳራ ለመሸፈን የራሱ ድርሻ አለው። ተጨማሪ የተባለውን ኪሳራ የመሸፈን ግዴታ ያለበት ደግሞ የጃፓን መንግሥት ነው። ይህን ስምምነት ሁለቱ አካላት እአአ 2013 ላይ እንዳደረጉ ቢገለፅም የጃፓን ካቢኔ አባላት ዋና ፀሐፊው ዮሺሂዴ ሱጋ ስምምነቱ እንዳልተደረገ አስተባብለዋል። ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ አካላት መካከል ውዝግብ የተፈጠረ ሲሆን ተጨማሪ የተባለው ኪሳራ እስከ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል የጃፓኑ ክዮዶ ኒውስ ዘግቧል። የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አዘጋጅ ቃል አቀባይ ማሳ ታካያ በበኩላቸው የጃፓን መንግሥት፣ የኦሊምፒኩ አዘጋጅ ኮሚቴና ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩ በመራዘሙ ሊገጥሙ የሚችሉ እንቅፋቶችን በጋራ እንደሚወያዩና መፍትሄ እንደሚያስቀምጡ ተናግረዋል። ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ብቻ የጃፓን መንግሥትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ እንደሚገቡ ቀደም ሲል ተዘግቧል። የጃፓኑ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴም ገና ከመጀመሪያው ከፍተኛ ኪሳራ ሊገጥም እንደሚችል መናገሩ ይታወሳል። ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለዚህ ኪሳራ ስጋት ሰላሳ ሦስቱንም ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች የሚመለከት መድህን የገባ ቢሆንም በቂ እንደማይሆን ታምኖበታል። ፕሬዚዳንቱ ቶማስ ባኽም ኦሊምፒኩ መራዘሙን በገለፁበት ወቅት ከባድ ኪሳራ እንደሚኖር በማመን ሁሉም ባለድርሻ አካላት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ለመጠቆም ሞክረዋል። ከባዱን መስዋዕትነት ማን እንደሚከፍልና ጫናው በየትኛው ወገን ትከሻ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ግን ከመጀመሪያውም ግልፅ አልነበረም። አሁን ላይ ገና ኦሊምፒኩ አስራ አምስት ወራት ገደማ እየቀሩትም ሁለቱ አካላት ውድድሩ በመራዘሙ የገጠማቸውን ውስብስብ ችግሮች ከመፍታት ይልቅ ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ባለው ጉዳይ ላይ መነታረ ክ ጀምረዋል። የተለያዩ ተንታኞች እንደሚናገሩት ከሆነ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በዓለም ላይ ሙሉ ለሙሉ እስከ ቀጣዩ ዓመት በቁጥጥር ስር ካልዋለ ኦሊምፒኩ በተራዘመበት 2021ም ላይካሄድ ይችላል። ከዚህም በዘለለ የመሰረዝ ዕድል ሊገጥመው ይችላል። ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ብቻ በሚገጥመው ኪሳራ ትልቅ ውዝግብ የሚነሳ ከሆነ ከነጭራሹ ከተሰረዘ የሚገጥመው ኪሳራም በቀላሉ የሚሰላ እንደማይሆን ይታመናል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17 / 2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=31115
2a97e0aad4fa0ad56a585fd391b23a5b
709a028eb5f4d4950942dd58fb048c92
የአውሮፓ አትሌቲክስ ቻምፒዮናና ዳይመንድ ሊግ
ስፖርት
በርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በተሰረዙበትና በተራዘሙበት በዚህ ወቅት እንደሚካሄድ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የአውሮፓ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከመሰረዝ እንዳልዳነ ታውቋል፡፡ በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ እኤአ ከሐምሌ 25 እስከ 30 በቻርሌቲ ስቴድየም ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ቻምፒዮና በኮሮና ቫይረስ ስጋት እንደተሰረዘ አዘጋጆቹ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አሳውቀዋል፡፡ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ የተቻለው ሁሉ ጥረት ቢደረግም በአሁኑ ወቅት ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ በፈረንሳይ መሰብሰብ የተከለከለ በመሆኑ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴው፣ የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበርና የፈረንሳይ አትሌቲክስ ባለስልጣናት ውድድሩን ለመሰረዝ እንደተገደዱ አሳውቀዋል:: እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስም የፈረንሳይ የጤና ኮሚሽን በአትሌቶችና በተመልካቾች ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ከግምት ያስገባ ጥናት ማድረጋቸው ታውቋል:: የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ጂን ጋርሺያ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለፁት፣ ውድድሩን ለማካሄድ እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል:: «በርካታ ውድድሮች በተሰረዙበት ሰዓት ለአትሌቶች በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ሰዓት አንድ የሚያስደስት ነገር ለማድረግ አስበን ነበር» ያሉት ፕሬዚዳንቱ ውድድሩን ከቫይረሱ ስጋት ነፃ ለማድረግ የስቴድየሞች ተመልካች የመያዝ አቅም በግማሽ እንዲያንስ ለማድረግ ጥረት መደረጉን አብራርተዋል፡፡ ውድድሩን ከመሰረዝ ይልቅ ወደ ቀጣዩ ዓመት እንደ አማራጭ ታስቦ እንደነበረ የተናገሩት ግራሺያ የቫይረሱ ስጭት ምናልባት እስከ ቀጣይ ዓመትም ካልተገታ ማራዘሙ አማራጭ እንደማይሆን ታምኖበት ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ገልፀዋል፡፡ ለውድድሩ ከአስራ ስምንት ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት የተያዘ ሲሆን ሊገጥም የሚችለውን ኪሳራ ለማዳን የአገሪቱ መንግሥት ዋስትና እንደሚሰጥ ታውቋል:: የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበር ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ከወር በፊት ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ መካሄድ የሚችልበትን መንገድ ማጥናት እንደሚገባ የጠቆመ ሲሆን ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ ካልተካሄደ የሚራዘምበት ዕድል እንዲፈጠር ፍላጎት ነበረው፡፡ ያም ሆኖ አዘጋጆቹ ከማራዘም ይልቅ ለመሰረዝ ተገደዋል፡፡ በዚሁ በአውሮፓ በርካታ ከተሞች ይካሄዱ የነበሩ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በተያዘላቸው መርሃግብር መሠረት እንደማይካሄዱ የተገለጸ ሲሆን የሚካሄዱበት አዲስ መርሃግብር ከዓለም አትሌቲክስ ጋር በመወያየት እንደሚገለፅ ተጠቁሟል፡፡ ከግንቦት መጨረሻ አንስቶ በአስራ አራት የተለያዩ የዓለማችን ከተሞች የሚካሄዱት የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች የፓሪስና የዩጂን ዳይመንድ ሊጎችን ጨምሮ በርካቶቹ መራዘማቸው ታውቋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ በኖርዌይ ኦስሎ የሚካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ቢራዘምም አዘጋጆቹ በምትኩ አዲስ የውድድር አማራጭ ማቅረባቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ «የማይቻል» የተባለው ውድድር በኦስሎ አዘጋጆች ሲታቀድ በኤግዚቢሽን መልኩ በዝግ ስቴድየም እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ ውድድሩን ማህበራዊ ርቀትን በመጠበቅና የኮሮና ቫይረስ የሚፈልገውን ጥንቃቄ ተግባራዊ በሚያደርግ መልኩ ለማካሄድ የታሰበ ሲሆን በኖርዌያን የሜዳ ተግባራት አትሌቶች መካከል የዓለም ክብረወሰን የሚሻሻልበት ይሆናል ተብሏል፡፡ በተለይም ኖርዌያዊው የርዝመት ዘላይ ካርልስተን ዋርሆልም እንዲሁም የምርኩዝ ዘላዮቹ ሞንዶ ዱፕሌንቲስና ሪናውድ ላቪሌኒ የሚያደርጉት ፉክክር ተጠባቂ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህል የሚካሄደው ውድድር በኖርዌይ የሕዝብ ቴሌቪዥን ጣቢያ በቀጥታ እንደሚተላለፍ ተጠቁሟል፡፡ ይህ የኖርዌይ ውሳኔ ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር ተያይዞ ለብዙዎች የማይመስል ቢሆንም የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮ ጭምር አድናቆታቸውን ገልጸውለታል፡፡ አዲስ ዘመን ሚያዝያ 18/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=31149
0b53e5584199d63e553f453282c9e8c2
9244288241948d956f1e17db20f07627
ማዕድ የማጋራት ብሄራዊ ጥሪና የስፖርቱ ማኅበረሰቡ ምላሽ
ስፖርት
ኃያላኑን አገሮች ጨምሮ የዓለም ሳይንቲስቶች ከሁሉም በፊት ትኩረታቸውን በአንድ ነገር ካደረጉ አራት ወራት አለፈ።በቻይና ውኃን ግዛት በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መባቻ ለተከሰተውና በምህፃረ ቃሉ ኮቪዲ 19 የሚል መጠሪያ ላገኘው ኮሮና ቫይረስ።ወረርሽኙ ዘር፣ ቀለም፣ ትንሽና ትልቅ ሳይለይ ሁሉንም በማጥቃት የአለም ህዝብ በፍርሃት አቁማዳ ውስጥ እንዲገባ ካደረገ አራት ወራቶች አልፈዋል። በእነዚህ ወራት የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት የቻለ ምድራዊ ኃይል አልተገኘም። የአለም ሀያላን አገራት ከምድር ተሻግረን ጨረቃ ላይ እንወጣለን ሲሉ እንዳልተመፃደቁ፤ የኮሮና ወረርሽኝ ከቤታቸው ራሱ እንዳይወጡ አደረጋቸው። ሀገራቱ የወረርሽኙን ስርጭት በቶሎ የመቆጣጠር አቅም በማጣታቸው በአራት ወራት ብቻ ከሁለት መቶ ሺህ ሰዎች በላይ ህይወት ተቀጠፈ። የአለም ህዝብን እንደ ቅጠል ከማርገፍ በተጨማሪ በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ አስከትሏል። የኮቪድ 19 ስርጭት በማይታመን ፍጥነት ከመጨመር በተጓዳኝ መድሃኒት አልባ በመሆኑ ሀገራት ትኩረታቸውን ሁሉ ቅድመ መከላከል ላይ መስራትን መርጠዋል። ኢትዮጵያም የአለም ሀገራትን በአንድ ልብ እያስጨነቀ ካለውን ጠላት ህዝቦቿን ለመታደግ በብሄራዊ ደረጃ መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችሉ ሥርዓቶችን በመዘርጋት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። መንግስት የወረርሽኙ ባህሪ ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ አቋም አኳያ ስርጭቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚቸል በመገንዘብ ለህዝቡ ጥሪ በማድረግ የጋራ ተሳትፎን ያማከለ እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል። በዚህ ተግባር ላይ የተለያዩ አካላት ተሳትፏቸውን ባሳዩበት ተግባር ላይ በስፖርቱ ዘርፍ ባሉ አካላት በኩል አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የነበራቸው ተሳትፎ ትልቅ እንደነበር ለመታዘብ ተችሏል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ከታወቀበት ከመጋቢት መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ በቡድንም ሆነ በተናጠል ለወረርሽኙ መከላከያ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ነበር ይሄንኑ ያስመሰከሩት። የስፖርቱን ተቋማት ከሚመሩት አካላት ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከወራት በፊት መንግስት ላቀረበው ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ያሳዩት ተሳትፎ ዳግም ማሳየተቻው ተነግሯል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በጋራ ለማሸነፍ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ከሳምንታት በፊት የማዕድ ማጋራት ብሔራዊ ጥሪን አድርገው ነበር። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ከቢ. ጂ አይ ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ አንድ መርሃ ግብር ይፋ አድርገዋል። የስፖርቱ ተቋማት በኩል ይፋ የተደረገው መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ያቀረቡትን «የማዕድ ማጋራት ብሄራዊ ጥሪ»ን እውን ያደርጋል ተብሏል። መጋቢት መጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ “ማዕድ ማጋራት” ሲሉ በሰየሙት መንገድ መንግስት የኮሮና ወረርሽኝ የከፋ ጉዳት ቢያደርስ በየቤቱ ምግብ ለማድረስ አቅሙም ሆነ መንገዱ ስለማይኖረው፤ ሰዎች በምግብ እጦት እንዳይጎዱ አንድ ቤተሰብ በቀን አንድ ምግብ ሌላ ቤተሰብ ለማቅረብ ዝግጅት እንዲደረግ እና እንደቤተሰብ ምክክር እንዲደረግ ሲሉ ነበር ያሳሰቡት። የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጥሪ ተከትሎ በርካቶቸ ምላሽ ሰጥተዋል። የስፖርት ተቋማቱ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ሰሞኑን ይፋ ያደረጉት የምገባ መርሃ ግብር ይሄንኑ መሰረት አድርጓል። በዚህ መርሃ ግብር 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር ያህል እንደሚመግብ ተነግሯል። የስፖርቱ ን ማኅበረሰብ ህዝባዊነት የሚያረጋግጥ መሆኑ የተነገረለት መርሃ ግበር ሚያዝያ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲጀመር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደተናገሩት፤ የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገራችን ከገባ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የስፖርቱ መንግስታዊ እና ህዝባዊ አደረጃጀቶች፣ ታዋቂ አትሌቶች፣ የደጋፊ ማህበራት፣ በአጠቃላይ የስፖርት ቤተሰቡ ህብረተሰቡን በማንቃት እና ኢኮኖሚያዊ ጫናውን ለመቋቋም የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን አስታውሰዋል። የስፖርቱ ማኅበረሰብ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥልና የምገባ መርሃ ግብሩ መጀመር ለዚሁ ማሳያ ይሆናል ብለዋል። የጎዳና ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን በተወሰነ መልኩ ለማገዝ አንድ ወር የሚቆይ የምገባ መርሃ ግብሩ ይሄንኑ ሚና መሰረት ባደረገ መልኩ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ኤልያስ፤ በስታዲየም ዙሪያ መርሃ ግብሩ እንዲደረግ የተመረጠበትን ምክንያት መኖሩን አመልክተዋል።« በወቅታዊ የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ስርጭቱን ለመቆጣጠር ሲባል በተለይ ስታዲየም ዙሪያ የሚገኙ ባር እና ሬስቶራንቶች መዘጋታቸው እና በአካባቢው ያለው እንቅስቃሴ መቆሙ ይታወቃል። ሬስቶራንቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ ከሬስቶራንቶች ተመላሽ የሚሆኑ ምግቦችን ይጠቀሙ የነበሩ የጎዳና ተዳዳሪዎችም ሆነ በስታዲየም አካባቢ የተለያዩ ነገሮችን በመሸጥ ይተዳደሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል። በመሆኑም ጊዜው የከፋ ችግር ላጋጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እጃችን የምንዘረጋበት፤ የጋራ መከራችንን በመተጋገዝ የምናልፍበት መሆኑን በማመን እና ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ነው »ሲሉ አብራርተዋል። አቶ ኤልያስ በመጨረሻ የተጀመረው ተግባር የሚቋረጡ ሳይሆን በቀጣይም እነዚህ ወገኖቻችን በዘላቂነት ህይወታቸውን ሊመሩበት በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የስፖርት ቤተሰቡ በሙሉ አቅሙ የሚደግፍ መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የቢጂ አይ ኢትዮጵያ አመራሮች በጋራ በመሆን ባስተላለፉት መልዕክት ደግሞ፤ የምገባ መርሃ ግብሩ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። «በአሁኑ ሰዓት የገጠመንን ፈተና ለማሸነፍ ለመንግስት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም በአቅሙ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል »ያሉት ደግሞ፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ናቸው። ሚኒስትሯ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የምገባ ፕሮግራም ለሌሎች ድርጅቶች እና ባለሀብቶች አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑም ገልጸዋል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያቀረቡትን የማዕድ ማጋራት ብሔራዊ ጥሪ ተከትሎ የስፖርት ቤተሰቡ እና አመራሩ በዚህ በጎ ተግባር መሳተፉ ሊያስመሰግነው እንደሚገባ አመልክተዋል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ከቢ. ጂ አይ ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን ሚያዚያ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ይፋ ያደረጉት መርሃ ግብር ለአንድ ወር ያህል የሚዘልቅ ይሆናል። በመርሃ ግብሩ 300 ሰዎች ተጠቃሚ የሚሆኒ ሲሆን ተመጋቢዎቹ በቀን 2 ጊዜ እንዲመገቡ ይደረጋል። የተጠቃሚዎች ዝርዝር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት አማካኝነት ተለይተው እንዲቀርቡ የተደረጉ ናቸው። ለምገባ ፕሮግራሙ ከ800 ሺ ብር በላይ ወጪ የሚደረግ መሆኑ ታውቋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 20/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=31281
d22555101296306d5f0fdaf9e5dd78c5
cc41fe609d4ceb7bef911a1285183aa4
የመሬትና የብድር አጠቃቀም ችግር በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጫና ማሳደሩ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዋቅሹም ፍቃዱአዲስ አበባ፡- የመሬትና የብድር አጠቃቀም ችግር በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጫና ማሳደሩን የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አስታወቁ። በበጀት ዓመቱ ለ1ሺህ 117 ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ በሩብ ዓመቱ 543 ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን ገለጹ ።የከተማው ከንቲባ አቶ ዑመር መሀመድ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፣ አሶሳ ከተማ ከሁሉም የአገሪቱ ክፍል የሚመጡ የብሔር ብሔረሰቦች መናኸሪያ በመሆኗ በርካታ ወጣቶች ስራ ፍለጋ ወደ ከተማይቱ ይመጣሉ። የከተማ መስተዳድርም ያለምንም አድሎ አቅም በፈቀደ መጠን የስራ ዕድል ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ለወጣቶቹ የብድር አቅርቦት ሲመቻች አንዳንድ ወጣቶች ሰርተው ከመለወጥ ይልቅ ያገኙትን ገንዘብ ይዘው የመሰወር እንዲሁም የመጥፋት ሁኔታ ያሳያሉ ያሉት ከንቲባው ፣ በተመሳሳይ መልኩ አንዳንዶቹም ምንም እንኳ እንደሌሎቹ ገንዘብ ይዘው ባይጠፉም በአግባቡ ሰርተው ከተለወጡ በኋላ የተበደሩትን ገንዘብ ሳይመልሱ ተጨማሪ ብር የመጠየቅ ሁኔታዎች አሉ ብለዋል ። ይህ ደግሞ ሌሎች አዳዲስ ስራ ፈላጊዎች በአግባቡ እንዳይስተናገዱ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል። ከተማ መስተዳድሩ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ቢሆንም ፣በከተማው የስራ ቦታ እጥረት መኖሩን አመልክተዋል ። ያለውም ቢሆን ለህገ ወጥ ወረራ የተጋለጠ በመሆኑ ችግሩን ለማቃለል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ። የብድር አቅርቦትም ቢሆን ምናልባት ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተያይዘው እጥረት እንዳለም የጠቆሙት ከንቲባው ፣ በቀጣዩ ከፌዴራልም ሆነ ከክልሉ ለከተማይቱ ወጣቶች የሚመደበው በጀት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል ልዩ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም አስረድተዋል። በከተማው የመሬት ወረራ ትልቁ ራስ ምታት እንደሆነ ጠቁመው ፣ ወጣቶች የተሰጣቸውን የስራ ቦታ በአግባቡ ሰርተውበት ከተለወጡ በኋላ ለቀጣዩ ስራ ፈላጊ ከመልቀቅ ይልቅ አንዳንድ ወጣቶች የወሰዱትን መሬት ለሌሎች አሳልፈው እንደሚሸጡና የተሸጠው መሬትም ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር ይልቅ ለህገ ወጥ መኖሪያ ቤት ግንባታ እንደሚውል ከተማ መስተዳድሩ ባደረገው ክትትልና ግምገማ እንደ ደረሰበት ከንቲባው አክለው ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ አሶሳ ከተማ ለስራም ሆነ ለኑሮ ምቹ በመሆኗ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ አዳዲስ ፊቶችን፣ በተለይ ወጣቶችን በከተማይቱ ማየት እየበዛ መጥቷል። ወደ ከተማው የሚመጡ ሰዎች አሶሳ አገራቸው እንደሆነች በማመንና በመተማመን ስለሚመጡ የከተማ አስተዳደሩም እነዚህ ወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ አቅዶ እየሰራ ይገኛል። እስካሁንም የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከልም ግማሾቹ ከሌሎች አከባቢ የመጡ ናቸዉ። አቶ ዑመር ከብድር አጠቃቀም ጋር የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ለስራ ቁርጠኛ የሆኑና ሰርተው ለመለወጥ ጽኑ ዓላማ ያላቸውን ወጣቶች በጥንቃቄ እንዲመለመሉ በማድረግ በዋስ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሰሩ ጠቁመው፣ በመሬት አጠቃቀም ዙሪያም ጠንካራ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ችግሩን ለመፍታት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አመልክተዋል ። አዲስ ዘመን ታህሳስ 22/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38531
f84f419f074bb0e5b03b1af828fb9ad4
54bc176b47c4e76254c999d4b9a34bc9
በኦሊምፒክ መራዘም የ3ሺ ሜትር መሰናክል አትሌቶች ምን አሉ?
ስፖርት
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) የዓለም ስጋት ከመሆኑ አስቀድሞ በስፖርቱ ዓለም ተጠባቂ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ኦሊምፒክ ነበር። ነገር ግን ሊካሄድ ወራት ብቻ በቀሩትና ሀገራትም ብሔራዊ ቡድናቸውን ማዘጋጀት በጀመሩበት ወቅት መራዘሙ ተሰማ። አጋጣሚውም በተለያዩ አትሌቶች ዘንድ ሁለት ዓይነት ስሜት የፈጠረ ሆኗል። የመጀመሪያዎቹ አትሌቶች የጊዜውን መርዘም ተጠቅመው በ2021ዱ ኦሊምፒክ በተሻለ ብቃት ለመገኘት ዕድል ያላቸው ሲሆኑ፣ ሁለተኛዎቹ ደግሞ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኙና ምናልባትም መራዘሙ እክል ሊያስከትልባቸው የሚችሉ ናቸው። ኢትዮጵያም የአትሌቲክስ ቡድኗን መርጣ ልምምድ ለመጀመር ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ በነበረችበት ወቅት ነው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በመራዘሙ አትሌቶች እንዲበተኑ የተደረገው። ከተበተነው ብሔራዊ ቡድን አባላት መካከል የ3ሺ ሜትር መሰናክል አንዱ ሲሆን፤ ይህ ቡድን በዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና ውጤታማነቱን ያስመሰከረ ነበር። በኦሊምፒኩ ለአሸናፊነት የሚጠበቀውና ከፍተኛ ግምት ያገኘው ቡድኑና አባላቱ ምን ዓይነት ዝግጅት ሲያደርጉ ቆዩ፣ መራዘሙ ምን አስከተለባቸው እንዲሁም በዚህ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ በሚለው ጉዳይ ላይ የቡድኑ አባላት የሚናገሩት አላቸው። ለቡድኑ ከተመረጡትና ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በምርጥ አቋም ላይ ከነበሩአትሌቶች መካከል አንዱ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊው ጌትነት ዋለ ይጠቀሳል። አትሌቱ ኦሊምፒክን ጨምሮ በግሉ ይሳተፍባቸው ለነበሩ ውድድሮች ከአሰልጣኙ ጋር በመሆን ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ይገልጻል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ኦሊምፒኩ መራዘሙ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ጎልቶ የሚታየው ጌትነት፤ «አትሌት ባለበት አቋም መጠቀም የሚገባው በወቅቱ ነው» የሚል አመለካከት አለው። የየትኛውም አትሌት አላማ የሆነውን በኦሊምፒክ ሀገርን ወክሎ ድል ማስመዝገብ ካለመቻሉም በላይ ከሚወዱት ሥራቸውም መነጠል ያስከፋል። ነገር ግን ቫይረሱ በመላው ዓለም ሕዝብ ላይ ስጋትና አደጋ በመሆኑ፤ ወቅቱ ይለፍ እንጂ በርትቶ በመስራት ብቃትን መመለስ እንደሚቻል ያምናል። አቋሙ ባለበት እንዲቀጥልም በቤቱ ውስጥ ከቀደመው ጊዜ ያነሰ ልምምድ እየሰራ ጊዜውን በማሳለፍ ላይ ይገኛል። እንደ አጋጣሚ ሆኖ አሰልጣኙ እርሱ በሚኖርበት አቅራቢያ የሚኖር በመሆኑ አልፎ አልፎ በርቀት እየተገናኙ መመሪያዎችን የሚቀበልና በስልክም መረጃ እንደሚለዋወጡ ይጠቁማል። ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመገናኛ ብዙኃን ታግዞ በባለሙያዎች የሚሰጠውን መረጃም ይከታተላል። ሌሎች አትሌቶችም በዚህ መልኩ ከቤታቸው ሳይርቁና ሰዎች በብዛት ባሉባቸው ስፍራዎች ባለመገኘት በአቋማቸው ለመቀጠል እንቅስቃሴ እንዲያደርጉም ጥሪውን ያቀርባል። ኦሊምፒክ በጉጉት ይጠብቀው የነበረውድድርና ከአሰልጣኙም ጋር ልዩ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ መሆኑን የሚያስታውሰው ደግሞ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሥልጠናውን ያጠናቀቀውና ሌላኛው የ3ሺ ሜትር መሰናክል ወጣት አትሌት አብረሃም ስሜ ነው። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ይህ ቫይረስ መከሰቱ ቢያሳዝንም በዓለም የመጣ ነገር በመሆኑ የግድ ራስን ከቡድን ልምምድ ማራቅ ተገቢ ነው። የኦሊምፒክ መራዘም አማራጭ የሌለው ጉዳይ ቢሆንም እርሱን በመሰሉና በመልካም አቋም ላይ ለነበሩ አትሌቶች ጉዳት አለው። ይህ ቫይረስ እስኪያልፍ ድረስም ጊዜውን እንደ ማገገሚያ በመጠቀም በአቋሙ ለመቆየት በቤቱ እንቅስቃሴ ማድረግ አላቋረጠም። እንደ ቡድን አጋሩ ጌትነት አብርሃምም የሚኖረው ከአሰልጣኙ ጋር በቅርብ ርቀት አካባቢ በመሆኑ በስልክ ከመገናኘት ባለፈ በአካል ተገናኝቶ ለመወያየትም ዕድል ሰጥቶታል። በአሰልጣኞች እንዲሁም በጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ በመተግበርም እንቅስቃሴውን ቀጥሏል። በየማዕከላቱ የሚሰለጥኑ ታዳጊዎችን ጨምሮ በየክለቡ ያሉ አትሌቶች ተበትነው በየክልሉ ተመልሰዋል። በመሆኑም ጊዜው እስኪያልፍ ድረስ ከእንቅስቃሴ ሳይርቁ እንዲቆዩ መልዕክቱን ያስተላልፋል። በብሔራዊ ቡድን የ3ሺ ሜትር መሰናክል ዋና አሰልጣኙ ተሾመ ከበደ በብሔራዊ ቡድን ከተካተቱ አትሌቶች አብዛኛዎቹ ከእርሱ ጋር የነበሩ በመሆኑ ወጥ የሆነ ልምምድ ላይ እንደነበሩ ያስታውሳል። ከአትሌቶቹ ጋር በመሆን በቤት ውስጥ ቻምፒዮና ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተው ለዓመታዊው ዳይመንድ ሊግ ውድድር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፤ የኦሊምፒክ ሚኒማ ለማሟላት ሲሰሩም ነበር። ነገር ግን የኦሊምፒክ መራዘምን ተከትሎ ቡድኑ በመበተኑ አትሌቶች ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከል አቅማቸውን ሊያጎለብት የሚችል ቀላል እንቅስቃሴዎችን እየሰሩ እንዲቆዩ ተደርጓል። ቀድሞ ለአምስት ቀናት ያደርጉ የነበረውን መደበኛ ስልጠና እና ጫና በመቀነስም ክብደት እንዳይጨምሩ ቀላል እንቅስቃሴዎችን በየቤታቸው ይሰራሉ። አሰልጣኞችም በስልክና በሌሎች መንገዶች ከአትሌቶቻቸው ጋር በመገናኘት መስራት ያለባቸውን እየነገሯቸው መሆኑንም ይጠቁማል። የኦሊምፒኩ መራዘም እንደ ሀገር የሚያስከትለው ጉዳት መኖሩን የሚያነሳው አሰልጣኙ፤ እርሱ በሚያሰለጥንበት ርቀት ደግሞ አትሌቶች በጥሩ አቋም ላይ በመቆየታቸው ለኦሊምፒኩም የማሸነፍ ዕድል ነበራቸው። በአንጻሩ መራዘሙ የሚጠቅመው በጉዳት ላይ የቆዩና በወቅቱ በጥሩ አቋም ላይ ያልነበሩ አትሌቶችን ነው። ሁኔታውን ተጠቅመው አቅማቸውን አጎልብተው በመመለስ ብርቱ ተፎካካሪ የመሆን ዕድል ያላቸው በርካቶች እንደመሆናቸው ይህ ጊዜ ሲያልፍ ጠንካራ ሥራ ከአትሌቶች የሚጠበቅ መሆኑንም አሰልጣኙ ያመላክታል። በመጨረሻም አሰልጣኙ አትሌቶች ራሳቸውን ከዚህ ቫይረስ እንዲጠብቁ መልዕክቱን አስተላልፏል። ራሳቸውን ከበሽታ ሊከላከል የሚችልና ያሉበትን አቋም የሚጠብቅ እንቅስቃሴ ከማድረግ በዘለለ ራሳቸውን በጤና መጠበቅ እንዳለባቸውም ምክሩን ይለግሳል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 19/2012
https://www.press.et/Ama/?p=31209
1b49b04e2c22f69c691ac5f085d855b8
31430e6b6122d55b4e12362e084163ed
የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር የ4 ሚሊዮን ብር ሽያጭና የገበያ ትስስር እንደሚፈጠር ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲሱ ገረመው አዲስ አበባ፡- የ2013 በጀት ዓመት የ4 ሚሊዮን ብር ሽያጭና የገበያ ትስስር እንደሚፈጥር የፌዴራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አስታወቀ። ከተሳታፊዎች ውስጥ 50 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸው ተጠቆመ ። ኤጀንሲው ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በ2013 በጀት አመት አንደኛው ዙር የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር ‹‹ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር ለስራ ዕድል ፈጠራና ለኢንተርፕራይዞች ልማት መሰረት ነው ›› በሚል መሪ ቃል ከታህሳስ 22 እስከ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም በጀሞ አንድ አደባባይ ትራፊክ መብራት ፊትለፊት ለሰባት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ይሆናል። የ4 ሚሊዮን ብር ሽያጭና የገበያ ትስስር እንዲሚፈጥርም ይጠበቃል። በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ላይ ከሁሉም ክልሎችና ከተሞች የተውጣጡ 202 የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች 10 አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን፤ ሴቶች 50 በመቶ እና አካል ጉዳተኛ ሦስት በመቶ በማሳተፍ ምርትና አገልግሎታቸው ከ20ሺ በላይ በሚሆን ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍል እንዲጎበኝ ይደረጋል ብሏል ። ባዛሩ ከተለያዩ ክልሎችና አካባቢዎች የተሰባሰቡና በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሰማሩ ብቁና ተወዳዳሪ ኢንተርፕራይዞችንና አንቀሳቃሾችን የሚያሳትፍ ሲሆን፤ በአንድ ማዕከል በማገናኘት በሚፈጠረው ትውውቅና የልምድ ልውውጥ በመካከላቸው ጤናማ የውድድር ስሜት ለማቀጣጠል እንደሚያስችልም “ኤጀንሲው አመልክቷል ። ባህላዊና ዘመናዊ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ምርት ውጤቶች፣ ባህላዊና ዘመናዊ የቆዳ አልባሳትና የቆዳ ምርት ውጤቶች፣ ባህላዊ የዕደ-ጥበባትና ቅርጻ-ቅርጽ ሥራዎችና ውጤቶች፣ የብረታብረት፣ የእንጨት ሥራና የኢንጅነሪንግ ስራዎችና ውጤቶች፣ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ምርቶች እና የከተማ ግብርና ውጤቶች፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የፈጠራ ስራዎች፣ ፈሳሽ ሳሙና፣አልኮል፣ሳኒታይዘር፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል/ማስኮች/፣ እና ሌሎችም ምርቶች በኤግዚቢሽንና ባዛሩ እንደሚቀርቡ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ነጋዴ ሴቶች ማህበር፣ የሴቶች ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ፕሮግራም፣ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ማዕከል፣ ፋሽን ዲዛይን አሶሴሽን፣ የሴቶች ራስ አገዝ ድርጅት፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በዕደ ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና ሌሎችም ተሳታፊ ኢንተርፕራይዞች እንደሚሆኑ ጠቁሟል። ሁነቱ የተሞክሮ ልውውጥና የንግድ ልማት ግንዛቤ ከማዳበሩም ባሻገር፤ ኢንተርፕራይዞች ከተጠቃሚው ህብረተሰብ ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት ዘላቂ የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ምቹ አጋጣሚ ይሆንላቸዋል። ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን ለተጠቃሚዎች በቀጥታ በመሸጥም ተጠቃሚ እንደሚሆኑም እጀንሲው አስታውቋል ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 22/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38532
be0454755e017aa3d93b5dbe74382487
3e7abc4b9373e017c91a86544fde8cd1
የመቀሌ ከተማ በአስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ የመቀሌ ከተማ በአስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ላይ እንደምትገኝ የከተማው ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታወቀ ። በህብረተሰቡ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው የገንዘብ ቅያሪም ባንኮች ሥራ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንዲፈጸም ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።ከከተማዋ ኮሙኒክሽን ጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ በቤተ እምነቶችና በሌሎች ቦታዎች ላይ ተሰብስቦ የተገኘ ሰው ይገደላል፣ ታፍሶ ወደበረሃ ይወሰዳል እየተባለ ከፍተኛ ውዥንብር ይነዛ ነበረ፤ ሆኖም በትናንትናው እለት የማርያምን ወርሃዊ በዓል ለማክበር ህዝቡ በመቀሌ ከተማ እነዳማርያም ቤተክርስቲያን በብዛት በመገኘት በተረጋጋ ሁኔታ ለአሉባልታዎች ጆሮ ባለመስጠት ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ፈጽሟል። በከተማዋ የገበያ ስፍራዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ወደቀድሞ ስራቸው እየተመለሱ ነው፤ ህዝቡም ምንም ሳይሸበር በሰላማዊ መንገድ ወጥቶ የፈለገውን ጉዳዩን ፈጽሞ ተገበያይቶ ቤቱ እንዲገባ የማድረጉም ስራ እየተሰራና ውጤትም እየታየበት ይገኛል። በከተማዋ ክፍለ ከተሞችንና ወረዳዎችን የማደራጀት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያለው መረጃው፣ እስከ አሁን ለስድስቱም ክፍለ ከተሞች አመራር የመምረጥ ስራ ተጠናቋል። በእነዚህ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ላሉ ቀበሌዎች ደግሞ 20 አባላት ያሏቸው ካቢኔዎች ተደራጅተዋል፤ እነሱም የወረዳ አመራሮችን የመረጡ ሲሆን በትናንትናው እለት የአይደር ክፍለ ከተማ አመራር ተመርጧል። ከዚህ ቀደም 88 በመቶ የሚሆነው የመንግስት ሰራተኛ ወደ ስራው ለመመለስ ሪፖርት አድርጎ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ሪፖርት ካደረጉት ውስጥ ምን ያህሉ በስራ ገበታቸው ላይ ተገኙ የሚለውን ለማጣራት የታህሳስ ወርን የስራ አፈጻጸም በመሰራት ላይ መሆኑን የገለጸው መረጃው ፤ ስራው እንደተጠናቀቀም ውጤት እንደሚገለጽ ተብራርቷል። በሌላ በኩልም የመቀሌ ከተማ ንግድ ምክር ቤት እንደ አዲስ ተቋቁሞ የንግዱ ማህበረሰብ ህዝቡን ለማገልገል ስራዎች ወደነበነሩበት እንዲመለሱ የራሳቸውን ጥረት እያደረጉ ሲሆን በተለይም ከወልድያ መቀሌ ያለው መንገድ ክፍት መደረጉ በከተማዋ ያለው የንግድ እንቅስቃሴ ሞቅ እንዲል ብሎም ከዚህ ቀደም እጅግ ዋጋቸው ንሮ የነበሩ የእህል ምርቶች ዋጋ እንዲቀንሱ ማስቻሉን መረጃው ያመለክታል። “ባለፈው አንድ ወር ከተማው ትርምስምሱ ወጥቶ ፤ የታክሲ ታሪፍ ፣ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎች በውል እስካለመታወቅ ደርሰው ነበር ፤ አሁን ላይ ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች በሚገባ ተስተካክልውና ወደቦታቸው ተመልሰዋል፤ የትራፊክ ፖሊሶችም ወደመደበኛ ስራቸው ገብተው ህግ እያስከበሩ ነው” ብላል። በሌላ በኩልም የትራፊክ ፍሰቱን አውኮ የነበረው የጸጥታ ሁኔታ እንዲሁም የነዳጅ እጥረት በአሁኑ ወቅት መፈታት ስለቻለ ከባጃጅ ጀምሮ ታክሲና ሌሎች የትራንስፖርት አማራጮች ወደስራ ገብተዋል ያለው መረጃው፣ ህብረተሰቡም ይህንን በመገንዘብ ከአላስፈላጊ ውዥንብሮች ራሱን ጠብቆ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባም አመልክቷል። የከተማዋ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትም ከተማዋ ላይ በብዛት ተቆልሎ የሚገኘውን ቆሻሻ በማንሳትና የጽዳት ስራዎችን የመንገድ ዳር የማስዋብ ተግባራትን እያከናወነ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን የራሱን ሚና እየተጫወተ መሆኑ መረጃው አመልክቷል። የጁንታው ቡድን ከወህኒ ቤት ፈትቶ የለቀቃቸው የህግ ታራሚዎች በከተማዋ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ስጋት ጋርጠው እንደነበር ያስታወሰው መረጃው ፣ አሁን የክልሉ ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት በተቀናጀ ሁኔታ በሰሩት የህግ ማስከበር ስራ ከተማዋ ከእለት እለት መረጋጋት እያሳየች ትገኛለች። “ መንግስት ይሄዳል መንግስት ይመጣል ይህ ደግሞ ምንም አዲስ ነገር የለውም፤ ትግራይ ክልል ላይም የተከሰተው ይኸው ነው፤ አንዳንዶች ግን ለውጡን ለመቀበል ተቸግረዋል፤ አብዛኛው ህዝብ ግን የተቀየረውን መንግስት ደግፎ ሰላሙ ተረጋግጦ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እየጠየቀ ነው፤ በዚህ መካከል ግን ህወሓት ተመልሶ ክልሉን ያስተዳድራል በማለት በህዝቡ ላይ ጥርጣሬን የሚነዙ አሉ ህብረተሰቡ ይህንን ተረድቶ ወደ ኋላ ሳይሆን ወደፊት እየሄደ ልማቱን ማስቀጠል እንደሚኖርበት አሳስቧል። በተያያዘ ዜና ተቋርጦ የነበረውን የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ከታህሳስ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ14 ቀናት እንዲከናወን ብህራዊ ባንክ መወሰኑ ተገልጿል።የገንዘብ ኖቶ ቅየራው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እንደሚከናወን ያስታወቀው ባንኩ በብር መቀየሩ ሂደት የነበሩ መመሪያዎችና አሠራሮች እንደተጠበቁ መሆናቸውንም አስታውቋል።ከባንክ በጥሬ ገንዘብ የሚወጣው የገንዘብ መጠን ላይ በተሻሻለው መመሪያ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን ከ100 ሺ እስከ 1ነጥብ 5 ሚሊዮን አሮጌ ብር ያላቸው የመቀየሪያው የጊዜ ገደብ የህግ ማስከበሩ ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት የተጠናቀቀ በመሆኑ ብር መቀየር የሚችሉት ከ100ሺህ ብር በታች ያላቸው መሆናቸውን ባንኩ ጠቁሟል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 22/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38541
2db81eca975adbf5daa09559c11c31c5
c8fbe02c95e54c69ff124b6c97535312
በሬሳ ሳጥን ውስጥ መቆየት ያሸልማል
መዝናኛ
ጎበዝ የሬሳ ሳጥን ስትመለከቱ ምን ይሰማችኋል። አንዳንዶች ሟች ዘመድ ወዳጆቻቸውን ሊያስቡ ይችላሉ። አንዳንዶች ደግሞ ሞት አጠገባቸው የደረሰ ይመስላቸውም ይሆናል። አይደለም የሬሳ ሳጥን የሬሳ መኪና ሊፍት ሊሰጣቸው ሲቆም የሚሸሹም አጋጥመውኛል። የሚሪላንዱ ቲም ፓርክ ግን ጥንዶች በሬሳ ሳጥን ውስጥ ለበርካታ ሰአታት ሊቆዩ የሚችሉበትን ውድድር እያዘጋጀ ነው። በውድድሩ እንዲሳተፉ የሚጠበቁት ጥንዶች በሬሳ ሳጥን ውስጥ ለ30 ሰአታት እንዲቆዩ ይደረጋል። ውድድሩ የሚካሄድበት ስፍራም በጣም ያልተለመደ ነው። የሬሳ ሳጥኖቹ ስድስት ሰንደቅ አላማዎች የሚደረጉባቸው ሲሆን ፣ፍቅረኞች ፣ ጓደኛሞች፣ የቤተሰብ አባላት፣ወዘተ የሆኑ ስድስት ጥንዶች እንዲሳተፉ የሚደረግበት መሆኑን ዩፒአይ ሰሞኑን የለቀቀው መረጃ ያመለክታል። ጥንዶቹ በቀን ለሰላሳ ሰአት ከፈረንጆቹ መስከረም 27 ቀን ከጠዋቱ 4 ሰአት አንስቶ እስከ መስከረም 28 ቀን 10 ሰአት ድረስ በሬሳ ሳጥኑ ውስጥ መቆየት ይኖርባቸዋል። ጥንዶቹ በቆይታቸው ፓርኩ ስራ ላይ በሚሆንባቸው ሰአቶች በፓርኩ አቅራቢያ ጓደኛ ሊጠብቃቸው ይችላል።ፓርኩ ከተዘጋ በኋላ ግን ብቻቸውን እንዲሆኑ ይደረጋል።ይህ የሆነበት ምክንያት የጨለማው ወቅት አስፈሪ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የሚኖራቸውን ስሜት ለመፈተን ተፈልጎ ይመስላል። ተወዳዳሪዎቹ በውድድሩ ወቅት ስማርት ስልኮችን እንዲይዙ አይፈቀድላቸውም። ይህ ብቻም አይደለም ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስንም መያዝ አይኖርባቸውም። እነዚህ ቁሳቀስ መያዝ የሚችሉት በተፈቀደላቸው የእረፍት ጊዜ ብቻ ይሆናል። ‹‹ መጸዳጃ ቤት ለመጠቀምና ምግብ ለመብላት ከተፈቀደው ጊዜ ውጪ በተለያየ ምክንያት ከሬሳ ሳጥኑ የወጣ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጪ እንደሚደረግ ፓርኩ አስጠንቅቋል። ተወዳዳሪዎቹ ሰው ሰራሽ ጭጋግና መብረቅ እንደሚለቀቅባቸውም ተጠቁሟል። የፎቶግራፍ ፍላሾችና ከባድ የአየር ሁኔታ እንዲሚጠብቃቸውም ታውቋል። ይህን ሁሉ ፈተና አልፈው ለውድድሩ ከተያዘው 30 ሰአት በኋላ የሚገኙ ጥንዶች እያንዳንዳቸው 600 ዶላር የሚሸለሙ ይሆናል። አዲስ ዘመን  መስከረም 13/2012 ዘካርያስ
https://www.press.et/Ama/?p=19038
1565812f10a6db02c5f4ee53d3073b05
5e414daaaf06110cffcbf1e860041df3
የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው የእግር ኳሱ ዓለም ፈተና
ስፖርት
በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያንቀሳቅሰው የስፖርት ዓለም ላይ በመጣው ፈተና ምክንያት በእጅጉ እየተጎዱ ካሉት ዘርፎች መካከል እግር ኳስ አንዱ ሆኗል።በርካቶችን በአንድነት በማሰባሰብና በአንድ ስፍራ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾች ከሚገኙባቸው መዝናኛዎች መካከል አንዱ የሆነው ስፖርት ለቫይረሱ እጅግ አጋላጭ ሁኔታን እንደሚፈጥር ታምኖበታል።በመሆኑም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በቅድሚያ ያለ ደጋፊ እንዲካሄድ ቀጥሎም ሙሉ ለሙሉ ሊቋረጥ ችሏል።ይህ ደግሞ እንደሌላው የኢኮኖሚ ዘርፍ ሁሉ ኪሳራን እንዲያስተናግድ አስገድዶታል። እአአ በ2018 የስፖርቱ ዘርፍ 471 ቢሊዮን ዶላር ነበር ያስመዘገበው፤ ይህም እአአ ከ2011 ጋር ሲነጻጸር በ45 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ ነበር።አሁን ግን የስፖርቱ ሰንሰለት በኮቪድ 19 ምክንያት ተቋርጧል፤ ስፖርተኞች፣ ክለቦች፣ ሊጎች፣ ጨዋታዎችንና ውድድሮችን የሚያሰራጩ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ሌሎች የስፖርቱ አካላት እንደ ድሮ መንቀሳቀስ አልቻሉም።ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው ደግሞ ተወዳጁ የእግር ኳስ ስፖርት ቢሆንም፤ በዚህ ዓመት ገቢው ይጨምራል በሚል ቢጠበቅም ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ውድድሮች በመቋረጣቸው ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል። በዚህ ስፖርት እያንዳንዶቹ ክለቦች የየራሳቸው የሆነ መለያና አሰራር ቢኖራቸውም ዋነኛ ገቢያቸውን የሚያገኙት ከሶስት ምንጮች ነው።ይኸውም ከመገናኛ ብዙሃን የስርጭት መብት፣ ከስፖንሰርና ማስታወቂያዎች እንዲሁም በጨዋታ ወቅት ከስታዲየም የትኬት ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ ነው።10 በሚደርሱ ሊጎች ያለው ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነም ክለቦቹ ከሚዲያ መብት ብቻ ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገኛሉ።ይህም ከአጠቃላይ ገቢያቸው 60 ከመቶ የሚሸፍን መሆኑን ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም በዘገባው ያመላክታል። ተወዳጁና በዓለም ላይ ከፍተኛ ተመልካች ያለው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ባለፈው ዓመት አዲስ በገባው (ለሶስት ዓመታት) ኮንትራት 12 ቢሊየን ዶላር ከሚዲያ መብት ብቻ ለመሰብሰብ አቅዶ ነበር።ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ይህንን ማሳካት የሚቻል አይመስልም፤ ምክንያቱም ከተቋረጠ ሁለት ወራትን እንኳን ሳያስቆጥር ክለቦቹ ከ60 እስከ 150 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ ማስተናገዳቸውን እያስታወቁ ነው። እንደ ዴይሊሜይል ዘገባ ከሆነም ከቴሌቪዝን መብት ከሚገኝ ገቢ ብቻ እያንዳንዱ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለብ 750 ሚሊየን ፓውንድ ያጣል። በዚህም ምክንያት ክለቦቹ ከተጫዋችና አሰልጣኞች ቡድን ባሻገር የሚገኙ ሰራተኞቻቸውን በጊዜያዊነት እያሰናበቱ ነው።የተጫዋቾቻቸውን ደመወዝ ለመክፈል በመቸገራቸውም አንዳንዶች ግማሽ ክፍያ ሌሎች ደግሞ የተወሰነ ቅናሽ በማድረግ እንደሚከፍሉ እያሳወቁ ነው።በተያዘው ወር መጀመሪያ ላይም ሊጉ ሃያዎቹ ክለቦች ከተጫዋቾች ደመወዝ 30 በመቶ ለመቀነስ የተጫዋቾቻቸውን ስምምነት እንዲጠይቁ ማሳወቁን ጎል ዶት ኮም አስነብቧል።በስምምነቱ ማንቸስተር ዩናይትድ የመጀመሪያው ክለብ ሲሆን ተቀናሽ የሚሆነው ገንዘብ ቫይረሱን ለመከላከል ለሚደረገው ትግል ገቢ እንዲደረግም ወስነዋል። የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር በበኩሉ ክለቦች አቅሙ ካላቸው ሙሉ ክፍያ ለተጫዋቾች እንዲሰጡ፤ ካልቻሉ ግን የክለቦቻቸውን የፋይናንስ ኪሳራ እንዲጋሩ ለአባላቱ ጥሪውን አቅርቧል። ይህ በዓለም የመጣው አስቸጋሪ ሁኔታ በኢትዮጵያም መስተናገዱ አይቀርም።በተለይ የሊጉ ክለቦች በአብዛኛው በመንግስት የሚደጎሙ እንደመሆኑ ጠንካራ ፋይናንስ ያላቸው ክለቦች ያቃታቸውን ይወጡታል ማለት አስቸጋሪ ነው።በእንግሊዝና በሌሎች ሊጎች የታየው የደመወዝ ቅነሳም በኢትዮጵያ ክለቦችም እየታየ ይገኛል፡፡ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደግሞ በዚህ ረገድ ቀዳሚው ሆኗል።ፕሪምየር ሊጉን ዘንድሮ የተቀላቀለው ክለቡ በኮሮና ቫይረስ በተቋረጠው ሊግ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን የፋይናንስ ጫና ለመቀነስ በማሰብ ተጫዋቾች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ላለመውሰድ መወሰናቸውን ሶከር ኢትዮጵያ በዘገባው አስነብቧል። በቀጣይም የክለቦችና ተጫዋቾች ገቢ በምን ዓይነት ሁኔታ ይቀጥላል የሚለው የወቅቱ ፈተና እንደሚሆን ነው የሚጠበቀው፡፡አዲስ ዘመን ሚያዝያ 10/2012
https://www.press.et/Ama/?p=30594
bf1158e325e73dfeefb6e109f63d436e
e10eb64dc6d136aecb7fc5a3a35fdabe
የስፖርት ማኅብረተሰቡ- ማኅበራዊ ኃላፊነት የመወጣት ሰብዓዊው መንገድ
ስፖርት
የዓለም ሕዝብ ሁሉ ጭንቀትና ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ ከሀብታም እስከ ድሃ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዋነኛ ትኩረቱ እንዲሆን ካስገደደ ስድስት ወራት ተቆጠሩ፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በእነዚህ ወራት እንደ ሰደድ እሳት ያላዳረሰው የዓለም ክፍል ስለመኖሩ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ ሀገራት ዓለም በጋራ የገጠማት ጦርነት በድል ለመወጣት የሚያስችል መፍትሄ ለማበጀት ጥረት ማድረጉን ተያይዘውታል። የቫይረሱ ማንነትና፣ ምንነት ፈጣን መፍትሄ ማበጀት የሚያስችል አልሆነም። በእርግጥም የኮሮና ወረርሽኝ በዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ብቻ ነውን? በእኔ እሳቤ አዎንታዊ እንዳለው መካድ ንፍግነት ይሆናል! የኮሮና ቫይረስ ዓለምን እንደጎዳት ባለበት ደረጃ ባይሆንም በጎ መልኮችን ይዞ መምጣቱን በድፍረት መናገር ይገባል። ዓለም ከገባችበት የጋራ ማዕጥ ለመውጣት ከሚደረግ ጉዞ የሚቀዳው «ሰውነትን» ያስቀደሙ ደጋግ እጆችን፤ ኅብረተሰቡ ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ ሰብአዊነትን አርግዘው የሚወለዱ ድጋፎችን በዘመነ ኮሮና ሊበረክቱ ችለዋል። በዓለም አራቱም አቅጣጫዎች ሰብአዊነትን ባስቀደመ መልኩ ሲደረጉና እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን ብሶባቸው ታዝበናል። በተለያዩ መስኮች እንፋሎቱ ሳይበርድ የቀጠለው ልግስና ከስፖርቱ መስክ ያለውን ሁኔታ መመልከቱ ይበጃል። ስፖርት ሰላም፣ ፍቅር፣ የአብሮነትና የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የወንድማማችነት ልዩ መገለጫ ነው። ስፖርት ዘር፣ ሃይማኖት፣ ፆታና ቀለምን አይለይም። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አስኳል ሃሳብ ወዳጅነትና መተሳሰብ መሆኑ ይታወቃል። በታሪክ ገጾች እንደሰፈረውም በሰው ልጅ ታሪክ ባጋጠሙ በጎም ሆኑ መጥፎ ክስተቶች ስፖርት በአጋርነት ተሳትፏል። ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ሰላምንና አንድነትን የሚሰብኩ እንደመሆናቸው በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በመግባት ሚናቸውን ሲወጡም ኖረዋል። ስፖርት ሰብአዊነትን ያነገበ የልግስና ማዕድ መሆኑን ዘመነ ኮሮና በተጨባጭ አሳይቶናል። የቫይረሱ ስጋትነት በዓለም አቀፉ የጤና ተቋም ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ፤ ውድድሮችን ከማቋረጥና ከመሰረዝ ባለፈ የስፖርቱ ተዋንያን በተናጥልም ሆነ በተቋማዊ ደረጃ አበርክቷቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። በእግር ኳስ ጠቢብነታቸው ዓለም የመሰከረላቸው ተጫዋቾችና ስመ ጥር አሰልጣኞችም፤ ለደጋፊዎቻቸው መልእክት ከማስተላለፍና ገንዘብ ከመለገስ ባሻገር ሆቴሎቻቸውን ለህክምና አገልግሎት እንዲውሉም ጭምር መስጠታቸው ይታወሳል። በሀገራችን በተመሳሳይ የስፖርቱ ለጋስነትና ሰብአዊነት መገለጫ ያደረጉ ተግባራት ዛሬም እንደ ትናንቱ በዘመነ ኮሮና ከነበረው ብሶበት አለኝታነቱን እያሳየ ይገኛል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ከታወቀበት ከመጋቢት መጀመሪያ አንስቶ በስፖርቱ ማህበረሰብ ጠንካራ እንቅስቃሴ በማድረግ አጋርነቱን በፈጠነና በቀደመ መልኩ ያሳየው። በስፖርት ቤተሰቡ በቡድንም ሆነ በተናጠል ለወረርሽኙ መከላከያ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ከመንግስት ጎን በመቆም ወገን ላይ የተደቀነውን አደጋ በአንድነት ለመመከት ህዝባዊነቱን ማሳየት ችሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የድጋፍ መሠባሰብ ጥሪ ተከትሎ የስፖርቱ ማህበረሰብ ተሳትፎ በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉን ለመታዘብ ችለናል። ከመከላከያ ስፖርት ክለብ አካባቢ የተሰማው ዜና ይሄንኑ ያስረዳል። የመከላከያ ስፖርት ክለብ አዋቂ ወንዶች እና ሴቶች እግር ኳስ ቡድን እና ኮቺንግ አባላቱ 211 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል። የስፖርት ክለቡ ለኮረና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር እንዲውል በከተማ አስተዳደሩ ለተቋቋመ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ ነበር ገንዘቡን ያስረከበው። «የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባቀረበው የድጋፍ ጥሪ መሠረት የኮቪድ -19 ለመግታት በሚደረገው ርብርብ የበኩላችንን ለመወጣት ነው» ሲሉ ነበር የስፖርት ክለቡ አባላት በስፖርቱን ማህበረሰብ ዘንድ ሰብአዊነትን ባስቀደመ መልኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየተደረገ ያለውን ተሳትፎ ያመላከቱት። የሀገር ዳር ድንበር ህልውና ከሆነው የስፖርቱ ክለብ በተመሳሳይ፤ በስፖርቱ የሰብአዊነት ልግስናው ተጠናክሮ የመቀጠሉን ሁኔታ የጠዋት ጎህ አትሌቶች የልማት መረዳጃ ተግባርም ይነሳል። በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ድል በማድረግ የሀገራችንን ሰንደቅ አላማ በማወለብለብ ስሟና ዝናዋን ከፍ ባደረጉት አትሌቶች የተቋቋመው ዕድሩ 200 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን አስመስክረዋል፡፡ የአትሌቶቹ የመረዳጃ ዕድር አባላት አስተባባሪዎች ኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ፣ አትሌት ተስፋዬ ቶላ፣ አሰልጣኝ ንጋቱ ወርቁ ፣ ዶክተር በዛብህ ወልዴ እና ወይዘሮ አይናዲስ ተስፋዬ ድጋፍ ለማድረግ የመሻታቸውን ሚስጥር በጋራ እንዲህ አጋርተዋል። «ዓለም ብሎም ሀገራችን በጭንቅ ተውጣለች። ህዝባችንም በሲቃ ተኮራምቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኮረና ቫይረስ መከላከል ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ እኛም የዜግነት ግዴታችን ለመወጣት የገንዘብ ድጋፍ ልናደርግ ወደናል። ኢትዮጵያዊነታችን የሚደምቀው በዚህ በጭለማና በጭንቅ ወቅት ስንረዳዳና ስንተጋገዝ በመንፈስና በፀሎት አብረን ከማህበረሰባቸን ጎን ስንቆም ነው» የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከሆኑ አትሌቶች ልግስና ወረድ በማለት እንደ መቋጫ አንድ ክስተት ስንጠቅስ፤ በኢትዮጵያ የወንዶችና የሴቶች ብሔራዊ ቡድኖች አሠልጣኞች እንዲሁም የስፖርቱ ሙያተኞች የተደረገ ልግስና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ከስፖርቱ ቤተሰብ በኩል እየተደረገ ያለውን ልግስና የሚያሳየው ሁነት ነው። እነዚህ አካላት ህዝብን ለመታደግ በሚደረገው ርብርብ በየአቅጣጫው 120 ሺህ ብር መሰብሰብ ችለዋል። ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ለኢንጂነር ታከለ ኡማ አስረክበዋል፡፡ ይህ ተግባር በአጠቃላይ ከስፖርት ማኅብረተሰቡ ዘንድ የተንፀባረቁትን ወገናዊ ድጋፎችንና ችግርን በአንድነት ለመመከት እየተደረገ ካለው ጥረት በመነሳት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከፈጠረውና ካሳደረው አሉታዊ ተጽእኖ ጎን ለጎን የፈጠረው በጎ መልክ ስለመኖሩ የሚያስገነዝብ ይሆነናል። በስፖርት ማኅብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ጉዞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እሙን ነው።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 9/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=30621
7004703c5675339f68245554721d8e21
c2116d9c852f65fce77b7b7a9de24ef3
‹‹ፋሲል ከነማ›› – የትውልድ ቅብብሎሽ አርማ!
ስፖርት
 በአገራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በእግር ኳሱ ትልቅ ተፅዕኖ እያሳደሩ ከመጡ ክለቦች አንዱ ፋሲል ከነማ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አያስፈልግም። ክለቡ የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ መሆኑን ካረጋገጠ ወዲህ በጥቂት ዓመታት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልታና ማገር የሆኑ በርካታ ተጫዋቾችን ከማበርከት ባለፈ በፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ በመሆን በተደጋጋሚ ዓመታት ጥንካሬውን አሳይቷል። በቁጥርም በውበትም የእግር ኳሱን ቤተሰቦች ያስደመሙ ደጋፊዎችን በማበርከትም ካምቦሎጆን ካደመቁ ጥቂት ክለቦች መካከል አንዱ ሆኗል። የውብ ደጋፊዎች ባለቤት የሆነውን ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከብዙ በጥቂቱ በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችን እንደሚከተለው ለመመልከት ወደድን።1960 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ላይ የያኔ ወጣቶች በአገሪቱ የነበሩ ትልልቆቹን የእግር ኳስ ቡድኖች (አሥመራ ቡድን፣ ሸዋ ቡድን፣ አየር ኃይል ቡድን፣…) እያሰቡ፤ አንድ ትንሽ የእግር ኳስ ቡድን በራሳቸው ጥረት መሰረቱ። በጨርቅ ኳስ የተጀመረው የእግር ኳስ ቡድን ስብስብ ብዙ የተለየ እንቅስቃሴ ሳያድርግ ስድስት ዓመታት ተቆጠሩ። ስብስቡ የሰፈር ጨዋታዎችን ከማካሄድ ሳይሻገር ኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ አስተናገደች። ሕዝባዊ አብዮት። የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት የአገሪቱን ፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ መዋቅሮች ብቻከገጽ 20 የዞረሳይሆን ማህበራዊ መዋቅሩንም ቀየረው። የለውጡ አካል የነበረችው ጎንደር፤ በሥር ነቀል ሂደቱ ውስጥ ስታልፍ በከተማው ውስጥ ከስድስት ዓመታት በፊት የተመሰረተው የእግር ኳስ ቡድን እንደዘመኑ መንፈስ አዲስ የቡድን ስያሜ ያዘ። ‹‹ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን›› ተሰኘ። አሁን ጊዜው 1967 ዓ.ም ሆኗል።የትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች በአብዛኛው የቀበሌ 16 በተለምዶ ‹‹ቸቸላ›› ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ልጆች ናቸው። በጊዜ ሂደት ግን ከየአቅጣጫው ቡድኑን የተቀላቀሉት የከተማዋ ወጣቶች አልጠፉም። መካሻ፣ አባቡ፣ ሰጠኝ፣ አራጋው፣ … የትግል ፍሬ እግር ኳስ ቡድን ሞተር ነበሩ። በእግር ኳስ ያበደ ልባቸው በፖለቲካ ለመቅለጥ ጊዜ አልፈጀበትም። አብዛኛዎቹ የቡድኑ አባላት በኢህአፓ የፖለቲካ መስመር ተጠለፉ። እንደዘመኑ መንፈስ፤ ህብዑ ገቡ። ይህም ሆኖ ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ከአቻዎቹ ጋር የእግር ኳስ ግጥሚያ ከማካሄድ አልቆመም። የግጥሚያ ሜዳው በየጊዜው ይቀያየር ነበር። ጎንደር ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በተለምዶ ‹‹ኳስ ሜዳ›› ተብሎ በሚጠራው ሜዳ፣ ፋሲለደስ መዋኛ ግቢ ፊት ለፊት (ዛሬ ላይ ፋሲለደስ ስታዲየም ተብሎ የተሰየመው)፣ ፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ … የእግር ኳስ ውድድሮች በተዘጋጁ ቁጥር ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ተሳታፊ ነበር።የደርግ ምህረት የለሽ ቅጣት በኢህአፓ ወጣቶች ላይ እየበረታ ሲመጣ፣ የመላኩ ተፈራ ፈርዖናዊ እብሪት በጎንደር አደባባዮች ላይ ናኘ። ከተማዋ በደም አበላ ታጠበች። ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ቅርቃር ውስጥ ገባ። የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች መመናመን ጀመሩ። ያም ሆኖ የቀይ ሽብር ዘመን አልፎ እንኳ ቡድኑ አልከሰመም። መደብዘዙ ግን አልቀረም።ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ‹‹ዓለም የለምም›› ሳይባል ዓመታት ነጐዱ። ደርግ በድራማዊ አጀብ እንደተከሰተው፤ በትራጄዲ ሁነት ተሰናበተ። ትግል ፍሬ እንደ አጀማመሩ ባይሆንም ቡድኑ በሥም ደረጃ ይንቀሳቀስ ነበር። ከደርግ ውድቀት በኋላ ግን ትግል ፍሬ በስምም ከሰመ። ለሁለት ዓመት ብቻ። 1985 ዓ.ም የትግል ፍሬ ተከታይ ትውልድ በአዲስ መንፈስ ‹‹ፋሲል›› በሚል ሥያሜ የእግር ኳስ ቡድን ተቋቋመ። ፋሲል ከነማ የሚለው ስያሜ የሽግግር መንግሥቱ ጊዜ ካበቃ በኋላ በተፈጠረው የከተሞች አደረጃጀት የመጣ ስያሜ መሆኑ እዚህ ላይ ይነሳል።1985 እና ከዛ በኋላ የነበሩ ዓመታት እንደ ቀዳሚዎች ዓመታት ከፖለቲካና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች አኳያ ለጐንደር ፈታኝ ጊዜያት ነበሩ። ማህበራዊ ቀውሶች በተጨማሪነት ቢስተዋሉም በእግር ኳስ ረገድ ግን ጥሩ መነቃቃት ነበር። ዛሬ ላይ ‹‹ታየ በላይ ሆቴል›› የተገነባበት ቦታ ‹‹ሜክሲኮ ሜዳ›› ይባል ነበር። በዚህ መለስተኛ ሜዳ በመሬት አርድ የእግር ኳስ ደጋፊዎች የታጀበ የእግር ኳስ ውድድር መርሃ ግብሮች ይካሄዱ ነበር። አራዳ፣ ውሃ ልማት፣ ፖሊ፣ ኳሊበር፣ ኒያላ፣ ኢዲዲሲ … የተሰኙ የእግር ኳስ ቡድኖች ቀንደኛ ተፋላሚዎች ነበሩ። ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ የተሻለ የመጫወት ጥበብ ያላቸው ተጫዋቾች ለፋሲል እግር ኳስ ቡድን መጋቢ በመሆን አገልግለዋል። የያኔው ፋሲል ከ‹‹ሜክሲኮ›› ጨዋታ ከፍ ባለ መልኩ ከወረዳ የእግር ኳስ ቡድኖች ጋር ይጫወት ነበር። ‹‹ፋሲል ከነማ የትውልዶች ቅብብል ውጤት ነው›› የሚባለውም ለዚህ ነው።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አደረጃጀትና የአሰራር ዝግመታዊ ለውጥን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ለዓመታት በከተማ ደረጃና በብሔራዊ ሊግ ደረጃ ሲጫወት ቆይቶ፤ በ2008 የውድድር ዘመን ብሄራዊ ሊጉን በበላይነት በማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፕሪሚሪ ሊግ ተሳታፊ ለመሆን በቃ። የትውልድ ቅብብሎሽ በታየበት በዚህ የታሪክ ሂደት መሰረት ክለቡ 50 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ አንጋፋ ክለብ ነው።‹‹ፋሲል ከነማ በትውልዶች ቅብብል የቆመ የከተማችን እግር ኳስ ክለብ ነው›› የሚለው አቋም የክለቡ ደጋፊዎች የጋራ ምልከታ ነው። በተለይም ክለቡ በብሔራዊ ሊግ ቆይታው በነበረበት የገንዘብ እጥረት የተነሳ ፈታኝ ጊዜያትን አሳልፏል። በ2008 ዓ.ም የብሔራዊ ሊጉ የውድድር ዘመን ፋሲል ምድቡን በበላይነት እየመራ እንኳን ከተማ አስተዳደሩ ለክለቡ የበጀተው በጀት በዓመቱ አጋማሽ አልቆ ነበር። በክለቡ ስም የንግድ ትርዒት (ባዛር) እና የሙዚቃ ዝግጅት (ኮንሰርት) በማዘጋጀት ገቢ በማሰባሰብ፤ በጐንደር ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ፤ በከተማው ወጣቶችና አጋር የስፖርቱ ቤተሰቦች ጥረት እንዲሁም ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በሰጠው ገንዘብ ዓመቱን እንደምንም ቆይቶ ብሔራዊ ሊጉን በድል በማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለመቀላቀል በቃ።ለብዙዎቹ የአገሪቱ እግር ኳስ ተከታታዮች ክስተት በሆነ መልኩ የፋሲል ከነማ ስኬታማ የሚባል ጉዞ ያለ ደጋፊው ማዕበል የሚታሰብ አልነበረም። የክለቡ ደጋፊዎች ፋሲል ከነማን እንደ አንድ የጎንደር የታሪክ አካል አድርገው ይመለከቱታል። ከዚህ ምልከታቸው በመነሳት ለክለቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ ማቀጣጠያ ዘዴያቸውም ታሪክ ነው። ‹‹የጎንደር ክብሯ ታሪኳ ነው›› የሚሉት የክለቡ ደጋፊዎች፤ የፋሲል ከነማ ክለብ ዋና መለያ ‹‹አፄዎቹ›› ሆኗል። በፖለቲካ አፈና፣ በማህበራዊ ሕይወት ብክነትና በኢኮኖሚ መገፋት ተበታትነው የነበሩት የጎንደር ከተማና አካባቢዋ ወጣቶች ፋሲል ከነማ ምክንያት ሆኗቸው በአንድነት ጥላ ስር ተገናኝተዋል። በፋሲለደስ ስታዲየም፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ጓዶቹ ስማቸው እየተነሳ ተዘምሮላቸዋል። አርበኛ ጐቤ መልኬ ታስቦበታል። ዛሬ ላይ ፋሲል ከነማ በአገሪቱ ቀዳሚ የደጋፊ ሃብታም ከሚባሉ ክለቦች አንዱ ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ተፎካካሪም ሆኗል። የድጋፍ መሰረቱ የሰፋውን ያህል ግን የገቢ አቅሙን ማሳደግ አልቻለም። ትላንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ ዘመናዊ አደረጃጀትና ዘላቂ የገቢ/ስፖንሰር ምንጭ ዕጥረት የክለቡ ፈተና ሆነው ይቀጥላሉ። ፋሲል ከነማ ካስቆጠረው ዕድሜና ከመጣበት የታሪክ ሂደት አኳያ በአደረጃጀት ተገቢ በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል ማለት ስህተት ይሆናል። በየዘመኑ ግን ህያው የሕዝብ ድምፅ በመሆን የትውልድ ቅብብሎሽ አርማ ሆኖ አገልግሏል። እያገለገለም ነው።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=30665
b01ff77cac89bade19a4a87609aaeef2
b59dfc697e8e88156204e7b196042fb3
ኦሊምፒክን በተመለከተ አማራጭ እቅድ አልተቀመጠም
ስፖርት
በአስከፊው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ለአስራ ስድስት ወራት የተራዘመው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አሁንም ከአንድ ዓመት በላይ እየቀረው ከቫይረሱ ስጋት ነፃ መሆን አልቻለም። የቫይረሱ ስርጭት ከመሻሻል ይልቅ እየባሰበት መሄዱ ከአስራ ስድስት ወራት በኋላም የመቆሙ ነገር ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል። ይህም የቀጣዩን ዓመት ኦሊምፒክ ስጋት እንዲኖርበት ከማድረግ ባሻገር በርካታ ጥያቄዎች እንዲነሱ ሆኗል። በተለይም ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከዚሁ ስጋት ጋር በተያያዘ ኦሊምፒኩን ዳግም የማራዘም ወይም ሌላ አማራጭ እቅድ መያዙን በርካቶች እየጠየቁ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የኦሊምፒኩ ቃል አቀባይ ማሳ ታካያ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ውድድሩን በቀጣዩ ዓመት ከማካሄድ ውጪ ሌላ አማራጭ እንዳላስቀመጠ ከጃፓን ጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው መግለጫ ጠቁመዋል። ‹‹ኦሊምፒኩ በተራዘመበት ወቅት እንዲካሄድ እየሰራን ነው፣ በዚህ መሰረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፣ አሁን ላይ መናገር የምችለው ይህን ብቻ ነው›› በማለትም ቃል አቀባዩ ኦሊምፒኩን ዳግም የማራዘምም ይሁን የመሰረዝ ሃሳብ እንደሌለ አስረድተዋል። ቃል አቀባዩ በጀርመኑ እለታዊ ጋዜጣ ዳይ ዌልት ኦሊምፒኩ የመሰረዝ ወይም የመራዘም እድል እንዳለው ተጠይቀው በቀጥታ ምላሽ አልሰጡም። ወዲያው ግን የኦሊምፒክ አዘጋጆቹና የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ኦሊምፒኩን የመሰረዝም ይሁን የማራዘም ምንም አይነት ሃሳብ እንደሌለ ለመገናኛ ብዙሃን ለመጠቆም ሞክረዋል። ከተራዘመው የጉዞና የሆቴል ጉዳይ፣ የስቴድየም መግቢያ ትኬቶችና በአጠቃላይ ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ሊገጥም የሚችለውን ኪሳራ በተመለከተ ጥያቄ ተነስቷል። ይህ ኪሳራ ከሁለት እስከ ስድስት ቢሊየን የጃፓን የን እንደሚሆን ግምቶች ቢሰጡም አሁንም ትልቁ ጥያቄ የኪሳራው መጠን ምን ያህል ነው? ማንስ ይከፍለዋል? የሚል ነው። የዓለም አቀፍ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ተቋማቸው በመቶ ሚሊየን ዶላሮች ሊከስር እንደሚችል የጠቆሙ ሲሆን ጃፓንም አዘጋጅ አገር እንደመሆኗ ሊገጥማት የሚችለው ኪሳራ በቀላሉ የሚታይ አይሆንም። ቶኪዮ ኦሊምፒኩን ለማስተናገድ አስራ ሁለት ቢሊየን የን ማውጣቷን ትናገራለች። ባለፈው ዓመት የታተመው የአገሪቱ መንግስት ኦዲተር ሪፖርት እንደሚያመለክተው ግን ወጪው በሁለት እጥፍም ሊልቅ ይችላል። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ግን አምስት ነጥብ ስድስት ቢሊየን የሚሆነው በግል ባለሃብቶች ወጪ የተደረገ ሲሆን ቀሪው በአገሪቱ መንግስት ነው። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩ ወደ 2021 እንዲዘዋወር ውሳኔ ላይ ከደረሰ ወዲህ በቫይረሱ ስጋት በአስተናጋጇ ጃፓን ቶኪዮን ጨምሮ በሰባት ከተሞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ከቀናት በፊት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም በኮሮና ቫይረስ በጃፓን ከስድስት ሺ በላይ ሕዝቦች ሲጠቁ ከመቶ በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ኦሊምፒኩ እስከሚካሄድ ገና አስራ ስድስት ወራት የቀሩት ቢሆንም የቫይረሱን ስርጭት በነዚህ ጊዜያት በቁጥጥር ስር ማዋል ካልተቻለ ኦሊምፒኩ አሁንም ከስጋት ውጪ ሊሆን እንደማይችል የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ መናገራቸው ይታወሳል። ‹‹በዚህ ወቅት ማንም በእርግጠኝነት ቫይረሱን በቁጥጥር ስር አውላለሁ የሚል እምነት የለውም፣ ስለዚህ የተራዘመው ኦሊምፒክ ከቫይረሱ ስጋት ነፃ ይሆናል ብለን ለመናገር ይቸግረናል›› በማለትም ሃሳባቸውን አጠናክረዋል። በቫይረሱ ስጋት ኦሊምፒኩን ከአንድ ዓመት በላይ ለማራዘም እንደተወሰነ ያስታወሱት ስራ አስፈፃሚው፣ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዚህ ወቅት ለተራዘመው ኦሊምፒክ ጠንክሮ ከመዘጋጀት ውጪ ሌላ ነገር ሊያደርግ እንደማይችል አስረድተዋል። ይሁን እንጂ የሰው ልጅ እስከዚያው ቫይረሱን በቁጥጥር ስር ያውላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል። የተራዘመው ኦሊምፒክ ዘንድሮ ሊካሄድ በታቀደበት ተመሳሳይ ወቅት እንዲካሄድ ከመወሰኑ ውጪ በየትኛው ቀን እንደሚካሄድ ቁርጥ ያለ ቀን አልተቀመጠለትም። ይህንንም ለመወሰን ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተለየ አማራጭ እስካሁን እንዳልተመለከተ አስረድተዋል። ከዚህ ይልቅ ኦሊምፒኩን ቀጣይ ዓመት ላይ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ የሚቻልበትን አማራጭ ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ በቀጣዮቹ አስራ አምስት ወራት በቁጥጥር ስር እስካልዋለ ኦሊምፒኩ ቢካሄድም የደበዘዘ እንደሚሆን ከወዲሁ ግምታቸውን የሚያስቀምጡ ተበራክተዋል። በተለይም ውድድሮች በሚካሄዱባቸው ስቴድየሞች የሚታደሙ ተመልካቾች ጉዳይ በታላቁና ደማቁ የስፖርት መድረክ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንዳይጨምር ያሰጋል። ለበርካታ ወራት በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት የዓለም ሕዝቦች ራሳቸውን ለመጠበቅ የፊት ጭምብል የማድረግና ማህበራዊ ርቀትን የመጠበቅ ልም ምድ ውስጥ ገብተዋል። ታላቁን የስፖርት መድረክ በስቴ ድየም ተገኝቶ መመልከት የሚቻልበት እድል ቢኖር እንኳን ደጋፊዎች ከዚህ ረጅም ልማድ ሳይወጡ ውድድሮችን ለመመልከት እንደሚገደዱ ይጠበቃል። ይህም በስቴድየም ወንበሮች ተራርቆ ከመቀመጥ ጋር ተያይዞ የተመልካቾች ቁጥር በእጅጉ እንደሚቀንስ ይታመናል። ይህም በኪሳራ ላይ የሚገኙትን የውድድሩ አዘጋጆች ከትኬት ሽያጭ ጋር በተያያዘ ለሌላ ኪሳራ እንደሚዳርጋቸው ያሰጋል። ከደጋፊዎች ጋር በተያያዘ እንደቀድሞው የአገራቸውን ሰንደቅ አላማ አንግበው በስቴድየም በአንድ ላይ ተሰብስበው ማየት ብርቅ ሊሆን ይችላል። ደጋፊዎች የአገራቸው አትሌቶች ሲያሸንፉ እንደተለመደው በደስታ ተቃቅፈው የሚያነቡበት፣ አብረው ፎቶ ግራፍ የሚነሱበትና በጋራ ተሰብስበው ደስታቸውን የሚገልፁበት አጋጣሚ ብርቅ ሊሆን ይችላል። ይህ በአንድ አገር አትሌቶች መካከልም ይሁን በተለያዩ አገራት አትሌቶች መካከል የተለመደ የመጨባበጥ፣ ተቀራርቦ የመደናነቅና ‹‹ተቃቅፎ እንኳን ደስ ያለህ›› የመባባል የስፖርታዊ ጨዋነት መገለጫዎች ቅንጦት እንዳይሆኑም ያሰጋል። ይህ ሁሉ ስጋትና እንቅፋት የተደገነበት የቶኪዮ ኦሊምፒክን በተመለከተ በተራዘመበት ጊዜ ከማካሄድ ውጪ አዘጋጆቹ ሌላ አማራጭ እቅድ እስኪያጡ ድረስ ተጨንቀዋል። ይህም የዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ያህል ትልቅ ተቋም ከወዲሁ የሰላ ትችት እንዲሰነዘርበት እያደረገ ይገኛል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 12 /2012
https://www.press.et/Ama/?p=30712
fd03ba4834cc67e8f982fc141e737229
8e56a815cdee7aabfdbd7ad0612069df
የአውሮፓ እግር ኳስና ኮሮና ቫይረስ
ስፖርት
በአሁኑ ሰዓት ተቋርጦ የሚገኘው የአውሮፓ እግር ኳስ ከዚህ በኋላ በዝግ ስታዲየሞች እንዲደሚካሄድ ግልጽ ቢሆንም መቼ የሚለው ጥያቄ ግን ምላሽ እንዳላገኘ በአውሮፓ የሚገኙ ሊጎችን የሚወክለው ማህበር አስታወቀ። የማህበሩ ምክትል ኃላፊ አልቤርቶ ኮሎምቦ እንዳሉት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተቋረጠው የአውሮፓ ሊግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቷል። «አብዛኛዎቹ የማህበሩ አባል ሊጎች በተለይም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች እንዲጀመሩ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። ነገር ግን እንደ ቤልጂየም ያሉ ጥቂት አገራት ከነጭራሹ የዘንድሮው ውድድር እንዲሰረዝ ሀሳብ አቅርበዋል» ብለዋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዓርብ ዕለት የወደፊት እርምጃዎችን በተመለከተ ስብሰባ እንደሚያደርግ የሚጠበቅ ሲሆን ዘጠኝ ጨዋታዎች የሚቀሩት ሊግ መቼ ይቀጥል? የሚለው ዋና ርዕስ እንደሚሆን ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት አንዳንድ የጀርመን ክለቦች ወደ ስልጠና መመለሳቸውን ተከትሎ እግር ኳስ ማህበራትና የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በተስፋ ተሞልተው ነበር። አልቤርቶ ኮሎምቦ ግን ዋናው ትኩረታችን መሆን ያለበት ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ ጨዋታዎቹን እንዴት ማስቀጠል አለብን የሚለው ላይ ነው፤ ከዛ በፊት ያሉት ወራት ላይ ጨዋታዎችን ማካሄድ የማይታሰብ ሊሆን ይችላል ብለዋል። «በመጀመሪያ የተጫዋቾች ስልጠና መጀመር አለባቸው። በመቀጠል የጨዋታዎቹ አዘጋጆች የደህንነት ማረጋገጫ ስራዎችን ይሰራሉ። ጨዋታዎቹ በዝግ ስታዲየሞች መከናወናቸው የማይቀር ነገር ነው። እኛ ሀሳብ እናቀርባለን እንጂ የመጨረሻው ውሳኔ ያለው የአገራቱ መንግስት ላይ ነው። የተጣሉት እገዳዎች እንደተነሱ ጨዋታዎችን ከከፍተኛ ጥንቃቄ ጋር በዝግ ስታዲየም እናከናውናለን» ሲሉ ተናግረዋል። የጣልያን እግር ኳስ ፌደሬሽን እግር ኳስ ተጫዋቾች ሌላው ቢቀር ልምምዳቸውን መስራት እንዲጀምሩ በማሰብ ከመጪው ግንቦት ወር ጀምሮ ተጫዋቾቹ ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርምራ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በበኩሉ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተከሰተውን የሊጎችና ውድድሮች መቋረጥን በተመለከተ በሚቀጥለው ሳምንት ስብሰባ ያደርጋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 9/2012
https://www.press.et/Ama/?p=30623
e7dda6658291e3196108f7035175a384
c7490cbc30ca4cde47f18370fb5ddfa6
የተወዳጁ ስፖርት በመሰናክል የተዋጀው መንገድ
ስፖርት
በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ከሚዘወተሩ የስፖርት አይነቶቸ በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል ። በተለያዩ አገራት ከፍተኛ ተቀባይነትን ማግኘት የቻለው የዳርት ስፖርት መነሻው ጥንታዊቷ ግሪክ እንደሆነች የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ። በግሪክ ወታደራዊ ተቋማት ውስጥ የዳርት ስፖርት በተለየ ሁኔታ ይዘወተር ነበር። በአጭር ጊዜም በአገሪቱ የሚኖረው ሌላው ማህበረሰብ አውቆት በስፋት ወደ ማዘውተር መሸጋገሩ ይነገራል፤ የዳርት ስፖርት፡ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በስፋት ወደ መዘውተር ሊሸጋገር የቻለውም በዚህ ሂደት ውስጥ አልፎ ነው። ዳርት አካልንና አዕምሮን የሚያነቃቃ ባህሪ የተላበሰ ስፖርት ሲሆን፤ የማሰብ ችሎታን የማሳደግ አቅም ያለው መሆኑ ስፖርቱን ተወዳጅ እንዲሆን አድርጎታል። ስፖርቱ መነሻውን ግሪክ ያድርግ እንጂ በአሁኑ ወቅት አድማሱን በማስፋት በተለያዩ አገራት በመዘውተር ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ ስፖርቱ መዳረሻውን ካደረገባቸው አገራት መካከል አንዷ ናት። ስፖርቱ በአገሪቱ መዘውተር ከጀመረ ረጅም ጊዜ እንዳስቆጠረም መረጃዎች ያመላክታሉ። የስፖርቱ መዘውተር የጀመረበት ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም በሚፈለገው የዕድገት ደረጃ ላይ እንደማይገኝ ይስተዋላል። ስፖርቱ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት፣ የዘርና ቀለም ልዩነት ሣይገድበው ማንኛውም ሰው አካሉንና አዕምሮውን ለማዳበር፤ ጤናውን ለመጠበቅ፣ በመስኩም ተወዳዳሪ ለመሆን የሚሳተፍበት ስፖርት ቢሆንም፤ በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች እየተዝወተረ እንደማይገኝ ለስፖርቱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ወቀሳ ሲሰነዝሩ ይስተዋላል። ለዳርት ስፖርት እንደሌሎች የስፖርት አይነቶች ትኩረት አለመሰጠቱም ምክንያት ተደርጎ ይነሳል። የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን ጽፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን አላምረው፤ ስፖርቱ በሚፈለገው ደረጃ እንዳያድግ ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህም ስፖርቱን በብዙ መልኩ ጎድቶታል። የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን የዓለም አቀፍ ዳርት ፌዴሬሽን (WDF) አባል መሆኑን ተከትሎ እ.ኤ.አ በ2017 በጃፓን በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ኢትዮጵያ የመሳተፍ ዕድሉን አግኝታ ነበር። ለአገራችን የዳርት ስፖርት ይህ አጋጣሚ ትልቅ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ ባለበት የበጀት ውስንነት ምክንያት ብሔራዊ ቡድኑን በዚህ መድረክ ላይ ለማሳተፍ ሳይቻል መቅረቱን እንደ ማሳያ ያስቀምጣሉ። በአገሪቱ የዳርት ስፖርት በሚፈለገው ደረጃ እንዳይጓዝ የተለያዩ ፈተናዎች እንቅፋት ቢሆኑበትም፤ ፌዴሬሽኑ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሠራ መሆኑን አቶ ጥላሁን ያነሳሉ። ስፖርቱን ከማስተዋወቅ፣ ከማስፋፋት አኳያ በርካታ ሥራዎችን በተለየ መልኩ በማከናወን ውጤታማ መሆንም እንደሚቻልም ይጠቁማሉ። ለዚህም በአገር አቀፍ ደረጃ የውድድር መድረኮችን እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አማራጭ ተደርጎ እንደተወሰደም ያመለክታሉ። ለአብነትም በኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን አማካኝነት የሚዘጋጀው አገር አቀፍ የዳርት ቻምፒዮና ስፖርቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ተወዳጅና ተዘውታሪ እንዲሆን ባለፉት ዓመታት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በአገር አቀፍ ደረጃ፣ ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የሚሳተፉበት ዓመታዊ የዳርት ቻምፒዮና ስፖርቱን ከማስተዋወቅ፣ ተወዳጅና ተዘወታሪ ከማድረግ ባሻገር ታዋቂ ስፖርተኞችን ከማፍራት አኳያ አበረታች ውጤትም ማግኘት መቻሉን አብራርተዋል። የውድድር መድረኩ ለስፖርቱ ውጤታማነት ያለውን አስተዋጽኦ ለመጨመር በዘንድሮው ዓመትም ቻምፒዮናው የሚቀጥል ይሆናል። የኢትዮጵያ ዳርት ቻምፒዮና ለ14ኛ ጊዜ በመጪው ሰኔ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ለማካሄድ ዝግጅት ሲደረግ የቆየ ሲሆን፤ በዓለም ዓቀፍ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ሻምፒዮናው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ነው ያመላከቱት። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የስፖርቱን እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንዲህ አይነት ውድድሮችን በማዘጋጀት የሚወሰን አለመሆኑን ያነሳሉ። በማንኛውም ደረጃ የሚካሄዱ የዳርት ውድድሮች፣ ግጥሚያዎችና ጨዋታዎች ወጥ በሆነ መንገድ የሚመሩት ሥራዓቶችን በማበጀት እየተሰራ ይገኛል። ስፖርቱን ትክክለኛውን መስመር እንዲይዝ የሚያደርገውን ማንዋሉ በዘርፉ ባለሙያዎች በተዘጋጀና ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን ባካተተ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑ ውጤቱ የተሻለ እንዲሆን ያደርገዋል ሲሉ አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ ስፖርቱ ተወዳጅ ቢሆንም፤ እየተኬደበት ያለው መንገድ መሰናክል የበዛበት መሆኑን በመጨረሻ ያነሱት፤ ኃላፊው፤ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑም በቀጣይ የውድድር አማራጮችን መፍጠር ያስፈልጋል። በመሆኑም የዳርት ስፖርትን የበለጠ ተወዳጅና ተዘውታሪ ከማድረግ፣ ከማዘመን፣ ስፖርታዊ ጨዋነትን ከማስፈን፣ የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን ከማቀላጠፍ፣ በክልል ፌዴሬሽኖች፣ ማህበራትና ሌሎች ክበባት መካከል የጋራ ግንዛቤን ከማዳበር አንፃር ሰፊ ሥራዎቸን ለመሥራት ዕቅድ መያዙን አስታውቀዋል። የዓለምን ህዝብ ሥጋት ውስጥ የከተተው የኮሮና ቫይረስን በመቆጣጠር በሀገራችን መደበኛ እንቅስቃሴ መጀመር ሲቻል ፌዴሬሽኑ እነዚህና መሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ በማስገንዘብ ሐሳበቸውን ቋጭተዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=30805
88c6524c7dfabb9118ba2b29e71287da
7c62f1e6db6c324efffae8cba53943df
ኢትዮጵያዊቷ የ5 ሺህ ሜትር ሯጯ አትሌት መሰረት ደፋር
ስፖርት
በመንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል እያደረገ ለሚገኘው ርብርብ እንዲጠቀምበት ህንፃዋን በጊዜያዊነት አበረከተች። አትሌቷ ህንፃውን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም፣ በኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲቲዩት እንዲሁም የጤና ተቋማት ዝግጁነት እና ለይቶ ማቆያ ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኢሳያስ አገኘሁ ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ሹማምንቶች በተገኙበት አስረክባለች። አትሌት መሰረት ደፋር በወቅቱ እንደተናገረችው፤ ከዚህ ህብረተሰብ መሐል የተገኘሁ ሰው ነኝ። እኔም ሆንኩ የኢትዮጵያ ህዝብ ጤና ስንሆን ነው ሁላችንም አብረን በሰላም ሰርተን የምንኖረው። ይህን ህንፃ እኔ እና ባለቤቴ ቴዲ እንገንባው እንጂ የኛ ብቻ አይደለም። ከኛ ጋር በሃሳቡ አብሮ የሮጠ የጤና ችግር ሲገጥመኝ አብሮ የታመመ የተጨነቀልኝ፤ በስፖርቱ ዓለም ለነበረኝ ያማረ ጉዞ በሙሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ከጎኔ ሆኖ ሁሉን የተካፈለኝ የሀገሬ፣ የወገኔ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ህንፃ ነው ብላለች። ህንፃው አገሬንና ወገኔን በእንዲህ አስቸጋሪውን ጊዜ ካላገለገለና ካልጠቀመ ዋጋ እንዳለው የሚቆጠር አለመሆኑን ገልፃለች አያደርግም። በመሆኑም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ በሚገኘው ተግባር እንዲውል ህንፃውን በጊዜያዊነት ማስረከቧን ተናገራለች። እኛ ኢትዮጵያኖች ደግሞ አኗኗራችን በመረዳዳት፣ በመደጋገፍ፣ አብሮ በመኖርና በመብላት፣ የተሳሰር ነው። በሽታው «ደግሞ እነዚህን የማይወድ ክፉ በመሆኑ እኛም የገጠመን እባካችሁ አብሮ የመኖር አብሮ ሁሉን የመጋራት ልምዳቸንን ገታ በማድረግ ከመንግሥት ጤና ተቋማት የሚሰጡንን መመሪያዎች በመተግበር አስቸጋሪውን፣ ክፉ ጊዜ መሻገር አለብን »ብላለቸ። የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አበቤ በበኩላቸው፤ በእውነት መሰረት እና ባለቤቷ አቶ ቴድሮስ ህንፃው ገና ሥራ ሳይጀምር ለእንዲህ አይነት የተቀደሰ አላማ እንዲውል መስጠታቸው የሚደነቅ ተግባር ነው። ለንግድ ሥራ ተገንብቶ ሥራውን “ሀ” ብሎ ሲጀምር ለበጎ ሥራ የዋለ ወይም በበጎ ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የአትሌት ህንፃ ይመስለኛል። ይህን ማድረግ መቻል ደግሞ ትልቅ መባረክና ለሌሎችም አርአያ ጭምር መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ። በማህበሩ አባላት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይውል ዘንድ ከፕሪምየር ሊግ እና ከከፍተኛ ሊግ ቡድን ተጨዋቾች ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ዕርዳታ ከትናነት በስቲያ ለድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አስረክበዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የመስተዳድሩ እና የስፖርት ኮሚሽን ከፍተኛ ሃላፊዎች እንደዚሁም ደግሞ የየክለቡ ካፒቴኖች እና የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች አመራሮች በአዲስ አበባ ስታድየም በተገኙበት በእዚህ የገንዘብ ርክክብ ፕሮግራም ላይ ማህበሩ ይሄን ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል መርህ ኮረና ቫይረስን መነሻ አድርጎ ለሰራው ሥራ ከመስተዳደሩ ከስፖርት ኮሚሽንና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል። የመልካም ቤተሰብ – ተምሳሌት በስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን እና በስዊዝ ዋናው ሱፕር ሊግ ስኬታማ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ተጫዋቾች ሲነሳ በጥሩ ምሳሌነት ማረን ሃይለሥላሴ እና ቅዱስ ሃይለሥላሴ ይጠቀሳሉ። ታዳጊዎቹ ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ በቋሚነት ለሚረዱት የከለላ እግርኳስ ክለብ ታዳጊዎች እና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ኑሮ ለከበዳቸው የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አድርገዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2012ዳንኤል ዘነበኢትዮጵያዊቷ የ5 ሺህ ሜትር ሯጯ አትሌት መሰረት ደፋር በመንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል እያደረገ ለሚገኘው ርብርብ እንዲጠቀምበት ህንፃዋን በጊዜያዊነት አበረከተች። አትሌቷ ህንፃውን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም፣ በኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲቲዩት እንዲሁም የጤና ተቋማት ዝግጁነት እና ለይቶ ማቆያ ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኢሳያስ አገኘሁ ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ሹማምንቶች በተገኙበት አስረክባለች። አትሌት መሰረት ደፋር በወቅቱ እንደተናገረችው፤ ከዚህ ህብረተሰብ መሐል የተገኘሁ ሰው ነኝ። እኔም ሆንኩ የኢትዮጵያ ህዝብ ጤና ስንሆን ነው ሁላችንም አብረን በሰላም ሰርተን የምንኖረው። ይህን ህንፃ እኔ እና ባለቤቴ ቴዲ እንገንባው እንጂ የኛ ብቻ አይደለም። ከኛ ጋር በሃሳቡ አብሮ የሮጠ የጤና ችግር ሲገጥመኝ አብሮ የታመመ የተጨነቀልኝ፤ በስፖርቱ ዓለም ለነበረኝ ያማረ ጉዞ በሙሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ከጎኔ ሆኖ ሁሉን የተካፈለኝ የሀገሬ፣ የወገኔ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ህንፃ ነው ብላለች። ህንፃው አገሬንና ወገኔን በእንዲህ አስቸጋሪውን ጊዜ ካላገለገለና ካልጠቀመ ዋጋ እንዳለው የሚቆጠር አለመሆኑን ገልፃለች አያደርግም። በመሆኑም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ በሚገኘው ተግባር እንዲውል ህንፃውን በጊዜያዊነት ማስረከቧን ተናገራለች። እኛ ኢትዮጵያኖች ደግሞ አኗኗራችን በመረዳዳት፣ በመደጋገፍ፣ አብሮ በመኖርና በመብላት፣ የተሳሰር ነው። በሽታው «ደግሞ እነዚህን የማይወድ ክፉ በመሆኑ እኛም የገጠመን እባካችሁ አብሮ የመኖር አብሮ ሁሉን የመጋራት ልምዳቸንን ገታ በማድረግ ከመንግሥት ጤና ተቋማት የሚሰጡንን መመሪያዎች በመተግበር አስቸጋሪውን፣ ክፉ ጊዜ መሻገር አለብን »ብላለቸ። የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አበቤ በበኩላቸው፤ በእውነት መሰረት እና ባለቤቷ አቶ ቴድሮስ ህንፃው ገና ሥራ ሳይጀምር ለእንዲህ አይነት የተቀደሰ አላማ እንዲውል መስጠታቸው የሚደነቅ ተግባር ነው። ለንግድ ሥራ ተገንብቶ ሥራውን “ሀ” ብሎ ሲጀምር ለበጎ ሥራ የዋለ ወይም በበጎ ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የአትሌት ህንፃ ይመስለኛል። ይህን ማድረግ መቻል ደግሞ ትልቅ መባረክና ለሌሎችም አርአያ ጭምር መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ። በማህበሩ አባላት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይውል ዘንድ ከፕሪምየር ሊግ እና ከከፍተኛ ሊግ ቡድን ተጨዋቾች ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ዕርዳታ ከትናነት በስቲያ ለድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አስረክበዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የመስተዳድሩ እና የስፖርት ኮሚሽን ከፍተኛ ሃላፊዎች እንደዚሁም ደግሞ የየክለቡ ካፒቴኖች እና የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች አመራሮች በአዲስ አበባ ስታድየም በተገኙበት በእዚህ የገንዘብ ርክክብ ፕሮግራም ላይ ማህበሩ ይሄን ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል መርህ ኮረና ቫይረስን መነሻ አድርጎ ለሰራው ሥራ ከመስተዳደሩ ከስፖርት ኮሚሽንና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል። የመልካም ቤተሰብ – ተምሳሌት በስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን እና በስዊዝ ዋናው ሱፕር ሊግ ስኬታማ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ተጫዋቾች ሲነሳ በጥሩ ምሳሌነት ማረን ሃይለሥላሴ እና ቅዱስ ሃይለሥላሴ ይጠቀሳሉ። ታዳጊዎቹ ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ በቋሚነት ለሚረዱት የከለላ እግርኳስ ክለብ ታዳጊዎች እና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ኑሮ ለከበዳቸው የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አድርገዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2012
https://www.press.et/Ama/?p=30808
312f6330d11b67565093840c5afa2a91
c7440b35c4d40c37250e289c6ca75e58
ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ቫይረስን ከመዋጋት አኳያ
ስፖርት
ዓለምን በአንድነት እያስጨነቀ የሚገኘው ወቅታዊ ጉዳይ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ መሆኑ ይታወቃል። ታዲያ በዚህ ቫይረስ ላለመጠቃት አሊያም በቶሎ ለማገገም ከሚረዱ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋነኛው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ነው። በየዕለቱ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር አዕምሮን ከጭንቀት ነፃ ከማድረጉም በላይ አካላዊ ጤንነትን ለመጠበቅና በሽታ የመቋቋም አቅምን ለመገንባት እንዲሁም በቶሎ ከጉዳት ለማገገም ያለው ጠቀሜታ በቁጥር የሚተመን አይደለም። ይህንንም ጥናቶችና የዘርፉ ባለሙያዎች ይስማሙበታል። ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ትምህርት ቤቱ በኩል በሚያዘጋጀው ህትመት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መደረግ ካለባቸው ነገሮች መካከል አንዱ በሽታን የመከላከል አቅምን ማጎልበት መሆኑን ይጠቁማል። ሰውነት በሽታን የመከላከል አቅሙን እንዲያሳድግ ከሚያደርጉ ዋነኛ መንገዶች አንዱ ደግሞ አካላዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር ነው። የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በመደበኛነት ማካሄድ ከልብ፣ ከደም ግፊት፣ ከሰውነት ክብደት መጨመር እንዲሁም በርካታ በሽታዎች ሊከላከል ይችላል። በተፈጥሯዊ መንገድ በሽታ የመከላከል ችሎታን የመጨመርና በጤናማ ሁኔታ እንዲቆይ ያስችላል፤ በመሆኑም እንደ ወቅታዊው ወረርሽኝ ላሉ በሽታዎች መፍትሔ መሆኑን ይመክራል ጽሑፉ። በየቀኑ ለግማሽ ሰዓት ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማካሄድ በቫይረስ ከሚመጡና ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች የሚታደግ መሆኑን የሚያረጋግጡት ደግሞ የጥናትና ምርምር ዩኒቨርሲቲ በሆነው (UIUC) ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጄፍሪ ዉድስ ናቸው። ተመራማሪው የስፖርትና ጤና ሳይንስ ከሆነ ጆርናል ጋር ባደረጉት ቆይታ እአአ በ2000 ያደረጉትን ጥናት ዋቢ በማድረግ አካላዊ እንቅስቃሴ በሽታ የመከላከል አቅምን እንደሚያሳድግ በእንስሳት ላይ ማረጋገጣቸውን ያስረዳሉ። በኮሮና ቫይረስ ላይ እስከአሁን የተረጋገጠ ጥናት ባለመኖሩና አዲስ እንደመሆኑ እርግጥ የሆነ ነገር መናገር ባይቻልም፤ አካላዊ እንቅስቃሴን በጥንቃቄና የጤና ባለሙያዎች የሚመክሯቸውን የመከላከያ መንገዶች እየተገበሩ መሥራት ግን እጅግ ጠቃሚ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ዢን ያን በበኩላቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ በሳንባ ውስጥ የሚከሰቱ ህመሞችን አስቀድሞ መከላከልና መቀነስ እንደሚያስችል በጥናት መረጋገጡን ያስረዳሉ። እያንዳንዷ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የበሽታ መከላከል አቅምን በማሳደግ በኮሮና ቫይረስ መጠቃትን ለመቀነስ የሚችልበት ሚና እንዳለው በቁጥራዊ መረጃ አስደግፈው ለኒውሮ ሳይንስ ድረገጽ ገልጸዋል። ስፖርት ከበሽታ የመከላከል አቅምን ከመፍጠሩ ጎን ለጎን ‹‹በቤት ቆዩ›› ለሚለው መመሪያም ደጋፊ ሊሆን የሚችል ቁልፍ ጉዳይ ነው። ይኸውም አብዛኛው ሰው ከቤቱ ሳይወጣ እንዲሁም ከአካባቢው ሳይርቅ እንዲቆይ የሚያደርገው የእንቅስቃሴ ገደብ ስነ-ልቦናዊና አካላዊ ተጽእኖ ማድረሱ አይቀሬ ነው። ታዲያ በዚህ ሁኔታ አካላዊ ክብደት ከመጨመር ባሻገር ጭንቀትን ተከትሎ የሚከሰቱና ድምፅ አልባ ለሆኑ በሽታዎች አጋላጭ ነው። በመሆኑም ስፖርተኞች ብቻም ሳይሆኑ ማንኛውም ሰው በቤቱም ሆነ ባለበት ስፍራ በተቻለው አቅም ሰውነትን ማንቀሳቀስና ማፍታታት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም በሌሎች ዓለማት ባለሙያዎችና ተቋማት በስፋት በቤት ውስጥ መሠራት የሚችሉ የእንቅስቃሴ ዓይነቶችን ያፈራሉ። ዘርፈ ብዙ የሆነውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጠቀሜታ ከግንዛቤ ያስገቡ አካላት በኢትዮጵያም እየሠሩ ይገኛሉ። በእርግጥ እንቅስቃሴው በጅማሬ ላይ ያለ ቢሆንም፤ አበረታች ነገር ግን ስፖርታዊ ማህበራትና ሌሎች አካላትን ጨምሮ የበርካቶች ኃላፊነት እንደመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቋሚ ነው። በህዝባዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ረገድ ፈርቀዳጅ በመሆን የሚጠቀሰው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን በዚህ ወቅትም አበተታች ሥራ እያከናወነ ነው። ኮሚሽኑ በተለይ በጋራ መኖሪያ አካባቢ በመገኘት በባለሙያዎቹ አማካኝነት አካላዊ እንቅስቃሴ አካሂዷል። ነዋሪውም በእንቅስቃሴው ተካፋይ ከመሆኑ ባለፈ በቀጣይም በምን መልኩ ከቤቱ ሳይወጣ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ግንዛቤ ያገኘበት ነው። ሌላው ኢትዮጵያን ለዘመናት እያስጠራ ከዚህ የደረሰው የአትሌቲክስ ስፖርት ነው። ፌዴሬሽኑ በሃገሪቷ ከፍተኛ ሽፋን ባላቸውና ተደራሽም በሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ታግዞ በሺዎች ለሚቆጠሩ አትሌቶቹ በቤት ውስጥ ምን ማከናወን እንደሚገባ እያስገነዘበ ይገኛል። ይህም ጠቃሚ መልዕክቶችንና ሳይንሳዊ ትንታኔዎችን ያቀፈ በመሆኑ ከአትሌቶች ባሻገር ህዝቡም ጠቃሚ መረጃ ሊያገኝበት ያስችላል። በአፍሪካ ቀዳሚና በዓለምም ስመ ጥር ከሆኑ የጎዳና ላይ ሩጫዎች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም በተመሳሳይ በዚህ ወቅትም ህዝቡ ከስፖርት መራቅ እንደሌለበት ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ በዩቲዩብ ገጹ መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት ለግማሽ ሰዓት የሚቆይ እንቅስቃሴ በምን መልኩ እንደሚካሄድ በባለሙያዎች እያሳየ ይገኛል። ይህ ይበል የሚያሰኝ ሥራም ከስፖርታዊ አካላት ባለፈ ሁሉም ተሳታፊ ሊሆንበት የሚገባ መሆኑን በማስገንዘብ በኩልም ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መከናወን ይኖርባቸዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 14/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=30882
9f8a8d2d2ea30d31d305651baf1b9735
6aefcf1f956bdd3db8e17f245d84e6db
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡ ስምንት ትምህርት ቤቶች ለርክክብ ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
 መሀመድ ሁሴንአዲስ አበባ፡- በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በመገንባት ላይ የሚገኙ ግንባታቸው ከዚህ ቀደም ተጠናቆ ለአገልግሎት ከበቁ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ። የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፋንታ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የሚያስገነባቸው የትምህርት ተቋማት ፕሮጀክቶች በአብዛኛው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው። ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጠናቀው ስራ ከጀመሩት በተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል። ግንባታቸው ተጠናቆ ርክክብ የሚፈጸምባቸው ትምህርት ቤቶች በአፋር ክልል ዱብቲ፣ በጋምቤላ አኝዋክ ዞን፣ በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ እና መተከል ዞን ፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ዞን 02 እና 06 ቀበሌዎች፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ከተማ እና ዋግኸምራ ዞን ሳህላ ሰለምት ወረዳ የተገነቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።ግንባታቸው ቀድመው የተጠናቀቁና ርክክባቸው ተፈጽሞ ስራ የጀመሩት አምስት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤ በአማራ ክልል ጎንደር ሎዛ ቀበሌ፣ ደቡብ ወሎ ጦሳ ፈላና ቀበሌ (አልብኮ ወረዳ)፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ጭቋላ ቀበለ (ቢሾፍቱ አካባቢ)፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞን ውጫሌ ወረዳ ጃቴ ቀበሌ (ሙከጡሪ አካባቢ) የሚገኙት መሆናቸውንና አሁን ላይ ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል። በተጨማሪም ግንባታቸው እስከ ታህሳስ 30/2013 ባለው ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁ አራት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ ትምህርት ቤቶቹም በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሸካ ዞን፣ ጌዲኦ ዞን፣ ደቡብ ኦሞ እና በኦሮሚያ ክልል ሐዊ ጉዲና ወረዳ ሐሮ ቢሊቃ ቀበሌም እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በአዲስ አበባ የተሰራው የሕጻናት ማሳደጊያ፣ በሰበታ ከተማ የሚገኘውን ማየት የተሳናቸው ትምህርት ቤት እና በተለያዩ ክልሎች የተገነቡትን ክፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገንብቶ ለማጠናቀቅ ጽህፈት ቤቱ እስካሁን 760 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉንአስታውቀዋል። ገንዘቡም ከተለያዩ የውጭ አገራት ረጂ ድርጅቶች የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ዓመትም 10 ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ተይዞ የአምስቱ የግንባታ ቦታ መለየቱን የጠቀሱት አቶ ሙሉቀን፤ የእነዚህ ፕሮጀክቶች ወጪ የሚሸፈነውም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከመደመር መጽሀፍ ሽያጭ ያገኙትንና ለጽህፈት ቤቱ ባበረከቱት ገንዘብ መሆኑን አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38455
b8de3d7acbf2cdd29da93cac53507882
2aa5575f8d5d40c720c48d572bcadc14
ህብረተሰቡ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በመጠቀም የጤና ባለሙያዎችን እንዲያግዝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቀረቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲስ አበባ ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ህብረተሰቡ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአግባቡ በመጠቀም የጤና ባለሙያዎችን እንዲያግዝ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።በአሁኑ ወቅት የጽኑ ሕሙማን ክፍል ያለውን ዐቅም ሁሉ አሟጦ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመው ፥ በዚህ ወቅት የጥንቃቄ እርምጃዎችን ቸል ማለት እንደማይገባም አሳስበዋል። ህብረተሰቡ የራሱን ሕይወት እንዲታደግ የሌሎችንም ሕይወት እንዲያተርፍም ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38454
eb2df538fb0157813930823abbee19c9
877f90401cd7c14c35cd7c65fabf2ce4
ቂም በቀል በቁራዎች
መዝናኛ
ሰዎች በልዩ ልዩ ጉዳዮች በተለይ እነርሱ በማያምኑባቸው ምክንያቶች ቤተሰቦቻቸውን አልያም የቅርብ ወዳጆቻቸውን በሞት ሲነጠቁ በከባድ ኀዘን ውስጥ ይወድቃሉ። ዘመዳቸው ወይም የቅርብ ወዳጃቸው ሕይወቱ ሆን ተብሎ በግለሰብ እጅ ያለፈ ከሆነም አሟሟቱን በማሰብ በንዴት ይበግናሉ። በቂም በቀል ተነሳስተውም የገዳዩን ሕይወት እስከማጥፋትም ይደርሳሉ። በእኛም ሀገር ቀደም ሲል እንደነበረው አይብዛ እንጂ አሁንም ድረስ በተለይ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በዚህ መልኩ ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ የሟች ቤተሰቦች ደም ለመመለስ በሚል በቂም በቀል ተነሳስተው በገዳይ ቤተሰቦች ላይ እርምጃ ይወስዳሉ። ይህ ጉዳይ እንደባህል ተቆጥሮ ዛሬም አልፎ አልፎ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ገዳዩ ዘመድ እንኳን ባይኖረው ልጁን እስከመግደል የሚደረስበት ሁኔታም ይፈጠራል። ይህ የቂም በቀል ተግባር ታዲያ በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚታይና የተለመደ ቢሆንም፤ በእንስሳት በተለይም በአእዋፋት በኩል አለ ቢባል ግን ትንሽ ያስገርማል። ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ድረገፅ ከሰሞኑ ያወጣው መረጃም ልክ እንደሰው ሁሉ አእዋፍም በቂም በቀል ተነሳስተው ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ያሳያል። እንደዘገባው ከሆነ፤ ላለፉት ሦስት ዓመታት በሕንድ ማድሃያ ፕራዴሽ ግዛት ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ህልም የሚመስል ግን እውነተኛ ሕይወትን ከቁራዎች ጋር አሳልፏል። በቀን ሠራተኝነት የሚተዳደረውና ሱሜላ በተሰኘች መንደር ነዋሪው ሺቫ ኪዋት እርሱ ባልተረዳው መልኩ ከቁራዎቹ ጋር ያጋጠመው ችግር ከሦስት ዓመት በፊት እንደነበር ያስታውሳል። ከዕለታት በአንዱ ቀን በመንገድ ላይ ሲጓዝ አንዲት ቁራ በብረት መረብ ውስጥ ተጣብቃ ይመለክትና ወደ እርሷ ቀረብ ይላል። ይሁንና ቁራዋን ከተጣበቀችበት መረብ ውስጥ ለማላቀቅ ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካለት ቀርቶ ቁራዋ እጁ ላይ ትሞታለች። ይህ ሲሆን የተመለከቱት ሌሎች ቁራዎችም ምንአልባት የቁራዋን ሕይወት የቀጠፈው እርሱ ሳይሆን አይቀርም በሚል ሁሌም ቁራዋ በሞተችበት አካባቢ ሲያልፍ ጥቃት ያደርሱበታል። ጥቃታቸውንም አንዴ በቡድን ሌላ ጊዜ ደግሞ በተናጠል ያካሂዱበታል። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም ኪዋት ከቁራዎቹ ሹል መንቁርና ስል ጥፍር ጥቃት ለመሸሽ ሁሌም ልምጭ ይዞ መንቀሳቀስ ይጀምራል። ኪዋት «ቁራዋ የሞተችው እጄ ላይ ነው፤ ቁራዎቹ ሃሳቤን መረዳት ቢችሉ ኖሮ ቁራዋን ልረዳት እንደነበር እገልፅላቸው ነበር» ሲል ለታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ገልጿል። «ራሴን ለመከላከል ልምጭ እጠቀማለሁ፤ ይመስለኛል ቁሯዋን የገደልኳት እኔ መስያቸዋለሁ» ሲልም ተደምጧል። ኪዋት እንደተናገረው፤ እርሱ ብቻ የጥቃቱ ኢላማ መሆኑንና ቁራዎቹ ከሌሎች ሰዎች ጋር ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለባቸው እስኪያውቅ ድረስ የቁራዎቹን ጥቃት በደንብ እንዳላጤነው ተናግሯል። ቁራዎቹ እርሱን ለማጥቃት በአናቱ ላይ ሲያንዣብቡ በእርሱ ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለመመልከት በርካታ ሰዎች በየቀኑ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ እስከመሰባሰብም ደርሰዋል። ብዙዎቹ በጉዳዩ የተገረሙ ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ ድርጊቱን «ድንገተኛና አስደንጋጭ» ሲሉ ገልፀውታል። ከኪዋት ጎረቤቶች ውስጥ አንዱ «ቁራዎቹ ኢላማቸውን እንዳዩ ልክ እንደ ተዋጊ ጄቶች ዝቅ ብለው በመብረር ጥቃቱን በኪዋት ላይ ያደርሳሉ» ሲል የቁራዎቹን ድንገተኛ ጥቃት ገልጿል። በባራካቱላህ ዩኒቨርሲቲ በወፎች ባህሪ ዙሪያ ጥናት ያካሄዱት ፕሮፌሰር አሾክ ኩማር በበኩላቸው፤ ቁራዎች የማስታወስ ችሎታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፤ በተለይ በእነርሱ ላይ ጉዳት ያስከተሉትን እንደማይዘነጉ ተናግረዋል። የበቀል ሃሳባቸው ልክ እንደሰዎች የተወሳሰበ ባይሆንም፤ በሚያስቆጣቸው ጉዳይ ላይ በቡድን ወይም በተናጠል የማጥቃት ባህርይ እንዳላቸውም ጠቁመዋል። በመሰረታዊነት ቂም የሚይዙ በመሆናቸው ኪዋት ያገጠመው ችግርም ይኸው መሆኑን አመልክተዋል።  አዲስ ዘመን  ጳጉሜን 5 /2011 አስናቀ ፀጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=17594
1ac54b635f36ba4c23854a44067e8ac8
dca1c624b5554a6d6d019edd8b3606d6
ቦርዱ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሶሎሞን በየነአዲስ አበባ:- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገለጸ።የቦርዱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ቦርዱ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ቀደም ሲል ከተካሄዱ ምርጫዎች በእጅጉ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ ይገኛል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ባለፉት ከተካሄዱ ምርጫዎች በእጅጉ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ቁሳቁሶች 90 በመቶ ተገዝተው መጠናቀቃቸውን ያመለከቱት ስራ አስኪያጇ፣ የተገዙት የምርጫ ቁሳቁሶቹና ህትመቶች ከዚህ በፊት ምርጫ ከተደረገባቸው ቁሳቁሶችና ህትመቶች በእጅጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ አስታውቀዋል።የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹና የመራጭ ካርዶቹ ደግመው መታተም የማይችሉ፣ ከተነካኩ የሚያስታውቁ፣ የራሳቸው የሆነ ቀሪ ያላቸው፣ ኮፒ ለመደረግ የሚያስቸግሩ እንዲሁም የድምጽ መስጫ ሳጥኖቹ አስተማማኝና መራጩ ድምጽ ሲሰጥ በነጻነት ለመስጠት የሚያስችል መከለያዎች ያሉት እንደሆነም ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ የተለያዩ ማጭበርበሮችን የሚያስቀሩ የምርጫ ቁሳቁሶች መዘጋጀታቸውንም አመልክተዋል። ምርጫውን በህጉ መሰረት ለማከናወን የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መጠበቂያ ፕሮሲጀር መዘጋጀቱን የጠቆሙት ወይዘሪት ሶሊያና ፤ ይህም ምርጫው በህጉ መሰረት ተከናውኗል አልተከናወነም ብሎ ለመለየት የሚቻልበት እድል እንዲኖር የሚያደርግና የድምጽ ቆጠራው የምርጫ ሂደቱን ተከትሎ መከናወን አለመከናወኑን ለመለየት እንደሚረዳም አስታውቀዋል። ቦርዱ ከዚህ ቀደም እንደነበረው አሰራር ለይስሙላ የተዋቀረ ሳይሆን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባላቸው፣ የትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ባልሆኑና ገለልተኛ በሆኑ የቦርድ አባላት እንደ አዲስ የተዋቀረ መሆኑን ጠቁመው ፤ ቦርዱ ሪፎርም ከተደረገ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ባለው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት በተቻለ መጠን ጠንካራና ፍትሃዊነት ያላቸውን ውሳኔዎችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። በውሳኔ አሰጣጡ በኩል የተአማኒነት ችግር ወይም ጥያቄ እንደሌለበት የጠቆሙት ወይዘሪት ሶሊያና፣ ቦርዱ ይሄንን ጠንካራ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ የሆነ የውሳኔ አሰጣጥ አቅሙን ይዞ ወደ ምርጫው እንደሚገባ አስታውቀዋል። ይህም ለምርጫው ተአማኒ መሆን የራሱን አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ተናግረዋል። ለምርጫው የተገዙ ቁሳቁሶችና ምርጫውን ለማካሄድ የተነደፉ የአሰራር ስርዓት በተቻለ መጠን ምርጫውን ተአማኒ እንደሚያደርጉት ወይዘሪት ሶሊያና ገልጸው፤ መጪው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ምርጫዎች ለየት የሚያደርገው ምርጫው የሚካሄደው በምርጫ ህጉ የነበሩ ማነቆዎች ተስተካክለውና የቦርድ አመራሩ አደረጃጀትም በአዲስ መልኩ ተዋቅሮ መሆኑን አመልክተዋል። ይህም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38456
524db682bbc78ef68c712ba44ad20234
85fabd60d2f0bc03b8aae8f9e4a84f37
“በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ ነው” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ በኢትዮ- ሱዳን ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህ ሳምንት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 328 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ መቻሉን ገለጹ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስወቁት ፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ በአሁኑ ወቅት ውጥረቱ ቀንሷል።ችግሩ እንዲፈጠር ያደረጉት ቀጠናው እንዳይረጋጋ የሚፈልጉ ኃይሎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የሱዳን የተወሰኑ ልሂቃኖችም ከእነዚህ ኃይሎች ጋር መወገናቸውን አመልክተዋል።“እነዚህ ኃይሎች በግልጽ የሚታወቁ ናቸው” ያሉት ቃል አቀባዩ፣ በትርምሱ የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸምና ጥቅማቸውን ለማስከበር ያለሙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።እነዚህ ኃይሎች ለሱዳን ህዝብም ሆነ ለቀጠናው ጠቃሚ አለመሆናቸውን መንግሥት በተለይ ለሱዳን ህዝብ መልዕክት የማስተላለፍ ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ጎን ለጎንም እነዚህን ኃይሎችን የማጋለጥ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ ችግሮቹን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች መቀጠላቸውን ገልጸዋል።በመግለጫቸው በትግራይ ክልል መረጋጋት መስፈኑንና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ጠቁመዋል ።አንዳንድ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ክልሉ ላይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በሃቀኝነት መዘገብ እንዳልቻሉ አስታውቀዋል።እነዚህ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጉዳዩን በሚመለከት እየተከተሉት ያለው አካሄድ ትክክል ባለመሆኑ ሊታረሙ እንደሚገባም ጠቁመዋል። የውጭ ኢንቨስትመንትን አስመልክቶም የእስራኤል፤ የህንድ፣ የዱባይ፣ የቻይናና የቱርክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አመራጮችን ለመጠቀም ፍላጎት መሳየታቸውን አመልክተዋል። “በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አማካኝነትም ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ውጭ አገራት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ናቸው” ብለዋል።በተለይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ሳምንት ብቻ 328 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ መቻሉን ገልጸዋል። ከእነዚህ ውስጥ 286ቱ ከሳዑዲ አረቢያ የተቀሩት ከሊባኖስ መመለሳቸውን ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38465
fc8b0678f5fba8360725682e416e1991
f808482971c9194089aaa4d0c11afee5
አስከፊውን ጊዜ በብልሃት የማለፍ ጅምር
ስፖርት
የዓለም ሕዝብ ሁሉ ጭንቀትና ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ ከሀብታም እስከ ድሃ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዋነኛ ትኩረቱ እንዲሆን ካስገደደ ሰንብቷል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት እንደ ሰደድ እሳት ያላዳረሰው የዓለም ክፍል የለም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዓለም ሕዝቦች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ከቫይረሱ ቢያገግሙም የሟቾች ቁጥር ይህ ነው በማይባል ፍጥነት እየጨመረ ይሄዳል:: ከሁሉም በላይ በቫይረሱ ስጋት በየቤቱ የከተመው የዓለም ሕዝብ ጭንቀትና ድብርት ውስጥ እንዲገባ ማስገደዱ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እየሆነ ይገኛል፡፡ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የዓለምን ሕዝብ ያጠቃው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያልገባበበት ቤት፣ ያላንኳኳው በር የለም፡፡ ከዓለም ታላላቅ አገራት መሪዎች እስከ ተራው ሕዝብ፣ ከዝነኛ ሰዎች እስከ ሕፃናትና አዛውንት ድረስ የዚህ አስከፊ ወረርሽኝ ተጠቂ ሆነዋል፡፡ ቫይረሱን ለመቋቋም በሽታን የመመከት ከፍተኛ አቅም ያላቸው የስፖርቱ ዓለም ሰዎች ሳይቀሩ በዚህ ወረርሽኝ ተለክፈዋል፣ ሕይወታቸውን ያጡም ጥቂት አይደሉም፡፡ የስፖርት ቤተሰቡ በቫይረሱ ስርጭት ስጋት የዓለም ታላላቅ የስፖርት መድረኮች ተቆልፈውበት ሁነኛ የመዝናኛ አማራጩን አጥቶ በየቤቱ ቆዝሟል፡፡ የስፖርቱዓለም ታላላቅ ከዋክብትም ረብጣ ገንዘብና ዝናቸው ከደጃፋቸው እንዲወጡ አቅም አልሆናቸውም፡፡ ይሄ ክፉ ጊዜ እስኪያልፍ ሁሉም በየቤቱ እንዲቆይ ማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተሻለ አማራጭ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅትና መንግሥታት በየጊዜው ሲወተውቱ ይታያሉ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ኢኮኖሚያቸው ዝቅተኛ የሆኑ አገራት ዜጎች የተሻለ የመዝናኛ አማራጭና በየቤቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚቸገሩ መሆናቸው ከጭንቀትና ድብርት ጋር ተያይዞ ለሚመጣው ቀውስ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ አስቸጋሪ ጊዜ እስኪያልፍ ከስፖርቱ አኳያ ማህበረሰቡ በያለበት ሆኖ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርግ መላ መዘየድ እንደሚያስፈልግ ግልፅ ነው፡፡ ለዚህም የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ትናንት የወሰደው ርምጃ አንድ ምሳሌ ይሆናል፡፡ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግቢ እና በረንዳዎች ላይ ርቀትን በመጠበቅ ቀለል ያሉ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመስራት ኅብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ እራሱን እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡ በአዲስ አበባ ከተማ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉ በረንዳ ላይ ቀለል ያሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማካሄድም ግንዛቤ ፈጥሯል:: በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሳቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች ዝግ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከፊት ኮርነር ስፖርት ጋር በመቀናጀት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በረንዳ ላይ ነዋሪዎች በተገኙበት ተገቢውን ርቀት በመጠበቅ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሰርተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይ፣ «የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በቤታቸው ተወስነው ያሉ ነዋሪዎች በቤታቸው ሆነው ቀለል ያሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ከጭንቀት እና ከድብርት ተላቀው ጤናማ ኑሮ እንዲኖሩ ያስፈልጋል» ማለታቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት መረጃ ያመለክታል፡፡ ኅብረተሰቡም የማህበራዊና አካላዊ ርቀቱን ጠብቆ በዚህ ጊዜ በመጠኑ አካላዊ አዝናኝ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ያለጭንቀት ጤናውን በመጠበቅ ይህን አስከፊ ጊዜ ማለፍ እንደሚኖርበት ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይም በሌሎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ኅብረተሰቡ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲሰራ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ኮሚሽነር ዮናስ ተናግረዋል። በአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ፕሮግራም ላይ ከነዋሪዎች በተጨማሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አመራሮች ኮሜዲያን እና የስፖርት ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 30/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=30017
18019dc8dacaad11667167c7539ca6b1
936cf6c1b06d1d1678fc4cc0fee04050
ከፓራጓይ ሰማይ ሥር-የወደቀው የብራዚላዊው እግር ኳስ ኮከብ ዝና
ስፖርት
ዳንኤል ዘነበ በዓለም ዙሪያ በማራኪነቱ፤ በአዝናኝነቱም ሆነ በልብ ሰቃይነቱ ወደር አልተገኘለትም፣ ዘመናዊው የእግር ኳስ ስፖርት። ለእግር ኳስ ፍቅር በከፍተኛ ደረጃ ባለቤት በመሆን ረገድ ብራዚላውያንን የሚስተካከል ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ይነገራል፡፡ ብራዚል ብዙ ሚሊዮን የእግር ኳስ ስፖርት ፍቅር ያለው ሕዝብ ባለቤት ብቻም አይደለችም። ብራዚል የእግር ኳስ ክዋክብቶችን በማፍራት ተጠቃሽ ናት። በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ተጫዋቾችን በማፍራት ነጥፋ አታውቅም። የብራዚላውያን የኳስ ጥበበኛነትን ዓለም አምኖ እንዲቀበል ካደረጉ የዘመናቸን ድንቅ ተጫዋቾች መካከል ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሬራ!! ሮናልዲንሆ ጎቾ በተጫዋችነት ዘመኑ የሰራቸው ገድሎች «ዘመናዊ እግር ኳስ እንግሊዝ ውስጥ ተወልዶ ብራዚል አደገ» እስኪባል ድረስ ሀገሩን ብሎም ዓለምን በማስደመም ስሙን መትከል ችሏል። በዓለም ዋንጫ መድረክ ብቻም ሳይሆን ሌሎች መድረኮች ላይ በሜዳ ላይ በሚያሳያቸው እንቅስቃሴዎች፣ አብዶዎች ከስፖርት ቤተሰቡ ልብ ትዝታው ዛሬም የሚነሳለት ድንቅ ጥበበኛ፤ እኤአ በመጋቢት 1980 በብራዚል በደቡብ ብራዚል ፖርት ኤሌግሪ ተወለደ። እግር ኳስ ወዳድ ከሆነ ቤተሰብ የተገኘው ጎቾ ኳስን በ8 ዓመቱ ኳስ ከሰፈሩ ልጆች ጋር በፖርት አሌግሪ የባህር ዳርቻ በማንከባለል ነበር የጀመረው። ሜዳው ላይ በዕድሜው አነስተኛው ልጅ እሱ ሲሆን፤ በችሎታው የሰውን ዓይን በቀላሉ መማረክ የሚችልና ብዙዎች ከዓይን ያውጣህ ማስባል የጀመረው ያኔ ገና ነበር። ሮናልዲንሆ እስከ 13 ዓመቱ ከሰፈሩ በዘለለ ለትልልቅ ክለቦችም ሆነ ለታዳጊ መጫወት አልቻለም። ውሎው የባህርዳርቻ ነበር። በ13 ዓመቱ ግን አንድ ነገር ተከሰተ፣የወንድሙ ክለብ የሆነው የግሪሚዩ መልማዮች ጎበዝ ተጫዋቾችን ሊመለምሉ የነ ሮናልዲንሆ ሰፈር ደረሱ። ለምልመላው ይረዳቸው ዘንድም ተጫዋቾችን ለሁለት ከፍለው ግጥሚያ እንዲያደርጉ አዘዙ። ክፍፍሉም ፍትሃዊ እንዲሆን በሰፈር አደረጉት። የላይኛው ሰፈር ልጆችና የታችኛው ሰፈር ልጆች። ጨዋታው ተጀመረ። ልክ እንደተጀመረ ሮናልዲንሆ ተከላካዮችን አተራምሶ አስደናቂ ጎል አስቆጠረ። ከደቂቃዎች በኋላም የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ሌላ ጎል ደገመ። ውጤቱም 23 ለ 0 ነበር። የሚገርመው 23ቱንም ጎሎች ያስቆጠረው ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሬራ ነው። መልማዮቹ ወደ ካምፓቸው ሲመለሱ አንድ ሳቂታ ልጅ አስከትለው ተመለሱ። ሮናልዲንሆም ከወንድሙ ጋር አንድ ክለብ ውስጥ የመጫወት ዕድል አገኘ። ሮናልዲንሆ ለታዳጊዎቹ ሮቤርቶ ደግሞ ለዋናው ቡድን፡፡ ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ወንድሙ ሮቤርቶ በደረሰበት ጉዳት ከኳስ ተሰናበተ። ሮናልዲንሆ ወንድሙ ባጋጠመው ነገር ቢያዝንም ኳስ ከመጫወት ግን ለደቂቃም አልቦዘነም። በግሪሚዩ የእግር ኳስ ካምፕ ውስጥ ኳስን ጓደኛው አደረጋት። ቀኑን ሙሉ ውሎው ከኳስ ጋር ሆነ። ከጓደኞቹ ቀድሞ ልምምድ ቦታ መገኘት እንዲሁም ከሁሉም በኋላ መውጣት ባህሪው ሆነ። ይህ ታታሪነቱ ወደ ታላላቅ የዓለማችን ክለቦች አምርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ በእግር ኳሱ ዓለም እስከዛሬም የማይዘነጉ ተዓምሮችን መፍጠር ቢያስችለውም ዝናና ገንዘብ ይዞት የሚመጣውን ጣጣ እንዲቋቋም አላደረገውም፡፡ ውሎና አዳሩ በየጭፈራ ቤቱ ሆነ፡፡ አብዝቶ መዝናናት ከድህነት ሕይወት ያስመለጠውን ኳስ አስረሳው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥም ሆኖ ግን ዓለምን በእግር ኳስ ጥበቡ ማስደመም ለእሱ ቀላል ነበር፡፡ በታላቁ ኤልክላሲኮ ታሪክም ከማራዶና በኋላ በተቃራኒ ደጋፊዎች ሜዳ የተጨበጨበለት ተጫዋች እስከመሆን ደረሰ፡፡ በኳሱ ተዝናንቶበታል፣ ተመልካቹንም አዝናንቶበታል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ከአምስት ዓመታት በላይ እንዲዘልቅ አብዝቶ መዝናናቱ አልፈቀደለትም:: ብራዚላውያን ለዚህ ዘመን ድንቅ ኮከባቸው ያላቸው ጥልቅ ስሜት ዛሬም እንደ አዲስ እየተቀሰቀሰ በትዝታው አብረው ሲደሰቱና ሲኮሩ ይሰተዋላሉ። ብዙዎች ጥበቡን ሳይጠግቡ የእግር ኳስ ሕይወቱ በአጭሩ ሊቀጭ ችሏል፡ ፡ እኤአ 2002 ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችሏል። ሮናልዲንሆ የ2005 ባለንደኦር [የዓለም ኮከብ ተጫዋች ሽልማት] አሸናፊ ነበር። በኳስ ሕይወት ስኬትና ዝናንን በመጨበጥ አድናቆትን ማትረፍ የቻለው ሮናልዲንሆ በ800 ሺህ ዶላር ዋስ ሆቴል እንዲታሠር ታዘዘ ይላል የቢቢሲ ዘገባ። ሮናልዲንሆና ወንድሙ ፓራጓይ ውስጥ ሃሰተኛ ፓስፖርትና ሌሎች ሰነዶች ይዘው ተገኝተዋል በሚል በፖሊስ ሊያዙ ችለዋል። ወንድማማቾቹ በወቅቱ እንዲለቀቁ ይግባኝ አመልክተው የነበረ ቢሆንም ሰሚ ጠፍቶ ከአንድ ወር በላይ እሥር ቤት ውስጥ ለመሰንበት ተገደዋል። ብራዚላዊው የእግር ኳስ ጠቢብ ሮናልዲንሆ ጎቹ እና ወንድሙ ፓራጓይ ከሚገኘው እሥር ቤት ተለቀው ውሳኔ እስኪሰጣቸው ድረስ ሆቴል ታስረው እንዲቆይ ውሳኔ ተላልፏል። በተጨማሪ እያንዳንዳቸው 800 ሺህ ዶላር ዋስ ጠርተው የፓራጓይ ዋና ከተማ አሱንሲዮን የሚገኝ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ውስጥ እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተላልፎባቸዋል ሲል ዘግቧል። በብራዚላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሮናልዲንሆ ጎቾና ወንድሙ ላይ ውሳኔውን ያስተላለፉት ዳኛ ገንዘቡ ጫን ያለ እንዲሆን የተደረገው ግለሰቦቹ ሀገር ጥለው እንዳይጠፉ በማሰብ መሆኑን አስገንዝበዋል። «የ40 ዓመቱ የእግር ኳስ ሰው ሮናልዲንሆና ወንድሙ አሲስ እኛ ሃሰተኛ ሰነድ መሆኑን አላወቅንም ነበር »ሲሉ ቢሟገቱም፤ ጠበቃቸውም «የወንድማማቾቹ እሥር ሕገ-ወጥ ነው» ሲል ቢከራከርም ውሳኔው ተፈጻሚ ከመሆን አላዳናቸውም ሲል ቢቢሲ ዘገባውን ቋጭቷል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 2/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=30124
4f8419d9ac2daf6e9a4ea5a355c83689
40d2f498b59fb0bf9cf0548e21a15c61
ሉሲዎቹ ድጋፍ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው
ስፖርት
ስፖርት በባህሪው ተጽእኖ ፈጣሪ እንደመሆኑ በቀላሉ መልዕክትን ሊያስተላልፍና ንቅናቄ ሊፈጥር እንደሚችል እሙን ነው። ይህ በመሆኑም ዓለም በአንድነት ከተላላፊው ቫይረስ ጋር እያደረገ ባለው ፍልሚያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያም የስፖርት ማህበራት፣ ክለቦች፣ ስፖርተኞችና ሌሎች ባለሙያዎች የበኩላቸውን ማበርከት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ሉሲዎቹም በዋና አሰልጣኛቸው ብርሃኑ ግዛው አስተባሪነት የድርሻቸውን ለመወጣት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። እንደ ሀገር የመጣውን ፈተና ለመመከት የሚደረገውን እቅስቃሴ ለማገዝ በቅድሚያ የተነሱት የዋናው ሴት ብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ነበሩ። ነገር ግን የገንዘቡን መጠን በመመልከት ለ20 እና 17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን፣ የንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎች ጥሪ አቅርበው ተቀባይነት ማግኘታቸውን አስተባባሪው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ይገልጻል። በመገናኛ ብዙሃን የተደረገውን ጥሪ ተከትለው ብዙዎች ሚናቸውንለመወጣት እንቅስቃሴውን በመቀላቀላቸው ገንዘብ ማሰባሰቡን በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ ገቢ የሚደረግም ይሆናል። የገንዘብ ማሰባሰቡ ስራ ተጫዋቾች በውድድሮች ተሳታፊ በመሆን ሃገራቸውን ከመወከል ባሻገር ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያስችላቸዋል። ከዚያ ባሻገር ግን ተጫዋቾች ተጽእኖ የመፍጠር አቅማቸውን በመጠቀም ደጋፊዎችንና ህዝቡን ማነሳሳትን ዓላማው ያደረገ መሆኑንም አሰልጣኙ ይጠቁማሉ። ለማሰባሰብ የታቀደው የገንዘብ መጠን 100ሺ ብር ሲሆን እስካሁን የተዋጣው ከ55ሺ ብር በላይ ደርሷል፤ በቀጣይ ቀናትም እቅዱን ለማሳካት ጥረት ይደረጋል። ከድጋፉ ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለምን እያናወጠ ያለው ቫይረስ ማለፉ አይቀርምና ካለፈ በኋላ ላለመቸገር ተጫዋቾች ላይ መስራት ተገቢ ነው። በዚህ ላይም የግንዛቤ ችግር መኖሩን ያነሳው አሰልጣኙ ‹‹ በስፖርቱ ውስጥ ሆነን ኃላፊነታችንን ተወጥተናል፤ በዚያ ልክ ግን በየደጃችን ትንሽ እንቅስቃሴ የመስራትና የስፖርት ቁሳቁሶችን በማዘጋጀት በግል የመስራት ልምድ ችግር አለብን። ሁሌም አሰልጣኞችን እንጠብቃለን። ይህ ሁኔታ ካለፈ በኋላ ስፖርቱ አንዳይቀዛቀዝና እንደ አዲስ ከዜሮ ጀምረን ውጤት እንዳናጣ የትኛውን ስራ መቼ መስራት አንዳለበን አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን እያደረገን ነው። ይህ የበለጠ ጥሩ ይሆናል ብለን አንጠብቃለን፤ እኛ አንደ ባለሙያ ከምንሰጣቸው ባለፈ ተጫዋቾቹ ተዘናግተው ስራቸው ላይ ወደ ኋላ እንዳይሉ እየሰራን እንገኛለን›› ሲል ያብራራል። በዚህ ሁሉም ቤቱ እንዲቆይ በተደረገበት ወቅት ስፖርተኞች እንደ ቀድሞው ልምምዳቸውን ለመስራት ከባድ ይሆንባቸዋል። ባደጉት ሃገራት አሰልጣኞች ተጫዋቾቻቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘው ክትትል ያደርጉላቸዋል። ተጫዋቾቹም ከቤታቸው ሆነው በየግላቸው የሚያደርጉትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በተንቀሳቃሽ ምስል ለዓለም በማጋራት ላይ ይገኛሉ። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ግን ይህ የተለመደ ካለመሆኑም ባለፈ በምን መልኩ መስራት እንደሚቻል ግንዛቤውም የለም። ለዚህም አሰልጣኞች በማህበራዊ ትስስር ዘዴዎችን በመጠቀም (በቴሌግራም) ከተጫዋቾቻቸው ጋር ግንኙነት እንደሚያደርጉ አሰልጣኙ ያስረዳል። በዚህም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዴት መስራት እንደሚችሉ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ። ቴክኒካዊ የሆኑ የስልጠና ክፍሎችንም በተለያዩ የአሰልጣኝነት ስልጠናዎች ባገኟቸው ልምዶች ታግዘው ለተጫዋቾቻቸው ያጋራሉ። ከዚህ በተጓዳኝ ተጫዋቾች በመገናኛ ብዙሃን በሚሰሙትና በሚመለከቱት በመረበሽና በመጨነቅ ስነ-ልቦናቸው እንዳይጎዳ ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለማሳወቅ የአሰልጣኞች ቡድኑ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ለሉሲዎቹም ሆነ ለዋልያዎቹ, ባለውለታ እንደመሆኑ በዚህ ወቅት ስፖርት፤ ህዝቡ ሚናውን በመወጣት ከጎኑ መሆኑን ማሳየት አለበት። ዝናብ፣ ብርድና ጸሃይ ሳይል ቡድኑን ሲደግፍና እንዲሁም ወደ ውጪ ሃገራት ሲጓዝ ከጎኑ የነበረውን ህዝብ በዚህ ወቅት የማጽናናትና የማረጋጋት ግዴታ እንዳለበት አሰልጣኙ ይገልጻል። የስፖርቱ ቤተሰብ ህዝቡ በቫይረሱ ተጠቂ እንዳይሆን እንዴት መጠንቀቅ እንደሚገባው ከማስተማር ባሻገር በግልና በቡድን የሚያደርገው አስተዋጽኦ በቂ ነው የሚል እምነት የሌለው አሰልጣኙ፤ ከዚህ በላይ አስፈላጊ መሆኑን አመላክቷል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=30194
d766d08de2964491ac978054749e6b64
1dee20ef7f798a5f4f9393c780beb163
አትሌቶች ፈታኙን ጊዜ እንዴትይወጡታል?
ስፖርት
በአትሌቲክስ ስፖርት ዝና እና ክብሯን የገነባችው ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችንም አግኝታበታለች። ስፖርቱ አንድ የስራ ዘርፍ በመሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት አትሌቶችን ያቅፋል። አትሌቶችም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ሲሳተፉ ከውጤት ባሻገር የውጭ ምንዛሪን በማስገኘት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ያግዛሉ። በሚያፈሱት መዋዕለ ነዋይም ለበርካቶች የስራ እድል ፈጥረዋል። እንደሚታወቀው በዚህ ወቅት ይህ ዘርፍ እንደሌሎች ስፖርቶች ሁሉ ለውድድር ዝግ ሆኗል። ማልዶ ለልምምድ ይወጣ የነበረውና በዓመት ውስጥ ተደጋጋሚ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበረው እረፍት የለሽ አትሌትም ከተላላፊው ቫይረስ ጋር ተያይዞ ከቤት ውሏል። በብሄራዊ ቡድን የተያዙ፣ በተለያዩ ክለቦች የተካተቱ እንዲሁም የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ተቋማት ሰልጣኝ የሆኑ አትሌቶችም እንዲበተኑ ተደርጓል። በግላቸው የሚሰለጥኑትም ቢሆን እንደ ቀድሞው ከመኖሪያቸው ርቀው የማይጓዙበት ሁኔታ ተጋርጦባቸዋል። ለአንድ ዓመት የተራዘመውን ኦሊምፒክ ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ቻምፒዮናዎች ላይ ተሳታፊ ለመሆን በብሄራዊ ቡድን የተካተቱ አትሌቶች ደግሞ ከሌሎች በተለየ ሁለት አማራጮችን ያስተናግዳሉ። የመጀመሪያው ለተላላፊው የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ላለመሆን በሚደረገው የቤት ውስጥ ቆይታ ከልምምድ በመራቃቸው የአቋም መውረድን ማስተናገድ ነው። ሌላኛው ደግሞ የውድድሮችን መራዘም እንደ መልካም እድል በመጠቀም በተደጋጋሚ ውድድር ላይ ያሳለፉ አትሌቶች እንደ ማገገሚያ ጊዜ በመመልከት በተሻለ ብቃት ለመመለስ የራሳቸውን ጥረት ማድረግ ነው። በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ስፖርተኞች ከስፖርቱ ላለመራቅ ምን ማድረግ አለባቸው፣ ፌዴሬሽኑስ ሚናውን በምን መልኩ እየተወጣ ነው ለሚለው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ህክምና ከፍተኛ ባለሙያና እና የጸረ አበረታች ቅመሞች ተጠሪዋ ቅድስት ታደሰ ከአዲስ ዘመን ጋር ቆይታ አድርገዋል። የመጀመሪያው ነገር ስነ-ልቦና መሆኑን ባለሙያዋ ይገልጻሉ።በዓለምና በሃገር በመጣው በዚህ ቫይረስ ምክንያት በቤታቸው እስኪቆዩ ድረስ ኦሊምፒክን ጨምሮ ለዚህ የውድድር ወቅት በዝግጅት ላይ የነበሩ አትሌቶች በጥሩ አቋም ላይ ነበሩ። በዚህም ምክንያት አቋማቸው እንዳይወርድና ጂምናዚየሞችም በመዘጋታቸው በቤት ውስጥ የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ይገደዳሉ። ከትንፋሽ ጋር በተያያዘ ያለውን ደግሞ የሰዎች ንክኪ በሌለበት በግላቸው ጫካ አካባቢ መስራት ይችላሉ። ይህም ወቅታዊ ብቃታቸው እንዳይወርድ እንጂ ለውድድር በሚደረግ ልክ አይሆንም። ይህ እንዲሆን ደግሞ አስቀድሞ እንደተገለጸው ዋናው ነገር በመልካም ስነ-ልቦና ላይ መገኘት መሆኑን ይጠቁማሉ። በማብራሪያቸውም ‹‹የሰው ልጅ በተፈጥሮው በጭንቀት ወቅት ሰውነቱ በሚሰጠው ግብረመልስ የተለያዩ ቅመሞችን ስለሚያመነጭ ለውጥረትና ለመደበት ስሜት ይጋለጣል። አትሌትሌቲክስ የሙሉ ጊዜ ስራው የሆነው አትሌትም ውድድሮች ከሌሉ በእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ ሊገባ ይችላል። ይህ እንዳይከሰትም አትሌቶች ራሳቸውን በስነ-ልቦና ማዘጋጀት ይገባቸዋል›› ሲሉ ያስረዳሉ ባለሙያዋ። ሁኔታዎችን አእምሮ ሲቀበል ሌሎች አካላትን ማዘዝ ስለሚቻል ስነ-ልቦና የመጀመሪያውና ዋነኛው ጉዳይ ነው። ከዚህ ባሻገር በአትሌቲክስ ስፖርት የሚፈራው ነገር ክብደት መጨመር ነው። በክብደት ተወስነው እንደሚካሄዱት የቦክስና የማርሻል አርት ስፖርቶች ሁሉ የረጅም ርቀት በአትሌቲክስም ክብደት መጨመር የራሱ አደጋ ይኖረዋል። በመሆኑም የቡድን እና ጫና ያላቸውን ልምምዶችን በማስቀረት ሰውነትን ባለበት እንዲቆይና የብቃት መዋዠቅ እንዳይከተል የሚያደርግ መሆን እንዳለበት ባለሙያዋ ያስገነዝባሉ። አመጋገብ ላይም አትሌቶች የራሳቸውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፤ አመጋገብ ከሚወጣው ኃይል ጋር ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል። በዚህ ወቅት ቀለል ያሉ ልምምዶችን እየሰሩ እንደ ወትሯቸው የሚመገቡ ከሆነ ግን ሰውነት ያንን ለማስተናገድ ስለሚከብደው የክብደት መጨመር ይከሰታል። በመሆኑም ይህንን መከታተልና ከቻሉ በየዕለቱ ያሉበትን ሁኔታ በመመዝገብ ማስታወሻ እንዲይዙ ይመከራል። የዓለም አትሌቲክስም በየወቅቱ የሚያወጣውን መረጃ መከታተልም አስፈላጊ ነው። በዚህ ሂደት ሊዘነጋ የማይገባው ዋናው ነገር በቤት ውስጥ የሚሰሩ ማሳሳቢያዎችና ሌሎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ንጹህ አየር ባለበት ስፍራ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ሰው የማይበዛበትና ነፋሻማ አየር ባለበት ስፍራ ቢንቀሳቀሱ ደግሞ የተሻለ ይሆናል። እንደ ዓለም አትሌቲክስ መረጃ ከሆነ አትሌቶች በተለይም የረጅም ርቀት ሯጮች ትንፋሻቸው የዳበረ በመሆኑ ከሌላው በተለየ ተጋላጭነታቸው የሰፋ ይሆናል። በመሆኑም ራሳቸውን ለየት ባለመልኩ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ፈሳሽ በብዛት መውሰድና በሽታን ሊቋቋሙ የሚችሉ ምግቦችንም ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ሁኔታ ማዘውተርና በዓለም የጤና ድርጅት እንዲሁም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ከመሳሰሉ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎችን መከታተል ለአትሌቱ ጠቃሚም ነው። ምክንያቱም አብዛኛው የማህበራዊ ትስስር ገጾችን የሚጠቀም እንደመሆኑ መረጃዎችን የሚያገኙበት መንገድ በራሱ ጎጂ ሊሆን ይችላል። ይህንንና መሰል ግንዛቤዎችን ከማስጨበጥ አንጻር ባለሙያዎች አትሌቱን በአካል ለማግኘት አዳጋች በመሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ ስራዎችን እንደጀመረም ባለሙያዋ ይጠቁማሉ። የፌዴሬሽኑ አመራሮች ባደረጉት ውይይት አትሌቱ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ክልሎችም የሚገኝ እንደመሆኑ ሁሉንም ተደራሽ ለማድረግ በቴሌቪዥንና በሬዲዮኖች መልዕክቶችን ማስተላለፍ የተሻለ አማራጭ ሆኖ አግኝቶታል። በመሆኑም ሰፊ ሽፋን ካላቸውና ከክልል የመገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር፤ አትሌቱ ልምምዱን እንዴትና በምን ሁኔታ መስራት እንዳለበት በባለሙያዎች ግንዛቤ የሚሰጥ ይሆናል። ከዚህ ባሻገር ከወቅታዊው ሁኔታና ከቫይረሱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን፣ ስነ- ምግብ፣ ስፖርታዊ ስነ-ልቦና፣ የስፖርት ህክምና፣ የመረጃ ክትትል ምን መምሰል አለበት የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ነባራዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ለአትሌቱ እንዲደርስ ይደረጋል። በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ ግን መዘንጋት የሌለበት ዋነኛ ጉዳይ አበረታች ቅመም መሆኑን ያሳስባሉ። ይህንን ግንዛቤ የሚሰጡትም በስፖርቱ ላይ ለረጅም ጊዜ ያሳለፉ ባለሙያዎች እና ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች ላይ ስኬታማ የሆኑ አንጋፋና ተምሳሌት አትሌቶች ሲሆኑ፤ መልእክቶችን፣ ምክሮችንና በተግባር የታገዙ እንቅስቃሴዎችንም ለአትሌቶች የሚያስተላልፉ ይሆናል። ከፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ከስልጠና ጥናትና ምርምር ክፍል ጋር በመሆንም በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች መልእክቶችን ለማስተላለፍም በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ባለሙያዋ ጨምረው ገልጸዋል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 5/ 2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=30273
1b85a28f1c8b43de53d12014a7757109
e91a0bae5984a76af014e9c4a6097934
የሦስት ታላላቅ ክለቦች አለቃው መጨረሻ
ስፖርት
ዓለም በኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተሸበረች በምትገኝበት በዚህ ጊዜ የስፖርቱ ዓለም ተቆልፎበት ይገኛል። በቫይረሱ ሳቢያ የስፖርቱ ዓለም ሰዎች ከሚወዱት መድረክ እንዲቆጠቡ ከመገደዳቸው በተጨማሪ የቫይረሱ ሰለባ ከመሆን ባሻገር ሕይወታቸውን ያጡም አልጠፉም። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ዓለም ሌላ የጤና ፈተናዎች የሌሉባት እስኪመስል ድረስ ትኩረት ሁሉ ወደ አንድ አቅጣጫ አዘንብሏል። ከስፖርቱ ዓለም ሰዎች ማን በቫይረሱ ተያዘ? ማንስ ሕይወቱ አለፈ? በሚል የስፖርት ቤተሰቡ ትኩረት ወደ አንድ አቅጣጫ በተጓዘበት ወቅት የስፔን ሦስት ታላላቅ ክለቦችን በማሰልጠን ብቸኛው የሆነው ራዶሚር አንቲች ባለፈው ሰኞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የስፔን ታላላቅ ክለቦች የሆኑት ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎናና አትሌቲኮ ማድሪድ ብቸኛ አሰልጣኝ የሆነው ሰርቢያዊው አንቲች በሰባ አንድ ዓመቱ በማድሪድ ከተማ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ታሪካዊው አሰልጣኝ ስፔንን እያመሳት በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሕይወቱ እንዳለፈ በርካቶች ግምታቸውን ቢያስቀምጡም ለሞት የበቃው ላለፉት ዓመታት ሲያሰቃየው በቆየው ሌላ ሕመም ምክንያት እንደሆነ ተዘግቧል። በሰርቢያ ዛይቲስ ከተማ የተወለደው አንቲች እንደ በርካቶቹ የእግር ኳስ አሰልጣኞች በተጫዋችነት አሳልፏል። የተጫዋችነት ዘመኑ የሚጀምረውም በስሎቦዳ ዩዚስ ክለብ ሲሆን በርካታ የውድድር ዓመታትን በቤልግሬዱ ፓርቲዛን ክለብ እየተጫወተ አሳልፏል። ከዚህ ክለብ ጋርም እ.ኤ.አ በ1975/76 የውድድር ዓመት የዩጎዝላቪያ ሊግ ዋንጫን ማሳካት ችሏል። ወደ ቱርኩ ክለብ ፊነርባቼ በማቅናትም የሊጉን ዋንጫ አንስቷል። ወደ ሪያል ዛራጎዛ አምርቶም ሁለት የውድድር ዓመታትን አሳልፏል። እ.ኤ.አ በ1980 ወደ እንግሊዙ ክለብ ሉተን ታውን አቅንቶም ከአራት የውድድር ዓመታት ቆይታ በኋላ ጫማውን ሰቅሏል። አንቲች ጫማውን ከሰቀለ ወዲህ የአሰልጣኝነት ሕይወቱን የጀመረው በአገሩና ተጫውቶ ባለፈበት የቤልግሬዱ ክለብ ፓርቲዛን ሲሆን በክለቡ ቆይታው ሁለት የቻምፒዮንሺፕ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል። ከዚያም እ.ኤ.አ በ1988 በተጫዋችነት ወዳሳለፈበት ዛራጎዛ ክለብ አምርቶ ክለቡን የአውሮፓ ካፕ ተሳታፊ ማድረግ ችሏል። እ.ኤ.አ በ1990/91 የውድድር ዓመት አልፍሬዶ ዲ ስቲፋኖን በመተካት የታላቁ ክለብ ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ለመሆን በቅቷል። ይሁን እንጂ ከታላቁ ክለብ ጋር ውጤታማ ጊዜን ባለማሳለፉ ቆይታው አጭር ነበር። ከሪያል ማድሪድ ያልተሳካ የአሰልጣኝነት ዘመን አጭር ቆይታ በኋላ አንቲች ወደ ሪያል ኦቪዶ በማቅናት ለሁለት የውድድር ዓመታት ስኬቶችን አስመዝግቧል። ይህም ስኬቱ ወደ ታላቁ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ዋና አሰልጣኝነት በር የከፈተለት ሲሆን ገና በመጀመሪያ የውድድር ዓመቱ እ.ኤ.አ 1995/96 የውድድር ዓመት የሊጉን ዋንጫና የኮፓዲላሬ ስኬቶችን መጎናፀፍ ችሏል። ይህም በክለቡ ታሪክ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ሲሆን ዛሬም ድረስ የሚዘከር ነው። አንቲች በአትሌቲኮ ማድሪድ ያሳለፋቸው አምስት ዓመታትም ክለቡ ከምንም ተነስቶ አሁን ላይ ከስፔን ታላላቅ ክለቦች አንዱ ለመሆኑ መሰረት የያዘበት ሆኖ ይነገራል። ከአትሌቲኮ ማድሪድ ስኬታማ አምስት ዓመታት በኋላ ወደ ሪያል ኦቪዶ የተመለሰው አንቲች በውድድር ዓመቱ ክለቡ ከሊጉ በመውረዱ ብዙም ሳይቆይ እ.ኤ.አ 2003 ላይ ወደ ታላቁ የካታላን ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ሊውስ ቫንሃልን ተክቶ ሊፈርም ችሏል። በወቅቱ ባርሴሎና ወራጅ ቀጠና ከነበረው ክለብ በሦስት ነጥብ ከፍብሎ የመውረድ ሥጋት የተጋረጠበት ቢሆንም በአንቲች አሰልጣኝነት ስድስተኛ ደረጃን ይዞ ሊያጠናቅቅ ችሏል። ይህም በአውሮፓ ካፕ ተሳታፊነቱን አረጋግጦለታል። እንደ አጋጣሚ ሆኖ በቀጣይ የውድድር ዓመት ክለቡን ለመምራት የተመረጡት አዲሱ ፕሬዚዳንት ሁዋን ላፖርታ አንቲች በካታላኑ ሃያል ክለብ አሰልጣኝነት እንዲቀጥል አልፈለጉም። ይህም ወደ ሴልታቪጎ እንዲያመራ አድርጎታል። እዚያም ግን ቆይታው አጭር ነበር። እ.ኤ.አ 2008 ላይ የሰርቢያን ብሔራዊ ቡድን ወደ 2010 የደቡብ አፍሪካ ዓለም ዋንጫ ለማሳለፍ ሃላፊነቱን የወሰደው አንቲች በማጣሪያው ሊሳካለት አልቻለም። ከአገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር የነበረው ቆይታም በዚሁ በአጭር ተቀጭቷል። ከዚያ በኋላ ግን ለአራት ዓመታት እ.ኤ.አ እስከ 2016 ድረስ በቻይና ሊግ በርካታ ክለቦችን በአሰልጣኝነት መርቷል። ሦስቱን ታላላቅ የስፔን ክለቦች በአሰልጣኝነት በመምራት ብቸኛው ሰው የነበረው አንቲች ባለፈው ሰኞች ለረጅም ጊዜ በቆየበት ሕመም ሕይወቱ ካለፈ በኋላ የስፖርት ቤተሰቡ በተለያዩ መንገዶች ሐዘኑን እየገለፀ ይገኛል። ከነዚህ መካከል የአትሌቲኮ ማድሪዱ ፕሬዚዳንት ኪኮ ‹‹የአትሌቲኮ ማድሪድን ድንቅ መሐንዲስ አጣን፣ እሱ የአትሌቲኮ ማድሪድ ወርቃማ ዘመን የቀየሰ ድንቅ ሰው ነው›› ሲል ገልፆታል። የአትሌቲኮ ማድሪድ የቀድሞ ተጫዋች፣ የአሁን ፕሬዚዳንትና በባርሴሎና ኦሊምፒክ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ዋንጫ ያነሳው ኪኮ‹‹ አንቲች የፈጠራ ሰው ነው፣ የሊጉንና የኮፓ ዲላሬን ዋንጫ እንድናነሳ አድርጓል፣ እሱ ለእኔ ምርጡ አሰልጣኝ ነው›› በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። በአንቲች ስር ከሰለጠኑ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ፖርቹጋላዊው ፓውሎ ፉተር በበኩሉ‹‹አንቲች በአትሌቲኮ ማድሪድ ስለፈፀመው ገድል ለመናገር ቃላት የሉኝም፣ እሱ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ብቻ ሳይሆን ለእግር ኳስም ጀግና ነው፣ ነብሱን ይማር›› ብሏል። የቀድሞው የሊቨርፑልና አትሌቲኮ ማድሪድ ኮከብ ፈርናንዶ ቶሬስ በአንቲች አሰልጣኝነት ስር የማይረሳ ትዝታ ካላቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው። ‹‹አንቲች ጥሎን ሄዷል፣ እሱ እግር ኳስን ያስከበረ ጀግና ነው፣ በአትሌቲኮ ማድሪድ የድል ታሪክ ውስጥ ሁልጊዜም ሲዘከር ይኖራል›› በማለት ቶሬስ ሐዘኑን ገልጿል። አንቲች በአሰልጣኝነት ዘመኑ ባሰለጠናቸው ተጫዋቾች ብቻም ሳይሆን በተቀናቃኝ ክለብ ተጫዋቾች ክብር የሚሰጠው መሆኑን የሪያል ማድሪዱ ተከላካይና አምበል ሰርጂዮ ራሞስ አስተያየት ምስክር ይሆናል። ራሞስ ‹‹ተቀናቃኛችን አትሌቲኮ ማድሪድን ታላቅ ክለብ አድርጓል›› በማለትም ሐዘኑን ገልጿል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 4/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=30231
0fab72ded5333f3998b22a889ec0db02
68e0d292174be376b38240e51c8ccdb4
የዲያጎ ጋርዚያቶ ማረፊያ ታውቋል
ስፖርት
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ትልቅ አሻራን ማሳረፍ የቻሉ አሰልጣኝ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ኢትዮጵያ በታሪኳ በዓለም ዋንጫ ከ 20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በማሳተፍ አይረሴ ታሪክ ሰርተዋል። በትውልድ ፈረንሳዊው፤ በዜግነት ጣሊያናዊ ዲያጐ ጋርዚያቶ። በኢትዮጵያን ዘንድ የተለየ አክብሮት የሚሰጣቸው አሰልጣኝ ዲያጎ ጋርዚያቶ ርቀው ከነበሩት የአሰልጣኝነት ሙያ መመለሳቸው ተሰምቷል። የ70 ዓመቱ አዛውንት የዲሞክራቲክ ኮንጎው ክለብ ሴንት ኢሎይ ሉፖፖን ለማሰልጠን ከስምምነት መድረሳቸውን ታውቋል:: እኤአ በ1950 ሌስቲዛ የተወለዱት እኝህ አሰልጣኝ በተጨዋችነት ዘመናቸው የተከላካይ መስመር ተሰላፊ ነበሩ።ከ1984 እ.ኤ.አ ጀምሮ በአሰልጣኝነት ማገልገል ሲጀምሩ የፈረንሳይ ዝቅተኛ ሊግ ክለቦችን በማሰልጠን ነበር የቆዩት። የዲያጎ ጋርዚያቶ የአሰልጣኝነት ምዕራፍ ከፍ እያለ መምጣት የቻለ ሲሆን፤ ጅማሮውም ከኢትዮጵያ ይነሳል። አሰልጣኙ ትልቁን ኃላፊነት የተረከቡት በ2001 እ.ኤ.አ ላይ የኢትዮጵያ ሀ 20 ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ሲመደቡ ነበር። በዚሁ ጊዜም የኢትዮጵያን ወጣት ቡድን በአርጀንቲና ለተደረገው 14ኛው የዓለም ወጣቶች ዋንጫ እንዲሳተፍ አብቅተዋል። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት ቡድን ዋና አሰልጣኝነት ከለቀቁ በኋላ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት በክለብ ደረጃ ሲሰሩ ቆይተው በ2007 እ.ኤ.አ ላይ የቶጐ ብሔራዊ ቡድን ተረክበው ነበር። አሰልጣኝ ዲያጎ ጋርዚያቶ የቶጎ ቆይታቸው ከ2 ወራት አልዘለለም።በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ትልቅ ውጤት በማስመዝገብ የተደነቁ ሲሆን ለሁለት ጊዜያት ያሰለጠኑትን የዲ ሪፖብሊክ ኮንጎውን ቲፒ ማዜምቤ በ2009 እ.ኤ.አ የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ እንዲያሸንፍ አድርገዋል።የአሰልጣኙ ውጤታማነት በመረዳት ቲፒ ማዜምቤ ዳግም በአሰልጣኝነት ቀጥሯቸዋል። እኤአ በ2003 እስከ 04 ቲፒ ማዜምቤን ማሰልጠን የቻሉት ዲያጎ ጋርዚያቶ ክለቡ እኤአ በ2010 ዳግም አሰፈረማቸው። አሰልጣኙ አሰልጣኙን ክለቡን እንዲያሰለጥኑ ዳግም በተሰጣቸው እድል ውጤት አልቀናቸውም ነበር። ከቲፒ ማዜምቤ ጋር ለአንድ ዓመት ቆይታ ካደረጉ በኋላ መለያየት ግድ ብሏቸዋል። የዲያጎ ጋርዚያቶ ቀጣዩ አቅጣጫ ወደ ዋይዳድ ካዛብላንካም ሆነ። የዲያጎ ጋርዚያቶ ቆይታ በተመሳሳይ ውጤት አልባ መሆኑን ተከትሎ ክለቡን ጥለው ዳግም ወደ ኢትዮጵያ መጡ። በእኤአ 2012 ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮትጵያ የተመለሱት የ70 ዓመቱ አዛውንት ታሪክን መድገም ሳይችሉ ቀርተዋል። አሰልጣኙ ወደ ሀገራችን ሲመጡ በአወዛጋቢ ሁኔታዎች ዋና ብሔራዊ ቡድኑን በኃላፊነት መያዝ ቢችሉም ፤ ከ2 ወራት በኋላ ተሰናብተዋል።በዚሁ ዓመት ወደ አል ሂላላ ኦምዱር ማን ክለብ ያመሩት አሰልጣኙ የጉዟቸው ምዕራፍ ሁሉ ውጤት አልባ ነበር። የዲያጎ ጋርዚያቶ ከክለብ ወደ ክለብ መሽከርከር በሙያው ውጤት እየራቃቸው ከመምጣቱ ጋር ሰፊ ትችቶችን አስተናግደዋል። አሰልጣኙ በአል ሂላላ ኦምዱርማን ክለብ ጋር ቆይታቸው ውጤት አልባ በመሆኑ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ተሰናበቱ። እኤአ በ2014 አል ሜሪኤሪክ ክለብ ፊርማቸውን ያኖሩት ጋርዚያቶ ፤ከዚህ ክለብ ጋር ጥሩ የሚባል የሶስት ዓመት ቆይታ አድርገዋል። እኤአ በ2017 ከክለቡ ጋር የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ አል ኢተሃድ ተረክበው ነበር ። የ70 ዓመቱ አዛውንት ከሊቢያው ክለብ አል ኢተሃድ ጋር ከአጭር ጊዜ ቆይታ በኋላ ነበር የተለያዩት። የጣልያን ዜጋ የሆኑት ጋርዚያቶ ከሊቢያ ከተሰናበቱ በኋላ ፈላጊ ክለብ ለማግኘት አዳግቷቸው ነበር። የአሰልጣኙ ፈላጊ ማጣት ደግሞ ከውጤት ጋር የሚያያዝ ሲሆን፤ አዛውንቱ ላለፉት ዓመታት ከሙያው እንዲርቁ ያደረጋቸውም ነበር። በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው ዲያጎ ጋርዚያቶን ወደ ስራ መመለሳቸው ተሰምቷል:: አሰልጣኙ የዲሞክራቲክ ኮንጎው ክለብ ሴንት ኢሎይ ሉፖፖን ለማሰልጠን መስማማታቸው ታውቋል:: የዲያጎ ጋርዚያቶ የውጤታማነት ጀንበር እየጠለቀች ቢሆንም፤ ከአዲሱ ክለባቸው ጋር ለማድመቅ እንደሚታትሩ ይጠበቃል። የ70 ዓመቱ አዛውንት ፈታኙ ጉዞ ከሰማያዊ እና ቢጫ ለባሾቹ ጋር የሚነጉድ ይሆናል:: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 6/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=30329
3b15eebee18ecf6f6a811199d6c323de
5ee50a82042d7ab643a57d751bba12ed
ያልነጠፈው የስፖርት ቤተሰቡ ድጋፍ
ስፖርት
የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ስታድየም አካባቢ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ድጋፍ አደረጉ። የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ኮሮና ቫይረስን በጋራ ለመከላከል ይቻል ዘንድ ለበርካታ የጎዳና ተዳዳሪዎች ቫይረሱን ሊከላከሉ የሚችሉበትን የማክስ እና የሳሙና ድጋፍ አድርገዋል። የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ ስታድየም በነበረው ልዩ ፕሮግራም ላይ እስከ 350 ለሚደርሱ የጎዳና ተዳዳሪዎች ምሳ አብልተዋል። በምሳ ማብላት መርሃ ግብሩ ላይም ኮሮና ቫይረስን እንዴት መከላከል እንደሚቻል የግንዛቤ ማስበጫ ትምህርት ተሰጥቷል። «መርሃ ግብሩ የተዘጋጀበት ዋና ዓላማም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለጎዳና ተዳዳሪዎች እንደሌላው ማህበረሰብ ‹በአሁን ወቅት ማን አለላቸው› በሚል ከእነሱ ጎን ለመቆም ነው » ሲሉ የክለቦቹ ደጋፊ ተወካዮች ገልጸዋል። በተጨማሪም ከሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች የተሰባሰበው የገንዘብ እርዳታም ገቢው ለእነዚህ የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆኖ የመጪውን የፋሲካ በዓል በሌላ ልዩ ፕሮግራም እንዲያሳልፉበት እንደሚደረግ ተገልጿል። የስፖርት ማህበረሰቡ ወገናዊነት በቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እንደተፈጸመው ሁሉ፤ በሌሎች ማህበራትም በኩል ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠሉን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ አሰልጣኞች ይፋዊ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በእግር ኳስ ስፖርት የሚገኙ አሰልጣኞች የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠርና ለማጥፋት እየተደረገ ባለው ርብርብ በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ጽፏል። በመሆኑም በእግር ኳስ ሙያ ውስጥ የሚገኙ አሰልጣኞች ድጋፎቹን እስከ ሚያዚያ 06 ቀን 2012 ዓ.ም ረፋድ ድረስ ሲደረግ የነበረ ሲሆን ፤በዚህም 118 ሺ 500 ብር በመሰብሰብ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ገቢ ሊደረግ መሆኑ መረጃው አመልክቷል። በዓለማችን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከልና ለመግታት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ላለው ርብርብ የስፖርት ማህበረሰቡ እያደረገ ያለውን አበርክቶ አጠናክሮ መቀጠሉን የሚያስረዳ ተግባር ሆኗል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 6/2012
https://www.press.et/Ama/?p=30351
cfb6ec7f19f03bb1aa48ba58d40e9836
7d2188a7787361b54ce55de5bef8b537
የኮሮና ቫይረስ በተራዘመው ኦሊምፒክም ተፅዕኖው ሊቀጥል ይችላል
ስፖርት
የዓለምን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ወደተለየ አቅጣጫ ያዞረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በስፖርቱ ዓለም ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ተዘርዝሮ የሚልቅ አይደለም።አንዳች ውድድር በዓለም ላይ እንዳይኖር ከማስገደድ ባለፈ የስፖርቱን ዓለም ሽባ አድርጎታል።ብዙ ታቅዶባቸው፣ ብዙም ተለፍቶባቸው ለዓመታት በዝግጅት ላይ የነበሩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በትልቅ ኪሳራ የሚካሄዱበት ጊዜ እንዲራዘም ግድ ብሏል። ጃፓን ካለፉት ሰባት ዓመታት በላይ ከፍተኛ ዝግጅት ስታደርግበት የቆየችው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በትልቅ ኪሳራ ለአስራ ስድስት ወራት የተራዘመና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ታላቅ የስፖርት መድረክ ነው።ይህን ታላቅ የስፖርት መድረክ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እየተናነቀውም ቢሆን ለ2021 ለማራዘም ተገዷል።ኦሊምፒኩን ጨምሮ በርካቶቹ ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮችና ጉባዔዎች ወደ ቀጣይ ዓመት የተሸጋገሩት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በቁጥጥር ስር ይውላል በሚል ተስፋ ነው።ይሁን እንጂ በዓለም ላይ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከተስፋ በስተቀር የቫይረሱ ስርጭት በጊዜ የሚገታ ወይም ፈውስና ክትባት በዚህ ጊዜ እውን ይሆናል የሚያስብል እንዳልሆነ መታዘብ ይቻላል።ይህንን ከግምት ያስገቡት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ ኦሊምፒኩ የቫይረሱን ስጋት ለማምለጥ በአስራ ስድስት ወራት ቢራዘምም ከቫይረሱ ተፅዕኖ ሊያመልጥ እንደማይችል ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማመልከታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ አስነብቦታል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩ ወደ 2021 እንዲዘዋወር ውሳኔ ላይ ከደረሰ ወዲህ በቫይረሱ ስጋት በአስተናጋጇ ጃፓን ቶኪዮን ጨምሮ በሰባት ከተሞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።ከቀናት በፊት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም በኮሮና ቫይረስ በጃፓን ከስድስት ሺ በላይ ሕዝቦች ሲጠቁ ከመቶ በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸውን አጥተዋል።ኦሊምፒኩ እስከሚካሄድ ገና አስራ ስድስት ወራት የቀሩት ቢሆንም የቫይረሱን ስርጭት በነዚህ ጊዜያት በቁጥጥር ስር ማዋል ካልተቻለ ኦሊምፒኩ አሁንም ከስጋት ውጪ ሊሆን እንደማይችል ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።‹‹በዚህ ወቅት ማንም በእርግጠኝነት ቫይረሱን በቁጥጥር ስር አውላለሁ የሚል እምነት የለውም፣ ስለዚህ የተራዘመው ኦሊምፒክ ከቫይረሱ ስጋት ነፃ ይሆናል ብለን ለመናገር ይቸግረናል›› በማለትም ሃሳባቸውን አጠናክረዋል። በቫይረሱ ስጋት ኦሊምፒኩን ከአንድ ዓመት በላይ ለማራዘም እንደተወሰነ ያስታወሱት ስራ አስፈፃሚው፣ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዚህ ወቅት ለተራዘመው ኦሊምፒክ ጠንክሮ ከመዘጋጀት ውጪ ሌላ ነገር ሊያደርግ እንደማይችል አስረድተዋል።ይሁን እንጂ የሰው ልጅ እስከዚያው ቫይረሱን በቁጥጥር ስር ያውላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።የተራዘመው ኦሊምፒክ ዘንድሮ ሊካሄድ በታቀደበት ተመሳሳይ ወቅት እንዲካሄድ ከመወሰኑ ውጪ በየትኛው ቀን እንደሚካሄድ ቁርጥ ያለ ቀን አልተቀመጠለትም።ይህንንም ለመወሰን ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተለየ አማራጭ እስካሁን እንዳልተመለከተ አስረድተዋል።ከዚህ ይልቅ ኦሊምፒኩን ቀጣይ ዓመት ላይ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ የሚቻልበትን አማራጭ ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የቶኪዮ ኦሊምፒክ ወደ ቀጣዩ ዓመት በመራዘሙ ብቻ በጃፓንም ይሁን በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደሚያስከትል ቀደም ሲልም ሲነገር ነበር።ይሁን እንጂ ይህ ኪሳራ ምን ያህል እንደሚሆን አሁን ላይ ማስቀመጥ ከባድ እንደሚሆን ስራ አስፈፃሚው ጠቁመዋል።ነገር ግን ኪሳራው ከባድ እንደሚሆን አስቀምጠዋል። የኦሊምፒክ ውድድሩ ከመራዘሙ አስቀድሞ የወጡ ጥናቶች እንዳመለከቱት ኦሊምፒኩ ከተሰረዘ ወይም ከተራዘመ የጃፓን ጠቅላላ የአገር ውስጥ ገቢዋ 1ነጥብ 4 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ተጠቁሟል።ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ብቻ የጃፓን መንግስትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ እንደሚገቡ ቀደም ሲል ተዘግቧል።የጃፓኑ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴም ገና ከመጀመሪያው ከፍተኛ ኪሳራ ሊገጥም እንደሚችል ተናግሯል።ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለዚህ ኪሳራ ስጋት ሰላሳ ሦስቱንም ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች የሚመለከት መድህን የገባ ቢሆንም በቂ እንደማይሆን ታምኖበታል።ፕሬዚዳንቱ ቶማስ ባኽም ኦሊምፒኩ መራዘሙን በገለፁበት ወቅት ከባድ ኪሳራ እንደሚኖር በማመን ሁሉም ባለድርሻ አካላት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ለመጠቆም ሞክረዋል፡፡አዲስ ዘመን ሚያዝያ 8/2012
https://www.press.et/Ama/?p=30486
ac0585511f0ccf6ad4702e9fbd7ce30e
519cb5ef8931ca98cc474006d3a8f921
የስፖርት ማህበራት በአዲስ መልክ ይዋቀራሉ
ስፖርት
በአንድ አገር ስፖርት እድገትና ውጤታማነት ላይ ሚና ያላቸው በርካታ አካላትን መጥቀስ ቢቻልም፤ ስፖርቱን የሚመሩ አካላት መሰረት መሆናቸው ይታመናል። በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ስፖርቱ የሚመራው በሁለት አካላት ሲሆን፤ ይኸውም ህዝባዊ እና መንግስታዊ ውክልና ባላቸው ነው። ከህዝቡ የተወከሉና ስፖርቱን ለማገዝ በበጎ ፈቃዳቸው እውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ጊዜና ጉልበታቸውን የሚሰጡት አማተር ባለሙያዎች ስፖርትን በበላይነት ይመራሉ። መንግስታዊው አካል ደግሞ በስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ማህበራቱን ለመምራት በተሰጠው ስልጣን መሰረት ስራዎችን ያከናውናል። የመሪው አካል ጥንካሬ እና ድክመት በስፖርቱ እድገት ላይ ከፍተኛ ሚና ያለው እንደመሆኑ የስፖርት ማህበራቱ እንቅስቃሴ ወሳኝ ይሆናል። በኢትዮጵያ ስፖርት ማህበራት ባለው ሁኔታ ጥንካሬውም ሆነ ድክመቱ በአብዛኛው ከህዝባዊው አካል ጋር ማያያዝ የተለመደ ነው። ነገር ግን ከብሄራዊ እስከ ክልሎች ያሉት የስፖርት ማህበራቱ ባለሙያዎች ቅንጅት፣ ከዓለም አቀፍ ሁነት ጋር የመራመድ አቅም፣ ውድድሮችንና ስልጠናዎችን በተያዘላቸው ጊዜና ሁኔታ እንዲካሄዱ ማድረግ፣ ህግና ደንብን ባማከለ መልኩ መንቀሳቀስ እንዲሁም ለስፖርቱ እድገት መታተር ከስራዎቻቸው ጥቂቱ ናቸው። ሆኖም አብዛኛዎቹ ፌዴሬሽኖች ለውጤታማነት በአዲስ ስልትና በተሻለ ሁኔታ ከመቅረብ ይልቅ የበጀት እጥረትንና ሌሎች ጉዳዮችን እንደ እክል ሙጥኝ ማለታቸው ስፖርቱ በዘገምተኛ አካሄድ እንዲገፋ አድርጓል። ይህንን የተመለከተው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም በዚህ ላይ እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል። ኮሚሽኑ በቅርቡ አገር አቀፍ የስፖርት ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱ ይታወቃል። በዚህ ላይ ተመስርቶም የስፖርት ዘርፍ የአስር ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጅቷል። በሪፎርሙ የተጠቆሙ ጉዳዮች በእቅድ እንዲካተቱ የተደረገ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል የስፖርት ማህበራትን ማጠናከር አንዱ ነው። በዚህ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ የኮሚሽኑን የቀጣይ አስር ዓመት ስራ ሪፎርሙን መነሻ በማድረግ በተለዩ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ከስራዎቹ መካከል አንዱ ደግሞ የስፖርት ማህበራትን ማጠናከር ነው። ከዚህ አንጻር በእያንዳንዱ ፌዴሬሽን የሱፐርቪዥን ዝርዝር ስራዎች የሚከናወን ይሆናል። ከዚህ በኋላም ኮሚሽኑ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የማህበራቱን ደንቦችና መመሪያዎች የማሻሻል ስራ ይሰራል። በመቀጠልም አገሪቷ ባሏትና ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን የመቀመር ስራዎችን የሚመዝን አዲስ ስታንዳርድ የሚዘጋጅ ይሆናል። በስታንዳርዱ መነሻነትም በብሄራዊ ደረጃ ያለ አንድ ፌዴሬሽን ምን ምን ስራዎችን እንዲያከናውን ይጠበቅበታል እንዲሁም በክልል ደረጃ ያሉ ፌዴሬሽኖች ምን ማሟላት ይገባቸዋል የሚለው በአዲስ መልክ የሚለይ ይሆናል። ኮሚሽኑም የራሱን መስፈርት የሚፈትሽ ሲሆን፤ ፌዴሬሽኖች በስታንዳርዱ መሰረት ለስፖርት ማህበርነት ብቁ ከሆኑ ይመዘገባሉ፣ ካልሆኑ ደግሞ በምዝገባው የማይካተቱ ይሆናል። ፌዴሬሽኖቹን ተከትለው የተቋቋሙ ክለቦችም በተመሳሳይ የማጠናከር ስራም ጎን ለጎን የሚከናወን ይሆናል። ክለቦች ህዝባዊ መሰረት ያላቸው መሆኑ፣ የገቢ ምንጫቸው ከምን እንደሆነ፣ የክለብነት መስፈርቱን አሟልተው ስለመቋቋማቸው እንዲሁም ስላሉበት አጠቃላይ ሁኔታ የመፈተሽ ስራዎችም ይከናወናሉ። በታዳጊዎች የስፖርት ማሰልጠኛ ተቋማትም በተመሳሳይ ፍተሻ በማድረግ በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት እንዲሰሩ የሚደረግ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ያመላክታሉ። በማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማት ላይም በተመሳሳይ ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚሰራበትና በሚማርበት አካባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚደረግበት እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው በሚለው ላይም ምዘና የሚደረግ ይሆናል። መንግስት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማውጣት በሚያስገነባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ሪፎርሙ ትኩረት ያደርጋል። በተለይ በማዘውተሪያዎች መተዳደሪያ አዋጅ ላይ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ የሚሰራ ይሆናል። ከዚህ ባሻገር የስራዎቹ አካል በሆኑት ሰራተኞች ላይ ክለሳ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በተቋሙ ቢፒአር እየተሰራ ይገኛል። በስፖርቱ ልማት ላይ ለውጥ ባለመምጣቱ በሪፎርሙ ዝግጅት ወቅት በተደረገው ጥናት በተለዩ ጉዳዮች ላይ በመንተራስ ወደ ስራ ተገብቷል። መሰል ስራዎችን ማከናወን ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም የስፖርት ማህበራትን በአዲስ መልክ ማደራጀቱ ግን ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ኮሚሽነሩ አስረግጠዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ ዱቤ ጂሎ በበኩላቸው ከተወሰኑ ማህበራት ባሻገር አብዛኛዎቹ ያሉት በስም መሆኑን ይገልጻሉ። ዘርፉ በርካታ ችግሮች ያሉበትና ሰፊ ስራን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ስትራቴጂካዊ አካሄድ አስፈላጊ ነው። ማህበራት ካልተጠናከሩ፣ የክለቦች አደረጃጀት ላይ ካልተሰራ፣ ታዳጊና ወጣቶችን ላይ ከላይ ጀምሮ የአሰራር ስርዓት ካልተዘረጋ እንዲሁም አካዳሚዎች ላይ የተወሰነ ስራ ሳይከናወን ውድድር ብቻ ማዘጋጀት የትም ሊያደርስ አይችልም። ስራው ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም ማህበራት ራሳቸውን የሚችሉበትን ሁኔታ ከክልል እስከ ዓለም አቀፍ ድረስ የተስተካከለ ግንኙነት ያላቸው እንዲሆኑ የሚሰራ መሆኑን ያብራራሉ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 7/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=30421
752595b3b465c2774ad5485baddb731b
719b94f542105ed071d70ab0e6fcd2a1
የበዓል ሰሞን ስብሰባዎች!
መዝናኛ
አበባ አየሁ ወይ፤ ለምለም… አበባ አየሁ ወይ ለምለም….ባልንጀሮቼ፤ ለምለም ግቡ በተራ …” ጠዋት ቀድሜ የሰማሁት የአዲስ ዓመት መዳረሻ ብስራት መንገሪያ የልጃገረዶች ጨዋታ ነው ። እርግጥ የዘመኑን ያህል በለውጤ ላይ ባላምን ደስ ብሎኛል። አዲስ ዓመት እንደኛ የሚደምቅለት ወይም የሚደምቅበት አለ? ግን አይመስለኝም፤ ተፈጥሮ ሁላ አበባ አፍክታ፤ የሰማዩ ደመና ሁሉ ተገፍፎ፤ ብርሃኑ ሲገልጥ አዲስነት በተፈጥሮም ላይ ሲነግስ እኮ ነው ዘመናችንን የምንለውጠው፡፡ ይህ ከተፈጥሮ ጋር በጋራ የምንለውጠው አዲስነት አያስደስትም? በጣም እንጂ! “አዲስን ዘመን በአዲስ መንፈስ መጀመር ጥሩ ነው፤” ሲሉ ደጋግሜ ሰምቻለሁ ። ደስ ሲል! ያ ለውጥም በአዲስነት ላይ መገኘት ትልቅ ነው ። አዲስነት ተሰማኝ! ለዚያውም በማለዳ ስንት መርዶ በሚነገርበት ሀገር ላይ የአዲስ ዓመት ብስራት፤ አዲስ ዘመን ነጋ ዜማ መስማት መታደል አይደል? አዲስ አበባ የበዓል ሰሞን ሩጫዋ ሰርገኛ ጠርታ ደጅ ላይ ያስቆመች፤ የምታበላው ያለሰናዳች ሙሽራ ያስመስላታል ። የበዓል ሰሞንማ ባልዋን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየች ሙሽራ ያህል ጭንቀቷ ይበረታል ። የበዓል ድባቡ ከትርምስ ጋር የተደበላለቀ ሁነት፤ ደስም ጭንቅም ያሰኛል ። አውዳመት የኛን ያህል የሚደምቅለት አለ ግን? በዓሉን ለማክበር የምናሰናዳው ነገር መብዛቱ የምነከውነው ተግባር ማየሉ አንድ ቀን ብቻ አክብረነው የሚያልፍ እኮ አይመስለም ። እኔ ምለው? ይሄ ሁሉ የበዛ ክብረ ባዓላችን ድምቅምቅ አድርገን እያከበርን ምግብ በየአይነቱ፤ የሚጠጣ በየወንጪቱ፤ አቅርበን እየላፍን…፤ እያሻመድን የኑሮ መወደድ ሳያነቃንቀን፤ የጊዜ መቀየር ሳይለውጠን፤ የቀጠልነው በምን ይሆን? ኑሮ ተወደደ፤ ረከሰ፤ ተሰቀለ፤ ተዘፈዘፈ፤ ዓመት በዓል ዓመት በዓል ነው። ሁላችንም ዘንድ ከየትም ተጠረቃቅሞ ቤት ይሞላል ። በእኩልነት ሁሉም በጋራ ይስቃል፤ በአብሮነት ጨዋታው ይደራል ። እንደምናከብራቸው በዓላት ብዛት፤ እንደምንደግሰው ድግስ ስፋት አዘውትረን ችግር የምናወራ፤ ድሎት የራቀን አንመስልም እኮ! ውዶቼ፤ ትናንት ቤታችሁን የዋላችሁበትን አስቡት እስኪ? ከኑሮና አኗኗራችን በላቀ፤ ከምግብና አመጋገባችን በተለየ የአውዳመት ድግሳችን የተለየ ነው ። እንዲያው በበረከቱ ቤታችንን እየሞላው እንጂ ተማርረን የምንገልፀው አጥተን ነጣን የበዓል ቀን ላይ በልተን ወዛን ይለወጣል ። ሰው ግን ከየት ነው ይሄን ብር የሚመጣው፤ አውዳመት እየጠበቀ የሚረጨው? የሆነ ያልታወቀማ ምንጭ አለ ። ግድ የላችሁም ውዶቼ፤ ሰዎች ከገቢያቸው በላይ ሲያወጡ ካላቸው በላይ ሲነጩ መጠርጠር ጥሩ ነው ። በዓመት በዓል ላይ የሚፈልቅ፤ አውዳመት ላይ የሚፍለቀለቅ አንድ ያለታወቀማ ምንጭ አለ መሰለኝ ። የሰዎች ብር ማግኛ መንገድ የተለያየ፤ የገቢ ምንጫቸው ለየቅል ቢሆንም ሰሞኑን በአንድ አጋጣሚ ከስራ ባልደረባዬ የሰማሁት የበዓል ሰሞን ስብሰባዎች ገጠመኝ ግን ገርሞኛል ። በዓላት በደረሱ ጊዜ የስብሰባዎችን መብዛት ዋነኛ ምክንያት እንዳጤነው አደረገኝ። እኔ ምለው በዓውዳመት ሰሞን ስብሰባ የሚበዛው ለምን እንደሆነ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? ጉዳዩ ወዲህ ነው ወገኖች፤ ግርግሩን ተጠቅሞ ኪስ ለመሙላት፤ በዓልን አስታኮ ትርፍ ለመብላት ነው። የበዓልን ግርግርና አውዳመት በመጣ ቁጥር የሚዘጋጁ ስብሰባዎች የዛሬው ትዝብት ማጠንጠኛዬ ሆኗል ። የዓውዳመት ሰሞን፤ በተለይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በስብሰባ ይጨናነቃሉ ። በዓል ሲቃረብ ስልጠና መስጠት፤ ሰበብ ፈጥሮ መሰባሰብ ተለምዷል። ሰብሳቢውም ተሰብሳቢውም በስብሰባው አላማ ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ከስብሰባው የሚገኘው ብር ወይም አበል ላይ ያተኩራሉ ። በአንድ ጊዜ ሁለት ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ከሁለቱም ቱርፋት ለመቋደስ የማይወጡት ዳገት የማይወርዱት ቁልቁለት የለም። ለወጌ መነሻ የሆነኝ ባልደረባዬ በስራ አጋጣሚ በታደመባቸው ስብሰባዎች የገጠመውን ሲነግረኝ፤ የታዘበውን ሲያወጋኝ የተገረምኩበት ጉዳይ ለዚህ ጽሁፌ መነሻ መሆኑን ነግሬያችሁ የለ ። አግራሞቴ እንዲጋባባችሁ የራሴን ገጠመኝ አክዬ ገጠመኙን ላውጋችሁማ ። ስበሰባ የሚበዛበት የበዓል ሰሞን ላይ የተከሰተ ነው ጉዳዩ፤ ለበዓል መዋያ ይሆን ዘንድ አበል ተበጅቶ መርሀ ግብር ተነድፎ የሁለት ቀን ስብሰባ አራት ወይም አምስት ቀን ተብሎ የሚከፈልበት ሰሞን፤ አውዳመትን ለመውጣት የሚያስችል ገቢ ማግኛ ይሆን ዘንድ የታሰበ ስብሰባ፤ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኝ መስሪያ ቤቶች በክፍለ ሀገር አበል ለመክፈል ሲያስቡ ስብሰባ አብዝተው የሚያደርጉበት ከተማ ላይ ነው የባልደረባዬ ትዝብት መነሻ ቦታው፤ አንድ ተሰብሳቢ በሁኔታው የባልደረባዬን ትኩረት ይስብና ባልደረባዬ ሰውዬውን መከታተል ይጀምራል። ሰውዬው በተደጋጋሚ ከስብሰባው ወጥቶ ይገባል፤ በመሀል እየጠፋ አመሻሽ ላይ ይመጣል ። ይሄን የተመለከተው ወዳጄ “የት እየቆየህ ነው ምትመጣው?” ብሎ በገደምዳሜ ይጠይቀዋል ። ያ ወጥቶ ይገባ የነበረው፤ ጠፍቶ አምሽቶ ይከሰት የነበረው ሰው ምላሹ አስገራሚ ነበር ። ሌላ ቦታም ስብሰባ እየተካፈለ መሆኑንና በአንዴ ሁለት ስብሰባ ላይ እየታደመ መሆኑ አበል ሁለቱም ቦታ እንዳያመልጠው ለፊርማ እየተመላለሰ መሆኑን ነገረው ። ጉዳዩ አግራሞትን አጭሮበት ነበርና ከትውስታ ማህደሩ በጫወታችን መሀል አካፈለኝ ። የሰውዬው ሁሉ አይቅርብኝ ባይነት አያስገርምም? ባልደረባዬ የስብሰባ ገጠመኙ ሌላ ተመሳሳይ ሁለት ስበሰባ ተካፋይ ሰው ጋርም አገናኝቶት አልፏል። ይሄኛው ሰውዬ ግን አትራፊ ሳይሆን አጉዳይም ነበር ። ከአንደኛው ስብሰባ ወደሌላው እየተመላለሰ የትራንስፖርት ወጪ እያወጣ ለቀናት ሁለቱም ቦታ ‘አለው’ ሲል ከርሞ ስብሰባው አበል አልባ መሆኑ ተነግሮት አተርፍ ባይ አጉዳይ አድርጎታል። ሃላፊዎችስ ቢሆኑ የተቋማቸውን አደራ፤ የህዝብን ተልዕኮ ለመፈፀም ተቀምጠው የዓመት በዓል ኪስ መሙያ፤ የአውዳመት ወጪ መሸፈኛ የሚሆን አበል መፍቀዳቸው ለምን ይሆን? ይህቺ ሀገር ሌላ አሳቢ፤ ሌላ ተቆርቋሪ ያላት ይመስል ክፍተቷን መሙያ ደጅ ደጁን እያየች ከኪስዋ የምናጎድለው ለምንድን ነው? እንደ ዜጋ እንቆርቆር! የራሳችንን ለመሙላት ስንሮጥ ከሀገር ላይ ማጉደላችን ምን የሚሉት በደል ነው? አዲስ ዘመን ጀምረናል ። እኛ አዲስ ባንሆን እንኳን በተዘጋጀልን አዲስነት ውስጥ የምናልፍ፤ ባናቅድ እንኳን ለአዲሱ ዘመን በታቀደ የምንምቧች፤ ንቁዎች መሆን ግድ ይለናል ። ለሀገር ማሰብ፤ ለወገን መቆርቆር የተጣለብንን አደራ ለመወጣት የምንጥር አዲስ ሰው መሆን ያሻናል ። ተገቢ ያልሆነ አሮጌነትን ከውስጣችን አውጥተን የሚገባንን መልካምነት ወደኛ ማስረጫ አዲስ ጅማሮ፤ አዲስ ሀሳብ፤ አዲስ ዘመን! ውዶቼ፤ አዲስ ለመሆን ተዘጋጅታችሁ፤ አዳዲስ ውጥን ወጥናችሁ በአዲስ መንፈስ አዲሱን ዓመት ከጀመርን ይሄው ሁለተኛ ቀን ላይ ተገኝተናል ። አዲሱ ዓመት ለማንም አይገባም ለኛ ማድረግ በአዲስነቱ የምንታደስበት ሊሆን ይገባል ። ዘመኑን የኛ ለማድረግ ዘመኑ ላይ የሚመጥን መልካም ነገር ማቅረብ ተገቢ ነው ። በነገራችን ላይ፤ የዘመኑ ሳይሆን የኛ መቀየር የኛ መለወጥ ነው ለሀገርም ለኛም የሚጠቅመው ። ወቅቱማ ዑደት ነው። ዝነፍ ሳይል የሚለዋወጥ፤ በሁሉም ስብዕናቸው ውስጥ ለውጥ ሳይኖርም የሚሄድ የሚያልፍ ። የኛ ለውጥ ነው ወሳኝ፤ በውስጣችን የምንፈጥረው፤ በልካችን የምንሰፋው አዲስ ልብስ አዲስ የሆነ መልካም ነገርን የሚያለብሰን፤ በታደሰው ዘመን እኛ አሮጌ ሆነን ከተገኘን አዲስነታችን ግን ምኑ ላይ ነው? አዲስ መሆናችን ግን የቱ ጋር ነው? ዘመኑ ሲቀየር የኛን ለውጥ በዘመኑ ካልተለካ፤ ጊዜው ሲለወጥ የኛን ለውጥ ካላሳየ የወቅት መቀያየር የጊዜ መለዋወጥ ምንም እኮ ነው ። የዘመኑ በጎዎች፤ የወቅቱ ጀግኖች፤ የጊዜው ሰላማዊ ተጓዦች ሆነን ያረጀውን ሃሳብ ወዲያ ጥለን አዲስ ዘመንን የሚመጥን አዲስነት ተላብሰን እንጀምረው፤ ዛሬ ላይ የተገኘን የዘመኑ መታደስም ሆነ ማርጀት ምክንያት እኛው ነንና ነገ በሚታየው የታሪክ ማህደር ውስጥ ዘመን አዳሾች ሆነን እንጠቀስ ዘንድ የዘመኑን ያህል በአዲስ እና ጠቃሚ ለሀገር ገንቢ በሆነ ሀሳብ እራሳችንን እናድስ ። አበቃሁ፤ ቸር ይግጠመን!አዲስ ዘመን መስከረም 2/2011ተገኝ ብሩ
https://www.press.et/Ama/?p=17890
959a0341d23c69b534f21b85f895d85a
ab67a66be92828512f05c5478433fd3a
መልሶ ልማት እንዲህም ይካሄዳል
መዝናኛ
በሀገራችን እየተካሄደ ያለውን መልሶ ልማት ስንመለከት የግል ቤት ላለው ቦታ እና ቤት የመስሪያ ገንዘብ ፤በአስቸኳይ እንዲነሱ ሲፈለግ ደግሞ ለተወሰነ ጊዜ የሚሆን የቤት መከራያ ገንዘብም ይሰጣል።የኪራይ ቤት ውስጥ የሚገኙት ደግሞ ሌላ የኪራይ ቤት ወይም በጋራ መኖሪያ ቤት መንደር ቅድሚያ ክፍያ እንዲፈጽሙ ተደርጎ ቀሪውን በሂደት በሚከፍሉበት ሁኔታ ቤት ይሰጣቸዋል።እስከ አሁን ያለው አካሄድ ይሄው ነው። መልሶ ልማት በኛ ሀገር ብቻ የሚካሄድ ይመስለኝ ነበር። ለካስ ባደጉት ሀገሮችም መልሶ ልማቱ ይሰራበታል።የእነዚህ ሀገሮች አንዳንድ ከተሞች በተደጋጋሚ መልሶ ልማት እንዳካሄዱም የከተማ ልማት ባለሙያዎች ይገልጻሉ።ልዩነት የሚኖረው ልማቱ ሲካሄድ ለተነሺዎች አስፈላጊው ካሳ መስጠቱ ፣መጠለያ ማቅረቡ ላይ ሊሆን ይችላል ።ከዚህ በተረፈ ካሳ ይከፈላል።የመስሪያ ቦታ ይሰጣል። መልሶ ልማት ባደጉት ሀገሮችም ይካሄዳል። የጣልያኗ ሞሊይስ ግዛት አንድ ከተማ መልሶ ልማት ለማካሄድ ማቀዷን በቅርቡ የወጣ የዩፒአይ መረጃ ያመለክታል።ከተማዋ 106 መንደሮች ያሏት ስትሆን ፣ የሁለት ሺ ሰዎች መኖሪያም ናት። ይህችን ከተማ  እንደገና ለመገንባት ሲታሰብም ነዋሪዎቹ የት ሄደው ነው ልማቱ የሚካሄደው የሚለው በሚገባ መላ ተፈልጎለታል። ነዋሪዎቹ ለቤት ኪራይ የሚሆን ብር በየወሩ እየተከፈላቸው ለንግድ ሥራ የሚሆን ገንዘብ ተሰጥቷቸው በጣም ብዙ ሰው በሚኖርባቸው አካባቢዎች በመሄድ የንግድ ሥራ እንዲሰሩ ነው የሚፈለገው። በፈቃደኝነት ለሚነሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ይህ የተመቻቸው።ለእነዚህ ተነሺዎች የንግድ እንቅስቃሴ ማካሄጃ ከ27 ሺ ዶላር በላይ እንደሚሰጥ የከተማዋ ባለስልጣናት በቅርቡ ይፋ አድርገዋል። ይህ ብቻም አይደለም ይህን የከተማዋን ራእይ ለማሳካት በፈቃደኝነት ለሚነሱ ነዋሪዎች በወር 770 ዶላር ለሦስት ዓመት ለመስጠትም ተወስኗል ። የመልሶ ልማቱን ሀሳብ ያመነጩት የአካባቢው አማካሪ አንቶኒዮ ቴዴስቺ ‹‹ የከተማዬ ህዳሴ እውን እንዲሆን ፍላጎቱ አለኝ፤የተጎሳቆሉት መንደሮች ታምር የሚታይባቸው እንዲሆኑ እፈልጋለሁ››ሲሉ ተናግረዋል።ይህንንም እውን በማደረግ መሰረታችንን ለመጠበቅ እንሰራለን ሲሉም ለሲኤን ኤን መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል። አማካሪው በመልሶ ማልማቱ በመነሳት ሌላ አካባቢ የሚሄዱ ነዋሪዎችን የመመዝገቡ ሥራ በመጪው መስከረም 16 እንደሚጀመር ጠቅሰው፣ በቅድሚያም ልጆች ያሏቸው ወጣቶት ባለትዳሮች በተፈጠረው እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚደረግም ተጠቁሟል። የመልሶ ልማቱ ግብ በመንደሯ ላይ አዲስ አየር እንዲነፍስ ማድረግና የገጠሩን ኢኮኖሚ ማነቃቃት ነው ያሉት አማካሪው ፣ወደ አካባቢው የሚመጡ ሁሉ በፈለጉት መስክ ኢንቨስት በማድረግ የመንደሯ የፋይናንስ የገቢ ምንጭ እንደሚሆኑም ተናግረዋል።ሆቴሎች ሬስቶራንቶች ቡና ቤቶች መክፈት ፣አነስተኛ የከተማ ግብርና ማካሄድ ፣የልብስ ቤቶችንና የጌጣጌጥ መደብሮችን ፣ቤተመጻህፍት ሱቆችን መክፈት እንደሚችሉም ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን መስከረም 6 / 2012  ዘካርያስ
https://www.press.et/Ama/?p=18139
61f74052e7e32095b1bf9f1e04297c2c
16afee1fe8a5999fb9695d091aca4876
መንታ ልጆቿን ለእዳ መክፈያ እና ሞባይል መግዣ
መዝናኛ
በሀገራችን ወልዶ መሳም ብዙ ትርጉም አለው። ልጅ ሲወለድ ያለው ደስታም ከዚህ ሁሉ የመነጨ ነው።ልጅ መውለድ ዘር መቀጠሉን ማረጋገጥ ከመሆኑም በተጨማሪ ትዳርን ለማጽናት ወሳኝ እንደሆነም ይገለጻል። እናት የምትከበረውም አንድም ሕይወት በመስጠቷ ነው። እናቶችም ልጆቻቸውን በማጥባት እና የተለያዩ እንክብካቤዎችን በማድረግ ለቁምነገር ያበቃሉ። ከልጅ በላይ ምንም ነገር እንደሌለም በማመን ብዙ ጥቅሞቻቸውን እስከ ማጣት ይደርሳሉ። ሰሞኑን ከወደ ቻይና የወጣ መረጃ እንዳመለከ ተው ግን የልጅ ጉዳይ ብዙም ቁብ ያልሰጣት አንዲት እናት መንታ ልጆቿን መሳም ፣አሳድጎ ለቁም ነገር ማብቃት አልፈለገችም። ልጆቿን ስትል መጎዳትም  አልፈለገችም። ከዚህ ሁሉ ይልቅ የወለደቻቸውን መንታ እምቦቀቅላዎች በ65ሺ የን ማለትም በ9ሺ 100 ዶላር ትሸጣቸዋለች። ይህን በማድረጓም ተደርሶባት በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውላለች። ስሟ ያልተጠቀሰው ይህች ቻይናዊት መንታ ልጆቿን የሸጠችው እንደተራራ እየወለደና እየተከመረ ያለውን ዕዳዋን ለመክፈል እንዲሁም አዲስ ዘመናዊ የኪስ ስልክ ለመግዛት አስባ ነው። ኒኝቦ ኢኒንግ ኒውስ የተባለው የቻይና ጋዜጣ ዕድሜዎቿ በ20ዎቹ እድሜ ውስጥ የምትገኘው ይህች እናት መንትያ ህጸናቱን የሸጠቻቸው የዛሬ ዓመት ነው።ለመሸጥ ስታስማም የተጠቀመችባቸው ምክንያት በችልተኛነት መጠቃቷንና በዕዳ ውስጥ መዘፈቋን ነው ብሏል። በቅፅል ስሟ ማ የምትባለው ይህቺ ልበደንዳና እናት እንደተናገረችው ቤተሰቦቿ በቅድመ ጋብቻ ከተከሰተው እርግዝና ጀምሮ ሲናደዱና ሲንገበገቡ ቆይተዋል። በዚህ የተነሳም እርሷን ለመርዳትና ሕጻናቱን ለማሳደግ አልፈቀዱም። ዉ በመባል ብቻ የሚታወቀው የልጆቹ አባት ከህጻናቱ ጋር ምንም ነገር ማድረግ እንደማይፈልግ ግልፅ አድርጎላታል። የመንትያዎቹ እናት የአንድ ወር ዕድሜ ላላቸው መንትያ ልጆቿ ገዢዎችን ማግኘት እንዳልተቸገረች ገልጻለች። ፖሊስ ይህን አስደንጋጭ የጨቅላ ህጻናት ሽያጭ መረዳት የቻለው አንድ ተመሳሳይ አስደንጋጭ የህጻናት የሽያጭ ሁኔታዎች ፍንጭ ማየቱንና ምርመራም እያደረገ መሆኑን ነው። ፖሊሶች ጥልቅ ምርመራ ካደረጉ በኋላ ህጻናቱ በአንሁይ ግዛት ለሁለት የተለያዩ ጥንዶች መሸጣቸውን ደርሰውበታል። አንደኛው በፉያንግ ሌላኛው ደግሞ በሱዦይ ማለት ነው ሲል ፓሊስ አብራርቷል። ምንም ዓይነት ነገር ማድረግ ያልፈለገው ድምፁን አጠፍቶ የነበረው የህጻናቶቹ አባት ተቆርቋሪ መስሎና ለምን በሚል የአንደኛውን ህጻን ድርሻ ለመካፈል ከተሸጡ በኋላ መታየቱ ተጠቁሟል። እናትየው ለፖሊስ እንደተናገረችው ሕጻናቱን የሸጠችበትን ገንዘብ ለልጆቿ አባትም አካፍላለች። የራሱዋን ድርሻ የባንክ ዕዳዋን ለመክፈል እና አዲስ ስማርትፎን ለመግዛት የተጠቀመችበት ሲሆን፣ ዉ ደግሞ የቁማር ዕዳዎቹን ይወጣበታል እየተባለ ነው። ፖሊስ ህጻናቱን ለማግኘት በአንሁይ በመረባረብ ላይ ሲሆን፣ ከማ ወላጆች ዘንድ ለማኖርም ፈልጓል። በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ኃላፊነት የማይሰማቸው ወላጆች ፅኑ የእስራት ጊዜ ይጠብቃቸዋል። በተያዙ ጊዜ ለፈጸሙት የማይገባ ተግባርም የሸጡት ገንዘብም እነሱም በቁጥጥር ሥር ይውላሉ።አዲስ ዘመን መስከረም 6 / 2012  በኃይለማርያም ወንድሙ
https://www.press.et/Ama/?p=18142
ba89894053fb4c407b57be06e93ab0a4
9cdb90956f388f1367e4ff8f0a428b05
ከ32 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ መሆናቸው ተነገረ
ሀገር አቀፍ ዜና
ከ32 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ መሆናቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደስ ገለጹ። በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና የጤና መድህን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የንቅናቄ ዘመቻ ውይይት እየተካሄደ ሲሆን፤ በውይይቱ የክልሉ ርዕሸ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ ሃላፊዎች እንዲሁም የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።በዚህ ወቅት ዶክተር ሊያ ባደረጉት ንግግር፤ የጤና መድህን ሥርዓት በገጠርና በከተሞች መደበኛ ባልሆነው የኢኮኖሚ ዘርፍ ተሠማርተው ለሚገኙ ዜጎች ተጠቃሚነትን የሚረጋግጥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል። የሁሉን አቀፍ የጤና መድህን ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች እንዳለው የገለጹት ዶክተር ሊያ አንደኛው ከኪስ በሚወጣ ወጪ ለሚታከሙ ዜጎች ለድህነት እንዳይጋለጡና አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል።ሁለተኛው የጤና ስርዓት ዘላቂ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው በማድረግ ትልቅ ሚና የሚጫወት ፕሮግራም ለማድረግ ያለመ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ በሀገር ደረጃ በ2003 ዓ.ም በ13 ወረዳዎች ተጀመረው የጤና መድህን ሥርዓት በ2012 ዓ.ም በ770 ወረዳዎች ተተግብሮ 32 ሚሊዮን ዜጎች የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ብለዋል። ከአባላቱም 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን በመግለጽ፤ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች በጤና መድህኑ ወጪ ተሸፍኖላቸው የህክምና ጤና አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል። የጤና መድህኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ አባላት በማፍራት ያለው አፈፃፀም 82 በመቶ ሲሆን በአማራ ክልል ያለው አፈፃፀም ደግሞ 92 መሆኑን ገልጸዋል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንደ ሀገርና ክልል ስርጭቱ እና ወደ ፅኑ ህሙማን የሚገቡ የኮሮና ቫይረስ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ የመጣ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም ሚኒስትሯ አሳስበዋል:: የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው፤ የተቀዛቀዘውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከል ስራና የጤና መድህን ተደራሽነት ለማረጋገጥ ከጥር 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም የአንድ ወር የንቅናቄ ዘመቻ በአማራ ክልል እንደሚካሄድ ተናግረዋል:: የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በኩላቸው፤ ህብረተሰቡ በሠላም ማስከበር ያደረገውን የተቀናጀ ስራ የኮሮና ቫይረስን በመከላከልና የጤና መድህን ተደራሽነትን በማረጋገጥ ሊደግመው እንደሚገባ ገልጸዋል::የክልሉ መንግስት ከዚህ በፊት ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ አሁንም የኮሮና ቫይረስን የመከላከል እና የጤና መድህን ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን የዘገበው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ነው::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38384
db3948ec9c59c9d5a14a783e078d10bf
9c060d395d407710878ce238484a1089
ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደሚወያዩ ተገለጸ
ስፖርት
በስፖርት ማህበራት ስራ አስፈጻሚዎች መካከል የሚፈጠረውን አለመግባባት ለመቅረፍ ውይይት እንደሚካሄድ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ። ማህበራቱ በአዋጅና በህግ የተቋቋሙ እንደመሆናቸው ህጉን አክብረው መስራት እንደሚገባቸውም ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የውይይት መድረክ እንደሚዘጋጅም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ጠቁሟል። የሁለቱ የስፖርት ተቋማት ስራ አስፈጻሚዎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ለወራት የቆየ ሲሆን፤ በዚሁ ምክንያት ስፖርቱ በተለያዩ አመለካከቶች ለመንቀሳቀስ መገደዱ ይታወቃል። የስፖርት ቤተሰቡን በሁለት ጎራ የከፈለው ይህ ጉዳይ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ስፖርቱን አደጋ ላይ እንደሚጥለው የብዙዎች ስጋት ነበር። በቀጣዩ ዓመት እንዲካሄድ ከተራዘመው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጋር ተያይዞ አትሌቶች ወደ ስልጠና መግባት አለባቸው በሚል ኦሊምፒክ ኮሚቴው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ቢጀምርም ፌዴሬሽኑ በበኩሉ ዓለም ባለችበት የኮሮና ቫይረስ ስጋት አትሌቶችን ወደ ሆቴል ማስገባት ትክክል አለመሆኑን ገልጿል። ይህንን ተከትሎም የተቋማቱ ስራ አስፈጻሚዎች በየፊናቸው በተለያዩ ጊዜያት ተቃራኒ ሃሳቦችን በመያዝ በመገናኛ ብዙሃን መግለጫዎችን ሲሰጡ ነበር። ተቃርኖው በዚሁ ካልተገታም ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችልም እሙን ነበር። ኦሊምፒኩ በዚህ ወቅት ይሰረዝ እንጂ፤ በየወቅቱ የሚፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት ኮሚሽኑ አመራሮቹን ለማነጋገር ቀጠሮ መያዙን ኮሚሽነሩ ኤልያስ ሽኩር ጠቁመዋል። ተመሳሳይ ድርሻ ባላቸው በስራ ሂደቶች ውስጥ ተቋማዊ፣ የአሰራር አሊያም በግለሰቦች መካከል አለመግባባቶች መፈጠራቸው አይቀሬ ነው። ነገር ግን ማህበራቱ በአዋጅና በህግ የተቋቋሙ እንደመሆቸው ኮሚሽኑ ያወጣውን ደንብ አክብረው መስራት አለባቸው። ስለዚህም የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት በንግግር እንዲፈታ ጥረት ይደረጋል ሲሉ ማረጋገጫቸውን ሰጥተዋል። ቀደም ሲል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር የነበሩት የስፖርት ምክትል ኮሚሽነሩ ዱቤ ጂሎ በበኩላቸው፤ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አለመግባባት ከሁለት ዓመታት በላይ የቆየ መሆኑን ያስታውሳሉ። ፌዴሬሽኑም ሆነ ኮሚቴው የራሱ የስራ ድርሻ አላቸው የሚሉት አቶ ዱቤ፤ በቀጣይ ሁለቱም አካላት በየስራ ድርሻቸው እንዲሰሩ እንደሚደረግም ገልጸዋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 19 / 2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=29342
27ba3a5b65e0da6e224050b66b28fb76
a348b134447584285cd94bb502efaeaa
ብራዚላዊው ጥበበኛ በሌላ የሕይወት ምዕራፍ
ስፖርት
  እኤአ በመጋቢት 1980 የእግር ኳስ ሀገር በሆነችው ብራዚል እግር ኳስ ወዳድ ከሆኑ ቤተሰቦች በደቡብ ብራዚል ፖርት ኤሌግሪ ተወለደ። ስሙ እንደሚያመለክተው ጠረፍ ላይ የምትገኝ አነስተኛ መንደር ነች። ይህቺ መንደር በጣም ድሃ ሕዝቦች የሚኖሩባት ናት። ቤቶቹ የተጎሳቆሉ እንዲሁም ኑሮም ከእጅ ወደ አፍ የሆነባት መንደር፡፡ በዚህች ጎስቋላ መንደር በአንድ ወቅት ወደ ዓለም እግር ኳስ ብቅ ብሎ በአጭር ጊዜ ቆይታው ዛሬም ድረስ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ልብ ውስጥ እየኖረ የሚገኘው ሮናልዲንሆ በጣም ታታሪ ቢሆንም በጣም ድሆች ከነበሩ ቤተሰቦች ተገኘ። እናቱ ዶና ሚግዌሊና ትባላለች። የቀድሞ ሥራዋ የሽያጭ ባለሙያ ስትሆን በሂደት ነርስ ለመሆን በቅታለች፡፡ አባቱ ጃኦ ለኩርዜሮ የሚጫወት ጎበዝ ኳስ ተጫዋች ነበር። ነገር ግን ዕድሜው ሲገፋና እንደድሮው ኳስ መምታት ሲያቅተው ጫማውን ሰቀለ። የድሮ ኳስ ተጫዋቾች እንዳሁኖቹ የደላቸው አልነበሩምና ደመወዛቸውም ትንሽ ስለነበር ኳስ ሲያቆሙ ኑሮን ለማሸነፍ ሌላ ሥራ መስራት ግድ ይላቸዋል። ስለዚህ ጃኦም ኳስ እንዳቆሙ ወዲያው እዚያው ወደብ ላይ የመርከብ ሠራተኛ ሆኑ። ሁለቱም በየፊናቸው እንዲህ ቢታገሉም ኑሮን ግን ማሸነፍ አልቻሉም፣ እንዲያውም እየመራቸው መጣ። ጃኦና ዶና 3 ልጆች ያላቸው ሲሆን የመጀመሪያው ልጅ ሮቤርቶ ይባላል፣ ኳስ ተጫዋችም ነበር። ሁለተኛዋ ዴሲ ትባላለች:: ሦስተኛው ልጃቸው በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችን ልናስታውሰው የወደድነው ፈገግታ ከፊቱ የማይለየው መልከ ጥፉው ነገር ግን ጥበበኛው «ትንሹ ሮናልዶ» ሮናልዲንሆ ጎቾ ነው።ሮናልዲንሆ ዕድሜው 8 ሲደርስ አባቱ ጃኦ በድንገተኛ የልብ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ሌላ ከባድ ፈተና ለድሆቹ የሮናልዲንሆ ቤተሰቦች። አሁን እቤቱን የማስተዳደር ብቸኛዋ ኃላፊነት ነርሷ እናቱ ላይ ወደቀ። ሆኖም ብዙም ሳይቆዩ በዚያው ዓመት የቤቱ ትልቅ ልጅ የሮናልዲንሆ ታላቅና ብቸኛው ወንድሙ የሆነው ሮቤርቶ ግሪሚዩ ከተባለው ክለብ ጋር ኮንትራት ተፈራረመ። በሱም ጥሩ የሚባል ገንዘብ አገኘ። ቤተሰቡም ከተጎሳቆለ ቤት ወጥተው ወደ ተሻለ ቤት ገቡ። በዚህ ጊዜ ነበር ትንሹ ሮናልዶ አዕምሮ ውስጥ አንድ ጥያቄ መመላለስ የጀመረው፡፡«ኳስ ገንዘብ የሚያስገኝ ከሆነ ለምን ኳስ ተጫዋች ሆኜ ቤተሰቤን አልረዳም?» የሚል። ጥበብ ልጇን ጠራች:: ሮናልዲንሆም ወደ ተፈጠረለት እግር ኳስ ኑሮን ለማሸነፍ በሚል ምክንያት ገባ። ትንሹ ሮናልዶ ኳስን በ8 ዓመቱ ኳስ ከሰፈሩ ልጆች ጋር በፖርት አሌግሪ የባህር ዳርቻ እንደፈለገ ያዛት ጀመር። ሜዳው ላይ በዕድሜው አነስተኛው ልጅ እሱ ነበር። ነገር ግን በችሎታው የሰውን ዓይን በቀላሉ መማረክ የሚችልና ብዙዎች ከዓይን ያውጣህ ይሉት ገቡ። እዚህም ሜዳ ላይ ነው ሮናልዲንሆ የሚለውን ስም ያገኘው። ዛሬ ላይ በመላው ዓለም መለያ መጠሪያው ይሁን እንጂ ብራዚላውያን «ሮናልዲንሆ» በሚለው ስም አያውቁትም ነበር። ትክክለኛው ሮናልዲንሆ ትልቁ ሮናልዶ ወይም «ኤልፌኖሜኖ» በሚለው ቅፅል የሚታወቀው ነው። ብራዚላውያን ስመ ረጃጅሞች ቢሆኑም አጠር አድርገው ስያሜ በመፍጠርና በማቆላመጥ ጣጣ አይወዱም። ባጭሩ መጥራት ይቀናቸዋል። የቀድሞ መሪያቸውን «ሉላ» ይሏቸዋል። ባለብዙ ጅራቱ የባህር እንሰሳ «ስኩዊድ» የሚል ትርጉም ይኑረው እንጂ ሉዊዝ ኢግናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ እያሉ ጊዜ ማባከን አይፈልጉም። ሮናልዶ ሉዊዝ ናዛሪዮ ደ ሊማ ከማለት ይልቅ «ሮናልዶ» የሚቀላቸውም ለዚህ ነው። ግን ሁለት ድንቅ ሮናልዶች በአንድ ዘመን ተገኙና ብራዚላውያን ግራ ገባቸው። ያ ታላቅ ግብ አዳኝ ‹ሮናልዲንሆ› ተብሎ በሚጠራበት አገር ሌላ ‹ሮናልዲንሆ› የተባለ አስገራሚ ተጫዋች በእግር ኳስ ኮከቦች መፍለቂያ አገር ብቅ አለ። ትርጓሜው ‹ትንሹ ሮናልድ› እንደማለት ነው። ኤልፌኖሜኖ ‹ትንሹ› መባሉ አብቅቶ በዝናም፣ በክብርም ሲያድግ ብራዚላውያን ወደ ‹ሮናልዶነት› አሳደጉት።ሮናልዲንሆ እስከ 13 ዓመቱ ከሰፈሩ በዘለለ ለትልልቅ ክለቦችም ሆነ ለታዳጊ መጫወት አልቻለም። ውሎው የባህርዳርቻ ነበር። በ13 ዓመቱ ግን አንድ ነገር ተከሰተ፣ የወንድሙ ክለብ የሆነው የግሪሚዩ መልማዮች ጎበዝ ተጫዋቾችን ሊመለምሉ የነ ሮናልዲንሆ ሰፈር ደረሱ። ለምልመላው ይረዳቸው ዘንድም ተጫዋቾችን ለሁለት ከፍለው ግጥሚያ እንዲያደርጉ አዘዙ። ክፍፍሉም ፍትሃዊ እንዲሆን በሰፈር አደረጉት። የላይኛው ሰፈር ልጆችና የታችኛው ሰፈር ልጆች። ጨዋታው ተጀመረ። ልክ እንደተጀመረ ሮናልዲንሆ ተከላካዮችን አተራምሶ አስደናቂ ጎል አስቆጠረ። ከደቂቃዎች በኋላም የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ሌላ ጎል ደገመ። ውጤቱም 23 ለ 0 ነበር። የሚገርመው 23ቱንም ጎሎች ያስቆጠረው አንድ ልጅ ነው። ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሬራ!!መልማዮቹ ወደ ካምፓቸው ሲመለሱ አንድ ሳቂታ ልጅ አስከትለው ተመለሱ። ሮናልዲንሆም ከወንድሙ ጋር አንድ ክለብ ውስጥ የመጫወት ዕድል አገኘ። ሮናልዲንሆ ለታዳጊዎቹ ሮቤርቶ ደግሞ ለዋናው ቡድን፡፡ ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ወንድሙ ሮቤርቶ በደረሰበት ጉዳት ከኳስ ተሰናበተ። ሮናልዲንሆ ወንድሙ ባጋጠመው ነገር ቢያዝንም ኳስ ከመጫወት ግን ለደቂቃም አልቦዘነም። በግሪሚዩ የእግር ኳስ ካምፕ ውስጥ ኳስን ጓደኛው አደረጋት። ቀኑን ሙሉ ውሎው ከኳስ ጋር ሆነ። ከጓደኞቹ ቀድሞ ልምምድ ቦታ መገኘት እንዲሁም ከሁሉም በኋላ መውጣት ባህሪው ሆነ።ይህ ታታሪነቱ ወደ ታላላቅ የዓለማችን ክለቦች አምርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ በእግር ኳሱ ዓለም እስከዛሬም የማይዘነጉ ተዓምሮችን መፍጠር ቢያስችለውም ዝናና ገንዘብ ይዞት የሚመጣውን ጣጣ እንዲቋቋም አላደረገውም፡፡ ውሎና አዳሩ በየጭፈራ ቤቱ ሆነ፡፡ አብዝቶ መዝናናት ከድህነት ሕይወት ያስመለጠውን ኳስ አስረሳው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥም ሆኖ ግን ዓለምን በእግር ኳስ ጥበቡ ማስደመም ለእሱ ቀላል ነበር፡፡ በታላቁ ኤልክላሲኮ ታሪክም ከማራዶና በኋላ በተቃራኒ ደጋፊዎች ሜዳ የተጨበጨበለት ተጫዋች እስከመሆን ደረሰ፡፡ በኳሱ ተዝናንቶበታል፣ ተመልካቹንም አዝናንቶበታል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ከአምስት ዓመታት በላይ እንዲዘልቅ አብዝቶ መዝናናቱ አልፈቀደለትም፡፡ ብዙዎች ጥበቡን ሳይጠግቡ የእግር ኳስ ሕይወቱ በአጭሩ ሊቀጭ ችሏል፡፡ ያም ሆኖ በትንሽ ዓመታት የሰራው ተዓምር አሁን ላይ በመጫወት ላይ የሚገኝ የትኛውም ተጫዋች ያላሳካውን ዓለም ዋንጫን፣ ባሎንዶርንና ቻምፒየንስ ሊግን ያሸነፈ ተጫዋች አድርጎታል፡፡ አሁን ላይ ግን የጎቾ ሕይወት በሌላ የታሪክ መፅሐፍ ውስጥ በአሳዛኝ ሁኔታ እየተገለፅ ይገኛል። በፓራጓይ ከተጭበረበረ የፓስፖርት ሰነድ ጋር በተያያዘ እስር ቤት ውስጥ ሆና 40ኛ ዓመቱን ባሳለፍነው ሳምንት እንዲያከብር አስገድዶታል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ምቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=29389
99dc3d3af789a79ba305a715bf1b2a2a
21899956b5d85efbc79462ca38c89e30
የዓለም ከዋክብት በቤታቸው ከትመው ልምምዳቸውን ቀጥለዋል
ስፖርት
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪመየር ሊግ አዲስ ውሳኔ ካላስተላለፈ በቀር በተያዘው ወር መጨረሻ ዳግም ወደ ውድድር ለመመለስ ማቀዱ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎም ማንቸስተር ዩናይትድ ከቀናት በኋላ ልምምድ ይጀምራል:: ታዲያ ተጫዋቾች ከአቋማቸው ላለመውረድ በቤታቸው ሆነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ማተኮራቸውን በተለያዩ ጊዜያት ለደጋፊዎቻቸው በሚያጋሩት ተንቀሳቃሽ ምስል ያስመለክታሉ፡፡ ይህ ሁኔታም ቀድሞ ለረጅም ሰዓታት አብረዋቸው ያሳልፉ ለነበሩትና አሁን ግን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች መልዕክት ለሚለዋወጡት አሰልጣኞች መልካም መሆኑን የቀያዮቹ አሰልጣኝ ኦሊጉነር ሶልሻየር ለኢቭኒንግ ስታንዳርድ ገልጸዋል፡፡ ተጫዋቾች ጤናቸውንና አቋማቸውን በመጠበቁ ሂደት ቤተሰቦቻቸውም እንዲያግዟቸው ጭምር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በርካታ ስፖርታዊ ክንዋኔዎች መታገዳቸውን ተከትሎ ስፖርተኞች ከቤታቸው እንዳይወጡ በመከልከላቸው በቤታቸው ሆነው በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲያሳልፉ አስገድዷቸዋል፡፡ በተንቀሳቃሽ ምስል ሁሉም ከገዳዩ ቫይረስ ራሱን እንዲጠብቅ መልእክት በማስተላለፍና ቫይረሱን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ድጋፍ ከማድረግ ባለፈም በቤታቸው ውስጥ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በምን መልኩ እንደሚሰሩ ለሌሎች በማስመልከት ላይም ይገኛሉ፡፡ ከተራዘሙ ውድድሮች መካከል አንዱ ኦሊምፒክ እንደመሆኑ በብሄራዊ ቡድን የተካተቱ ስፖርተኞችም ለአንድ ዓመት በምን መልኩ ብቃታቸውን ጠብቀው መቆየት እንደሚችሉ ልምዳቸውን እያካፈሉ ይገኛሉ፡፡ እንግሊዛዊቷ የሁለት ጊዜ የወርልድ ቴኳንዶ የዓለም ቻምፒዮናዋ ጃዴ ጆንስ ለኦሊምፒኩ በተሻለ ብቃት ለመመለስ በአንድ ዓመት መራዘሙን እንደ መልካም አጋጣሚ የምትመለከተው መሆኑን ትገልጻለች፡፡ ውድድሮች፣ የልምምድ አካዳሚዎች እንዲሁም ጂምናዚየሞች በዚህ ወቅት የተዘጉ ቢሆንም በቤት ውስጥ ልምምድ በማድረግ በስፖርቱ የሶስት ጊዜ ቻምፒዮን በመሆን ታሪክ ለመስራት እየተዘጋጀችም ትገኛለች፡፡ ከዚህም ባሻገር ወቅቱን እንደማገገሚያ ጊዜ በመውሰድ ያለመዘናጋት ልምምድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን እንደገለፀች ዘ ጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል፡፡ ሌላኛዋ ዋናተኛም በተመሳሳይ የራሷንና የሌሎችን ህይወት አደጋ ላይ ላለመጣል በቤቷ መሆንን አማራጭ የሌለው መሆኑን ታምናለች፡፡ የአምስት ጊዜ ኦሊምፒክ ቻምፒዮናዋ ኬት ሌዴኪ ከሲኤንኤን ጋር በነበራት ቆይታ ከዓመት በኋላ በሚካሄደው ኦሊምፒክ በደካማ አቋም ላለመሳተፍ ልምምዱን በጎረቤቶቿ መዋኛ ገንዳ ላይ አጠናክራ መቀጠሏን ገልጻለች፡፡ በእርግጥ ለ800 ሜትር ነጻ ዋና ቻምፒዮናዋ ልምምድ የምታደርግበት ገንዳ በቂ ባይሆንም ከአቋሟ ዝንፍ ብላ ላለመገኘት ስትል በልምምድ ላይ ትቆያለች፡፡ አንጋፋው ህንዳዊ የስፖርት ጋዜጠኛ ሮሂት ብሪጅናዝ በበኩላቸው ስፖርቱ ሲመለስ የተሻለ ነገር ማግኘት ይሻል ይላሉ፡፡ በቤት ውስጥ መቆየት አስፈላጊ በሆነበት በዚህ ወቅት ውድድሮች ባይኖሩም ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ውድድሮችን እንዲሁም ዘጋቢ ፊልሞችን በመመልከት እያሳለፉ መሆኑን ዘ ስቴር ታይምስ አስነብቧል፡፡ በኢትዮጵያም ከዚህ ቫይረስ መስፋትን ተከትሎ ክለቦች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላት እንዲሁም ብሄራዊ ቡድኖች ስፖርተኞቻቸውን እንዲበትኑ ተደርጓል:: ስፖርተኞቹ በቡላቸው ባላቸው አቅም ቫይረሱን ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ከደጋፊዎቻቸውና በተናጥል በመሆን ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ብቃታቸውን ጠብቀው ለመቆየት ምን እያደረጉ እንደሆነ መረዳት አልተቻለም፡፡ ስፖርተኛ ሁሌም ብቁና ዝግጁ ሆኖ መገኘት ያለበት እንደመሆኑ ከሌሎች ተሞክሮ በመውሰድ ይህንን በቤት ውስጥ የማሳለፍ ወቅት አቅማቸው በቻለ መጠን ዝግጅታቸውን ማከናወን ተገቢ መሆኑን የስፖርት ባለሙያዎችም ይመክራሉ፡፡ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ስፖርተኞች በየግላቸው ጊዜውን እንዲያሳልፉና መመሪያዎችን መከተል እንደሚገባቸው በመግለጫው ጠቁሟል፡፡ በሌላ በኩል በአትሌቲክስ ስፖርት የምትታወቀው ኢትዮጵያ አትሌቶች ከአበረታች መድሃኒት የጸዳ ጊዜ ማሳለፍ እንደሚገባቸው ተመልክቷል፡፡ ብሄራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት አትሌቶች ሳይዘናጉ ራሳቸውን እንዲጠብቁና በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የህግ ጥሰት በሚፈጽሙት ላይ የእርምት እርምጅ ይወሰዳል፡፡ ከዚህ ቀደም ይከናወን የነበረው የአትሌቶችን ናሙና የመውሰድና የመመርመር ሂደትም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አሳስቧል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 24/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=29639
1e333a1335059e26246ee3d6bd623ec7
8f680d87be747024b1d0fe7df4aa9015
የዊምብልደን ፈተና ከ2ኛው የዓለም ጦርነት እስከ ኮቪድ- 19
ስፖርት
እኤአ ታኅሣሥ 31 ቀን 2019 በቻይና ዉሃን ግዛት የኮሮና ቫይረስ እንደተከሰተ የዓለም የጤና ድርጅት ማስታወቁን ተከትሎ የቻይና መንግሥት በአፋጣኝ የቫይረሱን ስርጭት በአጭሩ ለመቅጨት እርምጃ ወደ መውሰድ ገብቶ ነበር። የቫይረሱን ስርጭት እንደተባለው በቀላሉ ለመቆጣጠር ሳይቻል ቀርቷል። አሁንም ቢሆን በዓለም አራቱም አቅጣጫዎች የተሰራጨውን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያስቻለ ፈውስ በዓለም ሳይንቲስቶች፣ የህክምና ጠቢባንም ይሁን በሀያላን አገራት አቅም ማምጣት አልተቻለም። ይህም የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ከመለወጥ አንስቶ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በርካታ አሉታዊ ተፅዕኖው እንዲያርፍ አድርጓል፡፡ የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ተጽእኖ እያስተናገደ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ የኮሮና ቫይረስ ለዓለም ራስ ምታት እንደሆነ በመቀጠሉ የስፖርቱ እንቅስቃሴ ዛሬም መፈተኑን ቀጥሏል። ስፖርታዊ ክንውኖች ለማድረግ አስቸጋሪ የመሆኑን ያህል በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ግምት ያለውን ኦሊምፒክ ጨዋታ እንዲራዘም ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ከሳምንት በፊት የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ በምንም አይነት ሁኔታ ይካሄዳል የሚል አቋም የነበረ ቢሆንም በተቃራኒው ውሳኔ እንዲተላለፍ የቫይረሱ ስርጭት አስገድዷል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስፖርትን መፈተኑን እንደሚቀጥልም የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል። የዓለም ህዝብ የጋራ ስጋት በሆነው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ በስፖርቱ ላይ እየደረሰ የሚገኘው ተጽእኖ እየጨመረ ይገኛል። በእንግሊዝ ዊምብልደን ላይ የሚደረገው እና የዓለማችንን ሥመጥር የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾች የሚያሳትፈው ታላቅ ውድድር እንዲሰረዝ ውሳኔ ተደርሷል። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እጅግ ተጠባቂ የሆነው ውድድር ለመሰረዙ የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሆኗል። የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የስፖርቱን ገጽታን ምንኛ እየጎዳው እንደሚገኝ ይህ ትልቅ ማሳያ መሆኑንም ዘገባው ያትታል፡፡ ዘጋርዲያን ደግሞ፤ በእንግሊዝ ዊምብልደን ላይ የሚደረገው እና የዓለማችንን ሥመጥር የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾችን የሚያሳትፈው ውድድር ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተሰረዘ ጽፏል። የዊምብልደን ቻምፒዮና የተቋረጠው እኤአ ከ1940 እስከ 1935 ድረስ የዘለቀው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት እንደነበር አስታውሷል። በዚህ ጦርነት መጨረሻ የአክሲስ ሃያላት ማለትም ጀርመን፣ ጣልያንና ጃፓን ተሸነፉ። እኤአ ታህሣሥ 2019 በተነሳው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የ134ኛ ዊምብልደን ቻምፒዮና ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ሊደርሰው እንደቻለ ዘገባው ተመልክቷል። የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ስፖርታዊ ክንውን ለማድረግ ፈታኝ እንደሆነው ሁሉ በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ የዓለምን ህዝብ እያሸበረ መሆኑን ተከትሎ ቻምፒዮናውን በተያዘለት መርሃ ግብር ለማካሄድ እንዳይቻል አድርጎታል።በዚሁ መሰረት ለሁለት ሳምንታት የሚካሄደው ይህ ስፖርታዊ ውድድር በሜዳ ቴኒስ ስፖርት አፍቃሪያንና ተወዳዳሪዎች ዘንድ ትልቅ ስፍራ ነበረው። ውድድሩ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው በሐምሌ ወር መጀመሪያ እንደነበር ታውቋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስከ ሐምሌ ወር መጨረሻ ድረስ አንድም የቴኒስ ጨዋታ እንዳይካሄድም ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ዘጋርዲያን 134ኛው የዊምብልደን ቴኒስ ቻምፒዮና መርሃ ግበር መሰረዙን ተከትሎ የዓለማችን እውቅ ተጫዋቾች ልብ እንደ ደማ ዘግቧል። የዊምብልደን የ8 ጊዜ ቻምፒዮናው ሮጀር ፌደረር ለዚህ ታላቅ መድረክ ባለፉት ሁለት ወራት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደረግ ነበር። ‹‹በቻምፒዮናው ላይ አዲስ ውጤት ለማስመዝገብ የነበረንን ተነሳሽነት ጨምሮ ሁሉም ነገር ተበላሽቷል» ሲል መከፋቱን ፌደረር ገልጿል። ሰሬና ዊሊያምስ በተመሳሳይ «የተሰማው ዜና እጅግ አስደንጋጭ ነው» ስትል የቻምፒዮናው መራዘም በስፖርቱ ቤተሰብ ላይ ሀዘን እንደፈጠረ ተናግራለች። ዶቼቬሌ በበኩሉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የስፖርቱን እንቅስቃሴና ገቢ ክፉኛ መጉዳቱን እንደቀጠለ ዘግቧል። ቶኪዮ-ጃፓን ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የዘንድሮው ኦሊምፒክ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ወደ መጪው ዓመት እንደተራዘመው ሁሉ የዊምብልደን ውድድር መራዘሙ ትልቅ ሀዘን የፈጠረ ውሳኔ መሆኑን አመልክቷል። የቫይረሱን ስርጭት ተከትሎ በየአገሩ የተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ተቋርጠዋል። ክለቦች፣ ተጫዋቾች፣ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የስፖርት ጋዜጠኞችና ሌሎችም ገቢ ማጣታቸውን እያስታወቁም ይገኛል። በዚህ ወቅት የዌምብልደን ቻምፒዮና መሰረዙ በስፖርቱ ላይ ተጨማሪ ድብርትን የሚፈጥር መሆኑን አመልክቷል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ተከትሎ በዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ አደጋ እየጣለ መምጣቱን ዛሬም መቀጠሉን ተከትሎ በስፖርቱ ዘርፍ ላይ የማይሻር ጠባሳ እንዲያርፍ ማድረጉን ዘግቧል። አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29701
f68ce4769a660a6e00ef047d60af66d3
7d1c97ca5be7fde3506bae56ae7df06b
የስፖርት አጋርነት በኮሮና ቫይረስ ውጊያ
ስፖርት
  በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አስኳል ሃሳብ ወዳጅነትና መተሳሰብ መሆኑ ይታወቃል። በታሪክ ገጾች እንደሰፈረውም በሰው ልጅ ታሪክ ባጋጠሙ በጎም ሆኑ መጥፎ ክስተቶች ስፖርት በአጋርነት ተሳትፏል። ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ሰላምንና አንድነትን የሚሰብኩ እንደመሆናቸው በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በመግባት ሚናቸውን ሲወጡም ኖረዋል። የወቅቱ የዓለም ራስ ምታት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘም ስፖርት መገኘት ባለበት ሁሉ አጋርነቱን በማስመስከር ላይ ይገኛል። የቫይረሱ ስጋትነት በዓለም አቀፉ የጤና ተቋም ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ፤ ውድድሮችን ከማቋረጥና ከመሰረዝ ባለፈ የስፖርቱ ተዋንያን በተናጥልም ሆነ በተቋማዊ ደረጃ አበርክቷቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። በእግር ኳስ ጠቢብነታቸው ዓለም የመሰከረላቸው ተጫዋቾችና ስመ ጥር አሰልጣኞችም፤ ለደጋፊዎቻቸው መልእክት ከማስተላለፍና ገንዘብ ከመለገስ ባሻገር ሆቴሎቻቸውን ለህክምና አገልግሎት እንዲውሉም ጭምር መስጠታቸው ይታወሳል። ክለቦችም በተመሳሳይ ስታዲየሞቻቸውን ቫይረሱን ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት እያዋሉት ይገኛሉ። የነጫጮቹ ስታዲየም ሳንቲያጎ በርናባው ለቫይረሱ የሚሆኑ መድሃኒቶችና የህክምና እቃዎች ማከማቻ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እየደረሰ እንደሚገኝ ይታወቃል። ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያንቀሳቅሱ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው ስፖርትም በዚሁ ምክንያት የገንዘብ ችግር በማስተናገድ ላይ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው ሙሉ ደሞዛቸውን መክፈል ከማይችሉበት ደረጃ ደርሰዋል። ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በጊዜያዊነት እስከ መጪው ወር መጨረሻ ድረስ መቋረጡ ይታወሳል። ክለቦች ከስታዲየም ገቢ እና ለሌሎችም የሚያገኙት ገቢ ላይ መቀነስ ተከትሎ ከፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ተጫዋቾቹ የደመወዛቸው ግማሽ እንዲከፈላቸው በመስማማት ስፖርት የመተሳሰብ መድረክ መሆኑን አረጋግጠዋል። ጥያቄውን በቅድሚያ ያቀረበው የሊጉ ክለብ የሆነው በርሚንግሃም ሲቲ ሲሆን፤ ለአራት ወራት በዚህ መልክ ደመወዝ እንደሚከፍል ማስታወቁን ዘጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል። ቅድሚያ አንዳንድ ተጫዋቾች ሃሳቡን ባይቀበሉም በሂደት በበጎ ፈቃደኝነት መስማማታቸውን አሳይተዋል። ክፍያው ከተጫዋቾችና የአሰልጣኞች ቡድን ባለፈ ያሉ የክለብ ሰራቶችን እንደማይመለከትም ታውቋል። ወደ ኢትዮጵያ መለስ ስንልም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 2 ሚሊዮን ብር ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንዲሁም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ መስጠቱ ከትናንት በስቲያ የተሰማ ዜና ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉም በግሏ ለጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ በድምሩ 400ሺ ብር መለገሷ ታውቋል። የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች ሙያ ማህበርም በበኩሉ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የ 50ሺ ብር ድጋፍ አድርገዋል። የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ምክትል ፕሬዚዳንት የገንዘብ እንዲሁም የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ለመጓጓዣ እንዲውል የተሽከርካሪ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ሶከር ኢትዮጵያ በድረ ገጹ አስነብቧል። ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=29350
3a339ddab883c846be3063016e19c43f
2feeef4d19d76b7f12172cbc68c24aae
ሥራ ላይ ያልዋሉ ማዘውተሪያ ስፍራዎች በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ ጥረት እየተደረገ ነው
ስፖርት
በኢትዮጵያ ከ27 ሺ በላይ የጥርጊያ ሜዳዎች እንዲሁም 12 ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች መኖራቸውን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በሥራ ላይ ያልዋሉ ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን በፍጥነት ወደ ሥራ ለማስገባትም ኮሚሽኑ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ አገሪቷ በስፖርት ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ ከምታከናውናቸው ሥራዎች መካከል አንዱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ነው፡፡ በቅርቡ የማዘውተሪያ ስፍራዎች የወጣውን የመተዳደሪያ ደንብ ተከትሎ በተደረገው ቆጠራ በዚህ ወቅት ከ27 ሺ በላይ የጥርጊያ ሜዳዎች በአገሪቷ የሚገኙ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል፡፡ ግንባታቸው ሙሉ ለሙሉ ያልተጠናቀቁና አንዳንዶቹም የስታንዳርድ ችግር ያለባቸው ቢሆኑም በአገሪቷ ውስጥ የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታው የተጀመረውን ብሄራዊ ስታዲየም ጨምሮ 12 ትልልቅ ስታዲየሞች ይገኛሉ፡፡ ይህም በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገነቡት አጠቃላይ ስታዲየሞች ቢደመሩ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የሚያሳይ መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ገልጸዋል፡፡ መንግሥት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከትንንሽ እስከ ትልልቅ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ እያወጣ ቢሆንም በተለያዩ አካባቢዎች በተገቢው ጊዜ ተጠናቀው ወደ ሥራ ያልገቡ አሉ፡፡ በመሆኑም በፍጥነት ወደ አገልግሎት ማስገባት አስፈላጊ በመሆኑ ተጀምረው በወቅቱ ያልተጠናቀቁና ጥራታቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች በፍጥነትና በጥራት እንዲጠናቀቁ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡ ፡ የካፍና የፊፋን መስፈርት የማያሟሉትም ለማሟላት ጥረት እያደረጉ፤ ክልሎችም ሃብት መድበው ርብርብ እያደረጉ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ በኮሚሽኑ ስር ያሉትንም በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ በሲኤምሲ አካባቢ 31ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በስፖርት ኮሚሽን የተያዘና ለውሃ ዋና እና ለቴኒስ ስፖርቶች ማዘውተሪያ የሚውል ቦታ አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም በቅርብ ቀን ጨረታ አውጥቶ የማጠር እንዲሁም በቀጣይ ዓመት ወደ ግንባታ ለመግባት ታቅዷል፡፡ በተመሳሳይ በዚያው በሲኤምሲ አካባቢ ካፍ የገነባው ትልቅ ማዕከል ቢኖርም ለብዙ ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጥ ቆይቷል፡፡ ማዕከሉ ስታንዳርዱን የጠበቀ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ብሄራዊ ቡድን ለማሳረፍ ችግሮች እንዳሉበት ይነሳል፡፡ በመሆኑም ማዕከል በቅርቡ ወደ ሥራ እንዲገባ ይደረጋል፡፡ ለረጅም ጊዜ በብቸኝነት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው አዲስ አበባ ስታዲየም ተጎድቷል፡፡ በመሆኑም በጀት ለሚመለከተው አካል በማቅረብ በክረምት ወቅት እድሳትና ጥገና በማድረግ በድጋሚ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ማድረግ እንዲችል ጥረት የሚደረግ መሆኑን ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው አሳውቀዋል፡፡ እንደ ማዘውተሪያ ስፍራዎች በአጠቃላይ ያለው ሁኔታ ሲታይ መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው ዘርፍ ነው፡፡ ከቀበሌ ጀምሮ ለስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሆኑ የተዘጋጁ ስፍራዎች በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ሊካሄድባቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ ስፖርቱ የልማቱ አንድ አካል፤ ህብረተሰቡም በስፖርታዊ እንቅስቃሴ መሳተፍ መብቱ በመሆኑ በሚመለከታቸው አካላት ያለው የመሬት አቅርቦት መልካም የሚባል ነው፡፡ በቅርቡ በተዘጋጀው ብሄራዊ የስፖርት ሪፎርም ላይ በጉልህ ከተመላከቱ ጉዳዮች መካከል አንዱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማት ነው፡፡ ከማዘውተሪያ ስፍራዎች ጋር በተያያዘ የስፖርት ፖሊሲው ሲቀረጽ እንደ ጉድለት የተያዘው አንዱ የመተዳደሪያ አዋጅ አለመኖሩ ነው፡፡ በቅርቡ ደንብ መውጣቱን ተከትሎም እነዚህ ሜዳዎች ‹ስታንዳርዱን ያሟሉ፣ የይዞታ ማረጋገጫ አላቸው፣ ጥራትና ተደራሽነታቸው ከፍላጎቶች አንጻር ተገቢ ነው፡፡ እንዲሁም ሥራ ላይ ውለው ማህበረሰቡ እየተገለገለባቸው ነው?› የሚለው ዋነኛው ጥያቄ ነው፡፡ በመሆኑም ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሊሰጡ የሚችሉ ሥራዎች በኮሚሽኑ በኩል በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ነው ኮሚሽነሩ የጠቆሙት፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 26/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=29780
4837c08cf8c005b29cbe0953d63c38d1
1b08f73865713f1e30bc30dc44f23f87
በኮሮና ቫይረስ ሕይወቱን ያጣው የስፖርት ጋዜጠኛ
ስፖርት
ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊየን በላይ የዓለምን ሕዝብ ያጠቃው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያልገባበት ቤት፣ ያላንኳኳው በር የለም። ከዓለም ታላላቅ አገራት መሪዎች እስከ ተራው ሕዝብ፣ ከዝነኛ ሰዎች እስከ ሕፃናትና አዛውንት ድረስ የዚህ አስከፊ ወረርሽኝ ተጠቂ ሆነዋል። ቫይረሱን ለመቋቋም በሽታን የመመከት ከፍተኛ አቅም ያላቸው የስፖርቱ ዓለም ሰዎች ሳይቀሩ በዚህ ወረርሽኝ ተለክፈዋል፣ ሕይወታቸውን ያጡም ጥቂት አይደሉም። የስፖርት ቤተሰቡ በቫይረሱ ስርጭት ስጋት የዓለም ታላላቅ የስፖርት መድረኮች ተቆልፈውበት ሁነኛ የመዝናኛ አማራጩን አጥቶ በየቤቱ ቆዝሟል። የስፖርቱ ዓለም ታላላቅ ከዋክብትም ረብጣ ገንዘብና ዝናቸው ከደጃፋቸው እንዲወጡ አቅም አልሆናቸውም። የኮሮና ቫይረስ በስፖርቱ ዓለምና በስፖርት ቤተሰቡ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ በሳምንቱ አጋማሽ ወደ ሃዘን የቀየረ አጋጣሚ ፈጥሯል። ፈረንሳዊው እውቅ የስፖርት ጋዜጠኛ ፔፕ ዲዉፍ ባለፈው ረቡዕ በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት ሴኔጋል መዲና ዳካር ውስጥ በስልሳ ስምንት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የመለየቱ ዜና ተሰምቷል። ይህም በመላው ሴኔጋልና አፍሪካ እንዲሁም ፈረንሳይ ትልቅ የስፖርቱ ዓለም አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። ትውልዱን በቻድ አቢቼ ያደረገው ዲዉፍ ከሴኔጋላዊ ቤተሰቦች የተገኘ ሲሆን የቻድ፣ ሴኔጋልና ፈረንሳይ ዜግነት አለው። ገና የአስራ ሰባት ዓመት ወጣት እያለ ለብቻው ወደ ፈረንሳይ ያቀናው ዲዉፍ የፖለቲካል ሳይንስ ካጠና በኋላ የፈረንሳዩ ክለብ ኦሊምፒክ ደ ማርሴል ጋዜጣ ላይ ፅሁፎችን በማበርከት ነበር ወደ ስፖርት ጋዜጠኝነት ሕይወት የገባው። ይህም በኋላ ላይ የተጫዋቾች ወኪል ሆኖ ለመስራቱ ትልቅ በር የከፈተለት አጋጣሚ እንደነበር የታሪኩ ፀሐፊዎች ይናገራሉ። ዲዉፍ የተጫዋቾች ወኪልነት ስራውን የጀመረው የቀድሞውን ፈረንሳዊ ተከላካይ ባሲል ቦሊ እንዲሁም ካሜሩናዊው ግብጠባቂ ጆሴፍ አንቶኒ ቤልን ወደ ማርሴል ክለብ በማምጣት ሲሆን በሂደት ዊሊያም ጋላስ፣ ሳሚር ናስሪና ሌሎችም እውቅ ተጫዋቾችን በደንበኝነት ይዞ ወኪል በመሆን አገልግሏል። በተለይም ኮትዲቯራዊው ኮከብ ዲዲየር ድሮግባ እኤአ ከ2003 እስከ 2004 በማርሴል ቆይታው ወቅት ወኪሉ በመሆን የተሳካ ጊዜ እንደነበረው ይጠቀሳል። ይህም በእርግር ኳስ ውስጥ የነበረው የነቃ ተሳትፎ እኤአ 2005 ላይ የማርሴል ክለብ ፕሬዚዳንት እስከ መሆን አድርሶታል። ዲዉፍ በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚሳተፍ ክለብ ፕሬዚዳንት ሲሆን በታሪክ የመጀመሪያው ጥቁር ሆኖ ይነሳል። ዲዉፍ የማርሴል ክለብ ፕሬዚዳንት ሆኖ ሲያገለግል ክለቡ በፈረንሳይ የመጀመሪያው ሊግ ሁለት ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ትልቅ ሚና ነበረው። እኤአ 2009 ላይም ዲዉፍ አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሾን ወደ ማርሴል በማምጣት ክለቡ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ አድርጓል። ይህም ክብር ክለቡ ከአስራ ስምንት ዓመታት በኋላ ያጣጣመው ሆኖ ተመዝግቧል። አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሾ ባለፈው የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ፈረንሳይ ከሃያ ዓመታት በኋላ ስታሸንፍ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ እንደነበሩ አይዘነጋም። ከዚህ ድል በኋላ ከክለቡ ፕሬዚዳንትነት የለቀቀው ዲዉፍ የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበርን መርቷል። እኤአ 2009 ላይ በፊፋ ጠቅላላ ጉባዔ ዙሪክ ላይ ተገኝቶ በፈረንሳይ እግር ኳስ ደረጃና በአጠቃላይ እግር ኳስ ውስጥ ስላለው ዘረኝነት ያደረገው ንግግር በታሪኩ ይጠቀስለታል። ዲዉፍ በአውሮፓ እግር ኳስ ውስጥ አሳሳቢ ስለሆነው የዘረኝነት ጉዳይ ጥቁሮች ሰለባ እንዳይሆኑ በጠንካራ ቃላት በዓለም ሕዝብ ፊት ቆሞ በመሟገት ይታወቃል። በስፖርት ጋዜጠኝነት ሕይወቱም ብዙዎችን በማንቃትና ጠንካራ ስራዎችን በማቅረብ የተጨበጨበለት መሆኑን በርካቶች ይመሰክሩለታል። በዚህ ወቅት ዓለምን እያስጨነቀ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ተይዞ የነበረው ዲዉፍ በቤተሰቦቹ አገር ሴኔጋል እርዳታ እየተደረገለት የቆየ ሲሆን ለተሻለ ሕክምና ወደ ፈረንሳይ ለማቅናት በተዘጋጀበት ወቅት ሕይወቱ ማለፉ ተዘግቧል። ይህም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በሴኔጋል የተመዘገበ የመጀመሪያው የሞት ዜና ሆኗል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ የእግር ኳሱ ዓለም ከዋክብቶች በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሃዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። ዲዉፍ ድንቅ ታሪክ የሰራለት ማርሴል ክለብ በትዊተር ገፁ ‹‹ፔፕ ሁል ጊዜም በማርሴል ልብ ውስጥ ይኖራል፣ የማርሴል የምን ጊዜም ታሪካዊ ሰው ነው›› በማለት ሃዘኑን ገልጿል። የፕሮፌሽል ተጫዋቾች ማህበር በበኩሉ ‹‹ጋዜጠኛ፣ወኪልና የቀድሞ የማርሴል ፕሬዚዳንት ፔፕ ዲዉፍ ሕይወቱን ሙሉ እግር ኳስን ሲያገለግል የኖረ ሰው ነው›› በማለት አስታውሶ ሃዘኑን ገልጿል። ፈረንሳዊው የቀድሞ የሊቨርፑል አጥቂ ጅብሪል ሲሴ ዲዉፍ የማርሴል ፕሬዚዳንት እያለ ለክለቡ ተጫውቷል።‹‹የፈረንሳይ እግር ኳስ ዛሬ ድንቅ ሰው አጥቷል›› በማለት ሲሴ የተሰማውን ሃዘን በትዊተር ገፁ አስፍሯል። ሌላኛው ፈረንሳዊ የማንቸስተር ሲቲ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ቤንጃሚን ሜንዲ በበኩሉ ‹‹ድንቅ የክለብ ፕሬዚዳንት ነው፣ ከዚያም በላይ ሁል ጊዜ ለማርሴል እሴቶች የሚጨነቅ ትልቅ ሰው ነው›› በማለት ተናግሯል። አዲስ ዘመን መጋቢት 27/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=29803
9252ec3417bd6ce4edef640bdd44aaef
a6817872051fa117ab913c4d9ad9c3f2
ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከወዲሁ ፈተናዎችን መጋፈጥ ጀምሯል
ስፖርት
ኦ ሊምፒክ ከጤና ስጋት ጋር የተያያዘ ባይሆንም በተለያዩ ጊዜዎች የመሰረዝና የቦታ ለውጥ ሲደረግበት ታይቷል፡፡ እኤአ የ1916 የበጋ ኦሊምፒክ በጀርመን በርሊን ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት በአንደኛ የዓለም ጦርነት ሳቢያ ተሰርዟል:: በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም የ1940 የክረምት ኦሊምፒክና የ1944 የበጋ ኦሊምፒክ ውድድሮች የመሰረዝ እድል ገጥሟቸዋል:: እኤአ የ1976 የክረምት ኦሊምፒክም በዴንቨር ኮሎራዶ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የኮሎራዶ ግዛት ሕዝብ ለውድድሩ የሚወጣውን ወጪ በመቃወሙ ውድድሩ የቦታ ለውጥ ተደርጎበት በአውስትራሊያ ኢንስብረክ ለመካሄድ ተገዷል፡፡ ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ በወቅቱ እንደዘገበው የኮሎራዶው ኦሊምፒክ የቦታ ለውጥ እንዲደረግበት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ውድድሩ ከመካሄዱ ከሦስት ዓመታት አስቀድሞ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ኦሊምፒክ በታሪክ ተራዝሞ የሚያውቅበት አጋጣሚ አልነበረም:: ዓለም በአሁኑ ወቅት እየተሸበረችበት በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ግን የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለአሥራ ስድስት ወራት ሲራዘም በታሪከ የመጀመሪያው ለመሆን በቅቷል፡፡ ይህም ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ለውድድሩ አዘጋጆች አዲስ ተሞክሮ ብቻ ሳይሆን አዲስ ፈተና ይዞ መምጣቱ አልቀረም፡፡ ይህን አዲስ ፈተናም ለመጋፈጥና ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ከወዲሁ ለማስተካከል ዓለም አቀፍ ኮሚቴውና አዘጋጆቹ ከወዲሁ ሌት ከቀን እየሰሩ እንደሚገኙ ሰሞኑን ገልፀዋል፡፡ የኦሊምፒክ ስፖርቶች ዳይሬክተሩ ክሪስቶፍ ዱቢ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ‹‹ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ውስብስብ ብቻ ሳይሆን አዲስ ፈተና ገጥሞናል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከጃፓን መንግሥት ጋር በመሆን ይህን ፈተና ለመወጣትና አሁን ዝግጁ የሆኑ ነገሮችን ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ተግባራዊ እንዲሆኑ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ ይህም ማለት ኦሊምፒኩ ከመራዘሙ አስቀድሞ በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ ዝግጁ የነበሩ የኦሊምፒክ መንደሮችን፣አርባ አንድ ዋነኛየውድድር ቦታዎች፣ ከአርባ ሺ በላይ የሆቴል ክፍሎች፣ከሁለት ሺ በላይ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን እንዲሁም አገልግሎትና በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ቁሶችን ለማቅረብ የተደረጉ ውሎችን መልክ ማስያዝና ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ተግባራዊ የሚሆኑበትን አቅጣጫ የማስቀመጥና መልክ የማስያዝ ሥራዎች ከወዲሁ እየተሰሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የዓለምን እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሽባ ያደረገው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ነገሮችን መልክ ለማስያዝ በሚያደርገው እንቅስቃሴ አሁንም ፈተና እየሆነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አልሸሸጉም፡፡ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከተጠቀሱት ፈተናዎች በተጨማሪ ሌሎችም እንቅፋቶች ይኖሩበታል:: ከውድድር ጋር በተያያዘ ለኦሊምፒኩ አስፈላጊውን መስፈርት (ሚኒማ) በተለያዩ ስፖርቶች አሟልተው የነበሩ በሺ የሚቆጠሩ አትሌቶች መስፈርታቸው ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ ይስራ አይስራ እርግጠኞች አይደሉም፡፡ በኦሊምፒክ ለመሳተፍ በየትኛውም ስፖርት አንድ አትሌት መስፈርቶችን ማሟላት የግድ ይለዋል፡፡ ከአስራ ስድስት ወር በፊት መስፈርት ያሟላ አትሌት ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ያሟላል ወይም አሁን ያለውን አቋም ይዞ ይቆያል ማለት አይቻልም፡፡ የተራዘመው ኦሊምፒክ ሲቃረብ አትሌቶች ዳግም መስፈርት አሟልተው ይወዳደሩ ማለት ደግሞ ሌላ ጣጣ ይዞ ይመጣል፡፡ ዛሬ መስፈርቱን ያሟላ አትሌት ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ዳግም ላያሟላ ይችላል፡፡ ስለዚህ ይህን ጉዳይ ለማስተካከል ራሱን የቻለ ትልቅ የቤት ሥራ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ይሁን እንጂ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ኃላፊው ኪት ማክኮኔል አሁን መስፈርቱን ያሟሉ አትሌቶች ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ መስፈርታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ይቆያል ብለዋል፡፡ ይህ በራሱ ግን ኋላ ላይ ጭቅጭቅ አለማስነሳቱን እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ ከሰላሳ ሦስት ዓለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ከአስራ አንድ ሺ በላይ አትሌቶች መስፈርቱን አሟልተው ለውድድር እየተዘጋጁ ባሉበት ሁኔታ ኦሊምፒኩ መራዘሙ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በኦሊምፒክ እግር ኳስ ውድድር የሚሳተፉ የወንድ ተጫዋቾች እድሜ ከሃያ ሦስት እስከ ሃያ አራት መሆን እንዳለበት ይታወቃል፡፡አሁን ኦሊምፒኩ በመራዘሙ በርካታ ተጫዋቾች ከዚህ እድሜ ሊያልፉ መቻላቸው ሌላው ፈተና ይሆናል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴም ይህን ጉዳይ መልክ ለማስያዝ ጉዳዩ ከሚመለከተው ፊፋ ጋር በቅርቡ ውይይት ለማድረግ እንዳሰበ ተጠቁሟል፡፡ ኦሊምፒኩን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለማስተላለፍ የተዋዋለው የአሜሪካን ኩባንያ ኦሊምፒኩ በሚካሄድበት ወቅት ከምንም በላይ የሚጠብቀው የኤንቢኤና ሌሎች ታላላቅ የአሜሪካን ቅርጫት ኳስ ውድድሮች ስለሚኖሩበት የፍላጎትና የጥቅም ግጭቶች ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ አንዱን ወገን በቢሊዮን ዶላሮች ኪሳራ ላይ ሊጥል ስለሚችል ከባድ ፈተና እንደሚሆን ይታመናል:: በተመሳሳይ ከዚህ ዓመት የተላለፉ በርካቶቹ ዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚካሄዱበት መሆኑ ሌላ ጣጣ ይዞ መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ በነዚህ ወራት ከሚካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች መካከል የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናና የዓለም ውሃ ዋና ቻምፒዮና ዋነኞቹ ቢሆኑም ውድድራቸውን ለመሰረዝ ፍቃደኛነታቸውን መግለፃቸው ይታወቃል፡፡ ይህ አበረታችና ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተስፋ የሰጠ ቢሆንም በነዚህ አካላት መካከል ተጨማሪ የውል ስምምነት እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡ ይህ ምናልባትም ሌሎቹ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖችም ለኦሊምፒክ ቅድሚያ እንዲሰጡ ማነሳሳት ቢችልም ወቅቱ በጣም ከፍተኛ ሙቀት የሚኖርበት መሆኑ ለውድድሮች አስቸጋሪ እንደሚሆን ስጋት አሳድሯል:: ምንም ይሁን ምንም ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ብቻ የጃፓን መንግሥትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ እንደሚገቡ ቀደም ሲል ተዘግቧል፡፡ የጃፓኑ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴም ገና ከመጀመሪያው ከፍተኛ ኪሳራ ሊገጥም እንደሚችል ተናግሯል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለዚህ ኪሳራ ስጋት ሰላሳ ሦስቱንም ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች የሚመለከት መድህን የገባ ቢሆንም በቂ እንደማይሆን ታምኖበታል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ቶማስ ባኽም ኦሊምፒኩ መራዘሙን በገለፁበት ወቅት ከባድ ኪሳራ እንደሚኖር በማመን ሁሉም ባለድርሻ አካላት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ለመጠቆም ሞክረዋል:: ከባዱን መስዋዕትነት ማን እንደሚከፍልና ጫናው በየትኛው ወገን ትከሻ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ግን ዛሬ ላይ ቆሞ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 28/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=29896
6962d4ef1030ae85a4ba4af08a35f54c
c7359f79daf14553b513a2b8d155ceab
ኮቪድን ለመከላከል የስፖርት ቤተሰቡ ርብርብ ቀጥሏል
ስፖርት
በመላው ዓለም የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ-19) ለመዋጋት የሚደረገው ርብርብ እንደቀጠለ ነው። በኢትዮጵያም የስፖርት ቤተሰቡ ተሳትፎ ገና ከጅምሩ አበረታች የሆነ መንገድ ያሳየ ሲሆን፤ እውቅ ስፖርተኞችና የስፖርት ማህበራት ድጋፋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦችና ተጫዋቾች በገንዘብና በዓይነት ድጋፋቸውን በመስጠት ላይ ካሉት መካከል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። የሃዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና የጽህፈት ቤት ሰራተኞች የደመወዛቸውን 50 በመቶ መስጠታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል። በዚህም 443 ሺ 366 ብር ስርጭቱን ለመቆጣጠር ለሚቋቋመው ግብረ ኃይል አበርክቷል። የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና አጠቃላይ የክለቡ ሠራተኞች 130 ሺ ብር ድጋፍን አድርገዋል። የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾችና አባላት በበኩላቸው ሙሉ ደመወዛቸውን ለዚሁ ዓላማ እንዲውል ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ታውቋል። የሲዳማ ቡናው አጥቂ አዲስ ግደይ፣ የመከላከያው አጥቂ ሀብታሙ ወልዴ፣ የጅማ አባጅፋሩ አማካይ ንጋቱ ገብረስላሴ፣ የሃላባ ከተማው ልመንህ ታደሰ እና የጅማ አባጅፋር ተከላካይ መላኩ ወልዴ በጋራ ለትውልድ ከተማቸው አጋሮ በጥሬ ዕቃ ድጋፋቸውን አድርገዋል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች 80 ሺ ብር የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ማስረከባቸውን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪም ቆሼ ተብሎ ወደ ሚጠራው ስፍራ በመጓዝ ለ541 አቅመ ደካሞች ርዳታ ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ኮሚሽኑን ጨምሮ በስሩ የሚገኙ የስፖርት ማህበራት ድጋፋቸውን አጠናክረው ከቀጠሉት መካከል ይገኛሉ። በከተማው የውሹ ፌዴሬሽን 45 ሺ 800 ብር በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው ኮሚቴ የሚውል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስፖርት ኮሚሽነር አበርክቷል። ከዚህም ውስጥ በስራ አስፈፃሚው ውሳኔ ፌዴሬሽኑ 20 ሺ ብር፣ 15 ሺ 800 ብር እና የምግብ ግብዓቶች ከክለብ አሰልጣኞች እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ማስተር ፍሬህይወት ሽታዬ በግላቸው 10 ሺ ብር አበርክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽንም በስሩ ያሉ ማዕከላትን እስከ ታችኛው የወረዳ መዋቅር ድረስ ለቅድመ መከላከልና መቆጣጠር ለሚያስፈልጉ ተግባራት ሁሉ እንዲውሉ መወሰኑ ይታወቃል። ከዚህ መካከል አንዱ የሆነው የጃን ሜዳ ስፖርት ማዕከል በጊዜያዊነት ወደ አትክልት ተራነት ተዘዋውሮ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።አዲስ ዘመን መጋቢት 27/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29814
13133d5e11f3a88925fcaf1fe0c5fbea
5cb36a0cd9913e44800f30f6ed4ff301
የስፖርቱ በቫይረሱ ሳቢያ ብዙ ተጽዕኖ እያስተናገደ ነው
ስፖርት
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያስቻለ ፈውስ በዓለም ሳይንቲስቶች፣ የህክምና ጠቢባንም ይሁን በሀያላን አገራት አቅም ማምጣት አልተቻለም። ይህም የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ከመለወጥ አንስቶ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በርካታ አሉታዊ ተፅዕኖው እንዲያርፍ አድርጓል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ተጽዕኖ እያስተናገደ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን መረጃዎች ያመላክታሉ። የስፖርት ቤተሰቡ በቫይረሱ ስርጭት ስጋት የዓለም ታላላቅ የስፖርት መድረኮች ተቆልፈውበት ሁነኛ የመዝናኛ አማራጩን አጥቶ በየቤቱ ቆዝሟል። የስፖርቱ ዓለም ታላላቅ ከዋክብትም ረብጣ ገንዘብና ዝናቸው ከደጃቸው እንዲወጡ አቅም አልሆናቸውም። የቫይረሱን አደጋ ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፤ ለመከላከል የሚደረገው ርብርብ በተጠናከረ መልኩ እንደቀጠለ ነው። የአለም ህዝብ እያሸበረ ያለውን ተህዋሲ ለመቆጣጠርና ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ በስፖርቱ ማህበረሰብ በኩል እየተደረገ ያለው ተሳትፎ ትልቅ ስፍራ ይወስዳል። በተለያዩ ሀገራት በከፍተኛ ፍጥነት የዓለምን ክፍል እያዳረሰ የሚገኘው ቫይረስ ለመቆጣጠርና አደጋ ለመቀነስ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ የስፖርት ማህበራት፣ የስፖርቱ ቤተሰብ፣ ተጫዋቾች ትልቅ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ በተመሳሳይ ኮሮና ቫይረስ የቅድመ መከላከል ተግባራትን በመደገፍና በመሳተፍ ትልቅ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ለመታዘብ ተችሏል። የአዲስ አበባ ከተማ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን እንቅስቃሴ መሰረት በተለየ መልኩ ህዝብን አሳታፊ የሆነ የቅድመ መከላከል ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመዲናዋ የኮሮና ቫይረስን ቅድመ ጥንቃቄና መከላከል አስመልክቶ የተደረገው የድጋፍ ማሠባሰብ ጥሪ የዚሁ አካል ተደርጎ የሚጠቀስ ይሆናል። በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጥሪ ከተደረገ ጀምሮ የተጠናከረ ድጋፍ በከተማዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተደረገ ባለው ተሳትፎ ውስጥ የስፖርት ማህበረሰብ ተሳትፎ አንጸባራቂ እንደነበር መታዘብ ተችሏል። የስፖርቱ አንዱ ባህሪና መገለጫው በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ በማድርግ ኃላፊነት መወጣት እንደሆነ ይታመናል። የስፖርት ቤተሰቡ ይሄንኑ መርህ መሰረት በማድረግ ለከንቲባው ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ህዝባዊነታቸውን እያረጋገጡ ካሉት አካላት መካከል በፊት አውራሪነት ይቀመጣል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሎም በመዲናችን የስፖርት ቤተሰቡ ተሳትፎ ገና ከጅምሩ አበረታች የሆነ መንገድ ያሳየ ሲሆን፤ እውቅ ስፖርተኞችና የስፖርት ማህበራት የነበራቸው ድጋፍ ተሳትፎ ለዚህ ምስክር ይሆናሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር አባላት መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም የጀመሩት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ይሄንኑ ያመላክታል። የማህበሩ አባላት በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ ሊያጋጥም የሚችለውን አደጋ ለመከላከል እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ የሚያስችል ስራ ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር አባላት ይሄንኑ መሰረት በማድረግ «ወገን ለወገን ደራሽ ነው» የሚል መሪ ቃልን በማንገብ መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ስራ ተገብቷል። ማህበሩ ከህብረተሰብና ከተለያዩ ለጋሾች የምግብ፣ የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ህዝባዊነቱን የሚያሳይ ይሆናል። በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ በመገኘት አርዓያነቱ እንዲጠናከርና ተግባሩ እንዲቀጥል የተጋረጠውን ቫይረስ ለመግታት፣ ህብረትንና አንድነትን ለማሳየት፣ ወሳኝነቱን በመግለፅና ለማበረታታት በርካቶች የታሪኩ አካል በመሆን እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብርሀቱ እና የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ቢኒያም ምሩፅ ይፍጠር ደግሞ ፊት አውራሪ በመሆን ተግባሩን እየመሩ ህዝባዊነታቸውን ያሳዩ መሆናቸው ታውቋል። በማህበሩ በኩል በሚደረገው እንቅስቃሴ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ለዚህ አላማ እጃቸውን እየዘረጉ የወገን አሌንታነታቸውን እያሳዩም ይገኛሉ። ለዚህም እንደ ማሳያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግበሩ ለማጠናቀቅ የተያዘው ቀን ማክሰኞ ቢሆንም የተሳትፎው ከፍተኛ መሆን ወደ ረቡዕ መሸጋገሩ እንደ ማሳያ ይጠቀሳል። የማህበሩ አባላት አንዱ የሆነችው አሰልጣኝ ሰላም ዘርአይ፤ ቀደም ብሎ እስከ ሰኞ ድረስ ይጠናቀቃል በሚል ተይዞ የነበረው ቀነ ገደብ በመላ ሀገሪቱ ያሉ አሰልጣኞች የሚሰጡት ምላሽ እየጨመረ መጥቷል። በዚህ መሰረት መዋጮውን ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጊዜ እንዲኖር በመጣው ጥያቄ መሰረት እስከ ረቡዕ ስምንት ሰዓት ድረስ ሊራዘም ችሏል። ‹‹በመሆኑ አሰልጣኞች ቀደም ሲል በተጠቀሰው የባንክ ቁጥር አቅማችን የፈቀደውን እንድናደርግ ከአክብሮት ጋር እንጠይቃለን›› ስትል አሰልጣኝ ሰላ በፌስቡክ ገጿ አሳውቃለች። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር አባላት በዚህ መሰረት የገንዘብ፣ የአይነትና የቁሳቁሶች ድጋፍ እስከ ረቡዕ ከተካሄደ በኃላ በሚወጣ ፕሮግራም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት ያስረክባሉ ተብሏል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር አባላት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከመጋቢት 26 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የሚዘልቅ ይሆናል። አዲስ ዘመን መጋቢት 29/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29948
bcaef4b0e1ff4b26f46a8be220ecc18f
83694b27e4ed57c766428f100aef4977
ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንገድ፣ የወደብ አገልግሎቶችንና የመኪና ማቆሚያ ጣቢያዎችን ለማሻሻል ተስማሙ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንገድ፣ የወደብ አገልግሎቶችንና የመኪና ማቆሚያ ጣቢያዎችን ለማሻሻል መስማማታቸው ተገለጸ:: በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ ወደቦች ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር አቶ አቡባከር ኦመር ሀዲ ጋር የመንገድ፣ የወደብ አገልግሎቶችንና የመኪና ማቆሚያ ጣቢያዎችን ለማሻሻል ተስማምተዋል:: አምባሳደር ብርሃኑ፣ ለሁለቱ አገራት ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተው የዲኪል-ዳጉሩ መንገድ በፍጥነት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ክትትል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል::የመንገዱ ግንባታ ቀሪው 80 ኪሎ ሜትር መንገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል:: የዶራሌ ሁለገብ ወደብና የጅቡቲ ኮንቴይነር ተርሚናልን ከኢትዮጵያ-ጅቡቲ የባቡር ሀዲድ ጋር በማገናኘት የወደብ አገልግሎቶችን አቅም ማሻሻል በሚቻልባቸው ሁኔታ ላይ መምክራቸውንም ነው አምባሳደሩ የገለጹት:: ጅቡቲ በሆራይዘን ነዳጅ ማደያንና በአዋሽ የሚገኘው የኢትዮጵያ የነዳጅ ማከማቻን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት ከስምምነት ተደርሷል። ይህም የነዳጅ ጭነት ፍሰት በማቀላጠፍ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመከላከል ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል:: ከደረቅ የመኪና ማቆሚያ ተርሚናል ጋር ተመሳሳይ የሆነ አስተዳደራዊ አሠራር ለማስቀመጥ ለነዳጅ ተርሚናል የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረበው ጥያቄም በወደብ እና በነፃ ዞን ባለሥልጣን ተቀባይነት አግኝቷል:: ሊቀመንበሩ የባለቤትነት ማረጋገጫ ወረቀቱን ለኢትዮጵያ ወገን በፍጥነት ለመስጠት ቃል መግባታቸቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38387
d70c01d60b327c5350a7d87432d95b03
9bfe3902fcc7d47e7cbeccee5bd84b89
በመቀሌ ከተማ የባንክ አገልግሎት መስጠት ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
አማንሚካኤል መስፍን መቐለ፡- በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎት መጀመሩን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ። ከንቲባው አቶ አታክልቲ ሃይለስላሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ እንዳስታወቁት፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ከሰሞኑ ባካሄደው ተከታታይ ውይይት የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ በተደረገው የተቀናጀ ስራ ትናንት ከሰአት በኋላ ጀምሮ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በጁንታው አማካኝነት በመቀሌ ከተማ ሆን ተብለው በተለቀቁ የህግ ታራሚዎችና ሌሎች ዘራፊዎች የተነሳ በከተማዋ ላይ የጸጥታ ችግር መኖሩን በማንሳት ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲያስተካክልላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የጠየቁ ሲሆን፤ በትናንትናው እለት በነበረው የወጣቶች ውይይትም ወጣቱ የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ከአስተዳደሩ ጋር ሆኖ ለመጠበቅ ቃል መግባቱ ይታወሳል።የከተማዋ ነዋሪና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ከዛሬ ከሰአት ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኖ ደንበኞች መጠቀም መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ በየቅርንጫፎቹ ተገኝቶ ተመልክቷል። የግል ባንኮችም አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ትዛዝ እንደተላለፈላቸው የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38393
eb792439de81f67850ee25cf10b5c499
c560eec5db24c93dbf1b1f3c26bfc0dc
የፌዴራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ድንጋጌ ጸደቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- የፌዴራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ድንጋጌ ጅግጅጋ በተካሄደው የተቋማቱ የጋራ የምክክር መድረክ ቀርቦ ጸድቋል:: የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጫላ ለሚ የፌዴራል ተጠሪ ተቋማት የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ድንጋጌንም ለጉባኤ አቅርበው አጽድቀዋል::በመተዳደሪያ ድንጋጌው ዝግጅት ላይ ባለድርሻ አካላትና የህግ ባለሙያዎች መሳተፋቸውንና ሰፊ ውይይቶች መደረጉን አብራርተዋል:: መተዳደሪያ ድንጋጌውን ያቀረቡት አቶ ደበበ ወ/ጊዮርጊስ ሰነዱ ከመዘጋጀቱ በፊት በ9 ነፃና ገለልተኛ ሆነው በሚሰሩና ተጠሪ ተቋማት ከም/ቤቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ተጠያቂነት፣ ለህዝብ ያላቸውን ተደራሽነት፣ የበጀትና የሰው ሀብት አስተዳደራቸው እና ያጋጠማቸውን ችግሮች በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት መደረጉን ገልጸዋል:: አክለውም የተዘጋጀው መተዳደሪያ ድንጋጌም የፎረሙ አባላት በመደበኛነት በመገናኘት የጋራ ዕቅድ የሚያወጡበትና የአፈጻጸም ግምገማ እና የምክክርና የልምድ ልውውጥ የሚፈጥሩበትን ምህዳር ይፈጥራልም ብለዋል:: በቀረበው ሰነድ ላይም ከተሳታፊዎች በርከት ያሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል::ተቋማቱ ‹‹የዴሞክራሲ ተቋማት›› ከሚባሉ ‹‹ነፃ ወይም ገለልተኛ ተቋማት ቢባሉ›› የሚል ሃሳብ ተነስቷል:: የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ተቋማቱ ነጻና ገለልተኛ ሆነው የሚሰሩ ቢሆንም ተጠሪነታቸው ለም/ቤቱ በመሆኑ ‹‹ተጠሪ ተቋማት›› በሚል ቢጠሩ አግባብነት እንዳለው ጠቁመዋል:: የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፎርም ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል::የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድን ሪፎርም ያቀረቡት ም/ኮሚሽነር አቶ ውብሸት አየለ ሲሆኑ ቦርዱ አንድ አዋጅ እና 29 ማስፈጸሚያ መመሪያዎችን ማውጣት፣ የሰው ሃይልን ማደራጀት፣ የምርጫ ቁሳቁሶችን ማሟላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ እና የህዝብ ግንኙነት ተግባራት በዋናነት ማከናወኑን አብራርተዋል:: በተመሳይም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፎርም በዋና ኮሚሽነር በዶ/ር ዳንኤል በቀለ ቀርቧል::ኮሚሽኑ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ ለመስራት የሚያስችለውን የህግ ማዕቀፍ ከማሻሻል ጀምሮ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ከህዝብ ተወካዮች የተገኘው መረጃ ያመላክታል::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38390
5c60100317d4959308d299f96776eb61
d6886cef39a45f423e78f80aff975a26
ክልሉ የደን ሽፋኑን ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲሱ ገረመው አዲስ አበባ፡- የደቡብ ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚመጣውን ተግዳሮት ለመቀነስ ባደረገው አገራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የድርሻውን ለመወጣት እንዲችል የክልሉን የደን ሽፋን ከ23 በመቶ ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ::በተያዘው ዓመት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ እንደሚዘጋጅ እና 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ችግኝ እንደሚተከልም ተጠቁሟል:: የደቡብ ክልል አካባቢ ጥበቃ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ቀቀቦ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አጠቃላይ የክልሉ የደን ሽፋን 19 በመቶ የነበረ ሲሆን፤ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ደግሞ 25 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ በመሰራቱ 23 በመቶ ማድረስተችሏል::በቀጣይም እንደ አገር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ክልሉ የሚጠበቅበትን ለማበርከት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን፤ በአስር ዓመት ውስጥም ሽፋኑን 30 በመቶ ለማድረስ ይሰራል   እንደ አቶ ሳሙኤል ገለጻ፤ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ የደን ሽፋንን ለማሳደግ በተደረገው ሰፊ ርብርብም ባለፈው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የደን ሽፋኑን 23 በመቶ ማድረስ ተችሏል::የደቡብ ክልል አጠቃላይ የደን ልማትን በተመለከተ ዋና ዓላማ ተደርጎ እየተሰራ ያለውም የክልሉን የደን ሽፋን ለማሳደግ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ከ2013 እስከ 2022 ዓ.ም በሚደረገው አጠቃላይ እንቅስቃሴ በየዓመቱ ዜሮ ነጥብ ሰባት በመቶ የደን ሽፋን በመጨመር የክልሉን ደን ሽፋን 30 በመቶ ለማድረስ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ ነው::በዚህም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ በሚደረገው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ሥራ ክልሉ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው::ከዚህ አኳያ ክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታትም ይህንኑ መሠረት በማድረግ ሲሰራ ቆይቷል::በተለይ የአረንጓዴ አሻራ ስራን በተመለከተ በዋናነት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ጀምበር በርካታ ችግኞችን የመትከልና ሰፊ   አካባቢን በደን የመሸፈን ሥራ በትኩረት ተሰርቷል::በዚህም በ2011 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 55 ሚሊዮን ችግኞችን፣ እንዲሁም በ2012 ዓ.ም 77 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ተችሏል::የደን ዘርፉ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን ፋይዳ ከግምት በማስገባትም ነው በሚቀጥሉት አስር ዓመታት የደን ሽፋኑን 30 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ያለ መሆኑንም ነው አቶ ሳሙኤል የተናገሩት:: ግቡን ለማሳካት መጠነ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን እና በዋናነት በየአካባቢው ያለውን የደን ሁኔታ የማጥናት ሥራ መከናወኑን የገለጹት አቶ ሳሙኤል፤ በተለይ በደቡብ ምዕራብ አካባቢ ያለውን የተፈጥሮ ደን የጥበቃ ሥራውን በከፍተኛ ደረጃ ለማጠናከርና ደኖች በሳሱባቸው አካባቢዎች መልሶ የመተካት ተግባራት እንደሚከናወኑ ተናግረዋል::በማዕከላዊ ዞን አካባቢዎችም በተለይ ከፍተኛ የሆነ የደን ውድመት ያለበትና ከፍተኛ የሆነ የህዝብ መጨናነቅ ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ለተለያዩ ዓላማዎች ሊውሉ የሚችሉ የችግኝ ተከላ ሥራም ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል:: ባለፈው ዓመት በአንድ ጀምበር ወደ 40ሺ ሄክታር መሬት በችግኝ መሸፈኑንና በተያዘው ዓመትም ወደ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ በማዘጋጀት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ችግኝ እንደሚተከልም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል::ለዚህም የዛፍ ችግኝ ዝግጅት፣ ችግኝ ለማፍላት የሚያስችሉ ፕላስቲኮችን የማዘጋጀት፣ ችግኝ ጣቢያዎችን የማዘጋጀትና ሌሎችም ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰዋል::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38395
1dc01f2c6cb1b56a1f084167b866ee11
5e45edcdce70b2904a8207730751ec75
”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት አገራዊ የአንድነት ስሜት መፍጠሩን ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ገለጹ
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲስ አበባ፡- የገበታ ለአገር ፕሮጀክት እንደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ አገራዊ የአንድነት ስሜት መፍጠሩን የሃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ገለጹ። ኢዜአ በአካባቢ ጥበቃና ኢኮ ቱሪዝም ላይ የሚሰራውን በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝና በባለቤታቸው የተመሰረተውን የሃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚን አነጋግሯል። የፋውንዴሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ በአገሪቷ በተፈጥሮ ብቻ የተገኙ በርካታ ድንቅ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች መኖራቸውን ይናገራሉ። ወይዘሮ ሮማን ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የ”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፈጠረውን አይነት አገራዊ የአንድነት ስሜት ፈጥሯል::ኢትዮጵያ ያሏት በርካታ የቱሪስት መስህቦችም የተፈጥሮ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ታሪካዊ አሻራ ያረፈባቸው፣ እምቅ ሀብትና ቅርሶችን ጭምር የያዙ በመሆናቸው እንደ “ገበታ ለአገር” አይነት ፕሮጀክቶች መጠናከር እንዳለባቸው ነው የተናገሩት። ወይዘሮ ሮማን፤ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷ ብቻ በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ገቢ ስለሚያመጣ ሀብቱን ጥቅም ላይ በማዋል ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻልም አንስተዋል። በዚህም እንደ “ገበታ ለአገር” ያሉ ፕሮጀክቶችን አቅም በፈቀደ መጠን ማስፋት እንደሚገባና ሕዝቡም ለዚህ ድንቅ ዓላማ ድጋፍ በማድረግ የሚሳተፍበት መሆን እንዳለበት ነው የተናገሩት። ወይዘሮ ሮማን የ”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፈጠረውን አይነት አገራዊ የአንድነት ስሜት መፍጠሩንም ገልጸዋል:: መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም፤ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ሀብቷ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ከሆኑ አገሮች መካከል አንዷ ብትሆንም ከዘርፉ የሚጠበቀውን ያህል ጥቅም እያገኘች አይደለም። የቱሪስት መዳረሻዎችን በሚፈለገው ልክ ማስተዋወቅና ማልማት አለመቻሏ ደግሞ ለዘርፉ መቀጨጭ በምክንያትነት ይጠቀሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዘርፉ እንዲያንሰራራ ያደርጋል ያሉትን “ገበታ ለአገር” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። በዚህም ትኩረት ተነፍጎት የቆየው የአገሪቷን የተፈጥሮ ሀብት የማልማት ስራ በጎርጎራ፣ በኮይሻና በወንጪ አካባቢዎች ለመስራት ታቅዶ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38398