query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
7
297
category
stringclasses
6 values
passage
stringlengths
137
5.93k
link
stringlengths
28
740
588ef73a8e2b622ad7d756be2818c328
2899e4ebddd8619f89f61acbd90b9325
የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸው የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አባላትን ጎበኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲስ አበባ፡- ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸው የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አባላትን ጎበኙ:: በጉብኝቱ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የምዕራብ እዝ መከላከያ ሆስፒታል እና የልዩ ሃይል የቁስለኞች ማቆያ በመገኘት በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በመጎብኘት አበረታተዋል::በሕግ ማስከበር ሀገራዊ ተልዕኮው ወቅት ለደረሰው የአካል ጉዳት ድጋፍ እንዲሆን ለሆስፒታሎቹ የዊልቸር፣ ክራንች እና ዎከር ድጋፍም ተደርጓል:: በተመሳሳይ በተያያዘ ዜናም በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ይኖሩበት የነበረውና የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባን ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል::ለሀገር የዋሉ ጀግኖች ማግኘት የሚገባቸውን ክብርና ትኩረት ወደጎን በማለት የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ ከለውጡ በፊት በነበረው ስርዓት አገልግሎት እንዲያቆም በመደረጉ በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ለሀገር ያበረከቱትን ውለታ የዘነጋ ተግባር ሲፈፀምባቸው ቆይቷል:: በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋእት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ይኖሩበት የነበረውና የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባን ለማቋቋም በበጎ ፈቃደኝነት የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ አደራጅ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን ብሔራዊ የጀግኖችና የሕፃናት አምባ በጎ አድራጎት ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር ዶክተር አዳሙ አንለይ ተናግረዋል:: የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ መቋቋም ለሀገር ክብር ዘብ በመቆም እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለከፈሉና እየከፈሉ ላሉ ጀግኖችና ወላጆቻቸውን መስዋእት ላደረጉ የጀግኖች ልጆች ተገቢውን ቦታ እና ክብር መስጠት ያስችላል መባሉን የዘገበው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ነው::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38401
66799b2cb8fcaf7220cf9e2a8095e68a
268d846e1bb036e0c358014447c76c8a
የቄራ ድርጅቶች አፈጻጸም 25 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ ሙሉ ሰርተፊኬት ወስደው ወደምርት የገቡት አስር የቄራ ድርጅቶች ማምረት ከሚችሉት ውስጥ 25 በመቶውን ብቻ እያመረቱ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።በግብርና ሚኒስቴር የኤክስፖርት ቄራዎች ድርጅት ሰርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጌዲዮን ይልማ (ዶ/ር) በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በሀገር ደረጃ ሰርተፊኬት ወስደው ወደሥራ የገቡ የቄራ ድርጅቶች 14 ቢሆኑም አራቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሥራቸውን አቁመዋል።በሌላ በኩል በሥራ ላይ ያሉትም ቢሆኑ በአግባቡ እያመረቱ አይደለም ያሉት አቶ ጌዲዮን፣ በሥራ ላይ የሚገኙት አስሩ ቄራዎች ማምረት ከሚችሉት 25 በመቶ ብቻ እያመረቱ ይገኛሉ ብለዋል።እንደ ዶክተር ጌዲዮን ገለፃ የቄራ ድርጅቶቹ በሙሉ አቅማቸው ማምረት ያልቻሉት በገጠማቸው ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮች ሲሆን ከነዚህም አንዱ የግብአት አቅርቦት ማነስ ነው።በተለይም ለእርድ የሚሆኑ እንስሳት በሚፈለገው ልክ አይቀርቡላቸውም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ይህም የሚከሰተው ከአቅርቦት ሰንሰለቱ፣ የኮንትሮባንድ፣ የውጪ ገበያ ትስስር ውስን መሆን እና የእርድ እንስሳት አቅርቦት ማነስ ከችግሮቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ገልፀዋል።ለዚህም ጉዳዩ የሚመለከታቸው እንደ ግብርና ሚኒስቴር፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ማህበራት እና የመሳሰሉት ተቋማት ተቀናጅተው እና ተናበው በሚፈለገው ልክ አለመስራታቸው ምክንያት መሆኑንም ጠቁመዋል። በዚህ የተነሳ ከዘርፉ የሚገኘውን ምርት ወደ ውጭ በመላክ ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባው የውጭ ምንዛሪ በአግባቡ እንዳልተገኘ ጠቁመዋል። ድርጅቶቹ እስካሁን ድረስ ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ስምምነት አድርገው የሚልኩት በሁለት ሀገሮች ብቻ በተንጠለጠለ የንግድ ሰንሰለት ስለሆነ የሚፈለገውን ገቢ ለማግኘት ይቸግራል ያሉት ዶክተር ጌዲዮን ይህም የማምረት አቅማቸውን ሙሉ በሙሉ እንዳይጠቀሙ ማነቆ እንደሆነና የተቀባይ ሀገሮች በየጊዜው መለዋወጥ እና የቅበላ መስፈርታቸው በየጊዜው መቀያየር ሌላው እንቅፋት እንደሆነ ገልጸዋል። በሌላ በኩልም በቋሚነት ለውጭ ገበያ ተብለው እንስሳት እየረቡ የሚቀርቡበት ሁኔታ ባለመኖሩ ከገበሬ እየተለቀመ እየተወሰደ የሚታረደው እንስሳ ለወደፊትም ሌላ አደጋ እንደሚያስከትል ጠቁመዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በእንስሳት አቅርቦትና እንስሳት አቅራቢ ነጋዴዎችን አርብቶ አደሮችንና መሰል አካላትን ለማስተሳሰር በግብርና ሚኒስቴር በኩል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ቢደረግም ውጤት አልተገኘም ብለዋል። ይህ እንዳይሆን ያደረገው ደግሞ በዘርፉ ውጤታማ ሥራ ለመስራት ተብለው የተቋቋሙ ባለድርሻ አካላት በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያለው የኢትዮጵያ ወተት ሥጋና ልማት ኢንስቲትዩት፣ ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከቄራዎች፣ ከግል ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን መሬት ላይ የወረደ ሥራ በቅንጅት ባለመስራታቸው እንደሆነ ዶክተር ጌዲዮን ገልፀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38319
30f780a64e5b9bfe19c1086081c65244
49207beb36578f8e119afcf5b99b9427
በአሶሳ ከተማ ከ552 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ሕገ-ወጥ የትምባሆ ምርቶች ተያዙ
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲስ አበባ፡- በአሶሳ ከተማ በትምባሆ ምርቶች ላይ የኦፕሬሽን ሥራዎችን በማከናወን ከ552 ሺህ 750 ብር በላይ የሚገመት ሕገ-ወጥ የተለያዩ የትምባሆ ምርቶች መያዛቸውን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ባለሥልጣኑ እንዳስታወቀው፤ በጸጥታ እና በባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ክትትልና ቁጥጥር በአሶሳ ከተማ በትምባሆ ምርቶች ላይ የኦፕሬሽን ሥራዎችን በማከናወን ከ552 ሺህ 750 ብር በላይ የሚገመት ሕገ-ወጥ የተለያዩ የትምባሆ ምርቶች ተይዘዋል፡፡በደቡብ ምዕራብ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ተቆጣጣሪዎች ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ተቆጣጣሪዎች እና ከከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አባሎች ጋር በመቀናጀት ባከናወነው ኦፕሬሽን ሥራ የትንባሆ ምርቶቹ መያዛቸውን ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38316
53d08a3894cc5f7e43d5b88fbd5733e1
8d900c98c1599c1ee034790b209442b9
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋር ክልል ሕግ የማስከበር ዘመቻ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ድጋፍ አደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህወሓት ጁንታ ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በከፈተው ጦርነት ሳቢያ በተለያዩ አጎራባች ክልሎች በሕግ ማስከበር ሥራ ለተሳተፉ የልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት እንዲሁም የተፈናቀሉ ዜጐችን ለመደገፍ ቃል በገባው መሠረት 2ሺህ 400 ኩንታል እህል ለአፋር ክልል አስረክቧል።ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ እና የአዲስ አበባ ከተማ አቃቢ ሕግ ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር መሀመድ ለአፋር ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኃላፊ ለአቶ መሀመድ ሁሴን አስረክበዋል።የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕከት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍም በክልሉ ሕዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጁንታው የጥፋት እኩይ ተግባር ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለመደገፍ ለአፋር ክልል 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነት እና 94 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ በጠቅላላው 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ የተገኘው መረጃ ያመለክታልአዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38313
bc5048760f511d51e74e717001d4c21d
0144ad88e4be9c873dc8c3c50637e0f6
ለኦሎምፒክ የተመረጡ አትሌቶች ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ወደ ዝግጅት ይገባሉ
ስፖርት
ዓለምን እያሳሰበ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሳቢያ መካሄድ አለመካሄዱ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አምስት ወራት የቀሩት ቢሆንም በርካታ የዓለማችን አገራት በተለያዩ ስፖርቶች የሚያደርጉትን ዝግጅት አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ኢትዮጵያም በዚህ ታላቅ የስፖርት መድረክ በተለይም በአትሌቲክስ ረጅምና መካከለኛ ርቀቶች ውጤታማ እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አባዱላ ገመዳ የሚመራ ብሔራዊ የዝግጅት ኮሚቴ በማዋቀር የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያከናውን ሰንብቷል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውጤት በሚጠበቅበት የአትሌቲክስ ስፖርት ኢትዮጵያን እንዲወክሉ የተመረጡ አትሌቶች ከመጋቢት ሦስት ጀምሮ ወደ ሆቴል ገብተው ዝግጅት እንዲጀምሩ ውሳኔ ላይ መድረሱን ያሳወቀ ሲሆን፣ አትሌቶችና አሰልጣኞች ከትናንት ጀምሮ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ፅሕፈት ቤት በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሁለት ሳምንት በፊት በኦሊምፒኩ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችና አሰልጣኞችን መልምሎ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በመካከለኛ ርቀት፣ ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል፣ ረጅም ርቀት፣ ማራቶንና ርምጃ ውድድሮች አሰልጣኞችና አትሌቶች መመረጣቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት በመካከለኛ ርቀት አሰልጣኝ ብርሃኑ መኮንን፣ ሃብታሙ ግርማ፣ ኢሳ ሽቦ እና ጉዲሳ ታሱ በአሰልጣኝነት ተመርጠዋል፡፡ አሰልጣኝ አብርሃም ኃይለማሪያም እና ስንታየሁ ካሳሁን ደግሞ በተጠባባቂነት ተይዘዋል፡፡ በ3ሺ ሜትር መሰናክል ደግሞ አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ እና ዶክተር ብዙአየሁ ታረቀኝ ሲመረጡ አሰልጣን ከፍያለው አለሙ ተጠባባቂ ሆነዋል፡፡ አገሪቷ በኦሊምፒክ መድረክ በተለይ ውጤታማ በሆነችባቸው የ5ሺ እና 10ሺ ሜትር ርቀቶችም አራት አሰልጣኞች ተመራጭ ሆነዋል፡፡ አሰልጣኝ ሁሴን ሸቦ፣ ቶሌራ ዲንቃ፣ ንጋቱ ወርቁ እና ኃይሌ እያሱ ሲመረጡ፤ አሰልጣኝ ተፈሪ መኮንን እና በሪሁን ተስፋይ ደግሞ የተጠባባቂነት ስፍራን ይዘዋል፡፡ በረጅሙ የአትሌቲክስ ውድድር ማራቶን በማናጀር አሰልጣኝነት ስኬታማ የሆኑት አሰልጣኝ ሃጂ አደሎ ከሌላው ስኬታማ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ጋር በመሆን የርቀቱን እንዲመሩም ተመርጠዋል፡፡ አሰልጣኝ ጌታነህ ተሰማ እና ይረፉ ብርሃኑ ደግሞ ተጠባባቂ ሆነው ተይዘዋል፡፡ የእርምጃ ቡድኑም በሻለቃ ባየ አሰፋ አሰልጣኝነት የሚያመራ ይሆናል፡፡ ውጤት በሚጠበቅበትና ታሪካዊ ሊሆን እንደሚችል በሚታሰበው የወንዶች ማራቶን ውድድር የ5ና 10ሺ ሜትር የኦሊምፒክ ቻምፒዮኑና የዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ባለፈው መስከረም በበርሊን ማራቶን ባስመዘገበው ፈጣን ሰዓት መሰረት በዋናነት መመረጡ የሚታወስ ሲሆን ማራቶንን ጨምሮ በሌሎች ርቀትም ጠንካራ አትሌቶች በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ለመወከል ወደ ዝግጅት ይገባሉ፡፡ ከነዚህም መካከል በዶሃው ቻምፒዮና ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው አትሌት ሞስነት ገረመው 2፡02፡55 የሆነ ሰዓት ባለፈው ለንደን ማራቶን ላይ በማስመዝገቡ በማራቶን ቡድኑ ውስጥ በሦስተኛ ደረጃ ተመራጭ ሆኗል፡፡ ብርሃኑ ለገሰ በ2፡02፡48 በሁለተኛነት ሲመረጥ የዓለም ሻምፒዮኑ አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ ከሌሎች አትሌቶች አኳያ ያለው የቅርብ ጊዜ ፈጣን ሰዓት በቡድኑ ሊያካትተው እንደማይችል ይፋ ከተደረገው የእጩዎቹ ዝርዝር መረዳት ተችሏል፡፡ በሴቶች ማራቶን የዱባይ ማራቶን አሸናፊዋ ወርቅነሽ ደገፋ 2፡17፡41 ሰዓት በመያዝ በቀዳሚነት ስሟ ሲቀመጥ ሮዛ ደረጄ 2፡18፡30ና በ2፡18፡34 ሰዓት ሩቲ አጋ በቀዳሚነት ታጭተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን በሚጠበቁበት የአስር ሺ ሜትር ውድድር የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ዮሚፍ ቀጄልቻ 26፡49፡34 በሆነ ሰዓት ሲመረጥ አንዱአምላክ በልሁ 26፡53፡15ና በ26፡54፡34 ጀማል ይመር በቀዳሚነት ተመርጠዋል፡፡ በሴቶች የኦሊምፒክ ቻምፒዮኗ አልማዝ አያና ከዓመት በላይ በጉዳት ላይ የቆየች ቢሆንም ቀዳሚዋ ተመራጭ መሆን ችላለች፡፡የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ ለተሰንበት ግደይና ነፃነት ጉደታም ከቀዳሚዎቹ እጩዎች መካከል ተካተዋል፡፡ በወንዶች አምስት ሺ ሜትር በዶሃው የዓለም ሻምፒዮና የወርቅና የብር ሜዳሊያ ያጠለቁት ሙክታር ኢድሪስና ሰለሞን ባረጋ እንዲሁም ሃጎስ ገብረህይወትና ጥላሁን ሃይሌ በቀዳሚነት ሊመረጡ ችለዋል፡፡ በሴቶች ደግሞ ጸሐይ ገመቹ፣ ሐዊ ፈይሳና ፋንቱ ወርቁ ባስመዘገቡት ሰዓት መሰረት ሊመረጡ ችለዋል፡፡ኢትዮጵያ በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ከአትሌቲክስ ውድድሮች በተጨማሪ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ተሳታፊ መሆኗን ከሁለት ሳምንት በፊት ማረጋገጥ ችላለች፡፡ በሞሮኮ ራባት ተካሂዶ በነበረው የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት የኦሊምፒክ ማጣሪያ ውድድር ማስተር ሰለሞን ቱፋ በኦሎምፒክ እንደሚወዳደር ማረጋገጡ አይዘነጋም፡፡አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 28/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=28667
a8e4023ae18f8665b3e9ef434b721864
9329df34b8dfebb71bab8b039b0495cc
«ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ» የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል
ስፖርት
«ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ» በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ለማካሄድ ፍቃድ መገኘቱን አዘጋጁ ፍቅር ያሸንፋል በጎ አድራጎት ማኅበር አስታወቀ። የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅና መስራች አቶ ሚስባህ ከድር እንደገለፁት፤ ስፖርት ጉልህ ሚናውን ከሚጫወትባቸው መስኮች አንዱ በሰላም ላይ ተጽዕኖ የመፍጠር አቅሙ ነው። ማህበሩ ይሄንኑ መሰረት በማድረግ «ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ» በሚል መሪ ቃል መስቀል አደባባይ ባዘጋጀው ውድድር ላይ 40 ሺ ተሳታፊዎች የሚጠበቁ ይሆናል።የጎዳና ሩጫው ቀደም ሲል የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ለማካሄድ ታስቦ እንደነበር የገለፁት አቶ ሚስባህ፣ በወቅቱ በከተማው ላይ ሊከናወኑ የነበሩ የተለያዩ መርሐ ግብሮች ከመኖራቸው ጋር ተያይዞ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማድረግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል። አሁን ግን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽፈት ቤት ውድድሩን ለማድረግ በደብዳቤ ጥያቄ በማቅረብ ፍቃድ ማግኘት መቻሉን አብራርተዋል ለውድድሩ የሰላም ሚኒስቴር ዕውቅና የሰጠው ሲሆን አመስት ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ውድድር ለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል። «በዓይነቱና በይዘቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶችና ታዋቂ ግለሰቦችን፣ አርቲስቶች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ያለምንም የፆታና የዕድሜ ልዩነት ይታደሙበታል›› ያሉት አቶ ሚስባህ፣ ከሩጫው መርሐ ግብር በኋላ ትልቅ እንጀራ በማዘጋጀት በአንድ ላይ የመቁረስ ሥነ ሥርዓት እንደሚኖር አስረድተዋል ይህም ‹ሰፊ እንጀራ አለን ተካፍለን እንብላ፤ እርስ በርስ አንባላ› የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ታስቦ እንደሚከናወን አክለዋል። በሽብር ወንጀል ክስ ከአራት ዓመት በላይ በወህኒ ቤት መቆየታቸውን የሚናገሩት አቶ ሚስባህ፣ የማህበሩ የክብር አምባሳደር አርቲስት ቻቺ ታደሰ እና አርቲስት ዳዊት ፅጌን በማድረግ ባለፉት 12 ወራት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል። የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ የመጣውን ሰላም በጋራ በመጠበቅ የተሻለችውን ኢትዮጵያን ለትውልድ ማውረስ ይቻል ዘንድ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነም አመልክተዋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 1/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=28836
6529926190fe641603b75c1cbfe5b70c
990c386647d14237d680e961d3eda8ef
የኦሊምፒክ ችቦው ቅብብሎሽ ደማቅ ጉዞ
ስፖርት
4ተኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ችቦ መለኮስ ሥነ ሥርዓት ከትናንት በስቲያ በመቖለ ሮማናት አደባባይ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች በተገኙበት ተከናውኗል። በሥነ ሥረዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ የትግራይ ክልል በተለያዩ ስፖርቶች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን በማስመረጡ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል የትግራይ ክልል በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ በአትሌቲክስ 10 እና በብስክሌት 1 አትሌት ማስመረጥ መቻሉን ያስታወሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ክልሉ ስፖርቱን ለማጠናከርና የኦሊምፒክ ቡድኑን ለመደገፍና የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ከኦሊምፒክ ኮሚቴው ጎን እንደሚቆም በማረጋገጥ ከወዲሁ ለኦሊምፒክ ቡድኑ መልካም ዕድል ተመኝተዋል።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ የቶኪዮ 2020 ብሔራዊ የዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ በትግራይ የተለኮሰው የኦሊምፒክ ችቦ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹ትግራይ ብዙ ጀግኖችን አፍርታለች፣ በስፖርቱም በቀጣይ በተለያዩ ስፖርቶች አገርን የሚወክሉ አትሌቶች ማፍራት ይጠበቃል›› ብለዋል አቶ አባዱላ ንግግራቸውን በድንገት ገታ አድርገውም በቶኪዮ 2020 በብስክሌት ኢትዮጵያን በብቸኝነት የምትወክለው የትራንስ ኢትዮጵያ ክለብ ብስክሌት ጋላቢዋን ሰላም ዓመሀን ወደ መድረክ በመጥራት ‹‹በብቸኝነት ኢትዮጵያን በመወከልሽ ትልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ከህዝብ በስጦታ የተበረከተልኝ ነው›› በማለት ከአንገታቸው የወርቅ ሀብል አውልቀው ሽልማት አበርክተውላታል።በችቦ መለኮስ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ችቦውን ከትግራይ ክልል የተረከቡት የጋምቤላ ክልል አፈጉባኤ አቶ ላክደር ላባክ በበኩላቸው ‹‹የኦሊምፒክ ቡድኑን ለመደገፍ በቀጣይም በስፖርቱ መሠረተ ልማት ላይ የበኩላችንን ለመወጣት እድሉን በማግኘታችን ደስተኞች ነን›› በማለት ተናግረዋል 5ተኛው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ችቦ መለኮስ ሥነ ሥርዓት መጋቢት 6/2012 በጋምቤላ ክልል የሚከናወን ሲሆን የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ታይዶር ቻምባንግ መቖለ በነበረው የችቦ መለኮስ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ችቦው ሲረከቡ ‹‹በስፖርት ህብረተሰቡን ተሳታፊ ማድረግ እንዴት እንደሆነ ከትግራይ ክልል ትምህት ወስደናል›› ብለዋል። ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ቡድን እደክልል በተገቢው መንገድ እንደሚደግፉም አብራርተዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ከጀግናው አትሌት ሻበል ምሩፅ ይፍጠር ልጅና የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቢኒያም_ምሩፅ ጋር መገናኘታቸውን ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅትን በተለየ መልኩ ለማከናወንና ለትውልድ የሚተላለፍ ዘመናዊ የኦሊምፒክ አካዳሚን የመገንባት ዕቅድ በመያዝ የብሔራዊ ዝግጅት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራዎችን ከጀመረ ሰንብቷል። ኮሚቴው ሕዝቡን በነቂስ የሚያሳትፍ የመጀመሪያ መርሐግብሩን የካቲት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ የኦሊምፒክ ችቦ በመለኮስ መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ሌሎች ክልሎች እንዲዞር በማድረግ መጀመሩ ይታወሳል። የኦሊምፒኩን ችቦ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተረከበ ሲሆን ከድሬዳዋ ተከትሎ ሶማሌ፣ ትግራይ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ላይ መጨረሻውን ያደርጋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 1/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=28830
f60e2e4b225d6b2b43a1c308e0d4c2c2
62db70ce50bc06bee8fd179408ba0e6e
የሴቶችን የማራቶን ታሪክ የቀየረችው ታሪካዊ ቅፅበት
ስፖርት
 የታሪክ ድርሳናት እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ የዓለም ስፖርት ካንቀላፋበት ፆታን እኩል ያለመመልከት ቅዠት እንዳልነቃ ይመሰክራሉ። ባልተሞከረና ባልተረጋገጠ ሁኔታ ‹‹አትችልም›› የሚል መላ ምት ሚዛን ደፍቶ ዘመናትን በመሻገሩ እጅግ ተወዳጁና ተመራጩ የመዝናኛ ዘርፍ ወደ አንድ ጎን ያዘነበለ ነበር። ሴት በስፖርት ትጥቅ ከሜዳ መገኘቷን ባለመቀበል አስተሳሰብ የተሸበቡትን ለማሳመንም በርካቶች ባልተፈቀደ መንገድ መገኘት ግድ ሆኖባቸዋል። ‹‹ነውር›› ለሚሏቸው ጆሯቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን በሰጡ ደፋርና ቆራጥ ሴቶች መቻላቸውን በማስመስከር ዓለም የዛሬውን ቅርጽ እንዲይዝ አድርገዋል። የዛሬውን የሴቶች ቀን አስመልክቶም ‹‹ባልተፈቀደው›› መንገድ ከተጓዙ እንስቶች መካከል የአንዲትን ሴት ታሪክ ልናስታውስ ወደድን። በዓለም ላይ ዋና ዋና ከሚባሉት ስድስት ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ የቦስተን ማራቶን ነው። መነሻውን እኤአ 1897 ያደረገው አንጋፋው የጎዳና ላይ ሩጫ የ122 ዓመት እድሜ ባለጸጋም ነው። ታዲያ በዚህ ውድድር ተሳታፊ እንዲሆኑ ይፈቀድላቸው የነበሩት ወንድ አትሌቶች ብቻ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የሴቶች ተሳትፎ የሚጀምረው ዘግየት ብሎ ነው። በዓለም አትሌቲክስ ታላቅ ስፍራ ያለው ይህ ማራቶን የተለያዩ ክስተቶችን በተለያዩ ዓመታት ቢያስተናግድም ከሁሉም ይልቅ ሴቶች በሩጫው ላይ እንዲታዩ መሰረት የጣለው ድራማዊ ክስተት መቼም የሚዘነጋ አይደለም። እኤአ 1967 የቦስተን ማራቶን ተሳታፊ ለመሆን ከተመዘገቡት ወንድ ሯጮች መካከል ኬቪ ስዊዘር የሚል ስም ይገኝበታል። ስሙ በአጭሩ የተመዘገበ በመሆኑ ጾታው በትክክል የሚለይ ባይሆንም ለሩጫው ፈቃድ የሚያገኙት ወንዶች ብቻ በመሆናቸው ይህ ይከሰታል በሚል የጠረጠረ አልነበረም። የውድድሩ ዕለት ደርሶ የሩጫ ማስጀመሪያው ከተበሰረ በኃላ ግን ሯጮች ያዩትን ማመን አልቻሉም። ምክንያቱ ደግሞ በከባዱ የማራቶን ሩጫ ከእነዚያ ሁሉ ወንዶች መካከል አንዲት ሴት በመታየቷ ነው። ከቆይታ በኋላ ግን ክስተቱ ከሯጮችም አልፎ ከመንገዱ ዳር ቆመው ከሚያበረታቱና ለዘገባ በተሰየሙ የመገናኛ ብዙሃን እይታ ውስጥ ይገባል። ጉዳዩ ያስደነቃቸው የፎቶግራፍ ባለሙያዎችም ሩጫውን እየተከተሉ ካሜራቸውን ወደዚያው መደቀናቸውን ተያያዙት። ይህ ትዕይንት በዚህ ሁኔታ እንዳለ ግን በጎዳናው ግራና ቀኝ ካሉት ተመልካቾች መካከል ባልተለመደ መልኩ አንድ ሰው ሩጫውን ተቀላቀለ። የውድድሩን ክልል ጥሰው የገቡት አንጋፋ ሰውም እሳት ለብሰውና እሳት ጎርሰው ከሴቷ ሯጭ ጋር ግብግብ ጀመሩ፤ ነገር ግን ገላጋዮች በመሃል በመግባታቸው ከጀመረችው ሩጫ ሊገቷት አልቻሉም።ዕድሜ ሰጥቷት ዛሬን ለመመልከት የበቃችው የዚህ ታሪክ ባለቤት ካትሪን ስዊዘር ትባላለች። በጊዜው የሆነውን ስትተርክም ‹‹በረጅም ርቀት ሩጫዎች ላይ ሴቶች ለምን አይሳተፉም የሚለው የሁልጊዜም ጥያቄዬ ነበር። በሩጫው ላይ ለመሳተፍ ስነሳም እንዳይለዩኝ በሚል ስሜን አሳጥሬ ኬቪ ስዊዘር አደረኩት፤ በውድድሩ ዕለትም ከአሰልጣኜና የእግር ኳስ ተጫዋች ከሆነው ፍቅረኛዬ ጋር ተገኘሁ። ሩጫውን እንደጀመርንም ብዙዎች ሴት መሆኔን በመመልከት ተደንቀው ሲያዩኝ ‹‹አዎ እኔ ሴት ነኝ›› እላቸው ነበር፤ የካሜራ ባለሙያዎችም ፎቶ ሊያነሱኝ ሲከተሉኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። ከቆይታ በኋላ ግን የውድድሩ ዳይሬክተር በንዴት ወደእኔ መጣ፤ የመሮጫ ቁጥሩን ስጪኝና ከዚህ ውድድር ውጪ እያለ ይጮህና ይጎትተኝም ነበር። በፊቱ ላይ ይታይ የነበረው ብስጭት የሚያስፈራ ቢሆንም አብሮኝ የነበረው ፍቅረኛዬ በመሃላችን በመግባት እኔን ወደፊት እንድሄድ ነገረኝ። አንዳንድ ሯጮች ግን ከኋላዬ እስኪቀሩ ድረስ ‘መቻልሽን ለማስመስከር ነው ምትሮጪው፣…?’ በማለት ሲያሾፉብኝ ነበር›› ትላለች በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘውን የዚያኔውን ሁኔታ ስታስታውስ።ካትሪን ከዚያ በኋላ የነበሩትን ኪሎ ሜትሮች የሸፈነቻቸው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ነበር። ፍቅረኛዋ ሩጫውን ስለማጠናቀቅ በጠየቃት ጊዜም ‹‹በእጄና ጉልበቴ ድኼም ቢሆን እጨርሰዋለሁ አልኩት፤ ምክንያቱም ሩጫውን ካላጠናቀቅኩ ማንም የሴትን መቻል አይረዳም እያልኩ አስብ ነበር። እጨርሰዋለሁ እንዳልኩትም በ 4ሰዓት ከ20 ደቂቃ የመጨረሻውን መስመር ረገጥኩ፤ ምሽት ላይ ወደ ቤታችን ስንመለስም ክስተቱ ህይወቴን እንደቀየረው ተገነዘብኩ። ምክንያቱም በመንገዳችን ላይ ቡና ለመጠጣት ካረፍንበት ስፍራ ፎቶዬን የያዙና እኔን ዜና ያደረጉ በርካታ ጋዜጦችን በመመልከቴ ነው። በመጨረሻም ያደረኩት ነገር ሴቶች በስፖርት ያላቸውን ታሪክ ይቀይር ይሆናል በሚል ተስፋ አሳደረብኝ›› ትላለች ጠንካራዋ ካትሪን ስዊዘር። የ73 ዓመቷ ካትሪን ዛሬ ደራሲና የቴሌቪዥን አስተዋዋቂ ሆናለች። እርሷ የጀመረችው በቦስተን ማራቶን የሴቶች ተሳትፎም ከአምስት ዓመት በኋላ እኤአ በ1972 እውን ሲሆን፤ እኤአ በ1975 ለሁለተኛ ጊዜ ተሳትፋ የራሷን ምርጥ ሰዓት (2:51:37) በማስመዝገብ አሸናፊ ሆናበታለች። አሁን ዓመታዊው የቦስተን ማራቶን ሲካሄድ በክብር እንግድነት ትገኛለች፤ ሌሎች ሴቶች ሲመለከቷትም ለቅሶ እንደሚቀድማቸው ትናገራለች። የመጀመሪያ ሩጫዋን ባደረገችበት ዓመት የመሰረተችው የሴቶች ማህበርም እስከሁንም በአሜሪካ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። አዲስ ዘመን የካቲት 29 /2012  ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=28730
dd37204af6656536d88b1fc7bda89f01
e39364e17ec77a5d3d11f0901692fc9e
‹‹ወደ ቶኪዮ የምንሄደው ለተሳትፎ ሳይሆን ለማሸነፍ ነው››
ስፖርት
ኢትዮጵያ ለኦሊምፒክ ድል አዲስ ባትሆንም ውጤቷ በአትሌቲክስ ብቻ የተገደበ ስለመሆኑ እርግጥ ነው።ተሳትፎዋም ቢሆን ከቦክስ፣ ብስክሌትና ውሃ ዋና ስፖርቶች ያልዘለለ ነው።ጃፓን በመዲናዋ ቶኪዮ ከአራት ወራት በኋላ በምታስተናግደው የ2020 ኦሊምፒክ ግን ኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስ በሆነ ስፖርት ተሳታፊ መሆኗ ታውቋል።ይህ ብስራት የተሰማው ከኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ስፖርት ሲሆን፤ ወጣቱ አትሌት ሰለሞን ቱፋ የታሪኩ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል።ሰለሞን ለዚህ ስኬት እንዲበቃ ከስድስት ዓመታት በላይ በአሰልጣኝነት አብሮት የደከመው ማስተር አዲስ ኡርጌሳም ከዚህ ታሪክ ባለቤትነት ጋር አብሮ ይነሳል።በአፍሪካ ካሉ ስመ ጥር የወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ትልቁ ነው።በዓለም አቀፉ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ደግሞ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ የአሰልጣኞች እና የዳኞች አሰልጣኝ ነው። የአፍሪካ ወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ሊቀመንበር በመሆንም እያገለገለ ነው።ማስተር አዲስ ዑርጌሳ።በ2010/11 የውድድር ዓመት በተሳተፈባቸው ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮች ላይ ባልተመቻቸ ሁኔታ በጥቂት ስፖርተኞች ተሳትፎ 5 ወርቅ 2 ብር እና 3 የነሀስ ሜዳሊያዎች በሚያሰለጥናቸው ስፖርተኞች አማካኝነት ለኢትዮጵያ አስገኝቷል።ባለፈው ሪዮ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች በሁለቱም ፆታ ያሰለጠናቸው ተወዳዳሪዎች ወደ ታላቁ መድረክ ለማለፍ ከጫፍ ደርሰው ሳይሳካላቸው ቀርቷል።ከሃያ ዓመታት በላይ በስፖርቱ ውስጥ ያሳለፈው ማስተር አዲስ ዛሬ ላይ ህልሙ እውን ሆኖ ታላቁ የስፖርት መድረክ ላይ ደርሷል።በአገራችን ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ተስፋና ስጋት እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ይናገራል። አዲስ ዘመን፡- በዓለም ላይ ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ተከትሎ ኦሊምፒክ ሊራዘም እንደሚችል ስጋት አለ፣ ምናልባት የሚራዘመው ለረጅም ጊዜ ከሆነ እንደ ወርልድ ቴኳንዶ አይነት ብዙ ልፋትና ዋጋ የሚከፈልባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ዳግም ወደ ማጣሪያ የሚገቡበት አጋጣሚ ይኖራል? ማስተር አዲስ፡- አይመስለኝም፤ እስካሁንም እንዲህ የሚል ህግ አላየሁም።ምናልባት ከአንድ ዓመት በላይ የሚራዘም ከሆነ ሊባል ይችል ይሆናል።ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ እስከ መጨረሻው ነገሮችን ሳይመለከቱ ወደዚህ ውሳኔ ይገባሉ የሚል እምነት የለኝም፤ ቢያራዝሙ እንኳን ጥቂት ወራትን ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ነው ያለኝ። አዲስ ዘመን፡- የኦሊምፒክ ማጣሪያውን አልፋችሁ ትልቅ ደረጃ ላይ ስትደርሱ የነበረው ሂደት እንዴት ነበር? ማስተር አዲስ፡- ማጣሪያው ወደ 34 የአፍሪካ አገራት የተሳተፉበት ትልቅ ውድድር ነበር።ለአራት ዓመታት ያደረግነውን ዝግጅትም ከ100 በላይ ከሚደርሱ ስፖርተኞች ጋር ተወዳድረን ነው የመዘንነው።እንደሚታወቀው ሰለሞን ሶስቱን ዓመት እስከ አውሮፓ በመጓዝ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ነው ያሳለፈው።በቱርክና በፖላንድ ከተሳተፈባቸው ውድድሮች ባሻገር የአፍሪካ ዋንጫንና ፕሬዚዴንሺያል ዋንጫን ጠቅልሎ በመውሰድ በአፍሪካም ኮከብ በመባል ነበር ያጠናቀቀው።ይህም ወደ ማጣሪያው ሲገባ ትልቅ ደረጃን ይዞ በመሆኑ ውጤቱም መልካም ሆኗል፡፡አዲስ ዘመን፡- ቀደም ባሉት ዓመታት በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ውጤት ይመጣበታል የሚል ብዙም እምነት አልነበረም፣ ይህን አስተሳሰብ ሰብሮ ፈታኝ የሆኑ ማጣሪያዎችን በማለፍ ለኦሊምፒክ ስፖርተኛን ማብቃት ከባድ መሆኑን መገንዘብ አይከብድም፣ ነገር ግን ይህ ስኬት ትልቅ ቦታ ተሰጥቶታል ብለህ ታምናለህ? ማስተር አዲስ፡- በማጣሪያው ላይ ከሰለሞን ጋር ውድድር ያደረገው ስፖርተኛ በዓመት ውስጥ ከ13 ያላነሱ ውድድሮችን አድርጓል፤ በዓለምና በአፍሪካ ያለው ደረጃም በጣም ጥሩ ነው።ሰለሞን በአንጻሩ ከአራት ያልበለጡ ውድድሮች ላይ ብቻ ተሳታፊ ሆኖ ነው ለአሸናፊነት የበቃው።ይህንን ድል መድገም አይቻልም ነገር ግን የተሰጠው ክብር ብዙም አይደለም። አዲስ ዘመን፡- ከዚህ ቀደም በምትሳተፉባቸው ውድድሮች ብዙም ድጋፍ እንደማይደረግላችሁ ይታወቃል።በዚህ ማጣሪያስ ድጋፉ እንዴት ነበር? ማስተር አዲስ፡- ድሮ ከነበረው በጣም የተሻለ ነበር፤ በተለይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥሩ ድጋፍ አድርጎልናል።ፌዴሬሽኑም ያለውን አቅም ተጠቅሟል፤ ከዚህ ቀደም ውድድሮች ሲኖሩብን ለአጭር ጊዜ ነበር ቡድናችንን የምናዘጋጀው አሁን ግን ለረጅም ጊዜ በዝግጅት ላይ እንድንቆይ መደረጉ መልካም ነው።በአንጻራዊነት እንደ አጠቃላይ ያለው ነገር የተሻለ ነው ለማለት ያስችላል።አዲስ ዘመን፡- ማለፋችሁን ተከትሎስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምን አደረገላችሁ? ማስተር አዲስ፡- እስካሁን ምንም የተደረገልን ነገር የለም፡፡ አዲስ ዘመን፡- ከሰለሞን ባሻገር በአፍሪካ ደረጃ ውጤት ያስመዘገቡ ስፖርተኞች ተስፋ ቢጣልባቸውም አሁን ላይ አናያቸውም ምክኒያቱ ምንድነው? ማስተር አዲስ፡- በእኛ ስፖርት ችግሩ የክለቦች አለመኖር ነው፤ ስለዚህም ወጣቶቹ ስራ ሳይሰሩና ትምህርት ሳይማሩ ስፖርቱ ላይ ብቻ ተሳታፊ እየሆኑ መቆየት አስቸጋሪ ነው።ብዙዎቹ ሰልጣኞች ሌላ ገቢ ስለሌላቸው ከብሄራዊ ቡድን በኋላ ወደ ሌላ ነገር ይሰማራሉ፣ አሊያም ስፖርቱን ይተውታል።ስለዚህም ፌዴሬሽኑ አሁን የመጣው ውጤት ላይ ተመርኩዞ በርካታ ስራዎችን ማከናወንና የማስተዋወቅ ስራ ይጠበቅበታል።በመገናኛ ብዙሃን በኩልም አበረታች የሆኑ ስራዎች በይበልጥ መሰራት ተገቢ ነው።አዲስ ዘመን፡- በኢትዮጵያ እጅግ ተዘውታሪ ከሆኑ ስፖርቶች መካከል የማርሻል አርት ስፖርቶች ተጠቃሽ ናቸው።ነገር ግን በሺዎች ከሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ከዓመታት በኋላ ነው አንድ ስፖርተኛ ያገኘነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? ማስተር አዲስ፡- ከሩቅ ሆኖ ሲታይ ነገሮች ተመቻችተው ይመስላል፤ ነገር ግን እንደ ሌሎች አገሮች ስፖርቱ ኢንቨስት እየተደረገበት አይደለም።ሌሎች አገራት ዝግጅት የሚያደርጉት ለዓመታት ነው፤ በተለያዩ ውድድሮች ላይም ተሳታፊ በመሆን አቅማቸውን ይፈትሻሉ።እኛጋ ግን በዚያ ደረጃ እየሄደ አይደለም፤ ከስር በርካታ ማሰልጠኛ ማዕከላት ይኑሩ እንጂ ከዚያ የሚወጡትን ሰልጣኞች የሚያቅፍ ክለብ የለም።ለአብነት ያህል ከሰለሞን ጋር ዝግጅት የሚያደርግና በእርሱ ደረጃ የሚገኝ ስፖርተኛ ማግኘት ከባድ ነው።ወደ ሌሎች ክለቦች ሄደንም የወዳጅነት ልምምድ ለማድረግም ለእኛ ከባድ ነው።አዲስ ዘመን፡- በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ የተለየ እቅድ አላችሁ? ማስተር አዲስ፡- ከ20 ዓመት በፊት በተካሄደው የሲድኒ ኦሊምፒክ ላይ የመገኘት እድል ገጥሞኝ ነበር፤ ወቅቱ ቴኳንዶ የኦሊምፒክ ስፖርት የሆነበት ስለነበር ተጋባዥ በመሆን ነው የታደምኩት።የዚያኔ ለራሴ በኦሊምፒክ ተሳታፊ እንደምሆን ነግሬው ከዓመታት በኋላ ስኬታማ ሆኛለሁ።አራት ኦሊምፒኮችን ከሞከርኩ በኋላም በአምስተኛው እድል ቀንቶኛል።ወደ ቶኪዮ የምንሄደው ደግሞ ለተሳትፎ ሳይሆን ለማሸነፍ ነው።አዲስ ዘመን፡- የአገራችን በርካታ ፌዴሬሽኖች እንኳን ለ20 ዓመታት የአንድ ዓመት እቅድም ሲያወጡና ሲፈፅሙ አይታዩም፣ አንተ በግልህ ይህን አሳክተሃልና ከዚህ ምን መማር ይቻላል? ማስተር አዲስ፡- እኔ በተለያዩ አገራት ተዘዋውሬ እንደተመለከትኩት ከሆነ ለአንድ ስፖርት መሰረትም አስፈላጊውም አሰልጣኝ ነው።አሰልጣኞችን ለማብቃት ደግሞ ፌዴሬሽኖች መስራት ይገባቸዋል፤ ምክንያቱም አሰልጣኝ ሁሌም በልጦ መገኘት አለበት።መንግስትም የፌዴሬሽኖች በጀት ላይ ድጎማ ማድረጉ ተገቢ ነው፤ የሚሰሩትንም ማበረታታት ያስፈልጋል።ሌላው ነገር በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ መሆን ነው፤ ከዚያ በኋላ በደረጃ ወደ ዓለም ማውጣት ይቻላል።አዲስ ዘመን፡- እንዲህ አይነት ስኬቶች ሲመዘገቡ ከእውቅናና ማበረታቻ ጋር በተያያዘ ምን መደረግ ይኖርበታል ትላለህ? ማስተር አዲስ፡- ሁሌም ስለ አንድ ነገር መወራት ያለበት ውጤት ሲመጣ ብቻ መሆን የለበትም።ውጤት ባይመጣም ስፖርተኞች መበረታታት አለባቸው፤ ምክንያቱም በውድድር ዕለት በጥቂት አጋጣሚ ከውጤት ውጪ መሆን ይከተላል።በመሆኑም ውጣ ውረዱና ልፋቱ ሊታይ እንዲሁም ላሉበት ደረጃ በመብቃታቸው ሊበረታቱ ይገባል።ይህ ሲሆን ደግሞ ለቀጣይ መነሳትን ይፈጥራል። አዲስ ዘመን፡- ማስተር አዲስ ለሰጠኽን ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ማስተር አዲስ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 14 /2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=28968
6422e0e1a1c7d16245886023e13e7eb6
b85919181fd350bdcb22f9068b06c95f
ካናዳ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ እራሷን አገለለች
ስፖርት
ካናዳ በኮሮና ቫይረስ ስጋት በዚህ ዓመት ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ራሷን ማግለሏን ቢቢሲ ዘግቧል። ጃፓን ለማስተናገድ ለዓመታት ስትዘጋጅለት የነበረው የ2020ው ኦሊምፒክ ውድድር ከአራት ወራት በኋላ በሐምሌ ወር የሚካሄድ ቢሆንም በቫይረሱ ስርጭት ሳቢያ ላይካሄድ እንደሚችል ስጋት አድሯል፡፡ ኦሊምፒኩ ይካሄድም አይካሄድም በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ካናዳ ከኦሎምፒክ መድረክ ራሷን ከወዲሁ ማግለሏ ተረጋግጧል፡፡ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሊምፒክ ውድድሩ ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ እንደሚችል ከተናገሩ በኋላ ካናዳ ይህንን ውሳኔዋን ልትወስን መቻሏን የዘገበው ቢቢሲ ፤ካናዳ የጨዋታው ዋነኛ ተሳታፊ ከሚባሉት መካከል መሆኗን ገልጾ ፤እራሷን በማግለሏ በውድድሩ መካሄድ ላይ ተጨማሪ ጥርጣሬ ፈጥሯል ብሏል። የካናዳ የኦሊምፒክና ፓራኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔውን በተመለከተ እንደገለፀው፤ ከውድድሩ ለመውጣት ከውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከአትሌቶች፣ ከስፖርት ቡድኖችና ከካናዳ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ተመካክሯል፡፡ ኮሚቴው ጨምሮም ለዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ለዓለም አቀፉ የፓራኦሊምፒክ ኮሚቴና የዓለም የጤና ድርጅት የኦሊምፒክ ውድድሩ በአንድ ዓመት እንዲዘገይ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። «ውድድሩን ለሌላ ጊዜ በማሸጋገር ሂደት ውስጥ የሚያጋጥመውን ውስብስብ ሁኔታን ብንረዳውም፤ ምንም ነገር ከአትሌቶቻችንና ከዓለም ሕዝብ ጤናና ደህንነት የሚበልጥ አይሆንም» ሲል የካናዳ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫም አስታውቋል። ካናዳ በኦሊምፒክ መድረኩ አልሳተፍም ማለቷን ተከትሎ የአውስትራሊያ የኦሊምፒክ ቡድን ውሳኔውን በመደገፍ መግለጫ ማውጣቱን ቢቢሲ አስነብቧል። የአውስትራሊያ የኦሊምፒክ ቡድን እንዳለው አሁን ባለው ሁኔታ ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንደማይካሄድ ግልጽ እየሆነ በመምጣቱ ተሳታፊ አትሌቶች ለቀጣዩ ዓመት እንዲዘጋጁ ተነግሯቸዋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 15/ 2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29026
140f7f0aaf71057846ff7472b1a0bc11
c2c19c50dfe36b2204fac2582e0ac2fc
ስፖርቱ ስለምን ይሸበራል?!
ስፖርት
እኤአ ታኅሣሥ 31 ቀን 2019 በቻይና ዉሃን ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን የዓለም የጤና ድርጅት ማስታወቁን ተከትሎ የቻይና መንግሥት በአፋጣኝ የቫይረሱን ስርጭት በአጭሩ ለመቅጨት እርምጃ ወደ መውሰድ ገብቶ ነበር። የቫይረሱን ስርጭት እንደተባለው በቀላሉ ለመቆጣጠር ሳይቻል ቀርቷል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱ ወረርሽኝ ደረጃ መድረሱን ተከትሎ በዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ አደጋ ጥሏል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ለውጦችን ከማስተናገድ አልፎ ቆሞ ቀር ለመሆን ተገዷል፡፡ የስፖርት መገናኛ ብዙኃንም እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ መካሄድ አለማኬዱ ያለየለት ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ብቻ የዜና ግብዓታቸው የሆነ መስሏል፡፡ ዓለም በእንዲህ ዓይነት አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ ለረጅም ጊዜ ደረቅ አቋም መያዙ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣትና የአንድ ሀገር ስጋት ከመሆን ወደ ዓለም አቀፍ ስጋትነት እያደገ መምጣት ነገሮችን እንዲቀየሩ አድርጓል፡፡ በኦሊምፒክ መድረክ የሚሳተፍ አገራት «በመድረኩ እንሳተፍ» ወደሚል ውሳኔ ላይ እንዲደርሱም አድርጓል። የ2020 ኦሊምፒክ መካሄድ የለበትም የሚሉ ሀሳቦች ቀስ በቀስ መነሳታቸውም ውድድሩ ይራዘም የሚሉ ድምጾች ከቀን ወደ ቀን ብዛትና ጉልበት እንዲያገኙ አቅም ፈጥሮላቸዋል፡፡ የኦሊምፒክ መድረኩ የማይራዘም ከሆነ ስፖርተኞቻችንን ለአደጋ አናጋልጥም፣ ዓለም በጭንቅ ውስጥ እያለች ከሚካሄደው የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ይቅርብን ያሉ እንደ ካናዳ ያሉ አገራት ራሳቸውን እስከማግለል ደርሰዋል። የካናዳን እግር በመከተል እንደ አውስትራሊያ ያሉ አንዳንድ አገራት ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያም የተሳትፎ ጉዳይ በአንድ ልብ ውሳኔ መስጠት ሳይቻል ቀርቶ ከፍተኛ ውዝግብ እስከማስነሳት የደረሰ ነበር። «የኢትዮጵያ አትሌቶች በውድድሩ ለመሳተፍ አንድ ላይ ሆቴል ገብተው ዝግጅት መጀመር አለባቸው የለባቸውም» በሚል በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መካከል ብርቱ የሆነ እሰጣ አገባ መፈጠሩ አይዘነጋም፡፡ ይሁን እንጂ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከቀናት በፊት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለአንድ ዓመት ማራዘሙን ተከትሎ በሁለቱ አካላት መካከል የነበረው የሃሳብ ልዩነት መቋጫ አግኝቷል፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት አመራሮች መካከል ሰሞነኛው ውዝግብ ዓለም አቀፉ ኮሚቴ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የረገበ ይምሰል እንጂ ነገ እንደ አዲስ አለመነሳቱን በርካቶች ይጠራጠሩታል፡፡ በሁለት ጎራ የተቧደኑ የስፖርት አመራሮች ውዝግብ ከየት ተነሳ?ብለን በመጠየቅ ወደ ኋላ መለሰ ብለን የተፈጠረውን ጉዳይ እንመርምር። ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አዱላላ ሪዞርት፣የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዝግ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቷል። ወቅቱ ደግሞ የዓለም አገራት በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በጎ መልክ ለማስያዝ ሽርጉድ እያሉ የሚገኙበት ነው። የኦሊምፒክ ኮሚቴ በዝግ ስብሰባ የቶኪዮ ኦሊምፒክን መሠረት ያደረገ ውሳኔን ይዞ ከመምጣት ይልቅ፤ «የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የሥራ አመራር ቦርድ የአገልግሎት ዘመንና ተቋሙን በዋና ጸሐፊነት እንዲመራ፣ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የሥራ አመራር ቦርድ የቆይታ ጊዜ ከአራት ዓመት ወደ ስምንት ዓመት እንዲሻሻል ተደርጓል» የሚል ነበር። የኦሊምፒክ ኮሚቴ ይሄንኑ ውሳኔውን ተከትሎ ኮሚቴው ስፖርቱን ለማሳደግ የያዘውን ወንበር የሥልጣን ጊዜውን ለማሳደግ እየተውተረተረ መሆኑን አሳዛኝ እንደሆነ ከተለያዩ አካላት ትችቶች ሲሰነዘሩበት ነበር። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዚህ ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ጉባዔው ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮች ተገቢነት ላይ ‹‹አልተስማማሁም›› ሲል ተቃውሞውን አሳውቋል፡፡ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የፌዴሬሽኑን ሀሳብ በመደገፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ሊታረም እንደሚገባ እስከ ማስገንዘብ ደርሶም ነበር። በዚህ መልክ የሚደረግ ሙግት ስፖርቱን መሠረት በማድረግ እንዲህ ዓይነት የሀሳብ ተቃርኖዎች የሚበረታቱ ቢሆንም፤ የስፖርቱ አመራሮች በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በመውጣት የሚሰጧቸው ምላሾችና የቃላት ልውውጦች ስፖርቱን መሠረት ያደረጉ አልነበሩም። በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ በኩል በወቅቱ ይሰጧቸው በነበሩት ቃለ ምልልሶች ይሄንኑ በሚገባ የሚያንፀባርቁ ነበሩ። ስፖርቱን የሚመሩ ሌሎች አመራሮች የሚሰጡ አስተያየቶች ተመሳሳይ የነበሩ ሲሆን፤ ይህም ስፖርቱን መሠረት ያደረገ ቅራኔ አለመሆኑን በተጨባጭ መገንዘብ ያስችላል። ከስፖርቱ አመራሮች ውዝግብ ጀርባ ያለው ሴራ እንዳለ ሆኖ በክስተቱ ብዙዎችን ማስቆጣቱን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር። የስፖርት አመራሮቹ ሲወዛገቡበት የነበረበት ወቅት ለቁጣው ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ዙሪያ ከማተኮር ይልቅ፤ ባልተገባ ትርምስና ሽኩቻ ስፖርቱን ለመጥቀም ወይስ ለመጉዳት? ያስባለም ነበር። በዚህ ደረጃ ቅሬታን ካስነሳ በኋላ በሁለቱ ጎራ የነበረው ፀብ በይደር እንዲቆይ በማድረግ ተቋማቱ ትኩረታቸውን ወደ ኦሊምፒክ ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር፡፡ ስፖርቱን የማሸበሩ ዜና ግን ዳግመኛ ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ተፈጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቶኪዮ 2020 አሊምፒክ ላይ ለሚደረገው ዝግጅትና ተሳትፎ በሚመለከት ባለድርሻ አካላትን ጋር ያዘጋጀው የምክክር መድረክ ለዚህ እንደመነሻ ሆኗል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ‹‹በመድረኩ እንድንሳተፍ መልዕክት አልደረሰኝም›› ሲል ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ትልቁን ባለድርሻ አካል ሳያሳትፍ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱ ቅር መሰኘቱን አስታውቋል። አጋጣሚውም የሁለቱ ተቋማት ቁርሾ ለኦሊምፒክ እየተደረገ ያለው ዝግጅት በተናጠል እንዲሆን በር ከፍቷል፡፡ «በዝሆኖች ፀብ የሚጎዳው ሳሩ ነው» እንደሚባለው በስፖርቱ አመራሮች ሽኩቻ አገሪቷ ዋጋ እንዳትከፍል መፍትሄ መስጠት አስፈላጊ ቢሆንም በዝምታ ታልፏል፡፡ የአመራሮቹ ቁርሾ መፍትሄ አለማግኘቱን ተከትሎ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ ፤ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት እንደሚካሄድ ገልጿል፡፡ በዚህ መሠረት አትሌቲክሱን ጨምሮ ለቶኪዮ 2020 የተመረጡ ብሔራዊ አትሌቶች ዝግጅት መጀመር እንዳለባቸው አስታወቀ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ደግሞ ፤ «የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሔ ሳያገኝ ብሔራዊ አትሌቶችን በሆቴል አሰባስቦ ዝግጅት ማድረጉ አደጋ አለው» ሲል አስገነዘበ። ለብሔራዊ አትሌቶች የተደረገው ጥሪን ኃላፊነት የጎደለው እንደሆነ በመሞገት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ውሳኔ ፊት ለፊት ተጋፈጠ። የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አቋም እንደፀና የኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔው ተገቢና የማይቀለበስ መሆኑን አቋም በመያዝ ፍጥጫ ውስጥ ገቡ። በመጨረሻም ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ እንዲሰረዝ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ማስታወቁ ተከትሎ፤ በስፖርት አመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ግብ ግብ ረገበ። ይህ ሽኩቻ እንዳለፉት ጊዜያቶች ተዳፈነ እንጂ አልጠፋም፡፡ ነገ እንደረመጥ የሚቆሰቁሰው አንድ አካል እንደሚኖር ሁለቱ አካላት አንዴ ሲሻኮቱ አንዴም ተስማማን እያሉ ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ እንደሚባለው መሆናቸውን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ለዚህም የሁለቱም ተቋሞች የበላይ የሆነው ስፖርት ኮሚሽን ኦሊምፒክ ሲመጣ ሳይሆን ከወዲሁ የሚስማሙበትን መንገድ መፈለግ እንዳለበት ይታመናል፡፡ በግለሰቦች ፍጥጫና የግል ፍላጎት ትልቁ የአገር ገፅታ ኦሊምፒክ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የነገ ሳይሆን የዛሬ ጉዳይ ነው፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 18/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29263
67b01f858c38d6d0c4efe46d58c9437f
ba98f9daf5ec70deee510e34ba8b92b6
የማይቀረው ውሳኔ ተወስኗል
ስፖርት
የመላው ዓለም ሕዝብ ትኩረትና ጭንቀት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ፈጣንና አስደንጋጭ ስርጭት የተነሳ መደበኛ እንቅስቃሴዎች በብዙ የዓለማችን አገራት ተገተዋል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ለውጦችን ከማስተናገድ አልፎ ሽባ ሆኗል። የስፖርት መገናኛ ብዙኃንም በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ በማጠንጠን ቆመዋል። ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የሁሉም የስፖርት ቤተሰብ ልብ አንጠልጣይ ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል። ዓለም በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ ድርቅ ማለቱ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ያም ሆኖ የዓለም አቀፍ ኮሚቴውን ደረቅ አቋም የሚፈታተን አዲስ ዜና ከየአቅጣጫው ብቅ ማለቱ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠሩ አልቀረም። በተለይም ካናዳና አውስትራሊያን የመሳሰሉ አገራት ከቀናት በፊት ራሳቸውን ከኦሊምፒክ እንዳገለሉ መግለፃቸውን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከግትር አቋሙ እየተለሳለሰ እንዲመጣ አስገድዶታል። ፈረንሳይና እንግሊዝን የመሳሰሉ አገራትም ዓለም አቀፍ ኮሚቴው በአስቸኳይ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ መጠየቃቸውን ተከትሎ ኦሊምፒኩ ላይ ለውጥ ስለመኖሩ በርካቶችን እርግጠኛ ያደረገ ነበር። የኦሊምፒክ ትልቁ ባለድርሻ አካል የዓለም አትሌቲክስ ከቀናት በፊት የቶኪዮ ኦሊምፒክ እንዲራዘም ጥያቄ ማሳቱን ተከትሎም በቅርቡ አዲስ ነገር እንዲጠበቅ አድርጓል። የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮ ኦሊምፒኩ ወደ 2021 የሚሸጋገር ከሆነ በኦሬገን አሜሪካ በተመሳሳይ ወቅት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወደ ሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ እና ዝግጁ መሆናቸውን ለኮሚቴው ባስገቡት ‹‹ውድድሩ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍልን›› መጠየቂያ ደብዳቤያቸው ማረጋገጣቸውም ኦሊምፒኩ እንደሚራዘም ያረጋገጠ ርምጃ ነበር። ይህ ሁሉ ተፅዕኖ የተፈጠረበት የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴም እየመረረውም ቢሆን ውድድሩን ወደ 2021 ለማስተላለፍ ያስገደደውን የማይቀር ውሳኔ ማሳለፉን አሳው ቋል። የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ከትናት በስቲያ ምሽት ባደረጉት የቪዲዮ ኮንፍረንስ ከቫይረሱ ስርጭት ጋር በተያያዘ ያለውን አደጋ ከግምት በማስገባት ኦሊምፒኩ ወደ 2021 እንዲራዘም ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አሳውቀዋል። ኦሊም ፒኩ ወደ 2021 መሸጋገሩ ይጠቀስ እንጂ በየትኛው ወቅት እንደሚካሄድ የተገለፀ ነገር የለም። ያም ሆኖ የበጋ ኦሊምፒክ እንደመሆኑ መጠን በቀጣይ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ላይ ሊካሄድ እንደሚችል ተገምቷል። ይህንን ውሳኔ ተከትሎም የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከጦርነት ውጪ ባሉ ምክንያቶች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተላለፈ ሊሆን ችሏል። ኦሊምፒክ ከጤና ስጋት ጋር የተያያዘ ባይሆንም በተለያዩ ጊዜዎች የመራዘም፣የመሰረዝና የቦታ ለውጥ ሲደረግበት ታይቷል። እኤአ የ1916 የበጋ ኦሊምፒክ በጀርመን በርሊን ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት በአንደኛ የዓለም ጦርነት ሳቢያ ተሰርዟል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም የ1940 የክረምት ኦሊምፒክና የ1944 የበጋ ኦሊምፒክ ውድድሮች የመሰረዝ ዕድል ገጥሟቸዋል። እኤአ የ1976 የክረምት ኦሊምፒክም በዴንቨር ኮሎራዶ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የኮሎራዶ ግዛት ሕዝብ ለውድድሩ የሚወጣውን ወጪ በመቃወሙ ውድድሩ የቦታ ለውጥ ተደርጎበት በአውስትራሊያ ኢንስብረክ ለመካሄድ ተገዷል። ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ በወቅቱ እንደዘገበው የኮሎራዶው ኦሊምፒክ የቦታ ለውጥ እንዲደረግበት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ውድድሩ ከመካሄዱ ከሦስት ዓመታት አስቀድሞ ነበር። ይህም ከጥንት ጀምሮ የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የቦታ ለውጥ ለማድረግ ቢያንስ ከሁለት ዓመት በፊት ውሳኔ ላይ መደረስ ይኖርበታል። የሪዮ 2016 ኦሊምፒክም ከመድረሱ ከዓመታት በፊት የዚካ ቫይረስ ስጋት መሆኑ ቢታወቅ ሊሰረዝ፣ሊራዘምና የቦታ ለውጥ ሊደረግበት ይችል እንደነበር በርካቶች አስተያየት ሲሰጡ ይስተዋላል። የዚካ ቫይረስ የሪዮ ኦሊምፒክ ስጋት መሆኑ የታወቀው ውድድሩ ከመካሄዱ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መታወቁ የቫይረሱ ስርጭት ያን ያህል ስጋት ካለመሆኑ ጋር ተደምሮ የመሰረዝ፣ የመራዘምና የቦታ ለውጥ ሳይደረግበት ለመቅረቱ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የሚያብራሩም ጥቂት አይደሉም። ዘንድሮም ከአራት ዓመት በኋላ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከጥር ጀምሮ በቻይና በተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ተመሳሳይ አደጋ ሊራዘም በቅቷል። አዲስ ዘመን መጋቢት 17/2012
https://www.press.et/Ama/?p=29163
af74d61e304e94439a7791f53e23d53f
181f65790ddfc27c25d67d6cdd582fd3
ለእጅ ኳስ ስፖርት 40 ዓመታት የተዘረጉ እጆች
ስፖርት
በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ስፖርት ታሪክ ውስጥ አንቱታን ማትረፍ ችለዋል። የእጅ ኳስ ስፖርትና እርሳቸው የሚነጣጠሉ አለመሆኑን ብዙዎች ይመሰክሩላቸው። ለእጅ ኳስ ስፖርት ጥልቅ ፍቅር ያላቸው ኢንስትራክተር አሰፋ ገለቱ። በእጅ ኳስ ስፖርት በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ተጫውተው ከማለፍ ባሻገር በርካታ ወጣት አሰልጣኞችን ማፍራት መቻላቸው ለዚህ ክብር እንዲበቁ አድርጓል። የኢንስትራክተር አሰፋ የስፖርት ህይወት ጅማሮ ከ40 ዓመታት በፊት እንደነበር እንዲህ ይናገራሉ። «ስፖርታዊ እንቅስቃሴን የጀመርኩት በሰፈር ውስጥ ሲሆን ከልጅነት ጀምሮ ንቁ ተሳትፎ አደርግ ነበር። በስፖርቱ የነበረው ተሳትፎ ግን እግር ኳስን ያስቀደመ ነው።›› ኢንስትራክተር አሰፋ ከእግር ኳሱ እኩል ቅርጫት ኳስ እና እጅ ኳስን ይጫወቱም ነበር። በተለያዩ ስፖርቶች ተወጥሮ የነበረው የስፖርት ፍቅር በአንድ አጋጣሚ ነበር ወደ እጅ ኳሱ ብቻ ሊያመዝን እንደቻለ የሚናገሩት፡፡ ‹‹በወቅቱ ከአዲስ አባባ ፖሊስ የእጅ ኳስ ቡድን ጋር በመሆን እጅ ኳስ እጫወት ነበር። ከቡድኑ ጋር አደርገው በነበረው እንቅስቃሴ ከቡድኑ ተጫዋቾች ብሎም አሰልጣኞች በእጅ ኳሱ እንድገፋበት አድርጎኛል። በዚህ ግፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ የእጅ ኳስ ቡድንን በመቀላቀል ወደ እጅ ኳስ ስፖርት ሙሉ ለሙሉ መግባት ቻልኩ›› ይላሉ። ኢንስትራክተር አሰፋና እጅ ኳስ በዚህ መልኩ ትውውቅ ካደረጉ በኋላ በበርካታ የከተማ አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ውድድሮች ላይ የመጫወት እድሎችን አገኙ። በእጅ ኳሱ የተጫዋችነት ሂደት ውስጥ ከክለብ ባለፈ እስከ ብሔራዊ ቡድን ውክልና ዘልቋል፡፡ ለኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ብሄራዊ ቡድን በመመረጥ ለአምስት ዓመታት እስከ መጫወትም ደርሰዋል፡፡ ኢንስትራክተር አሰፋ በተጫዋችነት ብቻ 20 ዓመታት ማሳለፍ የቻሉ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ «በተጫዋችነት ዘመኔ የማይቆጩኝን 20 ዓመታትን አሳልፌያለሁ። በስፖርቱ ሀገሬን በመወከል በብሄራዊ ቡድን ደረጃ የተጫወትኩበት እነኚህ ዓመታት ለእኔ ልዩ ኩራቴና ትዝታዎቼ ነበሩ» ሲሉ ያለፈውን የተጫዋችነት ዘመን ያስታውሳሉ፡፡ ለሀገር ክብርና ፍቅር እንዳላቸው ደጋግመው የሚናገሩት ኢንስትራከተር አሰፋ የተጫዋችነት ዘመናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ አሰልጣኝነት ነበር የተሸጋገሩት። ኢንስትራከተር አሰፋ በእጅ ኳሱ አሰልጣኝ በመሆን በአዲስ መንፈስ እንዴት ብቅ እንዳሉ ሲያስታውሱ፤ «የእጅ ኳስ አሰልጣኝነትን የአዲስ አበባ ፖሊስ እጅ ኳስ ቡድን በመያዝ ነበረ የተጀመረው። ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በርካታ ጊዜያትን ካሳለፍኩኝ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻዬ የነበረው ኦሜድላ ነበር» ይላሉ። የኦሜድላን እጅ ኳስ ቡድን ወደ ማሰልጠኑ መሸጋገራቸው ለስፖርቱ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ እንዲጨምር እንዳደረገላቸው ይናገራሉ። በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ታሪክ በተለይ በ70ዎቹ ውስጥ በጥንካሬያቸው ከሚጠቀሱት ክለቦች መካከል ኦሜድላ ዋነኛው ነው። ከክለቡ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስፖርቱን ወደ ፊት ማራመድ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት እንዳስቻላቸው ኢንስትራክተር አሰፋ ይናገራሉ፡፡ በአሰልጣኝነት ቆይታቸው ጊዜ እየተመዘገቡ ባሉ ውጤቶች ደስተኛ የነበሩት ኢንስትራክተር አሰፋ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የእጅ ኳስ ስፖርት መዳከምና ውጤት አልባ እየሆነ መምጣት በቁጭት እንዲሞሉ ያደረጋቸው ነበር። በወቅቱ ስፖርቱ ረጅም ዓመት እንደቆየ ባለሙያ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባ ለሚመለከተው አካል ሃሳብ እስከ ማቀበል መድረሳቸውን ያስታውሳሉ፡፡ በሃሳብ ብቻ መወሰን ግን አልፈለጉም ነበር ። ከኦሜድላ ክለብ ጋር የነበራቸውን ጉዞ በመግታት መፍትሄው ላይ ወደ ማነጣጠር አዘነበሉ፡፡ ስፖርቱን መሰረት አሳጥቶ ውጤት አልባ ያደረገው የተተኪ ችግር እንደሆነ በማጥናት ታዳጊዎች ላይ መስራት ይጀምራሉ፡፡ በ1990 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤት ያጣውን የእጅ ኳስ ስፖርት ለመታደግ ታዳጊዎችን መሰረት ያደረገውን ተግባር በቁጭት ጀመሩ። ከአዲስ አበባ እጅ ኳስ ፌዴሬሽንና ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር በመቀናጀት ታዳጊዎችን በፕሮጀክት ደረጃ በማቀፍ ስልጠናዎችን በስፋት መስጠት ተያያዙት፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም ውጤታማ ስራዎች ማከናወን ቻሉ፡፡ የኢንስትራክተር አሰፋ ታዳጊዎችን መሰረት ያደረገ ስልጠና በትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ወደ መስራት ሽግግር ያደረገ ነበር። በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የአንድኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በመመልመል የእጅ ኳስ ስፖርት ወደ ማሰልጠን ነበር የተሸጋገሩት። ኢንስትራክተር አሰፋ ትምህርት ቤቶች ላይ መሰረት በማድረግ በርካታ ታዳጊዎችን አሰልጥነው ማስመረቅ እንደቻሉ ይናገራሉ። «የአምናውን ብቻ ብናስታውስ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆኑ 300 ታዳጊዎችን በፕሮጀክት ደረጃ በማሰልጠን ተመርቀዋል።በዘንድሮ ዓመትም በተመሳሳይ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ20 በላይ መንታዎች ሰልጠነው ተመርቀዋል» ሲሉ ይናገራሉ። በእጅ ኳስ ስፖርት ውስጥ ትልቅ አሻራ ማሳረፍ የቻሉት ኢንስትራክተር አሰፋ፤ የስፖርት ህይወት ጉዞን አስደናቂ የሚያደርገው ለስፖርቱ እድገት ታዳጊዎችን መሰረት አድርጎ መስራት እንደሚበጅ በማመን በሰሩት ውጤታማ ተግባር የተቸራቸው ምስጋና ሳያባራ፤ በሀገራችን ባልተለመደ መልኩ መስማት የተሳናቸውን ዜጎች እጅ ኳስ ለማሰልጠን የሚያስችል ንድፈ ሀሳብ በመያዝ መስማት የተሳናቸውን ታዳጊዎች ማሰልጠን መጀመራቸው ነው፡፡ ኢንስትራክተር አሰፋ ለዚህ እንደመነሻ የነበራቸውን አጋጣሚ ሲያስረዱ፤« በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ስልጠና በሚሰጡበት ወቅት የታዘብኳቸው ነገሮች ወደዚህ እንድገባ ያደረጉኝ። ለተማሪዎች እጅ ኳስ ስልጠና በምሰጥበት ወቅት እዛ አካባቢ መስማት የተሳናቸው እኔ የምሰጠውን ስልጠና ቁጭ ብለው ይመለከቱ ነበር። በእነዚህ ታዳጊዎች ተግባር ውስጤ ተነሳሳ። ስልጠናውን ወደ መስጠት ከመሸጋገሬ በፊት ግን ከተማሪዎቹ ጋር ለመግባባት እንድችል የምልክት ቋንቋ መቻል አስፈላጊ ነበር። በመሆኑም ቋንቋውን ለሶስት ወራት ያህል ተማርኩ። በዚህ መሰረት በአዲስ አበባ መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች ከሚያስተምሩ ሶስት ትምህርት ቤቶች ጋር በመነጋገር እንዲሰለጥኑ ማድረግ ችያለሁ» ይላሉ፡፡ ኢንስትራክተር አሰፋ በእጅ ኳስ ስፖርት ውስጥ ያከናወኗቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ቢሆኑም እሳቸው ዛሬም በአዲስ ወኔ ለመስራት ያሰቧቸው ስራዎች መኖራቸውን ይናገራሉ። «ስፖርት ለእኔ ህይወቴ ነው፤ ልጅነቴን ፣ ወጣትነቴን ከእጅ ኳስ ስፖርት ሳልነጠል አሳልፌያለሁ። ዛሬም ነጭ ፀጉር አብቅዬም ከስፖርቱ መለየት አልሻም። ስፖርቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ አማራጭ ያልኳቸውን ተግባራት ለማከናወን አልተኛም» የሚል ጽኑ እምነት አላቸው። ስፖርቱን ለማሳደግ እንደ እርሳቸው ሁሉ በርካታ ባለሙያዎች ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውና ለዚህ ደግሞ ስፖርቱን ከሚመሩት አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ የሚገባ መሆኑን ማስገንዘብ እንደሚፈልጉ ያብራራሉ፡፡አዲስ ዘመን መጋቢት 15/ 2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29023
a4634985fc9834dce40302640ba07231
c90adf0b7116e3eb91ba588d29379983
«ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ዓይነ ሥውርነት ሳይሆን የልብ ሥውርነት ነው” – ዶክተር ሙሉነሽ አበበ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- «ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ዓይነ ሥውርነት ሳይሆን የልብ ሥውርነት ነው» ሲሉ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ተናገሩ። «አካል ጉዳተኞችን አካታች፣ ምቹ እና ዘላቂ የተሻለ ዓለምን በድኅረ ኮቪድ 19 እንገንባ» በሚል መሪ ሐሳብ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም ለ29ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ28ኛ ጊዜ በባሕር ዳር ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ እንደሚያመለክተው ዶክተር ሙሉነሽ በበዓሉ ሥነሥርዓት ወቅት እንደተናገሩት፤ አካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው ሙሉ አካል እንዳላቸው ሰዎች እኩል ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ መሥራት ይችላሉ። ለዚህም በርካታ ምስክሮች አሉ። ዋናው ጉዳይ ግን ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ዓይነ ሥውርነት ሳይሆን የልብ ሥውርነት ነው። ልባቸው የተሠወሩት እኩያን ከሰው ስብእና ውጪ በመሆን ወገኖቻችንን በአሰቃቂ ሁኔታ እየጨፈጨፉ ይገኛሉ። በመሆኑም ከዚህ መጥፎ ተግባር ለመውጣት ሁሉም ቆም ብሎ ማሰብ ይጠበቅበታል።የፌዴራል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ለዓለማችን ታላላቅ አስተዋጽኦ አበርክተው ያለፉ አካል ጉዳተኞች ስማቸው ከመቃብር በላይ ሆኖ ሁሌም ሲዘከሩ ይኖራሉ። ለሀገራችንም እድገት እና ብልጽግና አስተዋጽኦ እያደረጉ የሚገኙ በርካታ አካል ጉዳተኞች አሉ። በመሆኑም አካል ጉዳተኞች ጠንክራችሁ ከሠራችሁ «ለሀገራችን ጠቃሚ እንጂ ተጠቃሚ አንሆንም» የሚለውን አስተሳሰብ መያዝ ይገባል። በሀገራችን የአካል ጉዳተኞች አስገዳጅ ሕግ አልነበረም፤ በዚህ ዓመት ግን የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ ይውላል፤ ይህም መንግሥት ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት መስጠቱን ያመላክታል።የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይነህ ጉጆ በበኩላቸው፣ የበዓሉ ተቀዳሚ ዓላማ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ያለውን የተዛባ አስተሳሰብ ግንዛቤ ፈጥሮ ማስተካከል መሆኑን ጠቁመው፣ ፌዴሬሽኑም የመንግሥት አካላት ስለአካል ጉዳተኞች ግንዛቤ ኖሯቸው በትምህርት፣ በጤና፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በፖለቲካ እና በማኅበራዊ ተግባራት አካትተው እንዲሠሩ የግንዛቤ ፈጠራ እየሠራ ነው።
https://www.press.et/Ama/?p=38342
2ed56a19309c9dddae2f7bac04989cb2
53b0a418ce57380fec0b2127aadfb596
ኤጀንሲው ከኦፓል የወጪ ንግድ 210 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት፤ ለ604ሺ በላይ ዜጎችም የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል
ሀገር አቀፍ ዜና
 ኤጀንሲው ከኦፓል የወጪ ንግድ 210 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት፤ ለ604ሺ በላይ ዜጎችም የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል  አስናቀ ፀጋዬአዲስ አበባ፡- ከኦፓል ማዕድን የወጪ ንግድ 210 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት በአስር ዓመቱ መሪ እቅድ ውስጥ አካቶ እየሰራ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ገለፀ። በዚሁ ዘርፍም ለ604 ሺ 210 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱን ተናግሯል።፡የአማራ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይታየው ተስፋሁን ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ ኤጀንሲው ከኦፓል ማዕድን የወጪ ንግድ በአስር ዓመቱ መሪ አቅድ ውስጥ 210 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አቅዷል። ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃርም በኦፓል ማዕድን ማምረት ሥራ ለ604 ሺ 210 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አስቧል።እንደ ኃላፊው ገለፃ፤ ከውጪ ምንዛሬ ገቢ በተጨማሪ በዚሁ የአስር ዓመት መሪ እቅድ ውስጥ ኤጀሲው ከሮያሊቲና ከአገልግሎት ክፍያ 1 ቢሊዮን 117 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ወጥኗል። ይህንኑ እቅድ ለማሳካትም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ለሚገኙ የዘርፉ ፈፃሚዎች ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙና በቀጣይም ስልጠናው ለሌሎች በተከታታይ የሚሰጥ ይሆናል። በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ኤጀንሲው ሃያ የሚሆኑ የምርመራና የማምረት ፍቃድ ለአልሚዎች መስጠቱንም የጠቀሱት ኃላፊው፤ ኅብረተሰቡና ባለሀብቱም ጥቅሙን በመረዳት ወደዚህ የማዕድን ማምረት ሥራ እየተሳበ እንደሚገኝም አመልክተዋል። ይህም በቀጣይ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል። በ2013 ዓ.ም ብቻ ባጠቃላይ 44 ሺ 125 ለሚሆኑ ዜጎች በማዕድን ዘርፍ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ኤጀንሲው እቅድ መያዙንም አያይዘው የገለፁት ኃላፊው፤ ከውጭ ምንዛሬ አኳያ 18 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘትና ከሮያሊቲና አገልግሎት ክፍያም 100 ሚሊዮን ብር የሀገር ውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ ማሰቡን ጠቁመዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=38345
767ccf285c06c8758d641e136b630722
2b5be8284f231b7ecfc8a45403e518f0
ኢንስቲትዩቱ በአሥር ዓመቱ መጨረሻ ዓመታዊ የኤክስፖርት ገቢን 1ነጥብ2 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየሰራ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
ውብሸት ሰንደቁአዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ወደውጭ ከምትልካቸው የኬሚካልና ኢንዱስትሪ ግብዓት ዘርፍ ምርቶች በአስር ዓመቱ መጨረሻ ዓመታዊ የወጪ ንግድ ገቢዋን ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማድረስ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሀላላ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ከኤክስፖርት በዓመት አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታስቧል። ይህንን ግብ ለማሳካትም በየዓመቱ በአማካኝ 120 ሚሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ገቢ አፈጻጸም ማስመዝገብ ይጠበቃል፡፡የኤክስፖርት ሥራ በዋናነት ሀገሪቷ እየተጠቀመች ካለችው በላይ ማምረትን ይጠይቃል ያሉት አቶ ሳሙኤል፤ በኦጋዴን አካባቢ የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ በከፍተኛ ደረጃ ለኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ምርት ምቹ መሆኑ ለዕቅዱ ስኬት መልካም አጋጣሚዎችን እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ አስር ዓመታትም በዚህ ረገድ ከውጭ የሚገቡ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ ከመሸፈን አልፎ በዕቅዱ ማጠናቀቂያ ዓመት ላይ የዘርፉ የኤክስፖርት ገቢ 1ነጥብ2 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በቀጣይ አሥር ዓመታት የመሠረታዊ ኬሚካል የማምረት ሥራ የሚሠሩ ኢንዱስትሪዎችን የማስፋት ሥራ በትኩረት እንደሚሠራና ይህም ያላለቀላቸው ግብዓቶች ከውጭ እያስመጡ ከመሥራት ይልቅ የሀገሪቱን የማዕድናትና የግብርና ግብዓቶችን መሠረት የሚያደርጉ ትላልቅና መሠረታዊ ኬሚካሎችን በሀገር ውስጥ ማምረት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ሥራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡ አቶ ሳሙኤል እንዳሉት፤ በስፋት ከፔትሮ ኬሚካል ውጤቶች የሚገኙ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ግብዓቶች የፕላስቲክ ወለል ንጣፎች፣ ፓይፖች እና የተለያዩ የቤቶች የማስዋቢያ ምርቶች በሀገር ውስጥ በስፋት እንዲመረቱ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ በተጨማሪም የአፈር ማዳበሪያ የሀገር ውስጥ ፍጆታ ተሸፍኖ ኤክስፖርት ለማድረግ እየተሠራ ይገኛል፡፡ ፔትሮ ኬሚካል ጋር በተያያዘ የብዙ ምርት ግብዓት መሆን የሚችሉ ጥሬ ዕቃዎችን የማምረት ሥራም ትኩረት እንደተሰጠና ሌሎች የስፔሻሊቲ ኬሚካሎችንም ማምረት በመጀመር ሰፊ ኤክስፖርት አቅም እንዲኖራት ይሠራል፡፡ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ያለ ኢንዱስትሪ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ግብዓት አምራቾች በጥሩ ሁኔታ እያደጉ ያሉ ሲሆን፤ በሀገር ውስጥ የሲሚንቶ ምርትን መተካት እንደተቻለው ሁሉ ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፉ ግብዓት የሆኑትን የእምነበረድ፣ የግራናይት፣ የቴራዞ፣ የጂብሰም እና የፊኒሽንግ ቁሶችን የማምረት አቅም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣ ነው፡፡ አብዛኛው ለነዚህ ምርቶች ግብዓት የሚውለው ነገር ከሀገር ውስጥ የሚገኝ ስለሆነ እነዚህን ግብዓቶች ተጠቅሞ በስፋት ለማምረት በትኩረት ይሠራል፡፡ይህንን ግብ ለማሳካት ደግሞ በየዓመቱ በአማካኝ 120 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከወጪ ንግድ ገቢ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚጠበቅ የታወቀ ሲሆን፤ ባለፉት አምሥት ዓመታትም 196 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው ምርት በኢንዱስትሪዎች መመረቱን እና ይህም በአማካይ ሲሰላ በየዓመቱ 39ነጥብ24 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ምርቶች መመረታቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2020
https://www.press.et/Ama/?p=38348
97f6ce62d77972ffc38c996ee8a92557
3baeae6bc0e7371f526fa3a836911ec6
ለስፖርት ማህበራት የሚላኩ አመራሮች በግለሰቦች ትውውቅ መሆን የለበትም
ስፖርት
የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ክልሎች ለሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት የሚላኩ አመራሮች በግለሰቦች ትውውቅና በተወሰኑ አካላት ፍላጎት ብቻ መሆን እንደሌለባቸው አስታወቀ። የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደተናገሩት፤ ክልሎች ለሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት አመራርነት የሚልኳቸውን ተወካዮች በተወሰኑ አካላት ፍላጎትና በግለሰቦች ትውውቅ መሆን የለበትም። በመሆኑም ለአመራርነት የሚላኩ ተወካዮች የተወከሉበትን ስፖርት ወደፊት ሊያሻግሩ ይችላሉ የሚለው በሚገባ ተተችቶ አሳታፊ በሆነ መልኩ ሊልኩ ይገባል ብለዋል። ለሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት የሚላኩ አመራሮች ምክንያታዊ አለመሆኑን ተከትሎ የሴቶችን በስፖርት ማህበራት የሴቶች ተሳትፎ ውስን እንዲሆን አድርጎታል። በሀገር አቀፍ ደረጃ 30 የስፖርት ማህበራት የሚገኙ ሲሆን በዚህ ውስጥ የሴቶች የአመራርነት ድርሻ ከ10 በመቶ አይበልጡም። ክልሎች በአብዛኛው የሚልኳቸው ዕጩ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ወንዶች በመሆናቸው ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል። ሴቶች በተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ በየደረጃው የሚገኙ እና የአመራርነት ዕድሉን ያገኙ ሴቶች ማሳየት ችለዋል። በስፖርቱ ዘርፍ ግን ክፍተት የሚታይ መሆኑን የገለጹት አቶ ኤልያስ፤ «ኮሚሽኑ በቀጣይ በትኩረት ከሚሰራቸው ሥራዎች አንዱ ሴቶች በስፖርት አደረጃጀቶች ውስጥ በበቂ ሁኔታ በአመራርነት እንዲሳተፉ ማድረግ ላይ ይሆናል። ለዚህ ደግሞ ከክልሎች ጋር ከመነጋገር ባሻገር በመመሪያ እና በአሠራር የሚደገፍ ይሆናል» ብለዋል። የሴቶች የአመራርነት ተሳትፎ ቢያንስ 30 በመቶ ሊሆን እንደሚገባ የኦሊምፒክ ቻርተርን ጨምሮ የዓለም አቀፍ የስፖርት ማህበራት ሕጎች ያስቀምጣሉ። በኮሚሽኑ የስፖርት ማህበራት ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ የአወጣው መመሪያ አንቀፅ 31 ንዑስ አንቀፅ 7 ይህን ሀሳብ የሚያጠናክር መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አዲስ ዘመን መጋቢት 18/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29266
53365e7e932af319fd569f726b34402b
f2cbdfb95e91f0871fe0229ac9269f50
“ በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያትም እንኳ፣ ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን የዜጎችን እና የተቋማትን የቅርብ ተሳትፎ የሚፈልጉ በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያትም እንኳ፣ ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን የዜጎችን እና የተቋማትን የቅርብ ተሳትፎ የሚፈልጉ በርካታ ርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳስታወቀቁት፤ የአስር ዓመቱ ብሔራዊ የልማት እቅድ ፍኖተ ብልጽግና ዘላቂ ሰላምን በሚያመጣ የልማት ጉዞን መሰረት ያደረገ ነው::ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን ደግሞ የዜጎችን እና የተቋማትን የቅርብ ተሳትፎ የሚፈልጉ በርካታ ርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ:: “ልማት ዘላቂ ሰላምን ያመጣል። የ10 ዓመት ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ፍኖተ ብልጽግና ይህንን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፤” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዕቅዱ ሰላምን እና የሕግ የበላይነትን ወሳኝ ግቦች አድርጎ ማስቀመጡ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል:: አያይዘውም፣ “በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያትም እንኳ፣ ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን የዜጎችን እና የተቋማትን የቅርብ ተሳትፎ የሚፈልጉ በርካታ ርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ፤” ሲሉ ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38376
5674f51ca4e8bb0178e5682c7af09399
1126c135988a9993dc3199738bcb5753
‹‹ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን እንደ እኔ ያሉ የፖርቲ አባል ያልሆኑ ግለሰቦች የተካተቱበት ስለሆነ አሁን ያለው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አቃፊ ነው›› – ዶክተር አሰፋ በቀለ የትግራይ ክልል መንገድና ትራንስፖርት አስተባባሪ
ሀገር አቀፍ ዜና
ክፍለዮሐንስ አንበርብር አዲስ አበባ፡- በትግራይ ክልል አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊና የተለያዩ የፖለቲካ አባላት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ያሳተፈ መሆኑን የትግራይ ክልል በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አሰፋ በቀለ ተናገሩ::ከአማራ ክልልና የፀጥታ አካላት ጋር በመነጋገር ከመቐለ አዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት መጀመሩም ተገልጿል::የትግራይ ክልል በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አሰፋ በቀለ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በትግራይ ክልል አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊና የተለያዩ ፖለቲካዊ እሳቤ ያዙ ሰዎችን ያቀፈ ነው::በዚህም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ ሆነው ህዝብን ለማገልገል ፍላጎት ያላቸውን አካላት ጭምር በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ውስጥ አካትተዋል:: ‹‹ቀደም ሲል የነበረው አሰራር ብዙ ጉድለት ነበረበት::አሁን ባለው አስዳደር ግን በፖለቲካ አመለካከት   ሳይገደብ ህዝብ ማገልገል ተችሏል፤” ያሉት ዶክተር አሰፋ፤ አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊ በመሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ አባላት በጊዜያዊ አስተዳደር ታቅፈው እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል::“እኔን ጨምሮ የፓርቲ አባል ያልሆንን ግለሰቦች ህዝቡን በማገልገል ላይ እንገኛለን›› ብለዋል:: “ህዝብ ለማገልገል የፖለቲካ ፓርቲ የበላይ መሆን አይጠበቅም” ያሉት ዶክተር አሰፋ፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በጣም የተሻለ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን እና የትግራይ ህዝብ ያጋጠመው ችግም ከየትኛው ፓርቲ በላይ መሆኑን ገልጸዋል:: በዚህ ወቅት ደግሞ ህዝብን ማገልገል ኩራት ነው ሲሉም ተናግረዋል::በዴሞክራሲ አኳያም በጣም የተሻለና አቀፊነት ስሜት ያለው እንደሆነ እና ሰዎች በአረዳዳቸው፣ የፖለቲካ ፓርቲነታቸው ሳይገለሉ በጊዜያዊ አስተዳደር መታቀፋቸው አበረታች እንደሆነ ጠቁመዋል:: እንደ ዶክተር አሰፋ ገለጻ፤ ቀደም ሲል ህዝቡ ከቤት ለመውጣት ስጋት የነበረውና ጦርነት ተመልሶ ይቀሰቀሳል በሚል እሳቤ እንቅስቃሴ ገታ ብሎ ነበር::ይሁንና የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቐለ ከገባ በኋላ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በአግባቡ ተጀምሯል::በአሁኑ ወቅትም ታክሲዎች በተሰጣቸው የጉዞ መስርመር አገልግሎት እየሰጡ ነው::ከታሪፍ አኳያ ማጋነን እና የተሰጠውን ቦታ አለመጠቀም ይስተዋል እንደነበርና ፌዴራል ፖሊስ፣ የትራፊክ ፖሊስና የክልሉ ፖሊስ ጋር የተቀናጀ ስራ በመጀመሩ በጣም የተሻሻለ ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል:: በአሁኑ ወቅት ደግሞ በዋናነት የማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ሲሆን፤ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትና የፌዴራል መንግስት መዋቅር ጋር በቅርበት እየሰሩም ነው::የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በተመለከተም ከፌዴራል ትራንስፖርት ጋር በመደዋወልና መረጃ በመለዋወጥ እየተሰራ ሲሆን አስፈላጊ በሆነ ቦታ እና ሁኔታ ሁሉ ድጋፍ ለማድረግም ቃል ገብተውላቸዋል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ከአማራ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመነጋገርም ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ትራንስፖርት መጀመሩን የገለጹት ዶክተር አሰፋ፤ በተጨማሪም ከመቀሌ ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎችም እንቅስቃሴ መጀመሩን አብራርተዋል:: የሀገር መከላከያ ሰራዊትም ፀጥታውን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝም ተናግረዋል:: በአሁኑ ወቅት ከውጭ አገር ጭምር ለእርሳቸው የሚደውሉላቸው ሰዎች መኖራቸውን የገለፁት ዶክተር አሰፋ፤ የሚደውሉላቸው አብዛኞቹ ሰዎችም ጊዜያዊ አስተዳደር የሚደግፉ መሆናቸውን ነው የገለጹት::ህዝቡን ለመታደግና ወደነበረበት ሠላም ለመመለስም ዳያስፖራው ከጎናችን እንደሆኑ እየነገሩን ነው ሲሉም አስረድተዋል:: ዶክተር አሰፋ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሙሉ ለሙሉ ካቢኔ አቋቁሞ ሥራ ያልጀመረ ሲሆን የቀሩ ካቢኔዎች ሲሟሉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ የሚገባ መሆኑን በመጠቆም፤ በአሁኑ ወቅት የዳያስፖራና ወጣት ምሁራን ተጋሩዎች ክልሉን መልሶ በማደራጀትና በመደገፍ ረገድ ሚናቸው የጎላ ስለሆነ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋልአዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38379
ee40f0e448763b77713e7a89cb07f901
e7584ff8435369f353abb110b2d103a6
በከተማው የክለቦች ቻምፒዮና ክብረወሰን ተሻሻለ
ስፖርት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓመታዊው ፔፕሲ የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለ37ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል።ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን የያዘው ውድድሩ በተለያዩ ርቀቶች የሩጫና ሜዳ ተግባራት አትሌቶችን በማፎካከር በርካታ ክብረወሰኖች እየተሻሻሉበት ይገኛል። በውድድሩ ሁለተኛ ቀን ውሎ ትናንት በተካሄደው የሴቶች አንደኛ ዲቪዚዮን አስር ሺ ሜትር ውድድር ክብረወሰን ተሰብሯል።በኢትዮጵያ ቻምፒዮና በአትሌት ለተሰንበት ግደይ 32፡10፡90 ተይዞ የነበረው የርቀቱ የኢትዮጵያ ክብረወሰን ዘንድሮ በአትሌት ዘይነባ ይመር በስድስት ሰከንድ ሊሻሻል ችሏል። በቻምፒዮናው ላይ በአንደኛ ዲቪዚዮን ከታቀፉ አምስት ክለቦች የተሳተፉ ሲሆን በሁለተኛ ዲቪዚዮን ከታቀፉ ሃያ ክለቦች የተውጣጡ በአጠቃላይ አንድ ሺ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።ውድድሩ ክለቦች የአትሌቶቻቸውን አቅም ከመለካት ባሻገር በሃገር አቀፉ የአትሌቲክስ ቻምፒዮና ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ምዘና የሚያደርጉበት እንዲሁም ስልጠናቸውን በመገምገም ራሳቸውን የሚያጎለብቱበት መድረክም መሆኑ ተነግሯል። ትናንት በተካሄደው የሁለተኛ ቀን ውሎ የተለያዩ የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድሮች ተካሂደዋል።በሁለተኛ ዲቪዚዮን የ100 ሜትር ሩጫ በሁለቱም ፆታ የፍፃሜ ውድድሮች የተከናወነ ሲሆን፤ በሴቶች ትዝታ ደጋ ከአራዳ ክፍለ ከተማ እንዲሁም ሜሮን ተመስገን እና ፍቅርተ ሽፈራው ከዳሎል ክለብ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።በወንዶች በኩል ኤርሚያስ ሻጠው ከኮልፌ ቀራኔዮ ክፍለ ከተማ አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዷል።የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲው አትሌት ሲሳይ አየሁ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ክለብ አትሌቱ ዘገየ ለገሰ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።በተመሳሳይ በ10ሺ ሜትር በወንዶችና ሴቶች ውድድር ፍጻሜያቸውን ሲያገኙ፤ በ1ሺ500 ሜትር፣ በአሎሎ ውርወራ እና በከፍታ ዝላይ አሸናፊ የሆኑ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ነገ ቀጥሎ በሚውለው ቻምፒዮና የተለያዩ የፍጻሜ ግማሽ ፍጻሜና የማጣሪያ ውድድሮች የሚካሄዱም ይሆናል።በ5ኪሎ ሜትር በሴቶች እንዲሁም በ10ኪሎ ሜትር የወንዶች እርምጃ ውድድሮች ፍጻሜያቸውን ከሚያገኙት መካከል ይጠቀሳል።በሁለተኛ ዲቪዚዮን የሱሉዝ ዝላይ በሴቶች የማጣሪያ፣ በዲስከስ ውርወራ ወንዶች ግማሽ ፍጻሜ፣ በሁለቱም ጾታ የ400 ሜትር ፍጻሜ፣ 5ሺ ሜትር ሴት ግማሽ ፍጻሜ፣ 100ሜትር መሰናክል የሴቶች ግማሽ ፍጻሜ እና በ110ሜትር መሰናክል ሴት ግማሽ ፍጻሜ ይከናወናሉ።በአንደኛ ዲቪዚዮን ደግሞ በ100 ሜትር ሴትና ወንድ ግማሽ ፍጽሜ እንዲሁም በ110 ሜትር መሰናክል የወንዶች ግማሽ ፍጻሜ ውድድሮች በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሰረት ይካሄዳሉ። ይህ ዓመታዊ ቻምፒዮና በ1975 ዓ.ም መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ በፌዴሬሽኑ የተመዘገቡ ብዛት ያላቸው ክለቦች ሲሳተፉበት መቆየታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።ከ1991ዓ.ም ጀምሮም ፌዴሬሽኑ አቅሙን በማጎልበት ከሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር ውድድሩ ለዓመታት በቋሚነት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ፍጻሜያቸውን ባያገኙ ውድድሮች በቀዳሚነት ለሚያጠናቅቁ አትሌቶችም የወርቅ፣ ብርና ነሃስ ሜዳሊያ የሚበረከትላቸው ይሆናል።ውድድሩ ከትናንት በስቲያ የተጀመረ ሲሆን በመጪው እሁድ 22/2012 ዓ.ም የሚጠናቀቅም ይሆናል። አዲስ ዘመን ረቡዕ የካቲት 18/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27938
b950f3291a996cd4aeee4b9736fe4a30
e713073883277182e3f12d501835f7f1
ኢትዮጵያዊው ብስክሌተኛ በቱር ደ ሩዋንዳ አሸነፈ
ስፖርት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓመታዊው ፔፕሲ የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለ37ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል።ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን የያዘው ውድድሩ በተለያዩ ርቀቶች የሩጫና ሜዳ ተግባራት አትሌቶችን በማፎካከር በርካታ ክብረወሰኖች እየተሻሻሉበት ይገኛል። በውድድሩ ሁለተኛ ቀን ውሎ ትናንት በተካሄደው የሴቶች አንደኛ ዲቪዚዮን አስር ሺ ሜትር ውድድር ክብረወሰን ተሰብሯል።በኢትዮጵያ ቻምፒዮና በአትሌት ለተሰንበት ግደይ 32፡10፡90 ተይዞ የነበረው የርቀቱ የኢትዮጵያ ክብረወሰን ዘንድሮ በአትሌት ዘይነባ ይመር በስድስት ሰከንድ ሊሻሻል ችሏል። በቻምፒዮናው ላይ በአንደኛ ዲቪዚዮን ከታቀፉ አምስት ክለቦች የተሳተፉ ሲሆን በሁለተኛ ዲቪዚዮን ከታቀፉ ሃያ ክለቦች የተውጣጡ በአጠቃላይ አንድ ሺ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።ውድድሩ ክለቦች የአትሌቶቻቸውን አቅም ከመለካት ባሻገር በሃገር አቀፉ የአትሌቲክስ ቻምፒዮና ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ምዘና የሚያደርጉበት እንዲሁም ስልጠናቸውን በመገምገም ራሳቸውን የሚያጎለብቱበት መድረክም መሆኑ ተነግሯል። ትናንት በተካሄደው የሁለተኛ ቀን ውሎ የተለያዩ የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድሮች ተካሂደዋል።በሁለተኛ ዲቪዚዮን የ100 ሜትር ሩጫ በሁለቱም ፆታ የፍፃሜ ውድድሮች የተከናወነ ሲሆን፤ በሴቶች ትዝታ ደጋ ከአራዳ ክፍለ ከተማ እንዲሁም ሜሮን ተመስገን እና ፍቅርተ ሽፈራው ከዳሎል ክለብ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።በወንዶች በኩል ኤርሚያስ ሻጠው ከኮልፌ ቀራኔዮ ክፍለ ከተማ አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዷል።የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲው አትሌት ሲሳይ አየሁ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ክለብ አትሌቱ ዘገየ ለገሰ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።በተመሳሳይ በ10ሺ ሜትር በወንዶችና ሴቶች ውድድር ፍጻሜያቸውን ሲያገኙ፤ በ1ሺ500 ሜትር፣ በአሎሎ ውርወራ እና በከፍታ ዝላይ አሸናፊ የሆኑ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ነገ ቀጥሎ በሚውለው ቻምፒዮና የተለያዩ የፍጻሜ ግማሽ ፍጻሜና የማጣሪያ ውድድሮች የሚካሄዱም ይሆናል።በ5ኪሎ ሜትር በሴቶች እንዲሁም በ10ኪሎ ሜትር የወንዶች እርምጃ ውድድሮች ፍጻሜያቸውን ከሚያገኙት መካከል ይጠቀሳል።በሁለተኛ ዲቪዚዮን የሱሉዝ ዝላይ በሴቶች የማጣሪያ፣ በዲስከስ ውርወራ ወንዶች ግማሽ ፍጻሜ፣ በሁለቱም ጾታ የ400 ሜትር ፍጻሜ፣ 5ሺ ሜትር ሴት ግማሽ ፍጻሜ፣ 100ሜትር መሰናክል የሴቶች ግማሽ ፍጻሜ እና በ110ሜትር መሰናክል ሴት ግማሽ ፍጻሜ ይከናወናሉ።በአንደኛ ዲቪዚዮን ደግሞ በ100 ሜትር ሴትና ወንድ ግማሽ ፍጽሜ እንዲሁም በ110 ሜትር መሰናክል የወንዶች ግማሽ ፍጻሜ ውድድሮች በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሰረት ይካሄዳሉ። ይህ ዓመታዊ ቻምፒዮና በ1975 ዓ.ም መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ በፌዴሬሽኑ የተመዘገቡ ብዛት ያላቸው ክለቦች ሲሳተፉበት መቆየታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።ከ1991ዓ.ም ጀምሮም ፌዴሬሽኑ አቅሙን በማጎልበት ከሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር ውድድሩ ለዓመታት በቋሚነት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ፍጻሜያቸውን ባያገኙ ውድድሮች በቀዳሚነት ለሚያጠናቅቁ አትሌቶችም የወርቅ፣ ብርና ነሃስ ሜዳሊያ የሚበረከትላቸው ይሆናል።ውድድሩ ከትናንት በስቲያ የተጀመረ ሲሆን በመጪው እሁድ 22/2012 ዓ.ም የሚጠናቀቅም ይሆናል። በቻምፒዮናው ከ1ሺ በላይ አትሌቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፣ ኢትዮጵያዊው ብስክሌተኛ በቱር ደ ሩዋንዳ አሸነፈ በሩዋንዳ በተካሄደ የ‹‹ቱር ደ ሩዋንዳ›› የብስክሌት ውድድር ኢትዮጵያዊው ሙሉ ኃይለሚካኤል አሸነፈ። ብስክሌተኛው 120 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በሸፈነውና ከዋና ከተማዋ ኪጋሊ ወደ ሁዬ ዲስትሪሲ የነበረውን ርቀት ለመሸፈንም 3ሰዓት ከ3ደቂቃ ከ21 ሰከንድ የሆነ ጊዜ እንደፈጀበት ዘ ኒው ታይምስ ዘግቧል።ለ12ኛ ጊዜ የሚካሄደው ውድድሩ እስከ መጪው እሁድ በተለያዩ ፉክክሮች የሚቀጥል ይሆናል። አትሌቶች ለቻምፒዮናው አልፈዋል ሰባት ዙሮች ያሉት የዓለም የቤት ውስጥ የዙር ውድድር የተጠናቀቀ ሲሆን ለዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና በቀጥታ ማለፍ የቻሉት 11 አትሌቶችም ተለይተዋል።ከእነዚህ አትሌቶች መካከልም የ3ሺ ሜትር ተወዳዳሪው ጌትነት ዋለ በወንዶች እንዲሁም በሴቶች ጉዳፍ ጸጋዬ 1ሺ500 ሜትር ማለፋቸውን ያረጋገጡ አትሌቶች ሆነዋል።ይሁን እንጂ የቻምፒዮናዋ አዘጋጅ የሆነችው ቻይና ከኮረና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ውድድሩ ወደ ሚቀጥለው ዓመት (እአአ 2021) መሸጋገሩ የሚታወስ ነው።በዙር ውድድሩ ቀዳሚ በመሆን ያጠናቀቁት አትሌቶች 20ሺ የአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ መሆናቸውንም የዓለም አትሌቲክስ በድረ ገጹ አስነብቧል። ሊጉ ከሁለት ሳምንት በኋላ ይመለሳል የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የካቲት 29 እና 30/2012 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑ ታውቋል።የግማሽ ዓመት ውድድር ከትናንት በስቲያ በቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ ከተማ መካከል በተደረገ ጨዋታ መጠናቀቁ ይታወቃል።ይህንንም ተከትሎ ሊጉን የሚመራው አቢይ ኮሚቴ ከሁለት ሳምንት እረፍት በኃላ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲጀመር ውሳኔ ላይ መደረሱ ተረጋግጧል። የወርልድ ቴኳንዶ ቡድኑ አቀባበል ሰሞኑን ሞሮኮ ላይ ሲካሄድ በነበረው የወርልድ ቴኳንዶ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ኢትዮጵያን የወከለው ቡድን ትናት አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፣የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፣ የአዲስ አበባ የወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ማህበር እና የስፖርቱ ቤተሰብ ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርስ ልዩ አቀባበል አድርጓል። ሰለሞን ቱፋ በማጣሪያ ውድድሩ በወርልድ ቴኳንዶ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለመሳተፍ የሚያስችለውን ውጤት ማስመዝገቡ ይታወሳል። ለሴት መምህራን ስልጠና ሊሰጥ ነው ለሴት የስፖርት ሳይንስ መምህራን የአሰልጣኝነት ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የ ‹‹ዲ ላይሰንስ›› አሰልጣኞች ስልጠና ለተመረጡ ሃገራት የሚሰጥም ይሆናል። ከሁሉም ክልሎች ለተወጣጡ 30 መምህራን የሚሰጠው ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 25/2012 ዓ.ም የሚቆይም ነው። ስልጠናው የሴቶች እግር ኳስ ልማትን ለማሳደግና ብቃታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችን ለማፍራት የሚጠቅምም ይሆናል። በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈው ስልጠናው በኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ኢንስትራክተር ሰላማዊት ዘርዓይ እና በተጋባዦች የሚካሄድ መሆኑንም የፌዴሬሽኑ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት በመረጃ ጠቁሟል። ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኃላም እድሜያቸው 15 ዓመት በታች በሆኑ 10 የሴት ተማሪዎች ቡድን መካከል ውድድር ይካሄዳል። ቀነኒሳ በዓለም የግማሽ ማራቶን የሃገር አቋራጭ ንጉሱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዓለም የግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና ለአሸናፊነት ይጠበቃል። ከቀናት በኃላ በፖላንድ በሚካሄደው ቻምፒዮና በማራቶን የሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ባለቤት የሆነው አትሌት ተሳታፊ እንደሚሆን የቢቢሲ ዘግቧል። አትሌቱ በውድድሩ ከእንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ፈታኝ ፉክክር ይገጥመዋል በሚል ቢጠበቅም፤ አትሌቱ በጉዳት ምክንያት የማይሳተፍ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የአሸናፊነት ግምቱን አግኝቷል። አዲስ ዘመን ረቡዕ የካቲት 18/2012
https://www.press.et/Ama/?p=27942
5d70c3a9afd2482a8003cdd600b74660
bef3d8c90d701c4d690430dd47f82b87
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ዓለም አቀፍ ኃላፊነቷን እየተወጣች መሆኗ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
 አዲሱ ገረመውአዳማ፡- ኢትዮጵያ የደን ሀብት መመናመንና የአየር ብረት ለውጥ እያስከተሉ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች ከግምት በማስገባት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ አገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በመዘርጋት ዓለም አቀፍ ኃላፊነቷን እየተወጣች መሆኗ ተገለጸ። በዘንድሮ ዓመትም ስድስት ቢሊዮን ችግኝ ለማፍላት መታቀዱም ተነግሯል።የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን እስካሁን የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤና ጥበቃ ሥራዎችን እንዲሁም የ2013 በጀት ዓመት የችግኝ ተከላን የተመለከተ የውይይት መድረክ ትናንት በአዳማ ከተማ አካሂዷል። በውይይት መድረኩ የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ እንዳሉት፤ የደን ሀብት መመናመንና የአየር ብረት ለውጥ እያስከተሉ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች ከግምት በማስገባት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ አገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በመዘርጋት የአረንጓዴ ልማት ሥራን በማጠናከር እየተሰራ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ኃላፊነቷን እየተወጣች መሆኑን ያሳያል። የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር እንደ ድርቅና ጎርፍ የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል ይረዳል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ዘንድሮ የሚከናወነው የችግኝ ተከላ ከኢትዮጵያ አልፎ ጎረቤት አገራትንም ተደራሽ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ስድስት ቢሊዮን ችግኞችን ለማፍላት እንደታቀደና ከነዚህ ውስጥም አንድ ቢሊዮኑ ለጎረቤት አገራት እንደሚውሉ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካና ታዳጊ አገራት ቃል ሆና በተለያዩ መድረኮች ስታነሳ እንደቆየች ሁሉ፤ ችግሩ በመድረክ ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ በተጨባጭ በአገር ቤት የሚሰራውን ሥራ በጎረቤት አገራትም ተግባራዊ በማድረግ ሚናዋን እንደምትወጣ አስታውቀዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ አረንጓዴ አሻራ በአገሪቱ የቆየውን የደን ሀብት ጥበቃ በማሻሻል ሌሎች የደን ሀብት ልማትን ለማሳደግና በእውቀት ለመምራት ያስችላል። በዚህም መንግሥት ኅብረተሰቡን በሰፊው በማሳተፍ ብሔራዊ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብርን ተግባራዊ ማድረግ ችሏል። በዚህም ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት ብቻ ከ9 ቢሊዮን በላይ የደን የጥምር ግብርናና የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን መትከል ተችሏል። በተለይም ባሳለፍነው ዓመት የኮቪድ 19 ያስከተለውን ኢ-ተገማች ተጽዕኖ በመቋቋም ሥራው ተሳክቷል። ይህም ራስን ከቫይረሱ በመከላከል ማምረት እንደሚቻል ተሞክሮ የተወሰደበት አዲስ ሀሳብና ተግባር ሆኗል።ኮሚሽነሩ አክለውም፤ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመቋቋምና ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚያስችል የልማት ስልት ቀይሳ እየሰራች ትገኛለች ብለዋል። ይህንን በማድረግና አገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የደን ልማት ያለው ጠቀሜታ ከግምት በማስገባት ተጨባጭ ስኬት ማምጣት በሚያስችል መልኩ ወደ ሥራ መገባቱንም ጠቁመዋል። ደኖችን በተገቢው መንገድ ማልማት ለማህበራዊ ብልጽግና የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ውጤቶችን እንደ ተሞክሮ በመውሰድ እንዲሁም የቀጣይ ጊዜ ሥራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል። ኮሚሽነሩ፤ እ.አ.አ በ2018፣ 15 ነጥብ 5 በመቶ ላይ የነበረውን የደን ሽፋን እ.አ.አ በ2030 ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ የተያዘውን ግብ ሊያሳካ በሚችል ሁኔታ ስትራቴጂካዊ ሥራዎች እንደተሰሩ ገልጸው፤ በአንድ ሰሞን ዘመቻ ተክሎ ገለል ማለት ብቻ ሳይሆን ለጽድቀቱም መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል። በእስካሁኑ ክንውን አበረታችና አዎንታዊ ሁኔታዎች ቢታዩም አሁንም መሻገር የሚገባቸው በርከታ ክፍተቶች እንደተስተዋሉ በማንሳት፤ ሁሉም ለችግኞች ተከላ ያሳየውን ርብርብ ለእንክብካቤና ጥበቃ ተግባር መነሳሳት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በምክክር መድረኩ ሥራውን በአቢይና በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ የሚመሩና የሚያስተባብሩ፣ ከፌዴራልና ከክልል መንግሥታት የዘርፍ መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብራት ትምህርት የተወሰደባቸውና በቀጣይ በተሻለ ለመሥራት የሚያግዙ መሆናቸው ተመላክቷል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38230
df217caf62a70fd800476a8257c09393
f4dee03198c135906875984f4de9f4e2
በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ሰላም በመጠቀም በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ሥራዎችን መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ሰላም በመጠቀም በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ሥራዎችን መስራት እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ አሳስበዋል። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ከታኅሣሥ 17 እስከ 21 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆይ የኢንዱስትሪ፣ የግብርና እና የተፈጥሮ ሀብት ውጤቶች ኤግዚቢሽን ተጀምሯል። ኢቢሲ እንደዘገበው፤ በክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በተዘጋጀው በዚሁ ኤግዚቢሽን ላይ የተገኙት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በሶማሌ ክልል የነበረው የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ተወግዶ በሰላምና በፀጥታ ተጠቃሽ ክልል መፍጠር በመቻሉ የክልሉ የለውጥ አመራር ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።«ዓለማችንን ለሥልጣኔ ካበቋት ተግባራቶች መካከል አንዱ ንግድ ነው» ያሉት አፈ ጉባኤው፤ የአውሮፓ የኢንዱስትሪ አብዮትም ለዚህ ተጠቃሽ መሆኑን ገልፀዋል። ሰላም የንግዱን እና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴውን ለማገዝ ቁልፍ ሚናን እንደሚጫወት በመግለጽም፤ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ባለሀብቶች በሶማሌ ክልል ኢንቨስት ቢያደርጉ አዋጭ መሆኑን ተናግረዋል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣ ከዚህ ቀደም የነበረው የሰላም እጦት በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የንግድና የኢንዱስትሪ አቅም በሚፈለገው ደረጃ ለመጠቀም አዳጋች አድርጎት እንደነበር ጠቅሰው፤ የክልሉ መንግሥት አሁን ላይ የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ከዳር እንዲደርስ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ባለሀብቶችን ለመሳብ በትኩረት እየሰራእንደሚገኝ አስታውቀዋል። የሶማሌ ክልል ሰፊ ያልታረሰ መሬት፣ የገፀ ምድርና የከርሰ ምድር ሀብት፣ የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ባለቤት መሆኑን የገለጹት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ ክልሉም እንዲህ ዓይነት ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀትና በመሳተፍ የክልሉን የኢንዱስትሪና የንግድ ዘርፍ ማሳደግ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህም ገቢ ምርትን ለመተካትና ወጪ ንግድን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል። የሶማሌ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ በሽር ሻፊ በበኩላቸው፤ የተዘጋጀው የኢንዱስትሪ፣ የግብርና እና የተፈጥሮ ሀብት ውጤቶች ኤግዚቢሽን የክልሉን እምቅ የኢንዱስትሪ እና የተፈጥሮ ሀብቶችን ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38228
0a63d66d81ca8b9363da40f683886109
f137420a22a0b9375c0af5a9580ba342
ሚኒስቴሩ በፀጥታ ችግር ትምህርት ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች ላይ ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዋቅሹም ፍቃዱአዲስ አበባ፡- በኮሮና ወረርሽኝ ዙሪያ ተገቢ ጥንቃቄ እየተደረገ በአብዛኛው አካባቢዎች ትምህርት ቢጀመርም በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ያልጀመሩ አካባቢዎችም ትምህርት እንዲጀምሩ እየሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፤ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም አካባቢ በሚባል ደረጃ ትምህርት ተጀምሯል። ነገር ግን ከወቅታዊ የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልልና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ትምህርት አልተጀመረም። በመሆኑም በእነዚህ አካባቢዎች ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።በዚህ ረገድ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በተለይ በትግራይ ክልል ትምህርት ለመጀመር ጁንታው ከተመደሰሰ በኋላ ነባራዊ ሁኔታን የሚገመግም ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ አካባቢው ልኳል። ሆኖም ግን ትምህርት ቤቶች በጁንታው ኃይል በመውደማቸው ምክንያት የመጠገን ሥራ ጊዜ መውሰዱ አይቀርም። በመተከል ላይም ተመሳሳይ ሥራ የሚሰራ ይሆናል።እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፤ በትምህርት ቤቶች የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል ለ25 ሚሊዮን ተማሪዎች 50 ሚሊዮን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮች ለማቅረብ ታቅዶ ነበር። እነዚህን ማስኮችም በሁለት ሳምንት ውስጥ አምርተን አናቀርባለን ብለው ስምምነት የፈረሙት የአዳማና የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግን በሁለት ሳምንት ቀርቶ በሁለት ወር ውስጥም ማቅረብ አልቻሉም። ይህ ደግሞ ሚኒስቴሩን ለትችት ዳርጎት ነበር።የመማሪያ ክፍሎችን በተመለከተም፣ አምና በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤቶች እንደ ተዘጉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ አንድ መፍትሔ አፈላላጊ ተዋቅሮ ነበር። ይህ የቴክኒክና የሁኔታ አጥኚ ኮሚቴ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች እንዲሰሩ ወሰነ። በዚሁ መሰረት ደረጃቸውን ጠብቀው 700ሺህ የመማሪያ ክፍሎች ተገንብተዋል።ከእነዚህ ውስጥም 34ሺህ የሚሆኑ በኦሮሚያ የተገነቡ ናቸው።በሌላ በኩል፤ ከዚህ በፊት የግል ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት የሚፈለገው ደረጃ የሚቆጣጠር አካል ባለመኖሩ ከአገሪቱ ሥርዓተ ትምህርት ባፈነገጠ መልኩ የመማር ማስተማር ሂደት ሲያከናወኑ መቆየታቸውን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ አሁን ግን ጉዳዩን የሚከታተል አካል ከመሰየሙም በተጨማሪ ቀጣዩ ዓመት አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ሥራ ላይ ስለሚውል በአጠቃላይ በግልም ይሁን በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በመማር ማስተማር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች እንደሚቀረፉ ተናግረዋል።የ12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መለቀቂያ ፈተናን በተመለከተም በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ። ይህንን ለማሳካት ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል። ለ270 ቴክኒሻኖችም ስልጠና ተሰጥተዋል። ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል፤ ሁለት ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል። በትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ወደ አገር ገብተው ለፈተናው የሚውሉ ሲሆን፤ ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።የመምህራን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ጋር ተያይዘው ከመምህራን የሚነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተም የሥራ ግምገማና ደረጃ የተደረገው ደመወዝ ለመጨመር ሳይሆን ሥራና ሠራተኛን ለማገናኘት ታስቦ እንደነበር የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ትምህርት ሚኒስቴርም ኃላፊነቱን ወስዶ መምህራን ተጠቃሚ በሚያደርግ መምህራንን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራቱን ተናግረዋል። በዚህም ማስተካከያውን የሦስት ወር ለመምህራን ከፍሎ የቀሩት የሦስት ወር ክፍያ ለመክፈል ሲል ኮሮና በመከሰቱ ምክንያት ለተጠባባቂነት በመያዝ ሳይከፍል ቀርቷል። ካሁን በኋላ ግን ሁሉም ክልሎች ይህንን ደመወዝ ለመምህራኖቻቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲከፍሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38242
1fb3456918fc5cea4f49c5e480d38113
7894b015fbd1563e1b6be55c927393a5
በ2022 የቱሪዝም ገቢን 23 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየተሰራ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
ለምለም መንግሥቱ አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ በ2022ዓ.ም ሰባት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን የሚሆን ቱሪስት በመሳብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ 23 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየሰራች መሆኑ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተናገረ። በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ዘርፍ አማካሪ አቶ አህመድ መሐመድ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በአስር ዓመቱ መሪ ዕቅድ የመጨረሻ ዓመት በሆነው 2022 ዓ.ም ሰባት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን የሚሆን ቱሪስት በመሳብ 23 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት እየተሰራ ነው። በዚህም አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል። አቶ አህመድ እንደሚሉት፤ በሀገር ደረጃ አዲስ የሆነውን የቱሪዝም ኤክስፖርት በመተግበርና 26 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው በማድረግ ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ወደ ትግበራ የተገባ ሲሆን፤ መሪ ዕቅዱም ለቱሪዝም ዕድገት ማነቆ የነበሩ ችግሮችን በመለየት ዘርፉን በሚያሳድጉት ላይ ቢሰራ የሚፈለግበት ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል የሚያሳይ ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ ተወዳዳሪነትን መፍጠር፣ የመረጃ ልዕቀትን ማጎልበት፣ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ላይ ትኩረት ማድረጉን የጠቆሙት አቶ አህመድ፤ በሀገሪቷ እየተገነባ ካለው ዕውቀት መር የኢኮኖሚ ሥርዓት ጋር ቱሪዝምን ለማስተሳሰር ጥራት ያለው ጥናትና ምርምር እንዲሁም ዕውቀት በማጎልበት ላይ ሥራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በትኩረት ከተሰራም ቱሪዝምን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ይቻላል የሚል እምነት መያዙን አስረድተዋል። በዓለም የቱሪዝም ገበያ ውስጥ እነ ቻይና፣ ጃፓን፣ ሩሲያ እና የመካከለኛ ምሥራቅ ሀገራት እየገቡ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ አህመድ፤ እነዚህን ማዕከል ባደረገ የቱሪዝም መዳረሻና አቅርቦት መኖር አለበት በሚል ዕቅዱ መቃኘቱንም አመልክተዋል። ተመልካች ብቻ ሳይሆን በሚጎበኘው አካባቢም ተሳትፎ ያለው ቱሪስት ነው የሚፈለገው ብለዋል። ቱሪዝም አካታች የቱሪዝም ገበያ ነው ያሉት አቶ አህመድ፤ ለሕግ የሚገዛ፣ በእውቀት የሚመራ፣ በቀጣሪና በተቀጣሪ መካከል መልካም ግንኙነት እንዲሰፍን የሚያደርግ ሥርዓት በመፍጠር የጎላ ሚና እንዲኖረው፣ በአነሥተኛ፣ በመካከለኛና በከፍተኛ የተደራጁ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ዘርፉን እንዲቀላቀሉ፣ ሆቴል ቤቶችም እንዲስፋፉ እስትራቴጂው የሚያግዝ እንደሆነ አስረድተዋል። ዕቅዱ በተዘጋጀበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ተገዳ ወደ አላስፈላጊ ጦርነት እንድትገባ ያደረጋት ነገር አዲስ ክስተት ነው ያሉት አቶ አህመድ፤ በአሁኑ ጊዜ ወደተረጋጋ ሥርዓት እየገባች በመሆኑ ዘርፉ መልሶ እንዲያንሰራራ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ሳይቀር በመጠቀም የማስተዋወቅ ሥራው ይጠናከራል ብለዋል። በመንግሥት ሕግን ለማስከበር የወሰደው እርምጃ ዓለምአቀፍ ተቀባይነትን ለመጨመር እንደ አንድ የፖለቲካ አቅም መወሰዱን አቶ አህመድ ጠቁመው፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ሳይቀር በመጠቀም ያደረገው እንቅስቃሴ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችል ነበር ብለዋል። ነገር ግን ፖለቲካል ካፒታል የሚባለው የዲፕሎማሲ እና ሌሎችም ጥረቶች ግጭቱን በፍጥነት ለመቀልበስ እንዳስቻላትም አንስተዋል። የአስር ዓመቱ የቱሪዝም መሪ ዕቅድ ላይ በዘርፉ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የሆኑ አካላት፣ በከፍተኛ አመራር ላይ ያሉ የተቋሙ ሠራተኞች፣ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ እውቀት ያላቸው የተካተቱበት አካላት ያዘጋጁትና ተተችቶ የዳበረ ሰነድና ለትግበራ የበቃ እንደሆነ አቶ አህመድ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38243
f206cd851026f5eba58d1e7764878854
a18db7eef3546008a2beb50ad54ddd72
በጁንታው ላይ የተመዘገበው ድል በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግድያዎች በማስቆም እንዲደግም የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የአገር መከላከያ ሰራዊት በትህነግ ጁንታ የጥፋት ቡድን ላይ ያስመዘገበውን ድል በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግድያዎችን በማስቆም እንዲደግመው የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ። በሕገ ወጡ የትህነግ ቡድን ታግተው መከራ እና ስቃይ ያሳለፉትን የሰራዊት አባላት ተቀብለው ለተንከባከቡት የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር በደባርቅ ከተማ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ወቅት እንደተገለጸው፤ በሕገ ወጡ የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት የኢትዮጵያውያንን ስሜት ክፉኛ ጎድቶ ነበር። ሕግ በማስከበሩ ርምጃም በአራቱም ጫፍ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመከላከያ ጎን መቆሙን ሲገልፅ ቆይቷል። ጥቃቱ በተፈፀመባቸው የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙ ሕዝቦች ደግሞ መከላከያ ኃይሉ ከተሰነዘረበት ጥቃት አገግሞ ለድል እንዲበቃ  ታሪክ የማይሽረው አኩሪ ገድል ፈፅመዋል።ትህነግ በሰነዘረው ጥቃት ቀጥተኛ ዒላማ መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ሕዝቦች በመሆናቸው ይህንን ጥቃት ከመከላከል አልፎ በተለያየ የጉዳት ደረጃ ላይ የነበሩ የመከላከያ እና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን ተቀብሎ አስተናግዷል። በሕገ ወጡ ቡድን አፈና ደርሶባቸው ለሳምንታት በርሃብ፣ በውሃጥም እና ድካም በሕይወት እና ሞት መካከል የነበሩት የመከላከያ አባላት በበየዳ እና ጠለምት ወረዳዎች በኩል አድርገው ወደ ሰሜን ጎንደር ዞን አካባቢዎች ሲገቡ ሕዝቡ በፍቅር ተቀብሎ አስተናግዷቸዋል።የአማራ ሕዝብ ለሰራዊቱ ላደረገው እንክብካቤ፣ ፍቅር እና ድጋፍ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ጎንደር እና ምዕራብ ጎንደር ዞን ኮማንድ ፖስት የምስጋና እና እውቅና መርሃ ግብር ከትናንት በስቲያ በደባርቅ ከተማ አዘጋጅቷል። በምስጋና መርሃ ግብሩ የተገኙት የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎችም የሀገር መከላከያ ሰራዊት የትህነግን የጥፋት ቡድን በማያዳግም መልኩ በማስወገድ ያሳየውን አኩሪ ጀብዱ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚፈጠሩ የሰላም መደፍረስ ችግሮችን እንዲያስቆም ጠይቀዋል። «የትናንቱ ድል የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድል ነው» ያሉት የደባርቅ ከተማ ነዋሪ አቶ መኳንንት ደሳለኝ፤ ጦርነቱ ቢያልቅም ዛሬም የተልዕኮ ፈፃሚዎች ሴራ ፈፅሞ አልከሰመም ብለዋል። በመተከል እና በሌሎች አካባቢዎች ያለውን ግድያና መፈናቀል ማስቆም የሰራዊቱን ተልዕኮ የሚሻ በመሆኑ የትናንቱን ገድላችሁን በመፈፀም ኢትዮጵያን መታደግ ይኖርባችኋል ሲሉም ጠይቀዋል።ሰራዊቱ ከልጆቻችን መካከል እንደ አንዱ ነው ያሉት ሌላዋ የደባርቅ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ እናንየ መስፍን፤ ከደረሰበት የስነ ልቦና ስብራት አገግሞ እና ተልዕኮን በብቃት ፈፅሞ በዚህ መልኩ ለምስጋና መገኘታችን አስደሳች ነው ብለዋል። የሰሜን ሕዝብ ያሳየው ፍቅር፣ እንክብካቤ እና ጀግንነትም አማራ ጠላቶቹ እንደሚሉት ሳይሆን ለኢትዮጵያ አንድነት ያለውን ጥልቅ ፍቅር ዳግም ያስመሰከረ በመሆኑ ኮርተንበታል ብለዋል። በዕለቱ ለምስጋና የተገኙት የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትም ሕዝቡ በሕግ ማስከበር ርምጃው ያደረገውን ገድል ታሪክ እና የመከላከያ ኃይሉ ዘላለም ሲዘክረው እንደሚኖር መግለጻቸውን የዘገበው የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ነው።
https://www.press.et/Ama/?p=38303
2b565e886bd47c4f1e6fd060e416f66e
cd6a57d313eac221797467ea6105f782
በሃይማኖታዊ በዓላት ወቅትና በአገልግሎት መስጫዎች የኮቪድ-19 መመሪያዎች እንዲተገበሩ ተጠየቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
በኃይሉ አበራአዲስ አበባ:- በሃይማኖት ተቋማትና በሁሉም አገልግሎት መስጫዎች የኮቪድ-19 መመሪያ ተግባራዊ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠየቁ። በተለይ በመጪው ሳምንታት የሕዝብ መሰብሰብን የሚፈልጉ ሃይማኖታዊ በዓላት ወቅት የኮቪድ-19 ይበልጥ እንዳይስፋፋ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች በብዙኃን መገናኛ በኩል እንዲሰሩም ተጠይቀዋል።የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ በመግለጫቸው ወቅት እንዳሳሰቡት፤ የኮቪድ -19 በዓለማችን ከተከሰተ አንድ ዓመት መሆኑን እና በቅርብ ጊዜም ባህሪውን ቀይሮ በመምጣቱ የዓለም ሀገራት ዳግም ገደቦችን እየጣሉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያም የብዙዎችን ሕይወት መቅጠፉን እና ዛሬም ቢሆን ተጨባጭ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት አይገባም በመሆኑም በሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የሚገኙ አማኞች የተቋማቸውን የኮቪድ-19 መመሪያ በምልዓት ሊተገብሩት ያስፈልጋል። ይህ እንዲሆን ደግሞ መመሪያዎችን አስመልክቶ በየቤተ ዕምነቱ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና ሁሉም አማኞች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የተጠቆሞ ሲሆን፤ በቀጣይ ሳምንታት እና ቀናት በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ተከታታይ ሃይማኖታዊ በዓላት የሚከበርበት ወቅት ከመሆኑ አንጻር የቫይረሱ ስርጭት እንዳይባባስ ሁሉም የበዓሉ አክባሪዎች ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ በአጽንኦት አሳስቧል።የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ በበኩላቸው፤ የኮቪድ 19 መመሪያ ቁጥር 30 ካስቀመጣቸው ድንጋጌዎች አንዱ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ እጅን በውሃና ሳሙና መታጠብ፣ የፊት ማስክ በትክክለኛው ማድረግ ሲሆኑ፤ እነዚህን የመመሪያውን ግዴታዎች መተግበር የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነትእንደሆነ አሳስበዋል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም «ማስክ ከሌለ አገልግሎት የለም» የሚለውን መርህ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።በሀገራችን እስካሁን ድረስ የአንድ ሺህ 882 ሰዎችን ሕይወት ያጣን መሆኑን አስታውሰው ቀጣይ ጊዜ የተሻለ እንዲሆን በመመኘት በተለይ እንደ ቁልቢ ገብርኤል ባሉ በዓላት ብዙ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች አካላዊ ርቀት እንዲጠበቅ፣ የአፍና የአፍንጫ ጭንብል ማድረግ አስገዳጅ እንዲሆኑ፣ እጅን በውሃና በሳሙና መታጠብ ካልሆነም ሳኒታይዘር እና አልኮል በመጠቀም አስፈላጊ ጥንቃቄዎች ሊደረጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።እነዚህን መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ የቫይረሱን ስርጭት እና ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መቀነስ እንደሚቻል የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳይ በመጠቆምም፤ በኮቪድ-19 መመሪያዎች ተግባራዊነት ላይ ከበጎፍቃደኞች፣ ከሴቶችና ወጣት አደረጃጀቶች እንዲሁም ከብዙኃን መገናኛዎች ጋር በስፋት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።በቀጣይ ስድስት ወራት የተለያዩ አካላት በሚሳተፉበት የዘመቻ መርሃ ግብር በጉራማይሌም ቢሆን በአዲስ አበባ ብቻ የሚስተዋለው የፊት ማስክ አጠቃቀም በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በትክክል ተግባራዊ እንዲደረግ፣ እጅን በውሃና በሳሙና መታጠብ ወይም ሳኒታይዘር ማጽዳት እንዲሁም አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ ሥርዓቶችን የማጠናከር ሥራዎች ይሰራሉ ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38246
6db58fd9d51d012d763a2a984cb5970d
15ea803cc0c235f4246ab9e63d7079e1
በሀዋሳ ከተማ በ1ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ የሆነው የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ በ1ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ሊገነባ ነው።ፋብሪካውን የሚገነባው አማ ቢዝነስ ግሩፕ ሲሆን፤ ለሚያስገነባው ፕሮጀክት የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል።በወቅቱ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ፖሊሲ የግል ባለሀብቶችን የሚያበረታታ ነው። በክልሉ ማልማት ለሚፈልጉ መሰል ባለሀብቶችም ለኢንቨስትመንት የሚሆን ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ወደክልሉ ሄደው መዋዕለ ንዋያቸውን ሊያፈስሱ ይገባል።የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ እንደሀገር ለዘይት ምርት በየወሩ 48 ሚሊዮን ብር እንደሚወጣ ገልጸዋል። የሀገራችን የዘይት ፋብሪካዎች 12 በመቶ ብቻ የሚሸፍኑ መሆኑን በመጠቆምም፤ ፕሮጀክቱ እንደ ሀገር የዘርፉን ችግር የሚቀርፍ መሆኑን አስረድተዋል።የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በበኩላቸው፤ እንደነዚህ ዓይነት ፕሮጀክቶች ሥራ አጥነትን ከመቀነስ አንጻር የጎላ ፋይዳ ያለው ብቻ ሳይሆን የከተማዋንም ተመራጭነት የሚያሰፋ መሆኑን ተናግረዋል። ከተሞችን ለሰው ልጆች ምቹ ለማድረግ አስተዳደሩ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።የድርጅቱ ባለቤት አቶ አንድነት ጌታቸው በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ወደ ኢንቨስትመንት መግባታቸውን ገልፀው፤ የዚህ ፕሮጀክት ግንባታ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ተናግረዋል። ድርጅቱ በፍጥነት እንደሚጠናቀቅ እና ለ2 ሺህ44 ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርም መናገራቸውን የዘገበው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38310
8c653737890d60da845dd6358e67fc2d
2f472d0cab46b5a0d3536cdb66ccbed5
የፕሪሚየር ሊጉ የአንደኛ ዙር ቆይታ- ከስፖርታዊ ጨዋነት አንፃር
ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመቱ አንደኛ ዙር መርሐ ግብር ከሦስት ወራት ቆይታ በኋላ ባሳለፍነው ሰኞ የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ተጠናቋል። የመጀመሪያው ምዕራፍ በተለያዩ ክስተቶች የታጀበ ሆኖም አልፏል።የመጀመሪያው ዙር ቆይታ የኢትዮጵያ እግር ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ከገባበት የስፖርታዊ ጨዋነት ስጋት አንፃራዊ በሆነ መልኩ መሻሻል የታየበት ነው።ፕሪሚየር ሊጉ ሲወቀስበት ከነበረው የስፖርታዊ ጨዋነት ስጋት ወጥቶ አዲስ መልክ እንዲይዝ በማድረግም የሊግ ኮሚቴው ውጤት ማሳየት የጀመረበት ነበር።በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተለይ ከሦስት ዓመት ወዲህ የስፖርታዊነት ጨዋነት ችግር የእግር ኳሱ ትልቅ ፈተና ሲሆን ታዝበናል። በየጨዋታዎች በደጋፊዎች መካከል የሚነሱ ፀቦች እንደ ፋሽን መታየት የጀመሩበት ጊዜም ነበር። በፌዴሬሽኑ፣ በክለቦች ፣በመንግሥት በኩል ለችግሩ መፍትሔ ማምጣት የሚያስችሉ ሥራዎች እንደተሠሩ ቢነገርም ስታዲየሞችን የፀብ መነኸሪያ ከመሆን መታደግ አልተቻለም ነበር።ስታዲየሞች የእግር ኳስ ስሜትን ሳይሆን የፖለቲካ ስሜትን ማንፀባረቂያ መድረክ ወደ መሆን እስከመሻገር ደርሰዋል።የትግራይና የአማራ ክልል ክለቦች ፤በደቡብ ክልል የሚገኙ ክለቦች እርስ በዕርስ ተገናኝተው ለመጫወት አዳጋች እስከመሆን ያደረሰንም ስርዓት አልበኝነት ሰፍኖ ነበር።በ2009 ዓ.ም በርካታ ቁጥር ያለው የስቴዲየም ሁከት በተለይም በፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቢከሰቱም ከብጥብጦቹ ጀርባ እግር ኳስን የሚሻገሩ ገፊ ምክንያቶች እምብዛም እንዳልነበሩ ይጠቀሳል። ከ2009 ወዲህ ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚለኮሱ የስቴድየም ግጭቶችና ረብሻዎች ቁጥር ከዘንድሮው የውድድር ዓመት በፊት አይለው ነበር።በ2010 የውድድር ዓመት ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዲግራት፣ ጅማና ወልዲያ ከተሞች ውስጥ የስቴድየም ሁከትና ግጭቶች ተበራክተው እንደነበር ይታወሳል።በተለይም በውድድር ዓመቱ በወልዲያ ስፖርት ክለብና በመቀሌ ከተማ መካከል ሊደረግ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት በሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወት የጠፋ ሲሆን ንብረት ላይ ዘረፋና ወድመት ተከስቷል። በዕለቱም ማገባደጃ ላይ በመቀሌ ከተማ መንገዶች ላይ ክስተቱን ለመቃወም በርካታ ሰዎች ወጥተው እንደነበር አይዘነጋም። ጨዋታው ካለመካሄዱ በተጨማሪም የግጭቱ አሻራ እስከ ቀጣይ ቀናት ሲሻገርና ከእግር ኳሳዊ ምክኒያት ይልቅ ፖለቲካዊ አንደምታው ሚዛን ሲደፋ ታይቷል።በወቅቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ጁነዲን ባሻ ክስተቱ ከእግር ኳስ የሚሻገር ገፅታ እንዳለው ተናግረው ነበር፡፡የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ከረብሻዎች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ ክለቦች ላይ የጣለው ቅጣት ግማሽ ሚሊዮን ብር ገደማ መሰብሰብ መቻሉ ግጭቶች በምን ያህል ደረጃ እንደተበራከቱ ማሳያ ነው።በእንቁላሉ ጊዜ ያልተቀጣው እግር ኳስ ከፖለቲካም በላይ ጦዞ ለፀጥታ አስከባሪዎች ፈተና ከመሆን አልፎ እንደ አገር ስጋት የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሶም ነበር።ሰላም በራቃቸው የስፖርት ማዘውተሪያዎች መደበኛ የውድድር መርሐ ግብሮች መተማመኛ ማግኘት አልቻሉም ነበር።በክልል የሚካሄዱ ጨዋታዎች በፖለቲካ ትኩሳት ሳቢያ ተጨማሪ ራስ ምታት እየሆኑ መምጣታቸውም አሳሳቢ ነበር።በስፖርቱ ዓለም የተመልካቾች ነውጠኝነት ምክንያቶች ብዙ መሆናቸውን በስፖርቱ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል።ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ወይንም ምጣኔ ሀብታዊ ብሶቶች ስቴዲየም ላይ ሊያጠሉ እንደሚችሉም ይታመናል።በኢትዮጵያ እግር ኳስን የታከከ ግጭትና ሁከት ሲከሰት የመጀመሪያው ባይሆንም በተለይም ባለፈው የውድድር ዓመት ቀይ መስመር አልፎ ነበር።የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ስናጤን ደግሞ ከእግር ኳስ ባሻገር ከእነዚህ ምክኒያቶች ሁሉ ለስፖርት ጠንቅ የሆነ የፖለቲካ አጀንዳ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ራሳቸው አስተውለውታል።እግር ኳስ ማኅበረሰባዊ መሰረት ከሌለው በስተቀር የጠነከረ የእኔነት ስሜት ሊፈጥር አይቻለውም የሚሉ ተንታኞች፤ ክለቦች ከማኅበረሰባዊ መሰረታቸው በዘለለ ብሔር ተኮር መልክን እየተላበሱ የመምጣታቸው አዝማሚያ አደገኛ መሆኑ የበርካታ ስፖርት ቤተሰቦች እምነት ነው፡፡ክለቦች ሲቋቋሙ ወይንም ሲዋቀሩ አካባቢያዊ መገለጫ ወይንም ከተማዊ ስያሜ ሊኖራቸው ቢችልም ከብሔር፣ ከዘር ወይንም ከኃይማኖት ጋር በተቆራኘ መልኩ መደራጀት ክልክል መሆኑን የስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ማኅበራት ማደራጃ መመሪያ አንቀፅ 50 ቁጥር 2 ይገልፃል። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት ብቻ ፌዴሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ሊጎች የብሔር ስም የተቀጠላላቸው በርካታ ክለቦች ውድድር እያደረጉ መጥተው ነበር።እግር ኳሱ ከአንዳንድ ሁከቶች አልፎ እጅግ ወደተደራጀ ነውጠኛነት እያመራ ስለመሆኑም ሲነገር ቆይቷል።ቀስ በቀስም ወደ መቧደን እየተጓዘ ነበር።ይህ አዝማሚያ የ2012 ዓ.ም የውድድር ዓመት ከመጀመሩ አስቀድሞ በእግር ኳሱ ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል በበርካቶች ዘንድ ስጋት ፈጥሮ ነበር።በዚህ ስጋት ውስጥ እያለ ኅዳር 21 ቀን 2012 ዓ.ም የተጀመረው ፕሪሚየር ሊግ ከፌዴሬሽኑ መሪነት ወጥቶ በሊግ ኮሚቴ መመራቱን ተከትሎ ቢያንስ ቢያንስ በመጀመሪያው ዙር የታሰበው ስጋት ሊረግብ ችሏል።በውድድር ዓመቱ በመጀመሪያ ዙር ከተደረጉ 30 ጨዋታዎች ቢያንስ 25 ጨዋታዎች ስፖርታዊ ጨዋነት የነገሠባቸው ነበሩ። ስፖርቱን ከፖለቲካ በመቀላቀል ስታዲየሞችን የፀብ መናገሻ የማድረጉ ዝንባሌ እንዳይኖሩ የተደረጉ ጥረቶችም ከሞላ ጎደል ፍሬያማ ነበሩ ማለት ይቻላል።ለዚህ ደግሞ የአማራ ክልልና ትግራይ ክልል ክለቦችን እንደ ማሳያ ማንሳት ይገባል። አምና በሁለቱ ክልል ክለቦች ደጋፊዎች መካከል የነበረውን መፋጠጥ በውድድር ዓመቱ እንዳይደገም ማድረግ ተችሏል። የባህር ዳር ወጣቶች የመቐለ 70 እንደርታ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች በወንድማዊ ስሜት ‹‹እንኳን ወደ ውቢቷ ከተማችሁ በደህና መጣችሁ›› ሲሉ በፍቅር በመቀበል ፀብን ለማራቅ የሄዱበት ርቀት ትልቅ ርምጃ ነበር።የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች ከባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች በጋራ በመሆን ከተማዋን በማፅዳት አንድነታቸውን ያሳዩበት ድርጊት የከረረውን ስጋት መበጠስ ችሏል።የሁለቱ ክለቦች ደጋፊ ማህበራት በአብሮነት መሥራት መቻላቸው ስፖርት ለሰላም፣ ለአንድነትና ለወንድማማችነት መርህን በተግባር እንዲታይ አድርጓል። የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ወደ መቐለ ከተማ ባቀናበት ወቅት የነበረው ሁኔታ ፤በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች መካከል ተጨማሪ የአንድነት ስሜት እንዲጎለብት ያደረገ ነበር። የመቐለ ከተማ ወጣቶች የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾችና ደጋፊዎችን ፍጹም ፍቅር በተሞላበት መልኩ ተቀብለው በመሸኘት የልዩነቱን ግንብ ማፍረስ የቻሉበትን አጋጣሚ ፈጥረዋል። በሁለቱ ክልሎች የሚገኙ የክለቦች ደጋፊ ማህበራት በኩል የታየው ቆራጥነት ለዚህ ውጤት መገኘት ትልቅ ድርሻ የያዘም ነበር። የሁለቱ ክልሎች የመንግሥት አመራሮች በኩል የታየው ቀናኢነትና ከደጋፊ ማህበራቱ መቀናጀት ጋር ተደምሮ የእግር ኳሱ ስጋት ሊረግብ ችሏል። በደቡብ ክልል የሚገኙ ክለቦች ደጋፊዎች ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲሰፍን ያሳዩት ቁርጠኝነትም የመጀመሪያው ዙር አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍንበት ትልቅ ሚና ነበረው።በወላይታ ድቻና ሲዳማ ቡና ክለብ ደጋፊዎች መካከል የነበረውን መፋጠጠ በውድድር ዓመቱ አዲስ የሰላም መልክ መያዝ መቻሉ ለዚህ ስኬት ምሳሌ ነው፡፡ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውበት ከሆኑ ክለቦች መካከል የሸገር ደርቢዎቹ ኢትዮጵያ ቡናንና ቅዱስ ጊዮርጊስን እዚህ ላይ ሳይጠቅሱ ማለፍ አይቻልም።የከተማዋ ተፎካካሪ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ተመልካቾች መካከል የተስተዋለው መከባበርና ሥነ ሥርዓት ለክልል ክለብ ደጋፊዎች እንደማሳያ መወሰድ እንዳለበት የብዙኃን አስተያየት ጭምር ነበር።ቀደም ሲል ሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ሲኖራቸው በከተማዋ የሚኖረው ውጥረትና የፀጥታ ስጋት በዚህ ዓመት ከከተማዋ ዋንጫ ጀምሮ ሰላማዊና የሚያስመሰግናቸው ጭምር ነበር።የሁሉም ክለቦች ደጋፊ ማኅበር ፕሬዚዳንቶች በጥምረት የመሠረቱትን ማኅበር ተከትሎ፣ እንደዚህ ዓይነት ችግሮች ዳግም እንዳይከሰቱ የሸገር ደርቢዎች የነበራቸውን ሚናም በጉልህ የሚጠቀስ ነው።የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሚና ከዚህ ስኬት ጋር አብሮ መነሳት ይገባዋል። ከንቲባው በተለያዩ ጊዜያት ከኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ክለብ አመራሮች ጋር በወቅታዊ እና መሠረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት በደጋፊዎች መካከል ይፈጠር የነበረውን ግጭት እንዲከስም ያላሳለሰ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። በሸገር ደርቢ ጨዋታ ወቅት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይሰማ የነበረው የፀብ ዜና በሰላም እንዲተካ በማድረግ ረገድ ምክትል ከንቲባውና የሁለቱ ክለቦች ደጋፊ ማህበራት ቆራጥነት ሳይደነቅ የሚታለፍ አይደለም።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2012 ዓ.ም የውድድር ዓመት አንደኛ ዙር ቆይታ ከስፖርታዊ ጨዋነት አኳያ አበረታች ውጤት የታየበት ቢሆንም በመጨረሻዎቹ ሁለትና ሦስት ጨዋታዎች እንከኖች መታየታቸው አልቀረም።ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ በነበራቸው ጨዋታ፣ ወልቂጤ ከተማና ሲዳማ ቡና በነበራቸው ጨዋታ በደጋፊዎች መካከል የተፈጠረ ግጭት ቢኖርም እንዳለፉት ዓመታት የተጋነነ ነው ለማለት አይቻልም።ያም ሆኖ የሊግ ኮሚቴው እንዲህ ዓይነት ግጭቶች ወደ ሁለተኛው ዙር እንዳይዛመቱ ሰሞኑን ፋሲል ከነማንና ቅዱስ ጊዮርጊስን ከዚሁ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር በተያያዘ ቅጣት እንዳስተላለፈባቸው ሌሎቹንም ተመልክቶ ፍትሐዊ ቅጣት ማስተላለፍ ይጠበቅበታል።ይህም ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ የመጀመሪያው ዙር በተሻለ ስፖርታዊ ጨዋነት እንደተጠናቀቀው ሁሉ ለሁለተኛውም ዙር ከወዲሁ የቤት ሥራዎችን ጨርሶ መሻገር ለነገ የሚባል አይደለም።አዲስ ዘመን አርብ የካቲት 20/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=28042
ca7271e4d9f99acc3c4b0f1c211cd069
694484fb34191456dfdb527c7e3e6706
የበጋ ወራት ውድድሮች ጠንካራ ፉክክር እያስተናገዱ ነው
ስፖርት
ካለፈው ታኅሣሥ አጋማሽ አንስቶ እየተካሄደ የሚገኘው የሠራተኞች የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር በጠንካራ ፉክክር ታጅቦ ቀጥሏል። በተለይም በሁለት ዲቪዚዮን ተከፍሎ የሚካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ጠንካራ ፉክክር በማስተናገድ ላይ መሆኑን የውድድሩ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) የስፖርት ክፍል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ካሳ ተናግረዋል። በስምንት ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የአንደኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ውድድር ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በአራት ጨዋታ አስራ ሁለት ነጥብና አስራ ሁለት ንፁህ ግብ በመሰብሰብ እየመራ ይገኛል። የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በሦስት ጨዋታዎች በሰበሰበው ዘጠኝ ነጥብና ሰባት ንፁህ ግብ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በቅርብ ርቀት እየተከተለ ይገኛል። አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በበኩሉ በአራት ጨዋታ ዘጠን ነጥብና ስድስት የግብ ዕዳ ይዞ በሦስተኛነት ይከተላል። አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በሦስት ጨዋታ ሦስት ንፁህ ግብና አራት ነጥብ ይዞ ጠንካራ ፉክክር እያደረገ ይገኛል። ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ከሦስት ጨዋታ ሦስት ነጥብና ሁለት የግብ ዕዳ ይዞ አምስተኛ ላይ ይገኛል። አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሦስት ጨዋታ አንድ ነጥብና ስምንት የግብ ዕዳ ይዞ ይከተላል። ኢትዮጵያ መድህን ድርጅትና መከላከያ ኮንስትራክሽን በሦስት ጨዋታ ስምንትና አስር የግብ ዕዳ ይዘው ካለምንም ነጥብ በአንደኛው ዲቪዚዮን እየተፎካከሩ የሚገኙ ቡድኖች ናቸው። በመጀመሪያው ዲቪዚዮን እሁድ ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ሲካሄዱ ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ከኢትዮጵያ መድህን በኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ የሚገናኙ ይሆናል። ቀሪው አንድ ጨዋታ በተመሳሳይ ዕለትና ቦታ አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ከአንበሳ አውቶቡስ ጋር የሚያገናኝ ነው። በሁለተኛ ዲቪዚዮን እየተፎካከሩ የሚገኙ አስራ ስምንት ቡድኖች የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ወሳኝ ጨዋታዎችን የሚያከናውኑ ሲሆን በምድብ ‹ሀ› ከሦስት ጨዋታዎች ሙሉ ዘጠኝ ነጥብና ሦስት ንፁህ ግብ ማግኘት የቻለው ሞዔንኮ ኩባንያ እሁድ ዕለት በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ቃሊቲ ብረታብረት ፋብሪካን ይገጥማል። ቃሊቲ ብረታብረት በምድቡ ከሦስት ጨዋታዎች ሰባት ነጥብና ስድስት ንፁህ ግብ በመሰብሰብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚሁ ምድብ በሦስት ጨዋታ ሰባት ነጥብና ዘጠኝ ግብ በመያዝ ሁለተኛ ላይ ይገኛል። አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ከኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ይሆናል። ሁለቱ ቡድኖች በምድብ ‹ለ›የሚገኙ ሲሆን አዋሽ ወይን በሁለት ጨዋታ አራት ነጥብና ሁለት ግብ ይዞ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ክፍያ መንገዶች በበኩሉ በሁለት ጨዋታ አንድ ነጥብና ሁለት የግብ ዕዳ ይዞ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚሁ ምድብ ሦስተኛ ላይ የሚገኘው ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ካምፓኒ(ኮካ ኮላ) በሁለት ጨዋታ ሦስት ግብና አራት ነጥብ ይዞ በአራት ጨዋታ ሰባት ነጥብና አንድ ግብ ይዞ ሁለተኛ ላይ የሚገኘው አምቼ ኩባንያን ይገጥማል። ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት፣ኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ከ ይርጋለም አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የሚያደርጉት ጨዋታም ይጠበቃል። ከእግር ኳስ በተጨማሪ ቅዳሜ ዕለት በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት በሴቶች ቮሊ ቦል የሚካሄዱ ሦስት ጨዋታዎች የሚጠበቁ ሲሆን በተመሳሳይ ዕለት በጠረጴዛ ቴኒስ በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የሚካሄዱ አምስት ጨዋታዎች ጠንካራ ፉክክር ያስተናግዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዳርት፣ ቼስ፣ ዳማና ከረንቦላ ጨዋታዎችም የተለያዩ ፉክክሮች ይጠበቃሉ። አዲስ ዘመን የካቲት 19/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=27995
d211199815327bf1f1a13ef128808eb6
f09ec51d75140a7e9ad31d454512eed4
የአዲስ አበባ ኢትዮ ዩናይትድ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ተመሰረተ
ስፖርት
ምስረታውን በ1985ዓም ያደረገው ኢትዮ ዩናይትድ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለው መከፋፈል መሰረት በኢትዮጵያም በሶስት አሶሴሽኖች ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በኢትዮጵያ በተለይ በወጣቱ ዘንድ እጅግ ከተስፋፉ ስፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የማርሻል አርት ስፖርት በፌዴሬሽን ደረጃ ለመደራጀትም ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን 2003ዓ.ም በወጣው የስፖርት ማህበራት ማቋቋሚያ መመሪያ መሰረትም የድሬዳዋ ኢትዮ ዩናይትድ ኢንተር ናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ሊመሰረት ችሏል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ስር የነበሩት ሶስት አሶሴሽኖችም በመጣመር ፌዴሬሽን ያቋቋመ ሁለተኛው ከተማ አስተዳደር ሆኗል። በፌዴሬሽኑ ማቋቋሚያ ጉባኤ ላይም የስፖርት ኮሚሽኑ ተወካይ አቶ መኮንን ገብረህይወት የፌዴሬሽኑን ምስረታ አብስረዋል። ተወካዩ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የአሰራር ሂደቱንና ደንቡን በተከተለ መልኩ የፌዴሬሽን ምስረታ መካሄዱን አረጋግጠዋል። ፌዴሬሽኑ በስድስት ክፍለ ከተሞች ውስጥ ብቃታቸው የተረጋገጠ 16 ክለቦችን ያቀፈ፣ በ ‹‹ኤ ላይሰንስ›› ሁለት፣ በ ‹‹ቢ ላይሰንስ›› ስድስት፣ በ ‹‹ሲ ላይሰንስ›› አስር ዳኞች እንዲሁም ከ2-7ኛ ዳን ያላቸው 16 አሰልጣኞች ያሉት በመሆኑ የማቋቋሚያ ጉባኤ ማድረግ የሚያስችላቸው መሆኑን ጠቁመዋል። በዚሁም መሰረት ስራ አስፈጻሚዎችን በመምረጥ ወደ ስራ እንዲገቡ፤ በሂደትም ጽህፈት ቤትና የስፖርት ማዘውተሪያ ገንብተው ከመንግስት ድጎማ እስኪላቀቁ በኮሚሽኑ ቢሮ እንዲሁም በትምህርትና ስልጠና ማዕከላት እንዲገለገሉ ፈቃድ ተሰጥቷል። በመጀመሪያው ጉባኤ ላይም አዲስ ፌዴሬሽን እንደመሆኑ ሪፖርት ማቅረብ ባይቻልም ቀጣይ እቅዶች ግን ለጉባየተኛው ቀርበዋል። በዚህም የክለቦችን ቁጥር አሁን ካለበት ቁጥር ወደ 33 ማሳደግ፣ ጠንካራ ፌዴሬሽን እንዲሆን መስራት፣ ገቢውን በማሳደግ ከኮሚሽኑ ድጋፍ የሚላቀቅበትን መሰረት መጣል፣ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላትን ማሳደግ፣ ስፖርተኞችን በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ማሳተፍ፣ የተለያዩ ቻምፒዮናዎችን በማዘጋጀት ከተማ አስተዳደሩን እንዲሁም ሀገርን ለመወከል የሚችሉ ስፖርተኞችን ማፍራት፣ በትምህርትና ስልጠና የዳኞችንና አሰልጣኞችን ቁጥር ወደ 100 ማሳደግ እንዲሁም በክትትልና ድጋፍ ላይ ለመስራት መታቀዱ ተገልጿል። ገለጻውን ያዳመጠው ጉባኤም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በመተዳደሪያ ደንቡ ላይም ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ በጉባኤው አባላት ይሁንታ ሊያገኝ ችሏል።ከተሳታፊዎች በተሰጠው አስተያየትም ስፖርቱ እስከ ወረዳ በመውረድ በይበልጥ እንዲስፋፋ ፌዴሬሽኑ ከክፍለ ከተሞች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት እና ከመንግስት ድጎማ ለመላቀቅ የሚያስችለውን መንገድ ማፈላለግ እንዲሁም የሀብት አሰባሰብ ላይ ማተኮር እንደሚገባው ተጠቁሟል። በተካሄደው የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫም አቶ በቀለ በዳዳ በ14 ድምጽ በማሸነፋቸው ከቀድሞው የአሶሴሽኑ ፕሬዚዳንት ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሲኒየር ሳቦም ተሾመ አበበ የስራ ደንብና መመሪያ ተረክበዋል። አቶ መንሱር ጀማል ምክትል ፕሬዚደንት ሲሆኑ፤ ወይዘሮ ሰብለወንጌል ቁምላቸው አቃቤ ነዋይ እንዲሁም ሌሎች አራት ግለሰቦች የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በመሆን ተመርጠዋል። ተመራጮችም በጋራ በመሆን ስፖርቱን ለማሳደግ የሚሰሩ መሆኑን ቃል ገብተዋል። ከማርሻል አርት ስፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ እአአ 1966 በጄኔራል ቾይ ሆንግ ሃይ ነው የተመሰረተው። የሁለቱን ኮሪያዎች መነጣጠል ተከትሎም ኢንተርናሽናልና ወርልድ ቴኳንዶ በሚል ሲከፈል፤ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ በሰሜን ኮሪያ በስፋት ይከወናል። በሲኒየር ማስተር አብዲ ከድር መስራችነትም በኢትዮጵያ አሶሴሽኑ እስካሁን ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በዚህ ወቅት የዓለም አቀፉ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን መቀመጫ በኦስትሪያ ቬና ሲሆን፤ ኢትዮጵያም አባል አገር ናት።አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 21/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=28137
a6923c06c4f8296153dd4b3318c05c94
a13d4682ea6c8101e24c752970fd973f
ለጥቁር ሕዝቦች የታገሉ የስፖርቱ ዓለም ከዋክብት
ስፖርት
የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከአስር ዓመት በፊት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው በተለያዩ ዓለምአቀፍ የስፖርት መድረኮች ስፖርተኞች በዘርና በቆዳ ቀለማቸው መገለል የተለመደ እንደሆነ ያትታል። ይህ እውነታ አሁን ላይ አደጉ በምንላቸው አገራት ስፖርት ላይ እንኳን ነቀርሳ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች እንመለከታለን። በተለይም እንደ አሜሪካ፤ አውስትራሊያና አውሮፓ የመሳሰሉ አገራት ላይ ጥቁር ስፖርተኞች አሁንም ድረስ በዘረኝነት ሲዘለፉ፤ ሲንቋሸሹና ዝቅ ተደርገው የሚታዩባቸው አጋጣሚዎች እየተበራከቱ መምጣታቸው ከዘር፤ ከሃይማኖትና ከፖለቲካ ነፃ መሆን የሚገባው ስፖርት ላይ መጥፎ አሻራ እንዲያርፍ እያደረገ ይገኛል። በስፖርት ጥቁሮች አሁን ላይ በየትኛውም ዓለምአቀፍ መድረክ ተፎካካሪ እንዲሆኑ ከማስቻል ባሻገር በትልቅ ደረጃ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ለማሳየት በርካታ ጥቁር ከዋክብት ብዙ ችግሮችን ተጋፍጠዋል። በተለይም ጥቁር አሜሪካውያን አትሌቶች በዚህ ረገድ ያዩት ፈተና ሳይጠቀስ የሚታለፍ አይደለም። አፍሪካውያንም ቢሆኑ በርካታ መከራዎችን ተጋፍጠው ለታላቅ ክብር በመብቃት ለአሁኖቹ አትሌቶች ፋና ወጊ ሆነው እኩልነትን ማንፀባረቃቸው አይካድም። ለዚህም ታሪካዊውን ኢትዮጵያዊ የማራቶን ኮከብ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በትልቁ የሚነሳ የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆኖ እናገኘዋለን። ኢትዮጵያውያን በስፖርቱ ብቻም ሳይሆን በዓደዋ ድል የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌትና የመዓዘን ድንጋይ ሆነዋል። የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነው የዓደዋ ድል የሚዘከርበት የካቲት ወር በመላው ዓለምም የጥቁር ህዝቦች መታሰቢያ ሆኖ ይከበራል። በስፖርቱ ዓለም ለእኩልነት የታገሉ ቁንጮ አትሌቶችም በዚህ ወር ሳይዘከሩ አይታለፉም። በእርግጥ በስፖርት መድረክ ዘረኝነትን የታገሉ፤ እኩልነትን ያንፀባረቁና በድላቸው የጥቁር ህዝቦችን አንገት ያቀኑ በርካታ ጥቁር ከዋክብቶች መኖራቸው አይካድም። ከእነዚህ ከዋክብቶች ግን ተፅዕኗቸው ከፍተኛ የነበረ፤ ድላቸው በርካታ ትርጉም የነበረውና በትልቅ ደረጃ የሚነሱትን ሦስት ጀግኖች ብቻ በዓድዋ ድል ዋዜማ ላይ ሆነን በስፖርት ማህደር አምዳችን እንመልከት። አበበ ቢቂላ 1928 ፋሺስት ጣሊያን በአምባገነኑ ቤኒቶ ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን ወረረ፤ ምስጋና ለማይዘነጉት ጀግኖቹ አርበኞቻችን ይግባና ሞሶሎኒና ግብረአበሮቹ ብዙም ሳይደላደሉ ከአገር ቤት በቅሌት ተባረሩ። ከሃያ አራት ዓመታት በኋላ ታላቁ አበበ ቢቂላ ሮምን በባዶ እግሩ ወሮ ዓለምን ጉድ አሰኘ፤ የምን ጊዜም የማራቶን ንጉሡ የአፍሪካውያን ኩራትና የነፃነት ተምሳሌት እንዲሁም፤ የመጀመሪያው ጥቁር የማራቶን ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ በጥቁሮቹ በጀግኖቹ መታሰቢያ ወር የካቲት የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆኖ ከሃምሳ አምስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ዋዜማ በሮም ኦሊምፒክ የፈፀመው ታሪካዊ ጀብድ በመላው ዓለም ያሉ ጥቁር አትሌቶችን በእጅጉ ያኮራና ያነሳሳ ነበር። ጷግሜ 5ቀን 1952 አስራ ሰባተኛው የሮም ኦሊምፒያድ በታላቋ ሮም ጎዳናዎች አንድ ተዓምር ታየ፤ በርካቶች ዓይናቸውን ለማመን ተቸገሩ፤ በአንባገነኑ ሞሶሎኒ አገር በበርካታ ነጮች መሃል አንድ ጥቁር በባዶ እግሩ ታየ። የጥቁር ህዝቦች ተዓምርን ለመቀበል የሚተናነቃቸው ዘረኝነትን በደማቸው ያሰረፁ ነጮች እንዴት ይህ ሊሆን እንደቻለ ግራ ተጋቡ። አፍሪካውያንን ያኮራ ኢትዮጵያውያንን ከልብ ያስፈነጠዘ ታሪካዊ ድል። የአራት ዓመት ታዳጊ ሆኖ እናት አገሩ ኢትዮጵያ በጣሊያን ፋሺስት ስትወረር መጥፎውን ጊዜ ገና ባልጎለበተ የሕፃን አዕምሮው የሚያስታውሰው አበበ ቢቂላ ሃያ ስድስት ዓመታት ጠብቆ ታላቁን የሮም ጎዳና በባዶ እግሩ ወሮ የማይደገመውን ታሪክ ሠራ። ከአራት ዓመት በኋላም 1956 በድጋሜ ጫማ አጥልቆ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፎ ጥቁሮች በማይደፈረው ርቀት አሁን ላይ ቁንጮ እንዲሆኑ መሰረቱን አኖረ። እሱ በከፈተው በርም ቁጥር ስፍር የሌላቸው የማራቶን አትሌቶች ለዘመናት ርቀቱን የግላቸው አድርገው አሁን ድረስ ዘልቀዋል። ጄሴ ኦውንስ ታላቁ የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ እንደ 1936ቱ በዘረኝነት የተጨማለቀበትን ወቅት ማስታወስ ከባድ ነው። ገና ከጅምሩ አይሁዶችንና ጥቁሮችን ከኦሊምፒኩ ለማግለል እንዲሁም የነጮችን የበላይነት አስተሳሰብ የመደገፍ አባዜ የተጠናወተው ዘረኛው የናዚ መሪ አዶልፍ ሂትለር ውድድሩ በአገሩ ጀርመን እንደሚካሄድ ካወቀ አንስቶ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። ይህ ኦሊምፒክ ብዙ ተቃውሞ ቢገጥመውም ከውድድሩ ራሳቸውን ያገለሉና እንዳይሳተፉ የተደረጉ አይሁዳውያን ነበሩ። በውድድሩ የተሳተፉትም ቢሆኑ በሂትለር ትዕዛዝ የተገለለ የመለማመጃ ሜዳና የውድድር ቁሳቁስ እንዲጠቀሙ ተደርገዋል። ጥቁሮችም በዚህ ኦሊምፒክ ተመሳሳይ ዕጣ ፋንታ የገጠማቸው ሲሆን የበታች እንደሆኑ ለማሳየት ያልተደረገ ጥረት አልነበረም። ይህን ጥረት ሁሉ ውድቅ አድርጎ የሂትለርን ቆሽት ያሳረረ አንድ ክስተት ግን በጥቁሩ አሜሪካዊ አትሌት ጄሴ ኦውንስ ተፈፀመ። ኦውንስ በዚህ የበርሊን ኦሊምፒክ በመቶ፤ በሁለት መቶ፤ በረጅም ዝላይና አራት በመቶ የዱላ ቅብብል ውድድሮች አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጠራርጎ በመውሰድ ጥቁሮች አንገታቸውን ያቀኑበት ነጮች ደግሞ የተሸማቀቁበትና ለመቀበል ያቃራቸውን ድል አጣጣመ። ይህ አልዋጥለት ያለው ሂትለር ግን በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ኦውንስን ላለመጨበጥና ለድሉም እውቅና ላለመሰጠት ራሱን አሳምኖ ስቴድየሙን በድንፋታ ለቆ ወጣ። የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ፍራንክሊን ሩዝቬልትም ቢሆኑ ለኦውንስ ድል እውቅና ሳይሰጡት ቀርተዋል። ኦውንስ ይህ ገድሉ በዘረኛ ነጮች እውቅና ይነፈገው እንጂ ነጮች ወደዱም ጠሉም ከጥቁሮች እኩል እንደሆኑ ልቦናቸው እንዲያምን አስገድዷቸዋል። በአንድ አገር ውድድሮች የነጭና የጥቁር ተብሎ ተከፍሎ በሚካሄድባት አሜሪካም በወቅቱ የኦውንስ ድል ትልቅ ትርጉም ነበረው። በዚህም ኋላ ላይ እኤአ 1976 የአሜሪካውያን ትልቁ ሽልማት የሆነውን የነፃነት ሜዳሊያ ሊሸለም በቅቷል። ኦውንስ ህይወቱን በሙሉም የጥቁሮች መብት እንዲከበር ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ጥብቅና ከመቆም ባሻገር የእሱን ፋና ተክለው ለመጡ ጥቁር አትሌቶች ሁሉ ትልቅ የመንፈስ ብርታት በመሆን ከጎናቸው ሲቆምና ሲሟገት ኖሯል። መሐመድ አሊየምን ጊዜም የቦክስ ስፖርት ንጉሡ መሐመድ አሊ የዓለም የቦክስ ቻምፒዮንና ታላቅ የቡጢ ተፋላሚ ብቻ አልነበረም። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፤ የጥቁር ህዝቦች ሰንደቅ፤ በመላው ዓለም በስፖርትና በታላቅ ስብዕና ተምሳሌትም ጭምር ነው። ብዙዎች ቦክስ ስፖርት ሳይሆን የጥጋበኞች ድብድብ አድርገው ከመሳል አስተሳሰብ አውጥቶ የቦክስን ስፖርት ጥበባዊ ገፅታ በማላበስ ተወዳጅና አሁን ላይ በዓለማችን በአንድ ጊዜ በርካታ ሚሊየን ዶላሮች የሚያሳቅፍ ግንባር ቀደም ስፖርት እንዲሆን ተፅዕኖውን አሳርፏል። መሐመድ የትውልድ ስሙ ካሴስ ክሌይ ቢሆንም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ባሮችን ነፃ ለማውጣት በታገሉ ታላቅ ሰው መታሰቢያነት የወጣለት ስም ነበር፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ የዓለም ከባድ ሚዛን ቻምፒዮን ከሆነ በኋላ በማግስቱ ስሙን ለመቀየር ወሰነ፡፡ የነፃነት ታጋዩን ማልኮለም ኤክስ ከጎኑ አድርጎ በሰጠው መግለጫ «ዘ ኔሽን ኦፍ ኢስላም» የተባለውን ተቋም መቀላቀሉን በማሳወቅ የባርያ ስም ይለው የነበረውን ካሴስ ክሌይ በመቀየር በቀድሞ ስሙ ላለመጠራት ወሰነ። በወቅቱ «ኔሽን ኦፍ ኢስላምን» ይመራ የነበረው ኤልጅያህ መሃመድ እኤአ በ1964 ላይ መሐመድ አሊ የሚለውን ስም ካወጣለት በኋላ እሱን በማፅደቅ እስከ ህይወት ዘመኑ መጨረሻ ተጠራበት። ታሪካዊው ኢትዮጵያዊ አትሌት አበበ ቢቂላ በ196o የሮም ኦሊምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ለጥቁር ህዝቦች የመጀመሪያውን የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ሲያስመዘግብ መሐመድ አሊም በቦክስ የወርቅ ሜዳሊያ አጥልቆ ነበር። ሁለቱ ታሪካዊ የጥቁር ህዝቦች ከዋክብት ፊርማቸውን ተለዋውጠውም ነበር። ይሁንና መሐመድ አሊ ይህን የወርቅ ሜዳሊያውን ለአገሩ ከማበርከት ይልቅ በሊውስ ቪል ግዛት በሚገኘው የኦሃዮ ወንዝ ጨምሮታል። ሜዳሊያውን ለአሜሪካና ለትውልድ ከተማው ሊውስ ቪል ቢቀዳጅም በርገር የመግዛት መብት ባለመኖሩ ተቃውሞውን ለመግለፅ ነበር ይህን ርምጃ የወሰደው። በ1996 አገሩ አሜሪካ ባስተናገደችው የአትላንታ ኦሊምፒክ ችቦውን እንዲለኩስ ከመደረጉ ባሻገር ወንዝ የጨመረው የወርቅ ሜዳሊያ ምትክ ሌላ ሜዳሊያ በአንገቱ ተጠልቆለታል። በ1970 የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ሽልማት የተቀበለው መሐመድ አሊ፤ የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነት ተምሳሌት ሆኖም ያውቃል። የተባበሩት መንግሥታት የሰላም መልዕክተኛ ሆኖም ከ1998 እሰከ 2008 በታዳጊ አገራት በመዘዋወር አገልግሏል። ታላቁን የደቡብ አፍሪካ ነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ከእስር እንደተፈቱ በአካል ተገኝቶ ደስታውን ለመግለፅ መሐመድን የቀደመው አልነበረም። አዲስ ዘመን የካቲት 22/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=28169
06c13cdd6749ad9b64c1d091309c1493
e69e93f180f59c3569cf0cb2bbc302a6
የኦሎምፒክ ተሳትፎ ያልተሳካለት ብሄራዊ ቡድን
ስፖርት
ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ በብዛት ተሳታፊ ከሆነችባቸው የአትሌቲክስና ብስክሌት ስፖርቶች በመቀጠል ይጠቀሳል፤ ቦክስ፡፡ በቦክስ ስፖርት የመጀመሪያው የኦሊምፒክ መድረክ ተሳትፎ እአአ በ1968 በተካሄደው የሜክሲኮ ኦሊምፒክ ሲሆን፤ በወቅቱም አራት ቦክሰኞች ተካፋይ ነበሩ። ከዚያ በኃላ በተካሄዱ ስምንት ኦሊምፒኮች ላይም ሃገሪቷ ስፖርተኞቿን ማሳተፏን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን መረጃ ይጠቁማል፡፡ በመድረኩ ለመጨረሻው ተሳትፎ ካደረገችበት እአአ የ2008 ቤጂንግ ኦሊምፒክ በኋላም ተሳታፊ የሚያደርጋትን እድል ሳታገኝ በመቅረቷ ኢትዮጵያ በስፖርቱ አልተወከለችም፡፡ ከወራት በኋላ ጃፓን በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ የአዘጋጅነት እድሉን ባገኘችበት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፤ ከአትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ቴኳንዶ እና የውሃ ዋና ስፖርቶች በተጓዳኝ ተሳታፊ ለመሆን ያቀደበት ሌላኛው ስፖርት ቦክስ ነበር፡፡ ለእቅዱ መሳካት ይረዳ ዘንድም በማጣሪያ ውድድር ላይ ብሄራዊ ቡድኑ ተካፋይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሴኔጋሏ ዳካር አስተናጋጅነት በተካሄደው በዚህ ቻምፒዮና ላይም ስድስት ወንድ እና አንዲት ሴት ቦክሰኞች፤ በ48፣ 52፣ 57፣ 63፣ 69፣ 75 እና 81 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪ ሆነው ነበር፡፡ ከዳካር የአየር ጸባይ ጋር ለመለማመድ እንዲያስችላቸውም መቀመጫቸውን በአርባ ምንጭ በማድረግ ለረጅም ጊዜ በልምምድ ላይ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥቂቱ መነቃቃት የታየበት የቦክስ ስፖርት በአህጉር አቀፍ ውድድሮች ላይ ሜዳሊያዎችን ማስቆጠርና ተወዳዳሪነቱን በማስመስከር ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ትናንት ወደ ሃገሩ የተመለሰው ብሄራዊ ቡድኑ በማጣሪያው የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ቶኪዮ ያቀናል የሚል ከፍተኛ ግምትም አግኝቶ ነበር፡፡ በሴኔጋል በነበራቸው ቆይታም የመጀመሪያዎቹን ዙሮች በብቃት በማለፍ ያላቸውን ተስፋ ማሳየት ችለዋል፡፡ ዙሩ እየገፋና እየከበደ መሄዱን ተከትሎም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ ይሁን እንጂ ሶስት ቦክሰኞች እስከ ስምንት ባለው ደረጃ በመግባት ጥቂት ትኩረት ቢያገኙ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚችሉ ማረጋገጣቸውን በኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን የውድድር ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ተስፋዬ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡ በአልጀሪያ በተካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ እንዲሁም በሞሮኮ ራባት የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው የ48 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪው ዳዊት በቀለ ስምንት ውስጥ ከገቡት መካከል አንዱ ነው፡፡ የ57 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪው ፍቅረማሪያም ያደሳ እና በ81 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪው ሰይፈ ከበደም ስምንት ውስጥ መግባት የቻሉ ቦክሰኞች ናቸው፡፡ ቡድኑ ባይሳካለትም ወደ ሴኔጋል ያቀናው በኦሊምፒኩ ተካፋይ ለመሆን የሚያስቻለውን ውጤት ለማስመዝገብ ካልተቻለ ደግሞ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ለመያዝ ነበር፡፡ ነገር ግን የትኩረትና የልምድ ማነስ እንዲሁም በልምምድ ወቅት ባጋጠመው የቁሳቁስ እጥረት ወደ ታላቁ የስፖርት መድረክ ማለፍ ሳይቻል መቅረቱን ባለሙያው ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህ ባሻገር ዳኝነት ላይም መስራት እንደሚገባም ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ አዲስ ዘመን የካቲት 23/2012  ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=28199
9814a087b269b74f41aae4af96a8ac14
ce05c9f4a505cf6c940856d39f7eba9a
የ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ በተመራጭ ፎቶ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንደሚሆን ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ጽጌረዳ ጫንያለውአዲስ አበባ፡- ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ መራጭ የሚያውቀውን ሰው በትክክል አውቆ እንዲመርጥ በፎቶ የተደገፈ መረጃ እንደሚሰጠውና ሙሉ ምርጫው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሁም የመረጃ ማስገቢያ ባለሙያ የተመደበበት ሆኖ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ። ስድስተኛው አገራዋ ምርጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ በጊዜያዊነት ቀን ተይዞለታል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተወያየበት ወቅት እንደተገለፀው፤ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ ጊዜያዊ የቀን ቀጠሮ የተያዘለት በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በርካታ አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎች ይተገበራሉ። ከእነዚህ መካከልም መራጭ ማንነቱንና ምንነቱን እየለየ እንዲመርጠው የሚያስችል ተመራጭ እንዲኖረው ለማድረግ በፎቶ የተደገፈ ምርጫ መሆኑ ተጠቃሽ ሲሆን፤ ሌላው በባለሙያ የተደገፈ መረጃ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ላይ እንዲኖር ለማድረግ የመረጃ ማስገቢያ ባለሙያ ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸው ነው። አጠቃላይ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተግባሩ የዘንድሮው ምርጫ ለየት የሚያደርገው እንደሆነ የገለፀው ቦርዱ፤ ከምርጫ ምዝገባ እስከ ውጤት ድረስ ያሉ ተግባራት በቴክኖሎጂው አማካኝነት የሚከናወኑ እንደሆነም አስታውቋል። የምርጫ ምልክቶችም ቢሆኑ በሚገባ እንዲመረመሩ የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱንም ጠቁሟል። ቦርዱ በዕለቱ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ፊርማ ማሰባሰቡ ሂደት ላይ፤ የእጩ ምዝገባና ምርጫው የሚደረገው በኮቪድ ውስጥ ሆነን በመሆኑ የወረቀት ልውውጦችና የሰው ለሰው ግንኙነቶች በተቻለ መጠ ንግድ ያልሆኑትን መቀነስ ስለሚያስፈልግ እንዲሁ የፓርቲ ድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ላይ የታዩ ውስብስብ ሂደቶች በመኖራቸው ምክንያት በሕግ የተቀመጠውን ምርጫ ቦርድ መወሰን ስለማይችል ምክርቤቱ ምላሽ እንዲሰጥበት ማስገባታቸውን የገለፁት ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ናቸው። ወይዘሪት ብርቱካን እንደተናገሩት፤ ምርጫው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ከማድረግ ጎን ለጎን ለፖለቲካ ፓርቲዎች የተደላደለ ሜዳ የመፍጠሩ ግዴታ የቦርዱ ሃላፊነት ነው። መንግሥትም ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የመሥራት ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል። ከዚህ ባለፈም ቀደም ሲል በነበሩ ምርጫዎች የተስተዋሉ የአሠራር ግድፈቶች እና ጫናዎች አሁን ላይ ቢሆን በታችኛው የመንግሥት መዋቅር አካባቢ በተወሰነ መልኩ የሚስተዋሉ በመሆኑ በዚህኛው ምርጫ እንዳይደገሙ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል።እንደብልጽግና ይህ ምርጫ የሚታየው በማሸነፍና በመሸነፍ ጠባብ ትርጉም ሳይሆን ታሪካዊ ክስተት በመፍጠር ታሪክ መሥራት እንዴት እንደምንችል አስበን እየተንቀሳቀስንበት ነው፣ ያሉት ደግሞ ገዢውን የብልጽግና ፓርቲን ወክለው በመድረኩ የተገኙት አቶ ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው፤ ታሪካዊ ምርጫ፣ ከተሸነፍን በሰላማዊ መንገድ ማስረከብ እንጂ እንደባለፈው የባከነ ዕድል እያሉ ከንፈር እየመጠጡ መቀጠል አንፈልግም ብለዋል። ካሸነፍን የበለጠ ብልጽግናን እናረጋግጣለን፤ ከተሸነፍን ደግሞ በታሪክ የሚጻፍ ሥራ ሠርተን ቦታውን ለተተኪው እንለቃለን። ምክንያቱም ይህ ምርጫ ለትውልዱ የሚሰጠውን ትርጉምም ስለምናውቅ ማጭበርበር ሳይሆን እውነተኛ ዴሞክራሲን በአገር ላይ ማሳየትም ዋና አላማችን ነው ሲሉም አብራርተዋል።ብልጽግና እንከን የለበትም፣ ንፁህ አባል ያለበት ነው ማለት አይቻልም የሚሉት አቶ ዛዲግ፤ የምርጫውን ሕግ የተላለፉ ሁሉ ቅጣታቸውን እንዲያገኙ እናደርጋለን ብለዋል። ከዚህ በፊትም የተለያዩ ስህተቶችን በማየታችን በሚገባ መፍትሄ ስንሰጥ ቆይተናል፤ ስለሆነም አሁንም አለ የተባለውን ነገር ከሥር መሠረቱ አጥንተንና አይተን መፍትሄ የምናስቀምጥ ይሆናል፤ ለዚህ ደግሞ መጀመሪያውኑ አባሎቻችን ሕግ ሲጥሱ መቃወም ያለብን እኛ በመሆናችን ይህንን ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።የትግራይ ክልል ምርጫ ቋሚ የሥራ አመራሮች እስኪመደብ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ በመድረኩ የተጠቀሰ ሲሆን፤ የአገር አቀፍ ምርጫው አጠቃላይ ውጤትም ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋ እንደሚሆንም ታውቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38161
8b2ad32a1438c10e90ffed756fb48fc3
f56301e5450eeb3bc3010d9dec47f46e
ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ለ“ትንሿ ኢትዮጵያ” ሕጋዊ እውቅና ሰጠች
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ለ“ትንሿ ኢትዮጵያ” ሕጋዊ እውቅና ማግኘቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍፁም አረጋ በማህበራዊ ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ አስታውቁ።አምባሳደሩ እንዳስታወቁት፤ የተሰጠው እውቅና ሁለቱ አገራት ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማሳደግ ባሻገር በማህበራዊና በባህላዊ ዘርፉ የሚደረጉ ግንኙነቶችን ይበልጥ የሚያጠናክረው ነው።አምባሳደር ፍፁም አረጋ የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አስተዳደር እና የአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለ”ትንሿ ኢትዮጵያ” እውቅና እንዲያገኝ ላበረከቱት ድጋፍና አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38158
3617ec1fb8484e313a3e070ca558d84d
849ea38013e759d393125c8ca749680c
መረጃ ፈላጊዎች ባሉበት ሆነው መረጃ ማግኘት የሚችሉበት የተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት ይፋተደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
መላኩ ኤሮሴቢሾፍቱ፡- የመረጃ ፈላጊዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በይነ መረብን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ማግኘት የሚችሉበት የተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት ይፋ ተደረገ፡፡አዲሱን የተቀናጀ የመረጃ ሥርጭት ሥርዓቱን የፌዴራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ሴክተር መሥሪያ ቤቶች እንዲጠቀሙበት ለማድረግና ሥርዓቱን የማስተዋወቅ ሥልጠና መርሃ ግብር በማዕከላዊ ስታትስቲክ ኤጀንሲ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፖፑሌሽን ፈንድ (UNF­PA) ትብብር በቢሾፍቱ ተካሂዷል፡፡በስልጠና መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሳልፈው አበረ እንደተናገሩት፤ ከዚህ በፊት በነበረው የመረጃ ሥርጭት ሥርዓት የመረጃ ተጠቃሚዎች በአካል በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በመገኘት በወረቀት፣ በሲዲ እና በፍላሽ መረጃዎችን ሲቀበሉ ነበር፡፡ ይህ ሥርዓት ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ አንፃር አዋጭ ባለመሆኑ አዲስ የተቀናጀ የመረጃ ሥርጭት ሥርዓት ተዘጋጅቷል፡፡አዲስ ይፋ የተደረገው ሥርዓት ውስጥ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የሚያሰባስባቸው ሳይንሳዊ እና ደረጃቸውን የጠበቁ መረጃዎች እንዲሁም ክልሎች የሚያጠናቅሯቸው የአስተዳደር መረጃዎች ተዓማኒነታቸው እና ጥራታቸው ተረጋግጦ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡ በዚህም የቴሌኮም መሠረተ ልማት ባለበት በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ የሚገኝ ዜጋ አዲስ ወደ ተዘጋጀው ድረ ገፅ በመግባት የሚፈልገውን መረጃ መጠቀም ይችላል፡፡እንደ አቶ አሳልፈው ማብራሪያ፤ የመረጃ ተጠቃሚዎች በአዲሱ ሥርዓት ውስጥ በመግባት የናሙና ጥናት፣ የቆጠራ፣ የአስተዳደር መዛግብት እና ከሌሎች ምንጮች የተሰበሰቡ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ እና ለሚፈልጉት ዓላማ እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል፡፡ሥርዓቱም በሥራ፣ በትምህርት ቤት እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች ሆነው የሚፈልጉትን መረጃ ከተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት አውጥተው እንዲጠቀሙ የሚያስችል በመሆኑ፤ ከዚህ ቀደም የመረጃ ተጠቃሚዎች መረጃ ከኤጀንሲው በአካል መጥተው ለመውሰድ በሚያደርጉት ጥረት ያጋጥማቸው የነበረ እንግልት እና ጉዞ የሚያስቀር መሆኑን ነው አቶ አሳልፈው ያብራሩት፡፡ከዚህም ባሻገር መረጃ ለመውሰድ በሚደረገው እንቅስቃሴ ይጠፋ የነበረው ጊዜ፣ ጉልበት እና ገንዘብ ለመቆጠብ የሚያስችል ሲሆን፤ ሥርዓቱ የመረጃ ተጠቃሚዎችን እርካታ ከማሳደግ ባሻገር፤ መሥሪያ ቤቱ የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት እንደሚያስችለውም አስረድተዋል፡፡እንደ አቶ አሳልፈው ማብራሪያ፤ ሥርዓቱ በርካታ መረጃዎችን የመያዝ አቅም ያለው ነው፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩ መረጃዎችንም ወደዚህ ሥርዓት ውስጥ የማስገባት ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ የ1987 እና የ1999 የሕዝብና ቤት ቆጠራ መረጃዎች ገብተዋል፡፡ እነዚህ መረጃዎች በዚህ ሥርዓት ውስጥ መግባታቸው ትልቅ ፋይዳ አላቸው፡፡ለተለያዩ ዓላማዎች የተለያዩ መረጃዎችን የሚፈልጉ ግለሰቦች እና ተቋማት ከአሁን ጀምሮ ከአዲሱ ሥርዓት መረጃ በመውሰድ መጠቀም እንደሚችሉም አቶ አሳልፈው ጠቁመዋል፡፡የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፖፑሌሽን ፈንድ ተወካይ አቶ አለማየሁ ገብረጻድቅ በበኩላቸው፤ ሥርዓቱን የመዘርጋት ሥራ ዓመታትን እንደወሰደ ገልፀው፤ አማራ እና ደቡብ ክልል ሥርዓት በመዘርጋት ጥሩ ጅምር ማሳየታቸውን አብራርተዋል፡፡ አንዳንድ የውጭ ተቋማት ጭምር መረጃዎችን ከአዲሱ ሥርዓት ወስደው እየተጠቀሙ መሆኑን በመጠቆምም፤ ሌሎች ክልሎችም በአጭር ጊዜ ውስጥ አሠራሩን ወደ መተግበር እንዲገቡ ይሠራል ብለዋል፡፡አዲሱ የመረጃ ማሰራጫ ሥርዓት ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ሰፊ ልዩነት እንዳለው የጠቆሙት አቶ አለማየሁ፤ በአዲሱ ሥርዓት አንዴ መረጃው ወደ ሥርዓቱ ውስጥ ከገባ መቀየር የማይቻል መሆኑ ለየት እንደሚያደርገው አብራርተዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38159
9d4dceaf4e1fe83473f1ddca19a96ce0
fa97e08d8bbff111a391166eb02bb2c3
መቀሌ ያሉ የመንግሥት መሥርያ ቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
 አማን ሚካኤል መስፍንመቀሌ፡- መቀሌ ያሉ የመንግሥት መሥርያ ቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ በሰማዕታት አደራሽ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት፤ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የደረሰው ክህደትና ጥቃት ያወገዙት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በአጭር ጊዜ ሕግ የማስከበሩን ሥራ በማጠናቀቁ አመስግነዋል። በአንፃሩ መቀሌ ያሉ የመንግሥት መሥርያ ቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል፤ በዚህም ህብረተሰቡ እየተጉላላ ይገኛል። የህወሓት ጁንታ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የሕግ ታራሚዎችን ሆን ብሎ በመቀሌ በትኖ ሄዷል ያሉት ተወያዮቹ፤ በእነዚህ ከማረሚያ ቤት ሆን ተብለው በተለቀቁ የሕግ ታራሚዎች ምክንያት በከተማው የፀጥታ ችግር እንዲፈጠር ተደርጓል ሲሉም ነው ያስታወቁት። የሀሰት ወሬ በመቀሌ ከተማ እየተነዛ ህዝቡ እየተሸበረ ስለሆነ አስተዳደሩ ይሄን ያጥራልን ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ ነጋዴው ከመሃል አገር ሸቀጥ እንዳያመጣ “ጦርነት አላለቀም” በሚል ወሬ እየተነዛ ወደ ሥራ እንዳይገባም አድርገውታል ነው ያሉት።በአገር ውስጥም ይሁን በውጭ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ጊዚያዊ አስተዳደሩንም ሆነ ህዝቡን ማገዝ አለበት ያሉት ተወያዮቹ፤ በደቡብ ትግራይ እና ምዕራብ ትግራይ አካባቢ ያሉ ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለበት ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል። የሰሜን ዕዝ አዛዡ ጄነራል በላይ ስዩም በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መከላከያ የአገር ዳር ድንበርን የሚያስከብር ሃይል ነው። ነገር ግን ጁንታው የገደለው ይሄንን ሃይል ነው በማለት የተፈፀመውን ክህደትና ግፍ ለተወያዮቹ አብራርተዋል። “እንደመከላከያ ጓዶቻችን በጁንታው ተገድለዋል፣ የሠራዊቱ ንብረት ተዘርፏል፤ እንደ አገርም በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖ ተፈጥሯል” ያሉት ጄነራሉ፤ የዘጠና ዓመት አዛውንቶች መጥተው ይመሩናል ብላችሁ ተስፋ እንዳታደርጉ፤ በእርግጠኝነት የምነግራችሁ ጁንታው ከዚህ በኋላ አይመለስም፤ ስለዚህ ተረጋግታችሁ ጊዚያዊ አስተዳደሩን ማገዝ አለባችሁ” ሲሉም ለመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።በውይይት መድረኩ ላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፣ የመቀሌ ከንቲባ አቶ ኣታኽልቲ ሃይለሥላሴ እና የሰሜን ዕዝ አዛዥ ጀነራል በላይ ስዩም የተገኙ ሲሆን፤ በወቅቱም የትግራይ ህዝብ የህወሓት ጁንታ ተመልሶ ይመጣል ከሚል ሃሳብ መውጣት እንዳለበት የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብረሃም በላይ ተናግረዋል፡፡በዚሁ መድረክ ላይ ለተነሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ምላሽ እየሰጡ ካሉት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራሩ ዶክተር አብረሃም በላይ እንዳሉት፤ በከተማዋም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ላይ የህወሓት ጁንታን በተመለከተ “ተመልሰው ይመጣሉ” የሚል የሀሰት ወሬ እየተሰራጨ ይገኛል። ይህ የተሳሳተ መሆኑን ህዝቡ ማወቅ አለበት።ህዝባችን በውሸት ሊደናገር አይገባም ያሉት ዶክተር አብረሃም፤ ድሮ ጃንሆይ ከወረዱ በኋላ ህዝቡ ይመለሳሉ ብሎ ሲጠብቅ ነበር፤ ደርግም ከወደቀ በኋላ ይመለሳል ብሎ የሚጠብቅ ሰው ነበር። አሁንም እንደዛ እየጠበቀ ያለ ሰው አለ። ይህ መሆን የለበትም” ሲሉ ተወያዮቹ ላቀረቡት ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ የመንግሥት ሠራተኛ ማለት የህዝብ አገልጋይ ነው፤ ሁሉም ወደ ሥራው ገብቶ ከልብ ማገልገል አለበት። በፊት ህዝብ ያሰቃዩ፣ ጥሩ ሥነ ምግባር የሌላቸው ማልያ ቀይረው ወደ አመራር እንዳይመጡ ህዝቡ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጎን ሆኖ ማገዝ ይኖርበታል፡፡ዶከተር ሙሉ አያይዘውም፤ “የትግራይን ህዝብ ከምትናገረው ስትሰማው ብዙ ትምህርት ትወስዳለህ። እኛ እየሠራን ነው፤ የቀረውን ህዝቡ ሊያግዘን ይገባል። ህዝባችን ያለንን ልንሰማ፣ ራሱ የፈለገውንም ሊመርጥ ይገባል” ሲሉ ለተወያዮቹ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38160
cfd0d75d32e93d4b6de5fed2b1b5f4a0
55c0f335dae61d69a53becfa7c83027f
ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ100 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ100 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ የብድር ስምምነቱን በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ያስሚን ወሀብሬቢ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተፈርሟል።በስምምነቱ ወቅት ሚኒስትር ዴታዋ ያስሚን እንደተናገሩት፤ ከዓለም ባንክ የተገኘው የ100 ሚሊዮን ዶላር የብድር በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍና አዳዲስ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያግዛል። ገንዘቡም በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የክህሎት ስልጠና አግኝተው ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል።አበዳሪ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትንና ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ቢሮዎች የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚረዳቸው የጠቆሙት ሚንስትር ዴኤታዋ፤ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የምታደርገውን የልማት ሥራ ለመደገፍ ለሰጠው የፈጣን ምላሽም አመስግነዋል።በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በበኩላቸው፤ ብድሩ በአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፍ የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶችን ለማገዝ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተደረገው የብድር ስምምነትም በአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ክህሎታቸውን በማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ አዳዲስ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ገቢን ለማሳደግ እንደሚስችላቸው ገልፀዋል።የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ሴቶችና ወጣቶችን ለማበረታታት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚያደርገው ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ የብድር ስምምነቱ ከ38 ሺህ በላይ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የሚውል መሆኑንም አንስተዋል። የሚገኘው ገንዘብ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ መቀሌ፣ አክሱም፣ ባህር-ዳር፣ ጎንደር፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ አዳማ፣ አሰላ እና በመላ አገሪቱ በሚገኙ ሌሎች 89 የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ማዕከላት (ሳተላይቶች) ተግባራዊ እንደሚሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ የገንዘብ እጥረት ያለባቸውን ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ብድር የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ብሎም ኮቪድ-19 በሥራቸው ላይ ጫና ያሳደረባቸውን ሴቶች ለመደገፍ እንደሚያግዝ ተነግሯል።በአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሥራ ፈጣሪ ሴቶችም ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ከፍተኛ ማስያዣ ብድር ለማግኘት እንደሚያስችላቸው፤ እንዲሁም በአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የካናዳ፣ ጣሊያን፣ የጃፓን መንግሥትና እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እገዛ ሲያደርጉ የቆዩ መሆኑን እና ወደ ፊትም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ስለመነገሩ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38170
2eea43a1d7107df1ab3fad08d87d4742
acb120ea2706d44a947613b1253582e0
ከመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የተፈናቀሉ ወገኖች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን ተናገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
መሀመድ ሁሴን አዲስ አበባ፡- በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በንፁሃን ላይ ከተፈፀመው ጥቃት አምልጠው በቡለን ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮች በረሃብና በጥም የተነሳ ለሞት አደጋ መጋለጣቸውን ተናገሩ፡፡ አስተያየታቸውን ትናንት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰጡት እነዚሁ ተፈናቃዮች፤ ከግድያው ለማምለጥ ምንም ነገር ሳይዙ ከቤታቸው በመውጣታቸው የተነሳ አሁን ላይ የሚበሉትና የሚጠጡት እንዳጡና ከመንግሥትም ያገኙት ድጋፍ እንደሌለ በምሬት ተናግረዋል። የስምንት ልጆች አባት የሆኑትና በበኩጂ ቀበሌ ከአስር ዓመታት በላይ የኖሩት አርሶ አደር ደረጀ በየነ እንደገለፁት፤ ከሞት አምልጠውና ከአርባ አምስት ኪሎ ሜትር በላይ በእግራቸው ተጉዘው ቡለን ወረዳ መድረስ ቢችሉም፣ በርሃብና በጥም የተነሳ ሌላ ሞት እንደተጋፈጡና ጠያቂ የመንግሥት አካል እስካሁን አላገኙም። በወረዳው ሥር የሚገኙ ሁሉም የቀበሌ ነዋሪዎች የእግር መርገጫ እስኪጠፋ ድረስ በቡለን ወረዳ ተሰባስበው በረሃብ እየተቆሉ ይገኛሉ ያሉት አርሶ አደር ደረጀ፤ ‹‹ህይወታቸውን ካጡት እህት ወንድሞቻችን ሐዘንና ድንጋጤ ሳንወጣ ይዘን የሸሸናቸውን ልጆቻችንን ልናጣ የምንችልበት አደገኛ የረሃብ ችግር ውስጥ ወድቀናል፡፡ ጠያቂ አካል አላገኘንም፡፡ ትምህርት ቤቶች እና አዳራሾች በተፈናቃዮች ሞልተው ተጨናንቀዋል፡፡ ህፃናት ልጆቻችን የሚልሱት የሚቀምሱት አጥተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም በከፍተኛ ጭንቀት ላይ እንገኛለን›› ሲሉ ሀሳባቸውን በምሬት ገልፀዋል፡፡ ‹‹በፍራቻና በሥጋት ሰቀቀን ውስጥ መኖር ከጀመርን ዓመት አልፎናል፡፡ ከወረዳና ከክልል የሚመጡ አመራሮች የጉሙዝ ማህበረሰብን ብቻ ለይተው ይሰበስባሉ፡፡ ለእኛ ዞረው ሰላም ነው፤ ምንም ችግር አይደርስባችሁም እያሉ ሲያዘናጉን ኖረዋል፡፡ ስለዚህ ከጀርባ ሌላ የጭፍጨፋ ሴራ እየተዘጋጀ ሕዝቡ እንዳይነቃ እና ወደሌላ አካባቢ እንዳይሸሽ ሲደረግ ኖሯል፡፡ በዚህ የተነሳም ከበኩጂ ብቻ ያለቀው ሰው ብዙ ነው፡፡ እኔ በዓይኔ ተሰብስቦ የተመለከትኩት 207 አስከሬን ነው” ያሉት አርሶ አደር ደረጀ፤ የወንድማቸው አምስት ልጆችና ባልና ሚስትን ጨምሮ ሰባት ቤተሰባቸው እንደተገደሉባቸው በሐዘን ተናግረዋል፡፡ የጭላንቆ ቀበሌ ነዋሪው የሆኑት ሌላው አስተያየት ሰጪ አርሶ አደር ወንድማገኝ ሻምበል በበኩላቸው፤ የተፈፀመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ አስከፊ ከመሆኑም በላይ በህይወት የተረፍነውም ለከፍተኛ መከራ ዳርጎናል ብለዋል፡፡ “ህፃናት እና ሴቶች ከጭፍጨፋው አምልጠው በቡለን ወረዳ በመሰባሰብ በከፍተኛ ረሃብ ላይ ወድቀዋል፡፡ ማንም የሚጠይቅ አካል የለም፡፡ በዚህ የተነሳ ከፍተኛ ተጨማሪ እልቂት መፈጠሩ አይቀርም” ሲሉ አርሶአደሩ ሥጋታቸውን አስረድተዋል፡፡ አመራሩ የችግሩ ዋና አካል መሆኑን ያነሱት አርሶ አደር ወንድም አገኝ ፤ ‹‹ከወረዳ ወደ ቀበሌ የሚመጡ አመራሮች እኛን ሊያስገድሉን ነበር፡፡ ከጭላንቆ ቀበሌ ሩጠን በማምለጥ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አዲስ ዓለም ከምትባል ቀበሌ ገብተን ተቀመጡ መከላከያ ሠራዊት መጥቶላችኋል ብለው አታለሉን። በዚህም የተነሳ ወንድማችን በአራት ቀስት ተመትቶ ሞቷል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሕብረተሰቡ አብሮ ከጉምዝ ብሔረሰቦች ጋር ቡና የሚጠጣ ሕዝብ ነው ያሉት አርሶ አደሩ፤ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እኛ ወደ ማሣ ሥራ ስንሄድ ከወረዳ ከሚመጡ አመራሮች ጋር ብቻቸውን ይመክራሉ፤ በዚህም የተነሳ ጥቃቱ እየጨመረ መጥቷል›› ብለዋል፡፡ “ብዙ ወገኖቻችንን በግድያው ከማጣታችን በላይ በመከራ ላይ መከራ፣ በችግር ላይ ችግር እያሰቃየን እንገኛለን፡፡ የሦስት ቀን አራስ ህፃን ልጅ በዘንቢል ይዘን ነው የወጣነው፡፡ አዝመራዬን ወቅቼ 180 ኩንታል ሜዳ ላይ እንደደረደርኩት ትቼው ወጥቻለሁ፡፡ መኪና እንኳን ማግኘት አልቻልንም፡፡ አምልጠን የወጣነውም በእግራችን ነው፡፡ ባዶ ራቁታችንን ወጥተን ቡለን ብንደርስም ሌላ መከራ ነው የጠበቀን፡፡ ወድቀን ያለነው ከሕብረተሰቡ ላይ ነው፡፡ እኔ አመራር ነኝ ብሎ ተፈናቃዮችን ያነጋገረና የጠየቀ አካል እስካሁን የለም›› በማለት ብሶታቸውን ተናግረዋል፡፡ በጉሙዝ ማህበረሰብ እና በሌላው ሕብረተሰብ መካከል ምንም አይነት ችግር እንደሌለ የገለፁት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ “የሚያስፈጁን በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው አመራሮች እኩይ ድርጊት በመሆኑ አጥርቶ እርምጃ መውሰድ እና የተፈናቀለውን ማቋቋም አስፈላጊ ነው” ሲሉ መፍትሄ ያሉትን ጠቁመዋል፡፡ እንደ ዝግጅት ክፍል የነዋሪዎቹን አስተያየት በመያዝ ወደሚመለከታቸው የቤንሻንጉል ክልል የሥራ ኃላፊዎች በመደወል ጉዳዩን ለማጣራትና አስተያየታቸውን እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ሆኖም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለኢቢሲ በሰጡት አስተያየት፤ በግድያው እጃቸው አለበት ተብለው የሚጠረጠሩት አመራርም ይሁን፣ ግለሰቦችም ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል። “አሁንም ቢሆን በህብረተሰቡ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ በግጭቱ ላይ የአመራሮች ተሳትፎ አለበት የሚል ነገር አለ፡፡ እኛ ዝግ አላደረግነውም፤ እንደክልል መንግሥት የሚወራው ወሬ እንደተጠበቀ ሆኖ የማጥራት ሥራዎች በመሥራት ተጨባጭ ማስረጃዎች ስናገኝ ማንኛውም ሰው ወደ ሕግ እንዲቀርብ እያደረግን ነው ያለነው” ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ። አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=38181
1d2e502eb68809b27e7408458ef69f51
6b07adb188e128bd441e9ee7b40d557e
በትግራይ ክልል ያሉ ኢንዱስትሪዎችን ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ፋንታነሽ ክንዴአዲስ አበባ፡-ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ሥራ ለማስጀመር እየሠራ መሆኑን አስታወቀ። በክልሉ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋርም ውይይት አድርጓል።የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዮሐንስ ድንቃየሁ በትግራይ ክልል ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ትናንት ውይይት ባካሄዱበት ወቅት እንደገለጹት፤ በክልሉ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ያሉበት ደረጃ እየተጣራ ሲሆን፤ ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በትግራይ ክልል በተወሰደው ሕግ ማስከበር እርምጃ ወቅት የተጎዱ ኢንዱስትሪዎች ካሉ በትክክለኛ መረጃ ላይ በመመስረት ተገቢውን ድጋፍ አግኝተው በተቻለ ፍጥነት ወደሥራ እንዲመለሱ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህንንም ተከትሎ በኢንዱስትሪዎች ላይ የደረሰውን ችግርና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ የሚያጠና ቡድን በሚኒስቴሩ መቋቋሙን አስታውቀዋል። በውይይቱ ላይ የተገኙ ባለሀብቶችም በሕግ ማስከበሩ ምክንያት ፋብሪካቸው ላይ የደረሰውን ጉዳትና ከመንግሥት የሚፈልጉትን ድጋፍ አቅርበዋል። በወቅቱ እንደገለጹትም፤ የፋብሪካዎችና ማምረቻ መሣሪያዎች ውድመት፣ ለሠራተኛ ደመወዝ ለመክፈል መቸገር፣ የወደብ ኪራይ፣ ምርት ለማቅረብ ውል ፈጽመው በወቅቱ ማቅረብ አለመቻል፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ከጉምሩክና ባንክ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች በባለሀብቶቹ ከተነሱት ችግሮች መካከል ናቸው። አንዳንድ ባለሀብቶች በደረሰባቸው ከፍተኛ ውድመት ምክንያት መንግስት ከፍ ያለ ድጋፍ ካላደረገላቸው ወደ ሥራ ለመመለስ እንደሚቸገሩ ሲገልጹ፤ ሌሎች ደግሞ በፋብሪካቸው ላይ የከፋ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው በመግለጽ የተወሰነ እገዛ ካገኙ በአጭር ጊዜ ሥራ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ እንዳሉት፤ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በአጭር ጊዜ፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን እየለዩ በፍጥነት እየፈታ ይሄዳል። ባለሀብቶችም ትክክለኛ መረጃ በመስጠት የሚያስፈልጋቸውን እገዛ እንዲጠይቁ አሳስበዋል። ከወደብ፣ ከመሰረተ ልማትና ከጉምሩክ ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ አብራርተዋል።በቅርቡ ሥራ መጀመር የሚችሉና የውጭ ምንዛሬ ችግር ያለባቸው ባለሀብቶች የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ በብሔራዊ ባንክ መፈቀዱን በመግለጽም፤ ሥራ ማስኬጃ የሚፈልጉ ካሉም ተገቢው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል። ኢንዱስትሪዎችም ሠራተኞችን ሳይበትኑ በተቻለ ፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38172
621350514e487af63cfeb3c71e87d20d
5dd76b59f07d435206f1c1f722dbc95f
«ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለግለሰብ እና ለቡድን ጥቅም ሲባል በእሳት መጫወት አደጋው ከፍተኛ ነው» ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት
ሀገር አቀፍ ዜና
 ዳንኤል ዘነበአዲስ አበባ፦ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለግለሰብ እና ለቡድን ጥቅም ሲባል በእሳት መጫወት አደጋው ከፍተኛ መሆኑ፤ በእሳት መጫወቱ ካልተጠነቀቁ ማንንም ወደማይምር ሰደድ እሳት እንደሚለውጥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አሳሰቡ።አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በቀን፣ በማታ ያሰለጠናቸውን 4ሺህ 87 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰላም ሚኒስትርና ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በተገኙበት ትናንት አስመርቋል። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ለተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት፤ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለግለሰብ እና ለቡድን ጥቅም ሲባል በእሳት መጫወት አደጋው ከፍተኛ ነው። በእሳት መጫወቱ ካልተጠነቀቁ ማንንም ወደማይምር ሰደድ እሳት ይለወጣል። እኔ ላይ አይደርስም ማለት የዋህነት ነው፤ ይህንን ደግሞ ከሌሎች ሀገሮች መማር ይገባል። በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ንፁሃን ዜጎቻችን እና ለፍቶ አደር ሕዝባችን በማንነት፣ በዘር እና በሃይማኖት ምክንያት ውድ ሕይወታቸውን እጅግ ዘግናኝ በሆነ መንገድ እያጡ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቷ፤ በሕይወት የመኖር መብትን የቀደመ ሌላ መብት ባለመኖሩ በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል ንፁሃን ሕይወታቸውን እንዲያጡ ማንም መፍቀድ እንደሌለበት ተናግረዋል።ከተደገሰልን እልቂት ለማዳን ሕግን የማስከበር ተግባራት በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ ለሁላችንም ተስፋ ሰጪ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፤ ሞትን እና ቀውስን የሚደግሱልን እንዳሉ አይተናል እያየንም ነው፤ በታሪካችን የሀገራችንን ኅልውናን የሚፈታተኑ አደጋዎች ጥለውብን ካለፉት ጥቁር ጠባሳዎች ተገቢውን ትምህርት ወስደን ማንኛውንም ስጋት አራግፈን በጋራ መነሳት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፣ «ዛሬ የተመረቃችሁ ተማሪዎች የሕይወታችሁን አዲስ ምዕራፍ ጀምራችኋል፤ ኢትዮጵያን ነገ የምትመሯት፣ የምታስተዳድሯት፣ የምትታገሉላት፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምትወክሏት እናንተ ናችሁ። የምትኮሩባት ሀገር ብዙ ተስፋ ያላት መሆኗ የማያጠራጥር ሲሆን፣ ያሳለፍናቸው እና እያሳለፍነው ያለው ጊዜ ግን ብዙ ፈተናዎች የተጋረጠበት ነው። እነዚህ የተጋፈጥናቸው ፈተናዎች ያነጣጠሩት በአንድነታችን፣ በሀገር ሉዓላዊነት፣ በኅልውናችን እና በሰላማዊ ዜጎች በሕይወት የመኖር መሠረታዊ መብት ላይ በመሆኑ ልዩ ትኩረት የሚሹ ናቸው፤ ዛሬ የሕይወታችሁን አዲስ ምዕራፍ ስትጀምሩ ልትጽፉበት የተዘጋጃችሁት አዲስ ነጭ ገጽ በታሪክ ስህተት እንዳይበላሽ፣ እንዳይበከል በእጅጉ ተጠንቀቁ» ሲሉ ተመራቂ ተማሪዎች ኢትዮጵያን እንዲጠብቁ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ አስገንዝበዋልም። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በበኩላቸው፤ የዘንድሮው የምረቃ ሥነ ሥርዓት በተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የተነሳ ከቀደሙት የምረቃ በዓላት በእጅጉ የሚለይ መሆኑን ገልጸዋል። የመማር ማስተማር ሂደቱ በተለይ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ቢቋረጥም፤ ተማሪዎቹ የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸውን አስታውሰዋል። በዕለቱም ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 4ሺህ 87 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችንለማስመረቅ መብቃቱን አመልክተዋል። ከተመረቁት አጠቃላይ ተማሪዎች ውስጥ አንድ ሺህ 452 ከምሩቃን ሴት ተማሪዎች ሲሆኑ ከጠቅላላው 35 ነጥብ 5 በመቶ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ከጠቅላላው ተመራቂዎቹ ውስጥ 48ቱ በዶክትሬት ዲግሪ የተመረቁ ናቸው ብለዋል። በ1953 ዓ.ም የተቋቋመው አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2012/2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትናንቱን ጨምሮ ለ70ኛ ጊዜ ያስመረቀ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ብቻ በሁለት ዙር ከ10 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ ፕሮግራም 809 ተማሪዎችን፣ በቀን 3 ሺህ 39 እንዲሁም በርቀት 18 ተማሪዎቹን ለምርቃት አብቅቷል። ከእነዚህ መሀከል 5045 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 313 በ3ኛ ዲግሪ እና 2226 በማታ ፕሮግራም ያሰለጠናቸው መሆናቸው ተጠቁሟል። እንዲሁም በርቀት 180፣ በክረምት 2252፣ በስፔሻሊቲ 265፣ ከፍተኛ ዲፕሎማ በመምህርነት ፕሮግራም 269 ናቸው። ዩኒቨርሲቲው በዓመቱ በአጠቃላይ 10561 ተማሪዎችን አስመርቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38229
b4f1963fe331f8e04cebbd923b798719
cc43bb70bb93e1c5e8505ddb81f7982a
ፌዴሬሽኑ አሰልጣኞችን መረጠ
ስፖርት
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞችን ስም ዝርዝር አስታወቀ። ፌዴሬሽኑ በቅርቡ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ እንደሚገባም ይጠበቃል። በጃፓን አስተናጋጅነት የሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ የወራት እድሜ ብቻ የቀረው መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወደ ዝግጅት ለመግባት የሚያስችለውን የአሰልጣኞች ምርጫ ማድረጉን አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ምርጫውን ባዘጋጀው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ ያከናወነ መሆኑንም በድረ ገጹ አስነብቧል። ፌዴሬሽኑ በአፋጣኝ ወደ ስልጠና ለመግባት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅርቡ ምክክር ማድረጉ የሚታወስ ነው። ከስድስት ወራት ያነሰ ጊዜ ብቻ ለቀረው ውድድር ካለፉት የሪዮ ኦሊምፒክና የዶሃ ዓለም ሻምፒዮና ተሞክሮ በመውሰድ ስልጠና እንዲታቀድና በአፋጣኝ ወደ ትግበራ እንዲገባ ሁኔታዎች እንዲመቻቹም አቅጣጫ አስቀምጧል። ለተግባራዊነቱም ፌዴሬሽኑ በሚያወጣው የምልመላና የስልጠና ዝግጅት ሚናውን እንደሚወጣ ባስታወቀው መሰረት የአሰልጣኞችን ምርጫ ያከናወነ ሲሆን፤ በቅርቡ አትሌቶችን በመምረጥ ወደ ስልጠና እንደሚገባም ይጠበቃል። ምርጫው እርምጃን ጨምሮ ኢትዮጵያ በምትታወ ቅባቸው አምስት ርቀቶች ተደርጓል። በዚህም መሰረት በመካከለኛ ርቀት አሰልጣኝ ብርሃኑ መኮንን፣ ሃብታሙ ግርማ፣ ኢሳ ሽቦ እና ጉዲሳ ታሱ ተመርጠዋል። አሰልጣኝ አብርሃም ኃይለማሪያም እና ስንታየሁ ካሳሁን ደግሞ በተጠባባቂነት የሚቆዩ ይሆናል። በ3ሺ ሜትር ደግሞ አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ እና ዶክተር ብዙአየሁ ታረቀኝ ሲመረጡ አሰልጣን ከፍያለው አለሙ ተጠባባቂ ሆነዋል። ሃገሪቷ በኦሊምፒክ መድረክ በተለይ ውጤታማ በሆነችባቸው የ5ሺ እና 10ሺ ሜትር ርቀቶችም አራት አሰልጣኞች ተመራጭ ሆነዋል። አሰልጣኝ ሁሴን ሸቦ፣ ቶሌራ ዲንቃ፣ ንጋቱ ወርቁ እና ኃይሌ እያሱ ሲመረጡ፤ አሰልጣኝ ተፈሪ መኮንን እና በሪሁን ተስፋይ ደግሞ የተጠባባቂነት ስፍራን ይዘዋል። በረጅሙ የአትሌቲክስ ውድድር ማራቶን በማናጀር አሰልጣኝነት ስኬታማ የሆኑት አሰልጣኝ ሃጂ አደሎ ከሌላው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ጋር በመሆን የርቀቱን እንደሚመሩም በዝርዝሩ ተመልክቷል። አሰልጣኝ ጌታነህ ተሰማ እና ይረፉ ብርሃኑ ደግሞ ተጠባባቂ ሆነው ተመርጠዋል። የእርምጃ ቡድኑም በሻለቃ ባየ አሰፋ አሰልጣኝነት ወደ ቶኪዮ የሚያመራ ይሆናል። ፌዴሬሽኑ ምርጫውን ያሳወቀው ከትናንት በስቲያ ሲሆን፣ በምርጫው ላይ ቅሬታ ያለው አካል እስከ ዛሬ ድረስ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ጽህፈት ቤቱ በመገኘት ማሳወቅ እንደሚችልም ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን ረቡዕ የካቲት 11/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27523
e56c91fec4578a4c41148dbccd5e9ec5
f1eb6ab8101ac38ce8efa30ae780b568
«የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ሆነው አያውቁም፤ ህወሓት ሳይፈጠር የትግራይ ሕዝብ ነበር»የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች
ሀገር አቀፍ ዜና
መቀሌ(ኢዜአ)፡- «የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ሆነው አያውቁም፤ ህወሓት ሳይፈጠር የትግራይ ሕዝብ ነበር ወደ ፊትም ይኖራል» ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ትናንት ተወያይቷል።የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች «የህወሓት ቡድን» በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት ያወገዙ ሲሆን፤ ቡድኑ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የትግራይን ሕዝብ የማይወክልና ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት መሆኑንም ነው የተናገሩት።ከዚህ ቀደም የፓርቲና የመንግሥት ሥራ ተደበላልቆእንደነበረ ያስታወሱት ነዋሪዎቹ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከዚህ ተምሮ ማስተካከል እንዳለበት የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ «የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ሆነው አያውቁም፤ ህወሓት ሳይፈጠር የትግራይ ሕዝብ ነበር ወደ ፊትም ይኖራል» ብለዋል። በከተማዋ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር ሕዝባዊ ፖሊሶች በአግባቡ ተደራጅተው ወደ ሥራ እንዲገቡም ጠይቀዋል። የትግራይ ሕዝብ ከስጋት ነፃ እንዲሆን የጁንታው አባላት ታድነው ለሕግ መቅረብ ይኖርባቸዋል ያሉት ነዋሪዎቹ፤ ለዚህም ሕዝቡና የፀጥታ ኃይሉ እንዲሁም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተባብረው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል። በመቀሌ ከተማ የተቋረጠው የባንክ፣ የትራንስፖርትና የኢንተርኔት አገልግሎት በአስቸኳይ እልባት አግኝቶ ሥራ እንዲጀምርም ጠይቀዋል። «በሰሜን ዕዝ ላይ የህወሓት ቡድን ያደረሰው ጥቃት ሕዝቡን እንደማይወክል እንረዳለን» ያሉት በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም፤ መከላከያው ወንጀለኞችን ከማደንና መልሶ ግንባታ በተጓዳኝ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በበኩላቸው፤ መንግሥት ጉዳት የደረሰባቸውን መሠረተ ልማቶች በመልሶ የመገንባት ሥራ ላይ ርብርብ እያደረገ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥም በርካታ የመሠረተ ልማቶች ወደ ሥራ እንደሚገቡ አረጋግጠዋል። የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ በበኩላቸው፤ «ከዚህ በኋላ በትግራይ ክልል የሰላም፣ የአንድነትና ልማት ጉዳይ በትኩረት ይሰራል» ብለዋል።  አሁን ላይ መቀሌ ከተማ ሰላምና መረጋጋት በመፈጠሩ በርካታ ማህበራዊ አገልገሎቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውም ታውቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38227
33a27a3da597d9efdadc3b586099f1c1
6759fcc5762fa5dd8affae6524dd8f39
ባየር ሙኒክ በኢትዮጵያ ሥልጠና ይሰጣል
ስፖርት
 የጀርመኑ ኃያል ክለብ ባየር ሙኒክ በኢትዮጵያ ለክለቦች የተለያዩ ሥልጠናዎችን እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ሥልጠናው ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ባለሙያዎቹም ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ጋር የተለያዩ ሥራዎችን በጋራ ለማከናወን ማቀዱ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎም ከዚህ ቀደም የልምድ ልውውጥና ሥልጠናዎችን ሰጥቷል፡፡ አሁንም ከፌዴሬሽኑ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክተር ጋር ባደረገው ቅድመ ዝግጅት፤ ለወጣት አሰልጣኞች ለ15 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና የሚሰጥ መሆኑን ፌዴሬሽኑ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡ ሥልጠናውን የሚሰጡት ባለሙያዎች ትናንት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ለቀጣይ 15 ቀናትም ቆይታ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡ ሥልጠናው የሚካሄደው በሁለት ዙር ሲሆን፤ የመጀመሪያው ዙር ሰልጣኞች ከየክልሉ የተውጣጡ ወጣትና ጀማሪ አሰልጣኞች ናቸው፡፡ ወጣቶቹ ከዚህ ቀደም በተሰጠው ሥልጠና ተገቢውን ውጤት በማሟላት ለቀጣይ ያለፉ 30 አሰልጣኞች ሲሆኑ፤ ለተከታታይ አምስት ቀናት በሥልጠና ላይ የሚቆዩም ይሆናል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚሰጠው ሥልጠናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 13/2012 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑም በዘገባው ተመላክቷል፡፡ሁለተኛው ዙር ሥልጠናም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወንድ ክለብ አሰልጣኞችንና አንደኛ ዲቪዚዮን ሴቶች ፕሪሚየርሊግ ክለብ አሰልጣኞችን የሚያካትት ነው፡፡ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናው ከየካቲት 16-18/2012 ዓ.ም ለሦስት ቀናት የሚሰጥም ይሆናል፡፡ ቀጣዩ መርሃ ግብርም ክለቡ በሚያዘጋጀው የባየር ሙኒክ የወጣቶች ዋንጫ ላይ ተሳታፊ ሊሆኑ የሚችሉ ከ15 ዓመት በታች ታዳጊዎችን መመልመል ነው፡፡ የሚመለመሉት አስር ተጫዋቾችም በሚያዝያ ወር መጨረሻ በጀርመን የሙኒክ ከተማ በሚካሄደው የባየርሙኒክ ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆኑበትን ዕድል የሚያመቻች መሆኑንም በዘገባው ተጠቁሟል፡፡ አዲስ ዘመን የካቲት 9/ 2012 ዓ.ም ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27414
8e6167f0783d82e9bd6068262e8fe0df
b91076268f89ce5d1de2ac6ab4f9b259
ለኦሊምፒክ ዝግጅት አትሌቶች በከፍተኛ ደመወዝ ወደ ልምምድ ይገባሉ
ስፖርት
እአአ የ1964ቱ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በታሪኳ ተሳታፊ የሆነችበት ሶስተኛው ኦሊምፒክ ነው። ታላቁ አትሌት አበበ ቢቂላ በኦሊምፒክ ማራቶን ለራሱ እና ለአገሩ ሁለተኛውን፣ በውድድሩ ደግሞ ብቸኛውን ሜዳሊያ ያገኘበትም ነበር። አሁን ደግሞ ጃፓን ከሃምሳ ስድስት ዓመታት በኋላ ኦሊምፒክን በምድሯ ለማስተናገድ ወራት ብቻ የቀሩበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። በዚህ ታላቅ የስፖርት መድረክም የተሻለ ታሪክ ለማስመዝገብ ኢትዮጵያ በተለየ ትኩረት በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች። በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ ከውጤታማነት ባሻገር ተሳትፎም ክብርን ያስገኛል። በውጤታማነት ድርብ ክብርን ለመጎናጸፍ ደግሞ ትኩረት፣ ጥረትና ጽናት አስፈላጊ መሆናቸው ይታመናል።በኦሊምፒክ መድረክ የአገሪቷን ስም በተደጋጋሚ ያስጠራው እንዲሁም ከፍተኛውን የውጤታማነት ስፍራ የሚይዘው የአትሌቲክስ ስፖርት ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ በዚህ ስፖርት በተመዘገቡ ሜዳሊያዎች አማካኝነት ከውጤታማዎቹ አገራት መካከል 36ኛ ስፍራ ላይ ትገኛለች። ነገር ግን በዚህ መድረክ ውጤታማ ያደረጓት አትሌቶች የኋላ ታሪክ ቢጠና በግላቸው የሚያደርጉት ጥረትና ጽናት ሰፊውን ድርሻ ይይዛል። በመሆኑም መንግስት የተሻለ ትኩረት በመስጠት ውጤታማነቱን ለማሳደግና ለማገዝ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል። ለዚህም የመጀመሪያው ርምጃ አትሌቶች የዝግጅት ጊዜያቸውን በትኩረት እንዲያሳልፉ በተሻለ ስፍራ እንዲያርፉ ማድረግ ነው። በመሆኑም የዝግጅት ኮሚቴው ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት ለውድድሩ የተመረጡ አትሌቶች ካምፓቸውን ከፍተኛ ደረጃ ካላቸው ሆቴሎች መካከል በአንዱ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተሰጥቷል። በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጥሪ የተደረገላቸው አትሌቶች ተሰባስበው ወደ ልምምድ እንደሚገቡ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም በብሄራዊ ቡድን የታቀፉ አትሌቶች የላብ መተኪያ ወጪ እጅግ አናሳ መሆኑ በቅሬታ መልክ የሚነሳ ነበር። ይህንንም ለመቅረፍ በመንግስት በኩል በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ለታዋቂ አትሌቶች 50ሺ ብር ደሞዝ እንዲያገኙ እንዲሁም ለሌሎች ጀማሪ አትሌቶች 10ሺ ብር በየወሩ የሚከፈላቸው ይሆናል። በልምምድ ግብዓት እንዲሁም ትጥቅ በኩልም ችግር እንዳይገጥማቸው እየተሰራ መሆኑም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ከትናንት በስቲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጧል። ዝግጅቱን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከስፖርት ማህበራትና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በመሆን ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ለዝግጅቱም የቶኪዮ ብሄራዊ ዝግጅት ኮሚቴ እንዲሁም የቶኪዮ ኦሊምፒክ ቴክኒክ ኮሚቴ በሚልም ሁለት ኮሚቴዎችን አዋቅሯል። ብሄራዊ ኮሚቴው በቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ የሚመራ ሲሆን፣ ትኩረቱን በሃብት አሰባሰብ፣ የልማት ስራዎች፣ የደጋፊ አባላት ላይ እንዲሁም በስፖርተኞች ሽኝትና አቀባበል ላይ ያደርጋል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ የሚመራው የቴክኒክ ኮሚቴው ደግሞ ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በአትሌቶችና አሰልጣኞቻቸው ምርጫ ላይ የሚሰራ ይሆናል። በዚህም መሰረት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እጩ አትሌቶችንና አሰልጣኞቻቸውን ከቀናት በፊት አሳውቋል። በማጣሪያ ውድድር ላይ ያሉት የቦክስና ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርቶችን ጨምሮ ከውሃ ስፖርቶችና ብስክሌት ፌዴሬሽኖችም ጋር ኮሚቴው በትብብር በመስራት ላይ ይገኛል። ቀደም ብሎ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ በመግባት ላይ የሚገኘው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበኩሉ 90 አትሌቶችንና 15 አሰልጣኞችን በማጨት ወደ ልምምድ ለመግባት በመንደርደር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ብሄራዊ ቡድኑ በሶስት ምዕራፍ የተከፈለ ዝግጅት የሚያደርግ ሲሆን፤ በመጨረሻም 50 አትሌቶች ወደ ቶኪዮ የሚጓዙ ይሆናል። ለጊዜው በተሳትፎ ደረጃ የተያዘው ከ800ሜትር እስከ እርምጃ ባሉት ርቀቶች ቢሆንም ሚኒማውን ማሟላት ከተቻለ በ400ሜትርም ተሳታፊ የመሆን እድል እንደሚኖር ተጠቁሟል።የቴክኒክ ኮሚቴው ቀድሞ ዝርዝራቸው ይፋ የተደረጉትን አሰልጣኞች የተመረጡበት መስፈርትም በርካታ አትሌቶችን በማስመረጥ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ባላቸው ልምድ መሆኑን ገልጿል። የአትሌቶች የምርጫ መስፈርት ደግሞ እአአ በ2019 ባስመዘገቡት ሰዓት መሰረት በመምረጥ በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የጸደቀ መሆኑ ተብራርቷል። ለኦሊምፒክ የሚደረገው ዝግጅት አገርን ለማስጠራት የሚደረግ እንደመሆኑ በሁሉም አካላት ዘንድ በተለይም በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በኩል ያለው አለመግባባትን ከወደ ጎን በመተው ለውጤታማነት በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑ በመግለጫው ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን አርብ የካቲት 13/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27626
d78d1eaed739df778b6cc838d9c2728d
b6305edd7b996674665952804200e176
አድዋን ለመዘከር በደብረ ብርሃን ከተማ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል
ስፖርት
በቀድሞዋ የስምንት መቶ ሜትር ኮከብ አትሌት ፋንቱ ሚጌሶ የተቋቋመው ‹ፋን ኢትዮጵያ የስፖርት አገልግሎት› ድርጅት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ከተሞች የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮችን እያካሄደ ይገኛል።የተለያዩ ወቅታዊ ነገሮችን መነሻ በማድረግ የጎዳና ላይ ውድድሮችን በተለያዩ ከተሞች የሚያካሂደው ፋን ኢትዮጵያ ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራት ባሻገር ለበርካታ አትሌቶች የውድድር እድሎችን እየፈጠረም ይገኛል።በተለይም የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች እምብዛም በማይካሄድባቸው ከተሞች ትኩረት በማድረግ አትሌቲክስን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ በመፍጠር በህብረተሰብ አቀፍ ስፖርት(ማስ ስፖርት) እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ውጤቶች እያስመዘገበ ነው።በሀዲያ ሆሳዕና፣ አርባ ምንጭና ሀላባ ከተሞች በቅርቡ የተለያዩ የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድሮችን በስኬት በማድረግ በርካታ ህዝብ አሳትፎ ተወዳጅነትን ማግኘት ችሏል።በቀጣይም የካቲት 22 ቀን 2012 ዓ.ም የ124ኛው አድዋ ድል በዓል ዋዜማ በደብረ ብርሃን ከተማ ‹‹ኑ ለእምዬ ምኒልክ ክብር እንሩጥ›› በሚል መሪ ቃል ተመሳሳይ ውድድር ለማድረግ ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ ታውቋል።የፋን ኢትዮጵያ መስራች አትሌት ፋንቱና የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ መርከብ ለማ ከትናት በስቲያ በውድድሩ ዙሪያ በኢልጌል ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።በውድድሩ ከአርባ ሺ በላይ ህዝብ ለመሳተፍ የቲሸርት ኩፖን መግዛቱን የገለፀችው አትሌት ፋንቱ ታዋቂና ወጣት አትሌቶች በውድድሩ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ተናግራለች።በውድድሩ ውጤታማ የሚሆኑ ወጣት አትሌቶችን ከክለቦች ጋር ከማገናኘት ባለፈ ዓለም አቀፍ ውድድር እንዲያገኙ ሁኔታዎች እንደሚመቻቹም አትሌት ፋንቱ ጠቁማለች።ፋን ኢትዮጵያ ብዙም ባልተለመደው የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ደፍሮ በመግባት አበረታች ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ የገለጸችው አትሌት ፋንቱ ካለፉት ውድድሮች ልምድ በመቅሰም ወደፊት የሚያካሂዳቸውን ውድድሮች በተሻለ የጥራት ደረጃ ለማከናወን ጥረት እንደሚያደርግ አስረድታለች።መሰል ውድድሮች በየዞኑ እና ወረዳው ማካሄድ ቢቻል፤ ህዝቡ ስፖርቱንና አትሌቶችን በባለቤትነት ስሜት በመደገፍ የተለያዩ አካባቢዎችን የአትሌቶች መፍለቂያ ማድረግ እንደሚቻልም አትሌት ፋንቱ ጠቁማለች፡፡ፋን ኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች የሚያደርጋቸው ውድድሮች ከስፖርታዊ ኩነትነቱ ባሻገር ሰላም፣ ፍቅርና አንድነትን የተመለከቱ መልዕክቶች የሚተላለፉበት ቢሆንም ውድድሩን ስፖንሰር በማድረግ በአጋርነት የሚሰሩ ድርጅቶች እንደሌሉ የተናገረችው አትሌት ፋንቱ መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ ከተሞች ውድድሩን ለማሳደግ ያሳዩትን ጥረት በመጥቀስ ምስጋና አቅርባለች።የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ መርከብ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ የምኒልክ የትውልድ ስፍራ የሆነችው ደብረ ብርሃንን ለማሳደግ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች መካሄዳቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል።ከተማ አስተዳደሩ የሰሜን ሸዋ ዞን መቀመጫ እንደመሆኑም የአድዋን ድል ለመዘከር ከሩጫ ውድድሩ ባሻገር የምኒልክን ጀግንነት የሚያሳዩ የተለያዩ መርሃግብሮችን ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።በውድድሩ ወቅት የጸጥታ ጉዳይ እንደማያሰጋ የገለፁም ሲሆን ዞኑና ከተማ አስተዳደሩ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል።ፋን ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች በማካሄድ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በሚደረገው አገር አቀፍ ርብርብ የራሱን ድርሻ እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን፤ ዘንድሮ የሀላባን ዘመን መለወጫ ‹‹ሴራ›› በዓልን አስመልክቶ በሀላባ ከተማ ጥር 2 ቀን የተሳካ የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ለ3ኛ ጊዜ ማካሄዱ ይታወሳል።ከዚያ በፊትም በሆሳህና ከተማ ላይ የመጀመሪያ የጎዳና ላይ ውድድር ያካሄደ ሲሆን ለ2ኛ ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ ማካሄዱ ይታወቃል።ውድድሮቹን  በየዓመቱ ለማካሄድ እንደታሰበም ታውቋል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 14/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=27704
d53f7e0957be92198763882ceebbea66
1025b616479452c4ebf4f8a54e79c921
ሳይበራ የጠፋው የረጅም ርቀት ኮከብ
ስፖርት
 በስፖርቱ ዓለም በወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ ጀግኖች በድንገተኛ አደጋ ሕይወታቸው የሚያልፍበት አጋጣሚ የተለመደ ነው። ይሁን እንጂ በአጭርም ይሁን በረጅም ጊዜ ሕመም ሕይወታቸው የማለፉ ዜና ሲሰማ የብዙዎችን ልብ የሚሰብርና ያልተለመደ መሆኑ አይቀርም። ከሳምንት በፊት አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ኮቤ ብርያንት በገዛ ሄሊኮፕተሩ በደረሰበት የመከስከስ አደጋ በአርባ ዓመቱ ከታዳጊ ልጁ ጋር ሕይወቱ በማለፉ ዓለማችን አዝናለች። ከዚህ የሃዘን ድባብ ሳትወጣም ከቀናት በፊት ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት አትሌት አባዲ ሃዲስ በህመም ምክንያት በመቖለ ሃይደር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 26/2012 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ ሳምንቱ ለስፖርት ቤተሰቡ መጥፎ ሆኖ አልፏል። በተለይም ኦሊምፒክን ጨምሮ በዓለም አቀፍና አህጉራዊ ውድድሮች አገሩን በመወከል የሚታወቀው የ22 ዓመት ወጣት አትሌት አባዲ ሀዲስ ሕልፈተ ሕይወት ለኢትዮጵያውያን አስደንጋጭና መሪር ሃዘን ነው። አትሌት አባዲ ሃዲስ ባደረጋቸው ውድድሮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ በአትሌቲክሱ ውጤታማ ከሆኑት አትሌቶች ተጠቃሽ ከመሆኑ ባሻገር እድሜው ገና ብዙ መስራት የሚችልበት ወጣት መሆኑ ሃዘኑን መሪር ያደርገዋል። አትሌት አባዲ ሃዲስ በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ ልዩ ስሙ እንዳመሆኒ ወረዳ ጥር 27/1990 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን የአትሌቲክስ ህይወቱን በእንዳመሆኒ የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ጣቢያ ነበር የጀመረው። በመቀጠልም በማይጨው አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብቶ መደበኛ ስልጠናውን ሲያጠናቅቅ ትራንስ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ክለብ በመቀላቀል ህይወቱ እስካለፈበት እለት ድረስ በውጤታማነት ክለቡን፣ ክልሉንና አገሩ ሲያስጠራ የነበረ ጀግና ነው። አትሌት አባዲ በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ በተካሄደው የ2016 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ10 ሺ ሜትር 27፡36.34 በሆነ ሰዓት 15ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ በዶሃ ኳታር በተካሄደው የ2019 የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ5ሺ ሜትር አገሩን ወክሎ ተሳትፏል። በለንደን በተካሄደው የ2017 የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናም በ10ሺ ሜትር 26፡59.19 በሆነ ሰዓት 7ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።በኡጋንዳ ካምላ በ2017 በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በአዋቂ ወንዶች 10 ኪሎ ሜትር. ውድድር በ28፡43 ሰዓት 3ኛ ደረጃ በመያዝ የነሐስ ሜዳልያ ለአገሩ ማስመዝገብ የቻለው አትሌት አባዲ በሞሮኮ ራባት በ2019 በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ10ሺ ሜትር 28፡27.38 7ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሎ ነበር። በ2016 በተካሄደው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ10ሺ ሜትር 28፡43.2 በሆነ ሰዓት 1ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀበት አጋጣሚም ከስኬቶቹ መካከል ይጠቀሳል። አባዲ ሩጫን በዓለም አቀፍ ደረጃ በ 5ሺ ሜትር ጀምሮ በ 5ሺ ሜትር ከአራት ወር በፊት በዶሃ የዓለም ቻምፒዮና ላይ አገሩን ወክሎ በመሳተፍ ይቺን ምድር ተሰናብቷል። አባዲ በአትሌቲክስ ሕይወቱ አገሩን ወክሎ በተሳተፈባቸው ውድድሮች ከግል ውጤቱ ይልቅ ለአገር ቅድሚያ የሚሰጥ፣ የቡድን ስራ ጠፍቷል በሚባልበት ወቅት ለቡድን ውጤት የሚጨነቅ ሩቅ አሳቢ ኮከብ መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ምስክርነታቸውን የሰጡት ሕይወቱ ከማለፉ በኋላ አይደለም። ታታሪው ወጣት አትሌት በአትሌቲክስ ሕይወቱ አንድ አትሌት ሊደርስበት የሚመኘው ደረጃ ላይ በአጭር ጊዜ መድረስ ቢችልም ህልሙና ግቡ እንዲህ በአጭሩ የሚቋጭ አልነበረም። አባዲ ሕይወቱ ከማለፉ አስቀድሞ በረጅም ርቀት ዓለማችን ላይ ካሉ ኮከብ አትሌቶች አንዱ ቢሆንም የበለጠው ስኬት ከፊት የሚጠብቀው እንደነበር ብዙዎች በቁጭት ይናገራሉ። ይህ የረጅም ርቀት ኮከብ እንዳለው አቅምና ህልም እስካሁን አላበራም። በረጅም ርቀት በበለጠ ስኬት የሚያበራበት ጊዜ ከፊቱ ቢጠብቀውም ሳይበራ ሞት ቀድሞታል። ከሩጫ ችሎታው በተጨማሪ በባህሪው ዝምተኛና ሰው ቀና ብሎ የማያይ የመልካም ፀባይ ባለቤት የሆነው አባዲ በአጭር ጊዜ የደረሰበት የስኬት ጫፍ ግን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ ሲታወስ እንዲኖር ያደርገዋል። አባዲ በዓለም አቀፍ ደረጃ 34 ውድድሮችን አድርጓል። የ 1 ሜትር ከ70 ሳንቲ ሜትር ቁመት እንዲሁም 63 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ኮከብ ዓለም አቀፍ ውድድር ማድረግ የጀመረው እ.ኤ.አ 2015 በ5 ሺ ሜትር ሲሆን በወቅቱ 13:13፡17 በመሮጥ 13ኛ ደረጃን አገኘ። የመጨረሻውን ውድድርም በዶሀ ዓለም ቻምፒዮና በ 5 ሺ ሜትር 13:42፡89 መሮጥ ችሏል። በ 3 ሺ ሜትር 7:39፡10 እ.ኤ.አ በ2018 ካናዳ ላይ ያስመዘገበው ፈጣን ሰዓቱ ሲሆን በተመሳሳይ ዓመት በ 5 ሺ ሜትር 12:56፡27 ብራሰልስ ላይ ያስመዘገበው የርቀቱ የግሉ ፈጣን ሰዓት ነው። በ10 ሺ ሜትር 26:56፡46 በሄንግሎ ያስመዘገበው ፈጣን ሰዓት ሲሆን በግማሽ ማራቶን 58:44 ቫሌንሲያ ላይ ያስመዘገበው ሰዓት ወደ ፊት ብዙ ተስፋ እንዲጣልበት ያደረገ ነው። አባዲ በአራት ዓመት የሩጫ ህይወት ቆይታው 3 ሺ ሜትርን ሁለት ጊዜ ሮጧል። ስኬታማ በሆነበት 5 ሺ ሜትር ደግሞ አስራ ሦስት ውድድሮችን አድርጓል።አገሩን በኦሊምፒክና በዓለም ቻምፒዮና በወከለበት የ10 ሺ ሜትር ርቀት ዘጠኝ ውድድሮችን ሲያደርግ በ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር አንድ ጊዜ ብቻ ሮጧል። 21 ኪሎ ሜትር ወይም ግማሽ ማራቶንን አራት ጊዜ በመወዳደር ትልቅ ተስፋ የሰጠ ሰዓት ማስመዝገቡም ይታወቃል። በአገር አቋራጭ ውድድሮች በ9፣ 10.4፣10.796 እና 11.1 ኪሎ ሜትር ውድድሮች አንዳንድ ጊዜ ብቻ ሮጧል። አዲስ ዘመን የካቲት 1 / 2012 ዓ.ም ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=26976
4aa72dafd11dcd7ab9559c9e03a02ab6
da5347c7846a191a2cef7948bae9c650
ብልጽግና በንጹሃን ዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈጸምን ጥቃት አወገዘ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ብልጽግና ፓርቲ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት በማድረግ እየተካሄደ ያለውን ጥቃት አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገለጸ።ፓርቲው እንዳስታወቀው፤ ዜጎችን በማንነት ለይቶ በማጥቃት ምንም አይነት የፖለቲካ ትርፍ ሊገኝ አይችልም። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተደጋጋሚ በዜጎች ላይ እየተካሄደ ያለው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት የትኛውንም የሕዝብ ክፍል የማይወክልና ኃላፊነት የማይሰማቸው የግጭት ነጋዴዎች ሴራ መሆኑን መላው የሀገራችን ሕዝቦች ሊገነዘቡ ይገባል።በጨካኝ አረመኔ የጥፋት ኃይሎች ጥቃት በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ላለው ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸን ለዘመናት ተከባብሮ ክፉና ደጉን አብሮ ያሳለፈን ህዝብ በማጋጨት ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚጣጣሩ የውስጥም ሆነ የውጭ ኃይሎች የማይሳካላቸው መሆኑን አጥብቀን ልንገልጽላቸው እንወዳለን።በዜጎች ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸውንና ችግሩ እንዲፈታ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባልተወጡ የስራ ኃላፊዎች ላይ ጥብቅ ፖለቲካዊ፣ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እንገልጻለን።ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን ለፍቶ አዳሪ ንጹሃን ዜጎችን በማንነታቸው ብቻ ለይቶ በማጥቃት ሀገርንና ሕዝብን ወደ ትርምስ ለማስገባት ተቀናጅተው የሚንቀሳቀሱ የውስጥም ሆነ የውጭ ጨካኝ የጥፋት ኃይሎችን አጥብቆ የሚያወግዝና በእነዚህ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶ የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ ብልጽግና ፓርቲ አጥብቆ የሚታገል መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38084
d1e15d22339035d6f2c85f6fa3da96d3
10899382e3f1a02bc48ef67ccba14e9f
የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች የኮቪድ-19 የሕይወት ኢንሹራንስ ሊገባላቸው ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
ፍሬህይወት አወቀአዲስ አበባ፡- ኮቪድ-19 ወረርሽኝ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ተከትሎ ለድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች እና ለረዳት አሽከርካሪዎች የሕይወት ኢንሹራንስ ሊገባላቸው መሆኑን የኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ገለጸ።የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ኤጀንሲው ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች የሕይወት ኢንሹራንስ እንዲኖራቸው ከባለድርሻዎች ጋር ሰፋፊ ውይይቶችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎችና ረዳት አሽከርካሪዎች በኮቪድ 19 ምክንያት ለሚደርስባቸው ጉዳት የሕይወት ኢንሹራንስ ሊገባላቸው ነው።እንደ ወይዘሮ ወርቅነሽ ማብራሪያ፤ አሽከርካሪዎች በወረርሽኙ ቢጠቁ ከኢንሹራንስ አንጻር ህብረተሰቡን እንዴት መጥቀምና መደገፍ ይቻላል የሚለውን በተለያየ መንገድ ማየትና መደገፍ አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል።የሕይወት ኢንሹራንሱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ሚና ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ ሀገር ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ የተለያዩ ምርቶችን የሚያመላልሱ ሾፌሮችን ያለስጋት እንዲንቀሳቀሱ ያስችላል።ሹፌሮችና ረዳቶች በስራቸው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለወረርሽኙ ተጋላጭ በመሆናቸው የተለያዩ መገለሎች የሚደርስባቸው መሆኑ ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ የሕይወት ኢንሹራንሱ መገባቱ ወሳኝ መሆኑን ያስረዱት ወይዘሮ ወርቅነሽ፤ ሾፌሮች ለሚያስተዳድሯቸው የቤተሰብ አባላትም ዋስትና እንደሚሆን ገልጸዋል። ሹፌሮችም ሆኑ ረዳቶች ዋስትና ያላቸው መሆኑን በመረዳት ስራቸውን በልበ ሙሉነት እንዲወጡ ያስችላቸዋልም ብለዋል።በወረርሽኙ ስርጭት ምክንያት የተቀነሱ በርካታ ረዳቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ሾፌሮች ብቻ ወደ ጅቡቲ ወደብ የሚገቡ መሆኑን ተናግረው የሕይወት ኢንሹራንስ መገባቱ ረዳቶቹንም ሆነ ስራ ፈተው የተቀመጡ ሹፌሮችን ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ያደርጋል ብለዋል።ሹፌሮችና ረዳቶች ያለስጋት መስራት ከቻሉ ባለንብረቶችም ተጠቃሚ ይሆናሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በሀገሪቱ ያሉት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በተለይም በሕይወት ኢንሹራንስ ብዙ ልምድ የሌላቸው በመሆናቸው በህብረተሰቡ ውስጥ ሰርጸው እንዲገቡና እንዲታወቁ ዕድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን አመልክተዋል። ከሚፈጥርላቸው ጥሩ አጋጣሚ ባለፈም ወደፊት ቀጣይነት ባለው መንገድ ከድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች በተጨማሪ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችም እንዲቀላቀሉት ያደርጋል። ከዚህም ባሻገር የኢንሹራንስ ኩባንያዎቻችን እያደጉ ሄደው ለሀገሪቱ ትልቅ አቅም መፍጠር የሚችሉ ኢንዱስትሪዎች እንደሚሆኑም ተናግረዋል። ለድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች የሕይወት ኢንሹራንስ በመስጠት ተባባሪ የሆኑት የመድህን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችና የድንበር ተሸጋሪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ማህበራት መሆናቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚና የኢትዮጵያ መድህን ሰጪዎች ማህበር ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ነጻነት ለሜሳ፤ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች በኮቪድ 19 ምክንያት ሞትና ስራ የማቋረጥ አደጋ ቢደርስባቸው ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን ለማቃለል ያለመ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል። ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ለሾፌሮችና ለረዳቶቻቸው ሊከፈል ከሚገባው የአረቦን መጠን 50 በመቶ ብቻ እንዲከፍሉ ያደረጉ ሲሆን ቀሪውን 50 በመቶ ደግሞ የተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች እንዲከፍሉ ማድረጋቸውንም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል። በዓመት የሚከፈል የአረቦን መጠን ለእያንዳንዳቸው በነፍስ ወከፍ ለሾፌር 2046 ብር ከስድስት ሳንቲም ሲሆን ለረዳቶች ደግሞ 754 ብር ከሃምሳ ሳንቲም ይከፈላል። በቫይረሱ ምክንያት የሞት አደጋ ሲደርስባቸው ለሾፌር 250 ሺ ብር ለረዳት ደግሞ 150 ሺ ብር የሚከፈል መሆኑን አቶ ነጻነት ገልጸው፤ በተጨማሪም በኮቪድ ምክንያት ታሞ ለሁለት ወራት ስራ ካቋረጠ ለሾፌር ስድስት ሺ ብር ለረዳት ደግሞ ሶስት ሺ ብር የሚከፈል መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደጀኔ ሉጬ በበኩላቸው፤ እንደ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ኮቪድ 19ኝ በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እንደተሰሩ አስታውሰው፤ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አደጋ ከደረሰ በኋላ ሰዎችን ለመርዳት ከመሄድ ይልቅ አስፈላጊውን በጀት መድበው በቅድመ ጥንቃቄ ላይ ቢሰሩ የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል። ከሕይወት ኢንሹራንስ ጋር ተያይዞም ቫይረሱ ባህሪውን እየቀያየረና እየተስፋፋ የመጣ በመሆኑ የሾፌሮችን ደህንነት መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተው፤ ሾፌሮች ከዚህ ቀደም በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ ሲያነሱት የነበረ ጥያቄ መሆኑንም ተናግረዋል።ለሾፌሮችና ለረዳቶች የሕይወት ኢንሹራንስ መገባቱ አስፈላጊና ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ደጀኔ፤ አሽከርካሪዎች እየተሳቀቁ መጓዝ የሌለባቸው መሆኑን ገልጸው እያንዳንዱ ባለድርሻ አካላትም ለተግባራዊነቱ የበኩሉን መወጣት እንደሚገባ አመልክተዋል። በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የአሽከርካሪዎች እጥረት መኖሩን የገለጹት አቶ ደጀኔ፤ ያሉትን ሾፌሮች በአደጋና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ማጣት የለብንም። አሽከርካሪዎች የኢትዮጵያ ወደቦች እንደመሆናቸው ሾፌሮችን በአደጋ የምናጣ ከሆነ ወደብ አይኖረንም። ስለዚህ ወደብ ሆነው እያገለገሉ ላሉት ሾፌሮች ልዩ ትኩረት መስጠት አስፈላጊ ነው ሲሉም ተናግረዋል።የሕይወት ኢንሹራንሱን ያቀላጥፋሉ ተብለው የሚታሰቡት ማህበራት በመሆናቸውና ማህበራት ደግሞ ከአደረጃጀት መመሪያ ጋር ተያይዞ የመፍረስ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ደጀኔ፤ ለዚህም አሰሪዎች ራሳቸው የህይወት ኢንሹራንሱን ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩና ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪ አስተላልፈዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38070
ee07b1a5d2012640481cad382aae63b8
4aae59a0d3f6cbb46547985bf8b6a26a
በተመድ ሲሰሩ የነበሩና በጡረታ የተገለሉ ሴት ኢትዮጵያውያን በህዳሴው ግድብ እየሰሩ ለሚገኙ ሴቶች የ600 ሺ ብር ስጦታ አበረከቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- ሀገራቸውን ወክለው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያየ ደረጃ ሲያገለግሉ የነበሩና በጡረታ የተገለሉ ሴት ኢትዮጵያውያን በህዳሴው ግድብ ላይ እየሰሩ ለሚገኙ ሴቶች የ600 ሺህ ብር ሥጦታ ማበርከታቸውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ብሔራዊ ምክር ቤት አስተባባሪ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።በሥጦታ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የፅሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሔ እንደገለፁት፤ ሀገራቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያየ የሥራ መስክ ሲያገለግሉ የቆዩ እና አሁን ላይ በጡረታ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ እናቶች በታላቁ በህዳሴ ግድብ ላይ በጥበቃ ለሚገኙ ሴት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለሳሊኒ ፕሮጀክት ሰራተኞች እያደረጉት ላለው ታሪካዊ ስራ ያላቸውን ፍቅር ‹‹የእናቶች መቀነት ለግድባችን ልማት›› በሚል ሀሳብ ስጦታ አበርክተዋል።እንደ ዶክተር አረጋዊ ገለፃ፤ በግድቡ ላይና በግድቡ ዙሪያ በበርካታ አካባቢያዊ ተፈጥሯዊና ማህበራዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነው የትውልድ ሃውልት በማቆም ሥራ ላይ እየተሳተፉ ላሉ 450 ወጣት ሴቶችና በግድቡ ግንባታ ያለውን የሰላም እና የፀጥታ ሥራ ለሚሰሩ ለእያንዳንዳቸው የአንድ ሺ ብር ቦንድ፣ ግድቡን ለሚገነባው ተቋራጭ 50 ሺብር፣ ለውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት 50ሺ ብር፣ በድምሩ 600 ሺ ብር ቦንድ በመግዛት ትውልድ የማይረሳው ትልቅ አሻራ አስቀምጠዋል።በሌላ በኩል በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መሥሪያ ቤት ለ27 ዓመት አገልግለው በጡረታ የተመለሱት ወይዘሮ ገነት ገብረ ክርስቶስ እንደገለፁት፤ ከራሳቸው ጡረታ ደመወዝና ልጆቻቸውን ጠይቀው በጭስና በእንጨት ሸክም ለሚደክሙ የኢትዮጵያ እናቶችን ችግር እንዲቀርፍ ለሚገነባው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የቦንድ ሥጦታ ለማበርከት እንደተነሳሱ ተናግረዋል።ግድቡ የሁላችን በመሆኑ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት እንዳለበት ጭምር ለማሳየት ተርፏቸው ሳይሆን ከሚያገኙት ትንሽ የጡረታ ደሞዛቸው ቀንሰው ማበርከታቸው የዜግነት ግዴታ ከመሆኑም ባሻገር ለሀገር ያላቸውን ፍቅር ለመግለፅ እንደሆነ ወይዘሮ ገነት ገልፀዋል።እናቶች ሥጦታውን ያበረከቱት የመከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል መሃመድ ተሰማ፣ የፌደራል ፖሊስ ተወካይ ኢንስፔክተር ፀደይ አቤኔዘር፣ የህዳሴው ግድብ ምክትል ስራ አስኪጅ አቶ በላቸው፤ የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ተወካይ አቶ ታምሩ እና የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍሬ ህይወት በተገኙበት በሴቶች፣ ህፃናት ወጣቶች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚኒስትሯ በተገኙበት ቦንዱን አስረክበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38083
f739bc758089e9153e6b5705d1533b9a
56896bdd81ecea429d72c618b908ed3d
በመተከል ዞን ለሕዝብ ጥቅም የሚሠራ አመራርና አደረጃጀት እንዲመቻች ተጠየቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
አሶሳ(ኢዜአ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በየጊዜው የሚከሰተው ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት ለሕዝብ ጥቅም የሚሠራ አደረጃጀት፣ አመራር እና አሰራር እንዲመቻች ተጠየቀ። በዞኑ የጸጥታ ችግር ላይ የክልሉ ነዋሪዎች በአሶሳ ከተማ ሲያካሂዱ የቆዩት የማህበረሰብ ምክክር ከትናንት በስቲያ ማምሻውን የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ነዋሪዎቹ በአስር ቡድኖች ተከፋፍለው ባደረጉት ውይይት በዞኑ ዋነኛ ችግሮች እና መፍትሔ ያሏቸውን ሀሳቦች አንስተዋል።ከቡድኖቹ አስተባባሪዎች መካከል አቶ ሞላ አስማረ ለዞኑ የጸጥታ ችግር መባባስ በየደረጃው የሚገኘው አብዛኛው አመራር አድሎአዊ አሠራር መከተሉ መሆኑን ነዋሪዎቹ ማንሳታቸውን አመልክተዋል። የዞኑ አመራር ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ የራሱን ሲያስቀድም እንደነበር ተወያዮቹ አንስተዋል ብለዋል።ችግሮች ሲፈጠሩ አመራሩ ኃላፊነት ወስዶ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ተጠያቂነትን ይሸሹ እንደነበር ያስታወሱት አስተባባሪው፤ በየደረጃው ባሉ አመራሮች በችግሩ ላይ በሚደረጉ ውይይቶች የሃሰት ሪፖርት ይቀርቡ እንደነበረ ጠቁመዋል።የዞኑ የጸጥታ ችግር በአብዛኛው በመገናኛ ብዙሃን ተገቢውን ሽፋን አላገኘም ያሉት አቶ ሞላ፤ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚቀርበው የፈጠራ ወሬም ችግሩን እንዳባባሰው አስረድተዋል። የሕግ የበላይነትን በማስከበር በዞኑ ፖሊስ፣ ፍርድ ቤት እና ሌሎችም ፍትህ አስከባሪ ተቋማት ችግሮች እንደሚታዩባቸው አንስተዋል።ሌላው የቡድኑ አስተባባሪ አቶ በሱፈቃድ አስረስ በበኩላቸው፣ የመሬት ወረራ ለዞኑ ግጭት ሌላው ተጠቃሽ ምክንያት እንደሆነ አመልክተው፤ በአጠቃላይ ሕግን በማስከበር ደረጃ የሚታየው ክፍተት የአካባቢው ጸጥታ ችግር በፍጥነት እንዳይፈታ እንዳደረገው ተናግረዋል። በዞኑ ብልሹ አሰራርን የሚታገል፣ ለሕዝብ ጥቅም የሚሰራ አመራር እና አደረጃጀት መፍጠር ዋነኛው እንደሆነ ነዋሪዎቹ ለችግሮቹ መፍትሔነት ሀሳብ ማቅረባቸውንጠቅሰዋል። የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረገ መሠረተ ልማት ማስፋፋት፣ የመንግስት አደረጃጀት እና መዋቅርን በጎጠኛ አስተሳሰብ ከሚያራምዱ አመራሮች ማጽዳት እንደሚገባም አመላክተዋል።በዞኑ በተለይም የመሬት አስተዳደር ሕግን በሚገባ የሚተገበርና መልካም ስነ-ምግባር ያለው እና ሕገ-መንግሥቱን የሚያስከብር አመራር መፍጠር ሌላው የውይይቱ ተሳታፊዎች ያስቀመጡት መፍትሔ እንደሆኑ ያመለከቱት ደግሞ ሌላው አስተባባሪ አቶ ሻምበል ተገኝ ናቸው።አቶ ሻምበል፣ በዞኑ አስተዳደር ከሕዝብ ስብጥር እና ቁጥር ጋር የተመጣጠነ ውክልና ያለው አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ነዋሪዎቹ ሀሳብ ማቅረባቸውንም ጠቁመዋል። በፍትህ ተቋማትም ሕጉን በአግባቡ የሚተገብር ባለሙያ እና አመራር መመደብ እንደሚያስፈልግም ተጠቅሷል።ሃዋርያ ክፍሌ ይልማ በበኩላቸው፣ እያንዳንዱ የዞኑ ነዋሪ ለጸጥታ አካላት ትክክለኛ መረጃ በመስጠት አብሮ መስራት እንዳለበት ጠቁመው ፤ መንግስትም ህብረተሰቡ የጸጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚሰጠውን መረጃ ተቀብሎ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥም ጠይቀዋል። የህብረተሰቡን ሠላም እያወከ በሚገኘው ሃሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መንግስት አፋጣኝ የመፍትሔ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ገልጸዋል።በተለይ ለህብረተሰቡ ቅርብ የሆኑ የጎጥ፣ ቀበሌ እና ወረዳ አደረጃጀቶች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አመልክተው ፤ የሚመደቡ አመራሮችም ንቁ፣ ታማኝ እና ሕዝቡን ያለአድሎ የሚያገለግሉ ሆነው መመረጥ አለባቸው ብለዋል። ከምንም በላይ የህብረተሰቡን አንድነት በማጠናከር ዘረኝነትን ማስወገድ እና አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያን መፍጠር አጽንኦት እንዲሰጠው ነዋሪዎቹ ማመልከታቸውን አስተባባሪዎቹ አብራርተዋል።ነዋሪዎቹ በምክክር መድረኩ ለችግሩ ያነሷቸውን የመፍትሔ ሀሳቦች መንግሥት ተቀብሎ እንዲተገብርም ጠይቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38086
cd495016ee848e3af4b26c3eaafedcb4
b79dd0302fad1d7113c4fc94ff167862
ሜጀር ጄኔራል ከድር አራርሳ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥና የሎጂስቲክስ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ከድር አራርሳ ትናንት ፍርድ ቤት ቀረቡ።እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ ሜጀር ጀኔራል ከድር አራርሶ የሰሜን እዝ የጦር መሳሪያ በሕወሓት ልዩ ኃይል እንዲዘረፍ መረጃ ሰጥተዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ ትናንት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል። እንደ ዘገባው፣ ተጠርጣሪው የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥና የሎጂስቲክስ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ በነበረበት ጊዜ ከሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር መረጃ ሲሰጡ ነበር ተብሏል። ከዚህ በፊት በእዙ ስር ያሉ መሳሪያዎችን ከአካባቢው ለማንሳት ሙከራ በተደረገበት ወቅት እንቅስቃሴው እንዲሰናከል ስለማድረጋቸው መረጃ ማሰባሰቡን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል። ተጠርጣሪው ከህወሓት ቡድን ጋር ባላቸው ግንኙነት በአድሏዊ አሰራር በተደጋጋሚ የውጭ አገር እድል ይሰጣቸው እንደነበርም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል። በመሆኑም ፖሊስ ለቀሪ የምርመራ ስራዎች 14 ቀን እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ተጠርጣሪው በበኩላቸው “በተባለው ጉዳይ ጥፋት የለብኝም ፍርድ ቤቱ በነፃ ያሰናብተኝ” ሲሉ ጠይቀዋል።የግራ ቀኝ ክርክሩን ያደመጠው ችሎቱ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀን 11 ቀን በመፍቀድ ለታሕሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38071
928713b70f0ae1ed2748f15cab6354b5
5e4d2ef8b38ea306d8d624c93f991a5a
ከመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የተፈናቀሉ ወገኖች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን ተናገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
መሀመድ ሁሴንአዲስ አበባ፡- በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በንፁሃን ላይ ከተፈፀመው ጥቃት አምልጠው በቡለን ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮች በረሃብና በጥም የተነሳ ለሞት አደጋ መጋለጣቸውን ተናገሩ፡፡አስተያየታቸውን ትናንት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰጡት እነዚሁ ተፈናቃዮች፤ ከግድያው ለማምለጥ ምንም ነገር ሳይዙ ከቤታቸው በመውጣታቸው የተነሳ አሁን ላይ የሚበሉትና የሚጠጡት እንዳጡና ከመንግሥትም ያገኙት ድጋፍ እንደሌለ በምሬት ተናግረዋል።የስምንት ልጆች አባት የሆኑትና በበኩጂ ቀበሌ ከአስር ዓመታት በላይ የኖሩት አርሶ አደር ደረጀ በየነ እንደገለፁት፤ ከሞት አምልጠውና ከአርባ አምስት ኪሎ ሜትር በላይ በእግራቸው ተጉዘው ቡለን ወረዳ መድረስ ቢችሉም፣ በርሃብና በጥም የተነሳ ሌላ ሞት እንደተጋፈጡና ጠያቂ የመንግሥት አካል እስካሁን አላገኙም። በወረዳው ሥር የሚገኙ ሁሉም የቀበሌ ነዋሪዎች የእግር መርገጫ እስኪጠፋ ድረስ በቡለን ወረዳ ተሰባስበው በረሃብ እየተቆሉ ይገኛሉ ያሉት አርሶ አደር ደረጀ፤ ‹‹ህይወታቸውን ካጡት እህት ወንድሞቻችን ሐዘንና ድንጋጤ ሳንወጣ ይዘን የሸሸናቸውን ልጆቻችንን ልናጣ የምንችልበት አደገኛ የረሃብ ችግር ውስጥ ወድቀናል፡፡ ጠያቂ አካል አላገኘንም፡፡ ትምህርት ቤቶች እና አዳራሾች በተፈናቃዮች ሞልተው ተጨናንቀዋል፡፡ ህፃናት ልጆቻችን የሚልሱት የሚቀምሱት አጥተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም በከፍተኛ ጭንቀት ላይ እንገኛለን›› ሲሉ ሀሳባቸውን በምሬት ገልፀዋል፡፡ ‹‹በፍራቻና በሥጋት ሰቀቀን ውስጥ መኖር ከጀመርን ዓመት አልፎናል፡፡ ከወረዳና ከክልል የሚመጡ አመራሮች የጉሙዝ ማህበረሰብን ብቻ ለይተው ይሰበስባሉ፡፡ ለእኛ ዞረው ሰላም ነው፤ ምንም ችግር አይደርስባችሁም እያሉ ሲያዘናጉን ኖረዋል፡፡ ስለዚህ ከጀርባ ሌላ የጭፍጨፋ ሴራ እየተዘጋጀ ሕዝቡ እንዳይነቃ እና ወደሌላ አካባቢ እንዳይሸሽ ሲደረግ ኖሯል፡፡ በዚህ የተነሳም ከበኩጂ ብቻ ያለቀው ሰው ብዙ ነው፡፡ እኔ በዓይኔ ተሰብስቦ የተመለከትኩት 207 አስከሬን ነው” ያሉት አርሶ አደር ደረጀ፤ የወንድማቸው አምስት ልጆችና ባልና ሚስትን ጨምሮ ሰባት ቤተሰባቸው እንደተገደሉባቸው በሐዘን ተናግረዋል፡፡ የጭላንቆ ቀበሌ ነዋሪው የሆኑት ሌላው አስተያየት ሰጪ አርሶ አደር ወንድማገኝ ሻምበል በበኩላቸው፤ የተፈፀመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ አስከፊ ከመሆኑም በላይ በህይወት የተረፍነውም ለከፍተኛ መከራ ዳርጎናል ብለዋል፡፡ “ህፃናት እና ሴቶች ከጭፍጨፋው አምልጠው በቡለን ወረዳ በመሰባሰብ በከፍተኛ ረሃብ ላይ ወድቀዋል፡፡ ማንም የሚጠይቅ አካል የለም፡፡ በዚህ የተነሳ ከፍተኛ ተጨማሪ እልቂት መፈጠሩ አይቀርም” ሲሉ አርሶአደሩ ሥጋታቸውን አስረድተዋል፡፡አመራሩ የችግሩ ዋና አካል መሆኑን ያነሱት አርሶ አደር ወንድም አገኝ ፤ ‹‹ከወረዳ ወደ ቀበሌ የሚመጡ አመራሮች እኛን ሊያስገድሉን ነበር፡፡ ከጭላንቆ ቀበሌ ሩጠን በማምለጥ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አዲስ ዓለም ከምትባል ቀበሌ ገብተን ተቀመጡ መከላከያ ሠራዊት መጥቶላችኋል ብለው አታለሉን። በዚህም የተነሳ ወንድማችን በአራት ቀስት ተመትቶ ሞቷል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ሕብረተሰቡ አብሮ ከጉምዝ ብሔረሰቦች ጋር ቡና የሚጠጣ ሕዝብ ነው ያሉት አርሶ አደሩ፤ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እኛ ወደ ማሣ ሥራ ስንሄድ ከወረዳ ከሚመጡ አመራሮች ጋር ብቻቸውን ይመክራሉ፤ በዚህም የተነሳ ጥቃቱ እየጨመረ መጥቷል›› ብለዋል፡፡“ብዙ ወገኖቻችንን በግድያው ከማጣታችን በላይ በመከራ ላይ መከራ፣ በችግር ላይ ችግር እያሰቃየን እንገኛለን፡፡ የሦስት ቀን አራስ ህፃን ልጅ በዘንቢል ይዘን ነው የወጣነው፡፡ አዝመራዬን ወቅቼ 180 ኩንታል ሜዳ ላይ እንደደረደርኩት ትቼው ወጥቻለሁ፡፡ መኪና እንኳን ማግኘት አልቻልንም፡፡ አምልጠን የወጣነውም በእግራችን ነው፡፡ ባዶ ራቁታችንን ወጥተን ቡለን ብንደርስም ሌላ መከራ ነው የጠበቀን፡፡ ወድቀን ያለነው ከሕብረተሰቡ ላይ ነው፡፡ እኔ አመራር ነኝ ብሎ ተፈናቃዮችን ያነጋገረና የጠየቀ አካል እስካሁን የለም›› በማለት ብሶታቸውን ተናግረዋል፡፡ በጉሙዝ ማህበረሰብ እና በሌላው ሕብረተሰብ መካከል ምንም አይነት ችግር እንደሌለ የገለፁት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ “የሚያስፈጁን በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው አመራሮች እኩይ ድርጊት በመሆኑ አጥርቶ እርምጃ መውሰድ እና የተፈናቀለውን ማቋቋም አስፈላጊ ነው” ሲሉ መፍትሄ ያሉትን ጠቁመዋል፡፡ እንደ ዝግጅት ክፍል የነዋሪዎቹን አስተያየት በመያዝ ወደሚመለከታቸው የቤንሻንጉል ክልል የሥራ ኃላፊዎች በመደወል ጉዳዩን ለማጣራትና አስተያየታቸውን እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ሆኖም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለኢቢሲ በሰጡት አስተያየት፤ በግድያው እጃቸው አለበት ተብለው የሚጠረጠሩት አመራርም ይሁን፣ ግለሰቦችም ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።“አሁንም ቢሆን በህብረተሰቡ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ በግጭቱ ላይ የአመራሮች ተሳትፎ አለበት የሚል ነገር አለ፡፡ እኛ ዝግ አላደረግነውም፤ እንደክልል መንግሥት የሚወራው ወሬ እንደተጠበቀ ሆኖ የማጥራት ሥራዎች በመሥራት ተጨባጭ ማስረጃዎች ስናገኝ ማንኛውም ሰው ወደ ሕግ እንዲቀርብ እያደረግን ነው ያለነው” ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38147
703dc9d35d45801b260a4826850e0270
1f35ffd690294983599ae0360f1b225b
ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በማጠናከር የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች በጋራ መክተው ማለፍ ይገባቸዋል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ከመቼውም ጊዜ በላይ ዜጎች አንድነታቸውን በማጠናከር በኢትዮጵያ እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በመመከት ለማሸነፍ ማለፍ እንደሚገባቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው የፌዴራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እንደተናገሩት፤ የለውጡ እውን መሆን ሕዝቡን ሲመዘብሩ የነበሩ ቡድኖች ጥቅማቸው መቅረቱን ተከትሎ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ዜጎች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ነው። ከሰሞኑም በነዚህ ቡድኖች ሴራ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በንፁሃን ዜጎች ላይ እጅጉን አሳዛኝ ግድያ የተፈፀመ ሲሆን፤ ተግባሩም እጅጉን የሚያሳዝን ነው፡፡በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ የገጠሟትን ፈተናዎች በልጆቿ የተባበረ ክንድ ማለፏን ያወሱት አፈ-ጉባኤው፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን በማጠናከር የሚገጥሙንን ፈተናዎች መሻገር ይገባናል ብለዋል። የዴሞክራሲ ተቋማትም ለዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር በትኩረት መሥራት ይኖርባቸዋል ብለዋል። ይሄን ኃላፊነታቸውን ለመወጣትም በተለይም የዴሞክራሲ ተቋማት ነፃና ገለልተኝነታቸውን ጠብቀው ለዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን በበኩላቸው፣ የሶማሌ ክልል ከለውጡ በፊት በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በዜጎች ሰቆቃ የሚታወቅ እንደነበር በማስታወስ፤ የለውጡ አመራር በወሰዳቸው ዘርፈ-ብዙ ማሻሻያዎች የክልሉ ችግር ደረጃ በደረጃ እየተፈታ መምጣቱን ተናግረዋል።በመድረኩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪዎችና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የፌደራል የዴሞክራሲ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ሲሆን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአምስት ዓመት ዕቅድ፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ስላላቸው የሥራ ግንኙነት ተቋማቱን ለማጠናከር በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የማሻሻያ ሥራዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38148
961620557992b77d8348dc2e420a5135
16afa0688866b1803cf512890d1cbb51
በወሰን አካባቢ የተከሰተው ግጭት የሁለቱ አገራትን ሕዝቦች እና መንግሥታት አለመሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ እና የሱዳን ወሰን አካባቢ የተከሰተው ግጭት የሁለቱ አገራትን ሕዝቦች እና መንግስታት የማይወክል፤ ይልቁንም በሁለቱ አገራት ሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እና ግጭት እንዲፈጠር ድብቅ አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት ሴራ መሆኑንም ነው የተገለጸው።እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ ክስተቱን አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በአረብኛ ባወጣው መግለጫ የተፈጠረው ችግር የኢትዮጵያም ሆነ የሱዳን መንግስት ፍላጎት አይደለም። እንዲያውም በሁለቱ አገራት ሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እና ግጭት እንዲፈጠር ድብቅ አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት ሴራ መሆኑን መንግስት ይገነዘባል። ይሁን እንጂ ሁለቱ አገራት ችግሩን በጋራ በሠላማዊ ውይይት ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል::ግጭቱ መፈጠሩ አሳዛኝ ቢሆንም በተለይም የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ሕግ የማስከበር ስራውን አጠናቆ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እያከናወነ ባለበት ወቅት እና በተመሳሳይ መልኩ ሱዳን ደግሞ በሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ደፋ ቀና በምትልበት ጊዜ መፈጠሩ የበለጠ አሳዛኝ እንደሚያደርገው የኢትዮጵያ መንግስት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል:: በሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የተከሰተው የፀጥታ ችግርም የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስትን የሚመጥንና የሚወክል አለመሆኑንም መግለጫው አስታውቋል:: ለዘመናት የዘለቀው የሁለቱ አገራት እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በሴረኞች እንደማይሰናከል የገለፀው መግለጫው፣ የሁለቱ አገራት ሕዝቦች ነጻነታቸውን ከማረጋገጥ ባሻገርም፣ ከራሳቸው አልፈው ለአካባቢውም ጭምር ስልጣኔና ቅርስ አበርክቷቸው በጋራ የሚያስተሳስራቸው መሆኑም ተመልክቷል::በፈተናም ጊዜ የሁለቱ አገራት ሕዝቦች ሲተጋገዙ እንደነበር በመግለጽም፣ በአሁኑ ጊዜም ቢሆን በዓለም አቀፍ መድረኮች ጭምር ኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ ጥቅሞቻቸውን በአብሮነት በማስከበር ላይ መሆናቸውንም መግለጫው አስታውሷል፣ይህም ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን አገራቱ ለዘመናት ባዳበሩት አብሮነት ጭምር የተገኘ እሴት መሆኑን ተመልክቷል::በሱዳን በቅርቡ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አብዮት ሕዝቡ በፍላጎት ያደረገው በመሆኑ እንዲሳካም ኢትዮጵያ ከሱዳን ሕዝብ እና መንግስት ጎን በመቆም ሠላም እና መረጋጋት እንዲመጣ ስታግዝ ቆይታለችም ብሏል:: ይህም በሁለቱ አገራት እና ሕዝቦች መካከል ያለውን ወንድማዊ ግንኙነት የሚያሳይ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል::ይሁን እንጂ በቅርቡ አንዳንድ አካላት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግስት በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን አስታውቋል:: ድርጊቱንም ሁለቱ አገራትን የማይወክል እና የተፈጠረውን ችግር በሠላማዊ ውይይት እንደሚፈቱት የኢትዮጵያ መንግስት አቋሙን ገልጿል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38074
dae585d5c89d5daab9339fa0e56ccab5
c1a3934ef128e2c24bafaf397641a09b
ኬንያዊው አትሌት የአስር ዓመቱ ምርጥ ተሰኝቷል
ስፖርት
ባለፉት አስር ዓመታት በአትሌቲክስ ስፖርት ውስጥ በርካታ ክስተቶች ተስተናግደው አልፈዋል። ለቁጥር የሚታክቱ ክብረወሰኖች ከመሻሻላቸውም ባለፈ በሰው ልጅ ሊደፈሩ ይችላሉ በሚል የማይጠበቁና የማይገመቱ ታሪካዊ ክንውኖችም ታይተዋል። ከእነዚህ መካከል በተለይ በስፖርቱ አጭር ርቀት ውድድር (100ሜትር) እና በረጅሙ ርቀት (ማራቶን) የተመዘገቡት ስኬቶች የሰውን ልጅ አቅም በትክክልም ማሳየት የሚያስችሉ ሆነዋል። ታዲያ በአስሩ ዓመታት ከታዩና ክብረወሰንም ካስመዘገቡ አትሌቶች መካከል የተሻለው ማን ነው? በዚህ ጥያቄ ላይ ተንተርሶ ምርጫውን ያካሄደው ደግሞ እአአ በ1940 መሰረቱን በአሜሪካ በማድረግ የተቋቋመውና ትኩረቱን በመምና ሜዳ ተግባራት ስፖርቶች ላይ ያደረገው መጽሄት ነው። መጽሄቱ እአአ ከ2010-2019 ድረስ ባሉት ዓመታት ከጎዳና ላይ ውድድሮች ባሻገር ባሉት ውድድሮች አስር አትሌቶችን በእጩነት በማቅረብ ምርጫውን በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ነበር የጀመረው። በተሰጠው ድምጽ መሰረትም ኬንያዊው የ800 ሜትር አትሌት ዴቪድ ሩዲሽያ ተመራጭ ሊሆን ችሏል። በእጩነት ከቀረቡት አትሌቶች መካከል አንዱ በአጭር ርቀት የአትሌቲክስ ተጽእኖ ማሳደር የቻለው ጃማይካዊ አትሌት ዩሲያን ቦልት ነው። አሁን ራሱን ከተወዳዳሪነት ያገለለው ቁመተ መለሎ አትሌት በ100 ሜትር የሸፈነበት 9ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ የምንጊዜም የርቀቱ ምርጥ አትሌት ያደርገዋል። በውድድር ተሳትፎው ከደረጃ ወርዶ የማያውቀው አትሌት አራት የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ከማጥለቅ ባሻገር የዓለም ቻምፒዮን በመሆንም ክብረወሰኑን አርቆ የሰቀለ አትሌት መሆኑ ምርጫውን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል በሚል ይጠበቅ ነበር። በረጅም ርቀት የመም ላይ ውድድሮች በኢትዮጵያዊያኑ ጀግና አትሌቶች እግር የተተካው እንግሊዛዊ አትሌት ሞሃመድ ፋራም በእጩነት ከቀረቡት መካከል ነበር። የዓለም ቻምፒዮናው በኦሊምፒክ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያሳካ ሲሆን፤ በ5ሺ እና 10ሺ ርቀቶች ሃገሩን በተደጋጋሚ ለማስጠራት ችሏል። አትሌቱ ምንም እንኳን ከመም ወደ ጎዳና ላይ ውድድሮች ባደረገው ሽግግር እንደሚጠበቀው ውጤታማ ባይሆንም ያለፉት አስር ዓመታት ግን ለእርሱ አስደሳች ነበሩ። ከመም ይልቅ በማራቶን ስሙ የገነነውና የዚህ ወቅት የርቀቱ ቁጥር አንድ አትሌት የሆነው ኬንያዊ ኢሉድ ኪፕቾጌም ቀዳሚ ተመራጭ ይሆናል በሚል ከሚጠበቁት እጩዎች መካከል ነበር። የዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ እንዲሁም ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች የመግባት ሙከራውን ያሳካው አትሌት በሮጠበት ጫማ ምክንያት ውዝግቦችን ያስተናግድ እንጂ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ንጉስነቱን ማንም ሊቀማው እንደማይችል ነው አዘጋ ጆቹ ያረጋገጡት። አሜሪካዊያኑ ክርስ ቲያን ቴይለርና አሽተን ኢትን፣ ደቡብ አፍሪካዊው ዋይዴ ቫን ኔኬርክ፣ ፈረንሳ ዊው ሬናውድ ላቪሌኔ፣ የኳታሩ ሙታዝ ባርሺም እንዲሁም ጀርመናዊው ሮበርት ሃርቲንግም ከአስሩ እጩዎች መካከል ይገኙበታል። ከእጩዎቹ መካከል በተለይ ‹‹የዓለም ፈጣኑ ሰው›› በሚል የሚታወቀው ጃማይካዊ አትሌት አብላጫውን ድምጽ ያገኛል የሚል ግምት ያግኝ እንጂ አሸናፊ የሆነው ግን ዴቪድ ሩዲሽያ ነው። የለንደንና ሪዮ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ እንዲሁም የዴጉና ቤጂንግ የዓለም ቻምፒዮናው አትሌት፣ በተለይ እአአ በ2012ቱ የለንደን ኦሊምፒክ ርቀቱን ያጠናቀቀበት ሁኔታ በአስር ዓመታት ከማይዘነጉ ትዝታዎች መካከል ቀዳሚው በሚል በዓለም አትሌቲክስ መመረጡ የሚታወስ ነው። አትሌቱን አስደናቂ ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል አንዱ፣ በርቀቱ የዓለም ክብረወሰንን ለሶስት ጊዜያት(1:41.09፣ 1:41.01፣ 1:40.91) መስበር መቻሉ ነው። መጽሄቱ መሰል ምርጫዎችን ማካሄድ የጀመረው እአአ በ1960ዎቹ ሲሆን፣ የመጀመሪያው አሸናፊም ኒውዝላንዳዊው ፒተር ስኔል ነበር። እአአ የ1970ዎቹን ክብር ደግሞ የሶቬት ህብረት አትሌት የሆነው ቪክቶር ሳኔይቭ ነበር የወሰደው። በ1980ዎቹ አሜሪካዊው ካርል ሉዊስ ምርጥ ሲሰኝ፤ የ90ዎቹንም ሌላኛው የሃገሩ ልጅ ሚካኤል ጆሃንሰን አሸናፊ ሆኗል። እአአ ከ2000-2009 ባሉት ዓመታት ምርጥ አትሌትነት ምርጫ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን፤ አንበሳው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቀዳሚ ሊሆን ችሏል። አዲስ ዘመን የካቲት 2/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27019
a8e0d49ce1faf5c1b27bfebb6e57bd5e
669b9a91b7de863580488379877838b8
በዜጎች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ ይወስዳል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በዜጎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ጥቃት እየፈፀሙ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። የብሔራዊ የሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ብሔራዊ ምክር ቤት የ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በዜጎች ላይ የተፈፀመው ድርጊት ጭካኔ የተሞላበት የወንጀለኞች ተግባር መሆኑን የገለፁ ሲሆን፤ በዜጎች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድም ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያዊያን የሚጋሩትና የወረሱት የዳበረ እሴት ባለቤቶች መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ደመቀ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አንዳንዶች በዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እየፈፀሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይሄ ችግር ወደ የት እያመራ እንደሆነ ሁሉም ቆም ብሎ ሊያስብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ዜጎችን እየጨፈጨፉ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን የገለፁት አቶ ደመቀ፤ ለዚህም የተለያዩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ድርጊቱን ለማስቆምና ወንጀለኞችን ለማደን የሁሉም ጥረትና ትብብር የሚያስፈልግ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ዜጎችን ለነዋይ ብሎ መደለል፣ ድንበር አሻግሮ ለወንጀለኞች አሳልፎ በመስጠትና ለከፋ ችግር የማጋለጥ ተግባሩ መቀጠሉን በመጠቆምም፤ ለዚህ ችግር ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ቢኖሩም ወንጀሉን ለመከላከልና ለማስቆም አሁንም የሁሉም ጥረትና ትብብር ያስፈልጋል በማለት ጥሪ ማስተላለፋቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡በተያያዘ ዜና፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር እና ችግሩን ለመቅረፍ ምቹ የሆነች ሀገርን የመፍጠር ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ በዚሁ መድረክ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መናገራቸውን ፋና ቢሲ ዘግቧል፡፡በዘገባው እንደተመላከተው፤ የመድረኩ አላማ በሕገወጥ መንገድ ለስደት የሚዳረጉ ዜጎችን ለመቆጣጠር እና ለችግር እንዳይጋለጡ ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እና ያለፉትንም መገምገም ሲሆን፤ በዚህም በ2012 እና 2013 ዓ.ም በሕገወጥ መንገድ ከሚሰደዱት በተሻለ የተመላሾች ቁጥር ከፍ ያለበት እንደነበር በመድረኩ ተነስቷል።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን በቀጣይ ዜጎችን ከሕገ ወጥ ስደት ለመታደግ በሚደረገው ጥረት አገርን ለመኖር ምቹ ማድረግ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩትን ሥጋቶች ማስወገድ እንደሚያስፈልግ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን፤ ለዚህም መንግሥት የሰላም የማረጋገጥ ሥራ ላይ አተኩሮ እየሠራ እንደሚገኝ አቶ ደመቀ ተናግረዋል።በመድረኩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ፣ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38149
d549feb9b9916dbb92c4c4335ec7f47e
cbe93c7208ee5934e55316e0def8fc86
“ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚናገሩት እና የሚተገብሩት አንድ ሊሆን ይገባል” ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር
ሀገር አቀፍ ዜና
ሙሉቀን ታደገ አዲስ አበባ፡- ቀጣዩን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ለማድረግ ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚናገሩት እና በተጨባጭ የሚተገብሩት አንድ አይነት ሊሆን ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናገሩ፡፡ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ባለው ሁኔታ ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚናገሩት እና በተጨባጭ የሚተገብሩት ለየቅል ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ ደግሞ አንዳንድ ፓርቲዎች ሲመቻቸው የሃይል አማራጭን በሌላ ጊዜ ደግሞ ሰላማዊ መስለው እንዲታዩ አድርጓቸዋል፡፡በመሆኑም ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ሕጉን እና የሥነ ምግባር ደንቡን አክብሮ መንቀሳቀስ ይገባቸዋል፡፡ በዚህም ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ጊዜ እና በደህረ ምርጫ በሀገሪቱ ማንኛውም አይነት ግጭት እንዳይከሰት ከማድረግ አንፃር ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የራሳቸውን ሚና መጫወት ይገባቸዋል፡፡ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳባቸውን በመሸጥ ህዝቡን አሳምነውእንዲመረጡ ለማድረግ በምርጫ ሕጉ እና በምርጫ ሥነ ምግባሩ መሰረት ሊንቀሳቀሱ ይገባል የሚሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ በዚህም ቀጣዩን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ማድርግ እንደሚቻል ጠቁመዋል።እንደ ፕሮፌሰር በየነ ገለፃ፤ ሰላማዊ ፖለቲካ የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀገሪቱን ሰላም የሚያናጋ እንቅስቃሴ ውስጥ አይገቡም። ምክንያቱም ሰላማዊ ፖለቲካ የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ሕጉ እና የምርጫ ሥነ ምግባር ደንቡን አክብረው የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ካለፉት ዓመታት የምርጫ ልምዶቻችን መገንዘብ እንደቻልነው የምርጫ ሂደትን የሚያደፈርሱ እንቅስቃሴዎች ብዙ ጊዜ በዋነኛነት የሚስተዋለው ከገዢው ፓርቲ ከሚፈፀሙ ያልተገቡ ተፅዕኖዎች እና የምርጫ ህጉን እና የስነ ምግባር ደንቡን ባልተከተሉ የመንግሥት አካላት መሆኑን የገለፁት ፕሮፌሰር በየነ፤ አሁንም በቀጣይ ለሚደረገው ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማድረግ በቀበሌ እና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ የገዢው መንግሥት ባለስልጣናት የምርጫ ህጉን እና የስነ ምግባር ደንቡን ማክበር እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል። እንደ ፕሮፌሰር በየነ ገለፃ፤ ምርጫ የሚካሄደው ከፌዴራልና ከክልል ባሻገር በቀበሌ እና በወረዳ ደረጃ ስለሆነ በቀበሌ እና በወረዳ ደረጃ ያሉ የገዢው ፓርቲ አባላት እና የመንግሥት የፖለቲካ ሥራ የሚሠሩ አካላት ከቀድሞው ከኢህአዴጋዊ መንፈስ የፀዱ ሊሆኑ ይገባል። ይህን በቀበሌ እና በወረዳ ደረጃ ያሉ ከኢህአዴጋዊ እንቅስቃሴ ያልተላቀቁ የገዢው መንግሥት የፖለቲካ ሹመኞች በምርጫ ህጉ እንዲገዙ ለማድረግ እስከ ምርጫ ባለው ጊዜ ድረስ የብልፅግና ፓርቲ ማስተካከያ ያደርጋል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልፀዋል።የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም እንደ አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ ደጋፊዎቹን እና ተከታዮቹን የምርጫ ሕጉን እና የሥነ ምግባር ደንቡን ተከትለው እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ፓርቲው እየሠራ እንደሚገኝ ፕሮፌሰር በየነ አመላክተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38146
24d5352ca71ea9f354c078442da43726
c57e934ef455f0c5e11129f3ed91d9ef
የስፖርት ለሁሉምና የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ፌስቲቫል
ስፖርት
የማህበረሰብ ስፖርትን «ሁሉም ሰው በስፖርት እንቅስቃሴ እንደ ፍላጎቱና ችሎታው አቅሙ በፈቀደ መጠን መሳተፍ የሚችልበት መድረክ ነው» ሲሉ የስፖርት አዋቂዎች ይገልጹታል። የተሳትፎው ሁኔታ እንደ ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ መርህ የስፖርት መርሃ ግብር ዓላማ፤ ሰዎች በተወዳዳሪነት ለአሸናፊነት ክብር እንዲበቁ የሚያደርግ አለመሆኑንም ያስቀምጣሉ። ከዚህ ይልቅ ሰዎች በስፖርቱ እንዲዝናኑ፣ ጤንነታቸውን እንዲጠብቁ፣ አካላቸው ለእለት ተዕለት ተግባራት ዝግጁ እንዲሆን፣ በሰዎች መካከል መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር የሚያደርግ መንፈስ እንደሆነ ብያኔ ይሰጣል። በ1990 ዓ.ም በማህበራችን ተግባራዊ የተደረገው የስፖርት ፖሊሲም ይህንኑ በመደገፍ ሕዝቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባውም አስቀምጧል።ስፖርት ለሁሉ ደግሞ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግና የውድድር አጋጣሚዎችን ቀርጾ ተግባራዊ በማድረጉ አንዱና ዋነኛው አማራጭ እንደሆነ ይታመናል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው የስፖርት ለሁሉም የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ፌስቲቫልም ይሄንኑ መሰረት በማድረግ ከሚከናወኑ የስፖርት ሁነቶች መካከል አንዱ ነው። በፌደራል መስሪያ ቤቶች መካከል በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች የሚሳተፉበት የስፖርት ለሁሉምና የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ፌስቲቫል ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በልዩ ድምቀት የተጀመረው ፌስቲቫሉ፤ ዘንድሮ በተለየ መልኩ ዝግጅት የተደረገበትና በርካታ ቁጥር ያላቸው የፌደራል መስሪያ ቤቶች የተሳተፉበት መሆኑ ተነግሯል ። “ስፖርት ለጤንነት፣ ለወዳጅንት፣ ለሠላም፣ ለአንድነትና ለብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ፤ ስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል አካላዊና አእምሯዊ ጤንነትን ከመገንባት ባለፈ የጋራ ዓላማ ያለው ኅብረተሰብ ለመገንባት እንደሚረዳ በመክፈቻው ላይ ተናግረዋል። የብሔራዊ ስፖርት ፖሊሲው የትኩረት አቅጣጫም ኅብረተሰቡን በሚኖርበት፣ በሚሰራበትና በሚዝናናበት አካባቢ እንደ ችሎታውና ፍላጎቱ በግልና በቡድን ተሳታፊ ማድረግ ስለሆነ የስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል ይህን ዓላማ ይዞ በየዓመቱ እንደሚከናወንም አመልክተዋል።የስፖርት ፌስቲቫሉ የተዘጋጀው በኦሊምፒክ መርህ መሰረት ህብረተሰቡ በሚማርበት፣ በሚሰራበትና በሚኖርበት አካባቢ በስፖርት እንቅስቃሴ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ እንደሆነም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል። በሌላ በኩል በመንግስት ተቋማት የሚገኙ ሠራተኞች በሚሰሩበት ቦታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የማድረግ ግንዛቤ፣ ፍላጎትና መነሳሳት እንዲኖራቸው ያደርጋልም ተብሏል።በተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች ሠራተኞች መካከል በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች የሚደረገው ውድድር እስከ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን፤ በየስፖርት ዓይነቱ የበላይነትን ይዘው ያጠናቀቁ መስሪያ ቤቶች በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት ሀገር አቀፍ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ። 1ኛው ሀገር አቀፍ የሰራተኞች ስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት ከሰኔ 05 -14/2012 ዓ.ም በባቱ ከተማ ይካሄዳልም ተብሏል።አዲስ ዘመን የካቲት 2/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=27020
6393a71abe633aaf31af60c20039247e
206c97d4656a506cfc55d25c16194439
ከተሞች ለቅርጫት ኳስ ያላቸውን ግምት ትዝብት ላይ የጣሉበት ውድድር
ስፖርት
የቅርጫት ኳስ ስፖርት በዓለማችን ላይ ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርቶች መካከል በቀዳሚነት ይቀመጣል። በአገራችንም ቢሆን የቅርጫት ኳስ ስፖርት ጥሩ እንቅስቃሴ የሚደረግበትና በተለይም በከተሞችና ትምህርት ቤቶች አካባቢ በወጣቶች እጅግ ተወዳጅ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ስፖርቱን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲካሄድ ማድረጉ አንዱ ትልቅ እርምጃ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን ስፖርቱ ሰፊ መሰረት ያለው በከተሞች አካባቢ እንደመሆኑ ከሰባት ዓመት በፊት የከተሞች የቅርጫት ኳስ ውድድርን በየዓመቱ በማካሄድ አበረታች እርምጃ ወስዷል። ፌዴሬሽኑ ዘንድሮም የከተሞችን የቅርጫት ኳስ ውድድር ከኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር በቢሾፍቱ ከተማ እንዲካሄድ አድርጓል። ለአምስት ተከታታይ ቀናት ተካሂዶ ባለፈው አርብ በተጠናቀቀው የከተሞች የቅርጫት ኳስ ውድድር በወንዶች መካከል በሚደረገው ፉክክር አዘጋጁ ቢሾፍቱ ከተማን ጨምሮ አዳማ፣ድሬዳዋ፣ሐረሪ፣ቡታጅራ ከተሞች እንዲሁም የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተሳታፊ ሆነውበታል። በሴቶች መካከል በሚደረገው ፉክክር ግን ባልተጠበቀ መልኩ አሰላ ከተማና የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ብቻ ተሳታፊ ሆነዋል። ከመሐል አገር ራቅ ያሉ ከተሞች በውድድሩ ለመሳተፍ ያሳዩትን ተነሳሽነት ያህል በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች በፉክክሩ ላይ መገኘት አለመቻላቸው ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ መሆኑ የአገራችን ከተሞች ለስፖርቱ እየሰጡት ያለውን ትኩረት ትዝብት ላይ የጣለ ነው። አንዳንድ ከተሞች በውድድሩ መሳተፍ ያልቻሉት የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው የቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው ሲሆን ራቅ ያሉት ከተሞች በአገራችን ከሚታየው የፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ ምክኒያት እንደሆነ የፌዴሬሽኑ የስራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ ይመር ሃይሌ ለአዲስ ዘመን ገልፀዋል።በዚህ ውድድር አግራሞትን ካጫሩት ሁነቶች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አፍንጫው ስር በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ በሚካሄድ ውድድር በወንዶችም በሴቶችም መሳተፍ አለመቻሉ ነው። ከተማውን በሁለቱም ፆታ ወክለው ለመወዳደር ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩት ወጣቶች ከበጀት እጥረት ጋር በተያያዘ መጨረሻ ሰዓት ላይ መሳተፍ እንዳልቻሉ ከተለያዩ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አዲስ አበባ በየወረዳው እንኳ መሳተፍ የሚያስችል እምቅና ሀይል ያለው መሆኑ ይታወቃል። በየትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ያለውን የአዲስ አበባ የወጣቶች ቅርጫት ኳስ ፍቅርና አቅምን አሰባስቦ አለመሳተፉ አሳፋሪ ነው። በአገራችን ከሚገኙ ከተሞች ሁሉ በአፍሪካ ደረጃ ለሚካሄዱ ውድድሮች ጠንካራ ቡድን መገንባት የሚያስችል የቅርጫት ኳስ ፍቅር፣ ጉልበት፣ የፋይናንስና የተጫዋቾች አቅም ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ነገር ግን በዚህ የወጣቶችን ችሎታ፣ አቅምና ጉልበት ለማወቅና ጠንካራ ቡድንን ለመገንባት የሚረዳ የከተሞች ውድድር ላይ አዲስ አበባ ለማሸነፍ ወይም ለመወዳደር ለምን እንዳልቻለ፣ ወይም እንዳልፈለገ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶት ማስተካከል መቻል እንዳለበት የብዙዎች እምነት ነው።አዲስ አበባ የአፍሪካና የኢትዮጵያ መዲና ናት። ወጣቶች፣ ታዳጊዎችና ህጻናት በስፖርት እንዲሳተፉ እድል በመስጠት በስነልቦናና በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ መገንባት፣ በአገር ደረጃ ትውልድን ከሱስና አልባሌ ስፍራ ማራቅ ብቻም ሳይሆን ከተሞቻችንንና ትውልድን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል ግዴታ እንጂ ውዴታ አይደለም። አዲስ አበባ በበጀት እጥረት በውድድሩ አለመሳተፉ የማይመስል ነገር ነው። የከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን የቅርጫት ኳስ ውድድሩ ከተጠናቀቀ አንድ ቀን በኋላ እዚያው ቢሾፍቱ ላይ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ የስፖርት ማህበራት አመራሮችን ለሁለት ቀን ሰብስቦ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሲሰጥ ነበር። በዚህ ስልጠና ላይ ሰላሳ አምስት ከሚጠጉ የስፖርት ማህበራት የተውጣጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል። ለዚህም የሁለት ቀን ስልጠና ከተማ አስተዳደሩ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ማድረጉ አይቀሬ ነው። ጥያቄው ከተማ አስተዳደሩ በስሩ የሚገኙ የስፖርት ማህበራት አመራሮችን አያሰልጥን ሳይሆን ቅድሚያ ለየትኛው መስጠት አለበት ይሆናል። በቅርጫት ኳስ ውድድሩ በሁለቱም ፆታ ለመሳተፍ ቢበዛ ሃያ የሚሆን ተጫዋችና የልዑካን ቡድን ነው የሚያስፈልገው። የበጀት እጥረት ቢኖር እንኳን ውድድሩ በቅርብ ርቀት እንደመካሄዱ ተጫዋቾች እየተመላለሱ እንዲሳተፉ ማድረግ ቀላሉ አማራጭ ነበር። የከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ በአመራሮቹ ስልጠና ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ‹‹ የአዲስ አበባን የስፖርት ማዕከልነት መልሰን እንገነባለን›› ሲሉ ተደምጠዋል። የከተማዋን የስፖርት ማዕከልነትና ገፅታ መገንባት ከተማዋ በስፖርቱ ያላትን ትልቅ አቅም አውጥታ በማሳየት እንደ ቅርጫት ኳስ ውድድሩ ባሉ አገር አቀፍ መድረኮች ተሳታፊ በመሆንና ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ በመስጠት እንደሚጀምር ሌሎቹም ቢሆኑ ሊማሩበት ይገባል። አዲስ ዘመን የካቲት 3/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=27070
67136c2f714c453eb600fc0899b09297
03113203decaadfcc71b27a06362f673
ስፖርቱን ለማሻገር ተስፋ የተጣለበት ስትራቴጂክ እቅድ
ስፖርት
የስፖርት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው በእጅጉ እየጨመረ እንደመጣ ይታወቃል። የዓለም አገራት የስፖርት ሴክተሩን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመረዳት ብቻ የሚቆሙ እንዳልሆኑ በዘርፉ ያስመዘገቡት ውጤት ማሳያ ነው። በዓለማችን በበርካታ አገራት ከሌሎች ሴክተሮች ባልተናነሰ መልኩ ለስፖርት ልማቱ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይን በማፍሰስ ስማቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ከማድረግ አልፈው ብዙ ማትረፍ ችለዋል፡፡ ለስፖርት ሴክተሩ ትልቅ ትኩረት መስጠት በማህበራዊ ፋይዳው አምራችና ጤናማ ዜጋን በማፍራት ረገድ ያለውን ውጤት ከመረዳት ይመነጫል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ትላልቅ ውድድሮች በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ከሚገኘው ድል ጀርባ ለአገር ፖለቲካዊ ትርፍ ማጣጣም ማስቻሉንም መታዘብ ይቻላል፡፡ ስፖርተኞች ከውድድር ድል በኋላ የሚያገኙት ረብጣ የሽልማት ገንዘብና የአገር ኢኮኖሚን በማንቀሳቀስ የሚገኘው ትርፍም ቀላል አይደለም፡፡ የስፖርቱን ዘርፈ ብዙ ፋይዳን በጥልቅ በመረዳት የስኬት ማማ ላይ የወጡ እንደ ጀርመን ያሉ አገራትን ማንሳት ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስፖርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ረገድ ጀርመን በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ናት። ይህች አገር ስፖርቱ በጠንካራ የፋይናንስ መሠረት ላይ ማቆም መቻሏ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መሠረቱን ሳይለቅ መጓዝ የቻለ አደረጃጀት መፍጠሯ ለስኬቷ ምክንያት ተደርጎ ይነሳል፡፡ የጀርመን መንግሥት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ከሚያፈስባቸው ዘርፎች ዋነኛው ስፖርት ሊሆን የቻለውም ለዚህ ነው፡፡ ስፖርት በጀርመን ኢኮኖሚ ውስጥ 2 ነጥብ 2 በመቶ ድርሻ ይይዛል። ስፖርቱን በፋይናንስ አቅም እንዲጎለብት ከማድረግ በተጓዳኝ፤ ጠንካራ አደረጃጀት የተዘረጋለት ነው። በጀርመን የስፖርት ዘርፍ ይህን መልክ መላበሱ ከዘርፉ የሚገኘው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ እንዲጎላ ማድረጉ ይነሳል። በኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ የተሰጠውን ትኩረትና ውጤት ከሌሎች አገራት አንጻር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በቀደሙት ጥቂት ዓመታት ለስፖርቱ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች፣ ከመንግሥትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በኩል ኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ ተገቢ ትኩረት መስጠቷ ይነገራል፡፡ ለስፖርት ዘርፍ በተገቢው ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ አለመሆኑንና የዘርፉ እድገት በቁልቁለት ጉዞ ውስጥ መሆኑም በሌላ ወገን ይነሳል። የስፖርት ሴክተሩ ውጤት አልባ መሆኑ ግን ሁለቱንም ወገኖች እንደሚያስማማ ለመታዘብ ይቻላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በመንግሥት ደረጃ ይኸው እውነታ ታምኖበት እየተሰራ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ እየተነገረ ይገኛል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንድሪስ አብዱ፤ በአገሪቱ ባለፉት ሁለት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመናት ዘርፉ ለአገሪቱ ማበርከት ካለበት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታዎች አንፃር በሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመገኘቱና ውጤቱም በመላ አገሪቱ ተደራሽነት ላይ ክፍተቶች መኖራቸው እንደታመነበት ይናገራሉ:: ለዚህም የስፖርት ሴክተሩን መሠረታዊ ችግር በተረዳ መልኩ የ10 ዓመት የስፖርት ሴክተር ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን በኮሚሽኑ በኩል እንቅስቃሴ ከተጀመረ መሰንበቱን ያስረዳሉ፡፡ ስፖርቱን ወደፊት ለማራመድ እንቅፋት ከሆኑ መሠረታዊ ምክንያቶች መካከል በዋነኛነት ከአደረ ጃጀት፣ ከፋይናንስ፣ ከሰው ኃይል ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች መሆናቸውን የጠቆሙት የኮሚሽኑ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ እንየው አሊ፤ የ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድ የተጠቀሱትን ክፍተቶች በጥናት እንዲመልስ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ያስቀምጣሉ፡፡ ስትራቴጂክ ዕቅዱ አገራዊ የስፖርት ሪፎርምን መነሻ በማድረግ በስፋት የተዘጋጀ መሆኑንም ይገልፃሉ። በመሆኑም በአገሪቷ ቀጣይ የስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ለውጥና ውጤት ማምጣት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡ የስፖርት ሴክተሩ ሪፎርም ፕሮግራም ዘርፍን መለወጥ የሚችሉ ብዙ ያመላከታቸው ነጥቦች እንዳሉም ያስረዳሉ። በዚህም ከአደረጃጀት ፣ ከፋይናንስ፣ ከሰው ኃይልና ሌሎችም ጉዳዮች አንፃር ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚቻል ተስፋ የተጣለበት መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ በሪፎርሙ ላይ የሴክተሩ ችግሮች የተለዩ ሲሆን በተመሳሳይ መፍትሄዎች መመላከታቸውንም ያክላሉ። ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገውና ከስፖርት ሪፎርሙ የሚቀዳው የ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድ ዘርፍን የተሻለ እንደሚያደርገውም ያላቸውን እምነት ይገልፃሉ፡፡ አቶ እንድሪስ በበኩላቸው፤ በቀጣይ ዓመት ተግባራዊ የሚደረገው ስትራቴጂክ ዕቅድ ትኩረት ያደረጋቸው አንኳር ጉዳዮች መኖራቸውን በመጥቀስ በሴክተሩ በቀጣይ 10 ዓመታት በትኩረት የሚሰራባቸው ተብለው የቀረቡት ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች እንዳሉ ይናገራሉ:: በመጀመሪያ መንግሥታዊ የስፖርት አደረጃጀቶችን የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም በማጎልበት፤ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን እና የአሠራር ሥርዓቶችን ተግባር ላይ ማዋል ፤ ሕዝባዊ የስፖርት አደረጃጀቶችን በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ መስፈርቶች መሠረት ማደራጀት የስትራቴጂክ እቅዱ ትኩረት መሆናቸውን ያስቀምጣሉ:: በሁለተኛ ደረጃ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የማሰልጠኛ ማዕከላት ተደራሽነት፣ ሕጋዊነት እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን መሠረት በማድረግ በጥራት የሚገነቡበትን ስልት ሥራ ላይ ማዋል ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ያስረዳሉ። በአህጉር እና ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች በተፈጥሮ ብቃታቸውን መሠረት በማድረግ አገራችንን የሚወክሉ እና ውጤታማ የሆኑ ተተኪ ስፖርተኞችን በሳይንሳዊ ስልጠናዎች ማፍራት ትኩረት ተደርጎ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑንም ያብራራሉ፡፡ ስፖርት ለማህበራዊ ልማትና ለአገር ብልፅግና ፣ ለሕዝቦች መቀራረብ ፣ ለገፅታ ግንባታ እና ለቱሪዝም ዕድገት መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ትኩረት ሰጥቶ መስራትም የስትራቴጂክ እቅዱ ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው። በስትራቴጂክ ዕቅዱ የተጠቀሱትን አንኳር ጉዳዮች መሠረት አድርጎ የተዘጋጀው ግብ ወደ ተግባር መቀየር ከተቻለም የስፖርት ሴክተሩ ውጤታማ መሆን እንደሚችል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፤ በአገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲ ባለፉት ሁለት አስር ዓመታት የተመዘገቡ በርካታ አበረታች ውጤቶች ቢኖሩም የአገራችን የስፖርት ዕድገት ከዕድሜው አኳያ ሲመዘን በሚፈለገው ደረጃ ባለማደጉ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ያመላክታሉ። በአሁኑ ወቅት መንግሥት ስፖርቱን እንደ አንድ የልማትና ብልፅግና መሣሪያ አድርጎ በመውሰድ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየሰራ እንደሚገኝ የሚናገሩት አቶ ሃብታሙ ፤ የስፖርት ዘርፍ በታሪኩ በዚህ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እንደማያውቅ ያብራራሉ:: የብሔራዊ የስፖርት ምክር ቤት በኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሰብሳቢነትና የበላይ ጠባቂነት መመራቱ መንግሥት ለስፖርቱ ሴክተር የሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳይም ያስቀምጣሉ፡፡ በመሆኑም የስፖርት ዘርፍን ከትናንት በተሻለ መልኩ ዛሬ ትኩረት በማግኘቱ ዕድሉን በአግባቡ በመጠቀም ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን አርብ ጥር 22/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=26437
cbbf8647719ec7339913803274b05b60
3a8f26005617a2af28416a8466fa1786
የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ
ስፖርት
የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በቻይና የሚካሄደውን የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ማራዘሙን አስታወቀ። እአአ ከመጋቢት 13 እስከ 15 ቀን 2020 በቻይና ናጂንግ ከተማ ሊካሄድ የነበረው 18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክውድድር ለ12 ወራት ያህል እንዲራዘም መደረጉን የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ዋቤ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል። የዓለም አትሌቲክስ የጤና ቡድን ከዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ጋር በቻይናና ከቻይና ውጪ በሌሎች አገራት የኮሮኖ ቫይረስን አስመልክቶ በቅርበት መረጃዎችን በመለዋወጥ ባገኘው መረጃ ኮሮና ቫይረስ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ለመረዳት መቻሉን ዘገባው አመልክቷል። በቻይና መነሻውን ያደረገው ኮሮና ቫይረስ 130 ሰዎችን የገደለ ሲሆን፤ በ16 ሀገራት ተስፋፍቷል። ከስድስት ሺህ ሰዎች በላይም በቫይረሱ መጠቃታቸውን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በመነሳት የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቻይና በተስፋፋው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ውድድሩን በተባለለት ጊዜ ማካሄድ አስቸጋሪ መሆኑን በማመን ውድድሩ እንዲራዘም ውሳኔ አሳልፏል። በመሆኑም እ.አ.አ በ2021 ውድድሩ እንዲካሄድ አማራጭ መቅረቡን አስታውቋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድሩን በሌሎች አገራት ለማድረግ አስቦ እንደነበር ያስታወቀው ፌዴሬሽኑ ቫይረሱ ከቻይና ውጪ ወደ ሌሎች አገራት የመሰራጨቱ ጉዳይ አሳሳቢ ስለሚሆን አገር የመቀየር ምርጫውን መሰረዙን አመልክቷል። ብዙ አትሌቶች ውድድሩ እንዲካሄድ ካላቸው ፍላጎት አንጻርም የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድሩን ሙሉ ለመሉ የመሰረዝ ምርጫውንም እንደተወውም ነው ተጠቀሰው። ይህ በመሆኑ ምክንያት ናንጂንግ እ.አ.አ በ2021 ውድድሩን የሚካሄድበት ምቹ ጊዜ ማግኘት እንደምትችል የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል። የዓለም አትሌቲክስ ከአትሌቶች፣ ከናንጂንግ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴና ከአጋሮች ጋር የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር እ.አ.አ 2021 የሚካሄድበት ቀን ለመወሰን በቅርበት እንደሚሰራም አስታውቋል። የዓለም አትሌቲክስ ቻይና የኮሮኖ ቫይረስን ለመከላከል እያደረገች ያለችውን ጥረት እየተከታተለ እንደሆነና ተቋሙ አገሪቷ እያከናወነች ላለው ሥራ ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል መግባቱንም አስፍሯል። ቫይረሱን አስመልክቶ ለአትሌቶች፣ ለብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖችና አጋሮች በፍጥነት እየተለዋወጡ ያሉ ጉዳዮችን ማሳወቅ ተገቢ እንደሆነም ማመልክቱን ቢቢሲ ዘግቧል። የእስያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በየካቲት ወር 2012 ዓ.ም በቻይና ሀንግዙ ግዛት ሊካሄድ የነበረውን ዘጠነኛው የእስያ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር መሰረዙን ከአራት ቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።አዲስ ዘመን አርብ ጥር 22/2012ዳነኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=26439
01bbbf1b016028279ffc7126fd76bc19
763e69a1ce3e1e4de76f19ef0274486d
በደቡብ ክልል በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ተሳትፎ ያደረጉ 711 አመራሮች ከኃላፊነት ተነሱ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በደቡብ ክልል ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ተሳትፎ ያደረጉ 711 አመራሮች ከኃላፊነት መነሳታቸውን የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሰናይት ሰለሞን አስታወቁ። ኃላፊዋ በክልሉ የተካሄደውን የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫው ወቅትም፣ በክልሉ በጉራፈርዳ፣ በወላይታ፣ በኮንሶ ዞን እና በዙሪያው ባሉ ልዩ ወረዳዎች የአደረጃጀት እና የወሰን ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ የሕዝቡን ጥያቄዎች በኃይል ማስፈጸም ይቻላል በማለት የህወሓት ጁንታ ለግጭት አመቺ የሆኑ ቦታዎችን በመጠቀም ህብረተሰቡ ያልተገባ ዋጋ እንዲከፍል ማድረጉን ተናግረዋል።በብዝሀነቱ የሚታወቅና ለሌሎች አካባቢዎችም ተምሳሌት የሆነውን የደቡብ ክልል ጽንፈኛው የህወሓት ጁንታ ኃይል ለእኩይ አላማ ሲጠቀምበት እንደነበርም በዝርዝር መገምገሙን የገለጹት ወይዘሮ ሰናይት፤ ጽንፈኛው ቡድን ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችንበመጠቀም ሀብት በመመደብ ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም አብራርተዋል።በዚህ ምክንያት በተፈጠረው ችግር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው መኖሩ የተረጋገጠ 711 አመራሮች ከኃላፊነት መነሳታቸውን በመጠቆምም፤ 918 የሚሆኑት ደግሞ ከቦታቸው እንዲሸጋሸጉ መደረጉን ተናግረዋል። በተጨማሪም 1 ሺህ 966 አመራሮች በማስጠንቀቂያ መታለፋቸውን መግለጻቸውን ነው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት የክልሉን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጠቅሶ የዘገበው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37996
d52d0a34a16f53fb4256930824745cd0
759a58c777b87995516473b2befd836b
ፎረሙ፣ የሕንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
በኃይሉ አበራአዲስ አበባ፡- የሕንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባሉ ሰፊ የኢንቨስትመንት ዘርፍ አማራጮች እንዲሰማሩ የማማከርና የግንዛቤ ድጋፍና እንደሚያደርግ በኢትዮጵያ የሕንድ ኢንቨስተሮች ፎረም አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከትናንት በስቲያ በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ሕግ ዙሪያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የሕንድ ባለሃብቶች ገለጻ አድርጓል።በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ የሕንድ ኢንቨስተሮች ፎረም ሊቀመንበር ማዮር ኮታሪ እንደገለጹት፤ ፎረሙ የህንድ ባለሀብቶችን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ነው። ኢትዮጵያ ያፀደቀችው አዲሱ የኢንቨስትመንት ዓዋጅ ደግሞ በተለይ ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ ዘርፎችን ክፍት በማድረጉ ባለሀብቶችን ያበረታታል። በመሆኑም የሕንድ ባለሃብቶች ይሄን እድል ተጠቅመው በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ፎረሙ ድጋፍ ያደርጋል።የሕንድ ባለሀብቶችና በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በእርሻ፣ በቱሪዝም፣ በትምህርትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በኬሚካል፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ በመድኃኒት መስኮች ተሰማርተው እየሰሩ መሆኑን ያስታወቁት ሊቀመንበሩ፤ ፎረሙ ከሕንድ የሚመጡ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ጥረት እንደሚያደርግም ገልጸዋል። እንደ ሊቀመንበሩ ገለጻ፤ የህንድ ቢዝነስ ፎረም ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የማበረታታት እና የማማከር ስራ እየሰራ ይገኛል። ከውጭ ሀገር የሚመጡ ኢንቨስተሮች ወደ ኤምባሲ ሲሄዱ ኤምባሲው የህንድ ኢንቨስትመንት ፎረም የማማከር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚልክበት የትስስር አሰራርም አለው። በመሆኑም በፎረሙ አማካኝነት ያሉትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ከፎረሙ ጋር በመወያየት አዋጭ በሆነው የኢንቨስትመንት ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እያዘጋጀ በሚገኘው ዓይነት ሴሚናሮችም ከመንግስት አካላት ጋር ውይይት የሚያስፈልግ ከሆነ በኤምባሲው በኩል የምክክር መድረክ በማዘጋጀት ፎረሙ የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ የገለጹት ሊቀመንበሩ፤ ይሄን አይነት አሰራር መኖሩ ደግሞ በርካታ ችግሮችን ተወያይቶ ለመፍታትም ሆነ በውጭ ያሉ ባለሃብቶች ግንዛቤ ፈጥረው ወደኢትዮጵያ እንዲመጡ እድል የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል።ከህንድ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ በመሆናቸው እና ባለሙያዎችም ጭምር አብረው የሚገቡ በመሆኑ ለቴክኖሎጂ ሽግግሩም ሆነ በኢትዮጵያ ካለው የኢኮኖሚ አቅም አኳያ በቀላሉ የሚለመዱ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑን በመግለጽም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ኢንጂነሮች እና ቴክኒሽያኖች ከህንድ ከመጡት ባለሙያዎች ልምድ እየወሰዱ በመሆኑ በተለያዩ ፋብሪካዎች የሚበረታታ የቴክኖሎጂ ሽግግር እየተስተዋለ መሆኑንም አመልክተዋል። “ኢትዮጵያ ገና በጣም የሚሰራባት አገር ነች፤ ለመስራትም ብዙ እድሎች ስላሉ የሚመጣው ኢንቨስተርንም ብዙ አማራጮችን መኖሩን እየተመለከተ ነው” ያሉት ሊቀመንበሩ፤ በማዕድን፣ በፋርማሲ፣ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ በኬሚካል፣ በቴክኖሎጂ፣ በሶፍትዌር ማበልጸግ እና ሌሎችም ዘርፎች ላይ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎች መጠቀም እንደሚገባም ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37995
3cf53491e3a35e8520813d27afa5091b
64b6c0f418df8a0cc1984d1c6272e712
በክልሉ በዘንድሮው መኸር ወቅት ለመሰብሰብ ከደረሰው ሰብል 94 በመቶው መሰብሰቡ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ጸጋዬአዲስ አበባ፡- በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከተዘሩ የተለያዩ የሰብል አይነቶች መካከል ለመሰብሰብ ከደረሰው ሰብል ውስጥ 94 በመቶ የሚሆነውን መሰብሰብ መቻሉን የኦሮሚያ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ።የቢሮው ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌቱ ገመቹ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የመኽር ሰብል ስብሰባን በተመለከተ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ ተገብቷል። በዚህም ወደፊት የሚደርሱ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ እንዲሁም በአንዳንድ አከባቢዎች ዘግይተው ከሚደርሱ ሰብሎች ባለፈ፤ አሁን ለመሰብሰብ ከደረስው ሰብል መካከል 94 በመቶ የሚሆነውን መሰብሰብ ተችሏል።እንደ አቶ ጌቱ ማብራሪያ፤ አሁን ላይ የተሰበሰበው ሰብል በወቅቱ በሰብል ከተሸፈነው ከ6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር ውስጥ አምስት ሚሊዮን ሄክታር የሚሸፍን ሲሆን፤ ቀሪውን የጥራጥሬ እህልና ገና ወደ ፊት የሚደርሱ ሰብሎችን ለመሰብሰብ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።በመጀመሪያ በክልሉ ከ6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬትን በሰብል ለመሸፈን ታቅዶ የነበረ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጌቱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ጾም የሚያድር ባዶ ቦታ እንዳይኖር ታስቦ በመሰራቱ በአርሶ አደሮች፣ በኢንቨስተሮች እና መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ስር ያሉ መሬቶች እንዲታረሱ በማድረግ ወደ 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማዘጋጀት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈን መቻሉን ተናግረዋል። ከዚህም ውስጥ 191 ሚሊዮን ኩንታል እህል ለመሰብሰብ ታቅዶ አሁን ባለው የመሬት ሽፋን መሰረት ግቡን ማሳካት እንደ ተቻለ ገልጸዋል። እንደ አቶ ጌቱ ገለጻ፤ አርሶ አደሩ ልጆቹን ቤተሰቦቹን በሙሉ ይዞ እንዲሰበስብ ከክልል እስከ አርሶ አደሩ ድረስ የሚደርስ ኮሚቴ በማቋቋም አቅጣጫ ወርዶ መስራት በመቻሉ የደረሱ ሰብሎች ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲሰበሰቡ ተደርጓል። በፍጥነትና የእህል ብክነት ሳይኖር ለመሰብሰብ ዘመናዊ ኮምባይነሮች ጥቅም ላይ ውለዋል። በተለይ የስንዴና ገብስ አምራች በሆኑ ቦታዎች በባሌ፣ በአርሲና በምዕራብ አርሲ አካባቢ በሰፊው መካናይዝድ በሆነ መንገድ እየተነሳ ነው። ይህንን ልምድ ወደ ሌላው አካባቢ በማስፋትም የደረሱ ሰብሎችን ሳይባክን ለመሰብሰብ እየሰራ ነው።ቀደም ሲል በኢንቨስተሮች እጅ የነበሩና በተያዘው አመት ብቻ ወደ ሰማኒያ የሚደርሱ ኮምባይነሮችን ለአርሶ አደሮች በማሰራጨት በጥቅሉ ከስድስት መቶ በላይ የሚሆኑ ኮምባይነሮችን ወደ ስራ በማስገባት ጥሩ ስራ ተሰርቷል። የኮምባይነሮችን ኪራይ በተመለከተም ከዚህ በፊት አንድ ኩንታል በመቶ ሃያ ብር ይሰበሰብ የነበረ ሲሆን፤ በዚህ አመት ግን በግማሽ ቀንሷል። አርሶ አደሮችም አሁን የሰብል መሰብሰብ አቅማቸው እና ዝግጁነታቸው ጥሩ እንደመሆኑ ይህን አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል። ሰብል በሚሰበሰብበት ጊዜ በርካታ ነፍሳትና ሌሎች ፀረ ሰብል ተባዮች መኖራቸውን የሚናገሩት አቶ ጌቱ፤ አርሶ አደሩ የእህል ብክነት እንዳይኖር በጥንቃቄ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። በሐረርጌ አካባቢ ሁለተኛ ዙር የአንበጣ መንጋ ተከስቶ ከባድ ስጋትን እየፈጠረ መሆኑን በመጠቆምም፤ በባሌም እህል ገና ባልደረሰበት ሁኔታ አስፈሪ የሆነ የአንበጣ መንጋ ከሱማሌ እየገባ በመሆኑ ትልቅ ስጋት መፍጠሩን ተናግረዋል። አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37993
9a8833fe90311d45b9ce27747a854085
d4438579e7dfea0f49a6653558b63f31
አትክልት ተራው ወደ ኃይሌ ጋርመንት መዛወሩ ለግብይትም ሆነ ለሕግ ማስከበር ስራ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡-መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ ለማግኘት፣ የግብይት ሁኔታ ምቹ ለማድረግ እንዲሁም ውጤታማ የገቢ ሕግ የማስከበር ሥራ ለማከናወን የአትክልት ተራው ወደ ኃይሌ ጋርመንት መዛወር ጠቃሚ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሃመድ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት በከተማ አስተዳደሩ ጥላ ሥር የከተማዋ፣ የክልልና የፌደራል ነጋዴዎች ተሰባጥረው የሚሰሩ በመሆኑ በሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር አዳጋች አድርጎታል።እንደ ኮማንደር አህመድ ገለጻ፤ አንድ የአዲስ አበባ ገቢዎች የሕግ አስከባሪ አካል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነጋዴ ነው ብሎ ሕግ ሲያስከበር ከጎኑ ያለው ነጋዴ በፌደራል ሥር ከሆነ በዝምታ የሚያልፍበት ሁኔታ ይታያል። በተመሳሳይም የፌደራል ነጋዴውም ሕገ ወጥ ስራ እየሰራ አንተ የአዲስ አበባ ነህ፣ አንተ የኦሮሚያ ነህ አይመለከትህም የሚል አስተሳሰብ ስለነበረ ችግሩ ውስብስብ ነው ያሉት ኮማንደር አህመድ፤ ሕግ የማስከበር ተግባር በአንድ ቢሮ ብቻ የሚፈታ ስላልሆነ የበርካታ አካላትን ተሳትፎና ቅንጅት የሚጠይቅ ነው ብለዋል።ኮማንደር አህመድ እንደገለጹት የሁሉም የሕግ አስከባሪ ስራ አላማ ሕገ ወጥ ንግድን መግታት ቢሆንም በጋራና በመናበብ የመስራት ልምድ ባለመዳበሩ ክፍተቶች ይታያሉ። ክፍተቶቹ የተፈጠሩት ከክፋት ሳይሆን ከአሰራር ክፍተት ነው። ለምሳሌ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ተግባሩ ተፅፎ ሲሰጠው “እነዚህን ጉዳዮች ትሰራለህ፣ ሕግ ታስከብራለህ፣ ገቢ ትሰበስባለህ” ተብሎ ስለሆ ከተሰጠው ሕግ የማስከበር ስራ ውጪ ሌሎች ነጋዴዎችን የሚከታተልበት አግባብ አይኖርም። ስለዚህ ሁሉም የራሱን ግብር ከፋዮች እየለየ ይሰራል። ይህ ሁኔታ ለሕግ ማስከበሩ ፈታኝ በመሆኑ የጋራ ህብረት ፈጥሮ በትብብር መስራት ይገባል።እንደ ኮማንደሩ ገለጻ በከተማ አስተዳደሩ በነበረው የአትክልት መሸጫ ቦታ ሕጋዊ ሆኖ የመሸጥ ሁኔታው ብዙም አልነበረም። በዚህ ሁኔታ ደግሞ ከገቢ አንፃር ሲታይ ነጋዴው ሲሸጥ ደረሰኝ እየቆረጠ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እያስገኘ ነበር ማለት ያስቸግራል። ምክንያቱም ቦታው አንዱ ሸጦ የሚሄድበት፣ ሌላው ተቀምጦ የሚሸጥበት፣ ከፊሉ ደግሞ ቆሞ የሚስተናገድበት የተዘበራረቀ ሁኔታ በመኖሩ ለመቆጣጠር አመቺ አልነበረም። በዚህ ሁናቴ የሕግ አካላት ንግድ ፈቃድ ያለውና የሌለውን ለመለየት የሚቸገሩበት ሁኔታ በመኖሩ አሰራሩን ዘመናዊ ማድረግ የግድ እንደሆነ ኮማንደር አህመድ ተናግረዋል።ይህንን ታሳቢ በማድረግም የአትክልት ተራው ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በዘመናዊ መንገድ ወደ ተደራጀው ቦታ በመዛወሩ ለቁጥጥርና ለክትትል አመቺ ሁኔታ መፈጠሩንና እያንዳንዱ ነጋዴም ቁጥር ተሰጥቶት የንግድ ፈቃዱን ማሳየት በሚችልበት አግባብ ተደራጅቶ እንቅስቃሴውን መለየት በሚያስችል መንገድ መሰራቱን ኮማንደሩ ገልፀዋል።በመጨረሻም የንግዱ ማህበረሰብ የትም ሆኖ ይሰራ የትም ንግድ ፈቃድ ኖሮት ሕጋዊ ሆኖ እንዲሰራ ማድረግ የገቢዎች ህግ የማስከበር ተግባር ነው የሚሉት ኮማንደር አህመድ፤ ማንኛውም ነጋዴ ህጋዊ ሆኖ ለሚሸጠው ነገር ደረሰኝ እየቆረጠ የሚጠበቅበትን ግዴታ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38005
fe96355341fe431ee2b886cb6e3cd1c2
8ddfe9980f30d234c091be647f4edd58
የጋዜጠኛ እና አርቲስት ኢብራሂም ሀጂ አሊ ስርአተ ቀብር ተፈጸመ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የሚታተመው በሪሳ ጋዜጣ በ1968 ዓ.ም ስራ ሲጀምር ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የነበሩት ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ዕድገት ውስጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተው ኢብራሂም ሀጂ አሊ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።ኢብራሂም ሀጂ አሊ ካለፈው ክረምት ጀምሮ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ የህክምና ክትትል ሲደረግለት ቆይቶ ትናንት ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል። የቀብር ስነስርዓቱም ትናንት 9፡00 ሰዓት ላይ ቤተሰቦቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ በተገኙበት በኮልፌ የሙስሊም መቃብር ተፈጽሟል።በ1968 ዓ.ም በሪሳ ጋዜጣ ስራ ሲጀምሩ ኢብራሂም ሀጂ አሊ አንደኛው ጋዜጠኛ ነበረው ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና የቋንቋ ተመራማሪው በሙዚቃ ህይወቱ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ያበረከተ ሲሆን፣ አራት ዓይነት የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጫወት ይችል ነበር። ኢብራሂም ሀጂ አሊ ሙዚቃን የጀመረው ተወልዶ ባደገበት በድሬዳዋ ሲሆን በ1967/68 የአርፈን ቀሎ ባንድ 2ኛ ትውልድ በመባል በሚጠራው ከአዱ ቢራ ባንድ መስራቾች ከሚባሉት የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ፣ ሂሜ የሱፍ፣ አብዱ ሸኩር፣ መሀመድ ጠዊል ጋር በመሆን አንደኛው መስራች ነበረ።ከዚያን ጊዜ በኋላ የጋዜጠኝነት ህይወትን እስከሚቀላቀል የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃን በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ለማስተዋወቅ እድል አግኝቶ ተጠቅሞበታል። ኢብራሂም የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንደነበረም በቅርብ የሚያውቁት እና የእርሱን ስራዎች የተጫወቱ ይመሰክሩለታል።በ1987 ዓ.ም ሬዲዮ ፋና ሲመሰረት ፋናን ከተቀላቀሉ አንጋፋ ጋዜጠኞች መካከልም አንደኛው ሲሆን፤ ተወዳጅ የሆነውን ፋና አፋን ኦሮሞ ፕሮግራምን አዘጋጅቶ በማቅረብም ይታወቃል። ኢብራሂም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለ ሲሆን ህይወቱ እስከሚያልፍ ድረስም የስፖርት ጋዜጠኛ ነበር። አፋን ኦሮሞ በጥናት ላይ ተመስርቶ እንዲያድግም ጥረት ካደረጉ ታላላቅ ሰዎች መካከል አንደኛው እንደሆነ የዘገበው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38008
55fb472f719fe88719e18a7586d5a9fa
1f2eae0dd35e237436a3e0f8fd100620
በቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናት ላይ የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ጥሰት እንደሌለበት ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲሱ ገረመው አዲስ አበባ፡- ከፍተኛው ፍርድ ቤት በትላንትናው ዕለት በቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን በአመክሮ እንዲለቀቁ ያሳለፈው ውሳኔ የትኛውንም ወገን እንደማይጎዳና የህግ ጥሰት እንደሌለበት ተገለጸ። የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኮሎኔል ብርሃኑ ባዬ እና ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሌፍተናንት ጄኔራል አዲስ ተድላ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ለኢትዮጵያ ቀጣይ ጉዞ የሚኖራቸው አንድምታ ከፍተኛ መሆኑም ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በሰብዓዊ መብት መርኅ አስተሳሰብ የሞት ቅጣት በጣም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለሚያስከትል ወደ እድሜ ልክ እሥራት መቀየሩ ተገቢና ፍትሐዊ እርምጃ ነው። በቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናት ላይ የተወሰነው ፍርድም ሕጉን ተከትሎ የተፈጸመ ሂደት ነው። እድሜ ልክ ቅጣት የሚፈረድበት ሰው 20 ዓመታት ከታሰረ በኋላ በአመክሮ ሊለቀቅ እንደሚችል የሚደነግግ ሥርዓት በመኖሩ ውሳኔው ማንንም የማይጎዳና የሕግ ጥሰትም የሌለበት ነው።እንደ ዶክተር ዳንኤል ገለጻ፤ የቀድሞ መንግስት ባለ ሥልጣናት የነበሩ ሰዎች በፍርድ ቤት ጥፋተኛነትና የቅጣት ውሳኔ ከተወሰነባቸው በኋላ የሞት ቅጣት ወደ እድሜ ልክ እስራት ሲቀየር የመጀመሪያው አይደለም። ከዚህ በፊትም የእስር ዘመናቸውን ጨርሰው የተለቀቁ ብዙ ታሳሪዎች የሞት ቅጣቱ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮላቸው ነው የእስር ዘመናቸውን ያጠናቀቁትና ከእስር የወጡት።በሰብዓዊ መብት መርኅ ደግሞ የሞት ቅጣት ወደ እድሜ ልክ እሥራት መቀየሩ ተገቢ እርምጃ እንደሆነ ይታመናል። ምክንያቱም የሞት ቅጣት በጣም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለሚያስከትል በተለይ ረጅም ጊዜ ለታሰሩ ሰዎች ወደ እስር መቀየሩ ተገቢና ፍትሐዊ እርምጃ ነው። ስለዚህ እርምጃው ሕጉን ተከትሎ የተፈጸመ ሂደት ነው።ዶክተር ዳንኤል እንደሚሉት፤ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ የሀሳብ ልዩነት ቢኖር አያስገርምም። ምክንያቱም ሁልጊዜም ቢሆን በዳኝነት ላይ ሦስት ዳኞች ሲሰየሙ ዳኞች የተለያየ አተረጓጎም ሊኖራቸው ስለሚችል ካልተስማሙ በአብላጫ ድምጽ ይወሰናል። እናም የአብላጫ ድምጽ ውሳኔው የሞት ቅጣቱ ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲቀየር መደረጉ፤ እድሜ ልክ ቅጣት የሚፈረድበት ሰው 20 ዓመት ከታሰረ በኋላ በአመክሮ ሊለቀቅ እንደሚችል የሚደነግግ ሥርዓት አለ። ከዚህ በፊት የተለቀቁት ብዙ የደርግ ባለሥልጣኖችም በዚሁ አይነት ሁኔታ ነው የተለቀቁት። ስለዚህ ይሄም ብዙ የተለየ አይሆንም።ምናልባት ይሄን ከዚህ በፊት ከነበሩት ለየት የሚያደርገው አሁን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሰዎች መንግስት እስር ቤት ውስጥ ሳይሆን ይሄንን 20 ዓመት ያሳለፉት ኤምባሲ ቅጥር ጊቢ ውስጥ መሆኑ ነው። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ የነበሩበት ሁኔታ ከእስር ጋር የሚመሳሰል መሆኑን መሠረት አድርጎ ነው ውሳኔውን ያሳለፈው።ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት እንደተለቀቁት የደርግ ባለስልጣናት በተለቀቁበት ወቅት ጥያቄ አስነስቶ ነበር። ከተጎጂ ቤተሰቦች አንጻር የዚህ አይነት ጥያቄ በተወሰነ መጠን ሊነሳ እንደሚችል ይገመታል። ነገር ግን ሁሉም የተጎጂ ቤተሰቦች አንድ ዓይነት ስሜትና አስተያየት አላቸው ማለት አይደለም። አንዳንድ የተጎጂ ቤተሰቦች ይሄን ያህል እስር ከተፈጸመ በቂና ተመጣጣኝ ቅጣት ነው፤ ከዚህ የበለጠ እስር ቤት መታሰር የለበትም የሚል አስተያየት ያላቸው ሰዎች ይኖራሉ። አንዳንድ የተለያየ አስተያየት ያላቸው ሰዎች ደግሞ ሊኖሩ ይችላል። ሁሉንም ሰው በእኩል ደረጃ ያስደስታል ተብሎ ባይታሰብም፤ በአብዛኛው አስተሳሰብ አንድ ሰው በጥፋቱ 20 ዓመት ያህል ከታሰረ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት አግኝቷል፣ ታርሟል፣ ተስተካክሏል ተብሎ ይገመታል።በመሆኑም በተመሳሳይ ሁኔታ ከ20 ዓመት በላይ ታስሮ ምህረት ሳያገኝ በእስር ላይ የሚገኝ ሰው ካለ ተፈጻሚ መሆን ይኖርበታል። ነገር ግን የፍርድ ምርመራቸውን ያልጨረሱ ሰዎች ይኖራሉ። ምክንያቱም አንዳንዶቹ መጀመሪያ የታሰሩ ሰዎች ሁሉ ሲታሰሩ አንድ ላይ የታሰሩ ሳይሆን በኋላ እየዘገዩ የታሰሩ ሰዎች አሉ። ከውጭ ሀገርም ታስረው የመጡ ሰዎች አሉ። ስለዚህ  እነሱ ቅርብ ጊዜ ስለነበረ የታሰሩት፤ ይሄ 20 ዓመት የሚለው ጊዜ ወይም የተፈረደባቸው የእስር ዘመን ገና አልሞላ ይሆናል። ስለዚህ ያ አንድ ሰው የተፈረደበትን የእስር ዘመን መጠበቁ የግድ ይላል።እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነብርሀን የኢትዮጵያ እርቀ ሠላም ኮሚሽን አባል ኮሚሽነር በበኩላቸው እንደሚሉት፤ የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት የነበሩት ኮሎኔል ብርሃኑ ባዬ (በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ) እና ሌፍተናንተ ጄኔራል አዲስ ተድላ (በወቅቱ ኤታማዦር ሹም የነበሩ) በጣሊያን ኤምባሲ የነበራቸው ከ29 ዓመታት በላይ ቆይታ በእስር ቤት ካለው ሁኔታ የማይተናነስ በመሆኑና መብታቸው ተገድቦ በመቆየቱ በአሁኑ ጊዜ ያለው የጤንነታቸው ሁኔታ እንዲሁም የዕድሜያቸው መግፋት ካሳለፉት የማህበረሰብ የመገለል ጊዜ አንፃር ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የሆነ የአካልና የስነ ልቦና ጫና አሳድሮባቸው ነበር።ስለሆነም ከሰብዓዊ ርህራሔ መብት አንፃር እና ያሉበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአመክሮ ምህረት ተደርጎላቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ መንግስትን እንድንጠይቅላቸው በተደጋጋሚ በቤተሰቦቻቸው በኩል ጥያቄ ቀርቦ ነበር። መንግስትም ጉዳዩን በሕግ አግባብ ለመፍታት የቀረበውን ጥያቄ ለማስተናገድ የሔደበትን ርቀት የሚደነቅ ነው። በተለይም ለክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለፍትህ አካሉና ለጠቅላይ አቃቢ ሕግ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል።መሰል ተግባራት ለሀገራችን ቀጣይ ጉዞ የሚኖራቸው አንድምታ ከፍተኛ እንደሚሆን በማመን፤ ለዚህ ሂደት መሳካት በተለየ አግባብ ለኮሚሽናችን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን ያሉት የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ለማስፈን ለምናደርገው ጉዞ አንድ እርምጃ ከፋች እንደሚሆን እናምናለን ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38059
378cbd6960e8e53ca8d4ab0f4d86f220
80a6e8146b71e17ae9306e124d09ff45
የቀድሞ መንግሥት ባለሥልጣናት በአመክሮ ተለቀቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዳግማዊት ግርማ አዲስ አበባ፡- የቀድሞ መንግሥት ባለስልጣናት ሌፍተናንት ጄኔራል አዲስ ተድላ እና ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ በአመክሮ መለቀቃቸውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገለጸ። በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሙስናና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ፀጋ ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የቀድሞ መንግሥት ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደታቸው በሌሉበት የታየ እና የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸው የሞት ቅጣት ተጥሎባቸው ነበር። የጣልያን ኤምባሲ የቀድሞው ደርግ ባለስልጣናት የነበሩት ሰዎች በተመለከተ በሰጠው ኦፊሴላዊ ገለጻ ግለሰቦቹ ለረጅም ዘመናት ነፃነታቸው ተገድቦ የቆዩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ከኤምባሲው ምንም አይነት ድጋፍ አይደረግላቸውም ነበር።በመሆኑም ከቤተሰቦቻቸው በሚላክላቸው ቀለብ በአንድ ቅጥር ግቢ በተወሰነ ስፍራ ብቻ ተወስነው ከእድሜ መግፋት እና ከተፈጥሮ ህመም ጋር በተገናኘም ተገቢውን ህክምና ለማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው መቆየታቸውን ኤምባሲው ማረጋገጡን ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ገልፀዋል።የእርቀ ሰላም ኮሚሽንም ግለሰቦቹ በሕግ አግባብ ተለቀው ቤተሰቦቻቸውን እንዲቀላቀሉ ለመንግስት ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን ያስታወሱት ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፤ በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ቆይተው የነበሩ የቀድሞው ደርግ አመራሮችም ከ10 ዓመታት በፊት ከእስር ወጥተው ከማህበረሰቡ ጋር እንዲኖሩ መደረጉን ገልጸዋል።በተቃራኒው በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ተወስነው ለ30 ዓመታት የቆዩት እነኚህ ሰዎች ከመደበኛው የእርምት ስፍራ ባልተናነሰ በተወሰነ አነስተኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ ወደ ህክምና ተቋማት እንኳን መውጣት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ከመንግስትም ሆነ ከቆዩበት የኤምባሲ ቅጥር ግቢ አስተዳዳሪ ምንም አይነት እንክብካቤ እና ድጋፍ ሳያገኙ መቆየታቸው በእስር ቢቆዩ ኖሮ ከሚፈጠርባቸው የመብት ገደብ አንጻር ቢበዛ እንጂ የሚያንስ እንዳልሆነ ግንዛቤ መወሰዱን አመልክተዋል።በመሆኑም መንግስት ከዚህም በላይ እነኚህን ሰዎች ከዚህ በኋላ ነጻነታቸውን ገድቦ ማቆየት የፍትህ አላማን ከማሳካትም አንጻር የሚጨምረው ውጤት የማይኖር በመሆኑ፣ ከፍርደኞቹ እድሜ እና የጤና ሁኔታ አንጻር የሰብዓዊነት እይታን ከግምት በማስገባት በግለሰቦቹ ላይ ተወስኖ የነበረውን የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀየር ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሃሳብ ማቅረቡን ጠቁመዋል። በዚሁ ሃሳብ መሰረት ፕሬዚዳንቷ ቅጣቱ ወደ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት ሕገ-መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት እንዲለወጥ መወሰናቸውን በመግለጽ፤ በዚህም መሰረት መንግስት ግለሰቦቹ ካሉበት ስፍራ መውጣት ስለሚችሉበት ሁኔታ ከሕግ ማዕቀፍ እይታ አንጻር አስፈላጊውን ጥናት አድርጎ ግለሰቦቹ እስካሁን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ነጻነታቸው ተገድቦ መቆየቱ አስተማሪነት ያለው መሆኑ ከግምት ገብቶ በአመክሮ እንዲለቀቁ አቤቱታ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የቀረበውን አቤቱታ ተቀብሎ ግለሰቦቹ በአመክሮ እንዲለቀቁ መወሰኑን አስረድተዋል።የመንግስት ስርዓት ለውጡን ተከትሎ በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ መንግስት በኃላፊነት ላይ የነበሩ እና በወቅቱ ተፈጽሞ በነበረ ወንጀል ተጠርጥረው እና ክስ ተመስርቶባቸው ከነበሩት አመራሮች እና የደርግ አባላት የተወሰኑት ተጠርጣሪዎች ቀደም ብለው በአዲስ አበባ ከተማ ወደሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ገብተው በዚያው ለ30 ዓመታት መቆየታቸው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38061
bfd6b7f4d45351227cefe11590efa6df
d1c9aef43a71a21f6f2fa1a69b92f7ea
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አዲስ የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- በትግራይ ክልል አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ወደ ስራ መግባታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ። እንደ ኢዜአ ዘገባ፣ የአስተዳደሩ የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሣ በክልሉ ከሚያስፈልጉ 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።በዚሁ መሠረት፡- ዶክተር ካህሣይ ብርሃኑ …… የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ …… የኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዶክተር ፋሲካ አምደ ስላሴ …… የጤና ቢሮ ኃላፊአቶ አበራ ንጉሴ ………. የፍትህ ቢሮ ኃላፊወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ ……… የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊአቶ ዮሴፍ ተስፋይ ………. የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን …….. የትምህርት ቢሮ ኃላፊዶክተር ገብረህይወት ለገሠ ……. የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ኃላፊአቶ ሰለሞን አበራ …….. የውሃ ሃብት ቢሮ ኃላፊአቶ አብርሃ ደስታ ……. የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ እና አቶ ገብረመስቀል ካሣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።ሌሎች ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣዮቹ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ ይገባሉአዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38069
909f92a2160e2c657fe5c05eb44ed711
313ede6ff644dcd62e4bc6d3b3c742de
በመተከል እየተፈጸመ ያለው ግድያ በክልሉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እጅጉን መዳከሙን እንደሚያሳይ ኢሰመኮ ተናገረ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እየተበራከተ የመጣው እና ከሰሞኑ ሌሊት ላይ የታጠቁ ኃይሎች በእንቅልፍ ላይ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ በለኮሱት እሳት እና በተኩስ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው በክልሉ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከመ መሄዱን የሚያሳይ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ። ኮሚሽኑ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ መሆኑንም ተናግሯል።ኮሚሽኑ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ላይ የታጠቁ ኃይሎች በእንቅልፍ ላይ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ በለኮሱት እሳት እና በተኩስ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው በክልሉ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከመ መሄዱን ነው። በመሆኑም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ ነው።በመግለጫው እንደተመላከተው፤ ኢሰመኮ የጥቃቱን ሂደት በተመለከተ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከሚመለከታቸው አካላት እና ከተጎጂዎች ጋር በመነጋገር ሲከታተልና ሲያጣራ ቆይቷል። በኩጂ ቀበሌ ከወረዳው መቀመጫ ከሆነችው ቡለን ከተማ 90 ኪ.ሜ. ርቃ የምትገኝ ሲሆን የሺናሻ፣ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ይኖሩባታል። ለቀበሌው የተመደበ የፖሊስ ወይም የፀጥታ ኃይል አለመኖሩን ኮሚሽኑ በክትትሉ መሰረት ተረድቷል። ኮሚሽኑ ሁኔታውን እስካጣራበት ጊዜ ድረስ በቡለን ሆስፒታል 36 ተጎጂዎች እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን አብዛኞዎቹ በጥይት ሌሎቹ በቀስት የቆሰሉ መሆናቸውን ኢሰመኮ በምልከታ አረጋግጧል። በተጨማሪም ሰዎች ጥቃት የደረሰባቸውን ሁኔታ የሚያሳዩና የሚረብሹ የፎቶግራፍ ማስረጃዎች ለኮሚሽኑ ደርሰውታል። በሰው ሕይወት እና በአካል ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የደረሱ ሰብሎችና የተሰበሰቡ ማሳዎች በእሳት ጋይተዋል። ቢያንስ 18 ያክል ነዶዎች ሲቃጠሉ ማየታቸውን አንድ ተጎጂ አስረድተዋል። በጨላንቆ እና ዶሼ ቀበሌዎች ቤቶች እየተቃጠሉ እንደሆነ ከአካባቢው ለኮሚሽኑ የተላኩ መረጃዎች ያመለክታሉ። በድባጤ ወረዳ ዶንበን ቀበሌ ስጋት የገባቸው ነዋሪዎች ከታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ቀዬአቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነም ኮሚሽኑ ረድቷል። አካባቢውን በቅርበት እንዲጠብቅ የተመደበው ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ለማረጋጋት ተግባር ወደቦታው ተልከው የነበሩ አንድ የፌዴራል እና ሁለት የክልሉ አመራሮችን ለማጀብ በሚል አካባቢውን ለቅቆ መሄዱ ታውቋል።ጥቃቱ የጀመረው ይህንኑ ተከትሎ እንደሆነና ሌሊቱን የጀመረው ጥቃት እስከ ቀኑ አጋማሽ ድረስ መዝለቁንም ለማወቅ ተችሏል። ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው ተጎጂዎች እንደሚሉት በጥቃቱ ከሞቱ ሰዎች መካከል አብዛኛው የሺናሻ ተወላጆች ናቸው። ከዚህ ቀደም በነበሩ ጥቃቶች ፈጻሚዎቹ ከ”ጫካ” የሚመጡ ሰዎች የነበሩ ቢሆንም፣ በዚህኛው ጥቃት “በስምና በመልክ የሚያውቋቸው”የበኩጂ ቀበሌ ነዋሪዎች ጭምር መሳተፋቸውን ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጂዎች ገልጸዋል። ኢሰመኮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ተደጋጋሚነትና የክልሉን ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ አስመልክቶ፣ የፌዴራሉንና የክልሉን መንግሥታት የተጠናከረ ትብብርና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሻ ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወሳል። ይሁንና ጥቃቶቹ በመልክ እና በስፋት እየተባባሱ መጥተዋል። ስለሆነም፣ በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ሰዎች የህክምና እና ሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ፣ እንዲሁም ተገቢው ማጣራትና ጥቃቱን ባለመከላከልም ሆነ በሌላ መልኩ ጥቃቱን የፈጸሙና ያባባሱ ሰዎችን ሕግ ፊት የማቅረቡ ሂደት ከወዲሁ እንዲጀመር ኮሚሽኑ ያሳስባል። በአካባቢው የሚገኘውን የፀጥታ ኃይልና መዋቅር የሰዎችን ደኅንነት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በከፍተኛ ደረጃ በአፋጣኝ እንዲጠናከር ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38060
95cb9e8664c2e8508162c96aace57e72
e3a7c8765c1837ce08ffd1f1a47bb24c
የቦስተን ማራቶን አሸናፊዎች ከዓለም ቻምፒዮኖች ጋር ይፋለማሉ
ስፖርት
ከዓለም ምርጥ የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የቦስተን ማራቶን ከዚህ ቀደም ማሸነፍ የቻሉና የዓለም ቻምፒዮን የሆኑ አትሌቶች ዘንድሮ የሚፋለሙበት በመሆኑ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል። የዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ የሰጠው ይህ ውድድር በተለይ በሴቶች ምድብ ባለ ክብረወሰኗን ኢትዮጵያዊት አትሌት ወርቅነሽ ደገፋን ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ አምስት ከ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ እንዲሁም አስራ ሁለት 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ በታች ማራቶንን ማጠናቀቅ የቻሉ አትሌቶች ተሳታፊ መሆናቸው ውድድሩን ተጠባቂ አድርጎታል። የአሸናፊነት ቅድመ ግምቱ ለቦታው ባለ ክብረወሰን ለሆነችው አትሌት ወርቅሽ የሚሰጥ ቢሆንም፤ ከባድ ፉክክር የሚገጥማት መሆኑ ውድድሩን ይበልጥ አጓጊ አድርጎታል። እአአ በ2018 የውድድሩ አሸናፊ የነበረችው አሜሪካዊቷ ዴስሬ ሊንደን፣ የሁለት ጊዜ በየዓለም ቻምፒዮናዋ ኬንያዊት ኤድና ኪፕላጋት፣ እአአ በ2015 የቦታው ባለ ድል ካሮላይን ሮቲች እንዲሁም እአአ በ2014 የቦታውን ክብረ ወሰን የሰበረችው ኢትዮጵያዊቷ ብዙነሽ ዳባ የቦስተን ከተማ በምታስተናግደው ታላቁ የጎዳና ላይ ሩጫዋ ድምቀት የሚሆኑና ከ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ በታች መሮጥ የቻሉ አትሌቶች መሆናቸውን አዘጋጆቹ አረጋግጠዋል። እአአ በ2015 የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ነሃስ ሜዳሊያ ባለቤቷ ማሬ ዲባባ እንዲሁም በዚያው ቻምፒዮና የ10 ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ያገኘችው ገለቴ ቡርቃ፣ መስከረም አሰፋ፣ የብርጓል መለሰ፣ በሱ ሳዶ እንዲሁም ሃፍታምነሽ ተስፋይ ደግሞ ሌላኛዎቹ በውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው። የ2017ቱ የዓለም ቻምፒዮን ባህሬናዊቷ ሮዝ ቺሊሞ፤ ያለፈው ዓመት የቶሮንቶ ማራቶን አሸናፊዋ ማግዳላይኔ ማሳይ፣ በሮም ማራቶን የሶስት ጊዜ ባለድል ራህማ ቱሳ፣ በ2018 ቦስተን ማራቶንን በሶስተኝነት ያጠናቀቀችው ክሪስታ ዱቼኔ እንዲሁም የሁለት ጊዜ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮናዋ ሜሪ ንጉጊም በዚህ ማራቶን ላይ ተሳታፊ የሚሆኑና ለአሸናፊነቱ ቀላል ግምት የማይሰጣቸው አትሌቶች ናቸው። በወንዶች በኩልም ብርቱ ፉክክር እንደሚኖር ማሳያ የሆኑ አትሌቶች እንደሚካፈሉ የታወቀ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል አስር የሚሆኑት ማራቶንን 2 ሰዓት ከ07 እና ከዚያ በታች የሆነ ሰዓት ማጠናቀቅ የቻሉ አትሌቶች ናቸው። ያለፈው ዓመት የቦስተንና የቺካጎ ማራቶን አሸናፊው ኬንያዊ አትሌት ላውረንስ ቼሮኖ ክብሩን እንደያዘ ለመቆየት፤ ከዚህ ቀደም የነበሩ የቦስተን ማራቶን አሸናፊ አትሌቶችን መጋፈጥ የግድ ይለዋል። የሁለት ጊዜ የቦስተን ማራቶን አሸናፊውና የዶሃው የዓለም ቻምፒዮና ባለድሉ ሌሊሳ ዴሲሳ ዘንድሮም ሌላ ድል ለማስመዝገብ በቦስተን የሚገኝ መሆኑን አስታውቋል። እአአ የ2017 አሸናፊው ጃፓናዊ ዩኪ ካዋቺ እና የ2018ቱ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ ጂኦፈሪ ኪሩይም በቦታው ድላቸውን ለመድገም ተዘጋጅተዋል። ኡጋንዳዊው የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮን ስቴፈን ኪፕሮቲች፣ አልበርት ኮሪር፣ ኤርትራዊው አብራር ኦስማን፣ ኢትዮጵያውያኑ ደጀኔ ደበላ፣ ፍቅሬ በቀለ፣ ጀማል ይመር እንዲሁም ከሌሎች አገራት የተውጣጡ በርካታ አትሌቶችም በአሜሪካው ግዙፍ የጎዳና ላይ ሩጫ ተሳታፊ መሆናቸውን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጥር 23/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=26509
142df6b666e72843b7fbbbdab92690bd
9451fdd8f47dc4441314b6ee4fe1c003
የከዋክብቶች አርዓያው ኮከብ አሳዛኝ መጨረሻ
ስፖርት
ዓለማችን በታሪኳ ካየቻቸው የቅርጫት ኳስ ከዋክብቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ከስፖርቱ ዓለም ስኬቱ ባሻገር በተለያዩ ታላላቅ መድረኮች የሚያደርጋቸው አነቃቂ ንግግሮች ተወዳጅነትን ከማፍራት ባሻገር ለበርካታ የዓለማችን ወጣቶች አርዓያ መሆን ችሏል። ከቅርጫት ኳስ አፍቃሪዎች አልፎም ተፅዕኖው በሌሎች ስፖርተኞችና ከስፖርቱ ዓለም ውጪ ባሉ ወጣቶች ላይ ማረፍ ችሏል። ለዓለማችን በርካታ ከዋክብት ስፖርተኞች የአሸናፊነትና ጥሩ ምግባር አርዓያ የሆነው ኮከብ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቤ ቢን ብርያንት ባለፈው ሳምንት በድንገተኛ የሄልኮፕተር መከስከስ አደጋ ሕይወቱ ማለፉ የስፖርት ቤተሰቡን ቢያስደነግጥም አመለ ሸጋው ኮከብ ወደ ፊትም ሲታወስ ይኖራል። ኮቢ ብራይንት እ.ኤ.አ በ1978 በፊላዴልፊያ የተወለደ ሲሆን ወላጅ አባቱ ጆኢ ብራይንት የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ነበር። ኮቢ ማለት በጃፓን ተወዳጅ የስጋ ምግብ ነው። ይህም የቅርጫት ኳስ ፈርጥ ስሙን ከዚሁ አግኝቷል። 1 ሜትር ከ98 ሴንቲ ሜትር የሚረዝው ኮቢ ብራያንት 96 ኪሎ ግራም ይመዝናል። የ41 ዓመቱ ኮቢ አምስት ጊዜ የኤን ቢ ኤ ቻምፒዮን በመሆን በቅርጫት ኳስ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝና ማትረፍ ችሏል። በ 20 ዓመት የቅርጫት ኳስ ፕሮፌሽናል ህይወቱ አያሌ ክብሮችን የጨበጠው ኮቢ ሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ ቻምፒወን ሲሆን በ 2008 በመድረኩ ውዱ ተጫዋች መሆን ከመቻሉም በተጨማሪ 2006 ላይ ከቶሮንቶ ራፕቶርስ ጋር በገጠመበት ጨዋታ 81 ቅርጫቶችን በማስቆጠር 2ኛው የምንጊዜም ከፍተኛ ቅርጫት አስቆጣሪ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። የሀብት መጠኑ እስከ 650 ሚሊየን ዶላር የሚገመተው ኮቢ ብራያንት ለበርካታ ክዋክብት ስፖርተኞች እውነተኛ አርዓያ በመሆን መነሳሳትን የፈጠረ ታሪክ አኑሮ በካሊፎርንያ በደረሰው የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ በ 41 ዓመቱ ህይወቱ አልፏል። ሁነቱን አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ በአደጋው ወደፊት የአባቷን ሌጋሲ ለማስቀጠል ተስፋ የተጣለባት የ 13 ዓመቷ ጂያና ብራያንት ከአባቷ ጋር ህይወቷ ማለፉ ነው። ሌሎች ሰባት ሰዎችም በአደጋው ህይወታቸው አልፏል። የ 13 ዓመቷ ታዳጊ ጂያና ለመምባ ስፖርትስ አካዳሚ እየተጫወተች የምትገኝ ሲሆን በታሪካዊው የቅርጫት ኳስ ባለሟል በሆነው አባቷ እየሰለጠነች ጨዋታዋን ለማከናወን አገር አማን ብላ እየበረረች ባለበት ሰዓት ያልታሰበውና የሚሊዮኖችን ልብ የሰበረው የእርሷንና አባቷን ህይወት የቀጠፈው መሪር አደጋ ተከሰተ። ከ 4ቱ ልጆች 2ኛ የሆነችው ጂያና ፈጣን ፣ ቀልጣፋና ለቅርጫት ኳስ ጥልቅ ፍቅር የነበራት ሲሆን ከአባቷ የወረስችው እምቅ የክህሎት ሀብት ወደፊት የአባቷን ሌጋሲ ከማስቀጠልም ባለፈ ለቅርጫት ኳሱ አዲስ አብዮት እንደምታመጣ በርካቶች አመኔታ ጥለውባት ነበር። ለስፖርት የተጻፈን የፍቅር ደብዳቤ የሚተርክ 5 ደቂቃ የሚቆይ የአንሜሽን ፊልሙ በ 2018 ታላቁን የኦስካር ሽልማት አሸናፊ ያደረገው ኮቢ ብራያንት ከውድ ልጁ ጋር ወደ ማይመለስበት ዓለም ለመሄድ ተገዷል። የኮቢ ብራይንት ህልፈት የዘንድሮውን 62ኛውን የግራሚ ሽልማት ላይ የኀዘን ድባብ የፈጠረ ሲሆን የመድረኩ መሪ የሆነችው አሊሻ ኪስ መታሰቢያነቱ ‹‹ለእርሱ ይሁን›› ብላለች። ‹‹ከደቂቃዎች በፊት ሎስ አንጀለስ ፣ አሜሪካና መላው ዓለም ጀግናውን ተነጠቀ። ኮቢ ብራያንት የተለየና ለሚሊዮኖች መነሳሳትን የፈጠረ ዘመን ተሻጋሪ ነው። በሆነው ነገር ልባችን ክፉኛ ተሰብሯል›› ስትልም ታሪካዊውን የቅርጫት ኳስ ባለሟል አስባለች። በሎስ አንጀለስ ሌከርስ የክለብ ቆይታው 5 ጊዜ ቻምፒወን የሆነው ኮቢ ብራያንት ህልፈቱ ከተሰማ በኋላ በአሜሪካ የተሰናዱት ዝግጅቶች በታላቅ ክብር አስበውታል። የቅርጫት ኳስ ጨዋታዎች ሲከናወኑ አባታቸውን በማሰብ ለደቂቃ የቆየ የህሌና ጸሎት አድርገዋል። የእግር ኳሱ ዓለም ኮከቦችና ዝነኛ ክለቦች በኮቢ ብራያንት ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ከመግለፅ ወደ ኋላ አላሉም። ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ጁኒየር ከሊል ጋር በተደረገው ጨዋታ 2 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን 2ኛውን ጎል መታሰቢያነቱ ለኮቢ ብራያንት አድርጓል። ቄንጠኛው ተጫዋች የእጆቹን ጣቶች ወደ ሰማይ ከፍ በማድረግም ኮቢ ብራያንትን በልዩነት አስቧል። ‹‹በመልካም ስነምግባር የታነጸው የአሸናፊነት መንፈስህ አሁን ላለሁበት ጥሩ ደረጃ መሰረት ሆኖኛል። አንተ ሁልጊዜም ለየት ያለ ማንነትን በመላበስ ነገን ለሚኖሩ ተምሳሌት ሆነሃል ፣ ጥለኸን በመሄድህ ልቤ በኀዘን ተሰብሯል፣ እጅግ በጣም እወድዳለሁ›› ሲል ቤልጄማዊው አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ የህይወት ምሳሌው ስለነበረው ኮቢ ብራያንት ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ገልጿል። በቅርጫት ኳስ ሜዳ ላይም ሆነ ከሜዳ ውጪ ለሁሉም ስፖርተኞች እውነተኛ ምሳሌ መሆኑን የጠቀሰው የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ ‹‹በሆነው ነገር አዝነናል ለቤተሰቦችህና በአጠቃላይ ለሚወዱህ መጽናናትን ከልብ እንመኛለን›› ሲልም ባርሰሎና እንደ ክለብ ተመኝቷል። ፖርቱጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በተፈጠረው ነገር መደናገጡን ገልጾ ‹‹ኮቢ ብራያንት ለበርካቶች አርዓያ የሆነ›› ሲልም አክሏል። ሮናልዶ ቀጥሎም ለቤተሰቦቹና በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉም ቤተሰቦች መጽናናትን ከልብ ተመኝቷል። ኤሲ ሚላን ‹‹ጨለማውን ክስተት ለመግለጽ ቃላቶች የሉንም ፣ በስፖርቱ ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑ ጀግኖች ዋና ተዋናዩን አጥተናል። ስላበረከትከው እጹብ ድንቅ ነገር እና ስለደገፍከን ልባዊ ምስጋናችን በአለህበት ይድረስ፣ ስለ እውነት ሁላችንም ተደናግጠናል ሲል ደጋፊው ስለነበረው ኮቢ ኀዘኑን ገልጿል። ‹‹ለዚህ ትውልድ ትልቅ ተምሳሌት በመሆን ለበርካቶች በተስፋ ውስጥ መልካም ህይወት እንዳለ መምህር ሆነሃቸዋል። ለነብስህ ፍጹም ሰላምን ይስጣት›› አንድሪያ ፒርሎ የተመኘው ልባዊ የኀዘን ምኞት ነው።አዲስ ዘመን ጥር 24/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=26562
aaf8a6f85051d27a5fdaed808e41329c
5dda612370ba1f9820197ea13a3bf182
ኢትዮጵያ የፊፋን ጠቅላላ ጉባኤ ለማስተናገድ ዝግጅት ላይ ነች
ስፖርት
የዓለምን እግር ኳስ የሚመራውና 211 አባላት ያሉት ፊፋ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ከአራት ወራት በኋላ ያደርጋል። ለአዘጋጅነቱ ደግሞ አፍሪካ የተመረጠች ሲሆን፤ የአህጉሪቱ መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባም ኃላፊነቱን ተረክባ ወደ ዝግጅቱ በመንደርደር ላይ ትገኛለች። ከሁለት ዓመታት በፊት የካፍን 60ኛ ዓመት ምስረታ ተከትሎ ጠቅላላ ጉባኤውን በስኬት ያጠናቀቀችው አዲስ አበባ ፤ 69ኛውን ጉባኤ ባሰናዳችውና ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖን ዳግም ለመሪነት በተመረጡበት የፓሪሱ ጉባኤ ላይ 70ኛውን መድረክ እንድታዘጋጅ መመረጧ ይታወቃል። ለዚህ የሚሆነውን ዝግጅት አስቀድማ የጀመረችው ኢትዮጵያ ለጉባኤው አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ከሰሞኑ ምክክር ያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በድረ ገጹ አስነብቧል። ዝግጅቱን ለማድረግም ከስፖርት ኮሚሽን፣ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት፣ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት፣ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ አየር መንገድ፣ ገቢዎችና ጉምሩክ፣ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር፣ የብሮድካስት ባለስልጣን፣ ብሄራዊ መረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተውጣጡ አካላት ጥምረት ፈጥረዋል። ለጉባኤው ዝግጅት የሚያደርግ ብሄራዊ አብይ ኮሚቴም የተዋቀረ ሲሆን፤ የኮሚቴው የበላይ ጠባቂም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ናቸው። ሰብሳቢዎቹ ደግሞ ኮሚሽነሩ አቶ ኤሊያስ ሽኩርና የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያሥ ጂራ መሆናቸው ታውቋል። በመጠናቀቅ ላይ ባለው ሳምንትም ኮሚቴው በዕቅድ ዝግጅቱ ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን፤ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያሥ ጂራ፣ የካፍ ተወካይ ወይዘሪት መስከረም ታደሰ እንዲሁም ሌሎች ተገኝተዋል። ጉባኤው ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ የሚያስችል መነሻ ሰነድ ቀርቦም ምክክር ተደርጎበታል። በፊፋ ኮርፖሬት ኢቨንት ማናጀር ካትሪን አስተርበርገር በበኩላቸው ለጉባኤው ዝግጅት በቀዳሚነት መከናወን ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል። ከተማዋ ትልልቅ ስብሰባዎችን ለማስተናገድ አዲስ ባትሆንም ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች ላይ ግን በተለየ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል። የመጀመሪያውም ከፊፋ አባላት ባሻገር ቁጥራቸው በዛ የሚል ሌሎች አካላትም በጉባኤው ወቅት የሚገኙ መሆኑን ነው ማናጀሯ የጠቆሙት። 1 ሺ400 ከሚሆኑት የጉባኤው ተሳታፊዎች ባሻገር 600 ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚና አፍሪካ ህብረት የሚሰሩ እንዲሁም ጉባኤውን ውጤታማ ለማድረግ የሚረዱ 300 ባለሙያዎች ከጉባኤው ሁለት ሳምንት አስቀድመው አዲስ አበባ የሚገኙ ይሆናል። በጉባኤው ተሳታፊ ለሚሆኑ አባል አገራት ተወካዮች ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት የትኛውን የቪዛ ዓይነት መጠቀም እንደሚገባቸው መለየት እንዲሁም የህክምና አገልግሎት በምን መልክ ማግኘት አለባቸው በሚል ቅድመ ዝግጅት ማድረግም ሌላኛው ነው። ጉባኤው ሲካሄድ በመንገዶች የትራፊክ መጨናነቅ እናዳይፈጠር፣ የመጓጓዣ አማራጮች እንዲሁም መጓጓዣዎች የአቅጣጫ አመልካች መሳሪያ መግጠም እንደሚያስፈልግም ማናጀሯ አሳስበዋል። ለጉባኤው አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎች ወደ አገሪቷ ሲገቡ በገቢዎችና ጉምሩክ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ትብብር እንዲያደርጉ፣ ጉባኤውን ለመዘገብ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን የሚገቡበት ቪዛ ምን መሆን አለበትና የተሳታፊነት ማረጋገጫ ወረቀት በምን መልኩ ማግኘት አለባቸው በሚለው ጉዳይ ላይም ምላሽ መስጠት ይጠበቃል። ለቴሌኮም አገልግሎት የሚውሉ 400 ሲም ካርዶች፣ 4ጂ ኢንተርኔት እና የሬዲዮ መገናኛ ዘዴዎችን ማዘጋጀትም እንደሚያስፈልግና ለጉባኤው ተሳታፊዎች የደህንነት ዋስትና መስጠት እንደሚገባ ተጠቁሟል። አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጥር 23/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=26501
83ccb37e190b1debf40524a3457f8cfe
a96f3084f819dc453f4d6cfcc8d681e9
እግር ኳስ የሞተበት ዕለት
ስፖርት
ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ሜዳዎች ላይ ስርዓት አልበኝነት እየተንሰራፋ መምጣቱን ተከትሎ የ2012 ውድድር ዓመት ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ትልቅ ስጋት አንዣቦበት እንደነበር ይታወሳል፡፡ እርግጥ ነው ባለፉት ዓመታት የታዩት የስቴድየም ሁከቶች አዝማሚያቸው አዲሱን የውድድር ዓመት ስጋት እንዲሰፍንበት ቢያደርግ አይገርምም፡፡ ይሁን እንጂ አስፈሪው ስጋት የበለጠ ጥፋት ሳያስከትል አልፎ አዲሱም የውድድር ዓመት በመልካም መንገድ ላይ ጉዞውን ቀጥሎ ፕሪሚየር ሊጉ ስምንተኛ ሳምንቱ ላይ ይገኛል፡፡ የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ ግን አልፏል ብለን የምንተወው ወይም ስጋት ሲፈጥርብን ብቻ የምናነሳው ጉዳይ አይደለም፡፡ ይልቁንም ካለፈው የምንማርበት ዘወትር የሌሎችን ተሞክሮና ታሪኮች አንስተን ነገን የተሻለ ለማድረግ የምንታትርበት መሆን ይገባዋል፡፡ በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችንም አንድ ሰው ለኩሶት የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ ዓለማችን የማይረሳ የስቴድየም ግጭት መለስ ብለን በማስታወስ ከታሪኩ የምንማርበት እንዲሆን ወደድን፡፡ የዚህ ዘግናኝ የስቴድየም ግጭት ታሪክ ከዚህ ይጀምራል፡፡እኤአ ሰኔ 29 ቀን 1985፣ በሄይሰል ስታዲየም፣ ቤልጅየም የአውሮፓ የክለቦች ውድድር ፍፃሜ ነበር። የሊቨርፑልና ጁቬንቱስ ጨዋታ ሊጀመር ደቂቃዎች ቀርተዋል። በ1920ዎቹ በተገነባው ያረጀ ስታዲየም 58ሺህ ተመልካች ተጠቅጥቋል። የጁቬንቱስ ደጋፊዎች ከስታዲየሙ ‹‹Z›› ክፍል የላይኞቹ ደረጃዎች ወደ ታችኞቹ፣ አንዳቸው ሌላቸው ላይ ተነባብረው እየተገፋፉ ጎረፉ። የብረት ዘንግ የያዙ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ያባርሯቸዋል። ተቀጣጣይ ነገሮች ይወረወሩባቸዋል። ሁከት ነገሠ። የራስን ነፍስ ለማዳን ሲባል በሌሎች ላይ መረማመድ ግድ ሆነ። መራወጡ፣ መደራረቡ፣ መተፋፈጉ ቀጠለ። ማዕበሉ ሄዶ፣ ሄዶ በስታዲየሙ ግድግዳዎች ተገደበ። የሰው ልጅ በማይቆጣጠረው ኃይል ተገፍቶ ከሸክላና ጡብ ከተሰራ አጥር ጋር ተጣበቀ። ግድግዳዎቹም ግፊቱን መቋቋም አቅቷቸው ፈረሱ። የስፖርት ቤተሰቡ ከአርማታ ስብርባሪ ጋር ተደባልቆ ተጨፈላለቀ። የ20 ዓመቱ ሲሞኔ ስተርን ወደ ጨዋታው የመጣው በአባቱ ጉትጎታ ነበር። የገዛው ቲኬት ጣዕረ ሞት በተንሰፈሰፈበት የስታዲየሙ ደቡባዊ ክፍል ‹‹Z›› ያስገባል። አንድ መግቢያ ብቻ ስለነበር በራፉ ላይ ትርምስ ተፈጥሯል። በቅጡ አልተፈተሸም፣ ደጋፊዎች ያለቲኬት በሩን ሲያልፉ፣ የቢራ ጠርሙስ የያዙም ሲገቡ ማየቱን ያስታውሳል። ወንበር የሌላቸው ደረጃዎች መቀመጫ ከሆኑበት ከዚህ የስታዲየሙ ክፍል የሊቨርፑል ደጋፊዎች ከተሰጣቸው ሌላው ክፍል ጋር ይጎራበታል። የሚለያቸው በኋላ የተደረመሰው የሽቦ አጥር ብቻ ነው። የመጀመሪያው ቁስ በአንድ ደጋፊ ገና እንደተወረወረ አባቱ ‹‹ከስታዲየም እንውጣ›› ብለው ሲሞኔን አጣደፉት። ጨዋታውን ሳይመለከት መውጣትን ባለመፈለጉ አባቱን ለመከተል አመነታ። በመዘግየታቸው ሁለቱም በሺዎች ተገፍተው ከግድግዳ ጋር ተጣበቁ። ነፍስ ግቢ፣ ነፍስ ውጪ ሆነባቸው። ሲሞኔ የሞት ሞቱን ግድግዳ ቧጦ፣ ሽቦ ተንጠላጥሎ በስታዲየሙ መፀዳጃ ቤት ጣሪያ ላይ ወጣ። ከዚያም አባቱን ከመታፈግና መረጋገጥ ለማዳን ከላይ ሆኖ ወደ ታች እጃቸውን ይዞ መጎተቱን ቀጠለ።‹‹አብሮን እንደነበረ የማናውቀው አንዳች ጉልበት በዚያች ሰዓት መጣልን። አባቴን ጎትቼ ወደ ጣሪያው አወጣሁት›› ይላል ሲሞኔ። ከመታፈጉ ሲወጡ ግን አባት እጃቸው ይደማ ነበር። የሞት ሞታቸውን ራሳቸውን አድነው በስታዲየሙ አጠገብ ወዳለ የቀይ መስቀል እርዳታ ማዕከል ሲሄዱ ተረጋግጠውና ተጨፈላልቀው የሞቱ ደጋፊዎችን አስከሬን መሃል ራሳቸውን አገኙ፡፡ ስርዓት አልበኝነት ባስከተለው ጣጣ 32 ጣልያናዊያን፣ አራት ቤልጅየማዊያን፣ ሁለት ፈረንሳዊያን እና አንድ ብሪታኒያዊ ህይታቸውን አጡ። የልጅ ልጆች ያሏቸው ኦቴሎ ሎረንቲን የ‹‹Z›› ታዳሚ ነበሩ። ከልጃቸው ሮቤርቶ እና ከሁለት የልጅ ልጆቻቸው አንድሪያ እና ግራኒ ጋር በዚሁ ቦታ የፍፃሜውን ጨዋታ ለመመልከት ወደ ሄይሰል መጥተዋል። ከእነርሱ ጋር የህክምና ባለሙያው ሮቤርቶ ሎረንቲን ነበር። በመገፋፋቱና በመረጋገጡ ሰዎች በመጎዳታቸው ሮቤርቶ የሙያውን ለማበርከት ጉዳተኞችን ሊታደግ ወደኋላ ቀረ ። ‹‹እንግሊዛዊያኑ የማይወረውሩብን ነገር የለም። ሮቤርቶ!… ሮቤርቶ!… ና ውጣ!… እንሂድ! ብዬ ተጣራሁ። ብረት፣ የአርማታ ፍንካችና ድንጋይ ወደኛ ይዘንባል። ህፃናትና ሴቶች አብረውን አሉ። እየተገፋን፣ እየተገፋን ከግድግዳው ጥግ ደረስን። ከዚያ ራሴን በቅፅበት በመጫወቻ ሜዳው ላይ አገኘሁት›› በማለት ኦቴሎ ክፉውን ቀን ያስታውሳሉ።‹‹ወደ ደረጃዎቹ እያየሁ ሮቤርቶን መጣራቴን ቀጠልኩ። በፍለጋዬ መሃል የእህቴ ልጅ አንድሪያ ጭንቅላቱን በሁለት እጁ ይዞ ከድንጋጤ ጋር ቆሞ አየሁት። የጠራሁት ሮቤርቶ በስታዲየሙ መቀመጫ ደረጃ ላይ ተንጋሏል። ጆሮዬን ከደረቱ ላይ አጣብቄ አዳመጥኩ። የሚሰማኝ የራሴው የልብ ትርታ ብቻ ነበር። ህይወቱ አልፏል። ይህን ሳደርግ የቴሌቪዥን ካሜራ ባለሙያ ይቀርፀኛል። በኋላም የሞተውን ልጄን ስፈልግ የሚያሳየውን ፊልም በቴሌቪዥን አየሁት።›› ይላሉ፡፡ሮቤርቶ ሌሎችን ለመርዳት ሲል ህይወቱን አጥቷል። የደጋፊዎች አስከሬን ተሰብስቦ በጊዜያዊ ማዕከል ተከማቸ። አባት ኦቴሎ ሌሊቱን የልጃቸውን አስከሬን ለመረከብ ወደ ሆስፒታል ሄዱ። ‹‹በሆስፒታል ከሶስት ሰዓታት በላይ አስጠበቁን። ሌሊት 9:00 ሰዓት ላይ የልጄን አስከሬን አየሁት። የአንገቱ ሃብልና የጋብቻው ቀለበት ተወስደዋል። ‹ማንነቱን ለመለየት ብለን ነው ያወለቅናቸው› የሚል ምክንያት ሰጡኝ። ነገር ግን በልጄ ጌጣጌጥ ላይ ስሙ አልተፃፈባቸውም ነበር። ሰርቀዋቸው ነው›› ይላሉ።የሞት ትራፊዎቹ ደጋፊዎች ስለሄይሰል ማውራት አይፈልጉም። ለብዙ ጁቬዎች የሄይሰል ስም ነውር ነው። ከአደጋው በኋላ አንድ ደጋፊ የመናገር አቅም አጥቶ ደንዝዞ ቃል ለመተንፈስ ወራት አስፈልገውታል። ሌላው ደጋፊ ደግሞ ከጓደኛው ጋር ወደ ስታዲየሙ መጥቶ በአደጋው ያጣውን ባልንጀራውን አስከሬን ከሙታኑ መሐል አገኘው። በሃዘን ወደ መኪናው ቢመለስም የመኪናው ቁልፍ እርሱ ዘንድ እንዳልሆነ አስታወሰ። በአስከሬኑ ኪስ ውስጥ ነበር። በወቅቱ የ14 ዓመት ታዳጊ የነበረ ደጋፊ የአባቱን መሞት ሳያውቅ በሰዎች ላይ በእግሩ ተረማምዶ ራሱን ማዳኑን ዛሬ በፀፀት ያስታውሳል። “ቢሆንም በባዶ እግሬ ነበርኩ። ጫማዬ በግርግሩ ከእግሬ ላይ ወልቆ ጠፍቶብኝ ነበር” እያለ ያዝናል። ከዚህ ሁሉ ትራጀዲ በኋላ ጨዋታው እንዲደረግ መወሰኑ አወዛጋቢ ነበር። በዚያ ርጉም ቀን ጨዋታው ቢቀጥልም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሊቨርፑሉ ማርክ ላውረንሰን የትከሻ ውልቃት ጉዳት ደርሶበት ተቀይሮ ወጣ። ጉዳቱ ከበድ ያለ ስለሆነ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ተወሰደ።“አምቡላንስ ውስጥ ተኝተህ ተጓዝ ተባልኩ። እኔ የፈለግኩት ደግሞ ተቀምጬ መሄድ ነበር። በድጋሚ እንድተኛ ታዘዝኩ። አሻፈረኝ አልኩኝ። እንደገና ኮስተር ባለ ትዕዛዝ እንድተኛ ተነገረኝ” ይላል። ትዕዛዙ የጠነከረበት፣ አንድ የሊቨርፑል ተጫዋች በአምቡላንስ ውስጥ መኖሩ እንዳይታወቅ ተብሎ ነበር። የመጣው ከእነ ማሊያው ነው። በላዩ ላይ የደረበበት የቱታ ጃኬትም ቀይ ነው። ማሊያውም ስለሚታይ ማንነቱን ለመለየት ቀላል ነበር። ሆስፒታል ሲደርስ በጓሮ በር አስገቡት። በሆስፒታሉ የሞቱትና ክፉኛ የቆሰሉት ደጋፊዎች ወገኖች ይገኛሉ። ሁሉም በሊቨርፑል ላይ አምርሯልና ላውረንሰን ተደብቆ መግባቱ ተገቢ ነበር። የወለቀ ትከሻውን በቦታው የመለሰው ቀዶ ጥገና ከተጠናቀቀ በኋላ ተጨዋቹን እዚያው አልጋ ላይ ተውት። አቅሉን መልሶ አግኝቶ ቀና ቢል አውቶማቲክ ጠብመንጃ የታጠቀ ወታደር በግርጌው ተቀምጦ አየ። ወታደሩም እጁን ዘርግቶ ፈጥኖ እንዲተኛ ምልክት ሰጠው። ላውረንሰንም ፈጥኖ ወደ አልጋው ተመለሰ።በነጋታው ጠዋት በባለቤቱና ከረዳት አሰልጣኞች በአንዱ ታጅቦ በድብቅ ከሆስፒታሉ ወጣ። የቤልጅየም ባለስልጣናትም አፋጥነው የሊቨርፑልን ተጨዋቾች ወደ ኤርፖርት ወስደዋቸው ወደ ሃገራቸው በረሩ። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሪት ታቸር ግፊት የእንግሊዝ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቦቹ ከአውሮፓ ውድድሮች እንዲገለሉ አደረገ። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ደግሞ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን ጥፋት ተመልክቶ የእንግሊዝን ክለቦች ለአምስት ዓመት ከማንኛውም ውድድር አገደ። ቅጣቱ ሄይሰል የተወውን የህሊና ጠባሳ ሊሽረው አልቻለም። በአንድ ደጋፊ የተጫረ ረብሻ ለብዙ ቤተሰቦች ጥልቅ ሐዘን ምክንያት ሆነ። ‹‹አዎን›› ይላል የወቅቱ የሊቨርፑል አምበል ፊል ኒል። ‹‹አዎን! በዚያ ቀን ምክንያት ከህይወት አስፈሪ ቅዠት ጋር ተጋፈጥኩ። ከጉዳቱ ለማገገምም ዘመናት አስፈለጉኝ።››አዲስ ዘመን ጥር 3/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=25533
2ffab085bcde96878ab471f77c129a1b
4abdda6159a37f75babcfa93a4eb706b
አትሌቶች የፖለቲካ መልዕክት እንዳያስተላለፉ የተሰጠው አወዛጋቢ ማሳሰቢያ
ስፖርት
በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አትሌቶች የትኛውንም ዓይነት የፖለቲካ፣ የሃይማኖት፣ የዘርና መሰል ተቃውሞና መልዕክት እንዳያስተላልፉ የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ አሳሰቡ። ፕሬዚዳንቱ የ2020 የፈረንጆች አዲስ ዓመትን በተመለከተ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ‹‹የኦሊምፒክ መድረክ በፍፁም የፖለቲካ ተቃውሞ፣የሃይማኖትና የዘረኝነት መልዕክት የሚተላለፍባቸው መሆን የለበትም›› ብለዋል። በኦሊምፒኩ ወቅት በየትኛውም ስፍራ አትሌቶች ለተፎካካሪዎቻቸው ክብር ማሳየት እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። ቶማስ ባኽ ስፖርትን የፖለቲካ መጠቀሚያ የማድረግ አዝማሚያ እየሰፋ በመጣበት በዚህ ወቅት በኦሊምፒክ መድረክ አላስፈላጊ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ምንም ጥቅም እንደሌለውና የዓለምን ሕዝቦች ከመነጣጠል የዘለለ ፋይዳ እንደማይኖረው አብራርተዋል። ‹‹የኦሊምፒክ መድረክ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው አትሌቶች ስፖርታዊ ብቃታቸውን የሚያሳዩበት እንጂ የፖለቲካ ወይም ሌላ ፕሮፓጋንዳ የሚያስተላልፉበት አይደለም›› ያሉት ቶማስ ባኽ ስፖርትን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለመታገል በመድረኩ እንደዚህ ዓይነት ማሳሰቢያዎችን ቀድሞ ማሳወቅ እንደሚገባ ተናግረዋል። አትሌቶችም ከፖለቲካ ነፃ ሆነው ለንፁህ ስፖርት ያላቸውን ወገንተኝነት ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል። በኦሊምፒክ መድረክ መሰል ተቃውሞና መልዕክት ማስተላለፍ እንደማይቻል የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባለፈው ወር ሉዛን ላይ በነበረው ስብሰባም ሃሳብ መነሳቱ ይታወሳል። ይሁን እንጂ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች የፖለቲካ ተቃውሞ፣ የሃይማኖትና የዘረኝነት መልዕክቶች በአትሌቶች በኩል ሲተላለፉ ማየት እየተለመደ መጥቷል። በተሸኘው 2019 የፈረንጆች ዓመት እንኳን በሃያ አራት ሰዓት ልዩነት ውስጥ አሜሪካውያን አትሌቶች በፓን አሜሪካን ጨዋታዎች የፖለቲካ ተቃውሞ በስፖርት መድረክ ሲያደርጉ በዓለም የውሃ ዋና ቻምፒዮና ወቅት አውስትራሊያዊው አትሌት ማክ ሆርተንና እንግሊዛዊው ዱንካን ስኮት ቻይናዊው ሰን የንግ አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚነት ጋር ተያይዞ ስሙ የሚነሳ በመሆኑ በአንድ ላይ ቆመው ሽልማት አንቀበልም ማለታቸው መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የአትሌቶች ኮሚሽን ሊቀመንበር ኪርስቴይ ኮቬንትሪ ባለፈው ጥቅምት ወር በርካታ አትሌቶች ኦሊምፒክ መድረክ ላይ የፖለቲካ ተቃውሞ ለማድረግ ተገቢው ቦታ መሆኑን እንደሚያምኑ በመናገር የአትሌቶቹን ሃሳብ መደገፋቸው በዓለም አቀፉ ኮሚቴ ውስጥ የተከፋፈለ ሃሳብ እንዳለ አሳይተዋል። ይህንንም ተከትሎ አትሌቶች በኦሊምፒክ መድረክ የፖለቲካ ተቃውሞ ማድረግ፣የሃይማኖትና የዘረኝነት መልዕክ ማስተላለፍ አለባቸው የለባቸውም የሚለው ሃሳብ አከራካሪ ሆኖ ቆይቷል። በታሪክ አጋጣሚ ግን አትሌቶች በተለያዩ ዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች የፖለቲካም ይሁን ሌሎች መልዕክቶች ማስተላለፍ የተለመደና አሁንም ድረስ ያለ ተግባር ነው። ከቅርብ ጊዜ ክስተቶች ስንነሳ የኦሊምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤቱ አሜሪካዊ አትሌት ፌንሰር ኢምቦደን በሽልማት ላይ እያለ የአሜሪካን ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር በአንድ እግሩ ተንበርክኮ በአሜሪካን ስደተኞች ላይ የሚፈጸም እንግልት፣ ዘረኝነትና የጦር መሣሪያ ዝውውርን በተመለከተ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያላቸውን አቋም ተቃውሟል። የመዶሻ ወርዋሪዋ ዌን ቤሪም በተመሳሳይ የስፖርት መድረክ የሜዳሊያ ሽልማት ሥነሥርዓት ወቅት የቀኝ እጇን ከፍ አድርጋ የአሜሪካን መንግሥት ላይ ተቃውሞ አሳይታለች። በዚህም የአሜሪካ ኦሊምፒክና ፓራሊምፒክ ኮሚቴ ሁለቱን አትሌቶች ለጥያቄ ያቀረባቸው ሲሆን ሌሎች አትሌቶችም የቶኪዮ ኦሊምፒክን ጨምሮ በሌሎች ውድድሮች ከተመሳሳይ ድርጊት እንዲቆጠቡና ድርጊቱን ፈፅመው ከተገኙ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አሳስቧል። ወደ አገራችን አትሌቶች ስንመጣ በሪዮ 2016 ኦሊምፒክ የተፈጠረውን አጋጣሚ የስፖርት ቤተሰቡ አሁንም ድረስ ያስታውሰዋል። አትሌት ፈይሳ የኦሊምፒኩ የመዝጊያ ውድድር በነበረው የወንዶች ማራቶን ላይ በመሳተፍ የብር ሜዳልያ ለመጎናፀፍ ሲበቃ ርቀቱን በ2፡09፡54 ሰዓት በማጠናቀቅ ነበር። በዕለቱ አርባ ሁለት ኪሎ ሜትሩን ከኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ ቀጥሎ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁን ሲያረጋግጥ መላው ዓለም ባልጠበቀው ሁኔታ፤በወቅቱ በአገራችን የነበረውን የፖለቲካ ሥርዓት በመቃወም እጆቹን አጣምሮ ተቃውሞውን በመግለጽ የዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕስ መሆን ችሏል። ከዚያም በኋላ በሰጣቸው መግለጫዎች ይህን አቋሙን ደጋግሞ አንፀባርቋል። እጆቹን አጣምሮ ከፍ በማድረግ የተቃውሞውን ምልክት ካሳየ በኋላ ወደ አገር ቤት ሳይመለስም ቀርቷል።በወቅቱ የነበሩ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ፈይሳ ወደ ሀገር ቤት ቢመለስ ምንም ዓይነት ችግር እንደማይገጥመው ቢገልፁም እርሱ ግን ለመመለስ አልፈቀደም ነበር። ሌታስ ራን በተባለው ታዋቂ የአትሌቲከስ ድረገፅ የቀረበ አንድ አስተያየት ፈይሳ ሌሊሳ በአሜሪካ ተወዳጅነት እያገኘ መምጣቱን ጠቅሶ ያነሳው አጀንዳ ነበር። ፈይሳ አሜሪካ ከገባ በኋላ የተለያዩ መግለጫዎችን ለአሜሪካ እና ለሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሰጥቷል። በእነዚህ መግለጫዎች የተቃውሞ ምልክቱን በተደጋጋሚ ከማሳየቱም በላይ የዓለም ግዙፍና ተጽዕኖ ፈጣሪ መገናኛ ብዙኃን ትኩረትን ማግኘት ችሏል። የዋሽንግተን ፖስት የአፍሪካ ቢሮ ኃላፊ ‹‹የ2016 ሪዮ ኦሊምፒክ ብልህ ተግባር›› ብሎ አደነቀው። ከዚያም በኋላ የቢቢሲ ጋዜጠኛ የኦሊምፒኩ እጅግ አስደናቂ ክስተት ብሎ አስተያየት ሰጠበት። አልጄዚራና ሌሎችም ታላላቅ መገናኛ ብዙኃን «ብልሁና ጀግናው ኦሊምፒያን» በማለት አሞካሽተውታል። በአሜሪካዋ የሲያትል ከተማ የሚንቀሳቀሰው የአፍሪካ አትሌቶች ማህበር በየዓመቱ የሚያካሂደውን የ5ኪሜ የጎዳና ላይ ሩጫውን በፈይሳ ሌሊሳ ጀግንነት ሰይሞታል።በ1968 እአአ ላይ በሜክሲኮ ኦሊምፒክ ላይ ሁለት ጥቁር አሜሪካውያን አትሌቶች ቶሚ ስሚዝ እና ጆን ካርሎስ ካሳዩት የተቃውሞ አቋም ጋር እሱም ባለታሪክ ሆኖ እየተጠቀሰ ቆይቷል። ሁለቱ ጥቁር አሜሪካዊ አትሌቶች በ200 ሜትር እንደቅደም ተከተላቸው የወርቅ እና የነሐስ ሜዳልያ ከተሸለሙ በኋላ በሜዳልያ ሽልማት ሥነሥርዓት ላይ የአሜሪካ መዝሙር ሲዘመር የብላክ ፓወርን የሚያንፀባርቅ ክንዳቸውን አሳይተው ነበር። በዚህ ተቃውሟቸው ሁለቱም ሜዳልያቸውን ተነጥቀዋል። ሁለቱ ኦሊምፒያኖች በወቅቱ በሽልማት ሥነሥርዓቱ ላይ ተቃውሟቸውን ክንዳቸውን በማንሳት ሲገልፁ አንድ አንድ እጃቸው ላይ ጥቁር ጓንት አድርገው፤ ጥቁር ካልሲዎች ያለጫማ አድርገው የነበረ ሲሆን በጊዜው ተንሰራፍቶ የነበረውን ዘረኝነት በመቃወም ያደረጉት ነው። ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በዘረኝነት ላይ የተቃውሞ ተግባር ማሳየታቸውን አውግዞ ቅጣት አስተላልፎባቸዋል። ሁለቱ ጥቁር አሜሪካዊ ኦሊምፒያኖች ሜዳልያዎቻቸውን ቢነጠቁም በትውልዳቸው ጀግኖች ነበሩ። በሳንሆዜ ሐውልት የቆመላቸው ሲሆን ዘጋቢ ፊልሞችም ተሰርቶላቸዋል። የኦሊምፒክ ቻርተር አንቀፅ 50 መሠረት በኦሊምፒክ መድረክ ማናቸውንም ዓይነት የፖለቲካ አጀንዳ፤ ተቃውሞ ወይንም ተግባር የማይፈቀድ እና የሚያስቀጣ መሆኑን ይደነግጋል። አዲስ ዘመን ጥር 2/2012 ዓ.ም ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=25498
77c62b39a4ed1398813f149cfd92c6b4
31e5bf9ac963fa6c7f5c24fc32d4c389
በክልሉ ያለውን ሰፊ የቱሪዝም ሀብት አልምቶ ጥቅም ላይ ማዋል ላይ ክፍተቶች መኖራቸው ተነገረ
ሀገር አቀፍ ዜና
 ሃይማኖት ከበደ አዲስ አበባ፡- በኦሮሚያ ክልል ሰፊ የቱሪዝም ሀብት ቢኖርም ሃብቱን አልምቶ በጥቅም ላይ በማዋል ረገድ ክፍተቶች እንዳለበት የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሁንዴ ከበደ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በክልሉ በርካታ የቱሪስት መስህቦች ቢኖሩም ያለውን ሀብት በሚፈለገው ልክ አልምቶ ለቱሪስቶች ምቹ ሆኖ እንዲጎበኝና ጥቅም ላይ እንዲውል አልተደረገም። ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ ያለመሰራቱም በክልሉ ያለውን የቱሪስት ፍሰት አነስተኛ አድርጎታል። እንደ አቶ ሁንዴ ገለጻ፤ ለዘርፉ ከተሰጠው አናሳ ትኩረት ባለፈ ለክልሉ የቱሪስት ፍሰት አነስተኛ መሆን ምክንያት የሆኑት ነገሮች መካከል የሰላምና የፀጥታ ጉዳይ፣ በየደረጃው ያላው ግንዛቤ አናሳ መሆን፣ በዘርፉ ዕውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሀይል እጥረት፣ የመሰረተ ልማት ችግሮችና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው። በክልሉ በአመት ውስጥ በሚከበሩበት በሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት፣ለኢሬቻ፣ ለድሬ ሼክ ሁሴንና የመሳሰሉት በዓላት ምክንያት የሀገር ውስጥ ቱሪስት ፍሰቱ ከፍተኛ ቢሆንም የውጪ ሀገር ቱሪስት ግን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል ምክትል ቢሮ ኃላፊው። ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እያደገ ያለ ዘርፍ ነው ያሉት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፤ የቱሪዝም ስራ ብዙ ወጪ የሚጠይቅ ስራ በመሆኑና ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር ዘርፍ ስለሆነ መንግስትም ከዚህ በበለጠ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባ ገልጸዋል። አሁን ላይ በክልሉ የቱሪዝም ሀብቶችን በመለየት የቱሪዝም ፍኖተካርታ ተዘጋጅቶ በመሰራት ላይ መሆኑን በመጠቆምም፤ ያለው የቱሪዝም ሀብት ለምቶና ተዋውቆ ጎብኚን እንዲስብ የተለያዩ የማስተዋወቂያ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል። እንደ አቶ ሁንዴ ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ቱሪስት እንዲመጣ የሚያደርጉት በአብዛኛው አስጎብኚ ድርጅቶች ናቸው፤ በሀገሪቱም በርካታ የአስጎብኚ ድርጅቶች ቢኖሩም የክልሉን ሀብት ፓኬጅ ውስጥ አስገብቶ መስራት ላይ ክፍተት አለ። ከቱሪስት ፍሰቱ ጋር ተያይዞ በክልሉ ትልቅ ችግር የሚነሳው ከልማት ጋር ተያይዞ ያለው ነገር ሲሆን፤ ቱሪስቶች ወደ ክልሉ ሲመጡ በቂ የሆነ የሚያድሩበትና የሚመገቡበት ስፍራ አለመኖሩ አንዱ ችግር ነው። ለአብነትም፣ በባሌ አካባቢ የተለያዩ ለዩኔስኮ የታጩ ቦታዎች ቢኖሩም፤ ወደ እዛ ሲኬድ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሉም። ስለዚህ ቱሪስት ቢሄድም የሚያድርበት የሚዝናናበት ቦታ ስለሌለ ይሄ ነገር እንደ ስጋት ይታያል። ከዚህ አንፃር በክልሉ በቀጣይ አስር ዓመታት ወደ 25 የሚሆኑ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች እንዲለሙ በዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ጠቁመዋል። በተለይ የመሰረተ ልማት ስራዎች ቅድሚያ ተሠጥቷቸው እንዲሰሩ ቢሮ ትኩት አድርጎ እየሰራ መሆኑን እና ከመንግስትና ከግል ባለሀብቱ ጋር በጋራ በመሆን ቱሪስቶች ሊጠቀሙባቸው ነገሮችን ለማሟላት እየተሰራ ነው ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37934
2f2cbf4dddbc7b4082297bc69c93ca50
30bda8c63d28386ab69be25196b788c0
ሰባት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- እነ ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዴን ጨምሮ 7 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል። ኢቢሲ እንደዘገበው፤ በሀገር ክህደት ወንጀል የተጠረጠሩት የመከላከያ የመገናኛ ሬዲዮ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት እነ ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዴን ጨምሮ 7 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ትናንት ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ ከዚህ ቀደም ሲያቀርብ ከነበረው የወንጀል ተግባራት ባሻገር “በርካታ የመገናኛ ሬዲዮ ይወገድ በሚል ምክንያት ከማዕከል አጓጉዘው ለትግራይ ልዩ ኃይል ስለማስረከባቸው ያገኘሁት ማስረጃ ያመላክታል” ብሏል። የምርመራ ቡድኑ ተጠርጣሪዎች የሰሜን ዕዝ መገናኛ ሬዲዮ እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ሰጥተዋልም ብሏል፤ ሌሎችንም በመጥቀስ ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን ጠይቋል። የተጠርጣሪ ጠበቆች የደንበኞች የወንጀል ተሳትፎ ተለይቶ አልቀረበም፣ ተጨማሪ ጊዜ ለምርመራ ቡድኑ መፈቀድ የለበትም ብሏል። ችሎቱ ትዕዛዝ ለመስጠት ለታኅሣሥ 15 ቀን 2013 ቀጥሯል።በተያያዘ ዜና፣ ከመከላከያ ሰራዊት በጡረታ የተገለሉ አባላትን በማሰባሰብና በመመልመል የትግራይ ልዩ ሃይልን እንዲቀላቀሉ ሲያደርጉ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ዘግቧል። በዘገባው እንደተመላከተው፤ ከአራቱ መካከል ከኮሎኔል ገብረመድህን ገብረመስቀል በስተቀር ቀሪዎቹ ከሰባት አመት በፊት በጡረታ የተገለሉ ሲሆኑ፤ ተጠርጣሪዎቹ ህገ መንግስቱን እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በሃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተከናወነባቸው ይገኛል። እነዚህም 1ኛ ኮሎኔል ምሩፅ በርሄ፣ 2ኛ ኮሎኔል ገብረመድህን ገብረመስቀል፣ 3ኛ ኮሎኔል ተስፋዬ ሃጎስ እና 4ኛ ኮሎኔል መብራቱ ተድላ ናቸው። መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው 12 ቀናት ውስጥ የሰራቸውን በርካታ የምርመራ ስራዎች ለችሎቱ አብራርቷል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ከሜጄር ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ (ወዲ ነጮ) ጋር በመሆን በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ኔትወርክ ግንኙነትን በማቋረጥ ተሳትፎ እንዳላቸው በሰው ምስክርና በቴክኒክ ምርመራ በማስረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል። የስምንት ሰዎችን የምስክርነት ቃል መቀበሉን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ፤ በትግራይ ክልል የፌደራል ፖሊስ አባላትና ተቋማት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ለይቶ በማስረጃ በማረጋገጥ ከመዝገቡ ጋር ማያያዙንም ጠቅሷል። ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው በመጥቀስ የወንጀል ተሳትፏቸው ተለይቶ አለመቅረቡን በማንሳት በነጻ አልያም በዋስ እንዲወጡ ጠይቀዋል። መርማሪ ፖሊስም የእያንዳንዳቸውን ተሳትፎ ያብራራ ሲሆን በዚህም 1ኛ ተጠርጣሪ በሚሰሩበት የጥበቃ ስራ ላይ የራሳቸውን አባላት መልምለው በፌደራል ተቋማት ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ እንደነበር በሰበሰብኩት ማስረጃ አረጋግጫለሁ ነው ያለው። እንዲሁም 2ኛ ተጠርጣሪ ሁለት ጊዜ በተሰማሩበት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ አባላትን አደራጅተው የትግራይ ልዩ ሃይልንእንዲቀላቀሉ ማድረጋቸውን ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሶ፤ 3ኛ ተጠርጣሪም ወንጀሉ ሲፈጸም ህክምና ላይ ነበሩ ተብሎ በጠበቃቸው ለተነሳው መቃወሚያ መርማሪ ፖሊስ ወንጀሉ ሲፈጸም ብቻ ሳይሆን ለወንጀሉ መፈጸም ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ ለፀረ ሰላም ቡድኖች መረጃ ሲያቀብሉ እንደነበርም ማስረጃ መሰብሰቡን አስረድቷል። 4ኛ ተጠርጣሪም ቢሆኑ ከሜጀር ጀኔራል ገብረመድህን ጋር በመገናኘት ከመከላከያ በጡረታ የወጡ ሰዎችን በመሰብሰብ ለትግራይ ልዩ ሃይል አባላትን ሲመለምሉ እንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡንም ነው ያስረዳው። ከዚህ ባለፈም በአዲስ አበባ ከተማ እያንዳንዳቸው ያደርጉት የነበረውን እንቅስቃሴ ማጣራቱንም ጠቅሷል። የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱ ተጠርጣሪዎቹ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት እንዳላቸው ጠቅሶ መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን በፍጥነት እንዲያከናውን ትዕዛዝ ሰጥቷል። ለተጨማሪ ምርመራም ለፖሊስ 10 ቀናትን ፈቅዷል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37931
b13e364ea43412e6c1d98be8a97ddf8b
9381533f96944e97db4dfc88fa8f54f1
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ግጭት ውስጥ እንድትገባ ወጥኖ የሚሰራ ኃይል መኖሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቅርብ አመታት ወዲህ የህዳሴው ግድብ መገንባትን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ግጭት ውስጥ እንድትገባ ወጥኖ የሚሰራ ኃይል መኖሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።አምባሳደር ዲና እንደገለጹት፤ የምስራቅ አፍሪካን ሰላም የማይሹ ኃይሎች ሱዳን እና ኢትዮጵያ መሃል ክፍተት መፍጠር እንደ ትልቅ ሎተሪ እየተመለከቱት በመሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሚጋሯቸው ድንበሮች ሰሞኑን እየተሰሙ ላሉ ግጭቶች አንዱ የዚህ ኃይል በጉዳዩ አጀንዳውን ለማስረፅ የሚሞክር እንደሆነ የጠቆሙት አምባሳደር ዲና፤ የድንበር ማካለሉ ስራ በትእግስት የሚሰራ ስለመሆኑም አንስተዋል።ባለፈው ሳምንት የተከናወኑ አበይት ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ መግለጫ የሰጠው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሰባት ሀገሮች ዲፕሎማቶችን የሹመት ደብዳቤ የተቀበሉ እንደሆነ ተገልጿል። አምስት የኤዥያ ሀገራት እና ሁለት የአፍሪካ ሀገራት በኢትዮጵያ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ በተሳካ መልኩ በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ማስተላለፋቸውም ነው የተገለፀው። የሰባት ሀገራት ዲፕሎማቶችን ሹመት ማስተናገድ ከህግ ማስከበር ጎን ለጎን ኢትዮጵያ በትክክለኛ የዲፕሎማሲ ጎዳና ላይ መሆኗን እና ከዓለም አቀፉ የዲፕሎማሲ ስርአት ጋር በመናበብ እየተንቀሳቀሰች መሆኗን ያጎላ ነው ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ። ከኢጋድ 38ኛው አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ጋር በተያያዘ አባል ሀገራቱ ችግሮቻቸውን ካለማንም ጣልቃ ገብነት በውይይት የመፍታት ባህል የማዳበር አቅጣጫ ተቀምጦ በስኬት መጠናቀቁንም አስረድተዋል። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው፤ በተለያዩ ሀገራት መሪዎችና ተቋማት በተለይም በህግ ማስከበር ዙሪያ በመንግስት ግንዛቤ በሚገባ ያስጨበጡ ስራዎች እንደተሰሩ የተገለፀ ሲሆን፤ እንደ ፊንላንድ ያሉ ሀገራት በህግ ማስከበር ጉዳይ ከመግባባት ባለፈ በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል።ከዚህ ባለፈም በዚህ ሳምንት ብቻ 327 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ መሰራቱንም አምባሳደሩ ጠቁመዋል። በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ረገድም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ስራዎች የተሰሩበት ሳምንት መሆኑን የገለፁት አምባሳደር ዲና ፤የኢትዮጵያ እና ግብፅን የንግድ ግንኙነት የተሻለ ለማድረግም የኢትዮ-ግብፅ የንግድ ስምምነቶችን የተሻለ ለማድረግም ጥረቶች ተደርገዋል ብለዋል። የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ይሰጥ የነበረውን ዘጠና ሚሊየን ዶላር ተሰረዘ ተብሎ የተወራው ሀሰት ስለመሆኑም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁን የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37932
17b5d047202eeb8d8e04365cf4057514
919b1cace0692a46e34aa1c9083bbdf6
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት ወራት 83 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸው ተነገረ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት ወራት 83 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 4 ሺህ 359 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸውን በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ አስታወቁ።በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት ወራት 83 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ የገቡ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 3 ሺህ 519 ወደ ባለሀብትነት የተሸጋገሩ አርሶ አደሮች ሲሆኑ 316ቱ ወጣቶች መሆናቸው ተገልጿል። 450ዎቹ ሀገር በቀል ባለሀብቶች እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና 74 የማስፋፊያ ጥያቄ ያቀረቡ መሆናቸውንም የተጠቆመ ሲሆን፤ ለእነዚህ አልሚዎች 35 ሺህ 920 ሄክታር መሬት ተላልፏል ያሉት አቶ አዲሱ፤ ፕሮጀክቶቹ በሙሉ አቅም ወደ ስራ ሲገቡ ለ313 ሺህ 566 ወጣቶች የስራ ዕድል ይፈጥራሉ ሲሉ አቶ አዲሱ መናገራቸውን የዘገበው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ነው፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37944
4744d84045051e757dbc087a5f13d311
d38745a7b8d8c7ddb26b0394ab1593d6
አገርን ከብተና ያዳነው ርምጃና ቀሪ የቤት ስራዎች
ሀገር አቀፍ ዜና
ጽጌረዳ ጫንያለው በሀገራችን ከለውጡ ወዲህ ከ113 በላይ ግጭቶች መከሰታቸውን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መጥቀሳቸው ይታወሳል። የነዚህ ግጭቶች ዋነኛ ዓላማ ደግሞ አገርን መበተንና የማያባራ የእርስ በርስ ግጭት መፍጠር እንደነበር ይገለጻል። ሆኖም የብልጽግና ፓርቲ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ እንደገለፀው፤ መንግስት በወሰዳቸው ጠንካራ እርምጃዎች ሃገርን ከብተና ማዳን ተችሏል። የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራንም ይህ እሳቤ ትክክል መሆኑን በመጥቀስ፤ በቀጣይ በርካታ የቤት ስራዎች እንዳሉ ይጠቁማሉ።በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና አለማቀፍ ግንኙነት መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ እንደሚናገሩት፤ አገር በብዙ መንገዶች ልትበተን እንደደረሰች የሚያሳዩ ምልክቶች ነበሩ። ከእነዚህ መካከልም እያንዳንዱ ክልል ከማዕከላዊ መንግስት ጋር ያለው ግንኙነት የተራራቀ መሆኑ አንዱ ነው። ህወሓት ወታደራዊ፣ የፋይናንስ ዘርፍና የፖለቲካ ግንኙነቱን ከፌደራሉ መንግስት በወጣ መልኩ ሲያከናውን ታይቷል። ስልጣንና ኃላፊነቱ የፌደራል መንግስት ሆኖ ሳለም በራሱ በአደባባይ የክልል መከላከያ ማቋቋሙን ሲናገር ነበር። ምርጫ ማካሄዱ፤ ከኢትዮጵያውያን ይልቅ የሌሎች አገራት ዜጎች ይሻሉኛል ማለት መጀመሩም ሌላው በመርህ ብቻ ሳይሆን በተግባርም አገር የማፍረስ ዘመቻ መኖሩን አመላካች ነበር። እንደ ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ገለጻ፤ የህወሓት ጁንታ 27 ዓመት ሙሉ ከትጥቅ እስከ ሀሳብ ማስታጠቅ ድረስ ሰርቷል። በክልሎች ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖርም አድርጓል። ከኢትዮጵያ ክልልነት ውጪ አገር እንመሰርታለን ብለው የሚነሱ አካላትን ስፖንሰር ሲያደርግም ቆይቷል። ይህ ደግሞ አገር የማፍረስ እንቅስቃሴ እንደሆነ የሚያነሱት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ የቡድኑን የሥነልቡና፤ ቁሳዊና የፋይናንስ አቅሙን ማዳከም መቻሉ ጥሩ ጅማሮና አገርን ከትልቅ አፍራሽ ሀይል መታደግ ነው። ሆኖም ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ አይደለም። ምክንያቱም የጽንፈኛው ቡድን ተላላኪዎች፣ በስልጣን የቆዘሙ ሀይላት በተለያዩ ክልሎች ይገኛሉ። ነገ ችግርም የሚሆኑበት አጋጣሚ አለ። የፌደራል መንግስት አሁን እየሰራ ያለው ስራ እንዳለ ሆኖ በዚህ ሂደት የሚረሱ ይኖሩና በማን ይነካኛል ስሜት የህወሓትን ጁንታን ሊያዩ ስለሚችሉ፣ የዚያን ጊዜ ደግሞ ይህንን ያህል ዋጋ አገር እንድትከፍል ትሆናለች የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ የህወሓት ጁንታ መንግስትን ልፍስፍስ አድርጎ መሳሉና በይፋም ከሌሎች አገራት ጦር መሳሪያ መግዛትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማድረጉ መታየቱን ገልጸዋል። ዛሬም ይህ አስተሳሰብ ካልተገራ የአገር መበተን እርሾ ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል ይላሉ። በደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ የስነዜጋና ስነምግባር መምህርና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ አቶ ሀሳቡ ተስፋ በበኩላቸው፤ ከ1983 በኋላ ያለው የፌደራል መንግስት አደረጃጀት ብሔር ተኮር መሆኑ በራሱ አገር ለማፍረስ መሰረት እንደነበር ያነሳሉ። የጋራ ማንነቶችና ታሪኮች ኮስሰው ልዩነቶች እንዲጎለብቱ አድርጓል። የአንድነት ቀን ሳይሆን የልዩነት ቀኖች እንዲከበሩም እድል ሰጥቷል። አካባቢያዊ ማንነቶች ጎልብተው የአንተ አይደለም አስተሳሰቦችም ቦታ አግኝተዋል። በዚህም አገር ለመበተን ደርሳ እንደነበር ይናገራሉ። ኢትዮጵያ የምትባለው አገር ብትኖርም ኢትዮጵያዊነት ሳይሆን አካባቢያዊነት የተለየ ትኩረት እንደተሰጠው የሚናገሩት መምህር ሀሳቡ፤ ህዝቦችም ሆነ መንግስት አገር ላይ ሳይሆን አካባቢ ላይ የሚደርስ አደጋን እየለየ እሳት እንዲያጠፋም አስገድዶታል። ስለሆነም አሁን የተጀመረው ሥራ አገርን ከመበተን ታድጓል ይላሉ። ነገር ግን ብሔርን መሰረት ያደረገ የፌደራል ሥርዓት በህግ ጭምር መፍትሄ ካላገኘ መልሶ አገር የመበተኑ እንቅስቃሴ የሚያገረሽ እንደሚሆን ይገልጻሉ። አንድን አካል በማስወገድ ብቻ አገር ማዳን አይመጣም። አብዲ ኢሌ በሱማሌ ክልል ሲያደርስ በነበረው የጥፋትና የመከፋፈል ሥራ ወቅት የተወሰደው እርምጃ የዚህ ማሳያ ነው። ከዚህ ያልተማረው የህወሓት ጁንታም ብቻዬን አገር ካልመራሁ ብሎ ለማፍረስ ሲጣጣር ሴራው መምከን ችሏል። ይሁን እንጂ ከህወሓት ጁንታ በኋላም ሌላ ላለመምጣቱ ማረጋገጫ የለም። እናም አሁን የተደረገው አገርን ከመበተን የማዳን ጅማሮ እንጂ ፍጻሜ አይደለም። ምክንያቱም አገር መመስረት ህገ መንግስታዊ መብት ነው። በመሆኑም ሥራው በህገ መንግስት ምላሽ ካላገኘ አገር እንደማይድን ይናገራሉ።መፍትሔው ጅምሩን እያደነቁ የወደፊት የአገራዊ አንድነት እየሸረሸሩ የሚሄዱ ጉዳዮችን ከመሰረቱ እያደረቁና እየፈቱ መሄድ እንደሆነ የሚገልጹት ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው፤ ፖለቲካዊ፣ ህገመንግስታዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ማለትም ማህበረሰቡን በትምህርት በስነልቦና መስራት ይገባል። የፖለቲካና የስነልቦና ትርክቶች አንድነትን ለማምጣት በሚያስችሉ ሁኔታዎችን መቅረጽ ያስፈልጋል። የህወሓት ጁንታ ኢትዮጵያዊነትን በሚያቀነቅን ህዝብ የተጠላ በመሆኑ ህዝብ እንቢ ብሎት ለመንግስት እድል እንዲሰጠው ሁሉ በህዝብ መወደድ ላይም መስራት ይገባል ይላሉ። እንደ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገለጻ፤ የለውጡ መንግስት በድርድር ቢሆን ኖሮ ከህወሓት ጋር አንድም ጥይት አይታኮስም። ነገር ግን ህወሓት የግራ ዘመሙ ጉዳይ የተጠናወተው በመሆኑ በዚህ መሸነፍ አልቻለም። ስለሆነም በቀጣይም አፈንጋጩንና ኢትዮጵያን የሚጠላውን በሚገባው ቋንቋ ማናገርና አገርን ማዳን መሰረታዊ ጉዳይ መሆን አለበት። ለስርዓቱም ሆነ ለህዝብ አደጋ የሆነ አካልን መቅኔውን መስበር ከተቻለ አገር አዳንን ሊያስብል ይችላል። አገርን ከማዳን አንጻር የተጀመረው ነገር ህዝብ ከአመጽ አይነኬ የሚባለውን ሁሉ እንደሚያሳፍር የታየበት ነው። ስለዚህም ይህንን ማስቀጠልና ትርክትንማስተካከል፣ የጋራ ራዕይን በትምህርት መገንባት፣ የፖለቲካ ትርክቶችን ገዳይ አስገዳይ ፣ በዳይ አስበዳይ ከሚለው ማውጣት፤ የጋራ የሚያደርጉትን ማጉላትና ልዩነቶችን መቀነስ እንዲሁም የነበረ ማውደምን ሳይሆን ጥሩውን መምረጥንም መማርና በተግባር ማሳየት ላይ መስራት እንደሚገባም ያስረዳሉ። አቶ ሀሳቡ እንደሚሉት ደግሞ፣ ህወሓትን ማጥፋት አገርን በዘላቂነት ከብተና የሚያድን ተደርጎ መወሰድ የለበትም። መፍትሄው ተመሳሳይ ሀሳብ ያላቸውን አካላት አሁን በተጀመረ መልኩ መግታት ነው። የአገረ መንግስት ግንባታውንም እንደ ብልጽግና ውህድ ፓርቲ መስርቶ ሁሉም ዜጋ ለአገር ያገባኛል እንዲል ማስቻል ይገባል። እናም ይህ ተግባር በቋሚነት ውጤት በሚያመጣ መልኩ መቀጠል ይኖርበታል። ከ27 ዓመት በላይ በስነልቦና የተለያየ ህዝብ ወደ ጋራ ታሪኩ መመለስ ላይ መስራትም ይገባል። በችግር ውስጥ ተሆኖ የመጣውን ለውጥ ፍርደ ገምድል ሳንሆን መደገፍና አንድነት ላይ መስራት ከሁሉም እንደሚጠበቅ አስረድተዋል። በተለይ ግን ለሁሉም መፍትሄ የሚሆነው ህገመንግስቱን በታኝ ሳይሆን ከብሔር አስተሳሰብ ወጥቶ በአንድነት ውስጥ ልዩነትን መጥኖ እያስተናገደ ማሻሻል ሲቻል እንደሆነ ይገልጻሉ። ቀደም ሲል በደርግ ሥርዓት አገር ለማፍረስ የተሞከሩ ተግባራት ታይተዋል። ከእነዚህ ውስጥም አገር ሊያፈርስ የሚችሉ ውሳኔዎች መኖራቸው የመጀመሪያው ነው። በፍርድ ቤት እንዲገደሉ ያልተወሰነባቸውን 12 ጀነራሎችን ጸረ አብዮት በማለት መረሸናቸው ለአገር መከታ የሚሆኑትን ከማሳጣቱም በላይ አገርን ለብተና የዳረገ ነበር። አገር መፍረስም መዳንም የሚችለው በእሳቤና በህግ ወይም በሀሳብ ፍሰት መሆኑ ይታወቃል። ስለዚህም በቀጣይ ሊመጡ የሚችሉ ብዙ ቂም ያረገዙ ነገሮች ይኖራሉና እነርሱን መመለስ በሚያስችል መልኩ መሆን እንዳለበት ምሁራኑ ይናገራሉ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37980
6572de1e11f6beda2c812812083283c9
fc3f99ba8e0ba8fd5826f6b7d886bb24
ባለፉት 5 ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
መላኩ ኤሮሴአዲስ አበባ፡- ባለፉት 5 ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 44 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ገለጹ። የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ ባለፉት አምስት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 44 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል። በዚህም ለማሳካት ከታቀደው 94ነጥብ3 በመቶ ማሳካት ተችሏል። የአምስት ወር አፈጻጸም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ224 ሚሊየን ብር ወይም የ20 በመቶ ብልጫ እንዳለው ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ የህዳር ወር ብቻ ከታየም የ23 በመቶ ብልጫ የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል። የኮቪድ ወረርሽኝ በአለም ላይ ከፍተኛ ጫና ባሳደረበት እና እንደ ሃገርም ሰፊ የህግ ማስከበር ስራ እየተሰራ ባለበት ወቅት ይህ አፈፃፀም ከፍተኛ መሆኑንም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት። እንደ አቶ መላኩ ማብራሪያ፤ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ከወጪ ንግድ 191 ሚሊየን ዶላር የተገኘ ሲሆን በዚህኛው ዓመት በህዳር ወር ብቻ 232 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል። ይህም ከአምናው 43 ሚሊየን ዶላር ብልጫ አለው። ይህ ውጤት እንዲገኝ በማድረግ ረገድም የግብርናው ዘርፍ አጠቃላይ የወጪ ንግድ ወደ 62 በመቶ ሲሸፍን፤ ኢንዱስትሪ 12 በመቶ እንዲሁም ማዕድን ወደ 23 በመቶ እንደሚሸፍን ተናግረዋል። ባለፉት አምስት ወራት የግብርና የወጪ ንግድ ከእቅዱ 76 በመቶ ማሳካቱን ያብራሩት አቶ መላኩ፤የኢንዱስትሪ ውጤቶች ከእቅዱ 93 በመቶ እንዲሁም ማዕድን ከመቶ ፐርሰንት በላይ ማሳካት እንደተቻለ ተናግረዋል። እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፤ በፖሊሲ ደረጃ የተሰሩ ስራዎች እና እስከ ታች ድረስ ተቀናጅቶ መሰራቱ በወጪ ንግድ ዘርፍ ለተመዘገበው መልካም አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው። አሁን የተጀመረው ሰላም የማስከበር ሁኔታ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ማሻሻያ ስራዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ሲገቡ ደግሞ የወጪ ንግድ ስራዎች ከዚህ የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ። ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፣ አነስተኛና መካከ ለኛ ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊነት፣ በሀገራችን ኢንዱስትሪዎቹን እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች፣ ችግሮቹን ለመፍታት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዲሁም መሰረታዊ ምርቶች አቅርቦትን ለማሻሻል የተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህም የሀገሪቱ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የተቀናጀ ድጋፍ አላገኙም፤ መሬት የኤሌክትሪክና ሌሎች መሠረተ ልማቶች፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የውጭ ምንዛሪ፣ የሰለጠነ የሰው ሃይል፣ የገበያ ችግር ኢንዱስትሪዎችን እየተፈታተናቸው መሆኑን ተናግረዋል። እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ የፋይናንስ አቅርቦት ችግሩን ከመፍታት አንጻር ለሊዝ ፋይናንስ 2ነጥብ2 ቢሊየን ብር፣ ለስራ ማስኬጃ 3ነጥብ2 ቢሊየን ብር፣ እንዲሁም ለፕሮጀክት ፋይናንስ 3ነጥብ2 ቢሊየን ብር በድምሩ 8ነጥብ6 ቢሊየን ብር መቅረቡን አስረድተዋል። በዚህም 1ሺ990 ኢንዱስትሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የኢንዱስትሪዎቹን የቅንጅት ችግሮችን ለመፍታትና በቂ ድጋፍ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር ውይይት መደረጉን እና ከትናንት ጀምሮ እስከ ታህሳስ 20 ድረስ ከሁሉም ክልል የካቢኔ አባላት ጋር ቀደም ሲል በነበረው አፈፃፀምና ቀጣይ በሚኖረው ላይ ውይይት እንደሚደረግ አብራርተዋል። ለኢንዱስትሪዎቹ ቋሚ ድጋፍ የሚደረግበት የጋራ አሰራር መቀየሱን እና የግንዛቤ ፈጠራ ስራም በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። እንደ አቶ መላኩ ማብራሪያ፤ ተበዳሪዎች በበቂ ዕውቀት ስራቸውን እንዲሰሩ ከኢንስቲትዩቶች ጋር የተቀናጀ ስልጠና በመስጠት ሙያቸውን እያሻሻሉ እንዲሄዱ ይደረጋል። የአቅርቦት ችግርን መፍታት ሌላኛው ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ በመሆኑም፤ የመሳሪያና የግብዓት አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት ኢግልድና ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ በአዲስ መልክ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37943
2842a65a0dca6920e9f35de4c720888f
82db90507d2ac100827b203f9f318d6d
በሱዳን ካርቱም ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የኢትዮጵያ-ሱዳን የድንበር ጉዳዮች ከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውይይት ተጠናቀቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ታህሳስ 13 እና 14 ቀን 2013 ዓ.ም በሱዳን-ካርቱም ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የኢትዮጵያ-ሱዳን የድንበር ጉዳዮች የከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውይይት ትናንት ተጠናቀቀ፡፡በውይይቱ፣ ሁለቱ ወገኖች በጋራ የድንበር አካባቢ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሃሳቦችን የተለዋወጡ ሲሆን፤ ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ በጋራ ድንበር አካባቢ በሱዳን በኩል የተደረጉ አዳዲስ ለውጦችና እንቅስቃሴዎች የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ እና መሬት ላይ ያለውን እውነታ የሚለውጡ በመሆናቸው በአስቸኳይ እንዲቆሙና ወደ ቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ ኢትዮጵያ አሳስባለች።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በገበሬዎች እና ባለሃብቶች ንብረት ላይ የደረሰ ከፍተኛ ጉዳት እና የዜጎች መፈናቀል ትኩረት እንደሚያሻው እና በአስቸኳይ መታረም ያለበት መሆኑን ኢትዮጵያ አሳስባለች።በተጨማሪም የሁለቱ አገሮች የጋራ ድንበር በተመለከተ ያሉ ማናቸውንም ዓይነት ልዩነቶች ሁሉንም በሚያስማማ መንገድ በውይይት ስለመፍታት እና የወደፊት አቅጣጫ ምን ይሁን በሚለው ዙሪያ መክረዋል።በኢትዮጵያ በኩል የድንበሩን ጉዳይ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ከቀደሙ ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መንገድ ከድንበሩ ጋር በተያያዘ የተቋቋሙና ስራቸውን ያላጠናቀቁ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን ስራቸውን እንደገና እንዲጀምሩ በማድረግ መፈታት እንዳለበት ተገልጿል። ይህም የሁለቱን አገራት ስትራቴጂካዊ እና ወንድማማቻዊ ግንኙነት እና የሁለቱን ሕዝቦች ዘላቂ ፍላጎትና ጥቅም የሚያስጠብቅ እንደሚሆን ተገልጿል።ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ ምክክራቸውን ለሁለቱ ወገኖች በሚመች ጊዜ በአዲስ አበባ ላይ ለማካሄድና ለመሪዎቻቸው የዚህኛውን ስብሰባ ሂደትና ውጤት ሪፖርት በማቅረብ በሚሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት ምክክራቸውን ለመቀጠል በመስማማት ስብሰባውን አጠናቅቀዋል። በቀጣይ ስብሰባ በአካባቢው ያሉ ለውጦችን በመገምገም የድንበር ኮሚቴዎች ስራቸውን የሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በክቡር የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ሲሆን፤ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ እና የሉዓላዊ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37982
bf7e9fd86cc55225799972b38b5c0eed
b9b061b8a07fb2412bbd4d1b0da91348
ሚሊዮን ወልዴ ወደ አትሌቲክስ አሰልጣኝነት ገብቷል
ስፖርት
ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት ባስመዘገበችበት የሲድኒ ኦሊምፒክ 5ሺ ሜትር ካሸነፈ በኋላ ደስታውን የገለፀበት የተለየ መንገድ በብዙዎች ዘንድ እስካሁንም እንዲታወስ ያደርገዋል፡፡ በወቅቱ ወጣት አትሌት የወርቅ ሜዳሊያ ማስመዝገቡ ከፍተኛ ደስታ የፈጠረ ቢሆንም በአትሌቲክስ ቤተሰቡ ዘንድ ተተኪ አትሌት መታየቱ ግን የተለየ ስሜት ያስገኘ ነበር፡፡ ነገር ግን ድንገት የታየው ተስፋ በቀጣይነቱ ሊገፋ አልቻለም፡፡ የያኔው ወጣት አትሌት ሚሊዮን ወልዴ ከሲድኒ ኦሊምፒክ ጣፋጭ ድሉ በኋላ በሌሎች ታላላቅ ውድድሮች ተጨማሪ ስኬት ያስመዘግባል ተብሎ እምነት ቢጣልበትም በውድድሮች ሳይታይ ቀርቷል፡፡ ውድድሩን እንዳጠናቀቀ ድሉን ያከበረበት መንገድ ከአብዛኛው ህዝብ የትዝታ ማህደር የማይደበዝዘውና እስካሁንም ለዓመታት መጥፋቱ የስፖርቱ ቤተሰብ ጥያቄ የሆነው የቀድሞው አትሌት ሚሊዮን ወልዴ ከጥቂት ዓመታት በፊት ለትምህርት ወደ አሜሪካን አገር እንደተጓዘ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ በጀግኖች አትሌቶቿ አራት የወርቅ፣ አንድ የብርና ሶስት የነሃስ በጥቅሉ በስምንት ሜዳሊያዎች ከምንጊዜውም የተሻለ ውጤት ባስመዘገበችበት የሲድኒ ኦሊምፒክ አንድ የወርቅ ሜዳሊያ እንዲመዘገብ ምክንያት የሆነው ሚሊዮን ለረጅም ጊዜ በትራክ እንዲሁም በተለያዩ ውድድሮች ባይታይም አሁን በባህር ማዶ ታዳጊዎችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡ አትሌቱ በተለይ የታወቀው በሲድኒው ኦሊምፒክ ይሁን እንጂ በዓለም አቀፍ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው እአአ በ1998 ሲሆን፤ በተሳተፈበት ርቀት የዓለም ወጣቶች ቻምፒዮን ነበር፡፡ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ በቤት ውስጥ ቻምፒዮና ሃገሩን በመወከል ከታላቁ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ጋር ተሳትፎ በ3ሺ ሜትር የነሃስ ተሸላሚ ሆኗል:: ራን ብሎግ ራን የተሰኘው ድረገጽ ከአትሌቱ ጋር በነበረው ቃለምልልስ አንጋፋው አትሌት በአሜሪካ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሃገር አቋራጭ አትሌት ተማሪዎችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡ ወደ አትሌቲክስ ስፖርት እንዴት እንደገባ የተጠየቀው ሚሊዮን ‹‹ልጅ እያለሁ ኳስ ነበር የምጫወተው፤ ለሌሎች ስፖርቶችም ፍላጎት ነበረኝ፡፡ እኔ ከጓደኞቼ ጋር ኳስ በምጫወትበት ሜዳ ላይም በርካታ አትሌቶች በየቀኑ ልምምድ ሲሰሩ እመለከት ነበር፤ ይህም ፍላጎት አሳድሮብኝ ወደ ስፖርቱ ልገባ ቻልኩ›› ሲል መነሻውን አስታውሷል፡፡ ፈጣን ሯጭነቱ ወደ አትሌትነት ለመሸጋገሩ ምክንያት ሲሆን፤ ወደ ክለብ ለመቀላቀልም የወሰደበት ጊዜ አጭር ነበር፡፡ የገባበት ክለብ በሃገሪቷ የተሻለ ከሚባሉት መካከል በመሆኑም በውድድር ተሳታፊ ለመሆን ረጅም ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ አሁን እያሰለጠነ በሚገኘው የሃገር አቋራጭ ውድድር ተሳታፊ የሆነው እአአ በ1996 የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ ታውን አስተናጋጅ የነበረችበት ውድድር ነው፡፡ በወቅቱ አሸናፊ በመሆኑ ከሃገሪቷ መሪ ኔልሰን ማንዴላ እጅ ሜዳሊያ የተበረከተለትን አጋጣሚም የማይዘነጋው ነው:: ሌላኛው የማይዘነጋና አስደሳቹ አጋጣሚ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያን ማጥለቅ ነው፡፡ ‹‹በህይወቴ ትልቅ ስፍራ ያለውም ነው፤ መንግስትን ጨምሮ ከበርካታ አካላትም ሽልማቶችን አግኝተናል›› በማለትም ሚሊዮን ያለፈውን ስኬት ያስታውሳል፡፡ በአሜሪካውያንና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ያሉትን ልዩነቶች እንዲጠቅስ የተጠየቀው ሚሊዮን የጎላ ልዩነት አለመኖሩን አንስቷል፡፡ ነገር ግን አሜሪካ በተሟላ የስልጠና ቁሳቁስና በሳይንሳዊ ስልጠና አትሌቶችን ስትደግፍ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በተወሰነ መልኩ ለስልጠና አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁስን ብቻ ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ልዩነት እንዳለ ያብራራል፡፡ ለወጣት አትሌቶች ስኬታማነት ልምዱን ያካፈለው አሰልጣኝ ሚሊዮን ወጣት አትሌቶች ለራሳቸው ግብ በማስቀመጥ ጠንክረው መስራትና ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ያስቀምጣል:: ይህንን የሚያደርጉ ከሆነም በብቃታቸው ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ያለውን እምነት ገልጿል፡፡ አዲስ ዘመን ጥር 6/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=25653
c90a83f56698889e148828359bcbc76b
9c318ce05c97dcd4dd8c608b7a1fd4f8
የሕግ የበላይነት ባለመከበሩ፣ እንደ አገር ከተመዘገቡት ድሎች ያመለጡት ዕድሎች በእጅጉ የበዙ መሆናቸው ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዋቅሹም ፍቃዱአዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች፣ ህዝቦቿም በአንድም በሌላ በደም የተሳሰሩ ቢሆንም ሁሉንም በእኩል የሚዳኝ፣ የአገር ልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ህግ ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት ባለፉት ዓመታት እንደ አገር ከተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያመለጡ በረከቶች በእጅጉ እንደሚያመዝኑ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ገለጹ፡፡ኮሚሽነሩ፣ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፤ አገራችን በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች በመሆኗ በቀላሉ ሰርተው የሚለወጡባት፣ አየሯ ተስማሚና ለኑሮ የምትመች ናት፡፡ ይሁን እንጂ በከፋፋይ አስተሳሰብ የተቃኘና ከአገር ይልቅ የቡድኖች ህግ ለዘመናት ገዝፎ በመቆየቱ ለሌላ መትረፍ የምትችል አገር በምግብ እንኳ ራሷን መቻል አቅቷት ለውጭ እርዳታ እጇን ስትዘረጋ ቆይታለች፡፡ ዛሬም ከውጭ እርዳታ ባለመላቀቋ እና የዚህ ምክንያቱም ተፈጥሯዊ ሳይሆን ሰው ሰራሽ እንደመሆኑ ሁሉም ዜጋ በቀጣይ በኢትዮጵያ እድል ላይ አስቦና ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል።እንደ ኮሚሽነር አበረ ገለጻ፤ ህግና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ያለፉት ታሪኮች አገርና ህዝብ ባልተስተካከለ ሚዛን የሚመራ ህግ ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት ኢትዮጵያ አስከፊ ብጥብጥና ውድመት ለማስተናድ ተገዳለች። ይህ ደግሞ አገሪቱን አቅም አሳጥቶ፣ አመት ሙሉ ምርት ማምረት የሚያስችሉ ወንዞችና ለም አፈር እያላት የስንዴ ለማኝ ሆናለች።ወደ ዘመነ መሳፍንትና ከዚያ በፊት ያሉ ዘመናት በታሪክ ሲቃኙ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከዳር ወደ መሀል አገር እንዲሁም ከመሀሉ ወደ ዳር በተደረገው እንቅስቃሴ በጋብቻ ያልተሳሰረና ያልተዋለደ እንደሌለ የሚናገሩት ኮሚሽነሩ፤ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን ጎጠኝነት በመንሰራፋቱ ምክንያት በደም መተሳሰራችን ተረስቶ፣ የህግ የበላይነትም ጠፍቶ፣ ይልቁንስ ህግ በአገር እይታ ሳይሆን በቡድን እይታ የሚተረጎምበትና የሚተገበርበት ዘመናት እንደ ነበሩ ያስረዳሉ።በቡድን የሚቃኝና የሚዳኝ ህግ ለአገር ዕድገት ትልቅ ማነቆ ስለሆነ፣ ለአገር እድገት ከታሰበ ህግ ለሁሉም ክፍት መሆን እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ ህግ ከአገርና ከህዝብ ፍላጎት አንጻር እየተሻሻለ የሚሄድ እንጂ ከቡድን ፍላጎት አኳያ የሚሻሻል ወይም የሚተው አለመሆኑን ገልጸዋል። የቡድን ህግ ደግሞ በባህሪው ቡድኑን የሚጠቅምና የሌላውን የሚጎዳ በመሆኑ አገራችንን ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈላት ባለፉት 27 ዓመታትን ማየት ብቻ በቂ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ ህግና ህገ መንግስታዊ ስርዓት ተግባራዊ እንዲሆን እንዲሁም የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፣ በመጀመሪያ ደረጃ ሰው ህግን እንደ ቡድን ወይም እንደ ብሔር ሳይሆን እንደሰው በሳይንሳዊ ዘዴ ማሰብ አለበት። ካልሆነ የአገር ህልውናና የህዝቦች አብረው የመኖር ዋስትና አደጋ ላይ ይወድቃል። ሲቀጥል፣ የፍትህ ተቋማት በሙያዊ ስነ ምግባርን በተላበሰ መልኩ ያለምንም አድሎ ህዝብና አገር በቅንነትና በፍጹም ቁርጠኝነት ማገልገል ይጠበቅባቸዋል። ህዝብም እንደ ህዝብ ህግን አውቆ ለመብቱ ዘብ የመቆም፣ ግዴታውን በአግባቡ የሚወጣ መሆን አለበት። ከሁሉም በላይ ደግሞ መንግስት ለህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ግንባር ቀደም ሚና መጫወት ይጠበቅበታል።ለላቀ የአገር ልማት እና አንድነት ያገኘነው መልካም ውጤቶች በአግባቡ ለመያዝ እንዲሁም ያመለጡን ዕድሎች እጃችን ለማስገባት የህግ የበላይነት መከበር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነር አበረ፤ ሳይንሳዊ የህግ ምክሮችና የልማት ጉዳዮችን አስመልክተው በመጽሐፉ ያሰፈሩት ሀሳቦች በተቻለ መጠን በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ህዝቡ ጋር እንዲደርስ ጥረት በማድረግ፣ አገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።ኮሚሽነሩ፣ ጊዜያዊ ችግሮች ላይ ከመጠመድ ይልቅ ዘላቂ መፍትሔ ላይ በማተኮር ያደጉ አገሮች የተከተሉት የህግ ሳይንስ በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስተሳሰር “የህግ የበላይነት ለሀገራዊ ልማት” በሚል ርዕስ የጻፉት መጽሐፍ ለአንባቢያን እንደበቃም ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37981
19fecc44d8c51ef0ddd21013b4e99ccf
880a9eb18efac4ceb4de8b9c38372c82
ከጭጋጉ ማግስት ነዋሪዎቹን የተቀበለው ገደብ ወረዳ
ሀገር አቀፍ ዜና
ክፍለዮሐንስ አንበርብርወይዘሮ ሽታዬ ወትዬ፣ ጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ጎቲቲ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት በመንግስት እና ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍና አያሌ ጥረት የሠላም አየር መተንፈስ ቢችሉም፤ በ2010 ዓ.ም የጉጂ ኦሮሞዎች እና ጌድኦዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በሕይወታቸው የማይረሳ ክፉ ጠባሳ ጥሎባቸው ያለፈ ወቅት መሆኑን ያስታውሳሉ።ወይዘሮ ሽታዬ፣ ‹‹በወቅቱ መንታ ወልጄ ነበር። ምንጩ ምንድነው የሚለውን እስከዛሬ በቅጡ በማናውቀው ግጭት አካባቢው የጦር አውድማ ሆነ። ግራ እና ቀኝ እሳት ነው፤ የማያቋርጥ ጥይት ሩምታ ነበር። አዝመራው ወደመ፣ እንስሳት ተዘረፉ። የተገኘውን ቤት ንብረት ማውደምና ማቃጠል ሆነ። ነገሩ የውጭ ወራሪ ጠላት የመጣ እንጂ ወንድማማች በሆኑ ሕዝቦች መካከል የተከሰተ ጊዜያዊ ግጭት አይመስልም ነበር። ከሰፈር ውስጥ ወንድና ሴቱ ሁሉ እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ጫካ ተሰደደ። እኔም ሁለት ልጆቼን ታቅፌ በእግሩ ድክ ድክ የሚለውን ሌላኛውን ልጄን አስከትዬ ነብሴን ለማትረፍ ወደ ጫካ ብን ብዬ ሄድኩ። መሳሪያ በየአቅጣጫው ያለማቋረጥ ይተኮስ ነበር። በዚህ ጊዜ በእግሩ ይራመድ የነበረው ሕፃን ልጄ ወደየትኛው ሥፍራ እንደተሰወረ ማወቅ አልቻልኩም፤›› ይላሉ በወቅቱ ያሳለፉትን ከባድ ፈተና ሲያስታውሱ።በ2010 ዓ.ም በተፈጠረው ግጭት የመከራው ሰለባ ከሆኑት መካከል በአሁኑ ወቅት የ12ተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አቡሽ በቀለ ሌላኛው ባለታሪክ ነው። በወቅቱ የተከሰተው ችግር ሲያስታውስ እንባውን መቆጣጠር አልተቻለውም። “እንኳንስ ሰው ሣር ምድሩ ተጨንቆ ነበር። የዓለም ገበያን ትኩረት ይስብ የነበረው የቡና ምድር፤ የደም ምድር ሆኖ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መሳለቂያ መሆናችን ያሳዝናል። ያኔ! አካባቢው ተወረረ። ቤት፣ ሳር ቅጠሉ ነደደ። የተገኘውን ሁሉ መግደልና መዝረፍ ሆነ። አቅመ ዳካማ ሴቶችና አባቶች ሳይቀሩ ፍዳቸውን አዩ። ሮጦ ማምለጥ ያልቻለ ሰው የጥይት ራት ሆነ። ይህ የሆነው ደግሞ በደስታም በመከራም ተለያይቶ በማያውቅ የአንድ አካባቢ ማህበረሰብ ሲሆን፤ የሆነው ሁኔታ ግን ያሳዝናል፤” ሲል በትካዜ የሆነውን ይናገራል።‹‹ግጭቱ ቢያልፍም የዘመናት ህልማችንን ይዞት ሄዷል። ከ30 ዓመት በፊት አባታችን የሰራው ቤትና በቤቱ ውስጥ የነበረው ንብረት በሙሉ ወድሟል። ያፈራው ጥሪት ወደ ዶጋ አመድ ተቀይሯል። ለነገ ብለን ያሰብነው ለዛሬውም ትውልድ ሳይሆን መጥፎ ታሪክ ልናወራ ተገደናል። አሁን ያለነው በፈጠሪ መልካም ምህረትና ግብረ ሰናይ ድርጅት እገዛ ነው›› የሚለው ተማሪ አቡሽ፤ በአሁኑ ወቅት ግን ትምህርቱን ቢቀጥልም አንድ ዓመት በችግሩ ምክንያት በሠላምና ስንቅ እጦት ትምህርት ማቋረጡን ተናግሯል።የገደብ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሣይ ታደሰ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ ወቅቱን ለማስታወስና የሆነውን ለመናገር “የጨከነ ልብ” ያስፈልጋል። ያ ችግር እንዳይፈጠር ግን ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማቃለል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች ሲደረጉ ነበር። በአካባቢ ችግሮች ቢኖሩ እንኳን በአባገዳዎችና የሃይማኖት አባቶች ተግሳፅ አፈንግጦ ለንብረት ውድመትና ለሕይወት መጥፋት የሚዳርግ ክስተት አልነበረም። በ2010 ዓ.ም የተፈጠረው ግን በአካባቢ ነዋሪዎች ዘንድ በእጅጉ የከፋ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ነበር።ሆኖም ችግሩ ከተከሰተ ጀምሮ አጎራባች ወረዳዎች፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት፣ ኦሮሚያ ክልል መንግስት፣ የፌደራል መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ በማድረግ ነገሮች ወደ መደበኛ ሁኔታዎች እንዲመለሱ ጥረት ተደርጓል። በአሁኑ ወቅትም ነዋሪው በመንግስትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ትብብር ወደ ቀድሞ ቀያቸው ተመልሰው ኑሯቸውን በተለመደው ሁኔታ እያስኬዱ ለዘላቂ ሠላም ውይይት እየተደረገ ነው። በወረዳው 45ሺ ተፈናቃዮች እና በ13 ቀበሌዎች የሚገኙ 4ሺ200 ቤቶች ተቃጥለው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሲሳይ፤ በተደረገው ድጋፍ የወረዳው ነዋሪዎች ወደ ሰላማዊ መንገድ ከመመለሳቸውም በተጨማሪ፣ በአደጋው 855 ቤቶችና ቤተ እምነቶች በዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ግብረ ሰናይ ደርጅት ድጋፍ ተመልሶ መገንባታቸውን ተናግረዋል። በችግሩ ለተጎዱ ቤተሰቦችም የምግብና አልባሳት ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ፣ ዶሮዎችና በጎች መሰጠታቸውንም ገልጸዋል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በአርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ አስተባባሪነት በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2013 ሳዑዲ አረቢያ 163ሺ ኢትዮጵያውያንን አገሬ ለቃችሁ ውጡልኝ ብላ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስታደርስና ኢትዮጵያውያን ሲንገላቱ የተመለከቱ ኢትዮጵያውያን ተቆርቋሪነት የተመሰረተ የበጎ አድራጎት ደርጅት ሲሆን፤ በኢትዮጵያ አራቱም አቅጣጫዎች ችግሮች ሲከሰቱ በርካታ እገዛዎችን ሲያደርግ መቆየቱን የሚናገሩት ደግሞ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት የቦርድ አባል ፕሮፌሰር አቻለምየለህ ደበላ ናቸው።ፕሮፌሰር አቻምየለህ እንደሚሉት፤ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ከምስረታው ጀምሮ በውጭ እና በአገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጰያውያን እክል በገጠማቸው ጊዜ ከአጠገባቸው አልተለየም። ለአብነትም ከቡራዩ፣ ሻሸመኔ፣ ወልቃይትና ጉራፈርዳ በግጭት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ዜጎች በሚሊዮኖች የሚቆጠር ድጋፍ አድርጓል። የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ብሎም ከዓመታት በፊት የቆሼ የቆሻሻ ክምር ተንዶ በዜጎች ላይ ላደረሰው ጉዳትም ድጋፍ አድርጓል።በጌዴኦ በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች በወርልድ ቪዥን አማካኝነት የምግብና የአልባሳት ቁሳቁስ ሲያደርግ ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም 37 ሚሊዮን 700ሺ ብር በማውጣት በእሳት የወደሙ ቤቶችንን የመገንባትና ነዋሪዎችን ወደቀያቸው የመመለስ ሥራ ማከናወኑንና በቀጣይም ለኢትዮጵያውያን ክብርና ሥም የሚመጥን በጎ ተግባር እንደሚያከናውን እና በመላው ዓለም ድጋፍ የማሰባሰብና አገር የመታደግ ሥራውን እንደሚያጠናክሩ ፕሮፌሰር አቻምየለህ አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37992
f78a65526538650c216966ca4f4d3fa1
a2c556efd098fd7a747f8d67058974ba
“የህወሓት መኖር ለትግራይ ህዝብ ኪሳራ እንጂ ጥቅም አላስገኘለትም” ሲሉ የትግራይ ተወላጅ ዳያስፖራ አባላት ገለጹ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- የህወሓት መኖር ለትግራይ ህዝብ ኪሳራ እንጂ ጥቅም አላስገኘለትም ሲሉ በአሜሪካ፤ በካናዳና በአውሮጳ የምንኖር ዳያስፖራ የትግራይ ተወላጆች ገለጹ፡፡ የፌዴራል መንግስት በክልሉ የወሰደውን የሕግ ማስከበር እርምጃ የሚደግፉ መሆኑንም በውጭ አገር የሚኖሩ (ዳያስፖራ) የትግራይ ተወላጆች የፌደራል መንግስት የጀመረውን ሕግን የማስከበር እርምጃን አስመልክቶ ባወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ ገልጸዋል፡፡በመግለጫውም፣ እኛ በአሜሪካ፤ በከናዳና በአውሮጳ የምንኖር ዳያስፖራ የትግራይ ተወላጆች በሀገራችን በተለይም የህወሓት ጁንታ በለኮሰው እሳት ሳቢያ መንግስት እየወሰደ ያለው እልህ አስጨራሽ ሕግንና ስርዓትን የማስከበር እርምጃን አስመልክቶ ማሕበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ተሰባስበን በመወያየት በተስማማንባቸው ሃሳቦች መሰረት የለውጡን አጋርነታችንን እንገልጻለን፤” ብለዋል። በመግለጫው አያይዘው እንዳመለከቱትም፤ “የህወሓት መኖር ለትግራይ ሕዝብ ኪሳራ እንጂ ጥቅም አላስገኘለትም። ህወሓት የትግራይ ሕዝብን ደም፤ ጉልበትና ሃብት ለሶስት ቡድናዊ አላማዎች ተጠቅሞበታል። በዚህም አንደኛ፤ የትግራይ ለጋ ወጣቶችን ከደደቢት እስከ አዲስ አበባ ቤተ መንግስት በትረ ስልጣን ለመጨበጥ እንደመረማመጃ አድርጎ ከተጠቀመባቸው በኋላ እንደ ሳልቫጅ ዕቃ ሜዳ ላይ እንዲወድቁ አድርጓል።ሁለተኛም፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ለጋ ወጣቶች በሁለት ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ደም ለማቃባት ሲባል በኤርትራ በሳሕል በረሃዎች የአሞራ ሲሳይ እንዲሆኑ አድርጓል። ሶስተኛ፣ በትግራይ ሕዝብ ስም የሀገራችን አንጡራ ሀብት በጠራራ ፀሐይ ለመዝረፍ ተጠቅመውበታል። ነገር ግን ከግማሽ በላይ የትግራይ ሕዝብ እስካሁን ድረስ ከውጭ የስንዴ እርዳታ ልመና አልወጣም። ወጣቱ ከዓረብ ሀገር ስደትና ውርደት አልዳነም። የሚበላው ይቅርና ሁሉም የትግራይ ከተሞች የሚጠጣ ንፁህ ውሃ እንኳን ማግኘት አልቻለም፤” በማለት አስረድተዋል።በዚህ መግለጫቸው እንዳስታወቁት፤ የትግራይ ሕዝብ የሚበላና የሚጠጣ ብቻ አይደለም ያጣው ሰላምም ጭምር የጠማው ሕዝብ ነው። ህወሓት ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በትግራይ ምድር ከሰባት ጊዜ በላይ ደማዊ ጦርነት ተደርጓል። አብዛኞቹ የጦርነቱ መንስኤ ደግሞ በማሌሊታዊና አብዮታዊ ዴሞክራሲ የደረቀ የህወሓት ጭንቅላት ያመጣው ጣጣ ነው። ከዚህ ሁሉ የተዛባና ጦረኛ ባህሪው የተነሳ የሚፈጠሩ ግጭቶች በአፈሙዝ ካልሆነ በስተቀር በዴሞክራሲ አግባብ በውይይት ለመፍታት ተፈጥሮው አይፈቅድለትም። ህወሓት ከፌዴራል መንግስት ጋር የነበረው ግጭትም በተመሳሳይ ትዕቢት፤ ንቀት፤ ድንቁርናና ጦረኛ አመለካከት የወለደው መሆኑንም ነው የገለጹት።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37983
a613edea6b4d97c1a4e52f58c69e680f
0705c1c3e2345c10d3643df3aee2e7c5
ወደ ዳካር የሚያቀኑት ቦክሰኞች ተለይተዋል
ስፖርት
ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝጅግት በቦክስ ስፖርት ኢትዮጵያን የሚወክሉ የቡጢ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ ከወዲሁ ዝግጅት ተጀምሯል፡፡ ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ ስታዲየም የዚሁ ዝግጅት አካል የሆነ ውድድርም ተካሂዷል፡፡ ከዚህ ውድድር የሚመረጡ ስፖርተኞችም ከየካቲት 9 እስከ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር በሚካሄደው የአፍሪካ ቦክስ ቻምፒዮና ላይ በመሳተፍ ወደ ቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚወስዳቸውን ውጤት ለማስመዝገብ የሚፋለሙ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው ይህ የብሔራዊ ቡድን ምርጫ የቦክስ ውድድር በአዲስአበባ ስታዲየም በደማቅ ሁኔታ ሲካሄድ በውድድሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ የቦክስ ተወዳዳሪዎች በሁሉም ኪሎ ካታጎሪ የተዘጋጁትን ውድድሮች ማሸነፍ ችለዋል።በውድድሩ ከ52 እስከ 75 ኪሎ ግራም ስድስት ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን፣ በ52 ኪሎ ግራም የአዲስ አበባ ፖሊሱ ዳዊት በቀለ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ቦክሰኛው ያዕቆብ በለጠ ጋር ተገናኝተው ዳዊት ማሸነፍ ችሏል፡፡ በ57 ኪሎ ግራም የድሬዳዋ ብቸኛ ተወካይ የሆነው አብዱልሰላም አቡበከር ከአዲስአበባ ፖሊሱ ፍቅረሰላም ያደሳ ጋር ተገናኝተው ብርቱ ፋክክር ቢያደርጉም ፍቅረሰላም ያደሳ አሸናፊ መሆን ችሏል።በ63 ኪሎ ግራም የአዲስ አበባ ፖሊስ ተወዳዳሪ አብርሃም ዓለም የፌዴራል ፖሊሱን ተጋጣሚ ሲያሸንፍ ፤ በተመሳሳይ በ69 ኪሎ ግራም የአዲስ አበባ ፖሊሱ መስፍን ብሩ የፌዴራል ፖሊሱን ቢኒያም ተስፋዬን አሸንፏል። በመጨረሻ በተካሄደው 75 ኪሎ ግራም ውድድር የአዲስ አበባ ፖሊሱ ተመስገን ምትኩ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ተጫዋች ከሆነውን ባምላኩ ደጉ ጋ ተጋጥሞ በዳኛ ውሳኔ ማሸነፍ ችሏል።በሌላ በኩል በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል በተካሄደው የ63 ኪሎ ግራም የወዳጅነት ውድድር ኢትዮጵያዊው ካሳሁን ሀይሉ እና ቢኒያም ተስፋጋብር ተገናኝተው ካሳሁን ሀይሉ በጠባብ ውጤት አሸንፏል።በውድድሩ በርካታ የቦክስ አፍቃሪያን ተገኝተው የተከታተሉት ሲሆን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሸን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን አመራሮችና ሌሎች እንግዶች በውድድሩ ቦታ በመገኘት ጨዋታዎችን ተከታትለዋል፡፡ ለአሸናፊዎችም ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር እና ሌሎች እንግዶች የሜዳልያ ሽልማት አበርክተዋል።የውድድሩ ዋና ዓላማ በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር ከየካቲት 9/2012 ዓ.ም ጀምሮ የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ ለሚካሄደው የአፍሪካ ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለመምረጥ ነው። በዚህም መሠረት በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ቦክሰኞች በቀጥታ ወደ ዳካር እንደሚያቀኑ ይጠበቃል፡፡አዲስ ዘመን  ጥር 10/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=25862
35d7eb24115e1b4a69cd9067b54611f6
eaa1748dbf96270b2511e420391a2253
የለንደን ማራቶንን የተቀላቀሉ ኮከብ ኢትዮጵያውያን
ስፖርት
አትሌት ሞስነት ገረመውና ሙሌ ዋስይሁን በመጪው ሚያዝያ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን ከዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ ጋር ከሚፎካከሩ አትሌቶች መካከል እንደሚካተቱ አረጋግጠዋል። ሁለቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን ውድድሩን አራት ጊዜ በተከታታይ ካሸነፈውና የቦታውን ክብረወሰን ከጨበጠው ኬንያዊ አትሌት ኪፕቾጌ ተከትለው በመግባት ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። ይህም ባለፈው ዓመት ከአንድ እስከ ሦስት በውድድሩ ማጠናቀቅ የቻሉ አትሌቶች ዘንድሮም የሚፎካከሩበት ዕድል እንዲፈጠር አድርጓል። አምና በውድድሩ አራተኛ፣ ካቻምና ደግሞ ሦስተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ የቻለው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሹራ ቂጣታ ቀደም ብሎ በዘንድሮው የለንደን ማራቶን እንደሚወዳደር ያረጋገጠ አትሌት ነው። ሞስነት ገረመው ባለፈው የለንደን ማራቶን ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡02፡55 የሆነውን የዓለም አምስተኛ ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን ክረምት ላይ ተካሂዶ በነበረው የዶሃው የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ማጥለቅ ችሏል። በተመሳሳይ ባለፈው ለንደን ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡03፡16 ሰዓት ያስመዘገበው ሙሌ ዋስይሁን የዓለማችን አስራ አንደኛው ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነው። እነዚህን ኮከብ አትሌቶች ጨምሮ ሌሎች በርካታ የርቀቱ ጠንካራ አትሌቶች በዘንድሮው ለንደን ማራቶን ተሳታፊ መሆናቸውን ተከትሎ ውድድሩ ከወዲሁ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ‹‹ያለፈው ዓመት ውድድር በተለይም በወንዶች የምንጊዜውም ምርጡ ነበር›› ያለው የኢሊት አትሌቶች ኃላፊ ስፔንሰር ባርደን የዘንድሮው የተሻለ እንደሚሆን ያለውን እምነት ገልጿል። በአምናው ውድድር ሞስነትና ሙሌ ኬንያዊውን ድንቅ አትሌት እስከ አርባ ኪሎ ሜትር ድረስ የፈተኑበት መንገድ ከዚህ ቀደም እንዳልገጠመው የተናገረው ባርደን ዘንድሮ እነዚህ አትሌቶች በተሻለ የራስ መተማመን ሊያሸንፉ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ አብራርቷል። ከሦስት ወራት በፊት በቬና ማራቶን አርባ ሁለት ኪሎ ሜትርን ከ2፡00 ሰዓት በታች በማጠናቀቅ የመጀመሪያው የዓለማችን አትሌት የሆነው ኪፕቾጌ ዘንድሮ በለንደን ማራቶን ማሸነፍ ከቻለ አምስት ጊዜ ያሸነፈ ብቸኛው አትሌት በመሆን ተጨማሪ ታሪክ ያኖራል። በዘንድሮው ውድድር የ2017 የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ታምራት ቶላን ጨምሮ ኬንያዊው ማሪየስ ኪፕሴሬምና ኖርዌያዊው ሶንድሬ ኖርድስታድ ተፎካካሪ መሆናቸው እንደተረጋገጠ አትሌቲክስ ዊክሊ አስነብቧል። በሴቶች መካከል በሚካሄደው ፉክክርም የዓለም ክብረወሰን ባለቤቷና ያለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊዋ ኬንያዊት ብሪጊድ ኮስጌ ከትናንት በስቲያ ተሳታፊ መሆኗን ያረጋገጠች ሲሆን በቀጣይ ጊዜዎች ሌሎቹ ተሳታፊዎች ይፋ እንደሚደረጉ ይጠበቃል። አዲስ ዘመን ጥር 7/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=25696
a021c2fd7d4e693fae9052d88d7a3e37
5e8120159b7139f47cfec0b71a66854d
የሠራተኞች የበጋ ወራት ውድድር እሁድ ይጀመራል
ስፖርት
 ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚሰራበትና በሚማርበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማዘውተር ጤናማ እንዲሆን የስፖርት ፖሊሲው ይደነግጋል። ሰራተኛው ማህበረሰብ በብዙ ተቋማት በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በስፋት ሲሳተፍ ባይስተዋልም ዓመታዊ የሰራተኞች ስፖርት ውድድሮች ላይ ሲሳተፍ ይታያል። ይህም የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን(ኢሠማኮ)በዓመት የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚያከናውናቸው የስፖርት መድረኮች ናቸው። ከነዚህ የኢሠማኮ የስፖርት መድረኮች ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውም ዓመታዊው የሰራተኞች የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር በጉልህ ተጠቃሽ ሲሆን ከታኅሣሥ ወር አንስቶ እስከ ግንቦት መጨረሻ የሚዘልቅ ነው፡፡ የሰራተኞች የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር በአገራችን ስፖርት ታሪክ መካሄድ ከጀመረ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረና አንጋፋ ከመሆኑ ባሻገር አገርን ወክለው የመካከለኛና ምስራቅ አፍሪካ(ሴካፋ) ዋንጫን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች መሳተፍ የቻሉ ስፖርተኞችን ያፈራ ስለመሆኑ ይነገራል።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት የተለያዩ ማህበራትን እያሳተፈ የሚገኘው ይህ ውድድር የመገናኛ ብዙሃን ትኩረትን ከመሳብ ባሻገር በአገራችን ከሚከናወኑ ታላላቅ የስፖርት መድረኮች አንዱ እየሆነ ይገኛል፡፡ በዚህም አዳዲስ ተሳታፊ ማህበራትን ወደ ውድድር ከመሳብ በዘለለ ቀድሞ ዝነኛ ተፎካካሪ የነበሩና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከውድድሩ የራቁ ማህበራትን ወደ ውድድር እየመለሰ ይገኛል።የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ስቴድየም በሚጀመረው የበጋ ወራት ውድድርም አርባ አዳዲስና ነባር የሰራተኛ የስፖርት ማህበራት ተሳታፊ ለመሆን ዝግጅታቸውን እንደጨረሱ የኢሠማኮ የስፖርት ክፍል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ካሳ ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡ በሁለት ዲቪዚዮን ተከፍሎ በሚካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ከሰላሳ ማህበራት የተውጣጡ 750 ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉ ይሆናል፡፡ በሴቶች ቮሊቦል ውድድር ከአስራ አምስት ማህበራት 253 ተወዳዳሪዎች ሲሳተፉ በወንዶች ከአስር ማህበራት 150 ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ በሴቶች ቼስ ውድድር ከአምስት ማህበራት 25፣ በወንዶች ከአስር ማህበራት 50 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ፡፡ በጠረጴዛ ቴኒስ ወንዶች ከአስር ማህበራት 50 ተሳታፊዎች፣ በሴቶች ደግሞ ከዘጠኝ ማህበራት 45 ተሳታፊዎች ይወዳደራሉ፡፡ በወንዶች ዳርት ውድድር ከአስራ ሁለት ማህበራት 60 ተሳታፊዎች፣ በሴቶች ከስምንት ማህበራት 40 ተሳታፊዎች ይፎካከራሉ፡፡ በከረንቦላ ውድድር ከአስራ ሁለት ማህበራት የተውጣጡ 60 ተወዳዳሪዎች፣ በገበጣ ውድድር ከአስር ማህበራት 50 ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ በአትሌቲክስ ወንዶች ከስምንት ማህበራት 144 ተወዳዳሪዎች፣ በሴቶች ከሰባት ማህበራት 126 ተወዳዳሪዎች ተፎካካሪ ይሆናሉ፡፡ አዝናኝ በሆነው የገመድ ጉተታ ውድድር በወንዶች ከአምስት ማህበራት 75 ተፎካካሪዎችና በሴቶች ከሦስት ማህበራት 45 ተወዳዳሪዎች ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ በአጠቃላይ በውድድሩ 1945 የሰራተኛ ስፖርት ማህበራት ተወዳዳሪዎች ተካፋይ ሲሆኑ 605 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን አቶ ዮሴፍ ገልፀዋል፡፡ ውድድሩ እሁድ ሲጀመርም ጠንካራ ፉክክር በሚደረግበት እግር ኳስ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ ሼር ካምፓኒ(ኮካ ኮላ) ጋር የመክፈቻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ የሴቶች አራት መቶ ሜትርና የወንዶች አንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር የአትሌቲክ ውድድሮችም በውድድሩ መክፈቻ እለት ይከናወናሉ።የገመድ ጉተታና እን ቁላል በማንኪያ ይዞ የመሮጥ አዝናኝ ውድድሮችም በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ተካተዋል፡፡  አዲስ ዘመን ታኀሣሥ 16 / 2012   ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=24726
7cd45f2624073fd4cd56e96ee02352f2
9f63d4d60f8d5c288db935de5a57e6bb
ከአገሩ በላይ ጃፓን ያከበረችው ኢትዮጵያዊ ጀግና
ስፖርት
1928 ፋሺስት ጣሊያን በአምባገነኑ ቤኒቶ ሞሶሎኒ እየተመራ ኢትዮጵያን ወረረ። ምስጋና ለማይዘነጉት ጀግኖቹ አርበኞቻችን ይግባና ሞሶሎኒና ግብረአበሮቹ ብዙም ሳይደላደሉ ከአገር ቤት በቅሌት ተባረሩ። ከሃያ አራት ዓመታት በኋላ ታላቁ አበበ ቢቂላ የወራሪዎቹን መዲና ሮምን በባዶ እግሩ ወሮ ዓለምን ጉድ አሰኘ፤ የምን ጊዜም የማራቶን ንጉሱ የአፍሪካውያን ኩራትና የነፃነት ተምሳሌት እንዲሁም፤ የመጀመሪያው ጥቁር የማራቶን ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ በጥቁሮቹ በጀግኖቹ መታሰቢያ ወር የካቲት የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆኖ ከሃምሳ አምስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ዋዜማ በሮም ኦሎምፒክ የፈፀመው ታሪካዊ ጀብድ በመላው ዓለም ያሉ ጥቁር አትሌቶችን በእጅጉ ያኮራና ያነሳሳ ነበር። ጷግሜ 5 ቀን 1952 አስራ ሰባተኛው የሮም ኦሎምፒያድ በታላቋ ሮም ጎዳናዎች አንድ ተዓምር ታየ፤ በርካቶች አይናቸውን ለማመን ተቸገሩ፤ በአንባገነኑ ሞሶሎኒ አገር በበርካታ ነጮች መሃል አንድ ጥቁር በባዶ እግሩ ታየ። የጥቁር ህዝቦች ተዓምርን ለመቀበል የሚተናነቃቸው ዘረኝነትን በደማቸው ያሰረፁ ነጮች እንዴት ይህ ሊሆን እንደቻለ ግራ ተጋቡ። አፍሪካውያንን ያኮራ ኢትዮጵያውያንን ከልብ ያስፈነጠዘ ታሪካዊ ድል። የአራት ዓመት ታዳጊ ሆኖ እናት አገሩ ኢትዮጵያ በጣሊያን ፋሺስት ስትወረር መጥፎውን ጊዜ ገና ባልጎለበተ የህፃን አዕምሮው የሚያስታውሰው አበበ ቢቂላ ሃያ ስድስት ዓመታት ጠብቆ ታላቁን የሮም ጎዳና በባዶ እግሩ ወሮ የማይደገመውን ታሪክ ሰራ። ከአራት ዓመት በኋላም 1956 በድጋሜ ጫማ አጥልቆ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፎ ጥቁሮች በማይደፈረው ርቀት አሁን ላይ ቁንጮ እንዲሆኑ መሰረቱን አኖረ። እሱ በከፈተው በርም ቁጥር ስፍር የሌላቸው የማራቶን አትሌቶች ለዘመናት ርቀቱን የግላቸው አድርገው አሁን ድረስ ዘልቀዋል። የሻምበል አበበ ቢቂላ የህይወት ጉዞን የተመለከተ «ቤር ፉት ረነር» የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ያበቁት እንግሊዛዊው ፓል ራምባኒ«ድንቅ ድል ነበር። በጥቁር አፍሪካዊ የተገኘ የመጀመሪያው የወርቅ ድል! በእርግጥ በዚያን ወቅት ሌሎች ጥቁር አፍሪካውያን ሯጮችም ነበሩ። ግን የሚሮጡት ቅኝ ለገዟቸው የአውሮፓ ሀገራት ነበር። የአበበ ድል ታላቅ የሆነው ለዚያም ጭምር ነው። አዎን! አበበ ለዓለም አዲስ ነገር አሳየ። የአፍሪካ ህዝብ በእኩል መወዳደርና ማሸነፍ እንደሚችል አረጋገጠ›› ሲሉ የአበበ ድል ከስፖርትም የተሻገረ መሆኑን መስክረዋል። በታሪክ ላይ ሌላ የታሪክ ካባ ጥቅምት 11 ቀን 1957 ዓ.ም. ነበር። በጃፓን ዋና ከተማ በተሰናዳው ቶኪዮ ኦሎምፒክ ሮም ላይ በባዶ እግሩ በመሮጥ የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀው አበበ ተገኝቷል። አበበ ከአራት ዓመት በፊት የአሸናፊነት ግምት ሳይሰጠው ባለድል ቢሆንም፤ በቶኪዮ ዳግም ታሪክ ስለመስራቱ ብዙዎች ጥርጣሬ አድሮባቸዋል።«ማሸነፍ ቀርቶ ውድድሩን መጨረሱ ትንግርት ነው»ሲሉ መላምት የሰጡም አልታጡም። የሮሙ ጀግና አበበ የትርፍ አንጀት ቀዶ ሕክምና ማድረጉና ሳያገግምም ከውድድር ሥፍራ መድረሱ ነበር ለዚህ ድምዳሜ እንዲበቁ ያደረጋቸው። በውድድሩ ተሳታፊ የሆኑት 15 አትሌቶች የኦሎምፒኩን የወርቅ ሜዳሊያ ለማግኘት እንዲቋምጡ አድርጓቸዋል። የሮሙን የባዶ እግር ታሪክ ቀይሮ ካልሲ አጥልቆ፣ ጫማውን ተጫምቶ በመጣው አበበ ፊት ላይ የሚነበብ የነበረው ገጽታ አስገራሚ ነበር። ከኦሎምፒኩ መዳረሻ 6 ሳምንታት ሲቀሩት የቀዶ ህክምና ማድረጉን ረስቶ ለሌላ ድል ራሱን ሲያሰናዳ ነበር የሚታየው። በዚህ መልኩ ውድድሩ የጀመረው አበበ እስከ መጀመሪያዎቹ 10 ኪሎ ሜትር የአውስትራሊያው ሮን ክለርክ ቢፎካከረውም ጥሎት በመሔድ ያለአንዳች ተቀናቃኝ በ2 ሰዓት 12 ደቂቃ 11.2 ሰኮንድ በድል አድራጊነት ፈጸመ። ከእርሱ በፊት ማንም ያልፈጸመውን፣ ከርሱም በኋላ ማንም ያላደረገውን የኦሎምፒክ ማራቶን ሁለት ጊዜ አከታትሎ የመውሰድ ታሪክ ሰራ። በጃፓናውያን ልብ ያበበው አበበበቶኪዮ ኦሎምፒክ የሜዳሊያ ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ አንድ ትልቅ ክስተት ተፈጠረ። ክስተቱ ለኢትዮጵያውያን የሚያስቆጭ ቢመስልም ፤ በጃፓናዊያን ልብ ውስጥ አበበ ቢቂላ እድሜ ልክ እንዲታተም ያደረገ ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር የጃፓን ባለሥልጣኖችም ሆኑ የሙዚቃ ባንዱ አያውቁትም ነበር። የመድረኩ አዘጋጆች ጃፓናውያን አንድ ነገር ዘየዱ። የማርሽ ባንዱ አጋጣሚውን ተጠቀመ። የጃፓንን ሕዝብ መዝሙር ለኢትዮጵያ ድል ማብሰሪያ አደረገው። ሕዝቡም ፈነደቀ። 17 ቁጥር መለያን ያጠለቀው አበበም በጃፓን ሕዝብ ልቦና ውስጥ ታተመ። ጃፓናውያን ለአበበ ክብር በቀዬያቸው ሐውልት አቁመውለታል። ጃፓናውያን ለአበበ ቢቂላ ያላቸው ጥልቅ ከበሬታን በ2006 ዓ.ም ኢትዮጵያ የመጡት የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በ1957 ዓ.ም. በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ድል ያደረገውን አበበ ቢቂላ ለማክበር ከልጁ ከየትናየት አበበ ቢቂላ ጋር በሸራተን በመገኘት ይሄንኑ ነበር ያረጋገጡት። ጠቅላይ ሚኒስትር አቤ የቶኪዮውን ሩጫ በልጅነታቸው እንደተመለከቱትና የአበበ ቢቂላ ተወዳዳሪዎቹን በርቀት ጥሎ ማሸነፉ ትንግርት መሆኑንም መስክረዋል።በኢትዮጵያ ስፖርት ትልቅ ስፍራ ያላቸው ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ በአንድ ወቅት በጃፓናውያን ዘንድ ትልቅ ቦታ ስላለው አበበ ቢቂላ የተናገሩትን እንጥቀስ። ‹‹…አበበ በድጋሚ በማሸነፉ በጃፓን ሕዝብ ለዘለዓለም የማይረሳ ትዝታ ትቷል። ዛሬም በጃፓን እንደጣዖት ይመለከቱታል። ማራቶን በጃፓን ውስጥ እንዲህ ተወዳጅ ሊሆን የቻለው ከአበበ ቢቂላ ድል በኋላ ነው። አሁንም ይኸው መንፈስ ቀጥሏል።››ብለው ነበር። በቶኪዮ ኦሎምፒክ በአጋጣሚ የተፈጠረችውን ታሪካዊ ክስተትን ዛሬ ያልረሱት ጃፓናውያን ከሁለት ሳምንት በፊት ጀግናውን ዘክረውታል። ጃፓናውያን የፍቅራቸው ገጸበረከት ሳይቀንስ ለሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ውድድር በጃፓን ካሳባ አድርገውለታል። በዚህ ውድድር ላይ በሁለቱም ፆታ ሃገራችንን የወከሉት አብዮት አብነትና እታለማሁ ስንታየሁ ሲያሸንፉ ውድድሩን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ እና የፌዴሬሽኑ የጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ እንዲሁም የሻምበል አበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበ ከስፍራው ተገኝተው ታድመዋል። በመድረኩ እንደተገለጸውም አበበ ቢቂላን የመዘከር ተግባሩ ከትውልድ የሚሻገር መሆኑን ጃፓናውያኑ አረጋግጠዋል።ነብይ በሀገሩ ይከበርበኢትዮጵያውያን ዘንድ አንዲት የምትታወቅ አባባል አለች «ነብይ በሀገሩ አይከበርም»።ሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት የተፈጠሩና በተሰማሩበት መስክ ሀገራቸውን ለዓለም ያስተዋወቁ ዓለም አቀፍ ጀግኖች ባለቤት መሆኗ እሙን ነው። ለአብነት ከሚጠቀሱት መካከል ደግሞ አበበ ቢቂላ ቀዳሚ ነው። ጀግናው አበበ ቢቂላ በተለይ ከሮም እስከ ቶኪዮ በሰራቸው አንፀባራቂ ታሪኮች ኢትዮጵያን በዓለም ህዝብ ዘንድ አስተዋውቋል። አበበ እስከ ህልፈት ህይወቱ ድረስ ሀገሩን ሲያገለግል የኖረ የትውልድ አርዓያ የሆነ ጀግና ነው። የአበበ የታሪክ ተወዳሽነት በኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን በዓለም ሀገራት ሳይቀር ክብርና አድናቆት የተቸረው መሆኑ ክብሩን የበለጠ ያጎላዋል። የአበበ ቢቂላን ጀግንነት በማድነቅና በማክበርም በተለየ መልኩ ጃፓናውያን ይዘክሩታል። እንደ ጃፓናውያኑ ሁሉ ጣሊያንም ለአበበ ክብሩን አልነፈገችም። የሮም ኦሎምፒክ 50ኛ ዓመትን ስትዘክር አንድ ድልድይ በስሙ ሰይማለች። ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮም በስሙ ስቴድየም አኑራለታለች። በአሜሪካን አገር በየዓመቱ የሚካሄድ ዓለም አቀፍ ሽልማትም አበበን ለማስታወስ በስሙ ተሰይሞ ይገኛል።‹‹የአፍሪካ ማራቶን አባት›› ተብሎም በዶክመንተሪው ፊልም ላይ ታሪኩ ሰፍሯል። ታላቁን ሽልማትም ልጁ የትናየት አበበ ቢቂላ ተረክቧል። በኢትዮጵያ አበበ ቢቂላን በቋሚነት የሚዘክሩ አዲስ አበባና አዳማ ከተማ የሚገኙ ስታዲየሞች በስሙ ይጠራሉ። በቅርቡ በተመረቀው አንድነት ፓርክ ውስጥ ከቆመው መታሰቢያ በቀር ለአበበ በእናት ሀገሩ የቆመለት ታሪኩን የሚመጥን መታሰቢያ ሃውልት አይገኝም። ዓለም በተለይም ጃፓናውያን ያከበሩትን ያህል ግን ኢትዮጵያ አበበን አላከበረችውም። ወይም ስሙንና ታሪኩን የሚመጥን በብዛትም በጥራትም መታሰቢያ አላበጀችለትም። አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 19/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=24870
ab832e0c93d1c02de1ab3a22c9255d34
c6207ecebf17188361e6c7e2c5b878b9
“የጉዳዮችመዘግየትና ተደጋጋሚ ቀጠሮዎች የፍትህ ተቋማቱ ያልተሻገሯቸው ችግሮች ናቸው”አቶ ፉአድ ኪያር የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት
ሀገር አቀፍ ዜና
እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ የጉዳዮች መዘግየትና ተደጋጋሚ ቀጠሮ የፍትህ ተቋማት ያልተሻገሩትና እስከ አሁንም ድረስ አብሯቸው የቀጠለ ችግር መሆኑን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ተናገሩ፡፡ፕሬዚዳንቱ አቶ ፉአድ ኪያር ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ ቀልጣፋ የፍትህ አሰጣጥ፣ የጊዜ ቀጠሮ ማሳጠርና ሌሎች የፍትህ ሂደቶች ከለውጡ በፊትም ሆነ በኋላ የፍትህ ተቋማት በፍትህ ስርዓቱ ላይ መሻገር ካልቻሏቸው ነገሮች መካከል ይጠቀሳሉ።ለዚህ ችግር መሰረታዊ መፍትሔ ማምጣትና መሻገር የሚቻለው ደግሞ፣ አንድ ጉዳይ መቼ ተጀምሮ በምን ያህል ጊዜ ማጣራትና ክርክር ከተደረገበት በኋላ መጠናቀቅ አለበት በሚለው ላይ ቀመር አውጥቶ ከዳኞች በመግባባት ምክንያታዊ ጊዜ ሰጥቶ እንዲያልቁ ማድረግ ሲቻል ነው፡፡እንደ አቶ ፉአድ ገለጻ፤ የወንጀል ጉዳዮች ፍርድ ቤት ላይ ተጀምረው እዛው የሚያልቁ አይደሉም።ይልቁንም የሌሎች የወንጀል ፍትህ አስተዳደር አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ስለሚፈልጉ ናቸው።አንድ የወንጀል ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ሲውልም ከፖሊስ ጀምሮ አቃቤ ህግ፣ ፍርድ ቤት በመጨረሻም ማረሚያ ቤት በሂደቱ ላይ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ነው።ለምሳሌ፣ ተከሳሹን በማቅረብ ጥራቱን የጠበቀ ምርመራ በመስራት ክሱን ጥርት አድርጎ በማቅረብና በፍርድ አሰጣጥ በኩል ከፍተኛ የሆነ የቅንጅት ስራ ያስፈልጋል፡፡ይሁን እንጂ በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ላይ የሚሰጠው የጊዜ ቀጠሮ መራዘም በፍርድ ቤት የስራመጓተት ብቻ ሳይሆን ፖሊስ በቶሎ ምርመራውን ያለመጨረስ߹ አቃቤ ህግ ጉዳዩን በቶሎ ወደፍርድ ቤት ያለማምጣት߹ ፍርድ ቤት ከመጣ በኋላ ደግሞ ጉዳዮች በቶሎ እልባት የሚያገኙበት የተቀመጠ የጊዜ ገደብ አለመኖር߹ መዝገብ ምስክር ማስረጃና ሌሎች ነገሮችም አልቀረቡም በማለት በተደጋጋሚ በሚሰጥ ቀጠሮ ምክንያት መዘግየቶችና ተደጋጋሚ ቀጠሮዎች እንደሚያጋጥሙ ነው አቶ ፉአድ የገለጹት፡፡በዚህ ረገድ የፍርድ ቤትን ድርሻ ወስደን የዘገዩ መዝገቦች ቅድሚያ አግኝተው እንዲሰሩ አልተመረመረም የሚባል መዝገብ እንዳይኖር ለማድረግ አብዛኞቹ ዳኞች ረዳቶች እንዲኖሯቸው ተደርጓል ያሉት አቶ ፉአድ፤በዚህም ለውጦች እየመጡ በመሆኑ ይህ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ የባለጉዳይ መስተንግዶ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ እንደ ችግር የሚነሳ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ፉአድ፤ እንዴት ነው ባለጉዳይ የምናስተናግደው? የሚለው ከሰራተኛው ጀምሮ እስከ ዳኛ ድረስ የሚሄድና መስተካከል ያለበት እንደሆነም ገልጸዋል።በዚህ በኩል ያሉ ችግሮችንም ለይቶ በጥራት በቅልጥፍናና በውጤታማነት ለመስራት የተለያዩ ሙከራዎች መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡እንደ አቶ ፉአድ ገለጻ፤ እንደመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመዝገቦች መዘግየትን ለማጥፋት እድሜያቸው አንድ ዓመትና ከዛ በላይ ያስቆጠሩ መዝገቦች ላይ ልክ እንደ መኪና ታርጋ “የዘገየ” የሚል በመለጠፍ ዳኞች ከምንም ጉዳይ በፊት ቅድሚያ ሰጥተው እንዲያዩና እልባት እንዲሰጡ በማድረግ ባለፈው ዓመት ብቻ ከ 6ሺ 800 በላይ የሚሆኑ የተከማቹ መዝገቦችን እልባት መስጠት ተችሏል። በዚህም አንድ አመትና ከዛ በላይ የቆዩ መዝገቦች ተቃለዋል።ይህም ሆኖ ግን በየቀኑ የሚከፈቱ መዝገቦች ስላሉ ችግሩ ይቃለል እንጂ የመዝገቦቹ ብዛት እንዳለ ነው፡፡በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ያሉበትን ችግሮች ለመቅረፍ “የኬዝ ፍሎው ማኔጅመንት” አሰራርን ለመከተል ያቀደ መሆኑን በመጥቀስ፤ ለምሳሌ፣ አንድ በስርቆት ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ክስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በአራት ወር ውስጥ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ለማድረግ እና ከዚህ ጊዜ በላይ የሚጠይቁ ወንጀሎችን ደግሞ ታሳቢ በማድረግ ስራዎች እንደሚሰሩም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37863
3eb6c2a3f742c948c0876c0870ea65a9
ee203e37d248fe1f584b43566f3fb36d
ሁለተኛው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንሲ የምርጥ ቡና ቅምሻ ውድድር ይፋ ሆነ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሰላማዊት ውቤአዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቡና ላኪዎችን ብቻ ሳይሆን አምራቾችን በስፋት ለማሳተፍ ያለመው ሁለተኛው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንሲ የምርጥ ቡና ቅምሻ ውድድር ይፋ ሆነ።ይሄን አስመልክቶም የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበሌ፣ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ ፕሬዚዳንት አቶ ደሳለኝ ጀና እና የውድድሩ አስተባባሪ ወይዘሪት ቅድስት ሙሉጌታ ትናንት በሄልተን ሆቴል በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ኃላፊዎቹ በሰጡት የጋራ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ዓመታዊው ሁለተኛው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንሲ የምርጥ ቡና ቅምሻ ውድድር ከትናንት ጀምሮ ይፋ ሆኗል። በውድድሩ ናሙና ከአንድ የቡና ማሳ ይቀርባል። ከአንድ የቡና ማሳ በላይ በስሙ የተመዘገበ ማሳ ያለው አርሶ አደር ቢበዛ ሁለት ዓይነት ናሙና ማቅረብ ይችላል።ቡና ላኪዎችም የቡና ባለቤት አርሶ አደሮችን በመወከል ከአንድ በላይ ናሙና ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን፤ ነገር ግን የቡናውን ባለቤት አርሶ አደር ዝርዝር አድራሻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የቡና ማህበራት የቡና ማጠቢያ ጣቢያዎች ከአንድ በላይ ናሙና ማቅረብ ይችላሉ። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቡና ቅምሻ ውድድር በ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በሚደገፈው “ፊውቸር ኢትዮጵያ ቫልዩ ቻይን አክቲቪቲ” ጋር በመተባበር መካሄዱን ያስታወሱት የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበሌ፤ ለውድድር የሚቀርበው የናሙና ቡና መጠን ሦስት ኪሎ ግራም እንደሆነም ተናግረዋል።የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ ፕሬዚዳንት አቶ ደሳለኝ ጀና በበኩላቸው እንደገለፁት፤የውድድሩ ሂደት ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ በሦስት ደረጃዎች የሚያልፍ ሲሆን፤ በብሄራዊ ባለሙያ ዳኞች፣ በዓለም አቀፍ የታወቁ የቡና ላቦራቶሪዎች ተገምግሞ ማለፍ የሚጠበቅበት መሆኑን አብራርተዋል።የዚህ ውድድር ያለፈው ዓመት የኢትዮጵያ አሸናፊ እ.ኤ.አ ጁላይ 24 ቀን 2020 በተካሄደ ጨረታ አንድ ኪሎ ግራም ቡና በ407 የአሜሪካ ዶላር መሸጡን የተናገሩት የውድድሩ አስተባባሪ ወይዘሪት ቅድስት ሙሉጌታ፤ ሂደቱ ይፋ የሆነበት መድረክ የጅማሮ ብስራት መሆኑንና በቀጣይ በተለያየ ጊዜ የሚደረጉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ በበኩላቸው፤ ውድድሩ እ.ኤ.አ በ1999 ብራዚል የተጀመረ መሆኑን እና ውድድሩ ለዓለም ገበያ የሚፈለገው ምርጥ ቡና ተወዳድሮ የሚወጣበት ዘዴ እንደሆነ ተናግረዋል። ዘዴው በተሻለ ዋጋ እንዲሸጥ ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር የተሻለ ቡና እንዲመረት የሚያበረታታ የማስታወቂያ ዘዴ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ውድድር 1ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ማስገኘቱንና በዘንድሮው ዓመትም ከዚህ የበለጠ ይገኝበታል ተብሎ መታሰቡን ተናግረዋል።በመግለጫው ላይ የተገኙት የቡና ላኪዎች ማህበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አድማሱ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ለሁለተኛ ጊዜ የሚዘጋጀው የቡና ቅምሻ ውድድር ኢትዮጵያ በዓለም ቡና ገበያ ተገቢውን ዋጋ እንድታገኝ አመቺ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። ውድድሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቡና ላኪዎችን ብቻ ሳይሆን አምራቾችን በስፋት የሚያሳትፍና የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሪ የሚያሳድግ ነው። በቡና የውጪ ንግድ ከተሰማሩት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት በማህበሩ የታቀፉ ሲሆን፤ በማህበሩ ከተመዘገቡ 270 አባላት 245ቱ በዓለም ቡና ገበያ በከፍተኛ ደረጃ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37864
de4c9d9d2ae3c0b46f55f0b29057738e
097a510b2f5bdaf32d9d5ecc7f0cac2c
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ እና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በአዲግራት ከተማ የደረሰውን ጉዳት ጎበኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በአዲግራት ከተማ የህወሓት ጁንታ ያደረሰውን ጉዳት ጎብኝተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአዲግራት ከተማ ሰላም እየተመለሰ እንደሆነም ተነግሯል፡፡ኢዜአ እንደዘገበው፤ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና በትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ የተመራ ልዑክ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲና በአዲስ መድሃኒት ፋብሪካ ላይ የደረሰውን ውድመት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡በጉብኝቱም የህወሓት ጁንታ ለህዝብ የማያስብ እና ከህዝብ አብራክ የወጣ የማይመስል የጥፋት ቡድን መሆኑን በመሰረተ ልማቶች ላይ ባደረሰው ጥፋት ማሳየቱ በግልጽ እንደታየ የተገለጸ ሲሆን፤ የህወሓት ጁንታ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዝርፊያ ከመፈጸም አልፎ የቀረው ንብረት ለመጪው ትውልድ እንዳያገለግል ሰባብሮ እና ከጥቅም ውጪ አድርጎ መፈርጠጡም ተነግሯል።በአዲግራት ከተማ በሚገኘው አዲስ መድሃኒት ፋብሪካም ተመሳሳይ ድርጊት የፈጸመ ሲሆን፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዶክተር ሙሉ ነጋ ቡድኑ በህዝብና በመንግስት ንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል፡፡ የቡድኑ የህገወጥ ድርጊት ሰለባ የነበረችው የአዲግራት ከተማ ሰላም በአሁኑ ወቅት እየተመለሰ እንደሆነም ተናግረዋል።በቀጣይ በትግራይ ክልል አጠቃላይ በህወሓት ጁንታ የደረሱ ጉዳቶች ተጠንተው ለፌዴራል መንግስት ቀርበው መፍትሄ እንዲያገኙ የሚደረግ ስለመሆኑ የተጠቆመ ሲሆን፤ የጉብኝት ልዑኩ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅና የፈረሰውን የመንግስት መዋቅር መልሶ ለማቋቋም ከአዲግራት ከተማ ወጣቶች ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡ በምክክር መድረኩ በጋራ ለመስራት የሚያስችል መግባባት ላይ ተደርሷል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37855
b8d882a01aff078db2ac894299296f37
25f7a25047223f2c685c3d9b5d8f1f6d
ሙስናን በዘላቂነት ለመከላከል ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ሙስናን በዘላቂነት ለመከላከል ህዝቡን በአግባቡ በማሳተፍ መስራት እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ገለጹ።ሀገር አቀፍ የፀረ- ሙስና መድረክ ትናንት በጎንደር ከተማ ተጀምሯል።እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ አፈጉባኤው ሙስናን መታገል በዋናነት ከራስ እንደሚጀመር አመልክተው፤ የሀገሪቱን እድገት የሚፈታተን በመሆኑ ጊዜ ሳይሰጠው ህዝቡን በአግባቡ ማሳተፍ፣ በተደራጀ አግባብ መከላከልና ማስቆም እንደሚገባ አሳስበዋል። በሀገሪቱ ሙስናን ለመታገል የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል ያሉት አፈ ጉባኤው፤ ሙስና በሀገሪቱ የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ እንዳያስተጓጉል በፅናት መታገል እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት።በመድረኩ የፌዴራል የሥነ- ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፀጋ አራጌና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ በፀረ ሙስና ዙሪያ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ታውቋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37865
5c79fa87fc512e0781ea25a3dd0d013b
a68fd598cb6283e863eb3601fc7f7dde
በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ላይ የተከሰተው ችግር የሀገራቱን ወዳጅነትና ትስስር እንደማያሻክረው ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እና የሱዳን ግንኙነት እርስ በርሱ የተጋመደ በአብሮነትና በወንድማማችነት መሰረት ላይ የተገነባ በመሆኑ ከሰሞኑ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ የተከሰተው ችግር የሀገራቱን ወዳጅነትና ትስስር እንደማያሻክረው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ። አቶ ደመቀ መኮንን ሁለተኛው የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳዮች የከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውይይት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት፤ የኢትዮ ሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት በአብሮነትና በወንድማማችነት መሰረት ላይ ለረጅም አመታት የተገነባ በመሆኑ ከሰሞኑ በድንበር ላይ የተፈጠረው ክስተት ከሁለቱ ህዝቦች ፍላጎት በተቃራኒው የሆነ ተግባር ነው። የሱዳን ወታደሮች በአካባቢው ላይ በወሰዱት እርምጃ የአርሶ አደሮች ምርት በእሳት ቃጠሎ ደርሶበታል፣ ከመኖሪያ ቦታቸውም ተፈናቅለዋል፤ ንጹሐን ዜጎች ሕይወታቸው አልፏል። በአዲስ አበባ በተደረገው ስብሰባ ላይ ውጤታማ ውይይቶች ተደርገው ከስምምነት መደረሱን ያስታወሱት አቶ ደመቀ፤ በድንበር አካባቢ ያለው የጸጥታና የሰላም ጉዳዮችን በጋራ ለመፍታትና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ መልካም ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል። በቅርቡ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ የተከሰተው ችግርም የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደማያሻክረው ነው የገለጹት። እንደ አቶ ደመቀ ገለጻ፤ ሱዳን ከዓለም አሸባሪነት መዝገብ ዝርዝር ውስጥ በአሜሪካ መንግስት በመሰረዟ ሱዳን ከአጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላት ሲሆን፤ ይሄም የህዝቦቿን ልማት እና ዕድገት እውን ለማድረግ እገዛው የጎላ ይሆናል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37922
0603eedd69c17ccca8353f068fa845d6
2c71ad83faf2bc0c36890bc46df99a28
‹‹የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪን ለማሻሻል የዘርፉን ቴክኖሎጂ ወደአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ለውጦ መጠቀሙ ፋይዳው የላቀ ነው››ዶክተር አስረግደው ካሳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀድሞው አጠራሩ የህንጻ ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር
ሀገር አቀፍ ዜና
አስቴር ኤልያስ አዲስ አበባ፡- የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪን ይበልጥ ለማሻሻልና ለማስፋፋት የዘርፉን ቴክኖሎጂ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ መጠቀሙ ፋይዳው የላቀ ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀድሞው አጠራሩ ህንጻ ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር አስረግደው ካሳ ገለጹ፡፡ዶክተር አስረግደው ካሳ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂን በተመለከተ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በአሁኑ ወቅት በዘርፉ እየወጡ የሚገኙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪን እያሻሻሉ ሲሆን፤ የሚወጡትን ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ መጠቀሙ ጠቀሜታው ጉልህ ነው። ቴክኖሎጂን መጠቀም ያለምንም ጥያቄ ፋይዳው ከፍ ያለ ስለመሆኑ አያጠራጥርም ያሉት ዶክተር አስረግደው፣ በአሁኑ ወቅት ያሉትም ቴክኖሎጂዎች ቢሆኑ የትየለሌ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።በተለይም ከምርታማነት፣ ከደህንነት፣ ከጥራት፣ ከጊዜ፣ ከዋጋ፣ የግንባታን ሂደት ቀድሞ ከማየት አንጻር እንዲሁም ከሌሎች በርካታ ሁኔታዎች አኳያ ቴክኖሎጂ ወሳኝ ስለመሆኑ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም ብለዋል።እንደ ዶክተር አስረግደው ገለጻ፤ የቴክኖሎጂው ጠቀሜታ በስራ ላይ ስህተቶች እንዳይከሰቱ ከማድረጉም በተጨማሪ ድግግሞሾች እንዳይኖርም ጭምር የሚያደርግ ነው።ቴክኖሎጂን መጠቀም መቻል የተዋጣለት ዲዛይንም እንዲኖር በማድረጉ በኩል ከፍ ያለ ሚና ይጫወታል።የስራውን ሂደት የተሳለጠ በማድረጉም በኩል ድርሻው ጉልህ ነው።ስለዚህ የተሻለ ውጤትን ለማግኘት እና የተሻለ አሰራርን ለመቀየር የሚያስችል ነው፡፡እንዲህ ሲባል ግን ትልቁ እና ማስተዋልን የሚጠይቀው ነገር ቴክኖሎጂውን ወደራሳችን ነባራዊ ሁኔታ ማምጣቱ ላይ ነው ያሉት ዶክተር አስረግደው፤ ቴክኖሎጂውን ወደአገራችን በምናመጣት ጊዜም ጥንቃቄ ማድረጉ መልካም ነው ሲሉ አስረድተዋል።ተማሪውም፣ ድርጅቶችም ሆኑ የተለያዩ ተቋማት የሰለጠነው ዓለም የሚጠቀምበትን ቴክኖሎጂ ወደራሱ በማምጣት አሰራሩን ሊያበለጽጉለት እንዲችሉ ሲያደርግ የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ መሆን ይኖርበታልም ብለዋል።እርሳቸው እንዳሉት፤ ቴክኖሎጂን አምጥቶ መጠቀሙ መልካም ነገር ነው፤ ነገር ግን የምናመጣውን ቴክኖሎጂ መልሰን ከአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ምርምር በማድረግ እና በጥናት በማስደገፍ ማላመድ ተገቢነት ያለው አካሄድ ነው።የሚመጣው ቴክኖሎጂ ከጊዜው ጋር የሚሄድ መሆኑን ማረጋገጥ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ውጤታማ የሚያደርግ ነው።ቴክኖሎጂን የማላመዱ ሂደት ከትምህርት ቤት መጀመሩ ደግሞ የፈጠራ ክህሎታቸውን ስለሚጨምር ተማሪዎችን የመፍትሄ ሰዎች ያደርጋቸዋል፡፡ተማሪዎች ገና ከመጀመሪያው ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ማመቻቸቱ ሁሌም የሌሎች አገሮችን ቴክኖሎጂ አምጥተን ከማላመድ ሊያላቅቀን በመቻሉ ነው ሲሉም አክለዋል።የሌሎች አገሮችን ቴክኖሎጂ ለማላመድ በሚደረገው ጥረት መሰላቸትን ሊያመጣ ስለሚችል ከዚህ አይነት መሰላቸት ለመላቀቅ በራስ ወደተፈጠሩ መሄድን ከወዲሁ መጀመሩ ተገቢነት አለው ብለዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37854
b0d021ed4d037a52d01b43663561fc3e
bbbc4c2d3b2fa90eddb12059dc7bd956
በየዕለቱ ከ300 በላይ የኮቪድ ታማሚዎች ወደ ጽኑ ህክምና እንደሚገቡ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
 ፋንታነሽ ክንዴአዲስ አበባ፡- በየቀኑ ኮቪድ-19 ከሚገኝባቸው ሰዎች ውስጥ ከ300 በላይ የሚሆኑት ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን እና ከእነዚህ ውስጥ እስከ 50 የሚደርሱት የመተንፈሻ አካልን የሚረዳ ማሽን የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ይህን ተከትሎም ለስድስት ወራት የሚቆይ ኮቪድ 19ን የመከላከል ንቅናቄ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በኮቪድ የሚሞቱና ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በየቀኑ ቫይረሱ ከሚገኝባቸው ሰዎች ውስጥ ከ300 በላይ የሚሆኑት ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ፤ ከዚህ ውስጥ ከ40 እስከ 50 የሚሆኑት ደግሞ የመተንፈሻ አካልን የሚረዳ ማሽን ያስፈልጋቸዋል፡፡ በየቀኑ የሚገለጸው ቁጥር ምርመራ ከተደረገላቸው ውስጥ ብቻ ስለሆነ ትክክለኛውን ቁጥር አያሳይም ያሉት ዶክተር ደረጀ፤ አሁን እየተመረመረ ያለው በቀን ከ4ሺ እስከ 5ሺ ሰው በመሆኑ አሁን ከሚመረመረው በሶስትና አራት እጥፍ ከፍ ቢደረግ ውጤቱም በተመሳሳይ ከፍ ማለቱ እንደማይቀር ተናግረዋል። ከዚህ በፊት በሽታው የሚገኘው በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እንደነበረና አሁን ላይ ግን ከ900 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች እንደተገኙም ገልጸዋል። ከዚህ በፊት ከተመረመረው ከሶስት እስከ አራት በመቶ ብቻ ቫይረሱ የሚገኝባቸው እንደነበርና አሁን ግን ከ10 እስከ 15 በመቶ በአንዳንድ ቦታዎች ላይም ከ30 እስከ 40 በመቶ ቫይረሱ እየተገኘ መሆኑንም ተናግረዋል። እንደ ዶክተር ደረጀ ገለጻ፤ ቀደም ሲል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ ትልቅ ስራ ባይሰራ ኖሮ አሁን ላይ የሚኖረው ከዚህ የከፋ ይሆን ነበር። የአዋጁን መነሳት ተከትሎ ምክር ቤቱ መመሪያዎች እንዲወጡ በመፍቀዱ መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ተደርጓል። በመመሪያው ላይ ለህብረተሰቡና ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ መፈጠሩንም ተናግረዋል። የጤና ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ ተመስርተውም በትራንስፖርት፣ በትምህርትና ቱሪዝም ዘርፎችም የየራሳቸውን መመሪያ እንዲያዘጋጁ የተደረገ ቢሆንም፤ በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ አልተደረገም። በመመሪያው ላይ የህግ ክፍተት ባይኖርም፤ መተግበር ላይ ግን ክፍተቶች ተስተውለዋል። በህብረተሰቡ ዘንድ ህግን ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ተነሳሽነት እየታየ አለመሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ከታች እስከ ላይ ያለው የመንግስት አመራርም መመመሪያውን እያንዳንዱ ቦታ ላይ እንዲተገበር በማድረግ በኩል ቸልተኝነትና የቁርጠኝነት ማነስ እንደሚስተዋልበት አስረድተዋል። የሃይማኖት ተቋማትና ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ በወጣው መመሪያ መሰረት ምን እየተሰራ እንደሆነ መከታተል ላይ ክፍተት መኖሩንም ገልጸዋል። ጸጥታ አካላትም መመሪያውን መሰረት አድርገው ህጉ ተፈጻሚ እንዲሆን በማድረግ በኩል ብዙ እንዳልሰሩበት አስረድተዋል። እንደ ዶክተር ደረጀ ገለጻ፤ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ የስድስት ወራት ኮቪድን የመከላከል እቅድ አዘጋጅው ወደ ስራ ሊገቡ ተዘጋጅተዋል። በተለይ ማንም ሰው ማስክ ካላደረገ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት አገልግሎት እንደማያገኝ አውቆ እንዲስተካል፤ የህግ አካላትም በዚህ ላይ እንዲሰሩና የራሳቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ፤ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎችን ማጠናከርና ህብረተሰቡን ለማስተማርና ለማንቃት ስለተወነ በቅርቡ ወደ እንቅስቃሴ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ሚዲያዎች ከዚህ በፊትም በራሳቸው ተነሳሽነት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ አሁንም የሚችሉትን እንዲያደርጉና መንግስትም የሚችለውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅበት በመጠቆም፤ ወቅታዊ ነገር እንዳለ ሆኖ ኮቪድ ደግሞ ሌሎችንም ነገሮች ሊያበላሽ ስለሚችል ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሚያስፈልግ በመሆኑ በየደረጃው ካሉ የመንግስት የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር የተጠናከረ ስራ ለመስራት በእቅዳቸው ላይ ማስቀመጣቸውን ተናግረዋል። የሰዎች የመመርመር ፍላጎት መቀነስ፣ በመመርመሪያ ኪቶች ውድነትና በላብራቶሪ ስራ ላይ በሚሰሩ ባለሙያዎች በተወሰነ መልኩ እየታየ ባለው መሰላቸት ምክንያት በየዕለቱ የሚመረመሩ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ትልልቅ አቅም ያላቸው ብዙዎቹ ከዚህ በፊት የተገዙና በእጃችን ላይ ያሉ የአሜሪካ ማሽኖች ከዛው ከካምፓኒው የሚመጣ ‹‹ቴስት ኪት›› የሚጠቀሙ በመሆናቸው ምርመራውን ለማሳደግ እንቅፋት ሆኗል ብለዋል። ከዛ ውጪ በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውሉት አገር ውስጥ የሚመረተው ‹‹ቴስት ኪት›› መሆኑን እና ያሉ ችግሮችን በመፍታት በቀጣይ እስከ 10ሺ የሚደርስ ዕለታዊ ምርመራ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። እንደ ዶክተር ደረጀ ገለጻ፤ የጤና ባለሙያዎቻችን ምንም የተለየ ክፍያ ሳይከፈላቸው ለረጅም ጊዜ በርካታ ስራዎችን ሰርተዋል። በፌዴራል ደረጃ ቀጥታ በኮቪድ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የተወሰኑ ድጋፎችን ለማድረግ ተሞክሯል። በክልል ደረጃ ግን ብዙ ገንዘብም ስለሚጠይቅ በሙላት አልተደረገም። ባለሙያዎች ስራ ላይ ሲያድሩ ግን አበል ይከፈላል። እናም አቅም በፈቀደ እሱን አሻሽሎ በመክፈል ለመደገፍ እና በዚህ ላይም ከክልሎች ጋር እየተወያዩ ይገኛል። በዚህ መልኩ መቀጠል ከባድ ስለሚሆንም ብዙ የሚሰሩ ሰዎችን በማሰልጠን በፈረቃ እንዲሰሩና ባለሙያውም ሳይደክመው የተወሰነ ሰዓት እንዲሰራ ለማድረግ በሁሉም ሆስፒታሎችና ቦታ ላይ ኮቪድን አቀናጅተው እንዲሰሩ የሚደረግም ይሆናል። ከዚህ ባለፈ አዲስ አበባ ላይ የተጀመረውን ከኮቪድ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው ባለሙያዎች ከሚከፈላቸው ክፍያ ላይ ግብር እንዲቀር የማድረግ እርምጃ ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር የሚያስችል መመሪያ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርበው ውሳኔ እየጠበቁ መሆኑን በመጠቆም፤ የመድህን ኢንሹራንስ ለሁሉም የሚሰራ መሆኑንና አንድ ሰው በኮቪድ ህይወቱ ካለፈ ለቤተሰብ ካሳ እንደሚከፈል እና ከዚህ በፊት በኮቪድ ምክንያት ህይወታቸው ላለፉ ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ክፍያ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል። በአጭር ጊዜ ውስጥ በአለም ላይ ተስፋ ሰጪ የሆኑ ክትባቶች እየተገኙ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ደረጀ፤ ለአዳጊ አገራት ከአለም ጤና ድርጅት ጋር በመሆን ሌሎች ያደጉ አገሮችም እየደገፉ ክትባቱን እንዲያገኙ ስለተወሰነ ኢትዮጵያም የሚገባትን ድርሻ እንደምታገኝ ገልጸዋል። ሆኖም ክትባቱ ለሁሉም ህዝብ የሚደርስ ስላልሆነ ለጤና ባለሙያዎች፣ በበሽታው ሊጎዱ የሚችሉ የተለያዩ በሽታዎች ላሉባቸው፣ በእድሜ ለገፉና ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ እንደሚሰጥ አስረድተዋል። ሆኖም ክትባቱ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የሚተካ ስለማይሆን ክትባት መጣ ስለተባለ ለመከላከል የሚደረገው ጥንቃቄ ላይ ቸልተኝነት ማሳየት አገርን ዋጋ ሊያስከፍል ስለሚችል መጠንቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ለ1ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፤ ከ120ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ፤ 1ሺህ 860 በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን መረጃዎች ያሳያሉ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37921
6cbdfad4a3dc4b144811385eb9987d79
beee7e7893145ec105cd6cb0ad309985
ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን ሳተላይት አመጠቀች
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን ሳተላይት ማምጠቋን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ትናንት የመጠቀችው የኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሳተላይት በሰላም መምጠቋን ገልጿል፡፡ኢንስቲትዩቱ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ አሁን ያመጠቀቻት ሳተላይት ET-Smart-RSS የምትባል ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ETRSS-1 የተባለች የመጀመሪያዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ታኅሣሥ ወር 2012 ዓ.ም ማምጠቋ ይታወሳል።አምና የመጠቀችው ይህች ሳተላይትም መረጃ መላክ የጀመረች ሲሆን፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ ከግብርና ጋር የተያያዙ ጥናት እና ምርምሮችን ለመሥራት እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የመሠረተ ልማት ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደምትገኝም ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37920
109196fbfd295548867bb670973d7285
b699c0f168a68d173ffcc659dfaf81a2
ብልህ ከታናሹ ይማራል
ስፖርት
 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በእድሜም፣ በስምም፣ በተቋም ግዝፈትም ታላቅ ስለመሆኑ የሚጠራጠር አይኖርም።እነዚህ ታላቅና ታናሽ ተቋማት አሁን ያሉበት ቁመናና ተግባር ከእግር ኳሱ ጥቅም አኳያ እንደሚለያይ ብዙ ማሳያዎችን ማስቀመጥ ይቻላል።በተለይም እግር ኳሱን በዘመናዊ መንገድ ከመምራት አንፃር ታናሹ የተሻለ ስኬት እስመዘገበ በጥሩ ጎዳና ሲጓዝ ታላቁ ወደ ኋላ እየቀረ መምጣቱን በማስረጃዎች መከራከር የሚቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።ብልህ ከታናሹ ይማራልና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዘንድሮው የከተማዋ ዋንጫ ካሳካቸው ቁም ነገሮች ጥቂቶቹን እንኳን መማር ከቻለ ብዙ ነገር መለወጥ እንደሚችል ይታመናል። በእነ ኢንጂነር ሃይለእየሱስ ፍስሃ የሚመራው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ ባይሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለእግር ኳሱ የሚበጁና መደረግ ያለባቸውን ተግባራት በመፈፀም ላይ ይገኛል። ከጥቅምት 20 እስከ ህዳር 14/2012 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ስታድየም ሲካሄድ የነበረውን የአዲስ አበባ ዋንጫ ውድድርን መነሻ በማድረግ፤ በውድድሩ ተሳታፊ ለነበሩት ብቻ ሳይሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለስፖርቱ እድገት አስተዋፅኦ አላቸው ላሏቸው ግለሰቦችና ተቋማት ምስጋናና እውቅና ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ለክለቦች ከ150,000 ብር እስከ 752,000 ብር ድረስ እንደየደረጃቸው ሸልሟል።ለግለሰቦች ደግሞ ከ10,000 ብር እስከ 75,000 ብር ወጪ በማድረግ በድምሩ 2 ሚሊዮን ብር አካባቢ አበርክቷል። የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንኳን ዓመቱን ሙሉ በሚያከናውናቸው ውድድሮች በታሪክ አሳክቶት የማያውቀውን የሽልማት መጠን በማሳካት ክለቦች የሚመጥናቸውን ክብር በመስጠቱ አለማድነቅ አይቻልም።በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ፣ ደሞዝ፣ ትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች በዓመት በአማካይ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ያወጣሉ። በፕሪሚየር ሊጉ ሚሊዮኖችን ወጪ አድርገው ተሳትፈው የሚያገኙት አንዳች ነገር አለመኖሩ ግን አስገራሚ ነው።ዓመቱን ሙሉ ውድድር አድርጎ የፕሪሚየር ሊጉ ቻምፒዮን የሚሆን ክለብ 150 ሺህ ብር ይበረከትለታል። ይህ ደግሞ በአስር ቀን ውድድር ብቻ ከ750 ሺ ብር በላይ ሽልማት ከሚያስገኘው የአዲስ አበባ ዋንጫ አንፃር ምንም ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘንድሮ የአዲስ አበባ ዋንጫን በማንሳቱ ይህን ሽልማት ወስዷል።በፕሪሚየር ሊጉ ይህን ያህል የገንዘብ ሽልማት ለማግኘት ግን በተከታታይ አምስት ዓመታት ቻምፒዮን መሆን ይጠበቅበታል።ፕሪሚየር ሊጉን የሚያሸንፍ ክለብ 150 ሺህ ብር የሚሸለም ሲሆን፤ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአዲስ አበባ ዋንጫ ለተሳትፎ ብቻ 150 ሺህ ብር የመጨረሻው ሽልማቱ ነው። ከዚህ በመነሳት ብሄራዊ ፌዴሬሽኑም ሆነ አዲሱ ሊጉን የሚመራው ዓብይ ኮሚቴ ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሽልማት አሰጣጥ አንድ ነገር መማር እንዳለበት ብዙዎች ይስማማሉ። የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ታህሳስ 14 ቀን 2012 ዓ.ም በኢንተርኮንቴኔንታል ሆቴል ባዘጋጀው መድረክ እውቅና ከሰጣቸው ተቋማት አንዱ ዳሸን ባንክ ነበር። ባንኩ በአሞሌ አማካኝነት ተመልካቾች ሳይጉላሉ በየቤታቸው ሆነው ትኬት ቆርጠው ስቴድየም እንዲገቡ በማድረግ ላበረከተው አስተዋጽኦ ሽልማቱ ሊበረከትለት ችሏል። ከዚህ ሁነት በመነሳት ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ልምድ ሊወስድ የሚገባው የትኬት አሻሻጥ ሥርዓት እንዳለ መረዳት ይቻላል።የተመልካቾች ስታዲየም መግቢያ ቲኬት ሲሸጥ የነበረው በዳሸን አሞሌ አማካይነት የኦን ላይን የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ነበር። በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚስተዋሉ ረዣዥም ሠልፎችን ያስቀረ ከመሆኑ ባሻገር፣ የተጭበረበሩ (ፎርጅድ) ትኬቶች ሥራ ላይ እንዳይውሉ ያስቻለ ቴክኖሎጂ ነው። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ለ22 ዓመታት ከተጓዘበት መንገድ ለመውጣት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ለማድረግ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቶ ወደ ተግባር ሳይለውጥ መቆየቱን በማስታወስ፤ ከመዲናዋ እግር ኳስ መማር እንደሚገባውም የስፖርት ቤተሰቡ ያምናል። መስከረም 25 ቀን 2010 ዓ.ም ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በአዲስ አበባ ስታዲየም የመግቢያ ትኬት ለመቁረጥ የሚፈጠረውን ረጅም ሰልፍ የሚያስቀር ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ሊያውል እንደሆነ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። የፌዴሬሽኑ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ታፈሰ በጊዜው ቴክኖሎጂው ለዚሁ ስራ በሚከፈቱ ጣቢያዎች፣ በሞባይልና በኢንተርኔት አማካኝነት ጥቅም ላይ እንደሚውል ነበር የተናገሩት። የኢ-ቲኬት ሽያጭ አሰራሩን ተግባራዊ ለማድረግ ክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ከተሰኘ ተቋም ጋር ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። የኢ-ትኬት አገልግሎት ሽያጭ ከሚያዚያ 25 ቀን 2010 ዓ .ም ጀምሮ አገልግሎቱ በይፋ እንደሚጀመር ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፤ የተባለው መሬት ላይ ወርዶ አልታየም። የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለመገናኛ ብዙሃንና ለስፖርት ጋዜጠኞች እውቅናና ሽልማት ማበርከቱ ሌላ የሚያስመሰግነው ተግባር ነው።ይህ ተግባር በተለይ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ዝቅ ብሎ ሊቀስመው የሚገባ መልካም ተግባር እንደሆነ በብዙዎች ተነግሯል። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ለመገናኛ ብዙሃን በሩን ክፍት አድርጎ መረጃን እንደማይሰጥ በተደጋጋሚ ቅሬታ የሚሰማበት መሆኑና ፤ ጋዜጠኞችን በሚሰሩት ሥራ በማበረታታት በአብሮነት ከመስራት ይልቅ በሩን ዝግ አድርጎ የሚሰራ መሆኑ ዘወትር ሲያስወቅሰው ይሰማል። የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውድድሩን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሲያስተላልፍ የነበረውን የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክን ልዩ ተሸላሚ ያደረገ ሲሆን ፤ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ውድድሮችን በቀጥታ በማስተላለፍ ለህዝብ ተደራሽ ወደ ማድረግ አሰራር መግባት እንደሚገባው ልምድን መቅሰም እንዳለበት ያሳየ አጋጣሚ ነው።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ከሶስትና አራት ዓመት በፊት በፕሪሚየር ሊጉ የተመረጡ ጨዋታዎችን በቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ ስምምነት ላይ ደርሶ ነበር። በፕሪሚየር ሊጉ የሚደረጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ማግኘት ተከትሎ ለፌዴሬሽኑም ሆነ ለክለቦች ከስፖንሰር ሺፕ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ማግኘት የሚቻልበት አጋጣሚ ግን እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም። አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 23/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=25048