query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
7
297
category
stringclasses
6 values
passage
stringlengths
137
5.93k
link
stringlengths
28
740
f19fffecc6857bf94005a378992b12ed
0de9578024a6b5778da7b591ef0b42fd
በአማራ ክልል ከአምደወርቅ- ተኬዜ-እብናት የገጠር መንገድ ፕሮጀክት ተመረቀ
ቢዝነስ
በአማራ ክልል የተገነባው አምደወርቅ-ተኬዜ-እብናት የገጠር መንገድ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ፡፡በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ፤ የተለያዩ የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡የ124 ኪ.ሜ የሚሸፍነው መንገዱ በአካባቢው ያለውን የእንስሳትና የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ወደ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡በአካባው በኢኮኖሚ መነቃቃት ረገድ ጉልህ ሚና ከመጫወቱም ባሻገር የሁለቱን ዞኖች ህዝቦች ማህበራዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክርም ተገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/23921/
63b754c070d369ce4bc2094ba8309aa5
1fa2936c4df488ae70a537ea4b5437e2
ኢትዮጵያ እና ብሪታንያ የ120 ሚሊየን ፓውንድ የድጋፍ ስምምነት ተፈራራሙ
ቢዝነስ
ኢትዮጵያ እና ብሪታንያ የ120 ሚሊየን ፓውንድ የድጋፍ ስምምነት ተፈራራሙ፡፡ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ በዛሬው እለት ተፈራርመውታል፡፡ከድጋፉ 95 ሚሊየን ፓውንዱ የፋይናንስ ተቋማትን ለማጠናከር፣ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና ለንጹህ ውሃ አቅርቦት እንደሚውል ተገልጿል፡፡ቀሪው 25 ሚሊየን ፓውንድ ለአራተኛው ዙር የሴፍቲኔት ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል ነው ተብሏል፡፡የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና የውሃ ንጽህና አገልግሎት ድጋፉ ዓላማ በኢትዮጵያ በድርቅ በሚጠቁ አካባቢዎች የ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ያህል ዜጎችን የንጽህና እና የንጽህና አጠባበቅ ልምድ ለማሻሻል ያለመ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡ቀሪው 25 ሚሊየን ፓውንድ የሴፍቲኔት ድጋፍ በገጠር አካባቢዎች የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የምግብ ድጋፍ እና አደጋ ቅነሳ ስራ ለማከናወን የሚውል መሆኑም ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-የገንዘብ ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/23919/
62ea3a699f046144f4679b09edfca6bd
1bf23fa0c3d7bc7283e92b8035da3ce0
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማና ልዑካቸው ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ሁለቱ ወገኖች እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴዎች በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያ ውይይት አድረገዋል፡፡የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ፣ በኢትዮጵያ ያለው አገር በቀል ሪፎርምን አድንቀው፣ አገራቸው ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንግሊዝ ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡(ምንጭ:-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/31307/
38ad79399af19996eaa00dcfdf2a2c75
7b85823d1c597b0acad250a82fc39fdb
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ካውንስል አባላት ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የካውንስል አባላት ጋር በትናንትናው እለት ተወያይተዋል።በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባደረጉት ንግግር፥ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ በሌሎች ሀገራት ተሰርቶበት ለገፅታ ግንባታና ለመልካም ወዳጅነት በጎ ሚና መጫወቱን ጠቅሰዋል።በኢትዮጵያ ካለው አቅም ጋር ሲነፃፀር ግን ቨፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዘፍር ብዙ እንዳልተሰራ ያመላክተዋል ሲሉም ተናግረዋል።ስለሆነም ያለውን አቅም በተሻለ ለመጠቀም ቀደም ብሎ በነበረው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ላይ አዳዲስ አባላት በመጨመርና መመሪያ በማዘጋጀት እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ ተቃማትን በማስፋት ለአዲስ የዲፕሎማሲ ስራ ዝግጅቶች መጠናቀቁን አስታውቀዋል።የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ካውንስል አባላቱ በበኩላቸው መመርያው ላይ ቢሻሻል የበለጠ ውጤት ያመጣል ያሉትን እንዲካተቱ ሃሳበ አቅርበዋል።ከበፊቱ የላቀ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወን እንደሚችሉ ለዚህም ተግባር በመመረጣቸው ደስተኛ መሆናቸውን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን 75 አባላትን ያቀፈ ሲሆን፥ ከታዋቂ ሰዎች፣ ከሀይማኖት አባቶችና ተፅእኖ ፈጣሪ ግለስቦችን በማካተት ከስምንት አመት በፊት መዋቀሩ ይታወቃል።
https://waltainfo.com/am/31308/
6ca8330681b590f71d2b84fb570e08f3
0f35713bfb5b47d582ac313ac31d969a
ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር ላይ ያሳዩትን ህብረት በሁሉም መስክ እንዲደግሙ ተጠየቀ
ቢዝነስ
ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር ላይ ያሳዩትን ህብረት በሁሉም መስክ እንዲደግሙ ተጠየቀ፡፡የ2011 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃግብር የማጠቃለያ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ቤተመንግስት ተካሂዷል፡፡  በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በችግኝ ተከላ መርሃግብሩ ላይ የታየዉ ኢትዮጵያዊ ህብረትና ተሳትፎ ኢትዮጵያዊያን በሁሉም መስክ ላይ ከተባበሩ የማያስመዘግቡት ድል ላለመኖሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መረሃግብር ከታቀደለት በላይ ስኬታማ እንደነበርም ፕሬዝዳንቷ ጠቁመዋል፡፡በብሔራዊ ቤተመንግስት በተካሄደው የ2011 የችግኝ ተከላ መርሃግብር የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ በርካታ አርቲስቶች ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል፡፡እንዲሁም ብሔራዊ አንድነት ጎልቶ በተስተዋለበት በአንድ ጀንበር ከ350 ሚሊየን በላይ ችግኞች በተተከሉበት የሐምሌ 22ቱ ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃግብር በየክልሉ ተሰማርተው የነበሩ የአርቲስቶች ቡድን ከየክልሉ ይዘው የመጡትን ምልዕክት በማስተላለፍ ዘጠኙን ክልሎችንና ሁለት ከተማ አስተዳደሮችን የሚወክሉ አንዳንድ ችግኝ በቤተመንግስት ውስጥ ተክለዋል፡፡ክልሎቹንና ከተማ አስተዳደሮቹን ወክለው ከተተከሉ 11 ችግኞች በተጨማሪ በመሃከላቸው የኢትዮጵያ አንድነትን የሚወክል 12ኛው ችግኝ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን በመወከል ተተክሎ የመርሃግብሩ ማጠቃለያ ተደርጓል፡፡
https://waltainfo.com/am/23916/
956a648920531a808a71028b200ca50f
0115a648be9afda87b54572cdeff4cd6
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በዋግ ኽምራ ያስገነባው ትምህርት ቤት ተመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ የቀድሞውን የዳስ ትምህርት ቤት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አስገንብቶ አስመርቋል፡፡አትሌቱ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፃግብጂ ወረዳ ላይ ያስገነባው ገልኩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው ለምረቃ የበቃው፡፡ትምህርት ቤቱ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተሰኝቷል፡፡ሁለት ብሎኮችና ስምንት የመማሪያ ክፍሎች ያሉትን ይህን ት/ቤት ኃይሌ በሦስት ወራት በማስገንባት ነው ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ማስተማሪያ ዝግጁ ያደረገው፡፡በምረቃ ሥነ ስርዓቱ  ነዋሪነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አንድ ግለሰብ 8 ሺህ 500 የማጣቀሻ መጻህፍትን ለትምህርት ቤቱ መለገሳቸው ተገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/32670/
25eb36f1293d055528e522e6e3fb6704
fcbde641862a1387162210ce632184fb
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የለውጥ ዙሪያ የሚወያይ ኮንፈረንስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ አስጀመሩ
ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት፣ ወቅታዊ ሁኔታ፣ መፃኢ እድል እና ስጋቶች ዙሪያ የሚወያይ ኮንፈረንስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ አስጀመሩ፡፡ፕሬዝዳንቷ ኢትዮጵያ በታሪኳ ወሳኝ የሚባል የለውጥ መንደርደሪያ ላይ እንደምትገኝ ገልፀዋል፡፡ይህ ወቅት ኢትዮጵያ የህዝቦቿን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስና ፍላጎታቸውን ለማርካት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ ጅማሮ ላይ እንደምትገኝም አብራርተዋል፡፡በዚህ ሂደት ላይ የህዝቡን አንድነትና ተነሳሽነት ለማጠናከር ከቃላት ባለፈ በተግባር የሚገለፁ በርካታ መሰራት ያለባቸው ተግባራት ከፊት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡እስካሁን ድረስ የታዩት ተስፋዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ለሚፈለገው ድል ለመድረስ ከህዝቡ አቅም በላይ እንደማይሆን አምናለሁ ያሉት ፕሬዝዳንቷ ለዚህ ሂደት አቅጣጫ የሚያመላክት ፍሬያማ ውይይት ከኮንፈረንሱ እንደሚጠብቁ አብራርተዋል፡፡ መረጃው የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31306/
3c0bf0c2d123f5382fcda29378f695a4
1bc359b3e11a3f2600964aac0160e9be
የእነ ብርጋዲየር ጄነራል ተፈራ ማሞን የክስ መዝገብ ለመመርመር ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ
ሀገር አቀፍ ዜና
የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእነ ብርጋዲየር ጄነራል ተፈራ ማሞ የምርመራን መዝገብ ለመመርመር ለነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።ፍርድ ቤቱ በእነ ጄነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ መርማሪ ፖሊስ በጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለመመርመር በማስፈለጉ ነው ቀጠሮ የሰጠው።ብርጋዲየር ጄነራል ተፈራ ማሞ የብዙዎቻችን ተጠርጣሪዎች የባንክ ደብተሮች በመርማሪ ቡድኑ ስለተያዙብን፣ በቤት ኪራይ የሚኖሩ ቤተሰቦቻችን ለችግር ተዳርገዋል ሲሉ ለችሎቱ አቤት ብለዋል።የመርማሪ ቡድኑ በበኩሉ ከወንጀሉ ጋር የሚያያዝ ከሆነ የባንክ አካውንት የሚታገድበት እንጂ የባንክ ደብተሩ የሚያዝበት አግባብ እንደሌለ ለችሎቱ አስረድቷል።የተጠርጣሪዎቹ የባንክ ደብተር እና አልባሳት በቁጥጥር ስር በዋሉባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም መርማሪ ቡድኑ ጠቁሟል።ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎቹ በምርመራ ሒደት በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከሕግ አግባብ ውጭ የተያዙባቸው ንብረቶች እንዲመለሱላቸው ትእዛዝ ሰጥቷል።እንደ ኢቢሲ ዘገባ የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ተጠርጣሪዎቹ በመታሰራቸው ምክንያት የሚያስተዳድሯቸው ቤተሰቦች ችግር ላይ ወድቀዋል በሚል ለችሎት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ ለችግር የተጋለጡ የተጠርጣሪ ቤተሰቦች ቀለብ እንዲሰጣቸው ትእዛዝ አስተላልፏል።
https://waltainfo.com/am/32671/
df82179f33eae1521e422e4d46225d8b
d17c0f7bd3ab09118c07f5672121f3ea
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ መሠረት ማስፋት የሚያስችል የሦስት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
ቢዝነስ
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ መሠረት ማስፋት የሚያስችል ለሶስት ዓመታት የሚተገበር በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ (ዩኤስ ኤይድ) የሚደገፍ እና በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት የሚመራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ይደግፋል ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናግረዋል፡፡ፕሮጀክቱን ለማስፈፀምም መንግስት በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ታግዞ እንደሚሰራ የገለፁት ገዢው፤ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ፣ በስራ አጥነት ቅነሳ እና ጥናትን መሠረት ባደረጉ ፕሮጀክቶች ላይ ይሰራልም ብለዋል፡፡ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በተጀመረው የኢኮኖሚ ሪፎርም የፖሊሲ ምክረ ሐሳብ በማፍለቅ በኩል እገዛ እንደሚያደርግ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናግረዋል።ኢትዮጵያ የወሰደችውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአሜሪካ መንግስት እንደሚደግፍ የገለፁት በኢትዮጵያ የዐሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር ለማሻሻያው ተግባራዊነት እና ተፈፃሚነት መንግስታቸው ያላሰለሰ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡አሜሪካ ላላፉት ሦስት ዓመታት በትምህርት፣ በጤና እና በኃይል ልማት ዘርፎች ከሦስት ቢሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት ማድረጓንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።ፕሮጀክቱን  ዩኤ ኤይድ በገንዘብ የሚደግፈው መሆኑም ተገልጿል።
https://waltainfo.com/am/23918/
acc542a097fe2c6c510091ce473b2c66
cc6573b916461b69941b7ab611ff63c4
የሻዳይ፣አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በባሕር ዳር ከተማ በድምቀት ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
የሻዳይ፣አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በባሕር ዳር ከተማ በድምቀት ተከበረ፡፡በዋግ ሹሞች መዲና ሰቆጣና አካባቢዋ ሻደይ፣ በቆቦ አካባቢ ሶለል እና በላስታ እና በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አሸንድዬ በሚል የሚከበረው የልጅ አገረዶች ጨዋታ በዓል ዛሬ በባህርዳር ከተማ በድምቀት ተከብሯል።በዚሁ በክልላዊው የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል አከባበር ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ኂሩት ካሳው እና የተለያዩ የክልል እና የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል፡፡በስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከመገፋፋትና ከመጠላላት ወጥተን አንድ ስንሆን የጥበብ አውድማ እና የፍቅር ተምሳሌት እንሆናለን ብለዋል፡፡ዘመን ባልከለሰው አብሮነታችሁ አምራችሁና ደምቃችሁ ስትታዩ በእርግጥም ‘የአማራ ሕዝብ ታላቅ ነው’ ስንል ያለምክንያት አለመሆኑን ከመግለፁም ባሻገር ጥበብ፣ ኩራት፣ አብሮነትና ጀግንነት የክልሉ ህዝብ መገለጫዎች ማሳያ ጭምር እንደሆኑ ያሳያልም ብለዋል።የአብሮነታችን አሻራ፣ የአንድነታችን ተምሳሌት እና የፍቅራችን መገለጫ የሆነው የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰ ወካይ ቅርስነት ለማስመዝገብ ስራ መጀመሩንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ “ታላቅ ነን ስንል ራሳችንን አክብረንና አስከብረን ሌሎችንም የምናከብር ህዝቦች ነን ማለታችን ነው፤ ታላቅ ነን ስንል ችግር በገጠመን ጊዜ አንድ ሆነንና ተባብረን ከችግር የምንወጣ ብርቱ ህዝቦች ነን ማለታችን ነው፤ ታላቅ ነን ስንል በችግር አረንቋ ውስጥ ያሉ ሌሎች ህዝቦችን የምንታደግ ህዝቦች ነን ማለታችን ነው›› በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የሻዳይ፣አሸንድዬ እና ሶለል ባህል በዩኔስኮ በማይዳሰ ወካይ ቅርስነት ለማስመዝገብ ስራ መጀመሩንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛት አብዩ በበኩላቸው የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል ራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ እንዲሆን እንደሚሰራ ገልጸዋል።በአማራ ክልል በርካታ ዘመን ተሻጋሪ ባህላዊ ሁነቶች እንዳሉ የገለጹት አቶ ግዛት፤ የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ባህላዊ ክዋኔዎቹ ሳይበረዙ እና ሳይከለሱ የባህሉ ባለቤት በሆነው ሕዝብ ተጠብቀው፣ ተናፍቀው እና ተወዳጅነታቸውን አጎልብተው እንዲዘልቁም ይደረጋል ብለዋል።
https://waltainfo.com/am/32674/
f59d5e18c7391d796aae5b8a6f1e1a4f
f07586f7201a7d2e776fed001b616d40
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ለአዳዲሶቹ የሱዳን መሪዎች የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአዳዲሶቹ የሱዳን መሪዎች የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ባስተላለፉት መልእክት፥ ጀነራል አብዱል ፈታህ ቡርሀን 11 አባላት ያሉት ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል።እንዲሁም የነሐሴ 11 የሽግግር መንግስት ስምምነት ፊርማን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ለተመረጡት አብደላ ሀምዶክ የመልካም ምኞት መግለጫ ማስተላለፋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።ጄኔራል አብድል ፈታ ቡርሃን አዲስ የተቋቋመው እና 11 አባላት ያሉት የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ሆነው በትናንትናው እለት ነው የተመረጡት።11 አባላት ያሉት የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ሸንጎ ኦማር ሀሰን አል በሽር ከስልጣን ከወረዱበት ሚያዚያ 2019 ጀምሮ ሀገሪቱን ሲመራ የቆየውን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትን ተክቶ ትናንት ነው በይፋ ስራውን የጀመረው።ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አብደልራህማን ቡርሃን አዲስ የተቋቋመው የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት መሪ በመሆን በትናንትናው እለት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።ጀኔራል ቡርሃን ከሶስት ዓመት በላይ የሽግግር ጊዜ ውስጥ የሉዓላዊ ሸንጎውን ለ21 ወራት በበላይነት የሚመሩት ሲሆን፥ የሲቪል ተወካዮች ደግሞ ቀጣዮቹን 18 ወራትን ይመራሉ።11 አባላት ያሉት ሉዓላዊ ምክር ቤት በትናንትናው እለት በይፋ ስራውን መጀመሩን ተከትሎም አብደላ ሀምዶክ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በትናንትናው እለት ቃለመሃላ ፈፅመዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነታቸውን የለቀቁት ባለፈው ዓመት ነበር።አብደላ ሃምዶክ በኢኮኖሚ ተንታኝነት ከ30 ዓመት በላይ ልምድ ያላቸው ሲሆን፥ ከካርቱም ዩንቨርሲቲና ከታወቁ የእንግሊዝ ትምህርት ተቋሞት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።ወታደራዊ ምክር ቤቱና የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ጥምረት የአገሪቱን የሽግግር መንግሥት ለመጀመር ባለፈው ቅዳሜ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።(ምንጭ፦ ኤፍቢሲ)
https://waltainfo.com/am/31304/
87a0ba7482d6c850d92d233c6bc03f6a
c6ea3c48b2bb7b45bb31d952aec58b73
በተያዘው ክረምት ወራት በጎርፍ አደጋ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሊጠቁ እንደሚችሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
በክረምት ወራት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚከሰተው የጎርፍ አደጋ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሊጠቁ እንደሚችሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ብሄራዊ ሜትዎሮሎጂ እና የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን በጋራ በመሆን በሀገሪቷ የክረምት ወቅት ሊፈጠር ይችላል ተብሎ በሚታሰበው ቅጽበታዊ ጎርፍ አደጋ እና ሊደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ በሚዘንብ ዝናብ፣ በወንዞች እና ግድቦች መሙላት ምክንያት በተለያዩ የሃገሪቷ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋዎች እየተስተዋሉ ነው፡፡ በዚህም የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጎርፍ አደጋው የሚያስከትለውን አደጋ ለመቀነስ እና ለመከላከል በፌደራል እና በክልል ደረጃ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ ለቅድመ ጎርፍ መከላከል እና በጎርፍ ወቅት 1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ እንደሚችሉ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳመና ዳሮታ ተናግረዋል፡፡በደቡብ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች ከ23 ሺህ 900 በላይ ሰዎች ላይ በጎርፍ አደጋ ጉዳት እንደደረሰም ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡የብሄራዊ ሜትዎሮሎጂ ኤጀንሲ የ2011 የክረምት የአየር ፀባይ አዝማሚያን በተመለከተ በግንቦት ወር መረጃውን ለህዝብ ተደራሽ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት በአብዛኛው ሃገሪቷ ክፍል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡በሚቀጥሉት የክረምት ወራት ደግሞ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚከሰት እና በአንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ያጋጥማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የብሄራዊ ሜትዎሮሎጂ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ሃ/ማርያም ገልጸዋል፡፡በሀገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ ቆቃ፣ መልከዋከና፣ ግልገል ጊቤ፣ ተከዘ እና ሌሎች ግድቦች ላይ እየተከሰተ ባለው የውሃ መሙላት ሳቢያ የጎርፍ አደጋ እንሚያጋጥማቸው ተገልጿል፡፡ግድቦቹ በመሙላታቸው በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ እያስከተሉ እንደሚገኙ የገለጹት የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ግዛው በግድቦቹ አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሊያጋጥም የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የጎርፍ ስጋት ወደሌለባቸው አካባቢዎች መሄድ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32669/
887da3e1283687824d0f5c10c810ddac
d135b5021d88f21e7de7c4d770ffd0d3
33 የምግብ አምራችና አስመጭዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
ቢዝነስ
በ33 የምግብ አምራችና አስመጪ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ባለስልጣኑ የተቋሙን የ2011 እቅድ አፈፃፀም እና የ2012 እቅድ አስመልክቶ ትናንት መግለጫ ሰጥቷል።የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ሳምሶን አብርሃም እንደተናገሩት ህገ ወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ በተገኙ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡“ህገወጥ ተግባራትን በፈፀሙ አካላት ላይ ምርቶችን ከማስወገድ አንስቶ ተቋማቱን እስከ ማስዘጋት ደርሰናል” ያሉት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ከዘርፉ የማስወጣት እና በህግ የመጠየቅ ሥራ መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡ተቋሙ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ ጥቆማዎችን መሠረት በማድረግ መድሃኒት እና ምግብ አስመጪዎች ላይ ፍተሻዎችን በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ነው ያስታወቁት፡፡የታሸጉ ምግቦች በብዛት በበረሃማ አካባቢዎች ስለሚገቡ ወደ አደገኛ ኬሚካልነት እንደሚቀየሩና በኅብረተሰቡ ላይም ከፍተኛ የጤና ጉዳት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንደሚያስከትሉ ተመላክቷል።እንደ አዲስ ዘመን ዘገባ በበጀት ዓመቱ በኅብረተሰቡ ጥቆማ እንዲሁም ድንገት በተደረገ ፍተሻ ከ4 ሺህ 763 ቶን በላይ ምግብ መያዙን አቶ ሳምሶን አስታውቀዋል።
https://waltainfo.com/am/23915/
f53636096d8beaea8c1c4c1086ae0c15
4de5ca4e5316cc7792b338bba250db7e
የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ እየተካሄደ ነው
ፖለቲካ
የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ መድረክ በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡ጨፌ ኦሮሚያ በ4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤው የዜግነት አገልግሎት አዋጁን በማጽደቅ የክልሉ መንግስት ስራ ላይ ያዋለው መሆኑ ይታወቃል፡፡በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ አርቲስቶችና ሌሎች ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31305/
8866dd2963fce4d63d05340460f366cb
ca26afb0af01a9ca3955b8505350d3d3
ሞቃዲሾ አዲስ ከንቲባ አገኘች
ፖለቲካ
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የቀድሞውን የጦር አበጋዝና የመንግሥት ሚኒስትር የነበሩት ኦማር መሐመድን  የሞቃዲሾ ከንቲባና የባዲር ግዛት አስተዳደሪ አድርገው ሾመዋል።ሹመቱ ባለፈው ወር በአጥፍቶ ጠፊዎች ህይወታቸው ያለፈውን የቀድሞ ከንቲባ አብዱራህማን ኦማር ኦስማንን ለመተካት መሆኑ ተገልጿል፡፡አዲሱ ከንቲባ ኦማር መሐሙድ መሐመድ እ.አ.አ 2004 ላይ በተመሠረተው የሽግግር መንግሥት ውስጥ የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ከመሆናቸው አስቀድሞ ሞቃዲሾ ውስጥ የጦር አበጋዝ ነበሩ።እ.አ.አ እስከ 2009 ድረስም በሚኒስትርነት አገልግለዋል።ኦማር መሐመድ ለሞቃዲሾ ከንቲባነት የተመረጡት በመንግሥት ውስጥ ባላቸው ልምድ እንዲሁም የልማት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊነት ማስቀጠል የሚያስችሉ በመሆናቸው ነው መባሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው።
https://waltainfo.com/am/33328/
5bfea7ef5b0ae60f725e0b0e58b3ce9a
b631b6db6d36b1e96ad5355c4e49b48e
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመቐለ እየተከበረ በሚገኘው የአሸንዳ በዓል ላይ ተገኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአሸንዳ ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት በዛሬው ዕለት  መቐለ ገብተዋል፡፡ፕሬዝዳንቷ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በትግራይ ክልል ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልና በሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡የአሸንዳ   በዓል በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሰላም፣ አንድነትና ልማት ተምሳሌት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡በትግራይ ክልል በነሃሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ፣ ማሪያ እና ዓይኒ-ዋሪ በዓላት የክልሉን ባህል፣ ትውፊትና የቱሪዝም መስህቦች በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ሚና እንዳለው ይነገራል፡፡
https://waltainfo.com/am/32668/
3cf6744f9944f3194a4ac45001bc09b6
f4015ddcd5b0006cef1b9d6873f7700a
የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል የልጃገረዶች ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይከበራሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ጨዋታዎች በዋግ ኽምራ፣ በላል ይበላ እና በቆቦ ከዛሬ ነሐሴ 16 እስከ 21/2011 ዓ.ም ይከበራሉ።በበዓሉ ለመታደም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ትናንት ማምሻውን ሰቆጣ ከተማ ገብቷል።ለልኡካኑ የሰቆጣ ከተማና እና አካባቢዋ ነዋሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የየወረዳዎቹ ሻደይ ባህላዊ ተጫዋች ቡድኖችም በባህሉ ዜማና ጨዋታዎች ታጅበው ነው የአቀባበል ያደረጉላቸው። ሰቆጣም ከዋዜማው ጀምሮ የሻደይ ጨዋታን መከወን ጀምራለች።የዘንድሮው የሻደይ በዓል "ሻደይ ባህላችን ለዘላቂ ልማትና ሰላማችን" በሚል መሪ ሀሳብ ነው የሚከበረው።የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል የልጃገረዶች ጨዋታዎች ባለፈው ዓመት በክልል ደረጃ ባሕር ዳር ላይ መከበሩ ይታወሳል። በዚህ ዓመት ደግሞ ከክልል ባለፈ አዲስ አበባ ላይም እየተከበረ ነው። በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችም እንደሚከበር ታውቋል።በአዲስ አበባ በፓናል ውይይት በየክፍለ ከተሞች ሲከበር የቆየው በዓሉ የፊታችን ነሐሴ 19/2011 ዓ.ም በሚሊኒዬም አዳራሽ ይከበራል፤ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ለማስፈርም ጥረቱ ቀጥሏል።
https://waltainfo.com/am/32666/
7dbeb8e1b66fe5a5a5427a849fde2be2
fdf2e85a36298364562466351512d1e6
ኢትዮጵያ በኢንዶኔዢያ- አፍሪካ የመሰረተ ልማት ዓለም አቀፍ ጉባኤ እየተሳተፈች ነው
ቢዝነስ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የከተማ ልማትና ኮንስራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በባሊ ኢንዶኔዢያ በመካሄድ ላይ ባለው የኢንዶኔዢያ- አፍሪካ የመሰረተ ልማት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡በጉባዔው  በተካሄደው የፓናል ውይይት ማብራሪያ የሰጡት  ኢንጂነር አይሻ ባለፉት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ ጠንካራ የኢከኖሚ ዕድገት ማሰመዝገቧን ተናግረዋል፡፡በተለይም በመሰረተ ልማት ልማት ያላትን ተሳትፎ ይበልጥ ውጤታማና ተወዳዳሪ ለማድረግ እየሰራች መሆኗንም ገልፀዋል፡፡በመንገድ መሰረተ ልማት ፣ በባቡር ሐዲድ ፣ በብሔራዊ ሎጅስቲክስ ልማት ፣ በትራንስፖርት ዘርፍና በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች የተመዘገቡት ውጤቶች አስደናቂ መሆናቸውን ሚኒስትሯ ለጉባኤው ተሳታፊዎች  አብራርተዋል፡፡በተለይም  የኢትዮጵያ የባቡር ኮርፖሬሽኑ ዋና ከተማዋን ከጂቡቲ ወደብ ጋር የሚያገናኝ የ 656 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር መዘርጋቱንና ይህም ወደ ጅቡቲ ወደብ ለመድረስ ይፈጅ የነበረውን የ 84 ሰዓታት ቆይታ ጊዜ ወደ 10 ሰዓታት ድረስ ለመቀነስ መቻሉንም አንስተዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት የግንኙነት ትስስርን እና መሠረተ ልማቶችን ለማጎልበት ብሎም የአካባቢያዊ ና የአለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማሳደግ የኢትዮ-ቴሌኮም ፣ የኢትዮጵያ የመርከብና የሎጂስቲክስ አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድን የመሳሰሉ በመንግስት የተያዙ ኩባንያዎችን በከፊል በግል ለማዞር የሚያችል ዕቅድ መዘርጋቱን ገልጸዋል ፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ከኢንዶኔዥያና ከህዝቧ ጋር በመሰረተ ልማትና በሌሎች ዘርፎች ለጋራ ብልፅግናና ልማት እንደምትሰራ መናገራቸውን ከኢፌዴሪ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡የኢንዶኔዢያ- አፍሪካ የመሰረተ ልማት ጉባኤ በየዓመቱ ኤንዶኔዢያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትስሰስር ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳየች ላይ የሚመክር ጉባኤ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/23913/
7e52d33d9aa03468f41a4fa45a4a3278
bdaf23d19557d8524e71461dd4ad47ea
የአሸንዳ /አውርስ በዓል በትግራይ ክልል እየተከበረ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
የአሸንዳ /አውርስ በዓል በትግራይ ክልል በመከበር ላይ ይገኛል፡፡በዓሉ “አሸንዳ/አውርስ የሰላም፣ አንድነትና ልማት ተምሳሌት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመከበር ላይ ነው የሚገኘው።በዓሉ በክልሉ በሚገኙ ከተሞች እና የገጠር ወረዳዎች በሙሉ በመከበር ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ በአሁኑ ሰዓትም በክልል ደረጃ በዓቢይ ዓዲ ከተማ እየተከበረ ነው።በበዓሉ ላይም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት፣ በትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብረሃም ተኸስተን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልል እና የፌደራል የስራ ሃላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።በዓቢይ ዓዲ ከተማ በመከበር ላይ በሚገኘው በዓል ላይም ከሰቆጣ የመጡ ልኡካንም በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።አሸንዳ/አውርስ በዓል ከ8 ሰዓት ጀምሮ በክልል ደረጃ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት በመቐለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ይጠበቃል።በትግራይ ክልል በነሃሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ፣ ማሪያ እና ዓይኒ-ዋሪ በዓላት የክልሉን ባህል፣ ትውፊትና የቱሪዝም መስህቦች በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ስራ የሚሰራበት ፕሮግራም ነው።አሸንዳ እና ማሪያ ከነሃሴ 16 ጀምሮ የሚከበር ሲሆን፥ ዓይኒ-ዋሪ ደግሞ ነሃሴ 24 2011 ዓ.ም በአክሱም ከተማ እና አካባቢው የሚከበር የልጃ ገረዶች በዓል ነው።በዓሉ በህዝቦች መካከል ሰላም፣ አንድነት እና ፍቅር እንዲኖር ከሚሰጠው ጠቀሜታ በተጨማሪ ለቱሪዝም መስህብነት በማገልገል ለኢኮኖሚው አስተዋዕኦ እንዳለው ይታወቃል።እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ አሸንዳ/አውርስ በዓል የፊታችን ነሃሴ 26 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የሚከበር ይሆናል።
https://waltainfo.com/am/32667/
ba6c19f1d97269672d2a877898d1bdb8
b4543bd0ee5016fb9835a6b083fc6188
አምስት የአውሮፓ ሕብረት ሀገራት ስደተኞችን ሊቀበሉ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
አምስት የሚሆኑ የአውሮፓ ሕብረት አባል ሃገራት፤ ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሉክዘምበርግ እና ፖርቹጋል በጣሊያን ደሴት ላምፔሱዳ የደረሱ ስደተኞችን ሊቀበሉ መሆናቸው ተገለፀ።ስደተኞቹን የጫነችው የእርዳታ መርከብ ተቀባይ በማጣቷ ለሳምንታት በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ስትዋልል ቆይታ ጣሊያን ላምፔሱዳ የደረሰችው ባለፈው ማክሰኞ እንደነበር ተገልጿል።የአገሪቷ አቃቤ ሕግ መርከቧ እንድትለቀቅ ትዕዛዝ ማስተላለፈቻውን ተከትሎ ቁጥራቸው ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ስደተኞችን ያሳፈረችውና 'ባለሽበት ቆይ' የተባለችው መርከብ እንድትንቀሳቀስ ተፈቅዶላታል።ምንም እንኳን ከስደተኞቹ መካከል ህፃናትና በጠና የታመሙ ሰዎች ቢኖሩም የአገር ውስጥ ሚንስትሩ ማቴዎ ሳልቪኒ "ከዚህ በኋላ ወደቦቻችን ለስደተኞች ዝግ ናቸው።" በማለት ስደተኞቹ ከመርከቧ እንዳይወርዱ ለሦስት ሳምንታት ያህል ተከልክለው ቆይተዋል።ቀደም ሲል 10 ስደተኞች ደሴቷ ጋር በዋና እንደርሳለን በሚል ተስፋ ከመርከቧ ዘለው ባህር ውስጥ መግባታቸው ተጠቅሷል።በሥፍራው የሚገኙት ስደተኞችም ቆስለውና በፋሻ ተጥቅልለው ይታዩ እንደነበር ኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።ከስደተኞቹ መካከል አንዱ "ልቀውስ ትንሽ ቀርቶኝ ነበር" ሲል የነበረበትን ሁኔታ ለዜና ወኪሉ ገልጿል።እንደ ሮይተርስ የዜና ወኪል ከሆነ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን እነዚህን ስደተኞችን የሚቀበሉ ሃገራትን ሲያፈላልግ ቆይቷል።በመጨረሻም ስደተኞችን የጫነችው ሁለተኛዋ የእርዳታ መርከብ፤ ለ13 ቀናት በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ከቆየች በኋላ ሃገራቱ ከአደጋው የተረፉትን ከ100 በላይ ስደተኞች ለመቀበል ፈቅደዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/34129/
9e6ce4c7a2be1536c0b687a260eabf00
215677edc62de55e10b803b4ed2bd031
ሊድ አሲድ ለአካባቢ አየር ንብረት ለዉጥ የሚያበረክተዉን አስተዋፅኦ ለመቀነስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት ዉይይት ተካሄደ
ቢዝነስ
ባገለገሉ ባትሪዎች ዉስጥ የሚገኘዉ ሊድ አሲድ ለአካባቢ አየር ንብረት የሚያበረክተዉን አስተዋፅኦ ለመቀነስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት ዉይይት ተካሄደ፡፡በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለዉጥ ኮሚሽን የፖሊሲ ፤ ደረጃዎች ጥናትና ዝግጅት ጀነራል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አየለ ሄገና በዉይይት መድረኩ ላይ እንዳሉት ኢትዮጵያ ባለፉት 30 አመታት የአየር ንብረት ለዉጥን ተፅዕኖ ለመከላከል የተለያዩ ተግባራትን ስታከናዉን ቆይታለች፡፡ባለፉት 2 አመታትም የተለያዩ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ አዋጆችና ደንቦች ማሻሻያ እንዲደረግባዉ መደረጉን አዉስተዉ በቀጣይ ወደተግባር ለሚገባዉ የፍኖተ ካርታ ዝግጅት መንግስት የበኩሉን እንደሚወጣ ገልፀዋል፡፡የሊድ አሲድ በአለም አቀፍ ደረጃ 977 ቢሊየን ዶላር በማሳጣት ተፅዕኖ እንደሚያደርስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በአፍሪካም 134.7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ጉዳት ማድረሱንና ይህም በአህጉሩ 4 በመቶ ለሚሆነዉ የምርት መቀነስ ምክኒያት መሆኑ ተመልክቷል፡፡ይህ አሲድ በኢትዮጵያም 4 በመቶ ሃገራዊ ምርት እንዲቀንስ የበኩሉን አስተዋጾ ማበርከቱ ተነግሯል፡፡ፍኖተ ካርታዉ በመጀመሪያ ዙር 1.1 ሚሊየን ዩሮ ከባለድርሻ አካላት ተመድቦለት ወደተግባር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡በዉይይቱ ላይ የአዉሮፓ ህብረት፤ በሃይል አቅርቦት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23914/
c1bf7dd9cb763d1d5308fd24194ad98d
14bb71eac3c86404534eae8ebb645af7
ም/ቤቱ ባካሄደው 73ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ፖለቲካ
ም/ቤቱ ባካሄደው 73ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈምክር ቤት በቅድሚያ በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ተዘጋጅተው በቀረቡ ከፍተኛ ደረጃ የድንጋይ ከሰል ማዕድን እና አነስተኛ ደረጃ የክሮማይት ማዕድን ማምረት ፈቃድ ስምምነቶች ላይ የተወያየ ሲሆን፤ ስምምነቶቹ በህጉ መሰረት መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች ከተሟሉ በኋላ እንደተዘጋጁ ተገልጿል፡፡ምክር ቤቱም በቀረቡት የከፍተኛ እና የአነስተኛ ደረጃ የማዕድን ማምረቻ ፈቃድ ስምምነቶች ላይ ከተወያየ በኋላ በስራ ላይ እንዲውሉ መወሰኑ ተመልክቷል፡፡በመቀጠልም ምክር ቤቱ በሰው የመነገድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ በዚህ ዙሪያ የሚደርሱ ወንጀሎች በዜጎች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ወንጀሎቹን ለመከላከል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ አቅርቧል፡፡ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ማሻሻያዎችን በማዕከል ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡እንዲሁም የማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን የተለያዩ የማሪታይም አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያወጣውን ወጪ ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ የአገልግሎቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሆነው ተገልጋይ እንዲሸፍን ለማድረግ የሚያስችል የህግ መሰረት መኖሩ አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የአገልግሎት ክፍያውን ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ያቀረበ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም ደንቡ ላይ ተወያይቶ በስራ ላይ እንዲውል መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31310/
31f897b3c77b7ac6e87e10d81f7a70fa
222c77a2482855da801ae9f362f45559
የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንትና የእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩኒሌቨር ኩባንያን ጎበኙ
ቢዝነስ
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሎክ ሸርማ በኢስተርን እንደስትሪ ዞን የሚገኘውን የዩኒሌቨር ኩባንያን ጎብኝተዋል፡፡አቶ ሽመልስ አብዲሳና የብሪታኒያ የዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ በኢንዱስትሪ ዞኑ ባደረጉት ጉብኝትም የዩኒሊቨር ኩባንያ ስራዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።ዓለም አቀፍ ተቋም የሆነው ዩኒሊቨር ኩባንያ በዱከም በሚገኘው ኢስተርን ኢንደስትሪያል ዞን ውስጥ ለምግብነት እና ለመዋብያነት የሚያገለግሎ ምርቶችን እያመረተ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል።ኩባንያ ኢስተርን ኢንደስትሪያል ዞን ባለው ፋብሪካም ከዚህ ቀደም ክኖር የምግብ ማጣፈጫ፣ ላይፍ ቦይ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና እና ቫዝሊን ሎሽን እያመረተ ይገኛል። (ምንጭ:-የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ0
https://waltainfo.com/am/23912/
c62d22792111193c49d3c19d27c3af6a
7c514a94a9050b17c85fce65ffe020d5
የአዲሱ የትምህርት መዋቅር 6-2-4 በሚል ማሻሻያ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
አዲሱ የትምህርት መዋቅር 6 ዓመት የአንደኛ ደረጃ፣ 2 ዓመት የመለስተኛ ትምህርት እንዲሁም 4 ዓመት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሆን መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከዚህ በፊት የነበረው የትምህርት ፖሊሲ የውጭ ናፋቂና ሀገር በቀል እውቀቶችን ከመስጠት አንፃር ውንነቶች እንዳሉ በመረዳት የትምህርት ስርዓቱ የሃገሪቱን አንድነት የሚያስቀጥል፣ ከማህበረሰቡና ከተማሪው ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ሃገር በቀል እውቀቶችን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አዲሱ የትምህርት መዋቅር በሶስት ክፍሎች ተመድቦ እንደሚሰራ ጠቅሰው፥ 6 ዓመት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ 2 ዓመት የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሁም 4 ዓመት ደግሞ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሆን ተወስኗል ብለዋል።ተማሪዎች 6ኛ ክፍልን ሲያጠናቅቁ ክልላዊ ፈተናን የሚፈተኑ ሲሆን፥ ከዚህ በፊት ክልላዊ ፈተና የነበረው 8ኛ ክፍል ደግሞ ሃገራዊ ፈተና ይሆናልም ተብሏል።ከዚህ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በግል ዘርፍ ተይዞ የቆየው የቅድመ መደበኛ ትምህርት (የህጻናት ማቆያን ጨምሮ እስከ ኬጂ) በግልና በመንግስት እንዲያዝ ይደረጋል ነው የተባለው፡፡ከዚህ ቀደም ሲሰጥ የቆየው የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አይኖርም የተባለ ሲሆን፥ የ12ኛ ክፍል ፈተና ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሊሆንም ላይሆንም እንደሚችል ተጠቁሟል። በተጨማሪም የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠናዎች ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።በዚህም ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርት መርሃ ግብር ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 8 (እስከ ሶስተኛ ዲግሪ) ደረጃ ድረስ መማር እንደሚችሉም በመግለጫው ወቅት ተነስቷል።የመምህራን ድልድልን በተመለከተም መምህራኑ ያላቸውን የትምህርት ደረጃ መሰረት ባደረገ መልኩ ይተገበራልም ነው የተባለው።ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው መምህራን፣ ለሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) እንዲሁም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸው መምህራን የሚመደቡ ይሆናል።ፍኖተ ካርታው ከ3 እስከ 5 አመታት የሚፈጅ በሆንም መሰረታዊ ተብሎ የተለዩ ጉዳዮች በቀጣይ አንድ ወር በመጨርስ ወደ ትምህርት ማዕቀፉ በእቅድ ደረጃ እንዲገባ ይደረጋል በ2012 አጠቃላይ ስራው አልቆ በ2013 ወደ ትግበራ ይገባል፡፡ፍኖተ ካርታው ከትምህርት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎችንና  ያልተካተቱ ጠቃሚ ጉዳዮች ከማከተቱም በሻገር ትውልዱን ኢትዮጵያዊ  አውቀት እንዲኖረው ያደርጋል ተብሎም ይታሰባል፡፡ለሀያ አራት ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ እንዲሁም እስትራቴጂ ያመጣቸው በጎ ለውጦች ቢበዙም  ዘመኑን  ያላማከለ እንዲሁም  ከፍተቶች ያሉበት በመሆኑ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርትና ስልጠናው ፍኖተ ካርታ ሲዘጋጅ ቆይቷል፡፡ፍኖተ ካርታውን የሚመለከታቸው አካላት ካዘጋጁት በኋላ ከአምስት አመት በፊት ለህዝብ ይፋ ሆኖ  ምክክር ተደረጎበታል፡፡ከምክክሩና  በኋላም ከ357 በላይ ቢሻሻሉ የተባሉ የመፍትሔ ሀሳቦች የተሰበሰቡ ሲሆን፣ በዋናነት  36ቱ መሰረታዊ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ከእነዚህም ባሻገር በትምህርትና ስልጠናው ፍኖተ ካርታ ከተቀመጡት 37 የመፍትሄ አቅጣጫዎች መካከል ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተመረጡት 13 የርብርብ መስኮች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የትምህርት ሚኒስቴሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ  ገልፀዋል።የትምህርት ሚኒስትሩ መግለጫቸው ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ መንግስት በመልካም እሴት፣ ስነ ምግባርና በብቃት የታነጸ ዜጋን ለማፍራት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
https://waltainfo.com/am/32664/
89bdb5d082c7a14820878f39fa1633b7
7a97772a530923523dee5ff782a0fb29
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአየርላንድ አምባሳደር ሚስ ሶንጃ ሃይላንድን አሰናበቱ
ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአየርላንድ አምባሳደር ሚስ ሶንጃ ሃይላንድን አሰናበቱ፡፡አምባሳደሯ ባለፉት ሁለት ዓመታት ቆይታቸው በኢትዮጵያና በአየርላንድ መካከል የነበረው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ላደረጉት አሳተዋፅኦ ፕሬዝዳንቷ አመስግነዋል፡፡ በቀጣይ ለሚኖረው ግንኙነትም በተግባር ካዩት እውነታ ተነስተው በኢትዮጵያ ያለውን የሀገር ግንባታ እንቅስቃሴ እንዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡ተሰናባቿ የአይርላንድ አምባሳደር ሚስ ሶንጃ ሃይላንድ በበኩላቸው፣ በቆይታቸው በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለተደረገላቸው ሁለንተናዊ ድጋፍ አመስግነው በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንቨስትመንትና ሌሎች ዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ መረጃው የፕሬዝዳንት ጽጽቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31303/
cd33325a6d8dfd6525f7ab1962b1b628
5a714a6d2038a0f972df06caf787fbd8
ሱዳን ለሦስት ዓመታት ለሚቆየው የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች
ፖለቲካ
ሱዳን ለሦስት ዓመታት ለሚቆየው የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች።አዲስ የተሾሙት ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ የሽግግር መንግሥቱ መሪ በመሆን ቃለ መሃላ የፈፀሙ ሲሆን፣ በቃለ መሃላቸው በአገሪቱ ያለውን ሰላም ማረጋገጥ እና ለምጣኔ ሐብታዊ ቀውሶች እልባት መስጠት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዋል።ሌተናንት ጄነራል አብደል ፈታህ አብደልራህማን ቡርሃን ለሉዓላዊ ምክርቤቱ መሪ ሆነው መምራት ከጀመሩ በኋላ የተሾሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ እስከ ቀጣዩ የአገሪቷ ምርጫ ድረስ እንደሚያስተዳድሩ ተገልጿል።የሉዓላዊ ምክር ቤቱና ሃምዶክ በቃለ መሃላ ሥነስርዓቱ ላይ ሱዳን ኦማር አል በሽር ሥልጣን በኋላ ከወታደራዊ አገዛዝ ሥርዓት የተላቀቀችበት የመጀመሪያው ጊዜ ብለውታል።ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በበኩላቸው አሁን የተመሰረተው መንግሥት በአገሪቷ የነበረውን የወታደራዊ አገዛዝ ሥርዓት እንዲያከትም ያደርገዋል በማለት ተስፋ ሰንቀዋል።ጠቅላይ ሚንስትር ሃምዶክ ከአውሮፓዊያኑ 2011 ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ሆነው አገልግለዋል።መንግሥት ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል፤ ጦርነትን ማስቆም፣ ዘላቂነት ያለው ሰላም መገንባት፣ የምጣኔ ሐብት ቀውስን መፍታት እና ሚዛናዊነቱን የጠበቀ የውጭ ፖሊሲ መገንባት እንደሆኑ ሃምዶክ ለሮይተርስ ዜና ወኪል አስታውቀዋል።ባለፈው ዓመት ሃምዶክ የአገሪቷ የገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሆኑ ከሥልጣን በተወገዱት ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር የታጩ ሲሆን ጥያቄው ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።በሱዳን የተፈጠረው ቀውስ የጀመረው ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ሲሆን አገሪቷን ለ30 ዓመታት ያስተዳደሩት ኦማር አል በሽር ከሥልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ ነበር።የሲቪል መንግሥት እንሻለን የሚሉ የአገሪቷ ዜጎች ለወራት ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያትም የበርካቶች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
https://waltainfo.com/am/33327/
04f0c276df0fd8e0d9d084c68f99609f
9bca2fb52da29a04078ce44f5e4d4529
ቻይና እና ሩሲያ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በአሜሪካ ሚሳኤል ሙከራ ዙሪያ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቁ
ፖለቲካ
ቻይና እና ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጸጥታው ምክር ቤት በአሜሪካ ሚሳኤል ሙከራ ዙሪያ ስብሰባ እንዲጠራ መጠየቃቸው ተገለጸ፡፡ አሜሪካ ባሳላፍነው ሰኞ የመካከለኛ ርቀት ሚሳኤሎችን የማልማትና የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት መግለጫ መስጠቷ ይታወሳል፡፡ ቤጅንግ እና ሞስኮ ጉዳዩ ለዓለም አቀፉ ሰላምና መረጋጋት ስጋት በመሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንዲመክር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡ በሳለፍነው ሰኞ የአሜሪካ መከላከያ በሰጠው መግለጫ የመካከለኛ ርቀት ሚሳኤል ሙከራ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ሙከራው ከ500 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ኢላማውን መምታት መቻሉም ነው በመግለጫው የተመላከተው፡፡ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ማርክ ኢስፐር ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃለ ምልልስም የሚሳኤል ሙከራው ለቻይና እና ሩሲያ ብሎም ለሰሜን ኮሪያ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ማለታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡ አሜሪካ በቀዝቃዛው ጦርነት ከተፈራረመችው የመካከለኛው ርቀት ሚሳኤል መጠቀም ከሚከለክለው ስምምነት መውጣቷን ይፋ ካደረገች በኋላ ሙከራው የመጀመሪያው መሆኑምን ዘገባው ያስረዳል፡፡ (ምንጭ፡-አልጀዚራ)
https://waltainfo.com/am/33988/
4c3d480b95c90f5fadf1051f7a8e3ffb
2dd63f1560f4437a32cfcf106baff03f
ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ አዲስ አበባ ከሚኖሩ የኢጋድ አባል አገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ዛሬ ነሀሴ 14 ቀን 2011 ዓም አዲስ አበባ ከሚኖሩ የኢጋድ አባል አገራት አምባሳደሮች ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።የኢጋድ አባል አገራት አምባሳደሮች በቀጠናው ሰላምን በማስፈን ዘላቂ ልማት ለማስመዝገብ በሚደረገው እንቅሰቃሴ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሚኒስትር ዴኤታዋ አሳስበዋል።አምባሳደሮቹ በበኩላቸዉ በቀጠናው በተለይም በደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፈን እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከግብ እንዲደርስ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ሚኒስትር ዴኤታዋ  ውይይቱ በዋናነት የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ፈራሚ አካላት በነገው እለት በአዲስ አበባ ከሚያደርጉት ስብሰባ ጋር በተያያዘ ያለውን ቅድመ ዝግጅት ስራ በተመለከተ መረጃ መለዋወጥ ላይ ያተኮረ መሆኑን ነው የገለፁት።በውይይቱ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሱዳን፣ የሶማሊያ፣ የጅቡቲ፣ የኬንያ እና የኡጋንዳ አምባሳደሮች መሣተፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
https://waltainfo.com/am/31300/
298135669aeec01c5a9fc5cffc55db79
fdb3957196db739cf771df7df9a9b579
በአቶ አብዲ መሐመድ ዑመር የክስ መዝገብ  የተከሰሱ ሰዎች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ተወሰነ 
ፖለቲካ
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሐመድ ዑመር የክስ መዝገብ ተጠቅሰው ያልተገኙ 11 ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ብይን ሰጠ።በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ሳይቀርቡ በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ከተበየነባቸው ተከሳሾች የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ጄኔራል አብዱራህማን አብዱላሂ፣ ሻለቃ ሼክ ሙክታር እና ሄጎ የተሰኘውን የአመፅ ቡድንን በምክትልነት ሲመሩ ነበር የተባሉት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ መሐመድ አህመድ ይገኙበታል።ችሎቱ ከነዚህ በተጨማሪ በክስ መዝገቡ የመኖሪያ አድራሻ ተፈልገው ያልተገኙ ሌሎች 7 ተከሳሾችም እንዲቀርቡ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ እንዲደርሷቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል።በተሻሻለው ክስ ላይ 1ኛው ተከሳሽ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ዑመር ከጠበቆች ጋር ተማክሬ የክስ መቃወሚያ አቀርላሁ ብለዋል።ጉዳያቸውን በአካል እየተከታተሉ ከሚገኙ 14 ተከሳሾች የተፋጠነ ፍትሕ ተጠቃሚ መሆን አልቻልንም፤ ጉዳያችንን ፍርድ ቤቱ በትኩረት ይመልከትልን በማለት አመልክተዋል።ችሎቱ የክስ መዝገቡ በጋራ የሚታይ በመሆኑ የተከሳሾች የግል አቤቱታ የክስ መቃወሚያ እና ከሌሎች መሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የተጠቀሰውን ጊዜ ሊቆጠር ችሏል ብሏል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31296/
4df5c744c59e8be7206c45b89262410a
982a1599277e8a4eb68e6e1495574875
የመቐለ ከተማ ሴቶች የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ ችግኝ ተከሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
የመቐለ ከተማ ሴቶች የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በሰማዕታት ሐውልት ግቢ ችግኝ ተከሉ። ሴቶቹ ችግኞቹን የተከሉት በዓሉን ከማድመቅ በተጨማሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራምን ለማሳካት እንደሆነም ተገልጿል።ሴቶቹ ችግኞቹን ተንከባክበው ለማጽደቅ እንደሚሰሩም ተገልጿል።በተከላው ከተሳተፉት ሴቶች መካከል ወይዘሮ ፅጌ አብርሃ የሴቶች የነጻነት መገለጫ የሆነውን በዓል ለማድመቅና መነሳሳትን ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።እንዲሁም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የጀመሩትን የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም ከዳር እንደሚያደርሱ ተናግረዋል።ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ኮማንደር አበባ ነጋሽ በበኩላቸው በችግኝ ተከላው የተሳተፉት በአረንጓዴ ልማት መርሐ ግብር  ስኬት ተሳትፏቸውን  ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።ሴቶች በሁሉም መስኮች ከተሰማሩ የማያሳኩት ሥራ እንደሌለ ለማሳየትና በዓሉን ለማድመቅ ነው ብለዋል።የትግራይ ክልል ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር የትምወርቅ ገብረመስቀል እንዳሉትም ችግኝ ተከላው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም ስኬት የነበራቸውን ታላቅ አስተዋጽኦ ለማስታወስ የተዘጋጀ ነው። 
https://waltainfo.com/am/32662/
03f59ab317ffe5a3adf97c5f01ae6132
a65963efea008799304d0a58c35de08b
ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልእኮ በብቃት ማስፈም እንዲችል አዋጅና ደንቦችን የሚያሻሽል ረቂቅ አዘጋጀ
ሀገር አቀፍ ዜና
የፌዴራል የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የተሰጠውን ተልእኮ በብቃት ማስፈም እንዲችል አዋጅና ደንቦችን የሚያሻሽል ረቂቅ አዘጋጅቷል፡፡አዲስ በመዘጋጀት ላይ ካለው የከፍተኛ መንግሥት ባለስልጣናት የስነ ምግባር ደንብ በተጨማሪ በሀብት ማሳወቅና ማስመዝገቢያ እንዲሁም የስነምግባር መኮንኖች አሰራርን ለመወሰን በወጣው ደንብ ላይ ረቂቅ ማሻሻያዎች መዘጋጀታቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።ኮሚሽኑ የባለፈውና የቀጣይ በጀት አመቱን እቅድና አፈጻጸም አስመልክቶ በጋራ ከሚሰሩ የጸረሙስና ጥምረት አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሀብት ማስመዝገብ ላይ ያለው አፈጻጸም ደካማ መሆኑ በመድረኩ ተነስቶ ተገምግሟል።ኮሚሽኑ በስሩ የምርመራና አቃቤ ህግ ስራን አቀናጅቶ አለመስራቱ  ውጤታማ እንዳይሆን  አድርጎታል ተብሏል፡፡በሌላ በኩል ሙስና በሃገሪቱ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ያስችላል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት 3ኛው ሃገር አቀፍ የሙስና ቅኝት  ጥናት መጀመሩን  ኮሚሽኑ አስታውቋል።ከዚህ በተጨማሪም ሀገራዊ የፀረ ሙስና ፖሊሲና ስትራቴጂ የዝግጅት ሂደት መጀመሩንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አየልኝ ሙሉዓለም እንዳሉት የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅን ጨምሮ ተቋማዊ የውስጥ አሠራርን የተመለከቱ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።ብልሹ ስነ ምግባርንና ሙስናን የመዋጋቱ ስራ በተቋማዊ አደረጃጀት ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ የህብረተሰቡንና የሚመለከታቸው አካላትን የተቀናጀ ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32663/
62d6584434ce1456f93982c8c59bcdfe
242f77da3bfe3a0c0655cc4e8325e30c
የግብርና ሚኒስቴር ከቻይና አቻው 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የግብርና መሳሪያዎች ተበረከቱለት
ቢዝነስ
የቻይናው ግብርናና ገጠር ጉዳዮች ሚኒስቴር ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የግብርና መሳሪያዎችና ቁሳቁስ ለግብርና ሚኒስቴር አበርክቷል፡፡ርክክቡ ሲካሄድ የቻይናው አምባሳደር ሚስተር ታን ጄይን እንዲሁም በኢትዮጵያ በኩል የግብርናው ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ተገኝተዋል፡፡ርክክብ ከተደረገባቸው መሳሪያዎች መካል ትራክተር፣ ዘር መዝሪያ ማሽን፣ የአፈር መከስከሻ ማሽን፣ የሩዝና ስንዴ መውቂያ ማሽን፣ የጥጥ ዘር መፈልፈያ፣ ጀነሬተሮች እና የቢሮ መገልገያ እቃዎች ይገኙባቸዋል፡፡መሳሪያዎቹ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና ግብርናን ለማዘመን ከፍተኛ ሚና ያላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ ግብርና እድገት እያደረገ ላለው ድጋፍ የግብርናው ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ከፍተኛ ምስጋና ማቅረባቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/23911/
7c66cbe769e1cb45c356e261c0d563e5
459d7c28add12f1b09727b3888e6d82f
ኢትዮጵያና አሜሪካ የሕግ ማስከበር እና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት ተፈራረሙ
ፖለቲካ
የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚልና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይኖር መንግሥቶቻቸውን ወክለው የሕግ ማስከበር እና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱም ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ለፌደራል ፖሊስ እንዲሁም ለፍትህና ሕግ ማስከበር አካላት ድጋፍ በመስጠት የሕግ ማስፈጸም እና የፍትሕ ዘርፉን ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/31298/
c44f5c7231468258f3743ebf4e82b982
d69904632eba03cb6c2c7b324b02e290
ዛምቢያ ቀረጥ ያልከፈሉ ተሽከርካሪዎችን በድሮን እያደነች ነው ተባለ
ቢዝነስ
የዛምቢያ ግብር ባለሥልጣናት ቀረጥ ያልከፈሉ ተሽከርካሪዎችን በድሮን እያደነች ነው ተባለ፡፡ባለሥልጣናቱ ቀረጥ ሳይከፍሉ እቃዎችን የሚያዘዋውሩ ከባድ መኪናዎችን ለመቆጣጠር ድሮኖችን መጠቀም መጀመራቸው ነው የተገለጸው፡፡ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ የዛምቢያ ገቢዎች ባለሥልጣን በድሮኖች በመታገዝ ከዋናው መንገድ በመውጣት ተደብቀው የነበሩ ሰባት ተሽከርካሪዎች መያዛቸውን አስታውቀዋል።"ድሮኖቹ የፍተሻ ሠራተኞች በማይደርሱባቸው እንዲሁም አደጋ ባለባቸውና ጥንቃቄን በሚጠይቁ ቦታዎች ድረስ በመግባት አሰሳ ያደርጋሉ" ሲሉ የዛምቢያ ገቢዎች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ቶፕሲይ ሲካሊንዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።በዚህ ሰባት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ፍተሻ ድሮኖቹ 'ካፒሪ ስርነጅ' በተባለ መንገድ በመግባት ማሰስ የጀመሩ ሲሆን፣ ዋናው የተሽከርካሪ መንገድ ባዶ ሆኖ አግኝተውታል፤ ከዚያም ከዋናው መስመር 14 ኪሎሜትር በሚርቅ ጥሻ ውስጥ አመላክተዋል።በዛምቢያ ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በአብዛኛው ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ወይም ታንዛኒያ የሚመጡ ናቸው።ኃላፊው ሲካሊንዳ እንዳስታወቁት አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች በጣም በርካታ እቃዎችን ይጭኑና ወደ ፍተሻ ጣቢያው ሲቃረቡ በትንንሽ መኪና ቀንሰው ይጭናሉ ይህም ባለሙያዎቹ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገቡ ምክንያት ሆኗል።የዛምቢያ የገቢዎች መሥሪያ ቤት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ገቢውን ለማሳደግ ተስፋ እንዳለው የቀረጥ ባለሥልጣናት ጨምረው ተናግረዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/32902/
4d017611d6e72850179aca489eb27e6c
471016ee9772f625f38647278297913d
የጦር መሳሪያ በተሽከርካሪ ሲያዘዋውር የተያዘው ተከሳሽ በ2 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ
ሀገር አቀፍ ዜና
ተከሳሽ አብዱራህማን ዩኑስ ከሚመከለተው የመንግስት ፈቃድ ውጪ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ገደብ የተደረገባቸው የጦር መሳሪያዎችን በተሸከርካሪ ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲል ተይዞ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጥቷል፡፡ተከሳሽ 53 ቱርክ ስሪት ሽጉጦችንና 35 ሺህ 766 ጥይቶችን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A50931 አ.አ በሆነ ላንድክሩዘር መኪና ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲሞከር በተደረገው ክትትል በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ክልል ልዩ ቦታው ጣፎ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተሸከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ ተይዟል፡፡ተከሳሽ ክሱ በችሎት ተነቦለት እንዲረዳ ከተደረገ በኃላ ድርጊቱን ክዶ በመከራከሩ ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ ምስክሮች አሰምቷል፡፡ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ሽጉጥና ጥይት በመኪና ደብቆ በፍተሻ ስለመያዙ በመረጋገጡና መከላከልም ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ ጥፋተኛ መሆኑን በይኗል፡፡የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመመልከት ተከሳሽ በ2 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ5 ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል፡፡ምንጭ፡- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
https://waltainfo.com/am/32661/
bfaddc6489926597107a5a16b584bf5a
f094d0f1a768678f53f0869301d8de4e
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተወያዩ
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኳታር ምክትል ጠ/ሚርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተወያዩጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኳታር ምክትል ጠ/ሚርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራሕማን ቢን ጃሲም አል ታኒ ጋር ተወያዩ፡፡ሁለቱ ወገኖች ጠ/ሚሩ በመጋቢት ወር 2011 በኳታር ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተጀምረውን ውይይት በማስቀጠል በቁልፍ የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡ሼክ መሐመድ ከዚህ ቀደም ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተለይም በሆቴል፣ ስኳር ፋብሪካ፣ በቱሪዝም ልማትና አዳዲስ የኩላሊት ሕክምና ማዕከላት ግንባታን ለማስጀመር ዝግጁነት እንዳለ መግለጻቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።
https://waltainfo.com/am/31297/
d121ba09b55bfbdf66809442b0b8192b
fbdb68d7cc006275f5737ccefddba7d9
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የለውጥ ስራዎችን ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የለውጥ ስራዎችን ማስጀመሪያ መድረክ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም በተገኙበት በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገራችን የመጀመሪያውን የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ከሶስት አመታት በላይ ከፈጀ የዝግጅት ምዕራፍ በኋላ ከ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ፍኖተ ካርታው እስከ 2022 ዓ.ም የሚተገበር ሲሆን፣ 2012 ዓ.ም የመጀመሪያው የትግበራ አመት ይሆናል፡፡ ፍኖተ ካርታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ ችግሮችን ለይቶ መፍትሄዎችን አስቀምጧል፡፡የስርዐት ትምህርት አዘገጃጀት ይዘትና ትግበራ ችግር፣ የዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ አለመለየት፣ የትምህርት አደረጃጀት ችግር እና ሌሎችም አራት ችግሮች የተለዩ ሲሆን፣ በእነዚህ ችግሮች ምክንያትም የስነምግባርና የሞራል ውድቀት፣ ስርአት አልበኝነትና ምክንያታዊ አለመሆን፣ የስራ ጠባቂነትና ጥገኝነትን የመሳሰሉ ችግሮች በተማሪዎች ዘንድ ተስተውለዋል ተብሏል፡፡የአንደኛ አመት ተማሪዎችን የታሪክ፣ ጂኦግራፊና አንትሮፖሎጂ፣ የኮምፒውቴሽናል ክህሎት፣ የስነምግባር፣ የቋንቋ፣ የስነ ተግባቦት፣ ምክንያታዊነት፣ ቴክኖሎጂና አለምአቀፋዊ እውቀት ሊያስጨብጡ የሚችሉ ትምህርቶችን መስጠት፣ ዩኒቨርሲቲዎችን እንደ ተልዕኳቸው ትኩረት ማደራጀት ማለትም የምርምር፣ የአፕላይድ ሳይንስ እና ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲዎች አድርጎ ማደራጀት እና የዩኒቨርሲቲ ቆይታን አራት አመት እንዲሆን ማድረግ ለምህንድስና አምስት ለህክምና ስድስት አመት ለማስተርስ ዲግሪ ሁለት አመት እንዲሁም ለፒኤችዲ ዲግሪ ደግሞ አራት አመት ማድረግ ችግሮችን ከስር መሰረታቸው ለመፍታት በፍኖተ ካርታው የተቀመጡ የመፍትሄ ምክረ ሀሳቦች ናቸው ተብሏል፡፡ መረጃው የፕሬስ ኤጄንሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/32658/
ea8bc39e6fa56245ad7a594943fb9d8f
e72410a74b877de7766614e73221e56a
በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መድረክ በአሶሳ እየተካሄደ ነው::የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የአማራ፣የኦሮሚያና የጋምቤላ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መድረክ ሲሆን፤ የክልሎቹ አፈ ጉባኤዎች፣ የቢሮዎች ሀላፊዎች፣ እንዲሁም የአራቱ ክልሎች ተጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች አመራሮች በመታደም ላይ ናቸው፡፡የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከኦሮሚያ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጋራ የሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጋር በትብብር መድረኩን አዘጋጅተዋል፡፡ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበው የምዕራብ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሁለንተናዊ ሁኔታ፤ ፌዴራሊዝምና የሰላም እሴት ግንባታ፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝና የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች የጋራ ልማትና ሰላም ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
https://waltainfo.com/am/32659/
3146314a35ba1728df613058493da64e
2f719718200252d4a70ce08dbde2f454
በነብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ
ፖለቲካ
በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ የምርመራ ቡድኑ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በጠየቀው ይግባኝ ላይ የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ለነሐሴ 16/2011 አ.ም የጊዜ ቀጠሮ ሰጠ።በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ ሐምሌ 29/ 2011 ዓ.ም በነበረው የጊዜ ቀጠሮ የባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል ። ይህን ተከትሎም የምርመራ ቡድኑ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው የባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ዛሬ ጠይቋል።የምርመራ ቡድኑ “አዳዲስ ተከሳሾች ተይዘዋል። ቃል እየተቀበልን ነው። በድርጊቱ ዋና ተከሳሾች ካልተያዙ ክስ መመስረት አንችልም። በህክምና ላይ ያሉትን ምስክሮች ቃል የመቀበል ስራ እየተከናወነ ነው። በፌዴራል ከሚካሄደው ምርመራም ጋር የሚያያዙ ጉዳዮች አሉ። የቀዳሚ ምርመራ የሚሰሙ ብዙ ምስክሮች እያሉን የቀረቡት ጥቂቶቹ ናቸው” በሚሉ ምክንያቶች ተጨማሪ የይግባኝ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።የተከሳሾቹ ጠበቆች በበኩላቸው የጊዜ ቀጠሮው ይግባኝ የሚቀርብበት እንዳልሆነ እና ለምርመራ የተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ በቂ መሆኑን በመግለጽ ይግባኙን ተቃውመዋል።ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካደመጠ በኋላ በይግባኝ ክርክሩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነሐሴ 16/2011 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ቀጠሮ ሰጥቷል።(ዘገባው የአብመድ ነው)
https://waltainfo.com/am/31295/
82be198ac448fbed60ef19c3d03e8c59
b51ef2a18a3b2c813acf7160a7066921
የሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት የሉዓላዊ ምክር ቤት አባላትን ሰየሙ
ፖለቲካ
የሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት የሉዓላዊ ምክር ቤት አባላትን ሰየሙ፡፡አባላቱ ዛሬ ቃለ መሀላ እንደሚፈፅሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ከመሃላው በፊት ሀገሪቷን እያስተዳደረ የሚገኘው ወታደራዊው መንግስት ከሲቪል ተወካዮች በሁለት በልጦ አባል መርጦ አዘጋጅቷል፡፡አባላቱም በምክር ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የሚኖራቸው ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡ሱዳን ሰላም አጥታ ለበርካታ ወራት ስትታመስ ከቆየች በኋላ ለህዝቡ ጥያቄ የመጨረሻ እልባት መፍትሄ ሰጭ የተባለለት የስምምነት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡የሀገሪቷ የአስተዳደር አካል ከወታደራዊው አገዛዝ ይልቅ ህዝባዊ አካል ሀገሪቱን ሊያስተዳድር ይገባል የሚል ሀሳብ በተቃዋሚ የፖለቲካ አመራሮች ሲመራና ሲራመድ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡በዚህ ሀሳብ በገዥው ወታደራዊው መንግስት እና በህዝብ መካከል ከፍተኛ መተራመስ በመፈጠሩ ከ127 በላይ ሱዳናዊያንም ሞት እና ለባርካቶች አካላቸው ጉዳት ምክንያት ሆኗል፡፡ ሱዳን ሰላም እንድታገኝ እና በገዢው አካል መካከል ሰላም እንዲወርድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ጥረት ሲያደርጉም ቆይተዋል፡፡በስተመጨረሻም ሁለቱ አካላት ስምምነት ላይ ደርሰው ዛሬ መቋጫዉን ሊያገኝ ስልጣን ላይ ያለው ወታደራዊው መንግስት እና የሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ አባላት የስልጣን ክፍፍል ሊያደርጉ የሉዓላዊ ምክር ቤት አባሎቻቸዉን መርጠው አዘጋጅተዋል፡፡ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት ወታደራዊው መንግስት ከሲቪሊያኑ በሁለት ከፍ ብሎ ሰባት በምክር ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የሚኖራቸዉን አባሎቻቸዉን መርጠዋል፡፡በዘመነ አልበሽር ሱዳን በከፍተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ያን ያህል ነበር፡፡ ከዚህ አካሄድ ለየት ባለ መልኩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመረጧቸው አባላቶቻቸው ውስጥ ሴቶችን አካተዋል ነው የተባለው፡፡ሁለቱ አካላት ሰልጣን መጋራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ቅዳሜ ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ የመጨረሻ መሃላ ሊፈፅሙ የምክር ቤቱ አባላቶቻቸዉን አዘጋጅተዋል፡፡አባላቶቹ በምክር ቤቱ ከፍተኛ ስልጣን የሚኖራቸው ቢሆንም ትልቁ ኃላፊነታቸው ለካቢኒው የሚሰሩ ነው የሚሆነው፡፡ ሱዳን አጥታ ለነበረው ሰላም እና ህዝቡ ሲያነሳ ለነበረው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ ነው የተባለው ይህ ስምምነት ዛሬ ላይ በርካታ ሱዳናዊያን በካርቱም እና በሌሎች ከተሞች ጎዳና እንዲወጡ ምክኒያት ሆኗቸዋል፡፡ ደስታቸዉን ለመግለጽ እና የፊርማ ስምምነቱን ለማክበር ሲባል፡፡ሁለቱ አካላት ዛሬ የመጨረሻ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙ ሲሆን፣ በስምምነታቸውም መሰረት ወታደራዊው ሽግግር መንግስት ለ21 ወራት ስልጣን ላይ የሚቆይ ሲሆን የሲቪሉ አካል ደግሞ ለሚቀጥሉት 18 ወራት ስልጣን በመጋራት በጋራ ሱዳንን ያስተዳድራሉ፡፡(ምንጭ፡-ሚድል ኢስት እና አልጄዚራ)
https://waltainfo.com/am/33325/
0ca9d275c446783afdaed2dcab7bf279
92ccac663eae894c8ca1df1cb8e60e3f
የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በከተማዋ እየታደሱ የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በከተማ አስተዳደሩና በባለሀብቱ እየታደሱ የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ፡፡በከተማ አስተዳደሩ 488 የመንግስት ትምህርት ቤቶች እየታደሱ የሚገኙ ሲሆን፣ አሁን ወደ መጠናቀቅ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ነው የተባለው፡፡የትምህርት ቤቶቹ እድሳት ለተሻለ መማር ማስተማር እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር ለተማሪዎችም ሆነ ለአስተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት ማደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡ከእድሳት እና ጥገና ስራዎች በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ በየትምህርት ቤቶቹ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለተማሪዎች የአረንጓዴ ቦታ እና ምቹ የመመገቢያ አዳራሾች በአዲስ መልክ የሚደራጁ ይሆናልም ነው የተባለው፡፡ምክትል ከንቲባው በጉብኝታቸው ወቅት በየትምህርት ቤቶቹ በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ከፍተኛ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች ጋርም ቆይታ አድርገዋል፡፡ከንቲባው በዛሬ ጉብኝታቸው በአስሩ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች እድሳት ሂዴትን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡
https://waltainfo.com/am/32657/
8620ab35fd6596430e56fc2ef49a9879
7dd49c46bfb74798ea2255933bbae3a2
በካቡል ከተማ አንድ ሠርግ ላይ የፈነዳ ቦንብ 63 ሰዎችን ሲገድል 180 ሰዎችን አቁስሏል
ሀገር አቀፍ ዜና
በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል አንድ ሠርግ ላይ የፈነዳ ቦንብ 63 ሰዎችን ሲገድል 180 ሰዎችን አቁስሏል፡፡የዓይን እማኞች አንድ አጥፍቶ ጠፊ ቦንቡን ተሸክሞ መጥቶ እንዳፈነዳው የተናገሩት፡፡ቦንቡ የፈነዳው ቅዳሜ ምሽት 4፡40 ገደማ ሲሆን ሥፍራው ደግሞ የሺያ ሙስሊሞች የሚያዘውትሩት የካቡል ምዕራባዊ ክፍል ነው ተብሏል።ታሊባን 'እኔ እጄ የበለትም' ሲል አስተባብሏል። እስካሁን ለጥፋቱ ኃላፊነት የወሰደ ቡድን የለም። ራሳቸውን ከሱኒ ሙስሊሞች ጋር የሚያቆራኙት ታሊባን እና አይ ኤስ ከዚህ በፊት የሺያ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ይታወሳል።የአፍጋኒስታን ሃገር ውስጥ ሚኒስትር አደጋው ከደረሰ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የሟቾችን እና የተጎጂዎችን ቁጥር ይፋ አድርገዋል።ወንዶች እና ሴቶች ለየብቻ ሆነው የሚስተናገዱበት የአፍጋኒስታን የሠርግ ሥነ-ሥርዓት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ይታደሙበታል።'አጋጣሚ ሆኖ ቦንቡ ሲፈነዳ እኔ ከሴቶች ጎራ ነበርኩ' የሚለው ሞሐመድ ፋርሃግ 'ከፍንዳታው በኋላ ሰዎች ሁላ እግሬ አውጭኝ እያሉ ሲወጡ ተመልክቻለሁ' ሲሉ ኤኤፍፒ ለተሰኘው የዜና ወኪል ተናግሯል።ከ10 ቀናት በፊት ካቡል ውስጥ በሚገኝ አንድ ፖሊስ ጣብያ የፈንዳ ቦንብ የ14 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ አይዘነጋም። ታሊባን ጥፋቱን የፈፀምኩት እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነቱን ወስዷል።ባለፈው አርብ ደግሞ የታሊባን አለቃ ወንድም የሆነው ሂባቱላህ አኩንደዛዳ መስጅድ ውስጥ ሳለ በተመጠደ ቦንብ ሕይወቱ አልፏል።አፍጋኒስታን ውስጥ በርካታ ወታደሮች ያሏት አሜሪካ ከታሊባን ጋር ድርድር ውስጥ እንዳለች እና በጎ ጅማሬዎች እንደታዩ ዕለት አርብ ፕሬዝደንቷ ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ማወጃቸው አይዘነጋም። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34128/
f526033c11de4c5875b696672c701e7e
ba9fb1c1781eb2ab5610add702dd8efa
የመንግስታቱ ድርጅት ለሱዳን ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈ
ፖለቲካ
በሱዳን ህዝባዊ መንግስት እንዲመሰረት መደላድል የሚፈጥር ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጽሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለአገሪቱ ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሱዳን የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ያደረገ ስምምነት መፈረሙን አስመልክቶ የድጋፍ መግለጫ አውጥቷል፡፡በዚህም የሱዳን ህዝብን የቆየ የዲሞክራሲና የሰላም ምኞት ለማሳካት ብሎም የአገሪቱን የሽግግር ጊዜ ለመደገፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቁርጠኛ መሆኑን የተቋሙ ዋና ጽሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናግረዋል፡፡አያይዘውም የአገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲያገግም በማድረግ ዘላቂ ልማት ለማምጣት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡በሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤትና በተቃዋሚ ሀይሎች መካል የተፈረመው የስምምነት ሰነድ ሁለቱ ኃይሎች ስልጣን በመጋራት የሽግግር መንግስት መመስረት የሚያስችላቸው ነው፡፡ስምምነቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በተገኙበት ትላንት በካርቱም መፈረሙ ይታወቃል፡፡ (ምንጭ፦ ሽንዋ)
https://waltainfo.com/am/33324/
b0e470079a9bd7a21e66229b4e571690
ee4e8da8d63c8409821c3a8180eb38cc
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሳዑዲ  አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ጋር በስልክ ተወያዩ
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሳዑዲ አረቢያ አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡በዚህን ወቅት የሳዑዲው አልጋወራሽ ኢትዮጵያ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት እንዲፈፅሙ  የነበራትን የሸምጋይነት ሚና አድንቀዋል።በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት ሳዑዲ  እንደምትደግፍ መናገራቸውን የዘገበው የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ነው።የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል ስልጣን መጋራት የሚያስችላቸውን የመጨረሻ ስምምነት ከቀናት በፊት መፈራረማቸው ይታወሳል።
https://waltainfo.com/am/31294/
b80697cc1054d753174d598532d2293d
78f92e9fa93023a528d9d494201ea1d0
ሦስት ዓመት የነበረው የዩኒቨርሲቲ የዲግሪ መርሀ ግብር ቆይታ ወደ 4 ዓመት ከፍ እንዲል ተወሰነ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሦስት ዓመት የነበረው የዩኒቨርሲቲ የዲግሪ መርሀ ግብር ቆይታ ወደ 4 አመት ከፍ እንዲል ተወሰነ፡፡በ2012 ዓ.ም ወደ መንግሥትም ሆነ የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ አዲስ የመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩት በ15 አዳዲስ ትምህርቶች መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል።በሦስት ዓመታት ይጠናቀቅ የነበረው የዲግሪ መርሀ ግብርም ወደ አራት ዓመት ከፍ እንደሚል ነው የገለጸው።በዚህ ሂደት እንዲያልፉ የሚደረጉትም በ2012 ዓ.ም ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች እንደሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሚሰጡት የትምህር ዓይነቶች ለሁሉም የትምህርት ክፍሎች የጋራ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡ትምህርቶቹም ተማሪዎች በአስተሳሰብ ምጡቅ እንዲሆኑ፣ ብዝሀነትን፣ የሀገርን ባህል፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶችንና ታሪክ እንዲያውቁ የሚያደርጉ ናቸው ብሏል ኤጀንሲው፡፡የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት፣ ስነምግባር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በሚመለከት የሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት እንዴት ይቃኝ? በሚል ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በምሁራን ሰፊ ጥናት ሲደረግና ሕዝብም ሲወያይበት መቆየቱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱአለም አድማሴ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ አስረድተዋል፡፡ በሂደቱም ማሻሻያ እና ለውጦች ተደርገዋል።በዚሁ መሰረትም በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች አዳዲስ የትምህርት ዓይነቶችን መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሶ ለዚሁ ዝግጅት መደረጉን፣ አሁን ያለው ሁኔታም ትምህርቱን ለመጀመር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32654/
9fbad3d43f70f3a59dfeae8f7c0b66eb
251827161458c4b4f50a6eb12e1f9f62
ጳጉሜ ‘ጳጉሜን በመደመር’ በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይታሰባል
ፖለቲካ
‘ጳጉሜን በመደመር’ በሚል መሪ ሀሳብ ሀገራዊ የመርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የመደመር ስድስት ምሰሶዎችን ባማከለ መልኩ  ጳጉሜን በመደመር ሀገር አቀፍ መርሃ ግብር መዘጋጀቱን ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡ የተለያዩ የመንግስት አካላት የየዕለት እንቅስቃሴዎቹን ለማቀድ ፣ ለመምራት፣ ለማስተባበርና ለማስፈፀም ሀላፊነት ወስደው እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል እየፈፀሙ፡፡ በዚህም መሰረት  የጳጉሜን ስድስቱ ቀናት ስያሜ እና አስተባባሪዎች ይፋ የሆኑ ሲሆን ጳጉሜን 1 ብልፅግናን የወከለ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስተባባሪነት፣ ጳጉሜን 2 ደግሞ የሰላም ቀን ሲሰኝ በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፊሪያት ካሚል እንደሚመራ ነው የተገለፀው፡፡ ጳጉሜን 3 ሀገራዊ ኩራት የሚል ስያሜን ሲሰጠው በማስተባበር በኩል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ሀላፊነቱን ወስደዋል፡፡ ጳጉሜን 4 ዲሞክራሲ የሚል ስያሜን በትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተሰጠ ሲሆን ዕለቱን በአስተባባሪነት የሚመሩት ይሆናል፡፡ ጳጉሜን 5 የፍትህ ቀን ሆኖ እንዲታሰብና  የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ እንደሚያስተባብሩት ተመልክቷል፡፡ የመጨረሻው እና የአዲስ አመት ዋዜማው ጳጉሜን 6 ደግሞ የሀገራዊ አንድነት ቀን ሆኖ ታስቦ እንዲውል ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ህብረተሰቡም በእነዚህ ቀናት ሰፊ ተሳትፎ በማድረግ ወደ መጪው አዲስ አመት ተስፋን ሰንቆ ለመሻገር እንዲሰናዳ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡  
https://waltainfo.com/am/31302/
c25681405f265453af06484b8d0ce4dd
1a89439c204a9510e7cab71e2ad13c08
ጠ/ሚ ዐቢይ በሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ሸንጎና የነፃነትና ለውጥ ኃይሎች መካከል በተደረገው የመጨረሻ የስምምነት ፊርማ ላይ ተገኙ
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነሐሴ 11 ቀን 2011 ወደ ሱዳን ካርቱም በመጓዝ በወታደራዊ የሽግግር ሸንጎና በነፃነትና ለውጥ ኃይሎች መካከል የተደረገውን የመጨረሻውን የስምምነት ፊርማ ተከታተሉ::ይህ የመጨረሻው ስምምነት ወታደራዊ ያልሆነ መንግስት ለመመስረት መንገድ ከፋች ነው ተብሏል::ከስምምነት ፊርማው ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከነፃነትና ለውጥ ኃይሎች አባላት ጋር ተወያይተዋል:: አባላቱ  ለዚህ ስምምነት መፈረም የተጫወተችውን ሚና በማድነቅ እነዚህ ሕገ መንግስታዊና ፖለቲካዊ ስምምነቶች ለዘላቂ ዴሞክራሲያዊና ልማት መሰረት ይጥላል ብለዋል::ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው፣ ይቅርታንና አንድነትን በመንከባከብ እንዲተጉ በማበረታታት ስኬታማ ውይይት መልካም መነሻ እንጂ ብዙ ስራ የሚጠይቀው መንገድ ከዚህ ቀጣዩ ነው ብለዋል::ሴቶች በፖለቲካ አመራር ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ለዚህም አካታች እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በተያያዘም የኢትዮጵያን ልምድ በማንሳት የነፃነትና የለውጥ ኃይሉ ይህንን 50-50 የፆታ አካታች ካቢኔ እንዲተገብሩ አስታውሰዋል::በሱዳን ስምምነት ፊርማው ስነስርዓት በማስከተል ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀገሪቱ በሚደረገው የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ወቅት የሱዳን ህዝቦች የሰላማቸውና የክብራቸው ተንከባካቢዎች እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል::በሱዳን ጉዞአቸው ማብቂያም ከመቶ በላይ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወደሌላ ሀገር ለመሻገር ሱዳን የቀሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ይዘው ተመልሰዋል:: ከነዚህም ውስጥ በተለያየ ጥፋት እስር ቤት የነበሩም ይገኙበታል ነው የተባለው፡፡ መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31293/
08146dc22bf3e437baa507017471437e
f5e509c7d7e54b57753c6b3c6f677181
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በሱዳን የሽግግር መንግሥትን ምስረታ ስነ ስርዓት ላይ ለመታደም ካርቱም ገቡ
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ  የሚመሩት ልዑክ በሱዳን የሽግግር መንግሥትን ምስረታ ስነ ስርዓት ላይ ለመታደም  ካርቱም ገብቷል።በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማኅበራዊ ገጹ እንዳስነበበው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት ልዑክ ዛሬ ወደ ሱዳን ያቀናው በሱዳን የሽግግር መንግሥትን በይፋ ለመመሥረት በሚከናወነው ሥነ-ሥርዓት ለመታደም ነው፡፡ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሐሰን ኦማር አልበሽር መንግሥት የሦስት አስርት ዓመታት ቆይታው በሕዝባዊ ተቃውሞ ተናግቶ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሲመሠረት ሱዳን ወደ ቀውስ እንደምትገባ ብዙዎች ገምተው ነበር፡፡ነገር ግን ኢትዮጵያና የአፍሪካ ሕብረት ባደረጉት ተከታታይ ጥረት ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱና ሲቪል የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በዚህም ሱዳን ወደ መረጋጋት እንደምትገባ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ የሽግግር መንግሥቱ ምሥረታ ላይ ለመገኘትም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ  የሚመሩት ልዑክ ዛሬ ጠዋት ካርቱም ገብቷል፤ ደማቅ አቀባበልም ተደርጎለታል ሲል የአማራ መገናኛ ብዙሃን ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31292/
0f10341103d746180e7c6d733f4f18e9
a3f1423290663d9bde1897dd20ddc959
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የ2019 የዓለም የቱሪዝም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ በሀገሪቱ ቱሪዝም ዘርፍ ባበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የ2019 የዓለም የቱሪዝም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን በብሪታኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።ሽልማቱንም የፊታችን ህዳር ወር ላይ በለንደን ከተማ በሚካሄደው የዓለም የቱሪዝም ሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የሚቀበሉ ይሆናል።የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሀምሌ ወር መጨረሻ ላይ ከአለም የቱሪዝም ፎረም ፕሬዚዳንት ቡሉት ማግቺ ጋር መወያየታቸው ይታወቃል።በውይይታቸውም ተቋማቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 የሚካሄደውን የአለም የቱሪዝም ፎረም በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳለው በሉት ማግቺ መናገራቸው በማስታወስ ኤፍ ቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/32652/
9453d5723ec499b9f9b8bf8d3e640da6
ca97aed92c4bd754f09b776913e8d3e7
የፅዳት ዘመቻ ተግባር ባህል ሆኖ እንዲቀጥልና ህብረተሰቡ ለሀገራዊ ጥሪ የሚያሳየው ምላሽ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
የፅዳት ዘመቻ ተግባር ባህል ሆኖ እንዲቀጥል እና ህብረተሰቡ ለሀገራዊ ጥሪ የሚያሳየው ምላሽ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ፡፡አራተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ይፋ በተደረገው እና ወር በገባ የመጀመሪያው እሁድ በመላ ሀገሪቱ  የሚከናወነው የጽዳት ዘመቻ በአዲስ አበባ ከተማ ስቴድየም እና የኦሮሞ ባህል ማከል አካባቢ ተከናውኗል፡፡የኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የተሳተፉበት የፅዳት ዘመቻ በአዲስ አበባ ኦሮሞ ባህል ማእከልና አካባቢው የተካሄደ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ስቴድየም ደግሞ የከተማው ነዋሪዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የተለያዩ ተቋማት የጽዳት ስራውን አከናውኗል፡፡የኦሮሚያ ክልል ርአሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሴፈዲን መሀዲ ንጽህናው በተጠበቀ አካባቢ የሚኖርና  በጥሩ አስተሳሰብ የተገነባ ማህበረሰብ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በጽዳት መረኃግብሩ የተሳተፉ አካላትም አካባቢን ከቆሻሻ ጽዱ በማድረግ ጥላቻና መጥፎ አመለካከቶችን ማስወገድ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32655/
725b024510f5a7cf8793af2462dcf7c2
800d2ecdc60dd0d85e55e49c2373241b
የኬንያው ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲቫል ላይ ይሳተፋሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና የኮሚቴው አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ኢትዮጵያውያን በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነው የማይለወጡ እና ለድርድር የማይቀርቡ የኬንያውያን ወዳጆች ናቸው ብለዋል።ኢትዮጵያ ከቅድመ-ነጻነት ጊዜ ጀምሮ የኬንያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ እንደሆነች ያስታወሱት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ፤ በኢትዮጵያ በጳጉሜን 2 እና 3፣ 2011 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ፌስቲቫል ላይ "እንደ እንደራሳችሁ፤ እንደ ኢትዮጵያውያን ሆኜ እገኛለሁ" ብለዋል።መሪዎች ለሕዝቦቻቸው ሰላም እና ብልፅግናን እንጂ ውድቀትና ጥፋትን ማውረስ አይገባም ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።የሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ፌስቲቫሉን ያዘጋጀው እና በበጎ ፈቃድ የተቋቋመው የሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ አባላት ፕሬዚደንትዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፤ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲባል ላይ እንዲታደሙ ጋብዘዋቸዋል።ኬንያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ያወሱት ዶ/ር ሙላቱ፤ ከኬንያ ግጭትን የማስወገድ ተሞክሮ እንዲያጋሩም ጠይቀዋል። ከፕሬዚደንቱ በተጨማሪ ለቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኢላ ኦዲንጋ በፌስቲቫሉ ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ የቀረበላቸው ሲሆን፤ ለመሳተፍ ቃል ገብተዋል።ሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ ሰላሟ እና ልማቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚል ዓላማ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከስነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ከወጣቶች እና ከሲቪል ማህበረሰብ አባላት የተዋቀረ ኮሚቴ ነው።
https://waltainfo.com/am/32653/
9a54309a7672d2a8939a91b341c147be
d54a1d029a704569740e10ea2dc331d6
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሳተፉበት የጽዳት ዘመቻ በአርሲ ዞን ኢተያ ከተማ ተካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ታስቦ የሚካሄደውን አገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ኢተያ ከተማ በመገኘት አከናውነዋል፡፡የጽዳት ዘመቻው የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተካሄደው።ከጽዳት ዘመቻው ቀጥሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካናቸው ጋር በመሆን በአርሲ ዞን ዲገሉና ጢጆ ወረዳ ሙኔሳ አካባቢዎች የኩታ ገጠም ግብርናን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡አገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻው ዛሬ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ  አካባቢዎች ተካሂደዋል፡፡ (ምንጭ:-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/32656/
f2f8feb55d2d01f2f35cc7407c372881
9f6de2c79069c661157c8a872f9e13ce
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ
ፖለቲካ
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ ወደ ተጨባጭ እንቅስቃሴ እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን ያቀረቡት የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎቸ ከዚህ ቀደም የደረሱትን የቅድመ ሽግግር የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ሂደት ለመገመገም የተጠራው ስብሰባ ዛሬ አዲሰ አበባ በሚገኘው ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በተጀመረበት ወቅት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው።የቅድመ ሽግግር ጊዜው የደቡብ ሱዳን ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት እኤአ ሜይ 12 ቀን 2019 ዓም በአዲስ አበባ ባደረጉት ውይይት በደረሱት ስምምነት መሰረት እስከ ኖቬምበር 2019 ዓም ድረስ ለ6 ወራት ያህል መራዘሙ ይታወቃል።ስምምነቱ እንዲራዘም መግባባት ላይ ከተደረሰ ጊዜ አንስቶ ወደ ሌላ አገር የተሰደዱ የደቡብ ሱዳን ህዝቦች እና ተቃዋሚ ሃይሎች ወደ ጁባ በመመለስ መኖር መጀመራቸው በፓርቲዎች መካከል መተማመን የፈጠረ መሆኑን እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ያለው ግድያ እና ተኩስ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ በደቡብ ሱዳን ሰላምን ለማስፈን አበረታች ጅምር መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ገልጸዋል።ይሁን እንጂ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተግባራዊ መደረግ ያለባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ማለትም የጋራ የፀጥታ ሃይል ምስረታ፣ የሰው ሃይል ስልጠናና ስምሪት፣ የክልላዊ መንግስታትን ቁጥር የመወሰንና መስል ስራዎች አፈፃፀም አዝጋሚና ዝቅተኛ መሆኑን በማስታወስ ሁሉም ፓርቲዎች ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ጥቅም ሲሉ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ እንዲሆኑ ክቡር ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።በዛሬው ውይይት የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኢጋድ አባል አገራት፣ የኢጋድ ባለድርሻ አካለት ፎረም፣ የትሮይካ፣ የቻይና፣ የውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካለት ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።ስብሰባው በደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማደረግ የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት በማዳመጥ እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማመላከት በዛሬው እለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31301/
0ce38b93993ce9b149ecc4c8484fab49
ed34024040bc7aa534d79fa9ccde6162
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒን ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒን ጋር ተወያዩ፡፡ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማሳደግ በትምህርት፣ የመካከለኛ አመራር ደረጃን የማሳደግ ስልጠና እና የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም በማጎልበት ረገድ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ፕሬዝዳንቷ በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒ በበኩላቸው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ዘርፈ ብዙ መሆኑን አንስተው ይህንን ለማጠናከር በትምህርት፣ በጤና እና በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ሀገራቸው ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል፡፡ሚኒስትሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም መረጋገጥ እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀው በተለይ በቅርቡ በሱዳን መረጋጋትና በሰላማዊ የስልጣን ክፍፍሉ ላይ የነበራትን ሚና ልዩ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መረጃው የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31299/
2c5faa21aa891b855d234a53f20e36a4
4cab5669c067b9bfa47b772023fa19b2
በኬንያ ሠርግ ከታደሙ መካከል አንድ ሰው በኮሌራ ሲሞት 40 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
በኬንያ መዲና ናይሮቢ ባለፈው ቅዳሜ በተከናወነ የሠርግ ሥነ ሥርዓት ላይ ከታደሙት መካከል አንድ ተጋባዥ በኮሌራ ሳቢያ ሕይወቱ ሲያልፍ ሌሎች 40 የሚሆኑት ለሕክምና ሆስፒታል መግባታቸውን ዘ ስታር የተባለው ጋዜጣ ዘገበ።ጋዜጣው ጭምሮ እንደገለፀው የሠርጉ ተጋባዦች የሕክምና ምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው ተጋባዥ እንግዶቹ ሠርጉን ከታደሙ በኋላ ለኮሌራና የምግብ መመረዝ እንደተዳረጉ ያሳያል።አዲስ ተጋቢ ጥንዶቹ ግን ምንም ዓይነት የጤና መቃወስ ያልገጠማቸው ሲሆን፣ በሠርጋቸው ዕለትም ለጫጉላ ሽርሽር ወደ ዱባይ በረዋል።ይሁን እንጂ የሙሽራው አያት በዚሁ ምክንያት ባሳለፍነው ማክሰኞ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።በሠርግ ሥነ ሥርዓቱ ላይ 450 የሚሆኑ እንግዶች ተጋብዘው እንደነበር ጋዜጣው አስፍሯል።የሠርግ ሥነ ሥርዓቱ አሠናጅ ይህ ችግር እንዴት ሊከሰት እንደቻለ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።ኮሌራ በዲያሪያ ኢንፌክሽን የሚመጣ ሲሆን ባክቴሪየም ቫይብሪኦ ኮሌራ በተባለ በሽታ አምጭ ተህዋስ ምግብና ውሃ ሲመረዝ ይከሰታል።በኬንያ የኮሌራ በሽታ መከሰት የተለመደ ባይሆንም ከሁለት ዓመታት በፊት ግን በመዲናዋ በአንድ ሆቴል በተካሄደ ዓለም አቀፍ የጤና ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ላይ ወረርሽኙ ተከስቶ እንደነበር ተነግሯል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
https://waltainfo.com/am/33464/
7f6b39dbe30d9813a929aea245fe5c9c
da4160150eaafff4087ae1de41c0f564
የተመድ ዋና ጸሐፊ እና ስምንት የአፍሪካ ሀገራት ርእሳነ መንግሥታት በሱዳን የለውጥ ስምምነት ላይ ይገኛሉ
ፖለቲካ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት ርእሳነ መንግሥታት፣ የአውሮፓ ኅብረት ፕሬዚዳንት እንዲሁም የአረብ እና የምዕራባውያን ሀገራት መሪዎች ቅዳሜ ዕለት በሱዳን በሚደረገው የፖለቲካ ለውጥ እና ሕገ-መንግሥት የማፅደቅ ስምምነት ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።የሱዳን የነፃነት እና የለውጥ ኃይሎች እና የወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ታሪካዊ የተባለውን ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸው ይታወሳል።በስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ይገኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር የሆኑት የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ፣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፣ የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሞሳ ፋቂ ናቸው።በዚህ ታሪካዊ ስምምነት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች፣ ስድስት ሀገራትን ያከተተው የገልፍ ኅብረት ምክር ቤት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ሌሎች የባሕረ-ሰላጤ ሀገራት መሪዎች እንደሚገኙም ይጠበቃል።ቅዳሜ ዕለት ለሚደረገው ሕገ-መንግሥት የማፅደቅ ስምምነት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፤ ስምምነቱ የወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀበንበር አብዴል ፋታህ አል-ቡርሃንን የመጀመሪያው የሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ያደርጋቸዋል ተብሏል።(ምንጭ፦አልሸርቅ አል-አውሳጥ)
https://waltainfo.com/am/33323/
0aeffd520b1af60282af97f0748a19d9
a5c7f30cc9232a6d24006f3179d92370
የፌዴራል ፖሊስ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽንና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
ቢዝነስ
የፌዴራል ፖሊስ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽንና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሙስና ጨርሶ እንዳይፈፀም በጋራ ለመከላከልና ተፈፅሞም ሲገኝ ለመመርመር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ስምምነቱ በዋናነት የተደራጀ የፀረ ሙስና ዘመቻ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡በተለይም በአገሪቱ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የሆነ የሙስና ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያስችል ስምምነት መሆኑም ተገልጿል፡፡ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለመፍጠር በሚደረገው አገራዊ ጥረት ሶስቱም ተቋማት ተጠናክረው ተግባሩን በጋራ ለመከላከል በቅንጅት እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡የምርመራውን ስራ ፌዴራል ፖሊስ፣ የመክሰሱን ስራ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እንዲሁም ሙስናን የመከላከሉንና የማስተማሩን ስራ ፀረ ሙስና ኮሚሽን እንደሚሰሩ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህንኑ በቅንጅት ለመስራት ነው ስምምነቱ የተፈረመው፡፡ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመከላከል ደክሟል በሚል በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሳውን ቅሬታ በማስተካከል በቀጣይ ሙስናን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል የሚያስችል ስራ እያከናወነ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/23910/
90c6e80abfcf089746ce766265f4e53b
de54e50dad18307c066d422e514cd251
የደቡብ ክልል አደረጃጀት ጥናት የምክክር መድረክ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
ፖለቲካ
የደቡብ ክልል አደረጃጀት ጥናት የምክክር መድረክ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) በአዲስ አበባ እና በአዳማ ሲያካህድ የቆየውን የክልል አደረጃጀት ጥናት ምክክር መድረክ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል።በውይይት መድረኩ ላይ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ አመራሮች እና የቀድሞ ነባር አባላት ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ሲያካሄዱት የነበረው ውይይት እንዲሁም የአዳማው የአዲስ አበባ ከተማ የደኢህዴን አመራር መድረክ ሪፖርት ቀርቧል፡፡በዚሁም በውይይቱ ላይ የተንሸራሸሩ ሀሳቦች በየቡድን መሪዎች በሪፖርት መልክ ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡መድረኩን እየመሩ የሚገኙ የደኢህዴን ሊቀ መንበርና የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል፣ ውይይቶቹ አመራሮቹን በአንድነት ውስጥ ያለውን ሀይል እንዲገነዘቡ ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡በዛሬው ውይይት ላይ በደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥናትና በመጨረሻው ምክረ-ሃሳብ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶች መኖራቸውንና ሌሎች የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡ሰሞኑ ከክልል ውጭ ባሉ የደኢህዴን አመራሮች ደረጃ የደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥናት ዙሪያ ውይይት ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31291/
3e92fc15ebd5318f383cfd77091ee850
a27204ab28e0341787f84046001856aa
በሀገሪቱ የሚፈጠሩ ግጭቶችንና አለመረጋጋትን ለመፍታት የሴቶችን ከፍተኛ ሚና መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
በሀገሪቱ የሚፈጠረውን ግጭትና አለመረጋጋት ከመፍታት ረገድ ሴቶች ያላቸውን ሚና በሚመለከት ውይይት ተደረገ፡፡በኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽንና ሰላም ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡በውይይት መድረኩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ሲፈጠሩ የመጀመሪያ ተጎጂዎች ሴቶች የመሆናቸውን ያህል ችግሮችን ለመፍታት ደግሞ ሴቶች ከየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል በላይ ቅርበት አላቸው ተብሏል፡፡ሴቶች ልጆቻቸውን፣ ባሎቻቸውና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን በቅርበት የማግኘት ዕድሉ ስላላቸው ችግሮችን መፍታት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተፈጠሩ ችግሮችን ከመቅረፍ ረገድና ሰላም እንዲሰፍን ሴቶች ጉልህ ሚና እንደነበራቸውም ተጠቁሟል፡፡በውይይቱ ላይ የተገኙት የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ፤ ቀደም ባሉት ጊዜያት በሀገሪቱ በነበረው አለመረጋጋት ሴቶች የሚጠበቅባቸውን ያህል ሚናቸውን አልተወጡም ብለዋል፡፡በመሆኑም ይህንን ታሳቢ በማድረግ በቀጣይ በሀገሪቱ ሰላን በማስጠበቅ በኩል ሴቶች ተፈጥሯዊ ፀጋዎችን በመጠቀምና ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32651/
fe4f087cd5e757b6303b97e2b88d032d
f14ee68c5392f001ea0b9c8fc181277b
የኬንያው ፕሬዚደንት ጳጉሜ 2 እና 3 በአዲስ አበባ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲቫል ላይ እንደሚሳተፉ አስታወቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
የኬንያው ፕሬዚደንት ጳጉሜ 2 እና 3 በአዲስ አበባ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲቫል ላይ እንደሚሳተፉ አስታወቁፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና የኮሚቴው አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ኢትዮጵያውያን በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነው የማይለወጡ እና ለድርድር የማይቀርቡ የኬንያውያን ወዳጆች ናቸው ብለዋል።ኢትዮጵያ ከቅድመ-ነጻነት ጊዜ ጀምሮ የኬንያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ እንደሆነች አስታውሰው፤ በጳጉሜን 2 እና 3፣ 2011 ዓ.ም. በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ፌስቲቫል ላይ እንደ ኢትዮጵያውያን ሆኜ እገኛለሁ ብለዋል።መሪዎች ለሕዝቦቻቸው ሰላም እና ብልፅግናን እንጂ ውድቀትና ጥፋትን ማውረስ አይገባም ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።የሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ፌስቲቫሉን ያዘጋጀው እና በበጎ ፈቃድ የተቋቋመው የሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ አባላት ፕሬዚደንትዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፤ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲባል ላይ እንዲታደሙ ጋብዘዋቸዋል።ኬንያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ያወሱት ዶ/ር ሙላቱ፤ ከኬንያ ግጭትን የማስወገድ ተሞክሮ እንዲያጋሩም ጠይቀዋል።ከፕሬዚደንቱ በተጨማሪ ለቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኢላ ኦዲንጋ በፌስቲቫሉ ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ የቀረበላቸው ሲሆን፤ ለመሳተፍ ቃል ገብተዋል።ሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ ሰላሟ እና ልማቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚል ዓላማ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከስነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ከወጣቶች እና ከሲቪል ማህበረሰብ አባላት የተዋቀረ ኮሚቴ ነው።
https://waltainfo.com/am/33465/
abe52602ce28a0716ccbbdae2749d58d
3d355d9ebb13246efb966885a8fbb81d
በ2045 ሁለቱ ኮሪያዎች የመዋሃድ እድል እንዳላቸው የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ-ኢን ተናገሩ
ፖለቲካ
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት 100ኛ ዓመት በሚከበርበት እ.አ.አ 2045 ላይ ሁለቱ ኮሪያዎች የመዋሃድ እድል እንዳላቸው የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ-ኢን ተናገሩ፡፡ፕሬዚዳንት ሙን ይህንን ያሉት ኮሪያ እ.አ.አ ከ1910-1945 ባሉት ዓመታት ውስጥ ከነበረችበት የጃፓን አገዛዝ ነፃ የወጣችበትን 74ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ ነው።ሙን በሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን እና በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መካከል ከኒዩክሌር ነፃ መሆን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ አራተኛ ውይይት እንዲካሔድ እየገፋፉ ይገኛሉ።ከኒዩክሌር ነፃ መሆን እና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማድረግ በሰላጤው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል መሠረት ለመጣል ወሳኝ ነው ብለዋል።ሙን፣ ሴኡል እና ፒዮንግያንግ እ.አ.አ በ2032 በጋራ ኦሎምፒክን እንዲያዘጋጁ ለማድረግ እና እ.አ.አ በ2045 የሁለቱን ኮሪያዎች ውሕደት እውን ለማድረግ ቃል ገብተዋል።በመጨረሻም፣ “ለራሷ፣ ለምሥራቅ እስያ እና ለዓለም ሰላም እና ብልጽግና የምታመጣ አዲሲቷን የኮሪያ ሰላጤ እየጠበቅን ነው” በማለት ሐሳባቸውን ደምድመዋል። (ምንጭ:-ዘጋርዲያን)
https://waltainfo.com/am/33985/
cae22fa71658ebb09c91e7fdf9274274
8ca3ff3bad877a0c4ac54e826f11105f
በአዳማ ሲካሄድ የቆየው የደኢህዴን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች መድረክ ተጠናቀቀ
ፖለቲካ
በአዲስ አበባ የሚገኙ የደኢህዴን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በአዳማ ያካሄዱት መድረክ ተጠናቋል፡፡አመራሮቹ በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት አስመልክቶ ይፋ በተደረገው ጥናት ላይ ተወያይተዋል፡፡በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጠናዉ ጥናት የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ አለመሆኑም ተብራርቷል፡፡ የደኢህዴንና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤ ደኢህዴን የህዝቦችን ጥያቄ በግምት ሳይሆን በእውቀት ላይ ተመስርቶ በጥናት ለመመለስ በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በመነሳት በሀገር ደረጃ አዲስ ልምድ ይዞ የመጣና አማራጭ ሃሳቦችን እያበረከተ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡የክልሉ 2011 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን፤መድረኩ ብሄራዊና ሀገራዊ ማንነትን አጣጥሞ ለመሄድ መግባባት የተፈጠረበት መሆኑ ተገልጿል፡፡ለአራት ቀናት በቆየው በዚህ መድረክ ከክልል አደረጃጀት ጥያቄ በተጨማሪ በወቅታዊ፣ አገራዊ፣ ክልላዊ እና በከተማው የፖለቲካዊና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር  አድርገዋል፡፡በምክክር መድረኩ ከ1 ሺህ በላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የድርጅቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31290/
69a117292e81bd5154f6819f7544f694
c23a868419d7661bbd17adcd464c0f99
ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር እንደማትደራደር አሳወቀች
ፖለቲካ
ሰሜን ኮሪያ "በደቡብ ኮሪያ ያልተገባ ድርጊት ምክንያት" በሚል ሰበብ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ልታደርግ የነበረውን ቀጣይ ድርድር እንደማታካሂድ አሳወቀች።ሰሜን ኮሪያ እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሷን ያሳወቀችው የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሙን ጃኢን ትናንት ሐሙስ ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ አርብ ሰሜን ኮሪያ ሁለት ሚሳኤሎችን ወደ ምሥራቃዊ የባሕር ዳርቻዋ በመተኮስ ሙከራ ማድረጓን የደቡብ ኮሪያ ሠራዊት አሳውቋል። ይህም ሙከራ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለስድስተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።ይህ ተከታታይ የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራ የተደረገው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከሰሜን ኮሪያው መሪ ጋር ባደረጉት ውይይት የኒዩክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለማስወገድ ውይይት ለመጀመር ከተስማሙ በኋላ ነው።የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሃገራቸው ከጃፓን ነጻነቷን ያገኘችበትን ቀን በተከበረበት ወቅት ሁለቱ ኮሪያዎች በአውሮፓዊያኑ 2045 እንደሚዋሃዱ በመናገራቸው ነው ሰሜን ኮሪያ ቁጣዋ የተቀሰቀሰው።በቴሌቪዥን በተላለፈው ንግግር "ለራሱና ለምሥራቅ እስያ ብሎም ለዓለም ሰላምና ብልጽግናን የሚያመጣው አዲሱ የኮሪያ ልሳነ ምድር ከፊታችን እየጠበቀን ነው" ሲሉም ተናግረዋል- ፕሬዝዳንቱ።ሰሜን ኮሪያ፣ ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ እያካሄዱት ባለው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ላይ ተቃውሞዋን ያሰማች ሲሆን፣ ይህም ከፕሬዝዳንት ትራምፕና ከሙን ጃኢን ጋር ቀደም ሲል ያደረጉትን ስምምነት የሚጥስ መሆኑን በመግለጫዋ ላይ ጨምራ ገልጻለች።የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት በጻፉት ደብዳቤ ላይ ከፍተኛ ወጪ ስለሚወጣበት የደቡብ ኮሪያና የአሜሪካ የጦር ልምምድ ቅሬታቸውን ገልጸው ነበር።የሰሜን ኮሪያ የውህደት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፣ አካባቢውን ከኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ነጻ ለማድረግ የተጀመረው ንግግር መቋጫ እንዳያገኝ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱን ማድረጓ ዋኛው ምክንያት ነው ሲሉ ተናግረዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33986/
83d48bc1725fa9f8ecee2f8ddce21dd1
7597f528c7bcfca44c5519bf11b446e7
ህንድ ግዛቶቿን ወደ ነበረበት ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ
ፖለቲካ
ህንድ ግዛቶቿን በተመለከተ ወደ ነበረበት ታሪክ ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካሽሚር ጉዳይ በተለየ መልኩ የሚታይ እና ለሀገራቸው የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡የካሽሚር ግዛት ህንድ በኢንግለዝ ቅኝ ግዛት ከመገዛቷ በፊት የህንድ እንደነበረች የሚነገር ሲሆን፣ ሀገሪቱ በቅኝ ግዛት ስር መውደቋን ተከትሎ በቀጠናው ላይ መበጣጠስ ሲመጣ ጊዛቲቱ በተለያዩ ሀገራት ማለትም በፓኪስታን እና በህንድ ስር ተከፋፍላለች፡፡ታዲያ ህንድ የካሽሚርን ግዛት በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያቶች የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ የቆየች ብትሆንም በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት አልቻለችም፡፡ በዚህ ጉዳይ የካሽሚር ነዋሪዎች ለሚያነሱት ጥያቄ ህንድ መልስ ለመመለስ መጣር ብቻ ሳይሆን ከጎሮቤቷ ፓኪስታን ጋርም እሰጣ ገባ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል፡፡የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግልጫ ሀገራቸው ህንድ ወደ ነበረችበት የቀድሞ ታሪክ መመለስ አለባት፤ ለዚህም መንግስታቸው በቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉ መናገራቸው ተገልጸዋል፡፡ህንድ ከኢንግሊዝ ነፃ የወጣችብትን 70ኛ እና ከፓኪስታን የተለያየችበትን የነፃነት ዓመት ስታከብር ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካሽሚር ግዛት በህንድ ሉዓላዊነት እና ለእድገቷ ወሳኝ ሚና የምትጫወት ነች፤ ስለዚህም ሀገራቸው ከዚህ በኋላ ያለማመንታት ካሽሚር ወደ ቀድሞ ማንነቷ ትመለሳለች ማለታቸዉን የወጡት ዘገባዎች አስነብበዋል፡፡ናሬንደራ ሞዲ ሀገራቸው ሁሉን በልኩ ሊስተካክል የሚያስችል ህገ መንግስት እንዳላት ተናግረው ነገሮች ሁሉ በዛ ይስተካከላል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ከህንድ ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ያለችው ፓኪስታን ህንድ ለመውሰድ ለምተዘጋጀው እርምጃ አፀፋዊ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ብላለች፡፡የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚንስትር ኢምራን ካሃን እስከ መጨረሻው እስትንፋስ ድረስ ለመፋለም ተዘጋጅተናል ማለታቸዉን ቢቢሲ አስንበቧል፡፡የዓለም ሁሉ ዓይን በካሽሚር እና በፓኪስታን ላይ ነው፡፡ ህንድ ስለምታደርገው ነገር ሃይ ባይ ባጣችበት ውቅት ላይ እኛ ለእርምጃ ተዘጋጅተናል፡፡ ነገር ግን ለሚሆነው ሁሉ ኃላፊነቱን የዓለም ማህበረስብ ራሱ ይወስዳል ብለዋል ጠቅላይ መኒስትር ኢምራን ከሃን፡፡ በዚህ መልስ ግን ናሬንድራ ሞዲ ያሉት ነገር የለም ነው የተባው፡፡(ምንጭ፡-አልጀዚራ፣ ቢቢሲ እና ኢንዲያን ቱደይ)
https://waltainfo.com/am/33984/
237c8da9d98e1de2d149efd92780faf5
d8505295959ad8070015440cef676843
ሩዋንዳ በትምህርት የወጣቶችን ስብዕና በመገንባት ውጤታማ ሆናለች -ተመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
በሩዋንዳ የተዘረጋው የትምህርት መርሀ ግብር የወጣቶችን ስብዕና በመገንባት ውጤታማ እየሆነ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡የዓለም ወጣቶች ቀን በዚህ ሳምንት በመላው አለም እየተከበረ ይገኛል፡፡ወጣቶችን በትምህርት በማብቃት ማህበራዊ ለውጡን ማገዝ በሚለው መርህ መሰረት ሩዋናዳ  ይበል የሚያሰኝ ለውጥ ስለማስመዝገቧ ተዘግቧል፡፡የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማህበራዊ፤ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ረገድ ማስፋት ዓለም እየገጠማት ላለው ችግር ሁነኛ መፍትሄ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ትምህርት ዋነኛ የአመለካከት ለውጥ መሳሪያ መሆኑን ተከትሎም ሩዋንዳውያን ወጣቶች የለውጡን ፈር እየተከተሉ ስለመሆናቸው  ነው የሀገሪቱ መንግስት ይፋ ያደረገው፡፡በዓለም አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዜጎች እድሜያቸው ከ10 እስከ 24 ውስጥ እንደሚገኝ መረጃዎች የሚያመላክቱ ሲሆን፤ ከዚህ ውሰጥ 226 ሚሊየኑ በአፍሪካ  ይገኛሉ፡፡ሩዋንዳም 60 በመቶ ዜጎቿ እድሜያቸው ከ 25 በታች መሆኑን ተከትሎ በትምህርት እንዲዘልቁ በማድረግ በኩል አበክራ በመስራቷ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም ዪኒስኮ እውቅና ችሯታል፡፡ባሁኑ ሰዓት ከዓለማችን 262 ሚሊዮን ህጻናትና ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥናት ማመላከቱን ተከትሎ ሩዋንዳ ፍታዊ የትምህርት ተደራሽነትን ማሰካቷ ወደኋላ ለቀሩት ሀገራት ተምሳሌት እንድትሆን አሰችሏታል፡፡ከሁለት አመታት አስቀድሞ ይፋ ያደረገቸው የሰባት አመት የትምህርት ማሻሻያ ስትራቴጂ ለውጤቱ እንዳበቃት በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ እየተመዘገብ ባለው ውጤት መሰረትም ተመድ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ነው ሲል ዘ ኒው ታይምስ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/33463/
e669c6ef1eb5fded780118e7c706412f
4981696953999b5485cd44fe5469eeee
ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የወጣቱ ሚና የጎላ ሊሆን ይገባል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
በኢትዮጵያ የአብሮነት እሴት ተጠብቆ እንዲቀጥልና ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት 70 በመቶውን የሚሸፍነው ወጣት ሚና የጎላ ሊሆን ይገባል ተባለ፡፡ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ 1 ሺህ 400 ወጣቶች የተሳተፉበት አገር አቀፍ የወጣቶች የሰላምና የአንድነት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንንእንዳሉት፤ ወጣቱ በሰላም፣ ሀገር ግንባታ እና ዴሞክራሲ ያለውን ሚና በአግባቡ መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ሰላምን እውን ለማድረግ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥ አይገባም ያሉት ሚኒስትር ድኤታዋ፤ ሁሉም ጥያቄ በሰላም ማዕቀፍ ውስጥ ምላሽ ሊያገኝም እንደሚገባ ነው የገለጹት።የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ታረቀኝ አብዱልጀባር በበኩላቸው፤ ወጣቱ ሰላምን ለማስጠበቅ በሚደረገው ስራ ግንባር ቀደም መሆን ይኖርበታል ብለዋል።የሰላም እጦት ዋነኛ ሰለባ ወጣቱ እንደመሆኑ ለሰላም ዘብ ሊቆም እንደሚገባም  የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ገልጸዋል፡፡ “ወንድማማችነትን በማጎልበት ዘላቂ ሰላምን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው መድረክ በሰላም ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን  ትብብር በጋራ የተዘጋጀ ነው፡፡መድረኩ በውይይት የሚያምንና ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ የሚያቀርብ ትውልድ መፍጠርን ትኩረት አድርጎ መዘጋጀቱም ተገልጿል።  
https://waltainfo.com/am/32650/
0ffb018e29bff545031f64e1c553d831
b90cd6e26dda10b4a1cf867383d248c4
የሚኒስትሮች ም/ቤት በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተዘጋጅተው በቀረቡ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ
ቢዝነስ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 16ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተዘጋጅተው በቀረቡ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡በዚህም መሠረት የመንግስት ሠራተኞች የሥራ መደቦች ምዘና፣ ደረጃዎች ምደባና የደመወዝ ስኬል ረቂቅ ደንብ፣ ወደ ነጥብ የሥራ ምዘና ሥርዓት ለማሸጋገር በቀረበ ውሳኔ የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ስኬል ጥናትና የውሳኔ ሃሳብ እና የጡረታ አበል ተመን በተመለከተ ለሚኒስትሮቸ ምክር ቤት በቀረቡ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማሻሻዎችን በማከል ከሀምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፡፡(ምንጭ፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)
https://waltainfo.com/am/23908/
78138d2ab2c32a8b7ff970c26f737023
7938058259f264f7a69f09d8aed9d35d
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዞ አቤ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዮሽፉሚ ኦካሙራ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዩ መልዕክተኛው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና በአፍሪካ የአከባቢ ሰላም ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡(ምንጭ:-ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/31289/
33f51806c0f8207ad4fd1530dabddb57
f08618136a0c67a6bfe4dbc28f94380f
የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ
ሀገር አቀፍ ዜና
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረጉ፡፡ፕሬዝዳንቷ ኢትዮጵያ በ2025 የሴት ልጅ ግርዛትንና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የያዘችውን ዕቅድ ለማሳካት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።ባለፉት አምስት አመታት ሲዘጋጅ የቆየውና በቀጣዮቹ አምስት አመታት የሚተገበር ሀገራዊ  የጸረ ሴት ልጅ ግርዛትና ያለዕድሜ ጋብቻ ፍኖተ ካርታ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል፡፡በስነሥርዓቱ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለዕድሜ ጋብቻ ሴቶችን ለዕድሜ ልክ ችግር የሚዳርግ በመሆኑ፤ አሁን የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ኢትዮጵያ ችግሩን ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝኘት ያሳያል ብለዋል፡፡ባለድርሻ አካትና ህብረተሰቡ ለፍኖተ ካርታው ስራ ስኬት የበኩላቸውን እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወ/ሮ ያለም ፀጋይ በበኩላቸው፤ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለዕድሜ ጋብቻ በመላው ሀገሪቱ ያለ ችግር መሆኑን አንስተዋል። ፍኖተ ካርታውን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማከናወን  ሰፊ ማህበራዊ ንቅናቄ እንደሚደረግና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋርም በጋራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ፍኖተ ካርታውን ለማስፈጸም ሶስት ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግም በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል፡፡
https://waltainfo.com/am/32649/
35d11ef563b9f2a518820321a12c5c2b
42229f56961a523ad2308444cce4bf4f
በግንባታ ላይ የሚደርስ አደጋን ለመከላከል የወጡ ህጎች ባለመተግበራቸው ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ ተገለጸ
ቢዝነስ
በአዲስ አበባ በግንባታ ላይ የሚደርስ አደጋን ለመከላከል የወጡ ህጎች አለመተግበራቸው በሰራተኛው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ከፍተኛ አድርጎታል ተብሏል፡፡የህጎቹ በትክክል አለመተግበርም የግንባታ ባለቤቶች ለሰራተኛው ደህንነት መጠበቅ ትኩረት እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል ነው የተባለው፡፡ይህ የተባለው በአዲስ አበባ በተለይ በየካ፣ ቂርቆስ እና ቦሌ እንዲሁም የ20/80 እና የ40/60 የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በስፋት በሚከናወኑባቸው አካባቢዎች የጤና እና ግንባታ ደህንነት ላይ የተሰራ የህዝብ አስተያየት እና ጥናት ይፋ በተደረገበት ወቅት ነው፡፡የግንባታ ባለቤቶች የደህንነት ቁሳቁሶችን አለመጠቀማቸው እና የሚጠቀሙትም ቢሆኑ ርካሽ ዋጋን ፍለጋ ጥራታቸውን እና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መሳሪያዎችን ከውጭ አገር እያስገቡ ሰራተኛው እንዲጠቀምባቸው ማድረጋቸው በአዲስ አበባ ውስጥ በግንባታ ዘርፉ ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ጉዳት ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡እንደ ኢቲቪ ዘገባ ዘርፉ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ850 ሺህ በላይ የስራ ዕድል የሚፈጥር ቢሆንም፤ ለዘርፉ በቂ ትኩረት ባለመሰጠቱና እና ደህንነቱን እንዲጠብቅ ባለመደረጉ በሰራተኛው ምርታማነት ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ ተነግሯል፡፡
https://waltainfo.com/am/23907/
10bde65ea9094b3b620b6856fb5bba72
ec7443ed1e6e90bae0ddc7682902f862
በሩሲያ በሮኬት ፍንዳታ የተከሰተ የጨረር መጠን ከመደበኛው በ16 እጥፍ ይልቃል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
በሩሲያ ለአምስት ሰው ሞት መንስኤ የሆነው የሮኬት ፍንዳታ በአከባቢ ያለውን የጨረር መጠን ከመደበኛው በ16 እጥፍ ከፍ እንዳደረገው ተገልጿል።የሩሲያ የኒውክሌር ኤጀንሲ በወደብ ከተማዋ ሴቬሮድቪንስክ የሮኬት ፍንዳታ ከተከሰተ በኋላ በአካባቢው ያለውን የጨረር መጠን በመለካት ይፋ አድርጓል።180 ሺህ ህዝብ በሚኖርባት ሴቬሮድቪንስክ ከተማ በሚገኙ ስድስት የሙከራ ጣቢያዎች የጨረር መጠኑ የተለካ ሲሆን፥ በዚህም የጨረር መጠኑ ከመደበኛው ከአራት እስከ 16 እጥፍ መጨመሩ ተነግሯል።መደበኛው የጨረር መጠን በሰዓት 0 ነጥብ 11 ማይክሮ ሲኤቨርት ሲሆን በአንድ ጣቢያ በሰዓት 1 ነጥብ 78 ማይክሮሲኤቨርት መመዝገቡ ተነግሯል።ይህ መጠን አደጋኛ ከሚባለው ደረጃ በታች መሆኑ የተገለፀ ቢሆንም፥ በሰው ላይ መጠነኛ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል የኒውክሌር ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡ፍንዳታውን ተከትሎ የጨረር መጠኑ ከመደበኛው ከፍ ያለ እንደነበረ እና ከቆይታ በኋላ ግን ወደ መደበኛ ደረጃ መመለሱን የሴቬሮድቪንስክ ከተማ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።ባለስልጣናት ፍንዳታው በተከሰተበት አከባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች አካባውን  ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ቢሰጡም ሌሎች የሩሲያ ባለስልጣናት ግን ውሳኔውን መቃወማቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/34127/
15670f3e2f19f4503ce31e192f7cbeff
2a2c10a99f7e0eaad971a368ca358304
ሀምሌ 22 የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በይፋ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሀምሌ 22 የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በይፋ መጀመሩን የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ዘገባ እንደሚያመለክተው ኮሚሽኑ በአረንጓዴ አሻራ ቀን የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብና የመተካካት ስራን ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ የረር የመትከያ ጣቢያ አስጀምሯል፡፡የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ ለችግኞቹ እንክብካቤ በተደረገበት ወቅት በኮሚሽኑ ሰራተኞች የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራን አስጀምረዋል፡፡በስነስርዓቱ ላይ 100 የሚሆኑ ሰራተኞች ተሳታፊየሆኑ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት አረንጓዴ አሻራ ቀን በሚል ሀምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በአንድ ጀምበር ከ 350 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በአለም አቀፍ ደረጃ የተያዘውን ክብረወሰን መረከቧ ይታወሳል፡፡
https://waltainfo.com/am/32647/
a072097c4f31f6147a1b475d9669efb9
322f8792140a270f5c563b4af6f94aa2
“የክልል እንሁን” ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት እየሰራ እንደሆነ ደኢህዴን አስታወቀ
ፖለቲካ
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) በደቡብ ክልል የሚነሱ “የክልል እንሁን” ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንደሚፈታ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የድርጅቱን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ ሰብስቦ እያወያየ ባለበት ወቅት አስታዉቋል፡፡በስብሰባዉ ላይ ንግግር ያደረጉት የደኢህዴን ስራ አስፈፃሚ አባልና የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተበራከተ የመጣዉን “የክልል እንሁን” ጥያቄ ለመፍታት 7 ወራት የፈጀ ጥናት መካሄዱን አስታዉሰዋል፡፡አቶ ተስፋዬ እንደተናገሩት 20 አባላት ባሉት ቡድን የተካሄደዉ ጥናት ይፋ መደረጉን ተከትሎ በየደረጃዉ የሚገኙ አካላት እንዲወያዩበት ተደርጓል፡፡የዛሬዉ ዉይይት የዚሁ አካል መሆኑን የተናገሩት ኃላፊዉ በጥናቱ ላይ ግብረ-ሀሳብ ዉይይት ማድረግ፣ በክልልና ሀገርአቀፍ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዉይይት ማድረግና የአዲስ አበባ ደህዴን ቅርንጫፍ 2011ዓ.ም አፈፃፀም ግምገማ አጀንዳዎች ናቸዉ፡፡የዉይይቱ መድረኩ ከስሜት የፀዳ፣ እዉቀትን መሰረት ያደረገና ሀገራዊና ብሄራዊ ማንነትን ባገናዘበ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን አቶ ተስፋየ ገልፀዋል፡፡ዉይይቱ ለ 3 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ1005 በላይ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የድርጅቱን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነዉ ተብሏል፡፡  
https://waltainfo.com/am/31287/
a5abbd7e973949a3d4cd89a53846282c
915ed5ea3d96413c3e99899f486cc5da
በኦሮሚያ ከልል ከ80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ
ፖለቲካ
በስልጠናው 20 ሺህ ለሚሆኑ ከፍተኛ አመራሮች በአዳማና ጅማ ለአስራ አምስት ቀናት እነደተሰጠ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው አስታዉቀዋል፡፡  በ20 ዞኖች በተመረጡ አስራ ዘጠኝ ከተሞችና በሶስት መቶ ሀያ ሶስት  ወረዳዎች በሰባት ሺ ስልሳ ስድሰት ቀበሌዎች ለሚገኑ ስልሳ ሺ አመራሮች በአጠቃላይ ከሰማንያ ሺ በላይ  ለሚሆኑ አመራሮች ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡የስልጠናው ዋና አላማም በፈጣንን በተቀላጠፈ መልኩ  እየሄደ ያለውን  ለውጥ ለማስቀጠል የአመለካከትና የአገልጋይነት ስሜት ተፈጥሮ የህበረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና መሰረታዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ታስቦ የተዛጋጀ ነው ተብሏል፡፡በአስተሳሰብና በአመራር ሂደት ወጥ የሆነ መዋቅር መፍጠር ለውጡን ታች ድረስ በማድረስ ለክልሉም ሆነ ለሀገር የሚሰሩ በጎ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል፡፡ለዚህ ደግሞ በእውቀትና በክህሎት የዳበረ አመራር መፈጠር ያስፈልጋል ያሉት ሃላፊው ስልጠናው እጅጉን መጥቀሙን ጠቅሰዋል፡፡ከስልጠናው በኃላም በተገኘው ግብረ መልስና በተጨባጭ  በመጣው ለውጥ ስልጠናው አመርቂ መሆኑም ተነግሯል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31288/
d0c99b8dc04c0e9876278cb213915d92
a933c107c9a7822b06d1b6812fb3dae8
በታንዛኒያ ያላገቡ ሴቶችን ከመታለል ለመታደግ ያገቡ ወንዶች የመረጃ ቋት እንዲቋቋም ሃሳብ ቀረበ
ሀገር አቀፍ ዜና
በታንዛኒያ የዳሬሰላም ገዢ ያላገቡ ሴቶችን ከመታለል ለመታደግ ያገቡ ወንዶች የመረጃ ቋት እንዲቋቋም ሃሳብ አቅርበዋል፡፡በአጭበርባሪ ባለትዳር ወንዶች የሚሠቃዩ ሴቶችን ጉዳት መቀነስን ዓላማ ያደረገ እንደሆነ  ገዢው ፖል ማኮንዳ ተናግረዋል፡፡ባለፈው ዓመትበርካታ ያላገቡ ሴቶች ወደ ቢሯቸው በመጡበት ወቅት የችግሩን ስፋት በመረዳት  ሀሳቡ እንደመጣላቸው ፖል ማኮንዳ ገልጸዋል፡፡ሚስተር ማኮንዳ ስለ አዲሱ የመፍትሄ እቅድ  ሂደት ምንም ዓይነት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል፡፡ገዢው አወዛጋቢ መግለጫዎችን በመስጠት እንደሚታወቁ በዘገባው ያስታወሰው ቢቢሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/33462/
f6ffcbbf9219873266a899fa71cb122c
5bfa8c8f711a083f2f6d7534fcef40fd
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዉጤት ከ 11፡ 30 ጀምሮ ይፋ ይሆናል
ሀገር አቀፍ ዜና
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዉጤት ከ 11፡ 30 ጀምሮ ይፋ እንደሚሆን የሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡በዘንድሮዉ ፈተና የተቀመጡት ተማሪዎች ቁጥር በአጠቃላይ 319ሺህ 264 ሲሆን ፤ከነዚህ ዉስጥ 180ሺህ625 ወንደችና ቀሪዎቹ ደግሞ ሴቶች መሆናቸዉን ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡3453 ተማሪዎች በተለያየ ምክንያት ፈተናዉን አለመዉሰዳቸዉ ታዉቋል፡፡ከአጠቃላይ ተፈታኞች 48.59 ፐርሰንት የሚሆኑት ፈተናዉን ከግማሽ በላይ ያመጡ ሲሆን፤ አንድ ተማሪ ከአማራ ክልል 645 ነጥብ በማምጣት ከፍተኛ ዉጤት አስመዝግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/32648/
e925db3a8f0c72945b60db22f250917a
e00cca2b5e0c74c9660f6a57fbbdbf82
የተባበሩት መንስታት ድርጅት ተጠሪ ተቋማት ለኢትዮጵያዉያን ስራ ፈላጊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጁ
ሀገር አቀፍ ዜና
የተባበሩት መንስታት ድርጅት ተጠሪ ተቋማት ከ1800 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን   ስራ ፈላጊዎች ወደ ስራዉ አለም መቀላቀል በሚችሉበት ሁኔታ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡በመድረኩ የተገኙ ከ26ቱ የመንግስታቱ ድርጅት ተጠሪ ተቋማት የመጡ ተወካዮችም ስራ ፈላጊዎች እንዴት ስራዉን አለም መቀላቀል እንደሚችሉና በቀጣይ በየተቋማቱ የስራ እድል ማግኘት በሚችሉባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ አድርገዉላቸዋል፡፡የኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር ከ100 ሚልዮን በላይ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ ዉስጥም 11 ሚሊዮን የሚጠጋዉ የሀገሪቱ ዜጋ ስራ ፈላጊ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህ ሳይበቃ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ስራ ፈላጊዉን ማሕበረሰብ እንደሚቀላቀሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ታዲያ ይህንን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ መንግስት ጉዳዩን የሚከታተል የስራ ፈጠራ ኮሚሽን እስከማቋቋም ደርሷል፡፡ በተጨማሪ እስከሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ድረስ ለ3 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መግለፃቸዉም ይታወሳል፡፡
https://waltainfo.com/am/32646/
449c6c53038237f560ac03c9c17c4aea
c3510f23d562c110b1ec7d28ab023031
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ተማሪዎች ብቁ መሆን እንዳለባቸው ተገለፀ
ቢዝነስ
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡና በመምርነት ሙያ የሚሰለጥኑ ተማሪዎችን ውጤት መሰረት በማድረግ መመልመል እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሰልጣኖች ለመምህርነት ለመመልመል ከፍተኛ ውጤትና ፍላጎት ሊኖራቸው እንደሚያስፈልግ ነው የትምህርት ሚኒስቴር የ2011 በጀት ዓመት ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ያስታወቀው፡፡በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የቅድመ መደበኛ ትምህርትና የጎልማሶች ትምህርት ላይ በቂ ስራ አለመሰራቱም ተጠቁሟል፡፡በተለይም በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ወደ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይ መፍትሄ እንደሚበጅለት የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ ገልጸዋል፡፡በ2012 በጀት ዓመት መምህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመመለስ እንደሚሰራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡በተለይም የመምህራንን ጉዳይ በተመለከተ ከመምህራን ማህበር ጋር በመተባበር ጥናት እየተካሄደ መሆኑንና ጥናቱ እንዳለቀ ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግ መገለፁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/23903/
d29e0f0b1b91ffaf2cd10da2e064ab02
2eacd5ebc6be3325f77847443354970b
ኢትዮጵያ እና ቻይና በ300 ሚሊየን ዶላር አዲስ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነቡ ነው
ቢዝነስ
ኢትዮጵያ እና ቻይና በ300 ሚሊየን ዶላር የጋራ ወጭ በአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነቡ ነው።በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች ተጠሪ ሊው ዩ፣ በአዳማ የሚገነባው አዲሱ የኢንዱስትሪ ፓርክ በያዝነው የፈረንጆች 2019 ዓመት ከመጠናቀቁ አስቀድሞ ሊጀመር ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።85 በመቶ የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ ወጭ ከቻይና መንግሥት በሚገኝ ዝቅተኛና በተራዘመ ጊዜ በሚከፈል የብድር ወለድ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል። ቀሪው 15 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል።የሚገነባው ፓርክ በዋናነት መሣሪያዎችን የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ታሳቢ ያደረገ ነው ያሉት ሊው፣ በአሁኑ ወቅት መሬት እና ገንዘብ ማግኘት ጋር የተያያዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።በቻይና ድጋፍ እና ሞያዊ እገዛ የሚገነባው አዲሱ ፓርክ ለአዳማ ከተማ ሁለተኛው ይሆናል።የቻይና እና የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ውጤታማ የሆነ ጠንካራ ግንኙነት አላቸው ሲሉም ሊው ተናግረዋል። (ምንጭ:-ሽንዋ)
https://waltainfo.com/am/23905/
1937191123647ad2a6580151d7877838
d484e2ab3c0336c8e2ddb2dd0564915f
በአዲስ አበባ ከመስመር ጥገና ጋር ሳምንቱን ሃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ይፋ ተደረጉ
ቢዝነስ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዚህ ሳምንት በመዲናዋ ከመስመር ጥገና ጋር በተያያዘ ሃይል የሚቋረጥባቸውን አካባቢዎች ይፋ አደርጓል፡፡በዚህም መሰረት ረቡዕ ነሃሴ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በቸራልያ ፋብሪካ፣ በገነት መናፈሻ ኮንደሚኒየም፣ በማሩ ብረታ ብረት፣ በወህኒ ቤት ጀርባ፣ በቂሊንጦ ማረሚያ፣ በሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን፣ በቦሌ ቡልቡል ኮንዶሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ፣ በክሬሸር፣ በባሌስትራ ፋብሪካ፣ በጎፋ ካምፕ ኮንደሚኒየም፣ በመካኒሳ፣ በከፍያለው መድሀኒት ማከፋፈያ፣ በቫቲካን ኤምባሲ፣ በመካኒሳ አቦ ቤተ ክርስቲያን፣ በቄራ ይመስገን ጋራዥ እና በአካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል፡፡በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በቡና ቦርድ፣ በምርጫ ቦርድ፣ በዳችያ፣ በጎፋ መብራት ኃይል፣ በአየር መንገድ፣ በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማሕበር እና በአካባቢዎቻቸው ሃይል እንደሚቋረጥ ተገልጿል፡፡በማግስቱ ሐሙስ ነሃሴ 9 ቀን 2011 ዓ.ም በእሕል በረንዳ፣ በአውቶብስ ተራ፣ በአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት፣ በገነሜ ትምህርት ቤት፣ በአማኑኤል ቤተ ክርስቲያን፣ በሻወል ደማ ትምህርት ቤት፣ በሰባተኛ ትራፊክ መብራት፣ በዶሮ ተራ፣ በጦር ሀይሎች፣ በመኮንኖች ክበብ፣ በቶሎሳ ሰፈር፣ በገዳመ እየሱስ፣ በወንድማማቾች፣ በሜክሲኮ፣ በፍሬህይወት ትምህርት ቤትና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ሃይል አይኖርም፡፡አርብ ነሃሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ በለቡ፣ በጆሞ 1 በከፊልና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር የማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተቋሙ አሳስቧል።
https://waltainfo.com/am/23904/
6bb5edce8532d5d7bcb5c5e0fbd7267a
916f153ec93c616eaa02be79001eb6bc
ትራምፕ ሕጋዊ ስደተኞች የሚያገኙትን የምግብ ድጋፍ ለማስቀረት አልመዋል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሕጋዊ ስደተኞች የሚያገኙትን የምግብ ድጋፍ ለማስቀረት አልመዋል ተባለ፡፡አስተዳደሩ ያጡ የነጡ ሕጋዊ ስደተኞች ቪዛቸውን ለማራዘም አልያም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ) ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት ከባድ ለማድረግ እየሠራ መሆኑ ነው የተገለጸው።መመሪያው ታላሚ ያደረገው የምግብ፣ የመኖሪያ ቤት ድጋፍ ከአንድ ዓመት በላይ እያገኙ የሚቆዩ ሕጋዊ ስደተኞችን ነው።መንግሥት ከዚህ በኋላ እነዚህን ድጋፎች ማግኘት አትችሉም ብሎ ከወሰነ ማመልከቻቸው ውድቅ እንዲሆን ይደረጋል ተብሏል።ባለስልጣናት መመሪያው "ራስን መቻልን" ያበረታታል ሲሉ ተናግረዋል።ይህ አዲሱ መመሪያው "ፐብሊክ ቻርጅ ሩል" የሚሰኝ ሲሆን፣ በጥቅምት ወር አጋማሽ ሥራ ላይ መዋል ይጀምራል ነው የተባለው።በዚህ ሕግ በአሜሪካ በቋሚነት እየኖሩ ያሉ ስደተኞች ላይጎዱ ይችላሉ፤ እንዲሁም ጥገኝነትና መጠለያ የጠየቁትን አይመለከትም ተብሏል።ነገር ግን ቪዛቸው እንዲራዘምላቸው የጠየቁ፣ ግሪን ካርድ ወይንም የአሜሪካ ዜግነት ለማግኘት ያመለከቱ ላይ ተፈፃሚ የመሆን እድል አለው።የገቢ ደረጃቸው ከሚጠበቀው በታች የሆነ ወይንም እንደ መኖሪያ ቤትና ሕክምና የመሳሰሉ ጥቅማ ጥቅሞች ላይ ሕይወታቸውን የመሰረቱ ወደፊት ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ ሊታገዱ ይችላሉ።በአሜሪካ ውስጥም ያሉ ግለሰቦች ማመልከቻቸው ውድቅ ሊደረግ እንደሚችልም ተገልጿል።በአሜሪካ 22 ሚሊየን ይሆናሉ ተብለው የተገመቱ ሕጋዊ ስደተኞች ያለ ዜግነት የሚኖሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ አብዛኞቹ በዚህ መመሪያ መሰረት ሊጎዱ ይችላሉ ተብሏል።የመብት ተሟጋቾች መመሪያው ያጡ የነጡ ስደተኞች ላይ ፍትሀዊ ባልሆነ መልኩ ትኩረት ተደርጎባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።የብሔራዊ ስደተኞች የሕግ ማዕከል የተሰኘ ተቋም ይህ መመሪያ ስራ ላይ እንዳይውል የትራምፕ አስተዳደርን ከስሼ ሕግ ፊት አቆማቸዋለሁ ሲል ተናግሯል።ነገር ግን ዋይት ሐውስ ይህ ስርዓት "ራሳቸውን በገቢ የቻሉና የመንግሥትን ድጋፍ ከማይጠብቁ ይልቅ" አሜሪካ ቤተሰብ ያላቸው ስደተኞችን የሚደግፍ ነው ሲል ተናግሯል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34126/
168c09c90953d1f18442dd0668d4f3ad
23458bd38566a80b1e008cc93ceb9587
ተቋማት ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር በማካሄድ አምራች ኢንዱስትሪውን መደገፍ እንዳለባቸው ተገለፀ
ቢዝነስ
ኢንስቲትዩቶች ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር በማካሄድ አምራች ኢንዱስትሪውን መደገፍ አለባቸው ሲል ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሚኒስቴር በመስሪያ ቤቱ የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን በስሩ ካሉ 15 ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር በቢሾፍቱ ከተማ እየገመገመ ይገኛል፡፡የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር ኢንስቲትዩቶች ኢንዱስትሪውን በሚፈለገው ደረጃ እየደገፉ አይደለም ብለዋል፡፡ኢንስቲትዩቶች ሲቋቋሙ ዋና ተልኳቸው ጥናት በማካሄድ ኢንዱስትሪውን ማሳደግ ስለሆነ ወደዚህ መደበኛ ስራቸው ገብተው ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡የወጪ ንግድ ችግሮችን በመለየት የአገራትን የገበያ ፍላጎት እንዲሁም የአገር ውስጥ ምርቶች ገበያ የሚያገኙበትን አገራት መለየት የሚሉትን በማጥናት ለኢንዱስትሪው የመፍትሄ ምንጭ መሆን አለባቸው ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡በሌላ በኩል ኢንስቲትዩቶች የራሳቸው ቢሮና የጥናትና ምርምር ቦታ እንዲኖራቸው ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል፡፡በተጨማሪም የአገሪቷን አጠቃላይ ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ በአምራች ኢንዱስትሪው ሴክተር ለውጥ ማምጣት ይገባል የተባለ ሲሆን ለዚህም በዘርፉ ያላውን የስራ ባህል መቀየር እንደሚያስፈልግ ተነግሯል፡፡ምንጭ፦ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
https://waltainfo.com/am/23906/
7823ee84864a9fd394601bc370104dea
4cf59b6b3bc6440ca21fc649bd7ffa90
የሱዳን የቀድሞ የመረጃና ደህንነት ኃላፊ ሳላህ ጎሽ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ
ፖለቲካ
የሱዳን የቀድሞ የመረጃና ደህንነት ኃላፊ ሳላህ ጎሽ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መታገዳቸው ተገለፀ።የቀድሞ ኃላፊው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የታገዱት በሰብአዊ መብት ጥሰት እጃቸው አለበት በሚል ሲሆን፣ እርሳቸው ብቻም ሳይሆኑ ቤተሰባቸውም ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳው ተጥሎባቸዋል ነው የተባለው።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ እንደሚያትተው የቀድሞ ኃላፊው ሳላህ፤ የሱዳን ብሔራዊ የፀጥታና ደህንነት ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ሰዎችን በማሰቃየት እጃቸው እንዳለበት ተጨባጭ ማስረጃ አለኝ ብሏል።የቀድሞ የአገሪቷ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር ከሥልጣን እስከተወገዱበት ሚያዚያ ወር ድረስ ከመረጃና ደህንነት ኃላፊው ሳላህ ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንደነበራቸው ተገልጿል።እርሳቸው ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ በተቃዋሚዎች ግፊት ምክንያት ኃላፊነታቸውን ለቀዋልም ነው የተባለው።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማይክ ፖምፔዮ፤ ሱዳን በሲቪል የሚመራ መንግሥት እንዲኖራት ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉ በትዊተር ገፃቸው ላይ መልእክታቸውን አስፍረዋል።አሁን ሃገሪቷን እያስተዳደረ ያለው ምክር ቤት እና የተቃዋሚዎች ጥምረት በሦስት ዓመታት የሽግግር ጊዜ ስለሚኖራቸው ኃላፊነት ከአስር ቀናት በፊት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።በሚኖራቸው የሥልጣን ክፍፍል ላይም ለመጨረሻ ጊዜ በመጭው ቅዳሜ እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33322/
39da955487cbf1bc13051130a1f782f9
b4aed99dad09ad7d689b55a8e8a90d94
የመከላከያ አባላት ያላቸውን የላቀ ስብዕና እና የአገር ፍቅር ለተተኪ ማስተላለፍ እንደሚገባቸው ተገለፀ
ፖለቲካ
የመከላከያ አባላት ያላቸውን የላቀ ስብዕና እና የሀገር ፍቅር ለተተኪ ማስተላለፍ እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ።የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 100 የሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ዛሬ በታላቁ ቤተ መንግስት አስመርቋል።የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ዛሬ ካስመረቃቸው 100 ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ 92 ፖስት ስታፍ እና ስምንት የሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተከታተሉ ሲሆኑ 21 ተመራቂዎች ከጎረቤት አገሮች መሆናቸው ተገልጿል።ኮሌጁ ዛሬ ካስመረቃቸው ተመራቂዎች የጎረቤት አገራት ጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ ከፍተኛ መኮንኖች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድ የወታደር መኮንን መሆን ድርብ ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።በተለይም ለተመራቂ የኢትዮጵያ መኮንኖች የአገሪቱን ታሪክ የህዝቦችን ባህል፣ ማንነትና ድንበር ጠንቅቀው በማወቅ የላቀ ስብዕናን በመገንባት ለተተኪ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።የመከላከያ አባላት ያላቸውን የላቀ ስብዕና እና የአገር ፍቅር ስሜት ለተተኪ ማስተላለፍ እንደሚገባቸውም አክለዋል።አባላቱ የፖለቲከኞች ሽኩቻ ሳይወስዳቸው ከወረዱ ዘረኞችና ደካሞች ጋር ሳይወርዱ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለህዝቦች እኩልነትና ደህንነት እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።በመጨረሻም መከላከያን የማዘመን ሥራ በሁሉም ተቋማቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለአብነትም ዘመናዊ ጀቶችና ሄሊኮፕተሮች፣ ሰው አልባ ሚሳኤል እና የሳይበር ስራዎች ላይ የማዘመን ስራ በፍጥነት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።ለመከላከያ አባላት የሚሰጠው ከስልጠና እስከ ትጥቅ የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተመራቂዎች ተረድተው ለቀጣይ አዳዲስ ስልጠና እና ትምህርት ራሳቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሀመድ በበኩላቸው መከላከያ የሰራዊቱን ተልዕኮ የመፈፀም አቅም እና ብቃት ለማሳደግ የሚያስችለው የሪፎርም ሥራ ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል።ከዚህ ውስጥ የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ አንዱ በመሆኑ ዛሬ የተመረቁ ከፍተኛ መኮንኖች የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም ከግብ ለማድረስ ሚናቸው የጎላ መሆኑን አንስተዋል።ተመራቂ ከፍተኛ መኮንኖች በበኩላቸው የተሰጣቸውን ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ ለመወጣት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆነው ለህገ መንግስቱና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ ዘብ እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።ተመራቂ ከፍተኛ መኮንኖቹ በኮሌጁ ያገኙትን የወታደራዊ ሳይንስና አመራር ተጠቅመው ህገ መንግስታዊ ግዳጆችን በስኬት ለማጠናቀቅ ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል።/ኢዜአ
https://waltainfo.com/am/31286/
c1c8eada2bc0d2a79e99be4ac50ccbdd
024a43f4b2b2937220217bbc64b7304b
የሊቢያ ተዋጊዎች የኢድ በአልን በማስመልከት ጊዜያዊ የእርቅ ስምምነት አደረጉ
ፖለቲካ
የሊቢያ ዋነኛ ተቀናቃኝ ተዋጊ ቡድኖች ለሶስት ቀናት የሚከበረው የኢድ አል አድሃ በዓልን በማስመልከት ጊዜያዊ ስምምነት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።ይህንንም ውሳኔ የተባበሩት መንግሥታት ይበል የሚያሰኝ ነው ብሎታል።ቅዳሜ እለት ቤንጋዚ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ሶስት ሰራተኞቹን ያጣው የተባበሩት መንግሥት ድርጅት በዚህ የሰላም ስምምነትም እንደ አንድ አደራዳሪ ሆኖ ቀርቧል።በዚህ ስምምነት ላይ በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ ከፍተኛ ጥቃትን ሲፈፅም የነበረው ወታደራዊ ኃይል ኃላፊ ጄኔራል ካሊፋ ሃፍተር ዋነኛ ተደራዳሪ ናቸው።የአለም ጤና ድርጅት እንደዘገበው ከሚያዝያ ጀምሮ በነበረው ጥቃት አንድ ሺ ሰዎች ተገድለዋል።"ጄኔራሉ ለእርቁ የተስማሙት ሊቢያውያን የኢድን በአል በሰላም እንዲያከብሩ ነው" በማለት ቃል አቀባያቸው አህመድ አል ሜስማሪ ገልጿል።እርቁ ቅዳሜ ከ9 ሰአት የጀመረ ሲሆን፣ ሰኞ እስከ ከሰአትም እንደሚቀጥል ቃል አቀባዩ አክለው ተናግረዋል።ኢድ አል አድሐ በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ አምላክ ለአብርሃም በህልም ተገልፆ አንድ ልጁን እንዲሰዋ ትእዛዝ ካስተላለፈለት በኋላ፤ መስዋእቱን ለማድረግ በሚዘጋጅበት ወቅት በግ የላከበትን ቀን የሚታወስበት ነው።በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ 1 ሺህ 440ኛው ዓመተ ሒጅራ የኢድ አል አድሐ አረፋ በዓል በትላንትናው ዕለት ተከብሮ ውሏል፡፡ (ምንጭ፡-ቢቢሲ) 
https://waltainfo.com/am/33321/
e15862a02f9b735077bcb2015bde8723
cd348ec86efbab2724ed4a846c717983
በመዲናዋ 98 ሺ ለሚልቁ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
በአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፈቃደኞች የማጠናከሪያ ትምህርትና በስፖርት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በስነ ጥበብ ዙሪያ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ከ98 ሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች እየሰጡ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታወቀ።የቢሮ የበጎ ፈቃድ ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ትዕዛዙ እንደገለጹት÷ በ114 ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል እስከ 10 ክፍል ላሉ 62 ሺህ 700 ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል።በተጨማሪም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኪነ ጥበብ፣ በስፖርትና ኢትዮጵያዊነት ዙሪያም ለ36 ሺህ ተማሪዎች ለሁለት ወራት ስልጠና እየተሰጠ ነው።ወጣቱ ትውልድ የኢትዮጵያ ታሪክና ባህላዊ እሴቶችን የሚያትቱ መፅሀፎችን ከማንበብ ይልቅ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠምዶ የሚውል መሆኑን ዳይሬክተሩ አመልክተው ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚሰጠው ስልጠናም ወጣቱ በስሜት የሚነዳ ሳይሆን ምክንያታዊ ትውልድ ለመፍጠር እንደሚረዳ አመልክተዋል።የበጎ ፈቃድ ትምህርትና ስልጠና ከሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች መካከልም ዳግማዊ ምኒልክ፣ ጥቁር አንበሳ፣ ኮከበ ጽባህ እንደሚገኙባቸው ጠቅሰዋል።ትምህርቱ እስከ ነሀሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑ መገለፁን የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅ ዘገባ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32645/
7712f953b40851d6e95fc0f558b85a86
7478d39879e0dfe8162d281cd2577b97
ሚኒስትሯ በአዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ
ቢዝነስ
የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሔር እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የትራንስፖርት የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳነ እና ሌሎችም በመዲናዋ የትራንስፖርት ቢሮ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።በጉብኝቱ የመርካቶ አውቶብስ ተርሚናል በአንድ ጊዜ 20 አውቶብሶችን በማስተናገድ እስከ 2 ሺህ ሰው የመጫን አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል።ተርሚናሉ ለአካል ጉዳተኞች የሊፍት አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተብራርቷል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም በሰዓት 6 ሺህ ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ እንደሚችልም ነው የተገለፀው።የሸጎሌ እና የቃሊቲ አውቶብስ ተርሚናሎችም በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኙና የአውቶብስ ዴፖዎቹ የራሳቸው የጥገና ማዕከል፣የነዳጅ ማደያ፣ ዘመናዊ የመኪና የማጠቢያ ቦታና ሰፊ የማቆሚያ ቦታ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ቢሮ ኘሮጀክቶችን በቅርበት በመከታተል በወቅቱ ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሔርም በበኩላቸው ይህ ትልቅ ውጤትና ጅማሮ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ሊስፋፋና ህብረተሰቡም እንዲያውቀዉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ሊሰራ ይገባል ማለታቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር የተገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/23901/
f1f722ca3b44cf3af8faf8644b9da77a
4879360e7096f36e9eb3b0f426787ea7
በእስያ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የበርካቶችን ህይወት ቀጥፏል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
በእስያ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የበርካቶችን ህይወት መቅጠፉ ተገለጸ፡፡በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በጊዜያዊ መቆያ ጣቢያዎች ኑሮአቸውን ለመመስረት ተገደዋል ነው የተባለው፡፡ምንም እንኳን ቻይና በጎርጎሮሳውኑ 2019 ብቻ 9 አውሎ ንፋስ ብታስተናግድም የቻይናው የዜና አውታር ሽንዋ ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት ሊኪማ የተሰኘው የአሁኑ አውሎ ንፋስ ግን በሀገሪቱ ታሪክ በአመታት የታየው ከባዱ አውሎ ንፋስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በገንግ ዡ ከተማ ዤጀንግ ግዛት በአውሎንፋሱ ሳቢያ ተፈጥረው እንዳሻቸው የሚተሙ ወንዞች ያገኙትን እየጠራረጉ መውሰዳቸውን ቀጥለዋል፡፡በግዛቲቷ የተሰማሩ የነፍስ አድን ሰራተኞችም ሰዎችን ከጎርፍ አደጋው ለመታደግ ህይወትን እሰከማጣት የሚያደርስ ተግባር በጀግንነት ሲከውኑ ተስተውለዋል፡፡በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችም ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋልም የተባለው፡፡ምንም እንኳን ማእበሉ የመቀነስ አዝማሚያ ቢታይበትም ወደ ቻይናዋ ቅንጡ ከተማ ሻንጋይ ግን መገስገሱን አሁንም አላቆመም ተብሏል፡፡አስቸጋሪው የአየር ጸባይ በቻይና ብቻ ሳይገታ ጉዞውን ወደ ሌሎችም የእስያ ክፍሎች በማድረግ በፓኪስታኗ ካራቺም መዳረሻውን አድርጓል፡፡ጥቂት የማይባሉ ሰዎችም በሀገራቸው መንግስት ላይ ቁጣቸውን እየገለጹ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡በቻይና ሊኪሚያ በተሰኘው አውሎ ንፋሰአዝ ሳቢያ በትንሹ 36 ሰዎች ሲሞቱ፣ በፓኪስታን እና ህንድ ደግሞ መነሻውን ከውቂያኖስ ያደረገ ነፋስ ባስከተለው ከባድ ዝናብ ምክኒያት ከ160 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡165ሺ የሚጠጉት ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ለመጠለል መገደዳቸውን አልጀዚራ በዘገባው አመላክቷል፡፡
https://waltainfo.com/am/34125/
e489522bbe940cb7588749fde642f730
3bc9ae773b775ca0df8d5e347aad23fd
1 ሺህ 440ኛው የአረፋ በዓል በመላ ሀገሪቱ ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
የ1440ኛው የዒድ አልአድሀ (አረፋ) በዓል በመላ አገሪቱ  በደማቅ ስነ ስርዓት ተከበረ፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተወካይ ሼህ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለአገራችን አንድነትና ለሰላም፣ ለአብሮነት በጉልበታችን፣ በእውቀታችንና በገንዘባችን የሚፈለግብንን ሁሉ ማበርከት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡በበዓሉ ላይ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ በበኩላቸው፣ የአረፋ በዓል ለመላው የሙስሊም ማህበረሰብ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሳብ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር የሙስሊሙን ጥያቄ ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም በዘላቂነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተወካይ አቶ ዮሃንስ ምትኩ በዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የዘንድሮን የዒድ አልአድሀ በዓል ልዩ የሚያደርገው የሙስሊሙ አንድነት ከወትሮው በተለየ መልኩ የተጠናከረበት፣ በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና በሃይማኖት አባቶች ያጋራ ጥረት በሰላማዊ መንገድ ልዩነቶች የጠበቡበትና መቻቻል በታየበት ወቅት በድምቀት መከበሩ ነው ብለዋል፡፡(ኢቢሲ) 
https://waltainfo.com/am/32644/
086a4d54244921a355d2014ffbcdf2a5
ca5fe93a994865fe53497ca156b555e7
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለመቄዶንያ የ155 ሚሊየን ብር የአደጋ ስጋት የመድህን ሽፋን ሰጠ
ሀገር አቀፍ ዜና
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለመቄዶንያ አረጋዊያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ155 ሚሊየን ብር የአደጋ ስጋት የመድህን ሽፋን ሰጥቷል፡፡የድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች የአረጋዊያኑን መርጃ ማዕከል  በጎብኙበት ወቅት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ እንዳሉት መርጃ ማዕከሉ ቀጣይነት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችል ዘላቂ የመድህን ዋስትና ሽፋን እንዲያገኝ ጥረት እየተደረገ ነው ፡፡ማዕከሉ ለሚያስገነባው ሆስፒታል፣ ሰራተኞች እንዲሁም ተሽከርካሪዎች የሚሆን 155 ሚሊየን ብር የሚደርስ የአደጋ ስጋት የመድህን ሽፋን መስጠቱን አቶ ነፃነት ገልፀዋል፡፡የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በፊትም ለመቄዶኒያ የአረጋዊያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የተለያዩ ድጋፎችንና የመድህን ሽፋን መስጠቱ ይታወሳል፡፡  
https://waltainfo.com/am/32641/
8f18389f882b70166507b69412d17a42
de1f7f7d336274e4e7d6ab47a00a8652
አዲስ ወግ ውይይት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እየተካሄደ ነው
ቢዝነስ
አዲስ ወግ የውይይት መድረክ “አንድ ጉዳይ የምጣኔ ሃብት ሪፎርም መነሻና አቅጣጫ” በሚል ርዕስ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡በመድረኩ ባለፉት 17 ወራት የተተገበሩ አንኳር የማሻሻያ ስራዎችን በተመለከተ   የፋይናንስ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ብሩክ ታዬ ማብራሪያ ሰጥተዋል።ዘላቂ መፍትሄ የሚሹት እንደ የዋጋ ግሽበት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የብድር አከፋፈል ችግሮችንና ልሎችንም ለመፍታት የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር እንቅስቃሴዎች መደረጋቸውን አስታውሰዋል።ለዚህም ሲባል ከአበዳሪዎች ጋር በመደራደር እፎይታ ለማግኘት የሚያስችሉ ስልቶችን ተግባራዊ ማድረግ፣ ያላለቁ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ማጠናቀቅ እንዲሁም ሕጎችን የማብላላትና የመከለስ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል።በወጭ ንግድ ላይ አለም አቀፍ አሰራርን የመረዳት ክፍተት ችግሮች ባጋጠሙ ወቅት ሙሉ በሙሉ መርምሮ የመረዳት አቅም ማዳበር አለመቻሉን ያነሱት የንግድ እንደራሴው  አቶ ብሩክ ፍቅሩ÷የሕግና የአሰራር ማዕቀፎች ባለሃብቶችንና የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ሳይሆን ግለሰቦችንም መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡አዲስ ወግ የውይይት መድረክ  ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በድሬዳዋ ከተማ በቅርቡ መካሄዱ ይታወሳል፡፡
https://waltainfo.com/am/23902/
6e1292a8d0fd2c5d37ed741f0124e14b
719fb1741c7433e2c8939804642b0a56
የወሳን ኩነት ምዝገባ የዜጎችን ህገ መንግስታዊ፣  ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ስታቲስቲክስ ቀን ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሃላፊዎች እና የሚመለከታቻው አካላት በተገኙበት ተከብሯል፡፡“የልደት ምስክር ወረቀት ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና አድሏዊ አሰራርን ለማስወገድ መሰረት ነው” በሚል መሪ ቃል ነው የተዘጋጀው፡፡በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ የወሳን ኩነት ምዝገባ  ዜጎች ህገ መንግስታዊ መብታቸውንና  ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን የሚረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ዘይኑ ጀማል በበኩላቸው ከልደት እና ሞት ጋብቻ እና ፍቺ ምዝገባ የሚገኘው መረጃ ለሃገሪቱ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል፡፡የኢሚግሬሽን፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል በዓለም ከ1 ቢሊየን ሰዎች በላይ የማንነት መታወቂያ ሰርተፊኬት እንደሌላቸው በመግለፅ÷ በኢትዮጵያም 65 በመቶዎቹ ህጋዊ መታወቂያ እንደሌላቸው ነው የገለፁት፡፡ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የሚመዘገቡ ተማሪዎችም ምዝገባቸው ያለምንም ክፍያ የሆኑ በልደት የምስክር ወረቀት እንዲመዘገቡ እንደሚደረግም አክለዋል፡፡በ2063 የተያዘው ዘላቂ የልማት ግቡን ለማሳካት በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግም ነው የገለፁት፡፡በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ዳይሬክተር አደል ሆደር በኢትዮጵያ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት የተወለዱ ጨቅላ ህፃናትን የማስመዝገብ ባህሉ 3 በመቶ ብቻ የነበረ ሲሆን÷ የወሳን ኩነት ምዝገባ ከተጀመረበት በሶስት ዓመታት ውስጥ ቁጥሩ ወደ 20 በመቶ ከፍ ማለቱን አንስተዋል፡፡በዝግጅቱልጆቻቸውን ለልደት ሰርተፊኬትያስመዘገቡ ወላጆችና አዲስ ጋብቻቸውን በወሳኝ ኩነት ያስመዘገቡ ጥንዶች ከፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32643/
1eda9f9c004de2e1ea700068b9f60aed
45e8d4b246ef0790b961bd8f4dbb7ddf
ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለቡ ቫርኔሮ አከባቢ ሰሞኑን በፈረሰው አሊፍ መስጅድ በመገኘት የሀይማኖት አባቶችን አነጋገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለቡ ቫርኔሮ አከባቢ ሰሞኑን በፈረሰው አሊፍ መስጅድ በመገኘት የሀይማኖት አባቶችን አነጋግረዋል፡፡ኢንጅነር ታከለ ኡማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጪ የፈረሰውን የአሊፍ መስጅድ ጎብኝተዋል፡፡በዚሁ ጉብኝታቸውም ጥቂቶች በተንኮል ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ሊያጋጩ እና በሴራ ሊበትኑ ቢያስቡም እኛ ግን ችግሮችን በተሻለ መንገድ እናልፋቸዋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማምለኪያ ቦታዎችን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ከሁሉም የእምነት ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡መስጅዱን በማፍረስ የተሳተፉ አካላትን ተጠያቂ ከማድረግ ጎን ለጎንም መስጅዱን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባትም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ 4 ሺህ ካሬ ሜትር ተለዋጭ ቦታም ለአዲስ አበባ መጅሊስ መተላለፉም ነው የተገለጸው፡፡ከተጀመረው የለውጥ ጉዞ የሚያስተጋጉሉንን ለመግታት አሁንም የጋራ ጥረታችን ሊቀጥል ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ከከንቲባው ጽ/ቤት የተኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32640/
11277e57483664ef151377f8afb1c8e6
6b220bf48a36649c8313dcb57ae1e0bc
የግብርና ሚኒስቴር በ2011 በጀት ዓመት ለ1.3 ሚሊየን ዜጎች የገጠር ስራ ዕድል መፍጠሩን አስታወቀ
ቢዝነስ
የግብርና ሚኒስቴር በ2011 በጀት ዓመት ለ1.3 ሚሊየን የገጠር ስራ ዕድል መፍጠሩን አስታወቀ፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2011 በጀት ዓመት በግብርና፣ በማዕድን ማናፋክቸሪንግ እና በሌሎች አገልግሎት ሰጪ መስኮች ላይ 1.8 ሚሊየን የገጠር ስራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ 1.3 ሚሊየኑን ማሳካቱን አስታውቋል፡፡ሚኒስቴሩ በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ የ2011 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀምና የ2012 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ እየተወያየ ሲሆን፣ በባለፈው በጀት ዓመት በገጠር የስራአጥነት ችግርን ለመቅረፍ በተሰራው ስራ የእቅዱን 73 በመቶ ማሳካት አሳክቻለሁ ብሏል፡፡በዞን፣ ወረዳና ቀበሌ የአደረጃጀት እርከኖች ላይ የገጠር የስራ ዕድል ፈጠራ ባለቤት ማጣት በዘርፉ የሚታይ ዋነኛ ተግዳሮት እንደነበር  በውይይቱ ላይ የተገለጸ ሲሆን፤ የአቅም ማነስ፣ ተደራሽ የሆነ የመረጃ አያያዝ ችግር፣ የገበያ ትስስር ማጣት እንዲሁም የባለድርሻ አካላት በቅንጅት አለመስራት በማነቆነት ተለይቷል፡፡በ2011 በጀት ዓመት የኦሮሚያ ክልል የዕቅዱን 83 በመቶ፣ የአማራ ክልል ደግሞ 81 በመቶ በማሳካት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ቀዳሚ ነበሩ ተብሏል።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በተግዳሮትነት የተመዘገቡ ማነቆዎችን በማቃለል በ2012 በጀት ዓመት በመላ ሀገሪቱ 1.7 ሚሊየን የገጠር ስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሰራም አስታውቋል፡፡የግብርና ሚኒስቴር ከ2008 እስከ 2010 ዓ.ም በገጠር የስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ስራ ፈላጊዎች በፍላጎታቸው ወደ ስራ ከመግባት ይልቅ መንግስት ባስቀመጣቸው አማራጮች መሳተፋቸው በውጤታማነታቸው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንደፈጠረባቸውም ገልጿል፡፡በጥናቱ ከ2000 እስከ 2010 ዓ.ም በገጠር የስራ እድል ፈጠራ ከ3.8 ሚሊዮን በላይ የስራ እድል እንደተፈጠረም ተመላክቷል፡፡
https://waltainfo.com/am/23899/
4c7868b0825318e0d526eee72fe5d565
3a5c448353b3182613eb201e15514ed3
የአረፋ በዓል ሲከበር አቅመ ደካሞችን በማሰብና በመደገፍ ሊሆን ይገባል- ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር
ሀገር አቀፍ ዜና
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል እምነቱ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማሰብና ያለው ለሌለው በማካፈል እንዲያከበር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ አሳሰቡ።የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ 1 ሺህ 440ኛውን የአረፋ በዓል አስመልክተው ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ኢድ አል አድሃ አረፋ አላህ የነብዩ ኢብራሂምን ፍቅርና እምነት ለመፈተን ልጃቸውን ለመስዋዕትነት እንዲያቀርቡ ያዘዘበትን ዕለት ለማሰብ የሚከበር ሃይማኖታዊ በዓል ነው።ይህን ታሪክ ለመዘከር በዓሉ “የመስዋዕትነት በዓል” ተብሎ እንደሚጠራ የእምነቱ ሊቃውንት ያስረዳሉ፤ የእምነቱ ተከታዮችም የነብዩ መሃመድን ፈለግ ተከትለው በዕለቱ እርድ ይፈጽማሉ።ምዕመኑ በዓሉን ሲያከብርም እምነቱ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማሰብ፣ ያለውን በማካፈልና በማስደሰት መሆን እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።በአሁኑ ወቅት አንገብጋቢው ጉዳይ አንድነትና ሠላምን ማስጠበቅ መሆኑን የጠቀሱት ሃጅ ኡመር እድሪስ “በአገርም ሆነ በውጭ ያለን ሁሉ አንድነታችንንና ሠላማችንን ልንጠብቅ ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። (ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/32638/
f78788af119e3c36a439c6ff430ee66e
1da34c1e5f1b2d19dfde326b75b956df
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቀቀ
ፖለቲካ
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀቀ።የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባልና በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለኢቢሲ እንደተናገሩት፥ ኮሚቴው በወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የድርጅት ስራዎች እና የአመራር ቁመና ላይ ሀላፊነት በተሞላው መንገድ ህዝብና መንግስትን በሚያስቀጥል መልኩ ዝርዝርና ጥልቅ ግምገማዎችን አካሂዷል።በዚህ ድክመት ነው ያላቸውን በመለየት በዝርዝር መፍትሄዎችን ያስቀመጠው ኮሚቴው፥ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የመጡ በድክመት ያነሳቸውን ዝንባሌዎችን መመልከቱን ነው ያነሱት።ለውጡ ህዝቡ በሚፈልገው ደረጃ ወደፊት እንዲሄድ ህዝቡና ሀገሪቱ ወደሚፈለገው የከፍታ ደረጃ እንዲደርሱ የሚታትሩ እንዳሉ ሁሉ በለውጡ የቀድሞውን ይዞ የመቆዘም፣ ህዝበኝነት እና ወላዋይነት በአመረራር ደረጃ እንዳሉና ይህም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አንድ ሆነው በአንድ አቅጣጫና እና በተመሳሳይ ፍጥነት እንዳይሄዱ ማድረጉን በድክመት እንደገመገመ ገልፀዋል።በዚህ ላይም የጋራ ስምምነት መደረሱን በመጠቆም ከድርጅት በላይ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ መቀጠል እንዳለባቸው በማንሳት ለውጡን በመምራት ሂደት በተሸለ መረጋጋት፣ መደማመጥ እና ሀላፊነት በሚሰማ አግባብ ግምገማውን መካሄዱን ነው አቶ ፍቃዱ የተናገሩት።በሀገር ደረጃ የሚስተዋለው የብሄር ፅንፈኝነት ለሀገራዊ አንድነት እና ለፌደራላዊትና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ችግርና ተግዳሮት እንደሆነ በማንሳት መታገል እንደሚገባ ኮሚቴው ተመልክቷል።ማንነቶች መከበር ያለባቸው ቢሆንም ኢትዮጵያዊ ማንነትን አስታርቆና አቻችሎ ማስኬድ እንደሚገባ መነሳቱንና በማህበራዊ ሚዲያው ከሚንፀባረቁትና አመራሩም ከሚገዛቸው ፅንፈኝነት በመውጣት መታገል እንደሚገባ ዝርዝር ግምገማ ተካሂዷል ብለዋል።የህግ የበላይነትን ከማስከበር አንፃር ባለፉት ጊዜያቶች ህግና ስርዓትን ለማስከበር የህዝቡ የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያው መብቶች ተገድበው እንደነበር ከዚህም ለመውጣት በህዝቡ ገፊነት ኢህአዴግ ለውጡን እዚህ ደረጃ ማድረሱን ተመልክቷል።ነገር ግን ህዝቡ ነፃነቱን አጠቃቀም ላይ ክፍተቶች መታየታቸውን በማንሳት ኮሚቴው በነፃነት እና በደህንነት መካከል ሚዛኑ መጠበቅ እንዳለበት በማንሳት ማንኛውም ጥያቄ በሰለጠነ እና በሰከነ መልኩ ለሀገር ያለውን ፋይዳ በመመልት የተሰጠውን መብት መጠቀም እንደሚገባ መገምገሙን ነው አቶ ፍቃዱ ያነሱት።ከዚህ ውጪ የሚሄዱ ህገውጥ፣ ስርዓት አልበኝነት እና በሀይል ማንኛውንም ለመፈፀም የሚደረጉ ነገሮች ዋጋ የሚያስከፍሉ በመሆናቸው እና ነፃነቱን የሚፈታተኑ በመሆናቸው እነዚህን ክፍተቶች ከህዝቡ ጋር በመሆን በውስጡም ያሉትን ጉድለቶች በማረም የህግ የበላይነትን ሳይደራደር ማስከበር አለበት የሚል ድምዳሜ በግምገማው መደረሱን አስታውቀዋል።በለውጡ ላይ ያለውን ብዥታ የተመለከተው ኮሚቴው ለውጡ በህዝብ ግፊት ኢህአዴግ በውስጡ በወሰዳቸው እርምጃዎች የመጣ መሆኑን በማስመር ሁሉም በለውጡ ውስጥ ድርሻ እንዳለው ተመልክቷል።ኮሚቴው በግምገማው የደረሰባቸውን ድምዳሜዎች ያብራሩት አቶ ፍቃዱ፥ አንዱ ድምዳሜ እንድነትን የሚንዱ ነገሮች መታረም እንዳለባቸው የሚመለከተው ነው ብለዋል።በብሄራዊ ድርጅቶች መካከል በጋራ ያሳለፏቸው መልካም ነገሮች በጋራ የከፈሏቸው መስዋእቶች እና ትግሎች እንዳሉ ያነሱት አቶ ፍቃዱ፥ ዛሬ ላይ አነስተኛ እና ስትራቴጂክ ያለሆኑ ጉዳዮች አይደለም መታየት ያለባቸው ብለዋል።ይህንንም ታሳቢ በማድረግ ኮሚቴው አንድነትን የሚጎዱ ነገሮችን በግልጽ በመገምገም አንዱ ድርጅት ሌላው ላይ ጣት መቀሰር ሳይሆን ራሱን ከለውጡ አንፃር እንዲመለከት ድምዳሜ ላይ ተደርሷል ብለዋል።በጋራ በመስማማት ድምዳሜ የተደረሰባቸውን ነገሮችን በሁሉም ደረጃ መተግበር ላይ ክፍተቶች እንዳሉ ኮሚቴው ተመልክቷል።ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የደረሰባቸውን ድምዳሜዎች መሰረት በማድረግም ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንዳስቀመጠ አቶ ፍቃዱተናገርዋል።በሁሉም የሀገሪተ አከባቢዎች የዜጎች የመዘዋወር እና ንብረት የማፍራት ህገ መንግስታዊ መብት መከበር እንዳለበት በመመለክት የደህንነት እና ነፃነት ሚዛን በተጠበቀ መለኩ የህግ የበላይነት እንዲከበር አቅጣጫ አስቀምጧል።የለውጡ ስራዎች ተቋማዊ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር የሚያስፈልጉ ህጎች እና ደንቦችን በማውጣት ህዝቡን ባሳተፈ ሁኔታ እንዲተገበሩም የሚል አቅጣጫ ተቀምጧል።የለውጡን ትክክለኛ ምን ማለት እና ዓላማው ምንድነው በሚለው ላይ ግልፅነት መፍጠር ሌላው አቅጣጫ መሆኑን አንሰተዋል።መገናኛ ብዙሃን በህዝብ አብሮነትና መቻቻል እንዲሁም አንድነት እና የህግ የበላይነት ላይ እንዲሰሩ ለማስቻልም እንዲሰራ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡ ነው የተናገሩት።ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫም ህገመንግስቱ ባስቀመጠው መሰረት 2012 ላይ መካሄዱ አስፈላጊነት ላይ አቋም በመያዝ እንደ ድርጅትም እንደ መንግስትም ዝግጅት እንዲደረግ ነው አቅጣጫ ያስቀመጠው።በደቡብ ክልል እየተነሱ ባሉት የክልልነት ጥያቄ በተመለከተ ኮሚቴው መምከሩን የተናገሩት አቶ ፍቃዱ፥ ደኢህዴን በክልሉ እየተነሱ ላሉት ጥያቄዎች ሳይንሳዊ መፍትሄ ለመስጠት ያከናወነውን ጥናት ተመልክቷል።በጥናቱ መሰረት ደኢህዴን ያቀረበውን የክልልነት መዋቅር የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአወንታ መመልከቱን እና ለተግባራዊነቱም ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ገልፀዋል።ከኢህአዴግ ውህደት አንጻር በሀዋሳው ድርጅታዊ ጉባኤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የተካሄደ ጥናት አልቆ ውይይት እየተደረገ መሆኑን እና ሁሉም ብሄራዊ ድርጅቶች መክረውበት ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንዲያቀርቡ አቅጣጫ መቀመጡን ተናግረዋል።
https://waltainfo.com/am/31285/
46c302a78d1822f0dbbf0f8a5149a136
0858e1d55de6a1418e89860915e7a0b5
በሆንግ ኮንግ አዉሮፕላን ጣቢያ ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ አዲስ ተቃዉሞ መቀስቀሱ ተሰማ
ፖለቲካ
በቻይናዋ እራስ ገዝ አስተዳደር ሆንግ ኮንግ አዉሮፕላን ጣቢያ ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ አዲስ ተቃዉሞ መቀሳቀሱ ተሰማ፡፡በቻይናዋ እራስ ገዝ አስተዳደር ሆንግ ኮንግ ወንጀል ፈፅመዉ ጥፋተኛ የሚባሉ ዜጎች ለፈጸሙት ወንጀል ከቻይና መንግስት ፍርድ እንዲሰጣቸዉ የሚያስችል ህግ መዉጣቱን ተከትሎ የግዛቲቱ ነዋሪዎች ህጉን በመቃወማቸዉ ሆንግ ኮንግ ለወራት በህዝባዊ አመፅ ስትናወጥ ቆይታለች።ለሶስት ወራት የዘለቀዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ማብቂያዉ መች እንደሆነ ዛሬም በዉል የታቀወ ነገር የለም።  አልጀዚራ ባስነበበዉ መረጃ በግዛቲቱ አዉሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ አዲስ ተቃዉሞ ተቀስቅሷል። ተቃዋሚዎቹ በአዉሮፕላን ጣቢያዉ ድምፃቸዉን ያሰሙት በአዉሮፕላን ጣቢያዉ የሚመላለሱ አለም አቀፍ ተጓዦች የችግሩን መጠን እንዲረዱና አለም አቀፉ ማህበረሰብም በጉዳዩ ላይ የበኩሉን ተፅእኖ እንዲያሳድር በማሰብ ነዉ ተብሏል።የተቃዉሞዉ ዳግም መቀስቀስን ተከትሎ የሆንግ ኮንጓ ዋና አስተዳዳሪ ካሪ ላም መንግስታቸዉ ተቃዋሚዎችን የሚለማመጥበት ትዕግስት እንደሌለዉና አስፈላጊዉን እርምጃ ለመዉሰድ መሰናዳቱን አስታዉቀዋል።በቼክ ላፕ ኮክ አዉሮፕላን ጣቢያ የተሰባሰቡት ተቃዋሚዎቹ ጥቁር ቲሸርቶችን የለበሱና ቁጥራቸዉም በመቶዎች የሚቆጠር ስለመሆኑ ተነግሯል። ተቃዋሚዎቹ ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ተቃዉሟቸዉን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማድረስ መሰል ተቃዉሞ ያካሄዱ ሲሆን፣ የአሁኑም ለሁለተኛ ጊዜ ስለመሆኑ ተነግሯል።ተቃዉሞዉን ተከትሎም የአዉሮፕላን ማረፊያ ጣቢያዉ ኃላፊዎች በአከባቢዉ ያለዉ የፀጥታ ኃይል እንዲጠናከርና የአዉሮፕላን መሳፈሪያ ቅፅ ያልያዙ ሰዎች ወደ ቅጥር ግቢዉ እንዳይገቡ እግድ ጥለዋል።የአሁኑ ተቃዉሞ ከመንግስት አካላት እዉቅና የሌለዉ ቢሆንም ከዚህ ቀደም በአዉሮፕለን ጣቢያዉ የተደረጉ የተቃዉሞ ሰልፎች ግን በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቃቸዉ ነዉ የተሰማዉ። በመሆኑም ምንም እንኳን ተቃዉሞዉ ቢኖርም የአዉሮፕላን ጣቢያዉ መደበኛ ስራዉን እያከናወነ ስለመሆኑ ተገልጿል።የአልጀዚራዉ ሰዉ ሮብ ማክብራይድ ከስፍራዉ እንደዘገበዉ የአዉሮፕላን ጣቢያዉ ተቃዉሞ ይልቅ የግዛቲቱን ባለስልጣናት ስጋት ዉስጥ የከተታቸዉ በቀጣይ ቀናት ሀመላዉ ሆንግ ኮንግ ይካሄዳል ተብሎ የተሰጋዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ነዉ።በሆንግ ኮንግ የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ ካስከተለዉ የፀጥታ መደፍረስ ባለፈ የግዛቲቱን ምጣኔ ሀብትም ክፉኛ እየጎዳዉ ስለመሆኑ መረጃዎች አመላክተዋል። በግዛቲቱ ኃላፊዎች ይፋ የተደረገ መረጃ እንዳመላከተዉ ባለፈዉ ወር መጨረሻ ላይ የነበረዉ የቱሪስት ፍሰት ከባለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ26 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።   ይህ ደግሞ በግዛቲቱ ነዋሪወፖች ላይ የሚያስከትለዉ ምጣኔ ሀብታዊ ቀዉስ የከፋ እንደሚሆን ነዉ የሚጠበቀው። በሆንግ ኮንግ ለ250ሺ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረዉ የቱሪዝም ዘርፉ 4.5 በመቶ የሚሆነዉን የግዛቲቱን ምጣኔ ሀብት ዘርፍም ይሸፍናል።የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ካሪ ላምም ለወራት የዘለቀዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ያስከተለዉን ምጣኔ ሀብታዊ ቀዉስ ሱናሚ ሲሉ ከአስከፊዉ የአዉሎ ንፋስ ወጀብ ጋር አመሳስለዉታል።የሆንግ ኮንጉ ተቃዉሞ ግዛቲቱ በፈረንጆቹ 1997 ከእንግሊዝ ለቻይና ተላልፋ ከተሰጠች ወዲህ ከፍተኛዉ ስለመሆኑ አልጀዚራ በዘገባዉ አስታዉሷል።
https://waltainfo.com/am/33982/
e6389c9697486466de36b9997c09ed17
4af5692063bccf1137789060860fb8d7
ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት የባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች
ፖለቲካ
ሰሜን ኮሪያ ሁለት የባልሰቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ባህር ማስወንጨፏ ተነግሯል፡፡ይህም ሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ያደረገቻችውን የሚሳኤል ሙከራዎች  አምስት አድርሶታል፡፡ከደቡብ ሃምግዮንግ ግዛት ሃምሁን ከተማ እንደተተኮሱ የተነገረላቸው  ሁለቱ ሚሳኤሎች በጃፓን ባህር የኮሪያ ባህረ ሰላጤ አካባቢ ማረፋቸው ተነግሯል፡፡የባሊስቲክ ሚሳኤሎቹ  የመካከለኛ ርቀት ተወንጫፊዎች ሊሆኑ እንደሚችልም የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያ ሰላማዊ መልዕክት እንደደረሳቸው ከገለጹ በኋላ ሰሜን ኮሪያ ወደ ባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ተመልሳ ገብጻለች፡፡የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን በበኩላቸው የደቡብ ኮሪያና አሜሪካ የጋራ ወታደረዊ ልምምድ እንዳልተዋጠላቸው ገልጸው እንደነበረም ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡
https://waltainfo.com/am/33983/
0d62bb28a790a3494d82450bc3ffa874
431d51d5129c3c37cab6131b2ee74e6b
መቀንጨርን ዜሮ ለማድረግ መንግሥትና ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
መቀንጨርን ዜሮ ለማድረግ የመንግሥት እና የባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።የሰቆጣ ቃል ኪዳን የሙከራ ምዕራፍ ትግበራን አስመልክቶ የተዘጋጀ ከፍተኛ የምክክር መድረክ በሸራተን ሆቴል ተካሂዷል።በመድረኩ ላይ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ተሳታፊዎቹ የመቀንጨር ችግርን በሚፈለገው ደረጃ ለመፍታት በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡በቀጣይ የሰቆጣ ቃልኪዳን አፈፃፀም ላይ የሚታዩ የበጀት፣ የግብዓት እና ተያያዥ ችግሮችን በመፍታት በተያዘው በጀት ዓመት ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል። (ምንጭ፡-የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/32635/
f334b9e57bc2250d99c5976d660de7eb
c17c6702144a001c11a3994ad428c447
ፓኪስታን ከህንድ የካሽሚር ውሳኔ ጋር በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ ቻይና ላከች
ፖለቲካ
የፓኪስታኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻህ ሙሀሙድ  ህንድ በካሽሚር ግዛት ያሳለፍችውን ውሳኔ እንድትቀለብስ ለመድረግ ያለመ ጉዞ ወደ ቻይና አድርገዋል፡፡በቻይና ቆይታቸውም ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም ነው የሚጠበቀው።የአሁኑ  የህንድ ውሳኔ ከፍተኛ  የፖለቲካ ትኩሳት በነገሰበት አካባቢ ባለፉት ሰባት አስርት ዓመታት ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል ጠንካራው እንደሆነም ፖለቲከኞች ይናገራሉ፡፡ይህን ተከትሎም ፓኪስታን ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለመውሰድ መዘጋጀቷን ገልጻለች።ህንድ በቅርቡ የሻረችው አንቀፅ 370 የካሽሚር ግዛት የነበረውን የራስ ገዝ አስተዳደር እና ህግ የሚያግድ ሲሆን፤ ውሳኔውን ተከትሎ ህንድ በርካታ ወታደሮችን ወደ አካባቢው በማሰማራት ፖለቲከኞችን አስራለች፣ የኢንተርኔት እና  የስልክ ግንኙነትም እንዲቋረጥ አድርጋለች፡፡ይህ ውሳኔ ወትሮም ሻክሮ የቆየውን የሁለቱን  ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ወደ ውጥረት  ከቶታል፡፡ ህንድ ለካሽሚር ግዛት ልዩ መብት የሚሰጠውን ህገ መንግስታዊ ውሳኔ እንዲሻር ማድረጓ የሚታወስ ነው፡፡ምንጭ፦ አልጀዚራ
https://waltainfo.com/am/33981/