query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
7
297
category
stringclasses
6 values
passage
stringlengths
137
5.93k
link
stringlengths
28
740
608823f9f4635381c68222501123b2ed
465525198bd3bf4e5b137fe927e34ee1
የኦሊምፒክ ማጣሪያ ተሳታፊዎች የሚለዩበት ቻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል
ስፖርት
ብርሃን ፈይሳየኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የክለቦች ቻምፒዮና በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተሻለ ብቃት ያሳዩ ቦክሰኞች ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ታውቋል።በቦክስ ስፖርት ከሚካሄዱት ዓመታዊ ቻምፒዮናዎች መካከል አንዱ በክለቦች መካከል የሚካሄደው ነው፤ የዚህ ውድድር የመጀመሪያው ዙር በአዲስ አበባ ከተማ ተጀምሯል። የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ከአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ቻምፒዮና፤ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ ውድድርም ነው። በውድድሩም ላይ አምስት ክለቦች ከአዲስ አበባ (ፌዴራልፖሊስ፣ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ አዲስ አበባ ፖሊስ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እና ኦሞቲክ ቦክስ)፣ ሁለት ክለቦች ከአማራ ክልል (ጎንደር ከነማ እና ደሴ ከነማ) እንዲሁም ድሬዳዋ ከነማ በድምሩ ስምንት ክለቦች ተሳታፊ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያሳያል። በአጠቃላይ ክለቦቻቸውን ወክለውም 12 ሴትና 76 ወንድ ቦክሰኞች በጥቅሉ 88 ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ። ውድድሩ የሚካሄደው በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሲሆን፤ በ10 ክብደቶች በ49፣ 52፣ 57፣ 60፣ 63፣ 69፣ 70፣ 81፣ 89 እና 91 ኪሎ ግራሞች እየተካሄደም ይገኛል። የቦክስ ስፖርት ከንክኪ ስፖርቶች መካከል አንዱ እንደመሆኑ ጨዋታው በሚካሄድበት ወቅት ቦክሰኞቹ አካላዊ ቅርርብ ሊያደርጉ እና ሊነካኩ ይችላሉ። በመሆኑም በዚህ ረገድ ውድድሩ ሙሉ ለሙሉ የኮቪድ 19 ጥንቃቄን በተላበሰ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ነው ፌዴሬሽኑ ያረጋገጠው። ይኸውም ተወዳዳሪዎችና አሰልጣኞች የኮቪድ ምርመራ እንዲያደርጉና ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዳይገናኙ በካምፕ እንዲቆዩ በማድረግ ነው። ከዚህ ባሻገር ውድድር የሚደረግበት ሪንግ ቶሎ ቶሎ በኬሚካል እንዲጸዱ እንዲሁም ተመልካቾች ውድድሩ ላይ እንዳይገኙም ተደርጓል። ኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እንደመሆኑ በመላው ዓለም ስፖርታዊ ውድድሮች ተቋርጠው መቆየታቸው የሚታወስ ነው። ከእነዚህ ውድድሮች መካከል ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የቦክስ ስፖርት ማጣሪያ የሚካሄደው ውድድር ይጠቀሳል። ውድድሮች ወደ እንቅስቃሴ መግባታቸውን ተከትሎም ማጣሪያው የሚቀጥል ይሆናል። ኢትዮጵያም በዚህ ቻምፒዮና (በመጀመሪያው ዙር) የተሻለ ብቃት ያሳዩ ቦክሰኞችን በማጣሪያው የምታሳትፍ መሆኑ ታውቋል። ቻምፒዮናው አራት ዙሮች ያሉት ሲሆን፤ ሁለተኛው ዙር ከአማራ ክልል ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ጎንደር ላይ፣ ሶስተኛውን ከደቡብ ክልል ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ወላይታ እንዲሁም የመጨረሻውና የማጠቃለያው ውድድር አዲስ አበባ ላይ የሚካሄድም ይሆናል። ቻምፒዮናው ጥር 4/2013 ዓም የተጀመረ ሲሆን እስከ ጥር 7/2013 ዓም ድረስም ይቆያል።
https://www.press.et/Ama/?p=39481
65a4d23f1b9eedcdc2e06f1f3c9c4718
8cbcc5f269b0b8b7a519f07006145508
አዲስ ዘመን ድሮ
መዝናኛ
 የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ቀደምት ዘገባዎች በእጅጉ ተነባቢ ዛሬም ላገኛቸው በእጅጉ ተነባቢ ናቸው።እኛም ከእነዚህ ዘገባዎች ጋዜጣው በ1950ቹ ያስነበባቸውን ወጣ ያሉ ዘገባዎች ለዛሬ ይዘንላችሁ ቀርበናል። በዛሬው የአዲስ ዘመን ዱሮ አምዳችን አዲስ ዘመን ጋዜጣ በ1950ዎቹ ይዟቸው ከወጣ ዘገባዎች በአዘጋገባቸውና በይዘታቸው ተነባቢ ናቸው ያልናቸውን እና ሌሎች አስደናቂ ዘገባዎችን ይዘን ቀርበናል። ማገጃ ምልክት ይሰጠውማንኛውም የሥራ ድርጅት በብዙ ድካም ከተቋቋመ በኋላ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገለት የተሠራው እንዳልተሠራ የነበረው እንዳልነበር መሆኑ የማይጠረጠር ነው።በሲዳሞ ጠ/ግዛት ዋና ከተማ ይርጋዓለም የቴሌኮሙኒኬሽን ቦርድ ያቋቋመው ከፍተኛ መሥሪያ ቤት ይገኛል። የተቋቋመውም በትልቁ መኪና መንገድ አጠገብ ስለሆነ ፤ተሽከርካሪዎች የሚመላለሱበት ቦታ ነው።አንዳንድ ጊዜም ከባድ ጭነት የያዙ መኪናዎች ለምሳሌ አውቶቡስን የመሳሰሉት በሁለተኛው መንገድ እንዲያልፉ የሚታዘዙበት ቀን ስለሚያጋጥም በተጠቀሰው መሥሪያ ቤት አደባባይ የሚገኙትን ሽቦዎች ሳይመለከቱ ለማለፍ ሲሞክሩ በብዙ መጯጯህ ስልኩ ሽቦ ከመጣስ የዳነበትና መኪናውንም ለመመለስ የቻለበትን ጊዜ ለማታወስ የማይችል የለም፤ ታናናሽ መኪናዎችን ለማሳለፍ የቦታው ስፋት ይፈቅዳል።ስለ ታላላቅ መኪናዎች ግን የክፍሉ ባለሥልጣን የማገጃ ምልክት ቢያደርግበት የሚሻል መሆኑን አስታውሳለሁ። አቧራ አዋዜ አይደለም። በዚሁ ከተማ ትልቁን መንገድ በመከተል አልፎ አልፎ በሚገኙት ሰፈሮች ብዙዎች የልኳንዳ ሥጋ የተሰቀለባቸውና   ፉርኖ ይህንንም የመሳሰሉት ምግቦች የተደረደረባቸው ቤቶች ይገኛሉ። ሥጋው የሚገኝበት ብዙ ቦታ በረንዳ ስለሆነ ማናቸውም ተንቀሳቃሽና ይልቁንም በማይቋረጠው የመኪና ኃይል ከመንገዱ ላይ የሚነሳው አቧራ በሥጋውና በማናቸውም ምግብ ላይ ሲሰፍርበት ይታያል።ለማስረጃ ያህል በመንገዱ ዳር የሚገኘውን የቡና የሌላውንም ቅጠል የተመለከትን እንደሆነ በአንዱ ቅጠል ላይ ብቻ አንድ ጥርኝ የሚሞላ አቧራ ስለምናገኝ በየቀኑ በያንዳንዱ ብልት ሥጋ ላይ ተደባልቆ ወደ ሆድ የገባውን አቧራ ለመገመት እንችላለን። ስለዚህ ሥጋና ፉርኖ ይህንንም የመሳሰለ ምግብ የሚያሰናዱ ነጋዴዎች ለዚሁ አገልግሎት በዘመናዊ ዕቅድ በተሰናዳው መስታወት ውስጥ ማኖር ይገባቸዋል።ይህም ባይቻል አቧራ ወደሌለበት ሁለተኛው መንገድ እንዲዛወሩ ማድረግ ስለሚገባ ፤ሥራው የሚመለከተው ባለሥልጣን ያስብበት ዘንድ ሳስታውስ በትሕትና ነው። መመሳሰል ይገባዋልበዚሁ ከተማ የሚገኘው የጠቅላይ ግዛቱ በጅሮንድ ጽ/ቤት በሦስት ቦታ ተከፋፍሎ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ ቤቱም በጠላት ጊዜ የተሠራ አሁን መፍረስ የጀመረ ነው።ስለ የውስጥ ዕቃውም አጠባበቅ ከቤቱ ይልቅ ዘበኞቹንና ካዝናውን ማመን ግድ ሳይሆን አይቀርም። ይኸውም ሆኖ ለሥራው የተመጠነ ስፋት ያለው አይደለም። በአካባቢው የሚገኙት ቢሮዎች በአማረና በጥሩ ሕንፃ የተሠሩ ሲሆኑ፤ የተጠቀሰው መሥሪያ ቤት እርጅና የእነሱን ውበት ግርማ አሳንሶታል።ስለዚህ ጓደኞቹን እንዲመስል የክፍሉ ባለሥልጣን ይተጋበት ዘንድ ማሳሰብ የጋዜጣው ፋንታ ነው። የሲዳሞ ጠ/ግዛት አዣንስ ኃይለ መስቀል ወልደየስ (የካቲት 20 ቀን 1951 የወጣው አዲስ ዘመን) ሁለት ወንዶች ልጆችእናት በአስር ቀን ልዩነት ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደች። በወቅቱ ዜናው ጋዜጣችን ላይ ሲወጣ ርዕሰ ዜናው ከላይ እንደተጠቀሰው ሁለት ወንዶች ልጆች ብቻ ነበር የሚለው በሚከተለው መልኩ ተዘግቦ ስለነበር እንድታነቡት እንጋብዛለን። በደብረ ታቦር ከተማ ዙሪያ ቃናት ማርያም ከተባለው አገር የአቶ መኰንን ካሳ ባለቤት ያልጋነሽ አድማሱ የተባለችው ፤ጥር 22 ቀን 51ዓ.ም ከሌሌቱ 8 ሰዐት ሲሆን አንድ ወንድ ልጅ ከወለደች በኋላ 10 ቀን ቆይታ የካቲት 2 ቀን 1951 ዓ.ም ከጥዋቱ 1 ሰዐት ሲሆን አንድ ወንድ ልጅ ደግማ መውለዷንና ሁለቱም ልጆች እስካሁን በሕይወታቸው መኖራቸውን የነዚሁ ልጆች አባት አቶ መኰንን ካሳ አስታውቀውናል። የደብረ ታቦር ከተማው ዙሪያ ምክትል ገዥ ባላምባራስ ኃይሌ ታምራት በቁጥር100/1951የካቲት 10 ቀን በተጻፈ ደብዳቤ አረጋግጠውልናል።እኒህ የምክትል ወረዳ ገዥ እንደዚህ ያለው ሁኔታ በጋዜጣ እንዲገለጥ በቶሎ ለአውራጃው ግዛት አዣንስ ጽ/ቤት በማስተላለፋቸው እናመሰግናለን። ሌላዎችም ምክትል ገዥዎች የርሳቸውን አርአያ ተከትለው ይህን የመሰለ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው በፍጥነት የሚያስታውቁን ቢሆን ከፍ ያለ ምስጋና የሚያገኙበት መሆኑን እንገልጻለን።የደብረ ታቦር አውራጃ አዣንስ አሰፋ ረታ (የካቲት 17 ቀን 1951 የወጣው አዲስ ዘመን)
https://www.press.et/Ama/?p=38334
524ddf103c1b646d02bab34958c46ee4
e3564bee4dc397f060bc0d8c4a9a3ed4
የአረንጓዴ ጎርፍ በጎ አድራጎት አምባሳደሮች ተሰየሙ
ስፖርት
ቦጋለ አበበየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ የአትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር‹‹የገና በዓልን ከአንጋፋ አትሌቶች ጋር እናሳልፍ›› በሚል ትናንት በኢትዮጵያ ሆቴል በተዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መድረክ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ሁለት አምባሳደሮች ተሰይመዋል፡፡ በዚህም ከሴት ፈር ቀዳጇ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር የቀድሞ ኮከብ አትሌት ኮማንደር ቁጥሬ ዱለቻ የተሰየመች ሲሆን በወንድ ፋና ወጊው የኦሊምፒክ የሦስት ሺ ሜትር መሰናክል የነሐሴ ሜዳሊያ ባለቤትና የርቀቱ አሰልጣኝ ሻምበል እሸቱ ቱራ የዕውቅና አምባሳደርነት የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።አምባሳደሮቹ በተሰየሙበት መርሃግብር በህይወት ዘመናቸው ለኢትዮጵያ ስፖርት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የዕውቅናና የምስጋና ካባ እንዲሁም የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡ አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሐኪም ዶክተር አያሌው ጥላሁን እንዲሁም አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ሰለሞን ገብረእግዚያብሔር የዕውቅናና የምስክር ወረቀት ከተቀበሉ በኋላ በሞሀ ለስላሳ መጠጦች እንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው ቢርቦ የክብር ካባ ተጠልቆላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አትሌት መልካም ተገኝ፣ ‹‹መረዳዳት በህይወት›› በሚል ሀሳብ ለአገራቸው የሰሩ፣ የለፉ ፣ የደከሙና ለአገር ክብር የተጉ አትሌቶችንና ቀጣይ ተተኪዎችን በማንኛውም ማህበራዊ ህይወታቸው ለመታደግ በጎ አድራጎት ድርጅቱ መመስረቱን ጠቅሰው ለዚህ የተቀደሰ አላማ ሁሉም አካላት ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽነር በላይ ደጀን በበኩላቸው ‹‹መረዳዳት በህይወት›› የሚለው መሪ ቃል በጎ አድራጎት ድርጅቱን እንደሚወክል በመግለፅ፣ ለአገራቸው ክብር ፣ ህዝብና ባንዲራ የለፉ አንጋፋ አትሌቶችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች በዚህ ደረጃ ዕውቅና ማግኘታቸው ተገቢ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ በቀጣይ በጎ አድራጎት ድርጅቱ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በጋራ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል፡፡ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጅሎ በበኩላቸው ይህን በጎ አላማ እውን ላደረጉና መርሃግብሩን ላዘጋጁና ለዚህ ያበቁ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አመራሮችን አመስግነዋል። በርካታ አንጋፋ አትሌቶች በመርሃግብሩ ታድመውም የእውቅናና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=39010
841356db06403e817a5278c53afc2643
01c3a5732d6f5bdd77714d572c7bdf9f
የሊጉ በቢዝነስ ሞዴል መመራት አበረታች ጅምር መሆኑ ተገለጸ
ስፖርት
ብርሃን ፈይሳአዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሼር ካምፓኒ እንዲተዳደር መደረጉና የቴሌቪዥን ሽፋን ማግኘቱ ለሌሎች ስፖርቶችም አበረታች ጅምር መሆኑ ተገለጸ። በብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት የ2013ዓም የስፖርት ዘርፍ አፈጻጸም ሰነድ ላይ እንደተመለከተው፤የሃገሪቷ ስፖርት በቢዝነስ ሞዴል እንዲመራ በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሪሚየር ሊጉን (ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ) በሼር ካምፓኒ እንዲመራ ማድረጉ መልካም ጅማሬ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ የተደራጀው ካምፓኒው ውድድሩን የቴሌቪዥን መብት እንዲያገኝ እና የውድድር ስያሜውንም መሸጥ መቻሉ በስፖርት ላይ ትልቅ ተስፋን እና መነቃቃት ፈጥሯል። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ ሃገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ስፖርቱን በቢዝነስ ሞዴል ከመምራት አንጻር ሰፊ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው፣ ለእዚህም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ካምፓኒው መቋቋም ተጠቃሽ መሆኑን አመላክተዋል። የውድድሩ መሸጥ በተለይ ክለቦች በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያደርግ፣ ለተጫዋቾችም መልካም ዕድል የፈጠረና የሃገርን ገጽታ ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ ነው ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፣በተመሳሳይ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብም ወደ አክሲዮን የተለወጠበት ሁኔታ ሌሎች ክለቦች ልምድ የሚወስዱበት ነው ብለዋል። ይህም በቢዝነስ ሞዴል ከመመራት አንጻር የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉ ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል።የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው፤ በዓመቱ (2012ዓም) የሊግ ኮሚቴ በመፍጠር እግር ኳስ የስፖርታዊ ጨዋነትና የስፖርት መርህን የሚያከብር ዘርፍ እንዲሆን መደረጉ መልካም መሆኑን ጠቁመዋል። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ራሱን መቻልም ለሌሎች እንዴት ራስን በገቢ መቻል ይቻላል የሚለውን ያሳየ መሆኑን ተናግረው፣ ጥሩ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ጠቋሚ ነው ብለዋል። ይህንንም አጠናክሮና ተባብሮ ማስኬድ ከተቻለ በስፖርቱ የሚነሱ ጥያቄዎችና ችግሮች ይቀረፋሉ ሲሉም ተስፋቸውን አንጸባርቀዋል። ብሔራዊው የስፖርት ሪፎርም ክለቦችና የስፖርት ማህበራት በገቢ ራሳቸውን ችለው ከመንግስት ድጎማ እንዲላቀቁ እንዲሁም ሃብት እንዲያፈሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል። እንደ ኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የአፈጻጸም ሪፖርት፤ መንግስት እስካሁን ከክልል እስከ ፌዴራል ባለው ደረጃ 163 ሚሊዮን 177ሺ 165 ብር ድጋፍ አድርጓል። ይህንን ለመቅረፍም ሃገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ያሉበት ሁኔታና ቁመና ለማወቅ ቅኝት በማድረግ ያሉበትን ደረጃ ለመለየት ጥረት ተደርጓል። የስፖርት ማህበራት ስፖርቱን በቢዝነስ ሞዴል በመምራት ከድጎማ የሚላቀቁበትና የራሳቸውን አቅም በማጎልበት የ10 ዓመቱን የስፖርት ልማት እቅድ ግቦች የሚያሳኩበትን ቁመና መፍጠርም በተያዘው ዓመት የኮሚሽኑ እቅድ መሆኑም ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=39011
9f0d6f3852caca37e94c2b2a90b869e7
8f8010b037e30c19d8f3afa6d45e4f21
የኦሊምፒክ ሥራ አስፈፃሚው እስከ ቶኪዮ ኦሊምፒክ ማግስት ይቀጥላል
ስፖርት
ቦጋለ አበበ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አርባ አምስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባለፈው እሁድ በሐዋሳ ከተማ ሲያካሂድ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡፡ ባለፉት አራት ዓመታት ሲያገለግል ቆይቶ ዘንድሮ ይጠናቀቅ የነበረው የኮሚቴው የስራ አስፈፃሚና የፕሬዚዳንት የስልጣን ዘመን በመጪው ክረምት እስከሚካሄደው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ማግስት ድረስ እንዲቀጥል ጉባዔው ወስኗል፡፡ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአስራ ስድስት ወራት ተራዝሞ በመጪው ክረምት ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለታል፡፡ ኮሚቴውን ሲመራ የነበረው ሥራ አስፈፃሚ በኦሊምፒኩ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ዘንድሮ የስራ ዘመኑን አጠናቆ በጠቅላላ ጉባዔ ምርጫ ይካሄድ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ሲዘጋጅ የቆየው ስራ አስፈፃሚ የልፋቱን ውጤት እንዲመለከት እስከ ኦሊምፒኩ ማግስት እንዲቀጥል ጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ የአኖካን ጉባኤ ባስተናገደችበት ማግስት አስረኛ ክልል ሆኖ እንደ አዲስ በተዋቀረው የሲዳማ ክልል ጉባዔው መካሄዱ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክን በ2022 ለማስተናገድ እድል ባገኘችበት ማግስት በሲዳማ ክልል ዘንድሮ የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡ ኮሚቴው በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የአበበ ቢቂላን የ1964 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ገድል ለመድገም በምትዘጋጅበት ወቅት ጉባዔውን ማካሄዱና በኮቪድ-19 ስጋት ውስጥ ሆኖ መከናወኑ ጉባዔውን የተለየ እንደሚያደርገውም ተናግረዋል፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ ስፖርት የማህበራዊና ተፈጥሯዊ ሳይንስ ዘውግ መሆኑን ጠቅሰው ማህበራዊ ትስስርን በእጅጉ የሚፈጥር በመሆኑ ህብረተሰቡ ስፖርትን ባህሉ እንዲያደርግ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። እስካሁን ድረስ በስፖርት ዘርፍ የተፈጠረው ተወዳዳሪነት ዝቅተኛ መሆኑን በመጥቀስም በአትሌትክስ ስፖርት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ውጤት በሌሎችም እንዲደገም መሠራት እንዳለበት አብራርተዋል። ሚኒስትሯ የህብረተሰብ ስፖርትንም ለማስፋፋት በትምህርት ቤትና በስራ ቦታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት እንዳለበት ገልፀዋል። የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሸነር ኤሊያስ ሽኩር በበኩላቸው፣ 45ኛው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተካሄደው በስፖርት ህብረተሰቡ ዘንድ መነቃቃት በተፈጠረበት ወቅትና በብሔራዊ የስፖርት ምክር ቤት መደበኛ አንደኛ ስብሰባ ትላልቅ ውሳኔዎች በተላለፈበት ወቅት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ የአኖካ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰውም ሠላማዊና አስተማማኝ ሁኔታ በኢትዮጵያ መኖሩን አኖካ በማረጋገጡ ቀጣይ ስብሰባዎችን በራሱ ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ ለማካሄድ መነሳሳት እንዳሳየ አብራርተዋል። ለቶኪዮ 2020 የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ማድረግ በተጀመረበት ወቅት ላይ ጉባዔው በስፖርት ምክር ቤት በተቀመጡ ወሳኔዎችና አቅጣጫዎች መሠረት በጥልቀት መምከር እንዳለበት አስረድተዋል፡፡ ስፖርት ለሠላም፣ ለወዳጅነት፣ ለአንድነት፣ለወንድማማችነትና ለብልፅግና መሆኑን በመገንዘብ ጠቃሚ ውይይት እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱ ሲሆን፣በዕለቱ በስፖርት ላይ በመስራት እውቅና ለተሰጣቸው ፈርጦች ምስጋና አቅርበዋል። በጉባኤው በስፖርት አመራርነት በፌደራልና በክልል ደረጃ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ አመራር ቦታዎች ላይ ለሚገኙ አካላት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።ከነዚህም መካከል የቀድሞ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የቀድሞ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ፣ የቀድሞ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩትና አሁን የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ተስፋየ ይገዙ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ምክትል ስፖርት ኮሚሽነርና አሁን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው ባልቻ የእውቅና ሽልማት ከተበረከተላቸው መካከል ዋነኞቹ ናቸው። ጠቅላላ ጉባዔው የ44ኛው መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ፣ የ2012 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የውጪ ኦዲተር ሪፖርት መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን የ2013 ዓ.ም ዕቅድና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቀጣይ 46ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔን በተመለከተ መክሮ ውሳኔ አስተላልፏል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=39012
011166bfa21097cce9355a345d96d1ab
3b9c93b94fd66f9cc1b902020a88e47d
‹‹ሃገራዊ ችግሮችን ለማረምና አብሮነትን ለማጠናከር ስፖርት ወሳኝ ነው››- አቶ ደመቀ መኮንን የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ
ስፖርት
 ብርሃን ፈይሳ አዲስ አበባ፡- እንደ ሃገር እየታዩ ያሉትን ስብራቶችና ችግሮች ለማረምና የአብሮነትን ጉዞ ለማጠናከር ስፖርት ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ። ለስፖርቱ ዘርፍ ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቆመ። የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ደመቀ መኮንን ትናንት የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት የመጀመሪያ መደበኛ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት እንዳስታወቁት፤ ስፖርት የሰላምና የአብሮነት መሰረት፤ ሰላም ደግሞ ለስፖርት ሁነኛ ነባራዊ ሁኔታ ነው። በመሆኑም እንደ ሃገር ያሉትን ስብራቶችና በተለያየ መልክ የሚታዩ ችግሮችን ለማረምና የአብሮነት ጉዞን ለማጠናከር ስፖርት ወሳኝ ነው። አሁን ባለው ሃገራዊ ሁኔታ በጣም ብዙ ስብራቶች መኖራቸውን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ጠቅሰው፣ እነዚህን ከመጠገንና አብሮነትን ከማጠናከር አኳያ ስፖርት ሁነኛ መስተጋብር መሆኑን አመልክተዋል። የስፖርቱ መርሆዎች በአንድም ሆነ በሌላ መልክ በአስር ዓመት ሃገራዊ ዕቅድ መሪ ሃሳብ ውስጥ የተንጸባረቁ መሆናቸውን ተናግረው፣ ከየትኛውም ተቋም በላይ ሃገሪቷ በመጪዎቹ ዓመታት በሚሰራው ስራ አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌት ትሆናለች የሚል መሪ ሃሳብ ተይዟል ብለዋል። በዚህ ጭብጥ ውስጥም ዋና ዋና የስፖርት መርሆዎች ይገኛሉ ያሉት የምክር ቤት ሰብሳቢው፣ ‹‹የስፖርት መርሆዎች ከብልጽግና እንዲሁም የስፖርት መርሆዎች ከአብሮነት አኳያ፣ የስፖርት መርሆዎች በወንድማማችነት፣ በወዳጅነት፣ ጤናማ ማህበረሰብን በመፍጠር አብሮነትን የሚያስተሳስሩ እሴቶችን የተላበሱ ናቸው። በመሆኑም ለእዚህ ኢንዱስትሪ ትኩረት መስጠትና ማጠናከር ለራሳችንና ለሃገራችን ስንል ትውልዱ የሚታወቅባቸውን ስፖርቶች ለማስቀጠል ኃላፊነትና አደራም አለብን። የበለጠ ሆኖ ለመገኘት ስንልም በጣም መሰረታዊውንና ስፖርትን ከዚህ አኳያ ትርጉሙን ከፍ አድርጎ መመልከት ያሻል›› ሲሉም  አብራርተዋል። ስፖርት ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የሚለው በምክር ቤቱ የተለመደ አባባል መሆኑን ጠቅሰው፣ ወደ ተግባር ተሟልቶ እስካልተገባ ድረስ አጉልቶ መያዝ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ‹‹ታላላቅና የኩራታችን ምንጭ የሆኑ ስፖርተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እያስገኙ በመጡበት ሂደት አሁን ላይ ሆነን ሌጋሲውን እንዴት ማስቀጠል እንችላለን፤ ስፖርትስ እንዴት በሃገሪቷ ብልጽግና ጉዞ ውስጥ ሁነኛ ቦታ ይዞ ይሄዳል በሚለው ላይ ኃላፊነት አለብን›› ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ስፖርት በተወሰኑ አካላት ብቻ የሚታጠር መሆን እንደሌለበትም አስገንዝበዋል። ከታዳጊ ህጻናት እስከ ብሄራዊ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ድረስ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባም ሰብሳቢው አመላክተዋል።በብዙ ትውልዶችና በጀግኖች ጥረት ስፖርቱ ዓለም አቀፋዊ ሆኗል፤ እነዚህ ጀግኖችም ሃገራቸውንም አስተዋውቀዋል፤ አሁንም በብዙ መልኩ ስፖርቱ ዓለም አቀፋዊ መሆን ይኖርበታል፤ ለዚህ ደግሞ ምቹ ሁኔታ ያስፈልጋል፤ በተለይ በታዳጊ ህጻናት ላይ ከተሰራ መጪው ዘመን በስፖርት ያለውን አቅም ወደ ውጤት መመንዘር ያስችላል ብለዋል።አዲስ ዘመን ታኅሳስ 21/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38512
969a1adb3c275dfcb72c9a19b262ffbc
bd78535bcffacfe1ae1b0f84cba42cf0
በውድድር ወቅት በወረርሽኙ መከላከያ መመሪያዎች አተገባበር ላይ ስጋት እንዳለው ሚኒስቴሩ ጠቆመ
ስፖርት
ብርሃን ፈይሳ አዲስ አበባ፡- ስፖርታዊ እንቅስቃሴና ውድድሮች በሚከናወኑበት ወቅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎች አተገባበር ላይ ስጋት እንዳለው የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ትናንት በተካሄደው በብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በጤና ሚኒስትር እንዲሁም በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር የወጡ የኮቪድ 19 መከላከያ መመሪያዎችን ታሳቢ አድርጎ ውድድሮችንና እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑ መገለጹን አስታውቀው፣ የጤና ሚኒስቴር ግን በአተገባበሩ ላይ ስጋት እንዳለው ጠቁመዋል። በዚህ ወቅት የቫይረሱ ስርጭት ያለበት ምጣኔ ከ9-10 በመቶ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ስጋት አለባቸው በሚል ካስቀመጣቸው ሃገሮች ውስጥ ትመደባለች ብለዋል። መመሪያዎቹም ይህንን ተከትለው የወጡ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ አተገባበራቸው ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። እንደ ዶክተር ሊያ ገለጻ፤ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በስፖርት ዘርፍ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተወሰዱ እርምጃዎች በርካታና የሚያስመሰግኑ ናቸው። በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታየው በሽታውን የማቃለል ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፣ ይህም በሁሉም ዘርፍ እየታየ ይገኛል፤ ይህን ችግር ለመፍታት አመራሮች ትኩረት ሊሰጡ ይገባል። መመሪያውን መከተልና ውድድሮችን ያለተመልካች ማካሄድ ያስፈልጋል ሲሉም አስገንዝበዋል። ሚኒስቴሩ በዚህ በኩል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለእዚህም ከታላቁ ሩጫ አዘጋጆች ጋር እየተሰራ ያለውን በአብነት ጠቅሰዋል። ታላቁ ሩጫን ለማካሄድ በሚደረገው ዝግጅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአዘጋጆቹ ጋር እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰው፣ በውድድሩ የታቀደው ብዙ ቁጥር ያላቸው ተሳታፊዎችን ለማካተት መሆኑን አመልክተዋል። ይህን አሀዝ ለመቀነስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ውድድሩን ከዚህ ቀደም ከነበረው ለየት ባለ ሁኔታ ለማድረግም ፈቃደኝነት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በአዲስ አበባ ያለው የወረርሽኝ መጠን በጣም ከፍተኛ የሚባል መሆኑን አመልክተው፣ መመሪያዎቹን ብቻ ማዘጋጀት ሳይሆን ለተግባራዊነቱም መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ታኅሳስ 21/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38515
fd7e7687d7041a2b2aaf7fbf9e3ab5f6
fa5997abb25501d92753abc953d0c38c
የዓለም አትሌቲክስና 2020 የውድድር ዓመት
ስፖርት
ቦጋለ አበበ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የዓለም ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ ዝብርቅርቁ በወጣበት የፈረንጆች 2020 ዓመት የዓለም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችም ቀላል የማይባል አሉታዊ ተፅዕኖ አርፎባቸዋል። ኦሊምፒክን ጨምሮ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊና የአገር ውስጥ ስፖርታዊ ውድድሮች በተሰረዙበትና በተራዘሙበት የውድድር ዓመት የአትሌቲክስ ስፖርት በርካታ ፈተናዎችን ማሳለፉ ይታወቃል። በዓለም ሕዝብ ዘንድ ጥሩ ትውስታን ጥሎ ያላለፈው 2020 ተሸኝቶ ዛሬ በ2021 የውድድር ዓመት አንድ ብሎ የሚጀምርበት ቀን ነው። በአብዛኛው መጥፎ ትዝታውን ጥሎ ባለፈው ዓመት የአትሌቲክሱ ዓለም በርካታ አሉታዊ ተጽእኖዎች አርፈውበታል፤ በርካታ አዎንታዊ ክስተቶችንም አስተናግዷል። ከእነዚህ መካከልም አበይት ክስተት የሆኑት እንደሚከተለው ተዳሰዋል። ጥር የ2020 የውድድር ዓመት በጀመረበት ታህሳስ መጨረሻና ጥር ወር ላይ የአትሌቲክሱ ዓለም በርካታ የዓለም ክብረወሰኖችን አስተናግዷል። ኬንያዊው አትሌት ሮኔክስ ኪፕሩቶ የአስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የዓለም ክብረወሰንን ቫሌንሲያ ላይ 26፡24 በሆነ ሰዓት ያስመዘገበው በዚህ ወር ሲሆን፣ ሌላኛዋ ኬንያዊት ሼላ ቺፕኪሩይ በተመሳሳይ ውድድር የሴቶቹን የዓለም ከገጽ 46 የዞረክብረወሰን 29፡46 በሆነ ሰዓት በማሻሻል የውድድር ዓመቱን በስኬት ጀምራለች። በዚሁ ወር የማራቶን ቁጥር አንድና ቁጥር ሁለት የሆኑት ኢትዮጵያዊና ኬንያዊ አትሌቶች ቀነኒሳ በቀለና ኢሉድ ኪፕቾጌ በለንደን ማራቶን እንደሚፋለሙ ይፋ መደረጉም የውድድር ዓመቱ ትልቅ ክስተት ነበር። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በየዓመቱ የሚደምቁበት የዱባይ ማራቶን በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈው ኦሊካ አዱኛ አሸናፊ ሲሆን፣ በሴቶች ወርቅነሽ ደገፋ የኢትዮጵያውያንን የተለመደ ድል ማስቀጠል ችላለች። በቻይና ናጂንግ ባለፈው መጋቢት ወር ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ቻምፒዮና መራዘሙ የተሰማው በዚሁ ወር ነበር፤ ይህ ወድድር በኮቪድ-19 ስጋት የተራዘመ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ውድድርም ሆኗል። የካቲት ያለፈው የካቲት ወርም በዓለም አትሌቲከስ የተለያዩ የዓለም ክብረወሰኖች የተሻሻሉበት ሆኖ ይታወሳል። በተለይም ስዊድናዊው ምርኩዝ ዘላይ ሞንዶ ዱፕሌንቲስ 2014 ላይ በፈረንሳዊው ሪናውድ ላቪሌኒ ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረሰወን 6 ነጥብ 17 ሜትር በመዝለል በአንድ ሴንቲሜትር ያሻሻለበት አጋጣሚ ትልቁ ክስተት ነበር። ላቪሌኒ በተመሳሳይ ወር ግላስጎ ላይ 6 ነጥብ 18 ሜትር በመዝለልም ተጨማሪ የዓለም ክብረወሰን በአንድ ወር ውስጥ ያሻሻለበት አጋጣሚ የሚዘነጋ አይደለም። የውድድር ዓመቱን በበርካታ የዓለም ክብረወሰኖች ታጅቦ ያጠናቀቀው ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ የዓመቱን የስኬት ጉዞ ሞናኮ ላይ የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የዓለም ክብረወሰንን 12፡51 በሆነ ሰዓት በማሻሻል የጀመረው በዚሁ የካቲት ወር ነበር። ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ራስ አል ካይማህ 64፡31 በሆነ ሰዓት ያሻሻለችበትም አጋጣሚ በጉልህ የሚጠቀስ ነው። ቬንዙዌላዊቷ ስሉስ ዘላይ ዩሊማር ሮጃስ በማድሪድ በተካሄደው የቤት ውስጥ ውድድር ለአስራ ስድስት ዓመታት በታትያና ሌቢዴቫ ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረወሰን 15 ነጥብ 43 ሜትር በመዝለል ያሻሻለችበት አጋጣሚም ይታወሳል። መጋቢት የውድድር ዓመቱ ሦስተኛ ወር በሆነው መጋቢት ሕዝብ ባልተሳተፈበት የቶኪዮ ማራቶን ብርሃኑ ለገሰ ባለድል የሆነበት አጋጣሚ ሳይጠቀስ አይታለፍም። ቀነኒሳ በቀለም በለንደን ግማሽ ማራቶን አስደናቂ ብቃት አሳይቶያሸነፈበት ውድድርም አይዘነጋም። በዚህ ወር የኮቪድ-19 ስርጭት እየተስፋፋ መሄዱን ተከትሎ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮናም የመራዘም ዕድል ገጥሞታል። በተመሳሳይ ታላላቅ የሚባሉት የለንደንና የቦስተን ማራቶን ውድድሮችም በዚሁ የካቲት ወር እንደተራዘሙ ታውቋል። እንዲካሄድ በርካታ ጥረቶች ሲደረጉ ከቆዩ በኋላ የውድድር ዓመቱ ታላቅ የስፖርት መድረክ ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የተራዘመውም በዚሁ ወር ነበር። ሚያዝያ-ግንቦትበአሜሪካ ኦሪገን በሰኔ ወር ሊካሄድ የነበረው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ2022 እንዲካሄድ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በሚያዝያ ወር ነበር። የሚያዝያ ወር ምናልባትም በአትሌቲክሱ ዓለም ውድድሮችና ክብረወሰኖች የተመዘገቡበት ሳይሆን በርካታ ተጠባቂ ውድድሮች የተራዘሙበትና የተሰረዙበት መጥፎ ትዝታ ጥሎ ያለፈ ነው ማለት ይቻላል። ከቤት ውስጥ ቻምፒዮናው በተጨማሪ በፓሪስ ሊካሄድ የነበረው የአውሮፓ አትሌቲክስ ቻምፒዮና በዚህ ወቅት ለመሰረዝ በቅቷል። ጥቁር አሜሪካዊው ጂዮርጅ ፍሎይድ ሜይዌዘር በፖሊስ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን ተከትሎ የዓለም አትሌቲክስ ‹‹የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው›› በሚል በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን እንቅስቃሴ የተቀላቀለበት ወቅት ነው። የዓለም አትሌቲክስ አዲስ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ማረጋገጫ ሂደትን ይፋ ያደረገውም በዚህ ወቅት ነበር። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስፖርቱን እያዳከመው በመምጣቱም የዓለም አትሌቲክስ ስፖርቱን ለመደገፍ አዲስ ስትራቴጅክ ፕላን ይፋ አድርጓል። ተጠባቂው የኒውዮርክ ማራቶንም መሰረዙ የተሰማው በዚሁ ወቅት ነው። ሰኔ-ሐምሌ ውድድሮች ለወራት በዓለም ላይ አለመካሄዳቸውን ተከትሎ የስፖርቱ ዓለም በዘርፉ ፖለቲካ ተጠምዶ የቆየበት ጊዜ ነበር። በዚህም ከውድድርና ውጤቶች ይልቅ የተለያዩ ጉዳዮች የስፖርቱ ቤተሰብ መነጋገሪያ ሆነው ሰንብተዋል። በሰኔ ወር ትልቅ መነጋገሪያ ከሆኑ የአትሌቲክስ ጉዳዮች የቀድሞው የማራቶን ባለክብረወሰን ኬንያዊው ዊልሰን ኪፕሳንግ አበረታች ንጥረነገር ተጠቅሞ በመገኘቱ ለአራት ዓመታት ከስፖርቱ መታገዱ ትልቅ ትኩረት ስቦ ነበር። ተቋርጠው የቆዩ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በወሩ መጨረሻ እየተመለሱ መምጣታቸው ግን በወረርሽኙ ሳቢያ ድብርት ውስጥ ለነበረው የስፖርቱ ቤተሰብ ተስፋ ሆነው ነበር። በዚህም በዙሪክ የተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ተጠቃሽ ነው። ያም ሆኖ እንደ ቺካጎ ያሉ ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች በዚህ ወር ከመሰረዝ አልዳኑም። ወሩ ከመጠናቀቁ አስቀድሞም የዓለም አትሌቲክስ በመሮጫ ጫማዎች ላይ አዲስ ሕግ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ውድድሮች ከወራት በኋላ በሂደት መመለሳቸውን ተከትሎ ለረጅም ዓመታት ያልተደፈሩ የዓለም ክብረወሰኖች ጭምር ሐምሌ ወር ላይ ተሰብረዋል። በተለይም ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ሞናኮ ላይ በቀነኒሳ በቀለ ለአስራ አምስት ዓመታት ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረወሰን በ12፡35፡36 ማሻሻሉ ያልተጠበቀ የዓመቱ አበይት ክስተት ነበር። ነሐሴ ሐምሌ ወር ላይ የታየው ትልልቅ የዓለም ክብረወሰን የማሻሻል ሂደት በነሐሴም ተደግሟል። በተለይም በኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ኃይሌ ገብረስላሴና ድሬ ቱኔ ለረጅም ዓመታት ተይዘው የቆዩት የአንድ ሰዓት ውድድር የዓለም ክብረወሰኖች መሰበራቸው ያልተጠበቀ ነበር። ትውልደ ሶማሊያዊው የእንግሊዝ አትሌት ሞ ፋራህ የወንዶቹን ክብረወሰን ሲያሻሽል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን የሴቶቹን ክብረወሰን መጨበጥ ችላለች። ኬንያዊቷ አትሌት ፒርስ ጂፕቺርቺር በፓራጓይ ግማሽ ማራቶን የርቀቱን የሴቶች ብቻ የዓለም ክብረወሰን ያሻሻለችበት አጋጣሚም አይዘነጋም። የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዚዳንት ሴኔጋላዊው ላሚን ዲያክ በሙስና ቅሌት በፓሪስ ለዓመታት በቁም እስር ቆይተው ፍርድ የተበየነባቸውም በዚሁ ወር ነው። የውድድር ዓመቱን በክብረወሰኖች ታጅቦ ያሳለፈው ስዊድናዊው ምርኩዝ ዘላይ ሞንዶ ዱፕሌንቲስ ከቤት ውጪ ባሉ ውድድሮች በዩክሬናዊው ታሪካዊ አትሌት ሰርጌ ቡካ ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረወሰን በ6 ነጥብ 15 ሜትር ያሻሻለበት አጋጣሚም ትልቅ ነው። የዓለም የማራቶን ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው ኬንያዊት አትሌት ብሪጊድ ኮስጌ የለንደን ማራቶንን ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፋለች። በዚህ ውድድር ለወራት ሊፋለሙ ቀጠሮ ይዘው ትልቅ ትኩረት የተሰጣቸው ቀነኒሳ በቀለና ኢሉድ ኪፕቾጌ ፍልሚያ አንድ ቀን ሲቀረው ቀነኒሳ በጉዳት ከውድድር ውጪ መሆኑ አሳዛኝ ነበር። ያም ሆኖ የርቀቱ የክብረወሰን ባለቤትና ባለፉት ዓመታት ሽንፈት ያልገጠመው ኪፕቾጌ ባልተጠበቀው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሹራ ቂጣታ ከመሸነፉ ባሻገር ሰባተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አስገራሚ ነበር።ዩጋዳዊው ቺፕቴግ ቀነኒሳ ለአስራ ስድስት ዓመታት ይዞት የቆየውን የአስር ሺ ሜትር የዓለም ክብረወሰን ቫሌንሲያ ላይ ሲያሻሽል ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት የተያዘውን የአምስት ሺ ሜትር የዓለም ክብረወሰን ማሻሻሏ የውድድር ዓመቱ ግንባር ቀደም አበይት ክስተት ሆኖ አልፏል። ኬንያዊቷ ፒርስ ጂፕቺርቺር በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና የርቀቱን የሴቶች ብቻ የዓለም ክብረወሰን መስበሯም ወሩን አስደናቂ አድርጎት አልፏል። መስከረም -ታህሳስ የ2023 የአውሮፓ አትሌቲከስ ቻምፒዮናን ቱርክ ኢስታንቡል ላይ እንድታዘጋጅ ዕድል ባገኘችበት መስከረም ወር በአየርላንድ ደብሊን ሊካሄድ የነበረው የ2020 የአውሮፓ አገር አቋራጭ ቻምፒዮና ከመሰረዙ በቀር በአትሌቲክሱ ዓለም ብዙም አነጋጋሪ ጉዳዮች ሳይፈጠሩ አልፈዋል። ከዚያ በኋላ ባሉት ሦስት ወራት ግን የዓለማችን ፈጣኑ አትሌት ጃማይካዊው ዩዜን ቦልት እንዲሁም የረጅም ርቀት ንግስቷ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በእውቁ የእንግሊዝ የአትሌቲክስ መፅሔት የምን ጊዜም ምርጥ አትሌት ተብለው መሰየማቸው አብይ ጉዳይ ነበር። ቬንዙዌላዊቷ አትሌት ዩሊማር ሮጃስ እንዲሁም ስዊድናዊው ሞንዶ ዱፕሌንቲስ የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ተብለው ተሸልመዋል። ኬንያዊው ኪቢዎት ካንዲም በዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና ሲያሸንፍአዲስ ዘመን ታህሳስ 23/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38650
3937ddb483244f33d24e7d8e99f63c58
d7ff0b5545f060e154c21078eb959f90
ለራስ ሲባል ሌላውን …
መዝናኛ
ኧሯ! እንዴት ሆኖ እንዴት ሆኖ እኛንማ አይደፍርም! ብለን ነበር ደፈረን። በሩቅ ሆኖ የሰማነው ዜና ገስግሶ መጥቶ አጠገባችን ከደረሰ የወራት እድሜን አስቆጠረ። በሰው ሀገር ሲነገር፤ ሲወራ እኛ ዘንድ የማይደርስ መስሎን ተዘናግተንማል። እኛ ሀገር አይገባም ፤ ጥቁሮችን አይነካም በማለት እራሳችንን በማይሆን ተስፋ እያታለልን ቆይተናል። ቁርጡ ቀን ደርሶ በሀገራችን የቫይረሱን መገኘት እውነታ ሲነገር ሰምተን ላለማመን ያመነታነው ስንቶቻችን እንሆን? ታዲያ አስፈሪ ዝናውን አስቀድሞ በርካቶቻችንን ኮርኩሮ ሃሳብ በማሰንዘር ፤ ከሃሳባችን መደምደሚያ ሳንደርስ ከች ብሎ ጉድ ያደረገን እሱም አይደል ወይ ኮሮና። ስለ ቫይረሱ ያለን እውቀት እንደ ግንዛቤ የሚለያይ ነው። አንዳንዱ ህይወቱ ግድ ሰጥቶ ለራሱ ኖሮ ሌላውን ለማትረፍ የሚጥረው ነው። ሌላው ደግሞ ለራሱም ሆነ ለሌላው ግድ የሌለው ቢነገረው ቢዘከር ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶ እንዳላየ የሚሆን ነው። ራሱን በመኖርና ባለመኖር መካከል ከቶ በደመነፍስ እንደሚኖር ሰው ቫይረሱ ምንም እንደሚያመጣ የሚናገርም ዛሬ ድረስ አልጠፋም። ሰውን ለማዳን ራሱን ያልሰሰተውን ተመልክተን እሰየው በርታልን ጓድ እንዳላልን ሁላ ፤ በግዴለሽነት የሚኖረውን ደግሞ በትዝብት እያየን ከማለፍ ለመምከር የሞከርን እንኖራለን። የሚጠነቀቀውም ሆነ ግዴለሹ፤ የአንዱ ጤንነት የሌላው መኖር ዋስትና ነው ። የሰው ልጅ በምድር ላይ የሚኖረው ለራሱ ብቻ አይደለም፤ ለሌሎችም ነው። አንዱ ከሌለ የሌላው መኖር ትርጉም አልባ ነውና ። ህይወት ጣዕም የሚኖራት በመኖር ነው። መኖር ትርጉሟ ሙሉ የሚሆነው አንዳችን ለአንዳችን በሚኖረን አብሮነት ፤ መረዳዳትና መደጋገፍ ነው። ለዚህ ዋንኛው ደግም የኔ ጤንነት ሲጠበቅ የጎረቤት፤ የአካባቢዬ ፤ የሀገር፤ የሁሉም ጤና መሆን ግድ ይላል ። ታዲያ አለመታዘዛችን ከምን የመነጨ ይሆን? ለመኖር ራሳችን ከመጠበቅ ሌላው አማራጭ ይኖር ይሆን። ታላላቆቻችን፤ አባቶቻችን ማድመጥ፤ መደማመጣችንን እሴቶቻችንን ማን ነጠቀን? ለምን ረሳነው? በራሳችን ፈርደን በሌሎችም የመጨከን አባዜን ከየት አመጣነው? የሰውን ልጅ ሳይመርጥ ከምድረ ገጽ እያጠፋ ያለው ይህ ጨካኝ ቫይረስን እንዴት ልባችንን ሊያደነድን ቻለ። ሰው የሚችለውን ነውና የሚታዘዘው እራሳችንን እንመርምር ለመለወጥ መትጋት አለብን። የማንችለውን ትተን የምንችለውን መምረጥ ፤ ዛሬን መኖር ለነገ ተስፋ ነው። የእኛ ጥንቃቄ ለወገን መሆኑ ማመን አለብን። ነጭ፤ ጥቁር፤ ዘመድ፤ ባዕድ እያልን ራሳችንን ሳንከፋፈል ከስጋት ራስን ጠብቆ በማስመለጥ አብሮ ማምለጥ ይቻላልና ነው። ካለበለዚያ ግን “ከኑግ ጋር ያለህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” ከሆነ ጉዳይ የታሪክ ተወቃሽ መሆናችን አይቀርም። መቼም ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ማግስት ጀምሮ ብዙ ለውጦችን፣ አዳዲስ ነገሮችን ታዝበናል። ለመከላከል የሚረዱን እጅን በሳሙና ቶሎ ቶሎ በደንብ መታጠብን ፤ ፊት በእጅ አለመንካት፤ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በዋናነት ከህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክሮች ተግባራዊ ለማድረግ ተሞክሯል። ለራሱ ያለ ራሱ ተጠንቅቆ ሌላውን ለማዳን እየጣረ እየተጋ ታይቷል። ይገርማችኋል! ለዛሬ ትዝብቴ መነሻ የሆኑት ይህንን የሰሙ የማይመስሉ የሰፈሬ ወጣቶች ናቸው። በከተማችን የሚገኙ በርካታ ወጣቶች በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ከወገናቸው ጎን የቆሙበትን አይተናል፤ ሰምተናልም። የነገ የሀገሪቱ ተስፋዎች መሆናቸውንም አስመስክረዋል። የኔ ሰፈር ወጣቶች ግን ቫይረስ መኖሩን አልሰሙም!! በአንድ ላይ በጋራ በመሆን መጠጥ ይጠጣሉ ፤ ጫት ይቅማሉ፤ መንገድ ዳር ተዛዝለው በሚባል ሁኔታ ሆነው ያወጋሉ። የቫይረሱ የተከሰተ ሰሞን አልነበሩም፤ ጠፍተው ነበር ። እሰየው አልኩኝ፤ ራሳቸውን ለመከላከል ወስነው ቤት ለመቀመጥ የከተሙ መስሎኝ። አልሰሜን ግባ በለው አሉ። ለካ የቦታ ለውጥ በማድረግ ከሰው አይን ዞር ብለው ነበር። ታዲያ እኔም የግዴታዬን ለመወጣት ወደእነሱ አመራሁ። በእግዜር ስላምታ ተቀላቀልኳቸው። ስለቫይረሱ አስከፊነት የነሱ መጠንቀቅ ለሚወዷቸው ሁሉ ፤ ለወላጆቻቸው፤ ለሰፈራችን ሁሉም እንደሆነ አስረዳኋቸው። ለማዳመጥ ፈቃደኛ ባልሆነ ጆሮ ሰሙኝ ። መልስ አልሰጡኝም። አንደኛው እሺ አለኝ ቀልድ በተሞላበት ፌዝ ። በእውነት አመመኝ። ለምን አትተሳሰቡም እርስ በርሳችሁ እንኳን አትዋደዱም አልኳቸው። እሺ ሌላው ቢቀርስ ለምን አትታዘዙም አልኩት? አቀርቀረው ስልካቸውን መጎርጎር ተያያዙት ። ትቻቸው ስሄድ መታዘዝ ከመሰዋዕትነት ይበልጣል አልኩ ሰምተውኛል፤ ግን ዝምታን መርጠዋል። ለብቻዬ እንዳስብበት የቤት ስራ የሰጡኝ ወጣቶች ዞር ብዬ በማየት ጉዞዬን በሃሳብ ቀጠልኩ። “ለምን ይሆን የተከለከለ ነገር የሚያምረን?” አልኩኝ ለራሴ ። ወደ አፈጣጣራችን ተመለስኩ ለካ አዳምን ከገነት ያስባረረው አታድርግ የተባለው በማድረጉ ነው። እኛም ዛሬ ለመቅጽበት ለሚያልፍ ቀን ብለን አታደርጉ የተባልነውን በማድረግ በጎ ተግባር እንደፈጸመ ጀግና በየአደባባዩ እንታያለን። ማንንም መስማት አንፈልገም፤ እራሳችንን ብቻ ካልሆነ በስተቀር ፤ ራሳችንን በቅጡ አውቀን ብናዳምጥ ጥሩ ነው። በዓለም ያሉ ሀገራት እንደኛ አይነት ተው ተብለው የማይሰሙ ዜጎች በመያዛቸው ነው። ዛሬ ለመስማት የሚቀፍ ዜና እየሰማን የምንገኘው። እነሱ ቢጸጸቱም ወደ ኋላ ሊመልሱት የማይችሉት ነገር ሆኖባቸዋል። ለኛ ትምህርት መሆን አለባቸው። እኛ ላይ በቅድሚያ ያልተፈጸመብን መሆኑን እያመሰገን ከሰማነው፣ ካየነው ቀድሞ መገኘት የግድ ይለናል። ጊዜው ፈጣን ነው ፤ ዛሬ ላይ እንኳን ቆመን ነገን ለማየት በተሰጠን መልካም እድል መጠቀም አለብን። ያለመታዘዛችን ዋጋ እንዳያስከፍል መበርታት ያስፈልገናል። ለዚህም ቀኑ ዛሬ እንጂ ነገ አይደለም። የቤት ስራን ከወዲሁ በመፈጸም ለወገን አለኝታነታችን በመግለጽ እራስን ሆኖ መገኘት፤ ታዝዞ መታዘብ ማስተማር ፤ቀዳሚ ሆኖ ለሌሎች አርአያ በመሆን መስመሩን በመጥረግ ከመስመሩ ያፈነገጡትን መመለስ ይገባል። የዛሬ ሁላችንም አብሮነትና ትብብርን አንዱ ለአንዱ መኖር ግድ ይሆናል። ታላላቆቻችንን በማስቀደም እነሱን አድምጠን ከዚህ አስከፊ አደጋ ማምለጥ ይኖርብናል። አብረን ስንሆን፣ ስንተባበር፣ ስንደማምጥ፤ ስንረዳዳ ያምርብናል። ባህሩን አቋርጠን መሻገር እንችላለን። የሰው ልጆችን እየጠረገ ያለውን አስከፊ ወረርሽን ለመከላከል ወኔ አቅም ጉልበት ይኖረናልና ። መጪው ጊዜ መልካም ዜና የምንሰማበት ጊዜ ይሁንልን ። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 19/2012 ወርቅነሽ ደምሰው
https://www.press.et/Ama/?p=31198
faf8930d1795c69c309e5553a518ca52
949e7538c3640ef47ac37addfddefb84
የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ቀጥሏል
ስፖርት
 ቦጋለ አበበ ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ኮትዲቯር የ2023 አፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ የምታደርገው ዝግጅት በሚፈለገው ደረጃ ቀጥሏል።የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባለፈው ዓመት ከተከሰተ ወዲህ በርካታ የዓለማችን አገራት ስፖርታዊ ውድድሮችን ከማቆም ባለፈ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የሚያደርጉት ዝግጅት ተስተጓጉሏል።የ2023 አፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ዕድሉ የተሰጣት ኮትዲቯር ግን ወረርሽኙ ሳያግዳት ዝግጅቷን በተገቢው መንገድ እንደቀጠለች ኢንሳይድ ዘጌምስ አስነብቧል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የግምገማ ቡድን ከሳምንት በፊት ወደ ኮትዲቯር አቅንቶ አገሪቱ እያደረገች የሚገኘውን ዝግጅት የተመለከተ ሲሆን ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ለአፍሪካ ዋንጫው ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ሂደት ላይ እንደምትገኝ አሳውቋል።በዝግጅት ግምገማ ቡድኑ ውስጥ የካፍ ምክትል ዋና ፀሐፊ አንቶኒ ባፎይ፣ የውድድር ዳይሬክተሩ ሳምሶን አዳሙ፣ የብሔራዊ ቡድን ውድድሮች ማኔጀሩ ኢስማሊ ዋሊ እንዲሁም የአገልግሎትና የጉዞ ዋና ሃላፊው ራንዳ ሚትዋሊ ተካተው ወደ ስፍራው አቅንተዋል። የግምገማ ቡድኑ ከኮትዲቯር ከተመለሰ በኋላ ለኢንሳይድ ዘጌምስ አስተያየታቸውን የሰጡት ምክትል ዋና ፀሐፊው ባፎይ ምንም እንኳን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የዓለም ሕዝብ የጤና ቀውስ በመሆን ቢቀጥልም ያሳደረውን ጫና ተቋቁማ ኮትዲቯር በጥሩ ሁኔታ ዝግጅቷን እንደቀጠለች ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ‹‹ጉብኝቱ በደንብ የታሰበበት ነው፣ በጉዟችንና የውድድሩ አዘጋጆች እየሠሩ በሚገኙት ሥራ ረክተናል›› ያሉት ባፎይ አብዛኛው ለውድድሩ የሚገነቡት ስቴድየሞች በ2021 አጋማሽ እንደሚጠናቀቁ ጠቁመዋል።ይህም አዘጋጆቹ እስከ ውድድሩ ድረስ በቂ ጊዜ እንዳላቸው የሚያሳይ ሲሆን ለሙከራ የተለያዩ ጨዋታዎችን የማካሄድ ዕድልም እንደሚኖራቸው ባፎይ አብራርተዋል። የውድድሩ አዘጋጆች በዕቅዳቸው መሰረት እየተመሩ ትክክለኛ ሰዎችን በትክክለኛው ቦታ በማሰራት ተጨባጭ ነገር እንዳሳዩ የጠቆሙት ባፎይ‹‹ ሁሌም የምናገረው ነገር አንድ ነው፣ ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ ማስቀመጥ›› በማለት አዘጋጆቹን አድንቀዋል።ኮትዲቯር እ.ኤ.አ 2014 ላይ የ2021 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ ዕድሉን ያገኘች አገር መሆኗ ይታወሳል።ይሁን እንጂ የ2019 አፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ዕድሉ የተሰጣት ሌላኛዋ ምዕራብ አፍሪካዊት አገር ካሜሩን 2018 ላይ ውድድሩን ለማዘጋጀት የምትገነባቸው ስቴድየሞች በመጓተታቸውና በወቅቱ በአገሪቱ የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከደህንነነት አኳያ ስጋት ስለፈጠረ የአዘጋጅነት ዕድሉ ለግብጽ ተሰጥቷል።ካሜሩንም በምትኩ የ2021 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅና ኮትዲቯር የ2023 አፍሪካ ዋንጫን እንድታሰናዳ ሽግሽግ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ኮትዲቯር የአፍሪካን ትልቁ የስፖርት መድረክ በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጀት በቂ ጊዜና ዕድል ማግኘት ችላለች።ውድድሮቹንም ከ2023 ሰኔ ወር መጨረሻ አንስቶ በመዲናዋ አቢጃን፣ ቦኬ፣ ኮርሆጎ፣ ሳን ፔድሮ እና ያሙሱክሮ ከተሞች እንደ ምታከናውን ይጠበቃል።
https://www.press.et/Ama/?p=37905
07b0726cc39d3266376163a049b694ff
7e0a41e5a412b3fe6695933745a8541e
የባለሀብቶች ተሳትፎ ያልታከለበት የማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ
ስፖርት
ብርሃን ፈይሳወቅቱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ የሰፋበት መሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ። የማዘውተሪያዎች ዘመናዊነትና ጥራት የሰለጠኑ ከተሞች አንዱ መለያ እየሆነ ከመምጣቱም ባሻገር ኦሊምፒክ፣ ዓለም ዋንጫ እና የተለያዩ ስፖርት ቻምፒዮናዎችን ለማሰናዳት ዋነኛው መስፈርትም ነው። ሀገሮች ዜጎቻቸው በአእምሮና በአካል የተዋጣላቸውና ብቁ እንዲሆኑም በማዘውተሪያ ስፍራዎች አስፈላጊነትም እምነት ጥለዋል። በመሆኑም የከተሞቻቸውን ዲዛይን ሲያዘጋጁም ሆነ ግንባታውን ሲያከናውኑ ነዋሪዎቻቸው በቂ የጊዜ ማሳለፊያና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚከውኑባቸው ስፍራዎች ስለመኖራቸው ያረጋግጣሉ። የአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባም በዓለም ላይ ካሉና ታላላቅ ጉባኤዎችን ለማስተናገድ ከሚመረጡ እንዲሁም የአህጉር አቀፍ ተቋማት መቀመጫ እንድትሆን ተመራጭ ከሆኑት መካከል ትገኛለች። ይህም ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማስተናገድ ምቹ ሁኔታን ቢፈጥርላትም እስካሁን ግን ጉባኤዎችን ብቻ በማካሄድ ተወስናለች። ምክንያቱ ደግሞ ደረጃውን የጠበቀ የማዘውተሪያ ስፍራ የሌላት በመሆኑ ነው። አዲስ አበባ ከተማም ደረጃቸውን የጠበቁ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ብቻም ሳይሆኑ በየአካባቢው ለነዋሪዎቿ የሚበቃ የማዘውተሪያ ስፍራ ማግኘትም ፈተና ሆኖባታል። በመሆኑም የየከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረቱን በማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ላይ አድርጓል። ከሰሞኑ ጉባኤውን ያከናወነው የከተማዋ ስፖርት ምክር ቤትም አትኩሮቱን በተለይ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ አድርጎ ነበር። ምክር ቤቱ በጉባኤው ላይ ባቀረበው የ2012 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት የአዳዲስና ነባር የማዘውተሪያ ስፍራዎች ያሉበትን ደረጃ በዝርዝር አመልክቷል። በዚህም በበጀት ዓመቱ ብቻ 95 የሚሆኑ 3በ1 እንዲሁም የጥርጊያ ሜዳዎች እንዲገነቡና እንዲታደሱ ተደርጓል። እነዚህም በክፍለ ከተሞች እንዲሁም በ14 የጋራ መኖሪያ ስፍራዎች ላይ የተገነቡና የታደሱ ናቸው። ከፍተኛ ወጪ ተደርጎባቸው የሚገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በተመለከተም በዚህ ዓመት ተጠናቀው ወደ አገልግሎት የሚገቡና አዳዲስ የሚጀመሩ መሆኑም ተጠቁሟል። በዚህም የራስ ኃይሉ የመዋኛ ገንዳ እና የአበበ ቢቂላ ስታዲየም የግንባታ ምዕራፍ 99 ከመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በተያዘው በጀት ዓመት ወደ ሥራ ይገባሉ በሚል ይጠበቃል። በሁለቱም የማዘውተሪያ ስፍራዎች የውሃ እጥረት በመኖሩ ምክንያት የከርሰ ምድር ውሃ ለማውጣት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል። የአቃቂ ስታዲየም ግንባታም 70 ከመቶ ደርሷል፤ የአራት ኪሎ እና የጃንሜዳ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ በቴክኒክ ችግር ተቋርጦ ቆይቷል። በዚህ ዓመት ዕቅድም በዋናነት የማዘውተሪያ ስፍራ ቁጥርን ማሳደግና ሕጋዊነታቸውን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት መሰጠቱ በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል። በዚህም መሠረት የአቃቂና የአበበ ቢቂላ ስታዲየሞች እንዲሁም የራስ ኃይሉ የመዋኛ ገንዳዎች ግንባታን በዚህ ዓመት ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ አገልግሎት ለማስጀመር ታቅዷል። ግንባታው 67 ከመቶ ደርሶ የተቋረጠው የጃንሜዳ ጂምናዚየም እና ወደ ግንባታ ያልገባው የአራት ኪሎ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሕንፃም በዓመቱ ወደ ግንባታ የሚገቡ ይሆናል። በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች አንድ የአትሌቲክስ መንደር እና ሦስት ዞናል ስታዲየሞችን አስገንብቶ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግም የበጀት ዓመቱ ዕቅድ መሆኑም ተጠቁሟል። የቀረበውን ሪፖርትና ዕቅድ ተከትሎም የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ሃሳቦችን አንጸባርቀዋል። አጸንኦት የተሰጠው ሃሳብ ግን ከስፖርት ኢንቨስትመንት አንጻር በከተማዋ ባለሀብቱን የማሳተፍ ሂደት የሌለ መሆኑ ነው። የግል ባለሀብቱ በተለይ እጥረት ባለበት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ላይ የማሳተፍ አስፈላጊነት ተጠቁሟል። በዚህም ባለሀብቱን ከመጥቀም አልፎ ነዋሪውንም ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል።በከተማዋ የሚስተዋለው የግሉ ተሳትፎ ጂምናዚየሞች ላይ የተወሰነ ነው። በመሆኑም የኦሊምፒክ ስፖርት በሆኑ ሌሎች የቤት ውስጥ ስፖርቶች ላይም ተሳታፊ ለመሆን የሚፈልጉ ባለሀብቶችን በማበረታታት ስፖርቱን መደገፍ ይገባል። ለግል ባለሀብቶች ለስፖርቱ በዋናነት ግብዓት የሚሆኑ ቁሳቁስ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም በመድረኩ ተጠቁሟል። ከባለሀብቱ ባሻገር የስፖርት ክለቦችም በማዘውተሪያ ስፍራ ልማት ቢሰማሩ ለመንግሥት ላይ ብቻ የተተወውን ዘርፍ ሊደግፉ እንደሚችሉም ተነስቷል። ጉባኤተኞቹ የሚገነቡ ማዘውተሪያዎች ሁሉንም ስፖርቶች ያማከሉ መሆን እንደሚገባቸውም አመልክተዋል። በከተማዋ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአትሌቲክስ ቡድኖች እያሉ ለስፖርቱ የሚሆን ማዘውተሪያ ያለው በአዲስ አበባ ስታዲየም ብቻ መገኘቱ ሌላው አሳሳቢ ችግር መሆኑ ተጠቁሟል። ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን፤ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መንግሥታዊ በሆኑና ባልሆኑ አካላት በየአካባቢው ሊጠናከሩ እንደሚገባ ነው ያመለከቱት። እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ የታዳጊ ፕሮጀክት ስልጠናን ለማስፋፋትም ሆነ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚቻለው ማዘውተሪያዎችን ማስፋትና ማልማት ሲቻል ነው። የመዘውተሪያ ስፍራዎች ጉዳይ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ ቁልፍ ሥራ በመሆኑ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል። ከሚሽነሩ ትምህርት ቤቶች በአካልም በአእምሮ የበለጸገ ዜጋ ለማፍራት የሚያስችል ስፍራ እንደመሆናቸው 300 የሚሆኑ የሰውነት ማጎልመሻ መምህራን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ጠቅሰው፣ ይህንን ተከትሎ የመጣው ጥያቄ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የሚመለከት መሆኑን ይጠቅሳሉ። ስለዚህም ማዘውተሪያዎቹን በትምህርት ቤቶች ውስጥ ማልማት እንዲሁም ተማሪዎች ከሚጠቀሙበት ሰዓት በኋላ በሚኖረው ጊዜ የአካባቢው ወጣቶችና ታዳጊዎች የሚጠቀሙበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ ያብራራሉ። ከዚህ ባሻገር በከተማዋ የሚገኙ ነባር ማዘውተሪያዎችን በማደስና አዳዲሶችንም በጥራትና በፍጥነት ለማስገንባት ቢሮው በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል። ለዓመታት ጥያቄ ሲነሳባቸው የቆዩ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሞከረ ነው። ከባድ የሆነው ግን ከዚህ ቀደም የተጀመሩና በግንባታ ላይ የቆዩ ነባር ማዘውተሪያዎችን የጥራት ጉድለት እያለባቸው ወደ ሥራ ማስገባት ነው ሲሉ ያመለክታሉ። ለአብነት ያህል የአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሜዳውን ለእግር ኳስ መሙን ደግሞ ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች መስጠት ይቻላል ነገር ግን አሁን የጥራት ጉድለት አለ ይላሉ። በሌሎችም እንዲሁ የዲዛይን ችግር፣ የግንባታ ክፍተት፣ የክትትልና ቁጥጥር ድጋፍ የሚጎድላቸው እንዲሁም በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ያልተጠናቀቁም እንዳሉም ይናገራሉ። በእነዚህ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶበት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የስፖርት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አዳነች አቤቤም፤ በከተማዋ ታዳጊዎች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በማጣታቸው ባልተገባ ስፍራ እንደሚውሉ ጠቅሰዋል። ይህንን በመረዳትም በየአካባቢው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን ያመለክታሉ። ምክትል ከንቲባዋ ይህ ግን በቂ እንዳልሆነ ተናግረው፣ ከዚህም በላይ መስራት እንደሚገባም ይጠቁማሉ። የጠቅላላ ጉባኤው አባላት በተናጠልም ሆነ በጋራ ኃላፊነትን በመወጣት የተጀመሩትን ውጤታማ ማድረግና በሁሉም አካባቢ ማዳረስ እንደሚገባም አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38041
15bbe34e97927377b646d5f183751009
f9449b088f1a08d6bf35cd59620085c8
ቡናን ያለዛፍ ጥላ – በቀርጫንሼ ደበቃ
ሀገር አቀፍ ዜና
አስቴር ኤልያስስፍራው ሞቃታማ ቢሆንም ቅጥር ጊቢው ግን በቡና ችግኞችና በተለያዩ የፍራፍሬ ዛፎች በመሙላቱ ለአይን አርንጓዴነቱ ደምቆ፤ ለአፍንጫ ደግሞ መልካም መዓዛው ዘልቆ ስለሚመጣ ለጎብኚው ማየትም መማግም ግዴታ ሳይሆን በውዴታ የሚያጣጥመው ነገር ነው። ወዲህ ለቡና ተክሉ የተስተካከለ ውሃ ይደርሰው ዘንድ አዲስ የሆነና የውሃው ልክ በኮምፒውተር የሚታዘዝበት ቴክኖሎጂ ያለበት አንድ ክፍል ይታያል፤ ወዲያ ደግሞ ወደ 750 ሜትር ኪዩብ ውሃ የሚይዝ የውሃው ሪዘርቫይር ይስተዋላል ፤ ቦታው በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ልዩ ስሙ ደበቃ እርሻ ልማት ነው። የቀርጫንሼ እርሻዎች አስተባባሪ ስራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ዳባ እንደሚሉት፤ በቀርንጫንሼ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ቀደም ሲል ጥራቱን የጠበቀ ቡና ወደ ውጭ አገር በመላክ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ረገድ በግንባር ቀደምትነት እየሰራ ነው። ከንግዱ በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወደዚህ ጎን ለጎን በቡና እርሻ ልማት ተሰማርቷል። ድርጅቱ፣ በዓለማችን ላይ ዘመናዊ የሆነ በቡና ማምረት ቴክኖሎጂ ጫፍ ከደረሱ እንደብራዚል ካሉት አገራት ባልተናነሰ ዘመናዊ ቴክሎጂን ወይም ዲሪፕ እሪጌሽንን በመጠቀም ወደቡና ልማት እርሻ የገባ ነው። የቡና እርሻው የሚገኘው በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ልዩ ስሙ ደበቃ እርሻ ልማት ሲሆን፣ያረፈው ደግሞ በ72 ሄክታር መሬት ላይ ነው። በዚህም ላይ 110 ሺህ የቡና ችግኞችን በመተክል ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በአንድ ሄክታር ላይ ዘመናዊ የቡና ማፍያ የችግኝ ጣቢያ ወይም ዲጂታል ስፕሪንግ ክለር እሪጌሽ በመጠቀም 600 ሺህ ችግኞችን በማፍላት ለአካባቢው ህብረተሰብም ጭምር ለማደል ወደ ስራ መግባታቸውን ይናገራሉ። ቀደም ሲል በአገራችን ያለው አስተሳሰብ ቡናን ያለጥላ ዛፍ ማልማት አይቻልም የሚል ኋላ ቀር አስተሳሰብ ሲሆን፣ ይህን አስተሳሰብ በአዲስ አስተሳሰብ ለመቀየር እየሰራን ነው ሲሉ ያስረዳሉ። በድርጅቱ አግሮኖሚስት ሆነው የሚሰሩት የሆርቲካልቸር ባለሙያው አቶ ጉተማ ጎቤ በበኩላቸው፤ በድሪፕ እሪጌሽን (ጠብታ መስኖ) በአንድ አይነት መልኩ ውሃ ለቡናው እንዴት ሆኖ ይሰራጫል የሚለውን እንደሚከታተሉ ይናገራሉ። ውሃው ለችግኙ ሲደርሰው ለእያዳንዱ ቡና እኩል የሆነ የውሃ መጠን ነው በሜትር ኪዩብ የተለቀቀው ውሃ ወደ ቡናው ሲሄድ የሚደርሰው በሚሊ ሊትር ተቀይሮ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ይህ ቴክኖሎጂ የነበረውን ተልምዷዊ አሰራር ያለዛፍ ቡና መብቀል አይችልም የሚል አስተሳሰብን የሰበረ ነው። ቀደም ሲል ዛፍ ያስፈልግ የነበረው ብዙ ውሃ ስለማይጠጣ የዛፍ ጥላው ያለውን ውሃ እርጥበቱን ጠብቆ እንዲሄድ ስለሚያርገው ነው ይላሉ። አጠቃላይ የቀርጫንሼ ካምፓኒ ስራ አስፈጻሚ አቶ እስራኤል ደገፋ፣ ካምፓኒው የሚሰራው አጠቃላይ የአገራችን ኢኮኖሚ በሚፈልግበት በግብርናና ማኑፋክቸሪንግ ላይ መሆኑን ይገልጻሉ። በግብርናው ላይ ወደ 26 ሺህ የስራ እድሎችን በመፍጠር እንዲሁም ከ56 ሺህ አርሶ አደሮች ጋር የገበያ ትስስር በመፍጠር የሚሰራ ድርጅት እንደሆነም ያመለክታሉ። አቶ እስራኤል እንደሚሉት፤ ላለፉት አራት አምስት ዓመታት ትልቁን የአገሪቱን የቡና ኤክስፖርት ከሁለት አኃዝ በላይ ድርሻ በመውሰድ የሚልከው ይኸው የቀርጫንሼ ኩባንያ ነው። በየትኛውም የኢትዮጵያ ቡና አብቃይ ክልሎችም ሆነ ወረዳዎች ይገኛል። አጠቃላይ ወደ 57 ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም ደግሞ ወደ አምስት እርሻዎችን በቡናው ሴክተር ላይ ማኔጅ ያደርጋል። ጉብኝት የተደረገበት የደበቃ እርሻ ጣቢያ፣ ኩባንያው ካሉት እርሻዎች ሁሉ አነስተኛው ነው ያሉት አቶ እስራኤል፣ ነገር ግን እንዴት አድርገን ግብርናን ከተለምዶ አሰራራችን መቀየር አለብን ሲሉ በማሰብ በቡናው ፋርም ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱ አገሮችን ተሞክሮ ከእነእስራኤልና ብራዚል መውሰድ ላይ መሆናቸውን ያመለክታሉ። የወሰዱትም ቴክኖሎጂ ድሪፕ ኢሪጌሽን ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት በዓለም ላይ የመጨረሻው የሚባለው በግብርናው ዘርፍ የተገኘና ውጤታማ የሆነ የመስኖ ሲስተም ነው ይላሉ። ከዚህ አንጻር በደበቃ ያለው የተሻለው ቴክኖሎጂ  እንደሚያሰኘው ያስረዳሉ። አርሶአደሩ በተለምዶ በሄክታር ቡና የሚያገኘው ከስድስት ኩንታል የዘለለ አይደለም የሚሉት አቶ እስራኤል፣ እኛ በዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቅመን ግን በሄክታር እስከ 35 ኩንታል ማሳካት ችለናል ብለዋል። ይህ ሙከራ ደግሞ የመጀመሪያው ሲሆን፣ የሚጠበቀው በሄክታር እስከ 65 ኩንታል ድረስ ነው ብለን እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል። ያንን ማሳካት ከቻልን የአገራችንን የውጭ ምንዛሬ ማሳደግ እንዲሁም የአርሶ አደሮችን ገቢ ከፍ ማድረግ ይቻላል ብለዋል። የእኛ ትልቁ እቅዳችን የራሳችን ማሳ ላይ ትልቁን ምርት ማምረት ላይ ብቻ አይደለም። በአቅራቢያው የሚገኙ የአርሶ አደሮችንም ማሳዎች ወደእኛ ቴክኖሎጂ በመቀየር እነርሱም ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መሰረት ማደላደልና በፋይናንስም ለመደጎም ሲሆን፣ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ዲዛይን አድርገን ጨርሰናል ይላሉ። በዕለቱ ቀርጫንሼ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ኤክስፖርት ስታንዳርድ የቡና ላቦራቶሪን የመረቁት የግብርና ግብአትና ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ እና የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ሲሆኑ፣ ሚኒስትር ዴኤታዋ በዕለቱ እንደተናገሩት፤ የድርጅቱን የቡና ማዘጋጃ መጋዘንና የቡና መቅመሻ ላቦራቶሪ እንዲሁም እርሻዎቹን ጎብኝተናል። ከዚህ ደርጅት ባለቤት ጋር አርሶ አደሮችም አብረው ነው ያሉት። ለምርት መሻሻል ደግሞ ዋናው አርሶ አደሮቻችን ከባህላዊ የቡና አመራረት ዘዴ በመጠኑም ቢሆን በመቀየር የቡናን ምርታማነት ሊቀየሩ የሚችሉ አሰራሮችን ተግባራ እያደረጉ ነው ያሉት። ቡሌ ሆራ ላይ እንደማየውና ሞዴል አርሶአደሮችም እንዳረጋገጡልን በምርትም፣በአቅርቦትም ሆነ በገበያ ትስሰርም የተሻለ እድል ያለበት አካባቢ መሆኑን ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ እዚህ የሚሰሩ ባለሀብቶች የአርሶአደሩንም ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ስለመሆናቸው ማስተዋል መቻላቸውን ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚናገሩት፤ እንደግብርና ሚኒስቴር የበለጠ ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድግ የሚችል ስራ ይሰራሉ። ቡና ወደውጭ በመላክ ረገድ በተለይ ቀርጫንሼ ላለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት የቀዳሚነት ድርሻውን እየተወጣ ነው። በመጋዘን ውስጥ የተመለከትነውም ደረጃውን የማያስለቅቅ ለአገርም ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርግ የሚችል ክምችት የያዘ ቡና መኖሩን ነው፤ ለዚህም በጣም ደስተኞች ነን። አርሶአደሮቹ ጥሩ የቴክኖሎጂ ስራ ካላቸው ከግል ሴአልሚዎች ጋር በመቀናጀት ምርታቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ማዕቀፍ መዘርጋት ነው። የተሻለ ገበያ እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያ የተዘረጉ አሰራሮች አሉ፤ ትልቁ ነገር አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት ቀጥታ ወደ ገበያ ለማድረስ የሚያስችለው አቅም ገበያ የማፈላለግ ችሎታ የማዳበር ስራ መሰራት ይኖርበታል። እንዲህ ከሆነ በለፋው ልክ ጥቅም እንዲያገኝ ያችለዋልና በዚህ ደረጃ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል ብለዋል። ዶክተር አዱኛ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ባለስልጣኑ ቡና ከማብቀል ጀምሮ ውጭ አገር እስከ መላክ ድረስ ያለውን ሂደት በማገዝ እንዲሁም ገበያ በማፈላለግ ረገድ በመስራት ላይ ይገኛል። አርሶ አደሮቻችን እስከ ውጭ አገር በራሳቸው እንዲልኩ ይሰራል። 500 ያህል አርሶ አደሮች ወደውጭ አገር መላክ የሚያስችላቸውን ሰነድ አውጥተዋል። በዚህም እየሄዱበት ነው። ቀርጫንሼ የሰራው ስራ በአርአያነት መጠቀስ የሚያስችል ስራ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በቦታው ተገኝተን ያስተዋልነው ነገር ቢኖር ይህን ነው ብለዋል። ይህም ወደሌሎቹም መስፋፋት ያለበት ቴክኖሎጂ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ስራው ደግሞ እንደ መንግስት ድጋፍ እናደርግለታለን ብለዋል።አዲስ ዘመን ጥር 10/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=39687
d257408849ea5210d2920a7680699b15
1dd6701861055b016f1ec03cf6a04fb5
ኮቭድ-19- ዳግም የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሥጋት
ስፖርት
ቦጋለ አበበ ጃፓን ከሰባት ዓመታት በላይ ብዙ የለፋችበት የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ካለፈው ዓመት ጀምሮ የዓለም ሕዝብ የጤና ጠንቅ በሆነው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአስራ ስድስት ወራት ተራዝሞ ዘንድሮ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል። ኦሊምፒኩ በተራዘመው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚካሄድም እርግጠኛ ሆነው የውድድሩ አዘጋጆች መናገር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የተለያዩ አገራትም በአዘጋጆቹ ተማምነው የስፖርት ልዑካን ቡድኖቻቸውን እያዘጋጁ ይገኛሉ።የዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጨምሮ የውድድሩ አዘጋጆች አሁንም ድረስ ውድድሩ እንደሚካሄድ እርግጠኛ የሆኑት ወረርሽኙ ኦሊምፒኩ እስኪቃረብ አንድ መፍትሄ ያገኛል በሚልና በሙከራ ላይ የሚገኙትን የተለያዩ ክትባቶች ተማምነው ነው። ያም ሆኖ ሰሞኑን እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች ወረርሽኙ እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሚገኝ ያመላክታሉ። ጃፓን ውድድሩን በምታካሂድበት ወቅት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ከአገሪቱ ዜጎች በበለጠ ብዙ ቁጥር ያላቸው እንግዶች ስጋት ሊሆኑ እንደሚችሉ የገመተች ቢሆንም፣ በተቃራኒው ራሷ ጃፓን የእንግዶቿ ስጋት ልትሆን እንደምትችል በቅርብ የወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።ወረርሽኙ ለዓለም ስጋት ከሆነ ወዲህ ኦሊምፒኩን በዋናነት የምታስተናግደው ከተማ ቶኪዮ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ በቫይረሱ የተጠቁ አስር ሺህ ሰዎች የተገኙባት ሆናለች። ይህም በቀጣዩ ክረምት በሚካሄዱት የኦሊምፒክና የፓራሊምፒክ ውድድሮች ላይ ዳግም ተመሳሳይ ስጋት እንዲፈጠር ያደረገ ሲሆን በብዙዎች ዘንድ ጥያቄ እየተነሳበት ይገኛል።ኦሊምፒኩ ሊካሄድ ስድስት ወራት በቀሩበት በዚህ ወቅት ባለፈው ሐሙስ ብቻ ቶኪዮ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ስምንት መቶ ሃያ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ከተማ ሆናለች። ይህም ወረርሽኙ በሀገሪቱ ከተከሰተበት ወቅት ወዲህ የታየ ከፍተኛው ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል። የቶኪዮ ከተማ አስተዳዳሪ ዩሪኮ ኮኢኬ ከጃፓን ታይምስ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስም የቶኪዮ የጤና ተቋማት ከአቅማቸው በላይ ሕመምተኞችን እያስተናገዱ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ‹‹ሆስፒታሎች ተዘግተዋል፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት በቅርቡ መሰረታዊ አገልግሎት መስጠት ሊያቆሙም ይችላሉ›› በማለትም በከተማዋ ያለውን ሁኔታ ገልፀዋል።ቶኪዮ ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ እስካለፈው ሳምንት መጨረሻ ብቻ ሃምሳ ሁለት ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት ከተማ ስትሆን አምስት መቶ ያህል ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል። በአጠቃላይ በጃፓን ደግሞ እስካፈው ሰኞ ድረስ በአማካይ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተጠቁ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፤ እስካሁን ከሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸው ታውቋል።የቶኪዮ ተላላፊ በሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳይሬክተር ኖሮዪ ኦማጋሪ በበኩላቸው ‹‹የቫይረሱ ሥርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ከዚህ የበለጠ ብዙ ሰዎች በቫይረሱ እንዳይጠቁ ጠንካራ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው›› በማለት ለአገሪቱ ጋዜጣ ተናግረዋል።ጥቂት ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ አዲስ ዓመትና የገና በዓል አከባበር ወቅት በርካታ የአውሮፓ አገራት የወረርሽኙን ሥርጭት ለመቀነስ ጠንካራ መመሪያዎችን ከማውጣት ባሻገር በአገር አቀፍ ደረጃ እንቅስቃሴዎችን እስከ መግታት ደርሰዋል። ይህን በመመልከትም ጃፓን በአንፃራዊነት የተሻለ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የሚናገሩ አሉ። ከቀናት በፊት የእንግሊዝ መንግሥት የጤና ቢሮ ሃላፊ ክሪስ ዊቲይ በአይነቱ ልዩ የሆነና በፍጥነት የመዛመት ባህሪ ያለው የኮቪድ-19 ቫይረስ በአገሪቱ እንደተገኘ ለዓለም ጤና ድርጅት ጭምር በማሳወቅ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቡ ይታወቃል። በአገሪቱ የቫይረሱ ሥርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በአዲስ ዓመትና በገና በዓል ዋዜማዎች ወቅት በሚደረጉ መዝናኛዎች ላይ ጠንካራ እግድ አስቀምጠዋል። መዲናዋ ለንደንን ጨምሮ ቫይረሱ በስፋት በተሰራጨባቸው የደቡብ እንግሊዝ ከተሞችም ጠንካራ የተባሉ ገደቦች ተጥለዋል።አስቀድሞ በቫይረሱ ከፉኛ የተጠቃችው ጣሊያንን ጨምሮ ኔዘርላንድስና ጀርመን እስከ አዲሱ ዓመት ድረስ ማንም ከቤቱ እንዳይወጣ እግድ አስቀምጠዋል። አውስትራሊያም ከገና በዓል በኋላ ተመሳሳይ እርምጃ እንደምትወስድ መረጃዎች ጠቁመዋል። በቅርቡ በቤልጂየም ብራሰልስ የተካሄደውን የአውሮፓ ሕብረት ስብሰባ ከተካፈሉ በኋላ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑዔል ማክሮንና የስሎቫኪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢጎር ማቶቪች እንዲሁም ሌሎች የአገር መሪዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ይታወቃል። ባለፈው ዓመት በቫይረሱ ሥርጭት ስጋት የገባቸው የኦሊምፒክ አዘጋጆች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቁን የስፖርት መድረክ ለማራዘም መገደዳቸው ይታወቃል። በዚህም የተነሳ አዘጋጅ ኮሚቴው ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ከወር በፊት አሳውቋል። ወረርሽኙ ዳግም በከፍተኛ ሁኔታ ማገርሸቱን ተከትሎም የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላይ ጥያቄ ተነስቷል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽን ጨምሮ የተለያዩ ሃላፊዎች ግን አሁንም ውድድሩን በጥንቃቄ ለማካሄድ ሃሳብ አለወጡም።ቶኪዮ በኦሊምፒኩ ወቅት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በምትወስደው እርምጃ ከዘጠኝ መቶ ስልሳ ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ እንደምታደርግ የተዘገበ ሲሆን፣ የውድድሩ አዘጋጆች ቫይረሱን ለመዋጋት ከአገሪቱ መንግሥት ጋር በየጊዜው ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። በኦሊምፒኩ የሚሳተፉ አትሌቶችና የስፖርት ልዑካን ቡድኖች የፊት ጭምብል ማጥለቅና ርቀትን መጠበቅ እንደሚገባቸው አዘጋጆቹ በቅርቡ ጠቁመዋል፤ ከውድድሩ በኋላ በጃፓን የሚቆዩበት ጊዜ አጭር እንደሚሆንም አሳውቀዋል።እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ቻይናና ሩሲያን የመሳሰሉ የተለያዩ አገራት ለወረርሽኙ መፍትሄ ይሆን ዘንድ የተለያዩ ክትባቶችን በማምረት የተሳካ ሙከራ እንዳደረጉ መናገር ከጀመሩ ሰንብተዋል። ክትባቱ በምን አይነት ፍጥነት ለዓለም ሕዝብ ተዳርሶ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከስጋት ነፃ በሆነ መልኩ ይካሄዳል የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። በኦሊምፒኩ ለመሳተፍ ወደ ቶኪዮ የሚያቀኑ ከቫይረሱ ነፃ የሆኑ አትሌቶች ክትባቱን ለማግኘት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል አይሰጣቸውም የሚሉ ጥያቄዎችም ከወዲሁ እየተነሱ ይገኛሉ።የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ባለፈው ወር በጃፓን ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የተሳካ የኮቪድ-19 ክትባት ተገኘ መባሉን ተከትሎ እንኳን ስፖርተኞች የስፖርቱ አፍቃሪዎች ስቴድየም ገብተው የኦሊምፒክ ውድድሩን ካለ ስጋት እንደሚመለከቱ እርግጠኛ ሆነው ሲናገሩ ተደምጠዋል።የጃፓን መንግሥትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አትሌቶች የወረርሽኙን ክትባት እንዲያገኙ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። ከዚህ ባሻገር በኦሊምፒኩ የሚሳተፉ አትሌቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ወረርሽኙን ለመከላከል የተለያዩ ጥብቅ መመሪያዎችን ማክበር እንደሚገባቸው ቀደም ሲል አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።ባለፈው ዓመት ወረርሽኙ በኦሊምፒኩ አዘጋጅ ጃፓንም ይሁን በሌሎች አገራት እንዲህ እንዳሁኑ ባልጠነከረበት ወቅት ለመራዘም የተገደደውን ይህን ውድድር፣ ዘንድሮ ወረርሽኙ ‹‹ክትባት ተገኝቶለታል›› እየተባለም መልኩን እየቀያየረ የብዙዎች ስጋት በሆነበት ጊዜ እንዲካሄድ መወሰን ለብዙዎች አልተዋጠም። ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴውም ይሁን የጃፓን መንግሥት ውድድሩን ለማካሄድ እርግጠኛ ሆነው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙትም ኦሊምፒኩ ካልተካሄደ የሚደርስባቸውን ትልቅ ኪሳራ በማስላት ሊሆን እንደሚችል ትችቶች ይሰነዘራሉ።ኦሊምፒኩ ባለፈው ዓመት መካሄድ ሲገባው ወደ ዘንድሮ በመራዘሙ ብቻ ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንዳደረሰ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህን ኪሳራ ለመሸፈን የቶኪዮ ከተማ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ እንዳደረገ ተዘግቧል፤ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴው አንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ አድርጓል። ቀሪውን ሰባት መቶ ሚሊየን ዶላር ደግሞ የጃፓን መንግሥት እንደሚሸፍን ታውቋል። ኦሊምፒኩ ከመራዘሙ አስቀድሞ አስራ ሦስት ቢሊየን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ተገልጿል።በዘንድሮው ዓመት ሳይካሄድ ከተራዘመ ወይም ከተሰረዘ ቀድሞ ከተያዘለት በጀት እስከ አራት እጥፍ ኪሳራ ሊያደርስ እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38136
7ce6c012eb7aa2a7b8eff02d931ac55e
c97201fbb4638ada9cefa378d21a4d0d
ምክር ቤቱ አቅጣጫና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል
ስፖርት
ብርሃን ፈይሳ አዲስ አበባ፡- ብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤት ነገ የመጀመሪያ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያከናውን ተገለጸ። በጉባኤው ላይም አቅጣጫዎችን እንደሚሰጥና ውሳኔዎችንም እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት ህዳር 4 ቀን 2012 ዓ.ም መስራች ጉባኤውን ማካሄዱ ይታወሳል፤ ይሁን እንጂ ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን በተያዘለት ወቅት ማካሄድ አልተቻለም። በመሆኑም ነገ የመጀመሪያ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያከናውናል። በጉባኤው ላይም የጉባኤው አባላት የሆኑት፤ የክልልና ከተማ አስተዳደር ርዕሳነ መስተዳድሮች ከንቲባዎች፣ ከዘጠኝ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ ሚኒስትሮች፣ የስፖርት ኮሚሽነሮች፣ የሃገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት አመራሮች፣ የስፖርት ተቋማት እንዲሁም ለስፖርት ጉልህ ሚና ያላቸው የክብር እንግዶች ይገኛሉ። የጉባኤው አጀንዳዎችም የመስራች ጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፣ በወቅቱ የተሰጡ አቅጣጫዎችን አፈጻጸም መገምገም፣ በቀጣይ በትኩረት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የ10 ዓመቱ መሪ እቅድና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ እንዲሁም ልዩ ልዩ መመሪያዎችን አቅርቦ ማጸደቅ የሚሉት መሆናቸው ተጠቁሟል። አጀንዳዎቹን ተከትሎ አቅጣጫ እንደሚሰጥና ውሳኔዎችም እንደሚያስተላለፉ ይጠበቃል።የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ጉባኤው ትኩረት የሚሰጥበት አጀንዳም ምክር ቤቱ በመስራች ጉባኤ ወቅት ያስቀመጣቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች አፈጻጸምን በዝርዝር ተመልክቶ መገምገምን የተመለከተ መሆኑን አስታውቀዋል። የሃገሪቷ ስፖርት መሰረታዊ ችግሮችና መፍትሄ የሚል ጥናት በማካሄድ በተዘጋጀው የሪፎርም ሰነድ ምክር ቤቱ ተወያይቶ በዝርዝር እንዲከናወኑ አቅጣጫ የሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ግምገማ የሚያካሂድም መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ከአቅጣጫዎቹ መካከል አንዱ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ሰነዱ እንዲዳብር ነበር፤ ይህም እስከ ታችኛው እርከን በመውረድ የማዳበር ስራው ተከናውኗል። ሰነዱ ሲዘጋጅ የተቀመጡት ምክረ ሃሳቦች በእቅድ እንዲካተቱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እና የዓመቱ እቅድ ላይ እንዲካተት ተደርጓል። አሰራሮችን ከመፈተሽና አዳዲስ የአሰራር ማኑዋሎችን ከመፍጠር ረገድም የስፖርት ፖሊሲውን የማሻሻል ስራ ተጀምሯል፣ ሃገሪቷ የሌላት የስፖርት ህግም እየተረቀቀ ነው፣ ሃገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት የሚመዘኑበት ስታንዳርድ የማዘጋጀት፣ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ስታንዳርድና የስፖርት ፈንድ ሰነድ ማዘጋጀት እንዲሁም የስፖርት መመሪያ በማሻሻል ረገድ ያሉትን ፈትሾ በማስተካከልና የሌሉትን አዳዲስ በማዘጋጀት የተሳካ ስራ ማከናወን ተችሏል። ተጠናቀው ወደ ስራ የገቡ መኖራቸውንና ሌሎች ደግሞ እርከኑን ጠብቆ በሌሎች አካላት መጽደቅ ያለባቸውም በሂደት ላይ ይገኛሉ።የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን፣ የስልጠና ማዕከላትና የስፖርት ቁሳቁስን በሚመለከትም ትልልቅ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜና በጥራት እንዲጠናቀቁ እየተሰራም መሆኑም በመግለጫው ተጠቁሟል። ከጥርጊያ ሜዳ ጀምሮ በየአካባቢው ያሉ ማዘውተሪያዎችም የባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲኖራቸውና እጥረት ባለባቸውም ተጨማሪ እንዲያገኙም እየተደረገ ነው። ያሉት የስልጠና ማዕከላትም በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ የማድረግ ስራ እየተሰራ ከሚሽነሩ ጠቅሰው፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከማስፋፋት አኳያ ያለው ተነሳሽነትም መልካም የሚባል መሆኑን ኮሚሽነሩ ይጠቁማሉ። የህዝብ ተሳትፎን በሚመለከትም ኮቪድን እንደ ምክንያት በመጠቀም በህብረተሰቡ ዘንድ መነሳሳትን በመፍጠር ረገድ የተሻለ ጅማሮ ታይቷል ብለዋል። በጉባኤው ላይ በህብረተሰቡ የስፖርት ተሳትፎ ፍትሃዊነትና ተደራሽነት ላይም ውይይት ይደረጋል ተብሏል። በስፖርት አደረጃጀት ላይ ሕዝባዊ አካሉ በምን መልክ ሊደራጅ ይገባዋል የሚለውም ሌላው ውይይት የሚደረግበት መሆኑ ተጠቁሟል። በመግለጫው ላይ እንደተመለከተው፤ በ2011 ዓም አሳሳቢ የነበረው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደልም በወረርሽኙ መከሰት ውድድሮች እስከተቋረጡ ድረስ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን ተችሏል። ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ ከተከሰተ ወዲህም በስፖርቱ ላይ ያስከተላቸው ጉዳቶችን እና ቫይረሱ እያለ እንዴት ወደ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መገባቱን ተከትሎ ክትትል ለሚያደርገው ኮሚቴ አቅጣጫ የሚሰጥም ይሆናል። በቀጣይ የሚካሄዱ ሃገር እና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በሚመለከትና ለሚቀጥለው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በምን መልክ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል በሚለው ላይም ምክር ቤቱ ይመክራል።
https://www.press.et/Ama/?p=38365
8e4190b129f67d7639b1a6de7b8363b7
f90f3d408a2558dc0ea944a6e2cdb6f2
የከተማ አቀፍ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ተመልሷል
ስፖርት
ቦጋለ አበበ ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ አዲሱ ለሚ ኮራ ክፍለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ በይፋ ተጀምሯል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ‹‹ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ፤ ለመከላከያ ሰራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ›› በሚል መሪ ቃል በየካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አደባባይ ከትናንት በስቲያ የተካሄደ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም ተሳታፊ ሆነዋል ። በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ ‹‹በስፖርት የተገነባ ኃይል የትኛውንም ጠላት መመከት ይችላል፤ በመሆኑም በየትኛውም አካባቢ በተገኘው ቦታ ሁሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ እራሳችንን ከበሽታ ልንከላከል ይገባል›› ብለዋል። ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ‹‹መከላከያችን ባደረገው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድል የተቀዳጀው በስፖርት የተገነባ ስለሆነ ነው፣ መከላከያችንን እያሰብን ሁሌም ስፖርትን ባህላችን ልናደርግ ይገባል›› በማለትም አቶ ጃንጥራር  ተናግረዋል::የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር በበኩላቸው፣ የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በፍታሐዊነት ተደራሽ እና ባህል እስኪሆን ድረስ ከሚመለከታቸው አካላት በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል::በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለረጅም ወራት ተቋርጦ ከትናንት በስቲያ የተጀመረው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር በየሳምንቱ በአስራ አንዱም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች በወጣው መርሃ ግብር መሠረት ለአንድ ወር የሚቀጥል ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት በየካ ክፍለ ከተማ እንደሚካሄድ ታውቋል።በአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን፣ የለሚ ኩራ፣ የቦሌና የየካ ክፍለ ከተሞች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸው የየካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን የከተማዋን ሁለንተናዊ የስፖርት ልማት፣ የስፖርት ንቅናቄ ፣ የስፖርት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ስፖርት ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለፍቅር፣ ለጤንነት፣ ለመቻቻል፣ ለአብሮነት፣ ለልማትና ለትብብር ያለው ፋይድ ታላቅ መሆኑን ስፖርት በተግባር እያሳየ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38442
fd72453b45e97e412963a264d04ba723
ece7d77687d255e3d1e9c80aca73b820
አዳዲስ የአትሌቲክስ ማዘውተሪያዎች ግንባታ ይከናወናል
ስፖርት
ብርሃን ፈይሳአዲስ አበባ፡- ለአትሌቲክስ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ የሚሆኑ ቦታዎች ምልከታ ተደረገ። ማዘውተሪያዎቹ በአዲስ አበባ አቅራቢያ በሚገኙ አራት ከተሞች ላይ የሚገኙ መሆኑም ታውቋል። በቅርቡ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የተመረቀውን የአትሌቲክስ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ተከትሎ ሌሎች ግንባታዎችም እንደሚከናወኑ ተጠቁሞ ነበር። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፤ ከለገዳዲ ለገጣፎ ባሻገር በተለያዩ ከተሞች በአጭር ጊዜ ቦታ በማዘጋጀት ተጨማሪ ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሚገነቡ ጠቁመው ነበር። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በድረገጹ እንዳስታወቀው፤ለማዘውተሪያ ስፍራዎቹ ግንባታ በሚሆኑ ስፍራዎች ላይ ሰሞኑን ምልከታ ተከናውኗል። በመልክታው መሰረት ማዘውተሪያዎቹ የሚገነቡት በአዲስ አበባ አቅራቢያ በሚገኙት አራት ከተሞችም ቡራዩ ፣ ሰበታ ፣ ዱከም እና ሱልልታ ይሆናል። ለግንባታውም በቡራዩ 50 ሄክታር፣ በሰበታ 8 ነጥብ 5 ሄክታር፣ በዱከም 23 ሄክታር እንዲሁም በሱልልታ 20 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል። በምልከታው ላይም የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ ሚኒስትር ዲኤታው ሃብታሙ ሲሳይ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፣ ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጂሎ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገዛኸኝ አበራ እንዲሁም የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን አመራሮች ተገኝተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38042
90060745ec4e5be8a95c97dce4e79d9d
7d83b6b49f33f187012a3db986a60c93
የዓለም አትሌቲክስ በዶፒንግ ጉዳይ ጥርስ አውጥቷል
ስፖርት
ቦጋለ አበበ ኢትዮጵያ አበረታች ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም በስፖርቱ ዓለም በተለይም በአትሌቲክስ ትልቅ ስጋት ካንዣበበባቸው የዓለማችን አምስት አገራት አንዷ እንደሆነች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ሲያሳስቡ ቆይተዋል። በተቃራኒው ኢትዮጵያ ይህን ስጋት ለመቀነስ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በብሔራዊ ደረጃ የፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ፅሕፈት ቤት አቋቁማ አበረታች ለውጥ ማምጣቷንም የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ኤጀንሲ መስክሮላታል። ይሁን እንጂ ስጋት አለባቸው ከተባሉት አምስት አገራት ተርታ ለመውጣት ብዙ ስራ እንደሚጠብቃት ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ጽሕፈት ቤት አትሌቶች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የችግሩ ሰለባ እንዳይሆኑ የተለያዩ ግንዛቤዎችን ከማስጨበጥ ባሻገር የችግሩ ሰለባ ሆነው የተገኙ በርካታ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔዎችን ሲያስተላልፍ ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት አጋማሽ እንኳን አትሌት ወንድወሰን ከተማ ማሞና አትሌት እዮብ ኃብተስላሴ ጎሳ የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) የሕግ ጥሰቶችን በመፈፀም ተጠርጥረው ላለፉት ጊዜያት ጊዜያዊ እገዳ ላይ ሆነው ጉዳያቸውን ሲያጣራ መቆየቱን ገልጿል። በዚህም መሰረት በተካሄደው ተጨማሪ ምርመራ አትሌት እዮብ ኃብተስላሴ ጎሳ እ.ኤ.አ የካቲት 02/2020 ዓ.ም ታይላንድ በተካሄደ ውድድር ላይ (Cathinone) የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ ተረጋግጧል። በዚህም አትሌቱ እ.ኤ.አ ከሚያዝያ 03/2020 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ዓመታት በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ ቅጣት ተጥሎበታል። በውድድሩ የተገኘው ውጤትና ውጤቱን ተከትሎ የሚሰጥ የእውቅና ሽልማትም እንዲሰረዝ ተወስኗል። በተመሳሳይ መልኩ አትሌት ወንድወሰን ከተማ ማሞ ቀደም ሲል (Cathinone) የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ በመረጋገጡ እ.ኤ.አ እስከ የካቲት 01/2024 ድረስ በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ የተጣለበት መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ አትሌቱ የተሳሳቱ የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ የህግ ጥሰት የማጣራት ሂደቱን በተለያየ መልኩ በማስተጓጎልና በድጋሚ ለማጭበርበር በመሞከር ተደራራቢ የህግ ጥሰት በመፈፀም ተጠርጥሮ ጉዳዩ ሲጣራ ቆይቷል። በመሆኑም አትሌት ወንድወሰን ያቀረባቸው ሰነዶች የሐሰት መሆናቸው በመረጋገጡና በፀረ- ዶፒንግ ህጉ አንቀፅ 2ነጥብ5 ላይ የተደነገገውን የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን የማስተጓጎልና አቅጣጫ የማሳት የህግ ጥሰት መፈፀሙ በመረጋገጡ ቀደም ሲል ከተጣለበት የአራት ዓመት የእገዳ ቅጣት በተጨማሪ የመጀመሪያው ቅጣት ከሚያበቃበት የካቲት 01/2024 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ዓመታት እስከ የካቲት 01/2032 ዓ.ም በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር  ላይ እንዳይሳተፍ የእገዳ ቅጣት ተላልፎበታል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት በቀጣይም የምርመራና ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የዓለም አትሌቲክስም ከዶፒንግ ጋር በተያያዘ በስፖርቱ ትልቅ ክብርና ዝና ያተረፉ አትሌቶች ላይ ሳይቀር ጥርስ እንዳወጣ የሚጠቁም አቋም በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ አድርጓል። ኢትዮጵያን ጨምሮ የዓለምን አትሌቲክስ በበላይነት የሚመራው ተቋምና ሌሎች አገራት ባለፉት ዓመታት ከዶፒንግ ጋር በተያያዘ በስፖርቱ ትልቅ ክብርና ዝና ካላቸው አትሌቶች ይልቅ እምብዛም በማይታወቁና በአንፃራዊነት በትንንሽ ውድድሮች በሚካፈሉ አትሌቶች ላይ ትኩረት እንዳደረጉ ወቀሳ ሲቀርብባቸው መቆየቱ ይታወቃል።ማህበሩ በተለይም የዓለም አትሌቲክስ የስፖርቱ ስም እንዳይጠለሽና የተለያዩ አጋሮቹን ላለማጣት ሲል በስፖርቱ ትልቅ ስምና ዝና ላላቸው አትሌቶች ሽፋን እንደሚሰጥ ምክንያታዊ ሙግቶችን የሚያቀርቡ በርካታ ናቸው። ለዚህም በስፖርቱ ትልቅ ስም ያላቸው የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮን የሆኑ በርካታ የዓለማችን አትሌቶች እምብዛም የችግሩ ሰለባ ሆነው ቅጣት ሲተላለፍባቸው እንደማይስተዋል ያስቀምጣሉ። የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮ ሰሞኑን በዶፒንግ ጉዳይ አትሌቶች ትልቅ ስምና ዝናቸው ከጥፋተኝነት እንደማያስጥላቸው አስገንዝበዋል። ለዚህም ባለፉት ዓመታት አሜሪካዊው የመቶ ሜትር የዓለም ሻምፒዮን ክርስቲያን ኮሊማንን ጨምሮ በስፖርቱ ትልቅ ዝናና ስኬት ያላቸው አትሌቶች እንደተቀጡ አስታውሰዋል። እንደ ኮ ገለፃ፣ በአበረታች ንጥረ ነገሮች ላይ የሚደረገው ምርመራ እየተሻሻለ በሄደ ቁጥር ዶፒንግ ተጠቅመው ለሚወዳደሩ አትሌቶች ነገሮች ከባድ እየሆኑ ቢሄዱም የችግሩ ሰለባ ላለመሆን እንዲጠነቀቁ ያደርጋቸዋል። በተለይም በመጪው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ቁጥጥሩ ከምን ጊዜውም በላይ የጠበቀ እንደሚሆን ጠቁመዋል። የኮሊማ ቅጣት አትሌቶች የቱንም ያህል በስፖርቱ ስምና ዝና ቢገነቡ አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅመው ከተገኙ ከቅጣት እንደማያመልጡ ማሳያና የዓለም አትሌቲክስ የሚፈራው ነገር እንደሌለ ማረጋገጫ መሆኑንም የእንግሊዝ የቀድሞ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር የሁለት ኦሊምፒኮች አሸናፊው ኮ ለአገራቸው መገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል። የዓለም አትሌቲክስ እንደ አበረታች ንጥረ ነገሮች ያሉ ጉዳዮችን የሚያጣራ ገለልተኛ ቡድን አቋቁሞ ባለፉት ዓመታት ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ እንደሚገኝ የገለፁት ኮ፣ ዓለም አቀፍ ተቋሙ በራስ መተማመኑን በመገንባት ካለአንዳች ፍርሃት አበረታች ንጥረ ነገር የተጠቀሙ የትኞቹንም የዓለማችን አትሌቶች ለማጋለጥ ከልቡ እየሰራ መሆኑን አክለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=38366
e9c85591b5f0c51554d9fd285af332c7
553a04fff8da84e1fd944eaeedfeedc2
በቻን ውድድር ስቴዲየሞች በከፊል ለተመልካች ክፍት ይሆናሉ
ስፖርት
ቦጋለ አበበ በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚሳተፉ ተጫዋቾች የሚሳተፉበት የአፍሪካ ሁለተኛው ትልቁ የእግር ኳስ ውድድር(ቻን) ላይ ደጋፊዎች ስቴድየም ገብተው ጨዋታዎችን እንደሚመለከቱ ተገለፀ። ከመጪው ጥር አጋማሽ ጀምሮ በካሜሩን በሚካሄደው ውድድር የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ በማድረግ ተመልካቾች ስቴድየም እንዲገቡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) ማሳወቁን ኢንሳይድ ዘ ጌምስ ዘግቧል። ባለፈው ሚያዝያ ወር ሊካሄድ የነበረው የቻን ውድድር በኮቪድ- 19 ስጋት ወደ ዘንድሮው ዓመት መራዘሙ ይታወሳል። የውድድሩን ዝግጅት ለመገምገም ወደ ካሜሩን አማዶ አሂጆ ስቴድየም ያቀኑት የካፍ የግምገማ ቡድን አባላት ለአገሪቱ ስፖርት ሚኒስትር ናርሲስ ሞውሌ ኮምቢ እንደገለፁት ከወር በኋላ በሚካሄደው የቻን ውድድር ወረርሽኙ የሚፈልገውን ጥንቃቄ በማድረግ ተመልካች ስቴድየም እንዲገባ ካፍ ውሳኔ ላይ ደርሷል። እንደ ስፖርት ሚኒስትሩ ገለፃ፣ በውድድሮች ወቅት ጨዋታዎችን የሚያስተናግዱ ስቴድየሞች ከመያዝ አቅማቸው ሃያ አምስት በመቶውን ብቻ ተመልካች እንዲያስተናግዱ ይደረጋል። ካሜሩን በውድድሩ ወቅት በፊፋና በጤና ባለስልጣናት የተቀመጡ መስፈርቶችን ተግባራዊ በማድረግ ተመልካች ስቴድየም እንዲገባ ባደረገችው ጥረት ከካፍ ፍቃድ ማግኘቱንም ጠቁመዋል። ውድድሩ በሚካሄድባቸው የተለያዩ ስቴድየሞች በምድብ ጨዋታዎች ወቅት ስቴድየሞች ተመልካች ከመያዝ አቅማቸው ሃያ አምስት በመቶውን ብቻ እንደሚጠቀሙ የገለፁት ሚኒስትሩ፣ ከምድብ ጨዋታዎች በኋላ በጥሎ ማለፍ ውድድሮች ስቴድየሞች ተመልካች የመያዝ አቅማቸው ወደ ሃምሳ በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል አስረድተዋል። በዱዋላ ከተማ የሚገኘው ስቴድየም በተጎበኘበት የካሜሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ኢኦን ንጉቴ ‹‹ውድድሩ ካለፈው ዓመት ተራዝሞ ዘንድሮ በሚካሄድበት ወቅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጉዳይ በአፍሪካ እንደሚሻሻል እርግጠኛ ነኝ›› በማለት መናገራቸው ይታወቃል። የቅርብ ቀናት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በካሜሩን ከሃያ ስድስት ሺ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። የካሜሩን ከተሞች መዲናዋ ያውንዴን ጨምሮ ዱአላና ሊምቤ ውድድሩን የሚያስተናግዱ ይሆናል። በዋናው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በሌሎች አገራት ትልልቅ ሊጎች በሚጫወቱ ተጫዋቾች ተሸፍነው የመታየት እድል ያላገኙ በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች እንዲሳተፉ ለማድረግ ካፍ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተግባራዊ ያደረገው የቻን ውድድር በኮቪድ-19 ምክንያት ካለፈው ዓመት ወደ ዘንድሮው ዓመት ከተሸጋገሩት አንዱ ነው። ካሜሩን በመጪው ሰኔ አጋማሽ ዋናውን የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን የምታስተናግድ አገር መሆኗም ይታወቃል። የ2019 አፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት 2014 ላይ እድሉ የተሰጣት ምዕራብ አፍሪካዊት አገር ካሜሩን 2018 ላይ ውድድሩን ለማዘጋጀት የምትገነባቸው ስቴድየሞች በመጓተታቸውና በወቅቱ በአገሪቱ የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከደህንነነት አኳያ ስጋት ስለፈጠረ የአዘጋጅነት እድሉ ለግብፅ ተሰጥቷል። ካሜሩንም በምትኩ የ2021 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅና ኮትዲቯር የ2023 አፍሪካ ዋንጫን እንድታሰናዳ ሽግሽግ መደረጉ ይታወቃል።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38441
f8e86eaab16ed29170a5480a3e889a25
b8f3a3b3e8c4b13e79ea4fbcbe95f8f5
ከተራ – የጎንደር ልዩ ውበት
ሀገር አቀፍ ዜና
ክፍለዮሐንስ አንበርብርጎንደር አሸብርቃለች:: ተፈጥሮም ሰውም አጅቧታል:: ከተራ ለጎንደር፤ ጎንደርም ለከተራ ውበት ናቸው:: ቆነጃጅት ሽሩባቸውን በባህላዊ አሠራር አስውበው፣ በሐበሻ አለባበስ አምረውና ደምቀው ወደ ማደሪያው የሚሸኙትን ታቦታት ይከተላሉ:: ወጣት ወንዶች በሀገርኛ አለባበስ አምረውና ደምቀው፣ ሽመል ይዘው በሆታ እያደመቁ፤ በእግራቸው መሬት ረግጠው  እየነቀነቁ አቧራው ወደ ላይ ቡን! ቡን! ብሎ በሰዎች መሐል ወደ ላይ ቦለል ሲል እንደ ሰኔ ደመና እየተቆራረጥ ወደ ላይ ሲወጣ አንዳች የተለየ ውበት አለው::ጎንደር ከተማን በዙሪያ የከበበው ተራራ ታቦታቱን ያጅብ ይመስል ደረቱን ነፍቶ የቁልቁሊት እየተመለከተ የተለየ ውበት አላብሷል ለአካባቢው::የጎንደር ታቦታት በሰዎች ብቻ ሳይሆን ተራራ የሚታዘዝላቸው፤ ተራራ የሚከተላቸው ይመስላል::አንዳንዶቹ ደግሞ ፈረስ ላይ ሆነው ጎፈሬ አበጥረው እና በጃኖ ተሞሽረው እየተገማሸሩ፤ ጎንደር እሽሩሩ በሚለው ሙዚቃ ታጅበው ከፈረሶቹ ወገብ ላይ ሆነው እዩኝ እዩን በሚል ሁኔታ በታቦታቱ በቅርብ እርቀት ይጓዛሉ::የሰንበት ተማሪዎች በመለከት፣ በገና እና ከበሮ በታጀበ ህብረ ዝማሬ እያሰሙ ከታቦታቱ ኋላ ኋላ እየተከተሉ ወደ ማደሪያው ሥፍራ ሲሸኙ የጎንደር ከተራ በዓልን ውበት በእጁጉ ያጎላዋል::ካሜራቸውን ደቅነው ወዲህ ወዲያ ዝርው ዝርው የሚሉት ቱሪስቶች የታሪክ አካል ለመሆን የሚያደርጉት ሽሚያ በራሱ ዕይታን ይስባል::ቀሳውስቱ ግራ ቀኝ እያዘመሙ፣ ጽናጽል እየጸነጸሉ ታቦታቱን አጅበው ወደማደሪያው ሥፍራ ሲሸኙ ውበቱን በቃላት ለመግለፅ መሞከር አዳጋች ያደርገዋል::በአራቱም ነፋሳት የሚታጠነው ዕጣን አካባቢውን እንደ ናርዶስ ሽታ እያወደው ጥሩ መዓዛ አላብሶታል::ከተራ በጎንደር አንዳች የማይገለፅ መግነጢሳዊ ኃይል አለው::የአማራ ልዩ ኃይል በየአቅጣጫው ሆነው ከበጎ ፈቃድ ወጣቶች ጋር በመቀናጀት የአካባቢውንና የከተማዋ ሠላምና ፀጥታ ለማስከበር የሚያደርጉት መውተርተር ምንኛ የሀገር ፍቅርና የበዓል ክብር እንዳላቸው ያሳብቃል::እንደ ንሥር አሞራ ዓይናቸውን በርቀት በቅርበት እየላኩ አካባቢውን ይቃኛሉ::የከተራ ውበት በጎንደር፤ የጎንደር ከተማም ውበትም በከተራ ይገለፁ ዘንድ ተዋህደው የተሠሩ ይመስል አንዳቸው ካለአንዳኛው ምሉዕ አይመስሉም::ከተማዋ በዓል በዓል በሚሸቱ ሙዚቃ እና ዝማሬ ተንጣለች::በየህንፃዎቹ አናት ላይ የተሰቀሉት ሰንደቅ ዓላማዎች የከተማውን ድባብ በጠላት ጦር ላይ ድል በተቀዳጀ ማግስት የተገኘ ልዩ ድል አስመስለውታል::ጎንደር በሽለላ እና ቀረርቶም ለምን ይቅርብኝ ያለች ይመስላል::በርካታ ወጣቶች በአፄ ቴዎድሮስ አደባባይ እያቅራሩና እየፎከሩ በሐውልቱ ዙሪያ እየተሽከረከሩ ኢትዮጵያዊ ወኔ የሚቀሰቅሱና ለበዓሉ ድምቀት የሆኑ አያሌ ትዕይንተ ህዝብ ያሳያሉ::ሁሉንም እንቅስቃሴ በአንክሮ ለተመለከተው አንዳች ንዝረታዊ ኃይል አለው::በቃ ጎንደር ድምቅ! ብላለች::ወጣት ይድነቃቸው ታደሰ ከተራ ለእኔ ልዩ ስሜት ይሰጠኛል:: በዓሉ ነብስና ሥጋዬ ተዋህደው ደስታዬ እጥፍ ድርብ የሚሆንበት ነው::በተለይም ደግሞ በጎ አድራጎትን በመከወን ስለማሳልፍ ነብሴ በሐሴት ትረሰርሳለች ይላል::እርሱ ከከተራ እና ጥምቀት መቅረት አይሆንለትም::ጎንደር አፍ አውጥታ ትጠይቀው፤ በአሽሙር ወጋ ታደርገው ይመስል በዓሉን ሌላ ሥፍራ ማሳለፍ አይፈልግም::ወጣት ተረፈ መልካሙ ባለፈው ዓመት የምዕምናን መቀመጫ ደረጃ ተደርምሶ ጉዳት በማድረሱ በከተራውም ሆነ በጥምቀት በዓል ላይ ጥቁር ጥላ አጥልቶ ያላፈ በመሆኑ፤ መሰል ችግሮች እንዳይደገሙ ከከተማው ወጣቶች ጋር በመቀናጀት በጎ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል::በበዓሉ ወቅት ባህረ ጥምቀት ሄዶ መጠመቅና ከተራ በዓል ላይ መታደም ለእርሱ የፍሰሐ ጥግ ነው:: ከተራና ጥምቀትን በጎንደር ማሳለፍና መታደም የሁልጊዜ ዕቅዱ ነው::ከተራ ብሎም ጥምቀት በዓል የነፍስ የሥጋም በዓል እንደሆነ የሚናገሩት የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀህሩያን አባ ዮሴፍ ደስታ ናቸው:: በዚህ በዓል በርካታ የአገር ውስጥና የአገር ውጭ ታዳሚዎች ወደ ጎንደር የሚመጡ ሲሆን ይህም ለጎንደርና ለአካባቢው ነዋሪዎች ፀጋ ይዞ የሚመጣ እንደሆነ ያብራራሉ::ማህበራዊ እሴቶችን በማጠናከር፣ መንፈሳዊ ሕይወትን በማደስና ነብስን በማረስረስ የሚሰጠው ስሜት ልዩ ስለመሆኑም ያስገነዝባሉ::ሊቀህሩያን አባ ዮሴፍ ደስታ እንደሚሉት፤ የጎንደር ከተራ እና ጥምቀት በዓል ሁሌም አዲስ ሰርክ ልዩ እየሆኑ ዘመናትን አስቆጥረዋል::በቀጣይም የበዓሉ ድምቀት በዚሁ ድባብ እንደሚቀጥል ተስፋ አላቸው::ለዚህም የወጣቶች፣ የምዕምናን ትግስትና ፅናት፣ የሀገር ታሪክ ወዳድነት፣ ለቤተክርስቲያንና የባህል እሴቶች ያላቸው ክብር ህያው ምስክር ስለመሆናቸውም ይገልፃሉ::በዚህ ዓመት የሚከበረው የከተራ እና ጥምቀት በዓል ከመቼውም በላይ ደስታየው የተለየ ስለመሆኑም ይናገራሉ::አገሪቱ ሠላም ሰፍኖባት የኤርትራ ወንድምና እህቶች በበዓሉ ታዳሚ የሚሆኑበት መሆኑም ታላቅ ፍስሐ እንደሆነም ይጠቁማሉ::የከተራ በዓል ሠላማዊና ፍሰሐ እንዲሆንም የመንግሥት አካላት ከአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከወጣቶችና ከሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመናበብ ስለሚሠሩ ሁሉም ነገሩ ሸጋ ነው ይላሉ:: ከተራ እና ጥምቀት በጎንደር ልዩ ስሜትና እንደሚሰጥ በመጠቆም፤ የተቻላቸው ኢትዮጵውያን እንዲታደሙት ይመክራሉ::አዲስ ዘመን ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=39749
52ca0e09b18a40176a11892e27e0734d
b53972c39b090222a1e3a9ce90d1b72e
” የሱዳን ሃይል በተጠናከረ ሁኔታ ወደ ውስጥ እየተስፋፋ መሄዱ የግድቡን ግንባታ ለማስተጓጎል ነው‘ – ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
ዘላለም ግዛው  አዲስ አበባ:- የሱዳን ሃይል በተጠናከረ ሁኔታ ወደ ውስጥ እየተስፋፋ መሄዱ የግድቡን ግንባታ ለማስተጓጎል የተደረገ መሆኑን ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ አስታወቁ። ትዕግስቱ ከበቂ በላይ በመሆኑ የሃይል አጸፋ እንደሚያስፈልግ አመለከቱ። የቀድሞ መከላከያ ሰራዊት ባልደረባ ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፤ የሱዳን አሁናዊ የመሬት ወረራ ዋናው ግብ በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ የሚገኘውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስቆም፣ ወደ ሃይል ማመንጨት ሂደቱ ከመሸጋገሩ አስቀድሞ ለማስተጓጎል የተወጠነ ሴራ መሆኑን ነው። ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ ተርባይኖቹንም   ተክሎ ሃይል እንዲያመነጩ ስራ ለማስጀመር እያደረገች ያለው ሂደት በምንም ሁኔታ የማይቆም ነው ያሉት ብርጋዴል ጀነራሉ፤ ከሱዳን ድርጊት ጀርባ የግብጽ እና የሱዳን ተባባሪ የሆኑ አንዳንድ የአረብ አገራት እጅ ሊኖርበት እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል። በመንግስት በኩል እየታየ ያለው ትእግስት ከበቂ በላይ መሆኑን አመልክተዋል። ሱዳን በኃይለስላሴ አገዛዝና በደርግ ሥርዓትም የመስፋፋት አዝማሚያ ታሳይ እንደነበር ያስታወሱት ብርጋዴል ጀነራል፣ በአሁኑ ወቅት ድንበር ጥሶ የገባውን ሃይሏን በሰላም የሚወጣ ከሆነ መልካም፣ ካልሆነ ግን የሃይል አማራጭን መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል። ለሰላም አማራጩ ተገዢ ካልሆኑ ወታደራዊ አቅምን በመጠቀም ማባረር እንደሚገባም ጠቁመዋል። እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ መሬቷ ተወርሮ አሁንም ችግሩን በዲፕሎማሲ ለመፍታት እያደረገች ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው። ለጎረቤት አገራት ያላትን ፍቅር፣ የሰላም ፍላጎቷንና ለቀጠናው ሰላም መጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል። ትዕግስቱ፣ ስምምነት ላይ ለመድረስ መሞከሩና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ድርጊቱን ለማስቆም እና ለማስመለስ መንቀሳቀሱ ተገቢ ነው። መንግስት በከፍተኛ ጥንቃቄ ጉዳዩን ለመያዝ ያለውን ፍላጎት የሚያመለክት እንደሆነም አመልክተዋል። የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን እና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጉብኝት እና ውይይት ማድረጋቸውን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶክተር) እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ወደ ሱዳን ተጉዘው ተመሳሳይ ጥረት እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ፣ ወረራ ማካሄድ ተገቢ አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ትዕግስት ማድረጉ ከዚህ በላይ አያስኬድም ትዕግስትም ወሰን አለው ያሉት ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ፣ፍቅርና የሰላም ፍላጎት ያልገዛውን ሃይል እንደሚገዛ አስታውቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39619
25866e765997537f98dff658591bfaf7
114152130feb8e8599c38dc8d8e383ca
የአትሌቶችን ጥያቄ የሚመልስ ማዘውተሪያ
ስፖርት
 ብርሃን ፈይሳበኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኦሮሚያ ክልል ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነባው የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ የአሸዋ ትራክ ተመረቀ። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎችም ተመሳሳይ ማዘውተሪያዎች እንደሚገነቡ ታውቋል።በኦሮሚያ ክልል ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነባው የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ ስፍራ ትናንት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል። ግንባታው ለረጅም ርቀትና አጭር ርቀት አትሌቲክስ ስፖርት መለማመጃ የሚውለው የአሸዋ ትራክ እንዲሁም የአትሌቶች ልብስ መቀየሪያ፣ የማረፊያና የንጽህና መጠበቂያ ስፍራን ያጠቃልላል። ከለገዳዲ ለገጣፎ ባሻገር በክልሉ ባሉ የተለያዩ ከተሞችም ተመሳሳይ ማዘውተሪያዎች የሚገነቡ መሆኑም ተጠቁሟል። በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ከአትሌቶች ወቅታዊና አንገብጋቢ ጥያቄዎች አንጻር ለአትሌቲክስ ስፖርት ምቹ ከሆኑት አካባቢዎች መካከል አንዱን በመምረጥ ለምረቃ የበቃውን የለገጣፎ ለገዳዲ የአሸዋ ትራክ ለማስገንባት እንደተቻለ ገልጻለች። ፌዴሬሽኑ ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት የዲዛይን ስራ በማሰራትና ለግንባታውም ፌዴሬሽኑ 18 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ግንባታው ተካሂዶ ለምረቃ በቅቷል። ትራኩ 1ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ ወደ 2ኪሎ ሜትር እንዲያድግ ለቀረበው ጥያቄም የክልሉ መንግስት ፈቃደኝነቱን በመስጠቱ ምክትል ፕሬዚዳንቷ ምስጋና አቅርባለች። ግንባታው ፌዴሬሽኑን ብቻም ሳይሆን ከተማ አስተዳደሩን፣ ክልሉንና ኢትዮጵያንም ጭምር በማበልጸግና የስፖርት ቱሪዝምን በመሳብ ከሃገር ገጽታ በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታም እንደሚኖረው ጠቅሳ፣ ከፌዴራል መንግስት ጀምሮ ሁሉም አካላት የማዘውተሪያ ስፍራ ችግርን ለመቅረፍ በትኩረትና በርብርብ የሃገር በጎ ገጽታ መገንባት እንደሚኖርባቸው አስገንዝባለች። ማዘውተሪያውን የመረቁት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ፌዴሬሽኑ ማዘውተሪያውን በመገንባት በጎ ተግባር መስራቱን አስታውቀዋል። በፌዴሬሽኑ የቀረበውን 1ነጥብ6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ትራክ ወደ 2 ኪሎ ሜትር ለማሳደግ የክልሉ መንግስት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። ከለገዳዲ ለገጣፎ ባሻገር በሱሉልታ፣ በቡራዩ፣ ሰበታ እና ገላን ቦታዎችን በአጭር ጊዜ በማዘጋጀት፤ የማዘውተሪያ ስፍራዎች በፌዴሬሽኑ እና በክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚገነቡም ጠቁመዋል። ይህም አትሌቶችን ከመኪና አደጋ እና ከመሳሰሉት ጉዳቶች ተጠብቀው ልምምዳቸውን እንዲያደርጉ እና ለሃገራቸው ክብር እንዲቆሙ እንደሚያስችሉ አስታውቀዋል።ለእዚህም የክልሉ መንግስት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ፤ በርካታ አትሌቶች ከከተማው የአትሌቲክስ ክለብ በመውጣት በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጤት ማስመዝገባቸውን እንዲሁም ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ስድስት አትሌቶችንና ሁለት አሰልጣኞች ለብሄራዊ ቡድን መመረጣቸውን ጠቅሰዋል። ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለውም በመንግስት በተደረገለት ድጋፍ መሆኑን ተናግረው፤ ፖሊሲው ስፖርት በህዝባዊ አካል እየተመራ በመንግስት እንዲታገዝ ቢሆንም፤ በርካታ የማዘውተሪያ ስፍራዎች የተገነቡት በመንግስት ነው ብለዋል። በዚህም አትሌቶች የመለማመጃ ስፍራ አንድ ለእናቱ ከነበረው የአዲስ አበባ ስታዲየም ወደ አጎራባች ከተሞች በመውሰድ አትሌቶች አማራጭ መሮጫዎችን እንዲያገኙ ተደርጓል ያሉት ከንቲባዋ፤ እንደ ከተማም በስፖርቱ ምክንያት ወደ ማዘውተሪያው የሚጓዙ የሃገር ውስጥና የውጪ ሃገራት አትሌቶች ሰላማቸው ተጠብቆ ማዘውተሪያው ለታለመለት ዓላማ እንዲውል እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። መዋዕለ ነዋያቸውን በስፖርት ላይ ለማፍሰስ ለሚፈልጉ ባለሃብቶችም ከምንጊዜውም በላይ ድጋፍ እንደሚሰጥም ገልጸዋል። በእለቱ ከተካሄደው ምረቃ ስነስርአት ጎን ለጎን ፌዴሬሽኑ ለሚያስገነባው ባለ 12 ወለል ህንጻም የመሰረተ ድንጋይ በእለቱ ተቀምጧል። ይህም ጂምናዚየም፣ የህክምና እና የማገገሚያ ማዕከል፣ ከአትሌቲክስ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን የሚሰጥ እንዲሁም ገቢ የሚያስገኝ እንደሚሆንም ታውቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37292
e14c4527370b170a67dc2a94b63df019
3407396a6333f1b62dae159ed6064b4b
ከቅጣት ያመለጠው ታሪካዊ ጥፋት
ስፖርት
ቦጋለ አበበእግር ኳስን በመሳሰሉ ተወዳጅና ንክኪ በሚበዛባቸው ስፖርቶች ተጫዋቾች በእንቅስቃሴ ውስጥ እያሉ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች ላይ ጥፋት(ፋውል) ይሰራሉ። እነዚህ ጥፋቶች ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉና ያስከተሉበት አጋጣሚም በርካታ እንደነበር መመልከት ይቻላል። በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ወቅት ስፖርተኞች መሰል ጥፋት ሲሰሩ ውድድሩን በሚመሩ ዳኞች ከቢጫ የማስጠንቀቂያ ካርድ አስከ በርካታ ጨዋታዎች መታገድ ሊያደርሱ የሚችሉ ቅጣቶች ይከተሏቸዋል። ዳኞች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ከትንሽ እስከ ትልቅ ጥፋቶች በዝምታ ሲያልፉ የሚታይበት አጋጣሚም ጥቂት አይደለም። በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችንም እኤአ በ1982 የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ወቅት የተከሰተውን ከባድና ታሪካዊ ጥፋት ከቅጣት የዳነበትን አጋጣሚ እንደሚከተለው እንዳስሳለን።ታሪካዊው ፈረንሳዊ ተጫዋች ሚሼል ፕላቲኒ ያሻገራት ኳስ ፓትሪክ ባቲስቶን ከጀርመኑ ግብ ጠባቂ ጋር አገናኘችው። በአጠገቡ ተከላካዮች የሉም፣ ከጨዋታ ውጭ አይደለም። የተከላካይን መስመር ሰንጥቆ ያለፈ ለጎል የተመቻቸ ያለቀለት ዕድል ነበር። ሄራርድ ሹማኸር ኳሷን ማዳን አለበት። አለበለዚያ ጀርመን ለዓለም ዋንጫው ፍፃሜ ላትደርስ ትችላለች። ከባቲስቶ ጋር ፊት ለፊት ተጋፈጠ። በረኛው እየተንደረደረ ኳሷን ተከትሎ ወደ ፈረንሳዊው መጣ። ሁለቱም ወደ አንድ አቅጣጫ ፈጠኑ። ሁለቱም የሀገሮቻቸው ጀግና ለመሆን በየፊናቸው እየሮጡ ነው…።የ1982ቱ የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ነበር፣ ፈረንሳይ ከምዕራብ ጀርመን። ውጤቱ 1-1 እያለ ባቲስቶ ተቀይሮ ገባ። ከመግባቱ በፊት በተጠባባቂዎች ወንበር ላይ የምዕራብ ጀርመኑ በረኛ ባህሪይ አልተመቸውም ነበር። ከፈረንሳይ ተጫዋቾች ጋር ሲናቆር ታዝቦታል። የበዛ ግልፍተኛነት ይታይበታል። ከደቂቃዎች በኋላ አሰልጣኙ ወደ ጨዋታው አስገቡት። ከሰባት ደቂቃ በኋላም ከሹማኸር ጋር ተፋጠጠ። ፈረንሳዊያን ጎል ሲጠብቁ ሹማኸር ባለ በሌለ ጉልበቱ እንደ ፊጋ በሬ ተንደርድሮ በትከሻውና ዳሌው ተላተመው። ባቲስቶ ከሹማኸር ጉልበት ጋር አልተመጣጠነም። ከወገቡ በላይ ወደኋላው ተገፍትሮ አካሉን ሊቆጣጠር በማይችልበት ኃይል በጀርባው ከመሬት ተደባለቀ። በክርኑ መሬቱን የተደገፈው የቀኝ እጁ፣ ጣቶቹ እንደታጠፉ ቀና ብሎ ቀስ እያለ መሬቱ ላይ አረፈ። ከዚያም ተጫዋቹ በወደቀበት ሳይነቃነቅ በድን ሆነ። ግጭቱ እጅግ ከባድ ስለነበር ባቲስቶ ራሱን ሳተ። ሁለት ጥርሶቹ ወለቁ፣ ሶስት የጎድን አጥንቶቹ ተሰበሩ። በሜዳ ላይ የህክምና እርዳታ ሲደረግለት በተጫዋቹ ዙሪያ ሆነው አሰቃቂውን ጉዳት በቅርበት የሚከታተሉ የፈረንሳይ ተጫዋቾች ፊታቸውን ወደ ሹማኸር መለስ ቀለስ እያደረጉ ቁጣቸውን ይገልፃሉ። በረኛው ግን ከቁብም አልቆጠራቸው። በመጀመሪያ ወገቡን በእጆቹ ይዞ ባለበት ቆሞ ቆየ። ከዚያም ከሌላ የቡድን ጓደኛው ጋር ኳስ እየተቀባበለ ሰውነቱ እንዳይቀዘቅዝ ማድረጉን ቀጠለ። በኦክስጅን ጭምብል ከሜዳ እንዲወጣ ያስገደደ ከባድ ጥፋት ቢፈጽምም አርቢትር ቻርልስ ኮርበር ለሹማኸር ቀይ ካርድ ቀርቶ የማስጠንቀቂያ ካርድ እንኳን አልመዘዙበትም። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በረኛው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የባቲስቶ ጥርሶች መውለቃቸውን ሲነግሩት ‹‹እኔ ወጪውን እሸፍናለሁ›› በሚል ስላቅ እብሪተኛነቱን ጨምሮ አሳየ። በወቅቱ አንድ ቡድን መቀየር የሚችለው ሁለት ተጫዋቾችን ብቻ በመሆኑ ሁለተኛው ተቀያሪ በጉዳት ከሜዳ የወጣበት የፈረንሳይ ቡድን አጋጣሚው ለፍፃሜ የመድረስ አቅሙን ክፉኛ አዳከመበት። በጭማሪ ሰዓት ፈረንሳይ አከታትላ ባስቆጠረቻቸው ሁለት ጎሎች 3-1 መምራት ብትችልም፣ አልሞት ባዮቹ ጀርመናዊያን ሁለት ጎሎች አግኝተው በ3-3 የመጨረሻ ውጤት ወደ መለያ ምት ሄዱ። ከዚያም የሹማኸር ምዕራብ ጀርመን ለፍፃሜው በቃች። አጋጣሚው በፈረንሳይ ህዝብ ዘንድ ፀረ-ጀርመን ጥላቻን ፈጠረ። ሹማኸር የፈረንሳይ ቁጥር አንድ ጠላት ሆነ። አንድ የሀገሪቱ ጋዜጣ በሰበሰበው የህዝብ መጠይቅ ሹማኸር ከናዚው አዶልፍ ሂትለር በላይ በዚያች ሀገር እንደተጠላ ተረጋገጠ። የጀርመኑ መራሔ መንግስት ሄልሙት ሽሚድት ቁጣውን ለማቀዝቀዝ ለፈረንሳዩ አቻቸው ፍራንሷ ሚቴሯ የቴሌግራም መልዕክት ላኩ። የጋራ መግለጫ ሊያወጡም ተገደዱ። ተጫዋቾቹም እንዲገናኙ ለማድረግ ሞከሩ። በሰዎች ግፊትም ይሁን ዘግይቶ በመጸጸቱ፣ ሹማኸር ተጎጂው ባለበት ሄዶ ይቅርታ ሊጠይቀው ቢሞክርም በጋዜጠኞች መገኘት ምክንያት ያሰበውን ያህል ሳይሳካለት ቀረ። አሁን ባቲስቶ ከስልሳ ዓመት ያለፈው ጎልማሳ ሆኗል። ጉዳቱ በጀርባ አጥንቱ ላይ የፈጠረው አደጋ እስካሁንም የህመም ስሜት እንዳለው ይናገራል። ራስ ምታት ልማዱ ነው። በቃሬዛ ከወጣ በኋላ የተከናወነውን ቀሪ የጨዋታ ፊልም ላለማየት ወስኖ ቢቆይም በመጨረሻ ከሰላሳ ዓመታት በኋላ ተመልክቶታል። ወደ እርጅናው የተጠጋው ሹማኸርም አሁን ደርሶ በአጋጣሚው መጸጸቱን ይናገራል። ከጨዋታው ሁለት ዓመት በኋላ፣ በ1984፣ ፈረንሳይና ምዕራብ ጀርመን በወዳጅነት መርሃ ግብር ተገናኙ። ከጉዳቱ በኋላ ወደ ጨዋታ የተመለሰው ባቲስቶ በድጋሚ በብሔራዊው ማሊያ ከሹማኸር ጋር በተቃራኒ ቆመ። በመጨረሻ ሁለቱ ሰዎች ማሊያ ተቀያየሩ። ቅይይሩ ግን በህዝብና በሚድያው ፊት ሳይሆን በተጫዋቾች መልበሻ ቤት ውስጥ፣ ብቻቸውን ያደርጉት ነበር።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37293
e482a9b918a1d06c463ec3ea3436d092
bd9d938962843a2319cf059722b904bd
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሰበሩ ከሚገኙ የዓለም ክብረወሰኖች ጀርባ
ስፖርት
ቦጋለ አበበበኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ለበርካታ ወራት ተቋርጠው የቆዩ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ካለፈው ሐምሌ መጨረሻ ጀምሮ በሂደት ወደ መደበኛ መርሃግብራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ውድድሮች በተመለሱበት ጥቂት ወራትም በተለይም የረጅም ርቀት የዓለም ክብረወሰኖች ለማመን በሚቸግር መልኩ ሲሰበሩ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡ ይህም የስፖርቱን አፍቃሪዎች ከማነጋገሩ ባሻገር ተንታኞች ጭምር ግራ እንዲጋቡ ያደረገ ክስተት ሆኗል፡፡ በተለይም የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ከወረርሽኙ በፊትም ቢሆን ከሌሎች ርቀቶች በተለየ በሁለቱም ፆታ በተደጋጋሚ ሲሰበር መስተዋሉ አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡ የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በዓለም አትሌቲክስ እኤአ ከ2004 አንስቶ እውቅና እየተሰጠው ከመጣ ወዲህ በወንዶች አምስትና በሴቶች ስድስት የዓለም ክብረወሰኖች ተመዝግበዋል፡፡ ከዚህ ዓመት በፊት በርቀቱ የተመዘገቡ ሰዓቶች በዓለም አትሌቲክስ ‹‹የዓለም ፈጣን ሰዓት›› በሚል ይታወቅ ነበር፡፡ የወንዶች ግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለፈው እሁድ በቫሌንሲያ የተመዘገበ ሲሆን ኬንያዊው አትሌት ኪቢዎት ኬንዲ 57፡32 በሆነ ሰዓት የክብረወሰኑ ባለቤት ሆኗል::የሴቶቹ ደግሞ ባለፈው የካቲት በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የራስ አል ኪማህ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ በ1፡04፡31 በሆነ ሰዓት ያስመዘገበችው ነው፡፡ ይህም በጥቅምት 2017 ኬንያዊቷ ጆይስሊን ጂፕኮስጌ በቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን ካስመዘገበችው የቀድሞው የዓለም ክብረወሰን በሃያ ሰከንድ የተሻለ ነበር፡፡ በመስከረም 2019 ሌላኛዋ  ኬንያዊት ብሪጊድ ኮስጌ በኒውካስትል ታላቁ ሩጫ 64፡28 በሆነ ሰዓት ከቀድሞው ክብረወሰን በሃያ ሦስት ሰከንድ የተሻለ ፈጣን ሰዓት ብታስመዘግብም የዓለም አትሌቲክስ ለክብረወሰኑ እውቅና አልሰጠውም። እኤአ ከ2011 ጀምሮ የዓለም አትሌቲክስ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ክብረወሰኖችን በሴትና በወንድ አሯሯጭ የተመዘገቡ ብሎ በሁለት ከፍሏቸዋል።  በሴት አሯሯጮች የተመዘገበው የርቀቱ ክብረወሰንም በኬንያዊቷ አትሌት ፔርስ ጂፕቺርቺር 1፡05፡16 በሆነ ሰዓት ከወር በፊት በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና የተመዘገበ ነው። ባለፈው ሐምሌ መጨረሻ ለአስራ ስድስት ዓመታት ያልተደፈረው የቀነኒሳ በቀለ የአምስት ሺ ሜትር ክብረወሰን በዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ሞናኮ ላይ ከተሰበረ ወዲህ የዓለም ክብረወሰኖች በተለይም በረጅም ርቀት ውድድሮች እንደልብ የሚሰበሩ ሆነዋል። ከዩጋዳዊው ያልተጠበቀ ክብረወሰን በኋላ አንድ ወር ባልሞላ ልዩነት ትውልደ ሶማሊያዊው የእንግሊዝ አትሌት ሞ ፋራህ እኤአ 2007 ላይ በጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ተይዞ የቆየው ‹የአንድ ሰዓት ውድድር› የዓለም ክብረወሰን ብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ ላይ ከ21፡330 ወደ 21፡285 ተሻሽሏል። በተመሳሳይ ርቀት እንዲሁም በተመሳሳይ ቀንና ውድድር በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድሬ ቱኔ 18፡930 ተይዞ የቆየው የዓለም ክብረወሰን በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን 18፡517 በሆነ ሰዓት ተሻሽሏል። የሁለቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የአንድ ሰዓት ውድድር የዓለም ክብረወሰኖች በተሰበሩ በአንድ ወር ልዩነት ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ለአስራ አምስት ዓመታት ያልተደፈረውን የቀነኒሳ በቀለ የአስር ሺ ሜትር ክብረወሰን በ6፡53 ሰከንድ መስበር ችሏል። በተመሳሳይ ቀን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌትና የረጅም ርቀት ንግስት ጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት ተይዞ ሳይሰበር የቆየውን የአምስት ሺ ሜትር ክብረወሰን 14፡06 በሆነ ሰዓት ሰብራዋለች። ኬንያውያን አትሌቶችም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ባንሰራራው የአትሌቲክስ ውድድር የክብረወሰን ተቋዳሽ ናቸው። ለዚህም በዓለም ግማሽ ማራቶን በአርባ ሁለት ቀናት ልዩነት ሁለት የዓለም ክብረወሰኖችን የጨበጠችው ኬንያዊቷ ፔስር ጂፕቺርቺር ትክክለኛ ማሳይ ናት። መስከረም ላይ በፓራጓይ ግማሽ ማራቶን የሴቶችን ብቻ የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን በ1፡05፡24 ሰዓት ያሻሻለችው ኬንያዊት አትሌት ከአርባ ሁለት ቀናት በኋላ በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና የራሷን ክብረወሰን በአስራ ስምንት ሰከንድ ማሻሻል ችላለች። እነዚህ ሁሉ ክብረወሰኖች ሲሰባበሩና አትሌቶች በተለየ መልኩ አስደናቂ ብቃት ሲያሳዩ አብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ ሁለት ነገሮችን ጠርጥሯል። ይህም በወረርሽኙ ምክንያት አትሌቶች ለረጅም ጊዜ ከውድድር በመራቃቸው ሰፊ የዝግጅት ጊዜ በማግኘት ወደ ውድድር ሲመለሱ ምርጥ ብቃት ሊኖራቸው እንደቻለና በነዚያ የረፍት ጊዜያት በጉዳት ላይ የነበሩ አትሌቶች በበቂ ሁኔታ ማገገም በመቻላቸው እንደሆነ ይታሰባል። ስፖርቱን በጥልቀት የሚመለከቱ በርካታ ተንታኞች ግን ከዚህም የበለጡ ገፊ ምክንያቶች ከክብረወሰኖቹ መሰባበር ጀርባ እንዳሉ ያምናሉ። የልምምድ ስነልቦናና ሂደት በወረርሽኙ ምክንያት እየተለወጠ መምጣቱ ለክብረወሰኖቹ መሻሻል አንድ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም የወረርሽኙ ስጋት ቀደም ብሎ አትሌቶች በርከት ብለው በአንድ አሰልጣኝና በአንድ ካምፕ ውስጥ ሆነው የሚያደርጉትን የተለመደ ዝግጅት ወደ ጎን ትተው በተናጠል በሚመቻቸው ስፍራና በቤታቸው ሆነው እንዲዘጋጁ እድል መስጠቱ ነው። ይህ አጋጣሚ አትሌቶች አንዱ አንዱን ሳይጠብቅ በራሳቸው መርሃግብር መሰረት ወጥ በሆነ መልኩ እስከ አቅማቸው ጥግ ድረስ እንዲዘጋጁ ያስቻላቸው ሲሆን በስነልቦናውም ረገድ ጠንካራ እንዲሆኑ አድርጓል። ለዚህም ከወረርሽኙ በኋላ ክብረወሰኖችን ያሻሻሉ አትሌቶች ቀደም ሲል ይከተሉት የነበረው የልምምድ መልክ በወረርሽኙ ሳቢያ መቀየሩ ለክብረወሰኖች መሻሻል ቁልፍ ሚና እንዳለው የሚያስቀምጡ ባለሙያዎች በርካታ ናቸው። በሌላ መልኩ አትሌቶች በወረርሽኝ ምክንያት ውድድሮች ቢቆሙም የሆነ ጊዜ ላይ እንደሚቀጥሉ አውቀው ዝግጅታቸውን ሳያቋርጡ ተግተው መስራታቸው የክብረወሰን ባለቤት እንዳደረጋቸው ይታመናል። አትሌቶች ወረርሽኙ የጤና ስጋት ቢሆንም መጥፎን አጋጣሚ ወደ ጥሩ ለውጠው ተጠቅመዋል። አቋማቸው እንዳይወርድ በመጠንቀቅ መዘጋጀታቸው ኋላ ላይ ለስኬት አብቅቷቸዋል። በተለይም እቤት የመቀመጥ አስገዳጅ ሁኔታው ቀደም ሲል የነበረባቸውን የተጣበበ የልምምድና የውድድር ጫና በማስቀረቱ በበቂ ሁኔታ እንዲዘጋጁ በር ስለከፈተላቸው በደህናው ጊዜ ማሳካት ያልቻሉትን ክብረወሰን እንዲያሳኩ አድርጓቸዋል። ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ ሆነው የስፖርት ቴክኖሎጂ እየዘመነ መምጣት ለተመዘገቡት ክብረወሰኖች የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝም ዓለም አቀፍ የስፖርቱ ምሁራን የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ባለፉት ጥቂት ወራት ሲመዘገቡ ያየናቸው በርካታ ክብረወሰኖች አትሌቶች የሚያስመዘግቧቸው ሰዓቶች ላይ ሰፊ ልዩነት በሚፈጥሩ ዘመናዊ የመሮጫ ጫማ እንዲሁም አሯሯጮች በተለይም በመም ውድድሮች ከሰው ይልቅ ቴክኖሎጂ ሆኖ አትሌቶችን እስከ መጨረሻ ድረስ በሚፈለገው ደረጃ በማገዝ የተመዘገቡ ናቸው። ግዙፉ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ናይኪ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚያቀርባቸው የመሮጫ ጫማዎች ቀደም ሲል የዓለም ክብረወሰን ሲመዘገብባቸው ከቆዩ የመሮጫ ጫማዎች አንፃር በአትሌቶች ፍጥነት ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንዳላቸው አትሌቶችም ይሁን የስፖርት ቤተሰቡ ይስማማሉ። ከዚህ በላይ የጥሩነሽ ዲባባ የአምስት ሺ ሜትር ክብረወሰን በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና የቀነኒሳ በቀለ የአምስትና አስር ሺ ሜትር ክብረወሰኖች በዩጋዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ሲሰበሩ አትሌቶቹን በአሯሯጭነት ያገዛቸው በመሮጫው መም ዙሪያ የተገጠመው መብራት(Wave-lights) እንደነበር ይታወቃል። ይህ ቴክኖሎጂ አትሌቶቹ በምን ያህል ፍጥነት እያንዳንዱን ዙር ሮጠው ክብረወሰን እንደሚጨብጡ አስልቶ በማሯሯጥ እስከ መጨረሻ ድረስ ደግፏቸዋል። አሯሯጭ በአትሌቲክሱ ዓለም ክብረወሰኖችን ለማስመዝገብ ወሳኙ ነገር እንደሆነ ይታወቃል። አንዳንድ ጊዜ ሴት አትሌቶች በወንድ አሯሯጮች ታግዘውም አሯሯጮች በሚፈለገው ፍጥነት መጓዝ ካልቻሉ ክብረወሰን የማይሰበርበት አጋጣሚ ጥቂት እንዳልሆነ ይታወቃል። አሯሯጩ ቴክኖሎጂ ሆኖ እስከ መጨረሻ ድረስ ወጥ በሆነ ስሌት አትሌቶችን ሲያግዝ ግን የተለየ እንደሚሆን የቅርቦቹ ክብረወሰኖች ምስክር ናቸው።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 5/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37367
f987ec66d457048433bca69cb0296099
1c88714479b8677ce89eed85faa70f55
ታላቁ ሩጫን በጥንቃቄ
ስፖርት
 ቦጋለ አበበ የ20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጥር 2 ቀን ይካሄዳል። የውድድሩ ምዝገባ ባለፈው ታህሳስ 2 ቀን የጀመረ ሲሆን ፣ተሳታፊዎች በያሉበት የአሞሌን መተግበሪያ በመጠቀም ምዝገባውን እንዲያካሂዱ ተደርጓል ። የመጀመሪያዎቹ 200 ተሳታፊ ተመዝጋቢዎች ለውድድሩ መዘጋጃ የሚሆን የመለማመጃ ቲ-ሸርት በነጻ እንደሚሰጣቸውም የውድድሩ አዘጋጆች ከላኩት መግለጫ ታውቋል። 20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዘንድሮ ውድድሩ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ 12ሺ500 ተሳታፊዎች ብቻ ይኖሩታል። በተጨማሪም የአለም አቀፍ ተሳታፊዎችን ለማካተት ውድድሩ በሚካሄድበት ተመሳሳይ ቀን በቨርቹዋል ውድድር በያሉበት ተሳታፊ እንዲሆኑና የ20ኛውን አመት ክብረ በዓል አብረው እንዲያከብሩ ቅድመ ሁኔታ ተጠናቋል። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ከቀድሞ ተሳታፊ 25 በመቶ ብቻ አሳታፊ የሚያደርገው ታላቁ ሩጫ የሚከተሉትን የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄዎች ተግባራዊ ያደርጋል። ውድድሩ የሚጀመረው በሶስት የተለያዩ ማዕበሎች(አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ) ይሆናል። ሶስቱ ማዕበሎች ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጡበት አቅጣጫ በየቲሸርት ቀለሙ ተለያይቶ የተሰየመ ነው። እያንዳንዱ ማዕበልም ማህበራዊ ርቀትን ለማስጠበቅ ሲባል በ 3 እና በ4 ቡድን ይከፈላል። ሩጫው በሶስት የተለያዩ መነሻ ሰዓታት የሚደረግ ይሆናል፤ ተሳታፊዎች የሚጀምሩበትን ሰዓት እና አብረው የሚሮጡትን ቡድን ለመለየት ከሩጫ ቲ-ሸርታቸው ጋር አብረው የሚወስዱት የደረት የመሮጫ ፊደል ጠቋሚ ይሆናል። እያንዳንዱ ተሳታፊ ከሚመርጠው የቲ-ሸርት ቀለም ባሻገር የመወዳደሪያ የደረት ቁጥር በፊደል የሚወስዱ ይሆናል። ተሳታፊዎች የመሮጫ ቲ-ሸርታቸውን ሲወስዱ አብሮ የሚሰጣቸውን የአፍና አፍንጫ ጭንብል የውድድሩ መነሻ፤ የመሰበሰቢያ ቦታና ውድድሩን ከጨረሱ በኋላ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ከዚያም በተጨማሪ ተሳታፊዎች መወዳደሪያ ቦታው ላይ እንደደረሱ እያንዳንዱ ተሳታፊ የሰውነት ሙቀት ልኬት ይደረግለታል።እንዲሁም በውድድሩ መነሻና መድረሻ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር ይቀርባል። ‹‹ወፎችን ታሳቢ ያደረገ የሀይል መሰረተ ልማት›› የ2013 የሩጫው መልዕክት ሲሆን፣ ‹‹በርድ ላይፍ አፍሪካ- የነጩ ጆፌ አሞራ ፕሮጀክት›› የዚህ መልዕክት አስተላላፊና አጋር ድርጅት ነው።የዚህን ዓመት ታላቁ ሩጫ ለየት የሚያደርገው የውድድሩ መነሻ መስቀል አደባባይ ሆኖ መድረሻው አትላስ አካባቢ መሆኑ ነው። ተሳታፊዎች ውድድሩ ሊካሄድ 10ቀናት ሲቀሩት የመወዳደሪያ ቲ-ሸርት፤ የመሮጫ የደረት ቁጥር ፊደል እና ጭምብል ምዝገባ ሲያደርጉ በመረጡዋቸው የዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች በመሄድ መቀበል ይኖርባቸዋል።  አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 5/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37370
eb5aedce6adbdb0a4ed7ab8a22cb5329
5fde6f03d810d37932263bb6395869fa
የባዶ እግር ትሩፋቶች
ስፖርት
ብርሃን ፈይሳየበጋማው ወቅት ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ጎዳናውን ቢያግለውም፣ ባዶ እግሩን ሮጦ ከማሸነፍ አላገደውም። ጦር ያዘመተችባት ሃገር ሽንፈትን በተከናነበችበት ማግስት ብቻውን ዘምቶ እንደ አንድ ባታሊዮን ጦር አሸንፎ የኢትዮጵያዊያንን አንጀት አራሰ እንጂ፡፡ በእርሱ እግር የተተካውም፤ በቀናት ልዩነት በመም የተካፈለበትን ርቀት ከመጤፍ ሳይቆጥር በማራቶንም ዳግም ሃገሩን በክብር አስጠርቷል፡፡ሌላኛው ደግሞ እስርና ሌላ ኦሊምፒክን ማሳለፍ ተስፋ ሳያስቆርጠው በአንድ ኦሊምፒክ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማጥለቅ ዓለምን ‹‹አጀብ›› አሰኝቷል፡፡ሴቶች በኋላ ቀሩ ሶስተኛው ዓለም በዚህ ደረጃ እንደሚገኙ በማይገመትበት ወቅት በአፍሪካ የመጀመሪያውን የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ የግሏ ያደረገች እንስት የተፈጠረችው በዚህችው ሀገር ነው፡፡በቀደሙት መንገድ የተጓዙ አይበገሬዎች፤ የዓለምን ክብረወሰኖች በመሰባበር ኢትዮጵያ የማትነጥፍ የድል አድራጊዎች እናት መሆኗን አስመስክረዋል፡፡በጉዳት ያልተበገሩ፣ ታላላቆቻቸውን ያከበሩ፣ ሃገራቸውን አስቀድመው፤ ላብ እንባና ደማቸውን ያፈሰሱ ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች ጥቂት አይደሉም፡፡አንድን ውድድር መጨረስ ህልም የሆነባቸው ብዙ ሃገራት ባሉባት ዓለም አበበን የተከተሉ የባዶ እግር ትሩፋቶች፤ ህዝባቸውን በደስታ ጮቤ እያስረገጡና የሃሴት እንባ እያስነቡ ስድስት አስርት ዓመታትን ተሻግረዋል፡፡ሜዳሊያና ዲፕሎማ ከማስመዝገብም አልፈው ሃገራቸውን በተሳትፎ ያከበሩ አትሌቶች፣ በቡድን መሪነት፣ አሰልጣኝነት፣ የህክምና እና የቴክኒክ ባለሙያነት እንዲሁም በመገናኛ ብዙኃን ድሉን ለህዝብ በማድረስም ሚና የነበራቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ይሁን እንጂ እነዚህ የሃገር ባለውለታዎች በሚገባቸው ልክ ሳይከበሩና ሳይመሰገኑ ቆይተዋል፡፡የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ጀግናን ማክበር፤ ለመጪው ትውልድ ብርታት ነውና ከሜልቦርን እስከ ሪዮ ኦሊምፒኮች ሃገራቸውን ለወከሉ ምስጋናውን በልዩ ክብር አበርክቷል፡፡‹‹የባዶ እግር ትሩፋቶች›› በሚል በተካሄደው መርሃ ግብር ላይም ተሳትፎ ላስመዘገቡ አትሌቶችና ባለሙያዎች ከ25ሺ ብር ጀምሮ የሚጨምር የገንዘብና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡በህይወት0ቀዳሚዎቹ አትሌቶች፣ አሰልጣኝና ጋዜጠኛም እረፍታቸው በተደረገበት ስፍራ በመገኘት የአበባ ጉንጉን የማኖር ስነስርዓትም ተካሂዷል፡፡ በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይም የታላቁ አትሌት ልጅ የትናየት አበበ ቢቂላ የሁለት ሚሊየን ብር ሽልማት ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተቀብሏል፡፡ የሌላኛው ተአምረኛ አትሌት ልጅ ሳሙኤል ማሞ ወልዴ እና የልጅ ልጁ እንዲሁም የድርብ ድሉ ባለቤት ‹‹ማርሽ ለዋጩ›› ባለቤትና ልጃቸው ቢኒያም ምሩጽ ይፍጠር ደግሞ አንድ አንድ ሚሊየን ብር ተበርክቶላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስንና ድልን ያወዳጃቸው ጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ ቢሆንም፤ የድሉን ቀጣይነት ያወጀው ሌላኛው ወርቃማ አትሌት ሻምበል ማሞ ወልዴ ነው፡፡ማሞ የአበበን ፈለግ ተከትሎ ሃገሩ የለመደችው እንዳይጎድልባት በላቡ ክብሯን ከማድመቅም አልፎ ለተተኪ አትሌቶችም መንገድ ጠራጊ ሆኗል፡፡ ይህ በድል የተንቆጠቆጠ አትሌት ዛሬ በህይወት ባይኖርም ከሃገሩ የቀረበለትን ምስጋና በልጁ ተረክቧል፡፡ ሳሙኤል ማሞ ወልዴ፤ አባቱን ወክሎ ለተገኘበት መድረክ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማውም ገልጿል፡፡ለሃገሩ ብዙ ዋጋ የከፈለው አባቱ የሚገባውን ያህል ሳይደረግለት አልፏል፤ ቤተሰቦቹም ድጋፍ ይሹ ነበር፡፡ይባስ ብሎ ከ13 ዓመታት በፊት የመቃብር ሃውልቱ ፈረሰ፤ ይህንን ተከትሎም ልጁ በግሉ ብዙ ጥረቶችንም አድርጎ ሰሚ ባለማግኘቱ ትቶት ነበር፡፡አሁን ግን በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ጥረት ሃውልቱ በድጋሚ በመሰራቱና እውቅናው በመሰጠቱ እንዲሁም ሻምበል ማሞ ካረፈበት ጊዜ ጀምሮ ለቤተሰቦቹ ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ የወንዶች ተሳትፎ ቀዳሚ ቢሆንም አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን የሴት ኦሊምፒያኖች ድል በእኩል ደረጃ የሚጠቀስ ሊሆን ችሏል፡፡ በስፖርቱ ከቀዳሚዎቹና ፈር ቀዳጆቹ መካከል አንዷ በምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለሃገራቸው ስላበረከቱት አስተዋጽኦ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማታቸውን ወስደዋል፡፡ በአትሌትነትና አሰልጣኝነት ሃገራቸውን አገልግለው በጡረታ ላይ የሚገኙት ወይዘሮ ጽጌ ገብረመሲህ፤ እርሳቸውና መሰሎቻቸውን ተከትለው በየዘመኑ የወጡ አትሌቶች ሃገራቸውን በማስጠራታቸውና በዚሁ ምክንያትም የሽልማት ተካፋይ በመሆናቸው ክብር እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ተሸላሚዎች በጡረታ የተገለሉ፣ የተረሱ፣ ወደፊት ወጥተው ያልታዩ አንዳንዶች ደግሞ በሞት የተለዩ ቢሆኑም፤ ሁሉንም አስታውሶና አሰባስቦ ለሽልማት ማብቃት አስደሳች ነው፡፡ወደፊትም ይህን መሰል አትሌቶች አሰልጣኞችና አመራሮችም ጭምር በተመሳሳይ መልኩ እንዲታወሱ፤ በተለይ መገናኛ ብዙሃን የአትሌቲክስ ቤተሰቦች እንዲበረቱ ማስታወስ እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል፡፡ በመድረኩ ተገኝተው እውቅናውን ያበረከቱት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ አበበ ቢቂላና እሱን የተከተሉ አትሌቶች ለሃገራቸው ያበረከቱት አስተዋጽኦ የሚለካ ባይሆንም፣ እንደሚገባቸው አለመከበራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ይህ የምስጋና መድረክ መዘጋጀት በርካታ ጉዳዮችን ያስተምራል፤ ከምንም በላይ ኢትዮጵያን አስተዋውቀዋልና ጀግኖች ሊከበሩና ሊዘመርላቸውም ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ስትነሳ አብሯት የሚነሳው አበበ ቢቂላ፤ ዓለምን የማረከ፣ ባዶ እግሩን ሮጦ ኢትዮጵያን ያስተዋወቀ አትሌት ነው፡፡በተለይ ባንዲራዋን ከፍ ያደረገው በጣሊያን ሃገር መሆኑ ድሉን ከሩጫ በላይ ያደርገዋል።ይህም እጅግ የሚያኮራ በመሆኑ ጀግኖቻችንን ማክበር ከእነሱም መማር አለብን ብለዋል፡፡ጀግኖቹን የማያከብር ሃገር ወደፊት ሊሄድ እንደማይችልም ፕሬዚዳንቷ አመላክተዋል፡፡ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሰው በበኩላቸው፤ የሃገር ባለውለታ የሆኑ አትሌቶችን ማመስገን አሁን ላሉት አትሌቶች ስንቅ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ቶኪዮ ላይ በተካሄደ የአበበ ቢቂላ ድል 60ኛ ዓመት መርሃ ግብር ላይ እንደተሳተፉ የጠቀሱት ሚኒስትሯ፤ የኢትዮጵያ በበቂ መልክ አለመዘጋጀት ያስረዳ እንደነበረ ያስታውሳሉ፡፡አበበን ከኢትዮጵያ ይልቅ የሚያከብሩት ጃፓናዊያን ህጻናትም ሳቀሩ ስለ እርሱ ይጠይቃሉ ብለዋል፡፡በወቅቱ በቦታው የተገኙ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ስንቅ፣ ልምድና አሰራር ተምረው በመመለሳቸው መርሃ ግብሩን ለማዘጋጀት እንዳበቃቸውም አመላክተዋል፡፡ ስፖርት ኢትዮጵያን እንደ ሃገር የገነባት አንዱ ዘርፍ ነው፡፡በባዶ እግር ሮጦ ማሸነፍ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ውስጣዊና አካላዊ ጥንካሬ ያላቸው ህዝቦች መሆናቸውን ያሳየ ነው፡፡ይህም የይቻላል ስነልቦና ያለው ትውልድ ለመፍጠር የሚያስችል ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ፤ በርካታ ስራዎችን ያከናወኑ የአትሌቲክስ ጀግኖቻችንን ክብር በመሰጠቱ ደስታዋን ገልጻለች፡፡ፈር ቀዳጆቹን አትሌቶች ተከትለው በ13 ኦሊምፒኮች ላይ ሃገራቸውን ያስጠሩ በርካታ አትሌቶችን ማፍራት ተችሏል ያለችው ፕሬዚዳንቷ፣ የአበበ ቢቂላ ከሮም መልስ በጃፓን ቶኪዮም የሜዳሊያ ድል ባለቤት መሆን የቆራጥነትና ጽናትን በማስተማር ድሉን ያስቀጠለ ሆኗል ብላለች፡፡በቶኪዮ 2021 ለሚካሄደው ኦሊምፒክም አትሌቶች በዝግጅት ላይ እንደሚገኙም ገልጻ፣ የባዶ እግር ትሩፋቶች በሚል የተካሄደው መርሃ ግብርም የኦሊምፒክ ባለውለታዎችን ከመዘከር ባሻገር የማይቋረጥ የሃገር ፍቅር ስሜትን ለመፍጠር በማሰብ መሆኑንም አብራርታለች፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37432
d662787665fa6799e5cfc7a5b0f8e576
035e6da1ef177119d272c270d52a4dd9
የቀጣዩ አራት ዓመት የአትሌቲክስ መሪዎች
ስፖርት
ቦጋለ አበበየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከትናት በስቲያ ባደረገው 24ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በቀጣይ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን የሚመሩ ሰዎችን ለይቷል።ከአራት ዓመት በፊት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት የተመረጠው ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ሁለት ዓመት አገልግሎ በራሱ ፍቃድ ስልጣኑን ከለቀቀ በኋላ ሌላኛዋ ጀግና አትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ፌዴሬሽኑን ስትመራ ቆይታለች።ከትናንት በስቲያ ማታ በካፒታል ሆቴል በተደረገው ምርጫም ደራርቱ ለቀጣዩ አራት ዓመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት በጠቅላላ ጉባዔው ይሁንታ አግኝታለች።ምርጫው ከመከናወኑ ከሳምንት በፊት ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ዕጩ ሆነው በደቡብ ክልል የተወከሉት አቶ ተፈራ ሞላ፣ ለስፖርቱ ቅርበት ያላት ደራርቱ ከመሆኗ ባሻገር ባለፉት ሁለት ዓመታት በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ፌዴሬሽኑን በመምራት ያደረገችውን ጥረት እንድትቀጥል ከእጩነት ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወቃል።በዚህም ደራርቱ በፕሬዚዳንትነት ምርጫ ፉክክሩ ብቸኛ እጩ ሆና በመቅረብ አስቀድሞም ማሸነፏ የተረጋገጠ ነበር።በዚህም ጠቅላላ ጉባዔው በሃያ ሰባት ድምፅና በአንድ ተቃውሞ የደራርቱን ፕሬዚዳንትነት እንዳረጋገጠ በወቅቱ የተገለጸ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ ደራርቱ ካለምንም ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ማሸነፍ እንደቻለች ትናንት ገልጿል።በምርጫው በተሰጠው ድምፅ በአንድ ተቃውሞ መመረጧ የተገለጸው በስህተት መሆኑን የጠቆመው ፌዴሬሽኑ በድምፅ አሰጣጥ ወቅት በምርጫ ወረቀት ላይ ድምፅ ሰጪው የራይት ምልክት ማድረግ ሲገባቸው የኤክስ ምልክት በማድረጋቸው መሆኑን አረጋግጧል። ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ይልቅ ለሥራ አስፈፃሚነት በቀረቡት አስራ ስምንት እጩዎች መካከል የሚደረገው ፉክክር በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።ከአራት ዓመት በፊት በሥራ አስፈፃሚነት ለመወዳደር እጩ ሆኖ ቀርቦ በአንድ ድምፅ ተበልጦ ያልተሳካለት የሲድኒ ኦሊምፒክ የማራቶን ባለድሉ አትሌት ገዛኸኝ አበራ ዘንድሮ በኦሮሚያ ክልል እጩ ሆኖ በመቅረብ ተሳክቶለታል።በተመሳሳይ ኦሮሚያ ክልል እጩ አድርጎ ያቀረባቸው ወይዘሮ ሰሃራ ሃሰን አዲስ የሥራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል።አማራ ክልል እጩ አድርጎ ያቀረባቸው ወይዘሮ አበባ ዮሴፍም አዲስ የሥራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል።ወይዘሮ አበባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ወጣቶችና ሕፃናት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ መሆናቸው ይታወቃል።ባለፉት አራት ዓመታት የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ባለሀቱ አቶ በላይነህ ክንዴም ከአማራ ክልል ለሥራ አስፈፃሚነት ተወዳድረው በማሸነፍ የሚቀጥሉ ይሆናል።አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት ያቀረባቸው ሁለት እጩዎችም አሸናፊ መሆን ችለዋል።የስፖርት ሳይንስ መምህሩና በስፖርቱ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በማገልገል የሚታወቁት ዶክተር በዛብህ ወልዴ ባለፉት ዓመታትም ሥራ አስፈፃሚ አባል የነበሩ ሲሆን፤ ለቀጣዩ አራት ዓመትም እንደሚቀጥሉ አረጋጠዋል።ሌላኛዋ  የአዲስ አበባ እጩ ወይዘሮ ትልቅሰው ገዳሙም አዲስ ሥራ አስፈፃሚ አባል ሆነዋል።ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ራሳቸውን በማግለል በሥራ አስፈፃሚነት የተወዳደሩት አቶ ተፈራ ሞላም ከደቡብ ክልል ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተመርጠዋል።ባለፉት ዓመታት በሥራ አስፈፃሚነት ሲያገለግሉ የቆዩት የአፋር ክልል ተወካይ ወይዘሮ ፊዚያ ኢድሪስም የሚቀጥሉበት ዕድል አግኝተዋል።በጠቅላላ ጉባዔው ወቅት ስፖርቱን ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመምራት ምስጉን ሥራዎችን እንዳከናወነች በመግለጽ አድናቆት ሲቸራት የነበረችው ደራርቱ ከምርጫው በኋላ ፕሬዚዳንትነቷን በማረጋገጧ ባላት ልምድና እውቀት አገሯን በቅንነት ለማገልገል ቁርጠኝነቱ እንዳላት ተናግራለች።በእጩነት ያቀረባትን ኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ራሳቸውን በማግለል እድሉን እንድታገኝ ያደረጉትን አቶ ተፈራ ሞላን አመስግናለች።በቀጣይም ባለፉት ዓመታት ከነባሩ ሥራ አስፈፃሚ ጋር ስፖርቱ የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ያደረገችውን ጥረት ከአዲሱ ሥራ አስፈፃሚ ጋር እንደምትቀጥልበት ቃል ገብታለች።ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ስምንት ዓመታት የሚመራበት ስትራቴጂክ እቅድ ለጠቅላላ ጉባዔው ቀርቦ የፀደቀ ሲሆን፤ የተለያዩ ሃሳቦች ቀርበውም ውይይት ተደርጎባቸዋል።ፌዴሬሽኑ የተለያዩ እቅዶችን ሲያቀርብ አትሌቶችን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ወደተለያዩ አገራት በመላክ ለመወዳደር እንጂ በአገር ውስጥ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማዘጋጀት እቅድ ለምን አይኖረውም? የሚል ጥያቄ በመድረኩ ከተነሱ ሃሳቦች አንዱ ነው።ለዚህ ጥያቄ በተሰጠው ምላሽም ፌዴሬሽኑ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ጥረት እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፤ ዘንድሮ የአፍሪካ አገር አቋራጭ ቻምፒዮናን ለማስተናገድ እንደታሰበ ተጠቁሟል።ፌዴሬሽኑ በተለያዩ ዓመታዊ የውድድር መርሐግብሮቹ በሚያካሂዳቸው የጎዳና ላይ ውድድሮች የሕብረተሰብ ተሳትፎ አለመኖሩ ለብዙ ጊዜ ሲነሳ የነበረ ጥያቄ ሲሆን፤ ሕዝብ የሚሳተፍባቸው ውድድሮችን ለማካሄድ እቅድ እንዳለ ተጠቁሟል።ፌዴሬሽኑ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወጥሮ ስልጠናን በመዘንጋት ውጤቶች በሚጠበቀው ደረጃ እየተገኙ እንዳልሆነም ትችቶች ተሰንዝረዋል።አዲሱ የሲዳማ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጉባዔው ተሳታፊ ከመሆኑ ባሻገር በሥራ አስፈፃሚ ምርጫ ላይ አንድ እጩ ባቀረበበት መድረክ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክኒያት ስፖርቱ አስቸጋሪ ጊዜ ማሳለፉ ተገልጿል።ይሁን እንጂ በነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት ፌዴሬሽኑ እቅዶቹን በታሰበው ልክ ማከናወን ባይችልም እጁን አጣጥፎ ሳይቀመጥ በጥንቃቄ የተለያዩ ሥራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ ተጠቁሟል።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ‹‹ይህን ያህል ሜዳሊያዎች እናስመዘግባለን›› ብሎ ማቀድ አዳጋች እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት የፌዴሬሽኑ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ የስፖርቱ ባህሪ እየተቀየረ እንደሚገኝ አስረድተዋል።በተለይም ኢትዮጵያ በምትታወቅበት የረጅም ርቀት ውድድሮች ሌሎች አገራትም ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸው ለዚህ ፈተና አንዱ ምክኒያት እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፤ የሌሎች አገራት የኢኮኖሚ ጥንካሬና የዓለም አቀፍ ውድድር አዘጋጆች የአትሌቶች አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚነትን ሽፋን መስጠት ተፅዕኖው ቀላል እንዳልሆነ አብራተዋል።ፌዴሬሽኑ በጉባዔው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት በነበረው የስፖርቱ እንቅስቃሴ ጥሩ ሥራ ሠርተዋል ያላቸውን ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከክለቦች ስምንት ስምንት ተሸላሚዎችን መርጦ እንደየደረጃቸው ገንዘብ አበርክቶላቸዋል።በዚህም የኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቀዳሚ በመሆን 240ሺ ብር ተሸላሚ ሲሆን፤ የአማራ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 180ሺ ብር ተሸላሚ ሆኗል።አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 140ሺ፣ ደቡብ ክልል 100ሺ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 80ሺ፣ ሐረሪ 60ሺ፣ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 40ሺና ጋምቤላ 20ሺ ብር ተሸላሚ ሆነዋል።ከክለቦች መከላከያ ስፖርት ክለብ ቀዳሚ በመሆን ሦስት መቶ ሺ ብር ተሸላሚ ሲሆን፤ የፌዴራል ፖሊስ ስፖርት ክለብ 240ሺ ብር ሊሸለም ችሏል።ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ 180ሺ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ 140ሺ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100ሺ፣ ደቡብ ፖሊስ 80ሺ፣ ሲዳማ ቡና 60ሺና ኦሮሚያ ውሃ ሥራዎች 40ሺ ብር ተሸላሚ ሆነዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37493
48c4f0258c9a44ac079b744402780a5c
0c246c95c710d21f1133b25ca0340f7b
ቡድኑ ዝግጅቱን አስቀድሞ መጀመሩ ለውጤታማነት ያግዘዋል
ስፖርት
ብርሃን ፈይሳ የቶኪዮ 2021 ኦሊምፒክ ከመካሄዱ ወራትን አስቀድሞ ዝግጅት መጀመሩ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የሚያደርግ መሆኑ ተገለጸ። በኦሊምፒክ መድረክ ሃገራቸውን ለወከሉ አትሌቶች የተካሄደው የምስጋና መርሃ ግብር፤ ለመጪው ኦሊምፒክ ተሳታፊዎች መነሳሳትን እንደሚፈጥርም ተጠቆመ፣ ከዚህ ቀደም ይደረግ ከነበረው በተለየ ሁኔታ ከወራት በፊት ካምፕ በመግባት የረጅም ጊዜ ዝግጅት ማድረግ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የተሻለ ውጤት እንዲያመዘገብ ያስችላል ተብሏል። በ5ሺ ሜትር ሃገሩን ለመወከል በቡድኑ የተካተተው አትሌት ጫላ ከተማ፤ ብሄራዊ ቡድኑ ዝግጅቱን ከጀመረ አንድ ወር እንዳስቆጠረ ይገልጻል። ማረፊያውን በጥሩነሽ ዲባባ ሆቴል ያደረገው ቡድኑ በሰንዳፋ፣ አዲስ አበባ ስታዲየም እና በቃሊቲ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን፤ በውድድሩ ወቅት በጃፓን የሚኖረው የአየር ሁኔታ ሞቃታማ ሊሆን ስለሚችል ከባድ ሊያደርገው ይችላል ከሚለው ግምት ባሻገር መልካም ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ያረጋግጣል።እንደ አትሌቱ ገለጻ፤ ከዚህ ቀደም ከወራት በፊት ካምፕ በመግባት ለረጅም ጊዜ ዝግጅት ተደርጎ አያውቅም። ኢትዮጵያ የምትታወቀው በቡድን ስራ ቢሆንም በዝግጅት ወቅት ተለያይቶ መስራት ውጤት እንዲጠፋ አድርጎት ቆይቷል። አሁን ግን ለረጅም ወራት አትሌቱ በአንድ ተሰባስቦ መስራቱ አትሌቶች እንዲግባቡና ለቡድን ስራም የሚያግዝ መሆኑን ያምናል። በአሰልጣኞችና በፌዴሬሽኑ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም የተሻለ ውጤት ይመጣል የሚል እምነቱንም አትሌቱ ያንጸባርቃል። ከዚህ ባሻገር ቡድኑ ኮቪድ 19ን በመከላከል ረገድም አስፈላጊውን ሂደት እየተከተሉ መሆኑን አትሌት ጫላ ይጠቅሳል። ያረፉበት ሆቴል ከአትሌቶች ውጪ ሌሎች ሰዎች የማይገለገሉበት ሲሆን፤ በልምምድና በሌሎች እንቅስቃሴዎች ውስጥም ንጽህናቸውንና ርቀታቸውን ከመጠበቅ ጎን ለጎን በጤና ባለሙያዎችም ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ሲል ያብራራል። ‹‹የባዶ እግር ትሩፋቶች›› በሚል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በቅርቡ የተካሄደው የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር፤ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊ ለሚሆኑ አትሌቶች መነሳሳትን እንደሚፈጥርም በባለሙያዎች ታምኖበታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ኦሊምፒክ ለአንድ ዓመት መራዘሙ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም ለቶኪዮ 2021 ኦሊምፒክ አትሌቶችና አሰልጣኞች ከወዲሁ ዝግጅት መጀመራቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ ጠቁማለች። ለብሄራዊ ቡድን የተመረጡት አትሌቶች ለሁለት ተከፍለው በአሰለፈች መርጋ እና በጥሩነሽ ዲባባ ሆቴል መቀመጫቸውን በማድረግ ዝግጅት እያደረጉ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፌዴሬሽኑ ለቀደሙት የኦሊምፒክ ተሳታፊዎችና ባለድል አትሌቶች እንዲሁም ባለሙያዎች ማበረታቻ ማዘጋጀቱ፤ በቡድኑ ለታቀፉ አትሌቶች ሞራል እንደሚሆን ይጠበቃል። በምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለአትሌቶችና ቤተሰቦቻቸው ሽልማት ያበረከቱት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ ዘመኑ እንዳሁኑ ባልሰለጠነበትና መሰረተ ልማትም ባልተሟላበት ወቅት ኑሮ ከሩጫ ጋር የተያያዘ በመሆኑ አትሌቶች ስልጠናም ሳያስፈልጋቸው በኦሊምፒክ ሮጠው ማሸነፋቸውን ጠቅሰዋል። አሁን ግን ጊዜው እንደዚያ አለመሆኑን ጠቅሰው፣ አትሌቶች ለቶኪዮ ኦሊምፒክ በደንብ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል ብለዋል። በኦሊምፒኩ የሚሳተፉ አትሌቶች ሆቴል ቢገቡም ጊዜው እጅግም ሩቅ ባለመሆኑ በደንብ መጠበቅ እንዳለባቸውም ነው ያሳሰቡት። መጪው ኦሊምፒክም በሽልማት መድረኩ ስማቸው የተነሳው አትሌቶች ገድል የሚታደስበት ሊሆን ይገባል ያሉት ፕሬዚዳንቷ፣ ለቶኪዮ በሁሉም መንገድ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል። ኢትዮጵያንና አፍሪካን ከፍ ለማድረግና ቶኪዮ ላይ ያሸነፈውን የአበበ ቢቂላን ድል ለማደስ፤ የሚመለከታቸው ሁሉ አትሌቶችን በማዘጋጀትና በመደገፍ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል። በቶኪዮ 2021 በአሸናፊነት በተመሳሳይ መርሃ ግብር ለመገናኘት ፕሬዚዳንቷ ምኞታቸውን ገልጸዋል። የቶኪዮ ኦሊምፒክ መራዘም ለበጎ መሆኑን የሚያመላክቱት ደግሞ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሰው ናቸው። የቶኪዮ 2021 ድል ከዚህ ቀደም ከነበረው እጥፍ ድርብ እንደሚሆን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ ለአትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ አመራሮችና በስፖርቱ ላይ ለሚሰሩት ሁሉ የምስጋና መርሃ ግብሩ የብርታት ስንቅ እንደሚሆናቸው ነው የገለጹት። ከአንድ ዓመት በፊት በቶኪዮ በተካሄደ በሻምበል አበበ ቢቂላ ድል የ20 ኪሎ ሜትር የማስታወሻ ሩጫ ላይ የኢትዮጵያ ዝግጅት መልካም እንዳልነበር ለመታዘብ ተችሏል። በወቅቱ በጃፓን የተገኙ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ልምድና አሰራር ተምረው መመለሳቸውን ተናግረው፣ በዚሁ መሰረት በመስራት የጀግና እና የይቻላል ስነልቦና የተላበሰ ህዝብ ያለባት ሃገር መሆኗ ዳግም እንደሚታይም ያላቸውን ተስፋ አንጸባርቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37572
4f79f726b82aa9da10eea271f49f0917
24380bfbae78676c35a802682579d0f8
ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባለድርሻ አካላትን አመሰገነ
ስፖርት
ቦጋለ አበበ ባለፈው ህዳር 27/2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሁለት አህጉራዊ ስኬቶችን በስፖርቱ ዘርፍ አስመዝግቧል። በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ጠቅላላ ጉባዔን ማስተናገድ የመጀመሪያው ስኬት ነው። ከጉባዔው ጎን ለጎን ለመሪዎች የሚበረከተውን የአኖካ የስፖርት የክብር ኒሻን ሽልማት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በማሸነፋቸው የሽልማት ሥነሥርዓቱን ማስተናገድ ሌላው ስኬት ነው። ሁለቱን ታላላቅ የስፖርት ኩነቶች ኢትዮጵያ በአንድ ቀን በስኬት እንድታስተናግድ ከኦሊምፒክ ኮሚቴው ጋር በቅርበት በመስራት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ለዚህም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ‹‹ከስኬቴ ጀርባ ነበሩ›› ያላቸውን ባለድርሻ አካላት ከትናት በስቲያ ምሽት ያመሰገነበትን መርሃግብር አዘጋጅቷል። በብዙ የተመሰገኑት የስፖርት መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች በምስጋና መርሃግብሩ ተገኝተው የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል። ለአኖካ ጠቅላላ ጉባዔና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማት ሥነሥርዓት ከተለያዩ አገራት የመጡ ከሁለት መቶ ሃምሳ በላይ እንግዶችን ለመቀበል በነበረው ሂደት ውስጥ ጉልህ ድርሻ የነበረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትልቅ ምስጋና የተቸረው ሲሆን፣ ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የምስክር ወረቀቱን ተቀብለዋል። ‹‹የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአኖካ ሽልማት የተወሰኑ አገራትና መሪዎች ያገኙት እንደመሆኑ ትልቅ ስኬት ነው›› ያሉት አምባሳደር ዲና ለዚህ ስኬት እውን መሆን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ትልቅ ስራ በመስራታቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባ ገልጸዋል። የአኖካ ጠቅላላ ጉባዔ ካለ እንከን እንዲጠናቀቅም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች የተወጡት ትልቅ ሃላፊነት አድናቆት እንደሚገባው ተናግረዋል። ሁለቱ ስፖርታዊ ኩነቶች የአገር ገፅታ የተገነባባቸውና ትልቅ ዋጋ የሚገባቸው መሆኑንም አምባሳደሩ አስረድተዋል። ጉባዔውና የሽልማት ሥነሥርዓቱ የተሳካ እንዲሆን ከተዋቀሩት የመስተንግዶ ኮሚቴዎች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ በበኩላቸው፣ በወቅቱ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ እንደነበረች በማስታወስ ስፖርታዊ ኩነቶቹን በስኬት ለማስተናገድ ‹‹ከውጭ ሆኖ የሚመለከተው ብቻ ሳይሆን እኛም ጥርጣሬ ነበረን›› ብለዋል። ሆኖም ሁሉም ባድርሻ አካላት የቤት ስራቸውን በስኬት ተወጥተዋል። ይህም ጥሩ ልምድ፣ ትብብርና መልካም የስራ መንፈስ የታየበት እንደነበር አብራርተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ    የስፖርት ትልቅ ሽልማት በቀጣይ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥርም አክለዋል። የስፖርት መገናኛ ብዙሃን ከመነሻው አንስቶ ለጉዳዩ ሰፊ ሽፋን በመስጠት ያበረከቱት ትልቅ አስተዋጽኦም ብሮድካስት ባለስልጣንን እንዳስደሰተ ተናግረዋል። ‹‹በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን እንደዚህ ኮርቼ አላውቅም›› በማለት ምስጋናቸውን የጀመሩት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር፣ በወቅቱ ከፖለቲካና ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ጋር ተያይዞ ከነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ አንፃር የአገር ገጽታ እንዲገነባና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚገባቸውን ሽልማት እንዲያገኙ የስፖርት መገናኛ ብዙሃን ላበረከቱት ትልቅ አስተዋፅኦ ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል። አገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና ማህበራት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦችን በትልቁ ያመሰገኑት ዶክተር አሸብር፣ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ስፖርታዊ ኩነቶቹ በስኬት እንዲጠናቀቁ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ በመሆናቸው ልዩ ምስጋና አቅርበዋል። የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን በተቋም ደረጃም ኮሚሽነሩ ኤልያስ ሽኩርና የተቋሙ ባለሙያዎች ከስኬቱ ጀርባ ለነበራቸው ትልቅ ሚና ተመስግነዋል። በርካታ አገራትና መሪዎች የገፉትን የአፍሪካ ፓራሊምፒክ ቻምፒዮና ኢትዮጵያ ለማዘጋጀት ፍቃደኝነቷን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አማካኝነት ማረጋገጧን የጠቀሱት ዶክተር አሸብር፣ በተመሳሳይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁንታ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኦሊምፒክ ስምንት ወራት አስቀድሞ ዝግጅት ሊጀመር እንደቻለ አስታውሰዋል። ይህም በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ትልቅ ተነሳሽነትን መፍጠር እንደቻለ አብራርተዋል። ‹‹እንዲህ አይነት ልቡንም በሩንም ለስፖርት ክፍት አድርጎ የሚጠብቅ መሪ ባለበት ወቅት የስፖርቱን ትንሳዔ እውን ካላደረግን መቼም አናደርግም›› በማለትም ፕሬዚዳንቱ የምስጋና ንግግራቸውን ቋጭተዋል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዳዊት አስፋው ጉባዔውና የሽልማት ሥነሥርዓቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ምስጋና በማቅረብ ‹‹ሁለቱን ታላላቅ ስፖርታዊ ኩነቶች እኛ አመጣናቸው እንጂ ትልቁን ሃላፊነት የተወጣችሁት እናተ ናችሁ፣ በቀጣይም በርካታ እቅዶች አሉን፣ አብረን በመስራት እናሳካለን›› ብለዋል። የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽንም ለዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልዩ ሽልማት አበርክቷል።አዲስ ዘመን  ታህሳስ 10/ 2013
https://www.press.et/Ama/?p=37676
af07eaea6ac6599b1b9d41617fff1149
ae9bc8a3997d431210c2b66aee932e3c
በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም ምክንያታዊ ትውልድ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
መርድ ክፍሉአዲስ አበባ፡- በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለዘለቄታው ለማስቆም በምክንያት የሚያምን ትውልድ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። በአገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች በአገር ጉዳይ ምክንያታዊ የሆነ አስተሳሰብን መፍጠር የሚስችላቸው የሙግትና የንግግር መድረክ በአዲስ አበባ ተጀመረ። የብልጽግና ወጣት ሊግ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ወጣት አክሊሉ ታደሰ ትናንት መድረኩን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንዳስታወቁት ፤ በአገሪቱ በእምነት እና በፖለቲካ ልዩነት እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ወደ ግጭት እየተገባ ነው። ይህን ለመቀነስና ለማስቆም ምክንያታዊ የሆነ ወጣት መፍጠርና በንግግር የሚያምን ትውልድ መቅረጽ ያስፈልጋል ፤ ለዚህም መድረኩ ተመቻችቷል። የጋራ ባህል፣ እሴት፣ ታሪክ እንዲሁም መተሳስሮች ባይኖሩ ባለፉት ጊዜያት የእርስበርስ ግጭት ለመፍጠር የተሰራጩት የታዘቡ መረጃዎች ሀገርና ህዝብን ከሆነው በላይ ሀገርና ህዝብን ዋጋ ያስከፍሉ እንደነበር አመልክተዋል። በቀጣይም ተመሳሳይነት ችግሮች እንዳይፈጠሩ ምክንታዊ የሆነ ወጣት ለመፍጠር የንግግር መድረኮች እየተዘጋጁ መሆናቸውን ጠቁሟል። የንግግር መድረኮቹ በአገርና በብሄር መንግስት ግንባታ ዙሪያ ያጠነጠኑ መሆናቸውን የጠቀሰው ወጣት አክሊሉ፤ በሰላማዊ መንገድ የትኛውም አስተሳሰብ ያለው ወጣት በመምጣት መነጋገርና መሟገት እንደሚችል አስረድቷል። በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሱ አገር የሚያፈርሱ ወሬዎችን ለማስቆም የንግግር መድረኮች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጿል። የአዲስ አበባ ብልጽግና ወጣት ሊግ ፕሬዚዳንት ወጣት አዕምሮ አዱኛ በበኩሉ፤ በምክንታዊ ወጣት የንግግርና የሙግት መድረክ የአገርና የብሄረ መንግስት ምስረታ ሁኔታ መነሳቱ ወጣቱ በጉዳዮቹ ላይ ያለውን አመለካከት ለማስተካከል እንደሚረዳ አስታውቀዋል። በአገሪቱ የአገርና የብሄረ መንግስት ግንባታው ገና ያላለቀና ብዙ የሚቀረው መሆኑን የጠቀሰው ወጣት አዕምሮ፤ የአገርና የብሄረ መንግስት ግንባታውን ለማጠናቀቅ ወጣቱ ምንያታዊ ሆኖ መንቀሳቀስ እንዳለበት ጠቁሟል። ህብረ ብሄራዊ አስተሳሰብንም ለማምጣት በውይይት የሚያምን ወጣት ሊፈጠር እንደሚገባም አመልክቷል። በመድረኩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር የሆኑት መምህር ዮናስ ዘውዴ ‹‹የአገርና ብሄረ መንግስት ግንባታ ምንነትና የወጣቱ ሚና›› በሚል መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል። በቀረበው መነሻ ጽሁፍ ላይም ውይይት ተደርጓል።
https://www.press.et/Ama/?p=39630
29d712cac4d423d41375aa922009ff02
d5376f65bc6405d807246889c3777dcb
በጎንደር የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በደማቅ ሥነ- ሥርዓት ለማክበር የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
 መሃመድ ሁሴን አዲስ አበባ:- በጎንደር ከተማ የሚከበረውን የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት ለማክበር የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ። በከተማዋ በሚደረገው ክብረ በዓልም የተለያዩ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀቱን መምሪያው ገልጿል። በጎንደር ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ኃላፊ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ባህላዊና ሐይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉንና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀዋል። የጥምቀት በዓል በሰላምና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው እየሰሩ መሆናቸውን የገለጹት አቶ አደባባይ በጸጥታ፣ በእንግዳ አቀባበል፣ በባህልና ቅርስ ትውውቅ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። ከበዓሉ ዝግጅት ስራዎች ቀዳሚው ስራ የጥምቀተ ባህሩን ቦታ የማስተካከል ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አደባባይ፤ ከዚህ አንጻር የቦታው የእድሳት ስራ መቶ በመቶ ተከናውኖ ውኃ የመሙላት ስራው ዛሬ እንደሚጠናቀቅና ለበዓሉ ዝግጁ እንደሚሆን አስታውቀዋል። እንደ አቶ አደባባይ ገለጻ፣ በበአሉ እለት የሚፈጠረውን መጨናነቅ ለመቀነስና ታዳሚው በጥምቀተ ባህሩ ዙሪያ ሳይጨናነቅ መስተናገድ እንዲችል የተለያዩ አዳዲስ አሰራሮች ተግባራዊ ተደርገዋል። ከእነዚህ መካከልም ታዳሚው ከአጥር ውጪ ሆኖ የበዓሉን ክዋኔ መከታተል እንዲችል በአራት አቅጣጫዎች ሰፋፊ ማሳያ ስክሪኖች ተዘጋጅተዋል። ከሀገር ውስጥም ሆነ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው የሚታደሙ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ለእነዚህ እንግዶች ማስተናገጃ የሚሆንና ቅርሱን በማይጎዳ መልኩ ተነቃቅለው የሚሰበሰቡና መወገድ የሚችሉ ደህንነታቸው አስተማማኝ የሆኑ የብረት ማያዎች ተሰርተዋል። በመሆኑም የመጡት እንግዶች በቀጥታ ሐይማኖታዊ ክዋኔውን ያለስጋት መከታተል እንደሚያስችላቸውም ነው ያስረዱት። በዩኒስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆና እሴት በሚጨምር መንገድ ማክበር ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊው፤ ይህን ታሳቢ በማድረግ ለጥምቀተ በዓሉ መዳረሻ ከጥር አንድ እስከ ዘጠኝ ድረስ የበዓል ሳምንት ተከብሯል። ለጎንደር ከተማ ሰላም ውሎ ማደርና ለመልካም አስተዳደሯ የሚሰሩና እየሰሩ የሚገኙ ታላላቅ ሰዎች፣ ወጣቶችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችም የጥምቀት በዓል በሰላም ያለአንዳች ስጋት እንዲከናወን የተሰለፉ በመሆናቸው ምስጋና ይቸራቸዋል ነው ያሉት ሃላፊው። በክብረ በዓሉ ላይ ከ200 ሺህ በላይ ታዳሚዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቀሱት አቶ አደባባይ፤ ንግድና ባዛርን ጨምሮ በርካታ ትዕይንቶች የሚከወኑበት ሆኖ በዓለ ጥምቀቱ በደመቀ ሁኔታ መልካም ትዝታን ጥሎ እንዲያልፍ በትኩረት መሰራቱንም አክለው ተናግረዋል። በባለፈው አመት በጎንደር ከተማ በተከበረው የጥምቀት በአል በጥምቀተ ባህሩ አካባቢ ከእንጨት የተሰራ ማማ ተደርምሶ በታዳሚዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።
https://www.press.et/Ama/?p=39628
988b6a1a692b07ac3cb3a6cddd6bdcad
430c8d9066097f3359b2f48bb53a1754
አካል ጉዳተኞችን ተደራሽ ያላደረገው ስፖርት
ስፖርት
 ስፖርት እድሜ ጾታና የሰውነት አቋም የማይለይ አካላዊ እንቅስቃሴና የሰው ልጆች መብት ምት ጭምር ነው፡፡ ይህም ማለት አካል ጉዳተኞችንም አካቶ የአካላዊና አእምሯዊ ጤናን ለመጠበቅ የሚያስችል ሚዛን ነው፡፡ ይሁን እንጂ በብዙ ሃገራት አካል ጉዳተኞችን በስፖርት ማሳተፍ አልተለመደም፡፡ በእርግጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ አካል ጉደተኞችን በስፖርታዊ እንቅስቃሴና ውድድር ማካፈል እየተለመደ የመጣው ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ እንቅስቃሴ እንደሚጠበቀው ጎልቶ ባለመታየቱ አካል ጉዳተኞችን ለማሰብ ሁሌም በየዓመቱ ህዳር ወር ላይ ይከበራል፡፡ አካል ጉዳተኞች በሁሉም እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ የሚገድባቸው ነገር አለመኖሩን ለማስገንዘብም ከሚከናወኑ ነገሮች መካከል አንዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ስፖርት ህይወትን በመልካም መንገድ ለመምራት የሚያስችል፣ ጡንቻዎችን የሚያጠነክር፣ ከጉዳት የሚጠበቅና ፈጥኖ ለማገገም የሚረዳ እንዲሁም ድብርትና ተያያዥ የሆኑ ስነ-ልቦናዊ ችግሮችን የሚቀርፍ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህም በመሆኑ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በየአራት ዓመቱ ጉዳት አልባ ስፖርተኞችን ካወዳደረ በኋላ አካል ጉዳተኞች የሚካፈሉበትን ‹‹ፓራሊምፒክ›› ያዘጋጃል፡፡ በመላው ዓለምም እንዲህ ዓይነት ውድድሮችና ቻምፒዮናዎች እየታዩ መጥተዋል፡፡ በኢትዮጵያም ይኸው እንቅስቃሴ አካል ጉዳተኞችን በስፋት ተደራሽ ባያደርግም አዲስ አበባን በመሳሰሉ ከተሞችና ሌሎች ክልሎች ላይ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡ ነገር ግን ስፖርታዊ ውድድርና አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ የተዘጋጁ ምቹ ሁኔታዎች በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ የሚለውን መፈተሽ አስፈላጊ ነው፡፡አቶ ንጉሴ ግደይ የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ሲሆኑ፤ በየዓመቱ የአካል ጉዳተኞች ቀንን በማስመልከት ስፖርታዊ ውድድር እየተካሄደ ዘንድሮ አስረኛ ላይ መድረሱን ይጠቁማል። የዚህ መርሃ ግብር መካሄድ አንዱ ምክንያት በከተማዋ የሚኖሩ አካል ጉዳተኞች አካል ጉዳት ከሌለባቸው እኩል በማንኛውም የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መሳተፍ እንደሚችሉ ግንዛቤ መፍጠርም ነው። ከእነዚህ ጉዳዮች መካከል አንዱ ስፖርት ሲሆን በዋናነት ለጤናና ለአካል ጥንካሬ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ አካል ጉዳተኛ ስፖርተኞችን ለማፍራትም የውድድሩ መካሄድ ጠቀሜታ አለው። አካል ጉዳተኞች ከአካላቸው አንዱ ቢጎድልም ዘወትር አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ ለቀሪው አካላቸው ብርታት ይሆናቸዋል። አሁን በዓለም ደረጃ እነሱን ያማከሉ የስፖርት አይነቶችም በርካታ ናቸው። እነዚህ ስፖርቶች ላይ ቢሳተፉ ለአካል ጥንካሬ ስነ-ልቦናቸው እንዲገነባ እንዲሁም በራስ የመተማመን ብቃታቸው እያደገ እንዲሄድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ስለዚህ አካል ጉዳተኞች በሕመም እንዳይጠቁ እንዲሁም ጉዳታቸው እንዳይባባስና ባለበት እንዲቆም እንደሚረዳቸውም ፕሬዚዳንቱ ያስረዳሉ። ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ አካላዊ ቁመና እንዲኖራቸውም ይረዳል። በእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸውና ከሰዎች ጋር በሚኖራቸው ግንኙነትም ደስተኛ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል። አዲስ አበባ ከመቆርቆሯ አንስቶ በፕላንም ሆነ በተግባራዊ ስራው አካል ጉዳተኞችን መሰረት አለማድረጋቸውንም ፕሬዚዳንቱ ያስረዳሉ፡፡ ይህም አካል ጉዳተኞችን ከፍተኛ ዋጋ እየስከፈላቸው ሲሆን፤ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችም ይህንን ማካተት የተጀመረው በቅርቡ ነው፡፡ ከመግቢያ መውጫዎች ጀምሮ ውስጣዊ ይዞታቸውና ቁሳቁሶቻቸውም ጭምር አካል ጉዳተኞችን ከግምት ያስገቡ አልነበሩም፡፡ በተመሳሳይ ወጣት ማዕከላትም ወጣት አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ አይደሉም፡፡ በዚህም ምክንያት እንቅስቃሴያቸውን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም ማህበሩ የተለያዩ ግንባታዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ አድርገው እንዲካሄዱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ይጠቁማሉ፡፡ በከተማዋ በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደመኖራቸው በጥናት ተደግፎ ተሻሽለው ሁሉንም ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን እንዲሁም ተደራሽ የሚሆኑበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 12/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37833
566eb44a3ff177a71729515f017b86c0
4f5d1647ca86aca61fd41ca40bcd7120
በሲሚንቶ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ አሁንም ችግሮች እንደሚታዩ ሚኒስቴሩ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
አስናቀ ፀጋዬ አዲስ አበባ፡- በሲሚንቶ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ አሁንም ችግሮች እንደሚታዩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሀገሪቱ የሚታየውን የሲሚንቶ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አመለከተ። በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የብረታ ብረትና ኬሚካል ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ዱጋሳ ዶንሳ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት ፣ሚኒስቴሩ ከስድስት ወር በፊት በምርትና በአቅርቦት በኩል የተፈጠረውን የሲሚንቶ እጥረት መንስኤ ለማጥናት በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮሚቴ አቋቁሞ ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም በሀገሪቱ ያሉ ፋብሪካዎች ለረጅም ጊዜ የሚቆሙ፣ ገሚሶቹም ያረጁና መለዋወጫ የሚፈልጉ፣ የገበያ ፍላጎታቸውም በሶስት ኢንዱስትሪዎች ላይ መሰረት ያደረጉ መሆናቸውንና አብዛኛዎቹ ግንባታዎችም በተመሳሳይ ወቅት መከናወናቸው ችግሩ እንዲጎላ ማድረጉን ለማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። የሲሚንቶ ምርት ፍላጎትና አቅርቦት ልዩነት እንደነበር መረጋገጡን አመልክተዋል። የሲሚንቶ ምርት አቅርቦትና ፍላጎት በኩል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተወሰነ ሲሚንቶ ከውጭ ሀገር እንዲገባ መፍቀዱን ጠቁመው ፣ ከዚህ በፊት ተይዞ የነበረው የሲሚንቶ ኢንቨስትመንትም እንዲለቀቅ መደረጉንም አስታውቀዋል። በአማራ ብሄራዊ ክልል ደጀን አካባቢ የሚገኘው አባይ የሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ እንዲፋጠንም የ20 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ተፈቅዶለት ግንባታው እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልፀዋል። ቀደም ሲል የነበረውን የሲሚንቶ የማምረት አቅም ለመጨመርም የመለዋወጫ እቃዎች ከውጭ ሀገር እንዲገቡ 85 ሚሊዮን ብር መመደቡንም ጠቁመዋል። የክረምቱን ወቅት ተከትሎ በሲሚንቶ ፋብሪካዎች ላይ ያጋጠሙ የተፈጥሮ አደጋዎችና በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች እጥረቶች እንዳሉ ሆነው እነዚህን ስራዎች በመስራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሲሚንቶ አምራቾች ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ በበጀት ዓመቱ የሀገሪቱን አጠቃላይ ሲሚንቶ የማምረት አቅም ለማሳደግ ከያዘው 85 በመቶ እቅድ ውስጥ 79 ያህሉን ማሳካት እንደቻለም ገልጸዋል። በነሃሴ ወር መጨረሻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሲሚንቶ የመሸጫ መቁረጫ ዋጋ መመሪያ አውጥቶ እንደነበርም አማካሪው አስታውሰው፤ ዋጋው እንደገበያው መሆን እንዳለበት ታምኖ መመሪያው እንዲነሳ መደረጉንም ጠቁመዋል። የዋጋ መመሪያው ከተነሳ በኋላም የሲሚንቶ ዋጋው እንዳልወረደ ነገር ግን መመሪያው እንዳያሻቅብ ማድረጉን የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩ አመልክተዋል። አምና የተመረተውን 8 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ ወደ 11 ሜትሪክ ቶን በማሳደግ በአቅርቦቱና በፍላጎቱ መካከል ያለውን ክፍተት ለመማጥብ እየተሰራ እንደሚገኝም አማካሪው አስታውቀው፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባስቀመጠው እቅድ መሰረት ባደረገው ጥረት ከዚህ ቀደም በሃይል መቆራረጥ ምክንያት ሲቆም የነበረውን የሲሚንቶ የማምርት አቅም ችግር ሙሉ በሙሉ መፍታቱን አመልክተዋል። ፋብሪካዎች ከውጭ የሚያስገቧቸውን የድንጋይ ከሰል የመሰሉ የኢነርጂ ምንጮችን በሀገር ውስጥ እንዲጠቀሙ ከመአድን ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጥረት መደረጉንም አማካሪው ጠቁመዋል። በዚህም የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን ሳይጨምር በቀን በአማካይ 240 ሺ ኩንታል ማምረት እንደተቻለም ጠቁመዋል። ሆኖም ምርቱ ከወጣ በኋላ የአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ አሁንም ችግሮች እንደሚታዩ አስታውቀዋል
https://www.press.et/Ama/?p=39629
c884aa80e5ae2e6ce836f84ffb7c3e45
6695d2a28da370b035b3aaac016b2d35
“የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ በሁለትዮሽ ስምምነቶች እና በጋራ የድንበር መድረኮች አማካኝነት መፈታት አለበት” – ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ ባሉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እና የጋራ የድንበር መድረኮች አማካኝነት በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ አሳሰቡ። ከሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የብሔራዊ ድንበር ኮሚሽን ተቀማጭነታቸው በሱዳን ለሆኑ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች፣ ቆንስላዎች እና የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ገለጻ አድርጓል። በዚህም ወቅት፣ አምባሳደር ይበልጣል ከዳግልሽ ተራራ በስተሰሜን ከሰፈራ እና ከእርሻ መሬት ጋር  በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ሁለቱን ሀገራት የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ እንዲመጣ የሚደነግገው እና በሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እ.ኤ.አ. ሐምሌ 18 ቀን 1972 የተደረገው የማስታወሻ ልውውጥ ከፍ ያለ ፋይዳ እንዳለው አስታውቀዋል።በ1972ቱ የማስታወሻ ልውውጥ በተቀመጠው መሰረት የጉዊን መስመርን ዳግም ማካለል ከመጀመሩ በፊት ከዳግልሽ ተራራ በስተሰሜን ከእርሻ መሬት እና ሰፈራ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የጋራ ልዩ ኮሚቴው ሁለቱን ሀገራት የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ ያካተተ ሪፖርት ለጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ማቅረብ እንደሚኖርበት አመልክተዋል።የጋራ ልዩ ኮሚቴው ሁለቱን ሀገሮች የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ ለማቅረብ ስምንት ዙር ስብሰባዎችን ቢያካሂድም ኃላፊነቱን ገና እንዳላጠናቀቀ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበር የጋራ ልዩ ኮሚቴ ስራ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጥቅምት ወር መጨረሻ ህግ ለማስከበር ወደ ትግራይ ክልል ያደረገውን ስምሪት እንደ መልካም አጋጣሚ መጠቀሙን አምባሳደር ይበልጣል አመልክተዋል። በዚህም የሱዳን ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት ንብረት ከመዝረፉ፣ ወታደራዊ እና የእርሻ ካምፖችን ከማቃጠሉ ባሻገር በኢትዮጵያውያን ላይ እስራት፣ ጥቃት እና ግድያ መፈጸሙ እንዲሁም በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ማፈናቀሉን አስታውቀዋል ፤ ይህ የ1972 የማስታወሻ ልውውጥን በግልጽ የጣሰ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።በሁለቱ እህትማማች ሀገራት ጸንቶ ከቆየው አጋርነት እና ትብብር መንፈስ በተቃረነ መልኩ የሱዳን ሰራዊት አጋጣሚውን በመጠቀም  የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ   ሰራዊት ለቋቸው የወጣ ካምፖችን መቆጣጠሩን ጠቁመዋል።ሱዳን በችግር ውስጥ በነበረችበት ጊዜ ሁሉ ኢትዮጵያ ከሱዳን ህዝብ ጎን መቆሟን ያስታወሱት አምባሳደር ይበልጣል፤ ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ በተጠመደችበት ወቅት ከሱዳን ሰራዊት የደረሰባት ጥቃት የሚገባት እንዳልሆነ አመልክተዋል።የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት ካልተወሰደ፣ ታይቶ የማይታወቀው የሱዳን ሰራዊት ተግባር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ብሎም የጋራ ድንበሩን ዳግም የማካለሉን ስራ የሚያወሳስብ እና ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦች እንዲሁም ለቀጠናው ከፍ ያለ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አስታውቀዋል።የኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ልዩነቱን ሁለቱ ሀገራት በገቧቸው ስምምነቶች እና ባሉ የጋራ የድንበር መድረኮች መሰረት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል። ለችግሩ ዘላቂ እልባት ለመስጠት ፣ የሱዳን ሰራዊት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፈጸመውን ወረራ በመቀልበስ በ1972ቱ የማስታወሻ ልውውጥ በተቀመጠው መሰረት ወደ ቅድመ-ኖቬምበር 2020 (እ.ኤ.አ.) መመለስ እንዳለበት አስታውቀዋል።ከዚህም በተጨማሪ ወደ ድንበር ዳግም ማካለል ከመገባቱ በፊት የጋራ ልዩ ኮሚቴው በ1972 የማስታወሻ ልውውጥ መሰረት ከዳግሊሽ ተራራ በስተሰሜን ከሰፈራ እና እርሻ መሬት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ሁለቱን ሀገራት የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ የማቅረብ ስራውን ማጠናቀቅ እንዳለበት አመልክተዋል ።የጋራ ድንበሩን ዳግም ለማካለል ሁለቱ ሀገራት ያቋቋሟቸው የጋራ የድንበር ኮሚሽን፣ የጋራ የቴክኒክ የድንበር ኮሚቴ፣ እና የጋራ ልዩ ኮሚቴ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እና ስራቸውን እንዲያጠናቅቁ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ጠቁመዋል ።
https://www.press.et/Ama/?p=39551
075b8875b71f3bbde24f0f56eda9afc0
b9b17c39bdd2fcfcf7b3bdaf958ba6ee
የጎዳና ላይ ሩጫ በቢሾፍቱ
ስፖርት
ቢሸፍቱ ፦የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከወራት መቋረጥ በኋላ የመጀመሪያውን አገር አቀፍ የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አካሂዷል፡፡ ለ7ኛ ጊዜ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው በዚህ ውድድር ላይም በአጠቃላይ ነጥብ በሴቶች ኦሮሚያ ፖሊስ በሴቶች ደግሞ መከላከያ ስፖርት ክለብ ቀዳሚ በመሆን አጠናቀዋል፡፡ የመከላከያዋ አትሌት ገበያነሽ አየለ በሴቶች ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ፤ የገባችበት ሰዓት ደግሞ 1:47.03 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የግል ተወዳዳሪዎቹ ብርሃን ምህረቱ እና ንግስት ሙሉነህ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን ፈጽመዋል፡፡ በወንዶች በኩል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ክለብ አትሌቱ ኃይለማርያም ኪሮስ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ አትሌቱ 30 ኪሎ ሜትሩን ለመሸፈን የፈጀበት ጊዜም 1:31.18 ሆኗል፡፡ 1:31.23 የሆነ ሰዓት ያስመዘገበው ፌዴራል ማረሚያ አትሌት ዴሬሳ ገለታ እና 1:32.08 በሆነ ሰዓት የገባው የመከላከያው ሙስጠፋ ከድር ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው በማጠናቀቅ የብርና ነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡ በ7ኛው የኢትዮጵያ 30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አጠቃላይ ነጥብም በሴቶች ኦሮሚያ ፖሊስ ስፖርት ክለብ እንዲሁም በወንዶች የመከላከያ ስፖርት ክለብ የዋንጫ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36908
b36f04eab06336c0a8ecfc1fd411ebc1
310b702c671cc8e10f98729a26736d74
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የቫሌንሺያን የግማሽ ማራቶን አሸነፈች
ስፖርት
አዲስ አበባ፡- አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በስፔን በቫሌንሺያ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸነፈች። በመካከለኛ እና የአጭር ርቀት ሩጫ የምትታወቀው አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ግማሽ ማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ ተወዳድራ አሸናፊ መሆን ችላለች። ጀግናዋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ18 ሴኮንድ ፈጅቶባታል።የገባችበት ሰዓት የቦታው አዲስ ክብረወሰን በመሆንም ተመዝግቧል። ውድድሩን በሁለተኛነት ያጠናቀቀችው ኬንያዊቷ ሼይላ ቼፕኪሩይ ስትሆን፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ሰንበሬ ተፈሪ ደግሞ ሶስተኛ ሆናለች። የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤቷ ሰንበሬ ርቀቱን ለመሸፈን የወሰደባት ሰዓትም 1፡05፡51 ነው። በእለቱ በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ደግሞ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ከ4-7 ባለው ደረጃ ተከታትለው ገብተዋል። በተመሳሳይ በእለቱ በተካሄደው የወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያዊው ብርሃኑ ለገሰ 2፡03፡16 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ደረጃን ወጥቷል።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36915
4e288290a19ea18a81a6bcca3d227c76
e637ae7ddadabed4d44b390722c63ad5
ከተፋቀርን አባይ ይገደባል ፤ እኛም እንጠግባለን
መዝናኛ
ተሰልፈን ቆመናል አምባሳደር አካባቢ ታክሲ ተራ።ታክሲዎች ተሳፋሪውን ተራ በተራ እየጫኑ ወደ መድረሻቸው ይጓዛሉ።ተሳፋሪው ሌላ ታክሲ እስኪመጣ ይጠብቃል።አንድ ከፍ የለ ድምፅ በሰልፍ የቆመውን ተሳፋሪ ትኩረት ስቧል።ሁሉም ወደ ተሰማው ድምፅ አማተረ።አንድ ወጣት አንዲት ህፃን ልጅ አቅፎ ተሳፋሪውን ቀረበና በእጁ የያዘውን በፕላስቲክ ማሸጊያ የተለበጠ ወረቀት ላይ የተፃፈ ጽሁፍ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያነባል፡፡የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚሰማ ምልዕክት አይነት የመሰለው አይንና ጆሮው መለሰ። ልጁ ቀጥሏል፤ ወረቀቶችን ይዞ ድመፁን ከፍ አድርጎ ያነባል። “ከተፋቀርን አባይ ይገደባል እኛም እንጠግባለን። እባካችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርስ ተፋቀሩ ያኔ ኢትዮጵያ ከፍ ትላለች፡፡” ሰውየው ከፍ ባለ ድምፅ ይናገራል። ይሄን እዚያ ለመሳፈር የቆመው ሁሉ ጆሮ ሰጥቶ ይሰማው ጀምር፡፡ከሰውየው አንደበት የሚፈልቁ ቃላት የተመጠኑና ሁሉም ሰው ሊያዳምጣቸው የሚገቡ በመሆናቸው እንዲቀጥሉ ተመኘሁ።ታክሲ ለመያዝ ተጣድፌ የነበርኩትን ያህል፤ ታክሲ እንዲዘገይ ተመኘሁ።ሰውየው በፈገግታ ተሞልቶ ስለ ፍቅር ታላቅነት ይሰብካል።“እባካችሁ ተዋደዱ ያኔ ለውጥ ይመጣል ተከባበሩ ያኔ ድል ይመጣል….” ስለ ፍቅርና መዋደድ ስለ አብሮነትና ፍቅር በማይጠገብ አንደበቱ ያስረዳል። እናንተዬ ፍቅርን የሚሰብክ አንደበት፣ እድገት የሚያፀና ምክር፣ ህብረትን የሚሰብክ ንግግር ምንኛ ይጥማል።ታክሲ መጣና ተሳፈርኩ። ስራ ረፍዶብኝ ነበረና ቦታውን ሳልወድ ለቀኩ።ሰውየው ግን ከአይምሮዬ አልጠፋም ደጋግሞ ይታሰበኛል።ይህ ሰው ስለዚህ ጉዳይ እንዲናገር ምን አነሳስቶት ይሆን? የጎደለን ፍቅር መሆኑ ከኛ ከፍ ባለ ሁኔታ ገብቶት መንገርስ ላይ ያደረሰው ምን ይሆን? ብዙ አሰብኩ፤ እዚያው ቦታ ሆኜ የጎደለን ፍቅርና መተሳሰብ እንጂ እውነትም አባይ አይደለም ችግርና መከራችንም መገደብ እንችላለን የምር!!።ስለ ፍቅር ብለን እርስ በርስ ብንተጋገዝ ስለ ሀገር ፍቅር ብለን ለሀገራችን በጎ ካበረከትን ምን ሊጎለን ይችላል?ምንም! ለራሴ መልስ ሰጠሁ፡፡ታክሲ ውስጥ ረዳቱ ሒሳብ ሲለኝ ከሄድኩበት ሰመመን ተመለስኩ።አውጥቼ ሁለት ብር ሰጠሁት።“አምስት ብር ነው፡፡” እ…ከሁለት ወደ አምስት ብር ያደገው ከመቼ ጀምሮ ነው? አትነጫነጭ ሁሉም ከፍሏል። “በአቋራጭ ነው የምሄደው ጨምር።” ሹፌሩ በመሀል ረዳቱን ለማገዝ ቃላት መወርወር ጀመረ። “አንተ ሰው ስራ አይደል እንዴ ምን እያልክ ነው ለምን ገባህ እየተናገርን አይደል የጫንክ” ተሳፋሪውን ዞር ብዬ አየሁ ፊቱን ሁሉም ቅጭም ሲያደርግብኝ መኪናው ሙሉ በኔ ያኩረፈ መሰለኝ፤ አውጥቼ ሰጠሁ።እስክሰጠው ድረስ በስድብ እያጥረገረገኝ ነበር። ኦህ! አምላኬ ትግስቱን ስጠኝ ትርፍ ከፍዬም ተሰድቤም ከባድ ነው።ሰልፉ ቦታ ወደነበረው ሰው በሀሳብ ተመለስኩ።“ እርስ በርስ እንከባበር እንዋደድ፣ ፍቅር አተን ነው የተቸገርነው እባካችሁ እንፋቀር፡፡” ንዴቴ ረገበ።ስለፍቅር ብዬ ዝም አልኩ።እኛ ግን ምን ነካን።ፍቅራችን የት ገባ።ረዳቱና ሹፌሩ ግን ያንን ሰው ሰምተውት ይሆን ሲጭኑ እዚያ ቦታ ነበሩና ሳይሰሙት አይቀሩም።ችግሩ አያደምጡትም…። ወዳጄ ስላለን ብቻ የፈለግነው አንበላም እኮ አረ እንዋደድ ተዉ…። አብዝቶ መስገብገብ ምንድነው እንዴ? ሆድ ልክ አልባ ይመስል ሰውን መበደል፣ ሰውን መግፋት የሰውን መሰብሰብ አስጭኖና ቋጥሮ መቃብር ይዞ ላይሄዱት ነገር ኧረ ነውር ነው…!!።ሰው ከተዋደደ በደህነቱ ንፁህ ህሊናውን ይዞ ሊሰፈር የማይችል ደስታን ይጎናፀፋል።ህሊና ቢስ ከሆነ ግን ሰው ከሚለው ስብዕና የራቀ ክፉ አውሬ ከመሆን አይድንም። በክፉ ስራው ሰዎችን ክፉኛ ያቆስላል፣ ከሚታሰበው በላይ ክፋትን ይለምድና ለሰዎች ሴራን ይጎነጉናል ስለሌላው አይጨንቀውም ስለማንም አይገደውም።ይህ ሰው እያደረ ‹‹ሰው ጤፉ›› ነው።ሰውየው ግን አይቶናል ፍቅር በማጣታችን መቸገራችን ከኛ በላይ ገብቶት ጎዳና ላይ መስበክ ተያይዞታል… እንደው በዚህ በጎ ተግባሩ እስከ መቼ ይቀጥል ይሆን? ታድሎ።ውስጡ የሚሰማው ሰላምስ ምን ያህል ይሆን? እኔ ምለው ሰላም ግን ይሰፈራል። ምን ያህል ነው ክብደቱ? ኦህ! ይከብዳል አቻ የሌለው ነገር በምን ሊሰፈር ይችላል።ሰውየው ውስጡ ያ ሰላም ሳስበው ቀናው። ወዳጄ ደስታህ ከእጅህ እንዳይወጣ ባንተ ሰው እንዲደሰት ትፈልጋለህን? ውስጥህ ሰላም ከሆነ ባትበላ ረሀቡ አይቀፈድድህም፣ ባትለብስ የሰው ፍቅር ትሞቃለህ፣ በሰው ክብር ምቾት ይሰማሀል።የትም ጋደም ብትል ለሽ… ብለህ የሚያስቀና እንቅልፍ ትተኛለህ።ሰዎች ብዙ ጊዜ ስግብግብ የሚሆኑት ፈፅሞ ቢያገኙም በማይጠቀሙበት አግኝተውም በማይደሰቱበት መሻታቸው ላይ ነው። ይሰበስባል፣ ላይ በላይ ደራርቦ ከምሮም ከልክ በላይ ያደልባል እድሜውን ሙሉ ያለ እረፍት የሱ ያልሆነን የማይገባውን የሌሎችን እየነጠቀ ባለው ላይ እየጨመረ ቀዶ እንኳን የማይጨርሰው ሀብት ያከማችና ሰላሙን ያጣል።ሰውየው ግን ከየት ተልኮልን ይሆን “ተፋቀሩ ተዋደዱ” ያለው ፍቅር ከኛ መንጠፉ ምን ያህል ቢገባው ነው።ፍቅር አተን እንጂ ምን ይጎለን ነበር።በተጓዘበት በደረሰበት ሁሉ የሚሰብከው መልካም ነገር ስንቶቻችን ይሆን ጆሮ ሰጥነት የምንሰማው ምን ያህሎቻችንስ ነን ከልብ የምናዳምጠው።ዛሬ ላይ የምነሰማው መልካም ነገር ጎሎ ሳንፈልግ የሚቀርበን መጥፎ ዜና በተበራከተበት ለሁሉ ጉዳት መፍትሄ የሚሆነው ፍቅር ማጣታችን ዋንኛው ምክንያ ነው።ፍቅር ውስጥ የማይፈታ ችግር የማይታለፍ ፈተና የለም።መከባበር ውስጥ የማያስችል ጉዳይ የማያግባባ ሀሳብ አይኖርም ግን በተቃራኒው ከኛ ፍቀር ከራቀ ጥላቻ ቦታውን ይወርስና የማያርቅብን ጉዳይ አይኖርም፡፡አዲስ ዘመን የካቲት 30/2012ተገኝ ብሩ
https://www.press.et/Ama/?p=28753
32b6162afa720ddaa24903b80441e2c7
0634a8d957187a25e09eacba777eaf5e
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔን አካሄደ
ስፖርት
አዲስ አበባ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ትናንት አካሂዷል፡፡ ያለፈው ዓመት ባጋጠሙ በርካታ ውጣ ውረዶች ስፖርቱ አሉታዊ ተጽእኖ ቢደርስበትም የተሻለ አፈጻጸም የተመዘገበበት መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውን የካፍ አካዳሚን በማስጠገን ለአገልግሎት መብቃቱ፤ ፌዴሬሽኑ ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ ታድጓል። የአህጉርና ዓለም አቀፍ ግንኙነትን በማጠናከር ረገድም ጠንካራ ሥራ በመከናወኑ ኢትዮጵያ በሴካፋ የመሪነት ቦታ ማግኘቷም በጉባኤው ላይ መነሳቱን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በድረ-ገጹ አስነብቧል፡፡ በጉባኤው በቀረበው የ2012 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት ላይም ፌዴሬሽኑ የገንዘብ አቅሙን ማሳደጉ ተገልጧል፡፡ ለዓመታት የክለቦች ጥያቄ የነበረውን የሊግ ካምፓኒ ምስረታ እውን ማድረጉንም እንደ ስኬት ተነስቷል፡፡ በቀረበው ሪፖርት እና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይም በጉባኤው አባላት ውይይት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም የሲዳማ ክልል የጉባኤው አባልነት ጥያቄን ተቀብሎ በማፅደቅ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ በተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ለመወያየት እና ለማጽደቅ በሀዋሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚካሄድ በመወሰን ጉባኤው መጠናቀቁን በዘገባው ተመላክቷል።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36914
dc0014c798abfb279f5043c197e6519a
b53b76d935ddc0241d056dbf9e648942
የብስክሌት ኮርቻ ቀበኛው
መዝናኛ
ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል እንዲሉ አመለኛ ሌባ ያገኘውን ከመስረቅ ወደኋላ አይልም። ታዲያ ሌብነት ሁሌም አይቀናምና አንድም በሰዎች መደብደብን ባስ ሲልም በፖሊስ መያዝና ለአስር መዳረግን ያስከትላል። ሌባ ከትንንሽ እቃዎች አንስቶ አስከ ከፍተኛ ውድ እቃዎች ድረስ ፤ ከትንሽ አስከ ከፍተኛ ገንዘብ ድረስ ይሰርቃል። አንዳንድ ሌባዎች የሚሰርቋቸው እቃዎች ግን እንግዳና ያልተለመዱ ሆነው ‹‹ምን ሊያደርግላቸው ነው?›› የሰረቁት ያሰኛሉ። ከሰሞኑ ኦዲቲ ሴንትራል ይዞት የወጣው መረጃም ይህንኑ ያመለክታል። ነገሩ እንዲህ ነው፤ የ57 ዓመቱ ጃፓናዊ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ሂሮዋኪ ሱዳ ከወራት በፊት በአንድ የባቡር ጣቢያ በርካታ ብስክሌቶች በሚቆሙበት ቦታ ግምታቸው 8 ሺ የጃፓን የን ወይም 75 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ የሁለት ብስክሌቶች ኮርቻ ወይም መቀመጫ ሲሰርቅ በቅኝት ካሜራ በመታየቱ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። ሱዳ ድርጊቱን መፈ ፀሙን ያመነ ሲሆን ባል ተለመደ ሁኔታ የብስ ክሌት ኮርቻዎችን ወይም መቀመጫዎችን ያውም ለሃያ አምስት ዓመታት ሲሰርቅ መቆየቱን ለፖሊስ አስታውቋል። የሚገርመው ደግሞ የሰረቃቸውን እቃዎች በሙሉ በአንድ ላይ በመሰብሰብ በሚ ማርክ መልኩ እንዳስቀ መጣቸውም ለፖሊስ መና ገሩ ግርምትን ፈጥ ሯል። ‹‹የብስክሌት ኮርቻ ዎችን መስረቅ የጀመርኩት ከዛሬ ሃያ አምስት ዓመት በፊት በቶኪዮና ኦሳካ ነው። ስርቆቱን የጀመርኩትም በሥራ የሚገጥመኝን ውጥረት ለመቀነስ በሚል ሲሆን፣ በኋላ ላይ ግን ኮርቻዎቹን ሰርቄ መሰብሰብ ስጀምር ደስታን አጎናፅፎኛል›› ሲል ሶዳ ለፖሊስ ቃሉን ሰጥቷል። የ57 ዓመቱ የከባድ መኪና አሽከርካሪ የሚሰርቃቸውን የብስክሌት ኮርቻዎች ተከራይቶ ወደሚያስቀምጥበት ቦታ ፖሊሶችን መርቶ አሳይቷል። በቦታው 5 ሺ 800 የሚሆኑና ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት የተሰረቁ ኮርቻዎች መገኘታቸው ተረጋግጧል። የአሽርካሪነት ሞያውን በመጠቀም በጃፓን የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የብስክሌት ኮርቻዎችን ሲስርቅ መቆየቱንም ለፖሊሶች አስረድቷል። ከዚህ በፊትም ሌላ ጃፓናዊ በተመሳሳይ በአንድ ዓመት ውስጥ 159 የሚሆኑ የብስክሌት ኮርቻዎችን በመስረቅ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበርም መረጃው አስታውሷል። አዲስ ዘመን መጋቢት 1/2012አስናቀ ፀጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=28828
fa0f716b47584c419d2e18151765ee74
9be60c81f6d9b633b7259fa832d0c1cd
የእብድ ገላጋይ ያቀብላል ድንጋይ
መዝናኛ
 በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተፈተነች ትገኛለች፡፡ በቫይረሱም ምክንያት ሰው እንደ ቅጠል በእያንዳንዱ ሰከንድ ይረግፋል። በሽታው በትንፋሽና በንክኪ በቀላሉ የሚዛመት መሆኑ ደግሞ ስርጭቱን በቀላሉ ለመቆጣጠር አዳጋች አድርጎታል፡፡ ታዲያ በዚህ የዓለማችን ስጋት በሆነው በሽታ ስጋት የገባው አባወራ ራሱንና ልጆቹን ለማዳን ያደረገው ድርጊት የሰሞኑ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኖ ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው ግለሰቡ የሊትዌንያ ነዋሪ ሲሆን በኮኖራ ቫይረስ ተይዛለች በሚል ስጋት ባለቤቱን መታጠቢያ ቤት በማስገባት ቆልፎባት፤ እንዳትወጣም የከለከላት ሲሆን ይህ ድርጊቱም ዓለምን ጉድ አሰኝቷል፡፡ ባሳለፍነው የካቲት ወር አጋማሽ በሊትዌንያን ቪሊኒዩስ የሚገኝ ፖሊስ በአካባቢው ከሚገኝ አንድ ስፍራ አስጨናቂ የስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል፡፡ ለፖሊስ የደረሰው ጥሪም በመኖሪያ ቤቷ መታጠቢያ ቤት በባልዋና በሁለት ልጆቿ የተቆለፈባት አንድ እንስት ጥሪ ነበር፡፡ ወደ ጥሪው ቦታ ያመራው የፖሊስ ቡድን ወደ ትዕይንቱ ቦታ ሲደረስ ድርጊቱን የፈፀመው አባወራ ያለአንዳች ፍርሐት የመኖሪያ ቤቱን በር በመክፈት ሚስቱን በመታጠቢያ ቤት እንደቆለፈባት በመግለጽ ይህንንም ያደረገው ከኮሮና ቫይረስ ጥቃት ራሱንና ልጆቹን ለመከላከል አስቦ ያደረገው መሆኑን ተናግሯል፡፡ የአካባቢው ብሄራዊ ፖሊስ ቃል አቀባይ ራሙናስ ማቶኒስ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት “አባወራውና ሁለቱ ጎረምሳ ልጆቹ እማወራዋን ከመታጠቢያ ቤት እንዳትወጣ የከለከሏት በኮሮና ቫይረስ ተጠቅታ ሊሆን እንደሚችል እንደምትጠረጥር ስለነገረቻቸው ነው፡፡ ሴትየዋ ወደ ጣሊያን ሄዳ በነበረበት ወቅት ከወደ ቻይና ከመጡ ሰዎችም ጋር ተገናኝታ ስለነበር በዚህም ምክንያት በኮሮና ቫይረስ ተጠቅታ ሊሆን እንደሚችል ስጋት እንደገባት ለባለቤቷ ታጫውተዋለች፤ታዲያ በጉዳዩ ላይ ቀልድ የማያውቀው አባወራም ነገሩን በቸልታ አልተመለከተውም አባወራው በአስቸኳይ አንድ የህክምና ዶክተር ጠርቶ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅታ ሊሆን እንደሚችል ስጋቱን ነገረው። ሀኪሙም “የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል” እንደሚባለው ሙያውን ዘንግቶ ለሰውየው ሴትየዋን ገለል እንዲያደርጋት ይመክረዋል፡፡ አባወራውም የሀኪሙን ምክር በመስማት ከሁለት ልጆቹ ጋር በመሆን እማወራዋን በመታጠቢያ ቤት በማስገባት ቆለፉባት፡፡ ሰውየው እንደተናገረው በሚስቱ ላይ አንዳች ጉዳት ለማድረስ ወጥኖ የሠራው እንዳልሆነና እንዲያው ዝም ብሎ የዶክተሩን ምክር ተከትሎ ሚስቱ በሽታውን እንዳታሰራጭ ለመከላከል ያደረገው መሆኑን ገልጿል፡፡ በድርጊቱ የተከሰተ ምንም ጥቃት የሌለ ሲሆን በሴትየዋም በኩል የቀረበ ቅሬታ የለም፤ስለዚህ ፖሊስ አምቡላንስ በመጥራ ሴትየዋ በሽታዋን እንድትመረመር ወስዷታል፡፡ በመጨረሻ የባልየው ጭንቀትና ፍራቻ መሠረት የለሽ መሆኑንና ሴትየዋም ተመርምራ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆኗ ተረጋግጧል፡፡ ቢሆንም ግን ይህ ክስተት ኮቪድ 19 ምን ያህል ሰዎች ላይ ተፅዕኖ እያደረሰ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ሰዎች ራሳቸውን ከበሽታው ነፃ ለማድረግ የትዳር አጋራቸውን መታጠቢያ ቤት ውስጥ ቆልፈው መውጣት ከጀመሩ ጉዳዩ ምን ያህል አሳሳቢ መሆኑን ያሳያናል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 1/2012 ኃይለማርያም ወንድሙ
https://www.press.et/Ama/?p=28831
91277392701320c5cb323ac1d8563c95
b77c8ba81f69726e50f4a3aff664e0ec
ለአዳኞች እጅ የሰጠው ግዙፉ ተኩላ
መዝናኛ
በሩሲያ በረዷማ አካባቢዎች ላይ በሚገኙ ደኖች ውስጥ ተኩላዎች በብዛት ይኖራሉ። እነዚህ ተኩላዎች ታዲያ በጫካ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች እንስሳትን ይመገባሉ እንጂ ለአካባቢው ነዋሪዎች ብዙም ስጋት አይሆኑም። በሩሲያ አንዲት አነስተኛ መንደር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ግን በአንድ ግዙፍ ተኩላ ስጋት ገብቷቸው ሲቸገሩ ቆይተው ሰሞኑን እፎይ ብለዋል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ፅፏል። ነገሩ እንዲህ ነው፤ በሩሲያ አሌክሳንደሮቭካ በተሰኘች አንዲት አነስተኛ መንደር ውስጥ የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች በተደጋጋሚ ሲያስጭንቃቸው የቆየው አንድ ተኩላ በአዳኞች መመታቱ ሪፖርት ይደረጋል። እንዲህ መንደሪቷን ሲያምሳት የቆየው ተኩላ በአዳኞች መመታቱ ነዋሪዎችን እፎይ ያሰኘ ቢሆንም፣ ተኩላው ባለፉት አርባ አመታት በአካባቢው ውስጥ ያልታየ መሆኑና በዚህ የክረምት ወቅት ሰዎች በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ላይ መግባት መጀመሩ አነጋጋሪ ሆኗል። ተኩላው ወደዚች መንደር መግባት ከጀመረ ወዲህ ብዙ ውሾች ቅርጥፍ ጥፍ ተደረገው ተብልተዋል። ከሃያ በላይ የሚሆኑ ላሞች፣ በጎችና ፈረሶችም የዚሁ ተኩላ ሲሳይ ሆነዋል። ተኩላዎች፣ መምጣታቸውን ለማንቃት በየቤቱ በጠባቂነት የተያዙ ውሾችም ይህንኑ ተኩላ በመፍራት ድምፃቸውን አጥፍተዋል። ከዚህ ሁሉ ውድመት በኋላም ተኩላው በአካባቢው አዳኞች በመከራ የተገደለ ሲሆን፣ አዳኞች ተኩላውን ከበው ለማንሳት ሲታገሉ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ትስስር መለቀቁን ተከትሎ ተኩላው በግዙፉነቱ ወደር ያልተገኘለት መሆኑ ብዙዎችን አስደንቋል። ‹‹ውሾች እንኳን ሊጮሁ ራሳቸውን ነው የደበቁት፤ ምንም አይነት የውሾች ጩኸትም አይሰማም። ለምን እንደሆነ ባላውቅም ምን አልባት ውሾቹ ተኩላውን ፈርተው ሊሆን ይችላል›› ሲል አንድ የመንደሪቷ ነዋሪ ተኩላው ከመገደሉ በፊት የነበረውን ሁኔታ ገልጿዋል። የአካባቢው አዳኞች በኋላ እግሩ ሲቆም መካከለኛ ቁመት ካለው ሰው ጋር እኩል የሚሆነውን ይህን ግዙፍ ተኩላ ለመግደል ሲዘጋጁ የመንደሪቷ ነዋሪዎች ፍርሃት ነግሶባቸው እንደነበር በዘገባው ተመላክቷል። ጉዳዩ በማህበራዊ ትስስር ገፅ መለቀቁን ተከትሎ ደግሞ በርካቶችን አስገርሟል። የዚህ ግዙፍ ተኩላ መገደል በኢንተርኔት የብዙሃንን ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ቢሆንም፣የመንደሪቷ ነዋሪዎች ቤታቸውን በከበበው ደን ውስጥ አሁንም የዚሁ አይነት ግዙፍ ተኩላ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት እንዳደረባቸው በዘገባው ተመላክቷል። አዲስ ዘመን መጋቢት 15/ 2012 አስናቀ ፀጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=29010
21e86a8e2275084826169e59b140db12
336e37b4196b0d6f32aab1da2478c1ce
ባይሆን ጥሩ ነበር፤ ግን ሆነ
መዝናኛ
ሳንፈልግ የሚያስፈግጉን፤ ሳንወድ የሚያስቁን ብዙ ሁነቶች በሰሞኑ በውዝግብ ውስጥ አሳልፈናል። እርግጥ ነው እንደ ማህበረሰብ ለጉዳዮች ያለን ግንዛቤ እጅግ ያነሰ ነው። የኛ ያልሆኑ ነገሮች ደግሞ አዳዲስ ለሚፈጠሩ ጉዳዮች ማለቴ ነው። እንጂማ ስለኛ ከኛ በላይ የሚያውቅ እንደሌለ ዘንግቼው አይደለም። እናም ከሳምንት በፊት ወደ ሀገራች ገባ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ብዙዎቻችንን በሀሳብ ኮርኩሮናል። እጅግ ደጋጎችን አይተን “እናንተማ በርክቱልን፤ ስለኛ ህይወት ጣዕም ቅመሞች ናችሁና ጤናችሁ ይብዛልን” እንዳልነው ሁሉ፤ አንዳንድ ጉደኞች “ጉድ!” የሚያስብል ተግባር ውስጥ ገብተው መክረማቸውም ተሰምቷል። እርግጥ ተቆንጥጠዋል አሉ። ቁንጥጫው ተገቢ ነው ግን አይበቃቸውም። የምር በወገን ላይ ለጨከነ ቁንጥጫ ያረካል? በፍፁም። አቤት አቤት ጭካኔ! በወገን ላይ የምር ይደረጋል? ወይ ዘንድሮ! ባይሆን ጥሩ ነበር ወገን፤ መሆን የሌለበት ግን ሆኗል። ባንሰማ ጥሩ ነበር፤ ግን ደግሞ ባንወድም ሰማን። ባይደረግ መልካም ነበር፤ ግን ደግሞ ተደረገ። ስናሳዝን ግን! መተዛዘንናችንንና መተሳሰባችንን ማን ቀምቶን ይሆን? ማንስ ለውጦብን ይሆን? ግን የእኛ የምንለውን እኛነታችንን በ“እኔ” ቀየረብን። “እኔ ከሞትኩ…..ን” ከኛ ጋር ያጋባው ግን ማን ነው? ከዚህ ጋርማ መፋታት አለብን። ጉድ ነው! ይሄ ለማመን ይከብዳል። ወገን ስለወገን ሳይሆን ስለራስህ ብለህ ሰው ሰው ሽተት፤ ካልሆነ ኑሮህ ጣዕም ያጣል። በሰዎች ችግር ለመክበር መጣር ከባድ ነው። በሰዎች ስጋት ነግደህ፤ ለሽሮ የሚጋፋን ረግጠህ ቁርጥ ስጋ ለመብላት መስገብገብ የምር በጣም ያስተዛዝባል። ሰሞኑን የሆነው ይህ ነው። ምስኪኑ፤ የማያውቀው “መዓት መጣብህ” ተብሎ ወደአንተ ዘንድ ለመሸመት ደጅህ የመጣን አቅመ ቢስ ገፈተርክ አሉ። በደህናው ጊዜ ለአንተ መለወጥ የተጋውን ሚስኪን በክፉ ቀኑ ክፉ ሆንክበት ሲባል ለሰሚው ግራ ሆኗል። ኧረ በፍጹም በዚህ ሰዎች በፍቅር በኖሩበት ሀገር ነጋዴ ህዝቡን በክፉ ቀን አይገፋም፤ ሰዎች በአንድነት ጠብቀው ባቆዩት ፍቅር እንዳይበጠስ ሆኖ በተጋመደበት ምድር ነጋዴ በህዝብ ላይ አይጨክንም፤ መነጠል በሚከብድበት፤ መነጠል በማይቻልበት ማህበረሰብ እንዲህ አይደረግም ተብሎ ሙግት ቢገጥሙም እውነቱ የተገላቢጦሽ መሆኑ አስፈርቷል። አንዳንዴ ሳይፈልጉት የሚውጡት ሂስ አለ። ነጋዴ ሆይ “ዋጥ!” ተብለሀል ዋጠው። ይህን አድርገኸው ከሆነ ከባድ ነው። በወገንህ ላይ ጨክነህ ከነበር አጉል ነው። ይህ እውነት ሳይፈልጉትም የመረረ ነው። ወዳጄ! እሰኪ አስበው ምንአልባት የዚህ ህዝብ ቀና መሆን አንተን ጠብቆሀል። የዚህ ህዝብ እያንዳንዱ ጥረት አንተን ጠቅሞሀል። አይንህን አስፍተህ ከተመለከትክ በምንም መልኩ በራስህ የያዝከው አንዳች ነገር እንኳን የለም። ስለራስህ ብታስብ ይህንን ለማድረግ ባላሰብክ፤ ሌላውን ተወው። ስለራስህ ምቾት፤ ስለራስህ ደስታና የተቃና ኑሮ ሌላውን ማኖር ግድ ይልሀል። ወዳጄ ደሀው እኮ ላንተ ውበት ነው። ከመሀሉ ስትቆም አንተን የሚያስጌጥ፤ ደፋ ቀና ብሎ፤ ብዙ አምርቶልህ ትንሽ ጎርሶ የሚያድር፤ ብሎኬት ተቀባብሎ ቤትህን የሚያንፅ፤ ቀለም አስቀስሞ ልጆችህን በእውቀት የሚያበለፅግ፤ ጠዋት ቤትህን አንኳኩቶ ቆሻሻህን የሚያፀዳ፤ የእርሱ መኖር ነው አንተን የሚያኖርህ! እንዲያው ሌላው ይቅር፤ “ማነህ… “ እያልክ የፈለከውን የምታዝዘው፤ “እዚያ ጋ አምጣልኝ እንጂ!” እያልክ የምትጣራው “ሎሌ” ላንተ እንዴት ጠቃሚ መሆኑን ዘነጋህ? ያለ መስተንግዶ መኖር አይከብድህም፤ እንዲያው “ጌታው ምን ልታዘዝህ? ምን ጎደለህ?” የሚልህን አትወድድም? እና እንዴት ብለህ በዚህ ሰው ጨከንክ ታዲያ? ግን ካንተ ጋር በገቢው አነስ የሚል ከጎንህ ከሌለ በምን ትኮፈሳለህ? እንዲያው በሞቴ ወዳጄ ለአንተ ዛሬ እዚህ ላይ መቆም መሰረት ከእስርህ ያለው ያ ወገንህ መሆኑን እንዴት ዘነጋኸው? ኮሮና የሚባል ጉድ መጣልህ ፤እራስህን ጠብቅ፤ መጠበቂያውም እኛውልህ ተብሎ የተነገረውና እራሱን ለማዳን ለሸመታ ወዳንተ የመጣን ምስኪን “አምጣ” እያልክ ስትነጥቀው የዋልከው ገንዘብ እኮ እረፍት አይሰጥህም። ጥረው ግረው የበሉት ነው የሚጣፍጠው፤ በእርግጥ ጣዕም የሚገባህ ከሆነ ያ ነው ትክክለኛ ጣዕም የሚፈጥር፤ ያ ነው የራስ ከሆነ ልፋት ተገኝቶ ሲበሉት የሚጥም፤ ከወገንህ መንጭቀህ የሰበሰብከውን ገንዘብ መሽቶ ጣትህን ከምላስህ ምራቅ እያስነካህ ስትቆጥረው ቫይረሱን ወደ ውስጥህ ብታዘልቀውስ? ከባድ ነው! የተያዝክበት መንገድ እንኳን አጉል ነው። ወዳጄ ትላንት የጨከንክበት ወገንህ መታመምህን ሰምቶ የሚጠይቅህ ይመስልሀል? በፍፁም! ሰው የእጁን ፍሬ ነው የሚበላ፤ ስለ መልካም ውለታህ መልካም ምላሽ ጠብቅ፤ ካልሆነ ግን በተቃራኒው ነው። ሁሉም የተሰፈረ ልኬት አለው። ከዚያ ውልፍች አይልም። ስላግበሰበሰ ከተፈቀደልት አምልጦ ትርፍ አያሻምድም፤ ስለተወው የርሱ የሆነ ድርሻ በሌላ አይቀማም። ወገን ስለራስህ ምቾት ለሌሎችን ምቹ ሁን። ስለራሰህ መልካም ፍፃሜ ስትል መልካምነት ላይ አዘውትር! ሰው በቁርጥ ቀን ይለያል፤ ሳንፈልግ የለየናችሁ እነአጅሬ፤ ያደረጋችሁትን ባናውቅ መልካም ነበር። እናንተም ይሄንን ባታደርጉ ምንኛ በወደድን፤ ተግባር እኮ ጥላ ነው በሄዱበት ሁሉ የሚከተል፤ ሲበርድ ፀሀይ ሆኖ የሚያሞቅ፤ ሲሞቅ ምቾትን የሚፈጥር በጭለማ የፋኖስን ያህል ብርሀን የሚፈነጥቅ፤ የምር መንገድ የሚገራው በበጎነት ነው። ዛሬ ነገ ላይ ታሪክ ነው። ያ ታሪክ፤ ያ ትውስታ ነገ ላይ ሲገለፅ ሁለት መልክ አለው። አንዱ በተወሳ ቁጥር የሚያስፈግግ፤ ሌላኛው ደግሞ ምነው ባልተነሳ፤ አሁን የምር ይህንን የሰው ልጅ ያደርገዋል የሚያስብል፤ ከመጀመሪያው ማህደር ውስጥ እራስን ማስገኘት ነው። ቸር ያሰማን! አዲስ ዘመን መጋቢት 14 /2012 ተገኝ ብሩ
https://www.press.et/Ama/?p=28957
00d26359f62ba5cfd4e52e17efa83cb6
b3d84f41241974feeae15d9a25cca6a3
ስዕልን በሁለት እጅ
መዝናኛ
አለማችን ከሊዮናርዶ ዳቪንቺ እስከ ፓብሎ ፒካሶ ድንቅ ሰአሊያንን አፍርታለች። አሁንም በየሃገራቱ በተለያዩ የስነ ስዕል ዘርፎች የስዕል ጥበባቸውን ለዓለም የሚያሳዩ ዝነኛ አርቲስቶች አልጠፉም። ሃገራችንም ብትሆን ሰዓሊና ባለቅኔ ገብረ ክርስቶስ ደስታን ጨምሮ በርካታ አንጋፋና ወጣት የስነ ስዕል ጥበበኞችን አፍርታለች። ሰዓሊያን በተለያየ የስነ ስዕል ዘርፍ የየራሳቸውን የአሳሳል ዘይቤ በመከተል የስዕል ስራቸውን የሚሰሩ ቢሆንም፣ አብዛኞቹ ቀለም ነክረው በዘረጉት ሸራ ላይ የሚቀቡት በአንድ እጃቸው ብቻ ነው። ይሁንና አንዳንድ በተፈጥሮም ሆነ በአደጋ ሁለት እጃቸውን ያጡ ሰአሊያን በአንድ እጃቸው ብቻ ብሩሽ ወይም እርሳስ መጨበጥ ስለማይችሉ ስዕል ለመሳል ሁለቱንም እጆቻቸውን ይገለገላሉ። ኦዲቲ ሴንትራል ሰሞኑን ከወደ አሜሪካ ይዞት ብቅ ያለው መረጃ ደግሞ ሁለት ጤነኛ እጆችን በአንድ ጊዜ በመጠቀም ስዕል መሳል እንደሚቻል ያረጋግጣል። መክሊት ካልሆነና ከላይ ካልተሰጠ በቀር ስዕልን እንዲሁ በቀላሉ በአንድ እጅ እንኳን ለመሳል ያስቸግራል። በሁለት እጅ በአንድ ጊዜ ሲሆን ደግሞ ጭራሽ የማይታሰብ ይሆናል። ለአሜሪካዊው አማተር ሰአሊ ግን ይህ እጅግ የቀለለ ጉዳይ ነው ይላል የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ። እንደ ዘገባው፤ በአሜሪካ ዴትሮይት ግዛት ጠበቃና አማተር ሰአሊው ኮሊን ዳርክ የተለያዩ ቀለሞችን በመጠቀም ጠለቅ ያሉ የስዕል ጥበብ ስራዎችን በሁለት እጆቹ በአንድ ጊዜ የመስራት ችሎታው ረፍዶም ቢሆን፣ የብዙሃንን ትኩረት ለመሳብ በቅቷል። የ42 አመቱ ይህ ጎልማሳ ከታዋቂ የፊልም አክተሮችና ታዋቂ ሰዎች ጀምሮ የተለያዩ እንስሳትንና ተፈጥሮን የሚያሳዩ ስዕሎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የስዕል ስራዎችን ሁለቱን እጆቹን በአንድ ጊዜ በመጠቀም ለማሳል ብዙ አልከበደውም። ኮሊን ይህን በሁለት እጅ በአንድ ጊዜ የመሳል ጥበቡን ሚስጥር ለረጅም ጊዜ ደብቆ ካቆየው በኋላ በአነቃቂ ንግግር ተነሳስቶ የሚሰራቸውን ስዕሎች የሚያሳዩ ፎቶዎችና የቪዲዮ ክሊፖች በኢንስታግራም መልቀቅ ከጀመረ ወዲህ የብዙሃንን ትኩረት ለመሳብ ችሏል። ‹‹የተደረገልኝ ቀና ድጋፍ የስዕል ስራዎቼን ይበልጥ እንድሰራና ችሎታየን እንድጠቀምበት አነሳስቶኛል››ሲልም ተደምጧል። ‹‹በርግጥ የቀኝ እጄ ሲደክም ስዕል ለመስራት የግራ እጄን እጠቀማለሁም›› ብሏል። በአምስት አመቱ ስዕል መሳል የጀመረው ኮሊን ይህን ችሎታውን በመጠቀም በሆሊውድ ፊልም የሚታወቀውን የሃሪ ፖተር ገፀባህሪ፣ ሊዮናርዶ ዳቪንቺን፣ ኮቤ ብሪያንትንና ሩድ ባድረ የተሰኙ ዝነኞችን ከሰራቸው የስዕል ስራዎቹ ውስጥ ይጠቀሳሉ። በእንዲህ አይነቱ ስዕል የመሳል ጥበብ ኮሊን የመጀመሪያው ሰው እንዳልሆነ ዘገባው ገልጾ፣ከዚህ በፊትም ራጃሴና የተሰኘች ኔዘርላዳዊት በሁለት እጆቿ በአንድ ጊዜ ስዕል እንደምትሰራ መዘገቡን አስታውሷል። የስዕል ስራዎቿ በአንዳንድ ወገኖች የውሸት ናቸው በሚል የተፈረጁ ቢሆንም፣ይህን የሚያረጋግጥ ትክለኛ ማስረጃ ግን እስካሁን እንዳልተገኘ ዘገባው አመልክቷል። አዲስ ዘመን መጋቢት 15/ 2012 አስናቀ ፀጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=29017
7896cf55f1fedc0bd71063c4e7058eb6
1e4b5bcfc4318fb181c6d1baef25bc3a
ለአፍሪካ አገራትም ተምሳሌት የሆነው የኢትዮጵያ ስፖርት
ስፖርት
ብርሃን ፈይሳየአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) የዘንድሮ መዳረሻውን ኢትዮጵያን ማድረጉ ይታወቃል፡፡ በኮሚቴው ምስረታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በነበራትና የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ ጠቅላላ ጉባኤውን ከማካሄዱም ባሻገር ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በአህጉሩ ከፍተኛ የሆነውን የስፖርት የክብር ሽልማት አበርክቷል፡፡ ኮሚቴውና አባላቱ አጠቃላይ የነበራቸውን ቆይታ በተመለከተም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ለአዲስ ዘመን አብራርተዋል፡፡በመሪዎች ደረጃ ይህንን ሽልማት ያገኙ ጥቂት መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ጠቅሰው፤ ይህም ለኢትዮጵያ ስፖርትና ለስፖርቱ ቤተሰቡ ትልቅ የምስራች መሆኑንም ይጠቁማሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለሽልማት ሊያበቋቸው የቻሉና አርአያ ሊያደርጓቸው የሚችሉ መነሻዎች መኖራቸውም ያብራራሉ፡፡ እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ፤ በሀገሪቷ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች አብዛኛዎቹ ከስፖርቱ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን የእንጦጦ ፓርክን በማሳያነት ማንሳት ይቻላል፡፡ አረንጓዴ ልማት ከስፖርት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንደመሆኑ በየዓመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ከዚህ ቀደም አስቸጋሪ የነበሩ አካባቢዎችን ማልማትም ሌላኛው መነሻ ነው፡፡ የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዝግጅትን ተከትሎ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረገው ውይይት ያገኘው ቀና ምላሽም ሌላው ምክንያት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዝግጅቱን በተመለከተ ሁለት አቅጣጫዎችን ያስቀመጡ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ዝግጅቱ ቀደም ብሎ እንዲጀመርና ውጤት እንዲመጣ ማመላከታቸው ነው፡፡ የተሻለ ውጤት የሚመዘገብ ከሆነም መንግሥት የሚሰጠውን ማበረታቻ በማስቀመጥ ተነሳሽነትን ሊፈጥሩ ችለዋል፡፡ ሁለተኛው አቅጣጫ ደግሞ ለአንድ ኦሊምፒክ ብቻም ሳይሆን ለቀጣይ ኦሊምፒኮችም መሰረት መጣል ስላለበት የኦሊምፒክ መንደር መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም ሀብት ማሰባሰብ አስፈላጊ እንደመሆኑ፤ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ቃል ገብተዋል፡፡ በሌላ በኩል በርካታ በየክልሉ የተጀመሩ የስፖርት መሰረተ ልማቶችና ግዙፍ ስታዲየሞች ተጠናቀው ሌሎች መጀመር አለባቸው የሚል አቅጣጫም አስቀምጠዋል፡፡ በመሆኑም ከስታዲየሞች ባሻገር የማሰልጠኛ ተቋማትም በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ በማስገባት ሁሉም አመራር ትኩረት እንዲሰጠው አድርገዋል፡፡ ለስልጠና፣ ለውድድርና ለሽልማት አስፈላጊው የገንዘብ ድጋፍ በመንግሥት እየተሰጠ በመሆኑ እንዲሁም ስፖርቱን የሚመሩት መንግሥታዊና ህዝባዊ አካላቱ በነፃነት ነገር ግን በመንግሥት መደገፍ ባለባቸው መልክ ማስኬድ መቻሉም ሌላኛው ምክንያት ነው፡፡ እነዚህ ጉዳዮችም ለስፖርቱ ትልቅ ትኩረት መስጠታቸውን የሚያሳይ መሆኑን በመመልከትም የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሽልማቱን ሊያበረክት ችሏል፡፡ ለረጅም ጊዜ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየውና በአጠቃላይ በአዲስ አበባ የተካሄዱት የአኖካ መርሐ ግብሮች ለኢትዮጵያ ስፖርት ዕድገት እንዲሁም ለአገር ገጽታ ግንባታ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑንም ኮሚሽነሩ ያመላክታሉ፡፡ ለቀናት ከአፍሪካና ከሌሎች አገራት የተገኙ የስፖርት አመራሮች ከጉባኤው ባሻገር፤ የኮሚቴው ሥራ አስፈፃሚ አባላት ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱም ወቅት ኢትዮጵያ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ምን ሚና ነበራት ወደፊትስ የሚኖራት ሚና ምን ይመስላል በሚለው ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ሥራ አስፈፃሚውም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ስፖርት ተምሳሌት መሆኗን እንዲሁም መንግሥት ለዘርፉ የሚሰጠው የጎላ ድርሻ፣ ህዝባዊና መንግሥታዊ አካሉ በቅንጅት ስፖርቱን የሚመራበት ሁኔታ እንዲሁም ለስፖርት የሚመድበው በጀት ለሌሎች አፍሪካዊያን አገራት ምሳሌ እንደሚሆን መግለፃቸውንም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል፡፡ በአዲስ አበባ የተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤም ኢትዮጵያ የትኛውንም አህጉርም ሆነ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የማስተናገድ አቅምና ብቃት ያላት ሀገር መሆኗን በግልጽ ያሳየ ነበር፡፡ ከዚህ ባሻገር በሀገሪቷ እየተከናወኑ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በዘጋቢ ፊልምም ጭምር በማዘጋጀት ለማስረዳት ሙከራ መደረጉንም ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012
https://www.press.et/Ama/?p=36968
3421e9cf1ff00e433878c4297756bc80
df4d4d14e7f3613c8a3c56d0fc184f47
እግራችንን እንሰብስብ፤ ቤታችን እንዝጋ!
መዝናኛ
 የአለም አቀፍ ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ለሚደረገው ጥንቃቄ እያሳየነው ያለነው ዝግጁነት እንደ ጣሊያን ዋጋ እንዳያስከፍለን እሰጋለሁ። ብዙዎችም ሊመጣ የሚችለውን ችግር ቀድመው በመተንበይ እያስጠነቀቁን ነው። ነገር ግን አፍንጫው ላይ ነጭ ሽንኩርት፣ ሎሚና ጤናዳምን እስከነቅጠሉ አስሮ ከመሳለቅ በዘለለ ንክኪን ለማቆም የደፈረ የለም። ብዙዎቻችን ኮሮና ኢትዮጵያ አይገባም፤ ቢገባም አይጎዳንም የሚል ፌዝ ይዘን እራሳችን እያታለልን ነው። ማታለል ብቻም ሳይሆን ለሚመጣው ሰደድ እሳት ብዙዎችን አሳልፈን እየሰጠን ነው። ኋላ በኮሮና የተያዝኩት በማንነቴነው ምናምን አይሰራም። በሚገርም ሁኔታ ኮሮና የሚባል ነገር እንኳ በኢትዮጵያ በተቀረው የዓለማችን ክፍልም አለ ብሎ የማያምን ብዙ ሰው አለ። አብዛኛው ሕዝብ ደግሞ ኮሮናን ለማስደሰት እስኪመስል ድረስ እስከ አንድ ኪሎ ሜትር ድረስ የሚጮህ የእጅ ሰላምታ ሲለዋወጡ እየተመለከትን ነው። ሌላው ደግሞ ኮሮናን ለመከላከል ከሥራ ቀርቶ ካፌ ሲያሞቅ ይውላል። አንዳንዱ ሥራ አይገባም ነገር ግን በሠራተኞች ማመላለሻ ሰርቪስ ነጠላውን አጣጥፎ ይገባና ቤተክርስቲያን ያሳልፋል። የተቀረው ከመገናኛ እስከ ሜክሲኮ፤ ከአውቶቡስ ተራ እስከ ቃሊቲ ሰው በብዛት የሚሰበሰብበትን እየመረጠ ሲዘዋወር ይውላል። በሽታው ከሚሰራ ሰው ጋር ነው እንዴ ጥሉ? ይህ እኮ አግባብ አይደለም ስትላቸው መልሳቸውና ራሳቸውን የማታለያ መንገዳቸው «ፈጣሪ አለ» የሚል ነው። «ኢትዮጵያ ትፈተናለች እንጂ አትፈርስም። ይህ የአውሮፓውያን ሴራ ነው» ብለው ይመልሳሉ። እኔም አምናለሁ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቃል። ግን ደግሞ «አትፈታተኑኝ» ብሏል። ክፉ ቀንንና ጥምዝምዝን ማሳለፍ ጎንበስ ብሎ ነው ይባል የለም? ምን ችግር አለው ፈጣሪያችንን እያመንን ቤታችንን ብንዘጋ? ችግሩ ከየትም ይሁን ከየት ማንም ያምጣው ማን የሚጎዳን ከሆነ በመጠንቀቅ ፈንታ ሌሎችን መኮነን አግባብ አይደለም። ቤትን መዝጋት ብዙ ጥቅሞች ይኖሩታል። መጥፎ ከማየትና ክፉ ከመስማት በጥቂቱም ቢሆን ይቆጥበናል። ፈጣሪን መማፀኛ ሰፊ ጊዜም ይኖረናል። ፈጣሪ ሁሌም አለ። ግን ሰዎች በራሳቸው ስህተትና በማያውቁት ነገር ይሞታሉ። እና የሚሞቱ ኢትዮጵያውያን ፈጣሪ አያውቃቸውም ማለት ነው? ብዙ አታስወሩኝ ከፈጣሪዬ ጋር ታጣሉኛላችሁ። አንዳንድ ሰዎችማ ኮሮናን ደስ ለማሰኘት ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ከተጣሉት ሰው ጋርም ሳይቀር ሰላምታ ሳይለዋወጡ አይቀሩም። እናም እላለሁ እባካችሁ መመሪያ እናክብር። የኤሲያ ሀገራት ለቻይና ቅርብ እንደመሆናቸው በከፍተኛ ሁኔታ የመጠቃት ዕድል ነበራቸው፤ እነሱ ግን የበላይ አካላትንና ሕግን የማክበር ጠንካራ ባህል አላቸው። ይህም ጠቅሟቸዋል። መንግሥት ያወጣውን ሕግ ተግባራዊ ማድረግ በመቻላቸው በሽታው ሳይስፋፋ ብዙም ሳይጎዱ ማለፍ ችለዋል። አያችሁ ቤታቸውን ዘግተው ፈጣሪያቸውን የሚለምኑ እንዲህ ናቸው። እውነት እናውራ ካልን ብልህነት ይህ ነው! ‹‹በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ›› በቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ ከፈጣሪ ጋር መቀራረብ እንዲሁም ከበሽታው መትረፍ። ‹‹ስንቱን አስታወስኩት ስንቱን አሰብኩት ልቤን በትዝታ ወዲያ እየላኩት አንዴ በመከራው አንዴ በደስታየ ስንቱን ያሳየኛል ይሄ ትዝታየ›› አይደል ያለው መሀሙድ አህመድ ። መሀሙድን ትዝታው ብዙ ነገርን እንዳሳየው ሁሉ እኔንም ኮሮና ብዙ ፀባይ ያላቸው ሰዎችን አሳይቶኛል። አንዳንድ ሰዎችማ ግርም እኮ ነው የሚደርጉት በግድ ስለ ኮሮና ብዙ እንድታስብ ያደፋፍሩሃል። ጣሊያን በቫይረሱ በጣም ብዙ ሰዎች ሞቱ ሲባል «ኢትዮጵያ ስለወረረች ነው» ይላሉ። ግብፅ ሦስት ጀነራሎቿንና በርካታ ዜጎቿን በበሽታው መነጠቋ ታውቋል ሲል ዜናው ሰው ቀበል ይልና ማን ኢትዮጵያን ተንኩሽ አላት። የማይገባትን የአባይን ውሃ ለምን ለእኔ ብቻ ልጠቀም አለች?…ሲል ይጠይቅና ቀጠል አድርጎም አያችሁ አይደል ኢትዮጵያን ፈጣሪ ይወዳታል ይላል። በአንድ የቴሌቪዥን መስኮት ደግሞ በአሜሪካ የሟች ቁጥር ከአንድ ሺ በላይ ደረሰ። በቫይረሱም ከ60 ሺ በላይ ሰዎች ተይዘዋል ሲል ወንድሜ ምን ቢል ጥሩ ነው «አይ ትራምፕ በማያገባህ ገብተህ ሕዝብህን አስጨረስክ አይደል» አለ። ዞር አልኩና ምን ማለት ነው ስለው? «ለምን በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ በኩል ወገነ። » ሲል ሳልወድ ፈገግ አልኩ። ስለእውነት ከሆነ ይህ የዋህነት ነው። ፈጣሪ የሁሉም እንጂ ጥቂቶች እንደምናስበው አንዱን ደግፎ ሌላውን የሚበቀል አይደለም። ይህ ሁሉ ምክንያት ድርደራ እራስን ማዘናጊያ ነው። ግን ሁሉንም ትተን እንጠንቀቅ፤ መመሪያዎችን እንተግብር። አሁን ራስን መደለል አቁመን ወደ መጠንቀቁ ካልገባን ተያይዘን ማለቃችን ነው። በቦሊቪያ ከአንድ ቤተሰብ ከቤት እንዲወጣ የሚፈቀድለት አንድ ሰው ነው። ይህ የሆነው ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ታስቦ ነው። ደግሞም ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን በእዛ ሰው አማካኝነት እንዲያገኙ ነው። በእኛ ሀገርስ ይህ ሕግ ቢተገበር የሚቀበለው ስንቱ ነው? ከእንትና ብሔር ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ሰዎች እንዲወጡ ተፈቅዶላቸዋል። የእንትና ሃይማኖት ተከታዮች እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱ ነው። እኛ ተከለከልን መብታችን ተነፈገ ብሎ አቤቱታ የሚያቀርብ አይጠፋም። ግን ሁሉም አይሆንም ከሳሽም ተከሳሽም የማይሰማው ኮሮና ቫይረስ ለወሬ ነጋሬ ሳያስቀር እንዳይጨርሰን መጠንቀቁ ይበጃል። በማንነቴና የእንትን ብሔር ተወላጅ በመሆኔ ማለት ኮሮና ላይ ዋጋ የለውም፤ ዋጋ ያስከፍላል እንጂ። እራስን ፃዲቅ ሌላውን ሀጢአተኛ በማድረግ ኮሮናን ማምለጥ አይቻልም። ኮሮና ቫይረስን ማምለጫው ዋና መንገድ የሚሰጡ መመሪያዎችን በትክክል መተግበር መቻል ነው። ከሁሉም በላይ እግራችንን ሰብስበን ደጃፋችንን ዘግተን የኮሮናን ማህበራዊ ተጽዕኖ እንቋቋም።አዲስ ዘመን መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ምሞገስ ጸጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=29384
444c85a42ceb886c3d1ff7e5bfb4d6a4
a7908648a8118009f4808a922feb8dbb
ዶክተር ካትሪን ሀምሊን
መዝናኛ
   • “የኢትዮጵያ እናቶች እናት” በመባል የሚታወቁና የረጅም አመት የማህጸን ሀኪም በመሆን ያገለገሉ ናቸው። •እ.አ.አ በ1924 ሲድኒ አውስትራሊያ ውስጥ ተወለዱ።•እ.አ.አ በ1959 ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ እቅዳቸው ሦስት ሳምንት የመቆየት ብቻ ቢሆንም በርካታ ሴቶች ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው በመገንዘብ ከመሄድ ይልቅ መቆየትን መረጡ።•እ.አ.አ በ1974 አዲስ አበባ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነውን የፌስቱላ ሆስፒታል አሰሩ።•ይህ ሆስፒታል ከ45 ሺ በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ከህመም ፈውሶ መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ አድርጓል።•ዶክተር ካትሪን ሴቶችን የመርዳት ተግባራቸው ሴቶችን በማከም ብቻ የተገደበ አልነበረም። አዋላጅ ነርሶችን የማሰልጠን ሕልማቸውን ለማሳካት በ2000 ዓ.ም የሐምሊን አዋላጅ ነርሶች ማሰልጠኛ ኮሌጅ እንዲቋቋም በማድረግ በርካታ ባለሙያዎች በየገጠሩ እንዲሰማሩ ማድረግ ችለዋል።•ለ60 አመት በኢትዮጵያ የፌስቱላ ህሙማንን በማከም ሰርተዋል።•ዶክተር ካትሪን ሃምሊን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያለ እድሜ ጋብቻንና የተራዘመ ምጥን ተከትሎ በሚከሰት ሽንትንና ሰገራን መቆጣጠር ያለመቻል ችግር ይሰቃዩ የነበሩ በርካታ ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ሲታደጉ ኖረዋል።•ዶክተር ካትሪን የአዲስ አበባውን ጨምሮ በሃገሪቱ ስድስት የሃምሊን ፌስቱላ ሆስፒታሎችን በማቋቋም ሴቶች ከሚገጥማቸው የፌስቱላ በሽታ በነጻ ታክመው እንዲወጡ ከማድረግ ባሻገር ይደርስባቸው ከነበረ የመገለልና የስነ ልቦና ስብራት መታደግ ላይ ሰርተዋል።• በበጎ ተግባር ላይ ተሰማርተው የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ችግርን የቀረፉት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የኢትዮጵያ የክብር ዜግነትና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።• ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በዋጋ ለማይተመነው አበርክቷቸው በርካታ ሽልማቶችንና ክብሮችን ተቀዳጅተዋል። ከነዚህም መካከል• የቀዳማዊ ኃይለስለሴ የሰብአዊነት ሽልማት • የኦርደር ኦፍ አውስትራሊያ ሽልማት• የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ኮሌጅ የክብር ወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት• የአውስትራሊያ ከፍተኛ ብሄራዊ ሽልማት • አለም አቀፍ የጤና ምክር ቤት የላቀ አፈፃፀም ሽልማት• የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ሽልማት• የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአውስትራሊያ ማኅበር ሽልማት• የሮተሪ ኢንተርናሽናል አለም አቀፍ የሰላም ሽልማት• የእንግሊዝ ህክምና ማህበር ሽልማት• የሲዲኒ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሽልማት• የአውስትራሊያና ኒው ዚላንድ ጦር ዘማቾች የሰላም ሽልማት• የታላቁ የቅድስ ጊዮርጊስ የላቀ የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት• የዞንታ አለም አቀፍ ሽልማት• የኤደንብራ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች ኮሌጅ የክብር ሽልማት• የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የህይወት ዘመን ሽልማት• የ2009 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማት ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው።• ከነዚህ ሽልማቶች በተጨማሪ ካትሪን ሐምሊን እ.አ.አ የ1999ና የ2004 የኖቤል ሽልማት እጩ ሆነው ቀርበው ነበር።• እ.አ.አ በ2009 ‹‹ተለዋጭ ኖቤል›› በመባል የሚታወቀውና አስቸኳይ ምላሽ ለሚሹ አለም አቀፍ ፈተናዎች ተግባራዊና ተምሳሌታዊ የሆኑ መፍትሔዎችን ላፈለቁ አካላት የሚሰጠው የ‹‹ራይት ላይብሊሁድ ሽልማት ›› ተበርክቶላቸዋል።• ባለፈው ዓመትም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሀገራችን በተለይም በፊስቱላ የተጠቁ ሴቶችን ከችግራቸው በመፈወስ ለሰሩት ስራ ሽልማት አበርክተውላቸዋል።• ዶክተር ካትሪን ሀምሊን በ96 አመታቸው መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ስርዓተ ቀብራቸውም በጳውሎስ ወጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።አዲስ ዘመን መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=29379
9832322f36df1939ef60fb23bd9a64e0
fc1c402f9da6b05e36015b0cb49c27bd
አንዳንድ እውነታዎች ስለ ታላቁ ህዳሴ ግድብ
መዝናኛ
 የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በ2003 ዓ.ም ተጀመረ።• ግድቡ ሲጠናቀቅ ከ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በላይ ቦታ ይይዛል።• የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመሙላት የሚወስድባት ጊዜ እስከ ሰባት አመት ነው።• በሚመጣው ክረምት የውሃ ሙሌት ይጀ መራል። •ታህሳስ 2013 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ። እያንዳንዳቸው የኃይል ማመንጫ ተርባይን 375 ሜጋዋት በጠቅላላው 750 ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨ ይችላሉ።• በእያንዳንዱ ኢትዮጵያውያን የገንዘብ መዋጮ የሚገነባና የሁሉም ዜጋ አሻራ ያረፈበት ነው። • ግድቡ ሲጠናቀቅ 6ሺህ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል።• በርካታ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደልብ በማያገኝባት ኢትዮጵያ ግድቡ ሲጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣል። • ከዚህ ባለፈም እያደገ ለመጣው የማኑፋ ክቸሪንግ ዘርፍ ትልቅ እፎይታን የሚሰጥ ይሆናል።• ኢትዮጵያ ግድቡ ሙሉ በሙሉ ኃይል ማመንጨት ሲጀምርላት ለጎረቤት ሀገራት ኮረንቲ መሸጥ ትችላለች። በተለይ ደግሞ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራና ጂቡቲ ከሕዳሴው ግድብ ጥቅም የሚገኙ ሀገሮች ናቸው።• ታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ሒደት 72 በመቶ ደርሷል።• በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎቹ ከ42.3 በመቶ በላይ ተጠናቀዋል።•የሲቪል ስትራክቸር የግንባታ ሒደትም ከ20 በመቶ በላይ አፈጻጸም አስመዝግቧል።•መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ዘጠነኛ አመት የምስረታ በዓሉን ያከብራል።አዲስ ዘመን መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=29376
4502db2292cadf26351accd71b9a4dfe
b7ab928b164395002a477f98c03bdeec
የብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ተጀመረ
ስፖርት
 አዲስ አበባ ቀደምት ከሚባሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ተርታ ብትመደበም፣ መጠሪያዋን ስያሜው ያደረገ ብሔራዊ ስታዲየም ሳይኖራት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ዘመናዊ ስታዲየምም መመልከት ብርቅ ሆኖባት ዘመናት አልፈዋል:: አንድ ለእናቱ የሆነው የአዲስ አበባ ስታዲየም የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ለዚህ ወቅት የሚመጥን አይደለም በሚል ማንኛውንም አኅጉራዊም ይሁን ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን እንዳያስተናግድ ክልከላ ጥሎበታል:: በ2008 ዓ.ም. ታህሣሥ ወር ላይ «ሀ»ብሎ የግንባታውን መሠረት የተጣለለት የአደይ አበባ ስታዲየም አንድ ለናቱ የነበረውን የአዲስ አበባ ስታዲየም ን ያሳርፋል የሚል ተስፋ እንዲሰነቅ ያደረገ ነበር። ለአዲስ አበባ ተጨማሪ ውበትና ኩራት ይሆናል ተብሎ የታሰበውና በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ አካባቢ እየተገነባ ያለው ብሄራዊ ስታዲየሙ፤ የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ አካል የሆነው የስታዲየሙን ጣራ እና የማጠቃለያ ግንባታ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ከትናንት በስቲያ በይፋ ተጀምሯል።የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር በሥነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ፤ በሁሉም የሀገራችን ክልልሎች ከ 12 በላይ ስታዲየሞች በመገንባት ላይ ይገኛሉ ። በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው ግዙፍ አደይ አበባ ስታዲየም ከዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው ሲሆን ፤ስታዲየሙ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የእግር ኳስ ተመልካች ትልቅ ብስራት እንደሚሆን ገልጸዋል። የብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ስፖርት ኮሚሽን ከተቋራጩ የቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር ከወራቶች በፊት በተደረገው ስምምነት መሠረት በታቀደለት ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ መጠናቀቅ ይችል ዘንድ አስፈላጊው ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡የቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ሚንግ ቾ በበኩላቸው ፤ኩባንያው ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመስራት ከፍተኛ ልምድ ያለው መሆኑን ጠቅሰው የዓለም አቀፍ ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ በመቋቋም ስታዲየሙን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ አመልክተዋል።«በአሁን ሰዓት የካፍ እና የፊፋን መስፈርት ያሟላ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን ማስተናገድ የሚያስችል ስታዲየም የለም»ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ እግር ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፤ የአደይ አበባ ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ፍፃሜን ማስተናገድ የሚያስችል ስታዲየም እየተገነባ መሆኑን ትልቅ ደስታ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። የአደይ አበባ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ 900 ቀናት እንደሚፈጅ ተነግሯል ። ለስታዲየሙ መዋቅራዊ ይዘት (የመጀመርያ ምዕራፍ) ግንባታ 2.7 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፣ ለቀሪው ግንባታ ደግሞ 5 ነጥብ 57 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተብሏል:: በስምምነቱ መሠረት ተቋራጩ የተረከባቸው ዝርዝር ሳይቶች ስታዲየሙን ሳር የማልበስ ሥራና የመሮጪያ ትራክ፣ የመገናኛ ብዙኃን ቦታና የጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሎች፣ የተለያዩ መሰብሰቢያ አዳራሾችና የቪአይቪ ማረፊያ ክፍሎችና መቀመጫ ወንበሮች፣ አሳንሳሮች፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የካፌና የሬስቶራንቶች ክፍሎች፣ ለሁለቱም ፆታ አገልግሎት የሚሰጡ መፀዳጃ ክፍሎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃና የኤሌክትሪክ መስመሮች፣ የተለያዩ ሰው ሠራሽ ሐይቆች፣ ለአደጋ ጊዜ የሔሊኮፕተር ማረፊያና ዘመናዊ የደኅንነት ካሜራዎች እንዲሁም የሳውድ ሲስተም ገጠማ፣ ቡድኖች ከጨዋታ የሚለማመዱባቸው የተለያዩ ሜዳዎችና የፓርኪንግ አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ቦታዎች እንዲሁም ብሔራዊ ስታዲየሙ ከጨዋታ በኋላ ተመልካቾችን ጨምሮ ተሽከርካሪዎች ከአሥር እስከ አሥራ አምስት ባለው ደቂቃ ውስጥ አካባቢውን ለቀው መንቀሳቀስ የሚችሉባቸው መንገዶች ተከተዋል፡፡ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እየተገነባ የሚገኘው የአደይ አበባ ስታዲየም አራት ዋና ዋና በሮች ሲኖሩት፣ በወንበር 62 ሺህ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል፡፡ ለክብር እንግዶች (ቪአይፒ) እና ለሚዲያ አባላት 2 ሺህ ወንበሮችን መያዙን ታውቋል። በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪን ኮርፖሬሽን እየተገነባ የሚገኘውና በውጭ ምንዛሪና መሰል ችግሮች የፕሮጀክቱ የመጠናቀቂያ ጊዜ መጓተቱ ይታወሳል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 24/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=36398
d12fe24d1751afad52129fe75ad42bad
ba0430a10d73ea907fb452f93e417c2b
መልስ ያላገኘው የአፍሪካውያን የአገር አቋራጭ ሩጫ ጥያቄ
ስፖርት
አትሌቲክስን ፈታኝ ስፖርት ከሚያደርጉት ውድድሮች አንዱና ዋነኛው የአገር አቋራጭ ሩጫ ነው። የአገር አቋራጭ ውድድር አትሌቲክስን ፈታኝ ብቻም ሳይሆን ተወዳጅና ቀልብ ሳቢ ካደረጉት ምክኒያቶች አንዱ ነው ቢባል ስህተት አይሆንም። በገባ ወጣ መልክዓምድር፤ ኮረብታና ቁልቁለት እንዲሁም በጭቃና አልፎ አልፎም በበረዶ ክምር መሰናክሎች የታጀበው ይህ ውድድር አትሌቶች ከመምና ከጎዳና ላይ ውድድሮች ወጥተው ራሳቸውን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚፈትኑበት ነው።የአገር አቋራጭ ሩጫ የምስራቅ አፍሪካውያን የበላይነት እየገዘፈበት ከመጣ ጀምሮ ግን ተወዳጅነቱ እየቀነሰ የሚሰጠውም ትኩረት እያነሰ መጥቷል። ይህም ከአውራው የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ እንዲወጣ ከማድረጉ ባሻገር በአፍሪካውያን ላይ የፈጠረው ተጽዕኖ በቀላል የሚታይ አይደለም። የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በየሁለት ዓመቱ ራሱን ችሎ የሚካሄድ ቢሆንም በዋናው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናም ውጪ ነው። የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የአሁኑ የዓለም አትሌቲክስ በእንግሊዛዊው የቀድሞ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ኮከብ አትሌት ሴባስቲያን ኮ ፕሬዚዳንትነት መመራት ከጀመረ ወዲህ ውድድሩን ወደ ኦሊምፒክ ለመመለስ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።የአገር አቋራጭ ሩጫን ወደ ኦሊምፒክ የመመለስ እንቅስቃሴ አሁን የተጀመረ ባይሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠንከር ያሉ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ። ከዓመት በፊት በአርጀንቲና ቦነ ሳይረስ በተካሄደው የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ ላይ እንዲካተት መደረጉ አንድ ርምጃ እንደነበር ቢታወስም የአፍሪካውያን ጥያቄ አሁንም ድረስ መልስ አላገኘም።የአገር አቋራጭ ሩጫ ለመጨረሻ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ የተካሄደው እኤአ በ1924 የፓሪስ ኦሊምፒክ ነበር። ቦነ ሳይረስ በወጣቶች የኦሊምፒክ ጨዋታም ቢሆን ይህን ውድድር ከዘመናት በኋላ በአዲስ መልኩ የማዘጋጀቱን እድል አግኝታለች። በዚህ የወጣቶች ኦሊምፒክ የመካከለኛ ርቀት አትሌቶች በተለይም አንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር፤ ሦስት ሺ ሜትርና ሁለት ሺ ሜትር መሰናክል ተወዳዳሪዎች የማጣሪያ ውድድር በማድረግ በሁለቱም ፆታ አርባ ስምንት አርባ ስምንት አትሌቶች ተፎካክረውበታል፡፡ ይህም ጅምር አገር አቋራጭ ሩጫ በዋናው የኦሊምፒክ ውድድር እንዲካተት ትልቅ መሰረት ይሆናል ተብሎ ታምኖበታል። የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮ« የአገር አቋራጭ ሩጫን በኦሊምፒክ መድረክ ማየት የረጅም ጊዜ ፍላጎታችን ነው፤ በቦነ ሳይረስ የወጣቶች ኦሊምፒክ መካተቱም በዋናው ኦሊምፒክ ለማካተት የሚደረገውን ጥረት ያጠናክራል» በማለት ከዓመት በፊት አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎም ትልቅ ተስፋ ታይቶ ነበር። ሴባስቲያን ኮ አገር አቋራጭ ሩጫ በተለይም የመካከለኛ ርቀት አትሌቶች አካል ብቃት የሚታይበት በመሆኑ በኦሊምፒክ መድረክ መካተት እንደሚገባው ፅኑ እምነት አላቸው። በዚህ አቋማቸው መፅናታቸውን ግን እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡የአገር አቋራጭ ሩጫ በዋናው ኦሊምፒክ መድረክ እኤአ ከ1912 እስከ 1924 በወንዶች መካከል ብቻ ተካሂዶ ነው የተቋረጠው። ከዚህ በኋላ ግን የኦሊምፒክ መርሐግብር መሆኑ ቀርቶ የአትሌቲክስ ጉዳይ ብቻ ሆኖ ቀርቷል። ለዚህ ብዙ ምክኒያቶች በተለያዩ ጊዜዎች የሚቀርቡ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በተካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ በርካታ አትሌቶች ውድድሩ ከብዷቸው ሲፍረከረኩና ራሳቸውን ሲስቱ ጭምር ነበር። ይሁን እንጂ አገር አቋራጭ ሩጫ በተካሄዱባቸው ሦስት ኦሊምፒኮች የፊንላንድ አትሌቶች የበላይነት እንደነበር በታሪክ ተጽፎ ይገኛል። ከዚህ በኋላ የተፈጠረው የአትሌቲክስ ትውልድ በተለይም በረጅምና መካከለኛ ርቀቶች የአፍሪካውያን የበላይነት እየጎላ የመጣበት እንደመሆኑ በአገር አቋራጭ የዓለም ቻምፒዮናዎችም ይሁን በግል አፍሪካውያን የበላይነቱን ተቆጣጥረውታል። ይህም አገር አቋራጭ ሩጫ ወደ ኦሊምፒክ እንዲመለስ የሚደረገውን ሂደት እንዳዘገየው የሚያምኑ በርካቶች ናቸው። አፍሪካውያን ይህ ውድድር ወደ ኦሊምፒክ እንዲመለስ ብዙ ጊዜ ታግለዋል። ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፤ የመም ውድድሮችና የአገር አቋራጭ ውድድሮች ንጉሱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለና የኬንያው ታሪካዊ አትሌት ፖል ቴርጋት አገር አቋራጭ ውድድር ወደ ኦሊምፒክ እንዲመለስ ትግል ካደረጉት መካከል ይጠቀሳሉ። በተለይም እነዚህ ሦስት ድንቅ የምስራቅ አፍሪካ የምን ጊዜም ኮከብ አትሌቶች እኤአ 2008 ላይ ለወቅቱ የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ጃኩዌስ ሮግ በአንድ ላይ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል። ይህን ሃሳብ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበርና በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የደገፉት ቢሆንም ተግባራዊ ሳይሆን ዘመናትን ተሻግሯል።አገር አቋራጭ በኦሊምፒክ መካተት አይኖርበትም የሚሉ ሃሳቦች በብዛት ከምዕራባውያን ዘንድ ሲነሳ ይሰማል። ለዚህም የተለያዩ መላ ምቶችን ያስቀምጣሉ። በዋናነት አገር አቋራጭ ሩጫ የክረምት ኦሊምፒክ ስፖርት እንጂ የበጋ ኦሊምፒክ ስፖርት አይደለም የሚሉ በርካታ ናቸው። አገር አቋራጭ ሩጫ በተለምዶ ከአስር እስከ አስራ ሁለት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን በበጋ ኦሊምፒክ ወቅት መካሄዱ እኤአ በ1924 ላይ አትሌቶች እንደተፍረከረኩት አይነት ችግር ይፈጠራል ወይንም የአየር ብክለት ሊኖር ይችላል የሚል ሃሳብም በስፋት ይነሳል። በሌላ በኩል የመም ውድድሮችና ማራቶን በኦሊምፒክ ስለ ተካተተ አገር አቋራጭ ሩጫ አያስፈልግም ወይንም የሚፈጀው ጊዜ ረጅም ስለሆነ አያስፈልግም የሚሉ ሃሳቦች ሲንፀባረቁ ይስተዋላል። አገር አቋራጭ ሩጫ በኦሊምፒክ መካተት የለበትም የሚሉት ወገኖች ከነዚህ የበለጠ ጠንካራ የመከራከሪያ ሃሳብ ይዘው ሲቀርቡ አይታዩም። እነዚህ የመከራከሪያ ነጥቦች ቢሆኑም በራሳቸው ምክኒያታዊና አሳማኝ ናቸው ተብሎ አይታሰብም። ለምሳሌ ያህል ዋነኛ ምክኒያት የሆነው አገር አቋራጭ ሩጫ የክረምት ኦሊምፒክ ውድድር ነው መሆን ያለበት የሚለው ሃሳብ ከምዕራባውያን ጥቅም ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ማመላከት ይቻላል። አገር አቋራጭ ሩጫ በበጋ ኦሊምፒክ መካሄዱ የአየር ብክለት ሊኖር ይችላል ወይንም ከፍተኛ ሙቀት ይኖራል የሚለው ስጋት በራሱ የኦሊምፒክ አዘጋጅነት ከምዕራባውያን አይወጣም የሚል አንድምታ አለው። በእርግጥ ኦሊምፒክን ከዚህ ቀደም የሚያዘጋጁት አቅም ያላቸው አገራት አብዛኞቹ ምዕራባውያን ቢሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ደቡብ አሜሪካና ሌሎች የኤሽያ አገራት እየሄደ ነው። ለዚህም ያለፈውን የሪዮ ኦሊምፒክና መጪውን የቶኪዮ ኦሊምፒክ መጥቀስ በቂ ነው። ከዚህ በኋላም ቢሆን የዓለም ዋንጫን የማስተናገድ አቅም እንዳላቸው ያሳዩ አፍሪካ አገራት እድሉን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ምዕራባውያን በጋ ብለው በሚጠሩት ወቅት የክረምት ወራትን የሚያስተናግዱ አገሮች ኦሊምፒክን ሊያዘጋጁ እንደሚችሉ ልብ መባል አለበት። ከዚህ ጎን ለጎን ውድድሩ ረጅምና አድካሚ በመሆኑ በበጋ ወራት አይመችም የሚለው ሃሳብ በራሱ አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የማራቶን ውድድር በበጋ ኢሊምፒክ መኖሩን ልብ ያለው አይመስልም።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ ሃሳብ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገበት የሚገኝ ቢሆንም አሁንም ጠንከር ያለ ግፊት ያስፈልገዋል። አዲስ ዘመን ከሁለት ዓመት በፊት በዚሁ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮችን አነጋግሮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ በተገኘው አጋጣሚ ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኙ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል። ይህን ሃሳብ አሁንም አጠናክረው ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ጉዳይ የበለጠ አፍሪካውያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ የአፍሪካ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ሲ ኤኤ)፤ የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴ(አኖካ)፤ የአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ መገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች ግፊት ማድረግ አለባቸው ተብሎ ይታመናል። የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮ ምዕራባዊ ቢሆኑም በአትሌቲክሱ ያሳለፉ በመሆናቸው አገር አቋራጭ ሩጫ ወደ ኦሊምፒክ እንዲመለስ ጥረት እያደረጉ ነው። ይሁን እንጂ በዚህ ውድድር የአፍሪካውያን ብቻ የበላይነት የሚጎላ በመሆኑ ምዕባራውያን ወደ ኦሊምፒክ እንዲመጣ ፍላጎት አላቸው ማለት ይከብዳል።በኦሊምፒክ መድረክ አሜሪካና ምዕራባውያን በርካታ ሜዳሊያ በመሰብሰብ የበላይነት ይዘው የሚያጠናቅቁት በአንድ ስፖርት አይነት ብቻ ከአስር በላይ ሜዳሊያ መሰብሰብ የሚያስችላቸው እድል ስላላቸው ነው። ለዚህም በውሃ ዋና ውድድር አንድ አትሌት ብቻ ከአስር በላይ የወርቅ ሜዳሊያ የሚያፍስበት አጋጣሚ እንዳለ ማስቀመጥ ይቻላል። ምዕራባውያኑ እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ በኦሊምፒክ እንዲስፋፋና የበላይነታቸውን ይዘው እንዲዘልቁ ያገኙትን እድል ይጠቀማሉ። አሁንም በቀጣዩ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ እንኳን የነሱ ፍላጎት ያለባቸው በርካታ ስፖርቶች እንዲካተቱ ማድረግ ችለዋል። አፍሪካውያንም ከምዕራባውያን ጋር በኦሊምፒክ ተፎካካሪ ሆነው ለመገኘት እንደ አገር አቋራጭ ሩጫ አይነቶችን ሊጠቀሙ ይገባል። አገር አቋራጭ ሩጫ በኦሊምፒክ ቢካተት በውድድሩ አፍሪካውያን የበላይነት ስላላቸው በኦሊምፒክ የሚያገኙት የሜዳሊያ ቁጥርም ከፍ ሊል እንደሚችል ግልፅ ነው።አዲስ ዘመን ሐምሌ 23/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=36334
cf089f8abbbea5947b0b0f02322953ac
cfdb45e3039b64b45e3682ea59b31759
የግመሎቹን ቅስም እስከ ወዲያኛው የሰበረው የዓለም ዋንጫ ክስተት
ስፖርት
የ1982 የዓለም ዋንጫ ለኤሽያዊቷ አገር ኩዌት የእግር ኳሷ ወርቃማ ዘመን ሆኖ ይታወሳል። የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር ግን ይህ የኩዌት ወርቃማ የእግር ኳስ ዘመን ሲታወስ አይታይም። እግር ኳስ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እየረቀቀ ሲመጣ፤ በይነ መረብ ዓለምን ሲያቀራርብና ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭቶች እንደ ልብ እየሆኑ ሲመጡ እኤአ ከ199oዎቹ ጀምሮ በዓለም ዋንጫ የታዩ ወርቃማ ብሔራዊ ቡድኖች፤ በርካታ ከዋክብቶችና አይረሴ አጋጣሚዎች አሁንም ድረስ በእግር ኳስ አፍቃሪው ዘንድ ይታወሳሉ። ያም ሆኖ ከ1978 የዓለም ዋንጫ አስቀድሞ ከጣሊያንና አርጀንቲና ውጪ ያሉ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ ፓውሎ ሮሲና ማሪዮ ኮምፐስን የመሳሰሉ ተጫዋቾች ትልቅ እውቅና ነበራቸው። ከዚህ የዓለም ዋንጫ በኋላም መረጃዎች እንደ ልብ በሌሉበት ዘመን የዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ለመጀመሪያ ጊዜ ለአርጀንቲና ተሰልፎ ቤልጂየምን እስከ ገጠመበት ጨዋታ በበርካታ የዓለማችን እግር ኳስ አፍቃሪዎች በቴሌቪዥን መስኮት የመመልከት እድላቸው ጠባብ ቢሆንም ስምና ዝናው ይታወቅ ነበር።የዓለም ዋንጫ አይረሴዎቹ ኮከቦች ሚካዔል ላውድሩፕ፤ ህሪስቶ ስቶቺኮቭ፤ ጂዮርጅ ሃጂና ሌሎችም የጀገኑበት ዘመን ሩቅ ቢሆንም የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር ሳይታወሱ የማይታለፉበት ታሪክ አኑረዋል። በተመሳሳይ በብሔራዊ ቡድን ደረጃም የ1966 የሰሜን ኮሪያ፤ በ1982 የአልጄሪያና በ199o የካሜሩን ብሔራዊ ቡድኖች የሚዘነጉ አይደሉም። የኩዌት የ1982 ብሔራዊ ቡድንም ከነዚህ ብሔራዊ ቡድኖች እኩል የሚታወስ ነው። በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችንም ይህን ብሔራዊ ቡድን ለማስታወስ ወደድን፡፡የ1982 የስፔን የዓለም ዋንጫ የኤሽያን እግር ኳስ አንገት ቀና ያደረገ ድንቅ የብሔራዊ ቡድን ስብስብ ከኤሽያ አልፎ በመካከለኛው ምስራቅና የገልፍ አገራት እግር ኳስ ላይ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሮ ነበር። ይህ ከ197o መጀመሪያ እስከ 198oዎቹ መጀመሪያ ላይ ትልቅ የእግር ኳስ አብዮት የፈጠረ የኩዌት ወርቃማ የእግር ኳስ ትውልድ ኤሽያ እስካሁንም መልሳ ያላየችው ስብስብ ይዞ ነበር። ከ1976 እስከ 1978 በታሪካዊው ብራዚላዊ ማሪዮ ዛጋሎ እንዲሁም ከ1978 እስከ 1982 በሌላኛው ብራዚላዊ ካርሎስ አልቤርቶ ፔሬራ እየሰለጠነ ዓለምን ጉድ ያሰኘ የብሔራዊ ቡድን ስብስብ በድንቅ ባለ ተሰጥኦ ተጫዋቾች የተሞላም ነበር። ከግብ ጠባቂው አህመድ ታራቡልሲ አንስቶ እስከ አብዱላዚዝ አል አንባሪ፤ አህመድ አቡ ሐማድና ግብ አፈንፋኙ ጃሴም ያቆብ እንዲሁም አምበሉ ሳድ አል ሆቲና ፋሳል አል ዳክሂል ድረስ በከዋክብት የተሞላው የኩዌት ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ከእግር ኳስ በላይም ትልቅ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተጽዕኖዎች ነበሩት። ይህ ስብስብ በዓለም እግር ኳስ ላይም በትልቅ ደረጃ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለ የመጀመሪያው የገልፍ አገራት ብሔራዊ ቡድን ሆኖ ይታወሳል።የኩዌት ወርቃማ የእግር ኳስ ትውልድ በአንድ ጊዜ ተፈጥሮ በዓለም እግር ኳስ ላይ ድንገት ተፅዕኖ የፈጠረ ሳይሆን በሂደት እየተገነባ የመጣ ነው። ለዚህም በኤሽያና በገልፍ አገራት የእግር ኳስ ቻምፒዮና ሃያል የሆኑትን እንደ ኢራን አይነት አስደናቂ የቡድን ስብስብ ያላቸውን አገራት በሂደት አሸንፎ ዋንጫ በማንሳት ነው። ከዚህ በዘለለም ለ198o የሞስኮ ኦሊምፒክ አልፎ እስከ ሩብ ፍፃሜ ድረስ በመጓዝ በርካቶችን አሳምኖ ነው ወደ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጣው።በኤስያ አገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ኩዌት ኒውዘላንድ፤ ቻይናና ሳውዲ ዓረቢያ ከሚገኙበት ምድብ በፔሬራ አሰልጣኝነት እየተመራች በቀላሉ ወደ 1982 የዓለም ዋንጫ ማምራት ችላለች። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ግን ኩዌት በዓለም ዋንጫው ጠንካራ በሚባል ምድብ ውስጥ ተደለደለች። ይሁን እንጂ በቡድኑ ውስጥ የነበረው ጠንካራ ስነ ልቦና ጠንካራውን ምድብ አልፈው ወደ ጥሎ ማለፍ እንደሚገቡ ትልቅ ተስፋ የሰጠ ነበር።«ግመሎቹ» በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው የኩዌት ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያቸው በሆነው የዓለም ዋንጫ በምድብ ድልድሉ ከሦስቱ አውሮፓውያን አገራት ቺኮስላቫኪያ፤ ፈረንሳይና እንግሊዝ ጋር ነበር የተደለደሉት። ይህ ምድብ ከቺኮስላቫኪያ በስተቀር ፈረንሳይና እንግሊዝ ያላቸው ትልቅ ስም ለግመሎቹ ስጋት ቢሆንም የፔሬራ ልጆች ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ትልቅ ተስፋን ሰንቀው ነበር። በተለይም በመጀመሪያው የቺኮስላቫኪያ ጨዋታ ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዘው ለመውጣት ግምት የተሰጣቸው ቢሆንም ጨዋታው አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁ ያልተጠበቀ ነበር። ይሁን እንጂ ጠንካራዋ ፈረንሳይ በእንግሊዝ ሦስት ለአንድ መሸነፏን ተከትሎ ግመሎቹ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋቸው እንደገና ነብስ ዘራበት። ያም ሆኖ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታ ሚሼል ፕላቲኒ፤ አሊያን ጊረስና ጄን ቲጋና ለፈረንሳይ ግቦችን አስቆጥረው ፈረንሳይ በቀላሉ መምራት ቢችሉም ግመሎቹ ወደ ጨዋታው ተመልሰው ወይ ለማሸነፍ ወይንም የአቻ ውጤት ይዘው ለመውጣት ተስፋ አልቆረጡም። በዚህም ፈረንሳይን ተጭነው በመጫወት በአብዱላህ አል ቦኑሺ የግንባር ኳስ ሦስት ለአንድ መሆን ቻሉ። ይህም ተነሳሽነታቸውን ጨምሮ ሌላ ግብ ለማስቆጠር ጥረት በሚያደርጉበት ሰዓት አንድ ተስፋ አስቆራጭ ክስተት ተፈጠረ። ይህም አለን ጊረስ ከጨዋታ ውጪ የሆነ ግብ ኩዌት ላይ አስቆጥሮ ዳኛው ይሽሩታል ተብሎ ሲጠበቅ ማፅደቃቸው ነበር።ይህች ቅፅበት ግመሎቹን ተስፋ ከማስቆረጧም በላይ በወቅቱም የኩዌት ተጫዋቾች ውሳኔውን በመቃወም ጨዋታውን ሳይጨርሱ ሜዳውን ለቀው ወጥተዋል። በወቅቱ የኩዌቱ ኤሚር ወንድምና የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የነበሩት ሼክ ፋሃድ አል አህመድ አል ጃበር አል ሳባህ ከክብር ወንበራቸው ተነስተው ወደ ሜዳ በመግባት በዳኛው ውሳኔ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ከተጫዋቾቹ ጋር የገለፁበት አጋጣሚ አይረሳም። በዚህም ዳኛው አሁንም ድረስ የዓለም ዋንጫ አስገራሚ ክስተት ተብሎ እንዲታወስ ያደረገውን አጋጣሚ ያፀደቁትን ግብ በመሻር ጨዋታው እንደገና እንዲጀመር ማድረጋቸው ነበር። ያም ሆኖ ግን ግመሎቹ ወደ ጨዋታው ቢመለሱም ወደ ቀድሞው ተነሳሽነታቸው ሳይመለሱ ቀርተው ፈረንሳይ በመጨረሻ ሰዓት ሌላ ግብ አስቆጥራ አራት ለአንድ ማሸነፍ ቻለች። ከዚህም ቅፅበት በኋላ የኩዌት እግር ኳስ የተሰበረ ቅስም አሁንም ድረስ ሳይጠገን ደብዛው ሊጠፋ ችሏል።የ1982 የስፔን የዓለም ዋንጫ ለኩዌት እግር ኳስ ወርቃማ ዘመን እንደመሆኑ መጠን ደብዛው የጠፋበት አጋጣሚም ሆኖ ይታወሳል። አብዛኞቹ የኩዌት ተጫዋቾች እድሜያቸው የገፋ እንደመሆኑ ከዚያ የዓለም ዋንጫ በኋላ ሌላ ተዓምር ሳያሳዩ ጫማቸውን ለመስቀል ተገደዋል። በእርግጥ የተወሰኑ ተጫዋቾች ከዚያም ወዲያ የተወሰኑ ዓመታትን ተጫውተዋል። እነዚህ ተጫዋቾች ከዓለም ዋንጫው በኋላ በገልፍ አገራት ቻምፒዮና እኤአ 1986ና 1990 ላይ ዋንጫ ማንሳት ቢችሉም ኩዌት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያን ለማለፍ የተቃረበችበት ወቅት እንኳን አልተከሰተም። ከዚህም በኋላ እኤአ በ1990 ኩዌት በኢራቅ የተወረረችበትና ቀጥሎም የገልፍ አገራት ጦርነት የተከሰተበት አጋጣሚ የአገሪቱን እግር ኳስ ከተነቃቃበት ወደ ገደል ገፍትሮታል። በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ብሔራዊ ቡድኑ በተደጋጋሚ በፊፋ እገዳ እየተጣለበትም ከድጡ ወደ ማጡ ሲገባ ታይቷል። የኩዌት እግር ኳስ አፍቃሪዎችም የወርቃማ ትውልዳቸው ከዋክብቶችን አል ዳክሂል፤ ያቆብ እንዲሁም አል አንባሪን በማስታወስ የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር ይደሰታሉ።አዲስ ዘመን ሐምሌ 26/2012  ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=36497
3539bc3430f924ef143aed3b8ec081b6
6d433d0150840ea67e532f9662178373
የስፖርት ማህበራትን ለመከለስ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው
ስፖርት
ዘመናዊ ስፖርት ወደ ኢትዮጵያ ከገባ አንድ ምዕተ ዓመት ሊያስቆጥር መቃረቡን ሰነዶች ያሳያሉ። ይሁን እንጂ ስፖርት በኢትዮጵያ በዕድሜው ልክ እንዲሁም ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ አንጻር መድረስ ካለበት ስፍራ እንዳልደረሰ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። ስፖርት የአንድ ሀገር እድገት መለኪያ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ የህዝቡን ጥቅምና ፍላጎት አስጠብቋል ለማለት አያስደፍርም። ለስፖርቱ እድገትም ሆነ መዳከም ድርሻ ያላቸው የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ስፖርቱን የሚመሩ አካላት ጥንካሬና ብቃት ግን ወሳኝነት እንዳለው ይታመናል። ይሁን እንጂ እስካሁንም ድረስ በዚህ አቅጣጫ ሳይሆን በራሳቸው ጥረት የተሻለ ብቃት ያሳዩትን ስፖርተኞች በውድድር ላይ ማሳተፍ ላይ ያተኮረ አካሄድ እየተተገበረ ይገኛል። ስፖርትን ለልማት ከማዋል ይልቅ ውድድሮችን ብቻ ኢላማ ያደረገ አካሄድም ስፖርቱ በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ ያደረገ ገፊ ምክንያት ሆኖ በተደጋጋሚ ይነሳል። የአገራችን ስፖርት ከየት ተነስቶ ወደ የት ማምራት እንዳለበት የሚያሳይ የስፖርት ፖሊሲ አቅጣጫ በ1990 ዓ.ም ተቀርጿል። ነገር ግን በፖሊሲው በተቀመጠው ልክ በተጨባጭ ስኬታማ የሆነ ሂደት ባለማሳየቱ በአሰራሩ ላይ ፍተሻ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት በጥናት ላይ የተመረኮዘ ብሄራዊ የስፖርት ሪፎርም በቅርቡ በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን መዘጋጀቱ ይታወቃል። በሪፎርሙ ምክረ ሃሳብ መሰረትም መመሪያዎች በመከለስና በመሻሻል ላይ ይገኛሉ። ሪፎርሙ ካመላከታቸው ነጥቦች መካከል አንዱ የሆነው አደረጃጀቱን የሚመለከት ሲሆን፤ በተለይ መንግስታዊው አካል ላይ ክፍተት መኖሩን አመላክቷል። በኢትዮጵያ 30 የሚሆኑ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ይገኛሉ። ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ባለው አደረጃጀትም በጥቅሉ 397 ፌዴሬሽኖችና የስፖርት ማህበራት እንዳሉ ይታመናል። ከእነዚህ ማህበራት መካከል ራሳቸውን ችለው ከመንግስት ድጎማና ድጋፍ የተላቀቁት ግን ሁለቱ ብቻ ሲሆኑ፤ አትሌቲክስና እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች በዋናነት ይጠቀሳሉ። የተቀሩት እስካሁንም የመንግስትን ድጎማ የሚጠብቁ በሁለት እግራቸው ያልቆሙ ሲሆኑ፤ በግላቸው የሚያደርጉት እንቅስቃሴም አነስተኛና የተገደበ ነው። ለዚህና ለስፖርቱ አለማደግ በዋናነት እንደ ምክንያት የሚያነሱትም በመንግስት በኩል የሚመደብላቸውን አነስተኛ የበጀት ድጎማ ነው። ነገር ግን የየስፖርት ዓይነቱን በኃላፊነት የሚመሩትና በየደረጃው የሚገኙ የስፖርት ማህበራት (ፌዴሬሽኖች) ካሉባቸው ችግሮች ባሻገር ከራሳቸው ድክመት የተነሳ ስፖርቱ እንዲዳከም ምክንያት እንደሆነ ይታመናል። አሁን ባለው ሁኔታ ፌዴሬሽኖቹ ራሳቸውን ከተረጂነት ነጻ ለማውጣት ያላቸውን እድል ተጠቅመው ለውጥ ለማምጣት የሚፍጨረጨሩት ጥቂቶች ናቸው። መልካም ተሞክሮ ካላቸው ሌሎች ፌዴሬሽኖች ልምድ ለማግኘት የሚችሉበት መንገድም ዝግ መሆኑ ይስተዋላል። አንዳንድ ስፖርቶች በህዝቡ ዘንድ በቅጡ ያልታወቁና ተደራሽነታቸውም በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን በማህበር ታቅፈው የመንግስትን በጀት ለብክነት የሚዳርጉም አሉ። በአንጻሩ መልካም ድልና የተሻለ ውጤት ሊመዘገብባቸው የሚችሉ ስፖርቶች ደግሞ እንቅስቃሴያቸው የተገደቡ ሆነዋል። ሌሎች ደግሞ በተወሰኑ አካላት ተሸብበው እድገታቸው ቀጭጮ እንዲቀር ሆነዋል። ስፖርቱ በህዝቡ ዘንድ ተስፋፍቶ ጥቅም የሚገኝበት እንዲሁም በሀገር ደረጃ ውጤት እንዲመዘገብበት ካስፈለገም እነዚህ ችግሮች በቅድሚያ ሊቀረፉ እንደሚገባ ብዙዎች ይስማማሉ። በመሆኑም ሀገር አቀፉን የስፖርት ማህበራት ማቋቋሚያ መመሪያ ማሻሻል አስፈልጓል። ባለፈው ሳምንት ኮሚሽኑ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተሻሻለው መመሪያ ረቂቅ በኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን አልዩ ለተሳታፊዎቹ የቀረበ ሲሆን አስተያየትም ተሰጥቶበታል። በገለጻው ላይ እንደተመላከተው ከሆነም ለመመሪያው መሻሻል አስፈላጊ የሆኑት ምክንያቶች፤ በሪፎርሙ የተሰጠው ምክረ ሃሳብ፣ የማህበራዊ ወቅታዊ አቋም፣ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት እንዲሁም የስፖርት ምክር ቤቱ የውሳኔ አቅጣጫ ናቸው። የማህበራቱን አሰራሮችና አደረጃጀቱን በመፈተሽ ተገቢውን መስፈርት አሟልተው እንዲሄዱ ማድረግም አላማው ነው። አብዛኛዎቹ ማህበራት ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ የማህበር ስያሜ ብቻ በመያዝ እውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ውጤታማ መሆን አልቻሉም፤ በመሆኑም ዳግም ዕውቅና ማግኘት አስፈልጓቸዋል። መሆኑም ማሻሻያው የተለያዩ ሂደቶችን ተከትሎ ሊዘጋጅ ችሏል። ይኸውም ነባሩን መመሪያ መሰረት በማድረግ፣ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በመዳሰስ፣ ዓለም አቀፍ አሰራሮችን በመመልከት እንዲሁም ያጋጠሙ ተጨባጭ ሁኔታዎችን በመውሰድ መሆኑንም በመድረኩ ተጠቁሟል። በስራውም የኮሚሽኑ፣ የተለያዩ ፌዴሬሽኖች እንዲሁም የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ነበሩ። መመሪያው ከያዛቸው ሃሳቦች መካከል አደረጃጀትና ስያሜን የሚመለከት ሲሆን፤ በክልል ያሉ ፌዴሬሽኖች ‹‹አሶሴሽን›› ከዚያ በታች ያሉት ደግሞ ‹‹ኮሚቴ›› በሚል ቢጠሩ ለአሰራር አመቺ እንደሚሆኑ ተመልክቷል። የፌዴሬሽን ማቋቋሚያ መስፈርትን በተመለከተም የቡድንና የግል ስፖርቶችን በራሳቸው አሰራር መሰረት እውቅና የሚያገኙበት ሁኔታም ተካቷል። በዚህም የቡድን ስፖርቶች የሚያወዳድሯቸው ቢያንስ ስድስት ክለቦች ሊኖሯቸው እንደሚገባ፤ በአርት ስፖርቶች 10 ማዕከላት እንዲሁም በግል ስፖርቶች 250 የተመዘገቡ ስፖርተኞች ሊኖሩ ይገባል። ደረጃውን የጠበቀ የውድድርና የስልጠና ቁሳቁስ መኖሩ ሲረጋገጥ፣ የሀብት ምንጭ ሲኖራቸው እና የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት የዘረጉ ሊሆኑም ይገባቸዋል። የሀገር አቀፍ ስፖርት ፌዴሬሽኖች የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እጩ አቀራረብ፣ የመምረጫ መስፈርት እንዲሁም ተግባርና ኃላፊነትም በመመሪያው ተካቷል። በዚህም የኮሚቴዎቹ የስራ ዘመን አራት ዓመት ብቻ ሲሆን፣ በድጋሚ የሚመረጡትም ለአንድ የስራ ዘመን ብቻ ይሆናል። ይህም ቀድሞ በተለያየና በተበታተነ ሁኔታ ይከናወን የነበረው ምርጫ አንድ የኦሊምፒክ ጨዋታ በተጠናቀቀ ሶስትና አራት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ምርጫ እንዲከናወን የሚያስገድድ ነው። ከዚህ ጋር የተካተተው መመሪያም የትኛውም የስራ አስፈጻሚ ሊያገለግል የሚችለው በአንድ ስፖርት ላይ ብቻ መሆኑን የሚያመለክት ነው። የማህበራት ፈቃድ አሰጣጥ፣ እድሳትና መፍረስን በተመለከተም በምን መልኩ ይከናወናል የሚለውን የተሻሻለው የመመሪያ ረቂቅ በዝርዝር አስቀምጧል። የኦሊምፒክና ፖራሊምፒክ ኮሚቴዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ስፖርት ማህበር እንዲሁም የጤና ስፖርት ማህበር በበኩላቸው የተለያዩ ስፖርቶችን አቅፈው የሚያካሂዱ ማህበራት እንደመሆናቸው ከሌላው የተለዩ መሆናቸውም ተገልጿል። በመመሪያው ዝግጅት ላይ ተሳታፊ የነበሩትና ገለጻውን ያደረጉት የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አልዩ ምላሽ የተነሱ ሃሳቦች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። መድረኩ የተዘጋጀው ግብዓት ለመሰብሰብ እንደመሆኑ በተለያዩ አካላት ዘንድ የተለያዩ እይታዎች ይፈጠራሉ። በመሆኑም ጠቃሚ የሆኑትን ለማካተት ያስችላል፤ የስፖርቱ አደረጃጀት በምን መልክ ሊቃኝ ይገባል በሚለው ላይ ጠቃሚ ሃሳቦች እንጂ ፍላጎቶችን ለማስተናገድ እንደማይቻልም አሳስበዋል። አደረጃጀቶቹ ያሉባቸውን ክፍተቶች በመሙላት አደረጃጀቱን ለማጠናከር ይቻላል፤ ስለዚህም የተሰጡት ግብረ መልሶች በሰነዱ የሚካተቱ ይሆናል። በተጨማሪም መድረኩ የተዘጋጀው በምክር ቤት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በመሆኑ መንግስት ወደፊትም ለማህበራቱ እገዛና ድጋፍ ከማድረግ ወደኃላ እንደማይልም አመላክተዋል። በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጂሎ በበኩላቸው ይህ የቀረበው ረቂቅ መመሪያ ወደ ክልሎች ወርዶ የራሳቸውን ደንብና መመሪያ እንዲያወጡ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል። ማህበራቱ የየራሳቸውን መመሪያና ደንብ ካዘጋጁ በኋላም በዚህ ላይ ተመስርተው ክልሎች በስታንዳርዱ መሰረት የሚተዳደሩ ይሆናል፤ በመሆኑም በመድረኩ የተንጸባረቁ ሃሳቦች ጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል። አዲስ ዘመን ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ምብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=36457
a9b9e975b6eb0f146a7545ffe248be6a
1d1a1ad6453ac1b9d55f82607753f4f5
አይጦችን ከአገልግሎት ክፍያ ለማምለጫ
መዝናኛ
 በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ሆቴሎች እንደ የደረጃቸው ለደምበኞቻቸው አገልግሎቶችን ያቀርባሉ።ለአገልግሎቶቻቸውም ደምበኞቻቸውን ያስከፍላሉ።ደምበኞችም በሆቴሎቹ ቆይታቸው ከያዙት አልጋ ጀምሮ እስከተጠቀሟቸው ምግቦችና መጠጦች ድረስ ክፍያ መፈፀም ይጠበቅባቸዋል። ይሁን እንጂ አንዳንዴ ደንበኞች በሆቴሎች ውስጥ ያሻቸውን ተጠቅመው ሲያበቁ ሂሳብ ሲጠየቁ ድንጋጤ ውስጥ የሚገቡ፤ ለመክፈልም የሚያንገራግሩ አይጠፉም።ለተጠቀሙበት አልጋ፣ ምግብ፣ መጠጥና ሌላም የአገልግሎት ክፍያ ሳይፈፅሙ እንዲሁ በነፃ ከሆቴሉ ውልቅ ብለው ለመውጣት የሚዳዱም አልፎ አልፎ አይታጡም።ኦዲቲ ሴንትራል ከሰሞኑ ይዞት የወጣው መረጃም የሆቴል አገልግሎቶችን በሚገባ ተጠቅሞ ክፍያ ሳይፈጽም ስለተገኘ አንድ ግለሰብ አስነብቧል። የሰላሳ ሰባት አመቱ አሜሪካዊው የኡታ ግዛት ጎልማሳ ሪያን ቀልቡ ባረፈባቸው ሆቴሎች ሁሉ በመግባት ከአልጋ ጀምሮ የሚፈልገውን አገልግሎት በሙሉ ተጠቅሞ ምንም አይነት ክፍያ ሳይከፍል በተደጋጋሚ ውልቅ ብሎ ይወጣል።ሂሳብ ሳይከፍል የሚወጣው ግን ተደብቆ ወይም በስፖንሰር ተከፍሎለት አይደለም፤ በአይጦች እንጂ።እዚህ ላይ የእርሱ ከሆቴሎች በነፃ ተስተናግዶ መውጣት ከአይጦች ጋር ምን አያያዘው ሊሉ ይችላሉ።እውነታው ግን አይጦቹ ሪያንን ከከባድ ወጪ ያዳኑት መሆኑ ነው። ነገሩ ወዲህ ነው፤ ሪያን በቅድሚያ ወደ ሆቴሎች ሰተት ብሎ ይገባል። ከዛም አልጋ ይይዛል።ጥቂት ቆይቶም ከውጭ ወደሆቴሉ በሳጥን ደብቆ የሚያስገባቸውን አይጦች በያዘው ክፍል ውስጥ ይለቃቸዋል። በመቀጠልም ከሆቴሉ ስታፍ ለአንዱ ስልክ በመደወል በሆቴሉ የንፅህና አያያዝ ዙሪያ ቅሬታውን ያቀርባል፤ ይጮሃል። ታዲያ በዚህ ጊዜ የሆቴሉ ስራ አስኪያጆች የሆቴላቸው ስም እንዳይጠፋ ‹‹የአልጋ ሂሳብ አናስከፍልህም፤ የምግብና የመጠጥ ወጪህንም እኛ እንሸፍንልሃለን›› ይሉታል።እንዲህ አይነቱን የማታለያ ድርጊት በተደጋጋሚ በመፈፀምም ሪያን በተለያዩ ሆቴሎች በሚገኙ አልጋዎች ላይ በነፃ ተኝቷል፤ ሌሎች የምግብና የመጠጥ አገልግሎቶችን እንዳሻው ተጠቅሟል። መቼም እንዲህ አይነቱ የማታለያ ተግባር ሁሌም አያዋ ጣምና በዚህ ድርጊት በሶስት ሆቴሎች ላይ የጠረጠረው ፖሊስ ሪያንን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገበት ይገኛል። ሪያን እንዴት በፖሊስ ሊያዝ እንደቻለ በግልፅ የተነገረ ባይኖርም በሁለት ሆቴሎች የመኝታ ክፍሎች ወስጥ አይጦቹን ስለመልቀቁ ግን ራሱ አምኗል።ሌብነትና ማጭበርበርን ጨምሮ አምስት ክሶች እንደሚጠብቁትም ተነግሯል። አዲስ ዘመን የካቲት 10/2012 አስናቀ ፀጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=27458
dd42826ee9de53d2601d4cd9e0038d6c
4c64656042e6ddb504d280c730f6b584
ባድሚንተን-ትኩረት የተነፈገ ተወዳጅ ስፖርት
ስፖርት
 በስፖርቱ ዓለም ጥሩ የአካል ብቃት፣ሰውነትን እንደ ልብ የማዘዝ ችሎታ፣ፅናት፣ጥንካሬና ፍጥነትን ከሚሹ ጨዋታዎች መካከል ባድሚንተን ዋነኛው ነው። ከሜዳ ቴኒስ ወይንም ከጠረጴዛ ቴኒስ ጋር ተመሳሳይ አጨዋወትን የሚጋራው የባድሚንተን ስፖርት በብሪታኒያና ህንድ እንደጎለበተ የሚነገር ቢሆንም በአውሮፓዊቷ አገር ዴንማርክ ትልቅ ዝና አለው። ይህ ስፖርት ተወዳጅነቱን እያሰፋ በኤሽያ አገራት በስፋት መዘውተሩን ተከትሎም ባለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት የቻይና የበላይነት የሚንፀባረቅበት ሆኗል። እኤአ 1992 በባርሴሎና የበጋ ወራት ኦሊምፒክ ተካቶም በአራት የውድድር ዘርፎች አገራት ተፎካካሪ ሆነውበታል። በነጠላ ወንዶች፣ ነጠላ ሴቶች፣ በቡድን ሴቶችና በቡድን ወንዶች ኦሊምፒክ ላይ የነበረው ፉክክር አድጎም በድብልቅ ፆታ አምስተኛ የመወዳደሪያ ዘርፍ ለመሆን ጊዜ አልፈጀበትም። የባድሚንተን ስፖርት በኢትዮጵያ በይፋ መቼ እንደተጀመረ ሰነዶችን ማግኘት አይቻልም። ይሁን እንጂ ይህ ስፖርት በ1940ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በታወቁ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች፣ የሚሲዮን ተቋማትና በወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር (ወክማ) አካባቢ በውጭ አገር ዜጎችና መምህራን አማካኝነት እንቅስቃሴው እንደተጀመረ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በተለይም የባድሚ ንተን ስፖርት በ1970 ዎቹ ገደማ ከወክማ ባሻገር በህንድ ኤምባሲ ውስጥ በስፋት መዘውተር እንደ ጀመረ ይነገራል። በህዳር ወር 1978 ዓ.ም ስፖርቱ በአደራጅ ኮሚቴነት ተዋቅሮ በሂደት 1982 ዓ.ም ላይ አደረጃጀቱ ወደ ፌዴሬሽን አድጓል። ከዚህም በኋላ ከ1986 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያ ቻምፒዮናን በውድድር ደረጃ ማከናወን ችሏል። ባለፉት ዓመታትም በአገራችን በሚካሄዱ እንደ መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች፣የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል፣የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድሮችና ሌሎችም ፉክክሮች ላይ የምንመለከተው ስፖርት መሆን ችሏል። ከኦሊምፒክ ስፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው የባድሚንተን ስፖርት በተለይም በኤሽያ አገራት በስፋት የሚዘወተር ብቻ ሳይሆን እነዚህ አገራት በብዛት ኦሊምፒክ ላይ ተሳትፈው በሜዳሊያ ሰንጠረዥ የአገራት ፉክክር ውስጥ የሚገቡበት የስፖርት አይነት ነው። የባድሚንተን ስፖርት አሁን ላይ በአገራችን ብዙ እውቅና ከሌላቸው የስፖርት አይነቶች አንዱ ሆኖ እናገኘዋለን። የአገራችን መገናኛ ብዙሃንም አብዛኞቹ ለዚህ ስፖርት ትኩረት ሲሰጡት አይታይም። ስፖርቱን በቅርበት ከሚያውቁት ባሻገ ርም አብዛኛው ህዝብ ባድሚንተን ምን እንደሆነ ግን ዛቤ አለው ለማለት ይቸግራል። በአጠቃላይ የባድሚንተን ስፖርት በአገራችን ካለመስፋፋቱ ባሻገር ሌሎች የኦሊምፒክ ስፖርቶች በሚጓዙበት የእድገት ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው ለማለት አይቻልም። ለመሆኑ ይህ ስፖርት እንደ እግር ኳስና አትሌቲክስ ባይሆን እንኳን ሌሎች ደካማ የሚባሉት ስፖርቶች በሚንቀሳቀሱበት ደረጃ ለመንቀሳቀስ ለምን ተሳነው?፣ ክለቦችን መስርተው የሊግ ውድድሮችን በቀጣይነት ለማስኬድ ዳዴ ከሚሉት አንዳንድ ፌዴሬሽኖችስ በምን ይለያል? የሚሉ ጥያቄዎች በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ይነሳሉ። የስፖርቱ አፍቃሪዎች ከስፖርቱ ባህሪ ተነስተው ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ የባድሚንተን ትልቁ ችግር መሰረተ ልማት እንደሆነ ያብራራሉ። የባድሚንተን ስፖርት በባህሪው ከቤት ውስጥ ስፖርቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የተሟላ መሰረተ ልማት የሚጠይቅ ነው። ስለዚህ ስፖርቱን ለማስፋፋትና ለማዘውተር ቢያንስ መሰረታዊ የሆነ አዳራሽ ወይም ጅምናዚየም ያስፈልጋል። የባድሚንተን መጫወቻዋ ላባ(በተለምዶ እፉየ ገላ የምትመስል መጫወቻ) በጨዋታ ወቅት በንፋስ ምክንያት አቅጣጫ የመለዋወጥ ባህሪ ስላላት ስፖርቱን ከቤት ውጭ ማድረግ አስቸጋሪ ነው። ይህን ስፖርት ለመጫወት አዳራሹ ወይንም ጅምናዚየሙ ቢያንስ ሰባት ሜትር ከፍታ ያለውና ሁለት ጨዋታዎችን በአንድ ጊዜ ማካሄድ የሚያስችል መሆን እንዳለበት ዓለም አቀፍ ህጉ ይደነግጋል። በአገራችን አብዛኞቹ ስፖርቶች ከቤት ውጭ ሊዘወተሩ ይችላሉ። ባድሚንተን ግን ቤት ውስጥ ብቻ የሚደረግ ውድድር በመሆኑ በቀላሉ እንዳይዘወተርና እንዳይስፋፋ እንቅፋት መሆኑን የስፖርቱ ቅርብ ሰዎች ይናገራሉ። ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች በስተቀር ስፖርቱን ሌሎች ክልሎች ላይ እንደልብ ማካሄድና ማስፋፋት የሚያስችል መሰረተ ልማት የለም። በአዲስ አበባ ወክማ ውስጥ ባድሚንተን በስፋት እንደሚዘወተር ይታወቃል። ነፃ የሆኑ አዳራሾች ወይም ጅምናዚየሞች ቢኖሩ ስፖርቱ የሚፈልጋቸው ሌሎች ቁሶችን በቀላሉ ማግኘት እንደሚቻል ይታመናል። በእርግጥ የባድሚንተን ስፖርትን እንደ ቮሊቦልና ቅርጫት ኳስ አይነት ስፖርቶች ከቤት ውጪ ማዘውተር የሚቻልበት እድል ዝግ አይደለም። ይሁን እንጂ ባድሚንተንን ከቤት ውጭ ማዘውተር ስፖርቱን በፕሮፌሽናል ደረጃ ለማሳደግና ውጤታማ ለመሆን እንደማይቻል እውን ነው። አገር አቀፍ ፌዴሬሽኑ ስልጠናዎችን ለመስጠት አይደለም አገር አቀፍ ውድድሮችን ለማካሄድ እንቅፋት ከሆኑበት ነገሮች ዋነኛውም ይሄው ማዘውተሪያ ስፍራው መሆኑም ይታመናል። ስፖርቱ እጅግ የሚወደድና የብዙዎችን ቀልብ ሊስብ የሚችል ነው። በአገራችን በተለያዩ ውድድሮች ላይ እንደሚታየውም ወጣቱ ስፖርቱ ላይ ትልቅ ፍላጎት አለው። በተለይም በለጋ እድሜ ላይ የሚገኙ እድሜያቸው አሥራ አንድና አሥራ ሁለት አካባቢ የሚገኙ ታዳጊዎች ለባድሚንተን ስፖርት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። ሁኔታዎች ተመቻችተው እንደ ስፖርት ለሁሉም እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ቢያዘወትሩትም ይመከራል። የባድሚንተን ስፖርት በደንብ ትኩረት ተሰጥቶት ተከታታይ ስልጠናና በርካታ ውድድሮች ቢደረጉ ቢያንስ በአፍሪካ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ይታመናል። አሁን ባለው ሁኔታ ስፖርቱ ከነችግሮቹ እንኳን ውጤቱ ብዙ ባይሆንም በመላ አፍሪካና ሌሎች ዓለም አቀፉ ጨዋታዎች መሳተፍ እየተቻለ ይገኛል። መንግሥት ስፖርቱን በተመለከተ ሥራው በዋናነት ስፖርቱን ማስፋፋት ነው። የልማት ሥራዎችን መስራት ደግሞ ያለበት ፌዴሬሽኑ ነው። ፌዴሬሽኑን ሊመሩ የሚችሉ ደግሞ ሥራ አስፈፃሚዎች ተቀምጠዋል። እነዚህ ሥራ አስፈፃሚዎች ሃብት አሰባስበው ስፖርቱን በደንብ በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲያስፋፉ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ህዝባዊ አካል ናቸው። መንግሥት እንደማንኛውም የስፖርት ፌዴሬሽን ለባድሚንተንም ድጋፍ ያደርጋል። እንዲያውም መንግሥት አሁን የሚያደርገው ድጋፍ ከስፖርቱ እንቅስቃሴ አንፃር ጥሩ የሚባል እንደሆነ ማስቀመጥ ይቻላል። ባድሚንተን የኦሊምፒክ ስፖርት እንደመሆኑ እንደሌሎች መሰል ስፖርቶች በታዳጊ ወጣቶች የተለያዩ ፕሮጀክቶችና በአካዳሚ ደረጃ ሰፊ እንቅ ስቃሴ ሲደረግበት አይታይም። ባድሚንተን በሁሉም ክልሎች በታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ከሚሰራባቸው ስፖርቶች አንዱ ሆኖ እየተሰራ ይገ ኛል። ፌዴሬሽኑም በየዓመቱ የሚደረጉ የፕሮጀክቶች የምዘና ውድድሮችም ተሳታፊ ነው። በታዳጊ ፕሮጀክት ደረጃ የሚሰራባቸው በአካዳሚ ደረጃ ግን ስልጠና የማይሰጥባቸው ሌሎች ስፖርቶችም አሉ። በባድሚንተን ስፖርት በግለሰቦች የሚመሰረቱ ቡድኖች አሉ፣ እንደ ክለብ ግን ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ አይደሉም። በዚህ ሁኔታ በባድሚንተን ስፖርት በተለያዩ ክልሎች የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀ ክቶችን ቀርፆ መንቀሳቀስ እንደ አገር ስፖርቱን ከመጥፋት ሊታደግ ይችላል። ይሁን እንጂ ከነዚህ ፕሮጀክቶች የሚወጡ ታዳጊዎች ወደ አካዳሚ ገብተው ከዚያም ወደ ክለብ መሸጋገር ካልቻሉ ከስፖርቱ ጋር ያላቸው እህል ውሃ የሚዘልቀው እስከ ምዘና ውድድር ድረስ ነው። ይህ ደግሞ ብዙ ወጣቶች ወደ ስፖርቱ እንዳይመጡ እንቅፋት መሆኑ አይቀርም። ክለቦች ከሌሉ ከፕሮጀክት የሚወጡ ታዳጊዎች ተጎጂ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቢታመንም ከፕሮጀክት ከወጡ በኋላ ሌላ ማረፊያ የላቸውም። በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ክልላቸውን ወክለው መሳተፍ አንዱ አማራጫቸው መሆኑ ግን ይታመናል። ከባድሚንተን ጋር በተመሳሳይ በጀት ይንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ፌዴሬሽኖች ክለቦችን በማቋቋምና ውድድሮችን በብዛት በማድረግ ራሳቸውን እያሳደጉ እንደሚገኙ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። በአገራችን ከታሪካቸውም አንፃር የኳስ ስፖርቶች ላይ ትኩረት የማድረግ ልምድ ስላለ የኳስ ስፖርቶችና ባድሚንተን እኩል ማየት ተገቢ አይደለም። የኳስ ስፖርቶች የሚባሉት እግር ኳስ፣እጅ ኳስ፣ቅርጫት ኳስ ወዘተ በሚሊተሪ አካባቢ ሰፊ መሰረት ስላላቸው እነሱን ለማሳደግ ከባድሚንተን አይነት ስፖርቶች አኳያ ብዙ ልፋት እንደማይጠይቅ የሚሞግቱ የስፖርት ቤተሰቦች ጥቂት አይደሉም። የባድሚንተን ስፖርት በርካታ ችግሮች ቢኖ ሩበትም በአንዳንድ ክልሎች መሰረታዊ ነገር ሳይሟ ላላቸው ጭምር እየሰሩ ነው። ስፖርቱ የመሰረተ ልማት እጥረት ቢኖርበትም ፌዴሬሽኑ በተቻለው አቅም ከዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኑ ከሚያገኛቸው የቁሳቁስ ድጋፍ ተነስቶ ለክልሎች ድጋፍ እየሰጠ ነው። ይህ ስፖርቱ እንዲያንሰራራ ትልቅ እድል ነው። የመሰረተ ልማት ጉዳይ የባድሚንተን ስፖርት ብቻም ሳይሆን የበርካታ ስፖርቶች እንቅፋት እንደመሆኑና ከአገር አቅም ጋር የተያያዘ መሆኑ ችግሮች በአንድ ጀምበር ሊፈቱ አይችሉም። ያም ሆኖ ኢትዮጵያ በስፖርቱ መሰረተ ልማት ግንባታ ረገድ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ለመሆኗ በተለያዩ ክልሎች ግዙፍ ስቴድየሞችን ጨምሮ ጅምናዚየምና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ማስተዋል ይቻላል። ባድሚንተንን ለመሳሰሉትና በመሰረተ ልማት ችግር በአገራችን መራመድ ያልቻሉት ስፖርቶችም የነዚህን መሰረተ ልማት ግንባታዎች መጠናቀቅ በተስፋ የሚጠበቁ ይሆናል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 27/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=36543
e067a1ecc1a9d04b55d040cdb3f806bd
f2c16530eff05967a886de0081dad5f7
የሚወዱት -ሲወደድ” ደስ ይላል!
መዝናኛ
እነ ኒያላና ጓደኞቹ በመወደዳቸው፤ ዋልያና ቤተሰቦቹ አልቀመስ በማለታቸው አኮረፉ አሉ። ሰው የሚወደው ነገር ሲወደድ ደስ ሊለው ነው የሚገባው፤ አይደል? ምን ነካቸው? ሰሞኑን በፀደቀው አዋጅ ምክንያት አኩራፊዎች በዝተዋል ሲሉ ተገረምኩ። የእነ ሀበሻ አድናቂዎች የእነ ግስላ ቲፎዞዎች እንዲያው ምን ነካችሁ? ሰው ወዳጁ ወደላይ ከፍ እንዲልለት በብርቱ ሲመኝ እንዴት የወደዳችሁት ነገር መወደዱን ጠላችሁት ግን? አኮረፉ ‘ለምን? አሉ’ ሲሉኝ እኔ አላመንኩም ነበር። ግን አመንኩ፤ በቢራ መወደድ ማዘናችሁ፤ በሲጃራ ዋጋ ማሻቀብ ማኩረፋችሁ በገጠመኜ እኔም ታዘብኩ። አቤት ግን ግፋችሁ! ቆይ ስንት ሀገራዊ የሆኑ ውድ ውድ ስሞችን ተሸክመው እንዴት እስከ ዛሬ እንደረከሱ ይገርመኛል። ዋልያ የተሰኘ ብርቅዬ እንስሳችን መጠሪያው አድርጎ፣ ኒያላ የተባለው ተወዳጅ ልዩ ብርቅዬ እንስሳን የፓኮው ስያሜ አድርጎ አራክሶ ሲቸበችም ዝም ያልነው እኮ ስያሜያቸውን አይተን እንጂ ውስጡ ያሉትን ጤናን አቃዋሽ ጉዶችን አክብረን አልነበረም። ስለጤፍ መወደድ፤ ስለ ኑሮ ጣራ መንካት ግድ ሰጥቶት የማያውቅ ሰው እንዴት ሲርበው በልቶ፤ ጠግቦ ለሚጠጣው ኦክስጂን ሰልችቶኛል ሲጃራ ነው አምሮቴ ብለው ያኮርፋል? በነገራችን ላይ፤ ሱሰኞቹ “እኛን ብቻ ለምን?” በማለት ሲሞግቱ ነበር አሉ። በጫትና ሌሎች ነገሮች ላይም ታክስ ይጨመር፤ ካልሆነ ከሌላው በተለየ የእኛ መብት ተገፋ፤ በደል ተፈጸመብን” በማለት ሲሟገቱ ከረሙ የሚል ጭምጭምታ ሰምተናል። ስለትውልድ ሲታሰብ፤ የትውልዱን መለወጥ ሀገራዊ ለውጥ መሆኑ ይታመንበታልና ትውልድ ገዳይ፤ ሀገር አጠልሺ የሆኑ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ማስቆም፤ አሊያም የሚቀንሱበትን መንገድ ማበጀት ከሀገሬው የሚጠበቅ ነውና ጠቃሚው ተተገበረ። እርግጥ ይህ ሲታሰብ መልካምነቱ የማይካድ፤ ውጤቱም አመርቂነቱ የማይታበይ ሀቅ ነው። ታዲያ ጠጪዎች ይሄንን ማን ጋረደባቸው? ስለ ሀገሩ የሚያስብ፤ ስለ ትውልዱ የሚጨንቀው እንዴት “እኔ ፍላጎቴን ላስታግስ እንጂ ስለሌላው ምን ገዶኝ” ይላል? ሰው ሀገሩንና ህዝቡን ሊወድድ ለውጡንም ሊመኝ ይገባል። ሀገራዊ ለውጥንና እድገትን የወደደ ደግሞ ስለ ሀገሩ መልካም ያስባልና እንዴት መልካም የሆነ ሀገራዊ ነገር ይጠላል? እናም ውዶቼ ሀገራዊ ራዕይ ያለው የትውልድን መልካም ፍሬ ማየት የሚወድድ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮችን የሚያርቅ አዋጅ አይደለም ሊያሳድድ ሊደግፍ ይገባል። ትልቅ ሀገራዊ አላማ ያለው ስለ ለውጥና እድገት በእጅጉ የሚመኝ ሲጃራን “እምቢ” አልኮልን “አይ” ማለት ነው ያለበት፤አንድ ታወቂና በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁንጮ የሆነ አየር መንገድ በደንበኞች አያያዝና በመስተንግዶው ተወዳጅ ስለሆነ ብዙ መንገደኞች ይመርጡት ነበር። አንድ ሰው ከመኖሪያ አካባቢው ወደ ሌላ አገር መሄድ ይፈልግና ይህን አየር መንገድ ይጠቀማል። በአውሮፕላን ውስጥ አስተናጋጆች ደንበኞችን በልዩ ትህትና እያስተናገዱ ወደአንደኛው ሰው ይጠጋሉ። ቀድሞ የጠቀስነው ተጓዥ አጠገብ የደረሰች አንዲት መልከ መልካም አስተናጋጅ፤ ወደሰውዬው ቀርባ በእጇ የያዘችውን መጠጥና ብርጭቆ ታቀርባለች።የአስተናጋጇ ፍላጎት የደንበኛዋ ጉዞ በፍስሀ እንዲሞላና ሳይሰላች እንዲያሳልፍ ነውና ፈገግታ ተላብሳ አንድ ውድ የአልኮል መጠጥ ከብርጭቆ ጋር አቀረበች። ሰውዬውም እጅግ ትህትና በተሞላበት ሁኔታ ይቅርታ ጠይቆ እንደማይጠጣ ይገልፅላታል። አስተናጋጇ ከዚያ በፊት ይህንን ውድ መጠጥ በፍቅር ይጠጡት የነበሩ ደንበኞቿን እያሰበች በማነፃፀር እየተገረመች ሰውዬውን ትመለከተውና በድጋሚ ጠጋ በማለት “ሌላ አይነት መጠጥ ይሁንልዎ” ብላ ትጠይቀዋልች። ሰውዬው ግን ከአቋሙ ሳነቃነቅ በድጋሚ አለመፈለጉን ይነግራታል።አስተናጋጇ ደንበኛው በሆነ ጉዳይ ተከፍቶ እንጂ ይህንንማ አያልፈውም ነበር በማለት ለአለቃዋ ሄዳ ስለ ጉዳዩ ትነግረዋለች። አለቃዋም ከርስዋ ይበልጥ በመገረም “በሌላ በሚምያር ብርጭቆና ማራኪ በሆነ መልኩ በድጋሚ አቅርቢለት” በማለት ያዝዛታል አስተናጋጅዋን፤ አደረገችው። ግን የተለወጠ ነገር የለም። ይሄኔ አለቅየው እራሱ ቀርቦ ሰውዬውን ማናገር ይጀምራል።“ጌታዬ ችግር አለ? መስተንግዶዋችን አልተመ ቸዎትም? ምን እናስተካክል?” እያለ ትህትና የተላበሱ ተከታታይ ጥያቄዎችን ያቀርባል። ሰውዬው ፈገግታ በተሞላበት መንገድ ምላሹን ሰጠ። “አይ መስተንግዶዋችሁም በጣም ጥሩ ነው፤ ነገር ግን እኔ መጠጥ አልጠጣም” ይለዋል። ይሄኔ ኃላፊው ተገርሞ “እንዴ ለምን?” ብሎ ጠየቀው። ለዚህ ምላሽ ግን የሰጠው መልሶ እራሱን በመጠየቅ ነበር። “እስኪ ለኔ ልትሰጠኝ ካሰብከው ፊት ለፊት ባለው በር ከፍተህ ግባና ለፓይለቱ ስጠው በኔ ፋንታ ይጠጣ” ብሎ ጠቆመው።ይሄኔ ኃላፊው “እንዴ! እሱማ እንዴት ይጠጣል? ይሄን ማደረግማ አይችልም የስንት ሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። ስለዚህ እሱ የመጠጥ ሽታም ሊደርስበት አይገባም።” በማለት ፓይለቱ በመጠጣቱ ሊደርስ የሚችለው አደጋ ዘረዘረ። ተጓዡም የሚፈልገው እንዲህ እንዲለው ነበርና በመልሱ ላይ የራሱን አስተያየት በማከል የማይጠጣበት ምክንያት ተናገረ። “ወዳጄ እኔ የራሴ የሆነ ልዩ ዓላማ አለኝ አላማዬን ከስኬቱ እንዳደርስ ጥንቁቅ መሆን አለብኝና “ፈፅሞ አልጠጣም” ያልኩት ለዚህ ነው። በማለት መለሰለት።እናም ዓላማ ያለው፤ እሩቅ መጓዝ ያሰበ እርግጥም እራሱን ሆኖ የትኛውም ቦታ ይደርሳል። ሰሞኑን የወጣውን የኤክሳይዝ ታክስ ተከትሎ በመጠጥና በዘር ማንዘሮቹ፤ በሲጃራና በግብረ አበሮቹ ላይ የተደረገውን የታክስ ጭማሪ ጥቅም በትክክል ከተረዳን ጠጪዎችንና አጫሾችን ቢያስከፋም እነሱኑ የሚያድን መራራ መርፌ ነው። እናም በደንብ መውጋት/መወጋት ነው። ኧረ እንዲያውም ከፍ አድርጎ። ቸር ይግጠመን! አዲስ ዘመን የካቲት 16/2012ተገኝ ብሩ
https://www.press.et/Ama/?p=27764
103544261bbaba6529acf8c34e1db0e4
45ce0bb182143b58cebebdfdf922ef5d
ሹል ሹል !
መዝናኛ
ሱራ ሽቅብ ሽቅብ ያቃስታል። ግዝፈቱ ያስጨንቀዋል። ልብስ አይበቃውም። የጫማው ቁጥር 48 ነው። የትከሻው ስፋት የሰውነቱ ግዝፈት የቁመቱ ርዝመት የሰማይ ስባሪ አስመስለውታል። አባ ግድየለሽ ሱራ ወግ ጨዋታ ይወዳል። ሰው አያስቀይምም። ውፍረቱ አስፈሪ አስደንጋጭ ነው።የሰፈሩ ሰው ልጆች ሲያለቅሱና ሲረብሹ ዋ ሱራን ነው የምንጠራው ሲባሉ ያውቁታልና በፍርሀት ርደው ጭጭ ነው የሚሉት። ሲደሰትም ሲከፋም ሱራ የአላህ ልጅ፤ የአላህ ወዳጅ የሚለው ነገር አለው። ለወላጆች ምነው ምነው ሕጻናቱ እንዲጠሉኝ እንዲፈሩኝ ባታደርጉ ምን አደረኳችሁ ይላል – ሱራ። በዛ ቁመቱና ውፍረቱ ሲንጎማለል ሲታይ የሞላለት ቱጃር ይመስላል። ጫማ ሰፊው ሱራ በቀን ሰርቶ ከሚያገኘው ውጭ ምንም የለውም። እጁ ሲያጥር ደምበኞቹ ከሆኑት ሴቶች ይበደራል። የድሀ ገንዘብ አታድርገኝ ይላሉ – እማማ ጌጤ። ከቀናት በኋላ ሴቶቹ ከች ይሉና ብር መልስ ይሉታል። አንተ ሱራ ስማ እንጂ የተበደርከውን አታመጣም፤ አላበዛኸውም እንዴ እያሉ ሴቶቹ ወገባቸውን ሲነቀንቁበት ይጨነቃል። ሂጂ እዛው ምን ወገብሽን ትሰብቂያለሽ ይላል ሱራ፤ ሶርሷራው። ተናገር ምንድነው ሂጂ እዛው አንተ አይደለህም እንዴ ስንቱን … ይሉታል። ኧረ በሕግ አምላክ ስሜን አታጥፉ አልደረስኩባችሁም ይላል እንደ ማፈር ብሎ።ጫማው መስፊያ ጎን ያሉት እማማ ጌጤ ይቺ ሙጢ አሁን እውነት ሱራ ቢጠጋት ትተርፋለች፤ ሹል አፍ ሙጢ እንደው መቀላመድ ትወዳለች ልጄ አሉና አጉተመተሙ። የመንደሩ ሴቶቹ የተቦተረፈ ጫማቸውን ይዘው ስፋልን እያሉ የሚወስዱት ለሱራ ነው። ብዙ የሴት ወዳጆች አሉት። አንዳንዶቹ የሚበላው ቋጠር አድርገው ያመጡለታል። አላህ እናንተን ባይጥልልኝ ኖሮ ምን እሆን ነበር ይላል ሱራ። ሱራ የሰማይ ስባሪው ሲሉት እናንተ ኮስማኖች በልታችሁ አይጠጋችሁ፤ ነገር ስትበሉ ውላችሁ ታድራላችሁ ፤ታዲያ ሱራ ምን ያድርጋችሁ ይላል። መኖሪያ ቤቱ የቀበሌ ቤት ነች። ግን ማንንም አያስገባም። ቤት ውሰደን ሱራ ሲሉት ደሞ ምን ቀራችሁ፤ ከእኔ ቤት ምን ጉዳይ አላችሁ ይላል። ቤት እየመጡ እሱ ሲሰራ እየተቀመጡ በዚህ መዘዝ ድሮ ምን እንደመጣበት ሱራ ሲያስታውሰው ይዘገንነዋል። ራሱ አብስሎ ይመገባል። አንዳንዴ በጎርናና ድምጹ ያንጎራጉራል። ሱራ የአላህ ወዳጅ… የአላህ ልጅ እያለ። ተናግረው ሊያናግሩት ሲነካኩት አሁን ከእኔ ምን ታገኛላችሁ ተውኝ ስራ የላችሁም ይላል። ጫማ መስፋቱን ይቀጥላል። ይህን ዝምታ የወረሰው በደርግ ዘመን ከደረሰበት ችግር በመነሳት ነው። በማያውቀው ነገር ሊሞት ነበር። ጫማ የሚሰፋባት አንዲት ክፍል የኪራይ ቤት ነበረችው። ከበውት የሚውሉ የሚያመሹም ነበሩ።ፖለቲካ አይወድም። እሱ ጋ የሚገቡና የሚወጡት ወጣቶች በዛን ዘመን ኢህአፓዎች ነበሩ። ወረቀት የሚበትኑ፤ ግድግዳ ላይ ቀለም የሚቀቡ፤ በቀይ ቀለምና በቀይ ጨርቅ ሀገሩን የሚያሸበርቁ። በፌስታል አምጥተው ሱራ የማያውቀውን እቃ ወረቀት ምናምን አመጣን ሱራየ ይቺ እዚህ ጋ ትቀመጥ ሲሉት ሱራ በመጡ ሰአት ተመልሰው ይወስዱታል እያለ ጫማውን መስፋት ይቀጥላል። የሚያውቀው ነገር የለውም ምስኪኑ ሱራ። እቃቸውን አይነካም። ተጠራጥሮም አይሸፍንም። በል ሲለው ያንጎራጉራል። ሱራ የአላህ ወዳጅ የአላህ ልጅ የምትለዋ ቃል ከአፉ አትጠፋም። በዚህ ይታወቃል። ጊዜው 1969ዓ.ም ነው። አዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ። ሀገር ምድሩ ታምሷል። አንድ ቀን ቀበሌው የኢሕአፓ ወጣቶችን እያሳደደ ማሰር ሲጀምር እንዴ እነሱማ ተሰብስበው የሚውሉት ሱራ ጫማ ሰፊው ቤት ነው የሚል ጥቆማ አብዮት ጠባቂዎች ይሰጣሉ። ይታሰር ተብሎ ጠመንጃ ተሸክመው ሱራ ጋ ይሄዳሉ። ሱራ አይሞቀው አይበርደው አባ ግዴለሽ። እንደውም ቤቱ ይከበብ ተብሎ ከውጭ ብዙ ጥበቃዎች ይከቡታል። ሱራ ጫማውን አቀርቅሮ ይሰፋል። መሳሪያ ደግነው ዘው ብለው ገቡ። እጅ ወደ ላይ አሉት። ሱራ የአላህ ወዳጅ አለና ጠመንጃው ምን ያደርጋል ለአንድ ድሀ ጫማ ሰፊ የእኔ እጅ ስራ ይዟል ለምንድነው እጄን ወደላይ የማደርገው በእንጀራዬ ለምን መጣችሁ ይላቸዋል። ና ውጣ አንተ ኢህአፓ አሉት። ሱራ መለሰ ምንድነው ኢሕአፓ አላቸው። እሱንማ አንተ ታውቃለህ በደምብ ትመልሳለህ አሁን እስረኛ ነህ ና ውጣ ቀበሌ እንሂድ አሉት። ተውኝ ቢል ማን ሰምቶት። እያመረሩ ሄዱ። ሌሎች ሱራ ቀበሌ ሂድላቸውና ቃልህን ስጥ ምን ትሆናለህ አሉት። ሱቁን ቆለፈና በብዙ አብዮት ጠባቂዎች ታጅቦ የሠማይ ስባሪው ሱራ ቀበሌ ጽህፈት ቤት ገባ። ግቢው ውስጥ እሱ ጋ ገባ ወጣ ከሚሉት ወጣቶች ውስጥ የታሰሩ እንዳሉ አየ። ጮክ አለና ምን ሰርቃችሁ ነው የተያዛችሁት አላቸው። አብዮት ጥበቃዎቹም ወጣቶቹም ሳቁ። ሱራ ለምርመራ ገባ። ጠያቂዎቹን ያውቃቸዋል። የጫማ ደምበኞቹ ናቸው። ጫማቸው ሲቀደድ የሚሰፋላቸው።ሱራ አንተም አሉት። ተገረመና ምን አላቸው። ኢህአፓ አሉት። ምንድነው የምትሉት እሱን ሰውየ አላውቀውም። ቅድምም አብዮት ጥበቃዎቹ እንደሱ አሉኝ። የእኔ የጫማ ደምበኛ አይደለም። አሰርቶ አያውቅም። እኔም አላውቀውም አላቸው። ሱራ የአላህ ወዳጅ የአላህ ልጅ አለ ሰው በተሰበሰበበት። እስኪጣራ ታስረህ ትቆያለህ አሉት። ክፉኛ አዘነ። አላህ እንደ ስራየ ይስጠኝ፤ በተንኮል ለወነጀሉኝም ፍርዱን ይስጥ አለ- ደገመና። እስር ቤቷ ውስጥ ግዙፉ ሱራ አንገቱን አዝምሞ ገባ። ታሳሪው በተጨናነቀው ቤት ውስጥ ለሱራ ተጣበው ቦታ ሰጡት። ግድግዳውን ደገፍ ብሎ እንደቆየ ድብን አድርጎ እንቅልፍ ወሰደው። ማንኮራፋት ጀመረ።ቢጠሩት መች ሰምቶ። ለሊቱን እነዛን ልጆች ወደማይታወቅ ስፍራ ወስደዋቸዋል። ሲነቃ ልጆቹ የሉም። የሰፈሩ ሰው ሱራ ቀበሌ መታሰሩን ሲሰማ በእጅጉ አዘነ። ከፊሉ አሽሟጠጠ። ደሞ ሱራ ብሎ ፖለቲከኛ እያለ። ጠጅ ቤት መነጋገሪያ ሆነ። ሱራ ታሰረ— ሱራ ታሰረ — ባዩ በዛ። የሰፈሩ ሰው ጫማ የሚሰፋላቸው ሴቶች እየተጋገዙ ምግብ ያቀብሉት ጀመር። ቀለብ የማያገኙት እስረኞች ረሀባቸው ጠፋ። ሱራ ሱራ አሉት አቤት አላቸው። እንኳን ታሰርክ እንዲያውም መውጣት የለብህም አሉት። ተንከትክቶ ሳቀ። አንተ በመታሰርህ እስር ቤቱ ምግብ በምግብ ሆነ ሲሉት ቀበል አደረገና እኔ ፖለቲካ አላውቅም። ጫማ ሰፊ ነኝ። እኔን በሀሰት በወነጀሉኝ ሰዎች ላይ አላህ ፍርድ ይስጥ፤ ሱራ የአላህ ወዳጅ የአላህ ባሪያ አለና አይኖቹ በእምባ ተሞሉ። አይዞህ ሱራ አሉት። አይዞህ አይዞህ ሱራ። ለሊት በቀበሌያቸው አካባቢና ዙሪያ የቀለጠ ተኩስ ተሰማ። እስረኞቹ በተኙበት ይሰማሉ። ሱራ አላህ –አላህ ይላል። የመትረየሱ ድምጽ ተረረረረረም ሲል ሱራ አላህ ድረስ፤ የታሰሩት ልጆች አውጣን አውጣን ሆነ። አይነጋ የለም በጭንቅ ነጋ። ጠዋት ለሽንት ሊወጡ ሲሉ ሱራ ነበር የቀደመው። ያገኛቸውን ሰዎች ምንድነው ጉዱ አላቸው። መጥተው ፈጅተውን ሄዱ፤ አመለጡ አሉት። እነማን ናቸው አላቸው – ሱራ። ኢህአፓዎቹ ናቸዋ አሉት። ሰው ተጎዳ ብሎ ጠየቀ። ምን ሰው ተረፈ ብለህ ነው። በቀደም አንተን ከሱቅህ አስረው ያመጡህ በሙሉ ሞተዋል አሉት። ምን አለ ሱራ ደንግጦ። ደገመና ሱራ የአላህ ወዳጅ የአላህ ልጅ። እቺ ኢህአፓ የምትሏት አላህ ነች እንዴ አለ ሱራ። ሰዎቹ በሳቅ አሽካኩ። ሱራ ሱራ።ወንድወሰን መኮንንአዲስ ዘመን የካቲት 19/2012
https://www.press.et/Ama/?p=27990
c0955776ed2d1a7532f52f3febdc8ac1
cb3df388848d7e3e3cde1caf920c5062
የአርባ ሰባት ዓመታት ትዝታ የቀሰቀሰው ቀለበት
መዝናኛ
 ብዙ ጊዜ ጌጣጌጦች ጠፉ ሲባል ቢሰማም ፈልጎ የማግኘቱ ጉዳይ እንደ መግዛቱ ቀላል አይሆንም። በተለይ የወርቅ ጌጣ ጌጥ ጠፍቶ የመገኘት እድሉ ጠባብ ነው።ወርቅ ውድና ተፈላጊ እንደመሆኑ ያገኘውም ሰው ቢሆን የጠፋበትን ባለቤቱን አፈላልጎ ይሰጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።ሊገኝ የሚችልበት እድል አንድና አንድ ብቻ ነው። ሰው እጅ ያልገባ ከሆነ ብቻ።ይህ ሲሆን ከእለታት አንድ ቀን ሊገኝ ይችል ይሆናል። የጌጣጌጦች መጠን አነስተኛ መሆን ከሚጠፉበት ቦታ ውስብስብነት ጋር ተዳምሮ የመገኘት እድላቸውንም በእጅጉ ያጠበዋል። በዚህም የጠፉት ጌጣጌጦች ከናካቴው ተሰውረው ሊቀሩ አልያም ጥቂት ጊዜ ፈጅተው ባጋጣሚ ሊገኙ ይችላሉ ።ጌጣጌጦች ከጠፉ ረጅም አመታትን አስቆጥረው ሲገኙ ግን ግርምትን ያጭራሉ። ስካይ ኒውስ ከሰሞኑ ከወደ አሜሪካ ይዞት ብቅ ያለው መረጃም ይህንኑ ሃቅ ያረጋግጣል። በ1973 ገና አፍላ ወጣት የነበረችው ዴብራ ሜኬና ብረንስዊክ ሜይን በተሰኘችው የአሜሪካ የባህር ዳርቻ ከተማ በሚገኝ አንድ የእቃ ማስቀመጫ ክፍል ውስጥ ባሏ ያደረገላትን ቀለበት ትጥላለች። ቀለበቱ ከጠፋ ከአርባ ሰባት አመታት በኋላም በቅርቡ በአንድ የብረት ሰራተኛ በፊንላንድ ደን ውስጥ ተቀብሮ ተገኝቷል። ሜኬና በአሁኑ ወቅት 63 ዓመቷ ሲሆን፣ በሞርስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እያለች በፖርትላንድ ውስጥ ቀለበቱ እንደጠፋባት ባንጎር የተሰኘው ጋዜጣ በወቅቱ ዘግቦ እንደነበር ድረገጹ አስነብቧል። ትምህርት ቤቱን የሚለይ ምልክት ያለበት ይኼው ቀለበት የቀድሞ የሜኬን ባል በትምህርት ቤትና በኮሌጅ ተገናኝተው ሲያወሩ ያበረከተላት እንደነበር ታውቋል። ባለቤቷ ሻውን ለስድስት አመታት ያህል ከያዘው የካንሰር ህመም ጋር ሲታገል ቆይቶ በ2017 ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ባልና ሚስቶቹ ለአርባ አመታት ያህል በትዳር መቆየታቸውም ተጠቅሷል። ሸዋን የኮሌጅ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ቀለበቱን ለሜኬን የሰጣት ሲሆን፣ ሆኖም መጋዘን ውስጥ በድንገት እንደጣለችው አስታውሳለች።የብረት ሰራተኛው ቀለበቱን ከተቀበረበት እስካገኘበት ጊዜ ድረስ ተረስቶ እንደነበርም ገልፃለች። የብረት ሰራተኛው ሰማያዊ ፈር ያለውን ብራማ ቀለበት ሲያገኝ የብረት መመርመሪያ ተጠቅሟል፤ ብዙ ጊዜ ያገኝ የነበረው ግን የብረት ኩባያ ወይም ቁራጭ ብረት እንደነበረም የፊንላንድ ሚዲያ ዘግቧል። በቀለበቱ ላይ የተፃፈውን የትምህርት ቤት ምልክትና የምርቃ አመተ ምህረት በመያዝ አልሙኒ ከተሰኘ ማህበር ጋር እንደተገናኘም ሚዲያው ጠቅሷል። በዚሁ መሰረት መኬን ከረጅም አመታት በፊት የጠፋባት ቀለበት እንደተገኘና መውሰድ እንደምትችል በስልክ ሲነገራት እምባ እንደተናነቃትና የወጣትነት የፍቅር ጊዜዋን እንዳስታወሳት ገልፃለች። ‹‹ቀናነት በጎደለበት በዚህ ዘመን እንደዚህ አይነት ሰዎችን ማግኘት በጣም ይከብዳል›› ስትልም ተደምጣለች። ‹‹በአለማችን ጥሩ ሰዎች አሉ፤ ስለዚህ ተጨማሪ ጥሩ ሰዎችን እንፈልጋለንም›› ብላለች። ሜኬና ከጠፋ ረጅም አመታትን ያስቆጠረው ቀለበት እንዴት በፊንላንድ ደን ውስጥ ሊገኝ እንደቻለ ምንም የምታውቀው ምክንያት እንደሌለ አስታውቃለች። ምን አልባት ባለቤቷ ሹዋን በ1990ዎቹ አካባቢ አብዛኛውን ጊዜውን በፊንላንድ ያሳልፍ በነበረበት ወቅት እሱን ብላ ስትሄድ ቀለበቱ አካባቢው ላይ ሳይጠፋ እንዳልቀረ ጠቅሳለች። አዲስ ዘመን የካቲት 17/2012አስናቀ ፀጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=27863
e5b9bea8a620314d538c9dea92964481
b04d8a4613cbc6c23257e0e4a3ac13dd
ኮሮና ቫይረስን በአሻንጉሊት
መዝናኛ
የኮሮና ቫይረስ በተለያዩ የአለም ክፍሎች እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሉ ህዝቦች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል። አለም አቀፍ የሰዎች እንቅስቃሴም እንደወትሮው ሊሆን አልቻለም። በተለይ ደግሞ የቫይረሱ መገኛ በሆነችው ቻይና ሰዎች ቫይረሱ እንዳይዛቸው በተቻላቸው አቅም ሁሉ ራሳቸውን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ከሰሞኑ በሀገሪቱ ደቡብ ምእራብ ሲሽዋን ግዛት በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ህሙማንን ለመጎብኘት የመጣችና ስሟ ያልተጠቀሰ አንዲት ወይዘሮ ራሷን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ያደረገችው ጥረት ግን ብዙዎችን አስፈግጓል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል በድረገፁ አስፍሯል። በማህበራዊ ትስስር ገፅ በተለቀቀው በዚህ አጭር ቪዲዮ ወይዘሮዋ ከፊትለፊት ለማየት የሚያስችል አነስተኛ የመስታወት መስኮት ያለው ግዙፍ የቀጭኔ ቅርፅ ያለው የፕላስቲክ አሻንጉሊት ልብስ ለብሳ በሆስፒታል ውስጥ ስትንቀሳቀስ ትታያለች። ‹‹ለምን ይህን ግዙፍ የፕላስቲክ ቀጭኔ አሻንጉሊት ልብስ ለበሽ? የሚል ጥያቄ ይቀርብላታል። ወይዘሮዋ የኮሮና ቫይረስ በቻይና ከመከሰቱ በፊት አባቷ በመተንፈሻ አካል ችግር በሆስፒታሉ ብዙ ጊዜ ህክምና ሲከታተሉ አጥብቃ ትጠይቃቸው እንደነበር አስታውሳ፣የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ በኋላ አባቷን መጠየቋን አቁማ መቆየቷን ተናግራለች። በቅርቡ ግን ይህች ወይዘሮ አባቷን ለመጠየቅ ወደ ሆስፒታሉ ትመጣለች። በወቅቱም ሃኪሞች ፊቷን እንድትሸፍንበት የህክምና ጭምብል ይሰጧል።እሷ ግን ጭምብሉ የአገልግሎት ጊዜው ያለፈበት ነው በሚል ስጋት የኮሮና ቫይረስን በአስተማማኝ መልኩ ለመከላከል ግዙፉን የቀጭኔ አሻንጉሊት ልብስ ለመልበስ እንደወሰነች ገልፃለች። ‹‹ሃኪሞቹ የሰጡኝ የህክምና ጭምብል የአገልግሎት ጊዜ ያለፈበት ነው። በገበያ ላይም እንደልብ አይገኝም። በመሆኑም አሻንጉሊቱን ለመልበስ ተገድጃለሁ›› ስትልም ወይዘሯዋ ተናግራለች። ይህን እንግዳ ድርጊት የታዘቡት የሆስፒታሉ ሰራተኞችም ቪዲዮ በመቀረፅና በማህበራዊ ትስስር ገፅ በመልቀቅ በርካታ ቻይናውያን ፈገግ አሰኝተዋል። አዲስ ዘመን የካቲት 17/2012አስናቀ ፀጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=27860
fd4c1bcfdaa8448b23a6dbab94df4514
83fd508b17a12bd06e0c4b273852a71a
አማራጭ ሃሳብ አምጡ!
መዝናኛ
ከብዙ ጊዜያት በፊት በአንድ አገር ውስጥ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ነበሩ። እነርሱንም የሚያስተዳድር አንድ ንጉሥም ነበር። ይህ ንጉሥ የሚያስተዳድራቸውን ነዋሪዎች በደስታ ያኖራቸው ነበር። በእሱ የአገዛዝ ዘመን ሁሉም ነዋሪዎች በነፃነት ተገቢውን ነገር በማድረግ በሰላም ኑሯቸውን ይመራሉ። ንጉሣቸው እርሱ በመሆኑም በጣም ደስተኞች ነበሩ። በአንድ ወቅት ንጉሡ በአገሪቷ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን፣ የአምልኮ ስርዓት የሚፈፀምባቸው ቤተክርስቲያናትን እንዲሁም እርሱ በአገዛዙ ወቅት ያልተመለከታቸውን እና በርቀት ያሉ አካባቢዎችን ለመመልከት ይወስናል። እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው እርሱ የሚያስተዳድራቸውን ቦታዎች ለማወቅ እና ሁሉም ስፍራዎች ምቹ እና የማህበረሰብ ክፍሎችም በሰላም እና በተድላ መኖራቸውን ለማረጋገጥ ስለፈለገ ነበር።ንጉሡ ጉብኝቱን በእግሩ በመጓዝ ለማድረግ ይወስናል። አገልጋዮቹን እና አብረውት የሚጓዙ ቤተሰቦቹንም ከእርሱ ጋር በእግራቸው እንዲጓዙ አደረገ። ንጉሡ ይህንን ለማድረግ የወሰነበት ምክንያት በቀላሉ የሚያስተዳድራቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲያገኝ ስለሚያስችለው ነበር። በዚህ የተነሳ እርሱ ጉብኝት በሚያደርግባቸው አካባቢዎች የሚያገኛቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ንጉሣቸውን በማግኘታቸው እና ከእርሱም ጋር በማውራታቸው ፍፁም ደስተኛ ሆኑ። እነርሱ በዚህ ንጉሥ ስር ስለሚተዳደሩ እና ቅን ልቦና ያለው መሪ ስላላቸው ደስተኞች ሆኑ። ይህ ቅን ንጉሥ በርካታ የአገሩን አስደናቂ ቦታዎች መመልከት ቻለ። ታሪካዊ ቦታዎችን፣ የእምነት ስፍራዎችን በተፈጥሮ የተዋቡ አካባቢዎችን እንዲሁም በርካታ ባህል ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን ማግኘት በመቻሉ በጣም ደስተኛ ሆነ። አገሩ እጅግ የበለፀገች በመሆኗም የሚያምነውን አምላክ አመሰገነ። ይህ ንጉሥ በሚደርስበት አካባቢ ሁሉ እጅግ በከበረ ሁኔታ አቀባበል ይደረግለት ነበር። ነዋሪዎቹም ቅን እና ለማህበረሰቡ ከልቡ አሳቢ በመሆኑ እጅ እየነሱ ያመሰግኑታል። ከብዙ ቀናት የጉብኝት ቆይታ በኋላ ጉብኝቱን አጠናቀቀ ወደ መኖሪያ ስፍራውም ደስተኛ ሆኖ ተመለሰ። እርሱ የሚያስተዳድራቸው ሰዎች በተድላ እና በደስታ መኖራቸውንም በዓይኑ አይቶ መመስከር ቻለ። ሁሉም ነዋሪዎች ኑሯቸውን ያለምንም ችግር ይመሩ ነበር። አብዛኞቹ በግብርና ሥራ፣በከብት ማርባት እና በብረታብረት ምርት ላይ አድርገው ነበር። ኑሯቸውን የሚያቀልላቸው አዳዲስ ማሽኖች ይፈጥሩ እና ይገለገሉባቸውም ነበር። ነገር ግን ይህ ንጉሥ በጉብኝቱ ወቅት አንድ ያዘነበት እና ቢስተካከል ብሎ ያሰበው ጉዳይ ነበር። ረጅም ርቀት በመጓዝ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት እግሩን በጣም ታሞ ነበር። እግሩን የሚከላከልለት ምንም ነገር ስላልነበረም በጣም ለሚያስጨንቅ ህመም ተዳርጓል። የውስጥ እግሩም ቆስሎ መሬት ለመርገጥ በጣም ተቸግሮ ለትንሽ ጊዜም ቆየ። ባለሟሎቹ እና ቤተሰቦቹ በተፈጠረው ነገር በጣም በማዘን በቶሎ እንዲያገግም ዕርዳታ ያደርጉለት ጀመር። ከህመሙ እንዳገገመ አንደኛውን ሚኒስትሩን በመጥራት ስለተፈጠረው ነገር አናገረው። እንዲህም አለው «አገሪቷ ላይ ያሉትን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ሃይማኖታዊ ስፍራዎች በመመልከቴ በጣም ደስተኛ ነኝ። ህዝቦቼም በተድላ እና በደስታ በመኖራቸው እረክቻለሁ። ነገር ግን አንድ ጉዳይ አላስደሰተኝም። ይህም የተጓዝንበት መንገድ በጣም የማይመች እና ኮሮኮንቻማ ነበር። ጠጠር እና ሹል ድንጋዮችም ይበዙበት ነበር። እኔ ለጥቂት ግዜያት በእነዚህ አካባቢዎች ስጓዝ ይህ ችግር አጋጥሞኛል። ነገር ግን ሁል ጊዜ በእነዚህ መንገዶች የሚገለገሉት ህዝቦቼ ምን ያክል ይሰቃያሉ? ይህ ጉዳይ ለህዝቤ ምቾትን የሚቀንስ እንደሆነ ተረድቻለሁ። ነገሩ በጣም አሳስቦኛል» አለው። ለሚኒስትሩ ይህን ካለው በኋላ እንዲህ በማለት ትዕዛዝ ሰጠ « በሁሉም መንገዶች ላይ የበሬ ቆዳዎችን አንጥፉ። በዚህ ምክንያት ህዝቦቼ እንዲሰቃዩ አልፈልግም። ይህን ቆዳ ካነጠፋችሁ ግን ሁሉም ሰው በምቾት መንቀሳቀስ ይችላል» አለው። ሚኒስትሩ ንጉሡ ይህን ሲል በመስማቱ በጣም ግርምት እና ጥያቄ ተፈጠረበት። ምክንያቱም የንጉሡን ትዕዛዝ በማክበር እነዚህ ቆዳዎች እንዲነጠፉ ቢደረግ በጣም በብዙ መቶ ሺ የሚገመቱ ከብቶች መሞት ይኖርባቸዋል። ይህ ደግሞ አርሶአደሩ ለወተት ምርት እና ለግብርና ሥራ የሚጠቀምባቸውን ከብቶች ሊያጣ ይችላል። በመንገዶቹ ላይ ቆዳውን ለማንጠፍ ደግሞ በጣም ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅ እና ከባድ ነበር። የአገሪቷን ሀብትም በቀላሉ የሚያጠፋ ነበር። በዚህ የተነሳም ከንጉሡ ትዕዛዝ ሲቀበልና ሲወያይ የነበረው ሚኒስትሩ ለሥራ አጋሮቹ ሃሳቡን አጋራቸው። እነሱም በእርሱ ስጋት ተስማሙ። በርካታ ገንዘብ እና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ከብቶች መጥፋቱ አሳሳቢ ሆነባቸው። ሚኒስትሮቹ በጉዳዩ ላይ በጣም ተጨንቀው መፍትሔ በማፈላለግ ላይ ሳሉ፤ ከመካከላቸው የነበረ አንድ ብልህ ሚኒስትር ሃሳብ እንዳለው ተናገረ። ይህን መፍትሔም ለንጉሡ ማቅረብ እንዳለባቸው ተስማምተው ሰውዬው ወደ ንጉሡ ዘንድ ሄደ። ሚኒስትሩ አማራጭ ነው ብሎ ያቀረበውን ሃሳብ ንጉሡ ጠየቀው። ሚኒስትሩም እንዲህ በማለት መለሰለት «ንጉሥ ሆይ መንገዱን በቆዳ ከመሸፈን ይልቅ፤ ለምን በእግር ልክ ተስተካክሎ የተቆረጠ ቆዳ ሁሉም ሰው አያደርግም። ይህ ሲሆን አንድ ቆዳ ብዙ የእግር ሽፋኖችን መሥራት ይችላል» በማለት መለሰለት። ይህ ብልህ ሚኒስትር ባቀረበው ሃሳብ ንጉሡ በጣም ተገረመ። ሃሳቡም በጣም ትክክል እና በቶሎ መተግበር ያለበት ጉዳይ እንደሆነ ተናገረ። ለሚኒስትሩ አድናቆት እና ሽልማት አበረከተለት። በቶሎም ለራሱ ሁለት ከቆዳ ላይ የተቆረጡ መሸፈኛ ጫማዎችን አዘዘ። ህዝቦቹም ልክ እርሱ እንዳደረገው ጫማ እንዲያደርጉ እና እራሳቸውን ከጉዳት እንዲጠብቁ ጠየቃቸው። ህዝቦቹም ንጉሣቸው ከልቡ እንደሚያስብላቸው በማወቃቸው እና የቀረበላቸውን ሃሳብ ስላስደሰታቸው በሃሳቡ ተስማሙ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ህዝቡ በተለያየ ፋሽን ጫማዎችን ማድረግ እና እግሮቹን ከጉዳት መከላከል ጀመረ። የተሻለ አማራጭ ሃሳብ ያለው ሁልጊዜም ተመራጭ ነው።አዲስ ዘመን የካቲት 22/2012ዳግም ከበደ
https://www.press.et/Ama/?p=28167
1dc366a9969be64642dd9a02872e5b34
f5fd5f8429954acd23718946efefed41
ደንበኞች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያልተጠቀምንበትን የታሪፍ ክፍያ እያስከፈላቸው መሆኑን አመለከቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
– አገልግሎቱ በደንበኞች የሚቀርቡ ማናቸውንም ቅሬታዎች ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ በጋዜጣው ሪፖርተሮች አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያልተጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ አገልግሎት እያስከፈላቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አመለከቱ። አገልግሎቱ በበኩሉ በደንበኞች የሚቀ ርቡ ማናቸውንም ቅሬታዎች ለመፍታት ዝግጁ መሆ ኑን አስታወቀ። የጋዜጣው ሪፖርተር በሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ቁጥር ሁለት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ያነጋገራቸው የአገልግሎቱ ደንበኛ ምንተስኖት ፍሬው፣ “ቤቴ የንግድ አይደለም፤ ነገር ግን በየወሩ የምከፍለው ከአንድ ሺህ ብር በላይ ነው።አሁን ደግሞ እጥፍ ጨምሮ መጥቷል። ይህ ሁሉ ያልተጠቀምኩበት ነው። ሰሞኑን ብመላለስም ደረሰኝ አልመጣም እያሉ ከሥራዬ እያስተጓጎሉኝ ነው።ችግራችንን ለመናገር የሚሰማን ሰው የለም።በተከታታይ አራት ቀን መጥቼ መፍትሔ አላገኘሁም፤ መስተንግዶው ደካማ ነው።መንግሥት ይህንን ተቋም እታች ድረስ ወርዶ መቆጣጠር አለበት።ክፈል ከተባልክ መክፈል ነው፤ ከዚህ ውጪ ሰሚ የለም” ሲሉ ምሬታቸውን ያስረዳሉ።ከዚህ በፊት አምስት ሺህ ብር ቆጠረ ተብዬ ዋናው መስሪያ ቤት ስሄድ አምስት ሺ ብሩ ስህተት ነው የቆጠረው ሰባት ሺህ ብር ነው ተብዬ ከስድስት ሺህ ብር በላይ ከፍያለሁ። በየወሩ አስር አስር ብር ሲቆጥር ሄጄ ሳመለክት ቀደም ሲል ከዚህ እላፊ ከፍለህ ስለሆነ አሁን የቆጣሪ ግብር ብቻ ነው የምትከፍለው ተባልኩ።መጨረሻ ላይ ግን ውዝፍ ክፍል አሉኝ።ከዚያ በኋላ የምከፍለው ብር በጣም ያማርራል ይላሉ።ይመርመርለኝ ስል ብር ክፈል ተብዬ ከፈልኩ፤ ከዚያ ብመላለስ ብመላለስ መፍትሔ በማጣቴ ተውኩት።እንደገና ቆጣሪ ይቀየርልኝ ብዬ ሳመለክት ከቀበሌ አጽፍ ተባልኩ፤ አጽፌ ስሄድ ከነጭራሹ ያንተ ፋይል የለም ብለው አናስተናድህም አሉኝ፤ የምሄድበት አካል አጥቼ ተቸግሬ ነው ያለሁት ብለዋል። በዚያው ጣቢያ ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ ሃምሳ አለቃ መስፍን ተሾመ ፣የችግሩን አሳሳቢነት እንዲህ ሲሉ ይገልጻሉ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚተዳደርበት ህግ ያላቸው አይመስለኝም።ጠይቀን የሚያስረዳንም አካል የለም።መቁጠሩ ብቻ ሳይሆን አለመተላለፉ ሌላኛው ችግር ነው።ተሯሩጠን እያደርን ጊዜያችን ያለ አግባብ እየባከነ ነው።ቆጣሪው ቆጥሮ ወደ ሲስተም አልተላለፈም በማለት በራሳቸው ችግር ምክንያት መጥተው አገልግሎት እንዳናገኝ እና የተለያዩ ቅጣቶችን ይጥሉብናል ብለዋል። ለመንግሥት ብር ለመክፈል ለምነን መሆን የለበትም፤ መጥተው በትክክል አንብበው ተገቢውን ክፍያ ሊጥሉብን ይገባል። ቀድም ሲል ሁለት መቶ ብር ይቆጥር ነበር፤ አሁን ምክንያቱን ሳናውቀው በዕጥፍ እንድንከፍል ተደርገናል።የተከሉትን ቆጣሪ በትክክል አይቆጣጠሩትም፤ አያነቡትም ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ።ላለፉት ሁለትና ሦስት ወር አልተነበበልኝም የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ፍቃደኛ ያልሆኑ ቅሬታ አቅራቢው ሳምንቱን ሙሉ ሥራ ፈትቼ ብመላለስም ቅሬታዬን መርምሮ መልስ የሚሰጠኝ አካል አላገኘሁም ብለዋል።በየወሩ የሚቆጥረው እየጨመረ ነው፤ ነገር ግን ለማን ማመልከት እንዳለብን ጠፍቶኝ በግራ መጋባት ውስጥ ነኝ።ከሥራ ገበታችን እየተስተጓጎልን ተሰልፈን ብንውልም ምክንያት ፈጥረው ሳንስተናገድ እንባረራለን። መንግሥት መፍትሔ ካልፈለገልን ችግሩ አሳሳቢ ከመሆኑም በላይ ሳንጠቀም በግዴታ እንድንከፍል እየተደረግን ሲሉም ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡን የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እንዳሉት ተቋሙ ከ2011 ዓ.ም ታህሳስ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ዓመት የሚቆይ የታሪፍ ማስተካከያ እያደረገ ሲሆን፤ በቅርቡም በታህሳስ ወር ሦስተኛውን ዙር ማስተካከያ አድርጓል።ይህ ደግሞ አገልግሎቱን ለማሻሻል ወሳኝ ነው። አገልግሎቱ አሁንም ቢሆን የሚያስከፍለው ታሪፍ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ ነው ያሉት አቶ ሽፈራው፤ ለአብነትም ይህንን ማስተካከያ ስናደርግ አንድ ኪሎ ዋት ሃወር ኤሌክትሪክ የመሸጫ ዋጋ 1ነጥብ 8 የኤሪካ ሳንቲም እንደነበርና በወቅቱ ግን ኬንያ ለአንድ ኪሎ ዋት ሃወር 15 ሳንቲም ታስከፍል እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡በሌላ በኩል አገልግሎቱ ታሪፍ ማሻሻያ እያደረገ ቢሆንም የአገልግሎት ማሻሻያ ሥራዎች ገና ብዙ ሥራ እንደሚቀራቸው የጠቀሱት አቶ ሽፈራው ሆኖም የአገልግሎት ጥራት ለማምጣት እየተሠራ ነው ብለዋል።ለዚህም በዘንድሮ በጀት ዓመት ለጥገናና ለአቅም ማሻሻያ አንድ ቢሊየን ብር የሚጠጋ በጀት ተመድቦ እየተሠራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡በሌላ በኩል አንዳንድ ደንበኞች የማይገባ ክፍያ መጠየቃቸው ትክክል አለመሆኑን አቶ ሽፈራው ጠቁመው፤ የይጣራልኝ ጥያቄ ሲያቀርቡም በቅድሚያ ክፈሉ የሚል አሠራር አለመኖሩን ተናግረዋል።ነገር ግን እንዲህ የሚያደርጉ ካሉ ተቋሙ ለማስተካከል ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ ሽፈራው እንደጠቆሙት ቆጣሪ በየወሩ መነበብና በዚያ መሰረት ክፍያ መፈፀም አለበት።ይህ ካልሆነ ግን ደንበኞች በየደረጃው ቅሬታቸውን ማቅረብ አለባቸው።ከዚህ ውጪ ግን የተጠራቀመ ሂሳብ እንዲክፈሉ ማድረግ ትክክል ባለመሆኑ እንዲህ ዓይነት ችግሮች ካሉ መታረም አለባቸው ብለዋል፡፡ተቋሙ ከደንበኞች ለሚነሱ ማናቸውም ቅሬታዎች በየደረጃው ተገቢውን ምላሽ ለመስጠትና ችግሮች ካሉ ለመፍታት ዝግጁ ነው ያሉት አቶ ሽፈራው ለዚህም ህብረተሰቡ ህጋዊ አሠራርን ተከትሎ ለሚያጋጥሙ ችግሮች እስከ ማዕከል ድረስ ቅሬታውን ማቅረብ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ አዲስ ዘመን ጥር 5 ቀን 2013  ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=39377
ffd8355d6b5840699a9ce61fc8199c2f
83ed0d6fb8409ceca5bffbd47834e8fa
በአማራ ክልል ከ328 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚሸፍን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሰላማዊት ውቤ አርማጮሆ፦ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዘንድሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በሚገኝ ከ328 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን የአማራ ቤሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በሥራው 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች እንደሚሳተፉ ገለጸ። በቢሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር ተወካይ እስመለዓለም ምህረት ለጋዜጣው ሪፖርተር እንዳስታወቁት ከትላንት ጀምሮ እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ከ20 እስከ 30 ለሚደርሱ ቀናት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራው በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ ከ328 ሺህ ሄክታር በላይ በሆኑ የማሳ፣ የቦረቦር መሬቶችና የተራራ ሥፍራዎች ስነ ሕይወታዊ ሥራዎች ይከናወናሉ።በተጨማሪም በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተፈልተው ከ182 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የመትከል የስነሕይወታዊ ሥራ የሚሠራ መሆኑን የጠቆሙት ተወካዩ ፣ በሥራው 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን የክልሉ አርሶ አደሮች፣ ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላትና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ይካፈላሉ ብለዋል።የተፈጥሮ ሀብት ሥራ ከዚህ ቀደም የግብርና ሥራ ተደርጎ ይወሰድ እንደነበረ የጠቀሱት ኃላፊው፣ ሥራው የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ይሄ ዓይነቱ አስተሳሰብ መቅረት እንዳለበት አሳስበዋል። ባለሀብቱ በእርሻ መሣሪያም ሆነ መኪናውን ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማጓጓዝ እንዲውሉ በመፍቀድ እንዲተባበርና የራሱን አስተዋፅኦ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራው ስነ አካላዊ፣ ስነ ሕይወታዊ፣ ዘላቂነትና ተጠቃሚነትን ያካተተ እንደሆነና የሥራው የመጨረሻ ግብም አፈር መቆለል፣ድንጋይ መካብና ጉድጓድ መቆፈር ሳይሆን ተጠቃሚነትን ማምጣትና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሆነ አመልክተዋል። ሥራውን ለማከናወን ባለፉት ወራቶች ሥራው የሚሠራባቸውን አካባቢዎችና ከ8 ሺህ 300 በላይ ተፋሰሶች የመለየት፣ ክፍተት ያለባቸውን ባለሙያዎች የማሰልጠንና ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን የማዘጋጀትና ሕብረተ ሰቡን የማወያየት ሥራዎች ሲሠሩ መቆየታቸውን አስታው ሰዋል። የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ ሥራ መነሻው ታች ከተፋሰስ መሆኑን የጠቀሱት ተወካዩ ፣ ይሄው ዝግጅት እስከ ቀበሌ መውረዱን አስታውቀዋል። ባለፈው ሳምንት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የግብርናው ዘርፍ ኃላፊዎች ባሉበት መግባባት ላይ ተደርሶ የጋራ መደረጉንና ትላንትና በይፋ መጀመሩን ጠቁመዋል። ቀደም ሲል ቦረቦር የነበሩ፣የተራቆቱ መሬቶችና ተራራዎች የነበሩና በተፈጥሮ ሀብት ሥራው በመለወጥ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንሰሳት መኖ፣ለማገዶ እንጨት የሚውሉ ዝሪያዎች የለሙባቸውና የእንሰሳትና የንብ እርባታ እየተካሄደባቸው የሚገኙ ሥፍራዎች በፌዴራል፣ በክልል፣በዞንና ከተለያዩ አካባቢዎች በመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ተጎብኝተውና ልምድ ተቀስሞባቸዋል ብለዋል።“ሥራው ዓመቱን ሙሉ የሚሠራ ነው›› ያሉት ተወካዩ፣ በአማራ ክልል የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ በተደራጀና በንቅናቄ መልማት የጀመረዉ በ2003 ዓ.ም መሆኑን አስታውሰዋል።›› ‹‹ከንቅናቄው በፊት የክልሉ የደን ሽፋን 6 ነጥብ 5 በመቶ ነበር›› ያሉት ተወካዩ እስከ አሁን በተሠራዉ ሥራም የክልሉ የደን ሽፋን ወደ 14 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል። ዕድገቱን ዘላቂ ለማድረግ የዘመቻ ሥራው ከተጠናቀቀ በኋላም የተገኘውን ተሞክሮ በመቀመር በቀጣይ በግል ማሳና በሌሎች አካባቢዎች በቋሚነት ተጠናክሮ የሚሠራ መሆኑን አመልክተዋል። የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ ሥራ እንደ ሀገር ከጥር 1/2013 ጀምሮ በይፋ መጀመሩና እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ ችራ ቀበሌ በሶኒ ተፋሰስ ነው። በሥነ-ሥርዓቱ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል፣ ክልልና ዞን ከፍተኛ አመራሮችም ተገኝተዋል። አዲስ ዘመን ጥር 5 ቀን 2013  ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=39389
918c97b690f491d299ad7888f081c39c
0daf9551c748ce6e92c3f36b7beb2d94
የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች መያዝ የህግ የበላይነትን በተግባር ያረጋገጠ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ተስፋ አዲስ አበባ፡- የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች መያዝ የህግ የበላይነትን በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነ አዲስ ዘመን ያነጋገራቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።ለተንኮል ሸራቢ አካላትም ትልቅ ትምህርት የሰጠ መሆኑን አመለከቱ፡፡ አዲስ ዘመን ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌትነት ደምሌ እንደገለጹት፣ በቁጥጥር ስር የዋሉ የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች ለ27 ዓመታት ሀገርን እመራለሁ በሚል አምባገነናዊ የአገዛዝ ቀንበራቸውን በህዝብ ጫንቃ ላይ በግድ በመጫን ህዝብን በዘር፣ ኃይማኖት እና በጎሳ እያጋጨ ሀበት ሲመዘበሩ የነበሩ የጥፋት መሃንዲሶች ናቸው። በስልጣን ዘመናቸው ዜጎቿ በየቦታው የሚገደሉባት፣ በቋንቋ የሚጋጩባት፣ አንዱ ብሔር አንዱን በጥላቻ እንዲያይ ያደረገ ክፉ አረም የዘሩ መሆናቸውን ጠቁመው፣ እነዚህ የሀገር ቀንደኛ ጥላቶች ከስልጣን በተገፉ ማግስትም ከኛ ውጪ ሀገርን የሚመራ ኃይል የለም በሚል እብሪት በአደባባ ሲደነፉ የነበሩ ናቸው። የእነሱ መያዝ የዘሩትን በተግባር እንዲያጭዱ የሚያደርግ ትልቅ ትርጉም ያለው ክስተት ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ሥራ ለሠሪው›› እንደሚባለው የለኮሱት እሳት ራሳቸውን አቃጥሏቸዋል ያሉት አቶ ጌትነት ፣ የእኩይ ተግባር ቀያሾቹ መያዝ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል። ቀጣዩ ዘመን የህግ የበላይነት በተግባር የሚታይበት፣ ሀገር የምትለወጥበት ፣ በግለሰብ ደረጃም የተሻለ ኑሮ ለመኖር፣ ሠርቶ ለማደግ እና ለመለወጥ ለሚፈልግ ዜጋ ትልቅ የዕደገት እና የለውጥ ዘመን እንዲሆን የተሻለ ዕድል የሚፈጥር እንደሚሆን አመልክተዋል። እንደ አቶ ጌትነት አስተያየት፣ መንግሥት የህግ ማስከበር ዘመቻውን በታላቅ ሀገራዊ ወኔ እና ትብብር በተሞላበት ሁኔታ የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት በመጠበቅ፣ ብዙ ንብረት ሳይወድም በትንሽ መስዋዕትነት በድል መወጣቱ ትልቅ ስኬት ነው።ለዚህ ስኬት ቀጣይነት ደግሞ መንግሥት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ዜጋ ባቅሙ ጠንክሮ በመሥራት የጎደለውን በመሙላት ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ ጠቁመዋል። መንግሥት ህግን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን ዕርምጃ የሚመጥን ትክክለኛ መረጃ በመገናኛ ብዙሃኑ ለህዝቡ እንዲደርሱ መደረጉ በራሱ ትልቅ ስኬት መሆኑን አመልክተው ፣ የህግ ማስከበር ዘመቻው ሀገርን በቁማር እና ተንኮል መምራት የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ተጠያቂነት ማስከተሉ እንደማይቀር ያስተማረ ነው። ጁንታዎች በሠሯቸው ሥራዎች ኪሳራ እንጂ ትርፍ አላገኙም። ይህም ሀገርን ካለችበት ማማ ለማውረድ ለሚሠሩ ትልቅ መማሪያ እንደሆነ ገልጸዋል። ሌላኛዋ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ገነት አለማየሁ በበኩላቸው ፣ የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች ለበርካታ ዓመታት በህዝብ ላይ ያስከተሉት ጥፋት ሳያንስ ከስልጣን ከተገለሉ ማግስት ነፃነቱን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተገፎ ከቆየው የትግራይ ህዝብ ጉያ ገብተው በሰላም መቀመጥ አቅቷቸው ለዳግም ጥፋት የደገሱት የጥፋት ድግስ ራሳቸውን እንዳጠፋቸው አመልክተዋል። ጁንታው በስልጣን በቆየባቸው ዓመታት በተለይም በሴቶች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን አመልክተው ፣ የጥፋት ቡድኑ በቁጥጥር ስር መዋሉ የጊዜ እንጂ የቡድን ጀግና እንደሌለ በተጨባጭ ያሳየ ነው ብለዋል። የህግ የበላይነት ምን ማለት እንደሆነም ለቡድኑ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ትምህርት የሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ስዩም ይሁኔ የተባሉት ልላኛው መዲናዋ ነዋሪ ፣በሀገሪቱ ያሉ ስልጣን ለመያዝ እውቅና የተሰጣቸው ፓርቲዎችም ከጁንታው አመራሮች ትምህርት በመያዝ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የህዝብ ጥቅም መረጋገጥ ቢሠሩ ቀጣይነት ላላው ሰላም መስፈን ትልቅ ዋጋ ይኖረዋል ብለዋል።ከጀርባ ሆነው ግጭት ለመፍጠር ነገር በመጥመቅ፣ በማስታጠቅ ሀገሪቱ የተረጋጋች እንዳትሆን አቅደው ሲሠሩ የነበሩ የህዝብ ጠላቶች መያዛቸው ለህዝብ ሰላም መረጋገጥ እና ቀጣይነት ያለው የሀገር ዕድገት ለማስመዝገብ ትልቅ መደላ ድል እንደሆነ አስታውቀዋል። ሀገርን ሲያውኩና መጥፎ ሥራ ሲሠሩ የቆዩት አመራሮች መያዝ የህግ የበላይነት ያረጋገጠ ፣ ማንም ሰው ከህግ በላይ ላለመሆኑ ማሳያ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪው፣ መንግሥት በቀጣይ ለሚወስደው የህግ ማስከበር ዕርምጃ የህዝብ ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ ለትክክለኛ ፍትህ ዘብ በመሆን ከስጋት ተላቀን ልማቱን እንድናስቀጥል መንግሥት እና ከህዝብ ከቀደመው በተሻለ ተቀራርበው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። አዲስ ዘመን ጥር 5 ቀን 2013  ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=39385
8bf8cf5d1350c71e1264a4c325c9b10b
2723cab26f2297cdd7111d40f5e92159
የኮሮና ቫይረስን በቃሪያና በርበሬ?
መዝናኛ
ዓለም ሰሞኑን ከቻይና ተነሳ በተባለው ኮሮና ቫይረስ መታመስ ይዛለች። ዓለም አቀፉ ሚዲያ በስፋት እየዳሰሰውም ይገኛል። ኮሮና ቫይረስ የዓለማችን ቁጥር አንድ አሸባሪ ቫይረስ ሆኖ ተከስቷል። እንደ አልቃይዳ፤ አልሻባብ፤ ዓለምን ማሸበሩን ቀጥሏል።‹‹የጨነቀ ነገር መላው የጠፋ፤ ደሞ ምን ጉድ አመጡብን?›› አሉ አዛውንቷ እማማ አለሚቱ። ‹‹ከዚህ ከሚወራው መአት አምላክ ይጠብቀን እንጂ ምን ሊባል ይችላል›› አሉ በፍርሀት ጎብጠው። ‹‹ደሞ በትንፋሽ፣ በንክኪ ይተላለፋል የሚሉት ነው እኮ የበለጠ የሚያሸብረው። እንዴት እንዴት ልንሆን ነው። የእኛ ኑሮ እንደሁ በጣም የተቀራረበ፣ የተነካካ አንዱ ከሌላው መራቅ የማይችልበት ነው፤ ብቻ እሱ ይሰውረን›› አሉና አማተቡ። ቤታቸው ውስጥ ከጎናቸው የተቀመጡት ባለቤታቸው አቶ ደቻሳ ‹‹መቆየት ደጉ ስንት ጉድ አየን፤ የባሰ አታምጣ ማለት ይሻላል አለሚቱ›› አሉ። ‹‹እኛስ እሺ። ገና ምኑንም ያላዩት ሕጻናት ወጣቶች እንዴት ሊሆኑ ነው የእነሱ ያሳስበኛል›› አሉ ደቻሳ። ልጆቻቸው በሙሉ ባህር ማዶ ከተሻገሩ ዓመታት ተቆጥረዋል። አውሮፓና አሜሪካ ይኖራሉ። እዛው ከተለያዩ ሀገራት ዜጎች ጋር ተጋብተው ወልደው ከብደዋል። እንደው እንዴት ይሆኑ ይሆን ምን ይሻላል በሚል አባትና እናት ተጨንቀዋል። እናትና አባት ቶሎ ቶሎ ስልክ ወደ አውሮፓ ይደውላሉ። አቤት እማዬ፤ አቤት አባዬ፤ ሲሉ ከወዲያ እንዴት ናችሁ ለመሆኑ ይሄ አዲሱ ተውሳክ ከምን ደረሰ ይሉና ይጠይቃሉ። እኛ እኮ አሸባሪ ብለነዋል። እማዬ ምን ሆንሽ እዚህ ምንም የለም መንግስት እየተቆጣጠረው ነው ሰላም ነው›› ሲሏቸው ‹‹እልል እሰየው እመብርሀን የት ሄዳ ልጆቼን ትጠብቃለች›› ይላሉ። አቶ ደቻሳም እንዲሁ። ‹‹ጎረቤታቸው ያሉት አዛውንት ይሄን የሰሞኑን የአዲስ በሽታ ወሬ ሰምተው በፍርሀት ተውጠዋል። የእሳቸው ልጆች ሀገር ውስጥ ናቸው። ‹‹ማን አላችሁት የበሽታውን ስም›› አሉና ለመጥራት ለመስማትም ፈሩ። በየትና እንዴት አድርጎ እንደሚመጣ ነቅተው የሚጠብቁ ይመስላሉ። ‹‹በዱላ አይመታ፤ ሂድ ውጣ አይባል፤ ምን ጉድ መጣብን›› አሉ እነ አቶ ደቻሳና ወ/ሮ አለሚቱ። ቤታቸው ብቅ ያሉት አቶ ዘበርጋም ይናገራሉ። ዘበርጋ ቀጠሉ ‹‹የት አባቱንስና ኮረና ፎረና የለም። እኛ እኮ እግዚአብሔር የሰጠን ብዙ መድሀኒት አለን። ነጭ ሽንኩርት፤ ዝንጅብል፤ ቃሪያ ፤ፌጦ፤ ጥቁር አዝሙድ፤ ጤና አዳም ወዘተ›› እያሉ ዘረዘሩት። ‹‹ምናባቱንስና ደሞ ለቻይና በሽታ ማን ይሸበራል፤ ድምጥማጡን ነው የምናጠፋው፤ ደፍሮ እኛ ሀገር አይገባም ኤድያ አትሸበሩ ካለ መድኃኒዓለም›› አሉ ጭንቀታቸውን ትተው በልበሙሉነት። ‹‹የእኛ የአበሻ አረቄም እኮ ለእንዲህ አይነቱ የተስቦና የመጋኛ በሽታ ፍቱን መድኃኒት ነው፤ በእሱ እናቃጥለዋለን፤ የምን መረበሽ ነው አሉ።›› አቶ ደቻሳ ነገሩ ከትከት አድርጎ አሳቃቸው። ‹‹እንግዲህ እስከዛሬ የጠበቀን አምላክ ያውቃል። መቼም የማያመጡብን የማንሰማው መአት የለም። ኤድስ የመጣብን ከፈረንጅ ሀገር ነው። ሌላ ሌላም። በቴሌቪዥን ኢቦላ እንዲህ አደረገ ሰው ፈጀ ደም አስተፋ ሲሉ ሁሉ እንሰማለን። ይኸው ደግሞ አዲሱ በሽታ በትንፋሽ በጉንፋን በትኩሳት ወዘተ ይለያል ይላሉ።››‹‹የት ሄደን እንኑርላቸው እስቲ ሰው በገዛ ሀገሩ መኖሪያ ያጣል እንዴ?›› አሉ ወ/ሮ አለሚቱ። አቶ ደቻሳ ቀጠሉና ‹‹ውጭ ያሉት ልጆቼ አንድ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ሲያወሩ ፈረንጆቹ በሽታ የሚያመርት ፋብሪካ አላቸው ሲሉ ጆሮዬን ጣል አድርጌ ሰምቼአለሁ። ይሄ ነገር ያሳስበኛል። ዓለምን ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ ነው የሚመስለኝ ዝም ብዬ ባልተማረ ህሊናዬ ሳስበው አሉና ዝም አሉ። እኔም ቀልድ መስሎኝ እንጂ ሰምቼአለሁ›› አሉ ወይዘሮ አለሚቱ። ዘበርጋ ቀጠሉና የሁሉም በሽታ መነሻ እንስሶቹ ናቸው። ሊቀመላእክቱ ችግሩን አጥፍቶ ቢገላግለን ምን አለበት›› አሉ በጣም ተበሳጭተው። ‹‹በእኛ ዘመን ድሮ እንዲህ አይነት ጉድ አይተን ሰምተን አናውቅም። የጠና በሽታም አናውቅ። ግፋ ቢል ደማከሴውን፤ ጤና አዳሙን፤ ነጭ ባሕር ዛፉን አረግሬሳውን ቆርጠን ታጥነን ቶሎ መዳን ነበር። የበሽታው መብዛት አይነቱ ስሙ ጉድ ያሰኛል። ይህን ሁሉ ጉድ ድሀ እንዴት ይችለዋል። ሰውም በጣም ተሸበረ›› እያሉ ሲያወጉ ጎረቤታቸው ማንችሎት ሞቅ ብሎት እንዴት ናችሁ? ብሎ ገባ። እርስ በእርስ ተያዩና አመሉን ስለሚያውቁ የታፈነ ሳቅ ሳቁ። አባግድየለሽ ነው ማን ችሎት። ‹‹አዳሜ የምን መፍራት ነው ሞት እንደሁ አይቀር አላቸው። ሁሉም ደነገጡ። አዲስ መጣ ያሉት በሽታ ነው የሰው ሁሉ ወሬ። ጠጅ ቤቱን ጠላ ቤቱን ሰፈሩን መንደሩን ሁሉ የሞላው። እኛና እሱ እንተዋወቃለን። አይነካንም። አንንነካውም። መድኃኒቱ ጠጅና አረቄ መጠጣት፤ ቃሪያና በርበሬ አብዝቶ መብላት ብቻ ነው አዳሜ ትጨነቂያለሽ ምንም የለም›› አላቸው።‹‹ምን ትጨነቃላችሁ እናንተ ዘጠና ዓመት ውስጥ ናችሁ ለምኑ ብላችሁ ነው አላቸው። ወይዘሮ አለሚቱ የእድሜ ነገር ሲነሳ አይወዱም። አዋልደሀል አሉት። ምን ማዋለድ ያስፈልጋል እናንተ እኮ ሉሲ ስትወለድ የነበራችሁ ናችሁ›› አላቸው። አዲስ ዘመን ጥር 28/2012ወንድወሰን መኮንን
https://www.press.et/Ama/?p=26779
7ca6dd1f1e94a2f4b788a5c0fee8e87c
184c06230b785507685899e472310128
ልጃገረድነትን ማስመሰል የቻለው የ40 ዓመት ጎልማሳ
መዝናኛ
ስለ አንድ ነገር አይቶ መናገር ይቻላል፤ ሰምቶም እንዲሁ። አንዳንዴ ግን ያዩትንም የሰሙትንም ማመን ይከብዳል። ኦዲቲ ሴንትራል በቅርቡ ይዞት የወጣ መረጃ እንዳመለከተው፤ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የጃፓን ልጃገረድ የሚመስል ሰው፣ በመካከለኛ እድሜ ላይ የሚገኝ አባወራ ነው። በዊኪፒዲያ ላይ እንደተጠቀሰው፤ ታኩማ ታኒ የተባለው ይህ ጃፓናዊ ድምጻዊ የተወለደው እኤአ በ1977 ነው። ይህ መረጃ ግን ይህን ሰው በፍጹም አይገልጸውም። ሁሉም የግለሰቡ ምስሎች ተማሪ ልጃረገድ ነው የሚመስሉት። ታኩማ ከወጣትነቱ አንስቶ ለኪነጥበብ ከፍተኛ ዝንባሌ ነበረው። ገና በህጻንነት እድሜውም ፓያኖ እና የድምጽ መሳሪያዎችን አጥንቷል። በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት እድሜውም ግጥም መጻፍ ጀማምሯል። በ28 ዓመቱ ደግሞ ድምጻዊ በመሆን በተዋቂ የጃፓን ባንድ ውስጥ ሰርቷል። ታኩማ በ34 ዓመቱ ደግሞ ልጃገረድ ተማሪ ለመምሰል ይወስናል። ከዚያም ጊዜ አንስቶ ይህን ማስመሰሉን በሚገባም ያደርገዋል። የ40 ዓመት ጎልማሳ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ሳይቀር ልጃገረድ መምሰል በሚገባ ችሏል። በዚህም ብዙዎችን በማህበራዊ ሚዲያ እስከ ማደናገር ደርሷል። በህይወቱ ስኬታማ ከሆነባቸው ክንውኖቹ መካከል ልጃገረድ በመምሰል ያከናወናቸው ይበልጣሉ ያለው መረጃው፣ 1 ነጥብ 62 ሜትር እንደሚረዝም፣ 47 ኪሎ ግራም እንደሚከብድ፣ የጫማ ቁጥሩም በአማካይ ከሚታወቀው ቁጥር ያነሰ መሆኑን ያብራራል፤ ይህም ልጃገረድ ለመሆን ያደረገውን ጥረት እንዳሳካለት ይጠቁማል። መረጃው እንዳመለከተው፤ ታኩማ ልጃገረድ ለመምሰል ሲል ሜካፕ መጠቀሙ እንዲሁም ፎቶ ግራፎቹ እጅ ስራ ያያቸው መሆናቸው የማይካድ ቢሆንም፣ ለተላበሰው የልጃገረድነት ባህሪ የዓመታት ልምዶቹ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰ ጣቸው ናቸው። አመናችሁም አላመናችሁ ይህ ጥረቱ፣ የ40 ዓመት ጎልማሳውን ታኩማ የተለያዩ ሙያዎች ባለቤት እንዲሆን አስችለውታል። ያለው መረጃው፣ በዚህ የልጃገረድነት ገጸ ባህሪው በጃፖን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በተደጋጋሚ ለመታየት እንዲሁም የፉጂ ቲቪ ቫይኪንግ የአልባሳት ውድድር ሽልማትን በማሸነፍ ለመሸለም በቅቷል። ሙዚቀኛ ብቻ አይደለም። አቱኮስቬት ቶክዮ የተሰኘ የሴቶች ልብስ ፋሽን በመመስረትም ስራ ፈጠሪ መሆን ችሏል፤ ልብሶቹን በማስተዋወቅም በሞዴልነት ይሰራል። ልጃገረድ መመሰል መቻሉ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ አስችሎታል። በዚህ የተነሳም ብዙዎች ታኩማን የ40 ዓመት ሰው እንዲሁም ባለትዳር አርገው እንዳይቀበሉት አርጓል። እኤአ በ2016 ተማሪነት በተላበሰው መስሉ ህጻን አቅፎ የተነሳውን ፎቶ እና ‹‹እኔ አባት ነኝ›› የሚል መልእክት በማያያዝ በኢንተርኔት የለቀቀው መረጃም ብዙዎችን አስደንግጧል። ‹‹በህይወት ዘመንህ ምን መስራት እንዳለብህ ለሰዎች እያሳየሁ ነው›› ያለው ታኩማ፣ ‹‹ሌሎች ስለአንተ አለባበስና ስለመሳሰሉት ምን ይላሉ ብለህ እንዳትፈራ›› ሲልም ያሳስባል። የምትለብሰው ከእድሜህና ከጾታህ ጋር የሚሄድ እና የማይሄድ ስለመሆኑም ብዙም ትኩረት አትስጥ ያለው ታኩማ፣ ህይወትን በመሰለህ መንገድ ምራ ሲልም ያስገነዝባል። አዲስ ዘመን ጥር 26/2012
https://www.press.et/Ama/?p=26632
9e7683a6602fe9b07d7c83a6895dc8c9
2cd9675413e4de66d828b2a3a1ee5e47
ኮሚሽኑ ስኬታማ ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ
ስፖርት
የኮሮና ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) በየዘርፉ የተለያዩ ተጽእኖዎችን ማድረሱ ግልጽ ነው። ከእነዚህ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው ስፖርት ሲሆን፤ ጠቅላላ እንቅስቃሴው ተገቶ እንዳልነበር ለመሆን ተገዷል።በርካታ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ ስልጠናዎች፣ ጉባኤዎችና ሌሎች ክንዋኔዎች በቫይረሱ ስጋት ምክንያት ሲሰረዙና ሲራዘሙ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን የተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት ለተቋረጡት ስፖርታዊ ኩነቶች አማራጮችን በመፈለግ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል።እንደ መፍትሄ ባስቀመጧቸው ሃሳቦች ታግዘውም ክፍተታቸውን ሲሸፍኑ ሰንብተዋል፡፡ይህ በመላ ዓለም ጥላውን ያጠላው ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶም በርካታ እርምጃዎች በስፖርቱ አካባቢ ሲወሰድ ተስተውሏል። ስልጠናዎች፣ የውድድር ዝግጅቶች፣ ውድድሮች፣ ስብሰባዎችና ሌሎች ጉዳዮች መቋረጣቸው የግድ ቢሆንም፣ ስፖርቱን በበላይነት የሚመራው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን እና ጥቂት የስፖርት ማህበራትና ተቋማትም በሌላ አቅጣጫ ከተለመዱት ኩነቶች ውጪ የሆኑ ተግባራት ላይ አተኩረው ቆይቷል፡፡ነገር ግን በወቅታዊው ችግር ተቋማቱ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ባስቀመጡት መርሐ ግብር መሰረት ያከናወኗቸው እንዲሁም ያልሸፈኗቸው እቅዶች መኖራቸው አይቀርም።ኮሚሽኑ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ ይገልጻሉ። በተለይ በትኩረት ሲከናወን የቆየው የስፖርቱን ሁለንተናዊ ችግር ሊቀርፍ የሚችለውን ጥናት ወደ ተግባር በመቀየር ላይ ነው። ሃገር ዓቀፉ የስፖርት ሪፎርሙን ለመተግበር በሚያስችል ሁኔታ ግብረ ኃይል በማቋቋምና እቅዶችን በማውጣት በውድድር፣ በስልጠና፣ በማዘውተሪያ ስፍራና አደረጃጀት ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በመገምገም ስራዎች በዓመቱ ውስጥ ተከናውነዋል። የስፖርት መተዳደሪያ ደንቦችን እንዲሁም ስታንዳርዶችን በማዘጋጀት፣ የስፖርት ማህበራት ያሉበትን ደረጃ የማውጣት፣ ስፖርቱ የሚመራበት አደረጃጀት ላይ ዶክመንት የማዘጋጀት፣ የስፖርት ማህበራት አደረጃጀት ላይ ክለሳ ማድረግም በበጀት ዓመቱ ተችሏል።በመንግሥት በኩል ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት በመካሄድ ላይ የሚገኘው ብሄራዊ ስታዲየም ግንባታ፣ የካፍ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል እድሳት እንዲሁም በሲኤምሲ በሚገኘው ቦታ ላይ የማዘውተሪያ ስፍራ የመስራት እቅድ ላይም ኮሚሽኑ ሲሰራ መቆየቱንና ይህም ስኬታማ እንደነበር ምክትል ኮሚሽነሩ ያብራራሉ።በዓመቱ በርካታ ስራዎች ቢከናወኑም በአንጻሩ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ በታቀደው መሰረት ለመፈጸም ያልተቻሉ ጉዳዮችም መኖራቸው አልቀረም።ይኸውም የዓለም፣ አህጉርና ሃገር አቀፍ ውድድሮችን ማካሄድ እና በክልሎች የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ለመገምገም አለመቻል ነው።ከጥቂት የእግር ኳስ ሊጎች በቀር በዓለም ደረጃ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ዝግ መሆናቸውይታወቃል።በኢትዮጵያም የተሻለ እንቅስቃሴ የሚያደርጉት የእግር ኳስና አትሌቲክስ ስፖርቶች እንደቀደመው በመርሐ ግብራቸው መሰረት መስራት አልቻሉም።ሃገሪቷ የምትታወቅበት አትሌቲክስ ኦሊምፒክን ጨምሮ በርካታ ዝግጅት ሲያደርግ ቢቆይም፤ በወቅታዊው ሁኔታ ብሄራዊ ቡድኑን ለመበተንና ስልጠናዎችን ለማቋረጥ ተገዷል። በእግር ኳስም ተመሳሳይ ሁኔታ ያለ ሲሆን፤ ከማህበር ባለፈ በግላቸውም ስፖርተኞች ከቀደመው ጊዜ ገቢያቸው እንዲቀንስ አድርጓል። ነገር ግን በአንጻራዊነት ሲታይ በእነዚህ ስፖርቶች ያለው እንቅስቃሴ የተሻለ ሊባል የሚችልና ተጓዳኝ ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ ይጠቁማሉ።ቀድሞም እምብዛም እንቅስቃሴ ያልነበራቸው ሌሎች ስፖርት ማህበራት ደግሞ በዚህ ወቅት ይበልጥ ተዳክመዋል።በመሆኑም የስፖርት ኮሚሽን ዋነኛው ሥራ እነዚህን ማጠናከር ይሆናል።አብዛኛዎቹ ፌዴሬሽኖች ከላይ እስከ ታች ያለውን አደረጃጀት ማስተካከል አይደለም የውስጥ ውድድራቸውንም በትክክል መምራት ያልቻሉበት ሁኔታ መኖሩን በግምገማ ተለይቷል። በመሆኑም በአዲሱ በጀት ዓመት ስፖርቱን ከሚመሩት የጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ጀምሮ በትኩረት ለመስራት እቅድ ተይዟል።እንደሚታወቀው ለፌዴሬሽኖቹ በመንግሥት በኩል የሚመድበው ዓመታዊ ድጎማ እጅግ አነስተኛና ለሚሰሯቸው ስራዎች በቂ ባለመሆኑ ለመንግሥት ጥያቄ በማቅረብና ጭማሪ በማድረግ በአቅም እንዲጠናከሩ ይሰራል።በኢትዮጵያ ስፖርት መርሐ ግብር መሰረት ይህ የክረምት ወቅት ስልጠናዎችና ውድድሮች ተጠናቀው የታዳጊ ወጣት ፕሮጀክቶች ስልጠና የሚመዘንበት እንዲሁም ክለቦችና የማሰልጠኛ ተቋማት ደግሞ ምልመላ የሚያደርጉበት ነበር።ታዲያ በዚህ ውድድር ማካሄድ በማይቻልበት ወቅት ከታዳጊዎች ምልመላ ጋር በተያያዘ በኮሚሽኑ የታሰበ አማራጭ መንገድ ስለመኖሩም ምክትል ኮሚሽነሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።ሃገር አቀፉ የስፖርት ሪፎርም ምልመላን በተመለከተ የተለዩ ስፍራዎች መኖራቸውን ያመለክታል።እንደየስፖርት ዓይነቶቹ የተሻለ ችሎታ የሚገኝባቸው ስፍራዎች በጥናት ላይ ተሞርክዞ ተቀምጧል። በመሆኑም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የመንግሥትን ውሳኔና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመመልከት በባለሙያዎች ስራው የሚከናወን ይሆናል።የኮሮና ወረርሽኝ የስፖርቱን ዘርፍ ሙሉ በሙሉ ጎድቷል፤ እንቅስቃሴዎችንና ውድድሮችን ገድቧል።በስፖርተኞችና ሃገራትም ላይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን አስከትሏል፤ ይህም አደጋ ነው።ነገር ግን ይህ ጊዜ ያልፋል በሚል ተስፋ ሁሉም በአንድነት እየተጠባበቀ ይገኛል።መንግሥትም ሁኔታዎችን በማገናዘብ ምላሽ ይሰጣል የሚል ተስፋ አለ፤ ይህን ወቅት በመሻገርም ስፖርቱን ወደነበረበት የስፖርት ቤተሰቡም ወደ ተመልካችነቱ የሚመለስበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።በመሆኑም ይህንን ጊዜ በጋራ ለማለፍ ራስን ከቫይረሱ መጠበቅ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ እንዲቆዩም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=35740
39ae17924d00962075166fbaa4e196a8
2a4280ce4a5d321ea7ebe75a0df75e0c
ቶማስ ባኽ ተጨማሪ ዓመታት የመቆየት ፍላጎት አላቸው
ስፖርት
ዘጠነኛው የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው የኮሚቴው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ። ላለፉት ስምንት ዓመታት ኮሚቴውን የመሩት የ66 ዓመቱ ባኽ በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነም ለቀጣይ አራት ዓመታት በፕሬዚዳንትነታቸው የሚቆዩ ይሆናል። በህግ ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸውና በስፖርቱ ዓለምም የተዋጣላቸው ቶማስ ባኽ ኮሚቴውን መምራት የጀመሩን እአአ በ2013 ነበር።በምዕራብ ጀርመን የተወለዱት ቶማስ ባኽ በትምህርት ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ቢሆንም ሀገራቸውን በሻሞላ ስፖርት በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ (እአአ 1976 በተካሄደው የሞንትሪያል ኦሊምፒክ) የወርቅ ሜዳሊያ በማጥለቅ ሊያስጠሩ ችለዋል።በሦስት የዓለም ቻምፒዮና ተሳትፎዎችም አንድ የወርቅ ፣አንድ የብር እና አንድ የነሃስ በድምሩ ሦስት ሜዳሊያዎችን ለሃገራቸው አስገኝተዋል።ከስፖርቱ ወደ አመራርነት የገቡት እአአ 2006 ሲሆን፤ የጀርመን ኦሊምፒክ ስፖርት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆንም ነበር። ከዚያ በሂደት ዓለም አቀፉን የኦሊምፒክ ኮሚቴ በመቀላቀል በተለያዩ ሃላፊነቶች አገልግለዋል። እአአ በ2013 በተካሄደው 125ኛው የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።በምርጫውም አብረዋቸው የቀረቡትን አምስት እጩዎች በሰፊ የድምጽ ልዩነት በማሸነፍ የፕሬዚዳንትነት መንበሩን ሊቆናጠጡ ችለዋል።ለቦታውብቁ ሆነው በመገኘታቸውም ተጨማሪ አራት ዓመት ተሰጥቷቸው ለስምንት ዓመታት ሊያስተዳድሩ ችለዋል፡፡በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይም ከኮሚቴው አባላት ተጨማሪ እድል የሚሰጣቸው ከሆነ ለማስተዳደር ፈቃደኛ መሆናቸውን ሮይተርስ በድረገጹ አስነብቧል። ‹‹የኮሚቴው አባላት በድጋሚ የፕሬዚዳንትነት እድል የሚሰጡኝ ከሆነ የምንወደውን ኦሊምፒክ ለማገልገል ዝግጁ ነኝ›› ሲሉም ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ከኮሚቴው አባላት በስልጣን እንዲቆዩ ጥያቄ የቀረበላቸው መሆኑን ደግሞ ኢንሳይድ ዘ ጌምስ የተባለው ድረገጽ አስነብቧል።ፕሬዚዳንቱ አክለውም ‹‹እገዛችሁ ለቀጣይ ሥራ የሚያነሳሳኝ ይሆናል›› ብለዋል። ባኽ ከሌሎች ፕሬዚዳንቶች ልዩ የሚያደርጋቸው በኦሊምፒክ ተሳታፊና ውጤታማ በመሆናቸው ሲሆን፣ በስልጣን ዘመናቸው ካሳለፏቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎች መካከል በዋናነት የሚጠቀሰው በመንግሥት ጭምር የሚደገፈው የሩሲያ አትሌቶች የአበረታች ቅመሞች ተጠቃሚነት ቅሌት ሩሲያ በኦሊምፒክ መድረክ እንዳትሳተፍ ማድረጋቸው ግንባር ቀደሙ ነው።ሌላኛው ደግሞ በዚህ ወቅት በመላው ዓለም በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ተራዝሞና ተሰርዞ የማያውቀውን ኦሊምፒክ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ማድረግ ነው።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=35754
3cac16e6b6fd2fca6a297657ce7db907
e102093a75b3fa4bfed30677a5eeb468
“ከፍተኛ የክብር ኒሻን ሽልማቱ ከጀነራል ብርሃኑ ጁላ አልፎ ለአገርም ትልቅ ትርጉም ያለው ነው” – ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የጀግና ሜዳይ ተሸላሚ
ሀገር አቀፍ ዜና
 እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ከጅቡቲ መንግሥት የአገሪቱን የመጨረሻ ደረጃ ከፍተኛ ኒሻን መሸለማቸው ከግለሰቡ አልፎ ለአገርም ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ገለጹ።ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ሽልማት ማለት አንድ ሰው ለሠራው ሥራ ላበረከተው አስተዋጽዖ እውቅና መስጠት ነው፤ በተለይም እንደዚህ አይነት የእውቅና ሽልማቶች ሲበረከቱ ለግለሰቡ ብቻ ሳይሆን ለአገርም የሚኖራቸው ክብር በጣም ትልቅ ነው። በውትድርና ዓለም ላይ ላሳለፍን ሰዎች የእውቅና ሽልማት ማለት ለአገርም ለራስም ምን ዓይነት ትርጉም እንዳለው በሚገባ እንረዳለን ያሉት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ፣ ስሜቱ በጣም ከባድ የሚጥለው ኃላፊነትም ትልቅ ነው ብለዋል። እውቅናው በሰራዊቱ ላይ የሚያሳድረው ተነሳሽነት ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ የሞራል ድጋፍ እንደሆነም አስታውቀዋል። ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ብርሃኑ ጁላን የክብር ኒሻን ሽልማት ማግኘታቸውን መስማታቸው እጅግ እንዳስደሰታቸው የገለጹት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ፣ ከደስታም አልፈው በአገራቸው መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ኩራት እንዲሰማቸው እንደሆኑም አመልክተዋል። ሠራዊቱ በተለይም በህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ከፍተኛ የሆነ የህይወትና የአካል መስዋዕትነትን ከፍሏል፤ በጣምም አስደናቂ ጀግንነት በአጭር ጊዜ በትንሽ ወጪ አሳይቷል ፤ ከዚህ አንጻር ሽልማቱ ቢያንስበት እንጂ የሚበዛበት አይደለም ብለዋል። የጎረቤት አገር ጅቡቲ መንግሥት በዚህ መልኩ ሠራዊታችንን ሲያከብርና እውቅና ሲሰጥ የኢትዮጵያ መንግሥትም ዝም ማለት የለበትም ያሉት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ፣ ለእነዚህ ጀግኖች የሚገባቸውን ክብርና እውቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ይህ ሽልማት ሠራዊቱ የህይወት የአካል የደምና የላብ መስዋዕትነት የከፈለበት፣ የዚህ ሁሉ ውጤት ነው፤ እርሳቸውም ለሰጡት አመራር ላወጡት እቅድ የሚገባቸው ነው ፤ ግን ደግሞ የሳቸው ሽልማት የሠራዊቱ ብሎም የኢትዮጵያ ነው። ሽልማቱ እንኳን በቦታው ላይ ሆነው ተጋድሎ ለፈጸሙ ቀርቶ እኛ ጡረቶኞቹን ያስደሰተ ልባችንን ያሞቀ እንኳን ኢትዮጵያዊ አልፎም ወታደር ሆንን ያስባለ ነው ብለዋል። ይህ ዓይነቱ ስጦታ የተለመደ አይደለም የሚሉት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ከዚህ አንጻርም ከፍተኛ ክብር የሚገባው ሠራዊቱንም ለበለጠ ሥራ ትጋት ቆራጥነትና አገር ወዳድነት የሚያነሳሳ ስለመሆኑም ተናግረዋል።የጁንታው መሰሪ አካሄድ በዚህ ዓይነቱ ጀግንነት መስመር ማስያዝ ባይቻል ኖሮ ችግሩ ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጎረቤቶቻችን ይተርፍ ነበር ።ህንንም ጠንቅቀው ያውቃሉ ፤ ከዚህ አንጻርም ሽልማቱ “የእኛን ችግር ፈታችሁልን፣ እናንተ ሰላም ስትሆኑ ነው እኛ በሰላም መኖር የምንችለው “ የሚል መልክዕክትም ያለው ነው ብለዋል። ሠራዊቱ በጎረቤት አገራት እየተዘዋወረ በሚያደርገው የሰላም ማስከበር ሥራ ከፍተኛ እምነት እንዳደረባቸውም ማሳያ እንደሆነ ገለጸዋል። “ብላቴ ላይ አየር ወለድና ኮማንዶዎች ሲመረቁ በክብር እንግድነት ተገኝቼ ነበር ፤ በወቅቱም ባየሁት ነገር በአመራሮቹ ብቃት፣ በሙያዊ ክህሎታቸው፣ በስነ ስርዓታቸው እጅግ ከመደሰቴና ከመኩራቴም በላይ ሠራዊቱን የሚበግረው ምንም ኃይል እንደማይኖር ተናግሬ ነበር።አሁንም ጁንታው ለረጅም ዓመታት የተዘጋጀበትን ምሽግ ንዶ ይህንን የመሰለ ውጤት ማምጣቱ የግምቴን ትክክለኝነት አሳይቶኛል “ ብለዋል። ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ዓይነት ችግር ምን ጊዜም ሊገጥማት እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ሠራዊቱን አሁን ካለው አቋም እንዳይለቅ ከዚህም በላይ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ማድረግ ያስፈልጋል፤ ይህንን ማድረግ ከቻልን ምንም የሚገታን ኃይል አይኖርም ሲሉም ተናግረዋል። አዲስ ዘመን ጥር 5 ቀን 2013  ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=39376
9cacab0912af9a3a346a38e919da73be
d3790d6356985a77292a210004ae3d28
ከሌሊሶ ሜዳ እስከ ማልታ ደሴት
ስፖርት
በደቡብ ክልል ከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና ከተማ ዱራሜ ነው የተወለደችው። ሰባት ልጆች ላፈሩት እናት እና አባቷ አምስተኛ ልጅ ስትሆን፤ ከልጅነቷ ጀምሮ ነበር በኳስ ፍቅር የወደቀች። የእግር ኳስ መሰረቷን የጣለችው ተወልዳ ባደገበችበት ዱራሜ ከተማ በሰፈር ውስጥ ነው። ከሰፈር የተነሳው የኳስ ህይወት ከሀዋሳ ከተማ አንስቶ በደደቢት እና ብሔራዊ ቡድን በግብ አስቆጣሪነት ስሟ እስከመነሳት የደረሰም ነበር፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድንና በማልታ ቢርኪርካራ እግር ኳስ ቡድን አጥቂ ሎዛ አበራ። የሎዛ የእግር ኳስ ህይወቷ ሀ፣ሁ ከሌሊሶ ሜዳ ይጀምራል። የዱራሜዋ የትናነቷ ታዳጊ ባደገችበት ሠፈር ካሉ ወንድ እኩዮቿ ጋር እየተጋፋች በመጫወት ነበር የጀመረችው። ከወንዶች ጋር ሴት ሆና መጫወቷና ብቃቷ ለብዙዎች ግርምት ከመፍጠር ባሻገር ከሠፈሯ ‘ሌሊሶ’ ሜዳ አሁን ያለችበት ትደርሳለች ብለው ብዙዎች አልገመቱም። ሎዛ በኳሱ ወንዝ ተሻጋሪ ታሪክ መስራትን እንደምትችል በልቧ የነበረውን መሻትና ወኔ በአንድ ወቅት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዲህ ብላ ነበር ። «በእግር ኳስ ሃገሬን ወክዬ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ መጫወት የልጅነት ህልሜ ነው። ይሄንኑ ህልሜን እውን ለማድረግ እልህ አስጨራሽ ፈተናዎችን በመጋፈጥ እውን አድርጌዋለሁ» ስትል ገልፃለች። በሎዛ የልጅነት የኳስ ህይወት ውስጥ የነበሩት ማህበራዊ ተጽእኖዎችን ትልቁ ፈተና ፈጥሮባታል። ኳስ ያላት የበዛ ፍላጎት በቤተሰቦቿ ዘንድ ይህ የተወደደ አልነበረም። «ትምህርትሽን አጥብቀሽ መያዝ ነው ያለብሽ»የሚል ምክር አዘል ቁጣ አስከትሎባታል። «ከምንም ነገር በፊት ፍላጎት ይቀድማል። እግር ኳስ መጫወት ከሆነ ፍላጎታችን፤ ያንን ፍላጎታችንን ለማሳካት ሳይደክሙ መሥራት። ሌላም ከሆነ እንደዚሁ። ተስፋ ሳይቆርጡ እደርሳለሁ ያሉበት ቦታ እንደሚደረስ ሁሌም ለአእምሮ መናገር፤ ራስን ማሳመን፤ ሥራን ማክበር ማለትም አንድ ሙያ የሚጠይቀውን ዲሲፕሊን መከተል ያስፈልጋል» የምትለው ሎዛ ትምህርቷን ሳትለቅ ኳሱን ጠበቅ ማድረጉን አማራጭ አድርጋ ገፋችበት። በኳሱ የነበራት ተሳትፎ የከንባታ ዞንን ወክላ የመጫወት አጋጣሚን ፈጠረላት። ይህም የሎዛን ከልጅነት ህልሟ የሚያደርሷት ባቡር ውስጥ መግባቷን ያረገገጠ ነበር። የመጀመሪያ ፕሮፌሽናል ኳስ ተጫዋች ነት የተጀመረበት ይህ አጋጣሚ፤ ወደ ክልል አሻገራት። ደቡብ ክልልን ወክላ ለመላው ኢትዮጵያ ውድድር እንድትሳተፍ ሆነ። ለዱራሜዋ ህልመኛ በአደማ የተካሄደው ውድድሩ የባቡሩ ጉዞ ሃዲዱን ጠብቆ እየተጓዘ መሆኑን ያመላከተ ነበር። ሎዛ በመላው ኢትዮጵያ የነበራት እንቅስቃሴ በሐዋሳ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ የሆነው ዮሴፍ ገብረወልድ እይታ ውስጥ አስገብቷታል። ከሌሊሶ ሜዳ የተነሳው የኳስ ህይወቷ መዳረሻውን በሐዋሳ እግር ኳስ ክለብ አደረገ። ፈጣኑ የሎዛ ጉዞ ኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ላይ ታሪክ መስራቱን ተያያዘው። ሎዛ ከሐዋሳ ጋራ ዋንጫ ባታነሳም በቆየችባቸው ሁለት ተከታታይ ዓመታት የክለቡ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነበረች። በሐዋሳ የፈነጠቀው የኳስ ህይወት ታሪክ፤ ቀጣይ ማረፊያውን ደደቢት ላይ አደረገ። ሎዛ በኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በርካታ ክዋክብቶች የሚገኙበት ክለብን መቀላቀሏ በፍጥነት የበለጠ ጎልታ የመውጣት እድልን አስገኘላት። በደደቢት ቤት ክለቡ እስከፈረሰበት ጊዜ አራት ዓመታትን ቆይታ አድርጋለች። በእነዚህ ዓመታት በተከታታይ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ መሆን ችላለች። ክለቧን ለሶስት ተከታታይ ዓመት ደግሞ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሻምፒዮና እንዲሆን አስችላለች። የሎዛ የኳስ ህይወት ከፈረሰው ደደቢት ባህር ማዶ በመሻገር ሲውዲን አርፏል። ከብሔራዊ ቡድኑ የቀድሞ አምበል ቱቱ በላይ ጋር አብራ ወደ ሲውዲን አቅንታ፤ የሁለት ወር የሙከራ ልምምድ ማድረግ ጀመሩ። በሲውዲን የሚገኙ ሮዘንጋርድ እና ፒቲያ አይ ኤፍ ለአራት ወራት ያክል ቆይታ ማድረግ ቢችሉም፤ ሳይሳካ በመቅረቱ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። የዱራሜዋ ባለህልም ወንዝ የተሻገረው ህልሟ ከቆይታ በኋላ መዳረሻውን በማልታ ደሴት ከፍተኛ ሊግ ላይ ለሚሳተፈው ቢርኪርካራ አድርጓል። ከሠፈሯ ‘ሌሊሶ’ ሜዳ አሁን ያለችበት ትደርሳለች ብለው ብዙዎች ያልገመቷት ሎዛ፤ በማልታ ደሴት አዲስ ታሪክ መስራት ጀምራለች። በአውሮፓ የምትጫወት የመጀመሪያዋ ሴት ኢትዮጵያዊት እግር ኳስ ተጫዋች መሆን የቻለችው ሎዛ፤ በጥበበኛ እግሮቿ ሌላ ታሪክ በመስራት ነበር የውድድር ዓመቱን ያጠናቀቀችው። የግብ አዳኟ ሎዛ አበራ የኳስ ህይወት ከሌሊሶ ሜዳ እስከ ማልታ ደሴት የተሻገረ ስኬት ማስመዝገብ ችሏል። በእግር ኳሱ ተስፋ ሠንቀው እየተንቀሳቀሱ ለሚገኙ ለሀገራችን ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ ከፍተኛ የሆነ መነቃቃት ይፈጥራል ባይነን።አዲስ ዘመን ሐምሌ 14/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=35843
f073e10a1cf2fbbbb92cec4f67594636
8f817826468f39d01148b9da266bd2a8
ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከአቶስ ጋር ውሉን አራዘመ
ስፖርት
 ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከግዙፉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኩባንያ አቶስ ጋር ያለውን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማራዘሙን ገለፀ። አዲሱ ውል እስከ 2024 እንደሚዘልቅም ሁለቱ ተቋማት ባለፈው ሳምንት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል። ኮሚቴውና ኩባንያው እኤአ ከ1989 ጀምሮ አብረው እየሰሩ እዚህ ደርሰዋል። የፈረንሳዩ አቶስ ኩባንያ የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ግንባር ቀደም ስፖንሰር በመሆን 2014 ላይ ለስድስት ዓመታት የሚዘልቅ ውል ማሰሩ የሚታወስ ነው። የሁለቱ አካላት አዲስ ስምምነት ለ2022 የቤጂንግ የክረምት ኦሊምፒክና ለ2024 የፓሪስ የበጋ ኦሎምፒክ ውድድሮች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ማሟላትን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል። ይህ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ መራዘሙን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከገጠመው ኪሳራ በጥቂቱም ቢሆን ሊያገግምበት የሚችል መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ተጠቁሟል። ‹‹በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የዓለም አቀፍ አጋሮቻችን ድጋፍና በራስ መተማመን ከምን ጊዜውም በላይ አስፈላጊ ነው›› በማለት ቶማስ ባኽ አስተያየት ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም ዓለም አቀፍ ኮሚቴው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው አቶስ ውድድሮችን ዘመኑ በሚፈቅደው ቴክኖሎጂ በማገዝ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል። ቶማስ ባኽ የአቶስ ኩባንያ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጋርነቱ ባሻገር የኦሎምፒክን መርህ በዓለም ሕዝብ ዘንድ ለማስረፅ በሚደረገው እንቅስቃሴ አጋር ሆኖ በመዝለቁም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ኩባንያው የኦሎምፒክን እንቅስቃሴ እኤአ ከ2001 ጀምሮ እየደገፈ እንደሚገኝ ይታወቃል። በፓሪስ ሰሜን ምዕራብ ቢዞንስ አካባቢ በሚገኘው የአቶስ ኩባንያ ተገኝተው የውል ስምምነቱን የፈረሙት ቶማስ ባኽ በፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክን እንዲሁም የወቅቱ አሳሳቢ የጤና ጉዳይ የሆነው ኮቪድ 19 ዙሪያም ምክክር ማድረጋቸው ታውቋል። የአቶስ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሊ ጂራርድ ከዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በአጋርነት ሲሰሩ ቆይተው ውላቸውን በማራዘማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ኦሊምፒክንና የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን በቴክኖሎጂ በማገዝ ወደ ፊትም ኩባንያው ጠንክሮ እንደሚሰራ አብራርተዋል። በሁለቱ አካላት መካከል የታደሰው ውል የዓለም አቀፉ ፓራኦሎምፒክ ኮሚቴንም የሚያካትት ነው። አቶስ ኩባንያ በርካቶቹ የኦሎምፒክ ስፖንሰሮች ፓራኦሎምፒክ ኮሚቴውን ለመደገፍ ሲያመነቱ 2018 ላይ ስፖንሰር ለመሆን ፍቃደኝነቱን ማሳየቱ ይታወሳል። አቶስ ኩባንያ በ2018 ፒዮንግያንግ የክረምት ኦሎምፒክ ወቅት ‹ክላውድ› የተባለ ቴክኖሎጂ ይፋ በማድረግ ስራ ላይ ያዋለ ሲሆን በተራዘመው የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክም ይህን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይጠቀማል ተብሎ ነበር። ባለፈው ሰኔ ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ ኦሎምፒክ በመራዘሙ ስድስት መቶ ሃምሳ ሚሊየን ዶላር ኪሳራ እንደሚገጥመው የተነገረ ሲሆን ይህን ኪሳራ ለማካካስ እንደ አቶስ ያሉ አጋሮቹን ድጋፍ ከምን ጊዜም በላይ ይፈልጋል። የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ለአስራ ስድስት ወራት በመራዘሙ ምክንያት የአዘጋጅ አገሯ ጃፓን መንግስትና የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ገና ከጅምሩ በርካታ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ መዘፈቃቸው ሲነገር ቆይቷል። የኦሎምፒክ ውድድሩ በዓለም ላይ ከፍተኛ ስጋት በፈጠረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዞ ወደ ቀጣዩ ዓመት መራዘሙ ግድ መሆኑ ከታመነበት ወቅት አንስቶ አዘጋጆቹ በርካታ ፈተናዎችን መጋፈጣቸው የማይቀር ሆኗል። በተለይም ላለፉት ሰባት ዓመታት የበለጠ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው የኦሎምፒክ ውድድር መራዘሙ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ማስከተሉ የአዘጋጆቹ ራስ ምታት እንደሚሆን ቀድሞም የታወቀ ነው።ይህ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ የጃፓን መንግስትንም ይሁን ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴን በእጅጉ ሊፈትን እንደሚችል በባለሙያዎች አስተያየት ሲሰጥበት የቆየ ሲሆን ሁለቱ አካላት ኪሳራውን ለማካካስ እንደሚደጋገፉና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ለዚህ እንዲዘጋጁ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲገጥሙት ትልቅ ተቋም እንደመሆኑ የመድህን ዋስትና እንዳለው ይታወቃል። አሁን የገጠመው ግን ካለው የመድህን ዋስትና አቅም በላይ በመሆኑ ነው እዚህ ችግር ውስጥ የተዘፈቀው። ስለዚህ የመድህን ዋስትናው በሕጉ መሰረት የሚሸፍነው ኪሳራ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ ኪሳራውን የሚያካክስበት አንድ ነገር መፈጠሩ የግድ ይሆናል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 16/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=35901
eaadc85c63a9af3a8bf54f41f46060f8
66c5d001c1953acb5f324e83aafebc9d
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና እና ተስፋው
ሀገር አቀፍ ዜና
ጽጌረዳ ጫንያለው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለአፍሪካውያን ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ይናገራሉ::የአፍሪካ ነፃ ንግድ ሰነዱም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው::በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህሩ ዶክተር ዳዊት ሀዬሶ እንደሚናገሩት፤ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና አስፈላጊ የሚሆንበት ዋናው ምክንያት እንደ አህጉር የእርስ በእርስ ንግድ ትስስሩ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ እና ይህንን ወደ ከፍታ ለመመለስ ነው::ከዚያም ባሻገር ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር፣ ሰፊ የገበያ አማራጭ ለመፍጠር፣ ጥራት ያለው ምርት ለማግኘትና ለማቅረብ፣ ተጨማሪ ገቢ ለሠራተኛው፣ ለባለሀብቱና ለሸማቹ ለማስገኘት ይጠቅማል::በሌላ በኩል ሕገወጥ ንግድን ይቀንሳል፤ ግብር የሚከፍሉ ነጋዴዎችን ያበራክታል::ንግዱን ነፃ እንቅስቃሴ እንዲኖረው በማስቻል ተመጣጣኝ ዋጋ ገበያው ላይ እንዲኖርም ያደርጋል::በተለይ በአፍሪካ አገራት ያለውን የሰው ሃይል ከመሸጥ አኳያ ከፍተኛ ፋይዳ አለው::ይህ ማለት በሁለት መልኩ ሊሆን ይችላል::አንዱ የሥራ ዕድል በመፍጠር ሲሆን፤ ሁለተኛው በምርታማነት ደረጃ ሌሎች የሚገዙበትን ዕድል ይሰጣል::እንደ አፍሪካ ያለው ችግር ተመሳሳይ በመሆኑም አንዱ ከአንዱ ጋር ተመጋጋቢ ሆኖ ከላይ ወደታች ያለውን አሠራር ያስቀራል ይላሉ::ከአፍሪካ ጥሬ ዕቃ ሄዶ አውሮፓ ወይም እስያ ላይ ተመርቶ መልሶ በዝቅተኛ ታክስ ለአገር ውስጥ ይቀርባል::ይህ ነፃ የንግድ ቀጣና ተግባራዊ መደረጉ አምራቹ ሳይቀር አፍሪካ ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል::የቁጠባ ባህልን ከፍ በማድረግ የውጭ ምንዛሬን ዝውውር ያፋጥናል::የውጭ ምንዛሬ እጥረትንም የሚቀንስ መሆኑን ይናገራሉ::እንደ አየር ትራንስፖርት ላሉ አገልግሎቶችም የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ እንደሆነ የሚጠቁሙት ዶክተር ዳዊት፤ ከገበያ፣ ከእውቀት ሽግግር፣ ከውጭ ንግድ ዕድገት አንፃርም ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ያነሳሉ::የነፃ ቀጣናው ስምምነት መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ፤ የዓለም ንግድ ድርጅት ከተመሰረተ እ.ኤ.አ ከ1994 በኋላ አሁን የተመሰረተው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ትልቁ ሲሆን፤ 54 አገራትን አቅፏል። 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ሕዝብን ይይዛል፤ 3 ነጥብ 4 ትሪሊየን ዶላር በአጠቃላይ ምርት ይዞ አህጉሩን እርስ በእርስ ያስተሳስራል::በዚህ ሁሉ የማደግ ሁኔታን ያመቻቻል::የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጡን ከነበረበት 16 በመቶ ወደ 33 በመቶ ያሳድገዋል ተብሎ ይታመናል::የንግድ ሚዛን ጉድለቱንም ከ50 በመቶ በታች ይቀንሰዋል::ለአህጉሩ 2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር በዓመት የተጣራ ገቢ ያስገኛል ::እንደ መረጃው ከሆነ፤ የሸማቾች ገንዘብ ወጪ የማድረግ አቅምን 2036 ነጥብ 7 ትሪሊየን ዶላር እንዲደርስ ያደርገዋል::ይህ ሆነ ማለት የገንዘብ ዝውውሩ የተረጋጋ እንዲሆን ያግዛል::በዚህም ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል::የታሰበው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውጤታማ እንዲሆን ብዙ ተግባራት መከናወን እንዳለባቸው የሚገልፁት ዶክተር ዳዊት፤ የኢትዮጵያ የንግዱ ማህበረሰብን ተወዳዳሪ ለማድረግ በተለይም አብዛኛው ምርት የግብርና በመሆናቸው የኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ መሥራት ያስፈልጋል::ውጤታማ የምንሆንባቸውን ምርቶች ወደገበያ ለማቅረብ የማያስችሉ ልማዳዊ አሠራሮች ወይም ቢሮክራሲዎችን መቀነስ ይገባል::ያለንን ሀብት ማውጣት ላይም መሠራት አለበት::እንደ አፍሪካ የንግድ ሕጉን ማሻሻል፣ ተመሳሳይ የታክስ ታሪፍ ማስቀመጥ፣ ለነጋዴዎች የነፃ ቪዛ ሂደቱን ማስተካከልም አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ::እ.ኤ.አ በ2018 የወጣ መረጃ እንደሚያመላክተው፤ የአፍሪካ አገራት የእርስ በእርስ የንግድ ትስስር ከአጠቃላይ የንግድ ልውውጡ 19 በመቶ ብቻ ነው::ይህ ሲታይ ከ80 በመቶ በላይ የንግድ ልውውጡ የሚደረገው ከአፍሪካ ውጭ እንደሆነ ያመላክታል::የአውሮፓ አገራት የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ 69 በመቶ ይሸፍናል::እስያውያንም እንዲሁ 59 በመቶ የእርስ በእርስ ንግድ ልውውጥ ያደርጋሉ::አፍሪካ ውስጥ ግን በጣም ዝቅ ያለ በመሆኑ የንግድ ሚዛን ጉድለት ያስከትላል::ስለዚህም አህጉሩ እነዚህንና መሰል ችግሮችን ለመፍታት አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናዎችን መመስረት አስፈልጓቸዋል::ሁኔታው በሚገባ ከተሰራበት በቀጣይ እንደ አገርና አፍሪካ ብቻ ሳይሆን እንደ አለምም በንግዱ ዘርፍ ታዋቂና ኃያል የሆኑ አገራት ይወጣሉ::የሕዝብ ተጠቃሚነትም በዚያው ልክ ይረጋገጣል::ከድህነት የመላቀቁም ሁኔታ ይመቻቻል::
https://www.press.et/Ama/?p=39249
f5dd16666ec0062def5e1fca7e69bd09
2f5409753f23bd86990d6fe50dba82a4
የጁንታው መያዝ መንግስት እየወሰደ ላለው የሕግ ማስከበር ትልቅ ስኬት እንደሆነ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ሞገስ ተስፋ አዲስ አበባ፡- የጁንታው ቁንጮ አቦይ ስብሃት መያዝ መንግስት እየወሰደ ላለው የሕግ ማስከበር ትልቅ ስኬት እንደሆነ አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።ኢትዮጵያ በሴራ እና ተንኮል እንደማትፈርስ በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነም አመለከቱ ።አዲስ ዘመን ያነጋገራቸው አቶ ውብሸት ጌታሁን እንዳሉት፣የጁንታው ቁንጮ የሆኑት አቶ አቦይ ስብሃት ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው እያሉ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር ሲሰብኩ የነበሩ ናቸው::ነገር ግን በሴራ እና በተንኮል ኢትዮጵያ እንደማትፈርስ አይተዋል ያሉት አቶ ውብሸት፣ የግለሰቡ መያዝ ብለዋል::የመከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ያለው ሕግን የማስከበር ዘመቻ ፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለሚዳፈሩ እና ለወንጀለኞች ትልቅ ማስተማሪያ እንደሆነም አመልክተዋል ። ጁንታዎቹ በሥልጣን ዘመናቸው እጃቸው በብዙ ንጹሃን ደም የተጨማለቀ ቢሆንም መንግሥት ወደ ብቀላ ሳይገባ በሕግ የበላይነት በመተማመን እና በሕገ መንግሥቱ መመራት እየወሰደ ያለው ሕግ የማስከበር እርምጃ ለሕግና ለሕገመንግስታዊ ሥርዓት ያለውን ታማኝነት ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል:: ጁንታዎች አልመው ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብለው ሲናገሩ የማያፍሩ ሰዎች ናቸው የሚሉት አቶ ውብሸት፣ ሕዝብ ሲኖር ባለሥልጣን ይኖራል፣ ባለሥልጣን ሆኖ ለመኖር ደግሞ ሕዝብ መኖር አለበት::ሀገር ማለት ደግሞ ሌላ ነገር ሳይሆን ሰው ማለት ነው ብለዋል::እነዚህ ጁንታዎች ሥልጣን ተቆናጠው በኖሩበት ዘመን አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሚል አንዱ ከአንዱ ጋር በሰላም እንዳይኖር አቅደው በጥላቻ ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰው ፣ከስልጣን ከተወገዱ ማግስትም እኛ ስልጣን ካልያዝን በስተቀር ሀገር ትፈርሳለች ብለው በድፍረት ከመናገር በዘለለ አቅደው በተግባር ሀገር ለማፍረስ ሲሰሩ እንደነበር ጠቁመዋል ::እንደ አቶ ውብሸት ገለፃ ፣ጁንታው ‹‹ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል›› በማለት ሀገርን ለመበተን ቢሰራም ህልማቸው ሳይሳካ ቀርቷል::ለስልጣናቸው ማራዘሚያ በተደጋጋሚ ትልልቅ የሀገሪቱ ብሔሮችን በማጋጨት ሲጥሩ ነበር ::ይህ ሁሉ ሳይሳካላቸው ከዚህ በፊት የዘሩትን እያጨዱ ነው ብለዋል ::የጥፋት ቡድኑ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጭንብል ሲንቀሳቀስ ቢቆይም ፣ በዲሞክራሲ በፍፁም የማያምን ፣ በጥፋት የተተበተበ መሆኑን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የወሰደው አሳፋሪ ጥቃት ትልቁ ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል::ሌላኛዋ የአዲስ አበባ ነዋሪ ወይዘሮ ትህትና በላይ በበኩላቸው ፣ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከውጪም ከውስጥም ብዙ ሴራዎች ተሸርበዋል፣ ነገር ግን በቁርጥ ቀን ልጆቿ እና በፈጣሪዋ ታግዛ የቆየች ሀገር መሆኑዋን አመልክተዋል ::አሁንም መንግስት የወሰደው የደህንነት ተቋማትን የማጠናከር እርምጃ ተቋማቱ በሙሉ እግራቸው እንዲቆሙና የሕግ የበላይነትን እንዲስከብሩ ማድረግ የሚስችል አቅም እንደፈጠረላቸው በተጨባጭ ማየት እየቻልን ነው ብለዋል::በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር እርምጃ አንጋፋው የተንኮል ቀያሽ እና ስትራቴጂስት መያዙ ትልቅ ድል ነው ያሉት ወይዘሮዋ፣ ይህም በተለይም ሕግ የሚያስከብሩ ተቋማት እንደሀገር እየተጠናከሩ መምጣታቸው አመላካች እንደሆነ ጠቁመዋል :: የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ሲሰሩ የነበሩ ቁልፍ አመራሮች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው በሕግ ማስከበሩ ዘርፍ ትልቅ ስኬት እንደሆነ የገለፁት ፣የአዲስ አበባ ነዋሪው አቶ ይሁኔ ገበየሁ፣ በጁንታው የተንኮል ሴራ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ መደረጉን አስታውሰዋል::የጥፋት ቡድኖችን መልምለው፣ በማሰልጠን ፣ በማስታጠቅ እና ለጥፋት ስምሪት በመስጠት ዋነኛ ተዋንያን እንደነበሩ ገልጸው ፣ የጁንታው አድራጊ ፈጣሪ እና የተንኮል ቁልፍ ቀያሽ መያዙ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጥፋቶችን ሲያደርሱ የነበሩ ቡድኖች እንዲጠፉ ያደርጋል ብለዋል። ቀሪዎቹን የጁንታው ተፈላጊ አባላት ለቃቅሞ ለሕግ ማቅረብ ጥልቅ አቅም ይፈጥራል ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመላው ሀገሪቱ ሰላምን ለማረጋገጥ የግለሰቡ መያዝ ወሳኝ ድል እንደሆነ ገልፀዋል::አሁን ተረኝነት የሚያስከትለውን መዘዝ ያየንበት ጊዜ ነው፣ ተረኛ ነኝ ብሎ ሀገር ላይ ማሴር፣ የሀገሪቱን ሕዝቦች መከፋፈል፣ ከሕግ አግባብ ውጪ ዜጎችን መቅጣት ውጤቱ ምን እንደሆነ በተጨባጭ ያየንበት በመሆኑ ከዚህ መማር ያስፈልጋልም ብለዋል ::ስልጣን ያዝኩ ብሎ አንዱን ጠቅሞ ሌላውን መጉዳት ውጤቱ ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንደማያስገኝ በማሰብ ለአንድነት፣ ለዲሞክራሲ ለሕግ የበላይነት እና ለፍትህ ያለምንም አድሎ መስራት ከመሪዎች እንደሚጠበቅም አሳስበዋል::
https://www.press.et/Ama/?p=39248
91b551a776ebef4aae0451c04e846ee1
64fbaacb8f825f1c6038eaf460ace499
በግማሽ የበጀት ዓመቱ ለግድቡ ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ
ሀገር አቀፍ ዜና
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በግማሽ በጀት ዓመቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ከ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ እንደገለጹት÷ በስድስት ወራት በከተማው በቦንድ ግዢ ሽያጭ እና በስጦታ የተሰበሰበው ገንዘብ ባለፉት 8 ዓመታት በድምሩ ከተሰበሰበው የሚበልጥ ነው::ከ2003 ዓ.ም ሐምሌ ወር እስከ 2012 ዓ.ም ሐምሌ ወር ባሉ ዓመታት በከተማዋ የተሰበሰበው 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር እንደነበር ጠቁሟል :: ለገቢው ማደግ ምክንያት መንግስት ፕሮጀክቱን በግልፅነት መምራት መቻሉ እንደሆነ አመልክተዋል::ፕሮጀክቱ ላይ የነበሩ ችግሮች ይፋ ተደርገው የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በሕዝብ እና በመንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር መደረጉንም አስታውቀዋል::የግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መከናወንም ማህበረሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ እንዲያደርግ መነቃቃት መፍጠሩንም ጠቁመዋል::በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 789 ሚሊዮን ብር እሰበስባለሁ ያለው ከተማ አስተዳደሩ በግማሽ ዓመት ውስጥ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መቻሉንም አመልክተዋል ::
https://www.press.et/Ama/?p=39247
87d34fb4ca21656be9b9f5b19d005ad8
238790f6962b11e39b556fdfe12c1add
ስፖርቱ የማገገሚያ ድጎማ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ስፖርት
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የዓለም ወቅታዊው ሁኔታ፤ የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ፣ አስተሳሰብና ልማድ እንዲቀየር ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህ መንስኤነትም አካላዊና አእምሯዊ ጤናን ከመጠበቅና ከማዝናናት ባለፈ ከፍተኛ ገንዘብ የሚዘዋወርበት ስፖርትም በቀድሞ ቁመናው ላይ እንዳይገኝ ሆኗል፡፡ በዘርፉ በዓለም ደረጃ እአአ በ2011 ከተገኘው ገቢ በ45 በመቶ የላቀ ትርፍ ከሁለት ዓመታት በፊት መገኘቱን ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ያመላክታል፡፡ ይህ እአአ በ2018 የተገኘው 471ቢሊዮን ዶላር በዚህ ዓመት በእጅጉ ሊያድግ እንደሚችልም አመላካች ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተከስቶ መላውን ዓለም ባዳረሰው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ምክንያት እንቅስቃሴው ሊገታ ችሏል፡፡ እንደ ሌላው ዓለም ሁሉ የኢትዮጵያ ስፖርትም መዳከም አሳይቷል፡፡ በእንቅስቃሴው መገታት በስፖርተኞች፣ ክለቦች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ አወዳዳሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች መካከል የነበረው ሰንሰለት በቫይረሱ ተጠቅቷል፡፡ በጥቂት ውድድሮች ሽልማት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና የውጭ ምንዛሪ ለሀገር ያስገኙ ከነበሩ አትሌቶች፤ ‹‹ነገ ያልፍልኛል›› በሚል እሳቤ ከኑሮ ጋር እስከሚታገሉት ጀማሪ ስፖርተኞች ድረስ የጉዳቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ከአቅማቸው በላይ የሆኑትም ከበጎ ፈቃደኞች ተደጓሚ ሆነዋል፡፡ የስፖርት ማህበራትም ከውድድሮችና ስፖንሰሮች ማግኘት የሚገባቸውን ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ ይህንን አሳሳቢ ሁኔታ ያጤነው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ወረርሽኙ በዘርፉ ላይ ያሳደረውን ጫና በማመዛዘን እንዲሁም በተወሰነ መልኩ የሚያገግምበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚረዳ ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በጉዳዩ ላይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማብራሪያ የሰጡት ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጂሎ፤ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ እንደ ንግድ ሁሉ ስፖርትም ጉዳት ያስተናገደ ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ስፖርተኞች ቀድሞ የሚያገኙትን ገቢ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ ክለቦች የመፍረስ አደጋ የተደቀነባቸው በመሆኑ መሰል ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት ከመንግሥት ማገገሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንዲለቀቅ ጥያቄ መቅረቡንም ይገልጻሉ፡፡ ኮሚሽኑ ለመንግሥት ያቀረበው የዳሰሳ ጥናት ‹‹ኮሮና ቫይረስ በስፖርቱ ልማት ላይ ያሳደረው ተጽእኖ የማገገሚያ ስልት›› የሚል ሲሆን፤ ጥናቱ የተከናወነውም የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር ጭምር ነው፡፡ በዚህም እንግሊዝ፣ ናይጄሪያ፣ ኬንያ እና የመሳሰሉት ሀገራት በወረርሽኙ ወቅት ለማገገሚያ የተጠቀሙትን ስልት ለመዳሰስ መሞከሩንም አመላክተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስፖርት ሕዝባዊ መሠረት ያለው እንደመሆኑ በስፖንሰርና በስታዲየም ገቢ ከሚያገኙት ገንዘብ ባለፈ ለከተማ ክለብ ስፖርተኞች ደመወዝ የሚከፈለው ከሕዝብ ከሚሰበሰበው ታክስ ነው፡፡ ይህም ማለት አብዛኛውን ገንዘብ የሚሸፍነው መንግሥት ነው፡፡ ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ውድድሮችን ማካሄድ ባለመቻሉ በዘርፉ ያለው  እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ይህንን ጊዜ ለመሻገርም ከስፖርት ማህበራቱ ጋር በመተባበር ስትራቴጂ በመንደፍና ጥያቄውን ለመንግሥት በማቅረብ ኮሚሽኑ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ጥናቱ ስፖርተኞች በምን መልክ ወደሥልጠናና ውድድር ይመለሱ፣ እንዴትስ ፈቃድ ይሰጣቸው የሚለውን በመነሻነት መያዙንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ የሚጠቅሱት:: እንደ ኮሚሽንም ሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራቱ መርሃ ግብራቸውን እንዲያቀርቡም መመሪያ ተላልፏል፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን በውል አይታወቅም፡፡ ይህም መሰል ጥናቶች ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ፌዴሬሽን ይብዛም ይነስም በስፖንሰር የሚያገኙት ገቢ ይኖራል፤ ሆኖም በዓመት ይህን ያህል ይገኛል የሚለው በውል አይታወቅም፡፡ ለአብነት ያህል የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኢንተርናሽናል እና የሀገር ውስጥ ስፖንሰሮች ቢኖሩትም ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር በተያያዘ በትክክል ለማወቅ የሚቻልበት ሁኔታ አዳጋች ነው፡፡ ቢሆንም ቅድመ በግምቶችን በማስቀመጥ ጥናቱ መከናወኑንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስረዱት፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ የስፖርቱን ዘርፍ ሙሉ በሙሉ ጎድቷል፤ እንቅስቃሴዎችንና ውድድሮችን ገድቧል፡፡ በስፖርተኞችና ሀገራትም ላይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን አስከትሏል፤ ይህም አደጋ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ጊዜ ያልፋል በሚል ተስፋ ሁሉም በአንድነት እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሁኔታዎችን በማገናዘብ ምላሽ ይሰጣል የሚል ተስፋ አለ፤ ይህን ወቅት በመሻገርም ስፖርቱን ወደነበረበት የስፖርት ቤተሰቡም ወደ ተመልካችነቱ የሚመለስበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ በመሆኑም ይህንን ጊዜ በጋራ ለማለፍ ራስን ከቫይረሱ መጠበቅ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ እንዲቆዩም ምክትል ኮሚሽነሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 15/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=35809
f6511d76b02e901804596169e7dcc89b
b1081c38c755c9c6137ed675d8b2a725
የገዳ ስርዓት – የኦሮሞ ሕዝብ የትልቅነቱ ምልክትም ሀብትም
ሀገር አቀፍ ዜና
አስቴር ኤልያስ ስፍራው በተለያዩ የሴቶችና የወንዶች አልባሳት ደምቋል::በአልባሳቱ ላይ ገኖ የሚታየው ነጭ ቀለም በመሆኑም አስተውሎ ለተመለከተው ዙሪያ ገባውን የፈካ ማሽላ አስመስሎታል::በተለያዩ ድንኳኖች ውስጥ ደግሞ የጉጂ የባህል ምግቦች እንዲሁም የተለያዩ ጌጣጌጦችና አልባሳት ለእይታ ቀርበዋል::በዚሁ ስፍራ አምስት የጎጆ ቤቶች በመደዳ ተሰድረው ይታያሉ::ስፍራው በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ የጉጂ ኦሮሞ የባህል ስርዓት የሚካሄድበት ቦሌ ሀገላ ነው ::በዕለቱ የገዳ ስርዓቱን ደረጃ የሚያሳይ ትርዒት በስፍራው የተካሄደ ነው ፣ እነዚህም ደበሌ፣ ቀሬ፣ ኩሳ፣ ራባ፣ ዶሪ፣ ገዳ፣ ባቱ እና ዩባ የተባሉት ናቸው ትርዒቱን ያቀረቡት::በዕለቱ መርሐግብሩን በንግግር የከፈቱት የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፈርያት መሀመድ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ የብዙ ባህል ባለቤት ናት::የኦሮሞ ህዝብ ደግሞ ከትውልድ ወደትውልድ ሲያስተላልፍ የመጣው የገዳ ስርዓት አንዱ ነው ፣ ይህም የገዳ ስርዓት እንደ እሬቻ፣ ስንቄ፣ ሞጋሳና ሌሎችንም በርካታ እሴቶችን በውስጡ የያዘ ነው::እነዚህም እሴቶች ለኦሮሞ ብሎም ለአገሪቱ ሕዝቦች ወንድማማችነት እንዲጠናከር የሚያግዙ ናቸው ::የገዳ እሴቶች ውበታቸውንም ጥንካሬያቸውንም ጠብቀው ከትውልድ ወደትውልድ እንዲተላለፉ የሁሉም ድርሻ ነው የሚሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ሚኒስትር መሥሪያ ቤታቸው ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን በቅንጅት እንደሚሰራም ነው ያረጋገጡት::የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው፤ የገዳ ስርዓት ለኦሮሞ ሕዝብ ሀብቱም ምልክቱም መሆኑን ይናገራሉ::ኦሮሞ በዚህ ሥርዓት ሲተዳደር እንደነበር ሁሉ ዛሬም በመተዳደር ላይ እንደሚገኝም ጠቅሰው፤ በዚህ ሥርዓት ውስጥ መብት እንዳለ ሁሉ ግዴታ መኖሩን ያመለክታሉ::በተለይም ደግሞ ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግርን አጥብቆ ስለሚከተል በዚህም ዓለም እንደሚያውቀው ነው የተናገሩት::እርሳቸው እንዳሉት፤ ይህ ስርዓት ቀደም ሲል በተወሰነ ደረጃ ተዳክሞ ነበር::ይሁንና በተሰሩ ጠንካራ ስራዎች አማካይነት በዩኔስኮ ከመመዝገቡም በተጨማሪ በክልል ደረጃ ከአንድ እስከ ስምንተኛ ክፍል ትምህርት የሚሰጥ ሲሆን፣ በዩኒቨርሲቲ ደረጃም እስከ ሶስተኛ ዲግሪ እየተሰጠ መገኘቱ ይበል የሚያሰኝ ጉዳይ ሆኗል::በመሆኑም ኦሮሞ አሊያም ኢትዮጵያ ብቻ የሚኮራበት ሳይሆን አህጉሪቱ አፍሪካ እንዲሁ የምትኮራበት ስርዓት ነው::የምዕራብ ጉጂ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ከድር ኤሌሞ በበኩላቸው፤ የሕዝቦችን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ባህልን ማክበር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ የገዳ ስርዓት ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ የሚተዳደርበት የዴሞክራሲ መሰረት የሆነ በመሆኑ ሊከበርም ከትውልድ ወደትውልድ ለማሸጋገር በሚደረገው ሂደት መተባበርም ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል::የዴሞክራሲ መሰረት የሆነውን የገዳ ስርዓት ማጠናከር የሕዝብን አንድነት ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል::በዕለቱ ያነጋገርናቸው ወጣት ነጌቱ ደስታ እና ወጣት ሌሎ ሂርባዬ በየበኩላቸው፤ የገዳ ስርዓትን ለማስቀጠል በመጀመሪያ ግንዛቤን ከፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የተናገሩት::በተለይ የዴሞክራሲ መሰረት ነው የተባለውና በተግባሩም እየታየ የሚገኘው ይኸው ስርዓት በዩኔስኮ መመዝገቡ ብቻ በራሱ የዴሞክራሲን ስርዓት እንደማያስቀጠል ጠቅሰው፤ ስርዓቱን በማስቀጠል ረገድ ከወጣቱ ብዙ እንደሚጠበቅ ነው ያመለከቱት::የገዳ ስርዓት መለያ ምልክታቸው እንደሆነም ይናገራሉ::የገዳ ስርዓት አንደኛውን ትውልድ ከሌላኛው ትውልድ የሚያያዝ መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ ሌላኛዎቹ ወጣቶች ጫልቱ ደስታ እና ገመዴ ገናሌ ናቸው::ወጣቶቹ የገዳ ሥርዓት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ መሰጠት መጀመሩ ለቅብብሎሽ ትልቁን ሚና የሚጫወት ስለመሆኑም ጠቅሰዋል::እነርሱ የተማሩት ከቤተሰቦቻቸው እንደመሆኑ እነሱም በቀጣይ ለትውልድ ለማስተላለፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ይናገራሉ:: ከትናንት በስቲያ የገዳ ስርዓት ለዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት የመታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የገዳ ፓናል ውይይት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በትናትናው ዕለት ደግሞ የጉጂ ባህልን የሚያመለክቱ የተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂደዋል::ወጣቶች የገዳ ስርዓት የኦሮሞ ሕዝብ ሀብትም ምልክትም ነው የሚሉት::
https://www.press.et/Ama/?p=39254
74349306f8e6a43fd83bd75413ac64d1
961de908a42148c5a283d1f07e6fd103
ከድጡ ወደ ማጡ
መዝናኛ
ሰዎችን ከሱስ ለማላቀቅ የማይፈነቀል ድንጋይ የለም። ምክር፣ ህክምና፣ ለደግ ሲባል ማግለል እና የመሳሰሉት ሁሉ ይሞከራሉ። በተለይ ቤተሰብ ቤቱን ቆሌ ያራቀውን ይህን ችግር ለመፍታት ብዙ ይጥራል። ይህ ጥረት ጥቂቶችን ሲታደግ ቢስተዋልም፣ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይተውም እንዲሉ ይህን ሁሉ አሸንፈው እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ሱሰኛ የሚሆኑ ሰዎች ግን በርካታ ናቸው። ሜክሲኮዊቷ የባሏ መሸተኛነት መሆን በእጅጉ ያስመርራታል። መከረች ዘከረች አልሆን አላት። ቢራ መጨለጡን ሊተው ባለመቻሉ ከዚህ ችግር ሊገላግላት የሚችለውን መላ ማፈላለግን ትመርጣለች። አንድ ቀንም አንድ ሀሳብ ብልጭ ይልላታል። ቢራ እርም እንዲል ያረገዋል ያለችውን መላም ተግባራዊ ለማድረግ ትወስናለች። ሚቼል ኤን የተባለችው ይህች የሜክሲኮ ሲናሎአ ከተማ ነዋሪ፣ ለእዚህ ውሳኔዋ መሳሪያ ይሆኑኛል ስትል ያሰበቸውን ውህድ ከእንግሊዝ ጨውና ከዘይት መሰል ነገር ታዘጋጃለች። ንጥረ ነገሮቹ ቀስ በቀስ ሥራቸውን እንዲያከናወኑ ያስችላል ያለችውን ቅመማም ታደርጋለች። ለእዚህም የተለያዩ ድረ ገጾችን እስከማንበብ ትደርሳለች። ውሳኔዋን ስራ ላይ ለማዋልም ባለቤቷ ጆሴ በራያን ሳያይ ጥቂት ጠብታዎችን በቢራ ጠርሙሶቹ ውስጥ ትጨምራለች። ያህን ያላየው ባለቤቷም እንደ ወትሮው ቢራውን መጨለጡን ይቀጥላል። ቀስ በቀስ ግን ባልተለመደ መልኩ ሆዱን መታመም ይጀምራል፤ ክፉኛ ማስቀመጥም ይጀምረዋል። እሱ ግን ብዙም እንደ ችግር አልተመለከተውም። ሚቼል ግን ተቅማጡ የሆነ አለርጂ ያስከተለው ሳይሆን አይቀርም ስትል ትገልጽለታለች። ችግሩ ምንአልባትም ከአልኮሆል ጋር ሊያያዝ እንደሚችልም ትጠቁመዋለች። እሱ ግን የምትለውን ከቁብ ሳይቆጥር አሁንም እንደ ወትሮው መጠጣቱን ይቀጥላል። ለሆድ ህመሙም ማስታገሻ እየወሰደ መጨለጡን ይቀጥላል። ባለቤቱ ይህ ነገር አይሆንም መጠጣትህን አቁም ትለዋለች፤ተቅማጡ ቢያስቸግረውም መጸዳጃ ቤቱ አጠገቤ እስከ ሆንኩ ድረስ ይህ አያስጨንቀኝም እያለም በባለቤቱ እየቀለደ ይጠጣል። ሚቼል ግን የባለቤቷን ፌዝ ወደ ጎን በመተው አሁንም ሌላ መላ ማፈላለግን ስራዋ ታደርጋለች። በቢራው ውስጥ የምትጨምረውን ንጥረ ነገር መጠን በመጨመርም ቢራውን ማቅረብ ትጀምራለች። በቀጣዩ ቀን የባለቤቷ ተቀማጥ አሳሳቢ እየሆነ ይመጣል። መጸዳጃ ቤት ለመድረስ እንኳ እድል የሚሰጥ አልሆን ይለዋል። እሷም ጉዳዩ በጣም ያሳስባትና በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ ሆስፒታል ይዛው ትሄዳለች። ጆሴ በምርመራ ወቅት ለሀኪሞች ችግሩ ምናልባትም ከሚጠጣው ቢራ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይገልጽላቸዋል፤ ከህመሙ ለመፈወስ ሲል ሁለተኛም ቢራ በደረሰበት እንደማይደርስ ያረጋግጥላቸዋል። ቢራው ሆዱን ከማሳመም በተጓዳኝ መቀመጥ እንደከለከለውና ሰላም እንደነሳው ይነግራቸውና አለመጠጣቱን እንደሚመርጥ ይገልጽላቸዋል። ቫንጋርዲያ የተሰኘው የሜክሲኮ ጋዜጣ ጉዳዩን አስመልክቶ እንደሰራው ዘገባ፣ ያቀደችው ያልተሳካላት ይልቁንም ሌላ ጣጣ ያመጣባት ባለቤቱ በሰራችው ድርጊት ትጸጸታለች፤ ባሏ ቢራ እንዲጠላ ለማድረግ በቢራ ውስጥ ባእድ ነገር መጨመሯን በመግለጽ ለተቀማጡ ምክንያቱ እሷ መሆኗን ታስታውቃለች። ጉዳዩ ፖሊስ ዘንድ ይደርስናም ጆሴ ባለቤቱ ከፍታ በምታቀርብለት ቢራ ጠርሙስ ውስጥ አንዳንዴ ባእድ ነገር ይመለከት እንደነበር ለፖሊስ ገልጾ፣እሱ ግን ይህን ያህል ጎጂ ነገር ሊሆን ይችላል ብሎ አስቦም ገምቶም እንደማያውቅም ይናገራል። ፖሊስም ሚቼል በፈጸመችው ድርጊት በተጠ ርጣሪነት በቁጥጥር ስር ያውላታል፤ በእዚህ ድርጊቷም ፍርድ ቤት ቀርባ ቅጣት ሊጣልባት እንደሚችልም ፖሊስ መግለጹን ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ድረገጽ መረጃ ያመለክታል። የሚወዱትን ሰው ከችግር ለመታደግ ሲባል የሚወሰድ እርምጃ ሌላ ችግር እንዳያስከትል መጠንቀቅ እንደሚገባ ዘገባው ያመለክታል። አዲስ ዘመን ጥር 12/2012ዘካርያስ
https://www.press.et/Ama/?p=25947
12e255637a899407252ae3f3bbb2e663
75d675f81bcb7e190c21aebd0b8a2bb8
193 አትሌቶች ከዓለም አትሌቲክስ የገንዘብ ድጋፍ ተጠቃሚ ይሆናሉ
ስፖርት
የዓለም አትሌቲክስ ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት ከውድድር በመራቃቸው የገንዘብ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል ለተባሉ አትሌቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ባለፈው ሚያዝያ መጨረሻ ማሳወቁ ይታወሳል። የዓለም አትሌቲክስ ለዚሁ ድጋፍ እንዲውል አምስት መቶ ሺህ ዶላር ማዘጋጀቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህን ድጋፍ ለአትሌቶች ለማድረስ የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንቱ ሴባስቲያን ኮ በሊቀመንበርነት የሚመሩት የባለሙያዎች ቡድን ተቋቋሞ በስድስት ዞኖች በተከፋፈለው የዓለም አትሌቲክስ አባል አገራት የሚገኙ አትሌቶች የሚያቀርቡት የድጋፍ ጥያቄ ተጣርቶ ዕርዳታው መሰጠት ጀምሯል። በዚህም መሠረት መቶ ዘጠና ሦስት አትሌቶች ተለይተው ድጋፉ እንደደረሳቸው ታውቋል። ዕርዳታው የሚሰጣቸው አትሌቶች ከሃምሳ ስምንት የዓለም አትሌቲክስ አባል አገራት ፌዴሬሽኖች የተለዩ ሲሆን እያንዳንዳቸው በመጀመሪያው ዙር ድጋፍ ሦስት ሺህ ዶላር እንደሚደርሳቸው ተጠቆሟል። የድጋፍ ጥያቄውን ለማቅረብ የተሰጠው ቀነ ገደብ ባለፈው የፈረንጆች ግንቦት ሰላሳ ቀን የተጠናቀቀ ሲሆን ሁለት መቶ ስልሳ አንድ አትሌቶች የድጋፍ ጥያቄውን አቅርበው ጉዳዩን የሚመረምረው የባለሙያዎች ቡድን በተቀመጠው መስፈርት መሠረት አጣርቶ መቶ ዘጠና ሦስት አትሌቶች ድጋፉን እንዲያገኙ ውሳኔ አሳልፏል። የባለሙያዎቹ ቡድን ድጋፉን ለመስጠት በዋናነት ከተመለከታቸው መስፈርቶች መካከል አንድ ድጋፍ የሚሻ አትሌት በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አገሩን ለመወከል የተመረጠ መሆን እንዳለበት፣ ለገጠመው የገንዘብ ችግር አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ ካለፈው የውድድር ዓመት አኳያ የሚያገኘው ገቢ በእጅጉ የቀነሰና ከአበረታች መድሃኒት ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ክስ ያልቀረበበት መሆን እንደሚገባው ጠቁመዋል። በተጨማሪም በየትኛውም የውድድር አይነት በዓለም አትሌቲክስ የደረጃ ሰንጠረዥ ከአንድ እስከ ስድስት ባለው ውስጥ ስማቸው የሰፈረ አትሌቶች፣ በ2019 በየትኛውም የወርቅ ደረጃ ባለው የጎዳና ላይ ውድድር እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ያጠናቀቁ እንዲሁም በ2019 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች እስከ ስልሳ ሺህ ዶላር ድረስ ሽልማት ያገኙ አትሌቶች የድጋፍ ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንደሌለው ታውቋል። ድጋፉን የሚያገኙ አትሌቶች ወይም አገራት ስም ያልተጠቀሰ ሲሆን ጥያቄያቸው ተመርምሮ ድጋፍ የሚደረግላቸው አትሌቶች በዚህ ሳምንት መጨረሻ ገንዘቡ እንደሚደርሳቸው ተጠቁሟል። የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት እንዲሁም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ሴባስቲያን ኮ ይህን ድጋፍ ለአትሌቶች ለመስጠት እንደታሰበ በሰጡት መግለጫ ወቅት እንዳስቀመጡት፣ የገንዘብ ድጋፉ ባለፉት ጥቂት ወራት ከውድድር በመራቃቸው ምንም አይነት ገቢ አጥተው የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ለገቡ አትሌቶች ይውላል። እ.ኤ.አ በ1986 በሞናኮው ልዑል አልበርት ሁለተኛ አማካኝነት በአትሌቲክስ ስፖርት ለሚገጥሙ ችግሮች የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ለማከናወን የተቋቋመው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን ካለው በጀት ላይ ቀንሶ አትሌቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለገጠማቸው ችግር ድጋፍ እንዲውል ማድረጉ ይታወቃል። ድጋፉን ለመስጠት ከተቋቋመው ኮሚቴ መካከል የቀድሞው የኦሊምፒክ የ1500 ሜትር አሸናፊው ሞሮኳዊ አትሌት ሂቻም ኤልግሩዥ፣ የምርኩዝ ዝላይ የዓለም ቻምፒዮኗ ካተሪና ስቲፋኒዲ (የዓለም አትሌቲክስ ኮሚሽንን ወክላ)፣ የዓለም አትሌቲክስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሱኒል ሳብሃርዋልና ኤቢይ ሆፍማንና ሌሎችም ተካተዋል። ‹‹ሂቻም ኤልግሩዥ ይህን የድጋፍ ሃሳብ በማቅረቡና ልዑል አልበርት ይህን ፕሮጀክት እውን ለማድረግ ላበረከተው ጠንካራ ድጋፍ ላመሰግናቸው እወዳለሁ›› በማለት ሃሳባቸውን ያሰፈሩት ሴባስቲያን ኮ፣ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከዓለም አትሌቶች ጋር በተለያየ መንገድ የቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው በመጠቆም ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመሰረዛቸው በርካታ አትሌቶች የገቢ ምንጫቸው እንደ ደረቀና የገንዘብ ችግር እንደገጠማቸው አብራርተዋል። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የዓለም አትሌቲክስ ውድድሮች በእጅጉ መጎዳታቸውን ያስታወሱት ኮ፣ አትሌቶች ገቢያቸው ከውድድር የሚያገኙት ሽልማት እንደመሆኑ በዓመቱ መጨረሻ የተወሰኑ ውድድሮችን በማካሄድ ስፖርቱንና አትሌቶቹን እንዳይዳከሙ የማድረግ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። አትሌቶችን ለመደገፍ አሁን ከተያዘው በጀት ባሻገር የስፖርት ቤተሰቡ በሚያደርገው ድጋፍ ተጨማሪ የረድኤት ሥራዎች እንደሚከናወኑም ጠቁመዋል። ልዑል አልበርት ሁለተኛ በበኩላቸው ፋውንዴሽኑን ከመሠረቱ ከሰላሳ አምስት ዓመታት በላይ እንደሆነ በማስታወስ የፋውንዴሽኑ አላማ አትሌቲክስን ማበረታታትና ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች እንዲሁም አትሌቶች በችግር ጊዜ የገንዘብ ዋስትና እንዲኖራቸው ማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም መሠረት ፋውንዴሽኑ ባለፉት ዓመታት ሰላሳ ሚሊየን ዶላር ለተመሳሳይ አላማ እንዳዋለና አሁንም አትሌቶች በሚቸገሩበት በዚህ ወቅት ሊደርስላቸው በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። ይህ ድጋፍ አትሌቶች ኦሊምፒክን ጨምሮ ለዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዳያቋርጡና በገጠማቸው ችግር ውጥረት ውስጥ እንዳይገቡ ሊረዳቸው እንደሚችልም አክለዋል። የቀድሞው የ1500 ሜትር የዓለም ክብረወሰን ባለቤትና የድጋፉ ሃሳብ አመንጪ አትሌት ኤልግሩዤ በበኩሉ፣ የኮሮና ቫይረስ በሁሉም ዓለም ሕዝብ ላይ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ እንዳሳደረ በማስታወስ ሁሉም የዓለም ሕዝብ ይህን ችግር ለመጋፈጥ በጋራ የሚቆምበት ወቅት አሁን መሆኑን አብራርቷል። የዓለም አትሌቲክና ፕሬዚዳንቱ የድጋፍ ሃሳቡን በቅንነት ስለተቀበሉትም ምስጋናውን አቅርቧል። ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመታገዳቸውም በርካታ አትሌቶች ሊደርስባቸው የሚችለውን የኢኮኖሚ ጫና በማሰብ ይህን በጎ ተግባር መፈፀም እንደሚያኮራም ተናግሯል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 18/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=35069
86e48b5c7f4d195ab4aac4f43a133409
4d8d08f10d03419d1741f875a4783d34
የኦሊምፒክ ቀን በወርቃማ ኦሊምፒያኖች
ስፖርት
የዓለም ኦሊምፒክ ቀን እ.ኤ.አ ከ1948 ጀምሮ በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ አገራት ይከበራል። ይህም የኦሊምፒክ አባት በሆኑት ፒየር ዲ ኩበርቲን አማካኝነት በአዲስ መንፈስ የተመሠረተውን የኦሊምፒክ ጨዋታ ለማሰብ ይሁን እንጂ በዓሉ ሲከበር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማከናወን ተፈጥሮዊ መብት በመሆኑ ሁሉም ሰው ዕድሜ ፣ ፆታ ፣ ዘር እና ሃይማኖት ሳይገድበው በሁሉም ቦታ በግል እና በጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ በመቀስቀስ እና በማስተማር ጭምር ነው ።የዓለም ኦሊምፒክ ቀን ‹‹ኦሊምፒክ ለሰው ልጆች ጤንነት መልሶ መቋቋም እና ትብብር›› በሚል መሪ ቃል ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ሲውልም ጀግናው አትሌት ሃይሌ ገብረሥላሴና ከማሞ ወልዴ በኋላ በኦሊምፒክ ማራቶን ለኢትዮጵያ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ሲድኒ ላይ ያስመዘገበው ገዛኸኝ አበራን የመሳሰሉ ወርቃማ ኦሊምፒያኖች ደምቆ ውሏል። እነዚህ የኦሊምፒክ ጀግኖች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ከተራዘመው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያን ለመወከል ሲዘጋጁ የነበሩ ወጣት አትሌቶች አስከፊው ጊዜ እስኪያልፍ ራሳቸውን እንዲጠብቁና አቋማቸውም እንዳይወርድ ጠንክረው በመሥራት ከልምምድ መራቅ እንደሌለባቸው ምክራቸውን ለግሰዋል። ያለፉት ሁለት የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናዎች ላይ በአምስት ሺ ሜትር የነገሰው አትሌት ሙክታር ኢድሪስ እንዲሁም በዶሃው ቻምፒዮና ሙክታርን ተከትሎ በመግባት የብር ሜዳሊያ ያጠለቀው ወጣቱ አትሌት ሰለሞን ባረጋ፣ ሰንበሬ ተፈሪና በወርልድ ቴኳንዶ ለመጀመሪያ ጊዜ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክለው ሰለሞን ቱፋ የታላላቆቻቸውን ወርቃማ ኦሊምፒያኖች ምክር በሥፍራው ተገኝተው ተቀብለዋል። በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር፣ የስፖርት ቤተሰቡ የኦሊምፒዝም ፍልስፍናን የዕለት ከዕለት መመሪያው በማድረግ ተግባራዊ ሊያደርገው እንደሚገባ ተናግረዋል። ኦሊምፒዝም ሰላምን፣ ንፁህ ወንድማማችነትን ፣ እርስ በእርስ መግባባትን እና ትብብርን የሚያስተምር በመሆኑ ሁሉም የስፖርት ቤተሰብ የዕለት ከዕለት መመሪያው ሊያደርገው ይገባልም ብለዋል ።‹‹ወቅቱ በጣም አስቸጋሪ እና ፈታኝ በመሆኑ ይህን ክፋ ጊዜ ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ተባብረን እና ተደጋግፈን የወረርሽኙን ጉዳት መቀነስ ይገባል›› ያሉት ኮሚሽነሩ በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እያደረገ ያለው ድጋፍ ሊመሰገን የሚገባውና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል። ስፖርቱ ወደነበረበት እንዲመለስ እና በወረርሽኙ ምክንያት ለተጎዱ የስፖርት ቤተሰቦች መደገፍ የሚያስችል የማገገሚያ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ለመንግሥት መቅረቡንም አቶ ኤሊያስ አስታውቀዋል።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው፣ የዘንድሮውን የኦሊምፒክ ቀን ለማክበር የተደረገው ሰፊ ዕቅድ በወረርሽኙ ምክንያት ቢስተጓጎልም ከመቸውም ጊዜ በላይ በዚህ አጣብቂኝ ጊዜ ውስጥ በመሆን በዓሉን ሲከበር ለአትሌቶቻችን ፣ ለአሰልጣኞቻችን እና ለሙያተኞች ያለንንን ክብር የምንሰጥበት ብቻ ሳይሆን የኦሊምፒክ እንቅስቃሴ የተወለደበትን የምናስታውስበት ዕለት መሆኑን አስታውቀዋል።ዶክተር አሸብር አያይዘውም፣ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የቶኪዮ ኦሊምፒክ የተራዘመ ቢሆንም ይህን ድል ወደ መልካም አጋጣሚ መቀየር ከተቻለ ለሥራዎቻችን እና ለዝግጅቶቻችን በቂ ጊዜ ይፈጥርልናል ብለዋል ። ኮሚቴው በዓሉን ሲያከብርም 60 ለሚሆኑ የቀድሞ ስፖርተኞች ማለትም ለ41 ቬትራን አትሌቶች እና 19 ከተለያዩ ፌዴሬሽኖች ለተውጣጡ የቀድሞ ስፖርተኞች የዱቄት፣ መኮሮኒ፣ ዘይት እና ሳሙና ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም ጤናማ ስፖርት እና ስፖርተኛ ሊገኝ የሚችለው ከጤና አካባቢ መሆኑን በማመን የችግኝ ተከላ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።አዲስ ዘመን ሰኔ 18/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=35067
e1217978fa5b30f06dc81e154898bb93
a05aeb114450545a22415d9f42e50c22
ስፖርት – ሰብዓዊነትን ጋሻ ያደረገ ማኅበራዊ ክዋኔ
ስፖርት
ስፖርት የሰላም፣ ፍቅር፣ የአብ ሮነትና የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የወንድማማችነት ልዩ መገለጫ ነው። ስፖርት ዘር፣ ሃይማኖት፣ ፆታና ቀለምን አይለይም። በየት ኛውም ሁኔታ ውስጥ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አስኳል ሃሳብ ወዳጅነትና መተሳሰብ መሆኑ ይታወቃል። በታሪክ ገጾች እንደሰፈረውም በሰው ልጅ ታሪክ ባጋጠሙ በጎም ሆኑ መጥፎ ክስተቶች ስፖርት በአጋርነት ተሳትፏል። ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ሰላምንና አንድነትን የሚሰብኩ እንደመሆናቸው በማህበራዊ፣ ፖለቲ ካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በመግባት ሚናቸውን ሲወጡም ኖረዋል። ስፖርት ሰብዓዊነትን ያነገበ የልግስና ማዕድ መሆኑን የአለም ህዝብ እየፈተነ ባለው የኮሮና ወረርሽኝን ለመዋጋት ሲደረግና እየተደረገ ባለው ርብርብ ላይ በስፖርት ቤተሰቡ በኩል የታየው ተሳትፎ ትልቅ ማሳያ ይሆናል።የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የአለም ህዝብን እንደ ቅጠል ከማርገፍ በተጨማሪ በተለያዩ መስኮች ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል መቃወስን አስከትሏል።የስፖርት ኢንደስትሪው ደግሞ ዋነኛ ሠለባ ከሆኑ መስኮች በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል። የቫይረሱ ስጋትነት በዓለም አቀፉ የጤና ተቋም ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ፤ ውድድሮች ተቋርጠዋል፤ ተሰርዘዋል። ይህን ተከትሎ የአለምን ኢኮኖሚ በማንቀሳቀስ ረገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የስፖርት ኢንደስትሪውን በአጭር ጊዜ ለከፍተኛ የፋይናነስ ቀውስ ዳርጎታል።በአለም ስፖርት ላይ የተፈጠረው ከፍተኛ መቃወስ ግን የስፖርቱን ማኅበረሰብ የሰብዐዊነት ውሃ ልክ ከመሆን አላደናቀፈውም ነበር።የስፖርት ቤተሰብ በወረርሽኙ ጉዳት ከመቆዘም ይልቅ ,፤ የሰብዐዊነት ጋሻን በማንሳት አለምን ከጭንቅ ለማውጣት በሚደረገው ርብርብ ሰፊ ተሳትፎ ሲያደርግ ነበር፤እያደረገም ይገኛል። በስፖርቱ መስክ ዓለም አቀፍ ዝናን ካተረፉ ግለሰቦች እስከ ዓለም አቀፍ ተቋማት ድረስ ወረርሽኙን ለመመከት እየተደረገ ባለው ርብርብ ሲያደርጉ የነበረው ተሳትፎ ትልቅ ቦታ አጊንቷል።የስፖርቱ ዘርፍ ባለድርሻ የሚባሉት አካላት በተናጠልና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ድጋፍ ለሚሹ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ገንዘብ በማሰባሰብ ወረርሽኙን የመዋጋት ሂደቱን በፊት አውራሪነት ሲመሩ ታዝበናል።በተለያዩ ሀገራት ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ለመዋጋት በስፖርቱ ማኅበረሰብ ዘንድ የታየው ተሳትፎ በሀገራችንም ተመሳሳይ ሲሆን ታዝበናል። በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ይፋ ከተደረገበት ከወርሃ መጋቢት መጀመሪያ አንስቶ የስፖርቱ ማህበረሰብ ድርሻ ግዙፍ ነው። በስፖርት ዘርፍ የሚገኙ የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ የስፖርት ማህበራት፣ ተጫዋቾች፣ አትሌቶች፣ የእግር ኳስ ክለቦችና ተጫዋቾች ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ርብርብ ተሳትፎ ሲያደርጉ ነበር።በዘመነ ኮሮና የስፖርቱ ማኅበረሰብ ሰብዐዊነትን መሰረት ያደረገው እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ይገኛል። በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን አስተባባሪነት ሚያዝያ 17 ቀን 2012 ዓ.ም የተጀመረውን «ማዕድ ማጋራት» መርሃ ግብር ሶስተኛው ዙር ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ተጀምሯል።የስፖርቱ ማኅበረሰብ ህዝባዊነት የሚያረጋግጥ መሆኑ የተነገረለት ሶስተኛው ዙር ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ሲጀመር ፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደተናገሩት፤ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት የመደጋገፍ እና የመረዳዳት የቀደመ ባህላችንን የበለጠ እንዲጎለብት አድርጓል።የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገራችን ከገባ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የስፖርቱ መንግስታዊ እና ህዝባዊ አደረጃጀቶች፣ ታዋቂ አትሌቶች፣ የደጋፊ ማህበራት፣ በአጠቃላይ የስፖርት ቤተሰቡ ህብረተሰቡን በማንቃት እና ኢኮኖሚያዊ ጫናውን ለመቋቋም የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመጣት ላይ ያደረጉትን ተሳትፎ ጠቅሰዋል። የስፖርቱ ማኅበረሰብ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥልና የምገባ መርሃ ግብሩ መጀመር ለዚሁ ማሳያ ይሆናል ብለዋል። የጎዳና ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን በተወሰነ መልኩ ለማገዝ አንድ ወር የሚቆይ የምገባ መርሃ ግብሩ ይሄንኑ ሚና መሰረት ባደረገ መልኩ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ኤልያስ፤ በስታዲየም ዙሪያ መርሃ ግብሩ እንዲደረግ የተመረጠበትን ምክንያት መኖሩን አመልክተዋል። «በወቅታዊ የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ስርጭቱን ለመቆጣጠር ሲባል በተለይ ስታዲየም ዙሪያ የሚገኙ ባር እና ሬስቶራንቶች መዘጋታቸው እና በአካባቢው ያለው እንቅስቃሴ መቆሙ ይታወቃል። ሬስቶራንቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ ከሬስቶራንቶች ተመላሽ የሚሆኑ ምግቦችን ይጠቀሙ የነበሩ የጎዳና ተዳዳሪዎችም ሆነ በስታዲየም አካባቢ የተለያዩ ነገሮችን በመሸጥ ይተዳደሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል። በመሆኑም ጊዜው የከፋ ችግር ላጋጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እጃችን የምንዘረጋበት፤ የጋራ መከራችንን በመተጋገዝ የምናልፍበት መሆኑን በማመን እና ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ነው »ሲሉ አብራርተዋል። አቶ ኤልያስ በመጨረሻ የተጀመረው ተግባር የሚቋረጡ ሳይሆን በቀጣይም እነዚህ ወገኖቻችን በዘላቂነት ህይወታቸውን ሊመሩበት በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የስፖርት ቤተሰቡ በሙሉ አቅሙ የሚደግፍ መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የቢጂ አይ ኢትዮጵያ አመራሮች በጋራ በመሆን ባስተላለፉት መልዕክት ደግሞ፤ የምገባ መርሃ ግብሩ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።በስፖርት ኮሚሽን አስተባባሪነት የተጀመረው ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብሩ 3ኛ መጀመሩን በዘመነ ኮሮና የስፖርቱ ማኅበረሰብ ሰብዐዊ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ያመላክታል ተብሏል።ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም የተጀመረው ሶስተኛው ዙር «ማዕድ ማጋራት» መርሃ ግብሩ 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር ያህል እንደሚመገቡ ታውቋል።በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ከቢ. ጂ አይ ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን የመጀመሪያው ዙር ሚያዝያ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወራት የዘለቀ ነበር።የስፖርት ተቋማቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ያቀረቡትን «የማዕድ ማጋራት ብሄራዊ ጥሪን»ተከትሎ መርሃ ግብሩን የጀመሩት ሲሆን፤ 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር ያህል በመመገብ ሀሳቡን ተግብረውታል።ሁለተኛ ዙር ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል ተግባራዊ ተደርጎ በመጠናቀቁ ፤ሶስተኛው ዙር መርሃ ግብር ከሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 16 ቀን 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን በምገባ መርሃ ግብሩ ተጠቃሚ እንደሚደረጉ ታወቋል።በ3ኛው ዙር የምገባ ፕሮግራም የኢትዮጵያ መድን ድርጅት 600 ሺ ብር ድጋፍ በማድረግ የወገን አጋርነቱን ማሳየቱ ተነግሯል። የምገባ መርሃ ግብሩን ለሶስተኛው ዙር ማስቀጠል መቻሉ የስፖርቱ ማህበረሰብ በዘመነ ኮሮና ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የተጠናከረ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን አመላካች ሆኗል። የመርሃ ግብሩ ተግባራዊነት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ያቀረቡትን «የማዕድ ማጋራት ብሄራዊ ጥሪን» ወደ መሬት ከማውረድ በተጨማሪ፤ ስፖርት -ሰብዐዊነትን ጋሻ ያደረገ ማኅበራዊ ክዋኔ መሆኑን በተግባር እንዲረጋገጥ ያረጋገጠ መሆኑን ብዙዎች መስክረውለታል።አዲስ ዘመን ሰኔ 19/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=35130
96a8e8850782ebabc23f90d7451d46bd
a9d8021a3c08aa13dd1f9158c959625e
የአትሌቲክሱ ዓለም ከወራት በኋላ የሚጠብቀው የዓለም ክብረወሰን
ስፖርት
የዓለም ታላላቅ ስፖርት መድረኮች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ምክንያት ለበርካታ ወራት ከቆሙበት ለመቀጠል ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ለመመልከት ተችሏል። የእግር ኳሱ ዓለም ታላላቅ ሊጎች በዝግ ስቴድየምም ቢሆን ጨዋታዎችን እያስቀጠሉ ካንቀላፉበት እየነቁ ይገኛሉ። በዚሁ ወረርሽኝ ሳቢያ ክፉኛ የተጎዳው የዓለም አትሌቲክስ እንቅስቃሴም ከጥቂት ወራት በኋላ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለመመለስ ከወዲሁ እንቅስቃሴ መጀመሩ ለዓለማችን አትሌቶች መልካም ዜና ሆኗል። በተለይም የዓለማችን ኮከብ አትሌቶች በጉጉት የሚጠብቁት ዓመታዊው የዳይመንድ ሊግ ውድድር እንደሚመለስ መገለፁን ተከትሎ ለወራት ከውድድር ርቀው ለተቀመጡት አትሌቶች የምሥራች መሆኑ አይቀርም። በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የዓለም አትሌቲክስ ዓመታዊ መርሃግብሮች በተያዘላቸው ጊዜ ሳይካሄዱ በመቅረታቸው ተዘበራርቀዋል። የዓለም አትሌቲክስ ይህንን ለመካስም በጊዜያዊነትም ቢሆን እንደ ዳይመንድ ሊግ ያሉ ውድድሮች መርሃግብርን ለመከለስ ተገዷል። በብራሰልስ የሚካሄደውም ውድድር ከተከለሱት መርሃግብሮች መካከል የሚጠቀስ ነው። ዳይመንድ ሊጉ ወደ ውድድር ሲመለስ በመጪው የፈረንጆች መስከረም ወር መጀመሪያ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው የብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ ከወዲሁ ትኩረት አግኝቷል። እንግሊዛዊው የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮናዎች ጥምር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ አትሌት ሞሐመድ ፋራህ ከ2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መም ውድድሮች ተመልሶ በብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ ተፎካካሪ እንደሚሆን መናገሩን ተከትሎ ውድድሩ ትኩረት ማግኘት ችሏል። የሰላሳ ሰባት ዓመቱ ፋራህ ወደ ውድድር ከመመለሱ በተጨማሪ በ21 ነጥብ 285 ኪሎ ሜትር ፉክክሩን ከአንድ ሰዓት በታች ለማጠናቀቅና አዲስ የዓለም ክብረወሰን ለማሻሻል መዘጋጀቱን ተከትሎ የብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ ከወዲሁ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጓል። የርቀቱ ክብረወሰን በጀግናው አትሌት ሃይሌ ገብረሥላሴ የተያዘ ሲሆን ከአስራ ሦስት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ 2007 ኦስትራቫ ላይ ማስመዝገቡ ይታወሳል። በብራሰልሱ ውድድር የአውሮፓ የአስር ሺህ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት በሽር አብዲ ከፋራህ ጋር እንደሚፎካከር የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን የርቀቱ ፈርጦችም በቅርቡ ውድድሩን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል። ‹‹ከልምምድ አጋሬ በሽር አብዲ ጋር ውድድሩን ከአንድ ሰዓት በታች በማጠናቀቅ የዓለም ክብረወሰን ለማስመዝገብ እየተዘጋጀን ነው፣ ይህ ለእኔ ትልቅ አጋጣሚ ነው፣ በብራሰልስ ከዚህ ቀደም ባደረኳቸው ውድድሮች ጥሩ ትዝታዎች አሉኝ፣ ብራሰልስ ላይ ፈታኝ ሰዓት መሮጥ ይቻላል፣ ሁሉም ነገር ቀላል ነው›› በማለት ፋራህ ለመገናኛ ብዙሃን አስተያየቱን ሰጥቷል። በተመሳሳይ በሴቶች መካከል በሚካሄደው ውድድር ግን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተፎካካሪ ከመሆን ባለፈ አዲስ የዓለም ክብረወሰን ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን የውድድሩ አዘጋጆች ገልፀዋል። በዚህም አትሌት አባብል የሻነህ እና ብርሃኔ ዲባባ ተጠባቂ ሆነዋል። 18 ነጥብ 517 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ውድድር የዓለም ክብረወሰን የተመዘገበበት ጊዜ ከአስራ ሁለት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ 2008 ላይ ሲሆን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድሬ ቱኔ የክብረወሰኑ ባለቤት መሆኗ አይዘነጋም። በዚህ የውድድር ዓመት የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰንን በ1፡04፡31 ሰዓት መስበር የቻለችው አባብል የሻነህ ለአስራ ሁለት ዓመታት ያልተደፈረውን የድሬ ቱኔን ክብረወሰን እንደምታሻሽል ግምት የተሰጣት ሲሆን በማራቶን 2፡18፡35 የሆነ የራሷ ምርጥ ሰዓት ያላት ብርሃኔ ዲባባም ብራሰልስ ላይ ለክብረወሰን ተጠባቂ ሆናለች።አዲስ ዘመን ሰኔ 20/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=35203
8f259b6d2721605cf564ddcb7c77428c
18d5a4aa58f61c6bb5aa0567f93afbff
የካፍ አካዳሚ ወደ አገልግሎት የመመለስ ተስፋ
ስፖርት
 የኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ለመቀጨጩ በርካታ ምክንያቶች ሊዘረዘሩ ይችላሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱና ትልቁ ምክንያት ሆኖ በተደጋጋሚ የሚነሳው ታዳጊዎችን ለማሰልጠን የሚያበቃ አካዳሚ አለመኖሩ ነው። በእርግጥ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በአገር አቀፍ ደረጃ በተገነቡ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላትና አካዳሚዎች የተለያዩ ስልጠናዎች ደረጃቸውን ጠብቀው በተገነቡ የማሰልጠኛ ማዕከላት መሰጠት ጀምረዋል። ይሁን እንጂ በተገነቡት ዘመናዊ የማሰልጠኛ ማዕከላት እግር ኳሱን ከቁልቁለት ጉዞ ታድጎ አንድ ርምጃ ወደ ፊት የሚያራምድ ፍሬ ማፍራት እንዳልተቻለ ለማንም የተሸሸገ እንዳልሆነ መገንዘብ ይቻላል። የተገነቡትን ዘመናዊ የማሰልጠኛ ማዕከላት ፍሬ እንዲያፈሩ በአግባቡ እንዳልተሰራባቸው አንዱ ማሳያ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) የተገነባውና ከአስር ዓመት በላይ አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየው የካፍ እግር ኳስ አካዳሚ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ አያት አካባቢ የሚገኘው አካዳሚው ግንባታው የተጀመረው በ1997 ዓ.ም ሲሆን፤ በሶስት ዓመት ለማጠናቀቅ ነበር የታቀደው። ሆኖም ግንባታው በመዘግየቱና ከተጠናቀቀም በኋላ አገልግሎት መስጠት አለመጀመሩ በርካታ መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰበትን መሰረተ ልማት አገልግሎት ሳይሰጥ እንዲባክንና ጉዳት እንዲደርስበት ሆኗል። የስፖርት ቤተሰቡ በዚህ የተነሳ ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርብ ቆይቷል። ይህንንም ተከትሎ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተካሄደ እንቅስቃሴ አካዳሚው ስራ አስኪያጅ ተመድቦለትና ለብልሽት ለተዳረጉ ስራዎች እድሳት ተደርጎባቸው ተስፋ ማሳየት ጀምረዋል። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻም የስፖርት አመራሮች እንዲሁም የስፖርት ማህበራት ኃላፊዎች በቦታው ተገኝተው ጉብኝትና የችግኝ መትከል መርሃ ግብር አካሂደዋል። በወቅቱም አካዳሚው ስላለበትና ቀጣይ እጣ ፈንታው ምን እንደሚሆን ማብራሪያ ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ፤ የልህቀት አካዳሚው 15 ዓመት እንደሆነው በማስታወስ፣ ካፍ በአህጉሪቷ የእግር ኳስ ልህቀት አካዳሚውን ለመገንባት ሲነሳ የመረጣቸው አገራት ካሜሩን፣ ሴኔጋል እና ኢትዮጵያ መሆናቸውን ይናገራሉ። በወቅቱ የካፍ ፕሬዚዳንት የነበሩት ኢሳ ሃያቱ ካሜሮናዊ በመሆናቸው በአገራቸው የሚገነባውን ተመሳሳይ አካዳሚ ግንባታ ወደራሳቸው በማድላት በዲዛይኑ መሰረት በጥሩ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ማድረጋቸውን አቶ ኢሳያስ ያስረዳሉ። በዚህ ወቅትም ሁሉም መሰረተ ልማት የተሟላለትና ስፖርተኞችን እያፈራ እንደሚገኝ ይናገራሉ። በሴኔጋል የተገነባው ተመሳሳይ አካዳሚም ቢሆን ከዋና ከተማዋ ዳካር 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የአገሪቱ መንግስት ገንዘብ በመመደብና በማደስ ብሄራዊ ቡድናቸውን ያሳርፉበታል። የኢትዮጵያው አካዳሚ እስካሁንም ድረስ ባለበት የቆየ ሲሆን ከወራት በፊት ካፍ የባለቤትነት መብት እንዲሰጥ ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ ጽፎ ነበር። በዚህም መሰረት የሰነድ ርክክቡ ተጠናቆ የውልና ማስረጃ ስራዎች በመከናወን ላይ እያለ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመከሰቱ ሊቋረጥ ችሏል። ወደፊት ከኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበርና ሂደቱን በማጠናቀቅ ህጋዊ ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይህን እያደረገ በነበረበት ወቅትም ጎን ለጎን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲያከናውን እንደነበረ ፕሬዚዳንቱ አቶ ኢሳያስ ያስታውሳሉ። የጀርመኑ ክለብ ባየርሙኒክ የአካዳሚውን ሜዳ እንዲያሰራ፣ ጂአይዜድ ደግሞ ሁለት የተፈጥሮና አንድ የሰው ስራሽ ሜዳዎችን ለመስራት ቃል መግባታቸውን ጠቁመዋል። በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድኖችን ለተለያዩ ጨዋታዎች ለማዘጋጀት በሆቴሎች እንዲያርፉ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ እንደሚደረግ ይታወቃል። ከዚህ በኋላ ግን በዚህ አካዳሚ በማሳረፍ ዝግጅታቸውን እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚቻል አቶ ኢሳያስ ተናግረዋል። ከእግር ኳስ ባሻገር ያሉ ስፖርቶችም ብሄራዊ ቡድናቸውን ማሳረፍ የሚችሉበት አጋጣሚ እንዳለ ተገልጿል። ከዚህ ባሻገር በኢትዮጵያ አርፈው ወደ ሌሎች አገራት የሚጓዙ ብሄራዊ ቡድኖች በአካዳሚው እንዲያርፉ በማድረግ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንደሚቻልም ጠቁመዋል። ይህንን ለማድረግ ግን የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ያስፈልጋል። ይኸውም የልምምድ ሜዳ እና የጉድጓድ ውሃ መሆኑን ለመንግስት ጥሪ ተደርጓል። ይህ ሲሆንም የፌዴሬሽኑን ጽህፈት ቤት አካዳሚው ወዳለበት ስፍራ ለማዘዋወር እንደሚያመች አቶ ኢሳያስ አብራርተዋል። የቀድሞውም ሆነ የአሁኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት የሚገኝበት አካባቢ መሐል ከተማ እንደመሆኑ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ለማድረግ አይታሰብም። አፍሪካን ጨምሮ በሌሎች አገራት ስፖርቱ ሙሉ በሙሉ የሚንቀሳቀሰው በአንድ አካባቢ በተገነባ ዘመናዊ የስፖርት ማዕከል ነው። ይህ አካዳሚ እያለ ግን አገልግሎት መስጠት ሳይጀምር የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበት ነበር። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ባደረገው ጥረትና በመደበው 2 ሚሊዮን ብር ግን በድጋሚ ሊታደስችሏል። በቀጣይም መንግስታዊ አካላት ለትውልድ ሊተላለፍ የሚችለውን አካዳሚ ሊጠብቁ እንደሚገባ አቶ ኢሳያስ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው፤ የአካዳሚው ግንባታ የተጀመረው እርሳቸው የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ እያሉ መሆኑን አስታውሰው፣ ለዓመታት በዚህ ሁኔታ ውስጥ አልፎ አሁን እድሳት ሲደረግለትም በስፖርቱ ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። በመሆኑም ይህ ለእግር ኳስ እድገት እንዲሁም ስፖርተኞችን ለሚያፈራ አካዳሚ ኮሚቴው የሚጠበቅበትን የሚወጣ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሩ ዱቤ ጂሎ፤ ከወራት በፊት አካዳሚውን በጎበኙበት ወቅት አሳዛኝ ሁኔታ መመልከታቸውን ያስታውሳሉ። በወቅቱም ከፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ጋር በመሆን ወደ ስራ መግባት እንደሚኖርበት ተነጋግረዋል። በተከናወነው ስራም አሁን የተሻለ ሁኔታ ላይ ሊገኝ ችሏል። ስለ ስፖርት ሲታሰብ ዋናው ጉዳይ የማዘውተሪያ ስፍራዎች በመሆናቸው ኃላፊነት ያለበት ኮሚሽኑ አካዳሚው ስልጠና እንዲጀምር በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። አካዳሚው እንዲገነባ ያደረጉ አካላት ምስጋና የሚገባቸው ቢሆንም ለ15 ዓመታት ያለ ስራ መቀመጡ ግን ጥፋት ነው ሲሉም አቶ ዱቤ ተናግረዋል። በመሆኑም ይህንን ለማረም በቁርጠኝነት መነሳታቸውን አረጋግጠዋል። አካዳሚውን ለማፍረስ ሙከራ ያደረጉትንም የሚቃወሙና ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑንም ጠቁመዋል። በእርሳቸው ሃሳብ ላይ ያከሉት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር በበኩላቸው፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላትን መንከባከብ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል። ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መሬት ከመስጠት ባሻገር በቀጣይነት አብሮ መስራት አስፈላጊ ነው። የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና የስልጠና ማዕከላት ከተልእኳቸው አንጻር በሙሉ ኃይላቸው እየሰሩ አይደለም። በሌላ መልኩ በየአካባቢው የተገነቡት ማዕከላት ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አለባቸው። በመሆኑም በየአካባቢው ያሉ የስልጠና ማዕከላትና አካዳሚዎች ተገቢውን ግልጋሎት እንዲሰጡ ማድረግ ተገቢ ነው። በተለያዩ አካባቢዎች ውድ የሆነው መሬት ለስፖርት እንዲውል ቢሰጥም እንደ ካፍ አካዳሚ ሁሉ ለዓመታት ታጥረው መቀመጥ የለበትም። መንግስት፣ ህብረተሰብ እንዲሁም የስፖርት ቤተሰቡም በስፖርት ስም የተቀመጡ መሬቶችንና ግንባታዎችን ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል። የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው፤ አካዳሚው የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ብቻም ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት መሆኑን ጠቁመዋል። የአካባቢውን ማህበረሰብም ተጠቃሚ በማድረግ ገቢ ማስገኘት የሚቻልም ይሆናል። እስካሁን አካዳሚውን አለመጠቀም ‹‹ምን ዓይነት እንደሆን ያሳያል›› ያሉት ሚኒስትሯ፤ መንግስት ቦታውን ሰጥቶ መስራት ያለበት አካል በሚገባው ቦታ አለመገኘቱ አሳዛኝ መሆኑን ይገልጻሉ። ቦታውን ከተረሳበትና ከተጎዳበት በማስተካከል አሁን ያለበት ላደረሱ አካላትም ምስጋና ይገባል።አዲስ ዘመን ሰኔ 22/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=35323
d720d09f1dd8bf4ac343b4b0233a5383
bee57edfd11410b782271f076cd56864
‹‹ለሱዳን ትንኮሳ ቸኩለን ምላሽ መስጠት አይገባንም›› -ዶ/ር ኢንጅነር ጥላሁን ኤርዱኖ የታሪክና የጂኦግራፊ መምህር የነበሩና በአሁኑ ጊዜ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የካርታ ምህንድስና መምህር
ሀገር አቀፍ ዜና
ማህሌት አብዱል አዲስ አበባ፡- ሱዳን በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ላደረገችው የመሬት ወረራ ትንኮሳ ፈጥኖ የኃይል ምላሽ መሥጠት እንደማይገባ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ኢንጅነር ጥላሁን ኤርዱኖ አስታወቁ፡፡ዶ/ር ኢንጅነር ጥላሁን ኤርዱኖ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ለፈፀመው የመሬት ወረራ ቸኩሎ የኃይል ምላሽ መሥጠት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። በተለይም ውስጣዊውን ችግር በተሟላ ሁኔታ መፍታት ባልተቻለበት በዚህ ወቅት ወደ ኃይል ምላሹ መግባት አገሪቱን ያላሰበችው አደጋ ውስጥ ሊጥላት ይችላል፡፡እንደእርሳቸው ገለፃ፤ ሱዳንም ሆነች ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያሉት ትንኮሳ ዋነኛ አላማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል ነው፡፡ በተለይም ሱዳን የቅኝ ግዛት ውልን በማጣቀስ ያደረገችው ትንኮሳ ግድቡ የሚገነባበትን አካባቢ ሰላም በማወክ ውሃውን ከግብፅ ጋር ብቻ የመጠቀም ፍላጎታቸውን ለማስቀጠል ከመሻት ነው፡፡ ከትንኮሳ በስተጀርባም የግብፅ ወታደራዊ መንግሥት እጅ ያለበትና ከፍተኛ ድጋፍ የሚደረግለት ነው፡፡ ‹‹የሱዳን ዋነኛ ፍላጎት ቸኩለን እንድንገጥማት ነው›› ያሉት ዶክተር ጥላሁን ይህንን ማድረጉ ደግሞ አገሪቱ ካለችበት ፖለቲካዊ ችግር ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል ሥጋታቸውን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የትንኮሳውን ዋነኛ አላማ በመረዳት ትክክለኛውን ጊዜ መጠበቅ እንደሚገባው አመልክተዋል፡፡መላው ኢትዮጵያውያንም እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለአገራቸው ሰላም በህብረት መቆም እንደሚገባቸው የተናገሩት ዶክተር ጥላሁን ለዚህ ደግሞ በብሔርና በጎሳ ለመለያየት የሚደረገውን የጠላት ኃይሎች ጥረት እንዳይሰምር በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ዶክተር ጥላሁን እንደሚሉት ጠላቶቻችን ሌላ በጣም ጽንፈኛ የሆነ ጠላት ይፈጥሩልናል እንጂ በፍፁም አይተኙልንም፡፡ ይሄ በግርግር መሬት እናስመልሳለን የሚል ቢሆንም ዋነኛ አላማው ግን ኢትዮጵያን ሰላም በማሳጣት የህዳሴ ግድባችንን ግንባታ ማስተጓጎል ነው፡፡ ሱዳን ሁልጊዜ መሆን የምትፈልገው ከአሸነፈው ጋር ነው፡፡ ኢትዮጵያ የፖለቲካ የበላይነቱን ስትይዝ ኢትዮጵያ ያለችውን ትቀበላለች፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር ሲፈጠር ከግብጽ ጋር ነው የምትጎዳን ብለዋል ዶክተር ጥላሁን፡፡ እንደ ዶክተር ኢንጂነር ጥላሁን ገለጻ፤ የግብፅና የሱዳን መንግሥታት ወታደራዊ ናቸው። የሁለቱም አመራሮች ወደ ስልጣን የመጡት በመፈንቅለ መንግሥት ነው፡፡ ወታደራዊ መንግስቱ ኢኮኖሚውን ይዞ ነው ያለው፡፡ ከጎረቤት ጋር በሰላም መኖር አይችሉም፡፡ ሲቪል መንግሥት እንዲኖር አይፈለግም፡፡ ስለዚህ እነዚህ አገሮች ኢትዮጵያ አንድነቷን ካፀናች በምንም ተዓምር አያሸንፏትም፡፡ ግን እጃቸው ረጅም በመሆኑ ለሰላማችን መደፍረስ የሚመጡበት መንገድ አይታወቅም፡፡የውጭ ጠላቶቻችንን ማሸነፍ የምንችልበትና ያለን ብቸኛ መፍትሔ የኢትዮጵያን ሕዝብ አብሮነት መመለስ ነው ያሉት ዶክተር ጥላሁን፤ በቋንቋም ሆነ በብሔር መከፋፈላችንን ማስቀረት ይገባናል ብለዋል፡፡ ምክንያቱም ቋንቋ ከመግባቢያነት ያለፈ ጥቅም ኖሮት አያውቅም ብለዋል፡፡ሁለቱ አገራት በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመሰረተ ፖለቲካ አካሂደው አያውቁም፡፡ ስለዚህ የውስጥ የፖለቲካ ችግር ሲፈጠር የሕዝባቸውን ቀልብ ለመስረቅ ሲሉ ችግራቸውን ለኢትዮጵያ ይሰጣሉ። ሁሉንም ነገር ከአባይ ጋር ያያዙታል። በሱዳን በኩልም በዳቦም ሆነ በሌላ መልኩ የሚነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማስረሳት ሲሉ ተመሳሳይ ድርጊት ይፈፅማሉ ብለዋል ዶክተር ኢንጂነር ጥላሁን፡፡ይሁንና አሁን ከያዙት መሬት በተጨማሪ ገፍተው እንዳይመጡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በተጠንቀቅ ሊቆምና ዳር ድንበሩን ማስጠበቅ እንደሚገባው ዶክተር ኢንጂነር ጥላሁን አስገንዝበዋል፡፡ በተጨማሪም መንግሥት ግድቡ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ክልል አስተማማኝ ሰላም በመፍጠር የወራሪዎቹ አገር የማተራመስ አጀንዳ ከግቡ እንዳይደርስ ሚናውን እንዲወጣ አሳስበዋል።ከዶክተር ኢንጂነር ጥላሁን ኤርዱኖ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለምልለስ ገጽ 6 ላይ ይከታተሉ።
https://www.press.et/Ama/?p=39157
11f669b5184f7b1335d2efcc647e4a5f
2a1195b85117f85493b54888b566e53e
በድምጽ መስጫ ሳጥን የገባው ቀለበት
መዝናኛ
በሀገሮች መሪዎችን ለመምረጥ ምርጫ እንደሚካሄድ ይታወቃል። ለእዚህም ዜጎች ድምጻቸውን ይሰጣሉ ፤ ድምጽ በሚሰጥበት ስፍራ ምንም አይነት ሁከት ሊፈጠር አይገባም። በእዚህ አካባቢ ድምጽ በሚሰጡበት ወቅት ወርቅ፣ ገንዘብ ፣ወዘተ ቢጠፋ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ መጮህ አይቻልም፤ ሊያስጠይቅ ይችላል። ወርቅን ያህል ጠፍቶ ታዲያ እንዴት ዝም ይባላል ትሉ ይሆናል። ያሎት አማራጭ ተረጋግቶ በሰከነ መንፈስ ችግሩን ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቆ ድምፁ እስኪጠናቀቅ በትእግስት መጠበቅ ነው።በፈረንጆቹ ባለፈው ታኅሳስ መባቻ በእንግሊዝ ትራፎርድ ምክር ቤት ድምጽ ለመስጠት የተገኘች አንዲት እንግሊዛዊት ከወላጅ እናቷ በስጦታ የተበረከተላትን የወርቅ የጣት ቀለበት ድምጽ ሰጥታ እንደወጣች ከጣቷ ላይ ታጣዋለች። ብዙ ስታፈላልግም ትቆያለች። የቀለበቱ መጥፋት በእጅጉ ያሳስባታል። ለእናቷ ምን ብላ እንደምትነግራትም ግራ ይገባታል። ቻርሎቴ የተባለችው ይህች እንግሊዛዊት ጓደኛዋ በአንድ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ በድምጽ መስጫ ሳጥን ውስጥ ቀለበት ስለጣለ ሰው መረጃ መልቀቁን እስከ ገለጸላት ድረስም የት እንደጣለችውም ማስታወስ አልቻለችም። ቻርሎቴ ማንችስተር አቅራቢያ በሚገኘው በክሎቬራል መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ድምፅ እስከሰጠችበት ሰአት ድረስ ቀለበቱ ጣቷ ላይ አንደነበር ታስታውሳለች። ጓደኛዋ መረጃውን እስከላከላት ድረስም ቀለበቱ በድምፅ መስጫ ሳጥን ውስጥ ስለመግባቱም አላወቀችም።ነገሮችን መለስ ብላ ስታሰላስል ድምጽ በሰጠችበት ወቅት ሳንቲም የወደቀባት መስሏት እንደነበር አስታወሰች። ጓደኛዋ የሰጣትን መረጃ መሰረት በማድረግም ድምጽ ወደ ሰጠችበት ትራፎልድ ምክር ቤት ትደውላለች፤ ቀለበት እንደጠፋባትም ትገልጻለች። እነሱም በከተማው መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲቀመጥ ማድረጋቸውን ይገልጹላታል። ቀለበቱ በጠቋሚ ጣቴ ላይ ነበር ፤ ድምፄን ሰጥቼ እጄን ጎትቼ ሳወጣ ሳጥን ውስጥ ወድቆ ሊሆን ይችላል ስትል ትገልጻለች። ቀለበቱ አመልካች ጣቴ ላይ ነበር፤ ጣቴ ላይ ላላ ያለም ነበር፤ ለእዚህም ነው ድምጽ ስሰጥ በቀላሉ ከጣቴ ወልቆ ወደ ድምጽ መስጫ ኮሮጆ ውስጥ የገባው ያለችው ቻርሎቴ ፣በመገኘቱ በጣም መደሰቷን ተናግራለች። ‹‹የእናቴን ፊት እንዴት አያለሁ ብዩ ሳስብ ነበር፤ ለወደፊቱ እንዳይጠፋብኝ በደንብ ተጠንቅቄ እይዛለሁ። ምክር ቤቱ ላደረገልኝ ትብብር አመሰግናለሁ። “ስትል ገልጻለች።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21 ቀን 2012 ዓ.ምኃይለማርያም ወንድሙ
https://www.press.et/Ama/?p=24956
af521b829f54d23a7afb5934f6e67ad3
133007cdfae8837cce0e4f372ca9c95d
የአሰፋ ሳይንቲስት ውብ ወጎች
መዝናኛ
 ክፍል ሁለትባለፈው ሳምንት ክፍል አንድ ዝግጅታችን አሰፋ ሳይንቲስትን አስመልክቶ ጥቂት ወጎች ነበሩን። በጨለማው ዘመን የበሩት ፕሮፌሰር አሰፋ በፈረንሳይ ሀገር ኬሚስትሪ ያጠኑ ተመራማሪ ኢትዮጵያዊ ምሁር ነበሩ። እውቀቱ ገፋ ገፋ፤ ከመር ከመር ያደርጋቸው ነበር። ግን እኮ የቤተክህነቱንም ትምህርት ከግእዝ እስከ አራራይ የአማርኛውን ሰምና ወርቅ ጭምር ፈትለው ይገምዱት ነበር። ይሄ ምርምር የሚጠላውን ለማወቅ ጉጉት የሌለውን ደግሞ ‹‹ደናቁርት፤ ደነዝ፤ የሰው አጋሰስ፤ ሰው ነኝ›› ብሎ እኔ አሰፋ ሳንቲስት ሲሉ ካካታና ሳቅ ይበዛል። አሰፋ በተማሪው ዘንድ ምን አሉ? ምን ተናገሩ? እየተባለ እንደ አለቃ ገብረሃናም ፍቅር ዘርፈዋል፤ ይወደዳሉ። ተማሪ መሳቅ፤ መሳቅ፤ አብዝቶ መሳቅ መተረብ በተፈጥሮው ይወዳል። ሲጫወቱ አፍ ያስከድናሉ። በብዛት ወጋቸው ሕልማቸው ሃሳባቸው ሁሉ ሳይንስና ሳይንስ ብቻ ላይ ያተኩራል። ፈረንሳይ ከተማሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጋር ወጋቸው ብርቱ ነው። ለነገሩ ጃንሆይስ አሳምረው ፈረንሳይኛ ይናገሩ አልነበር። ሳባ— ዊ– ሳባ፤ ሲ– መርሲ–መርሲ– ቦኩ እንዲሉ። አሰፋ ሳይንቲስት ነገር ካልመሰላቸው ነቋሪም ነበሩ። ሸንቆጥ፤ ላጥ አድርገው ደርሰው ያጥረገርጋሉ። ሲያሻቸው በቅኔ ይደበድባሉ። በውስጠ ወይራ አማርኛ አያድርስ ነው። ድንዙዝ እንዲሉ መሪጌታ ማን ይፈታዋል ብለህ ነው ምርቃት ይሁን እርግማን ከአዋቂዎች በቀር። ብትሰደብም መሳቅ ነው። አሰፋ ሳይንቲስት የሚያስተምሩበት ስንቱን ታላላቅ ኢትዮጵያዊ ያፈራው የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የዘመኑ ካምብሪጅ ነበር። ኮከብ፤ ቀንዲል አውራ።ታላላቅ የጦር መሪዎች ጀነራሎች፤ ፓይለቶች፤ ማሪኖች፤ ሚኒስትሮች፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራን፤ የሕክምናና ሌሎችም ዶክተሮች ወዘተ ተምረው ተመርቀው የወጡበት በዘመኑ እጅግ ታዋቂ ስሙ የገነነ የተጠራ ትምህርት ቤት ነበር፤ ተፈሪ መኮንን። አሰፋ ሳይንቲስት ቁመተ አጭር፤ ቁንን እንደነበሩ የሚያውቁአቸው ይናገራሉ። በዚያ ዘመን ስለሳይንስና ምርምር የሚያውቁ ሰዎች አልነበሩም። ግፋ ቢል የሰይጣን ስራ ነው የሚባልበት ነበር። አጤ ምኒሊክ ከውጭ ፊልም አስመጥተው በግድግዳ ላይ እንዲታይ ሲያስደርጉ የሰዎቹን ምስል በስክሪኑ ላይ ያዩት አያቶቻችን እያማተቡ ‹‹በስመ አብ–ወ– ወልድ ወ–መንፈስ ቅዱስ እነዚህ ሰይጣኖች ናቸው›› በማለታቸው ነበር ፊልም ቤቱ ሰይጣን ቤት የተባለው።መኪናም ስልክም ሲገባ እንዲሁ የሰይጣን ስራ ነው የሚል ተቃውሞው የበረታ ነበር። በዚያም ዘመን ነው አሰፋ ሳይንቲስት የኖሩት፤ የሰሩት፤ ምርምር አድርገው ሮኬት ለማስወንጨፍ የሞከሩት። በራሳቸው ምርምር በሀገር በቀል እቃዎች በመጠቀም ሮኬት ወደ ጨረቃ ለማስወንጨፍ የሞከሩ የመጀመሪያው ኢትዮጰያዊ። ስራቸው የሚታወቀው የሚደመመው ግሩም እምግሩማን አሰፋ ሳይንቲስት የተባለላቸው የተጨበጨበላቸው ሰው። አሰፋ ሳይንቲስት በኢትዮጵያ የጠፈር ምርምር ታሪክ ውስጥ አንድ ቀን ብርሃን ሆነው ይገለጣሉ። ታሪካቸው አምሮ ይጻፋል። ምርምራቸው ዶክመንቶቻቸው ቢፈተሹ አንድ ቦታ ሊያደርሱ ይችላሉ። ‹‹አሴ፤ አሰፋ ሳይንቲስት›› እያሉ ነው ራሳቸውን የሚጠሩት። ሌሎችም እንዲሁ። ለዛ ያለው ወግ አዋቂ ስለነበሩ በእርሳቸው ንግግር ተማሪው ይመሰጣል፤ ይደመማል፤ ያውካካል። ሲያሻቸውም ይጨምሩበታል። አለማድነቅ አይቻልም። ግሩም ድንቅ ።አንድ ጊዜ አሰፋ ሳይንቲስት ክፍል ውስጥ ገብተው ማታ ሕልም ማየታቸውን ይናገራሉ። ተማሪው እንደተለመደው አፉን ከፍቶ ያዳምጣል። ተኝተው ከአልጋቸው ግርጌ ታላቁና ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የተንቆጠቀጠ ወርቅ ልብሱን ለብሶ ሰይፉን እንደያዘ ቆሞ ‹‹አሰፋ ሳይንቲስት ሲለኝ በመደንገጥ ተርበትብቼ አቤት ብዬ ተነሳሁ። እንካ ይሄ የአቶሚክ ቦምብ መስሪያ ፎርሙላ ቀመር ነው ተጠቀምበት አለኝ። በድንጋጤ ተውጬ እንደተቀበልኩ ተሰወረብኝ።›› እሺ አለ ተሜ አፉን ክፍቶ። ‹‹ይሄን ሚስጢር ለመከላከያ ሚኒስትርና የፈረንሳይ ተማሪ (ፍራንኮ ፎን) ለሆነው ለጀነራል አቢይ ወዳጄ ስለሆነ ሄጄ ነገርኩትና እባክህ ጃንሆይ ጋር እንድቀርብ አድርገኝ አልኩት›› አሉ።ጀነራል አቢይ ቀጠሮ አስይዞ አሰፋ ሳይንቲስትን ንጉሱ ዘንድ ይወስዷቸዋል። እጅ ይነሳሉ። ጉዳይህ ምንድነው አሰፋ ሳንቲስት ተብለው ሲጠየቁ በተለመደው ሥርዓት ለጥ ብለው ንጉሰ ነገስቱን እጅ ይነሳሉ። ቀጥለው በሕልማቸው የተነገራቸውን የቦምብ ፎርሙላ ቀመር ይናገራሉ። ‹‹እናሳ›› ሲባሉ ጃንሆይ እንድሰራ ይፈቀድልኝ ይላሉ። አሰፋ ሳይንቲስት አንድ አይናቸው በፈንጣጣ ሕመም በልጅነታቸው ጠፍቷል። በዚህም ትልቅ የአይን መነጽር ያደርጋሉ። ይሄን ንጉሱ ያውቃሉ። ንጉሱ በዙፋናቸው ሆነው ካዳመጡ በኋላ ለአሰፋ ሳይንቲስት መልስ ይሰጣሉ። ‹‹እሺ ልጃችን አሰፋ ሳይንቲስት አንተን ይህን ስራ ብሎ መፍቀድ ለኢትዮጵያ አንድ አይን ነህ፤ አንድ አይናችንን ማጥፋት ነው የሚሆንብን›› የሚል መልስ ሰጡ። አሴ በመጡበት ተመለሱ። ባለቅኔዋ ሀገሬ እንዴት ነሽ። ተማሪው ታሪኩን ሲጨርሱ ቅኔው ስለገባው በክፍሉ ከፍተኛ ሳቅ እየሳቀ አውካካ። አሰፋ ሳይንቲስት በክፍል ሲያስተምሩ ተማሪው የሚናገሩትን ለመስማት በናፍቆትና በጉጉት ይጠብቃል። ቀጠሉ ደግሞ በሌላ ቀን ተማሪዎች ክፍል ገብተው። ‹‹ሰማችሁ ተማሪዎች›› አሉ አሰፋ ሳይንቲስት ። ‹‹ከተማርኩበት ፈረንሳይ ሀገር ፓሪስ ከተማ በሚደረገው የሳይንቲስቶች ጉባኤ ላይ እንድገኝ ደብዳቤ ደርሶኛል›› ካሉ በኋላ ደብዳቤውን ለተማሪዎች እንዲህ ብለው አነበቡ። ‹‹ለተከበርከው ውድ ወዳጃችን ወንድማችን አሰፋ ሳይንቲስት፤ እንደምን ከርመሀል፤ በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የዓለም ሳይንቲስቶች ስብሰባ ስለሚካሄድ በዚሁ ስብሰባ ላይ እንድትገኝ በክብር ተጋብዘሃል። አክባሪህ ራስቤልድ።›› ብለው የፈራሚውን ታዋቂ የፈረንሳይ ሳይንቲስት ስም ያነባሉ። ተማሪው ፍንድት ብሎ በሳቅ ያውካካል። ያ ፈረንሳዊ ሳይንቲስት የሞተው ከ100 ዓመት በፊት ነበር። በዚያ ዘመን በሕይወት የለማ። አሴን አለማድነቅ አይቻልም። አሰፋ ሳይንቲስት ከትምህርት ቤት መልስ ሁል ጊዜ ማታ ማታ ሲዝናኑ የሚያመሹት ከጥንት ጀምሮ ታዋቂ በሆነው የአራት ኪሎው ቱሪስት ሆቴል ነበር። ተመርቀው ስራ የያዙ ተማሪዎቻቸው በብዛት ቱሪስት ሆቴል ነበር የሚርመሰመሱት። አሰፋ ሳይንቲስት ሲመጡ ወጉ ጨዋታው ይደራል። ተጋብዘው ጠጥተው ሲጨርሱ አሰፋ ሳይንቲስት ተነስተው ውልቅ ብለው ነው የሚሄዱት። አመላቸው ይታወቃል። ሲጀመር ተማሪዎቻቸው ስላሉ ማንም ሂሳብ አያስከፍላቸውም። ከተጋበዙ በኋላ አመሰግናለሁ ፤ ደህና እደሩ የሚል ቃል ከአሴ አፍ አይወጣም። ብለውም አያውቁ። ተማሪዎቹ እርስ በእርስ መከሩና አሰፋ ሳይንቲስት መቼም የሚለው አያጣ ቆይ እስቲ ብለው አንዱ ተማሪያቸው እንዲናገራቸው ተወከለ። አንድ ቀን ምሽት እዛው ቱሪስት ሆቴል እየተዝናኑ እያሉ ‹‹ጋሼ አሰፋ ሁሌ ግዜ እንጋብዝዎታለን ወደቤት ሲሄዱ አመሰግናለሁ እንኳን አይሉም፤ ለምንድ ነው?›› ይላቸዋል። ምን አልክ አሉት። እየሳቀ ደገመላቸው። እዛው አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ውስጥ ነበሩ። ‹‹ሰማሁህ ፤ሰማሁህ፤ ና፤ና ተከተለኝ›› ብለው ከሆቴሉ ይዘውት ይወጣሉ። ከሆቴሉ ፊት ለፊት ተኮልኩለው የሚሰሩትን ሊስትሮዎች አየሃቸው ብለው ያሳዩታል። አዎን አየኋቸው ብሎ መለሰ። ‹‹ይኸውልህ እኔ አሰፋ ሳንቲስት ባላስተምርህ ኖሮ እንደነሱ ሆነህ ትቀር ነበር። ስለዚህ የምትጋብዙኝ የልፋቴን ዋጋ ነው። ምስጋና አያስፈልገውም›› ብለው እርፍ። ተመለሱና አብረው ወደ ሆቴሉ ገቡ። ‹‹ምን አለ አሴ?›› አሉ ውስጥ የነበሩት ጓደኞቹ። ‹‹እሱን ማን ይችላል›› አላቸው። በመሃል እንደተለመደው ደህና እደሩም አመሰግናለሁ ሳይሉ አሰፋ ሳይንቲስት ውልቅ ብለው ወደቤታቸው እብስ አሉ። አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 23/2012 ወንድወሰን መኮንን
https://www.press.et/Ama/?p=25046
c61133e77363ceaf2c397876da612b95
ef3f2b6627928ee7b8c29222f3c9de45
የመጸዳጃ ቤት ቆይታን ለማሳጠር
መዝናኛ
ዘመናዊ መጸዳጃ በሀገራችን ብዙም አልተስፋፋም ቢባል ዋሾ አያሰኝም፤ ይህን እጥረት መንግሥትም በሚገባ ያውቀዋል። ከዚህ አኳያም የመጸዳጃ ቤት አገልግሎትን በከተማ ለማስፋፋት እየተሰራ ይገኛል። በከተሞች የህዝብ፣ የመንግሥትና የሆቴል መፀዳጃ ቤቶች በስፋት የሚስተዋሉ ሲሆን፣ የመኖሪያ ቤቶች መጸዳጃ ቤቶች በስፋት እየዘመኑ ናቸው። በገጠርም በዚሁ ላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ ሰዎች ጤናቸውን ለመጠበቅ በመጸዳጃ ቤት እንዲገለገሉ ለማድረግ በተለይ በጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በኩል እየተሰራ ነው። በከተሞች በተለይ በህዝብ መጸዳጃ ቤት አጠቃቀም ላይ ግን ተግዳሮቶች ይስተዋላሉ። መጸዳጃ ቤቶችን በንጽህና እና በአግባቡ አለመጠቀም አንድ መሰረታዊ ችግር ነው። መጸዳጃ ቤት ገብቶ ቶሎ አለመውጣት ሌላው ችግር ነው። አንዳንዶች ከጤና ጋር በተያያዘ በተለይ ድርቀት ያለባቸው ናቸው ይባላል መጸዳጃ ቤት እነዚህ ሰዎች መጽሀፍ ፣ጋዜጣ ወዘተ፣ ይዘው በመግባት እያነበቡ ብዙ ይቆያሉ። ሞባይላቸውን ይዘው ገብተው ኢንተርኔት ይሁን ሌላ የሚከታተሉም ጥቂት አይደሉም። ይህ አይነቱ የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀም በተለይ በሆቴሎችና በህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ተጠቃሚዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል። የእነዚህ ተገልጋዮች ተግባር የራሳቸውንም የሌላውንም ተጠቃሚ ጊዜ ያባክናል። ይህ ችግር የሌሎች ሀገሮችም ችግር ነው። ችግሩ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ተከትሎም አዲስ የመጸዳጃ መቀመጫ ዲዛይን ብሪታኒያ ውስጥ እስከ መስራት መደረሱን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን ይዞት በወጣ መረጃ አስነብቧል። ይህ መቀመጫ ሰዎች መጸዳጃ ቤት ውስጥ ከአምስት እስከ ሰባት ደቂቃ በላይ እንዳይቆዩ የሚያደርግ ነው። ይህ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ እንደ ሌሎቹ መቀመጫዎች ምቾት የሚሰጥ ባለመሆኑም ሰዎች ተቀምጠው እንዲያነቡም ሆነ ሞባይል እንዲነካኩ ብዙም እድል አይሰጥም ይለናል መረጃው። መቀመጫው ዲዛይን የተደረገው በእንግሊዛዊው መሀንዲስ ማሃቢር ጊል ሲሆን፣ ከመደበኛው መጸዳጃ መቀመጫ በ13 ዲግሪ ቁልቁል ያጋደለ ነው፤ ሰዎችም በዚሁ ልክ አጋድለው እንዲቀመጡ የሚያደርግ በመሆኑ ምቾት ይነሳል። ጊል የዚህ መቀመጫ ሃሳብ የተከሰተለት መጸዳጃ ቤት ተጠቃሚዎችን ምቾት ስለሚነሳቸው ቶሎ ጣጣቸውን ጨርሰው እንዲወጡና የኪስ ስልክ እያዩ ጋዜጣ ወይም እያነበቡ እንዳይቆዩ በማሰብ ነው። የተቀጣሪዎችን የሥራ ሰዓት ማስፋት ለሚፈልጉ ነጋዴዎችም መልካም አጋጣሚ መሆኑን ይገልጻል።“በእንግሊዝ ብቻ በአንድ የሥራ ቀን ሰራተኞች አለአግባብ የሚያባክኗቸው ጊዜያት የኢንዱስትሪና የንግድ ባለሀብቶችን በዓመት 4 ቢሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ እንደሚያስወጣቸው ይገመታል።” ሲል ሚስተር ጊል ጠቅሶ፣ አዲሱ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ሠራተኞቻቸው በመጸዳጃ ቤት አለአግባብ የሚያጠፉትን ጊዜ በማዳን ቀጣሪዎች የበለጠ ሀብት እንዲያፈሩ ያስችላል ይላል።አዲሱ መቀመጫ ለትርፍ ባልተቋቋመው የብሪቲሽ መጸዳጃ ቤቶች ማኅበር ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን ፤ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ግን የመጸዳጃ መቀመጫውን ዲዛይን በስላቅ አጣጥለውታል ።በመጸዳጃ ቤት ለረጅም ጊዜ መቆየት አይገባም ሲል በድረ ገፅ ላይ አስተያየቱን የሳፈረው ጊል፣ ለእዚህም ሲል አጨቃጫቂውን የመፀዳጃ ቤት መቀመጫ ዲዛይን መስራቱን ለዊርድ መጽሔት ጠቁሟል። አንዳንዴ ሠራተኞች በመጸዳጃ ቤት ተኝተው እንደሚገኙም ጠቅሶ፣ በሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችም ወረፋዎች እየበዙ ተራ የሚጠብቁ ተገልጋዮች ሲቆጡ እንደሚሰማ ይገልጻል። በአገልግሎት ላይ ያለው የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ለተጠቃሚዎች ጤና የሚሰጥ እና ተክለ ሰውነትን የሚያሻሽል እንደሆነ ጊል ቢያምንም ፣ አዲሱ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ግን ቀጣሪዎችን ከኪሳራ እንደሚታደግም ተናግሯል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ኃይለማርያም ወንድሙ
https://www.press.et/Ama/?p=24949
20f2600b6fd5f853fd36059ef33656a0
92201dc95013bc2bc58c6aee96926667
ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲባረሩ የአሜሪካ ሕገመንግሥት 25ኛው ማሻሻያ እየተጠቀሰ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
በኃይሉ አበራከትናንት ወዲያ የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች የመንግሥት መቀመጫና የሁለቱ ምክር ቤቶች አዳራሾች የሚገኙበትን ግዙፉን የካፒቶል ሒል ህንጻን ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የሴኔት ምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲባረሩ እየጠየቁ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧልበዘገባው መሰረት የአሜሪካ ሕገመንግሥት 25ኛው አሜንድመንት ወይም ማሻሻያ እየተጠቀሰ ሲሆን፤ ይህ ማሻሻያ አንድ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አካላዊ ወይም አእምሯዊ ጤና ከራቀው ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦታውን በተጠባባቂነት ተረክቦ አገሪቱን እንዲመራ ያዛል።ሆኖም ይህ እንዲተገበር የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲን ጨምሮ በትንሹ ስምንት የካቢኔ አባላት በጉዳዩ ላይ መስማማት አለባቸው። ነገር ግን ይህ የመሆን እድሉ ለጊዜው ጠባብ ነው ተብሏል።የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ጥሰው ሲገቡ ታህታይና የላዕላይ ምክር ቤት አባላት የባይደንን መመረጥ ከግዛት ተወካዮች የማረጋገጥ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ይህንኑ በማካሄድ ላይ ነበሩ። አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስም በሸንጎ ላይ ተገኝተው ነበር።ይህንን ለአሜሪካ እንግዳ የሆነ ድርጊት ተከትሎ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፔሎሲ 25ኛውን የሕገ መንግሥት ማሻሻያ በመጥቀስ ትራምፕ አሜሪካንን ለመምራት ብቁ ስላልሆኑ ከዋይት ሐውስ እንዲባረሩ ጥያቄ አቅርበዋል።ይህን ጥያቄ በርካታ ዲሞክራቶችና ጥቂት ሪፐብሊካኖች ጭምር ድጋፍ ሰጥተውታል። የሴኔት ዲሞክራት ተጠሪ ቸክ ሹመር ትራምፕ አመጽ በማቀጣጠላቸው ከሥራ ሊባረሩ ይገባል፤ “ምክትል ፕሬዚዳንቱ እና ካቢኔው ይህንን ለማድረግ የማይፈልጉ ከሆነ፣ ኮንግረሱ ዳግመኛ ፕሬዚዳንቱን ከሥልጣን እንዲነሱ ለማድረግ መሰብሰብ አለበት” ብለዋል።ዶናልድ ትራምፕ ከዋይት ሐውስ እንዲወገዱ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ለድርጊታቸው ክስ እንዲመሰረትባቸውም ናንሲ ፒሎሲ ጥሪ አድርገዋል። ክሱ ተፈጻሚ እንዲሆን ግን ዲሞክራቶች የሪፐብሊካኖችን ድጋፍ ማግኘት አለባቸው። ምክንያቱም ክሱ እንዲፈጸም የምክር ቤቱ ሁለት ሦስተኛው ድምጽ ስለሚያስፈልግ ነው። ይህ የመሳካት እድሉም አነስተኛ ነው።25ኛው አሜንድመንት ፕሬዚዳንቱ ኃላፊነቶቹን መወጣት በማይችልበት ጊዜ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ስልጣኑን በጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነት ተረክቦ እንዲያስተዳድር ይፈቅዳል። በአሁኑ ሰዓት መነጋገሪያ እየሆነ ያለው የዚህ አሜንድመት አንቀጽ አራት ነው። ይህ አንቀጽ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እንዲሁም የካቢኔው አብላጫ አባላት ፕሬዚዳንቱ ኃላፊነታቸውን መወጣት አልቻሉም ብለው እንዲወስኑ እድል ይሰጣቸዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቢደረግ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ አገሪቱን እንዲመሩ ይደረጋል። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፊርማቸው ያረፈበትን ደብዳቤ መላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ ሴኔቱም ፕሬዚዳንቱ ሥልጣንና ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ብቁ አይደሉም ሲል ያፀድቃል።ፕሬዚዳንቱ በኮቪድ-19 ተይዘው በነበረበት በጥቅምት ወር ላይ አገሪቱን ለመምራት ሕመማቸው አያስችላቸውም በሚል ተነስቶ ነበር። በዚሁ ወቅት የተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ፣ በ25ኛው አሜንድመንት ላይ መሰረት ያደረገ እና የፕሬዚዳንቱን ጤና ለሥራ ብቁ መሆን አለመሆኑን የሚፈትሽ ሕግ አስተዋውቀው ነበር።25ኛው አሜንድመንት በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1967፣ ጆን ኦፍ ኬኔዲ ከተገደሉ አራት ዓመት በኋላ፣ ፕሬዚዳንቱ በተለያየ ምክንያት ሥልጣንና ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ ወቅት ማን ይተካቸዋል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በሚል ጸድቋል።በዚህም የተነሳ በርካታ ፕሬዚዳንቶች ይህንን የሕግ ማሻሻያ [አሜንድመንት]፣ በይበልጥ ደግሞ በጊዜያዊነት ሥልጣንን ለምክትላቸው ማስተላለፍ የሚፈቅደውን ክፍል፣ አንቀጽ ሦስትን ተጠቅመውበታል።በ2002 እና በ2007 ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ የአንጀት ህክምና በሚያደርጉበት ወቅት ምክትላቸው እንዲተኳቸው አድርገዋል። ፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬገን በ1985 ለካንሰር ህክምና ሆስፒታል በገቡበት ወቅት ተመሳሳዩን አድርገዋል። ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ 25ኛው አሜንድመንትን በመጠቀም የትኛውም ፕሬዚዳንት ከሥልጣን እንዲወርድ ተደርጎ አያውቅም።አዲስ ዘመን ጥር 01/2013
https://www.press.et/Ama/?p=39204
f20aa2d6c617f7a664b21ada6e20eda9
443881c7490d28b55c3ddaa3c4b1d122
እንዲህ ቢባል ምን ችግር አለው?
መዝናኛ
በአውሮፓውቷ አገር ኖርዌይ ለትምህርት ከአንድ ዓመት በላይ ቆይቶ የመጣ አንድ ጓደኛዬ የነገረኝ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ በነገራችን ላይ ውጭ አገር ቆይቶ የመጣ ሰው ሳገኝ ቀድሜ የምጠይቀው የህዝቡን ሥነ ልቦና ነው፡፡ እንዲያው ይሄ ርዕስ በርዕስ መነቋቆር የሰለጠኑት አገሮችም አለ ይሆን የሚለውን ለማወቅ ስለምፈልግ፡፡ እናም ይሄ ጓደኛዬ የነገረኝ ነገር በሀገረ ኖርዌይ ያስተዋለው ህዝቡ ሐሜትና መነቋቆር ጉዳዩ እንዳልሆነ ነው፡፡ አለ ከተባለም አድናቆት ነው፡፡ ከከንቲባው ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ ያለ የትኛውም ባለሥልጣን ሲሰደብና ሲወቀስ አይወዱም፡፡ ለባለሥልጣኖቻቸው ትልቅ ክብር አላቸው፡፡ ይሄን ነገር በእኛ አገር ቢሆን ብየ አሰብኩት፡፡ አንድ ከሌላ አገር የመጣ ዜጋ ባለሥልጣኖቻችንን ሲያብጠለጥል ብንሰማው በደስታ የሚፍለቀለቀው አይበልጥም? እሰየው አብጠለጠለልን አንልም ነበር? መወቀስ ያለባቸው ቦታ ላይ መወቀስ የለባቸውም እያልኩ አይደለም፡፡ ችግሩ ግን ወቀሳችንም አድናቆታችንም ምክንያታዊ አይደለም፡፡ ሌላውን ሰው የሚያናድድ እየመሰለን ነው፡፡ከሰሞኑ ማህበራዊ ገጽ ላይ ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ እስከ ዶክተር አብይ አህመድ ያሉ የአገሪቱን መሪዎች የሚያመሰግን አንድ ፎቶ አየሁ፡፡ ከእያንዳንዱ መሪ ፎቶ ሥር የሚያስመሰግናቸው ሥራ ተጽፏል፡፡ የፎቶው አቀማመጥ በሥልጣን ዘመናቸው ቅደም ተከተል ነው፡፡ በነገራችን ላይ ይሄ ነገር ብርቅ የሆነው ካለው ወቅታዊ ብሽሽቅ አንፃር እንጂ ብርቅ መሆን የነበረበት ሆኖ አይደለም፡፡ ግን ጠዋት ማታ የምናየው አንዱ ሌላውን ሲያጣጥል ነው፡፡ የሚያደንቅም የሚወቅሱትን ለማናደድ ነው፡፡ አንዱን መሪ ለማድነቅ ሌላውን ማጣጣልና መሳደብ ግዴታ መስሏል፡፡ ግን እንዲህ ሁሉንም በሥራቸው ማመስገንም ይቻል ነበር፡፡ ጥፋት ብቻ እናውራ ከተባለ በእያንዳንዱ መሪ ዘመን የተፈፀመ ብዙ ጥፋት አለ፡፡ ግን ምነው የሠሩትን ጥሩ ሥራስ ብናወራላቸው?እዚህ ፎቶ ላይ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ‹‹ጠፈርን የደፈረ›› ይላል፡፡ በቅርቡ ኢትዮጵያ ሳተላይት አምጥቃለች፡፡ ሳተላይት ማለት የአንዲት አገር የብልጽና እና የሥልጣኔ ማሳያ ነው፡፡ የመዘመን ምልክት ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ በኋላቀርነትና በድህነት ስሟ ሲጠራ የቆች አገር ናት፡፡ ስለዚህ የዚች አገር ስም በእንዲህ አይነት ነገር ሲጠራ ጀግንነት ነው፡፡በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፎቶ ሥር ‹‹ሥልጣኑን በሰላም የለቀቀ›› ይላል፡፡ እንደሚታወቀው የአፍሪካ አገራት ስማቸው ተደጋግሞ የሚጠራው በምርጫ ማጭበርበርና በ‹‹ሥልጣን አልለቅም!›› ጦርነት ነው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች የሚታወቁት የሥልጣን ሽግግር በተደገረ ቁጥር አሻፈረኝ ሲሉና ግጭት ሲቀሰቀስ ነው፡፡ የራሷ የኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክም ይሄው ነው፡፡ ሥርዓቶች ሁሉ የተቀያየሩት በጦርነት ነው፡፡ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ግን በራሳቸው ፈቃድ ሥልጣን ለቀቁ። አቶ ኃይለማርያምና ዶክተር አብይ ተቃቅፈው የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ተረካከቡ፡፡ ይሄ አቶ ኃይለማርያምን ጀግና ያሰኛቸዋል፡፡በአቶ መለስ ዜናዊ ፎቶ ሥር ‹‹ዓባይን የደፈረ›› ይላል። ለዘመናት የዘፈንና የፉከራ ምንጭ ሆኖ የኖረው ዓባይ የኃይል ምንጭ ሊሆን የመሰረተ ድንጋይ የተቀመጠለት በአቶ መለስ ዜናዊ ነው፡፡ በርሃብና በድህነት የምትታወቅ አገር ከዓለም ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነውን የህዳሴ ግድብ ጀመረች፡፡ ኢትዮጵያዊ የአገር ፍቅር ታየበት። የማይደፈር የመሰለውን ዓባይ መገደብ ተጀመረ፡፡ ይሄ አቶ መለስ ዜናዊን ጀግንነት የሚያሰኝ ነው፡፡ በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ፎቶ ሥር ‹‹የሀገርን ዳር ድንበር ያስጠበቀ›› ይላል፡፡ የደርግ ዘመነ መንግሥት ስሙ የሚነሳው በጨቋኝነቱና በጨፍጫፊነቱ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያምን የሀገር ፍቅር ብዙዎች የመሰከሩት ነው፡፡ የደርግ ሥርዓትን ታግሎ ያሸነፈው ኢህአዴግ መሪ የሆኑት ራሳቸው አቶ መለስ ዜናዊ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያምን ‹‹በሀገሩ ጉዳይ አይደራደርም›› ብለው ነበር፡፡ ደርግ በዘመኑ የነበሩ ወረራዎችን ተቋቁሞ የአገሩን ዳር ድንበር አስጠብቋል፡፡ ይሄም ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያምን ጀግና ያሰኛቸዋል፡፡ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ፎቶ ሥር ‹‹ጣሊያንን የደፈረ›› ይላል፡፡ አንዲት አፍሪካዊት አገር አንዲት አውሮፓዊትን አገር ትደፍራለች ብሎ የማይታሰብበት ዘመን ነበር፡፡ የአውሮፓ ኃያልን ማን አለብኝ ብለው የአፍሪካ አገራትን ልክ እንደ ሸቀጥ መከፋፈል ጀመሩ፡፡ ኢትዮጵያ ላይ ሲደርሱ ግን አልተሳካም። ኃያልን አገራት ያልጠበቁት ሽንፈት አጋጠማቸው፡፡ ነጭ በጥቁር ተሸነፈ፡፡ ታሪክ ተቀየረ፡፡ የአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች ‹‹ለካ ነጭን ማሸነፍ ይቻላል›› አሉ፡፡ እነሆ ኢትዮጵያን አይተው የአፍሪካ አገራትም ነፃ ወጡ፡፡ ይሄ ዳግማዊ አፄ ምኒልክን ጀግና ያሰኛል፡፡አንድ ነገር ልብ ይባልልኝ፡፡ የተጠቀሰው ጀግንነታቸው ይሄ ብቻ ሆኖ አይደለም፡፡ በፎቶ ተቀነባብሮ ያየሁትን መነሻ አድርጌ ስለሆነ እንጂ፡፡ ማህበራዊ ገፆች ላይ እንዲህም ማመስገንና ማድነቅ ይቻላል የሚለውን ለማሳየት እንጂ የመሪዎች ሥራ ይሄ ብቻ ሆኖ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ይሄኛው ሥራቸው ነው መቅደም ያለበት የሚል ሐሳብም ሊነሳ ይችላል፡፡ ግን እንዳልኩት ነው፡፡ መነሻዬ ፎቶው ላይ ያየሁት ነው፡፡ ያደረገው አንድ ግለሰብ ሊሆን ይችላል፤ በፓርላማ የፀደቀ ወይም የምሁራን ውይይት የተደረገበት አይደለም፡፡ እንደ ምሳሌ ነው የተነሳ፡፡ ጀግና የሚያሰኙ ሥራዎች አሏቸው ለማለት ነው፡፡ የጀግና ችግር የለብንም፡፡ ያለብን የራስን የሆነ ነገር የማክበር ችግር ነው፡፡ የመሪዎቻችን፣ የሳይንቲስቶቻችን፣ የአርቲስቶቻችን ጀግንነት የሚታየን ፈረንጅ ሲሸልማቸው ነው፡፡ የመሪዎቻችን ነገር ጭፍን የፖለቲካ አስተሳሰብ ስለተጫነው የክርክርና የጭቅጭቅ ምክንያት ሆኗል፡፡ የሚያሳዝነው እኮ ደግሞ የዋናዎቹ የመገናኛ ብዙኃንም አጀንዳ ይሄው መሆኑ ነው፡፡ የሚያሳዝነው እኮ ትልልቅ ሰዎች ራሱ አጀንዳቸው ይሄው መሆኑ ነው፡፡ የማህበራዊ ገፆች ብቻ ቢሆን እኮ ቀላል ነበር፡፡ የተራ ሰዎች ብቻ ቢሆን እኮ ይሻል ነበር። ትልልቅ የሚባሉ ሰዎች ራሱ ንግግር የሚያደርጉት አንዱን ለማመስገን አንዱን በመሳደብ ነው፡፡ አቶ ዕገሌን ለማመስገን የግድ አፄ ዕገሌ መሰደብ አለበት፡፡ አፄ ዕገሌን ለማድነቅ የግድ አቶ ዕገሌ መሰደብ አለበት፡፡ ይሄው ነው የፖለቲከኞቻችንም ሆነ የምሁራኖቻችን ትንታኔ፡፡ እስኪ ማድነቅና ማመስገንንም እንልመድ! አፄ ዕገሌን ሳንሳደብ አቶ ዕገሌን ማድነቅ ወይም አቶ ዕገሌን ሳንሳደብ አፄ ዕገሌን ማድነቅ እንቻል! መልካም በዓል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 26/2012ዋለልኝ አየለ
https://www.press.et/Ama/?p=25183
e972d49758e31f60d8cbc8ea81d2a40a
20daf983e9542986441cf79b0053d6bd
ኢትዮጵያ በአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ ክለብ የሌላት ብቸኛ አገር ሆናለች
ስፖርት
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ እንደሌሎቹ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኩነቶች ሁሉ የዓለምን ስፖርት ውጥንቅጡን አውጥቶታል፡፡ ታላላቅ የዓለማችን ሊጎች የሚይዙትን የሚጨብጡትን አጥተው ከርመዋል፡፡ ከሳምንት በፊት አንስቶ ግን የዓለማችን ታላላቅ ሊጎች ወደ ውድድር እየተመለሱ ስፖርቱም እያገገመ ይመስላል፡፡ ወትሮውንም ችግር የማያጣት አፍሪካ የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ መሆኗ ነገሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚያደርግባት ቀድሞም የተገመተ ቢሆንም የአንዳንድ አገራት የእግር ኳስ መሪዎች አስቸጋሪውን ወቅት በብልሃትና በበሰለ አመራር ሰጪነት ለመሻገር ጥረት ማድረጋቸው አልቀረም፡፡ የቡርኪናፋሶ እግር ኳስ ተሞክሮም ለዚህ ጥሩ ምሳሌ መሆኑን መመልከት ይቻላል፡፡ ቡርኪናፋሶ እንደሌሎቹ የዓለማችንም ይሁን የአፍሪካ አገራት ሰሞንኛ ማህበራዊ ሁኔታዋ ጤነኛ አልነበረም። አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የኮሮና ቫይረስ ያጠቃቸው ፖለቲከኞች ተመዝግበውባታል። የቡርኪናፋሶ መንግሥት ይህ ቫይረስ ተስፋፍቶባቸዋል ብሎ ካወጀባቸው ቦታዎች መካከል የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ይገኙበታል፡፡ ጅምናዚየም ፣ የኳስ መጫወቻ ሜዳዎች ለዚህ ተጠቃሽ ከሚባሉት ቦታዎች ውስጥ ይገኛሉ። ስለዚህ ይህንን አደጋ ለመቀነስ እና ለማህበረሰቡ ዋስትና ለመስጠት ሊጉን ሰርዞ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የዘንድሮው የውድድር ዓመት እንደማ ይጠናቀቅ እና በዚሁ ውጤት እንደሚያልቅ፣ ሁሉም ክለቦች በውል ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾቻቸውን ውል እንዲያከብሩላቸው እና እስከውል ማለቂያው ድረስ ደመወዝ እንዲከፍሉ፣ ማንኛውም ክለብ ያለምንም በቂ ምክንያት ምንም አይነት የክለብ አባላት ቅነሳ እንዳያደርግ፣ የትኛውም ተጫዋች ተበደልኩ ቢል ለፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት እንዲያመለክት፣ ከሁሉም በላይ በዘንድሮ 2019 የውድድር ዘመን በኢንተርናሽናል መድረክ አገሪቱን የወከሉት ቡድኖች ማለትም (ራሂሞ ኤፍ ሲ) እና (ሳሊታስ) የተባለው ክለብ በክለቦች ኮንፌዴሬሽን ጨዋታ በሚመጣው ዓመት አገሪቱን እንዲወክሉ አድርጓል። ይህንን ያደረገውም የዘንድሮ ልፋታቸው ሽልማት እንኳን ቢሆን ብሎ በማሰብ ነው ። አሱማ ሲሪማ የቡርኪናፋሶ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ይህንን ውሳኔ ሲወስኑ ሁሉንም እንደሚያስማማ በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል:: ቡርኪናፋሶን የወከሏት ቡድኖች የተገኙት አምና ባስመዘገቡት ውጤት ነው ። ይህ አንዳንዴ የተቀመጠን ህግ እና አሰራር ወቅቱ በሚፈቅደው ነገር እንደሚጠመዘዝ ማሳያ ነው ። የኢትዮጵያ ሊግ ካምፓኒ ምንም አይነት ቡድን ኢትዮጵያን በኢንተርናሽናል ውድድር አይወክልም የሚል ውሳኔ ከወር በፊት አስተላልፏል። ይህ እንደ አገር በድጋሚ ሊጤን የሚገባው ውሳኔ እንደሆነ በርካቶች አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡ ውሳኔው ስህተት መሆኑን ወሳኞቹ አካላት ቢያምኑም የተወሰደ ርምጃ የለም፡፡ ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ በአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ ክለብ የሌላት ብቸኛ አገር ሆናለች፡፡ የደቡብ አፍሪካው ሱፐር ስፖርት ከቀናት በፊት ‹‹ኮሮና እና የአፍሪካ ሊጎች›› በሚለው ሰፊ ዘገባው በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከሶስት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረውን የአፍሪካ አገሮች ወረርሽኙ ባይጠፋም የሊግ ውድድሮች ቀስ በቀስ ከተቋረጠበት እያስጀመሩ እንደሆነ አስነብቧል። ሱፐር ስፖርት በሰፊ ዘገባው አያይዞም ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች በተለየ መልኩ ሊጓን ሙሉ ለሙሉ መሠረዟን እና በሯን መዝጋቷን አስነብቧል። በዚህም ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት ክለቦቿ በአፍሪካ ውድድር ባለመሣተፍ ብቸኛዋ አገር መሆኗ ተረጋግጧል:: በኢንተርናሽናል ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉት ቡድኖች ከየትም ወገን ይምጡ የሚወክሉት ሊጉን ነው ። ሊጉ ደግሞ በድግግሞሽ በየዓመቱ ኢትዮጵያን በጥራት የሚወክሉ ቡድኖችን ይፈልጋል። ይህንን ጥራት ለማምጣት ደግሞ የቡድኖችን የኢንተርናሽናል ተሳትፎ መንገድ መቁረጥ ሌላ ፈተና ይዞ እንደሚመጣ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይህን መቁረጥ በአንድ ዓመት የኢንተርናሽናል ልምድ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኝን ተጫዋች ራሱን የማሳየት ተስፍ ማጨለሙ አይቀርም፡፡ የክለቦችን የአስተዳደራዊ ዝግጅት ደረጃ ከፍ የማድረግ ልምድ ማሳነስም ሌላኛው ኪሳራ ነው፡፡ እንደ ላይቤሪያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ቡርኪናፋሶ ያሉ የአፍሪካ አገራት የዘንድሮ ፕሪሚየር ሊግ ውድድራቸውን ቢያቋርጡም በአፍሪካ ውድድሮች ላይ የሚወክሏቸው ክለቦች አሏቸው። በዚሁ ወረርሽኝ ሳቢያ ከአፍሪካ ክፉኛ ተጎጂ የሆነችው ግብፅም ብትሆን ሊጓን ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት አልተጣደፈችም፡፡ እንዲያውም ከትናንት በስቲያ የአገሪቱ ስፖርት ሚኒስትር አሽራፍ ሶቢሂ ሁሉም የእግር ኳስ ክለቦች ከአንድ ሳምንት በኋላ ልምምድ እንዲጀምሩ ማሳሰባቸው እየተዘገበ ይገኛል፡፡ አዲስ ዘመን ሰኔ 11/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=34598
a9d9b59c6268b73757d0058a47ba97a5
ed1349c7a3a3792606c14c89ef1f693d
የለንደን ማራቶን ሊሰረዝ ይችላል
ስፖርት
በቀጣዩ መስከረም ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ‹‹የግሬት ኖርዝ ረን›› ግማሽ ማራቶን ውድድር መሰረዙን ተከትሎ ጥቅምት ላይ እንደሚካሄድ የተነገረው የለንደን ማራቶንም ሊሰረዝ እንደሚችል ጥርጣሬ ፈጥሯል:: በእንግሊዝ አገር ከሚካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች መካከል ትልቁን ስፍራ የሚይዙት ሁለቱ የማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውድድሮች ከኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ስጋት ጋር በተያያዘ ቀደም ብሎ ከሚካሄዱበት ወቅት እንዲራዘሙ ተደርጎ በቀጣዩ መስከረምና ጥቅምት ወር ሊካሄዱ ቀጠሮ ተይዞ ነበር፡፡ ዘንድሮ አርባኛ ዓመቱን የያዘው ‹‹ግሬት ኖርዝ ረን›› የግማሽ ማራቶን ውድድር ከመሰረዙ አስቀድሞ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ስልሳ ሺ ተሳታፊዎችን በመያዝ በብሪታኒያ ትልቁ የጎዳና ላይ ውድድር መሆን ችሏል፡፡ ከሰላሳ አንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ከውድድሩ በመሰብሰብ ለበጎ አድራጎት እንዲውል ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ እንዳልተቻለ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ውድድሩ ሊሰረዝ እንደቻለ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል:: ውድድሩ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚደረገውን ጥንቃቄ ከግምት በማስገባት እንዲካሄድ አዘጋጆቹ ከጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተው በመስራት ጥረት ቢያደርጉም እንዳልተሳካ አሳውቀዋል፡፡ በዚህ ታላቅ ውድድር ባለፈው ዓመት እንግሊዛዊው የኦሊምፒክ ጥምር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው አትሌት ሞሐመድ ፋራህ ለስድስተኛ ተከታታይ ጊዜ ሲያሸንፍ ኬንያዊቷ የማራቶን ባለክብረወሰን ብሪጊድ ኮስጌ የውድድሩን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር ማሸነፏ ይታወሳል፡፡ ይህ የግማሽ ማራቶን ውድድር መሰረዙን ተከትሎ ጥቅምት ላይ ሊካሄድ የታሰበው ትልቁ የለንደን ማራቶንም ሊሰረዝ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የለንደን ማራቶን እንደወትሮው ቢሆን ባሳለፍነው ሚያዚያ ላይ የዓለማችን የርቀቱ ኮከቦችን ያፋልም ነበር፡፡ በተለይም በወንዶች የማራቶን ባለክብረወሰኑ ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌና የርቀቱ ሁለተኛው ፈጣን አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዚህ ውድድር የሚያደርጉት ፉክክር በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ ነበር፡፡ ውድድሩ መሰረዝ አለመሰረዙን ግን አዘጋጆቹ የገለፁት ነገር የለም፡፡ በርካታ የማራቶን የዓለም ክብረወሰኖች የሚ ሻሻሉበት የበርሊን ማራቶን በዚህ ዓመት የመሰረዝ ወይም የመራዘም እድል ያልገጠመው ብቸኛው ውድድር ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ታላቅ የማራቶን ውድድር የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ ከመከሰቱና ከመስፋፋቱ አስቀድሞ መስከረም ወር ላይ በመካሄዱ የሌሎቹ ታላቅ ውድድሮች እጣ ፋንታ ሳይገጥመው ቀርቷል፡፡ ያም ሆኖ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እስካሁን የሚያቆመው ባለመኖሩና ወደ ፊትም መፍትሄ ማግኘቱ አጠራጣሪ እየሆነ በመምጣቱ በቀጣዩ መስከረም የበርሊን ማራቶን የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ የውድድሩ አዘጋጆች ባለፈው ወር እንደጠቆሙትም፣ ውድድሩን በተለመደው ወቅት ለማካሄድ እስካሁን ውሳኔ ላይ መድረስ አልቻሉም፡፡ ውድድሩን ለማካሄድ ወይም ለማራዘም ውይይት እየተደረገ ሲሆን ውሳኔ ላይ ለመድረስ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቀዋል፡፡ የጀርመን መንግስት በኮሮና ቫይረስ ስጋት እስከ መጪው ጥቅምት ወር መጨረሻ ከአምስት ሺ ሰው በላይ የሚሰበሰብባቸው ማንኛቸውም መርሐግብሮች ማገዱን ተከትሎ የውድድሩ አዘጋጆች ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ ጠቁመዋል፡፡ እንደ በርሊን ማራቶን ሁሉ ዋነኞቹ የዓለማችን የማራቶን ውድድሮች ከሆኑት አንዱ የቦስተን ማራቶንም በተመሳሳይ ምክንያት መካሄድ ከነበረበት ወቅት የመራዘም እድል እንደገጠመው ይታወሳል፡፡የበርሊን ማራቶን አዘጋጆች ውድድሩ ካለው ስፋትና ከሚያሳትፈው የሰው ብዛት አኳያ የሚካሄድበት እድል መኖር አለመኖሩን በማጥናት ላይ የሚገኙ ሲሆን ውሳኔ ላይ ለመድረስም የተወሰነ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቀዋል፡፡ ለዚህም የውድድሩ አዘጋጆች አሁን ላይ በቫይረሱ ስጋት የተነሳ በሙሉ ኃይላቸው ተገናኝተው መስራት አለመቻላቸው አንዱ እንቅፋት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በርካታ የዓለም ክብረወሰኖች የሚመዘገቡበት የበርሊን ማራቶን 2018 ላይ ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ 2፡1፡39 የሆነ አዲስ የዓለም ክብረወሰን በርቀቱ እንዳስመዘገበበት ይታወሳል፡፡ ባለፈው መስከረም ደግሞ ቀነኒሳ በቀለ ይህን ክብረወሰን ለማሻሻል በሁለት ሰከንድ የዘገየ ሰዓት ማስመዝገቡ አይዘነጋም፡፡ አዲስ ዘመን ሰኔ 11/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=34601
88b836aeb0d8c1e3a9a50dbd9ec4884b
11e63b0d77c5ea376e275c9a8cdf9848
በ «አረንጓዴ አሻራ» መርሃ ግብሩ የስፖርት ቤተሰቡ አሻራ
ስፖርት
በኢትዮጵያ የደን ልማት ለማጎልበት የሚያስችለው የዘንድሮ «አረንጓዴ አሻራ» መርሃ ግብር ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መርሃ ግብሩን ሲያስጀምሩ፤ በዘንድሮ ዓመት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አምስት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ መያዙን ተናግረዋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ችግኞችን እንዲተክል «አሻራችንን በማኖር ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ምንጣፍ እንዘርጋ» ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን አስጀምረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ጥሪ መሰረት በማድረግ በዘጠኙም ክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ ተቋማት፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥሪውን በመቀበል አረንጓዴ አሻራቸውን በማሳረፍ ላይ ይገኛሉ። የ2012ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ተግባራዊ ካደረጉት ተቋማት መካከል ደግሞ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል። በ2012 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ 156 ሺህ ችግኞች በመትከል ለሀገር አቀፍ ስኬቱ የበኩሉን ሚና ለመወጣት እቅድ ይዞ ሲንቀሳቀስ ነበር የቆየው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የበጀት ዓመቱን መርሃ ግብር በቅርቡ ማስጀመራቸውን ተከትሎ ፤ ኮሚሽኑ የስፖርት ቤተሰቡንና ማህበረሰቡን የሚያሳትፈውን መርሃ ግብር ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል። መርሃ ግብሩም «ለስፖርት ልማት አረንጓዴ አሻራችንን እናስቀምጥ» በሚል መሪ ቃል በይፋ ተጀምሯል። ለአረንጓዴ ልማቱ አሻራ የስፖርት ቤተሰቡ አሻራ ለማሳረፍ እድል የሚከፍተው መርሃ ግብሩ በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰሚት ኮንደሚኒየም ሁለተኛ በር በሚገኘው የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራ በታላቅ ድምቀት ሊጀመር። በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይም የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የኢትዮጵያን ባንዲራ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ እንዲል ያደረጉ አትሌቶች፣ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና ደጋፊዎች ተገኝተዋል። በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አስተባባሪነት የተሰናዳውን አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ ትግበራው ከሰሚት ኮንዶሚኒየም የተነሳው የተከላ መርሃ ግብሩ በመቀጠል በሌሎች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ተከናውኗል። ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦችን በማካተት የኮረና ቫይረስ ተጋላጭነት በማይኖረው መልኩ እንዲሁም ጥንቃቄ በታከለበት ሁኔታ ችግኝ በመትከል ለስፖርቱ ልማት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይ በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ወቅት ፤ ለስፖርተኛውና ለስፖርት ቤተሰቡ የሚያስፈልገው ንፁህ አየርና ጤናማ ለመሆን ችግኝ መትከል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። «የስፖርት ማዘውተሪያዎች በኮንክሪት ብቻ ሳይሆን በአረንጓዴ ተክሎችም መዋብ አለባቸው። ስለዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን በቀሪ ወራትም አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስገንዝበዋል። «በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ በከተማዋ በሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ተይዞ ወደ ተግባር ተገብቷል። በዚህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 34 የስፖርት ፌዴሬሽኖች የሚሳተፉ ይሆናል» ብለዋል። በከተማዋ የስፖርት እንቅስቃሴው ላይ ተጨባጭ ለውጥና ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ እየተመዘገበ መሆኑን አክለው የገለጹት አቶ ዮናስ ፤ ለዚህም ስኬታማ ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ተከትሎ እንደሆነ ገልጸዋል። ለስፖርቱ ስኬታማነት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንና የሚሰሩትን ስራ በአብሮነት በመሆን ሲደክሙ እንደነበር ገልጸዋል። ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለመዲናዋ ስፖርት እድገት መነቃቃት እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራው መርሃ ግብር ላይ አሻራቸውን በማሳረፍ ላበረከቱትና ወደፊትም ለሚያበ ረክቱት የመሪነት ሚና አመስግነዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው፤ ስፖርት እና አረንጓዴ ቦታ እንደማይነጣጠሉ ተናግረዋል። ይህን በመገንዘብ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን ለማኖር የተገኙ ስፖርተኞችን አመስግነዋል። «በአረንጓዴ አሻራ ላይ የስፖርት ቤተሰቡ ችግኝ በመትከል በመንከባከብና በማሳደግ ከተማችንን ማስዋብ ፣ ማሳመርና ንፁህ አየር በማግኘት ውጤታማ ስፖርተኛ እንዲሆኑ መትጋት ይኖርባቸዋል» ብለዋል። የስፖርት ቤተሰቡና ማህበረሰቡ በከተማዋ ሁለንተናዊ ለውጥ ላይ እያደረጉት ያለውን አስተዋፅኦ እና ርብርብ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ኢንጂነር ታከለ ለስፖርት ቤተሰቡና ማህበረሰቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በተጨማሪም በመርሃ ግብሩ ለይ የተገኙት የኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ተወካዮች አዲስ አበባን አረንጓዴ ለማ ድረግ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በቀዳሚነት እንደሚሰለፉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ አረንጓዴ አካባቢ ከአትሌቶች የሥልጠና ቦታ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በዛሬው ዕለት አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖራቸው ደስተኛ መሆናቸውን አትሌት ገንዘቤ ዲባባና አትሌት ጌጤ ዋሚ የገለጹ ሲሆን ፤ ችግኝ ከመትከል ባለፈ ተገቢ እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባም አመልክተዋል። አዲስ ዘመን ሰኔ 12/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=34666
1f99a2af8244cefebeede126afa942fc
10b865936a842ae58ec9b052edf442f2
ላሚን ዲያክ የአራት ዓመት እስር እንዲፈረድባቸው ተጠየቀ
ስፖርት
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፓሪስ ውስጥ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዚዳንት ላሚን ዲያክ አራት ዓመት የእስር ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ተጠየቀ፡፡ የሰማንያ ሰባት ዓመቱ አዛውንት ላይ ክስ የመሰረቱት የፈረንሳይ አቃቤ የላሚን ዲያክ ልጅ በሆኑት ፓፓ ማሳታ ዲያክ እንዲሁም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የቀድሞ የማርኬቲንግ አማካሪ ላይ የአምስት ዓመት እስርና የአምስት መቶ ሺ ፓውንድ ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ለፍርድ ቤት ጥያቄ እንዳቀረቡ ሮይተርስ ትናንት ዘግቧል፡፡ አዛውንቱ ላሚን ዲያክ እድሜያቸው መግፋቱን ተከትሎ የእስር ቅጣት ከተላለፈባቸው ሕይወታቸው በወሕኒ ቤት ሊያልፍ እንደሚችል በመጠቆም ጠበቆቻቸው ፍርዱ እንዲቀል መጠየቃቸው ታውቋል፡፡ የመጨረሻው የፍርድ ሂደት ላይ የተሰየመው የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለማስተላለፍም ለመጪው መስከረም ቀጠሮ ይዟል፡፡ እኤአ ከ1999 እስከ 2015 የዓለም አቀፉን አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የመሩት ላሚን ዲያክ መንበረ ስልጣናቸውን ባስረከቡ ማግስት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በሰማንያ ስድስት ዓመታቸው ነበር ወደ ፓሪስ ባቀኑበት ወቅት በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ የሃምሳ አራት ዓመቱ ልጃቸው ፓፓ ማሳታም ዓለም አቀፍ ማህበሩን ተገን አድርጎ ህገ ወጥ ገንዘብ ህጋዊ በማድረግና ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም እንዲሁም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው አባት ወህኒ ሲወርዱ ልጅየው ወደ ትውልድ አገሩ ሴኔጋል ተመልሶ የፍርድ ሂደቱን ባለበት እንዲከታተል የተደረገው፡፡ ይሁን እንጂ ፓፓ ማሳታ በመጨረሻው የፍርድ ቤት ውሎ ችሎት ሳይቀርብ ቀርቷል፡፡ ይህም ላሚን ዲያክን እንዳስቆጣ ተዘግቧል፡፡ አባትና ልጅ ቀደም ሲል ከተጠረጠሩበት ወንጀል በተጨማሪ የሩሲያውያን አትሌቶችን የአበረታች ንጥረ ነገር ምርመራ ውጤት በማሸሽ የተጠረጠሩ ሲሆን ጠበቆቻቸው ወደ አገራቸው ሴኔጋል ተመልሰው የክስ ሂደቱን እንዲከታተሉ ያቀረቡት ጥያቄ በፈረንሳይ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ፓፓ ማሳታ፣ የቀድሞው የሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቫሌንቲን ባላክኒቼቭ እንዲሁም የቀድሞ የሩሲያ አትሌቲክስ አሰልጣኝ አሌክሲ ሜልኒኮቭ እኤአ 2016 ላይ በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ከስፖርቱ እድሜ ልክ እንዲርቁ ማገዱ ይታወሳል፡፡ ቫሌንቲን ባላክኒቼቭና አሰልጣኝ አሌክሲ ሜልኒኮቭ በዚሁ የክስ ሂደት ውስጥ ጉዳያቸው እየታየ ቢሆንም የፈረንሳይ መንግስት ለረጅም ጊዜ በያዘው ምርመራ ለፍርድ ለመቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ በክስ ሂደቱ ከአዛውንቱ ዲያክ በተጨማሪ አማካሪያቸው የነበሩት ሃቢብ ሲሴና የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የአሁኑ (የዓለም አትሌቲክስ) ፀረ አበረታች መድሃኒት ጉዳዮች መሪ የነበሩት ገብርኤል ዶል ጉዳይ እየታየ ይገኛል፡፡ ዲያክ በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከ አስር ዓመት የሚዘልቅ እስር ሊፈረድባቸው እንደሚችልና ቀሪ የእድሜ ዘመናቸውን ወሕኒ ሊያሳልፉ እንደሚችሉ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡ የፈረንሳይ የፋይናንስ አቃቤ ህግ ቢሮ እኤአ 2018 ላይ እንዳሳወቀው ዲያክ ስፖርትን ተገን አድርገው በሴኔጋል ለፖለቲካ ቅስቀሳ የሚውል ገንዘብ ከሩሲያ መንግስት ተቀብለዋል፡፡ ለዚህም የሩሲያውያን አትሌቶችን የአበረታች ንጥረ ነገር ምርመራ ውጤት በመሸሸግ ተደራድረዋል፡፡ በዚህ ድርድር ወቅትም ዲያክ ሞስኮ ካስተናገደችው የ2013 የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ቀደም ብለው ውድድሩን ከሚያሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና ስፖንሰሮች ጋር በገንዘብ ተደራድረዋል፡፡ አዲስ ዘመን ሰኔ 13/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=34738
27943446e34b5bd1cddc1e4b2137fc9a
94abbf8e37da82febbb057ee77459c41
ሰብዓዊነትን የታጠቀው የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሀሳብ
ስፖርት
ስፖርት ሰላም፣ ፍቅር፣ የአብ ሮነትና የአንድነት፣ የመተሳ ሰብ፣ የወንድማማችነት ልዩ መገለጫ ነው። ስፖርት ዘር፣ ሃይማኖት፣ ፆታና ቀለምን አይለይም። በየት ኛውም ሁኔታ ውስጥ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አስኳል ሃሳብ ወዳጅነትና መተሳሰብ መሆኑ ይታወቃል። በታሪክ ገጾች እንደሰፈረውም በሰው ልጅ ታሪክ ባጋጠሙ በጎም ሆኑ መጥፎ ክስተቶች ስፖርት በአጋርነት ተሳትፏል። ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ሰላምንና አንድነትን የሚሰብኩ እንደመሆናቸው በማህበራዊ፣ ፖለቲ ካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በመግባት ሚናቸውን ሲወጡም ኖረዋል። ስፖርት ሰብዓዊነትን ያነገበ የልግስና ማዕድ መሆኑን ዘመነ ኮሮና በተጨባጭ አሳይቶናል። የቫይረሱ ስጋትነት በዓለም አቀፉ የጤና ተቋም ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ፤ ውድድሮችን ከማቋረጥና ከመሰረዝ ባለፈ የስፖርቱ ተዋንያን በተናጠልም ሆነ በተቋማዊ ደረጃ አበርክቷቸውን ሲወጡ ታዝበናል።በስፖርቱ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ዝናን ካተረፉ ግለሰቦች እስከ ዓለም አቀፍ ተቋማት ድረስ ወረርሽኙን ለመመከት እየተደረገ ባለው ርብርብ ከተሳትፎ አልጎደሉም።በተለያዩ ሀገራት ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ለመዋጋት በስፖርቱ ማኅበረሰብ ዘንድ የታየው ተሳትፎ በሀገራችንም ተመሳሳይ ሲሆን ታዝበናል። በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ይፋ ከተደረገበት ከወርሃ መጋቢት መጀመሪያ አንስቶ የስፖርቱ ማህበረሰብ ድርሻ ግዙፍ ነው።በስፖርት ዘርፍ የሚገኙ የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ የስፖርት ማህበራት፣ ተጫዋቾች፣ አትሌቶች፣ የእግር ኳስ ክለቦችና ተጫዋቾች ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ርብርብ ተሳትፎ ሲያደርጉ ነበር።በስፖርት ማህበረሰቡ በኩል ሰብዓዊነትን መሰረት አድርጎ ህዝባዊነትን በመታጠቅ «ወገን ለወገን » ደራሽነቱን በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ ሲደረግ የታዘብንበት ሁኔታ ፤ስፖርት ሰላም፣ ፍቅር፣ የአብሮነትና የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የወንድማማችነት ልዩ መገለጫ የመሆኑን እውነታ በተግባር አስረድቷል።የኮሮና ወረርሽኝ በዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ ያሳደረው ተጽእኖ መዘዙ ዓለም አቀፉን የስፖርት ቁመና የኪሳራ መልክ ያላበሰው ነበር ።በስፖርቱ ላይ የደረሰው ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ቀውስ የተጽእኖው ሰንሰለት ዛሬ ላይ የሚቆም ሳይሆን እስከ ቀጣዮቹ አስር ዓመታት የሚጓዝ እዳን ያስከተለ መሆኑን ነው ጥናቶች ያመላከቱት።በወረርሽኙ ምክንያት ከፍተኛ መቃወስን ካስተናገዱ መካከል የስፖርት ዘርፍ ዋነኛ ነበር።ይህም በስፖርቱ ማህበረሰብ በኩል ወረርሽኙን ለመዋጋት እየተደረገ በሚገኘው ርብርብ እያደረገ ያለው ተሳትፎ ስፖርት ትልቅ ማህበራዊ ኃላፊነትን የተሸከመ ግዙፍ ተቋም መሆኑን ያመላክታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደታዘብነው ሁሉ በሀገራችን የስፖርት ማህበረሰቡ ከነጉዳቱ ትልቅ ተሳትፎ ሲያደርግ ነበር።በዘመነ ኮሮና የስፖርት ቤተሰቡ ሰብዓዊነትን ያነገበ ተግባር በይበልጥ ተጠናክሮ እንደቀጠለ የሚያሳይ መረጃ ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አካባቢ የወጣው መረጃ ያመላክታል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኮሮና ቫይረስ ( ኮቪድ_19) ወረርሽኝ ምክንያት ለተቸገሩ 300 የሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለብ አትሌቶች፣ ዳኞችና አሰልጣኞች የሰብዓዊ ድጋፍና ስለ ቫይረሱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል።«ለአትሌቶቻችን እንቁም» በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ስታዲየም ዛሬ ማለዳ የሚደረገው የድጋፍና ግንዛቤ የማስጨበጫ መርሐ ግብር የስፖርቱ ቤተሰብና ማህበረሰብ ለሰብዓዊነት ተግባር የሚሰጠው ቦታ ምን ያህል ሰፊና ጥልቅ መሆኑን በዘመነ ኮሮና በይበልጥ የሚያሳይበት እንደሚሆን ተጠቁሟል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ቢኒያም ምሩፅ ይፍጠር እንደተናገሩት፤የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ስጋት በአትሌቲክሱ ስፖርት እና ስፖርተኞችም ላይ ጥላውን ያጠላ መሆኑን ገልጸዋል ።በመሆኑ ከዚህ ችግር ተሻግረን ነገ የምንፈልገውን ውድድርና ውጤት ለማስመዝገብ ዛሬ መረዳዳት ይኖርብናል።ስለዚህ በሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለብ የሚገኙ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት አሰልጣኞች፣ እና ዳኞች ቁጥራቸው 300 ለሚሆኑ የስፖርቱ ቤተሰቦች በዛሬው እለት የሰብዓዊ ድጋፍ ሊደረግ መሆኑን አመልክተዋል። በኢትዮጵያ አትሌቲክስ የትልቅ ታሪክ ባለቤት ከሆኑት አትሌቶች አንዱ የሆነው ማርሽ ቀያሪው ምሩጽ ይፍጠር ልጅ የሆኑት አቶ ቢኒያም ፤«ነገን እንሻገራለን፣ የምንፈልገውንና የምንወደውን አትሌቲክስ ስፖርታችንን እናስቀጥላለን ዛሬ ላይ በህብረትና በአንድነት ቆመን ልንደጋገፍና ልንረዳዳ ይገባል» ሲሉም ሰብዓዊነትን የታጠቀውን መርሐ ግብር አስፈላጊነት የተናገሩት። የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቲክስ የዘወትር አጋር ከሆነው ከሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር የሰዋዊ ድጋፍና የግንዛቤ ማስጨበጫው የሚከናወን መሆኑንም ነው ያስታወቁት። አዲስ ዘመን ሰኔ 12/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=34669
2377f2f27ff1b9c0ebc3ff81ed590acc
51da772166285795b33f37e5c94534e9
የ3ሺ ሜትር መሰናክል የመጪው ዘመን ተስፋ
ስፖርት
ያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በእርግጥም አንድ እውነት በዓለም አትሌቲክስ ልቆ ያንጸባረቀበት ወቅት ነበር። በሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ውድድር ለዓመታት ወደ አንድ ወገን ያደላው የበላይነትም ባልታሰበ አቅጣጫ የተጓዘበት ሆኖ ይታወሳል። በበርካታ ዓመታት የአትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች ዓለምን ያስደመሙትና በውጤት ያሸበረቁት በመምና ጎዳና ላይ የረጅም ርቀት ሩጫ ነበር። ለኢትዮጵያ ቀንደኛ ተፎካካሪ ከሆኑት ሃገራት መካከል ቀዳሚዋ ኬንያ በተለይም በ3ሺ ሜትር መሰናክል ሩጫ እስካለፈው ዓመት ድረስ በዓለም ውጤታማና ከሌሎች ተፎካካሪዎቿ ፍፁም የበላይ ነበረች። እአአ በ2019 ግን በዚህ ርቀት ኢትዮጵያም ተስፋ ያላት ሃገር መሆኗን በተለያዩ ውድድሮች ማረጋገጥ እንደተቻለ የዓለም አትሌቲክስ ሰሞኑን በድረ ገጹ ያሰፈረው ሰፊ ሐተታ ይጠቁማል። ለኢትዮጵያ በታላቅ የውድድር መድረክ በርቀቱ የመጀመሪያው ድል የተመዘገበው በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሲሆን፤ በኳታር ዶሃ በተካሄደው ውድድር ለሜቻ ግርማ በጥቂት ማይክሮ ሰከንዶች ተቀድሞ የብር ሜዳሊያ በማጥለቅ ታሪክ ማስመዝገብ ችሏል። በወቅቱ አትሌቱ 8:01.36 የሆነ ሰዓት ሲያስመዘግብ በኬንያዊው ኮንሴሉስ ኪፕሩቶ የተቀደመበት አጋጣሚ እጅግ የሚያስቆጭ ሆኖ ይታወሳል። በርቀቱ ለኢትዮጵያ ተስፋ ሰጪ የሆነው ሌላኛው ድል ደግሞ በውድድር ዓመቱ ዳይመንድ ሊግ ላይ ነበር የተመዘገበው። ወጣቱ አትሌት ጌትነት ዋለ በርቀቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ከሆኑ አስር የተለያዩ ርቀት ተወዳዳሪ አትሌቶች መካከል አንዱ ሊሆን ችሏል። እነዚህ በዓለም ታላላቅ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን በአዲስ ርቀት ተስፋ እንድታደርግ ያስቻሉ አትሌቶች የሚሰለጥኑት በአንድ አሰልጣኝ ስር ነው። ይህ አሰልጣኛቸውም ብሄራዊ ቡድንን የሚወክሉ በርካታ አትሌቶችን በማፍራት ላይ የሚገኘው ተሾመ ከበደ ነው። በተለይ ጌትነት በ3ሺ ሜትር መሰናክል በዓመቱ ያሳየው ብቃት እጅግ አበረታች በመሆኑ ድረገጹ ትኩረት የሰጠው ሲሆን፤ ቀጣዩ የርቀቱ ኮከብ እንደሚሆንም ነው ተስፋውን የገለጸው። አትሌት ጌትነተ ዋለ በደቡብ ምሥራቅ የሃገሪቷ አካባቢ በምትገኘው ሰቀላ የተባለ ስፍራ ስምንት ልጆች ካሏቸው ቤተሰብ መካከል የተገኘ ፍሬ ነው። ዛሬ አትሌት ለመሆኑ ምክንያቱ ደግሞ በየዕለቱ በጠዋት እየተነሳ ከቤቱ በአራት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ትምህርት ቤቱ የሚያደርገው ሩጫ ነበር። ይህ ልምድም ትምህርት ቤት ውስጥ ለሚካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ሲያሳጨው፤ በ13 ዓመቱ በ1 ሺ 500 እና 3 ሺ ሜትር አሸናፊ መሆንም ችሎ ነበር። ይህ ሁኔታ ለቀጣይ የአትሌቲክስ ህይወቱ መንገድ የጠረገለትን አጋጣሚ የፈጠረም ነበር። ይህም ጌትነት በትምህርት ቤቱ ተገኝቶ ብቃቱን ለተመለከተው የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አሰልጣኝ እይታ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ጌትነት ከዚያ በኋላ የሆነውን ሲያስታውስም ‹‹አሰልጣኙ በእኔ ላይ ፍላጎት ስላሳደረ ቤተሰቦቼን አስፈቅጄና የትምህርት ማስረጃዎቼን ይዤ ወደ አዲስ አበባ አብሬው እንድሄድ ጠየቀኝ›› ይላል። ያ አሰልጣኝ ዛሬም ድረስ በስኬቱ ከጎኑ ያለው ተሾመ ሲሆን፤ ለዓመታት በነበራቸው የአብሮነት ቆይታ አትሌቱ በመሰናክል የተሻለ ብቃት እንዳለው መረዳት በመቻሉ ወደዚያው እንዲገባ አድርጓል። እአአ 2016 በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ቻምፒዮና ደግሞ የአሰልጣኙ ጥረትና የጌትነት ችሎታ በእርግጥም ለስፖርት ቤተሰቡ በግልጽ ሊታይ የቻለበት ነው። ይህ ተስፈኛ አትሌት በፖላንድ ባይዳጎዝ ከተማ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፎ የነሐስ ሜዳሊያ ቢያገኝም፤ በወቅቱ ብቃቱ ያን ያህል ትኩረት ያገኘ አልነበረም። ይሁን እንጂ ሁለተኛ ከወጣው አትሌት በ16 ሰከንዶች የዘገየውና 8፡22.83 የሆነ ሰዓቱ የግሉ ፈጣን ሰዓት ነበር። በወቅቱ የነበረው ብቃት በአትሌቲክስ ቤተሰቡ ዘንድ እምብዛም ትኩረት ባያገኝም በሪዮ ኦሊምፒክ ግን ለብሄራዊ ቡድን ለመመረጥ ዕድሉን አስገኝቶለታል። ወጣቱ አትሌት በታላቁ መድረክ ሃገሩን በመወከሉ ደስ ቢሰኝም በበዛ የጭንቀት ስሜት በመዋጡ እንዳሰበው ሜዳሊያ ማግኘት ሳይችል ቀረ። በባይዳጎዝ በተካሄደው የወጣቶች ቻምፒዮና ብቃቱን ለተረዳው ማናጀሩ ግን ይህ ምንም ማለት አልነበረም። ማናጀሩ ሁሴን ማቄ ‹‹ጌትነት ትልቅ ልብ ያለው አትሌት ነው። በውድድሩ ላይ ሁለት ጊዜ ወድቆ ከሜዳሊያ ሰንጠረዡ ሳይወጣ ለብር ሜዳሊያ በተጠጋ ውጤት ማጠናቀቅ መቻሉ አስደናቂ ነው›› ሲል ይገልጸዋል። ጌትነት በቀጣዩ ዓመትም ውጤታማነቱ እንደቀጠለ ነበር። በሃገር አቀፉ ቻምፒዮና አሸናፊ ከሆነም በኋላ በሄንግሎ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች ውድድር በብሄራዊ ቡድኑ ተካተተ። ውድድሩንም 8፡12.28 በሆነ ሰዓት የክብረወሰን ባለቤት በመሆን አጠናቀቀ። ይኸውም በዚያው ዓመት (እአአ 2017) በተካሄደው የለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሃገሩን እንዲወክል አደረገው፤ በ17 ዓመቱም ልምድ ካላቸው አትሌቶች ጋር ተፎካክሮ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ። እአአ በ2018 የውድድር ዓመት በፊንላንድ የወጣቶች ቻምፒዮና ተሳታፊ ቢሆንም፤ ባልተጠበቀ መልኩ በሌላኛው የሃገሩ ልጅ ተቀድሞ የነሐስ ሜዳሊያ ነበር ያጠለቀው። ይህ ተደጋጋሚ የውድድር ልምድም እአአ 2019 የውድድር ዓመት በሚገባ እንዲዘጋጅና ያለውን ብቃት በተገቢ መንገድ እንዲያሳይ አደረገው። የስልጠና ጫናውን በመጨመርም በሳምንት ከ100-120 ኪሎ ሜትር በመሸፈን ልምምዱን ይሠራም ነበር። ከቡድን አጋሩ ለሜቻ ግርማ ጋር ጠንካራ ልምምድ በመሥራታቸውም ሁለቱም የግል ውጤታቸውን ማየትና ለሃገራቸውም ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። ጌትነት ከዓለም አትሌቲክስ ድረገጽ ጋር በነበረው ቆይታም ‹‹ከለሜቻ ጋር በአካዳሚው አብረን የምንኖር ጓደኛሞች ነን። በልምምድ ጊዜ ጠንክረን የምንሠራ በመሆናችን የሥራችንን ፍሬ ልናገኝ ችለናል›› ይላል። የዳይመንድ ሊግ ውድድሮቹን ሲያስታውስም ‹‹ራባት በጭራሽ የሚዘነጋ አይደለም፤ ምክንያቱም ከዚያ ቀደም የምሠራቸውን ስህተቶች ያረምኩበት ውድድር ነው። በቅድሚያ ሩጫውን ለመቆጣጠር ቻልኩ ከዚያም በመጨረሻው ዙር የመጨረሻውን ውሃ በጥንቃቄ በመዝለል ቀዳሚ ሆኜ በአሸናፊነት አጠናቀቅኩ›› ሲል ውጤታማውን ውድድር መለስ ብሎ ያስታውሳል። በውድድሩ ያስመዘገበው ሰዓትም የኢትዮጵያ የርቀቱ ክብረወሰንና በዳይመንድ ሊጉ ሦስተኛው ፈጣን ሰዓት ነበር። አሸናፊ ከሆነም በኋላ ‹‹አሸናፊነቴ ለኢትዮጵያ ትልቅ ድል ነው፤ ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በዳይመንድ ሊግ የ3ሺ መሰናክል ውድድር አሸናፊ የሆነ አትሌት አልነበረም። በመሆኑም በራስ መተማመን ሰጥቶኛል፤ ወደፊት ደግሞ ከስምንት ደቂቃ በታች መሮጥ እንደምችል ፍንጭ ያገኘሁበት ነው›› በማለት ስሜቱን ያጋራል። በዓለም ቻምፒዮናው ተሳታፊ የነበረው ጌትነት የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ካገኙት አትሌቶች መካከል ቢሆንም፤ ያጠናቀቀው በሜዳሊያ ሰንጠረዡ የቅርብ ርቀት ላይ አራተኛ ሆኖ ነበር። በዓመቱ በተካሄደው የቤት ውስጥ የዙር ቻምፒዮና ተሳትፎውም ከሦስቱ ውድድሮች በሁለቱ አሸናፊ መሆን ችሏል። በብራሰልስ በነበረው የዳይመንድ ሊጉ ማጠናቀቂያ ውድድር ያሳየው ብቃትና አጨራረስ ለዚህ የውድድር ዓመት ይደገም ይሆን በሚል የስፖርቱ ቤተሰብ እንዲጠብቀው ያደረገም ነበር። የእርሱም እቅድ በዚህ ዓመት ሊካሄድ በታሰበው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በርቀቱ ታሪክ መሥራት ነበር። ሆኖም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ምክንያት እንደ ውድድሩ ሁሉ ብቃቱም በቀጠሮ ለሚቀጥለው ዓመት ሊራዘም ችሏል። ሆኖም በቤቱ ውስጥ ሆኖ በሳምንት ሦስት ቀናት ልምምድ ማድረጉን አላቋረጠም። ‹‹በብቃቴ ለመቆየት ማድረግ ያለብኝን እያደረኩ ነው። በቅርቡ ወደ ውድድር እንመለሳለን የሚል ተስፋም አለኝ›› ሲል ተስፈኛው አትሌት ይናገራል። በዚህ ወቅትም ኑሮውን ካደረገባት አዲስ አበባ ወደ ተወለደበት አካባቢ በማቅናት ቤተሰቡን በመርዳት ላይ ይገኛል። ውድድሩ በተመለሰ ጊዜም በ3ሺ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያዊያን ለሌሎች ተፎካካሪ አገራት አትሌቶች ፈተና እንደሚሆኑ እምነቱ ነው። ‹‹በመሰናክል ጠንክረን በመሥራት መልካም ውጤት ማስመዝገብ በመቻላችን ደስተኞች ነን›› የሚለው ጌትነት ይህም የበላይነቱን ለረጅም ጊዜ ይዘውት ለቆዩት ኬንያዊያን ማስጠንቀቂያ መሆኑን ድረ ገጹ በሰፊ ሐተታው መደምደሚያ አስምሮበታል። አዲስ ዘመን ሰኔ 15/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=34859
f1d9fde6c996fc3d25d55403f4ea035c
dca33b176ecc5ddc4df0206a6d83ede4
« የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው»!
ስፖርት
የምን ጊዜም የቦክስ ስፖርት ንጉሱ መሐመድ አሊ የዓለም የቦክስ ቻምፒዮንና ታላቅ የቡጢ ተፋላሚ ብቻ አልነበረም። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፤ የጥቁር ህዝቦች ሰንደቅ፤ በመላው ዓለም በስፖርትና በታላቅ ስብዕና ተምሳሌትም ጭምር ነው። ብዙዎች ቦክስ ስፖርት ሳይሆን የጥጋበኞች ድብድብ አድርገው ከመሳል አስተሳሰብ አውጥቶ የቦክስን ስፖርት ጥበባዊ ገፅታ በማላበስ ተወዳጅና አሁን ላይ በዓለማችን በአንድ ጊዜ በርካታ ሚሊየን ዶላሮች የሚያሳቅፍ ግንባር ቀደም ስፖርት እንዲሆን ተፅዕኖውን አሳርፏል። ሙዚቀኛም ሆኖ ለሂፕሆፕና ራፕ የሙዚቃ ስልቶች ጉልህ ሚና ተጫውቷል። በቦክስ ስፖርት ታሪክ የምንግዜም ምርጥ ቦክሰኛ የተባለውም በተለያዩ የቡጢ ፍልሚያዎች ዘመን የማይሽራቸው ገድሎችን በማስመዝገብ ነው። መሐመድ አሊ የቦክስ ጓንቱን ሰቅሎ ስፖርቱን በቃኝ ብሎ ከተሰናበተ ከሦስት ዓመታት በኋላ እኤአ በ1984 ከስፖርቱ ልምድ ጋር በተያያዘ ፓርኪንሰንስ በተባለ በሽታ ተይዞ ነበር።ለሰላሳ ሁለት ዓመታት ከዚህ ህመሙ ጋር ሲታገል ቆይቶ ከአምስት ዓመት በፊት በሰባ አራት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።ባለፉት ሳምንታት በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ከተማ ነጭ ፖሊስ ያልታጠቀ ጥቁር አሜሪካዊ አንገትን በጉልበቱ እረግጦ ለሞት ማብቃቱን ተከትሎ የዓለም ሕዝብ ትኩረት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወደ ሟቹ ጆዮርጅ ፍሎይድ ጉዳይ ዞሯል።ይህ ዘግናኝ ክስተት ከዓመታት በፊት በተመሳሳይ ቁጣን የቀሰቀሰውና በነጭ የፖሊስ አባላት ጭካኔ የሞተውን ኤሪክ ጋርነርን ያስታወሰ ሆኗል። ኤሪክ በወቅቱ በፖሊስ አንገቱ ተቆልፎ ‹‹እባካችሁ መተንፈስ አልቻኩም›› እያለ ነበር የሞተው። የጂዮርጅ ፍሎይድ አሰቃቂ ግድያ ዛሬም ድረስ በሞተባት አገሩ አሜሪካና ሌሎች የዓለማችን ክፍሎች ትልቅ ቁጣን ቀስቅሶ ይገኛል።በታላላቅ ከተሞችም‹‹ የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው›› የሚሉ መፈክሮች በተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ተፅዕኖ ፈጥረዋል።አዲስ ዘመን ስፖርትም በሳምንታዊ የስፖርት ማሕደር አምዱ ‹‹የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው›› ብሎ ለጥቁሮች እኩልነት ስለታገለው የቦክሱ ዓለም የምንጊዜም ኮከብ መሐመድ አሊ ሕይወት ላይ ትኩረቱን ለማድረግ ወደደ።መሐመድ አሊ ወደ ቦክስ ሕይወት የመጣበት አጋጣሚ አስገራሚ ነው። የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ በነበረበት ወቅት ብስክሌቱ ተሰርቆበት በሊውስቪል ኬንታኪ ለሚገኝ ጆ ማርቲን ለተባለ ፖሊስ አመለከተ።«የሰረቀኝን ባገኘው ልክ አገባው ነበር» ብሎም ምሬቱን ይገልፃል።የቦክስ አሰልጣኝ የነበረው ፖሊስ ትንሹን መሐመድ ራሱን እንዴት ከጥቃት መከላከል መማር እንዳለበት መከረው።የተወሰኑ ስልጠናዎችን ሲወስድ ቆይቶም ብስክሌቱ ከተሰረቀች ከስድስት ሳምንታት በኋላ በሰፈሩ በአንድ አማተር የቦክስ ግጥሚያ ላይ ተሳተፈና በነጥብ አሸናፊ መሆን ቻለ።ይህች አጋጣሚም በዓለም በገነነበት ስፖርት የመሰረት ድንጋይ ነች። መሐመድ የትውልድ ስሙ ካሴስ ክሌይ ቢሆንም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ባሮችን ነፃ ለማውጣት በታገሉ ታላቅ ሰው መታሰቢያነት የወጣለት ስም ነበር።ለመጀመርያ ጊዜ የዓለም ከባድ ሚዛን ቻምፒዮን ከሆነ በኋላ በማግስቱ ስሙን ለመቀየር ወሰነ።የነፃነት ታጋዩን ማልኮለም ኤክስ ከጎኑ አድርጎ በሰጠው መግለጫ «ዘ ኔሽን ኦፍ ኢስላም» የተባለውን ተቋም መቀላቀሉን በማሳወቅ የባርያ ስም ይለው የነበረውን ካሴስ ክሌይ በመቀየር በቀድሞ ስሙ ላለመጠራት ወሰነ። በወቅቱ «ኔሽን ኦፍ ኢስላምን» ይመራ የነበረው ኤልጅያህ መሃመድ እኤአ በ1964 ላይ መሐመድ አሊ የሚለውን ስም ካወጣለት በኋላ እሱን በማፅደቅ እስከ ህይወት ዘመኑ መጨረሻ ተጠራበት። ለሃያ አንድ ዓመታት በፕሮፌሽናል ቦክሰኛነት በርካታ የቡጢ ፍልሚያዎችን ከአሜሪካ እስከ አፍሪካ እንዲሁም ሌሎች ዓለማት ላይ የተፋለመው መሐመድ አሊ ለሦስት ጊዜ የዓለም ከባድ ሚዛን ቻምፒዮን ሆኗል።ለመጀመርያ ጊዜ የዓለም የከባድ ሚዛን ቻምፒዮን ለመሆን የበቃውም የሃያ ሁለት ዓመት ወጣት እያለ ነው። ዓለም አቀፍ ደረጃ ባላቸው ፕሮፌሽናል የቦክስ ግጥሚያዎች ላይ ስልሳ አንድ ጊዜ ተሳትፎ ሃምሳ ስድስቱን ማሸነፍም ችሏል። ከነዚህ ድሎቹም ሰላሳ ሰባት ያህሉን ተጋጣሚዎቹን በበቃኝ በመዘረር ነው። አስገራሚው ነገር በሰላሳ አንድ ተከታታይ የቦክስ ግጥሚያዎች ሳይሸንፍ ለመጀመርያ ጊዜ የተሸነፈው የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ፍልሚያ በተባለው ግጥሚያ በጆ ፍሬዘር ነበር።በፕሮፌሽናል የቦክሰኛነት ዘመኑም ሽንፈትን የቀመሰው አምስት ጊዜ ብቻ ነው። የመጨረሻው ፍልሚያም እኤአ በ1981 ከትሬቨር ቤሪቢክ ጋር በማድረግ ስፖርቱን በቃኝ ብሏል። አሜሪካ በቬትናም በ1970ዎቹ መጀመርያ ያደረገችውን ጦርነት በመቃወሙ ለሦስት ዓመታት ከፕሮፌሽናል ቦክስ ውድድሮች ታግዶ የቆየው መሐመድ አሊ እገዳው በተጣለበት ወቅት ከአስር የማያንሱ የዓለም ከባድ ሚዛን ቻምፒዮናዎች ባያመልጡት አሁን ካሉት የበለጠ በርካታ ክብሮችን መጎናፀፍ ይችል ነበር። በዚህም ከሰማንያ ሚሊየን ዶላር በላይ ሀብት ማፍራት ችሏል። ለዚህም ሀብቱ ምንጭ ስፖርቱን ከተሰናበተ ወዲህ ግንባር ቀደም ተዋናዮቹ ስሙንና ምስሉን የሚጠቀሙ ከአርባ በላይ ኩባንያዎች ናቸው። ታሪካዊው ኢትዮጵያዊ አትሌት አበበ ቢቂላ በ1960 የሮም ኦሊምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ለጥቁር ህዝቦች የመጀመሪያውን የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ሲያስመዘግብ መሐመድ አሊም በቦክስ የወርቅ ሜዳሊያ አጥልቆ ነበር። ሁለቱ ታሪካዊ የጥቁር ህዝቦች ከዋክብት ፊርማቸውን ተለዋውጠውም ነበር። ይሁንና መሐመድ አሊ ይህን የወርቅ ሜዳልያውን ለአገሩ ከማበርከት ይልቅ በሊውስ ቪል ግዛት በሚገኘው የኦሃዮ ወንዝ ጨምሮታል። ሜዳልያውን ለአሜሪካና ለትውልድ ከተማው ሊውስ ቪል ቢቀዳጅም ለጥቁሮች በርገር የመግዛት መብት ባለመኖሩ ተቃውሞውን ለመግለፅ ነበር ይህን ርምጃ የወሰደው። በ1996 አገሩ አሜሪካ ባስተናገደችው የአትላንታ ኦሊምፒክ ችቦውን እንዲለኩስ ከመደረጉ ባሻገር ወንዝ የጨመረው የወርቅ ሜዳልያ ምትክ ሌላ ሜዳሊያ በአንገቱ ተጠልቆለታል። በ1980 በላስቬጋስ በተካሄደ የቡጢ ፍልሚያ በቴክኒካል የበቃኝ ውጤት ቢሸነፍም መሐመድ ትልቁን ክፍያ ስምንት ሚሊየን ዶላር ያፈሰው በዚያ ውድድር ነው።« ራምብል ኢን ዘ ጃንግል» በተባለውና እስካሁንም ከስፖርት ቤተሰቡ አዕምሮ በማይጠፋው በአፍሪካ ምድር በተካሄደው ፍልሚያ መሐመድ አሊ ምን ጊዜም ይታወሳል። እኤአ በ1974 መሐመድ አሊ በሰላሳ ሁለት ዓመቱ ሽንፈትን አይቶ ከማያውቀው ከሃያ አምስት ዓመቱ ጆርጅ ፎርማን ጋር በኮንጎ ኪንሻሳ የቡጢ ፍልሚያ ገጥሞ ነበር። በወቅቱ የኮንጎ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሞቡቱ ሴሴኮ ለሁለቱ ቦክሰኞች በኪንሻሳ ከተማ እንዲጫወቱ በነፍስ ወከፍ አምስት ሚሊዮን ዶላር ከፍሏቸው ነበር።መሐመድ አሊ በውድድሩ ስምንተኛ ዙር ላይ በዝረራ ቢሸነፍም ከወጣት ተፋላሚው ጋር ያደረገው እልህ አስጨራሽ የቡጢ ፍልሚያ እስካሁንም ከህሊና የሚጠፋ አይደለም። በ1970 የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ሽልማት የተቀበለው መሐመድ አሊ፤ የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነት ተምሳሌት ሆኖም ያውቃል። የተባበሩት መንግስታት የሰላም መልዕክተኛ ሆኖም ከ1998 እስከ 2008 በታዳጊ አገራት በመዘዋወር አገልግሏል። በህይወቱ ዙርያ በሚያተኩሩ ጥናታዊና የሙሉ ጊዜ ፊልሞች የሰራ ሲሆን በተለይ ለመጀመርያ ጊዜ በተዘጋጀውና ዘ ግሬተስት በተባለ ፊልም ላይ ተውኗል።የህይወት ታሪኩ ላይ በማተኮር ከተሰሩ ፊልሞች የኦስካር ሽልማት በጥናታዊ ፊልም ዘርፍ ያገኘው «ዌን ዊ ዌር ኪንግስ»ና ዝነኛው የሆሊውድ ተዋናይ ዊል ስሚዝ በመሪ ተዋናይነት የተጫወተው «አሊ» የተባሉት ይጠቀሳሉ።ታላቁን የደቡብ አፍሪካ ነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ከእስር እንደተፈቱ በአካል ተገኝቶ ደስታውን ለመግለፅ መሐመድን የቀደመው የለም። በአካል ካገኛቸው ታላላቅ መሪዎች የእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤት፤ የሮማው ሊቃነ ጳጳስ ፖፕ ጆን ፖል፤ የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ እንዲሁም የኢራቁ ሳዳም ሁሴን ይገኙበታል።አይም ዘ ግሬተስትና ስታንድ ባይ ሚ ከዘፈን ስራዎቹ መካከል የሚጠቀሱት ናቸው።በንግግር ችሎታው፤ በልዩ የግጥም ስንኞቹም ተወዳጅነት ያተረፈ መሐመድ አሊ ነው።«በማይሞት እምነትና ፍቅር ዓለም የተሻለ ዓለም መፍጠር እንደሚቻል አሳይቶናል።ሁሌም ቻምፒዮን ነው»።በማለት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪና ታላላቅ ሰዎች በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው መሐመድን ወደማይመለስበት ሸኝተውታል። እሱ ቢያልፍም ጥቁሮች ዛሬም ድረስ ‹‹የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው›› ብሎ ከዘመናት በፊት ትግሉን የጀመረውን ጀግና ያስቡታል።አዲስ ዘመን ሰኔ 14/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=34797
0c70d98fe7a98997cda682e549d5392a
ca1d6c666bf66670c8f808c4b0031a68
“የኢትዮ -ሱዳን የድንበር ግጭት የአገሪቱን ልማትና ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች ሴራ ነው” ዶክተር ደመቀ አጭሶበአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የፖሊቲካል ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር
ሀገር አቀፍ ዜና
ዋቅሹም ፍቃዱ አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያና ሱዳን ለዘመናት አብረው በሰላም የኖሩና ሰፊ ድንበር የሚጋሩ ጎረቤት አገራት ቢሆኑም በቅርብ ጊዜ በድንበር አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ከድንበር በዘለለ የኢትዮጵያን ልማትና ሰላም የማይፈልጉ ሃይሎች አገሪቱን የማተራመስ ሴራ መሆኑ ተገለፀ:: በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የፖሊቲካል ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ደመቀ አጭሶ የድንበር ግጭቱን አስመልክቶ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያና ሱዳን ሰፊ ድንበር የሚጋሩ፣ ለዘመናት በሰላም አብረው የኖሩ ሕዝቦች ናቸው።በአገራችን እየተካሄደ ያለውን የሕግ ማስከበር ሂደት ተከትሎ ሱዳን በድንበር አካባቢ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት መክፈቷ ያልተለመደ ክስተት መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ደመቀ፤ ከግጭቱ በስተጀርባ የአገራችንን ሰላም የማይፈልጉ ግብጾችና የኛው አኩራፊ ሃይሎች መኖራቸው ቅንጣት አያጠራጥርም ብለዋል:: ኢትዮጵያ ከግብጽ ይልቅ የሱዳን ታሪካዊ ወዳጅና አጋር መሆኗን ያመለከቱት ዶክተሩ፤ እ.ኤ.አ በ1973 እስከ 1983 በኮሎኔል ኒሜሪ ዘመን በታሪክ ተረጋግታ የማታውቀው ሀገር ሱዳን ለአስር ዓመታት ያህል በንጉሥ ኃይለ ሥላሴ እገዛ ሰላም ሰፍኖባት እንደነበር አስታውቀዋል:: በወቅቱ አንፃራዊ ሰላም የሰፈነው ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ኮርድ አማካይነት ለደቡብ ሱዳኖች እውቅና ሰጥታ ወደ ፌዴራል መንግሥት እንዲካተቱ በማገዟ እንደሆነም አመልክተዋል::እ.ኤ.አ በ1989 በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን በያዙት በኮሎኔል ኦማር አልበሽር ዘመንም በደቡብ ሱዳንና በሱዳን መካከል በተፈጠረው ግጭት፣ በተለይ በዳርፉር ግጭት አስከፊ ሰብዓዊ ቀውስ እንዳይፈጠር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ድርሻ ጉልህ መሆኑንም ጠቁመዋል::ሱዳን በዓባይ ወንዝ፣ በድንበር፣ በህዝቦች አሰፋፈር ወይም ትስስርና በሌሎች ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ጋር የተሳሰረች በመሆኑዋ፤ አገሪቱን በጥንቃቄ መያዝ እንደሚያስፈልግ ገልፀው፤ የህዳሴው ግድብ ድርድር ፍትሐዊ እንዲሆን ሱዳን ለኢትዮጵያ ያደረገችው ድጋፍ ቀላል ባይሆን ግብጾች ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሱዳንን አጥብቀው እንደሚፈልጉ መዘንጋት የለብንም ብለዋል:: በእጅ አዙር ኢትዮጵያን ለመጉዳት ፈልጋ ነው እንጂ፤ ግብጽ በታሪክ የሱዳን አጋዥና ወዳጅ ሆና እንደማታውቅ ይልቁን ከቅኝ ገዥዋ ከእንግሊዝ ጋር በመሆን ደቡብና ሰሜን ሱዳንን በሃይል መግዛቷን ዶክተሩ አስታውቀዋል። እ.ኤ.አ በ1929 እና በ1959 የዓባይ ውሃን አጠቃቀም አስመልክቶ በግብጽና በሱዳን መካከል የተደረገው ስምምነት እንኳ የሱዳንን ብሔራዊ ጥቅም በእጅጉ የሚጋፋ መሆኑን በማስታወስ፤ ግብጽ በታሪክ ሱዳንን ከመጉዳት ወደኋላ ያለችበት ዘመን እንዳልነበር አስታውቀዋል::እንደ ምሁሩ ገለፃ፣ ሱዳን በብዙ ምክንያቶች በርካታ ጥንቃቄ የምትፈልግ ጎረቤት አገር ናት:: አንደኛ ሱዳን በታሪኳ ዘመናዊ /ህዝባዊ/ መንግሥት አቋቁማ ስለማታውቅ በዘመናዊ መንገድ የመደራደር አቅሟ አስተኛ ነው:: በሌላ በኩል ደግሞ ሁኔታን በማየት አቋሟን የምትቀያይር አገር ናት:: በኢትዮጵያ በኩል ነገሮች ጥሩ ሲሆኑ ወደ ኢትዮጵያ ፣ ሲከፋት ደግሞ ከግብጽ ጋር የመወገን አዝማሚያ አላት:: ሌላው ችግሯ ደግሞ አሁን አገሪቱን እያስተዳደሩ ያሉ ሃይሎች በተለይ ወታደራዊ ሃይሉ የውስጥ ችግሩን በማዳፈን ሥልጣን ላይ ለመቆየት ከግብጽ ድጋፍ ለማግኘት ከኢትዮጵያ ጋር የሚጋጨውን የግብጽ አጀንዳ ለማራመድ ይገደዳል ያሉት ዶክተር ደመቀ፤ ለዚህ ማሳያ ደግሞ የሱዳን ሚሊሻዎች በድንበር አካባቢ እየፈጠሩ ያሉት ችግር በቂ ነው ብለዋል::ኢትዮጵያ በታሪክ የሌላውን ድንበር ጥሳ ባታውቅም፣ የግብጽም ሆነ የሌሎች አኩራፊ ሃይሎች ድብቅ ዓላማ ለማክሸፍ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የአገራችን ሉዓላዊነትን ባስከበረ መልኩ የሱዳንንም ጥቅም ባልጎዳ ሁኔታ ታሪካዊ ሁኔታዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ድንበር የማካለል ሥራ ከወዲሁ መጀመር እንዳለባት ጠቁመዋል። ሰላም ማውረድ በአንድ አገር ፈቃደኝነት ብቻ የሚረጋገጥ ስላልሆነ በሌላኛው ወገን ከዲፕሎማሲ አልፎ በጉልበት ተገፍቶ በአገር ሉዓላዊነት ላይ የሚመጣው ማንኛውንም ጥቃት ለማስተናገድ ታሪካችንም ስለማይፈቅድ መመከት የመጨረሻ አማራጭ እንደሚሆን ገልፀዋል:: አሁን የተፈጠረው ችግር በጥንቃቄ ካልተያዘ በብዙ ነገሮች የተሳሰሩ የምሥራቅ አፍሪካ አገራትንም ቀውስ ውስጥ ሊከት እንደሚችልም ምሁሩ አሳስበዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=39077
0fed57323c23fc1885acc7a3da084f0e
b174af5f494c5f9f4397da73fecb56bb
የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ መሠረተ ቢስ መሆሙ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
 በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ በሚል እየተሰረጨ ያለው መረጃ መሠረተ ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።ባንኩ ለዝግጅት ክፍሉ በላከው መግለጫ እንደሚታወቀው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የብር ኖት አሳትሞ ሥራ ላይ አውሏል። ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በመላ አገሪቱ የብር ኖት ቅያሪ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡የብር ኖት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚታተም የሕዝብ ሀብት መሆኑን በመግለጫው የጠቆመው ባንኩ፣ የብር ኖቱ በጥንቃቄ ተይዞ ሕብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ሊገለገልበት እንደሚገባ አመልክቷል። ከዚህ አንፃር ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት በብር ኖት ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት እንዲሁም ብዛት ያለው ገንዘብ ሕግን ባልተከተለ መልኩ ያለአግባብ እንዳይከማች ለማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር CMD/01/2020 ማውጣቱ አስታውሷል፡፡በመሆኑም፣ የብር ኖቱ ረጅም ጊዜ እንዲያገለግል በማስብ) በብር ኖቱ ላይ መፃፍ፣ መቅደድና በቀለም ማበላሸት፣ የትኛውንም ዓይነት ጉዳት ማድረስና ምልክቶቹን ያለፈቃድ ማባዛት የተከለከለና በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አስታውቋል።ለማስታወቂያሥራ ከተፈለገ ለማባዛት የባንኩን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁሞ፣በጣም የተጎዱ የብር ኖቶች ሲያጋጥሙ ከዝውውር ስለሚወጡበት ሁኔታ ዝርዝር መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።ባንኩ መመሪያውን ወደ አማርኛ በማስተርጎምና በማብራራት ስለብር ኖት አጠቃቀም በየጊዜውለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ የሚሠራ መሆኑን አመልክቶ፣ “የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ” እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን አስታውቋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=39076
a8abb541b4baaab971eace42bb00ac77
a295232d2472edff94d8c4f1ef5dc51f
በመተከል ዞን የማንቡክ ከተማ ነዋሪዎች የፀጥታ ኃይል አባላት ሰንጋዎችን አበረከቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
 መተከል (ኢዜአ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የማንቡክ ከተማ ነዋሪዎች በዞኑ ሕግ በማስከበር ሥራ ላይ ለሚገኘው የፀጥታ ሃይል አባላት ለገና በዓል 210 ሺህ ብር ወጪ የተደረገባቸው ስድስት የእርድ ሠንጋዎችን አበረከቱ።በፌዴራል መንግሥት የተቋቋመው ግብረ ሃይል በመተከል ዞን ፀረ ሰላም ሃይሎችን በማደንና በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር እየሠራ ይገኛል።ግብረ ሃይሉ ከዞን እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር በተንኮልና ሴራ ውስጥ የገቡ አመራሮችን የማጥራት፣ ህዝባዊ አንድነትን የማጠናከርና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን የመፍታት ሥራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል። በአካባቢው በዜጎች ላይ ጥቃት በመፈፀም በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ሽፍቶችን በማደን ለሕግ የማቅረብ ሥራም በማከናወን ላይ ነው።ግብረ ሃይሉ ባከናወነው ተግባር በርካታ አካባቢዎች ወደ ቀደመ ሰላማቸው እየተመለሱ ሲሆን ህዝባዊ የውይይት መድረኮችም በመካሄድ ላይ ናቸው።በዚህም ደስተኞች ነን ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ በዞኑ ዳንጉር ወረዳ የማንቡክ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።ነዋሪዎቹ ለፀጥታ ሃይሉ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት የበዓል መዋያውን ማበርከታቸውን ገልፀዋል።ግብረ ሃይሉ በአካባቢው ስላመጣው አንፃራዊ ሰላም ደስተኞች መሆናቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ፤ ድጋፋቸው እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።በዳንጉር ወረዳ ህዝቡ ባደረገው ውይይት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨትና ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲፈፀም ያደረጉ አካላት ተለይተው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል።የአካባቢው ማህበረሰብ ማንኛውንም በዓል በጋራ የማክበርና የአብሮነት ልምድ እንዳለው የገለፁት የአካባቢቅው ሽማግሌዎች “የገና በዓልን በለመድነው አብሮነት እያከበርን ነው” ብለዋል።ማህበረሰቡ የለገሰውን ስጦታ የተረከቡት ሻለቃ ፍቃዱ ጃፍራ ለተደረገው ድጋፍ ሁሉ በሠራዊቱ ስም አመስግነዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=39087
91604f5e4f61a53b72c94ac4fb111208
28261b71f98d88d96d6d45cfc834543c
በአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ መመስረት የኢንቨስትመንት ፍሰትን እንደሚያሳድግ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
ራስወርቅ ሙሉጌታአዲስ አበባ፦ በአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ መመስረት የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግና ግሽበትን ለመቀነስ ብሎም የእውቀት ሽግግር እንዲስፋፋ ለማድረግ እንደሚረዳ ተገለፀ። የአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ ትስስር በጥንቃቄ ከተመራ እያንዳንዱን የአፍሪካ ሀገር ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተጠቆመ። በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ዶክተር ደመላሽ ሀብቴ በጋራ የነፃ ገበያ ዙሪያ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በአፍሪካ አገራት መካከል የተቀናጀ የኢኮኖሚ ግንኙነት ባለመኖሩ አህጉሪቱ ከሰማንያ በመቶ በላይ የንግድ እንቅስቃሴዎች እያደረገች ያለችው ከአውሮፓ፣አሜሪካና እስያ አገራት ላይ ጥገኛ በመሆን ነው። በዚህም የተነሳ አህጉሪቱ ደካማ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የሚከሰትባትና ዝቅተኛ የእውቀት ሽግግር የሚስተዋልባት ሆና ቆይታለች። ከዚህ ቀደምም የአፍሪካ አገራት እርስ በእርስ ያላቸውን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የተሠሩ ጅምሮች ቢኖሩም ውጤታማ ባለመሆናቸው እስከ አሁን እርስ በእርስ ያላቸው ግንኙነት ከሃያ በመቶ የዘለለ አልነበረም ያሉት ዶክተር ደመላሽ፤ በተመሳሳይ ደረጃ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ግብአቶችንም ሆነ እንደ ነዳጅ ያሉ ያለቀላቸውን ምርቶች አፍሪካ አገራት ውስጥ በስፋት እየተመረቱ ቢሆንም ሌሎች ተጠቃሚ ጎረቤት አገራት የሚያስገቡት ካደጉት አገራት ነው ብለዋል። በአህጉሪቱ የተጠናከረ የንግድ ልውውጡና የዳበረ የነፃ ገበያ ተፈጥሮ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው የተቀላጠፈ እንዲሆንና በሚጠበቀው ደረጃ እንዲያድግ የአፍሪካ አገራት የንግድ ልውውጥ በጋራ ነፃ ገበያ ሊጠናከርና ሊስፋፋ ይገባዋል ብለዋል። በተጨማሪም የአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ መመስረትና ወደተግባር መግባት አፍሪካ እንደ አህጉር ከሌላው ዓለም ጋር ለሚኖራት የንግድና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች በር የሚከፍት እንደሚሆንም አመልክተዋል። ነፃ ገበያው በአሁኑ ወቅት በስፋት የሚታየውን ወደመካከለኛው ምሥራቅና ሌሎች አገራት የሚደረገውን የሰው ኃይል ፍልሰት ወደአፍሪካ እንዲሆን ያግዛል ያሉት ዶክተር ደመላሽ፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የእውቀት ሽግግሩም በየደረጃው የተቀላጠፈ እንዲሆን ይረዳል፤ በአገራት መካከል የሚኖረውም የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተጠናከረ እንዲሆን ያግዛል ብለዋል። የአፍሪካ አገራት የጋራ የነፃ ገበያ ከመሰረቱ ከፈለጉ በዶላር ወይንም በራሳቸው በሀገራቱ የመገበያያ ገንዘብ እንዲሁም እቃ በእቃ የመገበያየት ዕድሉ ስለሚኖራቸው የውጭ ምንዛሬ እጥረትን እንደሚቀንስ ጠቁመው፤ ይህም ሆኖ የመንግሥት ታክስ ሊቀንስ ይችላል እንዲሁም በአገራቱ መካከል የተመጣጠነ ዕድገት ባለመኖሩ የሚፈጠር ጫና ሊኖር እንደሚችል አመልክተዋል።የአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ ትስስር በጥንቃቄ እየተቆጣጠሩ መሥራት፣ ትልልቅ ተቋማትን መገንባትና ጥራት ያላቸውን ምርቶች በማምረት ለጠንካራ ውድድር መዘጋጀት ከተቻለ እያንዳንዱ የአፍሪካ አገር ተጠቃሚ ይሆናል ሲሉም ዶክተር ደመላሽ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=39078
27e86dfabaacaa7aa8b8c446e7f7b972
9287ae4f121adfc202dd9ca1ee55926b
የአዲስ ዘመን ስፖርት ትዝታዎች
ስፖርት
በ1933 ዓ.ም ተቋቁሞ በየእለቱ ለአንባቢያን የሚደርሰው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ባለፉት ሰባ አምስት ዓመታት በስፖርቱ ዙሪያ የተለያዩ የአገር ውስጥ ውድድሮችንና ታላላቅ ዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮችን በመከታተል ታሪካዊ ዘገባዎችን አስነ ብቧል። ከታላቁ የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ አንስቶ እስከ ዓለም ዋንጫና የአፍሪካ ዋንጫ እንዲሁም የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናዎች ድረስ በርካታ አይረሴ ዘገባዎችን ለአንባቢዎቹ እንካችሁ ብሏል። አዲስ ዘመን አሁን ሰባ ዘጠነኛ ዓመቱን እያከበረ በሚገኝበት በእዚህ ወቅት ካለፉት ሰባት አስርት ዓመታት በላይ በተለይም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ኦሊምፒክንና የአፍሪካ ዋንጫን በመሳሰሉት መድረኮች በደመቀችባቸው ዘመናት ለንባብ ያበቃቸው ታላላቅ ዘገባዎች የስፖርቱ ማህደር አንድ አካል ናቸው። ከነዚህ ታሪካዊ ዘገባዎች መካከልም በተወዳጁ የአፍሪካ ዋንጫ በተለይም ኢትዮጵያ ባነሳችው ዋንጫ ወቅት የነበረውን ታሪካዊ ዘገባ እየቀነጨብን መለስ ብለን እንመለከታለን።አዲስ ዘመንና የአፍሪካ ዋንጫ ትዝታዎቹኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ የመሰረት ድንጋይ ያኖረች አገር እንደመሆኗ መጠን የመድረኩን ጣፋጭ ድል ለአንድ ጊዜም ቢሆን መጎንጨት ችላለች። ኢትዮጵያ በወርቃማ የእግር ኳስ ዘመኗ የአፍሪካ ዋንጫን ከአምስት አስርት ዓመታት በፊት ማንሳት ስትችል አዲስ ዘመን ጋዜጣ ኢትዮጵያ አዘጋጅ አገር እንደመሆኗ መጠን ከመስተንግዶው ጀምሮ እስከ ዋንጫው ፍፃሜ ዘገባዎችን ለአንባብያን ሲያደርስ የነበረ ግንባር ቀደም የህትመት ውጤት ነበር። ጥር 6 ቀን 1954 የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ የመክፈቻ ጨዋታውን ከቱኒዚያ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ እውቁ የስፖርት ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ ጥር 9 ቀን 1954 ለአንባቢያን በበቃው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የስፖርት አምድ ላይ ያቀረበው ዘገባ የሚከተለውን ይመስል ነበር። « የሦስተኛው ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ የፉትቦል ውድድር ጥር 6 ቀን 1954 ዓም ከቀትር በኋላ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስታድዮም ላይ በኢትዮጵያና ቱኒዚያ ብሔራዊ ቡድን መካከል ተጀምሮ የኢትዮጵያ ቡድን 4ለ2 ማሸነፉን ከጨዋታው ስፍራ በመገኘትና በራዲዮን በመስማት ሴት ወንዱ፤ ልጆችና ሽማግሌዎች ተባብለው ሳይከፋፈሉ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከልብ የተደሰተ በመሆኑ ሰሞኑን በመስሪያ፤ በመኖሪያ፤ በሆቴልና በቡና ቤቶች፤ በገበያና ንግድ ሱቆች፤ በሴይቼንቶና በአውቶብስ ውስጥ እንዲሁም በልዩ ልዩ አደባባዮች የሚወራው ወሬ አንዳችም ጣልቃ ሳይገባበት የኢትዮጵያን ቡድን አድናቆት የተመልካችን ሁኔታና ይኽንኑ የመሳሰሉ ወሬዎች ብቻ ናቸው»። ሰለሞን የጨዋታውን መክፈቻ በእዚህ መልኩ ካካተተ ከቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተመሳሳይ ውጤት ግብፅን በፍፃሜ ጨዋታ በመርታት እስካሁን የምንጠቅሰውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ ስኬት ማስቀረት ችሏል። በወቅቱም አዲስ ዘመን ማክሰኞ ጥር 15 ቀን 1954 ዓም ባወጣው እትሙ የፊት ገፅ ላይ « ቀልጣፋው የኢትዮጵያ ምርጥ ቡድን የግብፅን ቡድን 4ለ2 አሸነፈ» በሚል ርእስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለቡድኑ አምበል ሉቺያኖ የአፍሪካ ዋንጫውን ሲያበረክቱ የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ ይዞ ወጥቷል። የዘገባው መግቢያም የሚከተለውን ይመስላል« ለ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚደረገው የእግር ኳስ ውድድር ጥር 13 ቀን 1954 ዓም ባለፈው እሁድ ቁጥሩ ከ5o ሺህ የማያንስ ህዝብ በተሰበሰበበት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስታድዮም ተደርጎ ፤ የኢትዮጵያ ምርጥ ቡድን የግብፅን ብሔራዊ ቡድን 4ለ2 አሸንፎ የአፍሪካን ዋንጫ ወስዷል። በሁለቱ አፍሪካዊ ቡድኖች መካከል የሚደረገውን ውድድር ለማየት በስታድየሙ ውጭና ግቢ አሰፍስፎ ይጠብቅ የነበረው ተመልካች ታሪካዊ አቀባበል የሚመሳሰል ነበር። ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ግርማዊ ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግሥት ወራሽ ልዑል መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰንን፤ ልዑል ራስ እምሩንና ሌሎችንም የክብር ተከታዮቻቸውን አስከትለው በፖሊስ ሰራዊት ሞተር ብስክሌተኞች ታጅበው ከስታድየም ደረሱ»።በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከፍተኛ ንቅናቄን በፈጠረው የ2o13 የደቡብ አፍሪካ ዋንጫም አዲስ ዘመን ከዘመኑ ጋር ተጉዞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሰላሳ አንድ ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ሲመለስ በርካታ ጨዋታዎችን ተከታትሎ ዘገባዎችን ለአንባቢ አቅርቧል። በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እየተመራ ቤኒንን ከእዚያም ሱዳንን በመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ በደርሶ መልስ ውጤት ዋልያዎቹ ድል አድርገው ወደ አፍሪካ ዋንጫ ሲመለሱ ጥቅምት 3ቀን 2oo5 ዓም ይዞት በወጣው እትሙ በፊት ገፁና በስፖርት ባለቀለም ገፁ የአሰልጣኞች፤ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ስሜትን የሚገልፁና በቃለ መጠይቅ የዳበሩ በርካታ ዘገባዎችን ማቅረብ ችሏል።አዲስ ዘመን ሰኔ 1/2012  ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=34012
c07771743f2adb00b19e7505a849f34b
846b2f87050a5a93510236ec8a3a9149
ለእግር ኳስ አሰልጣኞች ስልጠና ሊሰጥ ነው
ስፖርት
በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና በአሰልጣኝ አምሳሉ ፋንታሁን አማካኝነት በሀገራችን ላሉ የእግር ኳስ አሰልጣኞች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ ተነገረ።የአሰልጣኞች ስልጠናው በካፍ ኢንስትራክተር እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በሆነው አብርሃም መብራቱ የተዘጋጀ ሲሆን በዋናነትም በኢንስትራክተሩ ይሰጣል ተብሏል። በተጨማሪም በርካታ ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች ወደ አሜሪካና ስፔን ተጉዘው ስልጠና እንዲወስዱ ከዚህ ቀደም ሲያመቻቹ የነበሩት በአሜሪካ የሳክሬም የእግር ኳስ አካዳሚ ሴቶች ዳይሬክተር እና አሰልጣኝ አምሳሉ ፋንታሁን አማካኝነት ከአስር ቀናት በኋላ ይሰጣል። ስልጠናው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች በዋናነት የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም በሴቶች እግር ኳስ ላይ ለተሰማሩ አንድ አንድ አሰልጣኞች የሚካተቱበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።የአሰልጣኝ ስልጠናው በዋናነት የሚያጠነጥነው አሰልጣኞች አሁን ካለው ሁኔታ በመነሳት ራሳቸውን ማሻሻል በሚኖርባቸው ሁኔታዎች፣ በሀገራችን እግር ኳሳዊ ሃሳቦች፣ በአሰልጣኝነት ብቃት ላይ ይሆናል። ስልጠናው በኮቪድ -19 ምክንያት ስፖርታዊ ውድድሮች በመበተኑ በቤታቸው እያሳለፉ የሚገኙ አሰልጣኞች ከሙያው እንዳይርቁና፤ ውድድር ሲጀመር ከዜሮ እንዳይነሱ በማድረግ መነቃቃት የሚፈጥር መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል ። የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አቋማቸውን እየፈተሹ ይገኛሉ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑ በርካታ ክለቦች የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ፕሪሚየር ሊጉ ከቀናት በኋላ ወደ መደበኛ ውድድር ሊመለስ መሆኑን ተከትሎ ክለቦቹ ቀደም ብለው የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች እያደረጉ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።አለም ዓቀፍ ስጋት በሆነው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ፕሪሚየር ሊጉ ዳግም ለመመለስ እኤአ ሰኔ 10 ቀን 2020 ቀጠሮ ተይዟል።ክለቦች ወደ መደበኛ ጨዋታቸው ሊመለሱ ቀናት የቀሩት በመሆኑ ወደ ነጥብ ጨዋታ ከመግባታቸው በፊት አቋም መፈተሻዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተመልካች እንዳለው የሚነገርለት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰኔ 10 ይጀመራል።ፕሪሚየር ሊጉ ከተቋረጠ ከወራት በኋላ ወደ ውድድር መመለሱ በክለቦችና ተጫዋቾች ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለመቀነስ ከዛ በፊት በርካታ የሊጉ ክለቦች እርስ በእርስ አልያም ከሌሎች ክለቦች ጋር የአቋም መፈተሻ ግጥሚያዎችን በማድረግ ላይ እንደሆኑ ታውቋል። በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ከሆኑ ክለቦች አንዱ የሆነው ማንችስተር ዩናይትድ በኦልድ ትራፎድ ሃሪ ማጉዌር በአምበልነት የመራው ቡድን በሜዳው በብሩኖ ፈርናንዴስ የሚመራውን ቡድን ገጥሟል። በአቋም መፈተሻ ጨዋታው የሃሪ ማጓየር ቡድን የብሩኖ ፈርናንዴዝን ስብስብ 2 ለ 0 መርታት ችሏል። ከወራት በኋላ ማርከስ ራሽፎርድ እና ፖል ፖግባ ደግሞ ወደ ሜዳ ተመልሰዋል።የማይክል አርቴታ መድፈኞቹ ግን ከእርስ በእርስ ግጥሚያ ይልቅ የቻምፒየን ሺፕ ክለብን በሜዳቸው ማስተናገድን መርጠዋል። ከቻርልተን ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ ያደረጉት አርሰናሎች 6-ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።ከዚህ በተጨማሪም ቼልሲ፣ ሊቨርፑል፣ ዌስት ሃም አስቶን ቪላ እና ኒው ካስል ዩናይትድም ከ10 ቀናት በኋላ ለሚጀመረው ሊግ እራሳቸውን ዝግጁ ለማድረግ እርስ በእስር ግጥሚያ የሚያደርጉ ክለቦች መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። አዲስ ዘመን ሰኔ 2/2012
https://www.press.et/Ama/?p=34005
c2d4d82ca3f59d97647be48f7b9523f9
8e2a666e20fe37bfd69acf094aab1b0d
የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር ዋለ
ሀገር አቀፍ ዜና
ራስወርቅ ሙሉጌታአዲስ አበባ፦ የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ። የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ትናንት እንዳስታወቁት፣ በአገራችን ላለፉት 27 ዓመታት የማተራመስ ስትራቴጂ የነደፈ ያስተባበረና ያደራጀ በመጨረሻም ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግ በሀገራችን ሰራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ጦርነት በመክፈት ሰራዊቱን ያስጨፈጨፈው የጁንታው ቁንጮ፣ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገለጹት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ፣ የጥፋት ቡድኑ አባላት በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀውት እንደነበርም አመልክተዋል። ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ፣ ከተደበቀበት በማውጣት በቁጥጥር ስር እንዳዋሉትም ጠቁመዋል። ከመከላከያ የከዱ ሌሎች ከሃዲ የጁንታው አባላት ከስብሃት ነጋ ጋር አብረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፣ አባላቱ ከመከላከያ በመክዳት የጁንታውን ታጣቂ ኃይል በማዋጋትና በማሰልጠን እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈፀም ሲሰሩ እንደነበር አስታውቀዋል። የጁንታውን አመራር ዙሪያ ጥበቃ ሲያስተባብሩ ቆይተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ገልፀዋል። ጁንታውን ለመያዝ በተካሄደው ኦፕሬሽን የጁንታውን አመራሮች ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ ታጣቂ ኃይል መደምሰሱን አስታውቀዋል።እንደ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ መግለጫ፤1. የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስት፣ ስብሃት ነጋ 2. ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤትና ቀደም ሲል በጦር ኃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበረች፣ በኋላም በጡረታ የተገለለች 3. ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዳ 4. ኮሎኔል የማነ ካህሳይ- ከመከላከያ የከዳ 5. አስገደ ገ/ ክርስቶስ -ከመሃል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለና ለጊዜው ኃላፊነቱ ያልታወቀ 6. አምደማርያም ተሰማ ተወልደ፣ የክልሉ የቅሬታ ሰሚ ፅ/ቤት ኃላፊ የነበረ፤7. ኮማንደር በርሄ ግርማ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል ሎጀስቲክ ኃላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።ከተደመሰሱትና ከተያዙት በተጨማሪ የሜጀር ጀነራል ሃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረችና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ጁንታው ተቀላቅላ የነበረች፣ ወይዘሮ አልጋነሽ መለስ ጁንታውን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል ገብታ ሕይወቷ ማለፉን ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገልፀዋል።በተመሳሳይ ዜና አራት የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸው መደምሰሳቸን፤ ዘጠኝ የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ከትናንት በስቲያ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡በዚህም መሰረት፣1. የጁንታው ቃል አቀባይ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጪ አድርገነዋል ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን የተናገረ ፤2. ዘርአይ አስገዶም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበረ፤3. አበበ አስገዶም የድምጸ ወያኔ ኃላፊ የነበረ፤4. ዳንኤል አሰፋ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ የነበረ ከሹፌሮቻቸውና ከጥበቃዎቻቸው ጋር በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ በፌዴራል የጸጥታ ተቋማትና በትግራይ ሕዝብና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተደረገ የተቀናጀ ዘመቻ መደምሰሳቸውን ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አስታውቀዋል።ከተደመሰሱት በተጨማሪም 9 የጁንታው ቁልፍ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም፣1. ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ የቀድሞ የክልሉ አፈጉባኤ የነበረች፣2. ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮኃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበረ፣3. አቶ ተክለወይኒ አሰፋ የማረት ሥራ አስፈጻሚ የነበረ፣4. አቶ ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ የነበረ፣5. አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበረ፣6. አምባሳደር አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበረና የጁንታውን ፖለቲካ ክንፍ የተቀላቀለ፣7. አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ኃላፊ የነበረ፣8. ወይዘሮ ምህረት ተክላይ የክልሉ ምክር ቤት ሕግ አማካሪ የነበረች እንዲሁም9. አቶ ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ሥራ ሂደት ኃላፊ የነበረ ነው። የህወሓት ጁንታ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በጫካና ዋሻ ለዋሻ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ ጠንካራ አሰሳ መሆኑን የገለጹት ብርጋዴር ጀኔራሉ፣ የአገር መከላከያ ሰራዊት እነዚህ የጁንታው ቁልፍ የጥፋት ቡድን አባላት እንዲደመሰሱና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያላሰለሰ ድጋፍ ላደረገው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስጋናውን አቅርቧል። ሰራዊቱ ወንጀለኞቹን አድኖ ለመያዝ ቃል በገባው መሰረት ግዳጁን እየተወጣ መሆኑን አመልክተው፣ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የጀመረውን ቀሪ የጁንታውን ርዝራዦችን አድኖ ለመያዝና በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ሕዝቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍና ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39156
2022e41b2194c76f05b4f9bdf8f5c33b
12db259907fb260bf60b4983c23a53fe
የላቁ ስፖርተኞችና ብቃት ያላቸው የስፖርት ባለሙያዎችን ለማፍራት
ስፖርት
በስፖርት ማሰልጠን፣ መምራትና ማስተባበር ተሳታፊ የሆኑ ባለሙያዎች ለስፖርት እድገትና ውጤታማነት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚጫወቱ እሙን ነው። በዚህ ምክንያትም ሀገር አቀፉ የስፖርት ሪፎርም ፍኖተ ካርታ እንደ ግብ ከያዛቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት ማፍራት ነው። የማዕከላዊው ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በ2004 ዓ.ም ባወጣው መረጃ መሠረት በወቅቱ 2ሺ376 ዳኞችና 2ሺ476 አሰልጣኞች እንደነበሩ ያመላክታል። ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ደግሞ በተለያዩ የስፖርት ሙያ ዘርፎች 30ሺ560 ባለሙያዎችን በአጭር፤ 2ሺ388 ባለሙያዎችን ደግሞ በረጅም ጊዜ ሥልጠና ለማፍራት መቻሉ በፍኖተ ካርታው ሰፍሯል። ይሁን እንጂ ሥልጠናውን ለተገቢው ባለሙያ ከማድረስ አኳያ፣ በብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ደረጃቸውን የጠበቁ የሥልጠና ማኑዋሎች አለመኖር፣ የሥልጠናው ግብ አለመታወቅና ተያያዥ አለመሆኑ፣ የንድፈ ሃሳብና የተግባር ሥልጠናው አለመመጣጠን፣ በምዘና እና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ችግሮች መኖር፣ ቅንጅታዊ አሠራር ባለመኖሩ የሥልጠና አሰጣጥ ባለድርሻ አካላት አለመናበብ፣ ተመሳሳይ እና በማይሰሩበት ሙያ ሥልጠና መውሰድ እንዲሁም መሰል ችግሮች መኖራቸውንም ሰነዱ ያመላክታል። ይህንን ችግር ለመቅረፍም ፍኖተ ካርታው ወጥ የሆነ የባለሙያዎች የእድገት መሰላል፣ የሥልጠና ካሪኩለም እንዲሁም የሥልጠና ማኑዋል በብሔራዊ የስፖርት ማህበራት ማዘጋጀት እንደሚገባም በመፍትሄነት ያስቀምጣል። በዚሁ መሠረትም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የላቁ ስፖርተኞችንና ብቃት ያላቸውን የስፖርት ባለሙያዎችን ለማፍራት፤ ብሔራዊ የሥልጠና ሞዴል እና አገር አቀፍ የስፖርት ባለሙያዎች የእድገት መሰላል እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል። ባለሙያዎች በአጭርና መካከለኛ ጊዜ ሥልጠና እንዲሁም በረጅም ጊዜ ትምህርት ብቃታቸው እየተሻሻለ አቅማቸው እየተገነባ ሊሄድ ይገባል። በመሆኑም የሀገር አቀፍ የስፖርት ሪፎርም ጥናቱ ውጤት የሆነውንና የለውጥ ሃሳቦችን ለማስተግበር የሚያስችሉ ሰነዶች ዝግጅት መጀመሩን በኮሚሽኑ የትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ሳሙኤል ማስገንዘባቸውንም ኮሚሽኑ በድረ ገጹ አስነብቧል። የስፖርት ባለሙያዎች ልማት እና ጥራት አንዱ የሀገሪቷ ስፖርት ልማት ማዕዘን ነው። የስፖርቱን ችግር ይፈታል የተባለው የስፖርት ሪፎርም ፍኖተ ካርታው ለይቶ ካስቀመጣቸው ዘጠኝ ዋና ዋና ምሰሶዎች አንዱም የስፖርት ባለሙያዎች ልማት እና ጥራት ነው። ለአንድ ሀገር ስፖርት እድገት የባለሙያዎች ብቃት፣ ጥራት እና አቅርቦት እጅግ ወሳኝ መሆኑን የሪፎርም ፕሮግራሙ ያመላክታል። በመሆኑም ባለሙያዎች በአጭር እና መካከለኛ ጊዜ ሥልጠና እንዲሁም በረጅም ጊዜ ትምህርት ብቃታቸው እየተሻሻለ አቅማቸው እየተገነባ ሊሄድ እንደሚገባ የጥናት መርሃ ግብሩ ይጠቁማል። በሰነድ ዝግጅቱ ላይም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከስፖርት ፌዴሬሽኖች፣ ከሥልጠና ማዕከላት፣ ከብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች እና ሌሎችም በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ያላቸው ምሁራን ተሳታፊ እንደሚሆኑም ታውቋል። አጠቃላይ ዝግጅቱን በተመለከተም በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን አልዩ የሥራ መመሪያ ተሰጥቶ ወደ ሥራ መገባቱም ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን ሰኔ 4/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=34184
e0bb3e3c5c355cdca8c12f4459144b2a
47f9450967032091dad5b0edc43ff344
ያልተዘጋው የፓሪሱ ዶሴ
ስፖርት
 እ.ኤ.አ ሰኔ 7 ቀን 1933 በሴኔጋል ዳካር ከተማ አንድ ህጻን ተወለደ። በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው ሴኔጋል መወለዱ ለቤተሰቦቹ ቅር ቢያሰኝም፤ ከህጻኑ አይኖች ያነበቡት ተስፋ መጽናናትን የሰጣቸው ነበር። የህይወት ውጣ ውረዱም ደስታን ከሀዘን እያፈራረቀ ቀጠለ። በሴኔጋል ምድር የበቀለው ህፃን የህይወት ውጣ ውረድን በመጋፈጥ፤ በአንካራ የልጅነት ጊዜውን አሳልፏል። በጊዜ ቅብብሎሽ ልጅነቱ ወደ ወጣትነት ሽግግር አደረገ። ከልጅነት ጀምሮ የሚፍለቀለቀው የስፖርት ፍቅር በዘመን ሳይሻር አብሮ ያደገ ነበር። በአንካራ ህይወት ቀላል አልነበረምና በፈታኙ የህይወት መንገድ ነገን የተሻለ ለማድረግ መጓዝ አማራጭ እንደሌለው በማመን ጉዞው ቀጠለ። ከልጅነት ጀምሮ ለስፖርት የነበረው ፍቅር ግን ወጥ በሆነ መስመር የተጓዘ ነበር። በስፖርት ፍቅር መሰረት የተገነባው የህይወት ኡደት የስኬት ቁልፍንም በስፖርቱ አማካኝነት እስከ መጨበጥ የደረሰ ታሪክ ባለቤት ናቸው የቀድሞ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ፕሬዚዳንት ላሚን ዲያክ።ላሚን ዲያክ ስፖርትን እንደ መሰላል በመጠቀም ስኬትን መጨበጥ ከቻሉ ጥቂት አፍሪካዊያን ውስጥ ይመደባሉ። የ86 ዓመት አዛውንቱ ላሚን ዲያክ በህይወት ፈተና ውስጥ ሳይሰናከሉ ያደረጉት ጉዞ ለዚህ ደረጃ መዳረሻ እንደሆናቸው «በሥራ ዘመኔ ከፍተኛ የፖለቲካ ፈተናዎች ገጥመውኝ ነበር።ዓላማ ስለነበረኝ ሁሉም አልፏል፣ ስለ አፍሪካ አንድነት በማውራት ጊዜውን ሁሉ ተጠቅመናል»ሲሉ ይደመጣሉ። ሴኔጋላዊው ዲያክ ወደ ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ አመራርነት በመምጣት ሀገራቸውን ከማስጠራታቸው ቀደም ብሎ በዝላይ ውድድር ሀገራቸውን ሲያስጠሩ ነበር። በወጣትነት ዘመናቸው በዝላይ ውድድር ሃገራቸውን በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች በመወከል ተሳትፈዋል። ከብዙዎቹ በጥቂቱ እኤአ 1950 በፍረንሳይ በተካሄደው የአትሌቲክስ ቻምፒዮን በመሳተፍ ባለድል ሆነዋል። ዲያክ በተደጋጋሚ የቻምፒዮናነት ክብር ባለቤት መሆን የድልን ጣዕም ለሀገራቸው በማቅመስ ትልቅ ታሪክ መስራታቸው ይነገራል።ሴኔጋላዊያን እርሳቸው ካስመዘገቧቸው ድሎች መካከል በተለይ በዝላይ ውድድር ከ1957 እስከ 1960 የምዕራብ አፍሪካን ክብረወሰን መያዝ የቻሉበት አጋጣሚ ትልቅ ስፍራ ይሰጡታል።የአፍሪካን እግር ኳስ በማነቃቃት ግንባር ቀደም የሆነችው ሴኔጋል ያበቀለቻቸው ላሚን ዲያክ በአትሌቲክሱ የተወዳዳሪነት ጊዜያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ስፖርቱ አመራርነት ነበር ያዘነበሉት።በዚህም የተሳትፎ ደረጃቸውን በፍጥነት ማሳደግ ችለዋል። እኤአ 1999 እስከ 2013 የአለም ዓቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል በመሆን አገልግለዋል።በኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል በመሆን ሲያደርጉ የነበረው ተሳትፎ ወደ ሌላ ምዕራፍ ያሸጋገራቸው ነበር።እኤአ 1995 የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ፕሬዚዳንት እንዲሸጋገሩ መሰላል ሆኗቸዋል። የላሚን ዲያክ ወደ መሪነት መምጣት በሴናጋል ብቻም ሳይሆን በአፍሪካዊያን ዘንድ ትልቅ ደስታን የፈጠረ ነበር።የዓለምን አትሌቲክስ በአፍሪካዊያን መመራቱ አዲስ ታሪክ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለአፍሪካዊያን የይቻላል መንፈስን ያወረሰ ተብሏል።የዲያክ የዓለምን አትሌቲክስ የመምራት ሂደት ለ16 ዓመታት ነበር የተጓዘው።እኤአ በ2015 ላሚን ዲያክ ስልጣናቸውን ለተመራጩ ለሴባስቲያን ሎርድ ኮ አስረክበዋል።ሴኔጋላዊው ላሚን ዲያክ በስልጣን ዘመናቸው በአትሌቲክሱ ዓለም የተበላሹ የአመራር ክፍተቶችን እንዳሉ በስፋት የሚነሳ ቢሆንም ከሞላ ጎደል ጥሩ ሥራዎችንም ማከናወናቸውን አብሮ ይነሳል።በተለይ ለአፍሪካ አትሌቲክስ የነበረቸው አበርክቶ የሚጠቀስና እስከ ሽልማት የተሻገረ ነበር።በአህጉሪቱ የአትሌቲክስ ስፖርት ላይ የሚያጠነጥነው «አፍሪካ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን »ለላሚን ዲያክን እውቅና በመስጠት ረገድ ግንባር ቀደም ነበር። የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ላሚን ዲያክ ባገለገሉባቸው ዓመታት የአፍሪካ አትሌቲክስ ህዳሴ መሆን ጉልህ ድርሻ ነበራቸው። ለዚህም እውቅናና ሽልማት ይገባቸዋል ሲል አመስግኗቸዋል።የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን በተመሳሳይ እውቅናውን አልነፈጋቸውም።እኤአ መጋቢት 4 ቀን 2015 የኮንፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚዎች 26ኛውን ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት ለዲያክ ምስጋናና እውቅና ቸሯቸዋል። በወቅት ኮንፌዴሬሽኑ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፤ የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን በጋራ የእውቅና እና የስንብት ዝግጅት በማድረግ ለአበረከቷቸው አመስግነዋቸዋል።ዲያክ በፈተና የተሞላውን ጉዞ በድል መወጣት ቢችሉም፤ የህይወት ፈተና አላበቃም ነበር። የአለም አትሌቲክስ መሪነት ዘመናቸው ጨርሰው ስልጣናቸውን ካስረከቡ ማግስት ወደ ሌላ ፈተና ተሻገሩ። የአለም ዓቀፍን አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበርን ለ16 ዓመታት የመሩት ላሚንዲያክ መንበረ ስልጣናቸውን ባስረከቡ ማግስት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በ86 ዓመታቸው ፍርድ ቤት ነበር የቆሙት። ዲያክ በፈረንሳይ ፓሪስ የቁም እስረኛ ሲሆኑ፤ እኤአ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ጀምሮ በፓሪስ ፍርድ ቤት ዲያክ የሩስያ አትሌቶች አበረታች መድሃኒት መውሰዳቸውን ለመደበቅ ረብጣ ሽልንግ ተቀብለዋል፤ የምርጫ ድምፅን በገንዘብ ገዝተዋል፤በሕገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር ጋር ተያይዞ ነበር ክስ የተመሰረተባቸው። በተጠቀሱት ወንጀሎች ዲያክን ጨምሮ አራት ግለሰቦች ተከሳሽ ሲሆኑ፤ የዲያክ ልጅ ፓፓ ማሳታ ዲያክ አንዱ ነው። ፓፓ ማሳታ ሴኔጋል ሆኖ የክስ ሂደቱን እየተከታተለ ይገኛል። ሴኔጋል ልጅዬውን አሳልፋ ለፈረንሳይ እንድትሰጥ ጥያቄ ቢቀርብም ሴኔጋል አሻፈረኝ ብላለች።በዚህ መሰረት ፓፓ ማሳታ አባቱንና እሱን ነፃ ያወጣል ያለውን ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ በማስገባት ሙግቱን እያደረገ ቢሆንም፤ የክሱ ሂደት አላግባብ መጓተቱን ተከትሎ ወላጅ አባቱ ላሚን ዲያክ ለእንግልት መዳረጋቸውን እየተናገር ይገኛል።የክስ ሂደቱ ከተጀመረ አምስት ዓመት ቢያስቆጥርም መቋጫ እንዳላገኘ ገልጿል።በዲያክም ሆነ እርሱ በቀረበበት ክስ ላይ በቂ የሆነ ማስረጃ የሌለ በመሆኑና ካለወንጀላቸው ክስ የተመሰረተ ነው ሲል ቅሬታውን ያሰማል። በጠበቆቻቸው በኩል ይሄው በተደጋጋሚ እየተነሳ ሲሆን ወደ አገራቸው ሴኔጋል ተመልሰው የክስ ሂደቱን እንዲከታተሉ ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ።በፈረንሳይ ፍርድ ቤት ግን ውድቅ ተደርጓል። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ከአምስት ዓመት በፊት የተጀመረው የዲያክ የክስ ሂደቱ መፍትሄ ለማበጀት በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማግስት እንዲታይ ቀጠሮ ይዞ ነበር። ፍርድ ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ሰኔ ወር እንዲዛወር አድርጎታል። በፈረንሳይ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የ87 ዓመቱ ላሚን ዲያክ በቀጠሮ መሰረት ባሳለፍነው ሰኞ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰምቷል።የፓሪሱ ፍርድ ቤትም በቀድሞዋ የአለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ላሚኔ ዲያክ ላይ ከሩሲያ ጋር በመመሳጠር ከዶፒንግ ጋር ተያይዞ በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የተመሰረተባቸውን የክስ ሂደትን ተከታትሏል።ፍርድ ቤቱ በዲያክ ላይም ዶፒንግን በሶስት ሚሊዮን ዩሮ በመለወጥ ሲል ክስ የመሰረተባቸው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። የ 87 ዓመቱ ላሚን ዲያክ ፊታቸውን ጭምብል በመሸፈን ፍርድ ቤት ተገኝተው የክስ ሂደታቸውን ተከታትለዋል።የፓሪሱ ፍርድ ቤትም ለቀጣዮቹ ስድስት ቀናት ችሎት ተሰይሞ የክስ ሂደቱን እንደሚሰማ ማስታወቁን አትቷል።የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ንግግር፤ «ሴኔጋላዊው ዲያክ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ ዓመታት ቢቆጠሩም ወንጀሉ ጥልቅ ምርመራ የሚፈልግ ከመሆኑ ጋር እንደሚያያዝ አስታወቋል።ዓመታትን በፈጀው ምርመራም የተዘበራረቀና ውስብስብ የሙስና ወንጀል መፈጸሙን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ተገኝተዋል። በተያዙት ሰነዶችም ከአውሮፓ እስከ እስያ እና አፍሪካ የተዘረጋ ጠንካራ የሆነ የወንጀል ሰንሰለት መኖሩን የሚያረጋግጡ ናቸውን»ሲሉ ማስረዳታቸውን ዘገባው አካቷል። የፓሪስ ፍርድ ቤት በዲያክ ላይ የሰበሰበውን ማስረጃዎች መሰረት በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በስድስት ቀናት ችሎት እነዚህን ማስረጃዎችን በማቅረብ ወደ ውሳኔ እንደሚኬድ ፍርድ ቤቱ ማስታወቁን ጽፏል።በፈረንሳይ ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተባቸው ላሚን ዲያክ በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከ 10 ዓመት የሚዘልቅ እስር ሊፈረድባቸው ይችላሉ ተብሏል። አዛውንቱ ዲያክ ቀሪ የእድሜ ዘመናቸውን ወሕኒ ሊያሳልፉ እንደሚችሉ ተነግሯል። ነገር ግን ከተከፈተ አምስት ዓመታት የሆነው የፓሪሱ ዶሴ የሚዘጋበት እለት አጓጊ እንደሆነ ቀጥሏል።አዲስ ዘመን ሰኔ 5/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=34246